ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ወንዶች በሴት አለም
(እሱባለው ኢ)
*
ማክስ ዌል ደራሲው
ስንኞችን ሲያርቅ
በሴቶች ሲደነቅ
*
ሲኦል ሆኖ ታየው ፤ ገነት ያለሚስቱ
አዘነ ለሕይወቱ
*
ከጻድቃኖች ተርታ ፤ ግራ ጎኑን ቢያጣ
እጅጉን ተቆጣ
'እሷ የሌለችበት ፤ ገነት ውስጥ ከምኖር'
ይሻለኛል ሲኦል
ከሷ ጋር ብቃጠል'
*
ያለው እውነቱን ነው።
***********
ያለ ሴቶች ስዬ ፤ያየኋትን አለም
ወና ምድር እንጂ፤ ፍጡር የለባትም።
*
ታላቁ እስክንድር
ግዛቱን ሊያሰፋ ፤ ቢመዝ ያንሁሉ ጦር
አላማው ሚስቱ ናት ፤ በሷ ለመከበር
በሷ እንዲደነቅ ፤ እሷም እንድትኮራ
ጦርነቱን አይቶ ፤ አለም እንዲፈራ።
*
ሌላው የወንድ አምሳል
ቢያሳንጽ ታጅ ማሃል
*
ሮማዊው ሴዛር ፤ አውሮፓን ቢመራ
ግዛቱን ለማስፋት ፤ሌተቀን ቢስራ
ከጁ እንድትገባ ነው
ውቧ ኪሎፓትራ ።
********
ወንዶች ባሮች ናቸው፤
ለሴት የሚኖሩ
ለሴቶች ተቀርጸው
ለሴቶች የሚያድሩ ።
*
እንጂማ
ወንዶች ጀግና አይደሉም ፤
በሰዉንታቸው
የሴት ዛርን ታቅፈው ፤
ታምር ቢያሰራቸው።
*
ተራራ ቢወጡ
ድንጋይን ቢፈልጡ
ሕዋ ላይ ቢደርሱ
አለምን ቢያስሱ
*
ያው ህልማቸው ሴት ነው ፤ መዳረሻው ቦታ
በዝናው አባብሎ፤ ሃሳቧን ሊረታ።
*
እንጂማ
የወንድ ጀግና የለም
ሴት ናት ያለም ጀግና
አሉ ሚባሉትን ባለሙሉ ዝና፣
ሱሪ አስወልቃ ፣
የምትገርፈው ታጥቃ፣
ሴት ናት ልዩ ፍጡር ፣
በዚህ ሰፊ ምድር።

ያለ ሴቶች ስዬ ፤ያየኋትን አለም
ወና ምድር እንጂ፤ ፍጡር የለባትም።
**************

( #ዛሬ_ፈላስፋው_በወንዶች_ላይ_ተነስቷል_ሴቶች_ተዘጋጁ )
Esubalew Ethiopian ሐምሌ 23/2010.

@getem
@getem
@lula_al_greeko
#ዛሬ በብሔራዊ ትያትር ከ 11:00 ጀምሮ !
ለምሽታችን
💚

#ዛሬ በወዳጄ በቀረበልኝ ግብዣ ምክንያት መሀል ሸገር አብዮት አደባባይ ላይ #አዲስአበባ ሙዚየም አደይ ሚክስድ አርት ኤግዚቢሽን ታድሜ ነበር .....ሸጋ ሸጋ የሆኑ የሚገራርሙ ሀሳብ ያላቸው ሚክስድ አርት አይቻለሁኝ...በጣም የወደድኳቸውን በስልኬ አስቀምጫለሁኝ አንድ ስዕል ብቻ ሳላነሳው መውጣቴ ቆጭቶኛል !!

ልጆቹ ከዚህም በላይ መስራት እንደሚችሉ ያስታውቃሉ.....ሁሉም ማለት ይቻላል ስለ ስራዎቻቸው ገለፃ ለማድረግ ያላቸው ፍላጎትና ተነሳሽነት የሚያስደስ ነው !!

ስዕል እና ግጥም የጥበብ ቁንጮ ናቸው በትንሽ ነገር ነፍፍፍፍፍፍፍፍ መልእክት ማስተላለፍ የሚችሉ የጥበብ ቁንጮዎች ንግስትና 👑 ንጉስ ናቸው #ለኔ!!

#በመጨረሻም እኔ አይቼ የወደድኳቸውን ሀሳባቸው እይታቸው ወድኩላቸው ስራዎችን ጀባ ልበላቹ እና ልሰናበት!

ሸጋ ምሽት!💚

@getem
@balmbaras
ለጁምኣችን
💚

#ዛሬ ከግጥም ወጣ ብለን ሸጋ የሆነች ወግ ብናወጋስ ማን ከልካይ አለን..? ማንም !!



ያው ጁመዐ አይደል ካነበብኩትና ከመሰጠኝ በኢራን የሚነገር ተረት ጀባ ልበላችሁ እነሆ
በረከት፦


አንድ ታላቁ መምህር የኢብን አል ሁሳይን ደቀ መዝሙር እንዲህ ሲል ጥያቄ ሰነዘረላቸው፦


በምን ያህል ጊዜ ልዩነት ዓለምን ከቆሻሻዋ ለማንፃት ይነሳሳሉ?


እርሳቸው ይህንን መለሱለት፦


በአንድ ወቅት በደማስቆ ከተማ የሚኖር አቡ ሙሳ አል ቁማሲ የሚባል ሼህ ነበር።
ከጥልቅ እውቀቱና ከጠቢብነቱ የተነሳ ማንም ሰው በተለየ አክብሮት እና አድናቆት
ይመለከተው ነበር። መልካም ሰው ስለመሆኑም የሚያውቅ ግን ማንም አልነበረም ።
በአንድ ወቅት ታዲያ ሼሁ ከሚስቱ ጋር የሚኖርበት ቤት በግንባታ እክል ምክንያት ወድቆ
ፈራረሰ። ያልተጠበቀው አደጋ ያደናገጣቸው ጎረቤቶቹም ፍርስራሹ መቆፈር ተያያዙት።
በዚህ ጥረታቸውም የሼሁ ሚስት የምትገኝበትን ስፍራ ማመላከት ቻሉ።


ወዲያውኑ ሚስት "ስለ እኔ አትጨነቁ ይልቅ ባለቤቴን ፈልጉት። ፈልጋችሁም አድኑት።
ወደዚያ ተቀምጦ ስለነበር ከውስጥ አንዳች ቦታ ተቀብሮ መኖር አለበት። እያለች መወትወት
ጀመረች። ጎረቤቶቹ ሚስት የጠቆመቻቸው አካባቢ ያለውን ክምር ፍርስራሽ በሙሉ
አንስተው ሲገላልጡት እንደተባለውም ሼሁን አገኙት ወዲያው ለጎረቤቶቹ የተናገረውን
ይህንን ነበር።


"ስለ እኔ አትጨነቁ። ይልቅ ቅደሙ እና ባለቤቴን ፈልጓት ፈልጋችሁም አድኗት። እዚያም
አከባቢ ጋደም ብላ ነበርና ፍርስራሹን ስር ተቀብራ ይሆናል።"
መምህሩም ታሪካቸውን በሚከታተለው ዓረፍተ ነገር ደመደሙ፦


"ሰው ሁሉ እንደነዚህ ጥንዶች መሆን ሲችል ዓለምን በጠቅላላ ከህመሟ ሁሉ እያነፃት
እንዳለ ይውቅ።"


መልካም ጁመዓ💚 "ናካይታ"💚

@getem
@getem
@balmbaras
#ዛሬ ራስ ሆቴል እንገናኝ!

# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 101ኛው ምሽት በራስ ሆቴል ይቀርባል


እንደምነው ሮብ፤ የሃሙስ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።

@getem
@balmbaras
#ዛሬ ራስ ሆቴል እንገናኝ!

# ጦቢያ ግጥም በጃዝ 102ኛው ምሽት በራስ ሆቴል ይቀርባል


እንደምነው ሮብ፤ የሃሙስ ጓደኛ ፤
እንገጥማለን ብለን፤ ሸዋ ገባን እኛ! !!!!
ነገር የመጣኝ ቀን ፤ ነገር እገጥማለሁ ፤
ግጥም የመጣኝ ቀን፤ ግጥም እገጥማለሁ ፤
ያገጣጠመኝ ቀን ግጣም እገጥማለሁ ፤
መግጠም ነው እንግዲህ ፤
ከዚህ ወዲያ ስራ ከወዴት ተገኝቶ ፤
አለም አይደለም ወይ ፤
መግጠም መገጣጠም ቁሞና ተኝቶ ።

ይኸው ነው!💚
@getem
@balmbaras
#ዛሬ አለም አቀፍ የራድዮ ቀን ነው ! የሸገሯን መዓዛ አለማመስገን ንፍጉነት ነው! መልካም የስራ ዘመን! ለሸገር ራድዮና ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ !


ማሪንጌ ቻ! !!!!!

ኧረ ሸገር ሸገር ፤ ሸገር ባውቶብሱ ፣
የመርካቶ ልጆች ፤
ሸ ከርተፍ እያሉ ፣ ከምኔው ደረሱ ።
ታምር አይደለም ወይ ፤ እንደ ሰማይ መና ፤
ሽበት ክብር ሲሆን ፤ እድሜና ቁመና ።
አስናቀ አስናቀ፤ አስናቀ ቢሉሽ ፤
ኬሬዳሽ በያቸው ፤አይስማ ጆሮሽ ፤
ቼ በይው ፤
ፈረሱን አቤ ነው ብለሽ ።
በደርባባው ዛትሽ ፤ በሁለመናሽ ፤
እንደ እቴጌ ማርዳ ፤ ያምራል ከራማሽ ፤
እድሜ ይቀጥላል ፤ ውብ አንደበትሽ ፤
መአዛ ማር ዘነብ ፤ መኣዛ ጥንቅሽ ።
ማሪንጌ ቻ ፤
ማሪንጌ ቻ ዘመናችን ይመር እንደ ማ'ዛ ብሩ ፤ እንደ አበበ በልቻ ።
ማሪንጌ ቻ! !!!

((( ጃ ኖ )))

መታፈር በከንፈር! !!!!! ያውም ደግሞ ልክ እንደ መኣዛ
ብሩ! !!!!


እናንት የጦቢያ እህቶቼ ሆይ! !!!!ከሴትነት ላይ የሰከነ
እውቀት ሲጨመርበት በዚያ ላይ ያደጉበትን ማህበረሰብ
ለዛና ወዘና ሳይለቁ የሚከወን ጋዜጠኝነት ከህዝባዊ
ሃላፊነት ጋር ተዋህዶ ሲገኝ ግዙፍ ከራማ ይሆንና ላገሩ
ለወንዙ የምትከብዱ እመቤታትና ወይዛዝርት አድርጎ
በጦቢያ ሰማይ ላይ ያነግሳችሃል! !! እንዲህም ያለ ነገር
በዚህች መአዛ ብሩ በምትባል የሸገር ራዲዮ ፊት አውራሪ
፤ ጦቢያዊት ደርባባ ሴት ዘንድ ሲፈጸም አይተናልና ደርባባ
እህትና እናት ያልነሳሃን ያገሬ ሰማይ በረካ ሁንልኝ እንጅ
ሌላ ምን እልሃለሁ! !!!

@Nagayta
@getem
@getem
#ዛሬ ፎቶ ብናነብስ ከላይ ያለውን ፎቶ ተመልከቱት ከዛም ሀሳባቹን አካፍሉን 🙏
@Ribki
@Nagayta
#ሀንግ #ኦቨር

የደሀውን ለቅሶ ~ የምስኪኑን ጩኸት
አላሰማም ብሎህ ~ የቢላዎች ፉጨት
ነብስህ ተከልላ ~ በስጋ አለም ስላቅ
ከታናሽ ላይ ቆርጠህ ~ አጉርሰህ ለታላቅ
ለማወራረጃ ~ ብርጭቆ ብትይዝም
ቀዝቀዝ ያለ ሁሉ ~ አያቀዘቅዝም
አያጠፋልህም
የነብስህን እሳት ~ ከስጋህ ነጥሎ
አያበርድልህም
የውጪው ቀዝቃዛ ~ የውስጥን ቃጠሎ
እውነቱ እንደዚህ ነው ~ እመነኝ ግዴለም
ከእርዛት ነጥቆ ~ በሚደርብ አለም
የሚያልበው ሁሉ ~ የሞቀው አይደለም

#ዛሬ
በንብረትህ ብዛት~ፍቃድ ስር ብትወድቅም
በጉብዝናህ ወራት ~ ለማሰብ ባትፈቅድም
ልክን ማሳወቅ ነው ~ የመለኪያ ጥቅም

#ከሰማህ #ልንገርህ
ግፍ እንደ ፍግ ሆኖህ
ከእድሜህ በላይ በቅለህ~ከሀገሬው ብትበልጥም
ደሀ ባፈሰሰው
የእንባ በረዶ ~ ውስኪ አይጨለጥም
===||===
ከሙሉቀን ሰ•

@getem
@getem
@getem
#ዛሬ ምሽቱን በድምፅ ጀምረነው በፅሁፍ እናጠናቀው ብዬ ነው ከላይ የሰማችሁት ሁለቱ ድምፆች "የመንፈስ ከፍታ በፋርስ መንገድ እና የህልሜ ደራሲ" ከሚለው 2005 የወጣው የገጣሚ በረከት በላይነህ መፅሐፍ ነው መፅሐፉ የሶስት ገጣሚዎች ማለትም የሩሚ ፣ ባባ ጣሂር እና የሀፊዝ የግጥም ስራዎች ትርጉም (ያ በረከት በመፅሐፉ መግቢያ ላይ "ተረጎሙኝም፣ተረጎምኳቸውም" ነው የሚለው።) የራሱ የበረከት በላይነህ ግጥሞች የተከተቡበት ሸጋ መፅሐፍ ነው ...በዚህ መፅሃፍ ከላይ የተጠቀሱትን ሶስቱ ገጣሚዎች የህይወት ታሪካቸው ለቅምሻ ለቅምሻ ያህል አሉበትና ስለወደድኳቸው ወደናንተ ይዣቸው መጥቻለሁ እንደጅማሮ "ሩሚ የናፍቆት መንገደኛ" የተሰኘውን ዛሬ እዚሁ የቴሌግራም ግርግዳ ለጥፌዋለሁ በቀጣይ ደሞ አላህ ቢሻ የሁለቱን አቀርባለሁ። አሁን ወደ ውብ ምሽታችን......

ለምሽታች እንካቹ ጀባታ!
💚

ግጥምና ገጣሚያን (በነብዩ) በካሕሊል ብዕር!
-
አራት ገጣሚያን ወይን በተሞላ ጽዋ ዙሪያ ተቀምጠው እየተወያዩ ነበር። ከመካከላቸው
አንዱ እንዲህ አለ፦
-
"እነሆ የዚህ ወይን ሽታ ሰማዩን እንደሸፈነ የአእዋፍ ደመና በጫካ አናት ላይ ሲያንዣብብ
በሦስተኛው ዓይኔ ተመለከትኩ!"
-
ሁለተኛውም ተቀበለና፦ "የነዚህን ጣፋጭ ወፎች ዝማሬ በውስጠኛው ጆሮዬ
አደመጠኩት፤ ጥዑም ነው ሲል ገለጸ!"
-
ሦስተኛውም፦ "ኦ! የሚያምር ላባቸው መዳፌን ሲዳስስ ይሰማኛል፤ እንዴት ይለሰልሳል!!"
በማለት ዐይኑን ጨፍኖ አደነቀ።
-
አራተኛው ግን በተራው እንዲህ አለ፦ "እኔ እንደናንተ ልዩ አይደለሁም። ሦስተኛ ዓይን፣
የውሰጠኛ ጆሮና ምትሀታዊ መዳፍ የለኝም። ወይንን የማደንቀው በማጣጣም ነው!" አለና
ያንን ጽዋ ሙሉ ወይን አነሳና ጨለጠው። ሁሉም በተጠሙ ዐይናቸው አፍጥጠው
ተመለከቱት!!
-
ግጥም የአመለካከት መግለጫ አይደለም። ከአመረቀዘ ቁስል የሚፈስ ደም ወይም በብሩህ
ጸዳል ፈገግ ካለ የፊት ገጽ ላይ እነደሚንቆረቆር ዜማ ነው። ገጣሚም ከተቃጠለ የቤተ
መንግስቱ አመድ ላይ ምስል ለመፍጠር እንደሚጥር፤ ከዙፋኑም እንደ ወረደን ንጉሥ ነው።
-
እነሆ በምሑርና በገጣሚ መካከል ሰፊ አረንጓዴ መስክ አለ። መስኩን ምሑሩ ቢሻገረው
ጠቢብ ይሆናል፤ ገጣሚው ቢሻገረው ግን ነብይ ይሆናል!

@getem
@getem
@Nagayta
ዘላለማዊ ጥሪ!


#ዛሬ ዓለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች በርካታ ትዝታዎችን ያስተናግዳሉ።
የሩቅም የቅርብም ዘመን ትዝታዎች።

ኢብራሒምን ያስታውሳል። የሚወዷትን ባለቤታቸውንና የአብራካቸውን ክፋይ። ልጃቸውን
ከባዶ በረሃ ላይ ለአላህ አደራ ሰጥተው ሲሄዱ ፣ እንዲህ እያሉ ሲለምኑት።
<< ጌታችን ሆይ ! ዘሮቼን አንድም አዝርዕት በሌለበት ሸለቆ ውስጥ ከተከበረው ቤትህ
አጠገብ ትቻቸዋለሁ። ጌታችን ሆይ …ቀልቦች ሁሉ ወደ እነርሱ እንዲዘነበሉ አድርግ።
ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍራፍሬዎች ለግሳቸው።>>
ሃጀርን ያስታውሳል ። በዚያ በረሃ ውስጥ ለሷና ለልጇ ውሃ ፍለጋ ከሶፋና መርዋ መሃል
ስትባዝን። ጥም አቃጥሏት። ከ7 ጊዜ ምልልስ በኋላ ውሃ ከምድር ፈልቆ ስታገኝና በደስታ
ስትዋጥ። ያ የተከበረው ውሃ ዘምዘም ነው። በደረቅ በረሃ ውስጥ የፈነዳ የአላህ እዝነት
መገለጫ።
ኢብራሒምም ትዝ ይሉታል።



ልጅ አልባ መሆናቸው ታስቧቸው አላህን ልጅ ሲለምኑት፣
እርሱም በጎ ምላሽ ሲሰጣቸው፣ እድሜያቸው ከገፋ በኋላ ኢስማኢልን ሲወልዱ፣ እርሱ
እድሜው በጨመረ ቁጥር የርሳቸው ደስታና ተስፋም እብሮ ሲጨምር ፣ በድንገት ግን
ልጃቸውን፣ ተስፋቸውን ፣ ኢስማኢልን እንዲያርዱ ሲታዘዙ ጭንቀታቸው ይታወሰዋል። <<
ልጄ ሆይ ፣ በሕልሜ እንዳርድህ ታዘዝኩ። ምን ታስባለህ? ሲሉት። ኢስማኢልም ቅንጣት
ሳያመነታ የአላህን ትዕዛዝ ሲቀበል ፣ << አባዮ ሆይ ፣ የታዘዝከውን ፈፅም። በአላህ ፈቃድ
ታዛዥ ሆኜ ታገኘኛለህ ሲላቸው በሕሊናው ይታሰባዋል። አባት ልጃቸውን ፣ ልጅ ህይወቱን
ለአላህ ክብር ሲለግሱ ፣ አላህ መስዋዕት በመላክ ሁለቱንም ከጭንቀት ሲታደጋቸው
ያስታውሳል።
አባትና ልጅ የአላህን ቤት ለማቆም ደፋ ቀና ሲሉም ይታወሰዋል። እንዲህ እያሉ ሲማፀኑት
<< …ጌታችን ሆይ ስራችንን ተቀበለን። አንተ ሰሚም አዋቂም ነህና። ጌታችን ሆይ
ሙስሊሞች አድርገን። ከዝርያችንም ሙስሊም ህዝብ አድርግልን።...>>
ምዕተ ዓመታትን ተሻግሮ ነብዩን (ሰዐወ) ያስታውሳል ። እነህ ታላቅ ስብዕና የወጡትን
መስክ በአድናቆት ይመለከታል። መላ ሕይወታቸው በአይነ ህሊና በረድፍ ይታየዋል።
የሕፃንነት ጊዜያቸው ፣ ሕይወታቸው፣ ለሰው ልጆች ደህንነት ሲሉ የከፈሉት ግዙፍ
መስዋዕትነት ፣ አቻ የለሽ ትግላቸው ፣ ያ ሁሉ ልፋትና ድካም ፣ ስደቱ ፣ መዲና ውስጥ
የመጀመሪው ትውልዱ አባት ሆነው ሲያሰግዱ፣ መምህር ሆነው ሲያስተምሩ፣ መንበር ላይ
ሆነው ኹጥባ ሲያሰሙ፣ ሃገር ሲመሩ ...።
ያ ትውልድም ይመጣበታል። ነብዩ (ሰዐወ) ኮትኩተው ያሳደጉት ድንቅ ማህበረሰብ።
አቡበክርና ኡመር፣ ኡስማንና አሊይ ፣ ጦልሃና ዙበይር ፣ እነ ዓዒሻ ፣ እነ ኢብኑ መስዑድ ፣
እነ ኢብኑ አባስ ሁሉም በአይነ ህሊናው በረድፍ ያልፋሉ ።
ይህ ሁሉ ትዝታ መንፈስን ያበለፅጋል። እምነትን ያጎለብታል። ስሜትን ያድሳል።
ሐጅ ከዚህም በቀር ዓለምአቀፍ ጉባኤ ነው። ሙስሊሞች በአንድ አቂዳ ስር ለአንድ ዓላማ
በየዓመቱ የሚያካሂዱት ታላቅ ስብሰባ። በእኩልነት። ዘር ፣ የቆዳ ቀለም ፣ ሃገር ሳይለያቸው
የአንድነታቸው መገለጫ የሆነውን ተመሳሳይ ልብስ ለብሰው።
አላህ (ሱወ) ወዳጆቹ፣ ህዝቦቹ የሚገናኙበት፣ የሚተዋወቁበት፣በረከቱን የሚያወድሱበት፣
የሚወያዩበት መድረክ አመቻችቶላቸዋል። ሙሰሊሙ ህዝብ በአንድ አንዲሰባሰብ፣
እንዲዋደድ፣ አንዲፋቀር፣ ፍፁም አንድ አንዲሆን፣ አንድ ህዝብ፣ አንድ መርህ፣ አንድ
አምነት፣ አንድ ዓላማ ፣ የዚህ ሁሉ ውህደትና አንድነት አንዱ መገለጫ መንገድ ሐጅ ነው።
የቦታ ርቀት ሳይበግራቸው፣ ቋንቋና የዘር መጋረጃ ሳይጋርዳቸው፣ ለአንድ ዓላማ፣ በአንድ
ልብ፣ ከአራቱም አቅጣጫ ተጠራርተው፣ አንድ አይነት ለብሰው፣ በአንድ ቆመው፣ ፊታቸውን
ወደ አንድ አቅጣጫ አዙረው፣ አንድ ጌታን እያወሱ፣ ለሱ እያለቀሱ ሊዋደዱ፣ ችግሮቻቸውን
በጋራ ሊያስወግዱ፣ ሊማማሩ፣ ሊመካከሩ፣ ሲገናኙ ከዚህ የበለጠ ውህደት፣ ከዚህ የበለጠ
አንድነት ይኖር ይሆን? የባህል ፣ የንግድ ፣ የተሞክሮ ፣ ልውውጥ ያደርጋሉ። በአላህ ቤት
ውስጥ። በአላህ ጥላ ስር።

ለኢስማኢል ፊዳ ሆኖ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን በግ ለማስታወስ መስዋዕት ያቀርባሉ -
ሃጃጆቹ። መስዋዕቱ ከዚህም በላይ ኢባዳ ነው። ድሆችም ከእርዱ ይመገባሉ።


ውሃ ከማይፈልቅበት፣ እርጥበት ከማይታይበት፣
ለዓይን አንኳ ለምለም ዛፍ ከጠፋበት፣ ጭው ያለ ደረቅ በረሃ ውስጥ ኢስላም ለዓለም
አለኝታን ለተጨቆኑት መከታ ለመሆን ከዘላን ህዝቦች መሃል መፍለቁን
ለ1400 ዓመታት ያህል ወደ ኋላ ተመልሶ በእፅንዖት ማስታወሱ ብቻ በቂ ነው።
ያ ጀግና ትውልድ ፣ ያ ተዓምረኛ ትውልድ ዓለምን ሊመራ ፣ ስለ እውነት ሊዋደቅ ፣ የአዳምን
ዘር ከብዙ አማልክት ባርነት ወደ አንድ አምላክ አምልኮ ነፃነት ፣ ከጠባብ ቁሳዊ ህይወት
ወደ ሰፊው ብሩህ እምነት፣ ከሰው ሰራሽ ስርዓቶችና አምነቶች ጭቆና ወደ ኢስም ፍትህ
ሊሸጋግር ከዚያ አሸዋማ መሬት የፈለቀ መሆኑን ማስታወስ ብቻ ወደር የለሽ ሀሴትን
ይለግሳል።
<<ጥቅሞቻቸውን ሊጣዱ>>


ለበይክ አሏሁመ ለበይክ
ለበይከ-ላሸሪከለከ-ለበይክ
ኢነል ሃምደ-
ወኒዕመተ
ለከረል ሙልክ-
ላ ሸሪከ-ለክ!!
-
አረፋ የመስዋዕትነት፣ የመታዘዝና የምህረት በዓል ነው።
ሁሉም ነገር በቦታውና በጊዜው ያምራል።❤️
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ

በዓሉን ለደካሞች በማካፈል ይበልጥ እናድምቀው!

@getem
@getem
@Nagayta
👍3
#እንዴት ናቹልኝ ባለፈው " የመንፈስ ከፍታ በፋርስ መንገድና እና የህልሜ ደራሲ " ከተሰኘው የገጣሚ በረከት በላይነህ የትርጉም እና የግጥም ስራዎች መሀል እዛው መፅሐፍ ላይ የሶስት ታላላቅ ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች የህይወት ታሪክ አለና #እኛም በጀላሉዱን ሩሚ ታሪክ ጀምረነው ነበር #ዛሬ ደሞ ባባ ጣሂር እንቀጥላለን .....ታሪኩን በድምፅ ከለጠቅነው ከግጥሞቹ ውስጥ አንዱን ለምን በፅሁፍ አንከትበውም በማለት ከተብነው.....

አንቺ ነሻ!

ጉልበተኛው ብርሃን ፣
ሀይለ-ሙሉው ፊትሽ ሳይሰንፍ የሚረጨው ፣
ሰንጥቆ ፣ በትኖ - ቀልቤን አቀጨጨው።

ስሚያቸው!
የተፈጥሮን ስሌት የማያውቁ ሁሉ ፣
"ባባ ገረጣብን!" "ጠቆረብን!" ሲሉ።
ገና ምን አዩና!
እንደጨው ሟሟለሁ፣
ነዳለሁ ፣ ከስላለሁ ፣ ረግፋለሁ - እንደጠል ፣
ድሮስ!
ፀሐይን አፍቅሮ ማነው ማይቃጠል?


መልካም ሰንበት!💚

@getem
@getem
@Nagayta
#ዛሬ ቅዳሜ ነው! እና ምን ይጠበስ? ከማለትህ በፊት አድምጠኝማ ሸጋው....

ጀመአው ወሎን እወዳለሁ ትላለህ።በጄ ብለን በደንብ ታውቃት ዘንዳ ትንሿን ወሎ በምሀል አዲስ አበባ ሰርተንልሀል።
ከትላንት ጀምሮ ሸገር ላይ ስንገማሸርበት ነበርማ አንተም ሰንዳ በል እንጂ

አድራሻ የት መሰለህ ኢቲዮ ኩባ ወዳጅነት ፓርክ (ሰምአታት ሀውልት)
ጥቁር አንበሳ ፖስታ ቤት ፊት ለፊት።

የወሎ አልባሳት ፣ የወሎ ጭስ ፣ የተለያዩ መፅሐፍቾች ያው 😁 እድለኛ ከሆንክም አንዷን የወሎ ቆንጆ ባዛሩ ላይ አግኝተህ የግራ ጎንህ ታደርግ ይሆናል ማን ያውቃል.....


ሸጋ ቅዳሜ!ከሰዓት እዛ እንገናኝ.....

@getem
@getem

@Nagayta
@balmbaras
👍18🤩2😱1