ክርስቶስ #የግል_አዳኝ ወይስ #መዳኃኔዓለም?
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ዛሬ በፕሮቴስታንቱ ዓለም "ጌታን እንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል።" የሚለው አባባል መስማት የተለመደ ሆኗል። ክርስቶስን "የግል አዳኜ" ሲሉም ይስተዋላል። ይህን ቋንቋ በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አመክንዮ ስንመለከተው ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አናገኘውም። የትኛውም ሐዋርያ ሰዎችን በክርስቶስ የግል አዳኝነት እንዲያምኑ ሲያደርግ አላየንም አልሰማንም። ነገር ግን ሁሉም የተባበሩበት በአንድ መንፈስ ቅዱስ ተነድተው የተናገሩት የጻፉትና ያስተማሩት የክርስቶስን #መድኃኔዓለም መሆንን ነው። እስኪ የተወሰኑ ማስረጃዎችን እንመልከት…
👉 ሉቃ 2:10–11 "መልአኩም እንዲህ አላቸው ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
ይህን ቃል የተናገረው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው። የክርስቶስን ወደዚህ ዓለም መምጣት ለእረኞቹ ባበሰረበት ቃሉ #ለህዝቡ_ሁሉ_የሚሆን… #መድኃኒት ተወለደላችሁ በማለት ነበር። መልአኩ ለህዝቡ ሁሉ አለ እንጂ ለአንተ ወይም ለአንቺ የግል አዳኝህ አዳኝሽ የሚሆን ክርስቶስ ተወለደ አላለም። እርሱ መድኃኔ ዓለም መድኃኒትነቱ ለዓለሙ (ለህዝቡ) ሁሉ ነውና። መልዓኩ ከዚህ ቀደም ለጻድቁ ዮሴፍ በህልሙ በተገለጠለትም ጊዜ "እርሱ #ህዝቡን_ሁሉ ከኃጢአታቸው ያድናቸዋል" ነበር ያለው። ማቴ 1:21 መልአኩ የክርስቶስን መድኃኔዓለም መሆን ከነገረን #የግል_አዳኜ የሚለው ምን የሚሉት ፈሊጥ ይሆን???
👉 ዮሐ 4:42 “አሁን የምናምን ስለ ቃልሽ አይደለም እኛ ራሳችን ሰምተነዋልና እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን ይሉአት ነበር።” የሰማርያ ሰዎች በግልጽ ንግግር ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት ነው ብለው ምስክርነት ከሰጡ #የግል_አዳኝ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን ፍጹም መቃረን መሆኑን ልናውቅ ይገባል።
👉 ዮሐ 1፥29 “ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።” ጌታችን ከተጠመቀ በኋላ ወደ አጥማቂው ለስንብት በመጣ ጊዜ ገና በእናቱ ማኅጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ክርስቶስ መድኃኔዓለም መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ስለገለጠለት #የዓለሙን_ኃጢአት_የሚያስተሰርይ ብሎ መሰከረ። በመንፈሰ እግዚአብሔር የሚመራውን መንገደ ክርስቶስን የጠረገውን መጥምቁን እንቀበል ወይስ ሉተርን????
👉 ዮሐ 3:16–17 "በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ #ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። #ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና።" የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው ዓለሙን ሁሉ ያድን ዘንድ ነው በማለት ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እየነገረን #ጌታን_እንደ_ግል_አዳኝ_አድርገህ_ተቀበል የሚለው አስተምሮ ጤነኝነት ነው ብላችሁ ታስቡ ይሆን??? አይመስለኝም።
👉 ይሁ 1:3 "ወዳጆች ሆይ ስለምንካፈለው ስለመዳናችን እጽፍላችሁ ዘንድ እጅግ ተግቼ ሳለሁ…" ሐዋርያው በማያሻማ ቃል #መዳናችን በማለት ክርስቶስ የፈጸመው የማዳን ሥራ ለሁሉም መሆኑን ተናገረ። ሰው ሁሉ አንድ ጊዜ ክርስቶስ ከፈጸመለት የማዳን ሥራ የሚካፈል እንጂ ክርስቶስን አንደ ግል አዳኝ አድርጎ የሚቀበለው እንዳልሆነ የሐዋርያው ንግግር ልብ ይለዋል።
👉 1ኛ ጢሞ 4፥10 “ይህን ለማግኘት እንደክማለንና ስለዚህም እንሰደባለን ይህም #ሰውን_ሁሉ ይልቁንም የሚያምኑትን #በሚያድን በሕያው አምላክ ተስፋ ስለምናደርግ ነው።” በግልጽ ቃል ሰውን ሁሉ የሚያድን በማለት ግላዊነት አስተሳሰብን ሳያንጸባርቅ ክርስቶስ አዳኝነቱ የዓለም መሆኑን ያስረዳናል።
👉 1ኛ ዮሐ 4፥14 “እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።” እንዳለ ሐዋርያው እኛም ያመነውን እንመሰክራለን። ምንመሰክረውንም ደግሞ እናምናለን። የሐዋርያውን ዐይን ዐይናችን አድርገን ክርስቶስ ዓለሙን ሁሉ አንዳዳነ ዐይተናልና መድኃኔዓለም አንለዋለን።
በመጨረሻ ሥሮቿ በምድር ምዕመናን ቅርንጫፎቿ በሰማይ ቅዱሳኑ እና መላእክት ራሷ ደግሞ ክርስቶስ የሆነ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መላእክት የመሰከሩትን ሐዋርያት የተባበሩበትን ክርስቶስ መድኃኔዓለም ሆኖ ደሙን ለዓለሙ ሁሉ ማፍሰሱን አምና ታሳምናለች። እኛም ክርስቶስን አንደ ግል አዳኝህ አድርገህ ተቀበል የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለውን ትምህርት በመቃወም የግላዊነት አስተሳሰብን አስወግደን ከክርስቶስና እርሱን ከመሰሉ ከቅዱሳን ሐዋርያት እንደተማርነው መድኃኔዓለም ብለን እናምናለን እንታመናለን።
የእግዚአብሔር አብ ጸጋ
የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር
የእግዚአብሔር መንፈስቅዱስ ሕብረት አንድነት አይለየን።
አጽራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን።
ይቆየን።
አዘጋጅ: #አቤኔዘር
👉 @AwediMeherit