Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እንደ ልጇ ተነሥታ ዐርጋለች።"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት"(መዝ 131:8) በማለት ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት የጌታችንና የእናቱን የእመቤታችንን ትንሣኤ አስተባብሮ ተናግሯል።"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ" ብሎ የጌታን "አንተና የመቅደስህ ታቦት" በማለት ጌታችን ብቻ ሳይሆን እናቱም እንደምትነሣ በእውነት ተነበየ።
#ኋላ ጻድቃን የሚቆሙትን የቀኝ ቁመት እመቤታችን ዛሬ ቆማዋለች።"በወርቅ ልብስ ተሸፋፍና ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" እንዳለ አባቷ ቅዱስ ዳዊት።
#ልጇ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ኋላ ለጻድቃን የሚያወርሳቸውን "ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን" (1ኛ ቆሮ 2:9) ዛሬ ለእናቱ አውርሷታል።
ለነገሩ ራሷ መንግሥተ ሰማያት ናት።ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ንጉሠ ሰማያት ወምድር ማኅፀኗን መናገሻ አድርጎ ነግሦባታልና።
#ልጇ "ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።"(ዮሐ14:3) እንዳለ እርሷም እርሷ ባለችበት እንሆን ዘንድ ከልጇ ታማልደናለች።ማርያም ማለት መርኅ ለመንግሥተ ሰማያት (በቃልኪዳኗ በአማላጅነቷ ረድታ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ) ማለት ነውና።
#ጌታ መጋቢት 27 በመስቀል ላይ ሞቶ መጋቢት 29 በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ እመቤታችንም በጥር 21 ዐርፋ ገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ቆይታ በነሐሴ 14 ቀን በጌቴሴማኒ ተቀብራ በነሐሴ 16 ቀን በክብር፣በይባቤ መላእክት ተነሥታ ዐርጋለች።
#አይ የሞተ አይነሣም ለምትሉ አባታችን ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን በመንፈስ እንጠራዋለን "ነገር ግን ሰው፤ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል።አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም።"(1ኛ ቆሮ 15:35) ብሎ ይዘልፍናል።
#ተነሥቶ ወደ ሰማይ አይወጣም የሚል ቢኖር ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን በሃይማኖት እንጠራዋለን፤እንዴትም ወደ ሰማይ እንደወጣ እንጠይቀዋለን።"ሲሄዱም እያዘገሙም ሲጫወቱ፤ እነሆ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።”(2ኛ ነገ 2:11)
ሞቶ ተነሥቶ ያረገ የለም የሚል ማንም ቢኖር ዳግመኛ ቅዱስ ጳውሎስ
"ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፤ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።"(1ኛ ተሰ 4:16-17) ሲል ይነግርልናል።
#አስተውሉ ያቀረብነው ማስረጃ ጻድቃንን የሚመለከት ነው።ጻድቃን እንዲህ ከከበሩ የጻድቃን እናታቸው የአምላክ እናት ቅደስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምማ ክብሯ ምን ያህል ይሆን !!!!!!!!???
እኛስ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም "አሕዛብ ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናመስግናት" እንላለን!!!
ነሐሴ ኪዳነምሕረት 2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ