#የመስኮት_ዳር_ምህላ
በባእድ አገር መኖር፣ የተራዘመ ሞት ፍርድ ነው
ብለው ሲሉኝ፣ እያለቀስኩ እስቃለሁ
ከሞት መታገል አውቃለሁ
ወደ ባሕር ስወረወር፣ አፀድ መሃል እወድቃለሁ።
ይሄ መስኮት ይመስክር
የመስታወት ሀውልት ሁኖ፣ ያሳለፍኩትን ይዘክር!
ይሄ ሁሉ መከራ
ይሄ ሁሉ የበረዶ ጭፍና
በኮቴው ደቅድቆኝ ያልፍና
ታሪኬን ለመንገር እቆያለሁ
የቅጠሎቼን ትንሣኤ አያለሁ!
በባእድ አገር መኖር፣ የተራዘመ ሞት ፍርድ ነው
ብለው ሲሉኝ፣ እያለቀስኩ እስቃለሁ
ከሞት መታገል አውቃለሁ
ወደ ባሕር ስወረወር፣ አፀድ መሃል እወድቃለሁ።
ይሄ መስኮት ይመስክር
የመስታወት ሀውልት ሁኖ፣ ያሳለፍኩትን ይዘክር!
ይሄ ሁሉ መከራ
ይሄ ሁሉ የበረዶ ጭፍና
በኮቴው ደቅድቆኝ ያልፍና
ታሪኬን ለመንገር እቆያለሁ
የቅጠሎቼን ትንሣኤ አያለሁ!