ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.83K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
391 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram
ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
🔽▶️ *⃣ #ሮሜ 8፥34 እና #የመናፍቃኑ እርስ በእርስ አለመግባባት፦ ‹‹ #የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ #የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው›› (ሮሜ 8፡34)፡፡ #በልማድ ለያዙት #የተሳሳተ ትምህርት አልመች ያለውና #በምንፍቅና #ጎዳና ላይ ሆነው #የአዳኛችንን #የኢየሱስ ክርስቶስ #የማዳን ግብር የሆነው #የምልጃ ሥራውን ሽምጥጥ አድርገው…
🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽🔽

#ቀደም ሲል ከቀረበው "ምንባቡ #ይማልዳል ሳይሆን #ይፈርዳል ነው ማለት የነበረበት" በሚል ከተቀመጠው "ከመጋቤ ዐዲስ ሮዳስ ታደሰ" #ሐሳብ የተለየ #ሐሳብ ያላቸው "መምህር ደምሰው ዘውዴ" ደግሞ #ይማልዳል የሚለውን ይቀበሉና እንዲህ ይላሉ..

〽️ 2፦ ‹‹[መናፍቃን] ለማታለል ሲሉ #በግእዝ #ይማልዳል ብለው ጽፈውታል፤ ቃሉ #ግእዝ ነው #ግእዝና #ፍቺውን የማያውቅ #ሊታለል ይችላል፡፡ እነርሱ ግን ግእዝን ይቃወማሉ፤ #ለማወናበጃ ግን #ሊጠቀሙበት ይሞክራሉ፡፡ #ቅዱስ ዳዊት ግን የቃልህ ፍቺ ያበራል… እንዳለ #ፍቺው ይመሰክርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም
/ #ይማልዳል/ የሚለው #የግእዝ #ቃል ሲሆን #ፍቺው / #ይፈርዳል/ ነው፡፡ አማላጅ ቢሆን ኖሮ ቅዱስ ጳውሎስ በግልጽ ዐማርኛ ‹ #ያማልዳል› ብሎ በጻፈ ነበር፡፡… እስኪ ፍረዱኝ››
📖/፤ (ደምሰው ዘውዴ (መምህር)፣ " ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ" (2001) ገጽ 30)፡፡

▶️ ጸሀፊው መጽሐፍ ቅዱስ በዐማርኛ የተጻፈ መስሏቸው ይሆን? ወይስ ምናልባት #አብርሃም ኢትዮጵያዊ ነው፣ #መልከ #ጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው፣ #ማርያም ኢትዮጵያዊት ናት፣… እንደሚባለው #ሐዋርያው ቅዱስ #ጳውሎስም ኢትዮጵያዊ ነው እያለ ይሆን? እነርሱ እንደ መሰላቸው መጽሐፍ ቅዱስ #በዐማርኛ #ቋንቋ የተጻፈ አይደለም፡፡ ይህን ማንም የሚያውቀው እውነት ነው። #ብሉይ ኪዳን #በዕብራይስጥ #ዐዲስ ኪዳን ደግሞ #በግሪክ ቋንቋ የተጻፉ ሲሆን መላው #ዓለም (ኢትዮጵያን ጨምሮ) ከእነዚህ #ቋንቋዎች ነው ወደ #የሀገራቸው #ቋንቋ የተረጐሙት፡፡ #የእኛ ሀገር ሰዎች (በተለይ ቤተ ክርስቲያናችን) ግን መጽሐፉን ወደ #ዐማርኛ ሲተረጉሙት #የግሪኩ የማይለውን #በማስፈር #እንግዳ ትምህርት ለማስተማር #ምክንያት ሆኑ እንጂ፡፡ ግሪኩስ የሚለው "ኢየሱስ ይማልዳል" ነው። ይህን ለማረጋገጥ ከፈለጉ #በ2000 ዓ.ም #የታተመውን 80 አሀዱ #በሮሜ 8፥34 የግርጌ ማስታወሻ ላይ "ግሪኩ <የሚማልደው> ይላል" የሚለውን ፎቶው ላይ ይመልከቱ።

ሌላው የኚህ ጸሀፊ አስጋራሚ ነገር ከላይ ከቀበረው የተለየ ሐሳብ ካላቸው "ከመጋቤ ዐዲስ ሮዳስ ታደሰ" ጋር #አለመስማማታቸው ነው፡፡ ቀደም ሲል ያየነው " #የሚማልደው ሳይሆን #የሚፈርደው ነው መሆን ያለበት #የሚማልደው የሚለው የተቀየረ ነው። #መናፍቃን የጨመሩት ነው ሲል" ከዚህ የተለየ ሀሳብ ያላቸው "መምህር ደምሰው ዘውዴ" ደግሞ " #የሚማልደው ነው መሆን ያለበት ምክንያቱም #የግእዝ ቃል ነውና፡፡ በግእዙ #የሚማልደው ማለት #የሚፈርደው ማለት ነው" በማለት ሀሳባቸውን ያስቀምጣሉ፡፡

▶️ በክፍል 2(የኢየሱስ አማላጅነት) ላይ #የምልጃ ትርጉም መቅረቡ ይታወሳል። በዛ #ትርጉም መሰረት #ይማልዳል የሚለው ቃል #ይፈርዳል ተብሎ ሊተረጎም የሚችልበት ምንም ዓይነት አግባብ እንደ ሌለ መመልከት ይቻላል። በመሆኑም ጸሀፊው የሌለ #ትርጉም በመስጠት ሰውን #ለማሳሳት እየሞከሩ ነው ከማለት ያለፈ ሊባል የሚችል ምንም ነገር የለም።

ይቀጥላል...(ሮሜ 8፥34)
@gedlatnadersanat @teeod