ግጥም ብቻ 📘
67.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
174 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተረኛ ነህ ተነስ !

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።

#እግዜርን ቀስቅሱት!

ከተኛበት አንቁት.. .

ዝም ብለህ ነበር ፥ አሸልበህ ነበር

ሲተራመስ ሀገር ፥ ቅጡን ሲስት መንደር

ብላችሁ ንገሩት! 

#አርምሞህ አይሎ ፥ እሳት ሆኖ ፈጀን

እንዳበደ ውሻ ...

አቅሉን እንደሳተ ፥ እኛን አናከሰን 

እንባችን ፈሰሰ 

ባለም ተዳረሰ 

ክብራችን ተጣለ 

ኩራትም ጎደለ 

አቀርቅረን ቀረን 

ጀርባ ሰጠን ዘመን

#በእረፍታችን ማግስት ፥ በሞታችን ሳልስት

"ኩራትን አክብሩ" ፥ ብሎ የሚቧልት

ተነሳብን መንግስት !

አሁን ምን ይሉት ነው ?

እንዲህ ያለ ፈሊጥ ፥ የነገር ጨዋታ

የኩራት ቀን ማክበር ...

ከራት በሞተበት ፥ የመቃብር ቦታ?

ብላችሁ ጠይቁት !

ጎደልን !

ጎደልን!

ከክብር ተጣልን ...

መውደድ ፅፈት ሆኖ ፥ ቀረ በወረቀት 

ፍቅር በቃል ወርዶ ፥ ሰማን እንደተረት

ህዝብህ ሽንቁር ሆነ ፥ ጠፋ አንዳች ውታፍ

ገላውን ገረፈ...

እርሱ ባበጃጀው ፥ በገመደው ጅራፍ ።

ብላችሁ ንገሩት!

#አሁን ምን ይሉት ነው ?

ፍቅር በሞተበት ፥ በሰነፎች ሀገር 

"የፍቅር ቀን" ብሎ ፥ የቃል ፍቅር ማክበር?

ብላችሁ ጠይቁት ! 

ዝም ያለም እንደሆን.. .

እንዳምናው ካቻምናው ፥ እንደዛኛው ዘመን 

ዛሬ ቀን ከፋብህ 

የስላቅ ጨዋታው ባንተም ደረሰብህ ።

የእኛ ቤት ፈርሶ ...

ቅጥራችን ተድሶ ...

ዝም ብለህ ስታፌዝ ፥ ስትስቅ በሰው ለቅሶ

ያንተም ቤት ነደደ ፥ መቅደስህ ፈራርሶ ።

አሁንስ ምን ቀረህ?

እናትህ ስትነድ ፥ እሳት ሲለቁባት 

በል ሰይፍህን ምዘዝ ፥ ዝምታህን ሻራት ።

ብላችሁ ንገሩት.. .

እግዜሩን ቀስቅሱት !!

@getem
@getem
@getem
#ቸል እያሉ መጉደል! 

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።።።።።።።።።።።።
ለቅፅበት ህላዌ ፥ ተግተው 'ሚባትሉ

በህብር ታጅበው ፥ ጭረው የሚውሉ

ዶሮዎች!

ለቅመው አዳሪዎች...

ከእጀባው ወጥታ.. .. ከመንጋው ተጠቅታ

በታደነች ጫጩት.. .

ሀዘን ተሸብረው ፥ ለስጋት ተድረው ፥ ጮኸው ይንጫጫሉ

ከአፍታ በኋላ.. .

ዳግም ፍርሀት ሽረው ፥ በኗሪነት ተስፋ ፥ ጥሬ ይለቅማሉ ።

#እነዛ ዶሮዎች.. .

አንድም በፍርሀት 

አንድም በቸልታ

አንድ ጊዜ በጩኸት

አንዴ በፀጥታ...

ጥሬ ሲናጠቁ ፥ መሬት እየጫሩ

ከቁጥር ተናንሰው ...

ከመንጋነት ጎድለው ፥ ምንም ሆነው ቀሩ።

#አሁን በዛ መሬት!

ለቅፅበት ህላዌ ፥ ተግተው 'ሚባትሉ 

በህብር ታጅበው ፥ ጭረው የሚውሉ

አዳዲስ ዶሮዎች.. .

ጭሮ አዳሪዎች.. .

አንድም በፍርሀት 

አንድም በቸልታ 

አንድ ጊዜ በጩኸት

አንዴ በፀጥታ...

ኗሪ ነን እያሉ ... ጥሬ ይለቅማሉ ።

#እኔ

#ድመት ይታየኛል!

እንደ ሙት መልዓክ ፥ ጥፍሮቹን ያሾለ

ነፍስን ጌጥ አድርጎ ፥ አይኖቹን የኳለ

ጨለማውን ህልፈት ፥ ጀርባው ላይ ያዘለ

ቀስ እያለ ይቀርባል.. .

...........................፥ ቸልታቸው አለ ።


@getem
@getem
@getem
ኢሬቻ ሀቻምና
# ዋቃ # ዝም # አትበል

ሙስዓብ ዑመይር



ምርቃት ያወዛው ቂቤ የጠገበ ዱላ ተመርኩዞ...፣
ዋቃን ሊለማመን ሚስት ልጁን ይዞ....፣
ኢሬቻን ሊያደምቅ ለምለም ሳሩን መዞ....፣
ፀብ ጥላቻን ሊሽር መከራን ሊከላ....፣
ለምለም አመት ሊመኝ ኪዳኑን ሊሞላ....፣
አማን ሰላም ብሎ ዋቃን ተወክሎ....፣
ከቀዬው ለራቀ ሁሉን ለሱ ጥሎ....፣


የስቃይ ጣር ማሾር የሞት ሾተል መምዘዝ....፣
ቀጤማውን አጭዶ ሬሳን መጎዝጎዝ....፣
ሀጫ ንክር ሸማን በደም አጨማልቆ....፣
እናትን ጉድጓድ ስር በአፍጢሟ ዘቅዝቆ....፣
አባት ከነ ዱላው በጥይት ታምሶ በጥይት ሲደቆስ....፣
አንዲት ፍሬ ጨቅላ አባቷን በለቅሶ የምትቀሰቅስ .....፣



በዚህ ሁላ መሀል ዋቃ ዝም ብሏል ...፣
ለግፈኞች ምላሽ ለምንዱባን ጋሻ ከመሆን ቦዝኗል...፣


በዚህ ሁሉ መሀል አንድ ጩኸት ሰማሁ....፣
ሚስት ልጄን አጣሁ ሁሉንም ተቀማሁ....፣
ኢሬቻ ምንድነው ዋቃ የት ነህ አንተ....፣
ለክብርህ ምስጋና ከደጅህ ለሞተ....፣
ማእረጉ ምንድነው ሁሉን ለተቀማ.....፣
የበዳዬስ እጣ ?? ተናገር ወይ ስማ....፣


ያዋቃ!! ዝም አትበል ዝምታህ ያመኛል....፣
የበደነ አካሌን በደንዝ ያርደኛል ....፣
ዋቃ ዝም አትበል.....፣
አዎ ዝም አትበል...፣
.
.
.
በደም የላቆጠ ሌጣ አካሉን ይዞ....፣
እሳት የሚተፋ በቀልን አርግዞ....፣
ሲጮህ ይሰማኛል....፣
ዋቃ ዝም አትበል ዝምታህ ያመኛል....፣
የበደነ አካሌን በደነዝ ያርደኛል......፣


#አሁን ያ ሁሉ አልፏል !!

"ናካይታ" 💚 ነጋቲ ቡላ!💚


@getem
@getem
@balmbaras
#በነፍስ መወራረድ!
(ሚካኤል አስጨናቂ )
።።።።።።።።።።።
የልቦናው እውነት ፥ ሳለ የረቀቀ
ለፈጠረው ፍጥረት.. .
መዳረሻ ግቡ ፥ ቀድሞ ከታወቀ
ኤልሻዳይ ነው ያልነው.. .
የአዳም ልጆች አባት ፥ የዓለሙ ቤዛ
ፍፃሜዋን ሲያውቀው ፥ የሰውን ነፍስያ
ነፃ ፍቃድ በሚል ፥ የነጋዴ ቋንቋ
ለፈተና ድሯት ፥ አወጣት ገበያ ።
#አሁን ይሄ ሸክላ !
አንዳንዴ ሲዘይድ...
ለእሳትና ውሀ ፥ ቀድሞ ተወስኖ
ከሲኦል ለመዳን...
ዱር ጫካ ሲከትም ፥ በስጋው መንኖ
በፅድቁ ጀግኖ ...
#አንዳንዴም ሲያጠፋ
ሕሊናው ሲያደብነው ፥ ገፅታው ሲከፋ
ሲጨነቅ ሲጠበብ ፥ በከንቱ ሲለፋ
እኔ ደግሞ እላለሁ ፥ እግዚሀር አጠፋ !

@getem
@getem
@paappii
ለምሽታችን!
💚


´ከላይ ያለች እጅ ከታች ካለች እጅ የተሻለች ናት!

በአንድ የገጠር ከተማ በርካታ ተማሪዎችን ሰብስበው የሚያስቀሩ አንድ ሸይኽ ነብሩ።አንድ ቀን ከነዚህ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ለሸይኹ ገንዘብ እንደሚያስፈልገውና ወደ ከተማ ሄዶ ይህንን ለቀለብ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ማፈላለግ እንዳለበት ይነግራቸዋል። #ሼይኹም ለተማሪያቸው ከፈቀዱለትና ስንቅ ካዘጋጁለት በኋላ መንገዱን ይጀምራል። ወደ እሚሄድበት ከተማ ለመድረስም ከመንገድ ያለን በረሀ ማቋረጥ ነበረበት። ይህንንም በረሃ አቋርጦ በሚሄድበት ወቅት አንድ የቆሰለ አሞራ ከመሬት ላይ መብረር የማይችል ሆኖ ይመለከተዋል። ታድያ ይህ ደረሳ በዚህ አሞራ ተፈኩር(ማስተንተን) ማድረግ ይጀምራል።


#በዚህ_በረሀ ውስጥ ምንም የሚቀመስ በሌለበት ይህ አሞራ ምን እየበላ ይሆን!?


#እንዴት_በህይወት መቆየትስ ቻለ!?
በዚህ መልኩ በተፈኩር ውስጥ ሳለ ከወደ ሰማይ ሌላ አሞራ ድንገት ከወደ ሰማይ ዱብ ይላል።


#ይህ_አሞራ የሚበላ ነገር በእግሮቹ አንጠልጥሎ ነበርና ለተጎዳው አሞራ ጥሎለት ሄደ። ያ የተጎዳው አሞራም የተጣለለትን ምግብ መመገብ ይጀምራል።
ተማሪውም በጣም ተገረመ። (መቼስ ፈጣሪ ነፍስን ከሪዝቋ ጋር እንጂ መች በባዶ ፈጠራት እና!) ብቻ ነገሩ እጅግ አስገርሞት እና አስደንቆት የሚሄድበትን በመሰረዝ ወደ ሸይኹ መመለስ ጀመረ። ለመመለሱ ምክንያትም ይህንን የተጎዳ አሞራ በዚህ በረሃ ውስጥ የሚመግብ እና የሚረዝቀው ፈጣሪ እኔንም ይመግበኛል ችግሬን ያስወግድልኛል የሚል ነበር። ወደ ሸይኹም እንደደረሰ የተመለሰበትን ምክንያት ይጠይቁታል።

ተማሪውም ያጋጠመውን ሁሉ ይነግራቸውና ፈጣሪው እሱንም ልክ እንደ አሞራው ሁሉ ከችሮታው እንደሚለግሰው ተስፋ አድርጎ መመለሱን ነገራቸው።

#ሸይኹም- ምነው !? እንደው እንተጎዳውና እርዳታ ፈላጊው አሞራ መሆንን ከመመኘት ለምን እንደ ረጂው እና ምግብን ተሸክሞ እንደተባበረው አሞራ መሆንን አልተመኘህም አሉት ይባላል።
---------------------------------------

#ሁሌም ቢሆን ትብብር እና እርዳታን ፈላጊ ከመሆን አንተው እራስህ ረጂ እና ተባባሪ መሆንን ምረጥ።
ከላይ ያለች እጅ ታች ካለች እጅ በላጭስ አይደለች!


#አሁን ወቅቱ ከመቼውም በላይ ቁጭ ብለን ለመረዳት ወይም ከመንግስት ብቻ መፍትሔ የምንጠብቅበት ጊዜ ላይ አይደለንም ሀገራችንን ፣ ወገኖቻችን ፣ ቤተሰቦቻችን ፣ ወገኖቻችን እንዴት ነው ከዚህ ችግር ልንከላከል የምንችለው ብለን በደንብ የምናስብበትና ወደ ተግባር የምንገባበት ጊዜ ነው....እናም ወንድምና እህቶቼ እቤት ከመቀመጥ በዘለለ ደሞ ማድረግ ስላለብን ነገሮች አስቡልኝ የኛ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ በየአካባቢው አይደል..? አቅም የሌላቸው የንፅህና ሳኒታይዘር ሆነ ምግብ መግዣ የሌላቸው ብዙ አሉ በየአካባቢያችን ስለዚህ እዚህ ቻናል ወንድሞችና እህቶች የምንችለውን እንርዳቸው ይሄን በሽታ የሚከላከሉበት ማቴሪያል እንርዳቸው ፣ የሚበሉትን ገዝተን እንስጣቸው በአቅማችን #ይሄኔ እኛም ለሀገራችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናደርጋለን.....ለምን አንድ ሳሙና አይሆንም ....

#ይሄን የምታነቡ ሰዎች ይሄን እንደምታደርጉ እናንተም የመፍትሔ አካል እንደምትሆኑ እምነት አለኝ🙏🙏🙏

ውብ ምሽት ትሁንላቹ!🙏

@getem
@getem
@Nagayta
እምወድሽዋ! ቅዳሜዋ! ሸጋዬዋ!


የእንጦጦ እናት መከራ!!

ወደ እንጦጦ ፓርክ አምርታቹ ከሆነ በፎቶ ላይ እንደምትታየው እናት በጀርባቸው እንጨት ተሸክመው፣ በድካም
- ላብ ጥቁርቁር ብላ ቁና ቁና እየተነፈሱ ቁልቁለቱን ፣ ዳገቱን ሲያዘግሙ የምታገኟቸው ብዙ እናቶች አሉ።

ለምሳሌ በፎቶ ላይ የሚታዩትን እናት አውርቻቸው ነበር ስንት ትሸጭዋለሽ አልኳት። "80 ወይም 90 ብር" አሉኝ። ልጆች
እንዳልዋት ነገረችኝ። እንጨቱን ለማግኘት ቢያንስ የሶስትና አራት ሰአት ተጉዛ፣ ለመስበርና
ለማሰር እንዲሁም ለመመለስ፣ ከዛ ወደ ከተማ አምጥታ ለመሸጥ የሚወስደውን ሰአት
ሳስበው ውስጤ በሃዘን ደከመ! በየቀኑ ይህን ማድረግ እንደማትችል ግልፅ ነው! በ90 ብር
ምን ልትገዛበት ትችላለች!? ይህችን እናት ለማስረጃነት አስቀረሁ እንጂ እንጦጦ ፓርክ የመሄድ እድሉ የነበራቹ ሰዎች ብዙ እናቶች በዛ ጠባብ መንገድ እንጦጦ ፓርክን የሚጎበኙ ባለመኪኖች በመኪና ካላክስ እያሳቀቋቸው እንጨት ተሽክመው በየእለቱ ይታያሉ። አስፋልት መንገዱ ጠባብ ከመሆኑ
የተነሳ ሁለት መኪና ሲታላለፍ የእነኚህ እናቶች ህይወት (የሽክሙ ወደ ጎን ርዝማኔ) ለአደጋ
የተጋለጠ ነው!

#አሁን ወደ ጊዜያዊ መፍትሔ እንዝለቅ :- እኔ እንደ ጊዜያዊ መፍትሔ ብዬ ማስበው #አሻም ቲቪ ላይ ከሰኞ እስከ አርብ ይመስለኛል ሁሌም ማታ 2:30 ላይ ማኣድ እናጋራ የሚል ምርጥዬ ፕሮግራም አለ። ብዙዎቻቹ ተመልክታችሁ ሊሆን ይችላል ....እኔ እንደ አማራጭ የምለው ይሄንን ነው......

ለምሳሌ:- እኝህ እናት በሳምንት 4 ቀን ቢወጡ ነው 90 ብር ነው የምሸጠው ብለውናል ....ቢበዛ በአንድ ወር ውስጥ 15 ቀን ይወጣሉ ማለት ነው።

#ለእኝህ እናት= 1350 ብንሰጣቸው አንድ ወር መሉ አላሳረፍናቸውም..? እንዲሁም እሳቸውን ለሚመስሉ ብዙ እናቶች...

#ስለዚህ የዚህ ቻናል ቤተሰብ የሆናችሁ እነዚህን እናቶች መርዳት ለምትፈልጉ ሰዎች ሁሉ የመስጠት የመርዳት ፍላጎቱ ካለን እጅግ ቀላል ዘዴ አለ ከጓደኞቻችን ጋር ገንዘብ አዋጥተን ቢያንስ እንኳን አንዲት እናትን ለአንድ ወር ማሳረፍ እንኳን ከቻልን እውነት ትልቅ የመንፈስ እርካታ ነው የምናገኘው። እነእርሱ ቀኑን ሙሉ የዋሉበት የተንከራተቱበት ሁለት ለእናንተ
cooffe or makiato ወጪ ቢሆን ነው....

💚 በተጠየቃችሁ ጊዜ መስጠት መልካም ነው።ግን ሳትጠየቁ መስጠት እንዳለባቹ ተገንዝባችሁ መስጠት የተሻለ ነው።

💛 ደፍሮ የማይለምን ተቀባይ መፈለግ፣እጁን ዘርግቶ ለሚጠባበቀው ከመስጠት የበለጠ ደስታ አለው።

ከሰው ሁሉ በላጩ ለሰዎች ጠቃሚ ነው

@getem
@getem
@Nagayta
1🔥1
ትላንት በየዓመቱ የሚደረገውን የበጎ ሰው ሽልማትን በባላገሩ ቲቪ የቀጥታ ስርጭት እያየሁኝ ነበር። በተለያዩ ዘርፎች ግለሰቦች ባደረጉት አስተዋጽኦ የዓመቱ በጎ ሰው እየተባሉ ሽልማቶችን ሲበረከትላቸው ነበር። ለምሳሌ የበጎ ሰው ሽልማት ካሸነፉት ውሰጥ የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳን የዓመቱ በጎ ሰው ተብለው ተሸልመው እንደነበር የሚታወስ ነው።

#አሁን ጉዞ ወደ ሀሳብ...🗣🗣🗣


በጎነት ምን ማለት ነው? በጎነት ባህሪ ነው ወይስ ችሎታ ነው? በጎነት ቋሚ ነው ወይስ ተለዋዋጭ ጊዜያዊ ነው?

መልሶቻቹን በእነዚህ ሊንኮች ብትልኩልን
👇👇
@Nagayta
@balmbaras
👍3
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
.
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
.
.
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
.
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
.
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
.
2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
.
3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)
.
.
.
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
.
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
#አሁን_ትዝታ_እንጂ.....
#ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
.
.
.


By ኤፍሬም ስዩም

@getem
@getem
@paappii
101👍73🔥14👎1