#ኖረሽ_እይው_በቃ
ጨለማ ነህ ብለሽ፣ እኔን ስትተቺ
ዘልለሽ አትጠግቢ፣ ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሀ-ጽጌ* ነው፣ አመት ሙሉ ላንቺ።
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
ለፍጥረት ሰቆቃ
ለጋ ነው አእምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
በየጎዳናሽ ላይ፣ አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፣ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ ፈልቶልሽ፣ አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፣ የብቻነት ሸከሙን።
አዎ
መፈቀር መታጀብ፣ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት፣ አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ንፋስ ማቀፍ
አንዳንዴ ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት፣ የማያልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
አንቺ ደስታ ወዳጅ!!
በለምለም አፀድ ውስጥ፣ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፣ እንደ ጣኦስ* ቀልማ
እንዳትሸወጂ፣ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ሕይወትም እንደጃርት፣ የሾህ ቀሚስ አላት።
ተድላም ከሀዘን ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሣቅ በስተጀርባ፣ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
ጨለማ ነህ ብለሽ፣ እኔን ስትተቺ
ዘልለሽ አትጠግቢ፣ ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሀ-ጽጌ* ነው፣ አመት ሙሉ ላንቺ።
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
ለፍጥረት ሰቆቃ
ለጋ ነው አእምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
በየጎዳናሽ ላይ፣ አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፣ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ ፈልቶልሽ፣ አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፣ የብቻነት ሸከሙን።
አዎ
መፈቀር መታጀብ፣ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት፣ አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ንፋስ ማቀፍ
አንዳንዴ ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት፣ የማያልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
አንቺ ደስታ ወዳጅ!!
በለምለም አፀድ ውስጥ፣ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፣ እንደ ጣኦስ* ቀልማ
እንዳትሸወጂ፣ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ሕይወትም እንደጃርት፣ የሾህ ቀሚስ አላት።
ተድላም ከሀዘን ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሣቅ በስተጀርባ፣ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላም አልልሽም፣ ኖረሽ እይው በቃ።
👍1