#የባከነ_ሌሊት
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኰከብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቆሜ
ቤተስኪያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ስር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ፣ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
“በዑራኤል ርዱኝ” ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ስር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ፣ ሲሻኝ ዶክተር ሆኜ
ወይ ምግባር አልሰራሁ
ወይ ጀብድ አልፈጸምኩኝ፣ ወይ ጽድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሊባከን ዝም ብሎ
እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ”
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋዬን ሳትሰብረው።
ወግ ቢጤ ምንጭሬ፣ ፈስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
እናትዋን ጨረቃ” የሚል ግጥም ሳልጽፍ።
አንዲት ሴት አዳሪ፣ ቺቺንያ መንገድ ላይ
ዕድሏ.ሰባራ ሰውነቷ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዘው የሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠብቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
ኧረ በናታችሁ በወላድ ማሕፀን
እህት የላችሁም?” ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው፣ በደሏ አንገብግቦኝ
ከኋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ፣ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ፣ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከኋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መካከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቴ ካልቻልኩ በሣቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳላረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለ ምንም ጣጣ ያለምንም ጸጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።
ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኰከብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቆሜ
ቤተስኪያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ስር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ፣ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
“በዑራኤል ርዱኝ” ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ስር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ፣ ሲሻኝ ዶክተር ሆኜ
ወይ ምግባር አልሰራሁ
ወይ ጀብድ አልፈጸምኩኝ፣ ወይ ጽድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሊባከን ዝም ብሎ
እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ”
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋዬን ሳትሰብረው።
ወግ ቢጤ ምንጭሬ፣ ፈስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
እናትዋን ጨረቃ” የሚል ግጥም ሳልጽፍ።
አንዲት ሴት አዳሪ፣ ቺቺንያ መንገድ ላይ
ዕድሏ.ሰባራ ሰውነቷ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዘው የሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠብቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
ኧረ በናታችሁ በወላድ ማሕፀን
እህት የላችሁም?” ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው፣ በደሏ አንገብግቦኝ
ከኋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ፣ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ፣ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከኋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መካከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቴ ካልቻልኩ በሣቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳላረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለ ምንም ጣጣ ያለምንም ጸጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።