ለምን አልሰለምኩም?
3K subscribers
52 photos
10 videos
42 files
187 links
ይህ ቻነል ቅዱሱ የአምላካችን ቃል በ1ኛ ጴጥ 3:15 ላይ ባዘዘን መሠረት ሙስሊም ወገኖቻችን በክርስትና ላይ ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች እና ትችቶች ምላሽ የምንሰጥበት፣ ጥያቄዎቻቸውን ከነመልሳቸው በየጊዜው እያዘጋጀን የምንለጥፍበት፣ ለምን እንዳልሰለምን ፣ እንደማንሰልምም የምንገልጥበት ፣ የኢስላምን የጨለማ መንገድነት በእውነት ብርሀን የሚገልጡ ፅሁፎችን የምናስነብብበት መድረክ ነው።
Download Telegram
የቁርአን ትርጉም ተፍሲር ይባላል። በጣም ታዋቂና ተቀባይነት ያላቸው ተፍሲሮች ደግሞ ኢብን ካቲር እና አል ጃለሊን ናቸው። ከነዚህ ውስጥም እንደ #ኢብን_ካቲር ያለ ተቀባይነት ያለው ተፍሲር የለም። በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይም የምናየው የኢብን ካቲርን ተፍሲር ይሆናል። እንዲህ ይላል:-

📚“(በሶስተኛዉ አበረታናቸዉ) ማለት፣ “እኛ በሶስተኛዉ መልዕክተኛ ደገፍናቸዉ ፣ አበረታናቸዉ” ማለት ነው። ኢብኑ ዩራይጅ ከ ዋህብ ኢብኑ ሱለይማን እና ከሹአይብ ያባይ እንዳስተላለፉት:-“ የመጀመሪያዎቹ የሁለቱ መልዕክተኞች ስም #ስምኦን(#ጴጥሮስ) እና #ዩሐንስ የሶስተኛዉ ስም ደግሞ #ጳዉሎስ ነበር። ከተማዋም አንፆኪያ ነበረች።”📚😳😳😳😳

እንግዲህ ምን ትሉ ይሆን? የዘመናችን ሙስሊሞች በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚያዘንቡት መሠረት የለሽ ውርጅብኝ ከየት የመጣ ነው? እናንተ ከመተርጉማኖቹ (ሙፈሲሮች) ትበልጣላችሁን? ማነዉ ሶስቱን የላካቸው? አላህ አይደለምን? ደግሞም የቅዱስ ጳውሎስ መምጣት ምን ያህል #_አበረታችና_አፅናኝ እንደነበር ተመልከቱ:: ማን ነው የሳተው? አላህ ወይስ በአላህ የተላከው ጳውሎስ ወይስ የዘመናችን ካለ ማስረጃ የሚለፈልፉት ሙስሊሞች

ይሄን አላምንም የሚል ሰው ካለ ከራሳቸው ከሙስሊሞች ድረ-ገፅ በመግባት ማየት ይችላል። ለማረጋገጥ የፈለገ ሰው “www.qtafsir.com” በመግባት የቁርአኑን ምዕራፍና ቁጥሩን በመፃፍ በአረበኛም በእንግሊዝኛም ማየት ይችላል።
👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳👳‍♀👳
ሙስሊሞች ደግሞ በተራችሁ ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ሐሰተኛነት ከቻላችሁ እንደኛ ከቁርአን ተፍሲር ካልቻላችሁ ከሐዲስ ማሳየት ትችላላችሁ። እኛ እውነተኝነቱንና የተላከውም በአላህ እንደሆነ አሳይተናል።

http://www.qtafsir.com/index.php?option=com_content&task=view&id=1491&Itemid=
የእስልምና ቀልድ ጥግ!!

መሬትን የተሸከመው ዓሠ-አነባሪ(whale)

እስልምና፣ ሙሓመዳውያን እንደሚሰብኩት ከሳይንስ ጋራ የተጣጣመ ትምህርት ሳይሆን ጭራሽ ሳይንስን R.I.P (rest in peace) "#ነፍስ_ይማር" በሚያስብሉ ትምህርቶች እንደተሞላ ጥቂት ምሳሌዎችን አንስተን ከዚህ በፊት አይተናል። ለመሆኑ፣ እስልምና ስለመሬት አፈጣጣር(earth) ሲያስተምር፣ 'መሬት 1 ብቻ ሳትሆን 7 መሬቶች እንደ ሳንድዊች ተደራርቦ እንዳሉና ሰባቱም ከስር ትልቅ ዓሳ-አንባሪ ላይ እንደተቀመጡ፣ ይህ ዓሳ-አንባሪም ስልሚንቀሳቀስ የመሬትን ባላንስ ለመጠበቅ አላህ ተራሮችን ችካል አድርጎ እንደተከላቸው' እንደሚያስተምር ያውቃሉ?? 😂


ሱራ 68:1: نٓ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
ነ. (ኑን)፤ (1) በብርዕ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት።
Nun. By the pen and what they inscribe,

ሙስሊሞች ይሄን ክፍል ሲተሮግሙት" نٓ" "noon" የምትለውን የአዕረብኛ ቃል ትርጉም ሳይሰጡት "ኑን" ብሎ አልፈዋል። እውነታው ግን፣ ትላልቅ የእስልምና ሙፋሲሮች፤ #ኢብን ከሢር፣ #አ_ጠበሪ#አል_ቁርጡቢ፦ "ኑን" ማለት "አሳ አንባሪ" እንደሆነ በተፍሲራቸው ጽፏል።
ስለዚህ ይህ ክፍል(68:1) ትርጉም ቢሰጠው፤
   "በ ዓሳ አንባሪ (ኑን) እና( و)በ ብርዕ( ٱلْقَلَمِ)እምላለው     በሚጽፉት.." ይሆናል።

ማስረጃዎቻችንን አንድ በ አንድ እንመልከት።
#ዓሳ_አንባሪ በ አረብኛ ምን ይባላል
   1. አል-ኑን  نٓ (noon)
   2. አል-ሁት الحوت (al-hoot)

ሀ. ከቁርዓን

ቁርአን 21:87፦ የዐሣውንም(ٱلنُّونِ al-noon)ባለቤት(man of the fish) ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፤ እርሱም ላይ ፍጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ፤ (ዐሳም ዋጠው)፤ በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ ፦ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ።
   እዚህ ጋር "አል-ኑን"  ሲተረጎም "#ዓሣ" ተብሏል።

ለ. የተፍሲሮች ትርጉም

1. አረቢኛው ተፍሲር ኢብኑ ከሢር ሱራ 68:1

እንዲህ ይላል፦ " نۤ حوت عظيم"። ትርጉሙም  " 'ኑን' 'ن'ۤ  #ትልቅ #አሳ_አንባሪ ነው" ' noon is a big whale'
፦በኢንጊልዘኛው ላይ አልተሮጎሙትም

2. ተፍሢር አል ጠበሪ፦ሱራ 68:1
هو الحوت الذي عليه الأرَضُون

"መሬት(መሬቶቹ, الأرَضُون)  ትልቅ ዓሳ-አንባሪ( الحوت, አል-ሁት) ላይ ነች/ናቸው።"

3. ተፍሢር አል ቁርጡቢ

'نۤ' الحوت الذي تحت الأرض السابعة
'Nun'- the whale (الحوت), which is (الذي) under (تحت) the Earth (الأرض) the seventh (السابعة).
'ኑን' 'ዓሳ አንባሪዋ' ከሰባተኛው መሬት ስር ያለችው..

4. ኢብኑ አባስ በተፍሲር ኢብኑ ከሢር (አረቢኛው)
በ ሱራ 68:1 ላይ

ابن عباس قال: أول ما خلق الله القلم قال: اكتب، قال: وماذا أكتب؟ قال: اكتب القدر، فجرى بما يكون من ذلك اليوم إلى قيام الساعة، ثم خلق النون، ورفع بخار الماء، ففتقت منه السماء، وبسطت الأرض على ظهر النون، فاضطرب النون، فمادت الأرض، فأثبتت بالجبال؛

"እብኑ አባስ እንደዘገበው: "በመጀመሪያ አላህ ብርዕ (pen)(القلم) ፈጠረ። እንዲፅፍም አዘዘው፣ከዚያም ብዕሩ እንዲህ አለ: ምን ልፃፍ፤ እሱም መልሶ፣ 'ሰለ ሰዎች እጣ-ፈንታ (القدر)' አለው። ብዕሩም ከፍጥረት እስከ ትንሳኤ ድረስ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ፃፈ። ከዚያም #አል_ኑንን (النون) ፈጠረ። ከዚያም ውሓ እና ሰማያትን ፈጠረ፣ ምድርንም በ 'ኑን'(አሳ) ጀርባ( ظهر) ላይ( على)
ሰራት።መሬትም በጀርባው ላይ ስትንቀሳቀስ በ ተራሮች እንደ ጭካል (እንዳትንቀሳቀስ) አፀናት።"  ልብ በሉ፣ ሓዲሡ ኢብኑ አባስ የዘገበው ሓዲሥ ሲሆን፣ይሄ ሓዲሥ ሳሂህ(sahih, ታማኝ, authentic)ነው። ኦንላይን በዚህ ገብታቹ ማየት ይቻላል።
(http://hdith.com/?s=ثم+خلق+النون+فوق+الماء،+ثم+كبس+الأرض+عليه)

የጋራዎችንም "ችካል" መሆን ቁርዓን ያስተምራል

ሱራ 78:7
"ጋራዎችንም #ችካሎች አላደረግንምን"

ትናንት የተወለዱት የዘመናችን ኡስታዝ ተብዬዎች "ከነ እብኑ ከሢርና አል-ጠበሪ እንበልጣለን" ይሉን ይሆን?? ከ ኢብኑ አባስስ??

እኛ እንዘግባለን፣ፍርዱን ለአንባቢው!!
@Jesuscrucified
@Jesuscrucified
ሮሜ 9:5

የእስልምና ሰባኪያን ደግመን ደጋግመን በማያውቁት ነገር ውስጥ እንዳይዘባርቁ ብንመክራቸውም፣ በተለይ የግሪክ ቋንቋን በተመለከተ፣ መስሚያቸውን ደፍነው አሳፋሪና ከእውቀት የራቀ ፅሁፋቸውን ከመለጠፍ እየተቆጠቡ አይደሉም። ይሄም ተራ የሆነ የማወናበጃ ስልት እንጂ ሌላ አይደለም።

ሮሜ 9:5ን አስመልክቶ ወሒድ የሚባል ግለሰብ (ባለፈው ተስፋዬ ሮበሌ ብሎ ስለ ግሪክ ሰዋ ሰው የዘባረቀውና ያጋለጥነው ሳያንስ) አሁንም ቅጥፈቱንና፣ ፋላሲውን(fallacy) እንዲውም ምንም እውቀቱ ሳይኖረው ቋንቋውን መዳፈሩን ቀጥሎበታል።

ልጁ ፅሁፉን የሚጀምረው ጳውሎስን እንዲህ ብሎ በማጣጣል ነው። “ለእኛ ለሙሥሊሞች ጳውሎስ የኢየሱስ ሐዋርያ ሳይሆን የግሪክንና የሮምን ዶክትሪን ከኢየሱስ ደክትሪን ጋር ለማስማማት የታገለ ጥሩ ፈላስፋ ነው።”

ለመሆኑ፣ የእስልምን ምሁራንና መፅሓፍቶች ልክ እንደ ወሒድ ጳውሎስ #ፈላስፋ ብቻ ነው ይላሉ ወይስ ወሒድ ከራሱ ሓይማኖት ጋር እየተጣላ ነው? ቁርአንና ተፍሲር ጳውሎስ ከአምላክ የተላከ መልዕክተኛ መሆኑን ይናገራሉ። ላስነባቹ:-

ወደነርሱ ሁለት ሰዎችን በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ፣ በሦስተኛው አበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ፣ (የሆነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)።” (ሱረቱ ያሲን (የያሲን ምዕራፍ) 36:14)

አሁን እዚህ ጋር ጳዉሎስ የሚለዉ የታለ? ትሉ ይሆናል:: ደግሞም ብላችኋል ግን አልተሳሳታችሁም ልክ ናችሁ "ጳዉሎስ" የሚል ስም የለም። ነገር ግን፣ ቁርአንን ለመረዳት የቁርአን መተርጉማን (ሙፈሲሮች) የተናገሩትን ማየት ያስፈልጋ፤ እንጂ ቁርአንን (ቁርአን የቃላት ውርጂብኝ ብቻ ስለሆነ) በቁሙ በማንበብ ብቻ መረዳት በፍጹም አይቻልም፡፡ ይሄንን ሙስሊሞችም ጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ።

የቁርአን ትርጉም ተፍሲር ይባላል። በጣም ታዋቂና ተቀባይነት ያላቸው ተፍሲሮች ደግሞ ኢብን ካቲር እና አል ጃለሊን ናቸው። ከነዚህ ውስጥም እንደ #ኢብን_ካቲር ያለ ተቀባይነት ያለው ተፍሲር የለም። በዚህ የቁርአን አንቀፅ ላይም የምናየው የኢብን ካቲርን ተፍሲር ይሆናል። እንዲህ ይላል:-

📚“(በሶስተኛዉ አበረታናቸዉ) ማለት፣ “እኛ በሶስተኛዉ መልዕክተኛ ደገፍናቸዉ ፣ አበረታናቸዉ” ማለት ነው። ኢብኑ ዩራይጅ ከ ዋህብ ኢብኑ ሱለይማን እና ከሹአይብ ያባይ እንዳስተላለፉት:-“ የመጀመሪያዎቹ የሁለቱ መልዕክተኞች ስም #ስምኦን(#ጴጥሮስ) እና #ዩሐንስ የሶስተኛዉ ስም ደግሞ #ጳዉሎስ ነበር። ከተማዋም አንፆኪያ ነበረች።

ስለዚህ ወሒድ ከእስልምና ጋር መጣላት ካልፈለገ በስተቀር መፅሓፍቶቹን ማመንና የጳውሎስን መልዕክተኛነት መቀበል ግድ ይለዋል።

ወደ ሮሜ 9:5 ስንመለስ፣ ልጁ እንዲህ ብሎ ፅፏል።
“ሮሜ 9፥5 አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና፤ *"ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ፥ ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱ ለዘላለም የተባረከ ይሁን! አሜን*"። καὶ ἐξ ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς εὐλογητὸς εἰς τοὺς αἰῶνας ἀμήν.
Whose are the fathers, and of whom as concerning the flesh Christ came. God, who is over all be blessed for ever. Amen.” Reivised standard version 1971 ,
ግሪኩ ላይ "ኤስቲን" ἐστιν ማለትም "ነው" የሚል ቃል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ "ከሁሉ በላይ የሆነ አምላክ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ይሁን" የሚል ፍቺ እንዳለው እሩቅ ሳንሄድ የዐማርኛ ምሁራን ይነግሩናል። በ 1971 ዕትም Reivised standard version "ይሁን"be" ብሎ አስቀጦጣታል "be blessed for ever"። "አሜን" የሚለው ቃል ለምስጋና የመጣ እስከሆነ ድረስ "ለዘላም የተባረከ ይሁን" ማለት ምስጋና ነው። ማነው ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው? ስንል ለዘላም የተባረከ ይሁን የተባለው "ከሁሉ በላይ" የሆነ አምላክ ነው። እርሱም ከኢየሱስ እና ከመላው ፍጥረት ሁሉ በላይ የሆነው አብ ነው”



በዚህች አንቀፅ ወሒድ ሁለት መሰረታዊ ስህተቶችና እውቀት ማጣትን አሳይቶናል።
1. ከግሪክ ሰዋሰው አንፃር
2. ከሎጂክ አንፃር

1. የግሪክ ሰዋሰው
ἐστιν (estin) የ eimi(I Am) ሶስተኛ መደብ ነጠላ verb ሲሆን ትርጉሙ “Is” ነው። ነገር ግን በግሪክ ቋንቋ ብዙ ግዜ ይህ verb to be መግባት እያለባትም ከአረፍተ ነገር ውስጥ ያወጣታል ወይም Drop ያደርጋታል። ለምሳሌ ሮሜ 7:12 Ο νομος αγιος και εντολη αγια… (The law is holy and the commandment is holy…) በዚህ ክፍል ውስጥ በግሪኩ ἐστιν (estin) የሚል የለም ነገር ግን ወደ ኢንግሊዘኛ ሲተረጎም የግድ Is ታስፈልጋለች። ይሄ የሆነበት ምክኒያት ግሪክ ይህቺን ግስ drop ስላረጋት ነው እንጂ እንዲህ ተብላ መፃፍ ትችላለች “Ο νομος αγιος(ἐστιν)…በተጨማሪም αγιος(ቅዱስ) የሚለው ቃል እንደ predicate adjective እየተጠቀመ ስለሆነ ትርጉሙ ግልፅ ነው። ስለዚህ፣ estin የምትለው ስላልገባች የመፅሃፍ ቅዱስ ትርጉም ስህተት ነው ብሎ መሞገት ተራ ሞኝነትና እውቀት አልባነት ነው።

ከላይ የፃፍኩት የልጁን አላዋቂነት ለማጋለጥ እንጂ ሲጀመር በሮሜ 9:5 ላይ verb to be ወይም የeimi, estin... በሌላ የግሪክ Mood ገብቷል። በግሪክ ቋንቋ ውስጥ ከTense በተጨማሪ mood የሚባሉ አሉ። አምስት mood አሉ፣ Indicative, imperative, infinitive, participle እና subjunctive. “Estin” አሁን indicative mood ነው።

በሮሜ 9:5 ላይ ግን የገባው የverb to be present paticiple mood ሲሆን እሱም ὢν የሚለው ነው። ትርጉሙም “being” ወይም “who is” ማለት ነው። ὁ Χριστὸς τὸ κατὰ σάρκα ὁ ὢν ἐπὶ πάντων Θεὸς (The Christ according to flesh WHO IS(being)OVERALL GOD ወይም ...በሁሉም ነገር ላይ አምላክ የሆነው ክርስቶስ)። ስለዚህ የቃል በቃል ትርጉሙ እንደዚህ ይሆናል። Who is የሚለው reflect የሚያደርገው ክርስቶስ ላይ መሆኑ ግልፅ ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ሁሉም ላይ አምላክ ነው እያለን ነው ክፍሉ።

2. የሎጂክ ግድፈት

ወሒድ አይናችን እያየ ቃሉ የሚናገረውን ሸምጥጦ፣ “ከሁሉ በላይ የሆነው” የተባለው እየሱስ አይደለም ካልን በኋላ ለዚህ ሙግቱ እንዲደግፈው የተጠቀማት ደግሞ ጳውሎስ አይሁድ ስለሆነ እየሱስ አምላክ ነው ብሎ አያምንም ብሎናል። ይሄ begging the question ይባላል። የተናገረውን prove ሳያረግ በፊት assume ማድረግ።

መፅሓፍ ቅዱስን ስናነብ ግን የክርስቶስን አምላክነት ከሰበኩት ውስጥ አንደኛው ጳውሎስ መሆኑን ነው።


(ወደ ቆላስይስ ሰዎች ምዕ. 1)
----------
15-16፤ እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።

17፤ እርሱም ከሁሉ በፊት ነው ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአል።
👍1