ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
አላህ በምዕራፍ #17:79 ሙሐመድን ምስጉን በሆነ ስፍራ ማለትም በራሱ ዙፋን ላይ የማስቀመጡ ብሂል እንዲሁ የሚታለፍ አደለም። ይህንን ለማስረዳት በትንሹ የአላህንና የዙፋኑን ምንነት እንይ፦
👉 የአላህ #ኩርሲው(ዙፋኑ) በ2:255 መሰረት በሰማያትና በምድር ሁሉ ላይ የተዘረጋ #የልቀቱ_የከፍተኛነቱ_ምልክት ነው። አላህ ዙፋኑ ወይም #ዐርሹ ማለት በ10:3 መሰረት ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀን ፈጥሮ ሁሉን #የሚያስተናብርበት ይህ ማለት በኢብን አባስ ተፍሲር እንደተቀመጠው #ፍጥረታቱን_የሚመራበት የሚቆጣጠርበት መገለጥንም ቢሆን የሚልክበት ማለት ነው። ሌሎችንም ጥቅሶች መጨመር ይቻላል ባጠቃላይ ግን ዐርሹ ዙፋኑ ኩርሲው የአላህ ከፍጥረቱ ጋር የፈጠረው፣ #ሉዐላዊነቱን፣ ብቸኛ መሪነቱን፣ #ፈራጅቱን ብቻውን የሚከውንበት የመለኮታዊ ስልጣኑን ምልክት መሆኑን እንረዳለን።

🤔ጥያቄ፦ ፩,አላህ ይህንን ሁሉ የሚያደርግበትን የሚከውንበትን ዙፋኑን ለሌላ "ፍጡር" #እንዲቀመጥበትና እንዲወስንበት መፍቀዱ ሉዐላዊነቱንና ብቸኛ ፈራጅነቱን #የሚያጋራ፤ ሙሐመድንም የዚህ ተካፋይ አምላክም የሚያደርግ አይሆንም ወይ? አይሆንም ከተባለ ማስረጃ?
፪, ሌላስ ከነብያት ወይንም ከሰዎች፤ #ከፍጥረታት ይህንን #የተጎነጨ አለን? ከሌለና ሙሐመድ ብቻ ከሆነ #አንድምታው ምንድነው?🤔

✍️ሙግት፦ ከላይ ባነሳሁት መንደርደርያ ሐሳብ መሰረት አላህ ሙሐመድን ተጋሪው አድርጎ አቅርቦታል‼️ ይህንን የማጠነክርበትም በዙፋኑ ላይ መቀመጥ #መቀመጥ_ብቻ እንዳልሆነ በማሳየትና አላህ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የሚከውነውን ሙሐመድም #መከወኑን በማስረገጥ ነው።
በቁርአኑ ምዕራፍ #17:111 ላይ አላህ ሉአላዊ የሆነና #ለንግስናው ምንም #ተጋሪ የሌለው መሆኑን፤ #18:26 ላይ #ፍርዱንም ለማንም #እንደማያጋራ ተቀምጧል። ስለዚህ አንድ አካል ልክ እንደ አላህ ዙፋኑ ላይ #ከተቀመጠ ከዛም ፍርድን ካስቀለበሰና የማይገባቸውን ካሰጠ ከፍርዱም ከንግስናውም #ተጋራ ማለት ነው። ይህንን አላህ ራሱ ፈቅዶ ካደረገው ደግሞ #አያጋራም እያለ #አጋርቷልና ቁርአኑ እርስ በእርሱ #ተጋጭቷል‼️
📚ኢብን ካቲር በ17:79 ተፍሲሩ ላይ ሙሐመድ ምስጉን በሆነ ስፍራ ላይ ተቀምጦ #እንደሚያማልድ ይነግረናል። ይህም ማማለድ በአይነቱ #ልዮ የሆነና እንደዚህም ያለ ማንም እንዳላደረገ እንደማያደርግም ያትታል። ሲለጥቅም እንዲህ ይላል፦

"... #እርሱ_ስራቸው_ገነት_ለማያስገባቸው ወደ ሲኦልም ይወርዱ ዘንድ ለታዘዘባቸውን ሰዎች ያማልዳል, እነርሱም ተመልሰው #ይመጣሉ።...በገነት ከሁሉም በላጭ የሆነችዋን #አል_ዋሲላህ የተባለችውን ስፍራ የሚደርስባትም እርሱ ነው።..." ተፍሲር ኢብን ካቲር 17:79

👉ይህ ማለት የተፈረደባቸውን እንኳ ሳይቀሩ፤ ስራቸው ገነትን የማያስወፍቃቸው እንኳ ሳይቀሩ እርሱ በአላህ ዙፋን ላይ ተቀምጦ በሚያደርገው ምልጃ ገነት ይገባሉ። ሙሐመድ የአላህ ኩርሲ ላይ መቀመጡና ይህን መሰል ድርጊት መፈፀሙ #ተውሂድ_አር_ሩቡቢያህን የአላህን ብቸኛ ሉዐላዊ ፈራጅነት ዳኝነት ፍጥረትን አስተናባሪነት #የሚጥስና የራሳቸውን ተውሂድንም #የሚንድ ቁርአናዊ አስተምሮት ነው። መቼም አንድ አካል በፈጣሪ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ፈጣሪ የሚያደርገውን ካደረገ፤ የተፈረደን ፍርድ እንኳ አስቀይሮ የማይገባቸውን ገነት ካገባ ይህ ራሱ አምላክ እንጂ፤ የፈጣሪ ተጋሪ እንጂ ሌላ ምንድነው ጎበዝ!
.................//................
" እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8:32)
🙏አርነት በእውነት ይሆንላችሁ ዘንድ ፀሎቴ ነው!🙏🙏🙏.