ገድላትና ድርሳናት በእግዚአብሔር ቃል ሲመዘኑ
2.81K subscribers
536 photos
68 videos
81 files
393 links
〽️ ገድላትና ድርሳናት
〽️ 80 አሀዱ መጽሐፍ ቅዱስ
〽️ አዋልድ መጻሕፍት
〽️ ሌሎችንም ያለቦታቸው የገቡ የመጽሐፍቅዱስ ጥቅሶችና ኢ-መፅሐፍቅዱሳዊ የሆኑ ትምህርቶቻቸው በመፅሐፍ ቅዱስ ሲመዘኑ

እውነትን ታውቃላቹ እውነትም አርነት ያወጣቹሀል [ዮሐንስ 8፥32]
@teedy
@teedy

ኢየሱስ ማነው?👇
@Who_is_jesus
Download Telegram


#ስለዚህም እግዚአብሔር ራሱ "እንደዚ አርጉ እንደዚ ሁኑ በእንደዚ አይነት እቃ ብቻ....ምናምን ሳይሆን ያለው #ማናቸውንም ነገር ብታደርጉ ለእግዚአብሄር ክብር አድርጉት ነው ያለን።
ስለዚህም ዋናው ነጥቡ ለማን ነው የተጠቀምነው?
ነው እንጂ
በምንድነው የምንጠቀመው? የሚል ነገር የለም።
ለእርሱ ክብር ነው ወይ ?
በጌታ በኢየሱስ ስም ነው ወይ?
እነዚህን ሁለቱን ያሟላ ማንኛውንም አምልኮ እግዚአብሔር በደንብ ይቀበለዋል።። ከእነዚህ ውጪ የሆነንም በተቃራኒው

ጌታ ኢየሱስም በዮሐንስ ወንጌል 4፥24 ላይ ሲናገር
"እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በእውነትና በመንፈስና ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል።

#ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:19 በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤

#ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:16 የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ። በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።

ለእግዚአብሔር የምናቀርበው አምልኮ መሠረቱ ከልብ ከመንፈስ የመነጨ እና እውነተኛ መሆን ነው::
በመሰረቱ አምልኮ ፎርሙላ አለውን??
ከዘለለው ሰውዬ ቆሞ ባጨበጨበው ነው እግዚአብሔር የሚደሰተው ያለህ ማነው??
እግዚአብሔር አምልኮ ፎርሙላ ሰቶናል ወይ?
እግዚአብሔር የሚያስደስተው ከልብ የሆነው ነው እንጂ እንዴት እንዳረገው ወይም አደራረግህ አይደለም።
አትሳት ብራዘር እግዚአብሔር መሳሪያህን አይደለም አካሄድህን አይደለም አወራርህን አይደለም አምልኮህን አይደለም በመሰሩቱ አምልኮ ፎርሙላ የለውማና አንገት ስለደፋህ አይደለህም በዝግታ ስለሄድክ አይደለም ወይም አንድ ቦታ ቆመህ ስላሸበሸብክ አይድለም። ለዛ ነው ሀዋሪያው ሲናገር

@ 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:13 #እብዶች ብንሆን፥ #ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።
መዝለል አይደለም ማንኛውንም ነገር ብታደርግ ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ አድርገው።። አራት ነጥብ
እንደ ፈሪሳውያን እስከ አለባበስህ ጭምር እግዚአብሔርን አስደስተዋለህ ብለህ አስበህ ከሆነ ስተሀል ።
ጌታ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ሲናገር እንዲህ አለ

#ማቴዎስ ወንጌል 15

8. ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤

9. የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።
ስለዚህም በሰው ስርአት በከንቱ መባዘናችንን ትተን ብፍጹም ልባችን እንቅረብ።
እያስመሰለ ከሚያሸበሽበው ከልቡ የሚዘለው ይሻላል እግዚአብሄር የሚቀበለው እሱን ነውና።
እርሱ ዝምታ ወይም ጩሀት
ስግደት ወይም ዝላይ አይገድበውም::
እግዚአብሔር በደስታ እንድናመልከው ይፈልጋል::
ሰዎች እግዚአብሔርን እራሳቸው በሳሉት ስእል ለመገደብ ይሞክራሉ: ይህም በአብዛኛው ካደጉበት ባህል እና ቀድሞ ሲከተሉት ከነበረ አምልኮ በመነሳት ነው::
እግዚአብሔር ግን እኛ እንደሳልነው ወይም ሌላው እንደሳለው አይደለም:: እርሱ የአቤልን መስዋእት ተቀብሎ የቃየንን አልተቀበለም:: የያዕቆብን መስዋእት ተቀብሎ የኤሳውን አልተቀበለም::
ስለዚህ እርሱ የሚወደው ከመንፈስ የሆነ ከልብ የመነጨ መስዋእት/ምስጋናና/አምልኮ መሆኑን እንጂ የእኛን የአምልኮ አቀራረብ ወይም አገላለጽ መሠረት ያደረገ አይደለም።
መዝለል አይደለም ብንገለባበጥ ለእግዚአብሄር ነው።
ካበድክም ለሰይጣን ሳይሆን ለኢየሱስ እበድ መጠጥ ቤት ሳይሆን ቤተክርስቲያን ለጌታ ዝለል።
🤷‍♂🤷‍♂

ጥያቄው እዚጋ ነው
#1፦ ቴክሎኖጂውን አንቀበልም ከሆነ ማይኩስ ፣ሚክሰሩ ፣ ማቀናበሪያው ፣ ገመዱ ፣ አምፖሉ... ሁሉ በዛ ጊዜ አልነበረምና ለምን ትቀበሉታላቹ??
ግማሽ ተቀብሎ ግማሽ አለመቀበል አለ እንዴ??
#2፦ በድሮ ጊዜ ጊታር ፒያኖ..ለሰይጣን ነው ወይም የዘፈን ብቻ ነው በገና ደግሞ ለእግዚአብሄር ብቻ ነው ተብሏልን???
ከላይ እንደተገለጸው ማናቸውንም ነገር ብታደርጉ ለእግዚአብሄር ክብር አድርጉት ነው የሚለው እንጂ በዚህ እቃ በዛ መሳሪያ መች ተባለ??
የሚለየው ለማን እንደተጠቀምነው ነው እንጂ በምን እንደተጠቀምን አይደለም።
መሳሪያውን ለእግዚአብሄር ክብር ስናደርገው ለእግዚአብሄር ይሆናል ለሰይጣን ካረግነው ደግሞ ለሰይጣን ይሆናል።
በገናና ከበሮ ለዘፈንም እንዳገለገለ ያውቁ ኖሯል?? 👇

ኦሪት ዘፍጥረት 31:27 ፤ ስለምን በስውር ሸሸህ? ከእኔም ከድተህ ስለምን ኮበለልህ? በደስታና #በዘፈን #በከበሮና #በበገና እንድሰድድህ ለምን አልነገርኸኝም?

ትንቢተ ዳንኤል 3:7 ፤ ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ #የመሰንቆውንና #የክራሩን#የበገናውንና #የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፥ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።

ስለዚህም በገና ራሱ የዘፈን መሳሪያ ነው ልንል ይሆን??
አስቡበት

መዝሙረ ዳዊት 149:3 #ስሙን #በዘፈን ያመስግኑ፥ በከበሮና በመሰንቆም ይዘምሩለት።

@gedlatnadersanat
@Literature_For_God
🔆 የማርያም የዘር ሃረግ 🔆

(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ- 3:)
...............

23፤ " ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር እንደመሰላቸው #የዮሴፍ ልጅ ሆኖ፥ #የኤሊ ልጅ፥".......
.........................................

32፤ " የዳዊት ልጅ፥ የእሴይ ልጅ፥ የኢዮቤድ ልጅ፥ የቦዔዝ ልጅ፥ የሰልሞን ልጅ፥"....................
...........................................

36፤ የቃይንም ልጅ፥ የአርፋክስድ ልጅ፥ የሴም ልጅ፥ የኖኅ ልጅ፥ የላሜህ ልጅ፥

37፤ የማቱሳላ ልጅ፥ የሄኖክ ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥

38፤ የመላልኤል ልጅ፥ የቃይናን ልጅ፥ የሄኖስ ልጅ፥ የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ የእግዚአብሔር ልጅ[10]።

▶️ የማቲዎስ የዘር ሃረግ ገለጻ
" #ከአብርሃም በመነሳት ወደ ፊት ወደ #ኢየሱስ ሲቀጥል " #የሉቃስ ግን #ከኢየሱስ ጀምሮ ወደ ኋላ ወደ #አዳም ይጓዛል።
#ማቲዎስ #የኢየሱስ ህጋዊ አሳዳጊ #አባት የነበረውን #የዮሴፍን #የዘር ሀረግ ሲሰጠን #ሉቃስ #የእናቱን #የማርያምን #የዘር #ሐረግ ይሰጠናል።

በሉቃስ 3-23
"ኢየሱስ አገልግሎቱን በጀመረበት ወቅት ዕድሜው 30 ዓመት ያክል ነበረ ይህም ኢየሱስ #የዮሴፍ ልጅ መሰላቸው እንጂ #የኤሊ...(የማርያም ዘር ማንዘር) ልጅ ነበር" ተብሎ ተገልጾአል።
ምንም እንኳ #ማቴዎስ 4 #ሴቶችን በዘር ሀረግ ዝርዝር ቢጠቅስም/ማቲ 1-3 ፣ 5 ፣ 16/ #ሴቶች #በህጋዊ #የዘር #ሐረግ ውስጥ ስለማይገቡ #ማርያም ራሷ ሳትጠቀስ #ከአባቷ #ከኤሊ ጀምሮ እስከ #ዘር #ማንዘሮቿ #አዳም ድረስ ተገልጾአል[11]።

ይህም #ኤሊ #የዮሴፍ #አባት መሆኑን እንደ ሉቃስ አጻጻፍ #ከተወሰደ ዮሴፍ #የያዕቆብ ልጅ እንደሆነ #ማቴዎስም በግልጽ #አስቀምጧልና #ዮሴፍ #የኤሊም #የያዕቆብም ልጅ ወይም #የሁለቱ #ውህድ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም 1 ሰው 2 #አባት የለውምና።
ይህ ከሆነ ደግሞ #በአዋልድ #መጽሀፍት
<< ጰጥሪቃና ቴክታ የማርያም ስምንተኛ ቅድመ አያት ዝርያዎች፤ ነጭ ጥጃ ከማህጸን ስትወጣ ያች ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲህ እያለ እስከ 7ኛ ትውልድ ድረስ 7ኛይቱም ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃም ፀሐይን ስትወልድ አይቻለሁ ብትል ቴክታ ህልም ፈችዎችን ጠርቶ ጨረቃይቱ ማርያም ናት ፅሐይ ግን አልተገለጠልኝም ቢላቸውና ቴክታ ሄኤሜን፤ ሄሜን ዴርዴም ፤ ዴርዴ ቶናን፤ ቶና ሲካርን፤ ሲካር ሄርሜላን፤ ሄርሜላ #ሃናን#ሃናም #ማርያምን ወለደች፡ #ሃና በባሏ #በኢያቄም እጅ በትር እንደተያዘች ያች በትር አብባና አፍርታ እንዳየቻት #ኢያቄምም #በሀና እጅ ከፍሬው ሁሉ የሚመስለው የሌላ የሚጣፍጥ መልካም ፍሬ ተይዛ እንዳየች እርሷም ልጃቸው #ማርያም እንደነበረች የሚገልጸው አፈ ታሪክ #ከቁርዓን ተኮርጆ #በነገረ #ማርያም የተጻፈ #ተረት ሆኖ #ይቀራል ማለት ነው[12]።>>

ስለዚህም እንዲህ የሚያደርጉትን #ከተጻፈው #አትለፍ የሚለውን #መመሪያ #እንዲያነቡና #እንዲተገብሩ እናሳስባለን።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
____________
[1] 📚፤ ንቡር ዕድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፤ <ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት> (3ተኛ መጽሀፍ፥ ቼምበር ማተሚያ ቤት አ.አ፤ *ገጽ 264-267፤ 1998 ዓም።

📚፤ አማረ አፈለ ብሻው፤
<ኢትዮጽያ የሰው ዘር የተገኘባት የእምነትና የስልጣኔ ምንጭ ናት>
*ገጽ 116-122፥ አ.አ ጥር 1996 ዓ.ም

📚፤ አባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ <ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋህዶ አንበሣም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው> (2ተኛ እትም ግንቦት 2001 ዓ.ም)

[2] 📚፤ በርሰ ሊቃነጳጳሳት ዩሐንስ ዳግማዊ ይፋ ካደረጉት ከዋናው የላቲን መጽሀፍ የተተረጎመ <የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ> *ገጽ 145፥ 1997 ዓ.ም።

[3] 📚፤ የኢ.ኦ.ተ.ቤ/ክ ተአምረ ኢየሱስ፤ ምዕራፍ 3(፫)፤ 10(፲) ፤ *ገጽ 16(፲፮)፥ ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ 1994 ዓ.ም።

[4] 📚፤ ድርሳነ ኪዳን ለማርያም ሳልስ፤ *ገጽ 48 1978 ዓ.ም።

[5] 📚፤ ተአምረ ማርያም፤ የዘውትር መቅድም (*ገጽ 4(፬)፤ 16(፲፮) 1989 ዓ.ም።

[6] 📚፤ ደቀመዝሙር መልአኩ ዘድሜጥሮስ። <ስንዴውን ለመስዋት እንክርዳዱን ለእሳት> አ.አ. ሰኔ 1998፤ *ገጽ 21።

[7] 📚፤ <ድርሳነ ጽዮን ዘሐሙስ> 44-13 *ገጽ 158። አ.አ. ኅዳር 1998 ዓ.ም።

[8] 📚፤ ወንጌል ቅዱስ፤ ዘማቲዎስ ወንጌል፤ ንባቡና ትርጓሜው በግእዝና በአማርኛ፤ 1፡ 16። *ገጽ 52። 1997 ዓ.ም።
[9] 📚፤ ሃይማኖተ አበው፤ ቃል ግዝት ኤጲስቆጶስ፤ ክፍል 6 ፤ *ገጽ 577 1986 ዓ.ም።

[10] 📚፤ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ፤ <ለጌታ የተገዛህ ሁን> ፧ የማቴዎስ ወንጌል; ትርጉም ግርማዌ፤ *ገጽ 9፤ S.A.M፥ ኤስ ኤይ ኤም ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1995 ዓ.ም

[11] 📚፤ ዋረን ደብልዩ ዌርዝቢ፤ <ሩህሩህ ሁን፥ የሉቃስ ወንጌል ትርጉም ፤ *ገጽ 31-32፤ S.A.M፥ ኤስ ኤይ ኤም ማተሚያ ቤት አ.አ፤ 1996 ዓ.ም

📚፤ ቄስ ኮሊን ማንሰል፤ <ትምህርተ እግዚአብሔር> ፩ኛ መጽሐፍ፤ *ገጽ 80፥ ንግድ ማተሚያ ድርጅት አ.አ፥ 1995።

[12] 📚፤ ተአምረ ማርያም 2፤ 8-9 3ተኛ እትም *ገጽ 17፥ ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት። አ.አ 1989 ዓ.ም

📚፤ ያዕቆብ ሰንደቁ <እናታችን ጽዮን> 3ተኛ እትም *ገጽ 7-12። አ.አ፥ 1997 ዓ.ም።

📚፤ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ 5፥38። *ገጽ 111። ትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፤ 1983 ዓ.ም።

📚፤ ቅዱስ ቁርአን ሱረቱ አል-ኢምራ 3፤ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት፤ አ.አ፥ 1998 ዓ.ም።

(1.2▶️ጥያቄ) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat
▶️ የማርያም #መጻሕፍት አብዛኞቹ እንደነ <<ውዳሴ ማርያም>>፣ <<ቅዳሴ ማርያም>> የመሳሰሉት #የእግዚአብሔርን ቃል ወስደው ወደ #ማርያም የማጠጋጋት #ባህሪ አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ #የተጋነኑና #አሳፋሪ #ሐሰት ይገኝባቸዋል። #የእግዚአብሔር ቃል #እውነትን በእጅጉ ይቃረናሉ ለምሳሌ <<መጽሐፈ አርጋኖን[1]>> የተባለው ፦

〽️ <<አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.6]
〽️ <<ኖህ ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12 ክፍል 8፤ ቁ.9]
〽️ <<አብርሃም ከሳራ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.10]
〽️ <<ይስሐቅ ከርብቃ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.11]
〽️ <<ዕብራዊው ያዕቆብም ከልጁ ከይሁዳ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.14]
〽️ <<ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ሁሉ ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.20]
〽️ <<ዳዊት ከመዘምራን ጋር ያመሰግንሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.23]
〽️ <<ማህበረ መላዕክት ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.26]
〽️ <<ማህበረ ነብያት ሁሉም ያመሰግኑሻል>> [ምዕ 12፤ ክፍል 8፤ ቁ.27]

▶️ እነዚህ የተጠቀሱ #የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሲሆኑ ክፍሎቹን ወደ #መጽሐፍ ቅዱስ ሄደን #በጥሞና ብናነባቸው የሚነግሩን፦ #አዳም #ከልጆቹ ጋር #እግዚአብሔርን እንጂ #ማርያምን አላመሰገነም። ጭራሽ #አይተዋወቁም። በመካከላቸው ያለው #የዘመን ልዩነት #የሰማይና #የምድር ርቀት ያክል ነውና። [ዘፍ 4፥3፣ ዘፍ 5፤ 1-5]። #ኖህ ከልጆቹ ጋር [ዘፍ 6፥9፣ ዘፍ 8፤ 20-22፣ ዕብ 11፥7] #አብርሃም ከሣራ ጋር [ዘፍ 28፥8፣ ዘፍ 21፥1፣ ዕብ 11፥8፣ 19] #ይስሐቅ #ከርብቃ ጋር [ዘፍ 27፥27]፣ #ያዕቆብም [ዘፍ 28፤ 18-22፣ ዕብ 11፥20]፣ #ሙሴ #ከእስራኤላውያን ጋር [ዘጸ 15፤ 1-26፣ ዕብ 11፤ 23-28]፣ #ዳዊትም [2ሳሙ 6፤ 12-33፣ መዝ 8፤ 1-9] #ማህበረ #መላእክትም [ኢሳ 6፥3፣ ራዕ 4፤ 7-11]። #የሐዋርያት ማህበርም [ሐዋ 2፤ 46-47፣ ሐዋ 16፥25]፣ ሁሉም በግልጽ #እግዚአብሔርን ብቻ እንዳከበሩ እንጂ #ማርያምን ያመሰግኑበትም ሆነ #ስሟን እንኳን የጠሩበት አንድም #ቦታ የለም።

▶️ ስለሆነም <<ማርያምን ያመሰግናሉ>> የሚለው #ኢ-መጽሐፍቅዱሳዊና #የነብያትን#የመላእክትን፣ እንዲሁም #የሐዋርያትን ስም ማጥፋትና #ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን የተባረከ #ምስጋናቸውን ወደራስ #ሃሳብና #መሻት ለመጠምዘዝ የተደረገ ከንቱ #የባእድ #አምልኮ #ሙከራ ነው።

ሌላው #ውሸት የታጨቀበት #መጽሐፍ ደግሞ <<መጽሐፈ ሰዓታት[2]>> የተባለው #መጽሐፍ ነው። ለምሳሌ ያክል

〽️ <<ለመጸብሐዊ ማቴዎስ እንተ ረሰይኪዩ ወንጌላዊ - ለቀራጩ ማቴዎስ ወንጌላዊ ያደረግሽው አንቺ ነሽ>> ይላል [መጽሐፈ ሰዓታት ርኅርኅተ ህሊና ገጽ 132 - 133]። ነገር ግን #ማቴዎስ ወደ #ወንጌላዊነት እንዴት እንደመጣ #ራሱ #ስለራሱ ሲናገር <<ኢየሱስም ከዚያ አልፎ በመቅረጫው ተቀምጦ የነበረ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው አየና። ተከተለኝ አለው። ተነሥቶም ተከተለው።>> [ማቴ 9፥9] ብሏል። ይህንን #መጽሐፍ ቅዱሳዊ #እውነት ክዶ #ማርያም #ማቴዎስን #ወንጌላዊ አደረገችው ማለት ምን ይሉታል?

▶️ ማህሌተ ጽጌ የተባለው #መጽሐፍ ደግሞ <<ቅዱስ ጴጥሮስ በ30 እስታቴር (በ30 ብር) በርተሎሜዎስን ለግብርና ስራ ሸጠው>> ይላል። በመቀጠልም <<የጴጥሮስ ጥላው የጳውሎስም ልብሱ ማርያም አንቺ ነሽ>> ይላል። አንባቢ ሆይ አረ #እናስተውል!!። ሐዋርያው #ጴጥሮስ ሐዋርያው #በርተሎሚዎስን እንደሸጠ ከየት የተገኘ #ወሬ ነው?። #ከታሪክ አንጻር እንኳን ብንመለከተው #ጴጥሮስም #በርተሎሚዎስም #ለወንጌል አገልግሎት ከመጠራታቸው በፊት #በሮማ ግዛት ስር የነበሩ ተራ #አይሁዳውያን ነበሩ እንጂ #ሰውን የሚሸጡ #ገዢዎች እንኳ አልነበሩም። ታድያ ሐዋርያው #ጴጥሮስ የወንጌል ጓደኛውን #በርተሎሜዎስን #ለግብርና ስራ #በ30 ብር ሸጠ ማለትና #የጴጥሮስ ጥላው #የጳውሎስም የልብሱ ዘርፍ #በሽተኞችን ሲፈውስ #ፈዋሹ #እግዚአብሔር ብቻ ሆኖ ተጽፎ እያለ <<ጥላና ልብሱ ማርያም ነበረች>> ማለት አያሳተዛዝብም? [ሐዋ 5፤ 15-16፣ 19፤ 11-12]። አረ ያስተዛዝበናል!

▶️ ይህ በብዙ የሳተ #መጽሐፍ #በግእዝና #በዜማ ለህዝቡ ስለሚቀርብለት አብዛኛው #ቋንቋውን ስለማያውቅ የሚባለውን #ሳይሰማና #ሳያስተውል #አሜን ብሎ ይሄዳል። ምናልባት ጉዳዩን በጥሞና #መረዳት ቢችልና ለማረም ቢሞክር ደግሞ #ተሐድሶ#መናፍቅ ወ.ዘ.ተ ተብሎ #የውግዘት ናዳው ይዘንብበታልና አብዛኛው #ዝም ማለቱን የመረጠ ይመስላል።

<<ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ። ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥ ይላል እግዚአብሔር።>> [ኤር 9፤ 5-6]።

✔️ ከተጻፈው አትለፍ /1ኛ ቆሮ 4-6/

🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆🔆

"ማጣቀሻዎች - References"
_________
[1] 📚፤ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ አርጋኖን የእመቤታችን ምስጋና፤ ተስፋ ገብረስላሴ ማተሚያ ቤት፡ አ.አ፥ 1989 ዓ.ም።

[2] ሰፊ ማብራሪያ
📚፤ GBV <መጽሀፈ ሰአታት በመቅደሱ ሚዛን> 2ተኛ ዕትም ጥቅምት፡ 1995 ዓ.ም፤ BGNLJ፤ አ.አ፥ ኢትዮጵያ።
ይመልከቷል።

@gedlatnadersanat
(8.6.6▶️) ይቀጥላል...
@gedlatnadersanat