#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ፀጋ አባቷ እቅፍ ላይ እንዳለች ፈገግ በማለት የራሄልን ትኩረት ለመያዝ ሞከረች፣ በዚህ ጊዜ እናቷ ጣልቃ ገብታ መናገር ጀመሩ ፡፡
‹‹ራሄል፣ ከዶክተር ኤሊያስን ጋር እንድትተዋወቂ እፈልጋለሁ። እሱ የፀጋ ሐኪም ነው…ዔሊ ይህች ልጃችን ራሄል ናት።››
ዶ/ሩ በስሱ ፈገግ በማለት ‹‹ሰለአንቺ ብዙ ሰምቼያለው ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ አምን ነበር›› በማለት እጁን ወደ እሷ ዘረጋ
ጨዋነት ያልጎደለው ፈገግታ ፈገግ አለችለት እና የዘረጋውን እጅን ጨበጠች፡፡ወላጆቿ ከእሱ ጋር አማች ለመሆን እያሴሩ እና እሱንም እያደፋፈሩት እንደሆነ ታውቃለች…ቢሆንም የሱ ጥፋት አልነበረም።
‹‹የሞተር ሳይክሉ ሰው ነህ አይደል?››
‹‹አዎ… ነኝ›› አላት፡፡
እጁ ሞቃታማ፣ ጣቶቹ ረዣዥም ነበሩ፣ እና ሲነካት ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የመወሰድ አይነት የግንዛቤ ብልጭታ በአእምሯዋ ተንፀባረቆ ነበር….ስሜቱን አልወደደችውም። ‹‹በዛ ፍጥነት ስታበር ገርሞኝ ነበር››አለችው፣ትንፋሽ ወሰደችና ‹‹ደግሞ ዶክተር መሆን እና …..››
‹‹እና ምን?›› ከአንደበቷ ቀልቦ ጠየቃት።
‹‹ከተሸከምከው ሃላፊነት አንፃር ሞተር ማሽከርከር….አንድ ነገር ቢደርስብህስ?››
‹‹ለጊዜው አቅሜ የሚፈቅደው ርካሹ እና ፈጣኑ መጓጓዣ ሞተር ነው. እና ደግሞ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ.››ሲል መለሰላት፡፡
ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ‹‹ሁሉም የሚያቀነቅናቸው ታዋቂ የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው…ጥንቃቄ አደርጋለው..››አለች በንዴት፡፡
በመጠኑ ደፍረስ ባሉት አይኖቹ በትኩረት ተመለከታት…ከመተዋወቃቸው እየሰጠችው ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግራ አጋብቷታል…
እናትዬው ፀጋን ከአቶ ቸርነት እቅፍ ወሰድና፡፡‹‹በሉ ወደምግብ ጠረጴዛው እንሄድ….ምሳ ዝግጁ ነው››ሲሉ አወጁ፡፡
ሁሉም ወደምግብ ጠረጴዛው ተከታትለው ሄዱ፡፡ራሄል፣ የተለመደውን ቦታዋ ላይ ተቀምጣለች፣ ዔሊያስ ከእሷ ፊት ለፊት ተቀምጠ።››
አቶ ቸርነት በቀኝ እጇቸው የሴት ልጇቸውን እጅ ግራ እጇቸው ደግሞ በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና። ‹‹ብዙውን ጊዜ ከምግብ በፊት እንፀልያለን››ሲሉ ለዔሊያስ ገለጹለት።
‹‹እኔ ደስተኛ ነኝ. በቤተሰቦቼ ቤትም ስርዓቱ እንዲሁ ነው.››ሲል መለሰ፡፡አባቷ እጇን ጨምቀው ነበር፣መጸለይ ሲጀምሩ አንገቷን ዝቅ አደረገች።አባቷ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ማዳመጥ ብትጀምርም ከጸሎቱ ጋር በልቧ መቀላቀል አልቻለችም። እሷ በሀይማኖት ስርዓት ውስጥ ተወልዳ ያደገች ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከመስመር ወጥታለች። አምላክ በህይወቷ ጣልቃ እንዲገባ አትፈልግም ወይም ደግሞም እሱ ራሱም ለእሷ ደንታ እንደሌለው ታምናለች።ስለዚህ ለምን ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ወላጆቿ በዚህ መሳኔዋ ደስተኛ እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃለች ቢሆንም ግን ርቀታቸውን በመጠበቃቸው ታመሰግናቸዋለች። እና ምናልባት ወደቀልቧ እንድትመለስ ዘወትር ለእሷ በድብቅ ይፀልዩላት ይሆናል፡፡
ፀሎቱ ተገባዶ በ‹‹አሜን›› እንደተዘጋ እናትዬው ‹‹በሉ እራሳችሁን አስተናግዱ ››አለቻቸው፡፡ሁሉም ፊት ለፊቱ ባለው ሳህን ላይ ፊለፊታቸው ከተደረደሩት በርካታ የምግብ ዓይነቶች የሚፈልጉትን መጠን መውሰድ ጀመሩ፡፡ተ
‹‹ከቻልክ ክትፎውን አቀብለኝ››ስትል ራሄል ወደኤልያስ እያየች አጉተመተመች፣
እናትዬው የራሄልን አስተያየት ውድቅ በማድረግ እጆቿን እያወዛወዘ ‹‹እስኪ እንደአንበሳ ስጋ ማሳደድሽን አቁሚ።››በማለት ገሰፃት፡፡ ቀጠል አደረጉና ‹‹ለሚያገባሽ ሰው አዝንለታለው።››ሲሉ አከሉበት፡፡
‹‹ደህና፣ ደስ ሚለው ነገር ፍቅረኛ የለኝም ››አለች ራሄል፡፡
‹‹እነዚህማ የተለመዱ ቃላቷችሽ ናቸው››
እናቷ በራሄል ንግግር ተከፍተው ‹‹አንድ ቀን ያንን በብቸኝነት የቀዘቀዘ አፓርታማሽን እርግፍ አድርገሽ ጥለሽ እንደ ዶ/ር ኤሊያስ ቤት አይነት ግቢ ወዳለው ቤት ትቀይሪ ይሆናል።››ሲሉ ምኞታቸውን ተናገሩ፡፡
እናትዬው ወደ ዶ/ሩ ዘወር አሉን‹‹ቤትህን በማስተካከል ላይ እንዳለህ ሰምቼያለው?››
‹‹በእውነቱ ወንድሜ ቢንያም ነው እየተከታተለው ያለው። እሱ አናጺ ነው። ስለ ኩሽና አሰራር አንዳንድ ውሳኔዎችን እንድወስን እየጨቀጨቀኝ ነበር, ነገር ግን ዘመናዊ ይሁን ወይም ባህላዊ ጭብጥ ይኑረው የሚለውን ለመወሰን እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም››
አቶ ቸርነት‹‹ራሄልን ይዘሀት ብትሄድ ልትረዳህ ትችል ይሆናል››የሚል ሀሳብ አቀረቡለት። ዔሊያስ የራሔልን መኮሳተር ችላ በማለት እንደ ተወደደ ልጅ ፊቱ እያበራ ነው።
አንቷም ‹‹አዎ የእኔ ልጅ …በኢንቴርዬር ዲዛይን ላይ በጣም ጎበዝ ነች።››ሲሉ የአባትዬውን ሀሳብ ደገፉ፡፡
ራሄል ስለእሷ የተሰጠ ያለው አስተያየት ከየት እንደመጣ አታውቅም። ወላጆቿ አፓርታማዋን በሚጎበኙበት ጊዜ በዕቃዎቾ፤በምንጣፎች እና በመኝታ ቤቷ ቀለም ..ብዙ ብዙ ኔጌቲቨ የሆነ አስተያየት ሲሰጧት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እንደውም እናቷ ‹ጥቂት እንኳን ለስሜቷ ሳይጨነቁ ቤቷን መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚየም እንዳስመሰለችው ነግረዋት ነበር፡፡
‹‹የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ። ትልቁ ችግሬ ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን ጊዜ ማግኘት አለመቻሌ ነው ›› ሲል ኤሊያስ መለሰ።
ራሄል የሆነውን ነገር የተረዳች መስላ‹‹እንድትጨርሰው የምትገፋፋህ ሴት የለችም?››ስትል ጠየቀችው፡፡
አባቷ ራሄልን በግንባራቸው ገፆት ፡፡
ዶ/ሩ ‹‹ለጊዜው አቋሜ ልክ እንደአንቺው ነው….ለሴት ዝግጁ አይደለሁም››ሲል መለሰ።
ራሄል ውይይቱ ወደ መሃል ከተማ የትራፊክ ፍሰት፣ የኑሮው ውድነትና ፣ እና የፖለቲካ ውዥንብር.እና የሰላም እጦት የመሳሰሉት ጉዳዬች ላይ ሲያተኩር እፎይ አለች፡፡
በመሀል ወደ ዶ/ሩ አትኩራ እየተመለከተች ‹‹በቅርቡ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አለ።በዝግጅቱ ላይ መገኘትህን ማረጋገጥ አለብህ››አለችው፡፡
‹አረ ችግር የለውም..አታስቢ እገኛለው››ሲል ቃል ገባላት፡፡
እናትዬው‹‹ቀኑ ደረሰ እንዴ..?እንግዲህ በስራ ጫና ድራሽሽ ሊጠፋ ነው››ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁላት፡፡
ራሄል ‹‹እማዬ ደግሞ ….እኔ ብቻዬን የማደርገውን አስመሰልሺው ። አብዛኛውን ስራ የሚሰሩልኝ ትላልቅ ሰራተኞች አሉኝ እኮ››
‹‹ነገር ግን ለሰራተኞችሽ በቂ ውክልና አትሰጪም።ቅድስትን ለመተካት እነዚያን ሁለቱን ረዳቶች መቅጠርሽን ስሰማ ብዙ የስራ ጫናሽን ያቃልሉልሻል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን አሁን እንደማየው ከሆነ የበለጠ ስራ ነው ያበዛብሽ፡፡››
‹‹ሰራተኞቹ በጣም አዲስ ናቸው ። ፋይሎቹን ብቻ ሰጥቻቸው ሁሉንም ነገር በራሳቸው እንዲቋቋሙት መጠበቅ አልችልም።››
‹‹ዬኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸውና …በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እኮ።››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን የፋውንዴሽኑን ስራ በተመለከተ ትንሽ ተጨማሪ ልምድ ያስፈልጋቸዋል፣ሁሉም ሰው ወደሆነ አዲስ ስራ ሲሄድ ለተወሰነ ጊዜ ከአሰራሩ ጋር እስኪለማመድ አዲስ ሆኖ መገኘት አይቀርም››ለእናቷ ሌላ የማስጠንቀቂያ እይታ ሰጠቻት። ይህን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በማያውቁት ሰው ፊት መወያየታቸውን አልወደደችውም ።
‹‹ውዴ እወድሻለሁ፣ ግን ደግሞ አውቅሻለሁ።››ሲሉ እናትዬው በአቋማቸው መፅናታቸውን አረጋገጡላት፡፡
የራሄልን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ‹‹እና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደምትችይ ማሰብ ማቆም አለብሽ። አንዳንድ ነገሮችን ለእግዚአብሔርን መልቀቅ አለብሽ።››ሲሉ ንግግራቸውን ደመደሙ፡፡

❤53👍5
‹‹እኔም ለእሱ ውክልና መስጠት አልፈልግም››ስትል ራሄል በመኮሳተር መለሰች።
የእናትና ልጅን ንግግር መክረርን የታዘቡት አባት ‹‹ርዕሱን መለወጥ እንችላለን?››ሲሉ ጣልቃ ገቡ፡፡
እናትዬው የፀጋን ፀጉር እየዳበሱ ‹እህትሽ መያዝ ትፈልጊያለሽ?››ብለው ጠየቋት።ራሄል በእናቷ እቅፍ ውስጥ ተመችቷት የተኛችውን ታዳጊ ተመለከተች። ይሄኛውም የሚመቻት የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ አልነበረም።እሺ ብላ ተቀብላ መያዝ እንዳለባት ታውቃለች፣ነገር ግን ስህተት እንዳትሰራ ፈራች።
ዔሊያስም ፍርሃቷን እንደተረዳ በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ‹‹አይዞሽ ..ታደርጊዋለሽ›› ሲል አበረታታት፡፡ማበረታቻውን ግን እንደለበጣ ነው የቆጠረችው፡፡ፀጋን በጎሪጥ ተመለከተች… ዓይኖቾ እየተቁለጨለጩ እሷን ሲመለከቱ አየች። እጆቾ ተዘርግተዋል …እግሮቿ ግትርትር እንዳሉ ነው…. ፀጋ በድንገት አሳዛኝ ለቅሶ አሰማች ።
‹‹ ልጄ፣አይዞሽ….›› ወ.ሮ ትራሀስ ለራሄል ሊያስታቅፏት ሞከሩ… ፀጋ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም። ራሄል ወደ ፊት ተወረወረች እና የፀጋን የተወጣጠረ ሰውነት በማየቷ ልቧ ደረቷ ውስጥ ዘሎ የተሰነቀረ መሰላት።ዶ/ር ኤሊያስም መቀመጫውን ለቆ ፈጠን ብሎ ስሯ ተቀመጠና የፀጋን ሰውነት እያገለባበጠ ተመለከታት ‹‹ የጡንቻ መወጠር ይመስላል እግሮቿን መታሸት አለባቸው››አለ ፡፡ ወ.ሮ ትርሀስ እንደተናገረው የፀጋን እግሮች ማሻሸት ጀመሩ… እናም ሰውነቷ ቀስ እያለ ሲዝናና ራሄል በእፎይታ ተነፈሰች።
‹‹አየሽ? መጥፎ አይደለም››
‹‹አይ. ቢሆንም ትንሽ ፈርቼ ነበር››አለች ራሄል፡፡
ወ.ሮ ትርሀስ ወደ ራሄል ተመለከቱና እና ‹‹አሁንስ እሷን መያዝ ትችያለሽ?››ሲሉ ድጋሚ ጠየቋት፡፡
ራሄል መልስ ከመስጠቷ በፊት ኪሷ ውስጥ ያለው ስልክ ጮኸ ፡፡ አውጥታ ስታየው የደወለላትን ሮቤል ነበር፡፡ልክ እንደአዳኟ መልአክ ነበር የቆጠረችው።
‹‹ይቅርታ እማዬ ይህን ጥሪ ማንሳት አለብኝ››በማለት ይቅርታ ጠይቃና ለተፈጠረው ችግር አመሰግናለሁ፣ ኮሪደሩን ተጠቅማ ወደ ጓሮ በመሄድ ስልኩን አነሳችው፡፡
‹‹ሮቤል እንዴት ነህ?››አለችው።
‹‹ደህና ነኝ …ሴትዬዋ እንደገና ሀሳቧን ቀይራለች››አእምሮዋ በዚህ አዲስ ችግር ዙሪያ ተወጣጠረ፡፡ ራሄል ሁል ጊዜ ስትጨናነቅ እንደምታደርገው ጥፍሯን በጥርሶቿ ቀረጠፈች።‹‹ዛሬ ልታገኘን እንደምትፈልግ ተናግራለች›› ሮቤል ቀጠለ። ‹‹በእርግጥም ከአርባ አምስት ደቂቃ በፊት እዚያ መሆን ነበረብሽ.. ነገር ግን በወላጆችሽ ቤት እንደሆንሽ ስለሰማው ተውኩት።››አላት፡፡
የእህቷ ረዳት አልባ ለቅሶ ድምፅ ስታስታውስ ትንሽ ደነገጠች። ይህቺን በህመም የምትሰቃይ እና ከፍተኛ እንክብካቤ የምትፈልግ ህፃን ልጅ ለማሳደግ ወስነው በመውሰዳቸው ወላጆቿን በጣም አደነቀቻቸው። እሷ በእንሱ ቦታ ብትሆን ፈፅሞ ማድረግ እንደማትችል ታውቃለች።
‹‹ይቅርታ አድርግልኝ?››
‹‹ግድ የለም አሁን ችግሩ ምንድን ነው?››
‹‹ወ/ሮ ላምሮት የፋውንዴሽኑን የሩብ አመት ሪፖርት ማየት ትፈልጋለች። በእድገት ላይ እንደሆነ ማረጋገጥ ትፈልጋለች።››
ዔሊያስን በበሩ ላይ በዛ ቁመቱ ተጋርጦ ቆሞ ተመለከተችው።
‹‹እናትሽ በበረንዳው ላይ ኬክ እና ቡና እየቀረበ እንደሆነ እንድነግርሽ ጠይቃውኝ ነው›› አላት፡፡
‹‹አመሰግናለሁ… ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሁላችሁንም እቀላቀላችኋለው››በማለት ጠንከር ያለ ፈገግታ ሰጠችው፣
እሱ ግን ምንም አይነት የስሜት ለውጥ ሳያሳይ ፊቱን አዙሮ ሄደ። ከእሱ ጋር በመተዋወቋ ግልፅ ያልሆነ ምቾት እንደተሰማት መካድ አትችልም።የፀጋ ማራኪ ሐኪም ስለ እሷ ምን እንደሚያስብ ለማወቅ ለምን እንደምትጨነቅ አሰበች..እንደምንም እራሷን አረጋግታ ትኩረቷን ወደ ሮቤል መለሰች።
‹‹በሰዓቱ እንደምገኝ ለወይዘሮ ላምሮት ንገርልኝ››በመስኮቱ አሻግራ በአባቷ ጥናት ክፍል ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የአያቷን ሰዓት ተመለከተች። ‹‹አንድ ሰዓት ያህል አላት››
‹‹ራሄል አንቺን ማጨናነቅ አልፈልግም ነበር….ግን ቶሎ ልታደርጊው ትችያለሽ?››
‹‹አዎ እችላለው፣ሴትዬዋ የምትኖረው በቸርቸል ጎዳና አካባቢ ነው...በ50 ደቂቃ እዚያ ለመድረስ ብዙም የምቸገር አይመስለኝም… ወላጆቼን ብቻ ተሰናብቼ አሁኑኑ ወጣለው ። ››
‹‹እሺ እንግዲህ፣ ስትደርሺ እዛው ቀድሜ እጠብቅሻለው::›› ራሄል ከንፈሯን ነክሳ የስልኩን ቁልፉ ተጫነችና ዘጋችው።አሁን ልሄድ ነው በማለቷ ወላጇቾ ደስተኛ አይሆኑም, ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ምንም ማድረግ አትችልም. ወ.ሮ ላምሮት ለፋውንዴሽኑ በጣም አስፈላጊ ሴት ነች። ዝግጅቶች በምታዘጋጅበት ጊዜ የታዋቂ እንግዶች ዝርዝር ለማውጣት በሚያስፈልግበት ጊዜ እሷ ከዋናዎቹ የዘወትር ለጋሾች ውስጥ ዋነኛዋ ነች።ወ.ሮ ላምሮት ባሏ ሲሞት ብዙ ገንዘብ በውርስ አግኝታለች፤በዛ ላይ በሀገሪቱ በብዙ ካምፓኒዎችን ታስተዳድራለች….እናም በባሏ ኑዛዜ መሰረት ከአመታዊ ትርፏ 25 ፐርሰንት ለበጎ አድራጎት ድርጅት መስጠት አለባት…እንግዲህ የእሷን ፋውንዴሽን ጨምሮ ሁሉም በሀገሪቱ በበጎአድራጎት ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች በጠቅላላ የእሷን ገንዘብ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ…. ። ራሄል ይህቺን ሴት በትክክል ካልያዘች፣በቀላሉ የእሷ ካምፑ በመልቀቅ ለተቀናቃኞ ፋውንዴሽን ገንዘቧን ለመስጠት ልትወስን ትችላለች። ህጋዊ የሚመስሉ ነገር ግን እስከ ሰማንያ በመቶ የሚሆነውን የለጋሾቻቸውን ገንዘብ “የአስተዳደር ክፍያ” ስም ለግል ጥቅማቸው ስለሚያውሉ ድርጅቶችን በሰማች ቁጥር የራሄል ደም እንዲፈላ ነው የሚያደርጋት፡፡እና የሴትዬዋን ልገሳ የማይሆኑ ድርጅቶች እጅ ገብቶ የግለሰቦች ኑሮ መዶጎሚያ እንዳይሆን መከላከልም አንደኛው አላማዋ ነው፡፡በእሷ ድርጅት የአስተዳደር ወጪ ከ25 በርሰንት መብለጥ እንደሌለበት ጥብቅ የሆነ መመሪያ አለ፡፡ለዛም ነው በዋናው ቢሮ ከሁለት ረዳቷቾ ጋር ሆና የአስር ሰው ስራ የምትሰራው፡፡
ወደውስጥ ስትገባ ወላጆቿ ቀደም ብለው በረንዳ ላይ ተቀምጠው ነበር ፣ የቀዘቀዘ ሻይ የያዘ ረጅም ኩባያ ከፊት ለፊታቸው ባለው የመስታወት ጠረጴዛ ላይ ይታያል።
ራሄል ስትደርስ ፀጋ በእግሮቾ ላይ ትልቅ ብርድ ልብስ ለብሳ እየተጫወተች ነበር፣ ለራሄል ፈገግ አለችላት፣ ቀላል ቡናማ አይኖቿ በምሽት መጀመሪያ ላይ ሲያበሩ ስትመለከት ደስ አላት። ራሄል ቆንጆ መሆኗን በውስጧ አሰበች፡፡
‹‹ እማዬ፣ አባዬ፣ ይቅርታ ዶ/ር …››ዓይኖቿ ዔሊያስ ላይ ተተከሉ ፣ ‹ አዝናለሁ ግን ሮቤል አሁን ደወሎኝ ነበር። ከለጋሾቻችን ከአንዷ ጋር ድንገተኛ ችግር ገጥሞናል ።ሄጄ ማስተካከል አለብኝ››
‹‹ኧረ ማር፣ ለምን እሱ ራሱ እንዲያስተካክለው አትተይለትም?››እናትዬው ተቃወሟት ፡፡
ወ.ሮ ትርሀስ ወደ ባላቸው ዞረው። ‹‹ቸርነት ፣ አናግራት እንጂ ።››አቶ ቸርነት ዝም ብለው ትከሻቸውን ከፍ በማድረግ ለልጃቸው ፈገግ አሉ።
‹‹ብትቆዪ ምኞቴ ነው ውዴ። ብዙ ጊዜ አናገኝሽም። ትንሿ እህትሽ እንኳን በደንብ አታውቅሽም…ከዚህ በተጨማሪ፣ እናትሽ ለአንቺ ብቻ ያዘጋጀችው የቸኮሌት ኬክ አለ›› አላት፡፡
ወ.ሮ ትርሀስም ‹‹አባትሽን ታውቂዋለሽ እና እኔም እንደዚህ አይነት ነገር አልበላም.››
‹‹በጣም አዝናለሁ እናቴ፣ ግን ኬኩን ብወስደው ደስ ይለኛል -››
‹‹እንግዲህ አልቆይም ካልሽ ምን አደርጋለው…አዘጋጅልሻለሁ።››ወ.ሮ ትርሀስ ከወንበራቸው ተነስተው ቆሙ‹‹በፍጥነት እመለሳለሁ››ብለው ወደውስጥ ገቡ፡፡

❤42👍5🥰2
ራሄል ሰዓቷን ለማየት በድብቅ የሸሚዟን እጅጌ ወደላይ ሰብሰብ አደረገችና ተመለከተች። ለመሰናበት ካሰበችው ጊዜ በላይ እየወሰደባት ነው፡፡በቀራት ደቂቃ ቀጠሮው ቦታ ለመድረስ የመኪናዋን ፍጥነት ከተገቢው በላይ ለመልቅ ልትገደድ እንደምትችል አሰበች፡፡የተጨናነቀ ትራፊክ እንዳያጋጥማት እየተመኘች ሸሚዞን ወደ ቦታው መለሰች፡፡ድንገት ዶ/ሩ በግማሽ ፈገግታ በትኩረት ሲመለከታት ያዘችው። ራሄል ይህን አልለመደችም። አብዛኞቹ ወንዶች ከእሷ ጋር እንዲህ አይነት የዓይን ጫወታ መጫወት አይደፍሩም፡፡
አባቷ ፀጋን በእቅፋቸው ይዘው እያጫወታት ነው‹‹አይዞሽ ልጄ ..ትደርሺያለሽ. .አትጨናነቂ…ሁሉነገር እግዚያብሄር ከፈቀደ ይሆናል…ካልፈቀደ ደግሞ ምንም ብትለፊ የቱንም ያህል ብትጥሪ አይሆንም››የሚል ምክር አከሉበት፡፡
የአባቷን ስብከት ውጦ ለመቀበል ትዕግሥት አጣች፡፡ ወዲያው ደግሞ እሳቸው እንደሚያምኑት ማመን ባለመቻሏ እፍረት ተሰማት። አባቷ በእምነታቸው ቅን ሰው ናቸው። እሳቸው በዚያ መጠን በእግዚያብሄር እያመኑ መቀጠላቸው እሷን ሊያበሳጫት አይገባም ነበር፡፡ እንዲያውም እሷም እንደእሳቸው በአምላክ ላይ ያላትን እምነት ለመጋራት የምትመኝበት ጊዜ አልፎ አልፎ ነበር። ግን ማድረግ አልቻለችም፡፡
ለአባቷ መልስ መስጠቱን ተወችውና እይታዋን ወደ ዶ/ሩ አዞረች፡፡እጆቹን ቁልቁል እያየ ነበር፣ የአንዱን እጁን ጣቶች ወደ ደረቱ ወሰደ ፤ከዛ በኋላ ነበር ከክርኑ አንጓ እስከ አውራ ጣት ግርጌ ድረስ የሚሄድ ረዣዥም የተሰነጠቀ ጠባሳ እንዳለበት ያስተዋለችው። በደንብ ያልተሰፋ ይመስል ነጭ እና የተቦጫጨቀ ሆኖ ይታይ ነበር። ሞተር ሳይክሉን ሲያበር ያገኘው አደጋ ይሆናል ስትል አሰበች ፡፡በዚያን ጊዜ ቀና ብሎ አያት።
‹‹ኬክሽ ይኸውልሽ ውዴ።››ወ.ሮ ትርሀስ አንድ መለስተኛ የታሸገ ካርቶን በሰማያዊ ፔስታል ውስጥ አድርገው አቀበሏት፡፡ ራሄል ፔስታሉን ተቀበለችና በእጇ እየመዘነች ‹‹ይህ ግማሹ ነው››አለች ።
‹‹ቀሪውን ደግሞ እኔና አባትሽ አንበላዋለን - ››
‹‹ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ምግቦቼ የቸኮሌት ኬክ እንደሆነ በምናቤ ሳስብ ደስታ ተሰማኝ ።››
‹‹ማር, እንዳታደርጊው››ወ.ሮ ትርሀስ ፊታቸውን በማኮሳተር ኬኩን መልሰው ሊወስድባት ሞከሩ፡፡
‹‹አይ, አታደርጊውም››ራሄል እናቷ እቃውን እንዳይነጥቋት እየተከላከለች ‹አትጨነቂ እኔ እየቀለድኩ ነው. ዛሬ ማታ አንድ ቁራጭ ከላዩ ላይ በላለትና የቀረውን ወደ ሥራ ቦታ እወስደዋለው፡፡እርግጠኛ ነኝ ሮቤል እና ሎዛ በዚህ ኬክ ላይ ይጣሉበታል.››
‹‹አዎ እንደዛ ነው ማድረግ ያለብሽ››
‹‹አሁን ሳሙኝ እና ብሄድ ይሻላል።››
ራሄል እናቷን በፍጥነት አቅፋ ሳመች እና ከአባቷ እና ከፀጋ ጋር ተመሳሳይ ነገር ለማድረግ ጎንበስ ብላ ሳመቻቸው።ከመሄዷ በፊት በዔሊያስ ላይ ዓይኗን ጣለች። እሱ በሁለት ሜትር ርቀት ላይ ነበር፣ ነገር ግን በዚያ ርቀት ላይ ቢሆንም ሰውነቷን የዳሰሳት አይነት ስሜት ነው የተሰማት።ወደ መኪናዋ ስትሄድ ስሜቷን ተናወጠ።
ስትመለስ ለወላጆቿ ሁሉን ነገር ግልጽ የምታደርግላቸው መስሏት ነበር። አስፈላጊው የእናት እና የሴት ልጅ ውይይት ጊዜ እንደደረሰ አውቃለች። በተቃራኒው ራሄል በአጀንዳው ላይ የሚቀጥለውን ንጥል ፋይል ስትከፍት ማዛጋት ጀመረች።
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

❤39👍7
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ከወ.ሮ ላምሮት ጋር የተደረገው ስብሰባ በጣም ረጅም ጊዜ ወስዶ ነበር እና ውጤቱ በጣም ጥቂት የሚባል ነበር፡፡
ራሄል በጣም የደክማት ቢሆንም ቢሮዋ ገብታም ስራዋን ቀጥላለች፡፡
‹‹ጥሩ ነው…በብሮሹሮች ላይ ስህተቶችን አግኝቻለሁ.››
ሎዛ ወረቀቶቹን በመካከላቸው ባለው የእንጨት ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠች። ራሄል በተቀመጠችበት የቆዳ ሶፋ ላይ ወደ ኋላ ተደግፋ ከፊቷ ያለውን ብሮሹር ቃኘች። ‹‹ይህ ሰማያዊ ቀለም በጣም ደማቅ ነው….እና ይህ ቢጫው ደግሞ እንዲጠናከር እፈልጋለሁ። የቀረውን ደግሞ ደውዬ አሳውቃቸዋለሁ››
‹‹ለምን ያን እኔ ራሴ እንድከታተል አትፈቅጂልኝም?›› አለች ሎዛ
‹‹አመሰግናለሁ ሎዛ.. ግን ማየት የምፈልገውን በትክክል አውቃለሁ።››
ሎዛ ራሷን በይሁንታ ነቀነቀች፣ ራሄል ግን በእሷ ውሳኔ ደስተኛ እንዳልነበረች አይታለች።
‹‹ለአሁን እንዳደርግ የምትፈልጊው ሌላ ነገር አለ?››ሎዛ ጠየቀች።
‹‹ አይ ምንም የለም… በቃ እጅሽ ላይ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጊ።››የሚል ትእዛዝ ሰጠቻት፡፡
ራሄል ወረቀቶቹን በጠረጴዛዋ ላይ አስቀመጠች እና ሎዛ ቢሮዋን ስትለቅ ወደ ሮቤል ዞረች።
‹‹ሮቤል አንተ የሆነ ነገር አንድታደርግልኝ እፈልጋለው››አለችው፡፡
ሮቤል ጎንበስ ብሎ ከቆዳው ቦርሳ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና‹‹ጥቂት ስልክ ደዋውዬ ከምንጩ ያገኘሁት መረጃ ነው።›› በማለት ተጨማሪ ወረቀቶችን አቀበላት።
‹‹ከስብሰባው ጥቂት ቀደም ብሎ ከድርጅቱ ኃላፊ ጋር በግል ተወያይቼ ነበር።››
‹‹ጉልበቱን ከየት አመጣው?››ስትል አሞገሰችው፡፡ ራሄል ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ከተገናኘ በኋላ ስላከናወናቸው ውይይቶችና ስለተለዋወጦቸው ቃላቶች በማሰብ ደክሞት ነበር።‹‹ይህ በጣም ጥሩ ነው፣ቀጣዩ እርምጃችን የበጎ አድራጎት ልገሳ ሁኔታቸውን ማረጋገጥ እና ከቻልን በእነሱ ላይ አንዳንድ ጥልቅ የጀርባ ስራዎችን መስራት ነው።››
‹‹እንደተፈጸመ ቁጠሪው.››ሲል ሮቤል ፈገግ አለ። በዚህ ጊዜ ስልኳ ጠራ…እናቷ መስመር ላይ ነበረች።‹‹እንደገና አመሰግናለሁ ሮቤል።በቅርብ ጊዜ ፋውንዴሽኑን እንደተቀላቀለ ሰው ምርጥ ስራ ሰርተሃል.›› ብላ ስልኩን አነሳች፡፡
ራሱን ነቀነቀና ዞር ብሎ ከቢሮ ወጣ።ራሄል ከኋላው ባለው ትልቅ የቆዳ ወንበር ላይ ለመቀመጥ በጠረጴዟ ዙሪያ ዞራ ሄደች።
‹‹ጤና ይስጥልኝ እናቴ››
‹‹ደህና ነኝ የእኔ ልጅ››
‹‹ እየሮጥኩ ያለሁት ባንቺ ጉዳይ እንደሆነ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልትደሰቺ ይገባሻል።››ስትል ራሄል ወንበሯ ላይ በመቀመጥ ተሸከረከረች፡፡
‹‹ውዴ፣ ሁሌም በአንቺ ደስተኛ ነኝ ፡ ታውቃያለሽ?››
‹‹እማዬ አውቃለው…የቸኮሌት ኬኩ በጣም ጥሩ ነበር. ሮቤል እና ሎዛ አመስግኚልኝ ብለዋል.››
‹‹እንደተካፈላችሁት በማወቄ ደስተኛ ነኝ። ግን አንቺን አንድ ውለታ ልጠይቅሽ ነው። አያቶችሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ወደ አድዋ ሄደን እንደንጠይቃቸው ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ፀጋን ይዘን ለመሄድ መድፈር አልቻልንም ።እስክንመለሰ እሷን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ነሸ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡ራሄል በድንጋጤ ስልኩ ሊያመልጣት ነበር..በመከራ ነው አጥብቃ የያዘችው።
‹‹ፈቃደኛ? ምናልባት…ቆይ እስኪ ፕሮግራሜን ልመልከት››አለችና የቀጠሮ ደብተሯን ለማየት ማስታወሻ ደብተሯን ከፈተች። በዛን ወቅት የማይሰረዝ ፕሮግራም ኖሯት ያንን እንደምክንያት ማቅረብ እንድትችል በውስጧ ፀለየች፡፡
የወሩ የመጨረሻ ቅዳሜና እሁድ…..ቢንጎ …የበጎ አድራጎት ፈንድ የመሰብሰብ ፕሮግራም አለባት። ‹‹ይቅርታ እማዬ ባልሻቸው ቀናት መሰረዝ የማልችላቸው ፕሮግራሞች አሉብኝ…በነዛ ቀናት አመታዊ የፋውንዴሽኑ ፈንድ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አለብኝ ።››
‹‹ኦህ ውዴ፣ አያትሽ ቤት የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ብቻ ነው።›› በለሆሳስ ተነፈሰች። እና ፀጋን ከማንም ጋር ልተዋት እችላለው? ….እንደምታውቂው እስካሁን በጣም ደካማ ነች።››
‹‹ለምን ስለችግርሽ ከዶክተር ዔሊያስ ጋር አታወሪበትም››ስትል ሀሳብ አቀረበች።
‹‹በእርግጥ ትክክል ብለሻል .. እሱ የግል ነርሲንግ ኤጀንሲን ወይም ተመሳሳይ ነገርን ሊመክረኝ ይችላል?››
ራሄል አሰበች፤ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማት አይገባም። ወላጆቿ ይችን ልጅ ለማሳደግ መወሰናቸው የሷ ሀሳብ አልነበረም። እና ፀጋ ብቃት እንደሌላት እና አቅመ ቢስነት እንዲሰማት ያደረጋት የሷ ስህተት አልነበረም።
‹‹እሷን መንከባከብ ካልቻልሽ ችግር የለውም…›› እናቷ ቀጠለች‹‹እርግጠኛ ነኝ ዔሊ ፀጋን የት ልንወስደት እንደምንችል ያውቃል።››
‹‹እንደሚያውቅ እርግጠኛ ነኝ››ስትል ራሄል ተስማማች፣ እፎይታም ተሰማት።
‹እና ስለ ዶክተር ዔሊያስ ምን አሰብሽ? ››እናትዬው እንደቀልድ ሌላ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹እሱ በጣም ደስ የሚል ሰው ነው…. ከፀጋ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለው ››
ከእሷ ጋር ሊጣመር የሚችልበት ምንም እድል እንደማይኖር ለእናቷ ግልፅ ለማድረግ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማት ‹‹ግን እሱ የእኔ ምርጫ አይደለም ።››ስትል መለሰችላት፡፡
‹‹ምን አልሽ?››
‹‹እማዬ… እባክሽ አሁን ለማንም ቢሆን ጊዜ የለኝም… ታውቂያለሽ››
‹‹ባለፉት ስምንት አመታት ውስጥ ለማንም ጊዜ አልነበራሽም። ብዙ ማህበራዊ ህይወት የለሽም። የምታደርጊው አንድ ነገር ቢኖር ስራ መስራት ብቻ ነው።››
ራሄል ወንበሯን ትንሽ እያወዛወዘች ፊቷን ከሰከሰች። ‹‹ይህን ስራ እፈልገዋለሁ እናቴ…ለህይወቴ ትርጉም የሰጠኝ ስራዬ ነው››
‹‹ከጌታ ጋር ያለሽ ግንኙነትስ? ያ እንዴት አድርጎ ነው ስራሽን የሚጋፋው?››ወደ ማትፈልገው ሌላ ርዕስ ከተተቻት፡፡
‹‹‹እናቴ ሆይ፣ የእኔ ስራ የተቸገሩ ህፃናትንና አቅመ ደካሞችን መርዳት ነው። ኢየሱስ በዚህ ምድር እንድናደርግ የሚፈልገውን ተግባር ነው እያደረኩ ያለሁት።››ራሄል እናቷን የሚያስደስት ትክክለኛ ቃላቶችን ታውቃለች እና ያለ እፍረት ተጠቀመችባቸው፡፡
‹‹ያለ እምነት ሥራ የሞተ ነው ውዴ።›› እናቷ ወደ እምነቷ ሲመጣ…ጥልቅ የማሰብ ችሎታ ስላላት ሁሉንም የልጇን የማጭበርበሪያ ስልቶች ታውቃለች።
ራሄል በመጨረሻ ‹‹እኔ ማድረግ የምችለው ይህን ብቻ ነው እናቴ››አለች. ቀጠለችናም ‹‹ለወንድ ጓደኛ ጊዜ የለኝም እና ለአንድም ሰው ፍላጎት የለኝም። ስለዚህ እባካችሁ ከአሁን በኋላ የማልፈልገውን አይነት አስጨናቂ እራት ለማዘጋጀት አትሞክሩ።››ስትል ንግግሯን በመኮሳተር ደመደመች፡፡
የእናቷ ዝምታ እጅ የመስጠት ምልክት እንደሆነ ተስፋ አድርጋ ነበር።‹‹ደስተኛ ነኝ እማማ›› እናቷ ብርሃኑን እንድታይ ለማድረግ ቆርጣ ገፋችበት። ‹‹ዓላማ እና ትርጉም ያለው ንቁ ህይወት ነው እየኖርኩ ያለሁት ። ጓደኞች አሉኝ እናም በማህበረሰብ ውስጥ አስፈላጊ የሚባል ስራ አለኝ። እና አንቺ እና አባዬ እና ፀጋም አለችሁልኝ። ተጨማሪ አያስፈልገኝም።››
‹‹እሺ፣ ይቅርታ፣ አንቺና ዔሊ ትመጣጠናላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነው። እሱ ጥሩ እና ደግ ሰው ነው..ለዛ ነው ከእሱ መዛመድ የፈለኩት ።››
ራሄል ፊቱ ላይ ስለተመለከተችው ፈገግታ አሰበች‹ደህና፣ ለአንድ ሌላ ሴት ግሩም ባል እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ግን ያቺ ሴት እኔ አይደለሁም፣ እማማ።››
ወ.ሮ ትርሀስ ቃተቱ። ‹‹ካስከፋሁሽ ይቅርታ።››
‹‹አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠርሺብኝ እንጂ አላስከፋሺኝም።››

❤61👍6
‹‹ደህና፣ በቃ ቻው፣ ከአንድ ፊዚዬቴራፒስት ጋር ቀጠሮ አለኝ እና ከዚያ በኋላ ዶ/ር ኤሊያስን አገኘዋለው። ሰላም እንዳልሽው ልንገረው?››እናቷ የማይበገሩ ነበሩ።
‹‹እናቴ የፈለግሽውን አድርጊ…. እወድሻለሁ።››
የእናቷ ድርጊት አንዳንድ ጊዜ እብድ ሲያደርጋት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ እንድታፍር ያደርጋታል… እንደዛም ሆኖ ራሄል ወላጆቿን በጣም ትወዳለች።‹‹አንቺንም እወድሃሸለው ውዴ።››
ራሄል ስልኩን ዘግታ በሀሳብ ተዋጠች። ራሄል እናቷ ፀጋን በማደጎ ወደቤቷ ስያመጣት ውስጣዊ ስሜቷን እንደምታረካላቸው እና እሷ ላይ የሚያደርጉትን ትኩረት ይቀንሳሉ ብላ ገምታ ነበር ግን አሁን እንደምታየው ምንም የተቀየረ ነገር የለም፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronoseቀ

👍32❤13
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
እሁድ የእረፍት ቀን ስለሆነ ኤልያስ ከወንድሙና ከጓደኛው ጋር ካፌ ቁጭ ብለው ቁምነገሩንም ቀልዱንም ሲጫወቱ አረፈድና ሌላ የሚሄዱበት ቦታ ስለነበር ተያይዘው ወጡ፡፡ሶስቱም የቢኒያም መኪና ወዳቆመችበት ቦታ እየተለፉ እየሄዱ ሳለ ድንገት ኤልያስ ከወንድሙ ከቢኒያም ጉሽሚያ ለማምለጥ ወደኃላው ሲሸሽ ከአንድ ውብ ሴት ጋር ተላተመ ፡፡ሴትዬዋ በእጇ የያዘችው ወረቀቶቿ ከእጆቿ ተንሸራተው ወደቁ እና ቦርሳዋ ከተከሻዋ ተንሸራቶ ሊወድቅባት ነበር…እሷም ተነገዳግዳ ሚዛኗን ለመሳት ስትጥር ኤልያስ በፍጥነት ተስፈነጠረና ክንዷን ያዛት ። ተረጋግቶ ሲያያት አይኖቹን ማመን ነው ያቃተው ።፡ራሄል ነች፡፡ ሞባይል ስልኳ አንድ ጆሮዋ ላይ ተጣብቆል…ስልክ እያወራች እንደነበር ተገነዘበ፡፡
አቀርቅራ የተበተኑ ወረቀቷቾን እያየች‹‹ምንድነው…አይንህ አያይም እንዴ? አብደሃል?››ስትል ጮኸችበት ።ከዚያም ቀና ብሎ አያት።ሀዘን ያረበባቸው አይኖቿ እሱን ሲያዩት ፣ ንዴቷ በጥልቀት ወደ ውስጡ ዘልቆ ሲገባ ተሰማው። በልቡ ክልል ውስጥ የሆነ ቦታ ላይ የብርሃን ብልጭታ ፈነጠቀ።ድንገት ወደጎን ዞር ብላ እሱ መሆኑን ስታውቅ በንግግሯ አፈረች፡፡‹‹እባክህ ይቅርታ አድርግልኝ››ብላ አጉተመተመች፣ክንዷን ወደኋላ ጎተተች። አሁንም እንደያዛት ረስቶት ነበር። ፈጠን ብሎ ለቀቃት። ርቀቱን ጠብቆ በጉጉት እያዩ ወደነበሩት ወንድሙ እና ጓደኛው እየተመለከተ። ‹‹ይቅርታ አላየሁሽም….ከወንድሜ ቢኒ ጡጫ እራሴን ለማራቅ እየሞከርኩ ነበር.››አላት፡፡
‹‹ምንም አይደለም፣ እኔም ቀልቤ የማወራው ስልክ ላይ ስለነበር መጠንቀቅ አልቻልኩም ።›› በማለት ወረቀቶቿን ለማንሳት ጎንበስ አለች።
‹‹ቆይ እኔ ላንሳልሽ›› ብሎ እሱም ጎንበስ አለ… ሁለቱም በአንድነት እጇቸውን ወደወረቀቱ ሲሰዱ እርስ በርስ ተነካኩ ፡፡በመሀከላቸው የኤሌክትሪክ ንዝረት አይነት ቅፅበታዊ ብልጭታ ተፈጠረ፡፡
‹‹እባክህ አትጨነቅ›› የውስጥ ስሜቱን የሚቆሰቁስ አይነት እንደገና የሚያነቃቃ ፈጣን ፈገግታ ሰጠችው።
ወረቀቶቹን ሰብስበው ከተነሱ በኋላ‹‹ለመሆኑ እዚህ ሰፈር ምን እግር ጣለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹ለስራ ጉዳይ››ስትል አፏ ላይ የመጣላትን ምክንያት ሰጠችው፡፡
‹‹ በእረፍት ቀን ትሰሪያለሽ እንዴ?››
ራሄል ፊቷን አኮሳትራ‹‹ስራ እስካለኝ ድረስ ቀን ሳልመርጥ ነው የምሰራው..ታውቃለህ …ሥራዬ በጣም አስፈላጊ ነው።››ስትል መለሰችለት፡፡
‹‹ደህና፣ በቃ እንገናኛለን።››
‹‹ተስፋ አደርጋለው።›› አለችና መንገዷን ቀጠለች ፡፡
‹‹አሁንም አለሽ ራሄል?›› ከያዘችው የሞባይል ስልክ የአንድ ወንድ ድምፅ ተሰማ። እናም ራሄል እስከአሁን ስልኳ እንዳልተቆረጠ ስትረዳ ‹‹ ሮቤል በቃ ቆይቼ ደውልሀለው … መንገድ ላይ ያልሆነ ነገር አጋጥሞኝ ነው›› ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
ከዛም እርምጃዋን ሳታቋርጥ ወደ ዔሊያስ ዞር ብላ ተመለከተች …በተገተረበት ቆሞ እያያት ነበር ..የሆነ ውርር የሚያደርግ ስሜት ተሰማት ፡፡መንገዱን አቋርጣ ወደካፌው ታጠፈችና ከእይታው ተሰወረች፡፡
ሁኔታውን በትኩረት ሲከታተሉ የቆዩት ቢንያም እና ጓደኛው ወደ እሱ ሮጠው ከጎኑ ቆመ
‹‹በቀጣዬቹ አመታት ውስጥ ያለህ የሕይወት እቅድ ውስጥ ሴት እንደሌለችበት ደጋግመህ ነግረኸኝ ነበር? ››አለው ቢኒያም፡፡
‹‹እና ታዲያ?››
‹‹እናማ ይህቺ ሴት ማን ነች?።››
ዔሊያስ ለወንድሙ ‹‹የህይወት እቅዴ ላይ ምንም ማስተካከያ አልተደረገበትም..ያንን ካወቅክ ይበቃል።››ብሎት ወደመኪናው ጉዞውን ቀጠለ፡፡
ወንድሙም ከኋላው ተከትሎት‹‹እቅድህን ማስተካከል ትችላለህ …በቅድሚያ ግን ብድርህን ክፈል፣ ሞተርህን ሽጥና ትክክለኛ መኪና ግዛ፣ ከዛ ኑሮህን የምትጋራ ሴት መፈለግ ትችላለህ››አለው
ዔሊያስ ሕይወት ሁል ጊዜ እንደማይተነበይ ከግል ተሞክሮ ያውቃል ። ዔሊ በስድስት ዓመቱ ወደ ማደጎ ቤት ለመግባት ተገዶ ነበር፡፡ በወቅቱ ጮርቃ ልጅ ነበር እና ስለ ተፈጥሮ ወላጆቹ የሚያውቀው ብቸኛው ነገር አባቱ ሉቃስ እናቱ ደግሞ ትእግስት እንደምትባል ብቻ ነው፡፡ስለ እነሱ ያለው የመጨረሻ ትዝታ ቤተሰቡ በአንድ ላይ ሆነው እየተጓዙ እያለ አባቱ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖት ሲጯጯሁ ነበር፡፡አንድ አመት ሙሉ በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ተጣለ፡፡በዛን ተመሳሳይ ወቅት ቢኒያምም የአንድ አመት ህፃን ሆኖ በወላጇቹ ተጥሎ እዛ ማደጎ ቤት ከእሱ ጋር ነበር፣ እንደእድል ሆኖ አሳዳጊዎቻቸው ለሁለቱም ልባቸው ራራና አንድ ላይ ወደቤታቸው ወስደው እንደገዛ ልጇቻቸው ተንከባክበው አሳደጓቸው..እነሱም እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚደጋገፉ ወንድማማቾች ሆነው አደጉ፡፡ አሳዳጊ ወላጆቻቸው ሁለቱንም በፍፁም ፍቅር እና …በስርዓት አስተምረው ለዚህ ደረጃ አበቁዋቸው፡፡
ቀጥታ ጓደኖቾ ይጠብቋት ወደነበረው ካፌ ገባች፡፡በጠረጴዛ ዙሪያ እየተጨዋወቱ እና እየሳቁ ካሉት ከጓደኞቿ ጋር ተቀላቀለች፡፡
‹‹ደህና ናችሁ ፣ ውድ ጓደኞቼ››
እንዴት ነሽ ንግስቲቷ›› ሜሮን ነች ቀድማ ለሰላምታዋ መልስ የሰጠቻት፡፡ከዛ ያሬድና ሌንሳ ተከተሉ፡፡እነዚህ ሶስቱ የልጅነት የትምህርት ቤት ጓደኞቾ ናቸው፡፡ራሄል ልጅ ሆና ፈጣን እና ጎበዝ ተማሪ ነበረች እና በዚህ ምክንያት ሁለት ክፍል በመዝለሏ ትምህርት ቤት ከገባችባቸው ልጆች ትንሿ ነበረች። አንድ ቀን በክፍሏ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ልጃገረዶች በመጫወቻ ስፍራው ላይ ወደ ጥግ ወስደው ይሳለቁባት ጀመር። እንደአጋጣሚ ሶስቱ ጓደኛሞች በአካባቢው ሲያልፉ ሁኔታውን ተመለከቱ ..ዝም ብለው ሊያልፉ አልፈለጉም…ጣልቃ ገብተው ራሄልን በክንፋቸው ስር ከልለው ታደጓት። ከዛን በኃላ ቋሚ ጓደኞቾ ሆኑ..ይሄው እስከዛሬ በህይወት ውጣ ውረዶች ውስጥ፣ የእርሷ ምስጢረኞች አማካሪዎች እና ውድ ጓደኞቿ ሆነዋል።እና ከአራት አመት በፊት ሌንሳና ያሬድ የጓደኝነት ግንኙነታቸውን ወደፍቅር ቀይረው በመጋባት መንታ ልጆችን ለመውለድ ችለዋል፡፡
ያሬድ የራሄልን የተዘበራረቀ ሸሚዞን እና የተበታተነ ወረቀቷን ተመለከተና ‹‹ደህና ነሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹አዎ..ደህና ነኝ››
‹‹ቆይ ምን ሆንሽ?››ሜሮን ተቀበለችው፡፡
‹‹ከመኪናዬ ወርጄ ወደእዚህ ስመጣ ..፣ከአንድ ጓረምሳ ዶ/ር ጋር ተጋጨው ››
‹‹ምን…!ከጎረምሳ…?ወይስ ከዶክተር?››ሌንሳ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ጓረምሳ የሆነ ዶ/ር ..ምነው ግልፅ አይለም እንዴ?››
‹‹እኔ ያልገባኝ..ጎረምሳ መሆኑን በእይታ አወቅሽ እንበል..ዶክተር መሆኑንስ?››ሜሮን ጠየቀች፡፡
‹‹ባክሽ የማውቀው ሰው ነው …የእህቴ የፀጋ ዶክተር ነው፡፡››ሸሚዙ እንደተከፈተ፣ እና ፀጉሩ በግንባሩ ላይ ተደፍቶ እንደነበረ ላለማሰብ ታገለች።
ሁሉም በአንድ ላይ አስካኩባት፡፡
‹‹ስሙ ማን ነበር?››ሌንሳ በማሾፍ ጠየቀች፡፡
ራሄል ግን ጥያቄዋን በቁም ነገር ወስዳ‹‹ዓሊ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ኤሊ ማለት?››ያሬድ በገረሜታ ጠየቀ፡፡
‹‹ማለቴ ኤልያስ….ዶ/ር ኤልያስ››
ሌላ የህብረት ሳቅ ተከተለ፡፡
‹‹ተመልከቷት ነገሩ ስር የሰደደ ይመስላል ። የዔሊን ስም ሲነሳ መልኳ በደቂቃ ተለወጠ›› ሜሮን ጮኸች።
‹‹እንዴት ነው ግን…?››ለሊሴ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ እሱ ቆንጆ ነው ማለት ይቻላል...›› ቡድኑን ዞር ብላ ተመለከተች እና በራሷ ሳቀች።‹‹እንደ ያሬድ ወንዳ ወንድ ነው›› ስትል አከለችበት፡፡
ሁሉም ሳቃቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡

❤56👍3
‹‹አሁን ማዘዝ እንችላለን? እየራበኝ ነው።››በማለት ርዕሱን ለመቀየር ሞከረች፡፡
‹‹ኤሊ ወንደላጤ እንደሆነ ሰማሁ ›› አለች ሜሮን
‹‹ሊሆን ይችላል ግን…ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም›› ስትል ራሄል አጽንኦት ሰጥታ ተናገረች።
‹‹ይቺ ልጅ በፍቅር ፍላጻ የተመታች ይመስለኛል።››ያሬድ ነው ተናጋሪው፡፡
ራሄል‹‹ሞተር ሳይክል ይነዳል…እሺ?››ስትል በመኮሳተር ነገረቻቸው፡፡ከዚህ ቃል በኋላ ያለው ዝምታ ነበር…ፀጥታው ምን ማለት እንደፈለገች ጓደኞቿ እንደተረዱት ያሳያል። በባለ ሁለት ጎማ የሞት ማሽን የልቧን ሰው እዳጣች እና ምን ያህል የልብ ስብራት እንዳጋጠማትና ከዛም ስብራት እስካአሁን እንዳላገገመች የቅርቧ ሰዎች ስለሆኑ በደንብ ያውቃሉ፡፡
‹‹እናንተ ሰዎች ለማዘዝ ዝግጁ ናችሁ?››ደግማ ጠየቅች፡፡
አስተናጋጁ ተጠራ እና ሁሉም የየፍላጎታቸውን አዘዙ ፡፡ከዚያ በኋላ፣ ወደ ተለመደው ንግግራቸው ሲገቡ፣ አንዳቸው የሌላውን ሕይወት ሲመረምሩ፣ ሌንሳ ስለ መንታ ልጆቿ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላላት ስራ ስትነግራቸው ራሄል ስለ ድርጅቷ እንቅስቃሴ ስትተርክ ቆዩ…ያዘዘችው በርገር መጥቶ ለመብላት ስትዘጋጅ የሞባይል ስልኳ ጮኸ።
‹‹ተይው…አታንሺው››አላት ያሬድ… ። የጥሪ ማሳያውን ተመለከተች። አባቷ ነበሩ።ጓደኞቿን ይቅርታ ጠይቃ በፈገግታ ስልኩን አነሳች፣ ከጓደኞቿ ዞር ብላ ማውራት ጀመረች።
‹‹ ሄይ አባዬ››
‹‹ራሄል የእኔ ማር››ድምፃቸው የደከመ ነበር።በራሄል ጭንቅላት ውስጥ ጭንቀት ተፈጠረ።
‹‹አባዬ ምን ችግር አለ?››
‹‹እናትሽ ናት …እኛ ሆስፒታል ነው ያለነው….እግሯ ተሰብሯል።››
‹‹መጣው አባዬ…አሁኑኑ መጣሁ ››ስልኳን ዘጋችና ቦርሳዋን አነሳች። ‹‹አባቴ ነበር የደወለው››አለች፡፡ ድምጿ እየተንቀጠቀጠ ነው።‹‹ይቅርታ ጓደኞቼ, መሄድ አለብኝ. እናቴ እግሯን ተሰብሮ ሆስፒታል ውስጥ ነች.››ለምግብ ክፍያ የሚሆን የተወሰነ ብር ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች።
‹‹አብረንሽ እንድንመጣ ትፈልጊያለሽ››ስትል ሜሮን ጠየቀቻት ፡፡
‹‹አይ, አይሆንም.፣ችግር የለውም…እናንተ መብላታችሁን ቀጥሉ.››ራሄል ተቃወመች።
ራሄል ከምግብ ቤት ፈጥና ስትሄድ ያሬድ ‹‹ከደረሽ በኃላ ሁኔታውን አሳውቂን››አላት፡፡
ከአስራ አምስት ደቂቃ በኋላ የሆስፒታሉን በር ደርሳ እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ወደውስጥ ገባች፡፡ እና በድፍረት ምትጋፈጠው የመሰላት የጸረ-ተባይ እና የአሞኒያ ጠረን በአፍንጫዋ ተመሰገ ። ያደፈነችውን ትዝታ እየጎተተ እንደ ማዕበል ያንገላታት ጀመር።እርምጃዋ ተንቀረፈፈ፣ ነገር ግን ስለእናቷ ህመም ስታስብ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ለሆስፒታሎችን ያላትን ፍራቻ ተቋቁማ እንድታልፍ የሚያስችላትን ብርታት አገኘች ።
‹‹ተይ…ተይ! አባትሽ ይፈልግሻል።››በማለት እራሷን ለማበርታት ሞከረች፡፡ከአንዱ ክፍል ውስጥ የአባቷን ድምፅ እንደሰማች በፍጥነት ወደእዛው ተራመደች። መጋረጃውን አልፋ ከፊት ለፊቷ ባለው ቦታ ላይ ቆመች።ፀጋ አልጋው ላይ ተቀምጣለች…እና ኤሊያስ ከሸሚዝና ከሰማያዊ ጂንስ በላይ ነጭ ጋወኑን ለብሶ ቆሟል ፡፡በየት በየት ብሎ ከእሷ ቀድሞ እዚህ እንደተገኘ ግራ ገባት፡፡ እንደገባች አባቷ ቀና ብለው አያትና በጥሩ ፈገግታ ተቀበላት።‹‹እናቴ የት አለች?››ራሄል እሷቸውን እቅፍ ወደ ፀጋ ተመለከተች፣ ማን እዚህ እንዳለ ለማየት ጭንቅላቷን አጠማዘዘች።
አባቷ ‹‹እናትሽ አሁን ቀዶ ጥገና ላይ ነች›› አሏት፡፡
‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?››ራሄል ጠየቀች።
‹‹ፀጋን ተሸክማ ደረጃውን እየወረደች ነበር፣ድንገት ሚዛኗን ስታ ወድቃ ተጠመዘዘች…ከዛ ተሰበረች። ››ሲሉ አስረዷት፡፡
‹‹አሁን ፀጋ እንዴት ናት?››ራሄል እህቷን በድጋሚ እየተመለከተች ጠየቀች፡፡
‹‹እስካሁን ደህና ነች ። ከመደበኛው ውጪ የሆነ ነገር አይታይባትም።››ኤሊያስ ጣልቃ ገብቶ ስለፀጋ ሊያስረዳት ሞከረ፡፡ አይኖቹ ራሔል ግንባር ላይ ብርሃን የሚረጩ ይመስላሉ ።
‹‹ራሄል ሆስፒታሎችን አትወድም። ››ሲሉ አባትዬው ለኤሊያስ ሊያስረዱት ሞከሩ፡፡
ዔሊም ‹‹አዝናለሁ፣ አላውቅም ነበር። ››አለ፡፡
‹‹ግን እናቴን ለማግኘት መሄድ እችላለሁ?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹ትችያለሽ››
ራሄል በጥንቃቄ ፈገግታ ሰጠችው ። ለረጅም ጊዜ ያላጋጠማት ስሜት ተሰማት።‹‹አሁን እመለሳለሁ.››በማለት ፀጋን አፍንጫዋ ላይ ነክቶ ሄደ።
ከጎናቸው ካለ አንድ ኪዩቢክ የወጣው የኦክሲጅን ጩኸት፣ የጋሪዎቹ እና የነርሶች ወከባ ወደ ኅሊናዋ ውስጥ ገብተው ትዝታዎችን ቀሰቀሱባት። ትንፋሽም አጠራት።አባቷ ተሳስተዋል። ሆስፒታሎችን አለመውደድ አይደለም። ንቃቸው ነው። እነሱ ተስፋዋን ቀረጣጥፈው የበሉባት የመቃብር ጉድጓድ ናቸው ፣ በእያንዳንዱ ኮሪደር የሞት ሽታ ነው ወደአፍንጫዋ የሚመሰገው እና አሁን ሀሳቧ እናቷ ላይ ነው፡፡ በእውነቱ ምን ያህል ተጎድታ ይሆን ? ምን ይደርስባት ይሆን?
‹‹የእኔ ማር ..እዚህ ጋር ተቀመጪ››አባቷም እጇን ያዘና በመጋረጃ በተሸፈነው ክፍል ውስጥ ባለው ብቸኛ ወንበር ላይ አስቀመጧት ፡፡
‹ኤሊያስ ትክክል ነበር፣ በጣም ገርጥታለች ።››ራሄል እያደገ የመጣውን ድንጋጤዋን ለመቆጣጠር ሞከረች።
‹‹ደህና ነኝ አባባ›› አለች፡፡
ፀጋ እጆቿን ወደ አባቷ እየዘረጋች ‹‹ወደ ታች አውርደኝ›› ስትል ተናገረች።
አቶ ቸርነት ከአልጋው ላይ ልትወርድ ወደ ምትሞክረው ፀጋ እየጠቆሙ ‹‹ራሄል ልትወስጂያት ትችያለሽ?›› ሲሉ ጠየቋት።አባቷ ወደሚያዩት አቅጣጫ ቃኘች፣ ዔሊያስ መጋረጃውን ወደ ጎን ሲያንሸራትተው ሌላ ዶክተር ተከተለውና ወደእነሱ መጣ። በድጋሚ ወደ ፀጋ ተመለከተች፣ በምንም ነገር እርግጠኛ ሳትሆን ልጁቷን ከአልጋው ላይ አነሳችና አቀፈቻት።
‹‹…አዝናለው ጥሩ ያልሆነ ዜና ልነግራችሁ ነው›› አለ ደ/ር ኤሊያስ።
የዶተሩ ከባድ የድምፁ ቃና ራሄልን በፍርሃቷ እንድትርበደበድ እና እንዳትወድቅ በመፍራት ግድግዳውን እንድትይዝ አደረጋት ‹‹ይህ ዶ/ር ምንያህል ይባላል። ሁኔታውን ያብራራላችኋል›› ሲል ተናገረና ቦታውን አዲስ ለመጣው ዶክተር ለቀቀ ፡፡የዶ/ር ምንያህል ፊቱ ፈገግታ ያልተለየው ቢሆንም የዶክተሮችን ስሜት ማንበብ ከባድ እንደሆነ ከብዙ አመት በፊት በደንብ አውቃለች፡፡ እናም ፍርሃቷ ጨመረ።
ምንያህል የተባለው ዶ.ር ወደአባቷ እየተመለከተ ገለፃውን ቀጠለ‹‹የባለቤቶት X ሬይ ውጤት አግኝተናል።››ጥቁሩ አይኖቹ በጥልቅ ርህራሄ ሁለቱንም አስተዋላቸው።‹‹በጣም ከባድ የሆነ የጭን አጥንት ስብራት ገጥሟቸዋል።ከአጥንት በላይ የሆነ ስብራት በሚመስል ነገር የተወሳሰበ ነው። ለረጅም ጊዜ እዚሁ ሆስፒታል ተኝተው መታከም አለባቸው››
አቶ ቸርነት እራሳቸውን ለማረጋጋት ያህል አይናቸውን ጨፈኑ.. ከዛ ከፈቱ …።ራሄል አሁንም ፀጋን በአንድ እጇ ይዛ ቀስ በቀስ ስሯ ያለ ወንበር ላይ ልትቀመጥ ስትሞክር ድንገት ክንዷ ላይ ያለችው እህቷን እንደያዘች ሚዛኗን በመጠኑ ስታ ልትወድቅ ስትል ሁኔታዋን በትኩረት ሲከታተላት የነበረው ዶ/ር ኤልያስ ተንደረደረና ክንዷን ይዞ በዝግታ እንድትቀመጥ ረዳት፡፡
‹‹አመሰግናለሁ››አለች ራሄል ።
ዔሊያስ እጁ አሁንም በትሁት ትከሻ ላይ ነው።

❤45👍4🥰2
የራሄል ሆዷ ሲገለባበጥ ይታወቃታል እንደገና የማዞር ስሜት ተሰማት።ራሄል ፀጋ ከእጇ ሾልካ ከመውደቋ በፊት ‹‹እባክህ ልትወሰዳት ትችላለህ?››በማለት ወደ ዔሊያስ ገፋቻት፣ ዶ/ር ኤልያስ ግራ አጋቢ እይታ ካያት በኃላ ፀጋን ወሰዳት እና በቀላሉ ወደ እቅፍ አስገባት።ራሄል ወደ ዶ/ር ምንያህል ትኩረቷን ሰበሰበችና ‹‹ይቅርታ ስለ እናቴ እየነገርከን ነበር …ሙሉ በሙሉ የማገገም እድሏ ምን ያህል ነው?"ስትል ጠየቀችው፡፡መልሱን ለመስማት ግን ብርታቱ አልነበራትም፡፡
‹‹በጣም ጥሩ የሚባል ነው:፡፡እርግጥ እንደእሷቸው ብርታትና ጥረት ይወሰናል…ቢሆንም ጊዜ ይወሳዳል እንጂ መዳናቸው አይቀርም፡፡››
‹‹ምን ያህል ጊዜ በሆስፒታል የምትቆይ ይመስልሀል?››አቶ ቸርነት ጠየቁት፡፡
‹‹ከሦስት እስከ አራት ሳምንታት ገደማ ምን አልባትም ከወር በላይ የግድ በሆስፒታል መቆየት አለባቸው…ከዛ በኃላ ያለውን ህክምና ምን አልባት እቤታቸው ሆነው የሚከታተሉበት መንገድ እናመቻች ይሆናል፡፡››
አቶ ቸርነት በቆሙበት አገጫቸውን በእጇቸው እያሻሹ፣ የቦዙ ዓይኖቻቸውን ግድግዳው ላይ ሰክተው በሀሳብ ጠፋ።ወደ ራሔል ተመለከቱ ‹‹ከእናትሽ ጋር ያን ያህል ረጅም ጊዜ መለየት አልችልም..አብሬት እዚህ ምቆየው እኔ ነኝ›› አሉ፡፡
‹‹አውቃለሁ አባዬ›› እጇቸውን ያዘችና ጨመቀቻቸው።
‹‹እና ስለ ፀጋስ?››አባቷ በጭንቀት እና ግራ በመጋባት ጠየቁ።
ዶ/ር ምንያህል ዔሊያስን ተመለከተ። ‹‹ዶክተር ዓሊ የቀሩትን ጥያቄዎችችሁን ሊመልስላችሁ ይችላል ብዬ አስባለሁ. አሁን ወደ ባለቤቶት ሄጄ አንዳንድ ምርመራዎችን ማድረግ አለብኝ፡፡››ብሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
‹‹አስደሳች ዜና ስለሌለኝ አዝናለሁ፣ ግን ደግሞ ከዚህም የከፋ ጉዳት ስላልደረሰባቸው ልናመሰግነው ይገባል።››ኤልያስ ነው ተናጋሪው፡፡
አቶ ቸርነት በኤልያስ ሀሳብ በመስማማት ‹‹ለቸሩ ጌታ ምስጋና ይድረሰው ››ሲሉ ተናገረሩ፡፡
‹‹ፀጋን ከእኛ ጋር እዚህ መሆን ትችላለች?›› አቶ ቸርነት ዶ/ር ኤሊያስን ጠየቁት፡፡
ኤልያስ ራሱን በአሉታ ነቀነቀ። ‹‹አይ እሷ እቤት መሆን ነው ያለባት … ።›› አለና ወደ ራሔል ተመለከተ፣ ከዚያም ወደ አቶ ቸርነት ተመለሰ። ‹‹እናትሽን ለመርዳት አባትሽ ሙሉ ትኩረታቸውን እሷቸው ላይ ማድረግ አለባቸው… እና ለፀጋ ጤና ደግሞ በዚህ ሁኔታ ውስጥ መገኘት ጥሩ ውጤት አያመጣም።››
‹‹ደህና, ስለ ትንሹ ልጃችን የሆነ ውሳኔ መወሰን እንዳለብኝ ይሰማኛል.››እጇቸውን ራሰ በራ ጭንቅላታቸው ላይ አሳርፈው ወደ ራሄል ዞሩና ፈገግ አሉ‹‹ራሄል፣ ማሬ፣ ፀጋን መንከባከብ ትችያለሽ?››ሲሉ ጠየቁ፡፡
‹‹እኔ? ፀጋን መንከባከብ?››የራሄል ድንጋጤ አስፈሪ ነበር፡፡
እጆቿን እርስ በርሳቸው አቆላለፈች….‹‹ግን ብዙ ስራ መስራት አለብኝ … ማለቴ ፀጋ የምትፈልገውን ያህል ጊዜ አብሬያት ለማሳለፍ እንደምችል እርግጠኛ አይደለሁም›› ራሄል ተርበተበተች፡፡ አቶ ቸርነት ተነፈሱ።
‹‹ሞግዚት እቀጥርላት ነበር፣ ግን እንደምታውቂው እሷ ከአዲስ ሰው ጋር በቶሎ መልመድ አትችልም…በዛ ላይ ትእግስት ኖሮት እሷን በስርዓቱ የሚንከባከብ ሰው ለማግኘት ይከብዳል….ቤት ካሉት ሰራኞች ጋር እንኳን ያላትን ግንኙነት የምታውቂው ነው››በማለት ያሳሰባቸውን ነገር በዝርዝር አስረዷት፡፡
ውይይታቸውን እና በአባትና ልጅ መሀከል የተፈጠረውን ውጥረት በትኩረት ሲከታተል የነበረው ዶ/ር ኤልያስ ሌላ አማራጭ ፕሮፖዛል ሊያቀርብ ሲዘጋጅ ድንገት ራሄል እጇን በአባቷ ትከሻ ላይ አድርጋ ፈገግ በማለት‹‹ ያልኩት የስራ ጫና እንዳለ ቢሆንም ..ነገር ግን ፀጋ እህቴ ነች። ለእሷ ቅድሚያ መስጠት እንዳለብኝ እገነዘባለው…እና አባዬ አንተ ምንም አታስብ ለእሷ አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደማደርግላት አረጋግጥልሀለው።››ስትል ሁለቱም ባልጠበቁት ወኔና ቁርጠኝነት ቃል በመግባት አስደመመቻቸው፡፡
አቶ ቸርነትም ትልቋን ሴት ልጇቸውን በፍቅር ትከሻዋን መታ መታ እያደረጉ ‹‹እናመሰግናለን ውዴ››ሲሉ አመሰገኗት ። ወደ ፀጋ ዞረው አቀፏትና‹‹ ከእህቷ ጋር ከመሄዷ በፊት እናቷን እንድታይ ማድረግ እችላለሁ?›› ሲል ደ/ር ዔሊያስን ጠየቁት።
ዔሊ መጋረጃውን ወደ ጎን ያዘና ‹‹ምን አልባት የመድሀኒቱ ተፅዕኖ ማንንም እንዳይለዩ ሊያደርጋቸው ይችላል ግን መሞከር እንችላለን።››
አቶ ቸርነት ፀጋን ይዘው ወደባለቤታቸው ክፍል ገቡ ፣ ራሄል ተከትላቸው ልትሄድ ስትል ዔሊ ትከሻዋን ያዘና አስቆማት። ወደ ኋላ ተመለሰች። ኮስተርተር አለችበት፡፡
‹‹ለአንድ አፍታ ላናግርሽ ፈልጌ ነበር››አለ ። ራሄል ወደ አባቷ ተመለከተች፣ ከዚያም ወደኃላ ቀረችና ‹‹ እሺ ይቻላል፡፡›› አለችው፡፡
‹‹ፀጋን መንከባከብ የሚከብድሽ ከሆነ ለአንቺ አማራጭ እንደማገኝልሽ እርግጠኛ ነኝ።››አላት፡፡
ራሄል አይኗ ጠበበ። ‹‹አማራጭ አያስፈልገኝም… እህቴ ነች። እሷን በጥንቃቄ መንከባከብና መጠበቅ እችላለሁ።››በንግግሯ ውስጥ ያለውን እርግጠኝነት አስገረመው።
በአስተያየቱ በእሷ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተረዳች‹‹አውቃለው…ከዚህ በፊት ልጅ ተንከባክቤ አላውቅም፣ ግን...››በራስ የመተማመን አቅሟ ለአፍታ ቢሆን ሲወርድ ታወቃት። ‹‹ይህን አደርጋለሁ››
‹‹ጥሩ እንደምታደርጊው እርግጠኛ ነኝ ..ወደ ቢሮዬ ለመምጣት ፈቃደኛ ከሆንሽ የሚያስፈልጉሽን መረጃ ልሰጥሽ እችላለሁ›› አላት፡፡
‹‹እሺ››አለችው።
ዔሊያስ የትንሿ ልጅ ጤንነትን በቅርበት የመከታተል ሞያዊም ሆነ ሞራላዊ ግዴታ እንዳለበት ያውቃል። ለዚች ሴት ኩራት ሲባል ያቺ ሚስኪን ልጅ እንድትሰቃይ አይፈቅድም።
‹ከሃያ ደቂቃ በኋላ ቢሮዬ እንገናኝ።››
በእሺታ ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም አልፋው ጥላው ሄደች፡፡

❤51👍17
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
‹ከሃያ ደቂቃ በኋላ ቢሮዬ እንገናኝ።››
በእሺታ ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም አልፋው ጥላው ሄደች፡፡
ከግማሽ ሰአት በኋላ ራሄል ቢሮው መጥታ ከጠረጴዛው ማዶ ተቀመጠች፣ በአንድ እጇ እስክሪብቶ፣ በሌላ እጇ ማስታወሻ ደብተር ይዛለች። ሁኔታዋ አስገረመው ፡፡
ዶ/ር ዔሊያስ መናገር ጀመረ ‹‹ፀጋ በቴክኒካል ተርሙ ሄሚፕሌጂያ ተብሎ የሚጠራ በሽታ ተጠቂ ነች፡፡በሌላ አነጋገር ሴሬብራል ፓልሲ ታማሚ ነች ማለት ነው፡፡ በሰውነቷ አንድ ጎን በግራ እጇ እና በግራ እግሯ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮባታል..አጥንቶቾ በጣም ደካማ ስለሆኑ እንደልብ ለመንቀሳቀስ ትቸገራለች…በተወሰነ መልኩ የመስማትና ቃላቶችን አቀላጥፎ የማውራት ችግርም አለባት።የእሷን ጤና ሁኔታ ለማሻሻል በሚደረገው ሂደት ውስጥ የሚሳተፉትን - ፊዚዬ ቴራፒስት ጨምሮ፣ ብዙ ባለሞያዎች አሉ.. እና እያንዳንዱን መቼ መቼ ማየት እንዳለባት አስረዳት፡፡
‹‹በተጨማሪም የጆሮ ኢንፌክሽንን እየተዋጋች ስለነበረ አንቲባዮቲክ ትወስዳለች።››ዔሊ የራሔልን እይታ በመሸሽ እስክሪብቶውን አንሥቶ መሞነጫጨር ጀመረ።
ራሄል ትዕግስት በማጣት‹‹ዶክተር ሌላ ልትነግረኝ የሚገባ ነገር እንዳለ ይሰማኛል››አለችው.
‹‹ትሁት ከጊዜ ወደ ጊዜ በንዴት በሽታ እየተሰቃየች ነው ። ስለዚህ ስሜቷን በጥንቃቄ መከታተል እና የሚያበሳጮትን ነገሮች ማስወገድ ያስፈልግሻል ማለት ነው ።ያው እንድትናደድ ከፈቀድሽላት የሚጥል በሽታ ስላለባት ነገሮች ይባባሳሉ… እንደ አለመታደል ሆኖ ይሄንን ጉዳይ በመድኃኒቷን ማስተካከል አልቻልንም።››
‹‹ትሁት ማለት?››ግራ በመጋባት ጠየቀችው
‹‹ይቅርታ..ፀጋ ወደእናንተ ቤት ከመምጣቷ በፊት ወላጅ እናቷ ትሁት ብላ ነበር ስም ያወጣችላት….ከዛ ነው አባትሽ ፀጋ ያለት፡፡እና እኔ ትሁት የሚለውን ስም ለረጅም ጊዜ ስለተጠቀምኩበት በቀላሉ ከአእምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም…..››
‹‹አይ ችግር ለውም..ትሁትም ደስ የሚል ስም ነው››
‹‹አዎ…እና እንዳልኩሽ ፀጋ ማለት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋት ልጅ ነች፣፣በተለይ መናደድ የለባትም….ምክንያቱም ከንዴቷ በኋላ የሚከሰተው የሚጥል በሽታ ሌሎች ብዙ የጤና ችግሯቾን ነው የሚያናጋባት››
በራሔል ፊት ላይ የፍርሃት ብልጭታ ሲያይ ተገረመ።
‹‹የሚጥል በሽታ ሊነሳባት መሆኑን እንዴት አውቃለሁ እና ምን ያህል መጥፎ ነው?››
‹‹ትለይወለሽ…እጆቿ ይንቀጥቀጣሉ… የዐይን ሽፋኖቿን ይርገበገባሉ እነዚህን እና የመሳሰሉት ምልክቶችን ታሳያለች፡፡የዛን ጊዜ አጓጉል ወድቃ እራሷን እንዳትጎዳ ጥንቃቄ መውሰድ ይገባሻል፡፡ ማንኛውም አሳሳቢ የጤና ችግር ሲያጋጥማት በአፋጣኝ ወደሆስፒታል ልትወስጂያት የግድ ነው፡፡ በመደበኝነት በሳምንት ሶስት ቀን ሆስፒታል የህክምና ክትትል አለት፡፡በመሀል አስፈላጊ ሲሆን ለእኔ በማንኛውም ሰዓት ልትደውይልኝ ትችያለሽ ፣ ወዲያውኑ ልመጣ እችላለሁ።..›› ዔሊያስ መጀመሪያ ያሰበው ለፀጋ ነው።‹ራሔል በዚህች ልጅ ላይ ያለውን ችግር በሙሉ ማወቅ አለባት› ሲል በውስጡ አሰበ፡፡
‹‹ፀጋን ከተወለደች ቀን ጀምሮ እየተንከባከባት ነበር…እናትዬው ተስፋ ቆርጣበት በሆስፒታል አልጋ ላይ ማሽን እንደተሰካካባት ጥላት ስትሰወርም አንደኛ እናትዬውን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቃት ጓደኛው ስለሆነች ሲሆን ሁለተኛም ከራሱ ህይወት ጋር አያይዞ ሲንከባከባትና እንደወላጅ ስለሚጨነቅላት ነው፡፡በመጨረሻም ከስድስት ወር የሆስፒታል ቆይታዋ በኃላ የራሄልን ወላጆችን በግሉ ፈልጎ በማግኘት በጉዲፈቻ እንዲወስዷት በማድረግ ሂደት ላይ የአንበሳውን ድርሻ የእሱ ነው፡፡ከዛም በኃላ በቃ በኃላፊነት የሚያሳድጓት እና የሚንከባከቧት ወላጆች አግኝታለች ብሎ አልተዋትም፤ በቆሚነት የእሷ ሀኪም በመሆን እነ አቶ ቸርነት ቤት ድረስ እየተመላለሰ ሁኔታዋን ይከታተላል፤ ታማለች ብለው ሲደውሉለት ያለምንም ማቅማማት ሞተሩን ተረክ አድርጎ በሮ ይሄድና ያያታል…እናም ይህቺ ልጅ ለእሱ እንደአንድ ታካሚው ብቻ አይደለችም…የህይወቱ አካል ነች….ስቃዮ ያመዋል…ለቅሶዋ ይሰማዋል….ፈገግታዋ ያስቀዋል….ለዛ ነው ራሄልን በትክክል እናቷ በምትንከባከባት መጠን ትንከባከባታለች ብሎ ሊያምን ያልቻለው፡፡
‹‹ራሄል ምን መሰለሽ ፀጋን እንዲህ ስታያት በአካላዊ እይታ ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለች ሊመስልሽ ይችላል, ግን ውስብስብ በሆነ የህክምና ሂደት ውስጥ እያለፈች ነው፡፡ ሰውነቷ እየሰጠ ያለው መልስ በጣም ደካማ ነው. ለሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በጤና እሷን ማቆየት ከቻልን ትልቅ ድል ነው…በህክምናው ሂደት ከባድ ችግር እያጋጠመን ነው ››
ራሔል በፍጥነት ማስታወሻ እየወሰደች ሲሆን በእጇ ላይ ትንሽ መንቀጥቀጥ አየ፡፡‹‹ስለ ምን ዓይነት የሕክምና ችግሮች ነው የምታወራው?››
‹‹በአእምሯዋ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ጀምሮል እና ተጨማሪ ኢንፌክሽኖች እና ሌሎች ችግሮችም እየተከሰቱባት ነው፡፡››
እሺ፣ ምናልባት ትንሽ አክብዶባት ሊሆን ይችላል ግን ማወቅ አለባት። የበለጠ መረጃ ባላት ቁጥር እሷ ማድረግ የምትችለው የተሻሉ ውሳኔዎች ትወስናለች፣ ።
‹‹ወላጆቼ ግን ፀጋ ያለባትን ይሄን ሁሉ የጤና ችግር ያውቃሉ?››
‹‹አዎ..እንደውም ለአንቺ በጥቅሉ ነው የነገርኩሽ እንሱ ግን እሷን ለማሳደግ ከመወሰናቸው በፊት እያንዳንዱን በዝርዝር አስረድቻቸዋለው…..ግን ለምን ጠየቅሺኝ?››
‹‹እኔ እንጃ…..በዚህ ሁሉ የጤና እክል ውስጥ ሆኖ ምን አልባትም የመሞቻ ቀኗን እየተጠባበቀች ያለች እና ክፉና ደጉን የማታውቅ ልጅ እንዴት ለማሳደግ እንደፈቀዱ ግራ ስለገባኝ ነው፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ….እኔም ወላጆችሽን በጣም የማከብራቸውና ከልቤ ማደንቃቸው በዚህ ውሳኔያቸው ነው…እነሱ ያደረጉትን ማንም ሌላ ሰው ያደርገዋል ብዬ አላስብም..እነሱ ለእኔ የህይወት ዘመን ጀግናዎቼ ናቸው፡፡››አለና ካርዱን ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ ሰጣት። ‹‹ይህ የሆስፒታሉ የድንገተኛ አደጋ ቁጥር፣የቤቴ ቁጥር እና የሞባይል ቁጥሬ ነው። በፈለግሺኝ ጊዜ ደዉይልኝ››ራሄል መረጃውን እንደያዘች ረጅም እና ዘገምተኛ ትንፋሽ ወደ ውስጣ ሳበች ከዛ ወደ ውጭ ተነፈሰች፡፡ ወረቀቱን እና ካርዱን በቦርሳዋ ውስጥ አስገባች።
‹‹ከመሄዴ በፊት ግን አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቅህ?››
‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ››አላት በጉጉት፡፡
‹‹ፀጋን ቤተሰቦቼ እንዲያሳድጓት በግል የጠየቅካቸውና ያሳመንካቸው አንተ ነህ….ለሌሎችም ታካሚዎችህ እንደዛ ታደርጋለህ?››ስትል ያለሳበውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር የፀጋ እናት የልጅነት ጎደኛዬ ነች…አንድ ሰፈር ነው ያደግነው…ህይወት ባልሆነ መንገድ መርታ ያልሆነ ማጥ ውስጥ ጨመረቻት እንጂ እንዲህ እንደቀልድ ልጇን ጥላ የምትሰወር ልጅ አልነበረችም….እና ፀጋን ዝም ብዬ ችላ ብዬ ማደጎ ቤት ስትገባ ማየት አልቻልኩም…የምተማመንባቸው አሳዳጊዎች መፈለግ ጀምርኩ..መጀመሪያ የራሴ ወላጆች ነበር የመጡልኝ..ግን የጽጌረዳ ሰፈር እዛው ስለነበረ ትንሽ ልክ መስሎ አልተሰማኝም….ከዛ ምክንያት ነው ወላጆችሽን ያገኘሁት…እናም ደግሞ ሁሉንም ነገር በግልፅ ነግሬያቸዋለው….ምንም የማያውቁት ነገር የለም፡፡››
‹‹አባቷስ?››
‹‹ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅ…አባቷ እንደሞተ ነው የነገረችኝ… ሌላ ጥያቄ ይኖርሻል?››
‹‹ አይ የለኝም..አመሰግናለው…. ››አለች… ቆመች… እጁን ለመጨበጥ ከጠረጴዛው አሻግራ እጇን ዘረጋች፡፡

❤66👍3
‹‹ለጊዜህ አመሰግናለሁ፣ ዶ/ር ኤሊያስ እንደምንገናኝ እርግጠኛ ነኝ።››አለችው፡፡
ዔሊያስም በሩን ሊከፍትላት በጠረጴዛው ዙሪያ ዞሮ ተራመደ..
ራሄል ስለጸጋ የጤና ችግር የሰማችው ነገር አእምሮዋ ሊሸከም ከሚችለው በላይ ነው የሆነባት፡፡እንዴት እንደምትወጣውም መገመት አልቻለችም፡፡
ዓሊ ከዚህ በፊት በግዴለሽነት የፍቅር ግንኙነት ቢጀምርም፣ ዘላቂነት ላለው ግንኙነት ግን ዝግጁ ሀኖ አያውቅም ነበር ። አሁንም እንደ ራሄል ካለች ሴት ጋር ተመሳሳዩን ማድረግ እንደማይችል ያውቃል፡፡ እሷ ሌሎች ምታስቀድማቸው ጉዳዮች እንዳሏት ተረድቷል, እርግጥ ቤተሰቦቿ ከእሱ ጋር እንዳትገናኝ ተስፋ እንዳደረጉ ያውቃል፡፡ በዋነኛነት የእሱን ጀርባ ምን እንደሆነ ባለማወቃቸው ነው። ወላጆቹን ማንነት ቢያውቁ እንደዛ እንደማያስብ እርግጠኛ ነው፡፡ ኮፍያውን ይዞ ቢሮውን ለቆ ወደ ቤቱ አመራ።
ወደ ቤቱ ሲገባ ስልኩ እየጮኸ ነበር እና የጥሪ ማሳያውን በጨረፍታ ተመለከተ ፈገግ አለና አነሳው።‹‹ሄይ እናቴ እንዴት ነሽ?›› ስልኩን በትከሻውና በጆሮው መካከል አድርጎ ጠየቀ። እናቱ የቤቱን ሁኔታ ማየት እንደማትችል ቢያውቅም የጥፋተኝነት ስሜት ተሰምቶታል።
‹‹ደህና ነኝ። ጧት የት ነበርክ?›› አሳዳጊ እናቱ ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሁለት ጊዜ ሞክሬልህ ነበር.›› በድምጿ ውስጥ የስጋት ስሜት ይነበባል ፣ ይህም ዔሊን የበለጠ የጥፋተኝነት ስሜት›› እንዲሰማው አድርጎታል።
‹‹ የእረፍት ቀኔ ነበር ..ግን ሆስፒታል ድንገተኛ ተደወለልኝና ስራ ገባው…ገና በር ከፍቼ ስገባ ነው የደወልሺልኝ.››
‹‹አንተም ሆንክ ቢኒ ቤተክርስቲያን ትመጣላችሁ ብዬ ጠብቄ ነበር..አንተስ እሺ ስራ ላይ ነኝ አልክ… የእሱስ ሰበብ ምንድነው?››
ሰበቡን ያውቃል..እሱ ብቻ ሳይሆን አሳዳጊ እናቱም ጭምር ለምን በቤተክርስቲያን መሄድ እንዳቆመ በደንብ ያውቃሉ..እሱ እንኳን ድሮም ለቤተክርስቲያን እስከዚህም ነበር ወንድሙ ግን ባለቤቱ በአንድሳምንት በሽታ ታማ ሳይታሰብ እስክትሞትበት ድረስ በጣም አካራሪ የሚባል ሀይማኖተኛ ሰው ነበር…ከዛ በኋላ ግን ቀስ በቀስ እግሩን ከቤተክርስቲያን ልቡን ደግሞ ከእግዚያብሄር ሰበሰበ…..በዚህ ጉዳይ ከራሄል ጋር ተመሳሳይ ታሪክ እንዳላቸው ያውቃል…አሁን ግን ይህንን የወንድሙን ጉዳይ ከእናቱ ጋር አንስቶ መጨቃጨቅ ስላልፈለገ በዝምታ ዘለለው
እሱ ከአሳዳጊ ወላጆቹ ጋር የነበረው ዝምድና ሁል ጊዜ ወጣ ገባ ያለው ነበር ። አሳዳጊዎቹ ከእሱ ይልቅ ከቢኒያም ጋር ንፁህ በፍቅር የተሞላ የወላጅ እና የልጅ ግንኙነት ነው ያላቸው፡፡ እሱ ግን ስለ ስጋ ወላጆቹ ማወቅ ይፈልግ ስለነበር ብዙ ጊዜ ባየተዋርነት ይሰማው ነበርና እቤት ውስጥ በራሱ ችግር ይፈጥራ ል… ስለወላጆቹ የሚያውቁትን እንዲነግሩት ያስቸግራቸው ነበር ..እነሱ ግን ምንም ሊነግሩት አልቻሉም።
ባለፈው ዓመት እሱ እና ቢንያም የወላጆቻቸውን ቤት እያፀዱ ሳለ በሰገነት ላይ የፎቶ ሳጥን አገኘ. እነዛን ፎቶዎች ከዚህ በፊት አይቷቸው አያውቅም ነበር ፡ የእሱ የስጋ ወላጆቹ ነበሩ። አሳዳጊዎቹ እሱን ከማደጎ ቤት በተረከቡት ጊዜ ፎቶውንም አብረው ነበር የተረከቡት… ከዛ ግን አርቀው አስቀመጡና ረሱት ፡፡
‹‹ወደ ሆስፒታል እንደተጠራህ ተናግረሃል›› ስትል እናቱ ተናገረች። ‹‹በጣም ከባድ ነገር እንዳልሆነ ተስፋ አደርጋለሁ.››ዔሊ ራሔልን እና ጸጋን አሰበ እና ግንባሩን በጣቱ አሻሸ።
‹‹ከታካሚዬ አንዷ ወደቀች፣ ግን ደህና ነች፣ አንቺ እና አባ እንዴት ናችሁ?››
‹‹ደህና ነን ፡ ግን አንዳንድ ጊዜ መጥተን አንተን እና ቢኒን ቤቱን እንደትጨረሱት ልንረዳችሁ እንፈልግ ነበር።››
‹‹እሺ እማማ፣ አንቺና አባባ በዚህ ጉዳይ ላይ እንድትጨናነቁ አልፈልግም። ››
የእናቱ ዝምታ ሌላ የጥፋተኝነት ስሜት ፈጠረ።
ተሰናበታቸውና እና ስልኩን ዘጋው፡፡
በዚህ ቤት ጉዳይ ወላጆቹንም ሆነ ወንድሙ ቢኒያምን ብዙ ማስቸገር አይፈልግም፡፡
- ይህንን ቤት መስራት መጀመሩ ለእሱ ትልቅ ስኬት ነው ፣ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ የራሱን ቦታ ይፈልግ ነበር ፡፡ እራሱን የሚገነባበት ቦታ። ይህንን ለአሳዳጊ ወላጆቹ በቀላሉ ማስረዳት የሚችለው ነገር አልነበረም፣ ። ገና ወንደላጤነቱን ሳያጣጥም ብድር ውስጥ ገብቶ እቤት ወደመገንባት ውስጥ የገባበትን ምክንያት ቢኒያም እንኳን አልተረዳውም።ምክንያቱም ወንድሙ እንደ እሱ ስለ ስጋ ወላጅቹ ምንም አይነት ትዝታ አልነበረውም። ለእሱ አሳዳጊ ወላጆቹ የስጋ ወላጆቹ እንደሆኑ ነው የሚሰማውም…የሚያምነውም፡፡
እርግጥ ኤልያስም አሳዳጊ ወላጆቹን ይወዳል ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእነሱ ጋር ለመኖር ወደቤታቸው ሲወስዱት የስጋ ወላጆቹን ትዝታዎች በጀርባው አዝሎ ስለነበረ በተለየ ሁኔታ በጣም ያስቸግራቸው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ ስለ ወላጆቹ በጭራሽ ማውራት አቆሙ፡፡ ኤሊ የዛሬ አመት ፎቶዎቹን እስኪያገኝ ድረስ ይህን ተቀብሎ ነበር።አሁን .የፎቶ ሣጥኑን ወደቤቱ አምጥቶታል እነኚያ ሰዎች እነማን እንደሆኑ ለማወቅ ሙከራ ላይ ነው፡፡ ህይወት የሰጡት ወደዚህ ምድር ጎትተው ያመጡት፤እነዛን የመጀመሪያዎቹን ጥቂት የህፃንነት አመታትን ይንከባከቡት የነበሩትን ሰዎች ማነነት የማወቅ ጉጉት እያሰቃየው ነው።
ሳያውቅ እጁን አዞረና ጀርባ ላይ ያለውን ጠባሳ አሻሸው፣ከአደጋውን ያተረፈው ቅሪት ነው ።ስለ ፀጋ አሰበ። ገና ህፃን ስለሆነች ወደፊት ስለ እናቷ ምንም ትዝታ እንዳማይኖራት ተስፋ አደረገ ። ግን ቢያንስ ለእሷ እሱ አለላት..እናቷ ምን አይነት ሰው እንደሆነች….ስለደግነቷ..ስለውበቷ እና ስለአስቂኝ ጫወታዋ …በዝርዝር ሊነግራት ይችላል፡፡ከፈለገችም…አሁን በህይወት ስለሌሉት አያቶቹም ጭምር ሊነግራት ይችላል…ምክንያቱም የእናቷ የፅጌረዳን እናትና አባት ከልጅነቱ ጀምሮ በደንብ ያውቃቸዋል…ፅጌረዳ ተከትሎ ብዙ ጊዜ እቤታቸው የመመላለስ እድል ነበረው..ደሆች ቢሆኑም ልበ ቀና መልካም ሰዎች ነበሩ…ይሄንን ሁሉ ሊያስረዳት ይችላል..ለእሱ ግን እንደዚህ አይነት ስለዋላጆቹ ጥቂት እንኳን አውቃለው የሚል ሰው የማግኘት እድል የለውም፡፡

❤71👍12
የራሄል ልብ በእፎይታ ተነፈሰ።አብሮት እየተራመደ ያለውን ተለማማጅ ዶ/ር ወደ ጎን ተመለከተው፣ እያወሩ ነበር ። ድንገት ዞር ሲል ከራሄል ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ የተሰማትን አይነት ተመሳሳይ ምላሽ ተሰማት። ተንደርድሮ ወደእሷ መጣ፡፡
ከዚያም የፀጋን የህክምና ቻርት ላይ የሆነ ምልክት እያደረገች ወዳለችው ነርስ ተጠጋና ተመለከተ። ‹ታዲያ ችግሩ ምን ይመስላሻል ?›› ብሎ ጠየቀ ከራሄል ወደ ፀጋ ከዚያም ወደ ነርሷ ተመለከተ። ራሄል ‹‹ከፍኛ ትኩሳት አላት›› አለችው.
ነርሷ ‹‹አሁን የሙቀት መጠንዋን ወስጃለሁ….ትንሽ ከፍ ያለ ነው፣ ግን ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም።››
ራሔል ነርሷ ላይ አፈጠጠች ፣ግራ ተጋባች፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለከተች። ‹‹ በጣም እኮ ነበር የምትሞቀው.››
ዔሊ ሰንጠረዡን ከነርሷ ተቀብሎ ተመለከተ እና እጁን በህፃኗ ግንባሩ ላይ አደረገ። ፀጋ በድንገት ሁሉም ነገር ደህና የሆነ ይመስል ፈገግ አለችለት‹‹አሁንም አንቲ ባዮቲኮችን እየሰጠሻት ነው?›››
‹‹አዎ ››
‹‹ደህና፣ እየሰሩ ያሉ ይመስላሉ፣ ግን ፈገግታዋ ጠፍቷል፣ የድምፁ ቃናዋም ተለውጣል፣ እሷን መናደድ የለባትም››
‹‹የምን መናደድ …ከሰአት በኋላ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ለመንከባከብ የተመሰከረለትን የመዋለ ሕጻናት አገኘሁ።እና እዛ ወሰድኳት..ከስራ ተመልሼ ልወስዳት ስሄድ ታማ አገኘኋት… እና አሁን የሚያስፈልገኝ በእሷ ላይ ያለውን ችግር እንድትነግሩኝ ነው።››
ዔሊያስ በትንሹ ተነፈሰ… ነገር ግን ዓይኖቿን ራሄል ላይ እያንከራተተች ወዳለችው ታዳጊ ልጅ ተመለከተ። የታችኛው ከንፈሯ ያብለጨልጭ ጀመር እና እንደገና ልታለቅስ ያሰበች ይመስላል ። ራሄል ጀርባዋን እየደባበሰች አባበለቻት፡፡
በወረቀት ላይ ማስታወሻዎችን እየጻፈ። ‹‹ደህና ነች..አዎ፣ የሙቀት መጠኑ በትንሹ ከፍ ብሏል፣ ግን ያ ስለተበሳጨች ሊሆን ይችላል። አንድ ጆሮዋ ትንሽ ቀላ ያለ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ በፀረ-ባዮቲክስ መድሀኒት ይወርዳል። መበሳጨት ከጀመረች ስጧት። የሙቀት መጠኗን መቆጣጠሪያ በእጅሽ ላይ ሊኖርሽ ይገባል.. የሚያስፈልጉሽን ነገሮች ዝርዝር ነገ እሰጥሻለሁ፤››አለና ወረቀቱን ከፓድ ላይ ቀዶ ዘረጋላት።ራሄል በድንገት ሞኝነት ተሰማት፣ነገር ግን ፀጋ ደህና መሆኗን በማወቋ እፎይታ አግኝታለች።
ወረቀቱን ወደ ቦርሳዋ እያስገባች‹‹ለምክርህ አመሰግናለሁ››አለችው
‹‹በዚህ ኢንፌክሽን ደረጃ ለማረጋገጥ ከነገ ወዲያ እሷን ማየት እፈልጋለሁ። ለአንቺ ስንት ሰዓት ይምችሻል?››በጥያቄው ስለተበሳጨች እኩለ ሌሊት ልትለው አሰበች. ፡፡
‹‹ለምን አንተ ቀጠሮ አትይዝልኝም እኔ ፕሮግራሜን ማሸጋሸግ እችላለው፡፡ ››አለችው፡፡
‹‹ቤት ላገኝሽ ካልቻልኩ… የት ላገኝሽ እችላለሁ?››
የቢሮ ቁጥሯን እና የሞባይል ስልኳን ሰጠችው።በስራ ቦታ ልታገኘኝ ካልቻልክ ለሎዛ መልእክት ተውልኝ። ሞባይል ስልኬ በአብዛኛው ክፍት ነው። በተጨማሪም የወላጆቼ ቁጥር አለህ። ››
የንዴት ፈገግታ አሳያት።‹‹እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች አያስፈልጉኝም?››
በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከወ.ሮ ላምሮት ጋር መገናኘት ነበረባት እና አሁን ለፀጋ የምትገዛቸው መድሀኒቶች አሉ..በዛ ላይ ምግቧንም መመገብ አለባት….በዚህ ሁኔታ ላይም እያለች ጥላት መሄድ አትችልም ፡፡ያላት ምርጫ ሴትዬዋን ይቅርታ ጠይቃ ሌላ ቀጠሮ ማስያዝ ነው፡፡
‹‹መሄድ አለብኝ››አለች.
‹‹ትሁትን ስላየህልኝ አመሰግናለሁ፣››አለችው በድጋሜ
‹‹ ከሁለት ቀናት በኋላ እንገናኝ።››አለና የድንገተኛ ክፍልን ለቅ ወጣ።

❤31🤔13👏6
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ
፡
፡
#ክፍል_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ
ይህ ፋውንዴሽን አሁን የደረሰበት ደረጃ የደረሰው በዚህ መንገድ ነበር, አሰበች እንደ ሮቤል ያሉ ሰዎች የወላጆቿ ሀብት የፋውንዴሽኑን የጀርባ አጥንት እንደሆነ ነው የሚያስቡት፣ ገንዘብ በቀላሉ ወደ ሣጥን ውስጥ እንደሚገባ ያስባሉ ። ፣ ከቅርብ ረዳቶቿ ከሆኑ በጣም ጥቂት ሰዎች በስተቀር፣ በዚህ ስራ ውስጥ ግንኙነቶች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አይረዱም። ግንኙነቶች፣ መተማመን እና ከፍተኛ የስራ ስሜት ወሳኝ ነገሮች ናቸው። ገንዘቡ ወደፋውንዴሽኑ ከሚገባት ፍጥነት ሚወጣበት ፍጥነት ይበልጣል።ራሄል የፋውንዴሽኑን አስተዳደር ስትረከብ፣ የሂሳብ መዝገቡ አሁን ባለበት ሁኔታ ጤናማ አልነበረም።
ወላጆቿ ጥሩ ልብ ያላቸው የሰው ልጅን ያለልዩነት ለመርዳትና ለማገዝ ከልብ የሚጥሩ ቀና ሰዎች ቢሆኑም የተሳሳቱ ሰዎችን አምነው ስለነበር ለከፍተኛ ምዝበራ ተጋልጠው ነበር።እና ራሄል ስራዋን ከወላጇቾ ሙሉ በሙሉ ከተረከበች በኃላ አጠቃላይ የፋውንዴሽኑን ተቋማዊ አቅም ለማሻሻል ጥቂት አመታትን እና አንዳንድ ከባድ ውሳኔዎችን እንድትወስድ አስገድዷታል፣ከዛ ቀስ በቀስ ፋውንዴሽኑን አሁን ያለበት አቋም ላይ እንዲገኝ ማድረግ ችላለች፡፡ የተቋቋሙ ያገኘውን ገቢ በጥንቃቄ ለተከበሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን እንደሙዳይ…ሜቅዶኒያ ላሉ ገንዘብን ለታለመለት አላማ ብቻ ለሚያውሉ ተቋማት ያከፋፍላል፡፡ቀዳዳቸውን ይደፍናል ጉድለታቸውን ይሞላል፡፡
‹‹ሮቤል፣ ስለዚህ ጉዳይ አሁን ማውራት አልችልም። አሁንም ከሎዛ ጋር መገናኘት እና ከዚያም ፀጋን ከመዋለ ሕጻናት መውሰድ አለብኝ።ከዛ ቀጥታ ወ.ሮ ላምሮትን ሄጄ አገኛታለው….ደውልላት እና ከአንድ ሰዓት በኋላ እቤቷ እንደምገኝ ንገራት፡፡››አለችው፡፡ ወይዘሮ ላምሮት ብዙ ጊዜዋን እየወሰደች ነበር፣ ሴትየዋን ወደ ሎዛ ለማስተላለፍ አልደፈረችም ፡፡ለዚህ ነው ቀጥታ እራሷ ልታገኛት የወሰነችው፡፡
ቦርሳዋን ይዛ ከቢሯዋ ወጣች፡፡
ከአስራ አራት ደቂቃ በኋላ ወደ መዋዕለ ሕጻናት ማእከሉ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ስትገባ ጎማ በጭቃ ውስጥ ገባ። ቦርሳዋን እና ቁልፏን ይዛ ከመኪናው ውስጥ ዘላ ወጣች፣ ጉልበቷን የበሩን ጠርዝ መታት..አቃሰተች እና ጎንበስ ብላ እያሻሸች መንገዷን ቀጠለች .. የሞባይል ስልኳ እየጠራ ቢሆንም ችላ ብላ የመዋዕለ ሕፃናት ማቆያውን የመስታወት በሮች ከፍታ ወደውስጥ ገባች ፡፡ለአባቷ የገባችው ቃል ኪዳን እና በኤሊያስ አይኖች ውስጥ ያነበበችው ጥርጣሬ ለፀጋ አስፈላጊውን ጊዜ መድቦ ተገቢውን እንክብካቤ ለማድረግ ቁርጠኛ እንድትሆን አድርጓታል። ከሁሉም በላይ ግን ፀጋ እህቷ ነበረች። እና ምንም አይነት አስቸጋሪ ቢሆንም በክፉ ቀን ቤተሰብ ለቤተሰብ መከታ መሆን እንዳለበት ታምናለች፡፡ ፀጋ ሰዓቱን በትኩረት በምትመለከተው የቀን ተንከባካቢ ሰራተኛ እቅፍ ውስጥ ሆና እየጠበቀቻት ነበር። አፏ እና ጠባብ አይኖቿ ስትመለከት ነገሮች ጥሩ እንዳልሄዱ ገመተች።
‹‹ሴት ልጃችሁን በፕሮግራማችን ስታስመዘግቡ ፖሊሲያችንን በግልፅ አሳውቀናችኋል።›› ሴትዬዋ በጠንካራ ንጭንጭ ተቀበለቻት፡፡
‹‹ይገባኛል... ›› አለች‹‹እና እህቴን በሰዓቱ ስላልወሰድኩ ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ››ስትል አከለችበት ፡፡
‹‹በጣም ዘግይተሻል››የሚለው ቃል አከለችበት ። ጎንበስ ብላ የፀጋን ዳይፐር ከቦርሳ አወጣች እና ከዚያም ወደ እህቷ ተጠጋች ።‹‹ቶሎ ልናገኝሽ ሞክረን ነበር።›› ወይዘሮ ባንቺ ወደ ፀጋ ተመለከተች እና ፊቷን አኮሰታተረች። ያን ጊዜ ነበር ራሄል የልጅቷን በእንባ የታጠበ ጉንጯች ያስተዋለች። ‹‹ፀጋ ጥሩ ቀን አላሳለፈችም። ነርሷ የሙቀት መጠንዋን ስትወስድ ከፍ ብሎ ነበር፣ በተቻለ ፍጥነት ሀኪም ቤት እንድትወስዷት ተናግራለች ።››
‹‹እንዴ አሁን?...ለማለት የፈለኩት ይህ ምን ያህል አጣዳፊ ነው? ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል ልውሰዳት ወይስ ሁኔታዋን መከታተል አለብኝ?››ስትል ጠየቀች፡፡
ወይዘሮ ባንቺ ‹‹ወዲያውኑ ብትወስጂያት መልካም ይመስለኛል.. እህትሽ ካለባት የጤና ችግር አንፃር የበለጠ ንቁ መሆን ይገባታል።
‹‹ያንን አስቤ ነው ወደዚህ ያመጣኋት… በቃ ወስዳታለው›› የፀጋ የሰውነት ሙቀት በልብሷ አልፎ እየተሰማት ነው። ላለባት ቀጠሮ ሰዓቷን ለማየት አልደፈረችም። ሆስፒታሉ ከመዋዕለ ህጻናት ብዙም ባለመራቁ አመሰገነች፡፡
ከሃያ ደቂቃ በኋላ ወደ ሆስፒታሉ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ገባች እና በድንገተኛ ክፍል በሮች ቸኩላ ስታልፍ ትዝታዎቹ እየተጣደፉ መጡባት።በእቅፏ ወደተቀመመችው ፀጋ ተመለከተች እና አዲስ ፍርሃት መላ ሰውነቷን ተቆጣጠራት። ወደ መቀበያ ጠረጴዛው እየገሰገሰች ስትሄድ፣ ቀድሞውንስ ይሄን ጉዳይ እንዴት አድርጋት ልትወጣ እንዳሰበች ተገረመች። ላለፉት ስምንት አመታት በድንገት የሚደፈርስ ስሜት እና ከቁጥጥር ውጪ የሚወጣ ድንገተኛ ብስጭትን ስትዋጋ ነው የኖረችው። አሁን የአንዲት ቀጫጫ ነርስን ማይረብ ጥያቄዎችን በትዕግስት እየመለሰች ነው።እንደጨረሰች በውስጧ እየበቀሉ ያሉ አሮጌ እና አዲስ ፍራቻዎችን እየታገለች፣ ለሆስፒታሎች ልዩ የሆኑትን የተለመዱ ሽታዎች እያሸተተች በተጨናነቀው የመጠበቂያ ክፍል ውስጥ ተመልሳ ተቀመጠች።
ከድንጋጤዋ የተነሳ መላ ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ነው ፡፡ለፀጋ ስትል ትኩረቷን ለመሰብሰብ መሞከር አለባት።ፀጋ እጆቿ ይንቀጠቀጣሉ፣ ከሰውነቷ የሚወጣው ሙቀት በየደቂቃው እየጨመረ ነው። ነርሶቹ በስራ ተጠምደዋል፡፡ችሎታ ያለው እና ኃላፊነት የሚሰማው ዶ ር ለማግኘት ዙሪያውን አማተረች። አንዳቸውም ወደ ራሔል ዞር ብለው አላዩትም።ሰዎች ወንበሮች ላይ ተቀምጠው ይንቆራጥጣሉ፣ አንዳንዶቹ ጎንበስ ብለው ያቃስታሉ፣ ሌሎች ደግሞ ደንዝዘው እያንጓላጅጁ ነው፡፡
እያንዳንዳቸው በራሳቸው መከራና ሀዘን ተይዘዋል..ስለ ራሄል እና በእቅፏ ውስጥ እየተቃጠለች ስላለችው ህፃን ደንታ አልነበራቸውም።ከዚያም ፀጋ እየደነዘዘች ሄደች፡፡ ድንጋጤ የራሄልን ጉሮሮ አነቃት። አምላክ ማንኛውንም ነገር እንደሚያደርግ ብታምን ኖሮ አሁን በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ትጸልይ ነበር።እግዚአብሔር ግን ከዚህ በፊት ከልቧ በፀለየችበት ጊዜ ትኩረት አልሰጣትም ነበር እና አሁንም እሱ ላይ መንጠልጠል አልፈለገችም፡፡ ፀጋ ማቃሰቱን አቁማ እንደገና በመጠኑ ዘና ስትል እፎይታ ተሰማት። ራሄልን ቀና ብላ ተመለከተች፣ታናሽ እህቷ ለስላሳ ቡናማ አይኖቿን ራሄል ላይ አንከባለለችባት፡፡ ራሄል በምላሽ ልቧ ሲዘል ተሰማት። ከዚያም ራቅ ብላ ተመለከተች።
ፀጋ ለእሷ ግዴታዋ ነበርች ይህች ልጅ ቀስ በቀስ የፍቅር እሳት በልቧ ዙሪያ እንዲቀጣጠል እያደረገች ነው። እንደ ፀጋ ካለች ልጅ ጋር መጣበቅ ማለት ልቧን ለህመም እና ማጣት እምቅ ስቃይ መከፈት ማለት እንደሆነ ታውቃለች።እና ያንን በራሷ ላይ እንደገና ማድረግ ፈፅሞ አትፈልግም ነበር ፡፡ግን ደግሞ በምርጫዋ እያደረገችው ያለ ነገር አይደለም፡፡ከአሰልቺ ጥበቃ በኃላ ነርሷ መጥታ በመጋረጃ ወደተሸፈነው ክፍል ወሰዳቻቸው። ራሄል እህቷን አልጋው ላይ በጥንቃቄ አስቀመጠቻት።ነርሷ የጥያቄዎችን ፣ የአለርጂዎችን ፣ የመድኃኒቶችን ዝርዝር ጠየቀቻት። ራሄል የምትችለውን ያህል መለሰች።እንደጨረሰች ነርሷ ጆሮዋ ውስጥ ቴርሞሜትር ጨመረች ..በዛ ቅፅበት አንድ ዶክተር ኮሪደሩን ሰንጥቆ ወደ እነርሱ ሲመጣ ተመለከተች። ነጭ ጋወን አድረጎ ስቴቶስኮፕ አንገቱ ላይ አንጠልጥሏል ።ኤሊ ነበር።

❤43
የራሄል ልብ በእፎይታ ተነፈሰ።አብሮት እየተራመደ ያለውን ተለማማጅ ዶ/ር ወደ ጎን ተመለከተው፣ እያወሩ ነበር ። ድንገት ዞር ሲል ከራሄል ጋር አይን ለአይን ተገጣጠሙ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገናኙ የተሰማትን አይነት ተመሳሳይ ምላሽ ተሰማት። ተንደርድሮ ወደእሷ መጣ፡፡
ከዚያም የፀጋን የህክምና ቻርት ላይ የሆነ ምልክት እያደረገች ወዳለችው ነርስ ተጠጋና ተመለከተ። ‹ታዲያ ችግሩ ምን ይመስላሻል ?›› ብሎ ጠየቀ ከራሄል ወደ ፀጋ ከዚያም ወደ ነርሷ ተመለከተ። ራሄል ‹‹ከፍኛ ትኩሳት አላት›› አለችው.
ነርሷ ‹‹አሁን የሙቀት መጠንዋን ወስጃለሁ….ትንሽ ከፍ ያለ ነው፣ ግን ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም።››
ራሔል ነርሷ ላይ አፈጠጠች ፣ግራ ተጋባች፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለከተች። ‹‹ በጣም እኮ ነበር የምትሞቀው.››
ዔሊ ሰንጠረዡን ከነርሷ ተቀብሎ ተመለከተ እና እጁን በህፃኗ ግንባሩ ላይ አደረገ። ፀጋ በድንገት ሁሉም ነገር ደህና የሆነ ይመስል ፈገግ አለችለት‹‹አሁንም አንቲ ባዮቲኮችን እየሰጠሻት ነው?›››
‹‹አዎ ››
‹‹ደህና፣ እየሰሩ ያሉ ይመስላሉ፣ ግን ፈገግታዋ ጠፍቷል፣ የድምፁ ቃናዋም ተለውጣል፣ እሷን መናደድ የለባትም››
‹‹የምን መናደድ …ከሰአት በኋላ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ለመንከባከብ የተመሰከረለትን የመዋለ ሕጻናት አገኘሁ።እና እዛ ወሰድኳት..ከስራ ተመልሼ ልወስዳት ስሄድ ታማ አገኘኋት… እና አሁን የሚያስፈልገኝ በእሷ ላይ ያለውን ችግር እንድትነግሩኝ ነው።››
ዔሊያስ በትንሹ ተነፈሰ… ነገር ግን ዓይኖቿን ራሄል ላይ እያንከራተተች ወዳለችው ታዳጊ ልጅ ተመለከተ። የታችኛው ከንፈሯ ያብለጨልጭ ጀመር እና እንደገና ልታለቅስ ያሰበች ይመስላል ። ራሄል ጀርባዋን እየደባበሰች አባበለቻት፡፡
በወረቀት ላይ ማስታወሻዎችን እየጻፈ። ‹‹ደህና ነች..አዎ፣ የሙቀት መጠኑ በትንሹ ከፍ ብሏል፣ ግን ያ ስለተበሳጨች ሊሆን ይችላል። አንድ ጆሮዋ ትንሽ ቀላ ያለ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ በፀረ-ባዮቲክስ መድሀኒት ይወርዳል። መበሳጨት ከጀመረች ስጧት። የሙቀት መጠኗን መቆጣጠሪያ በእጅሽ ላይ ሊኖርሽ ይገባል.. የሚያስፈልጉሽን ነገሮች ዝርዝር ነገ እሰጥሻለሁ፤››አለና ወረቀቱን ከፓድ ላይ ቀዶ ዘረጋላት።ራሄል በድንገት ሞኝነት ተሰማት፣ነገር ግን ፀጋ ደህና መሆኗን በማወቋ እፎይታ አግኝታለች።
ወረቀቱን ወደ ቦርሳዋ እያስገባች‹‹ለምክርህ አመሰግናለሁ››አለችው
‹‹በዚህ ኢንፌክሽን ደረጃ ለማረጋገጥ ከነገ ወዲያ እሷን ማየት እፈልጋለሁ። ለአንቺ ስንት ሰዓት ይምችሻል?››በጥያቄው ስለተበሳጨች እኩለ ሌሊት ልትለው አሰበች. ፡፡
‹‹ለምን አንተ ቀጠሮ አትይዝልኝም እኔ ፕሮግራሜን ማሸጋሸግ እችላለው፡፡ ››አለችው፡፡
‹‹ቤት ላገኝሽ ካልቻልኩ… የት ላገኝሽ እችላለሁ?››
የቢሮ ቁጥሯን እና የሞባይል ስልኳን ሰጠችው።በስራ ቦታ ልታገኘኝ ካልቻልክ ለሎዛ መልእክት ተውልኝ። ሞባይል ስልኬ በአብዛኛው ክፍት ነው። በተጨማሪም የወላጆቼ ቁጥር አለህ። ››
የንዴት ፈገግታ አሳያት።‹‹እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች አያስፈልጉኝም?››
በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከወ.ሮ ላምሮት ጋር መገናኘት ነበረባት እና አሁን ለፀጋ የምትገዛቸው መድሀኒቶች አሉ..በዛ ላይ ምግቧንም መመገብ አለባት….በዚህ ሁኔታ ላይም እያለች ጥላት መሄድ አትችልም ፡፡ያላት ምርጫ ሴትዬዋን ይቅርታ ጠይቃ ሌላ ቀጠሮ ማስያዝ ነው፡፡
‹‹መሄድ አለብኝ››አለች.
‹‹ትሁትን ስላየህልኝ አመሰግናለሁ፣››አለችው በድጋሜ
‹‹ ከሁለት ቀናት በኋላ እንገናኝ።››አለና የድንገተኛ ክፍልን ለቅ ወጣ።
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ከዚያም የፀጋን የህክምና ቻርት ላይ የሆነ ምልክት እያደረገች ወዳለችው ነርስ ተጠጋና ተመለከተ። ‹ታዲያ ችግሩ ምን ይመስላሻል ?›› ብሎ ጠየቀ ከራሄል ወደ ፀጋ ከዚያም ወደ ነርሷ ተመለከተ። ራሄል ‹‹ከፍኛ ትኩሳት አላት›› አለችው.
ነርሷ ‹‹አሁን የሙቀት መጠንዋን ወስጃለሁ….ትንሽ ከፍ ያለ ነው፣ ግን ምንም የሚያሳስብ ነገር የለም።››
ራሔል ነርሷ ላይ አፈጠጠች ፣ግራ ተጋባች፣ ከዚያም ወደ ዔሊ ተመለከተች። ‹‹ በጣም እኮ ነበር የምትሞቀው.››
ዔሊ ሰንጠረዡን ከነርሷ ተቀብሎ ተመለከተ እና እጁን በህፃኗ ግንባሩ ላይ አደረገ። ፀጋ በድንገት ሁሉም ነገር ደህና የሆነ ይመስል ፈገግ አለችለት‹‹አሁንም አንቲ ባዮቲኮችን እየሰጠሻት ነው?›››
‹‹አዎ ››
‹‹ደህና፣ እየሰሩ ያሉ ይመስላሉ፣ ግን ፈገግታዋ ጠፍቷል፣ የድምፁ ቃናዋም ተለውጣል፣ እሷን መናደድ የለባትም››
‹‹የምን መናደድ …ከሰአት በኋላ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ልጆች ለመንከባከብ የተመሰከረለትን የመዋለ ሕጻናት አገኘሁ።እና እዛ ወሰድኳት..ከስራ ተመልሼ ልወስዳት ስሄድ ታማ አገኘኋት… እና አሁን የሚያስፈልገኝ በእሷ ላይ ያለውን ችግር እንድትነግሩኝ ነው።››
ዔሊያስ በትንሹ ተነፈሰ… ነገር ግን ዓይኖቿን ራሄል ላይ እያንከራተተች ወዳለችው ታዳጊ ልጅ ተመለከተ። የታችኛው ከንፈሯ ያብለጨልጭ ጀመር እና እንደገና ልታለቅስ ያሰበች ይመስላል ። ራሄል ጀርባዋን እየደባበሰች አባበለቻት፡፡
በወረቀት ላይ ማስታወሻዎችን እየጻፈ። ‹‹ደህና ነች..አዎ፣ የሙቀት መጠኑ በትንሹ ከፍ ብሏል፣ ግን ያ ስለተበሳጨች ሊሆን ይችላል። አንድ ጆሮዋ ትንሽ ቀላ ያለ ይመስላል፣ ነገር ግን ይህ በፀረ-ባዮቲክስ መድሀኒት ይወርዳል። መበሳጨት ከጀመረች ስጧት። የሙቀት መጠኗን መቆጣጠሪያ በእጅሽ ላይ ሊኖርሽ ይገባል.. የሚያስፈልጉሽን ነገሮች ዝርዝር ነገ እሰጥሻለሁ፤››አለና ወረቀቱን ከፓድ ላይ ቀዶ ዘረጋላት።ራሄል በድንገት ሞኝነት ተሰማት፣ነገር ግን ፀጋ ደህና መሆኗን በማወቋ እፎይታ አግኝታለች።
ወረቀቱን ወደ ቦርሳዋ እያስገባች‹‹ለምክርህ አመሰግናለሁ››አለችው
‹‹በዚህ ኢንፌክሽን ደረጃ ለማረጋገጥ ከነገ ወዲያ እሷን ማየት እፈልጋለሁ። ለአንቺ ስንት ሰዓት ይምችሻል?››በጥያቄው ስለተበሳጨች እኩለ ሌሊት ልትለው አሰበች. ፡፡
‹‹ለምን አንተ ቀጠሮ አትይዝልኝም እኔ ፕሮግራሜን ማሸጋሸግ እችላለው፡፡ ››አለችው፡፡
‹‹ቤት ላገኝሽ ካልቻልኩ… የት ላገኝሽ እችላለሁ?››
የቢሮ ቁጥሯን እና የሞባይል ስልኳን ሰጠችው።በስራ ቦታ ልታገኘኝ ካልቻልክ ለሎዛ መልእክት ተውልኝ። ሞባይል ስልኬ በአብዛኛው ክፍት ነው። በተጨማሪም የወላጆቼ ቁጥር አለህ። ››
የንዴት ፈገግታ አሳያት።‹‹እነዚህ ሁሉ ቁጥሮች አያስፈልጉኝም?››
በግማሽ ሰዓት ውስጥ ከወ.ሮ ላምሮት ጋር መገናኘት ነበረባት እና አሁን ለፀጋ የምትገዛቸው መድሀኒቶች አሉ..በዛ ላይ ምግቧንም መመገብ አለባት….በዚህ ሁኔታ ላይም እያለች ጥላት መሄድ አትችልም ፡፡ያላት ምርጫ ሴትዬዋን ይቅርታ ጠይቃ ሌላ ቀጠሮ ማስያዝ ነው፡፡
‹‹መሄድ አለብኝ››አለች.
‹‹ትሁትን ስላየህልኝ አመሰግናለሁ፣››አለችው በድጋሜ
‹‹ ከሁለት ቀናት በኋላ እንገናኝ።››አለና የድንገተኛ ክፍልን ለቅ ወጣ።
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤27👍7🔥1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ራሄልም እህቷን ይዛ እቤት እንደገባች ጓደኛዋ ሜሮን ቤት እየጠበቀቻት ነው፡፡መጀመሪያ ቀጠሮውን ለመሰረዝ ፈልጋ ነበር…በኋላ ስታስበው ግን ሴትዬዋ ለስብሰባው ትኩረት እንዳልሰጠች አድርጋ ልትረዳት እንደምትችል ስላሰበች ለመሄድ ወሰነች፡፡ ከሆስፒታል እንደተነሳች ነበር ደውላ ቤት እንድትጠብቃት የጠየቀቻት፡፡፡‹‹ቀጠሮው በጣም ወሳኝ ስለሆነ ነው ያስቸገርኩሽ፡፡››
‹‹አረ ችግር የለውም..ያንቺ እህት ማለት እኮ የእኔ እህት ነች››አለች ሜሮን፡፡
‹‹እሱስ እውነት ነው››
‹‹አዎ ደግሞም አሪፍ የምስራች አለኝ…››
‹‹እባክሽ ንገሪኝ ቀኑን ሙሉ ስጨናነቅ ነው የዋልኩት…ፈገግ ማለት አምሮኛል››
‹‹አንድ እምቅ ችሎታ ያላት እና በነርሲንግ የሰለጠነች ሞግዚት አግኝቼልሻለው›› አለቻት….ከሁለት ቀን በፊት ለሁሉም ጓደኞቾ ስለፀጋ ነግራቸው የሰለጠነች ሞግዚት እንዲፈልጉላት አደራ ብላቸው ነበር፡፡
‹‹አንቺ እኮ ሕይወት አድን ነሽ›› አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጯን ሳመቻት፡፡
ወደቀጠሮ ቦታ ይዛ የምትሄደቸውን ወረቀቶች ወደ ቦርሳዋ አስገባች።
‹‹ሞግዚት ማግኘት ከቻልኩ የፀጋ ዶ/ር የሰጠውን መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ እንዲተገበር ማድረግ እችላለው። ውዴ ለአሁን ፀጋን ልትጠብቂልኝ ስለወሰንሽ ደስተኛ ነኝ። ነገሮች ሁሉ ሰላም እንደሚሆኑ አምናለው?››
‹‹ሄይ. ታውቂያለሽ እኔ በጣም ጥሩ ጓደኛሽ ነኝ.››
‹‹ብቃት ያለው ሞግዚት አግኝተሸልኝማ ያንን መካድ አልችልም… በጣም ጥሩ ጓደኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ህይወት አድንም ነሽ።››
‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ እስኪ በመጠኑ ዘና ለማለት ሞክሪ….››
ራሄል ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ላላት ቀጠሮ የምትጠቀምባቸውን መረጀጃዎች የያዙ ወረቀቶች እየለየች ‹‹ዘና ማለት እንኳን የምችል አይመስለኝም…ደክሞኛል… በአእምሮዬ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ,››ስትል መለሰችላት፡፡ቀጥላም‹‹‹‹በፋውንዴሽን ውስጥ ነገሮች በጥሩ መንገድ እየሄዱ አይደለም ፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ለጋሾችን አጥቻለሁ አሁን የምሄድባትን ሴትዬ ከዋና ለጋሾቻችን የመጀመሪያዋ ነች….እሷን የግድ ማሳመን አለብኝ ››
‹‹ለምን ሎዛ እንድትሰራው አታደርጊም?››
ራሄል ነገሩን በማሰብ ትንሽ ቆም ብላ ራሷን በአሉታ ነቀነቀች።‹‹ይህን ከባድ ኃላፊነት በእሷ ትከሻ ላይ መጣል አልችልም››
‹‹ስለዚህ በራስሽ ላይ ትጥያለሽ ..እሱ ችግር የለውም ማለት ነው?››
‹‹ትከሻዬ ከሷ የበለጠ ልምድ ያለው ነው›› አለች ፡፡
‹‹ጓደኛዬ ጥቂት ስራዎችን ለሌላ ሰው ብታስተላልፊ አለም አትገለባበጥም።እና ደግሞ የህይወት ሸክማችንን የሚያቀልልን ክርስቶስ ነው….በእሱ መታመን ችግራቸንን ያቀልልናል፡፡››
‹‹እና ለምን ያቺን አሁን በስቃይ የምታለቅሰውን ትንሽ ልጅ እንዲህ አጎጉል አደረጋት? በኢየሱስ አላምንም ብላ ይሆን ?››በራሄል ንግግር ሜሮን በጣም ደነገጠች፣
‹‹ራሄል .. አንቺ እኮ ከዚህ የበለጠ አስተዋይ ነሽ ››ራሄል እጇን ወደ ላይ ዘረጋች።
‹‹አዝናለሁ ስለ ኃጢአት እና ክፋት ሁሉን ነገር አውቃለሁ እናም እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ስር እንደሆነም አምናለው, ስለዚህ ስብከት አንዳትጀምሪኝ››
ሜሮን የጓደኛዋን ትከሻው በፍቅር እየዳበሰች‹‹ታውቂያለሽ አይደል …?ማመን ስለማትፈልጊ ብቻ ነው. እንዲህ የምትይው…ግን እወቂ አሁንም በኢየሱስ ጥበቃ ውስጥ ነሽ …አዎ፣ በግንኙነቶች ውስጥ ህመም አለ…በሆነ ግንኙነት ተሰብረን ሊሆን ይችላል፣ ቢሆንም ልባችንን ሁሌ ለፍቅር ክፍት መሆን አለበት ››
‹‹ደህና፣ አሁን ለልብ ጉዳዬች ጊዜ የለኝም።ደግሞ እስከአሁን ለእኔ የሚሆን ሰው አላጋጠመኝም።›› መስታወት አወጣች እና ሜካፕ እና ፀጉሯን በፍጥነት አስተካከለች።
ሜሮን ‹‹ዶ/ሩ በጣም የሚስብ ይመስለኛል››ስትል አዲስ ድንገተኛ ርዕስ ከፈተች፡፡
ራሄል የጓደኛዋን ሹፈት ችላ በማለት ቦርሳዋን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠለጠለች ፡፡
‹‹እሱ ማራኪ ነው…እንዳልኩሽ ግን ለጊዜው ለማንም ጊዜ የለኝም ።››በማለት መለሰችላት፡፡
ራሄል ወደ በሩ ስትሄድ ሜሮን ‹‹መልካም ጊዜ ይሁንልሽ›› ብላ ጮኸች።
////
ራሄል ከሴትዬዋ ጋር እያካሄደች ያለውን ስብሰባ አንድ ሰዓት በላይ ብታሳልፍም..እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ልታሳምናት አልቻለችም፡፡
‹‹ባለቤቴ በዚህ ገንዘብ በጣም ነው የሚያምነኝ… እናም ይህን በትክክለኛው መንገድ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹ይገባኛል››አለች ራሄል። ነገር ግን የባለቤቷትን እምነትን ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ገንዘቡን ለትክክለኛው ዓላማ ብቻ ለሚጠቀም በጎ አድራጎት መስጠት ነው።››
ወ.ሮ ላምሮት ፈገግ አለችላት፡፡
ወ.ሮ ላምሮት ራሄልን በትኩረት አየቻትና ‹‹አባትሽን ትመስያለሽ›› አለቻት። ‹‹እሱ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚሰራ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁልጊዜ ምሳሌ ነው.››ስትል አከለችበት፡፡
ራሄል መራራ ህመም ተሰማት። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአምላክ ጋር ብዙ ጊዜ አላጠፋችም። የወ.ሮዋ ቃላት አብዝታ ወደ ጸለየችበት፣ መጽሐፍ ቅዱሷን በሰፊው ታንብበት ወደ ነበረችበት ጊዜ አመጣት። ቤተክርስቲያን እና እምነት የመተንፈስ ያህል የእርሷ አካል ነበር። እምነቷን መልሶ ለማግኘት እና በአምላክ ላይ መታመን ለምን እንደሚያስፈልጓት አሰበች። ››
በወ.ሮ ላምሮት ፈገግ ብላ ሰዓቷን በጥበብ ተመለከተች። ለመውጣት ጊዜው ነበር፡፡
‹‹እኔ እንዳልኩት፣ እባኮት ይህን በትክክለኛው መንገድ ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ስጡኝ..ያንን ብቻ ነው የምጠይቀው››አለች ራሄል፣
ወ.ሮ ላምሮት ከግዙፉ መኖሪያ ቤቷ ስትሸኛት ራሄል የመጨረሻ የማሳመኛ ንግግሯን ተናገረች‹‹እርግጠኛ ነኝ .. ባለቤቷት በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲቸኩሉ አይፈልግም ››
ነገር ግን ከወ.ሮዋ ፊት ምንም ነገር ማንበብ አልቻለችም ፡፡ሴትዬዋን ለማሳመን የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች..ግን ይሳካላት አይሳካላት መገመት ስላልቻለች በጣም ተበሳጨች ፣ መኪናውን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው…መኪናዋን አቁማ ወደአፓርታማዋ ተጠጋች… የአሳንሰሩን ቁልፍ ተጫነች እና ገባች፤ውስጥ ያልጠበቀችውን ሰው አገኘች፡፡የቆዳ ጃኬት ለብሶ ነበር። የሞተር ሳይክል ሄልሜት በእጁ ይዟል።
‹‹ሰላም. እዚህ ምን እየሰራህ ነው?››ብላ ጠየቀችው፣ እስትንፋሶ ተቆራረጠባት፡፡
‹‹በቃ ጎራ ብዬ ከፀጋ ጋር እንዴት እየተለማመድሽ እንዳለሽ ለማየት አስቤ ነበር።››
‹‹ጥሩ አደረክ››አለችው
‹‹ወደ ውጭ ወጥተሽ ነበር?››
‹‹አዎ ጠቃሚ ስብሰባ ነበረኝ›
‹‹እንደ ሁሉም ስብሰባዎችሽ››አለ
‹‹አይዞህ አታስብ ጓደኛዬ በጣም ብቃት ያለት ሞግዚት ነች።እርግጠኛ ነኝ እሷ ከእኔ በተሻለ ከፀጋ ጋር ትግባባለች።››ሊፍት ሲቆም ወደ ኋላ ዞር አለላት።ራሄል ቀድማ ወጣች..ተከተላት፡፡ ኮሪደሩን እንደረገጡ የሚያለቅስ የህፃን ድምፅ በሁለቱም ጆሮ ገባ። የመጣው ከራሷ ቤት ነው።ሁለቱም ርምጃቸውን አፈጠኑና ተከታትለው ወደቤት ገቡ ፡፡ሜሮን የምትጮኸውን ፀጋን ተሸክማ እቤት ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ትሽከረከራለች፣ የልጁቷ ክንዶች በሜሮን ጀርባ ላይ ተዝለፍልፋው ይታያሉ፡፡
ራሄል ቦርሳዋን ጥላ ወደ ጓደኛዋ ሮጣ ሄደች። ጸጋ ራሄልን እንዳየች ከሜሮን እቅፍ ውስጥ ተስፈንጥራ እጇን ዘረጋች። እንባዋ በጉንጮቾ እየተንከባለሉ በመርገፍ ላይ ናቸው፡፡

❤50👍3🥰1😢1
ራሄል ወስዳ አቀፈቻትና ጀርባዋን እየደባበሰች‹‹ምንም አይደለም የእኔ እህት..አይዞሽ መጥቻለው ››እያለች ታባብላት ጀመር ። ፀጋ ምን ያህል ሙቀቷ እንደጨመረ ሲታወቃት የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማት።
‹‹ምንድን ነው ችግሯ ?››
‹‹ከግማሽ ሰአት በፊት እያለቀሰች ከእንቅልፏ ነቃች። መድሃኒቷን ሰጥቻታለሁ፣ ግን እየሰራላት ያለ አይመስለኝም።››
ከዚያም ፀጋ በእሷ ላይ ዝልፍልፍ አለች…ራሄል ደነገጠች። ‹‹ምን እየሆነች ነው? ደህና ናት? ››
ደ/ር ዔሊያስ እጁን በትሁት ጀርባ ላይ አደረገ፣ እሷን አረጋጋት። ‹‹ስንት ኪኒን ሰጠሻት?" ብሎ ራሄልን ጠየቃት።ነገረችው ፡፡
‹‹የእሷን የሙቀት መጠን መውሰድ አለብን.››ራሄል ወደ መታጠቢያ ቤት እያመራች ነው፡፡
‹‹ ቴርሞ ሜትር አለኝ››አለች.
ኤሊ ቴርሞሜትሩን በትሁት ጆሮ ውስጥ አስገባ። ከንፈሩን ነከሰው።
‹‹መድኃኒቱ እስከአሁን መስራት ነበረበት። በፍጥነት ማቀዝቀዝ አለብን። ››
ዔሊ በመታጠቢያ ገንዳው አጠገብ ተንበረከከ። ‹‹ውሃውን ላዘጋጅ, አንቺ ልብሷን አውልቂላት."
ኮቱን አውልቆ ቧንቧዎቹን ከፍቶ እጁን ከውሃው በታች በመደቀን… የሙቀት መጠኑን ፈትሸ።ራሄል ከመታጠቢያ ገንዳው አጠገብ ያለች ትንሽ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀመጠች የፀጋን ልብስ በጥንቃቄ አወለቀችላት። ዳይፐርዋን አወለቀችላት። አሁንም ደረቅ ነበር. እሷ እየተቃጠለች ነው እና ራሄል እንደዚህ ያለ ትንሽ አካል እንዴት በዚህ መጠን የሚፋጅ ሙቀት ማመንጨት እንደቻለች አሰበችና ተገረመች፡፡
‹‹እሺ በጣም በዝግታ ወደ ውሃው ውስጥ ንከሪያት።››
ራሄል ከጎኑ ተንበርክካ እንዳላት አደረገች። የፀጋ ገላ ውሃው እንደነካት በራሄል እቅፍ ውስጥ ሆና መጮህ ጀመረች።‹‹በጣም ይቀዘቅዛል ›› አለች፡፡ ራሄል እንደገና ወደ ኋላ ጎተተቻት እና ከውሀው አወጣቻት።
ዔሊ የራሄልን ክንድ ይዞ አስቆማት። ‹‹በጣም ስለሞቀች ለእሷ ቅዝቃዜ ይሰማታል.››ራሄል አንገቷን አዙራ አይኖቹን አየች። በአንድ ጉንጭ ላይ የዲምፕል ምልክት ተመለከተች.
‹‹አይዞሽ.. ደህና ትሆናለች›› ብሎ ሊያፅናናት ሞከረ፡፡ ራሄል ፀጋን በዝግታ ከእንደገና ወደውሀው መለሰቻት። እንደገና ጮኸች፣ በዚህ ጊዜ ግን ራሄል በተሻለ ሁኔታ ዘና ብላ ተሰማት።
‹‹ግንባሯ ላይ ትንሽ ውሃ አንጠባጥቢላት" አለ ዔሊ አጠገቧ ተቀምጦ።
በዚህ ጊዜ ሜሮን ስልክ ጆሮዋ ላይ ለጥፋ የመታጠቢያ ክፍሉን በር ከፍታ ‹‹ እኔን ትፈልጊኛለሽ እንዴ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡ ‹‹አሁን ማስተላለፍ የማልችለው አስቸኳይ ጥሪ ደረሰኝ።››
ራሄል አንገቷን ነቀነቀች እና እንድትሄድ በመፍቀድ ትኩረቷን ወደ እህቷ መለሰች። ‹‹ደህና እንሆናለን ብዬ አስባለሁ.››አጠገቧ የተንበረከከውን ዔሊን ተመለከተች።
‹‹አዎ ሁሉ ነገር ሰላም ይሆናል….እናደርገዋለን›› ብሎ አረጋገጠላት።
‹‹እሺ በቃ ሄጃለው።›› በማለት በራፉን መልሳ ዘግታላቸው ሄደች፣ እና በድንገት ራሄልና ዔሊ ብቻቸውን ቀሩ።ሲጨርሱ ፀጋ እየተንቀጠቀጠች ነበር እና ከንፈሮቿ ከደማቅ ቀይ ወደ ገረጣ አመዳም ቀለም እየተቀየሩ ነበር። ራሄል የሚንጠባጠበውን የፀጋን ገላ ከመታጠቢያ ገንዳው ውስጥ በማውጣት ዔሊ በሰጣት ለስላሳ ፎጣ ጠቀለለቻት።
ራሄል ፀጋን አደራረቀቻትና ይዛት ወደመኝታ ክፍሏ ስትወስዳት እሱ ወደሳሎን ሄደ፡፡
ከዛ ልብስ ቀይራለት፣ መድሀኒት ሰጥታት አስተኛቻት፡፡ ወዲያው በተረጋጋ ሁኔታ እንቅልፍ ወሰዳት ፡፡ራሄል ከአልጋዋ አጠገብ ቆማ ለረጅም ደቂቃ በሰስት አየቻት…ሳታስበው ይህቺን ልጅ እየወደደቻት ነው…በዚህ ጮርቃ እድሜዋ ለነፍሶ ስትታገልና በዚህ መጠን ስትሰቃይ ማየት ልቧ እንዲደማ ነው ያደረጋት፡፡
ቀስ አለችና ክፍሉን ለቃ ወጣች…ዶ/ሩን ሳሎኑ ውስጥ ሲንጎራደድ አገኘችው፡፡
የኮቴ ድምፅ እንደሰማ ወደእሷ ዞር አለና ‹‹እንዴት ነች?››ብሎ ጠየቃት፡፡
‹‹ተኝታለች ብዬ አስባለሁ…ቆይ ፀጋ በህፃንነቷም እንዲህ ቶሎ ቶሎ ትታመም ነበር እንዴ?››ስትል ጠየቀችው
ዔሊያስ ፈገግ አለ‹‹እናቷ ቅዳሜና እሁድን እሷን ላለመያዝ ስትል ሁሉ ጊዜ ወደ ሆስፒታል ላለመምጣት ሰበብ ትደረድር ነበር።››
‹‹ወላጆቼ ስለ ስለፀጋ እናት ብዙ ሲናገሩ አልሰማሁም ››
‹‹እሷን በጭራሽ አላገኟትም … የሆስፒታሉ ማህበራዊ ሰራተኛ ጉዳዩን በሚያውቅበት ጊዜ, ፀጋ ለብዙ ሳምንታት ከበሽታዋ እየታገለች እናቷ ከአሁን አሁን መጥታ ትወስደኛለች በሚል ጉጉት አይኖቾ እየተንከራተቱ ስትጠብቅ ነበር….የሰው ልጅ ሆነሽ ያንን የልጅቷን የናፍቆት ስቃይ ማየት እንዴት ልብን እንደሚሸረካክት ልነግርሽ አልችልም..ይገርምሻል እናትዬው ግን ተመልሳ ልትመጣላት አልቻለችም…ስናጠያይቅ አንደኛውን ሀገር ጥላ እንደጠፋች ሰማንና ተስፋ ቆረጥን… ለሚመለከተው አካል አመለከትን…እና እንዳጋጣሚ ከወላጆችሽ ጋር የተገናኘሁት በዛ ጊዜ ነበር…በአጋጣሚ ስለልጅቷ ሁኔታ እንደሰሙ ሆስፒታል ሄደን ካላየናት አሉ..ይዣቸው ሄድኩ…ልክ እንዳዮት ሁለቱም ወደዷት…ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ ያለባትን የጤና ችግር፤ምን አይነት እንክብካቤ እደሚስፈልጋት…ለእሷ ህክምና ሊያወጡት የሚችሉትን ገንዘብ ..እንደዛም ሆኖ ለመዳን ያላት እድል አናሳ እንደሆነ ሁሉንም በግልፅ አስረድቻቸውም እነሱ እሷን እንደልጃቸው አድርገው ለመቀበልና ወደቤታቸው ለመውሰድ ቅንጣት ያህል አላቅማሙም…እኔ በህይወት ዘመኔ እንደወላጆችሽ አይነት ትክክለኛ መንፈሳዊ ሰው አላውቅም….ከአእምሮዬ በላይ ናቸው፡፡እኔም በተቻኝ መጠን ከፀጋ ጎን ላለመራቅ የወሰንኩት የእነሱን ደግነት ካየው በኋላ ነው፡፡››
‹‹አዎ..እነሱ እንደዛ ናቸው…እውነቱን ንገሪኝ ካልከኝ..መጀመሪየ ውሳኔያቸውን ስሰማና ሆስፒታል ሄጄ ፀጋን የሀገር ቱቦና ማሽኑ ሰውነቷ ላይ ተሰክቶ ሳይ ምለውና ምናገረው ጠፍቶኝ ነበር…አፍ አውጥቼ ባልቃወምም በውስጤ ግን በጣም ተበሳጭቼ ነበር….አሁን ያንን ስሜቴን ትዝ ሲለኝ በጣም አፍራለው፡፡››
‹‹አትፈሪ…በሆድሽ አስበሽ ቢሆን እንኳን..በአፍሽ ተቃውሞ አለማሰማትሽ እራሱ አንድ ጥሩ ነገር ነው….አየሽ ልጅቷ በጣም አሳዝናሽ ነበር..ግን ደግሞ እድሜያቸው ለገፋ ወላጆችሽም የበለጥ ማሰብሽ እና መጨነቅሽ የሚያስወቅስሽ አይደለም…ተመልከቺ እናትሽ አሁን የት ነው ያለችው ሆስፒታል አልጋ ላይ …ምን ሆና..?ፀጋን አቅፋ ደረጃ ስትወርድ ሚዛኗን ስታ…እና አንቺ ክፉ ሴት ብትሆኜ ‹‹እናቴን እንድትሰበር አድርጋ ለዚህ አደጋ የዳረገችብኝ ይህቺ ልጅ ነች …ገፊ ነች ምናምን ብለሽ..እሷን ከህይወትሽ ለማስወገድ ነበር የምትጥሪው..ይሄው ግን አንቺ ከእሷ ጋር እየተሰቃየሽ ነው…ልክ እንደእናቷ ሲያማት እያመመሽ….ስታለቅስ እያለቀሽ ነው፡፡››
‹‹አንተ ….እስከአሁን እናቴ በእሷ ምክንያ እንደወደቀች እራሱ አያይዤ አላሰብኩትም ነበር››
‹‹እና ክፉ ነገር አሳሰብከኝ እያልሽ ነው?››
‹‹አረ በፍፅም…ለማለት የፈለኩት..አሁን ትክክለኛ እህቴ እንደሆነች ነው የማስበው….እናቴ እኔን አቅፋ ብትወድቅ እኔ ልወቀስ እንደማልችል ሁሉ ፀጋንም አቅፋ ወድቃ በመሰበሯ ህፃኗ መወቀስ የለባትም ልልህ ፈልጌ ነው፡፡››
‹‹ገባኝ..ስቀልድ ነው..ግን ልነግርሽ የምፈልገው ትሁት ማለቴ ፀጋ ሰዎች ጥለዋት ሲሄድ በጣም ብትናደድ ምንም አያስደንቅም…ምትወዳቸው ሁሉም ሰዎች ልክ እንደእናቷ ጥሏት ሚሄድ ይመስላታል….››
ራሄል በሰማችው ነገር ደነገጠች…‹‹እንደዛ ነው እንዴ…ሚስኪን !!እናም የሙቀት መጠኗ ከፍ የሚለው በዚህ ምክንያት ነው እንዴ?››
‹‹አዎ..ችግሯ ተያያዥ ነው…››

❤51
‹‹እሷን ለማገዝ በአቅራቢያዋ ስለነበርክ ደስ ብሎኛል.››አለችው
‹‹ምንም አይደል…ሁሌ ከእሷ ጎን ለመገኘት ለራሴ ቃል ገብቻለው..እሷ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አላት››
‹‹በጣም ጥሩ ››አለች፡፡
ውይይቱ ወደ ስንብት ወይም ለቡና ግብዣ እየቀረበ ነበር። ራሄል ትንሽ እንዲቆይ ልትጠይቀው አስባ ከንፈሯን ነከሰች። የወንድ ጓደኛ ረጅም ጊዜ አልነበራትም። እጮኛዋ ኪሩቤል በአደጋ ከሞተ በኋላ የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ የተወሰነ ሙከራ ሞክራ ነበር ፣ ነገር ግን ሁሉም ወንድ ከእሷ ሚዛን ቀሊል እየሆኑ ተቸገረችና እርግፍ አድርጋ ተወችው ፡፡ አሁን ምንም እንኳን የእጮኛዋ ትውስታዎች ቢደበዝዙም ፣ እምቅ ህመሟ በህይወቷ ውስጥ የተደበቀ ቁስል ነበር ።እንደገና ልቧን ለመክፈት አልፈለገችም፡፡
ኤሊያስ ከተቀመጠበት ተነሳ ፡፡የሞተር ብስክሌቱን ሄልሜት ከአንድ እጁ ወደ ሌላው አዘዋወረ ፡፡ ራሄል ከእሱ ለመራቅ ባደረገችው ውሳኔ ፀናች።
‹‹መልካም፣ የሆነ ነገር ከተቀየረ አሳውቂኝ››በማለት ሌላ ፈገግታ ፈገግ አለላትና ሄደ።በሩ ከኋላዋ ሲዘጋ፣ ራሄል በረጅሙ ተነፈሰች። እሱን እንዲቆይ አለመጠየቋ ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ አሰበች። እንኳን ፍቅር ተጨምሮበት ህይወቷ አሁንም በጣም የተወሳሰበ ነው፡፡ ታዲያ ለምን ድንገት ብቸኝነት ተሰማት? ለምን ታዲያ በአንድ ወቅት አስደሳችና ውብ የሆነው አፓርታማዋ አሁን በቅፅበት በጣም ቀዝቃዛ እና ባዶ መሰላት?የጭንቀት ስሜት ወረራት… ከተቀመጠበት ተነሳችና ወደ ፀጋ ክፍል ተመልሳ ሄደች፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
‹‹ምንም አይደል…ሁሌ ከእሷ ጎን ለመገኘት ለራሴ ቃል ገብቻለው..እሷ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አላት››
‹‹በጣም ጥሩ ››አለች፡፡
ውይይቱ ወደ ስንብት ወይም ለቡና ግብዣ እየቀረበ ነበር። ራሄል ትንሽ እንዲቆይ ልትጠይቀው አስባ ከንፈሯን ነከሰች። የወንድ ጓደኛ ረጅም ጊዜ አልነበራትም። እጮኛዋ ኪሩቤል በአደጋ ከሞተ በኋላ የፍቅር ጓደኛ ለመያዝ የተወሰነ ሙከራ ሞክራ ነበር ፣ ነገር ግን ሁሉም ወንድ ከእሷ ሚዛን ቀሊል እየሆኑ ተቸገረችና እርግፍ አድርጋ ተወችው ፡፡ አሁን ምንም እንኳን የእጮኛዋ ትውስታዎች ቢደበዝዙም ፣ እምቅ ህመሟ በህይወቷ ውስጥ የተደበቀ ቁስል ነበር ።እንደገና ልቧን ለመክፈት አልፈለገችም፡፡
ኤሊያስ ከተቀመጠበት ተነሳ ፡፡የሞተር ብስክሌቱን ሄልሜት ከአንድ እጁ ወደ ሌላው አዘዋወረ ፡፡ ራሄል ከእሱ ለመራቅ ባደረገችው ውሳኔ ፀናች።
‹‹መልካም፣ የሆነ ነገር ከተቀየረ አሳውቂኝ››በማለት ሌላ ፈገግታ ፈገግ አለላትና ሄደ።በሩ ከኋላዋ ሲዘጋ፣ ራሄል በረጅሙ ተነፈሰች። እሱን እንዲቆይ አለመጠየቋ ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ አሰበች። እንኳን ፍቅር ተጨምሮበት ህይወቷ አሁንም በጣም የተወሳሰበ ነው፡፡ ታዲያ ለምን ድንገት ብቸኝነት ተሰማት? ለምን ታዲያ በአንድ ወቅት አስደሳችና ውብ የሆነው አፓርታማዋ አሁን በቅፅበት በጣም ቀዝቃዛ እና ባዶ መሰላት?የጭንቀት ስሜት ወረራት… ከተቀመጠበት ተነሳችና ወደ ፀጋ ክፍል ተመልሳ ሄደች፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
❤37👍8
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
ወደ ሆስፒታሉ በሚወስደው መንገድ ላይ ሞተሩን እያስጎራ በመብረር ላይ ነው፡፡ ሀሳቡ ግን አሁንም ወደኋላ እየጎተተው ነው፡፡ በዚህ የሰንበት ማለዳ ወደእነራሄል ወላጆች ቤት የሄድኩት ራሄል ፀጋን እንዴት እያስተዳደረች እንደሆነ ለማየት ብቻ ነበር። ጉብኝቱ የህፃኗ ሐኪም በመሆኔ ያደረግኩት ነው።››ሲል ለራሱ ነገረው፡
አሁን፣ ፀጉሯን በትና እና የደበዘዘ ቲሸርት የለበሰች እንዲት ቆንጆ ሴት በአእምሮው ሰሌዳ ላይ ብልጭ ድርግም እያለች እየረበሸችው ነው፡፡ በባዶ እግሯ እና በሰማያዊ ጂንስዋ ምን ያህል ውብ እንደሆነች እያሰበ ነበር፣እሷ የምትኖርበትን ቤት እንዴት ግዙፍ እንደሆነ እና ወላጆቿ ምን ያህል ገንዘብ እንዳላቸው እያሰበ ነበር። እና የተከበረ የመኳንንት ዝርያ አለን ብለው የሚያስቡ ወላጇች እንዳሏት እያሰበ ነበር… እና ደግሞ እሱ ሰለወላጇቹ ምን ይሁኑ ምን የሚያውቀው ነገር እንደሌለም እያሰበ ነበር፡፡በዚህም ሆነ በዚያ ሀሳቡ በራሄል ዙሪያ ከመሽከርከር ሊያቅበው አልተቻለውም፡፡
ኤልያስ አሳዳጊ ወላጆቹ ስለስጋ ወላጇቹ ብዙ ጊዜ አይናገሩም ወይም የበለጠ እንዲያውቅ አያበረታቱትም። ወደፊት ፀጋም ልክ እንደእሱ ስለ እናቷ እና አባቷ ማወቅ እንደምትፈልግ ገመተ።ስለ ፀጋ ማሰቡ በትክክል ወደ ራሄል መለሰው።ሸሩባ የተሰራው ጥቁር ፀጉሯ ፊቷን እንዴት እንደአሳመረው እና ሀዘን ያጠላባቸው ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿ ከብለል ሲሉ እንዴት ልብን እንደሚያርዱ አሰበ። ሆስፒታል ደርሶ ሞተሩን ሲያቆም እንኳ ሀሳብን መግታት አልቻለም ነበር፡፡
///
ራሄል ትሁት ቁርስ ስትበላ ፊቷ ላይ የተዝረከረከውን በደረቅ ጨርቅ በጥንቃቄ ጠራረገችላት። እቃዎችን እያጣጠበች ሳለ ፀጋ ወደ በረንዳ በሮች ስትሄድ አየች። ሰራተኛዋ አለም ሁል ጊዜ መስኮቶቹን በሚያብረቀርቅ ንፅህና ነው የምትይዛቸው ፣ ዛሬ ግን እሷና ፀጋ ብቻቸውን ናቸው..ሰራተኛዋ የረፍት ቀኗ ስለሆነ ዘመድ ጥየቃ ሄዳለች።እቃ ማጠቧን እንዳጠናቀቀች..ትንሿን እህቷን ለማየት ወደበረንዳ ስትወጣ የጸጋ ትንሽዬ የእጅ ህትመቶች መስታወቱን ጠቅላላ አዳርሰውት ሌላ ቅርፅ ሰጥተውት አገኘች፡፡ መጀመሪያ መልሳ ለማፅዳት ስትሞከር ፀጋ ከኋላዋ እየተከተለች መልሳ ስታቆሽሽባት…በመናደድ ፋንታ ከት ብላ ሳቀችና ማፅዳቱን እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡
‹‹ከአንድ በላይ ልጅ ያላቸው ሰዎች እንዴት በህይወት መቆየት ቻሉ?››ስትል ገረሜታዋን ገለፀች ፡፡ከፀጋ ጋር በቀጣይ ምን ማድረግ እንደምትችል አሰበች.. ።ሰዓቱን ተመለከተች, ከዚያም ወደ እሷ ተመለሰች. ወላጆቿ ዘወትር እሁድ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሄዱ ታውቃለች። ወጣት ሳለች ሁልጊዜ አብራቸው ትሄድ ነበር፣ ነገር ግን እጮኛዋ ኪሩቤል ከሞተ በኋላ ወደቤተክርስቲያን መሄዱን እርግፍ አድርጋ ተወችው፡፡ ይህ ድርጊቷ ወላጆቿን በጣም እንደሚያበሳጫቸው ታውቃለች፣ እነሱ ስለሚፈልጉ ብቻ ነገሮችን ማድረግ እንዳለባት አታምንም። እሷ የራሷን ሕይወት እየመራች ነበር፣ እና እግዚአብሔር የህይወቷ አካል አይደለም።
ፀጋን ስትመለከት ግን በድንገት ተጨማሪ ሀላፊነት እንዳለባት ተሰማት። በእርግጥ የሁለት ዓመት ልጅ ነበረች፣ … ስለግል እምነቷ ለራሷ ውሳኔ ማድረግ እንደምትችል ብታምንም ለዚህች ልጅም ተመሳሳይ ነገር ማድረጉ ትክክል ሆኖ አልተሰማትም።ወላጇቾ ቢኖሩ ይዘዋት እንደሚሄዱ እርግጠኛ ነች፡፡
‹ስለዚህ ወደ ፀጋ ጎንበስ አለችና‹‹የእኔ ቆንጅዬ እህት .. ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ትፈልጊያለሽ?›› ብላ ጠየቀቻት ፡፡
ህፃኗ በደስታ እየዘለለች‹‹ቤተክርስትያን እንሂድ፣ ቤተክርስትያን እንሂድ››አለች ፡፡ ራሄልም ልብሷን ቀያይራ ካለባበሰቻት በኋላ ወደቤተክርስቲያን ይዛት ሄደች፡፡
ራሄል የኮሌጅ ትምህርቷን እስካጠናቀቀች ድረስ ንቁ ተሳታፊ ነበረች።ሁሉ ነገር የተቀየረው እጮኛዋ ከሞት በኋላ ነው።እና አሁን የመቅደሱ ዙሪያ ስትመለከት፣ የልጅነትና የጉልምስና ትውስታዎች ሁሉ ተግተልትለው በአእምሯ ውስጥ ብልጭ ድርግም አሉባት። የዚህ ቤተክርስቲያን መዘምራን አባል ሆና ለረጅም አመት አገልግላለች ፤እዚህ መድረክ ላይ ወጥታ ስለጌታ የአዳኝነት ስራ ስትዘምር ትዝ ይላታል፡፡ ድምፆ ተስረቅራቂ የሚባል አይነት ስለነበር ብዙውን ጊዜ ድምጽ ማጉያውን ይዛ መዝምራኖችን የምትመራው እሷ ነበረች፡፡እጮኛዋ ኪሩቤልንም እዚሁ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው የተዋወቀችው፡፡እሱም ልክ እንደ እሷ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ነበር…. ከዚያ ከመቀራረብና አብሮ ከመዋል ብዛት የፍቅር ስሜት በመሀከላቸው ተፈጠረ፡፡በቤተክርስቲያኒቷ ፊት ቃልኪዳን ተግባቡ …ሀይስኩል ጨረሱ ..ኮሌጅ ገቡ….እስከዛን ድረስ ሁለቱም በእምነታቸው የፀኑ ወጣቶች ነበሩ…ሁሉን ነገር ሀይማኖቱ በሚያዘው እና ቤተሰቦቻቸው በሚደሰቱበት አግባብ ለማድረግ ነበር እቅዳቸው…ሰርጋቸውን ባደጉበትና ባገለገሉበት ቤተክርስቲያን አደባባይ ላይ ለማድረግ ነበር ውጥናቸውና ጉጉታቸውም…ግን ምን ሆነ ህልማቸውን ሊኖሩ ወራት ሲቀራቸው..፣ኪሩቤል ድንገት ከእሷ ጋር ወደተቀጣጠረበት ቦታ ሞተር ሳይክሉን እያበረረ ሲመጣ እየተክለፈለፍ በፍጥነት ከሚያበር መኪና ጋር ተላትሞ በከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል ገባ…ይድንልኛል..መልሶ በእግሮቹ ቆሞ እንጋባላን ብላ ሆስፒታል ደረቅ ወንበር ላይ እየተኛች አንድ ወር ከግማሽ አካባቢ አስታመመችው…ግን አልተሳካም….የኪሩቤል ነፍስ ወደፈጣሪዋ ተጠርታ ሄደች..ከዛ ወዲህ ራሄል ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ሆነች…ሆስፒታል አስጠላት…የመድሀኒት ሽታ ቀፈፋት…ቤተክርስቲያንና እምነት አንገሸገሻት..የታመመ ሰው ማየት አቃታት…ይሄው አሁን ለታናሽ እህቷ ስትል እዚህ ያደገችበት ቤተክርስቲያን ስትመጣ ቁስሏ ሁሉ ክፉኛ ተቀሰቀሰ፡፡ እና የሚቀስፍ አይነት ህመም ተሰማት፣ ከዚሁ ሁሉ በጣም የሚገርመው ግን ለአፍታ ያህል ኪሩቤል ምን እንደሚመስል እንኳ ማስታወስ አለመቻሏ ነው ። ከሞቱ በኋላ አብዛኛዎቹን የኪሩቤልን ምስሎች በወላጆቿ ቤት አስቀምጧቸው ነበር እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አልተመለከቷቸውም። በጣም ተጎድታ ነበር። አሁን ምን እንደሚሰማት ግራ ተገባች።በመጨረሻም ጓዳኛዋ ሌንሳ ከወላጆቿ እና ከሁለት መንታ ልጇቾ ጋር ተቀምጣ አየች። ራሄል ከጎኗ ሾልካ ገባች።
‹‹ቤተክርስትያን መሄድ እርግፍ አድርገሽ የተውሽ መስሎኝ ነበር›› ስትል ወደጀ ጆሮዋ ቀርባ አንሾካሾከችላት፡፡
ሌንሳ ወደኋላ ዞረችና እያወራቻት ያለችው ራሄል መሆኗን ስታውቅ በመገረም ‹‹ራሄል እዚህ ምን እየሰራሽ ነው?›› ስትል ወደኋላ ተስባ አቀፈቻት፡፡
‹‹ፀጋን ማምጣት እንዳለብኝ ተሰማኝ››ስትል የመጣችበትን ምክንያት ነገረቻት፡፡
‹‹እሺ በምንም ምክንያት ይሁን በምንም እዚህ በመገኘትሽ ደስ ብሎኛል.››
የሌንሳ ወላጆችም በደስታ ሰላም አሏት፡፡
ዝግጅቱ እናዳለቀ ፀጋን እንዳቀፈች እነ ለሌንሳን ተከትላ ወደአውደ ምህረቱ ሄደች…ከረጅም ጊዜ በፊት የምታውቃቸውን በጣም ብዙ የድሮ ጎደኞቾንና ወዳጆቾን አገኘች፡፡ ብዙ ሰው ለምን እንደጠፋች እየጠየቃት በመምጣቷ እንደተደሰቱ ይነግሯት ነበር፡፡

❤36👍4👎1😁1