ዐውደ ምሕረት
3.68K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
መልሱን በቀጥታ ለመመለስ ይህል በአንድ ጥያቄ እንጀምር የእመቤታች ጸሎት ማለትም "እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን ....የሚለው ጸሎት ማለት ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ #የለም ያለው ማነው ???በደንብ አለ እንጂ መጻሕፍ ቅዱስን በደንብ ሳንመለከት ይህ አለው ያለ የለውም ማለት ተገቢ አይደለም ስለዚህ አጠያየቁ ይታረም ::ይህ ጸሎት መጻሕፍ ቅዱስ ውስጥ አለ ወይ ተብሎ ይጠየቃል እንጂ የለም ብሎ መጀመር መጻሕፉን አለማወቅ ያስመስልብናልና::


#ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥርዓቶቾን በሙል ሥትሰራ በግለሰብና በማሕበረ ሰብ የሥጋ ሀሳብ ወይም በድምጽ ብልጫ አይደለም:: ንባብን ከትርጓሜ ትርጓሜን ከምስጢር አስማምታና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሁሉን ታሰናዳለች እንጂ: በዚህም ስንዱ እመቤት ለብላ ትጠራለች::

አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ከቁጥር 8ጀምሮ ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማረው ጸሎት ነው :: ሙሉ ያስተማረውን ጸሎት ቃል በቃል ለመመልከት ያክል "፤ እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ "፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን። " ....የሚል ነው (የማቴዎስ ወንጌል 6 ÷ 8-13)

ታድያ ይህ ጸሎት በመጽሐፍ ቅዱስ ካለ የእመቤታችንስ በየት ቦታ ነው ያለው ሊባል ይችላል ::ይህ የእመቤታችን ጸሎት ከሁለት የ መጻሕፍ ቅዱስ ክፍል የተገኘ ነው የመጀመሪያው ከአብሳሪው መላእክ ከቅዱስ ገብኤልና ከቅድስት ኤልሳ ቤጥ የተገኘ የምስጋና ጸሎት ነው እስቲ ሁለቱንም ከግጥም እንመልከታችው

👉 የቅዱስ ገብርኤል ምሥጋና

"፤ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 28)

👉 የቅድስት ኤልሳቤጥ ምሥጋና

"፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። "
(የሉቃስ ወንጌል 1: 42)

አሁን ደግሞ እስቲ እኛ የምንጸልየውን እንመልከት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ የአሸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል አንቺ ከሴቶች ለተይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ(3)ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመዳኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን ለዘለዓለሙ አሜን
.....የሚል ነው
እስቲ ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ንግግር ውጪ የተጠቀምነው አዲስ የራሳችንን ምስጋና የቱ ጋር አለ?? በፍጽም የለም ሁሉንም ከእነርሱ ያገኘነው በመጻሕፍ ያነበብነው ነው
እመቤታችንም ፀጋን የተመላች ነችና ከተሰጣት ብዙ ፀጋዎች በአንዱ ነቢይት ነችና በአንዱ በቅዱስ ገብርኤልና በአንዱ በቅድስት ኤልሳቤጥ ብቻ ተመስግኜ አልቀርም ገና ትሁልድ ሁሉ ብጽይት ይሉኛል ስትል ከፈጣሪዋ ከልጇ ከወዳጆ ቀጥላ በአማኝ ትሁልዶች ሁሉ የምትመሰገን መሆኑን ነግራናለች ይህም ሐሰት የለውም የእውነት መንፈስ ሐሰት አያናግርምና እያመሰገናትም ነውና::

ሌላው አባታችን ሆይ የሚለው ጸሎት ከፈጣሪ የተሰጠ ነው ቢሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ የሚለውም ከፈጣሪ የተሰጠ ነው:: እንዴት ቢሉ ከላይ እንደ ተመለከትነው ጸሎቱን ያገኘነው ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ነው እነርሱን ልኮ ያናገረ ደግሞ እራሱ አባታችን ሆይ ብላችሁ ጸልዮ ያለው እራሱ እግዚአብሔር ነውና ::

"፤ በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደምትባል ወደ ገሊላ ከተማ፥ከዳዊት ወገን ለሆነው ዮሴፍ ለሚባል ሰው ወደ ታጨች ወደ አንዲት ድንግል #ከእግዚአብሔር ዘንድ #ተላከ፥ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ
(የሉቃስ ወንጌል 1÷ 26-27


"፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም #መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥ " በታላቅ ድምፅም ጮኻ #እንዲህ አለች። #አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ #የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው አለቻት"

(የሉቃስ ወንጌል 1÷41-42


ስለዚህ ሁለቱም ሊነጣጠሉ የማይገቡ በአንድነት እንደየ ክብራቸው የተሰደሩ ሥርዓታዊ መጻሕፍ ቅዱሳዊ የሆኑ ጸሎቶች ናቸው ...ይቆየን...
#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን በዐድዋ
_____________________________
ጦርነት አስከፊ ነው የጦርነት ደግ የለውም ሆኖም በዓለማችን ላይ ቅዱስ ጦርነት ፤የመስቀል ጦርነት ተብለው የተጠሩ የጦርነት ዐይነቶች ነበሩ።
በአለፉት ሺህ ዓመታት በጥንታዊ ሀገራችን ኢትዮጲያ ከተፈጸሙ ታሪካዊ ነገሮች አንዱ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊ ተራዳኢነት ጀግኖች አባቶቻችን በፋሽሽት ኢጣልያ ላይ የካቲት ፳ ፫ ቀን ፲ ፰ ፻ ፹ ፰ ዓ.ም የተቀዳጁት የዐድዋ ድል ነው ይህ ድል የመላው አፍሪካ ጥቁር ሕዝቦች ድልና የነፃነት ብርሃን በመባል ይታወቃል።
#ጀግኖች_አባቶቻችንን በአድዋው ጦርነት የረዳቸው የሰማዕታት አለቃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሕገ ወንጌልን በማስተማርና አምልኮተ ጣኦትን በመንቀፍ ስለ ፈጣሪያችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕሪ አምላክነት እየመሠከረ ከግፈኖች አረማውያን ብዙ መከራ ተቀብሎ በአደባባይ መራራ ሞትን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ሰባት ዓመታትን ከተጋደለ በኃላ ሚያዝያ ፳ ፫ ቀን የሰማዕትነትን አክሊል ተቀብሏል።
ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዝያ ፳ ፫ ቀን ሰማዕትነትን ጊዮርጊስ በተቀበለበት ዕለት ከፈጣሪው ከኢየሱስ ክርስቶስ ልዮ ልዮ የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብሏል።ከተቀበለው ቃል ኪዳን መካከል በስምህ ተማጽኖ መታሰቢያህን የሚደርገውን እኔ በመከራው ቀን እረዳዋለሁ የሚል ይገኝበታል።
#ሊቀ_ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የሰማዕትነትን አክሊለ ክብር ከተቀበለ በኃላ በአካለ ነፍስ ሆኖ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተማኅጽኖ አቀረበ ይኸውም " ምስለ ፍልሠትኪ ደምርኒ እሙ" የፈጣሪየ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት እመቤቴ ድንግል ማርያም ሆይ ሰማዕትነትን ከተቀበልኩባት ከፋርስ ምድር የአጽሜ ፍልሠት ቀን ከአንቺ የፍልሰትሽ በዓል ቀን ጋር ነሐሴ ፲ ፮ ቀን ተባብሮ እንዲከበርልኝ ፈቃድሽ ይሆን በማለት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለመነ።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም እንዳልከው ይሆንልሃል ስለሆነም አንተም ከእግዚአብሔር አስራት ሁና የተሰጠችኝን ኢትዮጵያን ገበዝ (ጠባቂዋ) ሆነህ ጠብቃት አለችሁ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም አንቺ እንዳልሽ ይሁን እመቤቴ አለ ስለዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ገበዝ ወይም ጠባቂ ሁኖ ከእግዚአብሔር ተሹሟል።
#የቅዱስ_ጊዮርጊስ ፍልሰተ አጽም ከፋርስ ወደ ልዳ በነሐሴ ፲ ፮ ቀን ማለትም የእመቤታችን ቅዱስ ሥጋ ከጌቴ ሰማኒ ወደ መንግሥት ሰማያት በፈለሰበት (በዕርገቷ) ዕለት ተፈጽሞለታል። ይህን የቅዱስ ጊዮርጊስና የእመቤታችን ስምምነት በሚገባ የምታውቀው ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወራሪ ጠላት እና ከክፉ ነገር ሁሉ እንደሚጠብቃት ዘወትር ታምናለች።
በመሆኑም በጥንት ኢትዮጵያ የሚታወቅና ይደረግ የተበረ አንድ ነገር አለ ከቅድመ አያቶቻችን ጀምሮ የሚደረገውም ወጣት ኢትዮጵያዊን የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ማኅበርተኞች በመሆን በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም በየጊዜው እየተሰበሰቡም ሰለ ፈረስ ግልቢያ ፣ስለ ጦር ጉግስ፣ የጦር ስልትና ወታደራዊ የጀግንነት ትምህርት እየተማሩ እንዲያድጉ ያደርጉ ነበር።
#አባቶቻችን በዚህ ዕድገታቸው የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስና የለገራቸው ኢትዮጵያ ፍቅር አብሮ ያድጋል የጀግንነት ወኔአቸውና ሥነ ምግባራቸውም የላቀ ይሆናል እንዲህ ሁነው የሚድጉት ኢትዮጵያዊያን በማናቸውም ነገር በቀላሉ የማይበገሩ ስለሆኑና የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት ስለማይለያቸው በየትኛውም የጦርነት ታሪክ የተሸነፉበት ጊዜ የለም።
እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ታሪክ አፄ አምደ ጽዮን የጦር ሰው ነበሩ።በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ያላቸው እምነትና ተማጽኖ በእጅጉ የላቀ እንደነበርም ይነገርላቸዋል። በኢትዮጵያ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም ቤተ ክርስቲያን መሥራት የተስፋፋውም በእርሳቸው ዘመን ነው።
#በኢትዮጵያ የሥልጣኔ ታሪክ ዘመናዊ አስተዳደር እንዲስፋፋ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ እንደ ቀድሞዎ አባቶቻችን ከኢትዮጵያ ገበዝ(ጠባቂ) ከሰማዕት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበራቸው ፍቅር እጅግ የላቀ ነበር ። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የነገሱበት ዘመን በጊዜው የነበሩ የኢጣልያ ባለ ሥልጣኖች ቃላቸውን እየለወጡና እያታለሉ ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀኝ ግዛት ለመያዝ ቆርጠው የተነሱበት ዘመን ነበር።
የኢጣልያን ጦር መረብን ተሻግሮ ወደ ትግራይ እየገሰገሰ መምጣቱ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በሰሙ ጊዜ በ ፲ ፰ ፻ ፹ ፰ ዓ.ም የክተት አዋጅ አድርገው በጥቅምት ወር ወደ ትግራይ ሄዱ ጣሊያንን ለመፋለም ወደ ትግራይ ሲሄዱ ሁል ጊዜ ኢትዮጵያን በመርዳት የሚታወቀውን የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስንእና የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦት ይዘው ነበር የሄዱት ወቅቱም የዐቢይ ጾም መጀመሪ ስለነበር አብሯቸው የዘመተው አብዛኛው አርሶ አደር ገበሬ ጾሙን ሳይታ እየጾመ ነበር የተከተላቸው። እርሳቸውም ቢሆኑ ምንም እንኳ ዕለቱ እሁድ ቢሆንም ቅዳሴ ገብተው እስከ ረፋዱ ሦስት ሰዓት አስቀድሰው ነው ወደ ጦርነቱ የገቡት ።

..............ቀጣዮን የመጨረሻ ክፍል ይመልከቱ........
#ዐውደ_ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/112544300256976/posts/277932900384781/?app=fbl
#ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን በዐድዋ
____________________________
...የመጨረሻውና አስደማሚው ኩነት...
#ዳግማዊ_አፄ ምኒልክ ታቦተ ጊዮርጊስ በድንኳን ይዘው አድዋ ላይ ሰፍረው በነበረ ጊዜ ባንዳ የነበረ ሰው በኢትዮጵያ የጦር ሰፈር መሰላቸት እንዳለና ስንቅ እያለቀ መሆኑን ለኢጣሊያኖት እየሄደ ያወራ ነበር። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ በድንኳኑ ውስጥ የቅዱስ የጊዮርጊስ ታቦት የሚገለግለውን ካህን ጠርተው እንደ አባቶቼ ተዋግቼ እንድሞት እባክህን ጦርነቱን አስጀምረው ብለህ ንገርልኝ ሲሉ ይልኩታል።እርሱም እንደታዘዘው ያደርጋል።
ጦርነቱ ሲጀመር የኢትዮጲያ ወታደሮች በኢጣልያን ጦር ይጠቁ ጀመር ለዚህም ትልቁ ምክንያት ጀግንነታቸው ነበር ጣሊያኖች ምሽግ ይዘው ሲተኩሱ ጀግኖች አባቶቻችን ግን ምሽግ ውስጥ ተደብቆ መተኮስን እና ማጥቃትን እንደ ነውር በመቁጠር ደረታቸውን እየገለበጡ ፊት ለፊት ይዋጉ ስለነበር ነው ።በእውነቱ ይህ.ግሩም ድንቅ የሆነ ጀግንነት ነው!...
#እቴጌ_ጣይቱም ኢጣሊያ ይጠጣው የነበረውን የውኃ ጉድጓድ አስያዙት በዚህም ጣልያን ትንሽ ተዳከመ ሆኖም ሐበሻ መጠቃቱን አልቀረም ነበር ። ይህን የሐበሻን መጠቃት የተመለከተው የልዳው ሰማዕት ከእመቤታችን ጋር የገባውን ቃል ይፈጽም ዘንድ በነጭ አባ ላይ ፈረሱ ተቀምጦ መጥቶ ኢጣልያኖችን ፈጃቸው ድሉም የኢትዮጵያ ሆነ። ይህንንም በምርኮ የተያዙ የኢጣሊያ ጭፍሮች በአድናቆት ሆነው መስክረዋል።
በዚህም የድል ወቅት በጎጃም ዲማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በፍሬም የተሰቀለ ትልቅ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ነበር:: ጠዋት የገዳሙ እማሆይ አቃቢ ግብረ ማህረዕ ለመፈጸም ይህን ሥዕል ሊሳለሙ ሲገቡ ሥዕሉን ከቦታው ያጡታል በኃላ ወደ ማታ ይህው ሥዕል እየበረረ መጥቶ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ሲገባ ያዩታል እማሆይም አቃቢም አባቴ ጊዮርጊስ የት ውለህ መምጣትህ ነው ? ቢሉት ጌታሽን " ምኒልክን ስረዳው ውዬ መምጣቴ ነው" ብሎ በስብአዊ ልሣን አናገራቸው።
#እማ_ሆይም ከሥዕሉ በጦርነቱ የኢትዮያን አሸናፊነት ተረድተው በዕልልታ አቀለጡት:: አፄ ምኒልክም ከድሉ ሲመለሱ ከደስታቸው የተነሳ በአዲስ አበባ ለሰማዕቱ ውለታ ይሆን ዘንድ ፒያሳ የሚገኘውን የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ሰሩለት::
ዋቢ:- ልሳነ ተዋህዶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ጥር ፪ ሺህ ፫ ዓ.ም ያሳተመው መጽሔት
................ይቆየን ...........
#የእግዚአብሔር_ቸርነት_የድንግል_ማርያም_አማላጅነት_የሰማዕቱ_የቅዱስ_ጊዮርጊስ_ጥበቃና_ረድኤት አይለየን!
" ዐውደ ምሕረት የእናንተ "
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/112544300256976/posts/277932900384781/?app=fbl
#ዛቲ_ዕለት_ቅድስት_ይዕቲ
(ይህቺ ቀን የተቀደሰች ናት)
*****************************
#ቅድስት_ማለት የተለየች የጸናች ክብርት ማለት ነው:: ቤተ ክርስቲያንም በዚህ በዐብይ ጾም ሁለተኛውን ሳምንት ቅድስ ብላ በመሰየም የሰንበትን ቅድስና ታስባለች ::
ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ምንድነው?
_________________________
ፈጣሪ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር በሰድስቱ ዕለታት ፍጥረታትን ከፈጠረ በኃላ በሰባተኛው ዕለት ከሰራው ሥራ ሁሉ አረፈ "ለሙሴም የሰንበትን ቀን ትቀድሳት ዘንድ አሰብ "የምትለውን ትዕዛዝ ሰጠ ስለዚህ ሰንበትን ቅድስት ያሰኛት ከስራ ሁሉ የሚታረፍባት ሕመምተኛ የሚጠየቅባት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የሚገሰገስባት ቀን በመሆኗ ነው ::
በግብራቸው የተነሳ ዕረፍት እየተባሉ የሚጠሩ
***********************************
1) (ሰንበት ክርስቲያን )ዕለት እሁድ :- ዕረፍት ተብላ ትጠራለች: ዕለተ እሁድ በሌላ ስሟ ሰንበተ ክርስቲያንም ተብላ ትጠራለች :: አንዳንድ ጊዜ ሰንበት እሁድ ከሆነች ቅዳሜ ታድያ ምንድነች??? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል :: አስቀድሞ ዕለተ ቅዳሜ የአይሁድ ሰንበት ነበረች ጌታችንም እንደተናገረው ሕግ ና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽራቸው አልመጣውም እንዳለ የአይሁድ ሰንበት ቅዳሜም አልተሻረችም ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ቀዳዊት ሰንበት የቀደመች ሰንበት ብላ ታስባታለችች :: ማቴ5÷17 አንድም ደግሞ የኦሪት ሥርዓቶች ሁሉ ለአዲስ ኪዳን ሥርዓቶች ምሳሌ ጥላ መርገፍ ናቸውና ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ቅዳሜን እንደ ምሳሌ አድርጋ እሁድን አማናዊት ሰንበት አድርጋ ታስባቸዋለች ::
ዕለተ እሁድ( ሰንበተ ክርስቲያን)
*ጥንተ ዕለት ናት :- ፍጥረታት መፈጠር የጀመሩባት ዕለት ናትና "ይህቺ ዕለት ከ7ቱ ዕለታት ቀድማ የተገኘች ናት እንጂ በኃላ የተገኘች አይደለችም " እንዳለ ቅዱስ አትናቲዮስ በኩረ በዓላት ናት :-
* #የበዓላት ሁሉ መጀመሪያ ናትና ዓለም የተገኘባት
* #ወልድ ሰው የሆነባት
* # ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሳባት
* #ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣበት ዕለት ጭምር ናት::
2) #እመቤታችን ዕረፍት ተብላ ትጠራለች
____________________________

ከ5500 ዘመን የድካም የመከራ ጊዜ ሁሉ በእርሷ እረፍትን አግኝተናልና :: እንዴት ቢሉ መላእኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ባበሰራት ጊዜ ለዓለም መዳን ምክንያት ትሆኚ ዘንድ መርጦሻል ብሎ ፍቃዷን በጠየቀ ጊዜ "ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ "እነሆኝ የጌታ ባርያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ" በማለት ለድኅነተ ዓለም ምክንያት እረፍት ሆናለች:: #ሉቃ 1÷26
3) #ቅዱሳን :- እረፍት ተብለው ይጠራሉ::ቅዱሳን በሳኦል መንፈስ ለተያዘችው ደካማዋ ዓለም እረፍት ናቸው " እንዲህም ሆነ፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሆነ ጊዜ ዳዊት በገና ይዞ በእጁ ይመታ ነበር፤ ሳኦልንም ደስ ያሰኘው ያሳርፈውም ነበር፥ ክፉ መንፈስም ከእርሱ ይርቅ ነበር። (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 16÷23) አንድም ጻድቃን በጸሎታቸው ሕዝብ የሚያሳርፉሁ ናቸው ጻድቃንም በበዙ ጊዜ ሕዝብ ደስ ይለዋልና በመወለዳቸውም ብዙዎች ደስ ተሰኝተዋልና ምሳ 29÷2 ሉቃ 1÷14 ያዕ 5÷16
4) #ቅድስት_ቤተ ክርስቲያን እረፍት ትባላለች :-
__________________________________
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እግዚአብሔር እረኛዬ ነው የሚያሳጣኝም የለም በለመለመ መስክ ያሰማራኛል በእረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል " ብሎ ቤተ እግዚአብሔርን እንደ እረፍት ሥፍራ በውስጧ የሚፈሰውን ቃለ እግዚአብሔርን ደግሞ እንደ መብል እንደ መጠጥ አድርጎ ተናግሯል:: መዝ 22(23)÷1 አንድም የእረፍት ቦታ የሆነችው የመንግስተ ሰማያት የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ምሳሌ ናትና ዕረፍት ተብላ ትጠራለች ::
5) #መንግሥተ ሰማያት ራሷ እረፍት ትባላለች
_______________________________
እስራኤል ዘሥጋ ድካም ከበዛባት ከምድረ ግብጽ ወተው እረፍት የሆነችውን ምድረ ከንዓንን ወረሰዋል እኛም እስራኤል ዘነፍሶች ከዚህች ድካም ከበዛባት ዓለም እረፍት የምናገኘው በመንግስተ ሰማያት ነውና መንግስተ ሰማያት እረፍት ትባላለች :: " ነገር ግን። ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንድተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2:9)
6) #ጌታችን_መድኃኒታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ዕረፍት ይባላል :-
___________________________________
" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" ብሏልና ዕረፍታችን ነው (የማቴዎስ ወንጌል 11:28) አንድም የእግዚአብሔር መንግስት(የዕረፍት ሥፍራ) ከወድየት አለች ብለው በጠየቁት ጊዜ " ደግሞም። እንኋት በዚህ ወይም። እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና አላቸው።" (የሉቃስ ወንጌል 17:21) ይህን ያለው በመካከላቸው የነበረው እርሱ መንግስተ ሰማያት የእረፍት ሥፍራ ወይም እረፍታችን በመሆኑ ነው ::
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች የሰንበትን ቅድስና ስናስብ እግዚአብሔርን እመቤታችንን ቅዱሳንን መንግስተ ሰማያትን ሁሉ ታሳቢ ማድረግ ይገባናል ማለት ነው::
#የግርጌ_ማስታወሻ
++++++++++++++
እረፍትን ለማግኘት አስቀድሞ ሥራ ሊኖር ይገባል ሥራ በሌለበት እረፍት የለም:: እንድ ሰው አረፈ ለማለት አስቀድሞ ሥራ ሰራ ሊባል ይገባዋል:: እግዚአብሔርም ከሰራው ሥራ ሁለ አረፈ ተብሎ ተጻፈ እንጂ አረፈ ተብሎ ብቻ አልተጻፈልንም በመሆኑም እኛ ክርስቲያኖች እረፍተ መንግስተ ሰማያትን እረፍት እግዚአብሔርን እረፍት እመቤታችንን እረፍት ቅዱሳንን ለማግኘት በጎ ሥራን ሁሉ ልንሰራ ያስፈልጋል :: አንድ ሊቅ በሰንበት አንድ ሥራ ሲሰሩ የኔ ቢጤ ጨዋ መቶ ምነው አባ እግዚአብሔር እንኳን ባረፈበት ቀን በሰንበት ለምን ሥራ ይሰራሉ አላቸው ሊቁም ፈገግ ብለው አዮትና ልጄ እርሱ ኮ ያረፈው ሥራውን ሁሉ ጨርሶ ነው እኔ ምን ሰርቼ ነው የማርፈው አሉት ይባላል :: በሰንበት ለሰንበት የሚገባ ሥራ ልንሰራበት ይገባል እንጂ ሥራ ፈተን መቀመጥ አይገባንም ሥራ የፈታ አህምሮ የሰይጣን ቢሮ ነውና ያለ ሥራ የተቀመጠ ሰው ሊስት ሊሳሳት ይችላል::
በሰንበት ዝም ብሎ ከመቀመጥ ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሄድ የታመመ ካለ መጠየቅ መጸለይ ሌላም ሌላም የትሩፋት ሥራ ልንሰራ ይገባል :: ይህን ካደረግን ቅድስት ከሆነችው ከሰንበት ረድኤትና በረከትን እናገኛለን::
.........ይቆየን...........
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ /ማርያም
የካቲት 12/2010 ዓም
#ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ !
__________________________
#የሀገር የሌማት ትሩፋት #ቅድስት_ቤተ_ክርስቲያን ናት !!!
ያለ እርሷ ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለም! ስለዚህ አትጨቁኟት

" የተሰወረ መና ያለብሽ #ንጹዑ_የወርቅ_መሶብ አንቺ ነሽ !
|ሶሪያዊው #ቅዱስ ኤፍሬም