#ይሄን_ታውቂው_ይሆን
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
.
ኤፊ ማክ
.
የቤቴን መግቢያ በር ፣
አሽሙረኛ አናፂ ፣ ወዳንቺ አቁሞት
ስትወጪ እንደ ፀሀይ ፣
ስትገቢ እንደጀምበር ፣ አያለሁ ባግራሞት
ታውቂው ግን እኔንጃ ፣
ተፈጥሮሽ ካይን ጋር ፣ እንዳለው ቃለ ውል
በሄድሽበት መንገድ ፣
ላፍታ ያየሽ ሁሉ ፣ አብሮሽ እንደሚውል
እንኳን የዘየርሽው ፣
ያኮረፍሺው ቢኖር ፣ እንዴት ሆኖ ሊሆን
የረገጥሽው አፈር ፣
ፍቅርሽ ለደቆሰው ፣ መዳኒት እንደሆን
ይሄን ታውቂው ይሆን?
ከሳቅሽ ሚቀዳው ፣
ካዘንሽ ሚሸመን ፣ የከተማው አየር
እንኳን የቤታችን ፣
የሰፈሩ ጠረን ፣ ባንቺ እንደሚቀየር
ሰንበት አስቀድሰሽ ፣
የቅድስናሽ ልክ ፣ በሰው አፍ ሲተረክ
እንኳን ጎረቤትሽ ፣
ሀገሬው በሙላ ፣ ባንቺ እንደሚባረክ
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አድባር እንደሚሉሽ ፣
ጥለት ሲዘቀዘቅ ፣ ሀዘን ቤት ሲጠና
አልቃሽ እና አስለቃሽ ፣
ሀዘንተኛ ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚፅናና
ፍቅር እና ክብር ፣
ሰዋዊ ግብረገብ ፣ በጎደላት አለም
ቅንዝረኛ ወጣት ፣
አየኋትኝ ብሎ ፣ እንደ ሚስለመለም
ኑሮሽ ሲስተካከል ፣
የቀበሌው ኗሪ ፣ ባንቺ እንደሚሸለም
ካንድ እራስሽ አልፈሽ ፣
ከስጡኝ ተላልፈሽ ፣ ስተርፊ ለብድር
አንዴ የማይበላ ፣
የድሃው ሰፈር ሰው ፣ ጠግቦ እንደሚያድር።
የማይሆነው ሁሉ ፣ ባንቺ እንደሚሆን!
ይሄን ታውቂው ይሆን?
አያድርገውና...
ድንገት ወንድ ካየን ፣ እቤትሽ ከትሞ
እኔና መሰሌ ፣
ወር እንደምንተኛ ፣ ጨጓራችን ታሞ
ይሄን ታውቂው ሆን?
አታውቂው ይሆናል ፣ እኔ ግን አውቃለሁ
በጉርብትናዬ...
ወድጄሽ ወድጄሽ ፣ ወድጄሽ አልቃለሁ።
።።።።።
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
አቦ ቅዳሜም አይደል የዳዊት ሙዚቃ እየሰማን ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው ...ምን ይላል ይሄ የኔ የሙዚቃ ንጉስ የመጀመሪያው የሙዚቃው የመጨረሻው የግጥሙ ስንኞች ላይ በዛ በሚገርም ድምፁ እንዲህ ይላል......
ባይወጉን አይደለም በነጭ ያልተገዛን
ተቸግረው እንጂ ስንሞት እየበዛን
ስንት ሺህ ጀግኖችሽ ከእነፈረሳቸው
ለፍቅር ሞተዋል ላንቺ ለእናታቸው
ምን ልሁን ባላገሩ❤️
ምን ልሁን ባለ-ሀገሩ❤️
#ይሄን እየሰሙ አለመገማሸር እንዴት ይቻላል ያውም በቅዳሜ ያውም በሸጋዋ ! ባለገር ሁኑ ሸጋ ቅዳሜ ጀባ!❤
@getem
@getem
@balmbaras

ለምሽታችን!
💚
“
´✍ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት!
በአንድ የገጠር ከተማ በርካታ ተማሪዎችን ሰብስበው የሚያስቀሩ አንድ ሸይኽ ነብሩ።አንድ ቀን ከነዚህ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ለሸይኹ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውና ወደ ከተማ ሄዶ ይህንን ለቀለብ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማፈላለግ እንዳለበት ይነግራቸዋል። #ሼይኹም ለተማሪያቸው ከፈቀዱለትና ስንቅ ካዘጋጁለት በኋላ መንገዱን ይጀምራል። ወደ እሚሄድበት ከተማ ለመድረስም ከመንገድ ያለን በረሀ ማቋረጥ ነበረበት። ይህንንም በረሃ አቋርጦ በሚሄድበት ወቅት አንድ የቆሰለ አሞራ ከመሬት ላይ መብረር የማይችል ሆኖ ይመለከተዋል። ታድያ ይህ ደረሳ በዚህ አሞራ ተፈኩር(ማስተንተን) ማድረግ ይጀምራል።
#በዚህ_በረሀ ውስጥ ምንም የሚቀመስ በሌለበት ይህ አሞራ ምን እየበላ ይሆን!?
#እንዴት_በህይወት መቆየትስ ቻለ!?
በዚህ መልኩ በተፈኩር ውስጥ ሳለ ከወደ ሰማይ ሌላ አሞራ ድንገት ከወደ ሰማይ ዱብ ይላል።
#ይህ_አሞራ የሚበላ ነገር በእግሮቹ አንጠልጥሎ ነበርና ለተጎዳው አሞራ ጥሎለት ሄደ። ያ የተጎዳው አሞራም የተጣለለትን ምግብ መመገብ ይጀምራል።
ተማሪውም በጣም ተገረመ። (መቼስ ፈጣሪ ነፍስን ከሪዝቋ ጋር እንጂ መች በባዶ ፈጠራት እና!) ብቻ ነገሩ እጅግ አስገርሞት እና አስደንቆት የሚሄድበትን በመሰረዝ ወደ ሸይኹ መመለስ ጀመረ። ለመመለሱ ምክንያትም ይህንን የተጎዳ አሞራ በዚህ በረሃ ውስጥ የሚመግብ እና የሚረዝቀው ፈጣሪ እኔንም ይመግበኛል ችግሬን ያስወግድልኛል የሚል ነበር። ወደ ሸይኹም እንደደረሰ የተመለሰበትን ምክንያት ይጠይቁታል።
ተማሪውም ያጋጠመውን ሁሉ ይነግራቸውና ፈጣሪው እሱንም ልክ እንደ አሞራው ሁሉ ከችሮታው እንደሚለግሰው ተስፋ አድርጎ መመለሱን ነገራቸው።
#ሸይኹም- ምነው !? እንደው እንተጎዳውና እርዳታ ፈላጊው አሞራ መሆንን ከመመኘት ለምን እንደ ረጂው እና ምግብን ተሸክሞ እንደተባበረው አሞራ መሆንን አልተመኘህም አሉት ይባላል።
---------------------------------------
#ሁሌም ቢሆን ትብብር እና እርዳታን ፈላጊ ከመሆን አንተው እራስህ ረጂ እና ተባባሪ መሆንን ምረጥ።
ከላይ ያለች እጅ ታች ካለች እጅ በላጭስ አይደለች!
#አሁን ወቅቱ ከመቼውም በላይ ቁጭ ብለን ለመረዳት ወይም ከመንግስት ብቻ መፍትሔ የምንጠብቅበት ጊዜ ላይ አይደለንም ሀገራችንን ፣ ወገኖቻችን ፣ ቤተሰቦቻችን ፣ ወገኖቻችን እንዴት ነው ከዚህ ችግር ልንከላከል የምንችለው ብለን በደንብ የምናስብበትና ወደ ተግባር የምንገባበት ጊዜ ነው....እናም ወንድምና እህቶቼ እቤት ከመቀመጥ በዘለለ ደሞ ማድረግ ስላለብን ነገሮች አስቡልኝ የኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ በየአካባቢው አይደል..? አቅም የሌላቸው የንፅህና ሳኒታይዘር ሆነ ምግብ መግዣ የሌላቸው ብዙ አሉ በየአካባቢያችን ስለዚህ እዚህ ቻናል ወንድሞችና እህቶች የምንችለውን እንርዳቸው ይሄን በሽታ የሚከላከሉበት ማቴሪያል እንርዳቸው ፣ የሚበሉትን ገዝተን እንስጣቸው በአቅማችን #ይሄኔ እኛም ለሀገራችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን.....ለምን አንድ ሳሙና አይሆንም ....
#ይሄን የምታነቡ ሰዎች ይሄን እንደምታደርጉ እናንተም የመፍትሔ አካል እንደምትሆኑ እምነት አለኝ🙏🙏🙏
ውብ ምሽት ትሁንላቹ!❤🙏
@getem
@getem
@Nagayta

#ይሄን ሞት ለመሻር !
....(ሚካኤል አስጨናቂ)....
፩
ለአዳም ዕፀ በለስ በእጇ አቀብላ
ለሞት ሞሸረችን ሄዋን ተደልላ
ፀጋችን ሲሸሸን ...
ሀፍረት ሲፈትነን ...
የቅጠሉን ገሳ ገላችን ላይ ጥለን
ክፉኛ ቆዝመን እየተማረርን
ሴትን ረገምን።
፪
ቃኤል በአቤል ላይ ድንጋዩን ሲያነሳ
ለስጋዊው መሞት ፍጥረት እጅ ነሳ
አቤል በመቃብር ወድቆ ስናስበው
የሞቱ መነሾ ምንጩ በሴት ልጅ ነው
ቃኤል በመንትያው ባይቀና በድንገት
መሞት ማሳረጊያ አይሆንም ለህይወት
ዳግም ሀዘን ወርሶን ያን ቀን እያሰብን
ሴትን ረገምን !
፫
የዮርዳኖስ ድንጋይ ፊርማ ውል ተሻረ
ፍጥረቱ ለገነት ደምቆ ተሞሸረ
በሞት ላይ ድል ያዝን ቆመን በሱባኤ
ፅልመትን የሚገልጥ በራልን ትንሳኤ
ከመነሳት ጀርባ ውሉን ስናጤነው
ከሞት የተነሳን ለካስ በሴት ልጅ ነው!
፬
ሄዋን የጠራችው በሴት ልጅ የመጣ
መሞት ተሸንፎ በሴት ልጅ ሲረታ
እኛም ደስ ብሎን በርሱ ስንኩራራ
የቃኤል ሞት አለ ከሰው ልጆች ጋራ
ዛሬም በዘመኔ
የበዙ ቃኤሎች.. . ድንጋይን የያዙ
ብዙ አቤሎችን.. . ከህይወት ሰረዙ
አሁንስ ምን ይሁን ... ይሄን ሞት ለመሻር
መፍትሄው ከሴት ነው ወይስ ነው ሁሌም ጣር?
ንገረን
ንገረን.. .
ሌላ ትንቢት አምጣ ...ሌላ ቃል ተናገር
ወይም መሲህ ሆነህ ...
ዳግም ኢትዮጵያ ላይ ከሴት ልጅ ተፈጠር?!
@getem
@getem
@getem
....(ሚካኤል አስጨናቂ)....
፩
ለአዳም ዕፀ በለስ በእጇ አቀብላ
ለሞት ሞሸረችን ሄዋን ተደልላ
ፀጋችን ሲሸሸን ...
ሀፍረት ሲፈትነን ...
የቅጠሉን ገሳ ገላችን ላይ ጥለን
ክፉኛ ቆዝመን እየተማረርን
ሴትን ረገምን።
፪
ቃኤል በአቤል ላይ ድንጋዩን ሲያነሳ
ለስጋዊው መሞት ፍጥረት እጅ ነሳ
አቤል በመቃብር ወድቆ ስናስበው
የሞቱ መነሾ ምንጩ በሴት ልጅ ነው
ቃኤል በመንትያው ባይቀና በድንገት
መሞት ማሳረጊያ አይሆንም ለህይወት
ዳግም ሀዘን ወርሶን ያን ቀን እያሰብን
ሴትን ረገምን !
፫
የዮርዳኖስ ድንጋይ ፊርማ ውል ተሻረ
ፍጥረቱ ለገነት ደምቆ ተሞሸረ
በሞት ላይ ድል ያዝን ቆመን በሱባኤ
ፅልመትን የሚገልጥ በራልን ትንሳኤ
ከመነሳት ጀርባ ውሉን ስናጤነው
ከሞት የተነሳን ለካስ በሴት ልጅ ነው!
፬
ሄዋን የጠራችው በሴት ልጅ የመጣ
መሞት ተሸንፎ በሴት ልጅ ሲረታ
እኛም ደስ ብሎን በርሱ ስንኩራራ
የቃኤል ሞት አለ ከሰው ልጆች ጋራ
ዛሬም በዘመኔ
የበዙ ቃኤሎች.. . ድንጋይን የያዙ
ብዙ አቤሎችን.. . ከህይወት ሰረዙ
አሁንስ ምን ይሁን ... ይሄን ሞት ለመሻር
መፍትሄው ከሴት ነው ወይስ ነው ሁሌም ጣር?
ንገረን
ንገረን.. .
ሌላ ትንቢት አምጣ ...ሌላ ቃል ተናገር
ወይም መሲህ ሆነህ ...
ዳግም ኢትዮጵያ ላይ ከሴት ልጅ ተፈጠር?!
@getem
@getem
@getem
👍2