ለምሽታችን!
💚
“
´✍ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት!
በአንድ የገጠር ከተማ በርካታ ተማሪዎችን ሰብስበው የሚያስቀሩ አንድ ሸይኽ ነብሩ።አንድ ቀን ከነዚህ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ለሸይኹ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውና ወደ ከተማ ሄዶ ይህንን ለቀለብ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማፈላለግ እንዳለበት ይነግራቸዋል። #ሼይኹም ለተማሪያቸው ከፈቀዱለትና ስንቅ ካዘጋጁለት በኋላ መንገዱን ይጀምራል። ወደ እሚሄድበት ከተማ ለመድረስም ከመንገድ ያለን በረሀ ማቋረጥ ነበረበት። ይህንንም በረሃ አቋርጦ በሚሄድበት ወቅት አንድ የቆሰለ አሞራ ከመሬት ላይ መብረር የማይችል ሆኖ ይመለከተዋል። ታድያ ይህ ደረሳ በዚህ አሞራ ተፈኩር(ማስተንተን) ማድረግ ይጀምራል።
#በዚህ_በረሀ ውስጥ ምንም የሚቀመስ በሌለበት ይህ አሞራ ምን እየበላ ይሆን!?
#እንዴት_በህይወት መቆየትስ ቻለ!?
በዚህ መልኩ በተፈኩር ውስጥ ሳለ ከወደ ሰማይ ሌላ አሞራ ድንገት ከወደ ሰማይ ዱብ ይላል።
#ይህ_አሞራ የሚበላ ነገር በእግሮቹ አንጠልጥሎ ነበርና ለተጎዳው አሞራ ጥሎለት ሄደ። ያ የተጎዳው አሞራም የተጣለለትን ምግብ መመገብ ይጀምራል።
ተማሪውም በጣም ተገረመ። (መቼስ ፈጣሪ ነፍስን ከሪዝቋ ጋር እንጂ መች በባዶ ፈጠራት እና!) ብቻ ነገሩ እጅግ አስገርሞት እና አስደንቆት የሚሄድበትን በመሰረዝ ወደ ሸይኹ መመለስ ጀመረ። ለመመለሱ ምክንያትም ይህንን የተጎዳ አሞራ በዚህ በረሃ ውስጥ የሚመግብ እና የሚረዝቀው ፈጣሪ እኔንም ይመግበኛል ችግሬን ያስወግድልኛል የሚል ነበር። ወደ ሸይኹም እንደደረሰ የተመለሰበትን ምክንያት ይጠይቁታል።
ተማሪውም ያጋጠመውን ሁሉ ይነግራቸውና ፈጣሪው እሱንም ልክ እንደ አሞራው ሁሉ ከችሮታው እንደሚለግሰው ተስፋ አድርጎ መመለሱን ነገራቸው።
#ሸይኹም- ምነው !? እንደው እንተጎዳውና እርዳታ ፈላጊው አሞራ መሆንን ከመመኘት ለምን እንደ ረጂው እና ምግብን ተሸክሞ እንደተባበረው አሞራ መሆንን አልተመኘህም አሉት ይባላል።
---------------------------------------
#ሁሌም ቢሆን ትብብር እና እርዳታን ፈላጊ ከመሆን አንተው እራስህ ረጂ እና ተባባሪ መሆንን ምረጥ።
ከላይ ያለች እጅ ታች ካለች እጅ በላጭስ አይደለች!
#አሁን ወቅቱ ከመቼውም በላይ ቁጭ ብለን ለመረዳት ወይም ከመንግስት ብቻ መፍትሔ የምንጠብቅበት ጊዜ ላይ አይደለንም ሀገራችንን ፣ ወገኖቻችን ፣ ቤተሰቦቻችን ፣ ወገኖቻችን እንዴት ነው ከዚህ ችግር ልንከላከል የምንችለው ብለን በደንብ የምናስብበትና ወደ ተግባር የምንገባበት ጊዜ ነው....እናም ወንድምና እህቶቼ እቤት ከመቀመጥ በዘለለ ደሞ ማድረግ ስላለብን ነገሮች አስቡልኝ የኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ በየአካባቢው አይደል..? አቅም የሌላቸው የንፅህና ሳኒታይዘር ሆነ ምግብ መግዣ የሌላቸው ብዙ አሉ በየአካባቢያችን ስለዚህ እዚህ ቻናል ወንድሞችና እህቶች የምንችለውን እንርዳቸው ይሄን በሽታ የሚከላከሉበት ማቴሪያል እንርዳቸው ፣ የሚበሉትን ገዝተን እንስጣቸው በአቅማችን #ይሄኔ እኛም ለሀገራችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን.....ለምን አንድ ሳሙና አይሆንም ....
#ይሄን የምታነቡ ሰዎች ይሄን እንደምታደርጉ እናንተም የመፍትሔ አካል እንደምትሆኑ እምነት አለኝ🙏🙏🙏
ውብ ምሽት ትሁንላቹ!❤🙏
@getem
@getem
@Nagayta

#አጣብቂኝ
የውልህ አንተዬ
የኛ ነገር ሆኖ ፥ ከድጥ ወደ ማጡ
ክርያላይሶ ብለን ፥ ሰግደን ሳንነሳ ፥ ዳሌ ላይ ማፍጠጡ
ነብሰ በላን ውህድ ፥ በጨለማ ተገን ፥ ለሊት የቀየጡ
ነብስ ማር እያሉ...በፀአዳ ልባስ ፥ ወዳንተ ሲመጡ
ግዝትን ተላልፈው ...
እንደ እስጢፋኖስ ፥ በድንጋይ ውርጅብኝ ፥ ሰው የቀጠቀጡ
ሌላ ሌላም ብዙ ...በደልና ጥፋት
እየተላለፍን በየነጋው...ንጋት...
አፈፃዲቅ እኛ...አንተም ባረምሞ
አይተህ እንዳላየህ ....አፍህ ተከርችሞ...
አልፈህ ስታስገባን ....ሳይቆለፍ ደጅህ
እስከ ትላንትና...እጅ በላን በእጅህ ።
ክፋት ተሸክሞም
የሆዳችን...ነገር
በሆድ እንደዋለ...
ጭንቅ ቀን አስማጠን...በሩቅ አስዋዋለ
አፀድህ ርቆ...አዳፋ ነብሳችን...ከቤት ዘግቶ ዋለ
ይህኔ ...... #ጨነቀን
በተራራ በደል...ቤት ውሎ ...ቤት ማደር
መተንፈሻ ቅጥር...ሲጠፋን እንዳገር
ላለፈው እንለምን....ወይስ ለበፊቱ ?
ማረን ነው የሚባል ?
አውጣን ነው ፀሎቱ ?
በንዲህ ያለ ዘመን...በጠፋ ብልሀቱ
ኋላና ፊት ሆነው ፥ ሀጥያት እና ጥፋት ፥ በመሳ ሲመጡ
ካልጋላይ ሳይወርዱ...ከጎጆም ሳይወጡ
በቀን ይጨልማል ፥ በደል ጎርፍ ሰርቶ ፥ ሜዳ ላይ ሲሰምጡ ።
፨፨
፨
#እንዴት_ታረገን_ይሆን ?
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh
@getem
@getem
@getem
የውልህ አንተዬ
የኛ ነገር ሆኖ ፥ ከድጥ ወደ ማጡ
ክርያላይሶ ብለን ፥ ሰግደን ሳንነሳ ፥ ዳሌ ላይ ማፍጠጡ
ነብሰ በላን ውህድ ፥ በጨለማ ተገን ፥ ለሊት የቀየጡ
ነብስ ማር እያሉ...በፀአዳ ልባስ ፥ ወዳንተ ሲመጡ
ግዝትን ተላልፈው ...
እንደ እስጢፋኖስ ፥ በድንጋይ ውርጅብኝ ፥ ሰው የቀጠቀጡ
ሌላ ሌላም ብዙ ...በደልና ጥፋት
እየተላለፍን በየነጋው...ንጋት...
አፈፃዲቅ እኛ...አንተም ባረምሞ
አይተህ እንዳላየህ ....አፍህ ተከርችሞ...
አልፈህ ስታስገባን ....ሳይቆለፍ ደጅህ
እስከ ትላንትና...እጅ በላን በእጅህ ።
ክፋት ተሸክሞም
የሆዳችን...ነገር
በሆድ እንደዋለ...
ጭንቅ ቀን አስማጠን...በሩቅ አስዋዋለ
አፀድህ ርቆ...አዳፋ ነብሳችን...ከቤት ዘግቶ ዋለ
ይህኔ ...... #ጨነቀን
በተራራ በደል...ቤት ውሎ ...ቤት ማደር
መተንፈሻ ቅጥር...ሲጠፋን እንዳገር
ላለፈው እንለምን....ወይስ ለበፊቱ ?
ማረን ነው የሚባል ?
አውጣን ነው ፀሎቱ ?
በንዲህ ያለ ዘመን...በጠፋ ብልሀቱ
ኋላና ፊት ሆነው ፥ ሀጥያት እና ጥፋት ፥ በመሳ ሲመጡ
ካልጋላይ ሳይወርዱ...ከጎጆም ሳይወጡ
በቀን ይጨልማል ፥ በደል ጎርፍ ሰርቶ ፥ ሜዳ ላይ ሲሰምጡ ።
፨፨
፨
#እንዴት_ታረገን_ይሆን ?
✍ #አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
@Abr_sh
@getem
@getem
@getem
#እንዴት ዋላቹልኝሳ ኣ
ከላይ በድምፅ ያለው እዚሁ ቻናል ላይ ከአንድ ዓመት በፊት ተለጥፎ የነበረ ነው። ስለ ኢትዮጵያን የወሎ ሙስሊሞች የሃጅ ጉዞ እና አጠር ያለች ግጥም ነች።
ከላይ የምታዩት ምስል በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1902
ከወሎ ወደ መካ ሃጂ ያደረጉ ወገኖቻችን ናቸው።
#ነገ በእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ ነገ የዐረፋ ቀን ነው። የወርሀ ዙል ሒጃ ዘጠነኛው ቀን።ይህንን ቀን የሀይማኖቱ ተከታዮች በፆም ያሳልፉታል።
‹‹የአረፋን እለት የፆመ ሰው ያለፈውን
የአንድ አመትና የሚመጣውን የአንድ አመት ወንጀሉን
ያስምርለታል ብየ እከጅላለሁ›› ማለታቸው ተዘግቧል።
(ሙስሊም)
የነገዋ ቀን በዱኒያ ላይ ካሉ ቀናቶች ሁሉ በላጭ ቀን
ናት፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ሙስሊም
ከጀሃነም ከእሳት ነጃ የሚልበት ቀን ነው፡፡ በዚህች
በተቀደሰች ቀን አላህ የወፈቃቸው በአረፋ ተራራ ላይ
ቆመው አላህን ሲማፀኑ ይውላሉ፡፡ ከሃጅ ስነ ስርአት ውጪ
ያለው በቢሊዬን የሚቆጠር ሙስሊም ደግሞ ቀኑን
በታላቅ ኢባዳ፣ በፆም፣ በዚከር፣በዱዓ፣በሰደቃ በአጠቃላይ
በመልካም ስራዎች ተጠድሞ ያሳልፈዋል፡፡
ለወንጀላቸው ምህረት የሚጠይቁበት፣ ከእሳት ነጃ
እንዲያወጣቸው አልቅሰው የሚማፀኑበት ፣ላስጨነቃቸው ሁሉ
ነገር መፍትሄ ለማግኘት ፈጣሪያቸውን አላህን የሚማፀኑበት ቀን ነው፡፡
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) " በላጩና ምርጡ ዱዓ በዐረፋ ቀን
ውስጥ የተደረገ ዱዓእ ነው" ብለዋል ፡፡ (ቲርሚዚ
እንደዘገቡት)
የነገን የአረፋ ቀን ፆማቹ ከእሳት ነጃ የምትባሉበት ፣ ሀጃቹ የሚሳካበት ፣ ወንጀላቸው ከሚማርላቸው እና በዱኒያም ሆነ
በአኼራ ስኬታማ ከሚሆኑት አላህ ያድርጋቹ!
አሚን !!

👍1
#እንዴት ናቹልኝ ባለፈው " የመንፈስ ከፍታ በፋርስ መንገድና እና የህልሜ ደራሲ " ከተሰኘው የገጣሚ በረከት በላይነህ የትርጉም እና የግጥም ስራዎች መሀል እዛው መፅሐፍ ላይ የሶስት ታላላቅ ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች የህይወት ታሪክ አለና #እኛም በጀላሉዱን ሩሚ ታሪክ ጀምረነው ነበር #ዛሬ ደሞ ባባ ጣሂር እንቀጥላለን .....ታሪኩን በድምፅ ከለጠቅነው ከግጥሞቹ ውስጥ አንዱን ለምን በፅሁፍ አንከትበውም በማለት ከተብነው.....
አንቺ ነሻ!
ጉልበተኛው ብርሃን ፣
ሀይለ-ሙሉው ፊትሽ ሳይሰንፍ የሚረጨው ፣
ሰንጥቆ ፣ በትኖ - ቀልቤን አቀጨጨው።
ስሚያቸው!
የተፈጥሮን ስሌት የማያውቁ ሁሉ ፣
"ባባ ገረጣብን!" "ጠቆረብን!" ሲሉ።
ገና ምን አዩና!
እንደጨው ሟሟለሁ፣
ነዳለሁ ፣ ከስላለሁ ፣ ረግፋለሁ - እንደጠል ፣
ድሮስ!
ፀሐይን አፍቅሮ ማነው ማይቃጠል?
መልካም ሰንበት!💚
@getem
@getem
@Nagayta
አንቺ ነሻ!
ጉልበተኛው ብርሃን ፣
ሀይለ-ሙሉው ፊትሽ ሳይሰንፍ የሚረጨው ፣
ሰንጥቆ ፣ በትኖ - ቀልቤን አቀጨጨው።
ስሚያቸው!
የተፈጥሮን ስሌት የማያውቁ ሁሉ ፣
"ባባ ገረጣብን!" "ጠቆረብን!" ሲሉ።
ገና ምን አዩና!
እንደጨው ሟሟለሁ፣
ነዳለሁ ፣ ከስላለሁ ፣ ረግፋለሁ - እንደጠል ፣
ድሮስ!
ፀሐይን አፍቅሮ ማነው ማይቃጠል?
መልካም ሰንበት!💚
@getem
@getem
@Nagayta
ግጥም ብቻ 📘
Audio
#እንዴት ናችሁልኝ በተከታታይ ጊዜ "የመንፈስ ከፍታ በፋርስ መንገድ እና የህልሜ ደራሲ " ከተሰኘው የበረከት በላይነህ መፅሐፍ ላይ ሁለት የተለያዩ ባለቅኔዎችን ታሪካቸውንና ስራዎቻቸውን አይተናል ...ዛሬ መደምደሚያችን የሚሆነው #ሀፊዝ ነው። ከላይ በድምፅ ያለው የሱ ቁንጥር ታሪኩ ስትሆን ከዚህ በታች ያለችው ደሞ ከመፅሐፉ ላይ ካሉት የሱ ግጥሞች መካከለሰ የወደድኳትን ናት....
ነገ ሲሰራ
ወንድሜ!
ጨንቆሀል?
ቀፎሀል?
ፈርተሀል?
ሰግተሀል?
በል አንሳ 'ጽዋህን' -ሀዘንህ እስኪጨንቀው፣
የቀረህን ፍሬ በወኔ ጭመቀው
ታዲያ ዋ!
የጭማቂህ ሙሌት እንዳይበዛው አረፋ፣
ትዝታ የወለደው ነስንስበት ተስፋ።
ሸጋ ምሽት!❤️
@getem
@getem
@Nagayta
ነገ ሲሰራ
ወንድሜ!
ጨንቆሀል?
ቀፎሀል?
ፈርተሀል?
ሰግተሀል?
በል አንሳ 'ጽዋህን' -ሀዘንህ እስኪጨንቀው፣
የቀረህን ፍሬ በወኔ ጭመቀው
ታዲያ ዋ!
የጭማቂህ ሙሌት እንዳይበዛው አረፋ፣
ትዝታ የወለደው ነስንስበት ተስፋ።
ሸጋ ምሽት!❤️
@getem
@getem
@Nagayta
👍1