#ያንቺው_ጉረኛ
አነጋገሬ የሰለጠነ
እረማመዴ የተመጠነ
ስደሰት ፊቴ፣ የግዚሀር ባውዛ
ስስም ከንፈሬ፣ ያበባ ጤዛ
ካለት ያወጋሁ፣ ከንብ የተጋሁ
እንደ ዘንገና፣ ውሃ የረጋሁ
ከጎህ ቀድሜ፣ ባይንሽ የነጋሁ።
ባስብ በመላ፣ ብናገር እውነት
ባቅፍሽ ክንዶቼ፣ የሐር መቀነት።
ጣትሽ ደባብሶኝ፣ ጥፍርሽ ቢበጣኝ
ዘቢብ ነው እንጂ፣ መች ደም ሊወጣኝ
ለምድር ቢቀርብ፣ ቁመቴ ቢያጥር
በጎልያድ ግንባር፣ የማነጣጥር
ልቤ በጣቱ፣ ሰማይ ሚነካ
ከነራስ ደጀን፣ ከንጦጦ የካ
ቁመት በኩራት፣ የሚለካካ
ብትደገፊኝ፣ የላባ ፍራሽ
ብትመገቢኝ፣ የመና ቁራሽ።
እንኳን በጃኖ፣ እንኳን በሱፉ
እንደ ቁጥቋጦው፣ ልክ እንደዛፉ
ቅጠል ለብሼ፣ የምሽቀረቀር
የተለጋ ልብ፣ ቀልቤ ማስቀር
ያንቺው በረኛ
ያንቺው ቁንን ነኝ፣ ያንቺው ጉረኛ።
አነጋገሬ የሰለጠነ
እረማመዴ የተመጠነ
ስደሰት ፊቴ፣ የግዚሀር ባውዛ
ስስም ከንፈሬ፣ ያበባ ጤዛ
ካለት ያወጋሁ፣ ከንብ የተጋሁ
እንደ ዘንገና፣ ውሃ የረጋሁ
ከጎህ ቀድሜ፣ ባይንሽ የነጋሁ።
ባስብ በመላ፣ ብናገር እውነት
ባቅፍሽ ክንዶቼ፣ የሐር መቀነት።
ጣትሽ ደባብሶኝ፣ ጥፍርሽ ቢበጣኝ
ዘቢብ ነው እንጂ፣ መች ደም ሊወጣኝ
ለምድር ቢቀርብ፣ ቁመቴ ቢያጥር
በጎልያድ ግንባር፣ የማነጣጥር
ልቤ በጣቱ፣ ሰማይ ሚነካ
ከነራስ ደጀን፣ ከንጦጦ የካ
ቁመት በኩራት፣ የሚለካካ
ብትደገፊኝ፣ የላባ ፍራሽ
ብትመገቢኝ፣ የመና ቁራሽ።
እንኳን በጃኖ፣ እንኳን በሱፉ
እንደ ቁጥቋጦው፣ ልክ እንደዛፉ
ቅጠል ለብሼ፣ የምሽቀረቀር
የተለጋ ልብ፣ ቀልቤ ማስቀር
ያንቺው በረኛ
ያንቺው ቁንን ነኝ፣ ያንቺው ጉረኛ።
#ንቀን_ያለፍነው_ቃል
ከለታት አንድ ቀን፣ ወደ ቤቷ ሄድኩኝ
ጥቅል ጎመን አርዳ፣ እንጉዳዩን ጠብሳ
ጋበዘችኝ ምሳ
ሙያዋን አደነቅሁ
ገበታው ሲነሳ
ካያቷ ተዋወቅሁ።
አረጋዊት ናቸው፣ እድሜያቸው የገፋ
ድሮ ልጅ እያሉ፣ አይናቸው የጠፋ
በድሜያቸው በረካ፣ በፅዋቸው ጭላጭ
አምሯቸው ብሩህ፣ ልሳናቸው ምላጭ
ወግ ማውጋት ጀመሩ
ቃል እያለዘቡ
ቃል እየጠረቡ፣ ቃል እያሳመሩ
ሀረግ አለዝበው፣ ዘይቤ እየነቀሱ
በጸጥታ ሞቶ፣ ያላጀብ ተቀብሮ
የተረሳ ታሪክ እየቀሰቀሱ
እንደ መቅረፀ ድምፅ፣ ጆሮየን ጠመድሁት
አጥብቆ ገረመኝ
ያረጋዊቷ ወግ፣ ቅድም ከበላሁት
ከንጉዳዩ ዝልዝል፣ የበለጠ ጣመኝ።
ጸሐፌ ትዛዛት ቸል ብለው ያለፉት
ዜና ነጋሪዎች፣ አይተው የገደፉት
ያገሬን ሰው ገድል፣ መከራ ፍስሐ
ሳልታክት ቀዳሁት፣ ልክ እንዳርብ ውሃ።
ከጥሞናየ ላይ ላፍታ ተፋትቼ
ጋባዤን ፈለግኋት
ፊትለፊቴ አየኋት
ያቻት ያቻትና
ከሶፋው ላይ ሆና
እግሮቿን ዝርግትግት፣ ሰውነቷን ዘና
እንደፊት መስተዋት
ዘመናይ ሞባይሏን፣ ፊቷ ስር ደቅና
ከስልኳ ሰሌዳ፣ ፊደል ትነካለች
ፎቶ ታምሳለች፣ ኢሜል ትልካለች
ያያቷ ጣፋጭ ወግ፣ ላፍታ እንኳ መች ደንቋት
ሜሴንጀር ዋትሳፕ፣ ኢሞ ቴሌግራም
ሁሉን የወሬ ቋት
ትበረብራለች፣
ካሥር አመት በፊት
ለረፍት ከከተማ፣ ወደ ገጠር ሄጄ
ደጅ ላይ ማለዳ፣ ፀሐይ ስር ተጥጄ
አያቴ ብቅ ብሎ
ከተቀመጥሁበት የወይራ ግንድ ላይ፣ ራሱን አዳብሎ
“ያኔ ጎበዝ ሳለሁ” ብሎ ወግ ሲወጥን
አልባሌ ወሬ፣ እኔን የማይመጥን
የሰማሁ ይመስል፣ በኀይል አዛግቼ
ከካፖርቴ ኪስ ውስጥ፣ መጽሐፍ አውጥቼ
(የማርክስ፣ የፍሮይድ ምናልባት የኒቼ?)
ገለብ ገለጥ ሳደርግ፣ እሱ ይህን አይቶ
የጀመረውን ቃል፣ አንጠልጥሎ ትቶ
ለጥናት ነው መሰል፣ እዚህ መቀመጥህ፣
ወግድልኝ በለኝ፣ እንዳልበጠብጥህ”
ብሎ ይወገዳል
አድማጭ ካጣጭ ጋራ ወደሚገኝበት፣ ጠላ ቤት ይሄዳል።
አያቴ ከሞተ፣ አመታት አለፉ
ፀፀት ጭንቅላቴን፣ በብረት መዳፉ
እየኮረኮመኝ
ሀፍረት በሸኮናው፣ እየረመረመኝ
በራሴ ስበግን
ምን ሆኘ ነበር ግን
ምን ነክቶኝ ነበር ግን?
በማለት አጥብቄ ራሴን ስረግም
ይሄውና ዛሬ
ጋባዤን አየኋት፣ ታሪኬን ስትደግም።
አንድም በመሰልቸት፣ አንድም በቸልታ
ወይ ባወቅሁሽ ናቅሁሽ፣ አለያም በወረት
የያዝነውን ዳቦ፣ ቆጥረነው ከኮረት
ጠላ ከሚጠጣ፣ ቆሎ ከሚበላ
እድፍ ከሚለብሰው
ለዐይን ከማይሞላ
ካንድ ስም አልባ ሰው
ምን ጥበብ ይገኛል? በሚል ተዘናግተን
በቻይና ቅፅር ጡብ፣ ጆሯችንን ዘግተን
ልቦና ቆልፈን
ንቀን ያለፍነው ቃል፣ ንቆ ነው ያለፈን።
#ክብር_ለአያቶቻችን_ለተንቀሳቃሽ #ላይብሬራችን
ከለታት አንድ ቀን፣ ወደ ቤቷ ሄድኩኝ
ጥቅል ጎመን አርዳ፣ እንጉዳዩን ጠብሳ
ጋበዘችኝ ምሳ
ሙያዋን አደነቅሁ
ገበታው ሲነሳ
ካያቷ ተዋወቅሁ።
አረጋዊት ናቸው፣ እድሜያቸው የገፋ
ድሮ ልጅ እያሉ፣ አይናቸው የጠፋ
በድሜያቸው በረካ፣ በፅዋቸው ጭላጭ
አምሯቸው ብሩህ፣ ልሳናቸው ምላጭ
ወግ ማውጋት ጀመሩ
ቃል እያለዘቡ
ቃል እየጠረቡ፣ ቃል እያሳመሩ
ሀረግ አለዝበው፣ ዘይቤ እየነቀሱ
በጸጥታ ሞቶ፣ ያላጀብ ተቀብሮ
የተረሳ ታሪክ እየቀሰቀሱ
እንደ መቅረፀ ድምፅ፣ ጆሮየን ጠመድሁት
አጥብቆ ገረመኝ
ያረጋዊቷ ወግ፣ ቅድም ከበላሁት
ከንጉዳዩ ዝልዝል፣ የበለጠ ጣመኝ።
ጸሐፌ ትዛዛት ቸል ብለው ያለፉት
ዜና ነጋሪዎች፣ አይተው የገደፉት
ያገሬን ሰው ገድል፣ መከራ ፍስሐ
ሳልታክት ቀዳሁት፣ ልክ እንዳርብ ውሃ።
ከጥሞናየ ላይ ላፍታ ተፋትቼ
ጋባዤን ፈለግኋት
ፊትለፊቴ አየኋት
ያቻት ያቻትና
ከሶፋው ላይ ሆና
እግሮቿን ዝርግትግት፣ ሰውነቷን ዘና
እንደፊት መስተዋት
ዘመናይ ሞባይሏን፣ ፊቷ ስር ደቅና
ከስልኳ ሰሌዳ፣ ፊደል ትነካለች
ፎቶ ታምሳለች፣ ኢሜል ትልካለች
ያያቷ ጣፋጭ ወግ፣ ላፍታ እንኳ መች ደንቋት
ሜሴንጀር ዋትሳፕ፣ ኢሞ ቴሌግራም
ሁሉን የወሬ ቋት
ትበረብራለች፣
ካሥር አመት በፊት
ለረፍት ከከተማ፣ ወደ ገጠር ሄጄ
ደጅ ላይ ማለዳ፣ ፀሐይ ስር ተጥጄ
አያቴ ብቅ ብሎ
ከተቀመጥሁበት የወይራ ግንድ ላይ፣ ራሱን አዳብሎ
“ያኔ ጎበዝ ሳለሁ” ብሎ ወግ ሲወጥን
አልባሌ ወሬ፣ እኔን የማይመጥን
የሰማሁ ይመስል፣ በኀይል አዛግቼ
ከካፖርቴ ኪስ ውስጥ፣ መጽሐፍ አውጥቼ
(የማርክስ፣ የፍሮይድ ምናልባት የኒቼ?)
ገለብ ገለጥ ሳደርግ፣ እሱ ይህን አይቶ
የጀመረውን ቃል፣ አንጠልጥሎ ትቶ
ለጥናት ነው መሰል፣ እዚህ መቀመጥህ፣
ወግድልኝ በለኝ፣ እንዳልበጠብጥህ”
ብሎ ይወገዳል
አድማጭ ካጣጭ ጋራ ወደሚገኝበት፣ ጠላ ቤት ይሄዳል።
አያቴ ከሞተ፣ አመታት አለፉ
ፀፀት ጭንቅላቴን፣ በብረት መዳፉ
እየኮረኮመኝ
ሀፍረት በሸኮናው፣ እየረመረመኝ
በራሴ ስበግን
ምን ሆኘ ነበር ግን
ምን ነክቶኝ ነበር ግን?
በማለት አጥብቄ ራሴን ስረግም
ይሄውና ዛሬ
ጋባዤን አየኋት፣ ታሪኬን ስትደግም።
አንድም በመሰልቸት፣ አንድም በቸልታ
ወይ ባወቅሁሽ ናቅሁሽ፣ አለያም በወረት
የያዝነውን ዳቦ፣ ቆጥረነው ከኮረት
ጠላ ከሚጠጣ፣ ቆሎ ከሚበላ
እድፍ ከሚለብሰው
ለዐይን ከማይሞላ
ካንድ ስም አልባ ሰው
ምን ጥበብ ይገኛል? በሚል ተዘናግተን
በቻይና ቅፅር ጡብ፣ ጆሯችንን ዘግተን
ልቦና ቆልፈን
ንቀን ያለፍነው ቃል፣ ንቆ ነው ያለፈን።
#ክብር_ለአያቶቻችን_ለተንቀሳቃሽ #ላይብሬራችን
#የባከነ_ሌሊት
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኰከብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቆሜ
ቤተስኪያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ስር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ፣ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
“በዑራኤል ርዱኝ” ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ስር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ፣ ሲሻኝ ዶክተር ሆኜ
ወይ ምግባር አልሰራሁ
ወይ ጀብድ አልፈጸምኩኝ፣ ወይ ጽድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሊባከን ዝም ብሎ
እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ”
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋዬን ሳትሰብረው።
ወግ ቢጤ ምንጭሬ፣ ፈስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
እናትዋን ጨረቃ” የሚል ግጥም ሳልጽፍ።
አንዲት ሴት አዳሪ፣ ቺቺንያ መንገድ ላይ
ዕድሏ.ሰባራ ሰውነቷ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዘው የሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠብቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
ኧረ በናታችሁ በወላድ ማሕፀን
እህት የላችሁም?” ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው፣ በደሏ አንገብግቦኝ
ከኋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ፣ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ፣ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከኋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መካከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቴ ካልቻልኩ በሣቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳላረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለ ምንም ጣጣ ያለምንም ጸጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኰከብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቆሜ
ቤተስኪያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ስር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ፣ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
“በዑራኤል ርዱኝ” ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ስር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ፣ ሲሻኝ ዶክተር ሆኜ
ወይ ምግባር አልሰራሁ
ወይ ጀብድ አልፈጸምኩኝ፣ ወይ ጽድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሊባከን ዝም ብሎ
እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ”
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋዬን ሳትሰብረው።
ወግ ቢጤ ምንጭሬ፣ ፈስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
እናትዋን ጨረቃ” የሚል ግጥም ሳልጽፍ።
አንዲት ሴት አዳሪ፣ ቺቺንያ መንገድ ላይ
ዕድሏ.ሰባራ ሰውነቷ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዘው የሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠብቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
ኧረ በናታችሁ በወላድ ማሕፀን
እህት የላችሁም?” ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው፣ በደሏ አንገብግቦኝ
ከኋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ፣ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ፣ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከኋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መካከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቴ ካልቻልኩ በሣቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳላረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለ ምንም ጣጣ ያለምንም ጸጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።
#አህያ_ሆይ_ማረን
የዘራም አጨደ
ያጨደም አስገባ
ያስገባም ጋገረ
የጋገረም በላ
ከዚያ ምን ይመጣል
ፍርፍር ሆኖ ገብቶ፣ ፍግ ሁኖ ይወጣል።
በሸመታም ይሁን፣ በወራሪ ዝርፍያ
በሥርዐት ይሁን፣ በሽምያ በግፍያ
በግብርም ይድረሰን፣ ወይ በመቀላወጥ
የምንበላው ኅብስት፣ የምንጨልፈው ወጥ
ማለፍያው ሰርገኛው፣ ዶሮና ምስሩ
ወደታች ስንምሰው፣ ብዝበዛ ነው ሥሩ።
የርግማኑን ራስ፣ ሆድ ይዘን ተፈጥረን
መቸገር ሳያንሰን
ለጠበቃ አልባዎች፣ ሸክም አሸጋግረን
ከጥንት እስከዛሬ
ጭንቅህን በልሳን፣ ተርጉመህ ባትነግረን
ይቅር በለን በሬ
አህያ ሆይ ማረን!!
የዘራም አጨደ
ያጨደም አስገባ
ያስገባም ጋገረ
የጋገረም በላ
ከዚያ ምን ይመጣል
ፍርፍር ሆኖ ገብቶ፣ ፍግ ሁኖ ይወጣል።
በሸመታም ይሁን፣ በወራሪ ዝርፍያ
በሥርዐት ይሁን፣ በሽምያ በግፍያ
በግብርም ይድረሰን፣ ወይ በመቀላወጥ
የምንበላው ኅብስት፣ የምንጨልፈው ወጥ
ማለፍያው ሰርገኛው፣ ዶሮና ምስሩ
ወደታች ስንምሰው፣ ብዝበዛ ነው ሥሩ።
የርግማኑን ራስ፣ ሆድ ይዘን ተፈጥረን
መቸገር ሳያንሰን
ለጠበቃ አልባዎች፣ ሸክም አሸጋግረን
ከጥንት እስከዛሬ
ጭንቅህን በልሳን፣ ተርጉመህ ባትነግረን
ይቅር በለን በሬ
አህያ ሆይ ማረን!!
#ላባቴ
ስው ብቻ እይደለህም፥ ካፈር ወጥተህ ላፈር
መላክ ነህ፥ ሉሲፈር
ክብርህ ማንነትህ፥ ባመጽ የሚታፈር
የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዙፋን፥ በርጩማ የምትመርጥ፤
ያለ ባሕር ሰርጓጅ፥ ያለ ሙሴ በትር
በመታገሰ ብቻ፥ ባሕር የምትመትር
ካዘልከኝ ጀምሮ፥ እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጅ፥ ዝቅታውን ሳላይ
እንደንስር መጠቅሁ፥ እንደ ምሥራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን፥ እንደ ዳንቴል ሠራሁ፤
በርግጥ ድሀ ነበርክ
ከሰላምታ በቀር፥ የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፥ ሰውነትህ የክት፤
በርግጥ ድሀ ነበርክ፥ የነጣህ የጠራህ
ከጦር ሜዳ ይልቅ፥ ገበያ ሚያስፈራህ
ቤሳ ባታወርሰኝ፥ አወረስከኝ ትግል
የትም እንዳይጥለኝ፥ ሕይወት እንደ ፈንግል፤
አባዬ ብርሃን
አባ የምሥራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፥ እንደ ካባ ጎበር
አባቴ ባትሆን፥ ምን ይውጠኝ ነበር።
ስው ብቻ እይደለህም፥ ካፈር ወጥተህ ላፈር
መላክ ነህ፥ ሉሲፈር
ክብርህ ማንነትህ፥ ባመጽ የሚታፈር
የማትንበረከክ
የማትርመጠመጥ
ከባለጌ ዙፋን፥ በርጩማ የምትመርጥ፤
ያለ ባሕር ሰርጓጅ፥ ያለ ሙሴ በትር
በመታገሰ ብቻ፥ ባሕር የምትመትር
ካዘልከኝ ጀምሮ፥ እንኮኮ ጫንቃህ ላይ
ከፍታውን እንጅ፥ ዝቅታውን ሳላይ
እንደንስር መጠቅሁ፥ እንደ ምሥራቅ በራሁ
የገዛ ክንፎቼን፥ እንደ ዳንቴል ሠራሁ፤
በርግጥ ድሀ ነበርክ
ከሰላምታ በቀር፥ የማታበረክት
ነጠላህ መናኛ፥ ሰውነትህ የክት፤
በርግጥ ድሀ ነበርክ፥ የነጣህ የጠራህ
ከጦር ሜዳ ይልቅ፥ ገበያ ሚያስፈራህ
ቤሳ ባታወርሰኝ፥ አወረስከኝ ትግል
የትም እንዳይጥለኝ፥ ሕይወት እንደ ፈንግል፤
አባዬ ብርሃን
አባ የምሥራቅ በር
ገመና ሸሻጊ፥ እንደ ካባ ጎበር
አባቴ ባትሆን፥ ምን ይውጠኝ ነበር።
#ኖረሽ_እይው_በቃ
ጨለማ ነህ ብለሽ፣ እኔን ስትተቺ
ዘልለሽ አትጠግቢ፣ ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሀ-ጽጌ* ነው፣ አመት ሙሉ ላንቺ።
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
ለፍጥረት ሰቆቃ
ለጋ ነው አእምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
በየጎዳናሽ ላይ፣ አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፣ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ ፈልቶልሽ፣ አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፣ የብቻነት ሸከሙን።
አዎ
መፈቀር መታጀብ፣ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት፣ አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ንፋስ ማቀፍ
አንዳንዴ ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት፣ የማያልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
አንቺ ደስታ ወዳጅ!!
በለምለም አፀድ ውስጥ፣ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፣ እንደ ጣኦስ* ቀልማ
እንዳትሸወጂ፣ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ሕይወትም እንደጃርት፣ የሾህ ቀሚስ አላት።
ተድላም ከሀዘን ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሣቅ በስተጀርባ፣ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
ጨለማ ነህ ብለሽ፣ እኔን ስትተቺ
ዘልለሽ አትጠግቢ፣ ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሀ-ጽጌ* ነው፣ አመት ሙሉ ላንቺ።
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
ለፍጥረት ሰቆቃ
ለጋ ነው አእምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
በየጎዳናሽ ላይ፣ አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፣ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ ፈልቶልሽ፣ አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፣ የብቻነት ሸከሙን።
አዎ
መፈቀር መታጀብ፣ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት፣ አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ንፋስ ማቀፍ
አንዳንዴ ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት፣ የማያልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
አንቺ ደስታ ወዳጅ!!
በለምለም አፀድ ውስጥ፣ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፣ እንደ ጣኦስ* ቀልማ
እንዳትሸወጂ፣ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ሕይወትም እንደጃርት፣ የሾህ ቀሚስ አላት።
ተድላም ከሀዘን ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሣቅ በስተጀርባ፣ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
👍1
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች "የለውጥ ኩርባ" አለችው አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ ወይ ድርጊቱ የሚቀየርበት።ወደ አዲስ ምእራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት።
=========================
“ማታ ከማን ጋር ባድር ደስ ይልሃል?” ወሬዋ እንዲያምርላት እና የወሬው አካል እንደሆንኩ እንዲሰማኝ (አብዛኛውን ጊዜ አይደለሁም::) ስትፈልግ ጥያቄ ታስመስለዋለች እንጂ ከእኒ መልስ ጠብቃ አታውቅም፡፡ ዝም ብላ ነው የምታወራው የምታወራልኝን ነገር መስማቴን ብቻ ካረጋገጠች ያለእረፍት
ትለፈልፋለች። እራሷ ትጠይቃለች። እራሷው ትመልሳለች።
"ከፍቃዱ ጋር!"
“ፍቃዱ ማን ነው?” ስላት በእርሷ ላይ እንዲሰማኝ የምትፈልገው የባለቤትነት ስሜት የተሰማኝ መስሏት ነው መሰለኝ ደስ ተሰኝታ ወሬዋን አድምቃ ቀጠለች። የማይገባኝ ባህርይዋ ይሄ ነው፡፡
በእርሷ ላይ ባለመብት እንድሆን ትፈልጋለች። ሌላ ሰው አየብኝ፣
ነካብኝ ኸረ አሰበብኝ ብዬ ሁሉ ዘራፍ! ብል ደስ ይላታል፡፡
“አርቲስቱ ነዋ! መጀመሪያ ስንሳሳም ነበር። በቃ ሲስመኝ ሲስመኝ...
ሊስመኝ ቆየና ምን ብናደርግ ጥሩ ነው?” እንዲህ ብዙ ጊዜ ያለማሰሪያ የምትበትነው ፀጉሯ እየተርገበገበ እና በእጆቿ አየሩን እየቀዘፈች እየተቅጠበጠች ስታወራ መላ ሰውነቷ
ከመወራጨቱ የተነሳ ልትበር የምታኮበኩብ ነው የምትመስለኝ።
“ምንም ብታደርጉ ጥሩ አይደለም፡፡” አልኳት ከአፏ ቀልቤ፡፡
“ጅል!” አለች። ከፍቃዱ ጋር ስትሰራ ያደረችውን የድሪያ ወሬዋን ስላናጠብኩባት በሽቃ፡፡ እንደዚህ ስትለኝ እንደሚያስጠላኝ ታውቃለች። ግን አትተውም። በበሽቀች ሰዓት ሁሉ “ጅል
ትለኛለች። የምጠላው ደግሞ ጅል መባል ብልጥ ከመባል ጋር ተነፃፅሮ ውድቀት ስለሆነብኝ አይደለም፡፡ ብቸኛው ምክንያቴ እናቴ ትለኝ ስለነበረ ነው። እናቴ የምትለኝ የነበረውን ነገር ሁሉ እጠላዋለሁ (እናቴ ውዳሴ ከአፉ አይወጣም እንጂ ውዳሴም ቢሆን ከስድቦቿ እንደአንዱ የሚሆንብኝ ይመስለኛል።)ምክንያቱም ከመገለፅ በላይ እጠላታለሁ።
ሴት ከብዙ አርጩሜና ከትንሽ ሰውነት የተሰራች ፍጥረት ትመስለኛለች፡፡ መግረፊያንና ሴትን ምን አገናኛቸው? ወለላ! ወለላን እናትህ ስለሚሉኝ እናቴ ናት እላለሁ። ከልቤ ግን ወለላን
ምኔም ባልላት ደስ ይለኛል፡፡
“የአባትህ ልጅ! ጅል የጅል ዘር!” የሚለው ስድቧ ገላዬ ላይ ከሚያርፈው ዱላዋ እኩል በቀን ለመዓት ጊዜ የምሰማው ነው፡፡ የአባቴ ካልሆነ የማን ልጅ ልሆን ነበር? ሲመስለኝ አባቴ እኔን
እንደሚመስል ስታወራ ሰምቻለሁ፡፡ ያን ማለቷ ይሆን? ወይስ አባቴ ጅል ነበር? እናቴን ጨምሮ ጅል የሚሉኝ ሁሉ የማይገባኝ ነገራቸው አለመዋሸቴን፣ አለማስመሰሌን፣ ያልመሰለኝን
አለማድረጌን፣ ለሚጠይቁኝ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ መመለሴን፣
ተንኮል አለማወቄን እና እነርሱ ብልጠት የሚሉትን ነገር ለመልመድ ራሴን አለማጣቴን ለምን ጅልነት እንደሚሉት ነው::
በተቃራኒው አፈቀላጤነትን፣ ያልሆኑትን መስሎ መታየትን፣መዋሽትን፣ ተንኮለኛነትን... እንደ ብልጥነት መቁጠራቸው ምነኛ አስተሳሰብ ይሆን?
ረድኤት አዳሯን እየነገረችኝ ከማታው የተረፈ ቡረቃዋ እንዳለቀቃት ነው የተሰማኝ፡፡ እኔ ግን ከልቤ ነበር፡፡ ፍቅረኛው ከሌላ ወንድ ጋር ያውም በዝና፣ በገንዘብ፣ በውበት እንደውም በቁመትም ጭምር ከሚበልጠው ታዋቂ አርቲስት ጋር ያሳለፈችውን የአዳር ተረክ ስትነግረው ጥሩ ነው' የሚል ፍቅረኛ
ይኖር ይሆን? በእርግጥ የኔ ፍቅረኛ ከፍቃዱ ጋር የባለገችው በህልሟ ነው፡፡ ቢሆንም 'ጥሩ አይደለም፡፡ አብሯት ማደሩን ከነገረችኝ ሰውዬ ጋር ራሴን ማነፃፀር የጀመርኩበት ምክንያት
ውሉ አልገባኝም፡፡ ህልሟን ባሰብኩ ቁጥር የሚረብሸኝ የትኛው እንደሆነ መነጠል አቃተኝ፡፡ እርሷ የሌላ ሰው መሆኗ ወይስ ሌላኛው ሰው እንደሚበልጠኝ ማሰቤ? ራሴን ከሌላ ሰው ጋር አነፃፅሬ ማወቄን እንጃ! ለንፅፅር የምቀርብ ስለመሆኔም እንጃ እኔ
በቃ ስህተት ነኛ! ስህተት ስሜ ነው ፣
መገለጫዬ ፣ ማንነቴ! ወለላ ልጇ መሆኔን እንኳን ለመናገር የምታፍርብኝ እናቴ ነበረች፣ ሰፈር ብዙ ሰው አያውቀኝም::
ቢያውቀኝም በስሜ ማንም አይጠራኝም እሷኑ ይለጥፉብኛል።የ'ወለላ ልጅ':: ትምህርት ቤት ስታስመዘግበኝ አፏን ሳያዳልጣት
“ስሙ ማን ነው?” ስትባል::
“ስህተት ወለላ” ብላ ነው ያስመዘገበችኝ፡፡ በህይወቴ ውስጥ
ትልቁን ስህተት ማስመዝገቧ አልገባትም፡፡ እሷ ከራሷ ውጪ
ለማንስ ግድ አላት? እኔ ለሷ ከዛ ያለፈ አልነበርኩም ስህተቷ ነኝ፡፡ ታዲያ ስህተት በምን ስሌት ለንፅፅር ይቀርባል?
የረድኤትን ህልም እያደረ ሳስበው በውን ብትባልግ ሳይሻል አይቀርም ነበር፡፡ ምክንያቱም ፍቅረኛዬ ይሄን ህልሟን ከነገረችኝ በኋላ ባህርይዋ የተቀየረ እየመሰለኝ መጣ፡፡ ቤት መዋል
የማትወደው ፍቅረኛዬ ስራ እየቀረች መተኛት ስትጀምር በህልሟ ያደረገችው ድሪያ እየወሰወሳት ልትደጋግም እየመሰለኝ ማሰብ ማቆም አቃተኝ። አጠገቤ ተኝታ በእንቅልፍ ልቧ ድምፅ
ባስማች ቁጥር ከፍቃዱ ጋር እየተላፋች እየመሰለኝ በቅናት ተብሰከሰኩ፡፡ 'አትተኚ አይባል? ህልም አታልሚ አይባል?
ህልሟን ጠላሁት፡፡ የማልጋፋው ባላጋራ ሆነብኝ፡፡ አንድ ዕለት በውድቅት ለሊት በውል ያልሰማሁትን ነገር ስታጉተመትም
ነቃሁ፡፡
“ረዲዬ.... ረዲ....”
“በስመአብ ወ ወልድ! ምነው?” አለችኝ ብርግግ ብላ ከእንቅልፏ እየባነነች።
“ምነው ፍቅሬ ከፈቃዱ ጋር እንትን እያደረግሽ ነበር እንዴ?”ስላት መብራቱን አብርታ ካፈጠጠች በኋላ “ጂላጅል! ከፈቃዱ ጋር አይደለም ከአለሙ ጋር ነው::” አለችኝ፡፡
“አለሙ ደግሞ ማነው? እሱም አርቲስት ነው?”
“እንከፍ! ኸረ ምን ዓይነቱን ነው የጣለብኝ?” ብላ እየተቆናጠረች
ጀርባዋን ሰጥታኝ ተኛች።
እሷ ህልሟን ካቆመችበት ለመቀጠል ይመስለኛል እንቅልፍ ጥሏት ስትወራጭ፣ ስታንኮራፋ እንቅልፍ አጥቼ እሰማታለሁ፡፡
ወለላ ደብድባኝ ስታበቃ ምንም የሚጎዳኝ ነገር እንዳላደረገች ተኝታ እንደምታንኮራፋው አልያም እያንጎራጎረች እንደምትኳኳለው።ወለላ እኔን ከመግረፍ በሚተርፋት ጊዜ የኔን
አባት ሳይጨምር እኔ የማውቃቸውን አምስት ባሎች አግብታ ፈታለች፡፡ አባቴን ጨምሮ ሁሉም ባሎቿ ጥለዋት ለመሄዳቸው ምክንያት እኔ እንደሆንኩ ትነግረኛለች፡፡ ምን እንደሚያገናኘው
ዛሬም ድረስ አይገባኝም፡፡ እሷ እንዳለችኝ አባቴ ማርገዟን ስትነግረው ጥሏት ስለሄደ እሺ ብዬ ገፊነቴን ልቀበልላት፡፡
ከአምስቱ ስንተኛው መሆኑን የማላስታውስው አንድም ዓመት
አብሯት ከኖረ በኋላ “አንቺ እኮ ልጅ እንዳለሽ እንኳን ያወቅኩት ካገባሁሽ በኋላ ነው:: ድብቅ ነሽ” ሲላት ሰምቻለሁ፡፡ ይሁን ለዚህኛውም ምክንያት ልሁናት፡፡ ከመታመሟ በፊት ለመጨረሻ
ጊዜ ያገባችው ባሏም ድሮ ሰራተኛዋ የነበረች ሴት ወልዳኝ ጥላባት ሄዳ እሷ እያሳደገችኝ እንደሆነ እንደነገረችው ሳላውቅ እናቴ መሆኗን ስነግረው መጨቃጨቃቸው ትዝ ይለኛል፡፡
ይሁንላት ለዚህኛውም ሰበብ ልሁናት፡ እራሷ ላጠፋችው ጥፋት፣ ባሎቿ ላጠፉት ጥፋት፣ ራሴም ላጠፋሁት ጥፋት
የምቀጠቀጠው እኔ ነኝ፡፡ እንደውም የማላውቃቸውን እና አብሬያቸው እንድጫወት የማትፈቅድልኝን የሰፈራችንን ልጆች ጥፋትም እኔ ሳልሆን እቀራለሁ የምቀጠቀጠው? የሰፈሩ እናቶች በሙሉ ቅጣታቸውን ሳይሰጧት ይቀራሉ?
ከረድኤት አጠገብ ተጋድሜ ሊነጋ ገደማ አንድ መላ መጣልኝ፡፡ 'እሾህን በእሾህ!!”
“መሌ በህልምህ ከሴት ጋር አድረህ ታውቃለህ? ማለቴ እንትን አድርገህ?” አልኩት መላኩን ሱቄ በር ላይ ከተሰበሰቡት

👍5❤1🥰1
ቋሚ ተገታሪዎች መሃል እንደምፈልገው ነግሬው ሱቅ ካስገባሁት
በኋላ፡፡ መላኩ ከስራ ፈትነቱ ባሻግር በሰፈሩ ብቅ ያለች ቆንጆ ሴት አታመልጠውም እያሉ የሚያወሩለት ባለገድል ነው፡፡ ..
“አዎ... ምነው?”
"አይ ላማክርህ ነበር፡፡” አልኩት ስለዚህ ጉዳይ ማውራቴ እያሳፈረኝ ቢሆንም ምርጫ አጥቼ፡፡
“ምንድነው የምታማክረኝ? ማታ.....?”
“ኸረ እንደሱ አይደለም፡፡ እንደሱማ ቢሆን ጥሩ ነበር፡፡”
“እና ምንድነው?”
“አለ አይደል በህልሜ ከቆንጆ ሴት ጋር እንትን ማድረግ እፈልጋለው።አርቲስት ከሆነች ሴት ጋር።ስለው ሳቁ አመለጠው
ሁሌ በነገሬ ስለሚያላግጥ እንደሚስቅ ጠብቄያለሁ። ሳቁን ማቆም አቃተው።
“እንዴ? ያቺን የመሰለች አበባ እቤትህ አስቀምጠህ?” የሆነውን ሁሉ ነገርኩት፡፡ ላስቀናት ማሰቤን ስነግረው ሳቀ ሳይሆን
ተንፈራፈረ ቢባል ይቀላል።ሱቄ በር ላይ
ድዳቸውን የሚያሰጡት የሰፈራችን ጎረምሶች ስለረድኤት ሲሉ የምሰማቸው
ይሄንኑ ነው።“ይህቺን የመሰለች፡፡፣ አፈስካት፣ ምን አዙረህባት ነው አንተ ላይ የወደቀችው?” ስለእውነቱ ግን እኔ
ከእርሷ ጋር ስሆን ደስ ከመሰኘቴ ውጪ ስለመምሰሏ አነፃፅሬ አላውቅም።
ልጅ ሆኜ ከመደብደብ በሚተርፉኝ ቀናት ትምህርት እየተማርኩ ስምንተኛ ክፍል አጋማሽ ፈተና ጨርሼ ወደ ቤት እየተመለስኩ ሳለ አንዲት አርጩሜ ከኋላዬ ስትሮጥ መጣች፡፡ ረድኤት ናት፡፡
የትምህርት ቤቱ ጎበዝ ተማሪ ነች፡፡ ጎረቤታችንም ናት፡፡
“ስህተት? ስህተት?" ሰው ስሙ ያስጠላዋል? ወይስ ስሜ ራሱ
ስህተት ስለሆነ ነው? በተለይ በሴት ድምፅ ስሰማው ጩህ ጩህ ይለኛል። አጠገቤ እስክትደርስ ጠበቅኳት፡፡
“እግርህን ምን ሆነህ ነው የምታነክሰው?”
“ወለላ መታኝ” ፊቷ ከገነትነት ወደ ሲኦልነት ሲቀየር አየሁት።
“እንዴ ለምን?”
“ተናዳ...”
“ምን አድረገሃት?”
“አጥፍቼ “
“ምን አጥፍተህ?” እየጠየቀችኝ ሳታስፈቅደኝ የለበስኩትን ካኪ
ሱሪ ከፍ አድርጋ ቁስሉን አየችው፡፡.....
💫ይቀጥላል💫
Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

👍2🥰1
#ውጊያ_ሲሆን_ኑሮ
በጃን ሜዳ ሰማይ
ሎሚ ተወርውሮ፣ መች መሬት አረፈ
ከምእመናን አንዱ
“ጎበዝ ተገን ያዙ አለና ለፈፈ
ጉድ ነው ከዚያ ወድያ
ሕዝባዳም ታመሰ
አጀቡ ፈረሰ።
ማታ፣
“አሳዛኝ ዜና
ዛሬ ጃንሜዳ በተባለው ሰፈር አቅራቢያ
በደረሰው የወከባና መረጋገጥ አደጋ ሳቢያ
ኑሮ ውጊያ ሲሆን፣ ውጊያ ሲሆን ኑሮ
ልክ እንደ እግዚአብሔር ፊት፣ ሰላም ተሰውሮ
መቶ ሰው ይገድላል፣ ሎሚ ተወርውሮ።
በጃን ሜዳ ሰማይ
ሎሚ ተወርውሮ፣ መች መሬት አረፈ
ከምእመናን አንዱ
“ጎበዝ ተገን ያዙ አለና ለፈፈ
ጉድ ነው ከዚያ ወድያ
ሕዝባዳም ታመሰ
አጀቡ ፈረሰ።
ማታ፣
“አሳዛኝ ዜና
ዛሬ ጃንሜዳ በተባለው ሰፈር አቅራቢያ
በደረሰው የወከባና መረጋገጥ አደጋ ሳቢያ
ኑሮ ውጊያ ሲሆን፣ ውጊያ ሲሆን ኑሮ
ልክ እንደ እግዚአብሔር ፊት፣ ሰላም ተሰውሮ
መቶ ሰው ይገድላል፣ ሎሚ ተወርውሮ።
#የመስኮት_ዳር_ምህላ
በባእድ አገር መኖር፣ የተራዘመ ሞት ፍርድ ነው
ብለው ሲሉኝ፣ እያለቀስኩ እስቃለሁ
ከሞት መታገል አውቃለሁ
ወደ ባሕር ስወረወር፣ አፀድ መሃል እወድቃለሁ።
ይሄ መስኮት ይመስክር
የመስታወት ሀውልት ሁኖ፣ ያሳለፍኩትን ይዘክር!
ይሄ ሁሉ መከራ
ይሄ ሁሉ የበረዶ ጭፍና
በኮቴው ደቅድቆኝ ያልፍና
ታሪኬን ለመንገር እቆያለሁ
የቅጠሎቼን ትንሣኤ አያለሁ!
በባእድ አገር መኖር፣ የተራዘመ ሞት ፍርድ ነው
ብለው ሲሉኝ፣ እያለቀስኩ እስቃለሁ
ከሞት መታገል አውቃለሁ
ወደ ባሕር ስወረወር፣ አፀድ መሃል እወድቃለሁ።
ይሄ መስኮት ይመስክር
የመስታወት ሀውልት ሁኖ፣ ያሳለፍኩትን ይዘክር!
ይሄ ሁሉ መከራ
ይሄ ሁሉ የበረዶ ጭፍና
በኮቴው ደቅድቆኝ ያልፍና
ታሪኬን ለመንገር እቆያለሁ
የቅጠሎቼን ትንሣኤ አያለሁ!
#አይመንን_አይጨምት
ጉብዝና ዘላን ነው፣ በመጣበት ሄደ
ጎፈሬ እንደ አቧራ
ነፋስ ተከትሎ
ካናት ተነጥሎ
ሩቅ ተሰደደ
ደረት ቆረፈደ
ትክሻ ተናደ
ተሸረሸረ አቅሙ
ጉልበትን በቁሙ
ስውር ነቀዝ በላው
ልብ ነው የደላው
ጊዜ ሄደ ብሎ
አቅሙን የማይገምት
እግርን ተከትሎ
አይመንን አይጨምት።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
ጉብዝና ዘላን ነው፣ በመጣበት ሄደ
ጎፈሬ እንደ አቧራ
ነፋስ ተከትሎ
ካናት ተነጥሎ
ሩቅ ተሰደደ
ደረት ቆረፈደ
ትክሻ ተናደ
ተሸረሸረ አቅሙ
ጉልበትን በቁሙ
ስውር ነቀዝ በላው
ልብ ነው የደላው
ጊዜ ሄደ ብሎ
አቅሙን የማይገምት
እግርን ተከትሎ
አይመንን አይጨምት።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
“እኔንጃ!! ትዝ አይለኝም ግን አጥፍቼ ነው።”
“ወላዲተ=አምላክ!!!!:: ቆይ በምንድነው እንዲህ የመታችህ?”
“እኔንጃ በጫማዋ ሹል መሰለኝ፡፡” እያየኋት ድርቅ ብላለች።
“ምነው አንቺ አትገረፊም እንዴ?”
“ወላዲተ አምላክ!!!! ሰው እንዴት እንዲህ አድርጎ ልጁን ይመታል? አንተ እኮ ትልቅ ሆነሃል!!”
ምን እንዳለችኝ በትክክል የገባኝ ከዛን ዕለት በኋላ ጠዋት ጠዋት ከሰፈራችን የሚያስወጣው መታጠፊያ ላይ መኪናቸው ቆማ እየጠበቀችኝ ትምህርት ቤት አብረን መሄድ ከጀመርን በኋላ
ነበር፡፡ ትምህርት ቤት ደርሰን ስትወርድ አባቷ እንዴት ነበር ያደረጓት? የአንደኛውን እጃቸወሁን ጣቶች ፀጉሮቿ መሃል
እንደማበጠሪያ ሰክተው ወደራሳቸው አስጠጓት፡፡ እንደተለመደ ነገር እንደትክክል ሁሉ ነበር የሚያደርጉት፡፡ ከጉንጭዋ ይልቅ ለአንገቷ የቀረበ ቦታ ላይ ሳሟት። ለኔ ግን የመሰለኝ እንደዛ
አይደለም፡፡ በጆሮዋ የሆነ መለኮታዊ ልሳን ያወሩላት፣በከንፈራቸው ወደሳሟት ቦታ አንዳች ልገልፀው የማልችለው
ዓይነት ምትሃተኛ ነገር እንዳስተላለፉላት፣ በጣቶቻቸው በሆነ ትስስር እንዳሰሯት
እንደዛ ነገር፡፡ መልሳ ጉንጫቸውን
ሳመቻቸው ልበል? በየጠዋቱ ይሄን ትዕይንት ማየት ልክ የሆነ ሌላ ዓለም መኖሩን ነገረኝ፡፡ የምፈራው፣ ያልኖርኩበት እና የማላውቀው የሆነ በሰው ልጆች መሃል ያለ መሳሳብ መኖሩን ነገረኝ፡፡ ወለላ ገረፈችኝ፡፡ ረድኤት ማን ናት? ለምንስ ት/ቤት ያደርሱሃል? ምን አሉህ? ወለላ ሴሰኛ ናት አሉህ? ወለላ ምን
አድርጋው ነው አባትህ ጥሏት የሄደው አሉህ? የማላስታውሰው ጥያቄ እየጠየቀችኝ ደበደበችኝ፡፡ ይሄን ግርፊያ
የሚለየው እንባዬ አልወጣ አለኝ፡፡ አልለመንኳትም፡፡ ፀጥ!ጭጭ ብዬ ተመታሁላት፡፡ አልታገልኳትም፡፡ መምታቷን አቁማ አየችኝ፡፡
“ምን ሆነሃል?”
“ምን ሆንኩ?”
“ምን ይዘጋሃል? ምን አስበህ ነው?” ዝም አልኳት፡፡ ያ የመጨረሻ ዱላዋ ነበር፡፡ “ምን ትጠላለህ?' በሉኝ ወለላን ቀጥለህ
ምን ትጠላለህ?” በሉኝ ወለላን ከዛ በተረፈህ ጥላቻ ምን ትጠላለህ?' በሉኝ ወለላን!!
በሚቀጥለው ቀን የአጥሩ በር ተንኳኳ፡ ረድኤት ነበረች፡፡ለሰላምታ እጄን ዘረጋሁላት፡፡ እጄን ጨብጣ ወደራሷ
አስጠጋችኝና ጉንጬን ሳመችኝ፡፡ አዎ ጉንጬን በከንፈሯ ነካችው። እርጥበቷ ጉንጩ ላይ ታትሞ የቀረ መሰለኝ፡፡
“ለምንድነው ትምህርት ቤት የቀረኸው?”
“ከዛሬ በኋላ ት/ቤት አልመጣም!!”
“እንዴ ለምን?”
“አንቺ ምን አገባሽ? የሚበጀውን ራሱ አውቋል፡፡ ምን ቤት ነኝ ነው?” ወለላ ናት ከየት መጣች ሳልላት አጠገቤ ደርሳ
የመለሰችላት፡፡
“ደሞ ስሚ ሁለተኛ ደጄ ድርሽ ብትዪ ውርድ ከራሴ” አለቻት ቀጥላ፡፡
ረድኤት መልስ ሳትሰጣት ጊቢያችንን ለቃ ወጣች። እኔም ት/ቤት ቀረሁ፡፡ ወለላ ለረድኤት አባት ስሞታ ስለተናገረችባት እቤትም መጥታ አታውቅም፡፡ መንገድ ብታየኝም በርቀት በግንባሯ ሰላም
ብላኝ ታልፋለች እንጂ አትጠጋኝም፡፡ ወለላን ትፈራታለች፡፡ወለላ ደግሞ የኔ ጥላ ናት፡፡ ከዚህ በኋላ ረድኤትን በቅርበት
ያየኋት የዩንቨርስቲ ተማሪ ከሆነች በኋላ አባቷ የሞቱ ጊዜ ነበር፡፡ ስታለቅስ በህይወቴ ከፍተኛውን ሀዘን ያዘንኩበት ቀን ይመስለኛል፡፡ አሳዘነችኝ፡፡ ከዓመታት በፊት በጆሮዋ ሹክ ያሏት የመሰለኝ የመለኮታዊ ቃል ትዝ አለኝ፡፡ ከሰው መሃል ስታየኝ ሮጣ መታ ተጠመጠመችብኝ
ምን ማለቷ እንደሆነ ገብቶኛል አባቷን እያስታወሰችኝ ነው።ሰዎች ቃል ሳይለዋወጡ የሚለዋወጡት ስሜት እንዳለ ገብቶኛል፡፡ ወደራሴ
አስጠግቼ መልሼ አቀፍኳት። ምን እንደተረዳችኝ ባይገባኝም ያለቃል እኔ የነገርኳት “አባትሽ ላንቺ ምን ማለት እንደሆኑ ይገባኛል፡፡ የሀዘንሽ ጥልቀት ተሰምቶኛል የሚለውን ነበር፡፡
ከረድኤት አባት ሞት በኋላ ብዙም ባልራቀ ጊዜ ወለላ ልትቆጣጠራቸው ባልቻለቻቸው ሱሶቿ ምክንያት ማገገሚያ
ገባች፡፡ ከዚያ ቀናት ቀደም ብሎ የምንኖርበትን ቤት ካርታ ሰጠችኝ፡፡በራሷ ስም ነው ያለው ያጠረቀመችውንም በዛ ያለ ገንዘብ ሰጠችኝ (ሱቅ የከፈትኩት በዚያ ብር ነው፡፡)
ወለላ ማገገሚያ ከገባች በኋላ ረድኤት እንደልቧ ቤቴ መመላለስ ጀምራለች፡፡ በሆነ ትምህርት ተመርቃ ስራ እየፈለገች ነበር።አንድ የሆነ ቀን እቤት ተቀምጬ እያለሁ መጣች። ዝም ብላ አጠገቤ ያለ ወንበር ላይ ተቀመጠች። እጄን ከጭኔ ላይ አንስታ እንደማሸት ነገር እንደመዳበስ አደረገችው፡፡ ዝም ብዬ አየኋት።
“ለምን እንደምወድህ ታውቃለህ?”
“አይደለም ምክንያቱን እንደምትወጂኝም አላውቅም፡፡” ስላት አናደድኳት መሰለኝ ተበሳጨችብኝ፡፡ የሚቀጥለውን ለመናገር
ጊዜ ወሰደች፡፡ ከልቤ ነው ያልኳት በማንም ስለመወደድም ማንንም ስለመውደድ ግድ ሰጥቶኝም አስቤም አላውቅም፡፡
“እወድሃለሁ!! የምወድህ ደግሞ ልብህ ስለሚያምር ነው፡፡”
“ልብህ ስለሚያምር?”
“አዎን ብዙ እውነትና ትንሽ ጥላቻ የተሸከመ ንፁህ ልብ ነው ያለህ!”
“ጥላቻ የሚያምር ነገር መሆኑን አላውቅም፡፡ ጥላቻን የተሸከመ
ልብ ንፁህ መባሉም አይገባኝም፡፡” አልኳት።
“አያምርም፡፡ አዎን ጥላቻ አያምርም፡፡ አየህ እውነትህን? ሁሉም ሰው በልቡ ለማንም ማሳየት የማይፈልገው ቆሻሻ ይኖረዋል፡፡ጥላቻ፣ ክፋት፣ ግልፍተኝነት፣ ራስን መውደድ... አንዱ ይኖርበታል፡፡ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎን ካልተገለጠ በስተቀር ንፁህ ፣ ቅን እና ፍፁም
እንደሆንን እናስመስላለን፡፡ አንተ እንደዛ አይደለህም፡፡የተሰማህንና የሆንከውን ብቻ ነው የምትኖረው፡፡ የኖርከው
ህይወት የፈጠረብህን ጥላቻና ሽሽት አትደብቀውም፡፡ ያ ደግሞ እንድትድን ያደርግሃል፡፡ አንተ ክፉ ልብ የለህም፡፡ ማንንም መጉዳት አስበህ አትጎዳም፡፡”
ያወራችው ብዙው አልገባኝም፡፡ ከዚህም በላይ ብዙ ነገር አውርታለች፡፡ ከወሬዋ ይልቅ እጄን እየዳበሰችው ያለችው የእጇ
ድብሻ ደስ ብሎኛል፡፡ ረዣዥም የእጇን ጣቶች በትኩረት እያየሁ የምታወራውን ሙሉ በሙሉ አልሰማኋትም፡፡ ተጠጋችኝ
መሰለኝ፡፡ በየትኛው ቅፅበት ከንፈሯ ከንፈሬ ላይ እንዳረፈ አላውቅም፡፡ መሳም ብቻ አይደለም የሳመችኝ : አንድ የሆነ ነገር አድርጋኛለች፡፡ ከገለፃ በላይ የሆነ ምትሃተኛ ነገር፣ ደም የሚመላለስበት አካሌ ብቻ ሳይሆን ፀጉርና ጥፍሬ እንኳን
የሚሰማው ዓይነት ምትሃት!በደነዘዝኩበት ጥላኝ ወጣች፡፡
ከዚያ ቀን በኋላ ግን ውስጤ አንድ የሆነ አዲስ ነገር ተፈጥሯል።
ወለላ ማገገሚያ መግባቷን ሳውቅም ልጠይቃት አልሄድኩም።እንደውም እንደማትመለስ እርግጠኛ እንደሆንኩ ሁሉ ወይም ባትመለስ ምኞቴ እንዲሰምር እየፈለግኩ ተነስቼ የወለላን የግል ንብረቶች መበርበር ጀመርኩ፡፡ምን እንደምፈልግ እንኳን በትክክል ሳላውቅ የሆነ ነገር እፈልጋለሁ። ያን ማድረጌ ረድኤት ያለችኝን በልቤ ያለች ትንሽዬ ጥላቻ ለመቀነስ ወይም ለማጥፋት
ይሆን? በየዕለቱ እያነበበች የምታለቅስባቸውን ደብዳቤዎቿን
ይዛቸው መሄዷን ስገነዘብ ለአፍታም ቢሆን ማን እንደሚፅፍላት የማወቅ ጉጉት አደረብኝ፡፡ በካርቶን ያጠረቀመቻቸው ብዙ ፖስታዎች ናቸው:: እስከቅርብ ዓመታት በየወሩ ፖስታ ቤት
እየሄደች አንድ አዲስ ፖስታ ይዛ ትመጣለች፡፡ አንብባ ስትጨርስ
ከቀደሙት ጋር ብትቀላቅለውም ሁሌም ብቻዋን ስትሆን ከምትቆልፍበት መሳቢያ ውስጥ እያወጣች ደጋግማ ታነባቸዋለች። አባቴ ይሆን? ወይ ከባሎቿ አንዱ? አልያም ከተለያየ ሰው የሚላክ ይሆናል። ብቻ ቅጥ ያጣ ራስ ወዳድነቷን ዘልቆ በልቧ ቦታ ያገኘ ሰው መሆን አለበት ምናልባት የበደለችው ሰው አልያም ደብዳቤውን መፃፍ ያቆመው ሞቶ
መሆን አለበት።

👍5
ወለላን እስከማውቃት ሀዘንም ሆነ ፈገግታ ፊቷ ላይ የሚነበበው ከነዛ ደብዳቤዎች ጋር ስትሆን ብቻ ነው፡፡ እናም አንዳንዴ ደብዳቤ በሚፅፍላት ስው እቀናለሁ:: ምክንያቱም አጠገቧ ካለሁ ብቸኛ ልጇ በላይ ዋጋ የምትሰጠው ሰው ነውና!
በፍለጋዬ ማገባደጃ የፎቶ አልበሟን አገኘሁት፡፡ እንዴት አንድስ እንኳን የአባቴ ፎቶ አይኖራትም? አንደኛው የፎቶ ቦታ ላይ ተጣጥፎ የተቀመጠ ወረቀት አገኘሁ እና ዘረጋሁት፡፡ ከዓመት ምህረቱና ከሀተታው እንደገባኝ አባቴ የፃፈላት ደብዳቤ ነው።ስሙን አልፃፈበትም፡፡ ጥሏት የሄደ ዕለት የፃፈላት ነው፡፡ አንድ ነገር የገባኝ መሰለኝ፡፡ እንደ ደብዳቤው ይዘት ወለላ ከአባቴ ታናሽ ወንድም ጋር በቤቱ በአልጋው ስትባልግበት አግኝቷት ነው ጥሏት የሄደው::
..
ረድኤት ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ አብራኝ ትሆናለች ይጨንቀኛል።ማውራት ስለማልችል አጠገቤ ስትሆን የማደርገው ይጠፋኛል፡፡
“ሱቅ አትምጪ!” አልኳት ከብዙ ቀን በኋላ፡፡
“ለምን? ምን አደረግኩህ?” የደነገጠች መሰለኝ፡፡ እኔ ግን ያልኳት ከልቤ ነው:: ከእናቴ ውጪ በቅርበት የማውቃት ሴት እርሷ ናት። አይደለም ከሴት ጋር ከሰው ጋር አውርቶ መወዳጀት አላውቅም:: እድሉም አልነበረኝም:: ረድኤት ደግሞ ከማውራትና ከመወራጨት ሌላ ተግባር የላትም።
“ምንም አላደረግሽኝም:: ብቻሽን ስታወሪ እጨነቃለሁ፡፡” ቀጥዬ ግን ወሬዋን አቁማ የሆነ ቀን እንዳደረገችው ብትስመኝ ደስ
እንደሚለኝ ልነግራት ነበር፡፡ እሷ እየተጣደፈች ጥላኝ ሄደች እንጂ፡፡ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ሱቅ አልመጣችም፡፡ አጠገቤ ሆና እንድትሄድልኝ ከፈለግኩት ስሜቴ በላይ ላያት መፈለጌ አየለብኝ፡፡ በጊዜ ሱቅ ዘግቼ ወደቤቴ ስሄድ ደጃቸውን ስታንኳኳ
አየኋት እና ጠራኋት፡፡
“ላይሽ ፈልጌ ነበር፡፡” አልኳት:: ሳትመልስልኝ እጄን ይዛ እየጎተተች ወደቤቴ ይዛኝ ገባች፡፡ እጄን፣ አንገቴን፣ ከንፈሬን፣ ጉንጩን፣ ፀጉሬን ብዙ የሚያቃጥል ትንፋሽ እየተነፈሰች
ሳመችኝ፡፡ ባልመለስ ከምወድበት ዓለም ድንገት መለሰችኝና
“ናፈቅኩህ አይደል?” አለችኝ፡፡
እኔ እንጃ! ናፍቀሽኝ አይደለም፡፡ ስለጠፋሽ ላይሽ ፈልጌ ነው።” መለስኩላት፡፡ ቅር አላት፡፡እውነተኝነትህን እወደዋለሁ.....
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

#ለሕዝቡ_ብሎ
ምነው ገለሌ
ምነው ገለሌ
አመሉ ቅጥፈት፣ ስሙም እገሌ
በከፊል መናኝ፣ ግማሽ ተጋዳይ
የማጀቱን ጉድ፣ የራሱን ጉዳይ
ከድኖ በማብሰል
ባገሩ ጣጣ፣ የሚብሰለሰል
ስብከት በጉንጩ
የግሣፄና የርግማን ምንጩ።
ፍሬ ከርስኪው የማይጠገብ
ካልጋው አጠገብ
ዘብ ቆሞ አዳሪው
ቆሪጥ ወታደር
ተልኮው ጥሪው
በካሜራ ፊት ሲያወራ ማደር።
ቢያምር ባያምር፣ ቢጣፍጥ ባይጥም
ካሜራና ጅል፣ ትይንት አይመርጥም።
በቅሎ አትሸልሙት
ፈረስ አትጫኑ
ፈረስ እኮ ነው የገዛ ጭኑ
ካንደኛው ዜጋ ወዳንዱ ዜጋ
እየጋለበ
በሀሜት ዘገር በስድብ ሎጋ
እያካለበ
የሚዋደቅ ነው በየስክሪኑ
በላፕቶፑ ላይ ሰርክ ተጥዶ
አንድ ሺ ዘልፎ
አንድ ሺ አዋርዶ
ዘመን የጣላት
ዘመድ የጠላት
ባልቴት ይመስል
ስድብ ሲቀቅል
ነገር ሲያማስል
ሲያማርር ውሎ
ለሕዝቡ ብሎ
ካልጋው ተነስቶ ፍሪጁ ድረስ
ጊዜ እያጠረው አይንቀሳቀስ
ለሕዝቡ ብሎ። .
ምነው ገለሌ
ምነው ገለሌ
አመሉ ቅጥፈት፣ ስሙም እገሌ
በከፊል መናኝ፣ ግማሽ ተጋዳይ
የማጀቱን ጉድ፣ የራሱን ጉዳይ
ከድኖ በማብሰል
ባገሩ ጣጣ፣ የሚብሰለሰል
ስብከት በጉንጩ
የግሣፄና የርግማን ምንጩ።
ፍሬ ከርስኪው የማይጠገብ
ካልጋው አጠገብ
ዘብ ቆሞ አዳሪው
ቆሪጥ ወታደር
ተልኮው ጥሪው
በካሜራ ፊት ሲያወራ ማደር።
ቢያምር ባያምር፣ ቢጣፍጥ ባይጥም
ካሜራና ጅል፣ ትይንት አይመርጥም።
በቅሎ አትሸልሙት
ፈረስ አትጫኑ
ፈረስ እኮ ነው የገዛ ጭኑ
ካንደኛው ዜጋ ወዳንዱ ዜጋ
እየጋለበ
በሀሜት ዘገር በስድብ ሎጋ
እያካለበ
የሚዋደቅ ነው በየስክሪኑ
በላፕቶፑ ላይ ሰርክ ተጥዶ
አንድ ሺ ዘልፎ
አንድ ሺ አዋርዶ
ዘመን የጣላት
ዘመድ የጠላት
ባልቴት ይመስል
ስድብ ሲቀቅል
ነገር ሲያማስል
ሲያማርር ውሎ
ለሕዝቡ ብሎ
ካልጋው ተነስቶ ፍሪጁ ድረስ
ጊዜ እያጠረው አይንቀሳቀስ
ለሕዝቡ ብሎ። .
#ቀላውጦ_ማስመለስ
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
ትለኛለች።እውነቱን ሳወራት ይከፋታል። አኮረፈች። ጥላኝ ግን አልሄደችም።
"አንተጋ ልደር?” አለችኝ፡፡“
“ደስ ይለኛል!” አልኳት እንድትሄድ አልፈለግኩም፡፡
“የት እተኛለሁ?”
"የተመቸሽ ቦታ"
የተመቻት ቦታ ከኔጋ አልጋዬ ላይ መተኛት ነበር፡፡ እንደዛ አደረገች፡፡ እንደብዙ ነገር አደረገች፡፡ ልብሶቼን ከላዬ እንዴት ገፋ
ጣለቻቸው? ከመቼው አልጋው ላይ ወደቅን?ከላዬ ነበረች? በየትኛው ቅፅበት ከስሬ አገኘኋት? የማላውቃት የሆነች ልጅ ነበረች፡፡ የደስታ ሲቃዬን ያበዛችው ግን የማላውቃት ባዕድ ነገር የሆነችብኝ፡፡ ከሰውነቴ አጣብቄ እንዳቀፍኳት ነጋ፡፡
“አትሂጂ አብረሽኝ ኑሪ!” አልኳት፡፡
ትወደኛለህ?” ብላ ጠየቀችኝ።
“እኔንጃ!” መለስኩላት።
ከእናቷ ጋር ብዙ ከተነታረከች በኋላ አብራኝ መኖር ጀመረች፡፡ልክ ያልሆነ ነገር ያለው አኗኗር መሆኑ ይገባኛል፡፡ አብራኝ
ልትኖር የወሰነች ቀን ማታ በድጋሚ “ትወደኛለህ ወይ?” ብላ ጠየቀችኝ፡፡ በማላውቀው ምክንያት ይሄ ጥያቄዋ የሚከብድ ነገር አለው፡፡ መውደድ፣ ናፍቆት፣ ፍቅር ዓይነት ላሉ ስሜቶች
እርግጠኛነቴን እንጃ፡፡ ስሜቱ ምን ስለመምሰሉም አላውቅም።
“ስትስሚኝ ደስ ይለኛል፡ ባለፈው ዕለት እንትን ስናደርግም በጣም ነው ደስ ያለኝ።
“አብሮ ለመኖር ይሄ በቂ አይደለም፡፡ ፍቅር ነው ዋናው! እንደወደድከኝ እስኪሰማህ ድረስ አብሬህ እሆናለሁ፡፡ ነገር ግን ምንም አናደርግም፡፡” ያለችው ምን ያህሉ እንደገባኝ አልገባኝም፡፡
“ቆይ አንቺ ስናደርግ ደስ አላለሽም ነበር?”
“ፍቅር የሌለበት ወሲብ ማድረግ አልፈልግም፡፡” የምጠይቃትና
የምትመልስልኝ አልገጣጠም ይለኛል፡፡ እኔ እስከገባኝ ያደረግነው የሁለታችንም ደስታ የነበረበት ነገር ነበር፡፡ ብቻዬን ያደረግኩ፣ደስታው የእኔ ብቻ እንደነበር፣ እርካታው የግሌ ብቻ እንደሆነ እንዲሰማኝ ለምን እንደምታደርግ አይገባኝም፡፡ እንድዋሻት ትፈልጋለች፡፡ ምክንያቱም ራስዋን መዋሸት ስለምትፈልግ።በፍቅር ስም ለፍቅር ብላ ጭኖቿን እንደከፈተችልኝ እንጂ ለስሜትዋና ለደስታዋ ስትል ከማይወዳት ወንድ ጋር እንዳደረገችው በማሰብ ለራሷ ያላትን ግምት ዝቅ ማድረግ አትፈልግም፡፡ ደስታን መፈለግ ክፋቱ አይገባኝም፡፡ ለምን ሌላ ምክንያት ይለጠፍበታል? ለሁለት ወራት እንደዚህ አብረን ከኖርን በኋላ ነበር ህልሟን የነገረችኝ፡፡ ከፈቃዱ ጋር የሰራችውን የህልም ፍቅር!
በመላኩ ምክር ቅደም ተከተል መሰረት ከመተኛቴ በፊት አንዲት ፍቅረኛዬ የምታደንቃትን ታዋቂ ሴት አርቲስት ገላ ለማሰብ ሞከርኩ፡፡ከፍቅረኛዬ ውጪ የማንም ሴት ገላ ሊከሰትልኝ አልቻለም፡፡ ከዛሬ ሁለት ወር በፊት ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ጊዜ ከላዬ ሆና ዛር እንዳለበት ሰው ካበደችው እብደት ውጪ
ምንም ወደ ሀሳቤ ሊመጣልኝ አልቻለም፡፡ በእርግጥ እንዴትስ ማሰብ ይቻለኝ ነበር? ከሷ ውጪ የሴት እርቃን በፊልም እንኳን
ማየቴ ትዝ አይለኝም፡፡ ያየኋቸውን በአንድ የእጅ ጣት የሚቆጠሩ ፊልሞችም እሷው ናት ያሳየችኝ፡፡ ሴቶቹ ልብሳቸውን አውልቀው የሚያሳይ ቦታ ነበረው? አላስታውስም፡፡
“እ? ተሳካልሽ? ማታ ቺኳ ከች አለች?” አለኝ መላኩ ሱቄን ጠዋት እንደከፈትኩ ለወሬ ቸኩሎ።
“አላለችም ::አንተ ነህ ከች ያልክብኝ!! አልኩት መናደዴን እንዲያውቅ ጥርሴን ነክሼ።ላለመሳቅ እየታገለ።
“ምን ሳደርግ?” አለኝ።
“ብዙውን አላስታውስም፡፡ በጥፊ ስታልሰኝ ነው ከእንቅልፌ የባነንኩት” ስለው እስኪበቃው አገጠጠ፡፡ በህልሜ ረድኤትን የማስቀናቱ ሀሳብ አልተሳካልኝም።
“መነጋገር አለብን!” አልኳት አዋርቻት በማላውቀው ድምፀት፡፡ስታወራ እሰማታለሁ እንጂ ራሴ ርዕስ ፈጥሬ አዋርቻት አላውቅም።
"ዛሬ ወለላን ሄደን መጠየቅ አለብን።" አለችኝ ያልኳትን እንዳልሰማች ሁሉ ርዕስ ቀይራ:: ትናንትና ከሰዓት የወለላ ነፍስ
አባት እቤት ድረስ መጥተው ጉበቷ አደገኛ ደረጃ ላይ ስለደረስ ከማገገሚያ ወጥታ ከፍተኛ ሆስፒታል ከተኛች መክረሟን ከነገሩን ሰዓት ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ፀብ ቀረሽ ንትርክ ላይ ነን፡፡
እኔ እናቴን ላያት አልፈልግም፡፡ እርሷ ደግሞ ምንም ቢሆን እናቴ ስለሆነች የኛ ጥየቃ ይገባታል እያላች ችክ ብላለች። እኔ
ላናግራት የፈለግኩት በየእርምጃዬ ልረሳው ስላልቻልኩት ህልሜ ነበር። ጭቅጭቋ ሊያሳብደኝ ስለደረሰ ቁርስ እንደበላን ሆስፒታል ሄድን፡፡ ወለላ ጉዷ ተጎትቶ የማያልቅ ሴት መሆኗን ባውቅም
ለአፍታ ሽው ባለች ቅፅበት አስቤው የማላውቀው ነገር ገጠመኝ።
የወለላ ልጅ የእኔ ታላቅ ወንድም ሲያስታምማት አገኘሁት፡፡የተፈጠረው ነገር የሆነ የተልወሰወሰ ነገር አለው። መቼ ነው የወለደችው? አላሳደገችውም ማለት ነው? ለነገሩ ተገላገለ ከድብደባ ነው የተረፈው። ያላሳደገችውን እናቱን እንዴት እናቴ ብሎ ይጠራታል? እንዴትስ እያደረ ያስታምማታል? ይሄን
የማስበው የወለላ ልጅ መሆኑን በነገረኝ ቅፅበት ረድኤት እየተውረገረገች ወንድሙ መሆኔን ስትነግረው እርሱም እልፍ እያሰበ በመሰለኝ ሽርፍራፊ የጊዜ ክፍተት ነው። ምክንያቱም እሱም ወንድም እንዳለው አያውቅም። እርሱ ዝም አላለም።የሰማው ነገር ልክ መሆኑን ሲያረጋግጥ እድሜዬን ጠየቀኝ እና
ከራሱ ጋር ማስላት ጀመረ። በስምንት ዓመት እንደሚበልጠኝ ነገረኝ። ስራ እንዳለበት ነግሮን ሲወጣ አንድ ጥያቄ ብቻ ጠየቅኩት።
"ደብዳቤ የምትፅፍላት አንተ ነበርክ?" በመገረም እያስተዋለኝ አለመሆኑን ነግሮኝ ወጣ: ወንድም ማግኘቴ ከመገረም ልቆ የሰጠኝን ስሜት አላወቅኩትም።ወንድሜ ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ወለላን መውደዱን ግን ማመን አልቻልኩም። ረድኤት ከስራ
እስክትመለስ ሱቅ ቆሜ በሀሳብ እዚህ እዚያ ስረግጥ ዋልኩኝ።ዛሬ ሳላናግራት አላድርም እያልኩ ስዝት ውዬ መጣች።
“ጠዋት ስለምን ነበር ልታወራኝ የነበረው?” አለችኝ እራት የበላንበትን ሰሃን እያነሳሳች።
“እየቀናሁ ነው!” አልኳት፡፡
“አልገባኝም!!” አለችኝ የያዘችውን ሰሃን መልሳ እያስቀመጠች።
“አየሁት ካልሽኝ ህልም ውጪ ምንም ማሰብ አልቻልኩም፡፡”ስላት ሳቀች፡፡ ከት ብላ ሳቀች፡፡
“ጅል ነህ! ጅልነትህን ግን እወደዋለሁ፡፡"
“ጅል አትበይኝ! አትበይኝ በቃ!! የኔ ብቻ እንድትሆኚ መፈለግ ጅልነት ነው? ሌላ ሰው እንዳይነካብኝ መሳሳት ጅልነት ነው?
ስራ ውለሽ እስክትመጪ ላይሽ መጓጓቴ ነው ጅልነት? አቅፌሽ እያደርኩ ለራሴ ስሜት ሳይሆን ላንቺ ቃል መጠንቀቄ ጅልነት ነው? የቱ ነው ጅልነት? ከንፈርሽን መናፈቄ ነው ጅልነት?ንገሪኝ ይሄ ጅልነት ነው?” እንደዚህ መናገር መቻሌን ያወቅኩት ዛሬ ነው።
“አይደለም፡፡” አለችኝ እኔ ከምናገርበት የቁጣ ጩኸት ተቃራኒ በሆነ ለስላሳ አንደበት፡፡
“ይሄ ጅልነት አይደለም ፍቅር ነው ማሬ” አለችኝ፡፡ በፈገግታዋ መሃል ዓይኖቿ እንባ ሲያረግዙ አየኋቸው፡፡ ሳማት ሳማት
የሚለኝን ስሜቴን ማቆም አልቻልኩም። ከማድረጌ ቀድሞ ግን ስልኬ ጠራ! ወንድሜ ነው:: ዛሬ ጠዋት አውቆኝ ፍቅር ፍቅር ሊጫወት ከሆነ እየተገረምኩ ዝም ብዬ ስልኩን አየዋለሁ።የማንሳት ጉጉት አልነበረኝም።ረድኤት እንዳነሳው ስትነግረኝ ግን አነሳሁት፡፡ ምንድነው ያለኝ?
"ስህተት እናታችን ሞታለች:: ማለቴ ተገድላለች::"ሲለኝ መሞቷ አልገረመኝም: አላሳዘነኝምም:: አሟሟቷ እንጂ!
ወለላ እኔን ስትቀጠቅጥ እና ባሎች አግብታ ስትፈታ ኖራ......ኖራ......... ኖራ........ የረሳሁላት ከፍተኛ ምግባር አለ፡፡ስትራገም ኖራ ኖራ....... በተጨማሪ ደብዳቤ ስታነብ ኖራ...ኖራ... ለእኔ የማያልቅ ከሚመስል ዘመን በኋላ በሀያ ሁለት ዓመቴ ሞተች፡፡ እሰይ ሞተች!

👍3❤1
“እንደሱ አይባልም!” ትላለች ሌላኛዋ አርጩሜ ረድኤት።
ሰዎች ለምን ይዋሻሉ? ለምንስ እንዲዋሹ ይፈልጋሉ? ማንም የሰፈር ሰው እንደማይወዳት አውቃለሁ፡፡ ታማ ተኝታ መጥተው ሊጠይቋት አልፈቀዱም፡፡ የሞተች ዕለት ለጎረቤቱ መሞቷን
ስነግራቸው ሲያፈቅሯት የኖሩ ያክል፣ ሊያጧት የማይፈልጉ ያህል ሀገር ይያዝ አሉ፡፡ ማንን ነው የሚዋሹት? ከኔ ውጪ
ሊታዘብ የሚችል እነርሱ የሚያውቁት ዘመድ እንደሌላት ያውቃሉ። ምክንያቱም እንኳን የሰፈር ሰው እኔ ራሴ ዘመዶቿን
ያወቅኳቸው ስትሞት ነው። ራሳቸውን ነው የሚዋሹት? ይባስ ብለው እኔም እንድዋሻቸው ይፈልጋሉ፡፡ ረድኤት አባቷ ሲሞት እንዳደረገችው ጉድጓድ ውስጥ ካልገባሁ ብዬ እንድግደረደር
ይጠብቃሉ፡፡ ምን ብዬ ነው የማለቅስላት? ማን ይደብድበኝ? ማን ይስደበኝ? ማን ይርገመኝ? ብዬ? ስለእናቴ ሊመጣልኝ
የሚችለው ምስል ይሄ ብቻ ነው፡፡ ከራሷ ውጪ ማንንም አለመውደዷ፡፡
ከወለላ ሞት በኋላ “አባትህ ነኝ ብሎ አንድ ደልዳላ ሰው መጣ፡፡ወለላን ከፈታ በኋላ ሌላ ቤተሰብ መስርቶ ሶስት ልጆች
መውለዱን ነገረኝ፡፡ ብዙ የምጠይቀው ጥያቄ ቢኖርም አንዱን ብቻ መጠየቅ ቻልኩ።
“ወለላ አንተ ጥላኻት ከመሄድህ በፊት እንዴት ዓይነት ሴት ነበረች?”
“ባወቅካት መንገድ ብቻ እወቃት:: ላንተ እናትህ ናት። ለኔ ሚስቴ ነበረች፡፡ በየቱም መንገድ ወለላ እንደ እናትና እንደ
ሚስት አንድ አይነት ሴት ልትሆን አትችልም፡፡” አለኝ፡፡
“እጅግ እጠላታለሁ!” ያልኩት አስቤው አልነበረም፡፡ ድምፅ ማውጣቴ የገባኝ የእርሱን መደንገጥ ሳይ ነበር፡፡ ብዙ ነገር
የገባው መሰለኝ፡፡ መሰለኝ ብቻ!! ጥሎኝ ከቤት ሲወጣ ተከትዬው ወጣሁ።
“ወለላ እንዳረገዘችህ ሳውቅ ስምህን ቅዱስ ነበር ያልኩህ፡፡ ቅዱስ ጌታነህ” የአባቴን ስም ገና ዛሬ መስማቴ ነው፡፡ ይሄን ብሎኝ የአጥሩን በር ከፍቶ ወጣ፡፡ የእርሱን እግር ተክታ ረድኤት ገባች፡፡
“ማነው?” አለችኝ ።
“አባቴ!” ወደቤት እየገባሁ መለስኩላት፡፡ የምትናገረው ነገር የጠፋባት መሰለኝ፡፡ ሆኖ እንደማያውቀው ለደቂቃዎች ዝም
አለች።
ስሜ ቅዱስ ነበር። ቅዱስ ጌታነህ!" አልኳት። ሰውየው ስሜን ሲነግረኝ የተሰማኝ ስሜት የስም ለውጥ
የተነጠቅኩትን ማንነቴን መልሼ ያገኘሁ ዓይነት እንጂ!! ራሴን የሆንኩ አልመሰለኝም።