መሆኗን ሲያንጎራጉር ኖሯል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥላሁን በሴት መስሎ በፍቅር አምሳል የተጫወታቸውንም ስራዎቹን ብናይ ትንፋሹ ሊገልፅና ሊወክል የፈለገው ሀገርን እንጂ አንዲትን ኢትዮጲያዊ ሴት ላለመሆኑ ግልፅ ነው…..ለምሳሌ የጠላሽ ይጠላ ሲል ፣ እኔ ልሁን እንጂ የማልጠቅም ርካሽ ሲል ፣ እዩአት ስትናፍቀኝ ሲል በዚያ ገፀ ባህሪው ኢትዮጲያ ናት….ቁስሉና ርሃቡ ሀገር ናት፡፡ ከመጀመሪያ ስራው ጥላ ከለላዬ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ስራው ቆሜ ልመርቅሽ ድረስ ሀገር በትንፋሹ ስትነግስ ፣ በድምፁ ስትከብር ኖራለች፡፡
በቀጣይነት ጥላሁንን እንደ አርበኛ ፣ እንደ ሙዚቀኛ ፣ እንደ ተዋናይ ምን ሰርቶ እንዳለፈ ፣ ምናችን እንደነበረ እንቃኘዋለን፡፡ ብሎም ብዙ ሊተነተኑ የሚችሉ ሙዚቃዎቹን እያስተነተንን በምናብ ከርሱ ጋር እናወጋለን …በመልክት ለቀጣይ ተተኪ የቤት ስራ እናኖራለን….በግርምት በስራዎቹ እንደሰታለን ብዬ አስባለሁ፡፡
‹‹ትንፋሼ ተቀርጾ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይህ ነው የሞትሁ’ ለት የኔ ማስታወሻ››
ብሎ ነበር ንጉሳችን፡፡ በእርግጥ እሱ እንዳለው ትንፋሹ ነው ማስታወሻችን ብለን ከሃሳቡ መስማማት እንችላለን…በትንፋሹ ውስጥ የገለፃት ኢትዮጲያ ነችና…..በውስጣችን ለዝንታለም ትንፋሹ ትንፋሻችን ኆኖ ዘልቋል ይዘልቃልም፡፡
መልካም ዕለተ መስቀል ይሁንላችሁ
# ከታቢው ስንታየሁ አለማየሁ
#እኛም ጋሽ ጥላሁንን ለመዘከር በድምፅ አንጎራጉረናል
ሸጋ ምሽት!💚
@getem
@getem
@balmbaras
በቀጣይነት ጥላሁንን እንደ አርበኛ ፣ እንደ ሙዚቀኛ ፣ እንደ ተዋናይ ምን ሰርቶ እንዳለፈ ፣ ምናችን እንደነበረ እንቃኘዋለን፡፡ ብሎም ብዙ ሊተነተኑ የሚችሉ ሙዚቃዎቹን እያስተነተንን በምናብ ከርሱ ጋር እናወጋለን …በመልክት ለቀጣይ ተተኪ የቤት ስራ እናኖራለን….በግርምት በስራዎቹ እንደሰታለን ብዬ አስባለሁ፡፡
‹‹ትንፋሼ ተቀርጾ ይቀመጥ ማልቀሻ
ይህ ነው የሞትሁ’ ለት የኔ ማስታወሻ››
ብሎ ነበር ንጉሳችን፡፡ በእርግጥ እሱ እንዳለው ትንፋሹ ነው ማስታወሻችን ብለን ከሃሳቡ መስማማት እንችላለን…በትንፋሹ ውስጥ የገለፃት ኢትዮጲያ ነችና…..በውስጣችን ለዝንታለም ትንፋሹ ትንፋሻችን ኆኖ ዘልቋል ይዘልቃልም፡፡
መልካም ዕለተ መስቀል ይሁንላችሁ
# ከታቢው ስንታየሁ አለማየሁ
#እኛም ጋሽ ጥላሁንን ለመዘከር በድምፅ አንጎራጉረናል
ሸጋ ምሽት!💚
@getem
@getem
@balmbaras
# ኤፍሬም_ስዩም እንደፃፈው
# ኑ_ግድግዳ_እናፍርስ_2008
# የማርያም_ንግስ_እለት ።
.
አዳፋ ነጠላ በቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ. ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፥ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች .........
ከቤተክርስቲያን አፀድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት .....ትለማመን ነበር
,
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል።
,
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
ከቤተክርስቲያን ጓሮ ቆማ ከዋርካ ስር።
,
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምዕመን ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል።
,
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደመወዝ ሊጨመር ግድ ይላል
3
ደጀ ሠላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ......
.
እናም.......
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እጃቹ የት - አለ?
እያለ።.....
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል።......
ለንግሱ የመጡ.....
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች....
ጥለት የለበሱ ፥ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ....እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሠላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በሺ .....የሚቆጠሩ
ብሮች ወረዋሩ....
.
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ውዛ
የሚወረወረው ብሩም በጣም በዛ።
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካ ስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር::
,
ኣደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል
አንቺ ነሽ ተስፋዬ የኔስ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች።
,
,
ግና ግን ለዛሬ ፥ ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጂ አምሃዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የኣንገት ሃብሌን::
#እኛም በድምፅ እንዲህ ሞከርነው....
@getem
@getem
@balmbaras
# ኑ_ግድግዳ_እናፍርስ_2008
# የማርያም_ንግስ_እለት ።
.
አዳፋ ነጠላ በቀጠነ ገላ ፥ ነፋስ የሚጥለው
የነተበ ጫማ. ጥቁር ያዘን ቀሚስ ፥ ኑሮ ያጨቀየው
ለብሳ የተገኘች .........
ከቤተክርስቲያን አፀድ ፥ ቆማ ከዋርካ ስር
አንዲት ምስኪን ባልቴት .....ትለማመን ነበር
,
አደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝ መሶቤ ተራቁቷል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል።
,
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር
ከቤተክርስቲያን ጓሮ ቆማ ከዋርካ ስር።
,
የደብሩ አለቃ
ካባ ላንቃ ለብሶ ምጣህቱን ደርቦ
ልክ የሌለው ቦርጩ ወደፊት ተስቦ
የንግሱን ምዕመን ወደፊቱ ስቦ
ጮክ ብሎ ያወራል
ጮክ ብሎ ያስተምራል።
,
1
የመቅደሱ ቀለም ሊታደስ ይገባል
2
የካህናት ደመወዝ ሊጨመር ግድ ይላል
3
ደጀ ሠላም ወንበር እጅጉን ያንሰናል ......
.
እናም.......
በዚህ ታላቅ ደብር ይህ ችግር ስላለ
ለማርያም የሚሆን እጃቹ የት - አለ?
እያለ።.....
ህዝቡን ያስተምራል
ህዝቡን ይደልላል።......
ለንግሱ የመጡ.....
ባለ ብዙ ብሮች
ብዙ ባለጠጎች....
ጥለት የለበሱ ፥ በሽቶ የራሱ
ቆመው የነበሩ....እፊት ከመቅደሱ
ቀለም እንዲቀባ እንዲታደስ ደብሩ
ለደጀ ሠላሙ ደግሞም ለወንበሩ
በሺ .....የሚቆጠሩ
ብሮች ወረዋሩ....
.
የደብሩ አለቃ ግንባር በጣም ውዛ
የሚወረወረው ብሩም በጣም በዛ።
.
የዛች የምስኪን ነፍስ
ያች ታላቅ መቅደስ
ቆማ ከዋርካ ስር
ተስፋዋ ማርያምን ትለማመን ነበር::
,
ኣደራሽን ማርያም
አደራሽን ማርያም
እበላው የለኝም መሶቤ ተራቁቷል
እጠጣው የለኝም ማድጋዬ ጎድሏል
እለብሰው የለኝም ጀርባዬ በርዶታል
አንቺ ነሽ ተስፋዬ የኔስ ተስፋ ሞቷል
ወድቃ እየተነሳች
እምባ እያፈሰሰች።
,
,
ግና ግን ለዛሬ ፥ ለክብርሽ እንዲሆን
ተቀበይ ስጦታ ውሰጂ አምሃዬን
የሟች ባሌን ማስታወሻ የኣንገት ሃብሌን::
#እኛም በድምፅ እንዲህ ሞከርነው....
@getem
@getem
@balmbaras
#እንዴት ናቹልኝ ባለፈው " የመንፈስ ከፍታ በፋርስ መንገድና እና የህልሜ ደራሲ " ከተሰኘው የገጣሚ በረከት በላይነህ የትርጉም እና የግጥም ስራዎች መሀል እዛው መፅሐፍ ላይ የሶስት ታላላቅ ገጣሚዎችና ባለቅኔዎች የህይወት ታሪክ አለና #እኛም በጀላሉዱን ሩሚ ታሪክ ጀምረነው ነበር #ዛሬ ደሞ ባባ ጣሂር እንቀጥላለን .....ታሪኩን በድምፅ ከለጠቅነው ከግጥሞቹ ውስጥ አንዱን ለምን በፅሁፍ አንከትበውም በማለት ከተብነው.....
አንቺ ነሻ!
ጉልበተኛው ብርሃን ፣
ሀይለ-ሙሉው ፊትሽ ሳይሰንፍ የሚረጨው ፣
ሰንጥቆ ፣ በትኖ - ቀልቤን አቀጨጨው።
ስሚያቸው!
የተፈጥሮን ስሌት የማያውቁ ሁሉ ፣
"ባባ ገረጣብን!" "ጠቆረብን!" ሲሉ።
ገና ምን አዩና!
እንደጨው ሟሟለሁ፣
ነዳለሁ ፣ ከስላለሁ ፣ ረግፋለሁ - እንደጠል ፣
ድሮስ!
ፀሐይን አፍቅሮ ማነው ማይቃጠል?
መልካም ሰንበት!💚
@getem
@getem
@Nagayta
አንቺ ነሻ!
ጉልበተኛው ብርሃን ፣
ሀይለ-ሙሉው ፊትሽ ሳይሰንፍ የሚረጨው ፣
ሰንጥቆ ፣ በትኖ - ቀልቤን አቀጨጨው።
ስሚያቸው!
የተፈጥሮን ስሌት የማያውቁ ሁሉ ፣
"ባባ ገረጣብን!" "ጠቆረብን!" ሲሉ።
ገና ምን አዩና!
እንደጨው ሟሟለሁ፣
ነዳለሁ ፣ ከስላለሁ ፣ ረግፋለሁ - እንደጠል ፣
ድሮስ!
ፀሐይን አፍቅሮ ማነው ማይቃጠል?
መልካም ሰንበት!💚
@getem
@getem
@Nagayta