ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#የገነት ወግ

ከምጽሐት በኃላ ገነት ውስጥ ነው። ቸርነቱ የበዛ መዐቱ የራቀ እግዚአብሔር አምላክ ከሦስት ወጣቶች ሦስት ነገሮች አግኝቶባቸው ገነት አስገባቸው። መቼም እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን የምታክል ቦታ በጥርኝ ውኃ የሚሸጥ ሞኝ ነጋዴን ይመስላል። #ማቴ10÷41

#ከወጣቶቹ የተገኘባቸው መልካም ነገርም እነኸህ ነበሩ። በአንዱ እምነት በአንዱ ማስተዋል በአንዱ የዋሕነት ነው። ከዚህ የተረፈ የጠለቀ መንፈሳዊ ትጋት የላቸውም በሳምንት አንድ ቀን እሁድ ግጥሚያና ትሬሊንግ ከሌለባቸው ያስቀድሳሉ ከአጽዋማት ሦስቱን መርጠው እንነገሩ ይጦማሉ በቃ ለገነት ዜግነት ያሳጫቸው ይህው ጥቂቱ ጥረታቸው እእና ብዙሁ የእግዚአብሔር ቸርነት ነው።

#ከገነት በአንዱ ዕለት ታድያ አንደኛው ወጣት እንዲ ይላል " እንተ ገነት ገነት እያልን ስንናፍቃት የነበረችሁ ይችሁ ናትን? እንዴ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ውዳሴ እረፍቱ ቆይ መቼ ነው ?
ሌላኛው ወጣት ቀበል አድርጎ ታገስ እስቲ በዚህኮ እረፍቱ ምስጋና ምስጋናው እረፍት ሆኖ ነው የሚኖረው ቢሆንም ግን ጥቂት ማረፋችን አይቀርም ሲል ለማጽናናት ሞከረ
ሦስተኛው ወጣት ግን የሱ ጭንቀት ሌላ እንደሆነ ነገራቸው እንዲህ ሲል እረፍት ብቻውን ምን ያደርጋል? በእረፍት ጊዜያችን ሻምፒዮን ስሊግና ላሊጋን የመሳሰሉት የእግር ኳስ ውድድሮችን መከታተል ካልቻልን

የመጀመሪያው ወጣት ጣልቃ ገብቶ አንተ ደሞ እሱንም ለማየትኮ ቅድሚያ የዕረፍት ጊዜ ሊኖረን ይገባል ማታ ውዳሴ ቀን ቅዳሴ ይህው ከገባን ጀምሮ ስንት ሰንበታት አለፉ በሰንበት እንኳ አናርፍም እኮ አለ ምርር ብሎ

#ለምን ካልሆነ እዚሁ ገነት ውስጥ wi fi እንዲገባ ና ለእያንዳንዳችን እስማርት ስልኮች እንዲታደሉን አናደርግም ከዛ በቃ ላሊጋ በል ሻምፒዮን ስሊግ በል በቃ ሁሉ በእጃችን ሆነ ማለት ነው በተጨማሪም ማኅበራዊ ድኅረ ገጾችን ከፍተን ምድር ካሉ ዘመዶቻችን ጋር ያለ ገደብ እንገናኝ ከናፍቆታቸውም እንገላገላለን አይመስላችሁም? ሲል ሀሳብ አቀረበ

ሁለተኛው ወጣት ድንገት ሳይታሰብ ገብቶ አይመስለንም ሲል አንቧረቀበት ጭራሽ ገነት ውስጥ ዋይ ፋይ ? ጭራሽ ገነት ውስጥ እስማርት ስልክ ? ገነትን ገነት ያሰኙት እኮ የነዚህ ነገር አለመኖር ነው አለዚያማ ከምድር በምን ተሻለ ሆሆሆሆ

#ሦስተኛው ወጣት ፈጠን ብሎ ምን ችግር አለው በምድር ሳለን ትዝ አይላችሁም ካህኑ በስማርት ስልክ ተደግፎ ተንስዑ ሲል ዲያቆኑት ቢሆን እያንዳንዱን የመቅደስ እንቅስቃሴ እየቀረጸ እዛው ማኅበራዊ ድኅረ ገጾች ላይ ሲለቅ አላያችሁም? ስለዚህ ብዙ ችግር ያለው አይመስለኝም አለ

እናንተ ሰዎች ያ በምድር ነው ሆኖም ትክክል ነው ማለት አይደለም።ምክንያቱም የምድሪቱ ቤተ ክርስቲያን የሰማያዊቱ ለዚህች ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናትና። (camera man) ቀራጭነትና ድቁና ፈሪሳዊነትና ክህነት አብረው አይሄዱም። ግማሽ መላጣ ግማሽ ጎፈሬ ብርሃንና ጽልመት እንዴት አንድ ይሆናሉ? ብንችል ለምድር ሰዎች እንጸልይላቸው እንዴት የነርሱን ስዕተት እዚህ እንደግማለን።

#አንዱ ወጣት የሆነ መላ ብልጭ ያለለት በሚመስል ሆናቴ ፍክት ብሎ ቆይ ከዚህ ሁሉ ጭንቅ ለምን ከገነት አንወጣም ?
ሌላኛው ወጣት ከዛስ ? ሲዖል ጥገኝነት እንጠይቅ?
አንተ ባክህ አቀልድ
በቃ ማለቴ ወደ ቀደመ ኑሯችን ወደ ምድር መልሱን ለምን አንላቸውም ???
ይቻላል እንዴ ? ገነትኮ ካገኙ ማጣት ከገቡ መውጣት የለም ማነው የሚያሶጣን?
ቀላልኮነው ለምን ገነት ውስጥ ያልተፈቀደ ነገር ለምን አናደርግም ከዛ በቃ በራሳቸው ጊዜ ያስወጡናል
አረ ባካችሁ ጓደኞቼ ምን ሆናችዋል? አዳምና ሔዋን በገነት ያልተፈቀደውን አድርገው ከገነት ሲባረሩ የምትገለባበጥ የኪሩቤል ሰይፍም ተመዞባቸው ነበር በኛ ደግሞ ይወድቅብን ይሆናል ማን ያውቃል ።
ማለት ገነት ሰይፍ አለ ? ታድያ ሰይፍ ካለ wifi ቢኖር ምን ችግር አለ? ቢያን አመስግነን ቀድሰን አወድሰን ስንጨርስ ትንሽ እንደበርበት ነበር እኮ ።

#ይህን ሲነጋገሩ ከቀደሙት ደጋግ አባቶች አንዱ በለወሳስ የምስጋና ውዳሴ እያቀረበ ወደ ወደ መንበረ መንግሥት ሲጓዝ አያቸው ከንግግራቸውም ያሉበት ቦታ እንዳልተመቻቸውና መውጣት እንደሚሹ ተረዳ መንገዱንም ገታ አድርጎ ወደ ወጣቶቹ ተጠግቶ ሰላምታ ሰጣቸው።
ከግርማ ሞገሱና ከንግግሩ ለዛ ተደመሙ የተነጋገሩትን አንዲቱንም ቃል ባልሰማን ብለውም ተመኙ። ያ ሰው ግን ያለ ዕውቀት እንደተናገሩ ያውቃልና እያለዛዘበ ጠየቃቸው ልጆች ምን ሆናችኋል የምረዳችሁ ነገር አለ አላቸው እነርሱ ግን ለማስቀየስ ተጠቃቀሱና አይ የለም አሉት በጋራ። መልካም ብሎ ጥሏቸው ጉዞዎን ሊቀጥል ሲል ግን አንደኛው ወጣት ግን አንተ ማነህ? ሲል የገነት ጠባቂ ጥጦስን የጠየቀውን ጥያቄ አቀረበለት አብርሃም ነህን አለው ያም ሰው ዝም አለ እሽ ሙሴ ነህን አለው ያ ሰው አለመለሰለትም በቃ ቅዱስ ጳውሎስ ነህን መሆን አለብህ አለው በጥያቄው ሳይሰለች ነኝም አይደለውምም ሳይለው እርሱ ይቆየኝ

ወጣትነት አስቸጋሪ ነው እኔም ወጣት ሳለው ብዙ ጠባያት እየተፈራረቁ አስቸግረውኝ ነበር ግን በእግዚአብሔር ቸርነት በእናቱ አማላጅነት ሁሉም አልፌያቸው እዚህ ደርሻለው ከፈለጋችሁ ከልምዴ በማካፈል ልረዳችሁ እችላለሁ አላቸው። ካልሆነ ግን በሉ በደህና ዋሉ ብሎ ፊቱን አዙሮ መንገዱን ቀጠለ በእውኑ ግን ጥሏቸው ሊሄድ ልቡ አልወደደም ነበር

#ቢያንስ ከልምዱና ከዕውቀቱ ሊያካፍለን ይችላል በገነት ብዙ ስለቆየ መግቢያ መውጫውንም ሊነግረን ይችላል ለምን ሀሳባችንን አንነግረውም ተባባሉ በለወሳስ ቀስ ብለው። ከዛም አንደኛው ፈጠን ብሎ አባት አባቴ አንዴ ቆይ ብሎ ከኋላ ከተል እያለ ተጣራ አንድ ጊዜ አባቴ ሁለት ደቂቃ ይኖሮታል እባካችሁ ለምስጋና ወደ መንበረ መንግሥት እየሄድኩ ነው ከፈለጋችሁ ግን አብራችሁኝ እየሄዳችሁ የፈለጋችሁትን ልትጠይቁኝ ትችላላችሁ አላቸው። እሺ ይሁን አብረኖት እንሄዳለን ብቻ እርሶ መፍትኤ ብቻ ይስጡን መፍትኤስ ከእግዚአብሔር ነው ግን ምን ገጠማችሁ ?

አንደኛው እጆቹን እያፍተለተለ በእግሮቹም ወደፊት አብሯቸው እየተራመደ ይህውሎት አባ እኛ የገነት ኑሮ ሰልችቶናል ወደ ቀደመ ቦታችን ወደ መሬት መመለስ እስፈልጋለን አለ ሁለቱ ሀሳቡን በመደገፍ በአውንታ ጭንቅላታቸውን አነቃነቁ ያ ባለ ግርማ ሞገስ ሰው ግን ፈገግ አለና ለአህያ ማር አይጥማት አሉ ሲል ተረተባቸው ቀጥሎም እርሷስ ሳያቀምሷት ነው አይጥማትም እያሉ የሚያሟት እናተ ቀምሳችሁ ሳለ እንዴት ሳይጥማችሁ ቀረ ለመሆኑ ገነት ምን ጎደለ?

#አንዱ ቀበል አድርጎ ሻምፒዮ ሲሊግ የለ ፤ ላሊጋ የለ ፤ facebook የለ ፤ instageram የለ ፤ ጠዋት ቅዳሴ ማታ ውዳሴ ይሰለቻልኮ አባ

አይ ልጆቼ ይህ ነው ጭንቀታችሁ ይህን እናንተ ያያችሁትን እኮ ብዙዎች ሊያዮት ወደው ሊያዮት አልቻሉም እስራኤል የሰማይ መና ሰለችን ሥጋ አማረን ቢሉ መና ("ና"ይላላ) ሆነው ቀሩ። የተመኙት ሥጋ ተሰጣቸው ከአፋቸው ከተው እንደቀመሱትም ሁሉም እረግፈው ሞቱ ቦታዋም እስከዛሬ ድረስ የምኞት መቃብር ተብላ እየተጠራች ነው። ምነው ከሕይወት ይልቅ የምኞት መቃብርን ሻታችሁ ከመና ይልቅ መና መሆንን ወደደዳችሁ?
#እናንተኮ ገነትን እንዲ የጠላችዋት አስቀድማችሁም ስላሎደዳችዋት ነው ።አስቀድማችሁ በምድር ሳላችሁ ብትወዷት ኖሮ ዛሬ ባልሰለቻችሁ ነበር።
እንዴ አባ በምድር ሳለን ገነትን የት አገኝተናት ጠላና እሷ ያለችሁ እዚህ የት ተገናንተን አባ አል አንደኛው ንግግራቸው ድፍን ቅል ሆኖበት ያ ሰው ግን አብራቹ ነበረች እንጂ። ምድራዊቷ ቤተ ክርስቲያን ዕለት ዕለተ ታስቀድሱ ነበር ? ትቆርቡ ነበር?ማኅሌቷን ሰዓታቷን ትካፈሉ ነበር?
አይ አባ አልፎ አልፎ ግጥሚያና ትሬሊንግ ከሌላን እናስቀድሳለን በየ5ዓመቱም እንቆርባለን ሰዓታትም ቢሆን እግር ካደረሰን መቆሚያ ተደግፈን ጥቂት እንቆማለን።

#እሱንኮነው የምላችሁ እናንተ የሥጋ ትሬሊንግ እንጂ የመንፈስ ትሬሊንግ አድርጋችሁ አታውቁም በምድራዊቷ ገነት በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ልምምዳችሁን በአግባቡ ስላልተለማመዳችሁ ሰማያዊቷ ገነት ሰለቸቻችሁ እናንተ ብቻ አይደላችሁም ብዙዎች በቤተመቅደሱ ሥርዓት ዝለው በሰማይ ገነት የሚበረቱ ይመስላቸዋል እንዲያ ግን አይደለም እግዚአብሔር ቸርነቱ በዝቶ ያለ ብዙ ትሩፋትና ድካም በየ ጥቂቱ ምሮ ሁሉንም ሰው ገነት ቢያስገባ እንኳን ከጥቂት ጊዜ በኋላ ብዙዎች ገነትን ይሰለቹና ካሎጣን ማለታቸው አይቀርም ምክንያቱም በምድር አልተለማመዷትምና ።

የዓለሙ ጫጫታና ውክቢያ አንዱን ቀራጭ ሌላውን ፈሪሳዊ አድርጎ እየጎተተ ያስቀረዋልና መልካም እንድትሆን በሚል ሰበብ የተሸከምከው በግ ውሻ ነው ጣለው እያሉ መልካሚቱን ቤተ ክርስቲያን ጥሎ ለሰማያዊቱ ገነት የተገባ ሆኖ እንዳይገኝም የልምዱን ጊዜ ከማያምኑ ጋር እንዲያጠፈ ይገደዳል ።በዚህ ዓይነት ታድያ ሦስት ሰዓት ቆሞ ማስቀደስ ጭንቅ የሚሆንበት እንዴት 24ሰዓት ከቅዱሳኑ ጋር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ለማለት ይቻለዋል።
#እግዚአብሔርምኮ ጸጋ የሚሰጠው በጣሩበት በለፉበት በወጡበት በወረዱበት በዋሉበት እኮ ነው "..እንበለ ድካም ወጻሕማ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር..."ያለ ድካምና ልፋት የእግዚአብሔር ጸጋ እንዲሁ አትሰጥም እዲል መጽሐፉ። ገባችሁ እንዴ ልጆቼ ሲሉ ጠየቋቸው ሦስቱም በአውንታ አገታቸውን ነቀነቁ። ስለዚህ አሁን ምን አሰባችሁ በገነት መኖር ወይስ ከገነት መውጣት? ሁሉም በአንድላይ በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው የሚል ሀሳብ መጣላቸውና ካቀረቀሩበት ቀና ሲሉ እራሳቸውን ከምስጋናው ከተማ ከውዳሴ ሀገር ከመንበረ መንግሥት አገኙና መሰልቸት በማያገኘው መንፈስ ደስ እያላቸው ለምስጋና ገቡ።
..............ይቆየን።
አ.አ አበባ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
መስከረም 1/1/2015 ዓ.ም
#በቅዱሳት መጻሕፍት አስተምህሮ " #ራስ " የክብር የበላይነትን የልዕልና መገለጫ ነው። ቤተ ክርስቲያናችንም ርዕሰ ዕሩሳን ክርስቶስ ርዕሳተ ደናግል ድንግል ማርያም ርዕሰ ነቢያት ሙሴ፣ ርዕሰ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ፣ ርዕሰ ባሕታዊያን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እያለች ታስተምራለች።
በሀገራች ታሪክም ከሥልጣን ማዕረጋት መካከል የራስነት ማዕረግ የተለመደ ነው። ራስ ተፈሪ፣ ራስ አሊ ፣ራስ መኮንን እንደሚባለው ። ዛሬ ዛሬ ግን ይህ ስም የዘፈን ናዝራዊያን የሆኑ ሰዎች ፀጉራቸውን በማስረዘም ራስ(ራስታ) ተብለው የጨለማው ዓለም ገዢ ኤሮድስን ለማስደሰት የሚዘፍኑ የዘማዊያን መጠሪያ ሆኗል።
#ሄሮድስ የወንድሙ የፊልጶስ ሚስት ሄሮድያዳን ያገባት ዘንድ ፈለገ ዮሐንስ ግን እርስዋ ለአንተ ትሆን ዘንድ አልተፈቀደም አለው። ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው። አሳስሮት በወህኒ(እስር ቤት) ዘጋበት፤ ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤ ስለዚህም የምትለምነውን ሁሉ እንዲሰጣት በመሐላ ተስፋ አደረገላት።
እርስዋም በእናትዋ ተመክራ፦ የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ በወጭት ስጠኝ አለችው። ንጉሡም አዘነ፥ ነገር ግን ስለ መሐላው ከእርሱም ጋር ተቀምጠው ስላሉት ሰዎች እንዲሰጡአት አዘዘ፤ ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ አስቆረጠው።
#ራሱንም በወጭት አምጥተው ለብላቴናይቱ ሰጡአት፥ ወደ እናትዋም ወሰደችው ። እናቷ የሄሮድያዳ የነቢዮን ራስ በወጪት ይዛ ምላሱን ወደ ውጪ አውጥታ አንቺ ነሽ የንጉሥ ሚስት ሆኜ ንግሥት እንዳልባል ያደረግሽኝ እያለች በወስፌ ትወጋው ትጠቀጥቀው ነበር የነቢዩ እራስም ክንፍ አውጥታ በራ ሄዳ ለ15 ዓመታት ዞራ ወንጌልን ሰብካለች #ማቴ 14÷3-12
አንባቢ ሆይ ዘፈንን ዕርም ብለህ ተው። ዘፋኞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት አይገቡምና #ገላ 5÷16 ደግሞ እኔ አልዘፍንም የሚዘፍኑትን እሰማለው፣ዐያለው እንጂ አልክን ? ሄሮድስን ለዘፉኝ ወለታ የነቢይ ራስን እንዲሰጥ ያደረገው ዘፈን መስማትና ማየቱ አይደለምን? ሄሮድስ ቅዱስ ዮሐንስን የመሰለ ርዕሰ ያጣው ዘፈንን በማየቱና በመስማቱ ነው። ዘፉኝ ካየህ ዘፈን ከሰማህ እራስህን ታጣዋለህ ራስ ክርስቶስን ነው ነውና እራስህን ጠብቅ ።
#ራስ የአካል ሁሉ መዲና ናት አካል ያለ ራስ ምንም ነው ወይም በድን ነው እራስ ግን ያለ አካል ሕያው ሆኖ መቆም ይቻለዋል። ለዚህም የነቢዮ ዮሐንስ ራስ ሆነኛ ምስክር ናት ከአካል ከተለየች በኋላ 15 ዓመት ዞራ አስተምራለችና። መጋቢ አዲስ የኔታ እሸቱ እንዳሉት የሰው ዋነኛ መገለጫው ራስ ነው ሰው ለመታወቂያ የሚያገለግል ፎቶግራፍ እንኳን የሚነሳው ከአንገቱ በላይ ያለውን የራሱን አካል ነው እንጂ እግሩን ወይም ደረቱን አይደለም።
ዋና ዋና ስብአዊ ተግባራት የሚፈጸሙትም እራስ ላይ ባሉ ልዮ ልዮ ባለ ድርሻ አካላት ነው። እነማ ቢሉ ዐይን ፣ጀሮ፣ አፍንጫ ፣አፍ /ምላስ። ገድለ ጊዮርጊስ ደግሞ አዳሪ በማኅደሩ ማኅደሩም በአዳሪው የመጥራት የመጻሕፍት ልማድን ተጠቅሞ ዐይን ፣ጀሮ፣ አፍንጫ ፣አፍ /ምላስ በማደሪያቸው በራስ ቅል አማካኝነት ራስ ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ ይላል። ግሩም ነው ! ዳዊት የጎልያድን ራስ ቆረጠ ሲባል ዐይን ፣ጀሮ፣ አፍንጫ ፣አፍ /ምላስ ን አልነካም ማለት አይደለም እነርሱም በራስ ያሉ ናቸውና እነርሱም ተቆረጡ ማለት ጭምር ነው።
#እንደ እባብ ልባሞች ሁኑ በማለት የእባብ ልባምነቱ የተገለጠበት ዋነኛ ምክንያትም እባባ ከአካላቱ ሁሉ እራሱን (ጭንቅላቱን) ከምት ከዱላ መጠበቁ ነው። ወገቡ ጢቆረጥ አይሞትም ጭራው ቢበጠስ እስትንፋሱ አይቋረጥም ጭንቅላቱን ከተመታ ግን ሕያውነቱ ያከትማል ስለሆነም ጥንቅላቱን ወይም የራስ ቅሉን በከፍተኛ ጥንቃቄ ከምት ይጠብቃል። እባብን ልባም ካሰኚት ጠባዮቹ አንዱ እራሱን መጠበቁ ነው ።
እራስ የተባለች ሃይማኖት ነች ሃይማኖቱ በምንፍቅና ሀሳብ የተመታ ሰውም ምንም ምግባር ትሩፋት ቢኖረው ዋጋ የለውም የሞተ ነው እራሳችሁ የሆነች ሃይማኖታችሁን ከመናፍቃን ጥርጥር ከአሕዛብ ክሕደት ጠብቋት ሲል ነው።
#ሐዋርያው ሃይማኖቴን ጠብቄያለው ማለቱ እራሴን ጠብቂያለው በክፉዎች ምክር አልሃድኩም በኃጢያተኞችም መንገድ አልቆምኩም በዋዘኞችም ወንበር አልተቀመጥኩም ማለቱ ነው። 2ኛ ጢሞ 4፥7 መዝ1÷1 “በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።” #ማቴ 7፥6

አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃ/ማርያም
መስከረም ፪ቀን ፳ ፻ ፲ ፫ ዓ.ም
የሚራሩለት #እሩሩሁ_መላእክ
______
|አሁን መላእክ ይልቁኑ የመላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ይራራል እንጂ ይራሩለታልን ያሰኛል። ግን በእርግጥም ቅዱስ ሚካኤል የሚያራራም እሩሩም የሆነ ድንቅ መላእክ ነው።
#ለዚህ አንድ ጥሩ ማሳያ በህዳር ወር ድርሳኑ የተጻፈውን አንጀት የሚበላና የሚራራ የመላእኩን ትዕይንት ማንሳት በቂ ነው።
የጭንቅና የመከራ ቦታ ከሆነችው ሲዖል ያሉ ነፍሳት በስቃይ ሲጮኹ የማያስችለው እሩሩሁ መላእክ የግራ የቀኝ ክንፉን እያፈራረቀ ወደ ሲዖል ያወርዳል ነፍሳትም እንደ ቀፎ ንብ ሰፍረው ከክንፉ ላይ ተጣብቀው ከመከራ ይወጣሉ። መላእኩም ከልዑል ዙፋን ፊት ቆሞ ስለ እነርሱ ይለምናል ልዑለ ባሕሪ እግዚአብሔርም ስለ ቅዱስ ሚካኤል ሲል ነፍሳቱን ይምራቸዋል ቅዱስ ሚካኤልም ወደ ሀገረ ሕይወት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባቸዋል።

#ዳግመኛም ወደ አብ ዙፋን መጋረጃ ገብቶ በግንባሩ ተደፍቶ ስለ ሕዋዎች ስለ ዝናባት በሰማይ ስለሚበሩ ወፎች በምድ ስለሚሽከረከሩ እንሰሳት ስለ ሰው ዘር ሁሉ ሰለ ባሕራትና ቀላያት ሳይቀር በታላቅ ተማጽኖ ይለምናል አብም ይቅር ብዬልሃለው እንከሚለው ድረስ ከወደቀበት አይነሳም! አንባቢ ሆይ ከዚህ በላይ ምን ያራራል ???

ድሆች አጥተው ቢለምኑ ያራራሉ ግን ያው ስለሌላቸው ነው ያለው ግን ሲለምን ማየት የበለጠ ያንሰፈስፋል። ሥልጣን የሌለው ባሪያ ቢሆን ያው ሥልጣን ስሌለለው ሊያደርገው የሚገባና የሚጠበቅ በመሆኑ አይደንቅም ባላ ሥልጣን ይልቁኑ የመላእክ አለቃ ሆኖ ስለ ሌሎች ተገብቶ ተንበርክኮና ተደፍቶ ማየት እንዴት አንጀት ይበላ ይሆን ???

#የምትራራልን እሩሩህ መላእክ ሆይ #እንራራልሃለን !
#የምትወደን መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ #እንወድሃለን
#የረከስን እኛን በኋላ ዘመን በምልጃህ ተማጽነህ የምታከብረን አክባሪያችን ሆይ #እናከብርሃለን !

|ቅድስት በረከቱ ትደረብን 🙏

አ.አ ኢትዮጵያ
ሐምሌ 12/2014 ዓ.ም
#ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
#ባንዲራዬ ይህ ነው !
#መስቀልን ላከብር እየወጣሁ በፍጹም ኮከብ አልይዝም
++ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግዶ በዓለም ላይ ያበራ ፀሐይ ++

#በመ/ር ዲ/ን #ቢትወደድ ወርቁ

የመልክዐ ተክለሃይማኖት ደራሲ በመልክዑ አርኬ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን "ቅዱስ አባት ሆይ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግደህ በዓለም የምታበራ ፀሐይ አንተ መዓዛህ የተወደደ ደብረ ከርቤን ነህ? ወይስ መሠወር የማይቻላት ደብረ ጽጌን ነህ? " በማለት ያመሰግናል፡፡ ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት እንዲሁም በየዘመኑ የተነሡ መምህራን ዋና ተልዕኮ ጣዖት አምልኰን በቃለ ወንጌል ማስወገድ ነው፡፡ በሰዎች ዘንድ የሚታይ የሚዳሰስ ጣዖት አለ፡፡ እንዲሁም የማይታይ የማይዳሰስ ልብም የማይባል ረቂቅ ጣዖትም አለ፡፡

በኑሯችንና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ልብ ሳንላቸው ከእግዚአብሔር አስቀድመን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ሳናውቃቸው ጣዓታት እንደሆኑብን ልናስተውል ይገባናል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን በየዘመናቸው ከሰዎች ልቡና የሚታዩትንም ሆነ የማይታዩትን ጣዖታት በቃለ እግዚአብሔር ሲያጠፉ ኑረዋል፡፡ በዚህም በነቢዩ ዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ "ጥበበኞቹ እንደሰማይ ፀዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡" (ዳን 12፡4) ተብሎ ትንቢት ተነግሮላቸዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በገድላቸው እንደተጻፈልን በዘመናቸው ጣዖታትን አጥፍተዋል፡፡ በጣዖታቱ ላይ አድረው ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃቸውን ሰዎች ሲያታልሉ የኖሩትንም እኵያን አጋንንት በወንጌል ትምህርት ሲያሳፍሩና ሲበቀሏቸው ኑረዋል፡፡ በዚህም ለብዙዎች ብርሃን ሆነዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ምን ያህል ጣዖታትን እንዳጠፉ ስንቶችን ከጣዖት አምልኰ እንዳላቀቁና አጋንንትን በወንጌል ትምህርት እንዴት እንዳወጡ ለመረዳት ገድላቸውን በእምነት ሆኖ ማንበቡ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይኽን በሕሊናችን እንያዝና በዚህ ክፍል ጻድቁ የተገለጡበትን የምስጋና ቃል እንመልከት፡፡

+++ ተክለሃይማኖት ፀሐይ +++

በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ብርሃን ፀሐይ ተብሏል፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት "እግዚአብሔር ብሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማነው?" (መዝ 26፡1) በማለት ዘምሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም፡፡" (ዮሐ 8፡12) በማለት አስተምሯል፡፡ ጌታችን ጨለማ ያለው እርሱን አለማወቅ እንደፈቃዱ አለመመላለስ በኃጢአትና በክሕደት መኖርን ነው፡፡ (ሮሜ 13፡11-13) ብርሃን የተባለ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በእምነት ጸንተው በምግባር ቀንተው በትሩፋት አጊጠው እንደፈቃዱ የተመላለሱትንና ያገለገሉትን ወዳጆቹችንም ብርሃናት መሆናቸውን "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" በማለት መስክሮላቸዋል፡፡ ጌታችን ወዳጆቹ የዓለም ብርሃን የሚባሉት ብርሃን ሲሆኑ መሆኑን ሲናገርም "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡" (ማቴ 5፡14-16) ብሎዋል፡፡ በመነሻችን እንደተመለከትነው ጻድቁ ጨለማ ጣዖትን በማስወገድ ለዓለም ብርሃን ሆነዋል፡፡ ሰዎች ልቡናቸውን ከጣዖታት መልሰው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩትም ምክንያት ሆነዋል፡፡ በመሆኑም ደራሲው የጌታችንን ቃል ይዞ ጻድቁን "ብርሃን ፀሐይ" በማለት አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ፡፡"(ያዕ 1፡17-18) በማለት የብርሃናት አባት ብሎ ጠርቶታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ብርሃናት ብሎ የጠራቸው የብርሃን ክርስቶስ ልጆች ወዳጆቹ ቅዱሳን መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ አምልኮ ጣዖትን እንዲያስወግዱ ኑፋቄንና ክሕደትንና እንዲያጠፋ የሰዎች ልጆችን ሕይወት በቅዱስ ቃሉ አማካኝነት እንዲያርሙና እንዲያስተካክሉ ወደ ዓለም የተላኩ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት በኋላ ዘመን የተነሡ ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ "እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ እግዚአብሔር አዞናል፡፡" በማለት በአንድ ቃል ተናግረዋል፡፡ (የሐዋ 13፡47) ቅዱሳን ጨለማ (ኃጢአት) በሞላው በሰው ልቡና ብርሃን ክርስቶስን የሚያበሩ ብርሃናት መሆናቸውን ትመለከታላችሁን? ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የንስሐ ስብከትን እየሰበከ የንስሐ ጥምቀትን እያጠመቀ በመንገድ የተመሰለ የሰውን ልቡና እያስተካከለ የተቀበለውን መጥምቁ ዮሐንስን "የሚነድና የሚያበራ ብርሃን" ብሎ ጠርቶታል፡፡ (ዮሐ 5፡35) መጥምቁ ዮሐንስ በጌታችን አንደበት የሚነድና የሚያበራ መብራት ተብሎ ስለምን ተመሰገነ? ወንጌልን በመስበኵ ጣዖታትን በማጥፋቱ ሰዎችን ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን በመመለሱ አይደለምን? ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፍቅር ነድደው ሰይጣንን ድል ነሥተዋል፡፡ በሕይወታቸው ክርስቶስን አብርተው በሰው ልቡና ነግሦ የነበረውን ጨለማ ኃጢአት ደርምሰዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅ (የእውነት ፀሐይ) እንደሆነ መንገዱን የተከተሉ ወዳጆቹም ፀሐይ ሆነው ፀሐይ ተብለዋል፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘሪውን ምሳሌ ባስተማረበት ክፍል "በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡" (ማቴ 13፡44) በማለትም ጭምር አስተምሮዋል፡፡ እርሱ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሐይ ሲሆን ወዳጆቹ ደግሞ ጨረቃ ናቸው፡፡ ጨረቃ ብርሃንን የምታገኘው ከፀሐይ እንደሆነ ቅዱሳንም ጸጋን ክብርን ሥልጣንንም ያገኙት ከክርስቶስ ነውና ጌታችን "እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡" ብሎ አስተማረ፡፡ እንግዲህ በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔርን ተከትለው ጨለማ ጣዖትን ያጠፉ ደጋግ አባቶችና እናቶች ብርሃናት ፀሐይ ከዋክብት መባላቸውን ስንመለከት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ብርሃን ፀሐይ ብለን እንጠራቸዋለን እንጂ በጥርጥር መንፈስ ሆነን እንዴት? ለምን? ብለን አንጠይቅም፡፡

በመ/ር ዲ/ን #ቢትወደድ ወርቁ
ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ ም
Audio
ርዕስ :- #ሚተራሊዮን
ደራሲ :- #ዶ/ር ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ
ምዕራፍ :- #15
ተራኪ :- #ተርቢኖስ ሰብስቤ
ቆይታ :- #31ደቂቃ ከ15ሰከንድ ብቻ
የቦታ ይዞታ :- #8.0mb ብቻ
#ዐውደ_ምሕረት_የእናንተ 🙏
_°°°°°°°°°°°___
#በቅርብ ቀን በአዲስ ትረካ ይጠብቁን🙏