Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
ለክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት:- ልደታ ለማርያም
እንኳን አደረሳችሁ!!
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከእናቷ ማኅፀን ጀምሮ ጥንተ አብሶ ካመጣው ፍዳና መርገም ጠብቋታል:: የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ዓለም በጥንተ አብሶ በነበረበት ዘመን በክርስቶስ ማዳን ዋዜማ ሲያበሥራት ቅድስት ኤልሳቤትም በፅንሰቷ ጊዜ ስታመሰግናት ደጋግመው "ጸጋን የሞላብሽ ሆይ" "አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ።" እያሉ ይህን እውነት መስክረዋል። (ሉቃ፩:፳፮-፵ በጥንተ አብሶና ውጤቱ (origional sin and its effects) ምክንያት ሰዎች "የእግዚአብሔር ክብር ጎድሏቸዋል በተባሉበት ዘመን ጸጋን የተመላች ብቸኛ ልዩ እርሷ ነበረች:: ።" (ሮሜ ፫:፳፫) እግዚአብሔር እርሷ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ለመውለድ ፈቃደኛ እንደምትሆን ስለሚያውቅ አስቀድሞ በአካል የሚመስለው በባሕርይ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ አንድያ ልጁን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንድትወልድ ቅድመ ዓለም መርጧታልና የእመቤታችን ልደት (ልደታ ለማርያም) የዓለም መዳን የማይቀር መሆኑ ለታወቀበት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መንገድ የጠረገ ልደት ነው እንላለን። (The nativity of the blessed virgin Mary prepares the way for the birth of Jesus Christ) እንዳለ ሊቁ። (The book of the nativity of Virgin Mary ,) የጌታችን ሰው መሆን "ከዘላለምና (ቅድመ ዓለም) ከትውልዶች ጀምሮ (ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ) ተሰውሮ የነበረ ምሥጢር ነው።" (ቆላ፩:፳፮) መባሉም የአምላክ ሰው መሆን እንዲሁም የእርሷ እርሱን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለድ ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ሕሊና የሚታወቅ መሆኑን ያስረዳናል። (ኢሳ ፯:፲፬ ፱:፮) እርሱ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ የአማልክት አምላክ ነው። (መዝ ፻፴፭:፩ ራእ፲፱:፲፮) እርሱ ፍጥረትን ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ፈጣሪ ነው:: "ሁሉ በእርሱ ሆነ ከሆነውም አንዳች ያለ እርሱ አልሆነም።" (ዮሐ ፩:፫) "መልካሙን ነገር ለማድረግ በክርስቶስ ተፈጠርን።" "የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናት ቢሁኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና።" እንደተባለ:: (ቆላ ፩:፲፭-፲፮፣ ኤፌ ፪:፲) እርሱ ለቅዱሳን የጸጋ አምላክነትን ክብር የሰጠ ሁሉን ፈጥሮ የሚገዛ የባሕርይ አምላክ ነው:: (ዘጸ ፯:፩፣ መዝ ፹፩:፩፣ ዮሐ፲÷፴፬፣ ሮሜ ፱:፭፣ ፩ተሰ ፫:፲፩፣ ቲቶ ፪:፲፩፣ ፩ዮሐ ፭:፳) እርሱ ቸር ከሆነ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአገዛዝ በሥልጣን በሕልውና በመለኮት አንድ ነው:: (ዮሐ ፲:፴፣ ፲፯:፲፣ ማቴ ፲፩:፳፯-፳፱፣ ዮሐ ፲፬:፮-፰) እርሱ ፀሐይ እናቱ ምሥራቅ ናት:: (ሕዝ ፵፬:፩፣ ዮሐ ፰:፲፪፣ ሚል ፬:፪) ምሥራቅ እናቱን ዘወትር መሻታችን የፀሐይ ክርስቶስን በረከት ፍቅርና ቸርነት ለማግኘት ነው:: እንኳንስ እናቱን ነቢዩ ዳዊት ስለ ወዳጆቹ "ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው ስለዚህም ነፍሴ ፈለገቻቸው።" ብሎ ዘምሯል:: (መዝ ፻፲፰:፻፳፭) እርሱ የባሕርይ አምላክ እርሷ ደግሞ ወላዲተ አምላክ ( Theotokos) ናት:: ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከተፈጠረም በኋላ መቸም መች አምላክን "ልጄ ወዳጄ" ማለት ከቶ ለማን ተችሏል? እርሱ ፈጣሪ እርሷ ደግሞ ወላዲተ ፈጣሪ ኩሉ ዓለም ናት:: እርሱ እውነተኛ ደስታ እርሷ የደስታ መፍሰሻ ናት። (መዝ ፵፭:፭) እርሱ ሕይወት እርሷ ነቅዐ ሕይወት (የሕይወት ምንጭ) ናት። ይህች ብርሃን ሙዳየ መድኃኒት ቤዛዊተ ኩሉ ብርሃንን ትሰጠን ሕይወት ክርስቶስን ትወልድልን ዘንድ ከተቀደሱ ተራሮች ከአብርሃም ከዳዊት ቤት ተወለደች። (መዝ ፹፰(፹፱):፩)
+++ የልደቷ ቀን +++
አንተ የራስህን እንዲሁም የምትወዳቸውን ሰዎች ልደት ሻማ አብርተህ ኬክ አስጋግረህ ወዳጅ ዘመዶችህን ጠርተህ በዳንስ በጭፈራና እስክስታ በመውረግረግ ታከብራለህ የአምላክ እናት ድንግል ማርያም የተወለደችበትን ቀን በማሰብ በዓለ ልደቷን የሚያከብሩ ሰዎችን ግን ለምን ያከብራሉ ብለህ ትተቻለህ:: ለመሆኑ አንተ ያንተ የሆኑትን ሰዎች ልደት ተገቢ በሆነ መንገድ ብታከብር አምላክ እንደማያዝንብህ ካወቅህ የእናቱን ልደት እርሱን እያመሰገንን እያወደስን እናቱ "ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል።" (ሉቃ ፩:፵፱) እንዳለችም እርሷንም እያመሰገንን "ብርቱ የሆን እርሱ በእኔ ታላቅ ሥራ አድርጓልና።" ብላ እንደመሠከረችም በእርሷ ለሰው ዘር የተደረገውን ታላቅ ሥራ እያሰብን ብናከብር የሚያዝንብን ይመስላሃልን? ከማዳኑስ በላይ ምን ታላቅ ሥራ አለ? ዓለም:- የኤድስ ቀን፣ የጉበት ቀን፣ የኩላሊት ቀን፣ የላብ አደር ቀን፣ የውሃ ቀን፣ የአፈር ቀን፣ የእናቶች ቀን፣ የአባቶች ቀን እያለ በልዩ ልዩ መንገድ ሲያከብር ቅር አይለውም የእናቱ የእመቤታችንን ልደት ለማክበር ግን ያመዋል::
ልደታ ለማርያምን ስናከብር
☞ ቤተ ክርስቲያንን በሚያስነቅፍ አብዝቶ በመብላትና በመጠጣት በዳንኪራና በአስረሽ ምስናከብር
ሆን በመንፈሳዊ ሥርዓት እናክብረው ያኔ የልጇ በረከት እጥፍ ድርብ ይሆንልናል። (ምሳ ፲:፯፣ ፩ጴጥ ፪:፲፪)
☞ የቤተክርስቲያን ባልሆነ የልደቷን ነገር በማይገልጥ በማይወክል መንገድ በአምልኮ ባዕድ ጨሌን በየዛፉ ዙርያ አረቄና ቡና በማፍሰስ የሚያከብሩትን ሰዎች በማስተማርና ትክክለኛውንና የክርስትናውን መንገድ በተከተለ መንገድ እንዲያከብሩት በማድረግ ድርሻችንን በመወጣት እናክብር ::
☞ ልደቷ "በመወለዱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።" ከተባለለት ከዮሐንስ ልደት የሚልቅ መሆኑን እንወቅ። እርሷ የዮሐንስ ፈጣሪ የክርስቶስ እናቱ ናትና። ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም " ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ።" እንዳለ:: እርሱ ክርስቶስ "ሁሉን በስሜ አድርጉት" እንዳለን እርሷን በእርሱ ስም ወላዲተ አምላክ እመ ብርሃን ብለን ተቀብለን ልደቷን እንደምናከብር እንረዳ:: (ሉቃ ፩:፲፬)
+++ አድባር +++
አድባር የሚለው ቃል የግእዝ ሲሆን ትርጉሙም ተራሮች ማለት ነው:: እመቤታችን በሊባኖስ ተራሮች መሐል ተወልዳለችና የልደቷን ወቅት አድባር እንላለን። (መኃ ፬:፰)
🚹የእናቱን በዓለ ልደት ማክበር ማኅበራዊ ፋይዳ 🚹
በዚህ ቀን የአንድ ቀዬ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ጸሎት በማድረግ እግዚአብሔርን በማመስገን እናቱንም በማወደስ ማክበራቸው ከሃይማኖታዊው ፋይዳ ባለፈ በልዩ ልዩ ምክንያት እየደበዘዘና እንደ ዳይኖሰርና ዶዶ ድራሹ እየጠፋ የመጣውን አብሮነት ማኅበራዊ ትስስር የሚያጠነክር መልካም ባሕላችንም ጭምር ነውና አጥብቀን ልንይዘው ይገባናል:: የድንግል ልጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ የልደት ቀን በረከት ያሳትፈን!!!
©️ መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ሚያዝያ ፴ ቀን ፳፲፮ ዓ ም

Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Eyob kinfe)
"ዕርገተ ክርስቶስ"
#ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት "አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ፤ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ"(መዝ46:5) በማለት ጌታው ሲሆን ልጁ ልጁ ሲሆን ጌታው ስለሚሆን ስለ ኢየሱስ ክርሰቶስ ትንቢት ተናግሯል።
#በዚህ ኃይለ ቃል ያለው ምሥጢረ ተዋሕዶ ምንድን ነው? ቢሉ "አምላክ" ብሎ አምላክነቱን "ዐረገ" ብሎ ሰውነቱን ያስረዳል።ማረግ (ከፍ ከፍ ማለት፣ወደ ሰማይ መውጣት) የሚስማማው ሥጋ ነውና በተዋሕደው "ሥጋ ማርያም" በሁሉ ላለ "ቃል ለሚባል እግዚአብሔር" ዕርገት ተነገረለት።
#ነገሩን ትንሽ ለመግለጥ ያህል፦አምላክ በሁሉ ቦታ (በምልዐት) የሚገኝ ስለሆነ ከዚህ ተነሥቶ እዚያ ደረሰ አይባልም።አምላክ በተዋሕዶ ሰው ሲሆን ግን ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር ለእኛ የሚነገረው ሁሉ ለእርሱም ተነገረለት።ተፀነሰ፣ተወለደ፣ተሰደደ፣ተጠመቀ፣ተሰቀለ፣ሞተ፣ተቀበረ፣ተነሣ፣ዐረገ ተባለለት።ይህ ሁሉ ግን በበጎ ፈቃዱ የተከናወነ ነው ፤ እንደኛ ግዳጅ ያለበት አይደለም።
#ክርስትና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስን የእግር አሻራ የመከተል ሕይወት ነውና እርሱ ስለኛ የፈጸማቸውን ሁሉ እንፈጽማለን።ኋላም እርሱ በኃይሉና በሥልጣኑ ተነሥቶ እንዳረገ እንዲሁ እኛንም አስነሥቶ ያሳርገናል።ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ "እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ" ማለቱም ለዚህ ነው።
#ወደ እኔ እወስዳችኋለሁ ብሎ ጌታችን የነገረን ቃል እኔን በመመሰል እንድታድጉ (Theosis:ሱታፌ አምላክ) አደርጋችኋለሁ ሲል ነው።ይኸውም በመንግሥተ ሰማያት የምንኖረው ኑሮ "ዕርገታዊ" (ከፍ ከፍ የማለት) እንደሆነ ያስረዳል።ከቅዱሳን መላእክቱ ጋር "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" በማለት ውስጥ እየተቀደስን በጸጋ ላይ ጸጋ በክብር ላይ ክብር በጣዕም ላይ ጣዕም እየተጨመረልን እግዚአብሔርን እየመሰልን ከፍ እንላለን።
ከበዓለ ዕርገቱ ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን!!!

"ዕርገተ ክርስቶስ እንደ ሃይማኖት"
#በጸሎተ ሃይማኖታችን ከምንመሰክራቸው ምስክርነቶች አንዱ "በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ" የሚል ነው።በዚህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተነሣ በኋላ እንዳረገ ማመናችንን እንገልጣለን።ይህንን ሃይማኖታችንን ያገኘነውም "የእግዚአብሔር መንፈስ ካለባቸው" ቅዱሳት መጻሕፍት ነው።(2ኛ ጢሞ 3:16)
ቅዱስ ዳዊት "በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" (መዝ 67:33) ቅዱስ ሉቃስ ደግሞ "ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ" (ሉቃ 24:51) ብለውናል።እነዚህም የቅዱሳት መጻሕፍት ምስክርነቶች ናቸው።
"ዕርገተ ክርስቶስ በነገረ ማርያም"
#የእመቤታችን ወዳጅ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ "ከምድር ወደ ሰማይ ለማረግ መሰላል ሆንሽ" ሲል ያመሰግናታል።ይኸውም ለቃል ርደት(መውረድ (ሰው መሆን) ) ለሥጋ ዕርገት ( ከፍ ማለት (አምላክ መሆን) )ምክንያት ድንግል ማርያም ናት ማለት ነው።ቃል ሥጋ ሲሆን ሥጋም ቃልን በመሆን ከፍ ያለው (ያረገው) በማኅፀነ ድንግል ማርያም ነው።ኋላም ከተነሣ በዐርባኛው ቀን ያረገው ከእመቤታችን ሰው በሆነበት ሥጋ ነው።በዕርገቱ ጊዜ ከእናቱ የነሣው (የተዋሐደው) ሥጋ አልተለየውም።"በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ..." በሚለው ኃይለቃል ውስጥ ያለው "ምሥራቅ" የሚለው ቃልም "ሥጋ ማርያም"ን ያሳያል።ጌታ ፀሐየ ጽድቅ ሆኖ ከእርሷ የወጣባት ምሥራቅ ድንግል ማርያም ናትና።ስለዚህ ኃይለ ቃሉ "በድንግል ማርያም ሥጋ ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" ተብሎ ይተረጎማል።
"ዕርገተ ክርስቶስ በአምልኮአችን"
#ቅድስት ቤተክርስቲያን የምትገለጥበት ትልቁ አምልኮዋ ቅዳሴ ነው።የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በቅዳሴዋ "አሜን" ( አሜን ለሃይማኖት ሲሆን ትክክል/እውነት ማለት ነው) እያለች ከምትናገራቸው ምስክርነቶቿ አንዱ "ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ" (ዕርገትህን እናምናለን ሁለተኛ መምጣትህንም) የሚል ነው።እንዲሁም ካህኑ "አልዕሉ አልባቢክሙ" (ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ) በማለት ከፍ ከፍ ያለውን አምላካችንን ሲያሳስበን ዲያቆኑ ደግሞ "ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ" ብሎ የጌታን በምሥራቅ ማረግ ያስታውሰናል።ልቡናን ከፍ ከፍ ማድረግም በዓይነ ልቡና ከሐዋርያቱ ጋር ጌታን ሲያርግ መመልከት ፤ በዕዝነ ልቡና የቅዱሳን መላእክቱን ዝማሬ ማድመጥ፤ በአንፈ ልቡና መዓዛ ዕርገቱን ማሽተት ፤ በእግረ ልቡና ከሐዋርያቱ ጋር በደብረ ዘይት መቆም፤በአብራከ ልቡና ለጌታችን መስገድና በዚህ ሁሉ መደሰት ነው።"እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ" እንዲል (ሉቃ 24:52)
"ዕርገተ ክርስቶስ በክርስቲያናዊ ሕይወት"
#ጌታችን ወደ ላይ ከፍ ከፍ እንዳለ ክርስትናም ከፍ ከፍ የማለት ሕይወት ነው።ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ዮሐንስ "በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል" (1ኛ ዮሐ 2:6) እንዳለ ጌታችን ከፍ ከፍ እንዳለ እኛም በቅድስና ከፍ ከፍ ልንል ይገባናል።ይህ የቅድስና ሕይወትም ከሥጋ ንጽሕና ወደ ነፍስ ንጽሕና ከነፍስ ንጽሕና ወደ ልቡና ንጽሕና የሚደረግ ጉዞ ነው።ከሁሉ አስቀድመን ግን ከስድብ ወደ ምስጋና፣ከጥላቻ ወደ ፍቅር፣ከቂም ወደ ይቅርታ፣ከዓለም ወደ ቤተክርስቲያን፣ከፍልስፍና ወደ ሃይማኖት፣ከገዛ አጉል እሳቤአችን ወደ እግዚአብሔር ሐሳብ ከፍ ከፍ ልንል ያስፈልገናል!!!
"ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ፤ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን።" (2ኛ ተሰ 4:17)
መድኃኔዓለም እንዲህ ያለውን የክብር መነጠቅ በቸርነቱ ያድለን !!!
ሰኔ 07/2016 ዓ.ም
#ኢዮብ ክንፈ

ዛሬ ይለቀቃል !!
በራሴ የዩትዩብ ቻናል ይጠብቁ
ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ ለሌሎችም በማጋራትና እዲቀላቀሉ በመጋበዝ ይደግፉኝ!!🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ

YouTube
🔴 አዲስ ዝማሬ "የዋኅ መልአክ" ዘማሪ ዳዊት ክብሩ || | Yewah Melak l Z Dawit Kibru
የዋኅ መልአክ
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል
ታዳጊያችን ነህ ምክሩ ለልዑል
የአምላክ ኀይሉ መገለጫው ነህ
የእልፍ አእላፍ መላእክት መስፍናቸው ነህ
ለሠራዊተ ሰማይ መላእክት አለቃቸው
ለፍጥረቱ ለባሕር ለየብሱ አጽንዖታቸው
የዋኅ ርኅሩኅ መልአክ ኀዳጌ በቀል
በልመናው በጸሎቱ ያስምረናል ቅዱስ ሚካኤል ።
የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ ቅዱስ ሚካኤል
ለሰው ልጆች የምታዝን ምታማልድ ከልዑል
እነሆ ሕይወታችንን…
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል
ታዳጊያችን ነህ ምክሩ ለልዑል
የአምላክ ኀይሉ መገለጫው ነህ
የእልፍ አእላፍ መላእክት መስፍናቸው ነህ
ለሠራዊተ ሰማይ መላእክት አለቃቸው
ለፍጥረቱ ለባሕር ለየብሱ አጽንዖታቸው
የዋኅ ርኅሩኅ መልአክ ኀዳጌ በቀል
በልመናው በጸሎቱ ያስምረናል ቅዱስ ሚካኤል ።
የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ ቅዱስ ሚካኤል
ለሰው ልጆች የምታዝን ምታማልድ ከልዑል
እነሆ ሕይወታችንን…
Forwarded from Eyob kinfe
❤ "ሕይወትን በሚሰጥ አዳኝ በሆነ ከአብ በሠረጸ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን" (ጸሎተ ሃይማኖት)❤
#እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በዛሬው ዕለት በእሳትና በነፋስ ተመስሎ ለቅዱሳን ሐዋርያት ወረደ።ይኸውም በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት የደስታ መፍሰሻ ወላዲተ አምላክን ከብበው በአንድ ልብ ሲጸልዩ ነው።
#ፍስሕት (ደስተኛዪቱን) ይዘው ቢጸልዩ የደስታ መንፈስ የሆነ መንፈስቅዱስ ወረደላቸው።
#መዝገበ ምሥጢር ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ከሣቴ ምሥጢር (ምሥጢርን የሚገልጥ) መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው።በዚህም በሚያውቁት አንድ ቋንቋ ላይ ሰባ አንድ ቋንቋ ተገልጦላቸው ቅዱስ ወንጌልን ሰብከዋል።
#ናዛዚት (የምታረጋጋ) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ናዛዚ (የሚያረጋጋ) መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቷቸዋል።
#ንጽሕት ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መንጽሒ (ከኃጢአት የሚያነጻ) መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።
#ጽንዕት (የጸናች) ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ መጽንሒ (የሚያጸና) መንፈስቅዱስን ተቀበሉ።
#መስተሥርዪ ኃጢአት (ኃጢአትን ይቅር የምታስብል) ርኅርኂተ ኅሊና ድንግል ማርያምን ይዘው ቢጸልዩ ኃጢአትን ይቅር የሚል መንፈስ ቅዱስ በእሳት ተመስሎ ወደ እነርሱ መጣ።
#እናታቸውን ይዘው ምን ሊያጡ ኖሯል?ጽዮንን (እመቤታችንን) ከብበው ቢጸልዩ በደብረ ጽዮን የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አደረባቸው።
#ይህቺ ቀን የቅድስት ቤተክርስቲያን የልደት ቀን ናት።ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው እንደ ጌታቸው ሁሉ ጾሙ ጸለዩ።መንፈስ ቅዱስ ያደረበት እንደሚጾም እንደሚጸልይ ያጠይቃል።በዓለም ሁሉ ዞረው ወንጌለ መንግሥተ ሰማያትን ሰበኩ።
#አምላካችን መንፈስ ቅዱስ በቸርነቱ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት አማላጅነት ከመፍገምገም ወደ ጽናት ፣ ከኃዘን ወደ ደስታ ፣ ከኃጢአት ወደ ንጽሕና ፣ ከመቅበዝበዝ ወደ መረጋጋት ፣ ከድንቁርና ወደ ዕውቀት ይመልሰን!!! አሜን !!!
#በዓለ ጰራቅሊጦስ
ወርኃ ሰኔ 16 / 2016 ዓ.ም

subscribe ያድርጉ 🙏🙏🙏
👇👇👇👇👇👇
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
👇👇👇👇👇👇
http://www.youtube.com/@ZemariDawitkibru2405 Youtube channel - Zemari Dawit kibru | Official ዘማሪ ዳዊት ክብሩ
Forwarded from Zemari Samuel Tekle Official || ዘማሪ ሳሙኤል ተክሌ (Samuel T)
YouTube
የቅዱሳን ታሪክ || አባ ሙሴ ጸሊም
የቅዱሱ አባት የአባ ሙሴ ጸሊም ሕይወቱና ድንቅ ምክሮቹ
#አባሙሴጸሊም #አባ #አባሙሴ #አባሙሴፀሊም #የቅዱሳንታሪክ #የቅዱሳንታሪክትረካ #የቅዱሳንታሪክፊልም #ትረካ #ፊልም
#ethiopiaortodoxtewahdo #ethiopianorthodoxtewahedomezmur #ethiopianorthodoxtewahedooldmezmurcollection #ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopi…
#አባሙሴጸሊም #አባ #አባሙሴ #አባሙሴፀሊም #የቅዱሳንታሪክ #የቅዱሳንታሪክትረካ #የቅዱሳንታሪክፊልም #ትረካ #ፊልም
#ethiopiaortodoxtewahdo #ethiopianorthodoxtewahedomezmur #ethiopianorthodoxtewahedooldmezmurcollection #ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopi…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
+++ ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ! +++
በፍጹም ተዋሕዶ አንድ የኾነ ክርስቶስን እየነጣጠለ በሰውነቱ እንዲህ በመለኮቱ እንዲያ እያለ ሊከፍል የሚሻ አስተሳሰብን ለመንቀፍ ሊቃውንቱ "ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ" በማለት መጻሕፍትን መሠረት አድርገው ከፊደል ላይ ሳይሆን ትርጓሜን መነሻና መድረሻ አድርገው በስፋት ያስተምራሉ "ተዋሕዶ ኹለትነትን አጠፋ" ለማለት። ሥግው ቃል (Incarnated logos) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ አይነጣጠልም አይከፋፈልም!!
በፍጹም ተዋሕዶ ሰው ሆኖ በሥጋ ማርያም የተገለጠ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከኹለት አካል አንድ አካል፤ ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ነው፡፡ ሥጋም ፍጹም በሆነው ተዋሕዶ የመለኮትን ገንዘብ (ግብረ ባሕርዩን፡- ሁሉን ዐዋቂነት ሁሉን ሰጪነት ልዕልና ምሉዕነት ሁሉን ቻይነት ….) ገንዘቡ አድርጓልና "ለአብ ያለው ሁሉ የእኔ ነው።" ብሎ ተናገረ፡፡ (ዮሐ 16፥15)
ለአብ ያለው ምንድነው? ለአብ ያለው ዕውቀት፣ ቸርነት፣ ከኃሊነት፣ ጥበብ ሁሉ ለወልድም አለውና የወልድም ጥበቡ፣ ዕውቀቱ፣ ቸርነቱ፣ ከኃሊነቱ ተቆጥሮ ተሠፍሮ አያልቅም ፡፡ ለእኛ ጸሎትን ምስጋናን ሊያስተምረን ሥጋም (ሰውነት) በተዋሕዶ መክበሩን በገለጠበት አንቀጹ "አባት ሆይ ያንተ የሆነ ሁሉ የእኔ ነው የእኔውም ያንተ ነው።" በማለት ተናግሯል፡፡ (ዮሐ 17፥10) ጌታችን ክብር ይግባውና ከባሕርይ አባቱ ከአብ ጋር በሥልጣን በሕልውና በአገዛዝም በምልአትም አንድ እንደሆነ በሥጋዌው ወራት ዋና ምሥክርነቱ ነበር፡፡ (ዮሐ 14፥8-11) "የእኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ ባደርገው ግን እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደሆነ እኔም በአብ እንደሆንሁ (በሕልውና፣ በአኗኗር፣ በዕውቀት አንድ እንደሆንን) ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።" ብሎ እንደተናገረ፡፡ (ዮሐ10፥38)
ወልድን መካድ (በወልድ ላይ የክሕደት ንግግር መናገር ) አብን መካድ ነው፡፡ ወልድን በገደምዳሜ ወደ ንስጥሮሳዊ ትምህርት ማስጠጋት አብንም መካድ ነው። ሊቃውንቱ "አብ ሲነክ ወልድ ይነክ።" እንዲሉ። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ "ወልድን የሚክድ አብ እንኳን የለውም በወልድ የሚታመን አብ ደግሞ አለው።" ብሎ የመሠከረውም ይህን ያመለክተናል፡፡ (1ዮሐ 2፥23)
መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ሠኔ 26 ቀን 2016 ዓ ም
https://www.facebook.com/bitwoded.worku?mibextid=ZbWKwL

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
"ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሣራ ተመልከቱ።" (ኢሳ 51:2)
ነቢዩ ይህንን ቃል ቅዱስ አብርሃምንና ቅድስት ሣራን ምሰሏቸው ለማለት ተናግሮታል።
#አብርሃም አበ መናንያን (የመናንያን አባት) ነው።ሁሉን ትቶ እግዚአብሔርን ተከትሎአልና።(ዘፍ 12:1)
#አብርሃም የሙሽሮችም አባት ነው።ሚስቱ ምን መካን ብትሆን አልተዋትምና።
#አብርሃም ለሰብዓ ዓለም (በዓለም ለሚኖሩ ክርስቲያኖች) አባት ነው።በሕገ ልቡና ሁኖ ወንጌልን ፈጽሟልና።አረ ግሩም ነው !!! የእግዚአብሔር እንግዳ ቤቴ ሳይመጣ ግብር አላገባም፤እህል አልቀምስም ማለት እንዴት ያለ ብፅዕና ነው!? ፍቅረ እግዚአብሔርና ፍቅረ ቢጽ እንዴት ቢጸኑለት ነው!?ደጉ አባታችን የእግዚአብሔር ሰው አብርሃም ወንጌልን ሲፈጽማት ተመልከቱልኝማ!!!
#"በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና"(ማቴ 5:3) ትሑቱ አብርሃም ባለጠጋ ሆኖ ሳለ ለእኔ የሚስማማ ደህነትነው፤ባለጠግነትማ የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው በማለት መንፈሱን ዝቅ አድርጎ ራሱን እንዳሳላፊ ቆጥሮ እግዚአብሔር የሰጠውን ለሌሎች ያካፍል ነበር።በዚህም መንግሥተ ሰማያት (የሰማያት መንግሥት) የሆኑ ሥላሴን አስተናግዷል።መንግሥተ ሰማያት የሚባል ጌታም ከእርሱ ዘር ተወልዷል።"የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ።"ማቴ 1:1እንዲል
#“የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፥ መፅናናትን ያገኛሉና።”
(ማቴ 5:4) ርኅሩኁ አብርሃም ለሦስት ቀናት ያህል ሰው ቤቱ ስላልመጣ እጅጉን አዝኗል።ሥላሴን በማግኘት ተጽናንቷል።
#"ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፥ ይጠግባሉና።"(ማቴ 5:6) መፍቀሬ ሰብእ ደጉ አብርሃም ስለ ሰው ፍቅር ሦስት ቀን ሦስት ሌሊት ተርቧል።ጽድቅ የሚባል እግዚአብሔርን በድንኳኑ ተቀብሎም ጠግቧል (ነፍሱ ተደስታለች) ።
#"ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።"(ማቴ 5:10) የሃይማኖት ሰው አብርሃም እግዚአብሔር "ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ።"(ዘፍ 12:1) ሲለው በፍጹም እምነት ወጥቷል።መንግሥቱንም ወርሷል።
"አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሤት አደረገ፤አየም ደስም አለው።" ዮሐ8:56 ማለት እንግዲህ ይህ ነው።በጨለማው ዘመን ሆኖ ብርሃንን ማየት ወንጌልን መኖር!!!ቅድስት ሥላሴን በቤቱ ተቀብሎ"የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተእመለሳለሁ፤ሣራምልጅንታገኛለች።"ዘፍ18፤14 ባለው ቃል መሠረት ለጊዜው ይስሐቅን እንደሚወልድ ለፍጻሜው ክርስቶስ ከእርሱ እንደሚወለድ ኪዳንን ተቀብሏል።
#በሕገ ልቡና ሕገ ኦሪት በሕገ ኦሪት ሕገ ወንጌል በተሰጠን በእኛ ቅዱስ አብርሃም ይፈርዳል፤ከአብርሃም የሚከብር ጌታ በሥጋ አብርሃም ተወልዶ በጥምቀት ልጅነትን፣በልጅነት መንግሥተ ሰማያትን ሰጥቶን የአብርሃምን ሥራ አልሠራንምና።
የአብርሃሙ ሥላሴ በሁላችን ቤት ይደሩ!!!
ሐምሌ ሥላሴ/2016 ዓ.ም

🛑አዲስ ዝማሬ "አንቺ ነሽ " ዘማሪ ዳዊት ክብሩ ◈New Mezmur "Anchi Nesh" Z Dawit Kibru (Lyrics)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያመሰገነሽ፤
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
ወላዲተ አምላክ ድንግል አንቺ ነሽ።
የመለኮት ማደሪያ ነሽ የብርሃን ድንኳን፤
ለመላእክት እኅት መሪ የኾንሽ ለጻድቃን።
የሕዝብ ሁሉ ኸኸ እናት ኸኸ የሁሉ እመቤት፤
የዓዳም ተስፋ ስንቅ የሆንሽ የዳነብሽ ከሞት
አንቺ ነሽ /2/ ብፅዕት ኪዳነ ምሕረት፤
ለዓለም ሁሉ መዳን ምክንያት የቃል እናት ታቦት
ለዓለም ሁሉ መድኃኒት የቃልኪዳኑ ታቦት።
ወርቅ የተጎናጽፈሽ፥…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
YouTube
🔴"በኢዮር በራማ " ዘማሪ ዳዊት ክብሩ | Zemari Dawit Kibru New 'Be Eyor Berama' Orthodox Tewahdo Mezmur
በኢዮር በራማ
በኢዮር በራማ በኤረር ላይ ያለች
የምትመሰገን በክብር የገነነች
የመላእክት ግርማ የክብር አክሊላቸው
የሥላሴ ዙፋን አንቺ ነሽ ጌጣቸው
አዝ.............
በምድረ ሎዛ ያዕቆብ ያየሽ
የወርቅ መሰላል ድንግል አንቺ ነሽ
የአምላክ ማደሪያ እናቱ የሆንሽ
ምዕራገ ጸሎት ንጽሕትም ነሽ
የአሕዛብ በረከት የአብርሃም ዘር
መርገም ተሻረልን /3/ አገኘን በአንቺ ክብር
የተነገረልሽ ትንቢቱ በምድር…
በኢዮር በራማ በኤረር ላይ ያለች
የምትመሰገን በክብር የገነነች
የመላእክት ግርማ የክብር አክሊላቸው
የሥላሴ ዙፋን አንቺ ነሽ ጌጣቸው
አዝ.............
በምድረ ሎዛ ያዕቆብ ያየሽ
የወርቅ መሰላል ድንግል አንቺ ነሽ
የአምላክ ማደሪያ እናቱ የሆንሽ
ምዕራገ ጸሎት ንጽሕትም ነሽ
የአሕዛብ በረከት የአብርሃም ዘር
መርገም ተሻረልን /3/ አገኘን በአንቺ ክብር
የተነገረልሽ ትንቢቱ በምድር…
Forwarded from የዘማሪ ዳዊት ክብሩ Zemari Dawit Kibru Official Telegram Channel (Dawit Kibru)
እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እንደ ልጇ ተነሥታ ዐርጋለች።"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት"(መዝ 131:8) በማለት ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት የጌታችንና የእናቱን የእመቤታችንን ትንሣኤ አስተባብሮ ተናግሯል።"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ" ብሎ የጌታን "አንተና የመቅደስህ ታቦት" በማለት ጌታችን ብቻ ሳይሆን እናቱም እንደምትነሣ በእውነት ተነበየ።
#ኋላ ጻድቃን የሚቆሙትን የቀኝ ቁመት እመቤታችን ዛሬ ቆማዋለች።"በወርቅ ልብስ ተሸፋፍና ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" እንዳለ አባቷ ቅዱስ ዳዊት።
#ልጇ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ኋላ ለጻድቃን የሚያወርሳቸውን "ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን" (1ኛ ቆሮ 2:9) ዛሬ ለእናቱ አውርሷታል።
ለነገሩ ራሷ መንግሥተ ሰማያት ናት።ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ንጉሠ ሰማያት ወምድር ማኅፀኗን መናገሻ አድርጎ ነግሦባታልና።
#ልጇ "ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ።"(ዮሐ14:3) እንዳለ እርሷም እርሷ ባለችበት እንሆን ዘንድ ከልጇ ታማልደናለች።ማርያም ማለት መርኅ ለመንግሥተ ሰማያት (በቃልኪዳኗ በአማላጅነቷ ረድታ መንግሥተ ሰማያት የምታገባ) ማለት ነውና።
#ጌታ መጋቢት 27 በመስቀል ላይ ሞቶ መጋቢት 29 በሦስተኛው ቀን እንደተነሣ እመቤታችንም በጥር 21 ዐርፋ ገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ቆይታ በነሐሴ 14 ቀን በጌቴሴማኒ ተቀብራ በነሐሴ 16 ቀን በክብር፣በይባቤ መላእክት ተነሥታ ዐርጋለች።
#አይ የሞተ አይነሣም ለምትሉ አባታችን ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን በመንፈስ እንጠራዋለን "ነገር ግን ሰው፤ሙታን እንዴት ይነሣሉ? በምንስ ዓይነት አካል ይመጣሉ? የሚል ይኖር ይሆናል።አንተ ሞኝ፥ አንተ የምትዘራው ካልሞተ ሕያው አይሆንም።"(1ኛ ቆሮ 15:35) ብሎ ይዘልፍናል።
#ተነሥቶ ወደ ሰማይ አይወጣም የሚል ቢኖር ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስን በሃይማኖት እንጠራዋለን፤እንዴትም ወደ ሰማይ እንደወጣ እንጠይቀዋለን።"ሲሄዱም እያዘገሙም ሲጫወቱ፤ እነሆ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በመካከላቸው ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ወጣ።”(2ኛ ነገ 2:11)
ሞቶ ተነሥቶ ያረገ የለም የሚል ማንም ቢኖር ዳግመኛ ቅዱስ ጳውሎስ
"ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፤ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።"(1ኛ ተሰ 4:16-17) ሲል ይነግርልናል።
#አስተውሉ ያቀረብነው ማስረጃ ጻድቃንን የሚመለከት ነው።ጻድቃን እንዲህ ከከበሩ የጻድቃን እናታቸው የአምላክ እናት ቅደስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያምማ ክብሯ ምን ያህል ይሆን !!!!!!!!???
እኛስ እንደ ቅዱስ ኤፍሬም "አሕዛብ ሁላችሁ ኑ ድንግል ማርያምን እናመስግናት" እንላለን!!!
ነሐሴ ኪዳነምሕረት 2016 ዓ.ም

+ የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ዘንድ ክቡር ነው! +
መዝ 115(116)፥6)
እንኳን አደረሰን!! (ለወዳጆችዎ ቃለ እግዚአብሔር ያጋሩ)
ጻድቁ ረጅሙን የዚኽ ዓለም ጉዞ በድል ያጠናቀቁበት ዋዜማ በመኾኑ ጽሑፉን አረዘምኩ። ላረዘምኩባችኹ "ይቅርታ" እየጠየቅኹ "ዘለግ" ወዳለው ጽሑፍ ልዝለቅ:-
ቤተክርስቲያናችን ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ የቅዱሳን አበውና እማትን በዓለ ዕረፍት ስብሐተ እግዚአብሔርን በማቅረብ በዓሉ የሚከበርለትን ጻድቅ ገድል በማንበብና ተጋድሎውን በማሰብ ምዕመናንም የጻድቃንን ጎዳና እንዲከተሉ በማስተማር ታከብራለች፡፡
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እንደተናገረውም "የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።" እያለች ትሰብካለች፡፡ (መዝ 115፥15)
ቅዱሳን ከልደታቸውም ቀን ይልቅ ወደ ፈጣሪያቸው የሄዱበት የዕረፍታቸው ቀን እጅግ የከበረና ገናና ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ይህን በተመለከተ ሲናገር "ከመወለድ ቀን የሞት ቀን ይሻላል።" ይላል። (መክ 7፥2) ጠቢቡ በግልጽ እንደተናገረ ቅዱሳን ሰዎች ከተወለዱበት ቀን የሞቱበት ቀን ይሻላል ይበልጣልም ፡፡ ለምን? ቢሉ የልደታቸው ቀን ወደ ተጋድሎ የገቡበት ቀን ሲሆን የሞታቸው ቀን ደግሞ ተጋድሎን የፈጸሙበትና የድል አክሊልን ለመቀበል የሚዘጋጁበት ቀን በመሆኑ ነው፡፡
- ይቀጥላል......
👉የዩትዩብ ቻናሌን ይቀላቀሉ 🙏🙏🙏
https://youtube.com/@zemaridawitkibru2405?si=FhlrmjjdcgwzXO_2
👉ቴሌግራም ቻናል
https://tttttt.me/zdk24_5_21_official

ከላይኛው የቀጠለ ......
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት እንደመሠከረው የደጋግ ሰዎች ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የከበረ ነው ፡፡ ክብራቸውንም በቃላት ተናግረን በብዕር (ብርዕ) ጽፈን ልንፈጽመው እንደማንችል መረዳት ይኖርብናል ፡፡ ዓለም የራሱ የሆነውን ሰዎች ዕረፍት ቀን በደመቀ ሥነ ሥርዓት ያከብራል ፡፡ እግዚአብሔርም በሕይወታቸው ሁሉ እርሱን እያመለኩ ለእርሱ እየተገዙ ፈቃዱን እየፈጸሙና የዚህ ዓለም ተጋድሏቸውም በሞተ ሥጋ የተቋጨ ወዳጆቹን ዕረፍት በማያልፍና ቃላት በማይገልጡት ክብር ያከብራል፡፡
የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው
ለምን ተባለ?
☞ የሥጋ ሞቱ ሕያው መሆኑ የሚገለጥበት በመሆኑ
በክርስትና ሃይማኖት መሠረታዊ አስተምህሮ መሠረት ሞት የሰው ልጅ የጉዞ ፍጻሜ አይደለም ፡፡ ከሞት በኋላ ዘላለማዊ ሕይወት ከመቃብር በኋላም ትንሣኤ አለና ፡፡ ሰው ከሞት በኋላ ለሚገጥመው ሕይወትና ለሚያገኘው ጸጋ ለሚወርሰው የማያልፍ ርስት የሚፈተነው በዚህ ዓለም በሚኖረው ቆይታ ነው ፡፡ ጌታችን በወንጌል "በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።" ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ "ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ ልንገባ ያስፈልገናል።" ማለቱ ይህ ዓለም ለደጋግ ሰዎች የመከራና የኋዘን ምክንያት መሆኑን ያሳየናል፡፡ (ዮሐ 16፥33፣ የሐዋ 14 ፥22)
ቅዱስ ጴጥሮስም የእምነታችንን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችንን መዳን (መንግሥተ ሰማያትን መውረስ) የምናገኘው በዚህ ዓለም የሚገጥመንን ፈተና፣ መከራና ኃዘን በድል ከተወጣን በኋላ መሆኑን ደጋግሞ መስክሯል። (1ጴጥ 4፥14 2ጴጥ 1፥5-9)
ይህ ዓለም የተጋድሎ ዓለም መሆኑን የተረዳ ሰው ደጋግ ሰዎች ነፍሳቸው ከሥጋቸው የሚለይበት በሥጋ ሞት ከዚህ ዓለም የሚወሰዱበት ቀን ሕያዋን መሆናችው የሚታወቅበት ቀን መሆኑን ለመረዳት አይቸገርም ፡፡ በዚህ ዓለም ስንኖር የነፍስ ከእግዚአብሔር ለመለየት መንሥኤ በሆነ ኃጢአት የመያዛችን ዕድል ሰፊ ነው ፡፡ ስለሆነም በአምልኮተ እግዚአብሔር ጸንቶ በምግባር ቀንቶ ለኖረ ሰው ዕለተ ሞቱ ወደ ኃጢአት ከሚያንደረድሩ ክፉ ምኞቶች ጋር የሚያደርገው ትግል የሚያበቃበትና ጽድቅ በተባለች የእግዚአብሔር መንግሥት በሕይወት ለዘላለም እንደሚኖር የሚታወቅበት ቀን ነው፡፡ ጌታችን በወንጌል "ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳን ሕያው ነው።" ብሎ መናገሩ ይህን የሚያጸናልን ነው፡፡ (ዮሐ 11፥25) "ቢሞት እንኳን" ሲል በሥጋ ሞት ቢወሰድ እንኳ ማለቱ ግልጽ ነውና፡፡
ጌታችን በዚህ ስፍራ ብቻ ሳይሆን ደጋግሞ እርሱን አምነውና ትእዛዛቱን በመፈጸም አስደስተውት በበጎ ምግባርም ተሸልመው በሥጋ ሞት ያለፉ እንደነ አብርሃም ያሉ ደጋጎች ዳግም ሞትን እንደማያዩና ሕያዋን እንደሆኑ መስክሯል ፡፡ "እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አያይም" እንዲል። (ዮሐ 8፥51)
☞ የዚህ ዓለም ተጋድሎው የሚያበቃበት በመሆኑ
ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚመሠክሩት እውነተኛ ክርስቲያኖች በዚህ ዓለም ከሰይጣን ክፉ ከሆነ የዓለም ምኞት ከሥጋ ፈቃድና እና ከክፉ ሀሳቦች ጋር የማያቋርጥ ተጋድሎ አለባቸው፡፡ ሐዋርያው "መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ነገር ግን በዚህ ዓለም ካሉ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።" ብሎ እንደተናገረ፡፡ (ኤፌ 6፥12-16) ተጋድሎ አንዱ እውነተኛ የክርስትና ሕይወት መገለጫ ነው ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዝሙሩ ለጢሞቴዎስ "መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል።" በማለት የመከረውም ምክር ይህንኑ ያስገነዝበናል ፡፡ (1ጢሞ 6፥12) ክርስቲያኖች በዚህ ዓለም ከርኩሳን መናፍስትና ከሠለጠኑባቸው ሰዎች ጋር ስለ ክርስቶስ የሚያደርጉት ተጋድሎ የክብር አክሊል የሚያገኙበት ጉዞ ነው ፡፡ በተጋድሎ ጸንቶ መኖር እንደሚገባ ሐዋርያው ሲያስተምር "ወዳጆች ሆይ ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።" ይላል (ይሁዳ 1፥3) የክርስትና ሃይማኖት የተጋድሎ ሕይወት የሞላበት መንገድ ነው የሚባለውም ለዚሁ ነው ፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወትን ያለ ተጋድሎ ማሰብ ጉዞውን ሳይጀምሩ ከመንገድ መቅረትን በመሐል መደነቃቀፍንና ፈጣሪያችን ልዑል እግዚአብሔርን ወደ ማማረር ያደርሳል። (ያዕ 5፥9) ሐዋርያት በመልእክቶቻቸው "ይሁን እንጂ መጥቼ ባያችሁ ወይም ብርቅ በአንድ ልብ ስለወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ በአ ንድ መንፈስ እንድትቆሙ ስለ ኑሯችሁ እሰማ ዘንድ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ ...በእኔ ያያችሁት አሁንም በእኔ እንዳለ የምትሰሙት ያው መጋደል ደርሶባችኋልና። " በማለት ያስተማሩን ትምህርት የክርስትናን መንገድ የሚከተል ሰው መከራ መንገዱ፤ መስቀል ምርኩዙ፤ እግዚአብሔር መሪው፤ ወንጌል መመሪያው፤ መንግሥተ ሰማያት ዓላማው መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ (ፊልጵ 1፥27-30)
ቅዱሳን አባቶቻችንና እናቶቻችን የዕረፍታቸው ቀን በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው "ከተወለዱበትም ቀን የሚሞቱበት ቀን ይሻላል" የተባለውም ከሥጋ ሞታቸውም በኋላ ዳግመኛ ወደማያለቅሱበት፣ ወደማይራቡበት፣ ወደማይጠሙበት፣ ዕንባቸውም ሁሉ ወደሚታበስበት ዓለም ስለሚጓዙ ነው፡፡ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራእዩ የተመለከታቸው አንድስ እንኳ ሊቆጥራቸው አይችልም የተባለላቸው ነጫጭ ልብስ ለብሰው የተገለጡት እነዚያ ቅዱሳን እነማን እንደሆኑ "እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው ልብሳቸውንም አጥበው (ንስሐ ገብተው) በበጉ ደም አነጹ (በሥጋ ወደሙ ታተሙ) ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል ከእንግዲህ ወዲህ አይራቡም አይጠሙም ፀሐይም ትኩሳትም ሁሉ ከቶ አይወርድባቸውም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና ወደ ሕይወትም ውኃ ምንጭ ይመራቸዋልና እግዚአብሔር ዕንባዎችን ሁሉ ከዓይናቸው ያብሳል።" ተብሎ ተነግሮታል። (ራዕይ 7፥14-17)
☞ የድል አክሊል የሚቀዳጁበት ቀን በመሆኑ
ጌታችን "እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለው ።" ብሎ የተናገረው ቃል የሕይወት አክሊል የተባለች መንግሥተ ሰማያት የምትሰጠው ከሥጋ ሞት በኋላ መሆኑን ይመሠክርልናል፡፡ (ራእይ 2፥9)
"የጻድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው " መባሉም የጻድቅ ሰው ዕለተ ሞት የክብር አክሊል የመቀዳጀቱ ማብሠሪያ ቀን በመሆኑ ነው ፡፡ ጌታችንም "እስከ መጨረሻው (እስከ ዕለተ ሞቱ) የሚጸና እርሱ ይድናል (መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳል)።" ማለቱ ይህን ያጠነክርልናል፡፡ (ማቴ 24፥12)
ቅዱሳን የዚህን ዓለም ተጋድሎ ፈጽመው ፈተናውን አሸንፈው መከራውን አልፈው በሞተ ሥጋ ሲወሰዱ በፍጡር ሚዛን የማይለካ በፍጡር አንደበት ተዘርዝሮ የማያልቅ ከፍጡር ሕሊና በላይ የሆነ ክብርን ይቀዳጃሉ ፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን "ጻድቃን ድል ባደረጉ ጊዜ ብዙ ክብር አለ።" ብሎ እንደተናገረ፡፡ (ምሳ 28፥12) ጠቢቡ ቅዱሳን ከሥጋ ሞታቸው በኋላ የሚጠብቃቸውን የክብር መጠን በቁጥር ሳይገድብ "ብዙ ክብር" ማለቱን ልብ ማለት ይገባል፡፡

"ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር"
"የጻድቅ ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።"
መዝ 115:6
- የዛሬው በዓል ደግሞ ልዩ ነው።የጻድቁ አባት የዓለም ብርሃን የኢትዮጵያ ፀሐይ የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት ነውና!!!
- ለጻድቁ ክብርም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ክብርት ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ቅዱስ ሚካኤልንና ቅዱስ ገብርኤልን፣15ቱ ነቢያትን፣12ቱ ሐዋርያትን ብዙዎች የሰማይ ሠራዊትን ይዞ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደሚገኙበት የደብረ አስቦ ዋሻ ወርዶ ብዙ ቃልኪዳንን ሰጥቷቸዋል።
- የጻድቁስ ሐሳብ በሰማዕትነት አደባባይ ለክርስቶስ ፍቅር ደማቸውን አፍስሰው፣ሥጋቸው ተቆራርጦ፣አጥንታቸው ተከስክሶ ለማረፍ ነበር።በጣም የሚገርመው ይህንን ሐሳባቸውን ለጌታ የነገሩት የቀራቸው ምንም ዓይነት ተጋድሎ ሳይኖር ነበር።ነገር ግን ጌታ ጻድቁ ለእርሱ ያላቸውን ጽኑ ፍቅር ያውቃልና ምንም የቀራቸው እንደሌለና በከፍተኛ የሆድ ሕመም እንደሚያርፉ፤ይህንንም እንደ ስቅለቱና እንደ ሰማዕታት ደም እንደሚቆጥርላቸው ነግሯቸው በዚያ በክብር ዐርፈዋል።
- ዋሻዪቱን ሊነገርና ሊሰማ የማይችል ብርሃንና በዚህ ዓለም የሌለ የልዩ ልዩ የሽቱና የዕጣን መዓዛ ሞልቶባት፤ምድሪቱም እየተንቀጠቀጠች፤የሰማይ ሠራዊት ቅዱስ ዳዊት"ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።"ሲል እንደተናገረ (መዝ 41፥4) በክቡር ዳዊት ምስጋና“እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤ ሐሤትን እናድርግ፥ በእርስዋም ደስ ይበለን።”በማለት እያመሰኑ የጻድቁ ነፍስ ከሥጋቸው ተለየች።(መዝ 117፥24)
- ጌታችን የጻድቁን ነፍስ በክብር ተቀብሎ አቅፎ ሳማት።"የጸራሽ ንጽሕት ነፍስ ሆይ" ሲልም አመሰገናት።አባታችንን በሕይወተ ሥጋ ሳለ እንደነገራቸው በ15ቱ የገነትና በ5ቱ የመንግሥተ ሰማያት አህጉር ላይ ሾመው።አስቀድሞ በቅዱስ ወንጌል
“በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር፤ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤” ያለ አምላክ ለጻድቁ የመንፈስ ልጆች ይሆኑ ዘንድ በእነዚህ ሁሉ ላይ ሾመው።(ዮሐ 14፥2)
- በጻድቁ ስም ለተራበ ያበላ፤ለተጠማ ያጠጣ፤የየታረዘውን ያለበሰ፤ገድላቸውን የጻፈ ያጻፈ የሰማ፤ለቤተ ክርስቲያናቸው ዕጣን፣ዘቢብ፣ወይን፣ ሜሮን፣ንጹሕ ስንዴ ልዩ ልዩ መባዕ ያገባ፤ለበዓላቸው ለሚዘጋጀው ዝክር ውኃ በመቅዳት፣እንጨት በመፍለጥ፣ቅጠል በመቁረጥ የተራዳ፤በዓላቸውን ደስ ብሎት ያከበረ፤ከእነዚህ ሁሉ ባይቻለው በበዓላቸው ቀን የታመመ የጠየቀ ወይም ያዘነውን ያጽናና፤ በበዓላቸው ቀን ከ ቅዱስ ሥጋው ከክቡር ደሙ የተቀበለውን፤ይህንንም ባይችል ለበዓላቸው ከተዘጋጀው ዝክር የቀምሰ፤ከእነዚህ ሁሉ የተቻለውን አንዱን ቢፈጽም እንደሚምርላቸው ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።
- ለቅዱሳኑ የሚሰጠውን ቃልኪዳን በተመለከተ ራሱ ጌታችን እንዲህ ሲል ተናግሯል"እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ዋጋው አይጠፋበትም።"(ማቴ 10:40-42)
- የእግዚአብሔር የምሕረቱ ብዛት እንዴት ብዙና ጥልቅ ነው።ጻድቁን የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ስሙ ይክበር ይመስገን!!!
ጻድቁም በጸሎታቸው በበረከታቸው ይጎብኙን፤በፍጹም ሰማያዊ መስቀላቸውም ይባርኩን፤በፍጹም ሰማያዊ ሥልጣነ ክህነታቸውም ከኃጢአት ማሠሪያ የተፈታን ንጹሐን ለመንግሥተ ሰማያትም የተዘጋጀን ድልዋን ያድርጉን!!! አሜን!!!
#ኢዮብ ክንፈ
ነሐሴ ተክለሃይማኖት/2016 ዓ.ም