++ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግዶ በዓለም ላይ ያበራ ፀሐይ ++
#በመ/ር ዲ/ን #ቢትወደድ ወርቁ
የመልክዐ ተክለሃይማኖት ደራሲ በመልክዑ አርኬ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን "ቅዱስ አባት ሆይ አምልኰተ ጣዖት ጨለማን አስወግደህ በዓለም የምታበራ ፀሐይ አንተ መዓዛህ የተወደደ ደብረ ከርቤን ነህ? ወይስ መሠወር የማይቻላት ደብረ ጽጌን ነህ? " በማለት ያመሰግናል፡፡ ቅዱሳን ነቢያት ሐዋርያት እንዲሁም በየዘመኑ የተነሡ መምህራን ዋና ተልዕኮ ጣዖት አምልኰን በቃለ ወንጌል ማስወገድ ነው፡፡ በሰዎች ዘንድ የሚታይ የሚዳሰስ ጣዖት አለ፡፡ እንዲሁም የማይታይ የማይዳሰስ ልብም የማይባል ረቂቅ ጣዖትም አለ፡፡
በኑሯችንና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችን ልብ ሳንላቸው ከእግዚአብሔር አስቀድመን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ሳናውቃቸው ጣዓታት እንደሆኑብን ልናስተውል ይገባናል፡፡ ቅዱሳን አባቶቻችን በየዘመናቸው ከሰዎች ልቡና የሚታዩትንም ሆነ የማይታዩትን ጣዖታት በቃለ እግዚአብሔር ሲያጠፉ ኑረዋል፡፡ በዚህም በነቢዩ ዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ "ጥበበኞቹ እንደሰማይ ፀዳል ብዙ ሰዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡" (ዳን 12፡4) ተብሎ ትንቢት ተነግሮላቸዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በገድላቸው እንደተጻፈልን በዘመናቸው ጣዖታትን አጥፍተዋል፡፡ በጣዖታቱ ላይ አድረው ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጃቸውን ሰዎች ሲያታልሉ የኖሩትንም እኵያን አጋንንት በወንጌል ትምህርት ሲያሳፍሩና ሲበቀሏቸው ኑረዋል፡፡ በዚህም ለብዙዎች ብርሃን ሆነዋል፡፡ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ምን ያህል ጣዖታትን እንዳጠፉ ስንቶችን ከጣዖት አምልኰ እንዳላቀቁና አጋንንትን በወንጌል ትምህርት እንዴት እንዳወጡ ለመረዳት ገድላቸውን በእምነት ሆኖ ማንበቡ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይኽን በሕሊናችን እንያዝና በዚህ ክፍል ጻድቁ የተገለጡበትን የምስጋና ቃል እንመልከት፡፡
+++ ተክለሃይማኖት ፀሐይ +++
በቅዱስ መጽሐፍ እንደተጻፈልን አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ብርሃን ፀሐይ ተብሏል፡፡ ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት "እግዚአብሔር ብሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማነው?" (መዝ 26፡1) በማለት ዘምሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም፡፡" (ዮሐ 8፡12) በማለት አስተምሯል፡፡ ጌታችን ጨለማ ያለው እርሱን አለማወቅ እንደፈቃዱ አለመመላለስ በኃጢአትና በክሕደት መኖርን ነው፡፡ (ሮሜ 13፡11-13) ብርሃን የተባለ አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር በእምነት ጸንተው በምግባር ቀንተው በትሩፋት አጊጠው እንደፈቃዱ የተመላለሱትንና ያገለገሉትን ወዳጆቹችንም ብርሃናት መሆናቸውን "እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ" በማለት መስክሮላቸዋል፡፡ ጌታችን ወዳጆቹ የዓለም ብርሃን የሚባሉት ብርሃን ሲሆኑ መሆኑን ሲናገርም "መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡" (ማቴ 5፡14-16) ብሎዋል፡፡ በመነሻችን እንደተመለከትነው ጻድቁ ጨለማ ጣዖትን በማስወገድ ለዓለም ብርሃን ሆነዋል፡፡ ሰዎች ልቡናቸውን ከጣዖታት መልሰው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩትም ምክንያት ሆነዋል፡፡ በመሆኑም ደራሲው የጌታችንን ቃል ይዞ ጻድቁን "ብርሃን ፀሐይ" በማለት አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን "መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ፡፡"(ያዕ 1፡17-18) በማለት የብርሃናት አባት ብሎ ጠርቶታል፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ብርሃናት ብሎ የጠራቸው የብርሃን ክርስቶስ ልጆች ወዳጆቹ ቅዱሳን መሆናቸው የታወቀ ነው፡፡ አምልኮ ጣዖትን እንዲያስወግዱ ኑፋቄንና ክሕደትንና እንዲያጠፋ የሰዎች ልጆችን ሕይወት በቅዱስ ቃሉ አማካኝነት እንዲያርሙና እንዲያስተካክሉ ወደ ዓለም የተላኩ ቅዱሳን ነቢያት፣ ቅዱሳን ሐዋርያት በኋላ ዘመን የተነሡ ጻድቃን ሰማዕታት ሁሉ "እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳን ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ ብሎ እግዚአብሔር አዞናል፡፡" በማለት በአንድ ቃል ተናግረዋል፡፡ (የሐዋ 13፡47) ቅዱሳን ጨለማ (ኃጢአት) በሞላው በሰው ልቡና ብርሃን ክርስቶስን የሚያበሩ ብርሃናት መሆናቸውን ትመለከታላችሁን? ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የንስሐ ስብከትን እየሰበከ የንስሐ ጥምቀትን እያጠመቀ በመንገድ የተመሰለ የሰውን ልቡና እያስተካከለ የተቀበለውን መጥምቁ ዮሐንስን "የሚነድና የሚያበራ ብርሃን" ብሎ ጠርቶታል፡፡ (ዮሐ 5፡35) መጥምቁ ዮሐንስ በጌታችን አንደበት የሚነድና የሚያበራ መብራት ተብሎ ስለምን ተመሰገነ? ወንጌልን በመስበኵ ጣዖታትን በማጥፋቱ ሰዎችን ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን በመመለሱ አይደለምን? ቅዱሳን በእግዚአብሔር ፍቅር ነድደው ሰይጣንን ድል ነሥተዋል፡፡ በሕይወታቸው ክርስቶስን አብርተው በሰው ልቡና ነግሦ የነበረውን ጨለማ ኃጢአት ደርምሰዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅ (የእውነት ፀሐይ) እንደሆነ መንገዱን የተከተሉ ወዳጆቹም ፀሐይ ሆነው ፀሐይ ተብለዋል፡፡ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዘሪውን ምሳሌ ባስተማረበት ክፍል "በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡" (ማቴ 13፡44) በማለትም ጭምር አስተምሮዋል፡፡ እርሱ መድኃኒተ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ፀሐይ ሲሆን ወዳጆቹ ደግሞ ጨረቃ ናቸው፡፡ ጨረቃ ብርሃንን የምታገኘው ከፀሐይ እንደሆነ ቅዱሳንም ጸጋን ክብርን ሥልጣንንም ያገኙት ከክርስቶስ ነውና ጌታችን "እንደ ፀሐይ ይበራሉ፡፡" ብሎ አስተማረ፡፡ እንግዲህ በቅዱሳት መጻሕፍት እግዚአብሔርን ተከትለው ጨለማ ጣዖትን ያጠፉ ደጋግ አባቶችና እናቶች ብርሃናት ፀሐይ ከዋክብት መባላቸውን ስንመለከት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ብርሃን ፀሐይ ብለን እንጠራቸዋለን እንጂ በጥርጥር መንፈስ ሆነን እንዴት? ለምን? ብለን አንጠይቅም፡፡
በመ/ር ዲ/ን #ቢትወደድ ወርቁ
ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ ም