ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ቃል ኪዳን ማለት #ውል #ስምምነት #መዕላ ማለት ነው

ሰው የሚምለው የሚዋዋለው ስምምነት የሚፈጥረው ከመረጠው ከወዳጁ ጋር ነው እንጂ ከወጪ ወራጁ #ከመንገደኛው #ሁሉ ጋር አይደለም::ልክ እንዲሁ #እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳን የሚገባው #ለመረጣቸው ሰዎች ብቻ ነው::
"#ከመረጥሁት ጋር #ቃል ኪዳኔን #አደረግሁ፥ " ብሎ እደተናገረ #መዝ 88÷3

ስለዚህ ቃል ኪዳን የተገባው ለሁሉ አይደለም ጸድቃን ቅዱሳን ቢመረጡ ከእራሳቸው ይልቅ ክርስቶስን ሰብከው ነው ::እንደ ዘመናችን አጥማቂ ነኝ ባዮች በክርስቶስ ዓውደ ምህረት ላይ ቆመው እራሳቸውን የሚሰብኩ መቁጠሪያና ሲዲ ቸብችበው አይደለም::
አጋንንት ያለ ጾምና ጸሎት በመቁጠሪያ እና በስልክ አይወጣም ዛሬ ዛሬ በስልክ አጋንንትን እናስለቅቃለን የሚሉ አሉ:: አጋንንትም ያወጣ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም
"፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17: 21)

"የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ #ጥቂቶች " "፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።" (የማቴዎስ ወንጌል 22: 14) እንደተባለ የተመረጡት ቃል ኪዳን ያላቸው ከንቱ ውዳሴን የሚጠየፉት ጽላት የተቀረጸላቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸላቸው ገድልና ተአምር የተጻፈላቸው የጥንቶቹ እነ አቡነ #ተክለ ሃይማኖት ናቸው

የክርስቶስ ማለያ ለብሰው ለዲያቢሎስ #የሚጫወቱ አሳዊያን(አሰተኞች )በዝተዋልና በእጁጉ እንጠንቀቅ መልክታችን ነው:: "፤ ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24: 5)

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ..... #ይቆየን 🙏
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ባለፈው ዓመት በምን እንጠይቅልዎ አምድ ከተጠየቁ እና በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሰ ብለሽ ጻፊበት። የሀሳብ እና የፊደል ምናምን መፋለስ ካለው አስተካክዪው። አውደ ምህረት ላይ ሚፖሰት ነው።

#ጥያቄ

ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ እህት ወንድሞቸ ፍጹም በወደደና ናሰባሰበን በልዑል እግዚአብሔር ሰላም እንዴት አደራችሁ
በእውነት ለሁላችሁም ጸጋውን ያብዛላችሁ ሰማያዊ ዋጋን ይክፈልልን እኛም የሰማነውን 30 60 100 ያማረ ፍሬ አፍርተን ቃሉን እንድንማር እግዚአብሔር ይርዳን ጥያቄ ነበረኝ ጸጋው የበዛላችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች አብራሩልኝ።
ቃልኪዳን ማለት ምን ማለት ነው⁉️ ለምሳሌ ለጻድቃንና ለሰማዕታት የኢየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው ቃል ኪዳን አለ ለምሳሌ እነ ቅድስት አርሴማ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ለነዚህና ለመሳሰሉት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል። ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን ምንድነው
ለመምህር ግርማና ላባ ዮሐንስ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ሰቷቸው ነው ወይስ እግዚአብሔር ጸጋውን አድሏቸው ነው⁉️ ብዙ ሰወች እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለሰጣቸው ነው ይሉናል ለነዚህ አይነት ሰወች ምን መልስ መስጠት እዳለብን ብታብራሩልን?

#መልስ

ቃል ኪዳን ማለት #ውል #ስምምነት #መዕላ ማለት ነው።

ሰው የሚምለው የሚዋዋለው ስምምነት የሚፈጥረው ከመረጠው ከወዳጁ ጋር ነው እንጂ ከወጪ ወራጁ #ከመንገደኛው #ሁሉ ጋር አይደለም::ልክ እንዲሁ #እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳን የሚገባው #ለመረጣቸው ሰዎች ብቻ ነው::
"#ከመረጥሁት ጋር #ቃል ኪዳኔን #አደረግሁ፥ " ብሎ እደተናገረ #መዝ 88÷3

ስለዚህ ቃል ኪዳን የተገባው ለሁሉ አይደለም ጸድቃን ቅዱሳን ቢመረጡ ከእራሳቸው ይልቅ ክርስቶስን ሰብከው ነው ::እንደ ዘመናችን አጥማቂ ነኝ ባዮች በክርስቶስ ዓውደ ምህረት ላይ ቆመው እራሳቸውን የሚሰብኩ መቁጠሪያና ሲዲ ቸብችበው አይደለም::
አጋንንት ያለ ጾምና ጸሎት በመቁጠሪያ እና በስልክ አይወጣም ዛሬ ዛሬ በስልክ አጋንንትን እናስለቅቃለን የሚሉ አሉ:: አጋንንትም ያወጣ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም
"፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17: 21)

"የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ #ጥቂቶች " "፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።" (የማቴዎስ ወንጌል 22: 14) እንደተባለ የተመረጡት ቃል ኪዳን ያላቸው ከንቱ ውዳሴን የሚጠየፉት ጽላት የተቀረጸላቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸላቸው ገድልና ተአምር የተጻፈላቸው የጥንቶቹ እነ አቡነ #ተክለ ሃይማኖት ናቸው

የክርስቶስ ማለያ ለብሰው ለዲያቢሎስ #የሚጫወቱ አሳዊያን(አሰተኞች )በዝተዋልና በእጁጉ እንጠንቀቅ መልክታችን ነው:: "፤ ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24: 5)

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ..... #ይቆየን 🙏

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ከዚህ ቀደም በምን እንጠይቅልዎ አምዳችን ከተጠየቁ ጥያቄዎች በወንድማችን #ተርቢኖስ_ሰብስቤ የተመለሱትን መልሶች ይዘን ቀርበናል።

#ጥያቄ
መምህር አንድ ጥያቄ ነበረኝ
መኖክሳት የሚለብሱት ብጫ ልብስ የምን ምሳሌ ነው
ወይም ብጫ ልብስ ለምን ይለብሳሉ?

#መልስ
በቅድሚያ ስለ ጥያቄዎት #እናመሰግናለን🙏

መነኮሳት ቢጫ ልብስ የሚለብሱበት ምክንያት ቢጫ ብርሃናዊ ነው አንተም እንደተናገርከው ብርሃናዊ አምላክ ነክ ሲሉ ነው "፤ ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 8: 12)

#አንድም ጻድቃን በአባታቸው መንግስት እንደ ፀሐይ ያበራሉ ተብሎ እንደተጻፈው በአባታችን ቤት እንደ ፀሐይ እናበራለን ሲሉ ቢጫ ልብስን ይለብሳሉ "፤ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 13: 43)

በሌላ መልኩ ቢጫ የብሩህነት የተስፋ ምልክት እንደሆነ ብሩህ የሆነች መንግስትህት ታወርሰን ዘንድ ተስፋ አለን ሲሉ ይለብሱታል

"፤ በጸሎታችን ጊዜ ስለ እናንተ ስናሳስብ፥ የእምነታችሁን ስራ የፍቅራችሁንም ድካም በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን #የተስፋችሁን መጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እያሰብን፥ እግዚአብሔርን ሁል ጊዜ በሁላችሁ ምክንያት እናመሰግናለን፤"
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 1: 2-3)

#ጥያቄ
ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ እህት ወንድሞቸ ፍጹም በወደደና ናሰባሰበን በልዑል እግዚአብሔር ሰላም እንዴት አደራችሁ
በእውነት ለሁላችሁም ጸጋውን ያብዛላችሁ ሰማያዊ ዋጋን ይክፈልልን እኛም የሰማነውን 30 60 100 ያማረ ፍሬ አፍርተን ቃሉን እንድንማር እግዚአብሔር ይርዳን። ጥያቄ ነበረኝ ጸጋው የበዛላችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች አብራሩልኝ
1.ቃልኪዳን ማለት ምን ማለት ነው⁉️ ለምሳሌ ለጻድቃንና ለሰማዕታት የኢየሱስ ክርስቶስ የሰጣቸው ቃል ኪዳን አለ ለምሳሌ እነ ቅድስት አርሴማ ተክለ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ለነዚህና ለመሳሰሉት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል። ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን ምንድነው
ለመምህር ግርማና ላባ ዮሐንስ እግዚአብሔር ቃልኪዳን ሰቷቸው ነው ወይስ እግዚአብሔር ጸጋውን አድሏቸው ነው⁉️ ብዙ ሰወች እግዚአብሔር ቃል ኪዳን ስለሰጣቸው ነው ይሉናል ለነዚህ አይነት ሰወች ምን መልስ መስጠት እዳለብን ብታብራሩልን?

#መልስ
ቃል ኪዳን ማለት #ውል #ስምምነት #መዕላ ማለት ነው

ሰው የሚምለው የሚዋዋለው ስምምነት የሚፈጥረው ከመረጠው ከወዳጁ ጋር ነው እንጂ ከወጪ ወራጁ #ከመንገደኛው #ሁሉ ጋር አይደለም::ልክ እንዲሁ #እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳን የሚገባው #ለመረጣቸው ሰዎች ብቻ ነው::
"#ከመረጥሁት ጋር #ቃል ኪዳኔን #አደረግሁ፥ " ብሎ እደተናገረ #መዝ 88÷3

ስለዚህ ቃል ኪዳን የተገባው ለሁሉ አይደለም ጸድቃን ቅዱሳን ቢመረጡ ከእራሳቸው ይልቅ ክርስቶስን ሰብከው ነው ::እንደ ዘመናችን አጥማቂ ነኝ ባዮች በክርስቶስ ዓውደ ምህረት ላይ ቆመው እራሳቸውን የሚሰብኩ መቁጠሪያና ሲዲ ቸብችበው አይደለም::
አጋንንት ያለ ጾምና ጸሎት በመቁጠሪያ እና በስልክ አይወጣም ዛሬ ዛሬ በስልክ አጋንንትን እናስለቅቃለን የሚሉ አሉ:: አጋንንትም ያወጣ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም
"፤ ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
(የማቴዎስ ወንጌል 17: 21)

"የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ #ጥቂቶች " "፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።" (የማቴዎስ ወንጌል 22: 14) እንደተባለ የተመረጡት ቃል ኪዳን ያላቸው ከንቱ ውዳሴን የሚጠየፉት ጽላት የተቀረጸላቸው ቤተ ክርስቲያን የታነጸላቸው ገድልና ተአምር የተጻፈላቸው የጥንቶቹ እነ አቡነ #ተክለ ሃይማኖት ናቸው

የክርስቶስ ማለያ ለብሰው ለዲያቢሎስ #የሚጫወቱ አሳዊያን(አሰተኞች )በዝተዋልና በእጁጉ እንጠንቀቅ መልክታችን ነው:: "፤ ብዙዎች፦ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 24: 5)

"፤ በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 7: 22)

ለመጨመር ያህል ቅዱሳን ቃልኪዳንን የሚቀበሉት በከበረ ዕረፍታቸው ነው።

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ..... #ይቆየን 🙏

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#እግዚአብሔር በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ።”
መዝ 4፥3

ብዙዎች እግዚአብሔር በጻድቃን እንደሚገለጥ ባለማወቅ የቅዱሳኑ ነገር የእግዚአብሔርን ነገር በልጦ የሸፈነው ይመስላቸዋል :: ግን ነገሩ እንዲህ አይደለም ውኃን ከጥሩ (ከጠራው) ነገርን ከሥሩ እንዲሉ የጻድቅን ትርጉም በመጀመሪያ በአጭሩ እንመልከት::
ጻድቅ የሚለው ግሥ እውነተኛ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን ለብዙ ቁጥር ስንጠቀመው ጻድቃን ብለን ማናበብ እንችላለን እውነተኞች ማለታችን ነው!::
በእውነቱ "ጻድቅ" የሚለውን መቀጽል በመጀመሪያ በተገባ የሚገባው ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው :: እግዚአብሔር አምላክ እቀደስ አይል ቅዱስ እጸድቅም አይል ነገር ጻድቅ ነው ጽድቁም እንደ ቅዱሳን የጸጋ (የስጦታ) እንደ ሰይጣንም የሐሰት ሳይሆን ማንም ያልሰጠው ማንም የማይቀማው በባህሪው ጻድቅ እውነተኛ ቅዱስም አምላክ ነው ::“እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለምና፥ እንደ #አምላካችንም_ጻድቅ የለምና፤ ከአንተ በቀር ቅዱስ የለም።” እንዲል መጽሐፍ 1ኛ ሳሙ 2፥2

ጻድቅ ወይም እውነተኛ ለመሆን በእውነት ማመን ፣ ስለ እውነት መናገር፣ ስለ እውነት ማስተማር፣ ስለ እውነት መኖር ይጠይቃል :: ታዲያ ይህ እውነት ማነው ካልን እግዚአብሔር ነው:: “እኔ መንገድና #እውነት ሕይወትም ነኝ፤ ” ዮሐ14፥6

ከእነዚህ እውነተኞቹ ጻድቃን መካከል የጽላሎሹ ኮከብ የእግዚ አርያ ዐይን ማረፊያ የፀጋ ዘአብ አብራክ የምመናን እረኛ የወንጌል አርበኛ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ግምባር ቀደም ናቸው:: ድካምን በማብዛት እንደ ነቢያት ወንጌልን በማስተማር እንደ ሐዋርያት በመገረፍ እንደ ሰማዕታት መሰለ ሥጋው አልቆ አጥንቱ እስኪቆጠር በጻም በድካም ሌት ተቀን ተጉ 22ዓመት በሁለት እግራቸው ከቆሙ በኃላ ከመቆም ብዛት አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራ ወደቀች በዚህም ለአፍታ ሳይዘናጉ ለ7ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው በትዕግሥት 29 ዓመት በጸሎት ተጋደሉ :: መጻሕፍ “እነሆ፥ በትዕግሥት የጸኑትን ብፁዓን እንላቸዋለን” ያዕ5፥11 ብሏልና " #ብፁህ " አልናቸው :: የሥራዬን ጽናት የሃይማኖቴን ደግነት ግለጥ እያሉ በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ክርስቶስን ሲሰብኩ ቆይተዋል እንዲያውም በከተታ አውራጃ በዚህ በታመኑለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲያስተምሩ ሀገሪው ሰምቶ ለዛፍ መስገድን ሊያስቆሙን ነው ከፈጣሪያችን ሊያጣሉን ነው ብለው እንደ አንበሳ ሊውጧቸው ተነሱ አባታችን ግን በልበ ሰፊነት በነገር አሳላፊነት እያለዛዘበ አስተማሯቸው ወደ ቀናች ሃይማኖትም መለሷቸው:: ይህ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ምን ያክል ድንቅ እንደሆነ የሚያመላክት ነው እንጂ የቅዱሳኑ ሕይወት የእግዚአብሔር ነገር ነገረ እግዚአብሔርን የሸፈነ አይደለም ጻድቃን ቅዱሳን “እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፥” የሚሉ ናቸውና 1ኛ ቆሮ1፥23

እንደ ልቤ የተባለውም ቅዱስ ዳዊትም “እግዚአብሔር #በቅዱሳኑ_ላይ_ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል፤ እግዚአብሔርም ይመስገን።”መዝ 67(68)፥35 ሲል የጻድቃን ሕይወት ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር የተገለጠበት ድንቅም የሚያደርግበት ለሕዝብም ኃይልን የሚያድልበት መሆኑን መስክሮልናል በዚህም ነገር እግዚአብሔር ይመሰገንበታል :: “መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።” ብሎ ያዘዛቸውም በእነርሱ መልካም ሕይወት የሰማይ አባታቸው እግዚአብሔር ስለሚገለጥበት ነው። ማቴ 5፥16

አንዳንድ አካላት ግን ይህን ባለ መገንዘብ ቤተክርስቲያን ከክርስቶስ ይልቅ ቅዱስ ጳውሎስን ከነገረ እግዚአብሔር ይልቅም ነገረ ቅዱሳንን አስበልጣ ትሰብካለች ይላሉ:: ነገሩ ከፈረሱ ጋሪውን እንደማስቀደም ያለ ነገር ነውና የትም አያደርስም :: ይህ ዓይነቱ አካሄድ የዋልዮሽ አካሄድ በመሆኑ መጨረሻው ገደል ነው:: የዚህ ትምህርት ምንጭም ክርስቶስ ብቻ በቂዬ ነው የምትለው የመናፍቁ ዓለም ጨዋታ ነች :: ለክርስቶስ የተቆረቆሩ በማስመሰል ምርጦቹ ቅዱሳኑን ለማራቅ አያስፈልጉም ለማለት የሚደረግ ዳርዳርታ ነች :: ቅዱሳን ማሰብ በስማቸው ዝክር ማዘከር ስማቸውን መጥራት ገድላቸውን መስማት ማሰማት የተገባ ደገኛ ሥርዓት ነው ሙሽራው ክርስቶስ ብቻ ሳይሆን ሚዜዎቹ ቅዱሳንንም መቀበል ይገባል::
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማቴ 10፥40-41 መቀበል ከነ ሚዜዎቹ ነው ማነው? እስቲ ከውጪ የመጣ ወዳጁን አንተ ና ወደ ቤቴ ግባ የያዝከው የሻንጣ ገንዘብ ግን ከቤቴ አይገባም ብሎ ወዳጁን ስለ ገንዘቡ አልቀበልም የሚለው? ቅዱሳን የክርስቶስ ገንዘቡ ናቸው :: ያለ እነርሱ ልንቀበለው አንችልም::

“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን #ዋኖቻችሁን_አስቡ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”ዕብ 13፥7 እንግዚህ እግዚአብሔር ያከበረውን ማን ያቀለዋል ?
“በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ” ብሎ በቤቱና በቅጥሩ የማይጠፋ የዘላለም የመታሰቢያ ስም የሰጣቸው እራሱ ባለቤቱ ነው ኢሳይ56፥5
እግዚአብሔር ለጻድቃን የሰጣቸው ወይም የሚሰጣቸው ክብር በሕይወተ ሥጋ ብቻ ሳሉ አይደለም ለሞታቸውና ለአጸደ ነፍሳቸውም ጭምር የሚሆን ከብረው የሚያከብሩበት ዘላለማዊ ሥጦታ ጭምር ነው እንጂ:: “የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።” መዝ116፥15

ጻድቁም ወደ ሰማዕታት አደባባይ ሄጄ በስምህ ሰማዕትነትን እቀበል ዘንድ አውዳለውና ያን እንዳደርግ እዘዝ አሉት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም መቀዳደምክን ጨረስክ ከሞት በቀር የቀረህ የለም ሁሉን ፈጽመሃል ሞትህንም እንደ ሰማዕታት ሙት አድርጌ እቀበለዋለው አላቸው :: ብዙ ቃል ኪዳንም ከሰጣቸው በኃላ አባታችን ነሐሴ 24 ቀን በ99 ዓመት ከ10ወር 10ቀናቸው ቅዱስት ነፍሳቸው ከቅዱስ ሥጋቸው ተለየች::
#የአባታችን የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት እረድኤት በረከታቸው ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትሁን !::አሜን!

#የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።” ዘኍልቁ 23፥10

.............#ይቆየን..........
ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ነሐሴ 24 ቀን 2012ዓም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
" #እነሆ_መንገድህ_በፊቴ_ጠማማ_ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ "
_____________________________________________
#ዘኍ ፳ ፪ ÷፴ ፪

ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው #ሊቀ_መላእኩ_ቅዱስ_ሚካኤል ነው ። የተናገረውም ለተራጋሚው በልዓም ስለተባለ ሰው ነው:: ቃሉን ጽፎ ያስቀመጠልን ሊቀ ነብያት ቅዱስ ሙሴ ነው::

#በልዓም ሃብተ መርገም ያለው የረገመው በቶሎ የሚደርስለት ሰው ነበር :: በዚህም ጸጋው ተጠቅሞ እስራኤልን ይረግም ዘንድ እጅ መንሻ ገንዘብን እንዲሰጡት ባላቅ ሰዎች ላከበት "፤ የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት። " #ዘኍ ፳ ፪÷ ፯
በልዓምም የተሰጠውን ሃብተ መርገም በገንዘብ ቀይሮ ሕዝበ #እግዚአብሔርን እስራኤልን ለመርገም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሽማግሌዎቹንም ከዋላው አስከትሎ ጉዞ ጀመረ ::ጥቂት እንደሄደ ግን አህያው አንድ ባታ ላይ ቆማ አልንቀሳቀስም አለችሁ:: #የእግዚአብሔር_መላእክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከፊቷ ቆሞ አይታዋለችና:: በልዓም ግን አህያይቱን አብዝቶ ደበደባት አህያይቱም ወደፊት ላለመሄድ ወደጉን ወደ እርሻው ተጠጋች

"፤ አህያይቱም #የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች፤ እርሱም ደግሞ መታት። " #ዘኍ ፳ ፪÷፳ ፭

#እግዚአብሔር አምላክ የሚረግሙህን እረግማለው የሚባእኩህንም እባርካለው ብሎ ቃል የገባላቸው የነ አብርሃም የነ ይስሐቅ የነ ያዕቆብ ዘር ናቸውና ሕዝበ እስራኤል እንዲረገሙ አልፈቀደም::ዘፍ 12÷3

የበላዓም ዓይኖች አሁንም አልተከፈቱም ልቦናውም ከአህያይቱ ልብ አልተሻለም አሁንም አብዝቶ ደበደባት ይህን ጊዜ በሰው አንደበት እንዲ ብላ ተናገረችው ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው። "፤ በለዓምም አህያይቱን። #ስላላገጥሽብኝ_ነው_በእጄስ_ሰይፍ_ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት።

"፤ አህያይቱም በለዓምን። ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም ። እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት። እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
#የእግዚአብሔርም_መልአክ። አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ አህያህ አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ ባትል ኖሮ በገደልኩ ነበር አለው ደግሞም በለዓምን ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ መልአኩ እየነገረው እስራኤልን ሊረግም ሄዶ መርቆ ተመለሰ::

#የእግዚአብሔር ሥራ ይገርማል ። የበልዓም አህያ የመላእኩን ክብር በማወቋና በመገንዘቧ የበላህምን ሕይወት ታድጋለች ዛሬ የቅዱሳን መላእክትን ክብር የማያውቁ የጸጋ ስግደት የማይሰግዱ አማላጅነታቸውን የማይቀበሉ ከአህያ ያነሱ ሰዎች በዝተዋል እግዚአብሔር አምላክ እንደ በልዓም ዓይነ ልቦናቸውን ከፍቶ ክብረ መላእክትን አውቀው ቅዱሳንን መርገም ትተው አንገታቸውን ደፍተው እንዲሰግዱ ያድርጋቸው ... .....ሌላ ምን እንላለን ከጌታችን የተማርነው ይህን ነውና

"፤ #የሚረግሙአችሁንም_መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። "
(ሉቃ ፮÷ ፳ ፰ )
....#ይቆየን......
በዛሬው ዕለት ለበልዓምና ለአህያው የተገለጠበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ የሚከበርለት የሊቀ መላእኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና ምልጃው አይለየን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
መጋቢት ፲ ፪ ቀን ፳ ፻ ፲ ዓ.ም የተጻፈ
#ሰኞ
#መርገመ_በለስ እና #አንጾሖተ_ቤተ መቅደስ

‹‹ያቺ በለስ ጌታ ወደርሷ ከመምጣቱ በፊት ለምልማ ቅጠል አውጥታ ነበር››
#ቅ/ዮሐንስ_አፈወርቅ

#በማለዳ(ሲነጋ) ወደ ከተማ(ሀገር) መጣ ሲል:- ጌታችን አዳም ወደ ወደቀበት ስፍራ ወደዚያ ሀገር መጣ፤ያን ጊዜም ተራበ መራቡም እንጀራና ሕብስትን ሳይሆን ስለ ሰው ድኅነት ተራበ ራሱ በወንጌልም ሲናገር ‹‹የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ነው እናንተም በላከኝ በአባቴ ታምኑ ዘንድ ነው ››ዮሐ4፤34 ፤ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ እንደ ማለዳ ጸሐይ ነው (የቀትርም የአመሻሽም ያይደለ) የማለዳ ጸሐይ ጨለማውን ገፎ ነው የሚመጣው ክርስቶስም ጨለማ የተባለ ክፉ ከይሲ ዲያብሎስን በጽንሰቱ ድል እየነሳው ተገለጠ፤የማለዳ ጸሐይ እንደ ቀትር ፀሐይ አይፋጅም አይለበልብም ክርስቶስም ለዓለሙ ተመጥኖ የሕይወት ብርሃን ሆኖ ከመዓቱ ምሕረቱ የቀረበ ሆኖ የተገለጠ ነው፡፡ጌታችን በወንጌሉም “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ የሚከተሉኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም “ዮሐ8፤12 ሲል በቃሉትምህርት በተአምራቱ በደሙ ፈሳሽነት በብዙ ወገን ድኅነተ-ብርሃኑን ሊሰጠን በመምጣቱ ነው፡፡ ፀሐይ ለሁለቱም እኩል ታበራለች ስለርሷ ብርሃንነት ራሷም ትመሰክራለች ሆኖም ግን ጸሐይን ማየት የተሳነው ሕልውናዋን አይረዳም እንዲሁ ክርስቶስም ጸሐይ ሆኖ ለእስራኤል ቢመጣ ፀሐይነቱን ተረድተው ለሞቁት ለሰውነታቸው ኃይልን ለልብ ዓይናቸው ማየትን የሰጠ ነው፡፡
#የበለስ_ፍሬ ፡- የተባሉ ጉባኤ አይሁድ (ቤተ አይሁድ) ናቸው፤ጌታችንም የሃይማኖት ፍሬ ፈልጎባቸው ቢመጣ ከመጽሐፍተ ኦሪት ከነቢያት በቀር አላገኘም ፤የተጻፈውን በተግባር ፍሬ አልተመለከተባቸውም፡፡ ያንጊዜም ረገማት ቤተ አይሁድም ክርስቶስን ባለማመናቸው በኋላም እንደ ወንበዴ በመስቀላቸው ርግማንን አትርፈዋል፡፡ነገር ግን አይሁዳውያን ቢረገሙም እነርሱን ያልመሰሉትን ቀትቷቸዋል ማለት አይደለም፡፡ምክንያቱም ከቤተ አይሁድ እስጢፋኖስን የመሰለ ሰማዕት ተገኝቷል፤እነ ቅዱስ ጳውሎስን የመሰለ ሐዋርያም ተገኝቷል ‹‹ በስምንተኛው ቀን የተገረዝሁ ከእስራኤል ትውልድ ከብንያም ወገን ከዕብራውያን ዕብራዊ ኝ ስለ ሕግ ብትጠይቁ ፈሪሳዊ ነበርሁ›› #ፊል3፤5

#የበለስ_ፍሬ :- ጌታችን የረገማት በለስ አዳምና ሔዋንን የጣለች ዕጸ በለስ ናት፤ጌታም ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ ማለት በሰው ላይ አትሰልጥኚ ብሎ ፍዳ መርገምን እንዳጠፋት አስረዳን፡፡ በርግጥ ፍዳ መርገሙን የፈጸመው በጽንሰት ጀምሮ በስቅለት ነው፡፡ በለስ ፍሬ የተባለ በሰው ላይ ሰልጥኖ የነበረ ምልዓተ ኃጢአት ነው መጽሐፍት ኃጢአትን በለስ ይሏታል፤ምክንያቱም የበለስ ቅጠል ሰፊ ደስ የምታሰኝ ናት እንዲሁም የኃጢአት መንገድ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር ናት፤የበለስ ፍሬ በመብላትና በማላመጥ ጊዜ ጣፋጭ ናት እንዲሁ ኃጢአት ሲሠርዋት ደስ ታሰኛለች ከሠርዋት በኋላ ግን መከራ ታመጣለች በሚሠርዋት ጊዜ ጣፋጭ ከሠርዋት በኋላ ግን መራራ ናት፡፡ አዳምና ሔዋንም ለጊዜው በለሷ ጣፋጭና ውብ ሆና ታየቻቸው በውሃላ ግን መራራ ሞት አመጣችባቸው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ከአመንዝራ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና አፍዋም ከቅ የለሰለሰ ነውና ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው ሁለት አፍ እንዳው ሰይም የተሳለ ነው እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ አረማመድዋም ወደ ሲዖል ነው›› #ምሳ5፤3-5 ማርን በቀመስናት ጊጊ ለአፍና ለጉሮሮ ጣፋጭ ናት ከዚያ በውሃላ ግን የሚጎዳ መራራ ሆኖ እናገኘዋለን፤አመንዝራም ሴት አንደበተ ለስላሳ ናት ከማር ከስኳር የሚጣፍጥ ነገርን ትናገርሃለች ወዲያውኑ መራራ ሞትም ከእርሷ ያገኝሃል ሲል ነው፡፡ አርዌ ምድር እባብም(ሰይጣን ተዋሕዷት) ሔዋንን ስትናገራት አንደበቷ የጣፈጠ ነበር፤በሽንገላዋ ግን መራራ ነበረች፡፡

#የበለስ ፍሬ:- የተባለ አዳም የበለስ ፍሬ ከበላ በውሃላ ፈርቶ የተሸሸገባት የበለስ ቅጠል ናት፡፡ ‹‹የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደሆኑ አወቁ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድ አደረጉ›› ዘፍ3፤7 አዳምና ሔዋን ፈርተው የተሸሸጉበት በለስ አስቀድሞ ዕጸ በለስን የቀጠፉባስ ዛፍ ቅጠል ነው፡፡

ነገር ግን በዚህ ቅጠል ይሸፈን ዘንድ የቁርበት ልብስ አለበሳቸው ፡፡ ጌታችን ያደረቃት በለስ ይህቺ አዳምና ሔዋን ተሸሽገውባት የነበረችውን ምክንያተ ፍዳ ወመርገም የሆነችውን ነው፡፡ ሊቁ አፈወርቅ ዕደ ወርቅ ዮሐንስ ‹‹አዳም በገነት ዕርቃኑን ሆኖ ሳለ በየትኛው ቅጠል ነበር መሸፈኛ ሰፍቶ ዕርቃኑን የሸፈነ ይህች ቅጠል እንዴት እንደደረቀች አየህን አዳም የለበሳት ዕርቃኑን የሸፈነባት አይደለችምን ጌታ ኢየሱስ ወደ ለመለመችው ዛፍ መጥቶ አዳም ዕርቃን የሸፈነባትን ቅጠል በቃ አደረቃት አዳምን ድኃ ሁኖ ስለዘገኘው ንጹሕ የሆነ የብርሃንንም
ልብስ ሰጠው ይኸውም ብርሃን ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ የተሰራ ነው ፤የበለስን ቅጠል አድርቆ የነፍስን ድኅነት ሰጠው ተድላ ደስታ ባለባት ገነት ፍጹም የሆነ የተድላ ደስታ ልብስ ተጎናጽፎ እንደ መላእክት ሕያው ሁኖ ሲኖር ከይሲ ያሳተችው አዳምን እንዴት እንደዳነ አስባለሁ›› #ግብረ_ሕማማት ገጽ 163/164 ቁ.ጀ50-54
#ፍሬ_ግን_አላገኘባትም
________________
ወንጌሉ እንዳስቀመጠው ጊዜው የፍሬ ወር አልነበረም;ለምስጢሩ ግን ወዲያውኑም ደረቀች ሲል ደግሞ ለዘመናት የሰለጠነ ፍዳ መርገም ሞት ዲያብሎስ ጠፋ ተሸረ ሲል ነው፡፡ #ኛ_ቆሮ 15÷55 ‹‹ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ፤ሲዖል ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ››የሚለው ተፈጸመ፤ምክንያቱም አስቀድሞ በትንቢት ተነግሮ ነበርና ‹‹ከሲዖል እጅ እታደጋቸዋለሁ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ ሞት ሆይ ቸነፈርህ ወዴት አለ ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ ርኅራኄ ከዓይኔ ተሰወረች›› #ት.ሆሴዕ 13፤14 ክርስቶስ በሰው ላይ የሰለጠኑ ክፉ በለሶችን አድርቆ አጥፍቶልናል ይህንንም ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ‹‹መጥቶም ፍትወታት እያትን ኃጣውዕ ርኩሳንን አጠፋ ሁከቱን ጸጥ አደረገ ዕጸ በለስንም አድርቆ
ብሩህ በሆነ ሕይወት በሃይማኖት የበቀለውን ዕጸ መስቀል ተከለልን ›› #ግብረ_ሕማማት ገጽ 167 ቁ.104 በበለስ የመጣውንም ርግማን በዕጸ መስቀሉ ድል ነሳው ፤በለሷን ሲረግም በአንጻሩ በለስ ዕጸ መስቀልን ተከለልን፡፡
#ይህ_የከበረ የተዘረጋ መስቀል ሥሩ በምድር ጫፉ በሰማይ ያለ ቅጠሉ የማይረግፍ አበባው ለጥፋት ፍሬው ለሞት ያልሆነ ነው፡፡ባለ በገናው ነቢዩ ዳዊትም ‹‹ወይከውን ከመዕጽ እንተ ትክልት ኅበ ሙሐዘ ማይ እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ ወቁጽላኒ ኢይትነገፍ -በውኃ ዳር የተተከለ በየጊዜው ፍሬውን የሚሰጥ ቅጠሉም የማይረግፍ ›› #መዝ1÷3 ክርስቶስ በዕጸ መስቀሉ ክፉ በለስ የተባሉ ዲያብሎስና ሠራዊቱን የቀጣበት ፤ዛሬም ለሚያምኑበት ወደ ሰማይ የሚያወጣ መሰላል ነው፡፡ይቺ ዕለትም መርገመ በለስ ተብላለች

#ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደ፤ ቤተ መቅደስ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምሥያጥ /የንግድ ቤት/ ሆኖ ቢያገኘው፤ «ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች… እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት» ማቴ. 21፤13 ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸዉ፣ ገርፎም አስወጣቸዉ፣ ይህም የሚያሳየዉ ማደሪያው ቤቱ የነበርን እኛ የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታ ችንን ሁሉ እንዳራቀልን
............ #ይቆየን ..........
ግብሐት :- ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት ቤት ሰሌዳ መጽሔት
#አንዳንድ ልጆች ከወላጆቻቸው የሚበልጡበት ጊዜ አለ አንዳንድ ወላጆች ደግሞ በነገሮች ዕይታ ከልጆቻቸው የሚያንሱበትም ጊዜ አለ ። እናታችን ቅድስት ኢየሉጣ ይህን በመገንዘቧ ነበር ልጇን ሕፃኑ ቂርቆስን ስለ መልካም ምክሩ ልጇ ሆኖ ሳለ አባቴ ብላ ለመጥራት የተገደደችሁ ።
በእርግጥም የሥጋ ሞት እጅግ መራራና አስፈሪ ነው ። መድኅን ዓለም ክርስቶስ እንኳን ወዶ ፣ፈቅዶ የሞታችንን ጽዋ ሊጠጣልን ለካሳ፣ ለቤዛ መጥቶ ሳለ ጊዜው ደርሶ በአሙስ ምሽት የአይሁድ ወታደሮች ሊይዙት ሲመጡ ግን በአትክልት ቦታ በጌቴ ሰማኔ ሆኖ "አባት ሆይ ብትወድስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ " ሲል ጸሎትን አድርጓል። #ማቴ 26÷39
#ይህም የሚያሳየን በመከራችን ጊዜ ወደ ሰማይ አባታችን መጸለይ እንደሚገባን ብቻ ሳይሆን የሥጋ ሞት ምነኛ አሰቃቂ ና አስፈሪ እንደሆነ ጭምር የሚያሳይ ነው ። ስለሆነም የቅድስት እየሉጣ ፍርሃት አያስደንቅም የሚያስደንቀውስ የልጇ እሳት መድፈር ነው ። “ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።” #ሉቃስ 10፥21
በቤተክርስቲያናችን ታሪክ ገና በአፍላ ዕድሜያቸው በበሳልነታቸውና በአስተሳሰብ አድማሳቸው የተነሳ አረጋዊ ወይም ሽማግሌ ተብለው የተጠሩ ቅዱሳን አሉ ለምሳሌ ወደ ሀገራችን ከመጡ ከዘጠኑ ቅዱሳን መካከል ሮማዊው ኮከብ ዘሚካኤል(አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ) ማንሳት ይቻላል:: ዘሚካኤል አረጋዊ የሚል ስያሜን ያገኙት ገና አስራ አምስት ዓመት እንኳን ሳይሞላቸው ነበር።
#ቅዱስ_ወንጌል ከአንዱ ከተማ ቢያሳድዷችሁ ወደ ሌላይቱ ከተማ ሽሹ እንዳለ ከሮም መኮንን ሸሽታ ወደ ሌላ ሀገር ልጇን ይዛ ብትሄድ ያን የሸሸችሁ ክፉ መኮንን በዚህም ሀገር አገኛት የምታመልከውን አምላክ ክዳ የእርሱን ጣዖት እድታመልክም ጠየቃት ቅድስት ኢየሉጣ ግን ከእግዚአብሔር በቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ የሚገባ ወይም የማይገባ መሆኑን ይህን የሦስት ዓመት ልጄን ጠይቀው እርሱ ይንገርህ አለችሁ
መኮንኑም ቅዱስ ቂርቆስን በተመለከተው ጊዜ ፊቱ ብሩህና ደስተኛ ሕፃን እንደሆነ አስተዋለ ቀርቦም አንተ ደስተኛ ሕፃን እንዴት ነህ ሲል የማግባባት ሰላምታን አቀረበለት ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን አዎን የኔ ደስታ ተጠብቆልኛል አንተ ግን ከዚህ እኩይ ሥራህ ካልተመለስ ልቅሶና ጥርስ ማፏጨት ጥልቅ ሐዘንም ይቆይሃል መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላና ደስታ የላቸውም ይላልና አለው።“ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ።” #ኢሳ 57፥21
#መኳንንቱንና ጣዖታቱንም ሁሉ እረገማቸው ከኃይሉም ጽናት የተነሳ ሁሉ አደነቁ እግዚአብሔር ንግግርንና ኃይልን ሰጥቶታልና "ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። ተብሎ እንደተጻፈ #ማቴ 10÷18-20
መኮንኑም የሕፃኑን ንግግር በሰማ ጊዜ አፈረ ታላቅ የውኃ ጋን አዘጋጅታችሁ ውኃው እስከሚፍለቀለቅ በእሳት ላይ ጣዱት ውኃውም ሲፈላ ሕፃኑንና እናቱን በዚያ ጨምሯቸው ብሎ አዘዘ ።
#ጭፍሮችም እንደተባሉት አደረጉ የውኃው ፍላትም ድምጹ እንደ ክረምት ጊዜ ነጎድጓድ የሚያስፈራና የሚያስገመግም ሆነ ይህ ጊዜ የሕፃኑ እናት ቅድስት ኢየሉጣ ፈራች ሃይማኖቷም ከልቧ ተሸረሸረ ልጄ ሆይ ይህ ነገር ይቅርብን ንጉሥ ያለንን እንፈጽም አለችው።
ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን ወደ ሰማይ አንጋጦ መላእክትን በጽረ አርያም ፣ ሐዋርያትን በስብከተ ዓለም ፣ ጻድቃንን በገዳም፣ ሰማዕታትን በደም ያጸናህ እናቴንም በሃይማኖት አጽናት ሲል ስለ እናቱ የእምነት መጉደል ወደ ፈጣሪው ጸለየ።
#እግዚአብሔርም የእናቱን ዐይነ ልቡና ገልጦ ለቅዱሳን ሰማዕታቱ ያዘጋጀውን የጽድቅ አክሊልን አሳያት ያን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ በመንፈስ ተጽናናች ፣ በሃይማኖት ጸናች ንጉሡንና ጣዖታቱን ናቀች ልጇ ቂርቆስንም " #ልጄ_ስትሆን_አባት_ሆንክኝ " አለችሁ ተያይዘውም በእሳት ወደ ተፍለቀለቀው የውኃ ጋን ውስጥ ገቡ
#ከእግዚአብሔር_የተላከ_የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ ገብርኤልም ከዐይን ጥቅሻ ፈጥኖ መጥቶ #በጌታችን_በመድኃኒታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ_መስቀል ያን ፍል ውኃ እንደ ክረምት ጊዜ ውርጭ አቀዘቀዘው። ሕፃኑና እናቱም ያለ ምንም ጉዳት ከጋኑ ወጡ። " #የእግዚአብሔር_መላእክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል " እንዲል #መዝ 33÷7
.......... #ይቆየን............
#የእግዚአብሔር ቸርነት የመላእኩ ጠባቂየት የቅዱሳኑ የእናትና ልጅ በረከታቸው አይለየን !

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ሐምሌ ፲ ፰/፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
#ሞት_በጥር_ነሐሴ_መቃብር

መቼም ዞሮ ዞሮ ከቤት ኖሮ ኖሮ ከመሬት የሚቀር የለም :: ሞትን ሳይቀምሱ በሥጋ የተሰወሩ ቅዱሳን ሰዎች ቢኖሩም በመጨረሻ ግን የሞትን ጽዋ መጠጣታቸው ግድ ነው ሞት ወደ ክርስቶስ መሄጃ መንገድ መሸጋገሪያ ድልድይ ነውና:: ለዚህ ነው ሐዋርያው "፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ " ያለው #ፊል ፩ ÷ ፳፫
#የዛሬን አያድርገውና ሞት እንዲ ተዋርዶ እና ዝቅ ብሎ መንገድ ተብሎ እንደ ተራ ከመጠራቱ በፊት እጅግ አስፈሪ ነበር :: ሰዎች መልካምም ይሁኑ እኩያት በሞት ተግዘው ሲዖል ወስዶ መማቀቃቸው አይቀርም ነበር "፤ ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል #ኢሳ ፷ ፬ ÷፮ እንዲል ነብዮ ::
በኋላ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወደዚህች ምድር መምጣት ሞት የቀደመ መፈራቱን አጣ በትንሳኤ ተደመሰሰ በዚህም አስቀድመው እንኳንስ በደላችን ጽድቃችን እንኳ ሳይቀር እንደ
መርገም ጨርቅ ተቆጠረብን እንዳላሉ "፤ ሞት ሆይ፥ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ፥ ድል መንሣትህ የት አለ? " እያሉ የሞትን ኃይል አቃለሉት #፩ቆሮ ፲፭÷፶፭
#ሞት በራሱ ምንም ያልሆነ የልደት ተቃራኒ ነው ነገር ግን በግብሩ ሞት ተብሎ የሚጠራው ዲያቢሎስ ነው:: ሞት የሁሉ ገዥ ሆኖ ሰልጥኟል የክብር ባለቤት መድኃን ዓለም ክርስቶስ ሳይቀር በፈቃዱ ሞትን ቀምሷል :: ይህም ከመላእክት እንኳ በጥቂቱ አነሰ ተብሎ እንዲነገርለት አድርጓል ሞት ሁሉን እንዲገዛ ያሰለጠነው እርሱ እራሱ ነው። ቢሆንም ግን ቅሉ ክብር ይግባውና ከሞት ያንሳል አያሰኘውም::

#መጻሕፍትም ይህን ግልጽ ሲያደርጉልን እንዲ ብለዋል "፤ የኃለኛው ጠላት የሚሻረው ሞት ነው ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዝቶአልና። ነገር ግን። ሁሉ
ተገዝቶአል ሲል፥ ሁሉን ካስገዛለት በቀር መሆኑ ግልጥ ነው። " #፩ቆሮ ፲፭ ÷፳፯ ሞት ለፈጣሪ ዓለማት ብቻም ሳይሆን ለእናቱ ለምክንያተ ድኅይን ለምትባል ለእመቤታችን ለማርያምም አልተመለሰም ::

#እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድር ላይ ስልሳ አራት ዓመታትን ቆይታለች ማለትም ከእናት ከአባቷ ቤት ሦስት ዓመት ከሰባት ወር፣ በቤተመቅደስ ፲፪ ዓመት፣ በቤተ ዮሴፍ ፴፬ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን እርገት በኋላ ከወንጌላዊው ዮሐንስ ጋር ፲፬ ዓመት ኖራለች፡፡ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን
አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት።

ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። እውነት ነው ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ይህ ነገረ ሞቷን &ሞትሰ ለመዋቲ
ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ፤( ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም
ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል ) ሲል አድንቋል ከዛም በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት።

#እሊህን_ከማርክልኝስ ይሁን አንድ ጊዜ
አይደለም ሰባት ጊዜ ልሙት አለችው። ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። "ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ" የማርያምስ ሞት ሠርግን ይመስላል እንዲሉ አበው የእመቤታችን እረፍት እንባ መራጨት፣ ጠጉር መንጨት፣ ደረት መድቃት እንዳለበት የሰው ሞት አልነበረም፡፡ ይልቁንም አንደ ሠርግ ቤት መላዕክት
በውዳሴ፤ በማህሌት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና ወደ ሰማይ ሸኟት እንጂ ቅዱስ ያሬድም "ተለዐለት እምድር ወበህየ ነበረት ዘምስለ ወልዳ በየማነ አብ ወመንፈስ ቅዱስ" እመቤታችን ድንግል ማርያም ከምድር ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለች፡፡
በዚያም ከልጇ ጋር በአብና በመንፈስ ቅዱስ ቀኝ ተቀመጠች በማለትም ዘምሯል፡፡ "፤የቅዱሳኑ ሞት
በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።" መዝ ፻፲፮ (፻፲፯) ÷፲፭ አስቀድመው ሐዋርያት ሥጋዋን በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ ብዙ ተግዳሮት ገጥሞቸው ነበር:: አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን? ኑ በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ።
#ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት። ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ
ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሦስተኛው ቀን ማክሰኞ “ #ከመ_ትንሣኤ_ወልዳ ” እንደ ልጇ ባለ ትንሣኤ ተነሥታለች።
ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ
አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ? አላቸው አግኝተን ቀበርናት አሉት #ሞት_በጥር_በነሐሴ_መቃብር ተው ይህ ነገርስ
አይመስለኝም አላቸው ። ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብዬ እንጅ #እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል።
#በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ፍቅሯን በልቡናችን ጣዕሟን
በአንደበታችን ያትምልን
......... #ይቆየን .........
#የእመቤታችን_አማላጅነት_የልጇም_ይቅርታና_ቸርነት_አይለየን አሜን!

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
ጥር ፳፩ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም
" #እነሆ_መንገድህ_በፊቴ_ጠማማ_ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ "
_________