አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
499 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል !


#በአሌክስ_አብርሃም

ሙና ትባላለች። መጀመሪያ እንዳየኋት የወደድኳት ቀይ ልጅ ስለሆነች ነው፡፡ ቀይ ሴት ቀልቤን
የምትነሳኝ፡፡ ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ቀይ ሴት ሳይ እንደ አንድ ነገር የሚያደርገኝ። “የቀይ ሴት አብሾ
አለብህ ይሉኛል ጓደኞቼ። እንዲህ ስላችሁ 'ልከስከስ' ትሉኝ ይሆናል፣ግንለፍርድ አትቸኩሉ። እመኑኝ ቀይ ትሁን ጠይም፣ ጥቁር ትሁን የቀይ ዳማ አንዲትም ሴት ጋር ተሳስሜ አላውቅም። አብረውኝ ይማሩ የነበሩ ሴቶች፣ “ይሄ ዝም ብሎ ያፍጥጥ እንጂ በየትኛው ወንድነቱ ነወ ሴት የሚጠይቀው እያሉ
ያሽሟጥጡኛል። ሴት መጠየቅን ማይጨው ከመዝመት እኩል የወንድነት መለኪያ ሲያደርጉ እኮ
ነው! የእኔ ማይጨው ሴት መጠየቅ አይደለም፤ ከጠየቋት ጋር በፍቅር መዝለቅ እንጂ። (አትፈላሰፍ ይሉኛል እንዲህ ስል…) ማፍጠጥን ለምን እንደ ወንድነት እንደሚያዩት አይገባኝም። ስንቱ ነው ሴት
ለማየት እያፈረ አንዴ ወደ ሰማይ አንዴ ወደ መሬት ዓይኑን የሚያቅበዘብዝ? እና በፅናት ማፍጠጥ በራሱ እንዴት ወንድነትን ግምት ውስጥ ይከትተዋል ?

በእርግጥ ቆንጆ ስለሆንኩ፣ ማለቴ በጣም ቆንጆ ሰለሆንኩ እየከጀሉኝ እንደሆነ አውቃለሁ፣ (ጉራ አይደለም) ወንዶች የከጀልናትን ሴት ማግኘት ሲያቅተን አደባባይ
“ደግሞ ይቺ መጣች ቀረች
እያልን እንደምንጎርረውና ቤታችን ገብተን እንደምናለቃቅሰው፣ በምኞትም እንደምንቃትተው ሁሉ
አንዳንድ ሴቶችም የከጀሉትን ሲያጡ ስም መለጠፍና ማሽሟጠጥ ይቀናቸዋል። “ይሄ ልክስከስ ሴት አይተርፈውም” እያሉ (ሴት ካልተረፈው እነሱ እንዴት ተረፉ ?) … “ይሄ ምን ወንድ ነው ሴታሴት እያሉ፣ ይሄ በባዶው ይኮፈሳል፣ ቤሳቤስቲን የለውም እኮ" እያሉ፣ ከውሸት ሳቅ ጋር ደባልቀው እርስ በእርስ “እውነትሽን ነው - ሙች” እየተባባሉ ይቦጭቃሉ። ደግነቱ ሆድ ለሆድ ስለሚተዋውቁ ካብ
ለካብ እየተያዩ ነው የሚቦጭቁት። ሴቶች ከጠሏችሁ ለናንተ ከፉም ደግም አያወሩም፣ በቁማቸው
ይረሷችኋል። ውስጣቸው ትንሽ ቅሪት ሲቀር ነው ቡጨቃውን ከፍ የሚያደርጉት። ታዘቡኝ አንዳዴ
ለምስት ሰዓት ያህል ስለሆነ ወንድ ያወሩና ሲያሙት የዋሉት ወንድ ሲደውልላቸው፣ ከነመፈጠርህ
ረስቼሁ” ይሉታል። ሙና ግን ልዩ ልጅናት።

መጀመሪያ ጊዜ ያየኋት ባንክ ቤት ነበር። ገንዘብ መከፈያው ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጣ። ይሄ ባለጌ
ወንበር ለካስ መጠጥ ቤት ብቻ አይደለም ድንበሩ! ለነገሩ ከብር የበለጠ ምን አልኮል አለ?! ሙናን
ፊት ለፊት ሳያት የባንክ ሒሳብ ቡኬ ከእጄ አምልጦኝ ወደቀ። ብዙ ብር የያዘ ይመስል ሲወድቅ
ብሎ ጮኸ፡፡ ድሮም ባዶ ነገር እንደጮኸ ነው። አነሳሁት። ቀና ስል እንደገና ስልኬ ከእጄ ላይ ወደቀ ባትሪው እዛ ጋ .… ቀፎው እዚህ። እንዳወዳደቁ ብርታት ቀፎው ብቻ ሳይሆን ስልክ ቁጥሬም የተበታተነ ነው የመሰለኛ። 09 እዛ 11 ደግሞ እዚህ ... ተዝረከረክኩ፣ ድንብርብሬ ወጣ። ምናባቴ
ላድርግ -ቅ ላ ቷ “ባንክ ቤት ብር ሳይሆን ፀሐይ ማስቀመጥ ጀመሩ እንዴ!” ያስብላል። የፀጉሯ
ጥቁረት በዛ ላይ ማብረቅረቁ፡ ጥቁር አልማገዝ በብዙ ሺ ክሮች እንደጨሌ የተሰከሰክ፣ ዓይኖቿ ልብ ላይ የሚፈጥሩት ውጋት ነገር አለ፡ አፍንጫዋስ ቢባል ቀጥ ብሎ ወደታች ወርዶ ከንፈሯን መሻገር
ፈርቶ ቀጥ ብሎ የቆመ ነው የሚመስለው። ቆንጆ ናት ነው መቼስ የሚባለው ሌላ ምን ቃል ኣለ ?!

በኋላ ሙና እንደነገረችኝ ከሆነ እሷም ስታየኝ፡ “ድንግጥ” ብላ እየቆጠረችው የነበረው ብር ቁጥሩ ተምታታባት። ደግሞ ክፋቱ ልክ 666 ብር ላይ ስትደርስ ነበር ቁጥሩ የጠፋባት። “ይሄ የሰይጣን
እጅ አለበት” ብላ አሰበች። ለነገሩ ጨዋታውን ልታሳምረው ፈልጋ ይሆናል እንጂ 666 ላይ ደርሳ
ከጠፋት 667 ብላ መቀጠል ነበር። ሰው መቼስ ሰይጣን አሳሳተኝ ለማለት መጠጋጊያው ብዛቱ። ታዲያ አልፎ አልፎ ሳበሳጫት፣ “ድሮስ 666 ላይ እስቁመኸኝ ምን ጤና ሊኖርህ ትለኛለች። አንዱ ስድስት እኔ፣ አንዷም ስድስት እርሷ፣ መሀላችን ያለችው ስድስት ፍቅር ትመስለኛለች፡፡ እኔ የምለው
ሰይጣን ቁጥር ሲሰጠው ለፍቅር ቁጥር አለመሰጠቱ አይገርምም? ይመስለኛል ፍቅር ቁጥር የሌለው
ስለማይደመር፣ ስለማይቀነስ ፍቅር ራሱ ውጤት ስለሆነ ሳይሆን አይቀርም።

ሙና ባንከ ቤት ስትሠራ ሰዎችን በሚያስገቡት አልያም በሚያወጡት ብር እንጂ በሌላ መነፅር ተመልክታቸው አታወቅም ነበር። ለእኔ ግን መለይካዎቹ ምን ሹክ እንዳሏት እንጂ ቀልቧ ወደደኝ።

"ስምህ ?”

"አብርሃም"

“ምትልከው ለማን ነው ?”

“ለእናቴ" ፈገግ ብላ አየችኝ።
ዓይኗ ውስጥ ወዳጅነት ይንበለበላል።

"የእናትህ ስም?”

“አሰለፈች በዙፋኑ ከልካይ ጃኖ …”

"ኧ..ረ በቃ” ብላ በሳቅ ፍርስስስስ (ሳቅ ትመስላለች ስትስቅ)

“ሰልክህ?”

“ስልኬ ኖኪያ ነች” ከትከት ብላ ሳቀችልኝ በወዳጅ ድምፅ 'አድርቅ' ነገር ብላኝ ሳቋን ቀጠለች።
እውነቱን ለመናገር የተናገርኳት ቀልድ ከጓደኛዬ የሰማኋት ያረጀች ያፈጀች ቀልድ ነበረች። ግን ሙና
ካሰብኩት ሰላይ ሳቀችልኝ። ሴቶች ቀልባቸው ከወደዳችሁ ስታስነጥሱ ሁሉ ፍርፍር ብለው እንባቸው እስኪፈስ ይስቁላችኋል፣ ሴቶች ለቀልዱ ሳይሆን ለቀላጁ
ማንነት የሚመፅውቱት ሳቅ የሆነ የነፍሳቸው ኪስ ውስጥ ሳይኖር አይቀርም !! ከጠሏችሁ ደግሞ በጭንቅላታችሁ ቆማችሁ እንደ ኳስ ብትነጥሩ የተቋጠረ ፊታቸው አይፈታም። ጥርቅና 'እንደተረገመ ጥቁር ሰማይ።

ለሙና ስልክ ቁጥሬን ሰጠኋት። እና እንዲህ አልኳት፣ “ያንቺስ?”

አሁን የራሴ ቀልድ ለእኔም አስቆኛል። ሙና በኋላ ቆይቶ ..ተግባባን በኋላ፣ “ደፋር እኮ ነህ .…. ባንክ ቤት ሄደህ ስልክህን ስትጠየቅ 'ያንቺስ' የምትል" ትለኛለች። ስልኳን ሳታንገራግር ነበር የሰጠችኝ።
ከሳምንት በኋላ ተመልሼ እዛችው ባንክ ሄድኩ (ፀሐይ ልሞቅ….) ሙና ገና ስታየኝ፣ “ለማሚ ነው
?” አለችኝ በፈንታ፡ ስትፈግግ ዓይኖቿ አነስ ይሉና ከንፈሯ ከፈት ይላል። ከንፈሯ ቀይ አይደሉም።
ጥቁርም አይደለም፡ ምንም አይደለም። የሆነ የብርጭቆ ጠርዝ ነው የሚመስለው። በከቡ ከፈት ብሎ ጥርሶቿ ብቅ ሲሉ ብርጭቆ ውስጥ የተሞላ በረዶ ያስታውሳል። ስትስቅ ጥርሷ ቀን ይወጣለታል። ነጭ ብርሃን ኩጥርሷ፣ ጥቁር ብርሃን ከፀጉሯ ከዓይኗ ብሌን ይ ነ ሳና ልቤ ላይ ይቀላቀላል። ነጭ አባይና
ጥቁር አባይ የት ላይ ይቀላቀላል ቢባል ሚስኪን ልቤ ላይ።

“ለማሚ ነው?” ስትለኝ ስላፈርኩ “አዎ አልኳት። እውነቱን ለመናገር የሄድኩት እግሬን መቆጣጠር
አቅቶኝ ነበር፣ በደመ ነፍስ። ያለችኝን አራግፌ ለእናቴ ላኩ ስወጣ ግን እየተነጫነጭኩ ነበር።
ምናለ ሙናን ሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ባገኛት ኖሮ? ቢያንስ ማስቲካ እየገዛሁ በየቀኑ አያት ነበር። ባንክ ቤት በምን ሰበብ ይኬዳል? አንድ የእኔ ቢጤ ኢትዮጵያዊ በየቀኑ ባንክ ቤት የመሄድ እድል የሚኖረው ባንክ ቤት ከተቀጠረ ብቻ ነው። “ለምን ቁጠባ አልጀምርም?” ስል አሰብኩ። በየቀኑ የታክሲ መልስ
ሳንቲሞቼን ይዤ ጎራ ማለት ነው…። ግን ደግሞ ሙና ሳንቲም ይዤ ስመላለስ ሥራዬ ደጀ ሰላም
ተቀምጦ መመፅወት ቢመስላትስ ? ኤዲያ!
👍354
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#በአሌክስ_አብርሃም


#ሁለት

..ቅርርቡ የነፍስ ሆኖ ነው መሰል ብዙ ውጣ ውረድ ሳይፈጠረብን ከሙና ጋ ሻይ ቡና ለመባባል በቃን። ከዛማ ማን ያቁመን፤ ከሙና ጋር አንድ ድፍን ዓመት እብድ ባለ ፍቅር ቆየን። እንደው በመተቃቀፍ፣ እንደው በመገባበዝ፣ እንደው በመተያየት፣ እንደው በመጎሻሸም እና በመደዋወል። አንድ ቀን ታዲያ፣

"ሙናዩ" አልኳት።

“ወይ" አለችኝ በዛ በሚነዝረኝ ድምጽ።

ዝም ብዬ አየኋት ገባት !! እናም እንዲህ አለችኝ፣

"አይሆንም፣ ስንጋባ ብቻ !” ቅር አለኝ። ቢሆንም ግን እንደዛው በፍቅር ማበዳቾንን ቀጠልን።
እንደውም የሆነ ጊዜ አንዱን ደንበኛ አቁማ ከእኔ ጋር በስልክ ስታወራ ክስ ቀርቦባት የደመወዟን አስር ፐርሰንት ተቀጣች። ኃላፊዋ ባለጌ ነው፤ ምሳሌው ሁሉ አያምርም። ምን አላት ?
(አረ ያሳፍራል.....)

ስሚ ሙና፣ አንድ የተላከለትን ብር ሊያወጣ ወደ ባንከ የመጣ ኢትዮጵያዊን ለግማሽ ደቂቃ ከማቆም መኝታ ቤት ምንትሱን አቁሞ የሚጠብቅ ፍቅረኛን ሙሉ ቀን ማስጠበቅ ይሻላል” ሙና በሐፍረት ቀይ ፊቷ ቀላ። አሁን እስቲ ከመቆም ጋር የሚያያዝ ስንት ምሳሌ እያለ ሙና ፊት ይሄን ብልግና መናገር ምን
ያስፈልጋል ?
እኔም ከቅጣት አላመለጥኩም። ሥራዬን ትቼ እሷ ጋር ዘና ብዬ በመዋሌ አለቃዬ አምስት ፐርሰንት
ቀጣኝ ባንኮች ከፍ አድርገው የሚቀጡት የብር ጥቅም ስለሚገባቸው መስሎኝ ነበር። ባንድ ፊቱ አስር ፐርሰንት ልቊጣ ብዬ ከሥራ እየጠፋሁ ከሙና ጋር (ሐሙስ ከሰዓት አትሰራም) ስውል አሰቃዬ ምንም ብር ሳይቀጣኝ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሚል ደብዳቤ ሰጠኝ። በእርግጥ አለቃዬ ከድርጅቱ ባለቤት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሰው ነበር። “ተያይዘን እንወጣታለን ብዬ
በሆዴ ፎከርኩ። ቀድሞኝ ተባረረ። የቅጣት ደብዳቤዬን ኪሱ ውስጥ አስቀምጦት ነው መሰል ከ
በኋላ የግል ማህደሬም ላይም ይሁን ሌላ ቦታ አልተገኘም፡፡ ይሄ ስድስት ስልሳ ስድስት የሆነ ፍዳ
ሰውሮትም እንደሆነ እንጃ…

ከስድስት ወራቶች በኋላ ሙናን እንደገና ትክ ብዬ አየኋት !!

ከጋብቻ በፊት አታስበው” አለችኝ ቆጣ ብላ። ግን በቁጣዋ መሃል የሆነች ትንሽ መላላት ውልብ ስትል ያየሁ መሰለኝ። ጨለማ ቤት ውስጥ ትንሽ ብርሃን እንደምታሳልፍ ስንጥቅ ዓይነት ቀጭን የይሁንታ ሰርጥ። ቢሆንም በእንቢታዋ ተበሳጭቼ አስር ቀን ዘጋኋት። አበደች!ስልክ ብትደውል፣ ቤት ብትመጣ
በቃ ዘጋኋት። ከአስረኛው ቀን በኋላ መደወል አቆመች፤ ከቤትም ቀረች። ስትቀር እኔ ሄድኩ። ዘጋችኝ
! የምትሰራበት ሄጄ ስቆም ኮስተር አለች፣

“ኧረ ደንበኛ ክቡር ነው አትገላምጪኝ…” አልኳት። ሳቋ ፈነዳ፤ ታረቅን። መልሰን በፍቅር ማበድ ሆነ። እንኳንም ተጣላን ! ፍቅራችን ጠፍታ ከርማ እንደመጣች ውኃ ኃይሏ ጨምሮ ተንዠቀዠቀች
(ፍቅረኞች ሆይ አልፎ አልፎ ተጣሉ … ደመ መራር ሆናችሁ በዛው ተለያይታችሁ እንዳትቀሩ ጠንቀቅ ብላችሁ)

በመጨረሻ ሙናን እንዲህ አልኳት …. (ምን እንዳልኳት እኔጃ ግን ለድፍን አራት ሰዓታት አውራን
አሳመንኳት፣

“ግን ወደ አጉል ነገር ውስጥ ከገባን በኋላ ብትተወኝስ” አለች ዓይኗ ስልምልም ብሎ። ሰውነቷ ሙሉ ለሙሉ ተሸንፎ አፏ ብቻ ነበር የሞት ሽረት ትግል ላይ የነበረው። ሚስ..ኪን!

“የሁሉም ሴቶች ጥያቄ ነው”

“አትቀልድ"

"ይሄ መያዣ ነው እንዴ ? ከተውኩሽ የአያቶቼ አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋኝ ሙናዬ …" ብዬ
ማልኩ። እነዚህ አያቶቻችን ስንቱን ይውጉ ? ደርቡሽን ተወግተውም ፣ ጣሊያንን ወግተው፣ ሱማሌን
ወግተው አሁን ደግሞ..

"እሺ በቃ አትነዝንዘኝ” አለችኝ። አትነዝንዘኝ የምትለው ቃል "እሺ” የምትለዋን ሽንፈት የምትደግፍ
ከዘራ መሆኗ ነው! እሺ የኔ ቆንጆ እናደርገዋለን፣ በደስታ፣ በፍቅር፣ ያውም በሙሉ ልቤ ... ወደፊት”
ቢባል ምን አለበት ? መሆኑ ላደቀር የምን በዘወርዋራው መናገር ነው …. ሃሃሃሃ ኡፍፍፍፍ ብዩ በደስታ እቅፍ።

እንዴዴዴ ! እንትኑ አሁን ነው እንዴ ?” ብላ ሁለታችንም በሳ.…ቅ። ያለነው እኮ የሆነ ካፌ ውስጥ
ነበር። እና ቀን ተቆረጠ። አርብ ማታ እኔ ቤት ትመጣና ታድራለች፣ (በታድራለች ውስጥ ስንት ጉድ
አለ) ቅዳሜ ትውላለች፣ (በትውላለች ውስጥ ቤቴ የጦርነት ዋዜማ ሲመስል ታየኝ -ጦርነት ያለበት ገነት) ከዛ ታድራለች .… እሁድ ወደ ቤቷ። እንዴት ነው የምለያት” ብዬ ካሁኑ ናፈቅኩ።

አርብ ማታ ቤቴን አበባ አስመስዬ ለራሴም ሌላ ሰው ቤት የሄድኩ እስኪመስለኝ አሳምሬ ጠበቅኳት
እየተንቆራጠጥኩ። ኮቴ ሰማሁ፣ የሴት ጫማ ተረከዝ ቋ ቋ ቋ ሙና ናት፣ መጣች !! በሩ ተንኳኳ …
ኳኳኳኳኳኳኳ ኳኳኳኳኳ ኳኳኳኳኳ …. ግማሹ ኳኳታ ልቤ ሲመታ መሆን አለበት።

ሙና በሬ ላይ ቆማለች። በሩን ስከፍት ረዥም ቀይ ቀሚስ በባለ ረዥም ተረከዝ ጫማ ለብሳ በረዥም ቁመቷ ከላይ ወደታች የሚፈስ ፏፏቴ መስላ (እኔጃ ለምን እንደሆነ እንደዛ መሰለችኝ። አንዳንዴ የሆነ ቅፅበት አለ እዛው ፊታችን ቆሞ ትዝታ የሚመስለን) አየችኝ፣ ተያየን፣ ገባች። አንደወትሮው አልተሳሳምንም፡ አልተቃለድንም፣ አልተሳሳቅንም … ፈርተናል። በጣም ፈርተናል። ተፈራርተናል።በሩን ይዤ እንድታልፍ ወደ ጎን ዘወር ስልላት እንደቆምኩ ታክካኝ አለፈች። ለስላሳ ጠረኗ አፍንጫዬን
አወደው። ጫማዋን እንጀቆመች ስታወልቅ ገድገድ አለች፡ ሁለቱንም ጫማዎቿን አውልቃ ባዶ እግሯ ስትቆም የቀሚሷ ጫፍ ምንጣፉን ነካው።

ቀስ ብላ ገባች። ተከትሏት ወላፈን ገባ። እንደ ኤርታሌ ዓይነት ነገር ቤቴ ውስጥ ተፈጠረ። እቃዎቹ
ሁሉ እየቀለጡ የፈሰሱ መሰለኝ። ሙና ዝም ብላ ተቀመጠች። ሄጄ አጠገቧ ስቀመጥ ሰወነቷ ሽምቅቅ አለ … ፈርተናል! “ፈራን፣ ፍቅር ፈራን” አለ ባለቅኔው።

"እሺ እንዴት ነበር ውሎ" አልኳት ፈገግ ለማለት እየሞከርኩ። ድምፄ ለዛ ቢስ ሆነብኝ። እጄን ጣል አደረግኩት። ዝም አለች። ሌላኛውን እጄን ትከሻዋ ላይ … ዝም ! ሦስተኛውን እጄን የሆነ ነገሯ ላይ፣ አራተኛውን እጄን ፀጉሯ ላይ፣ አምስተኛውን እጄን …. እጅ በእጅ ሆንኩ። ሁሉንም ነገር ባንዴ
መንካት ስለፈለግኩ ፈጣሪ ይውጣልህ ብሎ ብዙ እጅ ያበቀለብኝ እስከሚመስለኝ። እና ተነስቼ ሳብ አደረግኳት፣ ተከተለችኝ። ድክም ያላት ትመስል ነበር። በሕይወት ውስጥ አለ የሆነ ጊዜ፣ አዕምሯችንን ትተን በወደድነው ሰው አዕምሮ የምንመራበት። ሙና ዝም ብላ እንደማደርጋት ሆነች::

ወደ መኝታ ቤታችን...

ምን እንደሆነ ባይገባኝም አንድ የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል። ማለት እንዲህ አልነበረም መጀመርያ ይሰማኝ የነበረው፡፡ ፍላጎቴን የሆነ የማልገልፀው ዓይነት ቅዝቃዜ ወርሮታል። ተሳሳምን ሙና በስሜት አበደች። ደነገጥኩ። እንዲህ እሳት ለብሳ እሳት ጎርሳ ትመጣለች ብዬ በምን አባቴ ጠርጥሬ ልብሷን ከሰውነቷ ላይ በትብብር እየገፈፍን ጣልነው፣ የእኔንም ልብስ ሽቅብና ቁልቁል ገፈፍን እንደፈጠረን እርቃናችንን ቆምን። በየት በኩል እንደገባን እንጃ ኣንሶላው ወስጥ ተገኘን።

የሆነ ነገር ጎድሏል። አንድ የሆነ ነገር ጎድሏል። ሙና እየቃተተች፣ እንደምትወደኝእየነገረችኝ፣ ሰውነቷ እሳት ሆኖ እኔ ምን እንደነካኝ እኔጃ የሚያስደነግጥ ፍጥነት ቅዝቅዝ አልኩ። ቅዝቅዝ ! የሞትኩ መስሎኝ ነበር። ሙና ለብቻዋ የሆነ ነገር የምትሰራ መስሎ ተሰማኝ። በቃ ለታዛቢነት የተጠራሁ ይመስል የምታደርገውን ግራ በመጋባት ማየት ሆነ ስራዬ። እንዴት የሚያሳቅቅ ነገር ነው ? ምንድን
👍202
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ሶስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...ትከክክክክክ ብላ ስታየኝ እንዲህ እላታለሁ፣
“ከጋብቻ በኋላ”

በዚህ የጭንቅ ሰዓት ላይ እያለሁ ሙናን የምትሰራበት ባንክ ወደ መቀሌ ቅርንጫፍ ቀየራት። ይሄማ
የእግዜር እጅ አለበት። ደስ አለኝ። ስሸኛት አለቀሰች። ለአዲስ አበባ ሳይሆን ከእኔ በመለየቷ፤ እና ደግሞ ከብረት የጠነከረ መሻትን ድል ሰመታ ከእሳት ለተፈተነ ትዕግስቴ” (እሷ እንደዛ ነው የሚመስላት) ለእኔ ግን ጉዳዩን ለራሴ እንኳን ማመን ባልፈልግም ገብቶኛል። ስንፈተ ወሲብ !! ያውም እንደ መርዶ ለራሴም ድንገት ዱብ ብሎ የተገለጠ። ለሙና ምን ብዬ ልንገራት ? ልጅቱ ከቀን ወደ ቀን ጉዳዩን
እንድንፈፅመው አፍ አውጥታ በፅኑ መሻት ትጠይቀኛለች። እንደውም ከሌላ ሴት ጋር አንዳች ጉዳይ የጀመርኩና የገፉኋት እየመሰላት መጠራጠር ጀምራ ነበር ምነው ባደረገው..

መቀሌ እየሰራች ቢያንስ በየወሩ እርሷ ወይም እኔ እየመጣችና እየሄድኩኝ አስደሳች ጊዜ እናሳልፍ
ነበር። ግን ምን ያደርጋል ይሄ የእኔ ነገር ጥላውን አጠላብን።

“ከዚህ በላይ መታገስ አይችልም፡፡ችግር ካለብኝንገረኝ፤ ወይም ካስጠላሁህ በቃ አሳውቀኝ
ፕ…ሊስ አለችኝ አንድ ቀን የአይጥና ድመት ድብብቆሻችን አሰልችቷት። እናም ማስጠንቀቂያ ጨመረችበት፣ “ለሚቀጥለው ስመጣ ካላደረግን የእኔና ያንተ ጉዳይ አበቃ !' ሙና ታደርገዋለች። ጭካኔዋ በፍቅሯ ልክ ነው፤ ቀልድ አታውቅም። ተንቀዥቅዤ አነሳስቼ በምን ላስቁማት ? ቆይ ሰው ንብረቱ እንደሚሠራ እና እንደማይሠራ ሳያረጋግጥ እንዲህ ዓይነት እዳ ውስጥ ይዘፈቃል ?! ቢጨንቀኝ ነው እንጂ እሱማ
እንዴት ይረጋገጣል ?እንደ ደም ግፊት አይለካ ነገር።

ሳወጣና ሳወርድ አድሬ ለሃኒባል ሳማክረው ወሰንኩ። ሃኒባል አብሮ አደግ ጓደኛዬ ነው፧ የልብ ጓደኛዬ። ከሙናም ጋር በደንብ ይተዋወቃሉ። እናም ላሳውቀው ወሰንኩ። ሃኒባል ቢያንስ ለምንም
ነገር አይጨነቅም። መፍትሄም አያጣም። ከድሮውም ልጅ ሆነን እኮ ነው … በቃ ችግር በሃኒባል ፊት የቱንም ያህል ቢገዝፍ እንደ ዝንብ ነው በመፍትሄ ጭራ የሚያባርረው። ደወልኩለትና፣ና እሬሳህን ውሰድ ልለው አስቤ ተውኩት፤ እፈልግሃለሁ” ብቻ አልኩት።

ምን ጉድ ተፈጥሮ ነው እንዲህ እያግለበለብክ ያስመጣኸኝ ጃል ?" አለ ሃኒባል ያዘዘውን ቡና
አማሰለ።

"ባክህ ችግር ገጥሞኛል”

"ችግር የሚባል ነገር የለም ባክህ፤ የመፍትሄ እጥረት በለው” አለ (አላልኳችሁም ?)

"እ..እንዴት መሰለሀ ከሙናጋ የሆነ ትንሽ ችግር ... ኧረ ምን ትንሽ …. ትልቅ ችግር ውስጥ ገብተናል”
አልኩት።"

ቡና ማማሰሉን አቆመና ኮስተር ብሎ፣ “የምን ችግር…” አለኝ።

"እኔ ለካ … እንትን …. ማድረግ አልችልም አሁን ነው ያወቅኩት”

"ምን ማድረግ ?”

ኤጭ ሥሙን ቄስ ይጥራውና እንዴት እንደቀፈፈኝ፣

“ግንኙነት ማድረግ አልችልም"

“የምን ግንኙነት ?"

“የምን ግንኙነት ትለኛለህ እንዴ … ወሲብ ነዋ!" ስል አፈረጥኩት።

"እ...ንዴ ! እና እስከዛሬ ከሙና ጋር ስታድሩ ምን እየሰራችሁ ነበር የምታድሩት ?"

“በቃ ትኝት ነዋ አርፈን … ማለቴ አርፌ"

“ትኝት ትኝት .… ለሽሽ ?”

“አዎ !"

"አንተስ እሺ … ሙና እንዴት አስቻላት ?"

“ያው ላያስችል አይሰጥም”

“ኧረ ሰውዬ ተረቱን አቁምና ወደ መፍትሄው!”

"እኮ! መፍትሄው እኮ ነው የጠፋብኝ፤ ሙና ደግሞ ደበራት”

"እንዴት ነው የማይደብራት፣ ትቀልዳለህ እንዴ ?” ብሎ ተነስቶ ወጣ። አካሄዱ አስደንግጦኝ ዝም ብዬ እንደተቀመጥኩ ትንሽ ቆይቶ አንድ መፅሄት ይዞ ተመለሰ። ከነወንበሩ ጠጋ ብሎኝ የመጽሄቱ የኋላ ሽፋን ላይ በውስጥ በኩል የታተመ ማስታወቂያ ጠቆመኝ።

“ደብተራ ግዛው ደበሌ የባሕል ሕክምና አዋቂ” ይላል። ጥምጣማቸው የሚያምር አፍንጫቸው ደፍጠጥ ያለ ደብተራ ሳይሆን ቦክሰኛ የሚመስሉ ሰውዬ ባለቀለም ፎቶ ሩብ ገፁን ተቆጣጥሮ በኩራት ተገጥግጧል። የሰውየውን ኩራት ለተመለከተው መቼስ እንኳን ከበሽታ ከሞት የሚያድኑ ሳይመስለው አይቀርም። ከሥር “መፍትሔ የተገኘላቸው ሕመሞች” ዝርዝር ሰፍሯል...

ለዓይነ ጥላ

ለቡዳ

ትምህርት ለማይገባው (ከድድብና የባሰ በሽታ የለም ብለው ይሆን)

ለሽንፈተ ወሲብ

ለስንፈተ ወሲብ ….

ቢንጎ !! ግን ስንፈተና ሽንፈተ ወሲብ ልዩነታቸው ምንድን ነው ?


አድራሻ ጦር ኃይሎች! እፎይይይ ሙና ተመልሳ ልትመጣ ሰላሳ አራት ቀናት ብቻ ይቀራሉ።
“በዚህ ሰላሳ አራት ቀናት ደብተራ ግዛው ተዓምር ፈጥረው የወደቀውን እንደሚያነሱት፣ የተኛውንም እንደሚያቀኑት ተስፋ እናደርጋለን አይዞህ ወዳጄ” ሃኒባል አፅናናኝ።

እናም ታሪካዊው ጉዞ ወደ ጦር ኃይሎች። የጠፋውን ወንድነት ፍለጋ። ወንድነትን ለመፈለግ፣

መኮላሸትን እምቢ ልንል

እንኳን ጦር ኃይሎች ጦር ሜዳ እንዘምታለን።

ኧ…ረ

ጎራው…

አልዋጋም ብሎ የተኛውን አውሬ.

ቆስቁሰው ቆስቁሰው አደረጉት አውሬ ... አለ ያገሬ አሽቀራሪ - መጣንልሽ ሙና !!

“በመጪዎቹ ሰላሳ አራት ቀናት የወንድነት ሕዳሴን ለማረጋገጥ ከደብተራ ግዛው ደበሌ ጋር ወ ደ ፊ ት !!”

ይሄ ሃኒባል የሚባል ልጅ እኮ የማይቀልድበት ችግር፣ በንቀት የማይመለከተው መከራ የለም፤ እንዲህ ጨንቆኝ እንኳ በግድ ፈገግ ያስብለኛል።

ጦር ኃይሎች እስከምንደርስ ሃኒባል ቀልድ እያወራ ብሶቴን ሊያስረሳኝ ቢሞክርም በፍፁም መርሳት አልቻልኩም። “አቡቹ ጣጣ የለውም ሰውዬው አደገኛ ናቸው፤ እንደ መኪና ተረክ አድርገው ነው የሚያስነሱት” ይለኛል። አይ ተረክ ... በስንት ጉድ ግፊ፣ እንደ ነዳጅ በትኩሳት የምትነድ ልጅ አየተማፀነችው ለሽሽ ያለ 'እንትን' እንዴት ነው ተረክ ብሎ የሚነሳው ? መርሳት ብቻ ሳይሆን የሆነውን
ሁሉ ማመን አልቻልኩም። ብቻ ቶሎ ይሄ ሰውዬ የሚያደርጉትን ባደረጉና

ጦር ኃይሎች የተባለው ሰፈር ደረስን፤ ዓየር ጤና አካባቢ ነው
አሉን፤ ዓየር ጤና ሄድን - ዘነበ ወርቅ፣ ከዛ ወይራ ሰፈር ... አንዲት ጭርንቁስ በቅጠላቅጠል የታጠረች አጥር ውስጥ ያዘመመች የጭቃ ቤት። “ይሄ
ነው ቤቱ” አሉን። አሁን ማን ይሙት ይሄን ቤታቸውን በስርዓት ያላቆሙ ሰውዬ ሌላ ነገር ያቆማሉ ?
እንደዚህ እያሰብኩ አሮጌውን የቆርቆሮ በር ገፍተን ገባን።

አንድ የቆሸሸ ቱታ የለበሰ ጎልማሳ ሰው አገኘን።

“ደብተራ ግዛውማ ቦሌ ምን የመሰለ ቢላ ቤት ገዝቶ ሄደ እናትዬ፤ ዛሬ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማ ኃብታም ሁኗል። ሰው ሁሉ በባዶ እግሩ ከገጠር እየመጣ እንዲህ ባለፀጋ ይሆናል፤ እኛ ነን የአርባ ቀን እድላችን ከአፈር አትነሱ ብሎን.." እያለ ብሶቱን ይዘረግፈው ገባ።

ተመለስን።

“እንዳንከራተትሽኝ አላህ ያንከራትሽ አለ አሉ ሰውየው፤ ጨረቃን መግቢያዋን አያለሁ ብሎ ሲከተል ከርም አልሆን ቢለው እኮ ነው። ስንመለስ ሃኒባል እንዲህ አለኝ፣ “አቡቹ አየህ የዚህን አገር ነገር፡ አንተ በቀን ስምንት ሰዓት ቆመህ በየወሩ የቤት ኪራይ መክፈል የማትችል ደመወዝ ትከፈላለሁ አጅሬው እንትን ከቁሞ ቪላ ይገዛል ያውም ቦሌ”

“ተናግረህ ሞተሃል፤ እንትን ከማቆም በላይ ለአንዲት አገር ምን ትልቅ ሥራ አለ” ብዬ ገላመጥኩት:

“አብርሽ እንዲህማ አትነጫነጭ፣ ይቆማል አይዞህ”
👍282🔥1
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#አራት


#በአሌክስ_አብርሃም


..."እ..ጎረምሳው መቼ ጀመረህ?” አለኝ። (በቃ ምርመራ ተጀመረ ማለት ነው ?) ሰውዬውን ትኩረት
ስመለከተው ለካስ ዓይኑ ልክ አይደለም፤ ትንሽ ሸውረር ያለ ነው። ታዲያ መጽሔት ላይ ከየት አባቱ ያመጣውን ፎቶ ነው የለጠፈው ?..

“መቼ እንደ ጀመረኝ አላወቅኩም ድንገት ከፍቅረኛዬ ጋር…"

"እ … ድንገት ከፍቅረኛህ ጋር ዓለምሆን ልትቀጭ … ሱሪህን አውልቀህ .… ቡታንታህን አውልቀህ በልስትለው…. ባባቴም የለ ብሎ ድፍት፣ ቅዝቅዝ አለብህ … እ? አዋራጅ እኮ ነው!አዋራጅ! ስንቱ በዚህ ዓይነት አጉል ጊዜ በሴት ፊት መዋረዱ አሸማቅቆት ገመዱን ቋጥሮ ራሱን ሲጥ አድርጓል መሰለህ ! እኔ እንኳን ሁለት ምን የመሳሰሉ ልጆች በዚሁ ጠንቅ ታንቀው የሞቱ አውቃለሁ አንዱ እንኳን መርዝ ጠጥቶ ነው … ያው ነው!ቀላል ነገር እንዳይመስላችሁ፡ ሴቶቹ ደሞ ይችን ወሬ ካገኙ እየዞሩ ለሁሉ
ነው የሚያወሩት“ አለ ከአፌ ላይ ነጥቆ። ይሄ ሰውዬ እንዴት ነው የሚቀባጥረው በእግዚአብሔር
በአንድ ጊዜ መንፈሴንም አኮላሸው እኮ።

እና.እንዴት ነው ትንሽም አይላወስ፣ ወይስ ጀማምሮ መሃል ላይ ወገቤን ነው የሚለው ሲል
ጠየቀኝ።

"ምኑ ?” ብዬ ጠየቅኩት።

"ቆ..ህ ነዋ" ብሎ ቃሉን እንደተፈጠረ አፈረጠው! ስድ !

“አይ ምንም የለም” አልኩ እየተሸማቀቅኩ።

"ከዚህ በፊት ሌላ ሴት ጋር እንዴት ነው …አልጀማመርክም ?”

"ሌላ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም
“ተው ተው ! ለኃኪምና ለንስኃ አባት ሚስጥር አይደበቅም … ሃሃሃ እስቲ አንተኛው ወደ ውጭ
ውጣ¨ አለና ሃኒባልን እዘዘው። ሃኒባል ሹክክ ብሎ ወጣ (ይሄ ደግሞ ምን ያሽቆጠቁጠዋል)

ሃኒባል እስኪወጣ ጠበቀና፣
"እ… ጓደኛህ እንዴት ናት ”

“እንዴት ናት ማለት ?” አልኩት ጥያቄው ግራ አጋብቶኝ።

እንደው መልኳ፣ ጸባይዋ ማለቴ ነው። አንዳንዷ ሴት እኮ ትዘጋለች። እውነቴን ነው ዛላዋ አምሮህ፡፡
መልኳ ስብሆ ስትቀርባት አንዳንዷ ሴት እንኳን መተቃቀፍ ምግብ ትዘጋለች

"እ … ፀባይማ እናት ናት መልኳም ቢሆን" አልኩና ዋሌቴን አውጥቼ ፎቶዋን ሰጠሁት። መነፅሩን ፈልጎ ዓይኑ ላይ ሰካና ፎቶውን በትኩረት ወደ ዓይኑ ቀረብ ራቅ እያደረገ ተመልከቶ፣

"ኧረግ… ኧረግ ... ኧረግ ወንድሜን ! እውነትም ተይዘሃል። ይችን የመሰለች ልጅማ ካመለጠችህማ ሰውም አትሆን…” ብሎ አፉን ጠረገ። ዝም ብዩ አየዋለሁ፡፡ የሙናን ፈቶ እስኪበቃው ተመለከተውና
ጉሮሮውን ገርገጭ አድርጎ ምራቁን ከዋጠ በኋላ
እንደው ትንሽም አልሞከራችሁ ?” ሲል ጠየቀኝ።

"ኧረ ምንም የለም" ፎቶዋን እንደገና ተመለከተው።

"ምናምን አዙራብህ እንዳይሆን” አለኝ።

"ምንድነው ምናምን ?”

"የዛሬ ሰው አይታመንም። አንዳንድ ሴቶች ሌላ ሴት ጋር እንዳትሄድባቸው ሌላ ሌላ ነገር እንዳታደርግ ያሰሩብህና፣ ሲቆይ ለነሱም ይተርፋል ጠንቁ። እንደው አቋም ብቻ ሆንክ እንጂ አንተም ብትሆን ሸበላ አንዷ እንዳትቀማት አዙራብህ ቢሆን ማን ያውቃል"

"አረ እሷ" ሰለቸኝ ሰውዬው። እውነቱን ለመናገር ራሱን ቁልል ያደረገ ዘላባጅ ነገር ነው። ለስጋዬ
ፈውስ ብመጣ ጭራሽ ነፍሴንም ያቆስላታል እንዴ ?!

"ቀላል ነው አይዘህ !! የሰው እጅም ሆነ ሌላ መፍትሄው በእጃችን ነው' ሲለኝ ብስጭቴ ብን ብሎ ጠፍቶ ጆርዬ ቆመ።
አውርቶም ተሳድቦም ብቻ ያቁምልኝ፤ ሌላው ትርፍ ነው።

"እውነትዎትን ነው ቀላል ነው ” አልኩት በጉጉት።

"አዎ ! ይች ምንአላት ?” አለ ልክ ወደ ብልቴ አቅጣጫ በእጁ እየጠቆመና ቀማጣጣል ዓይነት ከንፈሩን ወደ ታች ጣል እያደረገ። እንኳን ይችን ስቱን አቁምነዋል!ይሄ ወዲህ ስትመጡ መታጠፊያው ጋ ያለውን ቀልቀሎ ሆቴል ታቀው የለም?”

"አዎ አውቀዋለሁ" አልኩ በጉጉት። ደግሞ አንድ የሆቴል ሕንፃ ከእኔ ጕዳይ ጋር ምን አገኘው ብዬ።

“ይሄውልህ የሱ ሕንፃ ባለቤት እንዲህ እንዳተ ፀሐይ የመሰለች ሚስት አለችው። መቼስ ብር አለን
ብነሆ ጉዳያቸውን ሳይፈትሹ ነው ትዳር ውስጥ የሚዘፈቁት። እቅፎ ቢለው ቢሰራው ወንድነት ከየት
ይምጣ ? ጭራሽ አጅሪት ውጭ ውጭ ታይ ጀመረልሃ ... ይሄን ሲሰማ ሊያብድ ሆነ። በኋላ እኔ ጋ
በሰው በሰው መጣና እንደሚሆን አድርጌ ላኩት። ይሄው ዛሬ እንኳን ለሚስቱ ለውሽሞቹም ተርፏል።
ሚስቱ እንዴት እንደምትንሰፈሰፍለት አገር የሚያውቀው ነው” የተቸገረ ሰው ሞኝ ነው፤ ዝም ብዬ
ሰውዬውን እሰማዋለሁ። አወራሩ ድራማ የሚሰራ ነው የሚመስለው።

“አንተ እሱን ትላለህ ! ይሄ በየቀኑ ቴሌቪዥን ሳይ 'እንትን' ፕሮግራም ላያ የሚቀርበው አውግቸው
” … በቴሌቪዥን ሲናገር ድምጹ ሲያስገመግም አንሰሳ ገዳይ አይመስልም ነበር ? ሃሃሃሃ ማታ ማታ ሚስቱ እያንከላፈተችው ስንት ዓመት አልቅሷል መሰለህ፡፡ እንደውም ይሄ ትልቁ ልጁ የሱ አይደለም እየተባለ ይታማልኮ። አሃ ምን ታርግ ታዲያ ያችን የመሰለች ቆንጆ በአምሮት ትሙት እንዴ ! የሱ እንኳን ሽንፈተ ወሲብ ነው”

“ሸንፈተ ወሲብ ምንድን ነው ?”
አልኩ መጽሔቱ ላይ አይቼው ያልገባኝ ነገር ትዝ ብሎኝ።

“እሱማ እንግዲህ … አገር አማን ብለህ ልትተቃቀፍ ገና ሴቷ ሰላም ብላ እጅህን ስትጨብጥህ አንተ
ጥንቅቅ ብለህ በቁምህ ጨራርሰሃል !! ሲበዛ እስከመሳሳም ብትዘልቅ ነው፡፡ አንዳንዱማ የተሞናደለ ዳሌ፣ ሎሚ የመሰለ ተረከዝ ሲመለከትም በቁሙ ሱሪው ላይ ይለቀዋል። ባንድ ፊቱ እንዲህ እንዳተ መዳፈን ይሻላል እንጂ፣ ሴቶች ሽንፈተ ወሲብ ያለበት ወንድ ላይናቸው ነው የሚቀፋቸው … ላይናቸው ወይ አይተወው ወይ አያደርገው … አጉል ነካክቶ የሰው አምሮት መቀስቀስና ሥም ነው ትርፉ ከፉ ችግር ነው። ያንተ በስንት ጣዕሙ፡ ያንተማ ምናላት ቢሆንልህ እሰየው ባይሆንም ሴት ቀረ አትሞት"

“ላይሳካ ይችላል እንዴ ?” ስል የነበረችኝ ተስፋ ኩስምን ብላ ጠየቅኩ።

“ምሳሌውን ማለቴ ነው እንጂ .. አንተማ ታሰታውቃልህ፤ የአገር ሴት አይመልስህም ቱ ግዛው ምናለ
ቀለኝ። ከዚህ ቤት እግርህ ሳይወጣ ነው እንደ ሚዳቋ ቀንድ ቀጥ ብሎ የሚቆመው። ወዮላት ለዛች ሚስኪን” አለና የሙናን ፎቶ እንደገና ወደ ዓያኑ እስጠግቶ ተመለከተው። ተስፋዬ መለስ አለልኝ።

“እግዲህ ሁለት ዓይነት አሰራር አለ፤ አንዱ .. ይሄ እንኳን ላንተ አይሆንም” አለ መልሶ።

“ለምንድነው ለኔ የማይሆነው ?”
“ውድነዋ ! ውድ ነው ... ዋጋውን ብትሰማ ከወንድነትህ በፊት ትንፋሸህ ነው እዚሁ የሚቆመው

"ወዳጄ"

"ግዴለም ይንገሩኝ ?"

"አይ ይቅርብህ። አሁን ጓጉተህ ነው፣ በኋላ ፍቅሩም አምሮቱም ሲወጣልሀ የከፈልከው ገንዘብ ትዝ ባለህ ቁጥር እንኳን እንትንህ ነፍስህም ጭምር ነው የሚሸማቀቀው። እንደውስ ተመልሰህ መጥተህ ብሬን መለስልኝ ልትል ነው ? ቅቅቅቅ' ሳቁ ይቀፋል። የሆነ ነገር ሲቧጠጥ የሚወጣው ዓይነት ድምጽ ነው።

"እሺ ሁለተኛውስ ?"

"ባይሆን እሷ ትሻላለች አንድ ሐያ ሺ ታስከፍልሃለች እንጂ ፍቱን ናት”

"ሐያ ሺ …?”

"አዎ! ምነው?”

"አልተወደደም ?”

"እኮ ! የመጀመሪያውን ብትሰማ ያልኩህ ለዚህ እኮ ነው ! ቢሆንም ዓይንን ባይን ለማየት ሒያ ሺ ምን
አላት ? እንኳን ለማቆም የቆመበት ልክስክስ ሁሉ እዚህ እኛ አካባቢ ላሉ ሴተኛ አዳሪዎች ሐያ ሺ
ይከፍል የለም እንዴ ?! ያውም ላንድ ሌሊት። መቼስ ሐያ ሺ ብር ሳይኖርህ ይችን የመሰለች ቆንጆ ላይ አትንጠለጠልም፤ እንግዲህ ምርጫው ያንተ ነው።” ብሎ ፎቶውን መለሰልኝ ወደ ቴሌቪዥኑ ዞሮ በሪሞት መቆጣጠሪያው ድምጹን ከፍ አደረገው፡፡
👍272🔥2
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#አምስት


#በአሌክስ_አብርሃም



...ከሃኒባል ጋር ሆነን ያልረገጥነው የባሕል ሕክምና አዋቂ ቤት የለም፤ ደከመን። ሃኒባል ለእኔ ሲል
ያለችውን የዓመት እረፍት ጨርሶ ካለ ክፍያ አንድ ሳምንት ከሥራው ቀረ። ግን ምን ያደርጋል፣ ሁሉም
ነገር ከንቱ ልፋት ብቻ ሆነ። የሄድንባቸው ሁሉ ለእኔ ችግር መፍትሔ ማምጣት ይቅርና፣ ማፅናናት እንኳን ያልፈጠረባቸው አጋሰስ ነጋዴዎች ነበሩ። ቢጨንቀን አንድ ሁለት የልብ ጓደኞቻችንን ጨምረን
ጉዳዩን ነገርናቸው።ኣንዱ ጓደኛችን ለትምሕርት ውጭ ቆይቶ ገና መመለሱ ነበረ፤ ማይክሮባይሎጅ
ነው።

ጉዳዩን በጥሞና አዳመጠና፣ “…እስቲ እንዲት ውጭ ኣብረን የተማርን የስነልቦና ባለሞያ አውቃለሁ”አለ። ደስ የምትል የተረጋጋች ልጅ ጋር ወሰደኝ። ቢሮዋ ይገርማል፤ ሁሉም ነገር ነጭ ከእስከርብቶና ወረቀቱ ውጭ። ተነስታ ተቀበለችን። ከአንድ ሰዓት በላይ ያወራሁ ሳይመስለኝ ብዙ አስወራችኝ

“እኔ የምልህ አብርሃምም
እ ?"

ፍቅረኛህ ምናልባት ከቤተሰብህ አንድኛቸውጋ በመልከ ወይ በባሕሪ ትመሳሰል ይሆን?ፀ

"ኧረ በጭራሽ !እህቴ አፍንጫ የሚባል ነገር አልፈጠረባትም፣ ሙና'ኮ ሰልካካ ናት። እህቴ ከማጠር ብዛት ከራሷ ቦርሳ ቻፕስቲክ ለማውጣት እንኳን ወንበር ላይ ቆማ ነው፤ ሙና'ኮ መለሎ ፈገግ አለች
የሥነልቦና ባለሞያዋ። ጥርሶቿ ያማምራሉ (ልብ አይሞት አሁንም ሴት አደንቃለሁ)
እናቴም ብትሆን ቁመቷ እህቴ ነው የወጣችው። በዛ ላይ እናቴ ጠይም ሙና እኮ ዝም አልኩ!
ምናልባት የወሲብ ፊልሞችን ትመለከት ነበር እንዴ ?
“ኧረ አይቼ አላውቅም" እውነቴን ነበር።
“ቤተሰባችሁ ውስጥ የሚበዙት ሴቶች ናቸው ወንዶች ?
“ልጆቹ እኔና እህቴ ነን.… በቃ ! የሥነልቦና ባለሞያዋ የሆነ ነገር ቀይ ወረቀት ላይ በቀይ እስክርቢቶ
ስትጽፍ ቆየችና፣ (እንዴት እንደሚታያት እኔጃ
«ኃይማኖት ላይ እንዴት ነህ ?» «ታጠብቃለህ ?”
«ኧረ የለሁበትም።"
ቤተከርስቲያን የሄድኩት ራሱ ኢህአዴግ አዲስ ኣበባን ሲቆጣጠር የበቅሎ ቤቱ
ፍንዳታ ጊዜ፡ እናቴ ሚካኤል ልትደበቅ ስትሄድ እጄን ይዛኝ ነው ከዛ በኋላ ሄጄ አላውቅም

ፍቅረኛህ ሌላ ወንድ ጋር ግንኙነት አላት ብለህ ታስባለህ ?”

ማን ሙና … ኧረረረረረረረረረረ"

ከዚህ በፊት ከሌላ ሴት ጋር ወሲብ ያልፈጸምከው ለምንድን ነው ”

"እኔጃ"

"ሴን ትፈራለህ እንዴ ?

"መፍራት ሳይሆን እንዲሁ መቅረብ ብዙም አልፈልግም።” ወንበሯ ላይ ተመቻችታ ወደኔ ዘንበል አለችና (ጡቶቿ አፈጠጡብኝ)

“ለምን ?” ስትል ጠየቀችኝ፤ ቁልፉን ያገኘችው ሳይመስላት አልቀረም።

ረዥም ሰዓት በስልክ እንዳያወሩኝና ሸኘኝ እንዳይሉኝ … ! ስል መለስኩላት። እንደው ይህ ምላሽ መታበይ ይመስል ይሆናል እንጂ ማንንም እንደመሸኘትና እና በስልክ እንደማውራት የምጠላው ነገር
የለም። እኔም ሲሸኙኝ አልወድም፤ ሰውም መሸኘት ያንገሸግሽኛል። ምንድን ነው መጓተት፣ ምንድነው
ስልክ ላይ ተለጥፎ ማላዘን ? እንዴት እንደሚያስጠላኝ ! ስልከ አልወድም።

እሺ አብርሽ ጨርሰናል፣ ስልክህን ስጠኝና እደውልልሃለሁ” እርፍ!!
የሥነልቦና ባለሞያዋ እየደወለች ልትረዳኝ ብትሞከርም ነገሩ ዋጋ አልነበረውም። የበለጠ ስለጉዳዩ
ባሰብኩ ቁጥር በእግሮቼ መሃል ሳይሆን በፍርሃት መሃል ቁም ነገሩ ጠፋ። ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም !! ወዶ ነው አበሻ፣ “ወንድ ልጅ ከነቃጭሉ" የሚለው። ትውልድን የሚሻገር ሕያው ድምጽ
መፈጠሪያው የት እንደሆነ ሲገባው እንጂ ! ኤዲያ!ወንድነት ደገፍ ብሎ የሚኮፈስበት ከዘራ ሸንበቆ ሲሆን አለ ከልብ የሚሰነጠር ወኔ ከተራ ብልግና የገዘፈ ሃቅ፤ ቃጭሉም ዝም ! ቤቴ ውስጥ ካሉት እቃዎች ምን አስጠላሀ ብባል አልጋዬ። የተሸነፍኩበት፣ የተማረክኩበት፣ የቆሰልኩበትና የተሰዋሁበት
ጦር ማዴ መስሎ ታየኝ። “ወኔዬን ያፈሰስኩበት አልጋ እኮ ነው ብዬ የልጅ ልጆቼ ላይ እኮፈስበት
ይሆናል። ያኔ ወኔው ያፈሰሰ ትውልድ ነፍ ነው የሚሆነው ! ወኔ ቢስነትም ክብር!
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሙና ልትመጣ አስራ አንድ ቀናት ቀሩ ። አስራ አንድ የሽብር ቀናት ! “አብርሽ ፈራህ እንዴ ?ሂሂሂሂሂ
እንደ ቀልድ ትጠይቃለች። ለምን ጀግና ለመምሰል እንደምጣጣር ለራሴም አይገባኝ፤ ፈርቻለው
አይደል እንዴ ? አዎ ፈርቻለሁ ብላት ምን ነበር ? እኔ ግን ኮስተር ብዬ እንዲህ አልኳት፣ “ለምኑ ነው
የምፈራው?

“ለብር አምባሩ ነዋ አለችና ትንፋሽ እስኪያጥራት በሳቅ ፈረሰች። ሳቋ ውስጥ ሺ ጊዜ ፍራ እንጂ
አሁንማ ቁርጥ ነው የሚል ንዝረት አለ። እኔ'ኮ የሚገርመኝ “ብር አምባር” ከእንትን” ጋር ምን
አገናኘው? እውነቴን እኮ ነው … ብዙ ወንዶች ከአንዲት ሴት ጋር ወሲብ ሊፈፅሙ “ፈረሱም ሜዳውም ያውላችሁ” ሲባሉ በስሜት ስለሚሳከሩ እንኳን ቃል ሊሰነጥቁና ሊመረምሩ አልጋ ላይ ይሁኑ ዓየር ላይ የሚያውቁት ከተረጋጉ በኋላ ነው። ከዛ በፊትማ ብር ይልሰር አምባር ይሰበር ብርጭቆ ይሰበር ቅስም
ይሰበር ምን ግዳቸው "ሰማዩን ሰበረው ጀግናው” ቢባልም አይሰሙም፤ እኔ ግን የያዘ ይዞኝ ቀልቤን አሰላሳይ አድርጓታልና “ብር አምባር” ከድንግልና ጋር ምን አገናኘው ብዬ አስባለሁ -- (ሰው ወዶ ፈላስፋ አይሆንም መቼስ ይሄ ሁሉ ሚዜ እና ታዳሚ ላንቃው እስኪደርቅ በየሰርግ ቤቱ“ብር አምባር ሰበረልዎ ጀግናው ልጅዎ እያለ ይዝፈነው እንጂ “ድንግልናን ከብር አምባር ምን አገናኘው ለሚለው ጥያቄ መልስ ያለው አይመስለኝም።

እኔ ግን ዝም ብዬ ሳስሰው፣ “ብር አምባር መስበር አስገድዶ ከመድፈር ጋር “ጥብቅ ቁርኝት ያለው ጉዳይ ይመስለኛል። ልጅቱ የብር አምባር እጇ ላይ አጥልቃለች፤ ያው ሴት የብር አምባር ማድረጓ ከጥንት የተለመደ ነገር ነው) እና ባሏ ወላ ወዳጇ እጇን ይይዛታል .… (ያዝ እጆን) እንዲል ዘፈኑ ከዛ ለማምለጥ ወይም ራሷን ለማዳን እንዳቅሟ መታገሏ አይቀርም፤ መቼስ ዝም ብሎ ያውልህ አይባልም።
በሩን ይዘጋል (ዝጋ ደጇን) እንዲል ቀጣዩ የዘፈኑ ስንኝ፤ ትግሉ ከበረታ እጇን ጠምዝዞ ጉንጯን (ሳም ጉንጯን ) የሚለው ልክ መጣ። ለከንፈሯ ያሞጠሞጠው ከንፈር በልጅቱ መወራጨት ስቶ
ጉንጯ ላይ አርፎም ሊሆን ይችላል፣ ወይም አየር ላይ እንደ ርችት የከሸፈ መሳም ብትን ! ሲታገላታ እጇ ላይ ያለው አምባር ስብር ! ከሽ ! “ይሰበር የታባቱ ቅዳሜ ገበያ ስወጣ ሌላ እገዛልሻለሁ ያውም ወርቅ የመስለ” እያለ ወደ ጉዳዩ !
እንዲህ የሚያስለፈሰፈኝ ወድጄ አይደለም፤ አምባሩ እኔ እጅ ላይ ያለ እስኪመስለኝ መዘዜ ሊመዘዝ
አስራ አንድ ቀን ቢቀረኝ እንጂ። ሙና ይቅርታ አታውቅም ! በአሁኑ ጉብኝቷ ጉንጯን ስሜ ብልካት
እርሷም እንደ ይሁዳ ስማ ነው ለብቸኝነት ስቅላቴ የምትሸጠኝ። ሙናን እኮ አፈቅራታለሁ። እንደ
ቀልድ ሳጣት ነው በቃ ? እሺ አሁን የእኔ ጥፋት ምንድን ነው? የሙና ጥፋትስ ? እግዚኣብሔር ግን
ምን አደረግኩት ? እስኪ አሁን ማን ይሙት ሊቃጣኝ ፈልጎ ከሆነ ሌላ ልምጭ አጥቶ ነው !? ለምሳሌ ሰፈራችንን በጎርፍ አጥለቅልቆ እኔን ብቻ በመግደል ዜና ማድረግ አይችልም ? መንገድ ላይ ሱክ ሱክ ስል መብረቅ አውርዶ ድምጥማጤን ማጥፋት ያቅተዋል ? ምን አድርጌው ከማን የተለየ ጥፋትና በደል ሰርቼ በውርደት የምወዳትን ልጅ ዓይኔ እያየ ያስነጥቀኛል ? አባታችን አብርሃም እንኳን በዘጠና ስንት
አሙቱ ተሳክቶለት ልጅ ሲወልድ እኔን ሚስኪኑ በሃያ ሰባት አመቴ እንዲህ ጉድ ስሆን እግዜር እንዴት
ሆዱ ቻለ ?

'አብርሽ” እለኝ ሃኒባል፣

"እ"

“ግን ችግሩ ከሙና ቢሆንስ ?"

“እንዴዴዴዴዴ ምን አገናኘው ከሙና ጋር”
👍231
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ስድስት


#በአሌክስ_አብርሃም


...ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ቤተክርስቲያን ሄድኩ። እንደ እብድ ብቻዬን ማውራት ጀምሬ ነበር። ቀጥ ብዬ ዋናውን በር አልፌ ገባሁ። ትዝ ሲለኝ አልተሳለምኩም፤ ተመልሼ ግራ ቀኝ በሩን ተሳለምኩ። ዘው
አይባልም ዘሎ፤ ፈጣሪ የተጎዳ ልቤን ቢመለከትም ቅሉ እዚህ ድረስ ልብ ውልቅ መሆኔ ለኔም ደግ አይደል ወደ ውስጥ ስገባ የቤተክርስቲያኑ ድባብ፣ የቤተመቅደሱ ወፋፍራም የጣውላ ከፈፎች ላይ የሰፈሩት ዋነሶች፣ እድሜ ጠገቦቹ ዛፎች፣ ከምንም በላይ ደግሞ ዝምታው ከውስጥ ብሶቴ ተዳምሮ አጃዬን አመጣው። ከምርም የሰው ልጅ ምናምኒት አቅም እንደሌለው የሚያውቅበት የሆነ ጭብጦ ነገር መሆኑን የሚረዳበት ቦታ ሲኖር ቤተክርስቲያን ይመስለኛል።

ፈጣሪን ምን ማለት እንዳለብኝ ግራ ገባኝ። ታቆምልኛለህ ወይስ አታቆምልኝም…” ከይባል ነገር። ቆይ ግን ከዘፍጥረት ጀምሮ በዚህ ጕዳይ እግዜር ፊት ቆሞ የፀለየ ሰው ይኖር ይሆን ? በሐሳቤ ስቀላምድ ቆየሁና ዞር ዞር ብዬ አካባቢዩን ቃኘሁ። ከእኔ ወደ ግራ ሲል ቢጫ ልብስ የለበሱ መነኩሴ ተቀምጠዋል።ምን እንደገፋኝ እንጃ ወደሳቸው ገሰገስኩ፤ ምናልባት እዛው እንደ ደንቡ እግዜርን በሚያዝንበት ቋንቋ
ቢያናግሩልኝ ብዬም እንደሆን እንጃ ! አጠገባቸው ስደርስ፣

“አባ " አልኳቸው።

"አቤት የኔ ልጅ፣ እንደምን ዋልክ” አሃ !ለካ ሰላምታም ነበር።

"ጓደኛዬ ልትመጣ ሦስት ቀን ቀራት፤ ከመቀሌ ከሦስት ቀን በኋላ ትመጣለች፤ ሙና ነው ስሟ
ሦስት ቀን ብቻ ቀና ብለው በእርጋታ አዩኝና ከጎናቸው ያለውን ግንድ መቁጠሪያ በያዘ እጃቸው
እያመሰከቱኝ፣

"ና እስቲ እዚህ አረፍ በል የኔ ልጅ” አሉኝ።

“አይ እሄዳለሁ" ብያቸው ያመለከቱብኝ ቦታ ላይ ተቀመጥኩ። (ሁለት ሰው የሆንኩ መሰለኝ፤)
የምናገረው ሌላ የማደርገው ሌላ

“ምን ሆነህ ነው የምታለቅስ ልጄ” ቢሉኝ እጄ ወደ ዓይኔ ሄደ አይገርምም ? እየተነፋረቅኩ ነበረ
ለካ፡ እንባዩን በእጄ ሞዥቄ አባን የሆነውን ሁሉ ነገርኳቸው። አቤት መስማት ሲችሉበት

በጥሞና ሲሰሙኝ ቆይተው፣ "የኔ ልጅ እግዲህ ዋናው ነገር … እግዜር የጊዜ አምላክ ነው፤ የሰውና የአግዜር አሰራር ልዩነቱ ይሄ ነው። ሰው የቻላትን ባሰኘው ጊዜ ያደርጋል፥ እግዜር ግን ሁሉን ይችላል የሚያደርገው ግን ለልጆቹ በሚጠቅመው ጊዜ በሚጠቅመው ልክ ነው። ካለጊዜው እንዲህ ያለው ነገር
ውስጥ እንዳትገባ ሊያስተምረህ ወድዶ ይሆናል አንድም ደሞ የምድር ጠቢባን ያቃታቸውን ሁሉ
የሚችል መሆኑን ሊገልጥልህ ሲወድ እንደሆነ ምኑ ይታወቃል ልጄ.."

"እና ምን ላርግ አባ፤ ሶስት ቀን ብቻ ቀራት እኮ"

“መምጣቷ መልካም ነው ! ታዲያ መውደድ ሲሞላ ብቻ አይደለም፣ ሲጎድልም እንጂ፤ መሳቅህን
ብቻ እያሳየህ በወዳጅህ ፊት ትልቅ አትምሰል ልጄ፡ ሰው ነህ ድከመት አለብህ፣ ድክመትህን ለራሷ ንገራት፤ እውነቱን ተናገር። የውሸትና ማስመሰል ዙፋን ከእንቧይ ገንብተህ ንገሽ ብትላት እሷንም ተንዶ ጉድ ይሰራታል፣ ላንተም ፀፀት ነው። የውሸት እና ማስመሰል ካባ ከነፍስ ከረምት፣ ከመንፈስም ቁር አያስጥልም፤ አትድከም! ግራ ቀኝም አትበል፤ እሷን ሸፋፍነህ ብታሳምናት ከራስህ ልብ የገባህው
አተካራ አያባራም። እውነቱን ንገራት፣ ከእውነት የበለጠ ፈውስ የለም የኔ ልጀ።”

"ከዛስ እባ ፤"

ከዛማ እውነት ከተናገርከ ሰውም ምክርም አያሻህ፤ እውነት ራሱ መንገዱን ይምራሄል።"ብለው ወደ
መቁጠሪያቸው አቀረቀሩ። ደህና ዋሉ ልበላቸው አልሰላቸው እንጃ ወደ ቤቴ ተመልሼ ጥቅልል ብዬ
ተኛሁ። እውነት መንገዱን ይመራሃል፤ እውነት ዋጋ ያስከፍላል ያውም ከነወለዱ። ከሆንስ ሆነና እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
እውነት ዋጋው ስንት ነው?
የቱንም ያህል ዋጋው ቢወደድ፣ በቃ ለሙና እውነቱን እነግራታለሁ። ወሰንኩ !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የቁርጥ ቀን!

እነሆ የተንኳኳ በሬን ከፈትኩ፤ ልብ የሚያቀልጥ የሙና ውበት ከወትሮው ሰባት እጅ ደምቆ በሬ ላይ ቆሟል። ሙናን አፈቅራታለሁ፤ ልለያት አልፈልግም። ሳያት ልክ ብርሃን ጨለማ ክፍልን ድንገት ቦግ ብሎ እንደሚሞላው ውስጤን የሚሞላው አንዳች ነገር አላት፤ እንደ ባዶ ፊኛ የሟሸሽ መንፈሴ ሙናን ሳያት በዓየር እንደተሞላ ባሉን በፍቅርና በደስታ ሕዋ ላይ ይንሳፈፋል። ይሄው የእውነት ዋጋው በሬ ላይ። እውነት ዋጋው ይሄን ያህል ውድ ነው። እቅጩን ተናግሬ የነፍሴን ግማድ ሙናን መክፈል፤አልያም ሰቆቃዬ ላይ ስሳቀቅ በየዕለቱ በማስመሰልና በሽሽት ሚስማር የፍርሃት ጉልላቴ ላይ መቸንከር።

በሐሴት የሚንሳፈፍ የነፍሴን ባሉን፣ ክፉ እሾህ ጠቅ አድርጎ ሊያተነፍሰው ወደኔ ሲወነጨፍም
እከላከልበት ዘንድ በእጄ ያለው መሳሪያ አባ ያስታጠቁኝ ጋሻ ብቻ ነው እውነት !! እውነቱን ተናግሬ
የመሸበት አድራለሁ። እስከመቼ የነገር አንጆ ሳመነዥክ ልኑር ? በቃኝ !!

ምን እንዳረጋጋኝ እንጃ በውስጤ "ሙና ብትሄድ ሺ ሙናዎች ይተካሉ” ስል ረጋ ብዬ ፎከርኩ። ላንዲት ሙና ያልሆንኩ እኔ ለሺ ሙና ስፎክር የሰማ ራሴ ቢታዘበኝም ግድ አልሰጠኝም። ፉከራ ከጀግንነት ብቻ ሳይሆን ጥልቅ ከሆነ ፍርሃትም እንደሚመነጭ የገባኝ ያኔ ነው።
ሙና በእቅፏ ሙሉ አፍሳኝ በሞቃት ከንፈሯ በናፍቆት ግጥም አድርጋ ስትስመኝ ነፍሴ ከተወዘፈችበት ኩርፊያ ተመንጥቃ ልትወጣ ተጣጣረች፤ ቢሆንም እንቅ አድርጌ ነፍሴን ያዝኳት። መቆጣት አለብኝ መኮሳተር አለብኝ። ሙና የሆነ ነገር ሆኗል ዛሬ ልለፈው" እንድትል የሆነ ነገር የሆንኩ መምሰል አለብኝ። ተሸከማ የመጣችውን እሳት በቁጣ ውኃ በር ላይ ማጥፋት፡ መደርገም አለብኝ። ቦርሳዋን
ጠረጴዛ ላይ ወርወር አደረገችና በናፍቆት አንዴ ቤቱን ከእግር እስከ ራሱ ዙሪያውን ቃኝታ በረዥሙ
ተነፈሰችና ለሞላ ቦታ መጥታ ጉልበቴ ላይ ተቀመጠች። ደረቷ ላይ አስጠግታ አቀፈችኝ ለሞላ
የሰውነት ክፍል ፀጉሬን ሳመችኝ።

“ፀጉርህ አድጓል” ብላ በጣቷ መንጨር መንጨርጨ አደረገችኝ። ወይ ነዶ ልጅቱማ የፍቅር ሰው
ነበረች፤ ካለቦታው ተከሰተች እንጂ። ተነስታ ወደ ውስጥ ገባችና የእኔን ቁምጣ ለበሰች፤ ቁምጣ የተሰራው የሙና ዓይነት እግር ላላቸው ሰዎች ይመስለኛል። የእኔን ቲሸርት ለበሰች፤ ቲሸርት
የተፈጠረው የሙና ዓይነት ጡት ላላቸው ሴቶች ብቻ ይመስለኛል። ከዛም ወደ ኪችን። ዝም ብዬ
አያታለሁ፤ ፊቷ ላይ ምንም ነገር የለም፤ ረጋ ያለ ለስላሳ ፊት፤ ትረጋጋ እንጂ እሷ ምን አለባት
የመጣው ቢመጣ ሁሉ በጇ፣ በአንድ እይታ ብቻ ወደ እሳት ነበልባልነት የሚለወጥ አረር ሰውነት ምን አስጨነቃት።

እያጠናኋት ነበር፤ መለያየታችን እንደማይቀር አንድ ነገር ሹክ ስሳለኝ እድሜ ልኬን እንዳልረሳ
እያጠናኋት ነበር። ሙናን መቼም ቢሆን መርሳት አልፈልግም፣ ፍቅረኛዬ ስለሆነች አይደለም
በሕይወት ውስጥ የመሰላል እርካን ሆነው አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርጉን ሰዎች አሉ፣ ሙና እንደዚ ናት ለእኔ። ምን ያህል ልትናፍቀኝ እንደምትችል አሁን ላይ ሆኜ አውቀዋለሁ። ዝም ብዪ አያታለሁ ድንገት ዞር ስትል ዓይናችን ተገጣጠመ ሳቀች። ፍፁም ገራገር እና ንፁህ ፊት። እኔ ግን ደነገጥኩ፡ ወይ ጉድ፡ ሰው በሰላም አገር እንደ ሌባ ደንጋጭ ሆኖ ይቀራል ?!
👍36🥰21
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ሰባት


#በአሌክስ_አብርሃም


....“አብርሽ እንቅልፌ መጣ” አለች ትልልቅ ውብ ዓይኖቿን እያንከባለለች (አሄሄ እንቅልፍ ሲመጣ እንደዚህ ነው እንዴ ?
ይህቺ አይነቷ መስለምለም የሌላ ጉዳይ ናት)

“ትንሽ እናውራ ናፍቀሽኛል”

“ከመቼ ጀምሮ ነው ወሬ የወደድከው ግን ?" አለችኝ። ትዝ ሲለኝ ለካ ለሙና ዝምተኛ ልጅ ነበርኩ
(ስምንተኛው ሺ አሉ እኚያ ሰውዬ)። እጄን ይዛ እየጎተተች ወሰደችኝ። መኝታ ቤት እንደገባን መሀል ሜዳው ላይ ቆማ ልብሷን በቁሟ ብትጥለው ማታ እኔ መኝታ ቤት ፀሐይ ፏ ብሎ ወጣ። ፀሐይ
ከምስራቅም ከምዕራብም ሳይሆን፣ በቃ ከልብስ ውስጥ ፍንትው ብሎ ወጣ። እስቲ አሁን እዚህ ፀሐይ ላይ ቆሞ የማይፍታታ ወንድ የት አባቱ ሄዶ ሊፍታታ ነው ? ሲጀመርስ ምናባቱ ሊሰራ ወደዚች ምድር መጣ ? ቀስ ብዬ ልብሴን ማወላለቅ ጀመርኩ። አወላለቄ ከመንቀርፈፉና ከፍርሃቴ ብዛት፣
“ልብስህን አውልቅና አርባ ጅራፍ ትሞሸለቃለህ” የተባልኩ እንጂ ውብ ፍቅረኛዬ ጋር ልተኛ የምዘጋጅ አልመስልም ነበር። የአልጋ ልብሱን ወደታች ገፈፍኩት፣ ብርድ ልብሱን፣ አንሶላውን፣ መቃብሬን የምቆፍር ነበር የመሰለኝ።
ቀስ ብዬ አንሶላዬ ውስጥ ገባሁና (ሙና ገና ከመግባቴ እንደ መዥገር ተለጠፈችብኝ ምን አስቸኮላት ለመርዶ) አንሶላና ብርድልብሱን ወደላይ ስቤ ስደርብ የመቃብር አፈር በላዬ ላይ የመለስኩ መሰለኝ።

“ውይ አፈንከኝ የተሸፋፈንበትን ብርድ ልብስ ገለጠችው፡፡ ገብቶኛል በነዛ ዓይኖቿ እየተስለመለመች የፈራሁትን አጀንዳ ልትከፍት ነው። ተንጠራርቼ መብራቱን አጠፋሁት፤ ትልቅ ስህተት ! ሙና መብራት ሲጠፋ በብርሃን የፈራሁትን በጨለማ ልዘምትበት መስሏት የበለጠ ተጠጋችኝ፡፡ ሰውነቴ ላይ
ከመጠበቋ ብዛት ሁለት ሰውም እንድ ሰውም ሳይሆን ግማሽ ሰው መሰልን። አንድ እግሯን ታፋዬ
ላይ ደርባ ተጠመጠመችብኝ። አሁን እንግዲህ .. አርማጌዶን !!

እና ለምን እንደምወድህ ሳልነግርህ አረሳሳኸኝ ሙና በጨለማው ውስጥ አንሾካሾከች።
“ለምንድን ነው ?"
እርጋታህ ! ማንም ወንድ እዚህ ድረስ ይታገሳል ብዬ አስቤ አላውቅም። ሰምቼም አላውቅ። ልዩ እኮ ነህ አብርሽ … እሟ” (ምኔን እንደሳመችኝ እኔጃ) እኔኮ ግራ የሚገባኝ ካለሥማችን ስም እየሰጡ ለምን ጨዋ ያደርጉናል ?! ኧረ የቸጎረቸግሮን ነው ቀዝቀዝ ያልነው(እስካሁን አገር ሰላም ቢሆን በሩጫ ሞያሌ
ደርሰን ነበር አሉ ጋሽ ምትኩ)። ስለጋሽ ምትኩማሰብ ጀመርኩ። ጋሽ ምትኩ በሕፃንነታችን ሰፈራችን ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የድሮ ወታደር ናቸው። ቆይ ግን ጋሽ ምትኩ የፂማቸው አበቃቀል አይገርምም? ልክ እንደ ፍየል ፂም ሹገጥ ያለች ሆና ደረታቸውን ትነካለች። ጋሽ ምትኩ እኮ በሕፃንነቴ ከእማማ ሊባኖስ ፅድ ላይ ወድቄ የግራ ክንዴን ተሰብሬ አሽተው አድነውኛል፡፡ የግራ ከንዴ ስል ትዝ አለኝና ላነሳው ስሞክር ሙና ተኝታበታለች። ሙና ትዝ አለችኝ። አሁንም እንገቴን እየሳመችኝ ነው። ሙቀቱ
ውቀት አይደለም፡፡ እሳት ተነስቷል እዚህ ብርድ ልብስ ውስጥ፡፡ (ደመዟን የሚከፍሏት እሳት ነው
እንዴ፤ አጠራቅማ ይዛው መጥታ ይሆን…)

ቆይ ግን የዓለም ሙቀት መጨመር ... ብዬ ሌላ ሐሳብ ውስጥ ልገባ ስል ድክ…ም ባለ ድምፅ የሆነ መካከለኛው አፍሪካ አካባቢ ቆማ ስሜን የጠራችው እስኪመስለኝ በራቀ ድምፅ…

“አ..ብርሽ” አለችኝ።

“አብርሽ የለም ! አሁን ወጣ” ማለት አምሮኝ ነበር።

“እወድሃለሁ" ውይ !ይሄ ሁሉ ጥሪ ለዚች ነው ? ብዬ መውደዷን ለመንኳስስ ብሞከር አልተሳካልኝም።
እኔም እንደ ራሴ ነው የምወድሽ ሙና” ብዬ ዓየር እስኪያጥራት ከንፈሯን ሳምኳት። እግሯ ተንቀሳቀሰ (ወዴት ነው…ባለህበት ቁም ብያለሁ የሙና ግራ እግር !) እንግዲህ ፊት ሲሰጧቸው…
በእንግሊዝኛ እንዲህ አለችኝ፣
'አር ዩ ሬዲ ?” እንደው አማርኛችን ወሲብ ላይ ሐሞቷ የሚፈስሰው ለምንድን ነው ? ወሲብ ነክ
ላይ እንግሊዝኛ ይቀለናል። “ሴክስ” “ኪሲንግ" ቋንቋችን መከበር አለበት !በራሳችን ቋንቋ የራሳችንን ጉድ ማውራት አለብን ! የራሱ ጉዳይ ... ! አሁን በዚህ ሰዓት አማርኛ ፤ ምንኛ ላይ
ምርምር ምን የሚሉት ፈሊጥ ነው ?ቁም ነገሩ በአማርኛ ይሁን በእንግሊዝኛ ይሁን በጀርመንኛ ወላ በእብራይስጥ ትናገረው እኔ እንደሆንኩ እንትን ላይ የለሁበትም !!
እንግዲህ ሙና ከመጠጋቷ ብዛት እልፉኝ ሙሄድ ቀራት፣ እኔ ዝም!
ሳመችኝ
ዝም
ነካካችኝ
ዝም
አፍ አውጥታ “በቃ እናድርግ" አለች
ዝም!
በመጨረሻ ሰውነቷን ከሰውነቴ ቀስ እድርጋ አላቀቀች። ሰውነታችን ሲላቅቅ ፕላስተር ከሆነ ነገር ላይ
ሲላጥ የሚያሰማውን ዓይነት ድምፅ አሰማ። በላባችን አጣብቆን ነበር፡፡ ምንም ላልተፈጠረ ቅጡ ይሄ
ሁሉ ላብ በከንቱ። ሙና ተንጠራርታ መብራቱን አበራችውና ቀጥ ብላ ፊቴን ተመለከተችኝ አቤት ስታስፈራ፡ አቤት ስታምር..

ምንድን ነው የሆንከው ስለኔ የሰማኸው መጥፎ ነገር አለ ?አለችኝ በሚንቀለቀል ቁጣ። ዝም ብዬ አየኋት። ዝም ብላ አየችኝ። ፊቷ ላይ ግራ መጋባት ያሁን ፍርሃት ያልገባኝ ስሜት ያንዣብባል።

ሌላ ሴት ጋር ጀምረኸል አይደል ግልፁን ንገረኝ ?” ቁጣዋ ተንቀለቀለ። እኔ ደግሞ እፌ ተያያዘ ዝም፡
ብርድ ልብሱን በንዴት ገፍፋ ወደዛ ጣለችውና ቤቱን በሚያደበላልቅ ጩኸት፣

“ምንድን ነው ችግርህ፣ ለምን ትዘጋኛለህ … ላንተ እንዲህ መሆኔ ለሁሉም ወንድ እንደዚህ የምሆን
ልክስክስ እንድመስልህ አድርጎህ ነው ወይስ … ለምን ትገፋኛለህ፣ ለምን ዝቅ አድርገህ ታየኛለህ
አንድ ቀን እንደ ሰው፣ እንደ ፍቅረኛ አይተኸኝ አታውቅም። ሁልጊዜም ሴትነቴን፣ ከብሬን ዝቅ አድርጌ ላንተ ነው የኖርኩት። ስንት እና ስንት ርቀት ተሰቃይቼ የምመጣው አንተን ብዬ ምንድነው ችግርህ ንገረኝ፣ አስጠላሁህ ? ያስቀየምኩህ ነገር አለ ? ለምንድነው እንደዚህ ቅዝቅዝ
የምትለው ? ችግር ካለ ንገረኝ። ልርቅህ አልፈልግም፡ አፈቅርሃለሁ … አፈቅርሃለሁ ... አፈቅርሃለዉ
እንባዋ ተዘረገፈ። ከወገቤ በላይ ራቁቴን እንደሆንኩ አልጋው ላይ ተቀመጥኩ። ሙና ሁሉም ሰውነታ
ተራቁቶ ነበር። የአልጋ ልብሱን ላለብሳት ስምከር ከነእጄ ወደዛ ወረወረችው፤ ፈራኋት። ተፋጠጥን!

አሁን ነው ጊዜው!እውነት እርቃኗን አልጋ ላይ ይቻት ይህ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ወሳኝ ጊዜ ነው። አለ አይደል ላይመለሱ በስደት ከአገር ሊወጡ ዞር ብለው ተራራ ሸንተረሩን፣ ያደጉበትን ሰፈር የሚመለከቱባት ቅፅበት። ሙና ለእኔ ሰፈሬ ናት፤ ፍቅር እየተራጨሁ ፍቅር ያደግኩባት። አለ አይደል የደከመች እናት በመጨረሻ እስትንፋሷ ከአልጋ ላይ ሽቅብ ልጇን ተመልክታ በተስፋ መቁረጥ ዓይኖቿን የምትጨፍንበት፣ አለ አይደል አብሮን የተፈጠረ አብሮን ያደገና የኖረ እግር፣ እጅ በሆነ በሽታ ምክንያት ሊቆረጥ የመጨረሻው ማደንዘዣ ሲሰጥ … ይሄ ጊዜ ያ ሁሉ ነው። በዚህች ቅፅበት ሴት
ብትሄድ ሴት ትተካለች አይባልም። ሙና ሴት ብቻ አይደለችም። ማንም ሴት ላፈቀራት ወንድ መልዓክ ምትሆንባት ነጥብ አላት። “ማንም ሴት በአካል የማይደገም ግልባጯን ልብ ላይ የምታትምበት ቅፅበት አለ፡ ጣጣ የለኝም የሚለውና የምትለው ሰዎች ሁሉ ጣጣ የሚኖርባቸው፡ ውጋት የሚለቅ ቅፅበት አለ ይሄው ያ ቅፅበት።.

ሙናን ወደኔ ስቤ ከንፈሯን ሳምኳት። የሆነ በቀል የሚመስል አሳሳም። ልቧ ሳይፈራ አልቀረም።
በፍርሃት አየችኝ። ፊቴ ላይ ምን እንዳየች እንጃ።

"ሙና"

"ወዬ አብርሽ” ፈርታለች። ለምን እንደፈራች አላወቅም። ብቻ እንድ ነገር መኖሩን የጠረጠረች
ይመስለኛል።
👍42
#ቀስ_ብሎ_ይቆማል


#ስምንት (የመጨረሻ)


#በአሌክስ_አብርሃም

...“ቆይ አብርሸ ምንድን ነው … ማለቴ…ተወው በቃ” ግራ ተጋባች። እናም እንዲህ አለችኝ፣ ችግር የለውም እንዳታስብ፣ ምንም ነገር እንዳታስብ !” ስትናገር ዓይኔን ማየት ፈርታ ነበር።እጆቿ እነዛ ቆንጆ
ጣቶቿ በሆነ ፍርሃት ሲንቀጠቀጡ ይታዩኛል። ብርድ ልብሱን ከጎኔ ገልባ ሸርተት ብላ ገባች።
ወዲያው ተመልሳ ተነሳችና የሌሊት ልብሷን ከትራስጌ በኩል አንስታ ለበሰች፤ ተመልሳ ተኛች። ድንብርብሯ ወጥቶ ነበር። በብርድ ልብነስ በታፈነ ድምፅ ችግር የለውም” እለች እንደገና።..

“ሙና” አልኳት ጀርባዋን ሰጥታኝ ነበር የተኛችው። ልክ ሰይጣን የጠራት ይመስል ድንግጥ ብላ፣

“እ” አለችኝ። ድንጋጤዋ እኔንም አስደነገጠኝ።

“ይቅርታ እስካሁን ስላልነገርኩሽ"

“ችግር የለውም ! ይሄ ማንንም ሊያጋጥም የሚችል ነገር ነው እንተኛ።” አነጋገሯ ምንም ለዛ የሌለው የሽሽት ይመስል ነበር፤ ዝም ላለማለት ያህል። ተኛች፤ እንቅልፍ የወሰዳት መሰለኝ። ልነካት ፈራሁ።የሆነ አተኛኘቷ ራሱ ትንሽ ከሰውነቴ ራቅ የማለት ነገር ነበረበት። ይሰማኛል እባብ የሆነ ነፋስ በመሐላችን በተፈጠረ ሰርጥ መለያየት ሲሳብ …

ተነስቼ ከአልጋዬ አጠገብ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ። ከፊቴ ትንሽ ጠረጴዛ አለች፤ መፃፍ ሲያምረኝ ከምኝታዬ ተነስቼ የምፅፍባት። ለምን ያህል ጊዜ እንደተቀመጥኩ እኔጃ፤ ሙና በእንቅልፉ ስትንቀሳቀስ ብርድ ልብሱ ተንሸራትቶ ግማሽ አካሏ .ተራቆተ። ህልም የሚመስል ቀይ ሰውነት፣ ከውስጡ ብርሃን የሚያመነጭ ሙልት ያለ ሰውነት፤ ውብ ሰውነት። በዚህች ቅፅበት ውስጤ በቅናት አረረ። የማላየው የወንድ እጅ እዚህ ሰውነት ላይ ሲያርፍ አሰብኩ። የሙና ሰውነት የደረቀ መሬት መስሎ ተሰማኝ። ውሃ የናፈቀ፡ የተቃጠለ፣ ማንም መቼም ሲዘንብበት ምጥጥ የሚያደርግ ምድረበዳ።

ዝም ብዬ አያታለሁ። ልቤ ታፍኗል። መረረኝ፣ ሕይውት አስጠላኝ። ሙና ስዕል ብትሆን ብዬ ተመኘሁ። የትም የማትሄድ፣ ለዘላለሙ እዚህ ተቀምጬ የማያት ስዕል፣ የምትታይ ብቻ። የስዕል፣የግጥም፣ የዘፈን የሁሉም ጥበብ መነሻ አለመቻል መሆኑ የገባኝ እዚህች ነጥብ ላይ ነው። ሰው አለመቻሉን ሲገልፅ መግለጫው መንገድ ላይ ይጠበብና ጥበበኛ ይባላል። ሰው በአካል ያልደረሰበትን ጥግ
ነው በጥበብ እጆቹ ተንጠራርቶ ለመንካት የሚፍገመገመው።

ሙና ተንቀሳቀሰች። ብርድ ልብሱ ሙሉ ለሙሉ ወደ እንድ ጎን ተሰበሰበ። በስስ የሌሊት ልብስ፣
ሰውነቷ ፍም መስሎ ቀልቷል። እዛጋ ሆና እዚህ ያለሁ እኔን ወላፈኗ ፈጀኝ። እንቁልልጭ የምታጣትን ልጅ ተመልከት.. እንዴት ውብ እንደሆነች እይ” የሚለኝ ሰይጣን ጭንቅላቴ ውስጥ የተቀመጠ መሰለኝ።

እየኋት …. ትክክከከ ብዬ አየኋት። ሕሊናዬ ትልቅ ሸራ ሆኖ መንፈሴ በማይጠፋ ቀለም ሙናን እየሳለ
ነበር። ልቤ ትልቅ ብራና ሆኖ ሙናን እየፃፋት ነበር። ከወንበሬ ተነስቼ የሙናን የእግር ጣቶች ተራ
በታራ ሳምኳቸው፤ አስሩንም። የተለኮሰ የሲጋራ ጫፍ የሳምኩ ይመስል የእግሮቿ ጣቶች ከንፈሬ ላይ ረመጥ ሙቀታቸውን አተሙት። ደግሞ የእግሯ ልስላሴ ! ወደ ቦታዩ ተመለስኩ። ብርድ ልብሱን አላለበስኳትም፤ ላያት ፈልጌያለሁ።

ወንበሬ ላይ ቁጭ ብዬ ሙናን ስመለከታት የገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ግጥም ልክ ጎረቤት እንደተከፈተ ዓይነት ከነድምፁ ጥርት ብሎ እንደ ጅረት ውኃ አዕምሮዬ ውስጥ ይፈስስ ጀመረ። ያውም በዓይኖቼ ሞልቶ በሚፈሰስ እንባዬ ታጅቦ። #ሶልያና የእኔ ኑዛዜ - የግጥም አልፋና ኦሜጋዬ … እያንዳንዱ ግጥም የኑሮ ዝባዝንኬ ድንጋዩን ቢጭንበትም አለ ጊዜ እንደ ከርሰ ምድር ውኃ የሚፈነዳበት። ገጣሚው እዚህ ተቀምጦ ሙናን እየተመለከተ የፃፈው እስኪመስለኝ፣ ሶሊያና የሙና የቤት ስሟ፣ የመኝታ ቤት
ስሟ እስኪመስለኝ … ገጣሚው የእኔን ሙሾ በደረቀ ሌሊት አወረደው ….

ሶ ሊ ያ ና

እኔን ከወንበር ላይ፤
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ፣
ወረቀት ላይ ወስዶኝ ….
እርሷን ካልጋችን ላይ፣
እንቅልፍ አሽኮርምሟት፣
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት፣
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ፣
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ፣
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ፣
ከደጋው ሐሳቤ በረሃ ስሰደድ፣
እንባን በፊደላት፣
ፊደልን በቃላት፣
ቃላትን በሐሳብ፣
ወረቀት ላይ ልወልድ፣
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ፣
"የኔ ነሽ” የምላት ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል
“ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋዬ ላይ፣
አንተን መናፈቅ በስሜት ስሰቃይ"
ቀና ብዬ ሳያት እውነት አለው ቃሏ፣
ፍም መስሏል አካሏ፣
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል፣
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል፣
እኔን በመጓጓት ደሟ ተቆጥቶ፣
ፍቅሯ ተሰውቶ፣
ስሜቷ ተጎድቶ፣
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ሕፃን፣
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉሯ ሲበታተን፣
ካልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን፣
ፍ ቅ ሬ ሶሊያና አወራችኝ መሰል በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ…
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰት ዓለም፣
የሰዎች ጥላ እንጂ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ፣
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ፧
ሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ፣
እኔ ውበቱ ነኝ ለፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም... ወዲህ እንዳትመጣ፣
በሌሊት ትጋትህ ሐዘን ሳይቀጣ፣
በኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ፣
ከየሰዉ ዓለም የሚመሳለሉ፣
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ፣
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፉ፣
ይህ ሁሉ ቢሆንም
የሰዎችን እንባ
አትፃፍ ግዴለም፡
የፍጥረትን ሐዘን ስለህ አትዘልቅም፣
እውነት እለው ብለህ ሐዘንን አታልም፣
((ያለቀሱም ሰዎች ሐቀኞች እይደሉም}
ይልቅ የኔን ስሜት፤
ያንተንም እንባዎች ሁለቱን አሳየኝ፣
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ ! እኔን ብቻ ፃፈኝ !
“ያልተደሰተች ሴት” በሚል መጽሐፍህ
ዘ ላ ለ ም አሻግረኝ፣
ዘ ላ ለ ም ውሰደኝ፣
ዘ ላ ለ ም አኑረኝ !!”
“የኔ ነሽ” የምላት፣ “ያንተ ነኝ የምትል፣
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ መሃል።


ቁጭ ያልኩበት ወንበር ላይ እንቅልፍ ወሰደኝ…

ሊነጋጋ ሲል….
“አብርሽ” የሙና ድምጽ እንደ ህልም ተሰማኝ። ዓይኖቼን ስገልጥ ፊቴ ቆማ ነበር። ልብሷን ለባብሳ፣አንድ እርምጃ የሚሆን ከእኔ ራቅ ብላ ቆማ ነበር። ሙና ስትቀሰቅሰኝ እንዲህ አልነበረም፡፡ ከተኛሁበት የምትቀሰቅሰኝ በከንፈሯ ነበር። በተኛሁበት ስትስመኝ ነበር የምነቃው። እና እዛጋ ምን አቆማት ፣
ሁሉን እንቅልፍ ባስረሳው በደበዘዘ አዕምሮ አያታለሁ።
“ተነስ ቁርስ ሰርቼልሃለሁ”
በዝምታ እንቁላል ፍርፍር በላን፣ ሻይ ጠጣን፤ (በዝምታ) ዕቃዎቹን አነሳስታ አጣጠበች እና መጥታ
ጎኔ ተቀመጠች። ሁለታችንም በአስፈሪ ዝምታ ውስጥ በዝምታ እንደተቀመጥን ድንገት የሙና እንባ ተዘረገፈ፤ እናም አቀፈችኝ። ከሙና እንዲህ ዓይነት ጉልበት ያለው አስተቃቀፍ አልጠበቅኩም ነበር።
👍251🥰1