ኢትዮጵያ በራሷ ገዳይ ነገር አላት እንዴ?
ድንቄም ትርጓሜ
ቅኔና ዝማሜ
ድንቄም ሶላት አዛን
ሁሌ መለካካት ሁል ጊዜ ሚዛን፡፡
ድንቄም ሀዘን ዕንባ
ሞትን ሰው ካረባ፡፡፡
አይ ቀስተደመና
ምደረ መና፡፡
ድንቄም ገዳም
እየተናከሰ አደምና አዳም፡፡
ድንቄም ገዳ
እንደወይን ግብዣ ደም እየተቀዳ፡፡
ድንቄም አክሱም አወይ ላሊበላ
እንደቅርጫ ስጋ ሰው እየተባላ፡፡
አይ አይ
ዋይ ዋይ፡፡
አይ እድገት
አይ ሰላም
በሰማይ አለኝ ላም፡፡
አወየው ሶፍ ዑመር
ሞት በሰው ቢከመር፡፡
አወይ አልነጃሺ
ስንቱን ተቀብሎ ዛሬ እሱ ቢሸሽ፡፡
(አናሳዝንም)
አይ ሸገር ፊነፊኔ
ለወያኔም ወይኔ
ለ..... ወይኔ፡፡
የዘሬ ያንዘርዝረኝ እንደተባባለነው
ይኸው....
ህይወት ድፍን ሲሆን በሞት ዘረዘርነው፡፡
ደሞ አለን በለኝ ተስፋና ዕድሉ
ታሪክና ባህል
ሲቆም አያምርበት ሰው እየገደሉ፡፡
አናሳዝንም???
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ድንቄም ትርጓሜ
ቅኔና ዝማሜ
ድንቄም ሶላት አዛን
ሁሌ መለካካት ሁል ጊዜ ሚዛን፡፡
ድንቄም ሀዘን ዕንባ
ሞትን ሰው ካረባ፡፡፡
አይ ቀስተደመና
ምደረ መና፡፡
ድንቄም ገዳም
እየተናከሰ አደምና አዳም፡፡
ድንቄም ገዳ
እንደወይን ግብዣ ደም እየተቀዳ፡፡
ድንቄም አክሱም አወይ ላሊበላ
እንደቅርጫ ስጋ ሰው እየተባላ፡፡
አይ አይ
ዋይ ዋይ፡፡
አይ እድገት
አይ ሰላም
በሰማይ አለኝ ላም፡፡
አወየው ሶፍ ዑመር
ሞት በሰው ቢከመር፡፡
አወይ አልነጃሺ
ስንቱን ተቀብሎ ዛሬ እሱ ቢሸሽ፡፡
(አናሳዝንም)
አይ ሸገር ፊነፊኔ
ለወያኔም ወይኔ
ለ..... ወይኔ፡፡
የዘሬ ያንዘርዝረኝ እንደተባባለነው
ይኸው....
ህይወት ድፍን ሲሆን በሞት ዘረዘርነው፡፡
ደሞ አለን በለኝ ተስፋና ዕድሉ
ታሪክና ባህል
ሲቆም አያምርበት ሰው እየገደሉ፡፡
አናሳዝንም???
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍23🔥9❤8😢2
አንቺን እንዲሰጠኝ ሆንኩኝ አምላክ ለማኝ
ጧፍ መባ ገዛሁ ልሰጠው ከሰማኝ፡፡
አንቺዬ
ፀሎቴን ሳልጨርስ ብትይ እመጣለሁ
እኔ እኮ ሞኝ ነኝ
ፈጣሪዬን ትቼ እጠብቅሻለሁ፡፡
እጠብቅሻለሁ
በተገተርኩበት
እጠብቅሻለሁ
በተፈጠረኩበት፡፡
ጊዜ አይፈራረቅ አይጮኹም አእዋፍ
አንቺን ስጠብቅሽ
ለኮስኩት ጨክኜ ለስለት እንዲሆን የገዛሁት ጧፍ፡፡
ትመጫለሽ አይደል?
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
ጧፍ መባ ገዛሁ ልሰጠው ከሰማኝ፡፡
አንቺዬ
ፀሎቴን ሳልጨርስ ብትይ እመጣለሁ
እኔ እኮ ሞኝ ነኝ
ፈጣሪዬን ትቼ እጠብቅሻለሁ፡፡
እጠብቅሻለሁ
በተገተርኩበት
እጠብቅሻለሁ
በተፈጠረኩበት፡፡
ጊዜ አይፈራረቅ አይጮኹም አእዋፍ
አንቺን ስጠብቅሽ
ለኮስኩት ጨክኜ ለስለት እንዲሆን የገዛሁት ጧፍ፡፡
ትመጫለሽ አይደል?
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍20❤9🔥2
የጨነቀው ሁሉ
"ማርያም ማርያም" ይላል ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀናና ኢያቄም?
~ ~ ~ ~ ~ ~
፩
ቤት የለውምና
አዳም ወጥቶ ቀርቶ ከፈጣሪ ደጁ
ምንድነው ሚስጥሩ?
ቤት አትልተወለዱም እናትና ልጁ።
፪
መስዋዕቱ ቀረ ርግብና ዋኖስ
ልጇን ልትሰጥ ነው እናት ከሊባኖስ።
የሊባኖስ ዝግባ ንፋስ የማይገፋው
ማርያም ስትወለድ እግዜር ዙፋን ሰፋው።
፫
እመብዙሃኗ
የሄኖክ የራስ ወርቅ ኢሳይያስ ትንቢቱ
የዳዊት የልጅ ልጅ የኖኅ መርከቢቱ።
፬
ምስጢሩ ነችና ሰምና ወርቅ ቃል
ቀራንዮን ያየ ሊባኖስን ያውቃል።
፭
የጨነቀው ሁሉ
"ማርያም ማርያም" ይላል ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀናና ኢያቄም?
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
"ማርያም ማርያም" ይላል ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀናና ኢያቄም?
~ ~ ~ ~ ~ ~
፩
ቤት የለውምና
አዳም ወጥቶ ቀርቶ ከፈጣሪ ደጁ
ምንድነው ሚስጥሩ?
ቤት አትልተወለዱም እናትና ልጁ።
፪
መስዋዕቱ ቀረ ርግብና ዋኖስ
ልጇን ልትሰጥ ነው እናት ከሊባኖስ።
የሊባኖስ ዝግባ ንፋስ የማይገፋው
ማርያም ስትወለድ እግዜር ዙፋን ሰፋው።
፫
እመብዙሃኗ
የሄኖክ የራስ ወርቅ ኢሳይያስ ትንቢቱ
የዳዊት የልጅ ልጅ የኖኅ መርከቢቱ።
፬
ምስጢሩ ነችና ሰምና ወርቅ ቃል
ቀራንዮን ያየ ሊባኖስን ያውቃል።
፭
የጨነቀው ሁሉ
"ማርያም ማርያም" ይላል ምጥም እንዳያቄም
በማን ስም ወለዱሽ ሀናና ኢያቄም?
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
❤56👍11🥰3🔥1
#ፀሎተ_ግንቦት
ለተቀረው አመት...ደግሞም እስካመቱ
አንድ ሲል ልደታ...ዘጠኝ ሲል ወራቱ
ቅዬው ሲሰበሰብ ...
ላድባር የሚጀ'በት ፥ ሸክፎ ከቤቱ
ዛሬ ያልጠገብ ፥ አይኑና ፣ አንጀቱ
በማጣት ይታሻል...ጓዳና ፣ ማጀቱ
እንዲለን ልማዱ...
ጋን..እጋን ሲጋባ...መብሉ ሲመሰኳ
ማቲ ሲተራመስ ...ጨዋታው ሲውኳኳ
ቡኑ ሲከታትም ...ጢሱ ሲትጎለጎል
አጥንት ፣ ጉልጥምቱ ...ከሳቱ ሲታጎል
እንኳንስ ያዳም ከርስ...ያሞራው ሲረካ
ይህን የለመደ ...
ለላመት ድረሱ ፥ ብሎ ይመርቃል ፥ ሆድና መለይካ።
ልማድ መጥፎ ህመም ...
ሲነጠሉ ግዜ .. ትዝታው በሽታ
የቀረ ለት ያማል...
ቀን በቀኑ ሲደርስ ...ክርሚያው በሽውታ
የሰው ልደት እንኳ ፥ ሲኮስስ ይከፋል ፥ እንኳን #ያዛኝቷ
እናም .... #እመቤቴ
ልማድሽ እንዳይቀር... #እመብርሀኒቱ
በለትሽ ምህላ ፥ እንዲሽር ፍጥረቱ
እንዳምና እንድንውል ፥ ለቀጣይ ለፊቱ
ጠርገሽ ወድያ ይጣል ...ነቀርሳ ልክፍቱ ።
🔘አብርሀም_ተክሉ🔘
ለተቀረው አመት...ደግሞም እስካመቱ
አንድ ሲል ልደታ...ዘጠኝ ሲል ወራቱ
ቅዬው ሲሰበሰብ ...
ላድባር የሚጀ'በት ፥ ሸክፎ ከቤቱ
ዛሬ ያልጠገብ ፥ አይኑና ፣ አንጀቱ
በማጣት ይታሻል...ጓዳና ፣ ማጀቱ
እንዲለን ልማዱ...
ጋን..እጋን ሲጋባ...መብሉ ሲመሰኳ
ማቲ ሲተራመስ ...ጨዋታው ሲውኳኳ
ቡኑ ሲከታትም ...ጢሱ ሲትጎለጎል
አጥንት ፣ ጉልጥምቱ ...ከሳቱ ሲታጎል
እንኳንስ ያዳም ከርስ...ያሞራው ሲረካ
ይህን የለመደ ...
ለላመት ድረሱ ፥ ብሎ ይመርቃል ፥ ሆድና መለይካ።
ልማድ መጥፎ ህመም ...
ሲነጠሉ ግዜ .. ትዝታው በሽታ
የቀረ ለት ያማል...
ቀን በቀኑ ሲደርስ ...ክርሚያው በሽውታ
የሰው ልደት እንኳ ፥ ሲኮስስ ይከፋል ፥ እንኳን #ያዛኝቷ
እናም .... #እመቤቴ
ልማድሽ እንዳይቀር... #እመብርሀኒቱ
በለትሽ ምህላ ፥ እንዲሽር ፍጥረቱ
እንዳምና እንድንውል ፥ ለቀጣይ ለፊቱ
ጠርገሽ ወድያ ይጣል ...ነቀርሳ ልክፍቱ ።
🔘አብርሀም_ተክሉ🔘
🥰24👍11❤3👏3
#ሀና_እና_እያቄም
ልጅ ቢሰጠን ብለው ቢያስገቡ ስለትን፣ እግዚአብሔር ሰጣቸው የእግዚአብሔር እናትን።
ሚካኤል ፣ ገብርኤል ፣ ዑራኤል …)
ስላሴ መንበር ፊት
ሰርክ የሚላላኩት፣
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው የሚያመልኩት።
(አምላክ ሰው)
እንደሚሆን ያኔ ትንቢቱን የሚያምኑ፣ ማርያም ስትወለድ እርግጠኛ ሆኑ።
ከአምላክ የራቁት፣
መዳን የናፈቁት፣
ከገነት ቤታቸው የወጡት በራቁት።
( አዳም እና ሄዋን )
ስትወለድ ቢያዩ ድንግል ከሊባኖስ፣
ከሲኦል ታያቸው የድህነት ፋኖስ።

👍41❤30
#የባርነት_አዚም
ኑ ባንዲራ እንሰቀል አንድ ላይ እናዚም፡፡
ኑ ሰነደቅ እንስቀል
በሰው ስም ይነገድ በሰው ስም ይሸቀል፡፡
ኑ
ቁስልን በማከክ ባይሽርም ህመሙ
ሀበሻን ግን ስሚው
ጥፍርን ሲለምን ለቁስል ለደሙ፡፡
"እከክ የሰጠ አምላክ
ጥፍርን ደግሞ ይላክ::"
እያለ የሚኖር
ብሂል ነው ሀበሻ ያውም ቃል አጋኖ
ሞኝ ሆኖ አየደለም
ኑሮ ሆነበት ነው መቁሰል ደምቡ ሆኖ፡፡
መቁሰል የለመደ የሀበሻ ገላ
ጥፍር ይለምናል ማከክ ላይሆን መላ::
ግን ምን ታደርጊዋለሽ?
ደዌ ነፍስ
ደዌ ስጋ
ደዌ መንፈስ
ተጣብቆት ሰንብቶ
ባይሽርም በኮሶ ባይሽርም ባረቄው
መቁስል ስለማይቆሞ ጥፍር ነው ጥያቄው፡፡
ጥፍር
ጥፍር
(ጠብቆም ይነበብልኝ)
ጥፍር
እስር
እስርስር
ጥፍርፍር::
ጥፍር
ለእከክ የጠየቅነው ደግሞ ሲወጣልን
የፀብ አምሮታችን ይኸው ተነሳልን
ጥፍር
ጥፍር
ጥፍር
አንድም ለቁስላችን
አንድም ለፀባችን፡፡
ሀበሻ ብልጥ ነው የመቁሰል ዘመኑ ስለማያበቃ
የሰርክ ልመናው ጥፍር ሆነ በቃ፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
ኑ ባንዲራ እንሰቀል አንድ ላይ እናዚም፡፡
ኑ ሰነደቅ እንስቀል
በሰው ስም ይነገድ በሰው ስም ይሸቀል፡፡
ኑ
ቁስልን በማከክ ባይሽርም ህመሙ
ሀበሻን ግን ስሚው
ጥፍርን ሲለምን ለቁስል ለደሙ፡፡
"እከክ የሰጠ አምላክ
ጥፍርን ደግሞ ይላክ::"
እያለ የሚኖር
ብሂል ነው ሀበሻ ያውም ቃል አጋኖ
ሞኝ ሆኖ አየደለም
ኑሮ ሆነበት ነው መቁሰል ደምቡ ሆኖ፡፡
መቁሰል የለመደ የሀበሻ ገላ
ጥፍር ይለምናል ማከክ ላይሆን መላ::
ግን ምን ታደርጊዋለሽ?
ደዌ ነፍስ
ደዌ ስጋ
ደዌ መንፈስ
ተጣብቆት ሰንብቶ
ባይሽርም በኮሶ ባይሽርም ባረቄው
መቁስል ስለማይቆሞ ጥፍር ነው ጥያቄው፡፡
ጥፍር
ጥፍር
(ጠብቆም ይነበብልኝ)
ጥፍር
እስር
እስርስር
ጥፍርፍር::
ጥፍር
ለእከክ የጠየቅነው ደግሞ ሲወጣልን
የፀብ አምሮታችን ይኸው ተነሳልን
ጥፍር
ጥፍር
ጥፍር
አንድም ለቁስላችን
አንድም ለፀባችን፡፡
ሀበሻ ብልጥ ነው የመቁሰል ዘመኑ ስለማያበቃ
የሰርክ ልመናው ጥፍር ሆነ በቃ፡፡
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
👍20❤7👎1
#እኔ
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም
#እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ
#እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)
#እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
በፀጉሮችሽ መሐል እልፍ ፂም ባገኝም
የት ነበረች ብዬ ሳስብ አልገኝም
#እኔ
የሺ ወንድ ጠረን ብስብም ከአንገትሽ
እከራከራለሁ አይደለም ካንጀትሽ
#እኔ
በጡቶችሽ ጫፎች እያየሁ አሻራ
እጠርግልሻለሁ ቆጥሬ እንዳቧራ
ይልቅስ የእኔ
ስጋቴ
ፍርሃቴ
ያ ሁሉ ተባዕት እንዳያስጨንቁሽ
ያ ሁሉ ተባዕት ቀምሰው እንዳይርቁሽ
የሚያብሰከሰከኝ ሲስሙ እንዳያንቁሽ
(ነበር)
#እኔ
ሁሉን ደስታ አይተሽ
እንደፀሀይ ገላ ሙቀሽ
ስትጨርሺ
እንዳላይሽ አዝነሽ
እንዳንላይሽ ደርቀሽ
(ነበር)
እንጂ
ያዘንሽ ቀንም ከአጠገብሽ አለሁ
የደስታሽን ቀብር አብሬ እውላለሁ
ያንቺን የሀዘን ቀን እንደኔ ቆጥሬ
እንጀመር እላለሁ መውደድን ከዛሬ
ከዛሬ
ከአሁን
ከቅፅበት
ህይወት ስታበቃ እኛ እንጀምረበት
እላለሁ፡፡
እላለሁ
እንዳዲስ እንጀምር እንዳልተለመደው
ይሰፋል እላለሁ የተቀዳደደው
ይፀናል እላለሁ የተንገዳገደው
እላለሁ፡፡
እንደማቱሳላ
አኑረኝ
ቀኔን ሳላሰላ
አክርመኝ፡፡
ላቧን እስክትጨርስ
በወንድ እንክትርስ
ዓይኗ እስከሚሟሟ
እስከሚደባለቅ እውንና ህልሟ
አኑረኝ እላለሁ
አክረመኝ እላለሁ
እድሜ ስጠኝ ብዬ እለማመናለሁ
ለምን
ሁሉም የጣለሽ ቀን እኔ አነሳሻለሁ፡፡
(እስከዛ ግን አለሁ)
🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍32❤15🔥3
እግዜሄር የጨበጣቸው ''ሳያቅፈን'' ብለው ሲቆጡ
እግዚሄር ያቀፋቸው
እልፍኙ ገብተን ካልበላን- ብለው በኩርፊያ ሲመጡ
የግዚያብሄር እልፍኝ የገቡት
እንጀራ ሳይሰጠን ብለው-ቂም ዘግነው ይዘው ሲወጡ
ባይ ..ደነቀኝ....ባይ ገረመኝ..
ምናለ እኔን ላ'ንድዜ
ገላምጦኝ ደስታ ቢገድለኝ።
🔘red-8🔘
እግዚሄር ያቀፋቸው
እልፍኙ ገብተን ካልበላን- ብለው በኩርፊያ ሲመጡ
የግዚያብሄር እልፍኝ የገቡት
እንጀራ ሳይሰጠን ብለው-ቂም ዘግነው ይዘው ሲወጡ
ባይ ..ደነቀኝ....ባይ ገረመኝ..
ምናለ እኔን ላ'ንድዜ
ገላምጦኝ ደስታ ቢገድለኝ።
🔘red-8🔘
🥰41👍17❤13
#አምስቱ_የስሜት_ህዋሳት_ስንት_ናቸው?
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
👍38❤9👏2
በደለችኝ ብዬ ሲነደኝ ሲቆጨኝ
ልወግራት ፈልጌ
ጠጠር ብወረውር አለት ኾኖ ፈጨኝ
በቃጣሁት ልምጭ ጀርባዬ ታረሰ
ቱፍ ባልኩት ምራቅ ጎጆዬ ፈረሰ
አልገባኝም እንጂ ልክ ነው ነገሩስ....
ንጹህ ነኝ ለማለት የወረወሩት ክስ
ዞሮ የመጣ እለት
አያድርስ....አያድርስ....
🔘red 8🔘
ልወግራት ፈልጌ
ጠጠር ብወረውር አለት ኾኖ ፈጨኝ
በቃጣሁት ልምጭ ጀርባዬ ታረሰ
ቱፍ ባልኩት ምራቅ ጎጆዬ ፈረሰ
አልገባኝም እንጂ ልክ ነው ነገሩስ....
ንጹህ ነኝ ለማለት የወረወሩት ክስ
ዞሮ የመጣ እለት
አያድርስ....አያድርስ....
🔘red 8🔘
👍47❤11
ከሆነ ጊዜ በኋላ እኮ ምንም ነን ፥
ምድር አታስታውሰንም ፤
ከብታቿ ቀብራ በተረኛ ታስረግጠናለች ። 😔
ምድር አታስታውሰንም ፤
ከብታቿ ቀብራ በተረኛ ታስረግጠናለች ። 😔
👍49😢15❤6🔥4😁4🥰2
የግርማዊ ጃንሆይ ቤተሰቦች በዓለም በቃኝ ወሕኒ ቤት ፤አሳዛኝ ቆይታ😔
ዘውዳዊ ሥርዓትን አስወግዶ ስልጣን መያዙን መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም በይፋ ያወጀው የደርግ ወታደራዊ መንግስት ፣ በዚሁ እለት ንጉሠ ነገሥቱን ከቤተመንግሥታቸው ይዞ 4ተኛ ክፍለ ጦር በተባለው የወታደር ሰፈር እንዲታሰሩ በማድረግ ፣ እስከ ጊዜ ሞታቸው ድረስ ለአንድ አመት ያህል አቆይቷቸዋል፡፡
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ንጉሳዊ ቤተሰቡ በጃንሆይ ልጅ በልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ መኖሪያ ቤት ውስጥ በቁም እስር እንዲጠበቁ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አረጋውያን ፣ ሴቶች እና ሕፃናት ይገኙበት ነበር፡፡ ደርጉ የጃንሆይ ቤተሰቦች በቁም እስር የሚጠበቁት ምክንያት “ሰፊው ሕዝብ በግብታዊነት ተነሳስቶ የበቀል እርምጃ እንዳይወስድባቸው ነው” በማለት ለውጪ ተመልካቾች ገልፆ ነበር፡፡
ሕዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም “ስልሳዎቹ” ተብለው ከሚታወቁት ከዘውድ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር የተሰውት፣ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል ጠቅላይ አዛዥና የጃንሆይ የልጅ ልጅ፣ ሪል አድሚራል እስክንድር ደስታ በደርግ የተገደሉ የመጀመሪያው የጃንሆይ ቤተሰብ አባል ናቸው፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ በነሐሴ 1967 ዓ.ም ያረፉት ግድያ ተፈፅሞባቸው ከሆነ ደግሞ ጃንሆይ በደርግ የተገደሉ ሁለተኛው የንጉሳዊ ቤተሰብ አባል ናቸው ማለት ነው፡፡
ደርግ በመስከረም ወር 1968 ዓ.ም በቁም እሥር የሚገኙትን ንጉሳዊ ቤተሰቦች በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት ውስጥ የእድሜ ልክ ፍርደኞች ከሚታሰሩበትና ዓለም በቃኝ ከተባለው ክልል ውስጥ በማዘዋወር አያያዛቸውም በእሥረኛ ደንብ እንዲሆን መወሰኑ ታወቀ፡፡ ከእነዚህ የንጉሳዊ ቤተሰብ እሥረኞች ውስጥ የሚበዙት ሴቶች የነበሩ ሲሆን ወጣት ወንዶችም ይገኙበት ነበር፡፡
እሥረኞቹ ልዑላን የአፄ ኃይለሥላሴ የቅርብ ዘመዶች ከመሆናቸው በስተቀር በዘውድ መንግሥት ውስጥ የያዙት ሥልጣን ወይም ሹመት አልነበረም። ለአንድ ዓመት በቁም እስር ሲቆዩም በወንጀል አልተከሰሱም ወይም ፍርድ አልተፈረደባቸውም፡፡ ከአንድ አመት የቁም እስር በኋላ ደግሞ ይባስ ብሎ ለረጅም ጊዜ ወደሚቆዩበትና የእድሜ ልክ ፍርደኞች ወደሚታሰሩበት የአለም በቃኝ የወህኒ ክልል ውስጥ እንዲዘዋወሩ ተደረገ፡፡
በዓለም በቃኝ ከታሰሩት ንጉሳዊ ቤተሰቦች ውስጥ ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ እና ልጆቻቸው ልዕልት ሰብለ ደስታ ፣ ልዕልት አይዳ ደስታ ፣ ልዕልት ሒሩት ደስታ ፣ ልዕልት ሶፍያ ደስታ እንዲሁም ልዕልት ሳራ ግዛውና ልጆቻቸው ልዑል ወሰንሰገድ መኮንን ፣ ልዑል ሚካኤል መኮንን ፣ ልዑል በዕደማርያም መኮንንና ልዕልት ምሕረት መኮንን በተጨማሪም የልዑል አልጋ ወራሽ አስፋ ወሰን የመጀመሪያ ልጅ ልዕልት እጅጋየሁ ይገኙበት ነበር፡፡
ከእስረኞቹ በእድሜ ዝቅተኛው የ 17 አመቱ ወጣት ልዑል በዕደማርያም መኮንን ሲሆን ከፍተኛ እድሜ የነበራቸው ደግሞ የ63 አመቷ ልዕልት ተናኘወርቅ ኃይለሥላሴ ነበሩ፡፡ በወህኒ ቤት ደንብ መሰረት ልዑላኑ ወንዶችና ሴቶች በዓለም በቃኝ የታሰሩት ተለያይተው በልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ ነበር፡፡
የወህኒ ቤቱ ክፍሎች ከድንጋይ የተሰሩ እና የሚያዡ በመሆናቸው ዘወትር ቅዝቃዜ አይለያቸውም፡፡ ከጥቂት የመመገቢያ ቁሳቁሶች በስተቀር ሌላ መገልገያ እንዳያስገቡ የተከለከሉት እሥረኞች የሚተኙትም በወለሉ ላይ ፍራሽ ብቻ በማንጠፍ ነበር፡፡
የደርግ መንግስት የልዑላኑን ቤትና ንብረት የወረሰ በመሆኑ፣ በምትኩ በየወሩ ብር 120 እየቆረጠላቸው ለጥቂት ጊዜ ሲቀበሉ የቆዩ ሲሆን በኋላ ላይ “ይበዛል” ተብሎ ወደ 50 ብር ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡ እሥረኞቹ ከዘመዶቻቸው በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ለመቀበል፣ በሳምንት አንድ ጊዜ አጭር ደብዳቤ ለመፃፍ እንዲሁም ለጥልፍ የሚያገለግሉ ቁሳቁስ ለማስገባት የሚችሉ ቢሆንም ጠያቂ ለማነጋገር የሚፈቀድላቸው ግን በአመት ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ብቻ ነበር፡፡
እሥረኞቹ ንጉሳዊ ቤተሰቦች በጣም በሚያስጨንቅ አካላዊና ሥነ ልቡናዊ ሁኔታ ላይ እንደነበሩ በጊዜው የፖለቲካ እሥረኞችን ሁናቴ እየተከታተለ መንግሥትን ይማፀን የነበረው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጊዜው ያወጣቸው ተከታታይ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡
የንጉሳዊ ቤተሰቡ ከነበሩባቸው በርካታ ችግሮች አንዱ የመሰረታዊ ሕክምና እጦት ነበር፡፡ ምንም እንኳን በወህኒ ቤቱ ውስጥ የጤና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒክ የነበረ ቢሆንም ፣ የንጉሳዊ ቤተሰቡ ሕክምና ሆነ ተብሎ እንዲዘገይ ይደረግ ነበር፡፡ ስለዚህም በጊዜ ቢደረስበት መፍትሄ ያገኝ የነበረ ቀላል ሕመም እየተባባሰ እሥረኞቹን ለከፋ አደጋ ሲያጋልጣቸው ተስተውሏል፡፡
ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት ልዕልት እጅጋየሁ አስፋ ወሰን ናቸው፡፡ እኒህ ሴት በወህኒ ቤት በተቆራኛቸው ደዌ ለረጅም ጊዜ ሲሰቃዩ አሳሪዎቻቸው ሕክምና እንዲያገኙ አልፈቀዱላቸውም ነበር፡፡ ህመማቸው ተባብሶ ከፍተኛ ደረጃ ከደረሰ በኋላ ግን በፖሊስ ሆስፒታል ተኝተው እንዲታከሙ ተወሰነ። ሐኪሞች ልዕልቷን ኦፕራሲዮን ቢያደርጉዋቸውም ያደረባቸው ደዌ ለረጅም ጊዜ መፍትሄ ሳያገኝ የቆየ በመሆኑ፣ ጥር 23 ቀን 1970 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
እሥረኞቹን ያሰቃዩዋቸው የነበሩት ሕመሞች የመነጩት ወይም ሥር ሰደው የተባባሱት ለረጅም ጊዜ ያለ ሕክምና በቆዩበት በዚህ ወህኒ ቤት ውስጥ ነበር። በከባድ ህመም ይሰቃዩ ከነበሩት መካከል ልዕልት ሒሩት ደስታ አንዷ ናቸው፡፡ እኒህ ልዕልት በእሥር ላይ እያሉ ከተከሰተባቸውና ከባድ ደረጃ የደረሰ የቆዳ ካንሰር የተነሳ ኦፕራሲዮን የተደረገላቸው ሲሆን በሕመሙ ሳቢያ የሰውነት ክብደታቸው በአደገኛ ሁኔታ አሽቆልቁሎ ነበር፡፡
ሌላዋ የእሥር ቤት ሕመም ሰለባ ደግሞ ልዕልት አይዳ ደስታ የነበሩ ሲሆን ሕመማቸው ደግሞ የማያቋርጥና ብርቱ ራስ ምታት ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሰውነታቸው አንዱ ክፍል እዚያው ወሕኒ ቤት ውስጥ ፓራላይዝድ በመሆኑ ከቦታ ወደ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚችሉት በከፍተኛ ችግር ነበር፡፡ የልዑል መኮንን ባለቤት የነበሩት ልዕልት ሣራ ግዛው በበኩላቸው፤ በወሕኒ ቤት በለከፋቸው የሄፒታይተስ በሽታ ክፉኛ ታመው ለረጅም ጊዜ ተሰቃይተዋል፡፡
መሰረታዊ የሕክምና እጦት፣ ከዛሬ ነገ ልንገደል እንችላለን የሚል ብርቱ ስጋት እንዲሁም በውጪ እና እዚያው እሥር ቤት ካሉ ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ጋር ለመገናኘት አለመቻል፣ ተደራርቦ እሥረኞቹን ለአስከፊ ስነልቡናዊ ስቃይ ዳርጓቸዋል። የደረሰባቸውን የመንፈስ ጭንቀት ለማስታገስም ቤተሰቦቻቸው እንቅልፍ እንዲያስወስድ የሚያደርጉ እና አእምሮን የሚያረጋጉ እንክብሎች እንዲያመጡላቸው በመጠየቅ፣ ያለ ሐኪም ፈቃድ ይወስዱ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
እነዚህ እሥረኞች ያለ ፍርድ ወደ ወህኒ የተወረወሩ በመሆኑ ለፍርድ እንዲቀርቡ ወይም እንዲለቀቁ፤ እንዲሁም አያያዛቸውም የሕግ እሥረኞች በሚጠበቁበት አግባብ ሆኖ መሰረታዊ ሕክምና ሳይዘገይ እንዲሰጣቸው፤ በማለት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ባለማቋረጥ የደርጉን መንግሥት ሲማፀን ቆይቷል፡፡
ይሁን እንጂ ሕክምናን ማዘግየት ወይም መከልከል እንደ መደበኛ ቅጣት ተቆጥሮ፣ እሥረኞቹ እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ መሰረታዊ ሕክምናን ተነፍገው ቆይተዋል። ንጉሳዊ ቤተሰቡ ከእሥር እንዲለቀቅ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ሳያቋርጥ ለደርጉ ይቀርብ የነበረው ተማፅኖ ፍሬ ማሳየት የጀመረው እሥረኞቹ ወደ ወህኒ ከተወረወሩ ከስምንት አመታት በኋላ ነበር፡፡

❤64👏3😢3👍1🤩1
ደርግ ዘጠነኛውን የአብዮት በዓል አስመልክቶ በጳጉሜ ወር 1975 ዓ.ም ለፖለቲካ እሥረኞች ይቅርታ ሲያደርግ ወጣቷ ልዕልት ምሕረት መኮንን ከንጉሳዊ ቤተሰብ እሥረኞች መካከል ለመለቀቅ የመጀመሪያዋ ሆነች፡፡ የደርግ “አብዮታዊ ምህረት” ሁሉንም እሥረኛ ንጉሳዊ ቤተሰብ ያካተተ ባይሆንም እሥረኞቹ እንዲፈቱ ለሚማፀኑት ዓለም አቀፍ ተቋማት ግን እንደ በጐ እርምጃ ተደርጐ ተወስዷል፡፡ ተቋማቱ ምህረቱን አስመልክተው ለኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋናቸውን በማቅረብ ቀሪዎቹ እሥረኛ ንጉሳዊ ቤተሰቦች እንዲለቀቁ የተለመደውን ልመና አቅርበዋል፡፡
ደርግ ለንጉሳዊ እሥረኞቹ ያደረገው 2ኛ ምህረት የተከናወነው ከመጀመሪያው ምህረት አምስት አመት ያህል ቆይቶ ሚያዝያ 13 ቀን 1980 ዓ.ም ነበር፡፡ ከአሥራ ሁለት አመት በኋላ ከእሥር የተለቀቁት የ75 አመቷ አዛውንት ልዕልት ተናኘ ወርቅ ኃይለሥላሴ፣ ልዕልት ሰብለ ደስታ፣ ልዕልት ሒሩት ደስታ፣ ልዕልት አይዳ ደስታ፣ ልዕልት ሶፍያ ደስታ እና ልዕልት ሳራ ግዛው ነበሩ፡፡
ደርጉ ለንጉሳዊ ቤተሰብ 2ኛውን ምህረት ከሰጠ ከአንድ አመት ከአራት ወራት በኋላ ደግሞ ሦስተኛውንና የመጨረሻውን ምህረት ጳጉሜ 2 ቀን 1981 ዓ.ም አደረገ፡፡ ከ13 አመታት በኋላ የተለቀቁት የንጉሳዊ ቤተሰብ እሥረኞች፣ ወርቃማውን የወጣትነት ጊዜያቸውን በወህኒ ቤት ያሳለፉት፡- ልዑል በዕደማርያም መኮንን ፣ ልዑል ሚካኤል መኮንን እና ልዑል ወሰንሰገድ መኮንን ነበሩ።

😢24❤16👍5
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ…
፡
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ
ራሄል ከሁለት ረዳቷቾ ከሮቤልና ሎዛ ጋር ስብሰባ ላይ እያለች ነበር ስልኳ የጠራው…ንግግሯን ሳታቋርጥ ስልኩን አነሳችና አየችው፤ አባቷ አቶ ቸርነት ናቸው የደወሉላት ፡፡ስብሰባ ላይ ነኝ ብላ ልትዘጋባቸው አልፈለገችም…አባቷ በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ባይሆን ኖሮ በዚህ ሰዓት አይደውሉላትም ነበር፡፡
‹‹አንዴ ይቅርታ… ይሄንን ስልክ ማንሳት አለብኝ››ብላ ከተቀመጠችበት ግዙፍ ተሸከርካሪ ወንበር ተነሳችና ቢሮውን ለቃ ወጣችና….ከዛ ስልኩን አነሳችው፡፡
‹‹ሄሎ አባዬ ..እንዴት ነህ?››
‹‹ሰላም ነኝ ልጄ››
ድምፃቸው ተጎተተባት‹‹ምነው አባዬ? ችግር አለ እንዴ?››
‹‹አይ ልጄ ሁሉ ነገር ሰላም ነው…እኔ እና እናትሽ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነበር››
‹‹ምንድነው?››
‹‹ይሄውልሽ ልጄ ምን መሰለሽ..እኔና እናትሽ ጡረታ ወጥተን ቤት መዋል ከጀመርን በኃላ ህይወታችንን ታውቂያለሽ…ብቸኞች ነን..አንቺም አሻፈረኝ ብለሽ በራስሽ ቤት ነው የምትኖሪው…፡፡››
ራሄል በምትሰማው ነገር ፊቷን አጨማደደች….የገመተችው አብረሽን ኑሪ የሚለውን የዘወትር ጥያቄያቸውን ደግመው ሊያነሱባት ነበር የመሰላት፡፡
አባቷ ትንፋሽ ወሰዱና ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹እህት እንዲኖርሽ ፈልገን ነበር››
ደነገጠች‹‹እህት!!››
‹‹አዎ ቅር ማይልሽ ከሆነ እኔ እና እናትሽ እህት እንዲኖርሽ ፈልገናል…የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት ያንቺን አስተያየት ማወቅ ስለፈለግን ነው የደወልንልሽ፡፡››
‹‹ብዥ አለባት…እናቴ በሰባ አመቷ አረገዘች እንዴ?››ስትል በውስጧ እራሷ ጠየቀች፡፡‹‹አባቴ የአብረሀምን አይነት የዋህነት ስላለው እግዜር በዚህ አድሜዋ የማዬን ማህፀን ቢከፍት አይገርመኝም››ስትል በራሷ ሀሳብ ሳቀችና ትኩረቷን ወደስልኩ መለሰች፡፡
‹‹አባዬ አልገባኝም..እንዴት ነው እህት ሊኖረኝ የሚችለው?››
አንድ የሁለት አመት ቆንጅዬ ሴት ልጅ በጉዲፈቻ ልንወስድ ነው….››
‹‹በጉዲፈቻ…በጣም ደስ ይላል….ጥሩ ውሳኔ ነው የወሰናችሁት..››
ሀሳባቸውን ለመደገፍ ጥቂት ማሰብ እንኳን አላስፈለጋትም…የሁለት አመት ጣፋጭ ልጅ እዛ ግዙፍ ቪላ ቤት ውስጥ ስትሯሯጥ…አንዴ አባቷ ላይ አንዴ ደግሞ እናቷ ላይ እየተንጠለጠች ስታስቃቸውና ሰታዝናናቸው፣እነሱም ሲያሞላቅቋት…እሷን መሀላቸው አድርገው ግራና ቀኝ እጇን ይዘው ወደቤተክርስቲያን ይዘዋት ሲሄዱ .... በአይነ ህሊናዋ ታያትና በደስታ ተፍለቀለቀች፡፡
‹‹ልጄ አሁን እሷን ልናይ ሆስፒታል ነው ያለነው ..ከቻልሽ ጋንዲ ነን …ብትመጪ ደስ ይለኛል፡፡››
መልሶ መደነጋገር ውስጥ ገባች‹‹ሆስፒታል…ምን ትሰራለች?››
‹‹ትንሽ አሟታል…ከቻልሽ ነይ፡፡››ደገሙላት፡፡
‹‹በቃ መጣው››……ስልኩን ዘጋችና ወደቢሮዋ ተመልሳ ለረዳቶቾ ወደስራ እንዲመለሱ ትዕዛዝ ሰጥታ ቦርሳውን አንጠልጥላ ወጣችና ቀጥታ ከፓርክ መኪናዋን በማንቀሳቀስ ስለአዲሷ እጩ እህቷ ምን እንደምትመስልና…ምኗን ታማ ሆስፒታል ልትገባ እንደቻለች እያብሰለሰለች ወደጋንዲ ሆስፒታል ነዳችው፡፡
ደርሳ ወደውስጥ ስትገባ ሰውነቷ መንቀጥቀጥ ጀመረ…ይሄ የተለመደ ስሜቷ ነው…ሆሲፒታል ሂጂ ከሚሏት ጦርነት ዝመቺ ብትባል ትመርጣለች…እንደምንም ግን ወደውስጥ ዘለቀች… አባቷን ደውላ አገኘችው…እጇን ይዞ እየመራ የተባለቸው ህፃን ወደተኛችበት ክፍል ይዟት ገባ፡፡ክፍሉ ውስጥ ከህፃኗ ጋር የገዛ እናቷ ብቻ ነች ያለችው፡፡ ከበራፉ አንድ እርምጃ ወደውስጥ ተራምዳ እንደቆመች ደንዝዛ ቀረች …ከዛ ማለፍ አልቻለችም፡፡
ፍፅም የሚባል ድንዛዜ ውስጥ ነው የገባችው…ልጅቷ ቢያንስ ከሶስት ማሽን ጋር በቱቦ ተያይዛለች…መልኳ ውብ ፀጉሯ ግንቧሯ ላይ ድፍት ያለ አጎጊ ብትሆንም ስልምልም ብላ እራሷን ስታ ተዘርራለች..እንደውም ነፍሷ ውስጧ እንዳለ እርግጠኛ መሆን አልቻለችም….
በቃ ውስጧ ግልብጥብጥ ነው ያለባት…ከአመታት በፊት ምትወደውና ልታገባው ስታልመው የነበረው እጮኛዋ ኪሩቤል እንዲህ እንደህፃኗ እራሱ ስቶና ዝርግትግት ብሎ በማሽን እገዛ ለመተንፈስ ሲያጣጥር የነበረው ትዝታ መጣባትና እራሷን ልትስት ተንገዳገደች..አጠገቧ ያለው አባቷ ፈጠን ብሎ ደገፋት…እናቷ በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ስሯ ደረሰች፡፡
‹‹ምነው ልጄ..አመመሽ እንዴ?››ሁለቱም ተቀባብለው ጠየቋት፡፡
‹‹አይ ደህና ነኝ …የመድሀኒት ሽታና የህክምና ማሽኖቹ ድምፅ ነው የረበሸኝ››
‹‹ቸሬ አንተ እኮ ነህ..እሷ ሆስፒታል እንዴት እንደምትጠላና እንደሚያማት እያወቅክ ነይ ያልካት፡፡››
‹‹እውነትሽን ነው አጥፍቻለው….በቃ ልጄ ነይ…ይሄን ያህል ካየሻት ይበቃሻል….ብለው እየጎተቱ ወደውጭ ወሰዷት…መኪናዋ ድረስ አደረሷት፡፡‹‹እርግጠኛ ነሽ ሰላም ነሽ…?መኪና መንዳት ትችያለሽ››
‹‹አታስብ አባዬ..ሰላም ነኝ..በቃ ተመለስ››
መኪና ውስጥ ገባታ ስትንቀሳቅስ አባትዬው ወደውስጥ ተመለሱ፡፡ቀጥታ ወደቤቷ ነው የሄደችው፡፡የልጅቷ ምስል ከአእምሮዋ ሊወጣ አልቻለም….ወላጆቾ ምን አስበው ያቺን በህይወት እና በሞት መካከል ባለች ቀጭን ክር ተንጠልጥላ ያለችን ልጅ በማደጎ ለመውሰድ እንዳሰቡ ሊገባት አልቻሉም…እንዴት አድርገው ሊንከባከቧት ነው…?ከለመዷትና ከወደዷት በኃላ ብትሞትባቸውስ…..?የሚወዱትን ሰው በሞት መነጠቅ እንዴት ልብን እንደሚሰብር እና ተስፋን እንደሚያከስም በራሷ ታውቀዋለች…እና በእሷ የደረሰ አይነት ሀዘን በዚህ እድሜያቸው በወላጆቾ እንዲድርስ አትፈልግም…፡፡
‹‹ግን ምን ማድረግ እችላለው?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡እንዲሁ ስትብሰለሰል አደረች…ሳምንት ሙሉ አሰበችበት..አንድ ውሳኔ ወስና ለወላጆቾ ምንም ነገር ማለት ሳትችል…ወላጆቹ ህጋዊ የአሳዳጊነት ፕሮሰሱን ጨርሰው ልጅቷን ወደቤታቸው እንደወሰዱ ሰማች፡፡በቃ ከዛ በጊዜ ሂደት የሚሆነውን ጠብቃ ለመመልከት ወሰነችና ወደወላጇቾ ቤት ሄዳ አዲሷን እህቷን አየቻት…ምንም እንኳን ከዛ ሁሉ ማሽን ነፃ ሆና ብታያትም..አሁንም ግን በጣም ደካማ እና የሰለለ ሰውነት ያለት ሆና ነው ያገኘቻት፡፡ግን ደግሞ በዛው ልክ አሳዛኝና ተወዳጅ ልጅ መሆኗን መካድ አልቻለችም፡፡
============
ራሄል ከረዳቷ ጋር እያወራች ነው፡፡
‹‹ሮቤል ወ.ሮ ላምሮት ልገሳዋን ለእኛ ፋውንዴሽን እንድታደርግ አሁን በስልክ አናግሬታለው፡፡እሷን ማሳመን ከቻልኩ እና ውሳኔዋ ለእኛ ለመለገስ ከሆነ ለፋውንዴሽናችን ትልቅ ስኬት ነው››
ራሄል ወረቀቶቿን ወደ ቦርሳዋ አስገባች፣ አንድ አይኗ በእንጨት በተሸፈነው የቢሮዋ ግድግዳ ላይ በተሰቀለው ሰዓት ላይ ተሰክቶ ነበር።
‹‹ ለማውራት ጊዜ የለኝም። በሃያ ደቂቃ ውስጥ በወላጆቼ መኖሪያ ቤት በተዘጋጀው የምሳ ግብዣ ላይ መገኘት አለብኝ ››አለች፡፡
ረዳቷ ማንኛውንም አይነት ቅሬታ ከማንሳቱ በፊት አቋረጠችውና ‹‹ እንደገና ሴትዬዋ ከደወለች ብቻ አሳውቀኝ።››አለችው፡፡
ስልኳን ዘጋችና ሞባይሏን ቦርሳዋ ውስጥ ለትንሿ እህቷ ጸጋ ከገዛችው ትንሽ ስጦታ ጋር አስቀመጠችው፣ ፀጋ ወላጇቾ ሊያሳድጓት በቅርብ የተረከቧት እህቷ ነች፡፡ ራሄል ወደ መኪና ማቆሚያ ጋራዥ በፍጥነት በምትወርድበት ጊዜ የኖብል ፋውንዴሽን ቢሮዎችና ኮሪደሮች በፀጥታ ተውጠው ነበር።

❤94🔥2😱1
እናቷ ከአዲሳባ ውጭ ለገጣፎ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው እንድትመጣ ነግራታለች፡፡ ይህ የግብዣና ጥሪ በየሳምንቱ የረፍት ቀኗን ጠብቆ የማይቀር ነው ፡፡ይሁን እንጂ የዛሬው የተለየ እንደሆነ ያወቀችው ፕሮቶኮሏን ጠብቃ እንድትመጣ ከሚያሳስብ ማስጠንቀቂ ጋር የተነገራት በመሆኑ ነው።ለምን ብላ እናቷን ስትጠይቅ ‹‹ወሳኝ እንግዳ ስለጋበዝኩ ዘንጠሸ እንድትገኚ ነው የምፈልገው ››ብለው ነበር በደፈናው የመለሱላት፡፡ እናቷ ሁል ጊዜ አንድትደሰትና እና ዘና እንድትል ከመምከር ተቆጥበው አያውቅም። ራሄል ግራጫ ቀለም ያለው ሙሉ ልብስ ለብሳ በላዩ ላይ የሐር ሻርፕ አንገቷ ላይ ጠምጥማ ቆንጆ ለመሆን ሞክራለች፡፡‹‹ እናቴ እኔን እንደፍላጎቴ እንድሆን መፍቀድ ነበረባት።››ስትል አጉረመረመች፡፡
ከአምስት አመት በኃላ ወላጆቿ ለገጣፎ ወደሚገኘው የእርሻ ቤታቸው ተመልሳ አብራቸው እንድትኖር ለምነዋት ነበር። ራሄል ግን ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጋ ለረጅም ጊዜ ብቻዋን መኖሯን ቀጠለች። በምትኩ መሀል ቦሌ በሚገኝ ባለሁለት መኝታ ክፍል አፓርታማ ቤት ውስጥ መኖርን መርጣለች።የእሷ ቤት በወላጇቾ ሀብት ልክ ዘመናዊ የሚባል ባይሆንም ለእሷ ግን ተስማሚ ነበር።
የተነሳችው ሰንጋ-ተራ ከሚገኘው የኖብል ፋውንዴሽን ዋና መስሪያ ቤት ነው፡፡መኪናዋን እራሷ እየሾፈረች በእጆቾ መሪውን እያሽከረከረች በአእምሮዋ ስለስራዋም ስለህይወቷም ብጥቅጣቂ ሀሳቦችን እያሰበች ፍጥነቷን ጠብቃ እየተጓዘች ሳለ…የትራፊክ መብራት አስቋማት፡፡ከኋላዋ የነበረ መኪና ከፊት ለፊቷ አልፏ ሲቀድማት በትዝብት ተመለከተችው፡፡ ከዛ ሌላ ሞተር ሳይክል በጎኗ ታኮ አጠገቧ ሲቆም ደነገጠች። የሞተሩ ጩኸት ከመኪናዋ ሲዲ ማጫወቻ የሚመጣውን የመሀመድ አህመድ ድምፅ ውጦ አስቀረው።ሞተረኛውን ተመለከተችው፡፡ የቆዳ ጃኬት፣ ጂንስ ሱሪ እና ቡትስ ጫማ አጥልቋል..ጭንቅላቱ ላይ ሄልሜት አድርጎል፡፡
ራሄል መሪውን አጥብቃ ያዘችው፡፡ ሞተር ሳይክሎችን ትጠላለች። እጮኛዋ ኪሩቤል በዚያ ምሽት መኪናውን እየነዳ ቢሆን ኖሮ-አሁን በዚህ ሰዓት ስለእሱ ሞት በማሰብ ልቧ በሀዘን አይኮመታተርም ነበር ። ይህም ሆኖ በሞተር ሳይክሉ ላይ ያለውን ሰው በጨረፍታ ለማየት ከመሞከር መቆጠብ አልቻለችም።ሄልሜቱን ወደ ኋላ ገፋ እና እያየችው እንደሆነ ሲመለከት ቀስ ብሎ ፈገግ አለላት፡፡ ረጅምና ባለፈርጣማ ጡንቻ ነው፡፡ጠይምና አይናማ ነው፡፡ለግላጋ ቁመናው በአእምሮዋ ብልጭ ድርግም እያለ ሲታያት ተናደደች ፡፡ወደ ፊት ተመለከተች።ወደ ወላጆቿ ቤት የሚያመራውን መንገድ ክፍት መሆኑን ተገነዘበች፡፡ ሞተር ሳይክሉን እየስጮኸ ቀድሟት ተፈተለከ፡፡
ሲዲውን አወጣች፣ የምትፈልገውን ሙዚቃ የሚጫወት ኤፍ ኤም ጣቢያ ፍልጋ አገኘች እና ድምጹን ከፍ አደረገች። በምቾት እየነዳች ነው ፣ ነገ ስለምትሰራው ሥራ ምን ማድረግ እንዳለባት እቅድ ማውጣት ጀመረች ።አዎ የእሷን ትኩረት በቀጥታ የሚፈልጉ በርካታ ስራዎች አሉ፤ውስጧን የሚሸረካክታትን በበፊት ህይወቷ የተከሰቱ ጨለማ ትዝታዎችን ወደኃላ መተው አለባት።በግዙፍ የዛፍ ጥላዎችና በተለያዩ አትክልቶች ወደተሞላው ግዙፉ የወላጆቾ ቤት ደረሰች፡፡ መኪናዋን በሁለት ረድፍ ተከርክመው ባማሩ የፅድ ቁጥቋጦዎች መካከል ባለው ጠባብ መንገድ እየሰነጠቀች ወደ ዋናው ቤት እየቀረበች ነው። ‹‹ምሽቱ ጥሩ ሊሆን ነው ››ስትል አሰበች ።እንደገና እራሷን መቆጣጠር እንደቻለች ተሰማት።
አራት መኪና ለማቆም ወደሚችለው ጋራዥ ስትቀርብ የልብ ምቷ ጨመረ ።መንገድ ላይ አበሰጭቷት ያለፈው ባለ ሞተር ሳይክል ሰውዬ አሁን ከጋራዡ ፊት ለፊት ባለው የጡብ ግድግዳ አጠገብ ቆሟል፣ ሄልሜቱን በሞተር ሳይክሉ መሪ ላይ አንጠልጥሏል።መኪናዋን አመቻችታ አቆመች፡፡ የዮጋ መምህሯ እንዳስተማራት ረጅም ትንፋሽ ወደውስጦ ሳበች…መልሳ አስወጣች ፣ከንደገና ሳበች …። እራሷን ያረጋጋች ሲመስላት ለፀጋ የገዛችላትን ስጦታ አንሥታ በጥንቃቄ እየተራመደች ወደ መግቢያው በር አመራች። ‹ምናልባት ባለሞተር ሳይክሉ የሽያጭ ሰራተኛ ወይንም የሆነ መልዕክት ሊያደርስ የመጣ ሰው ሊሆን ይችላል።›ስትል አሰበች …ወይም ከቤቱ አገልጋዬች የአንደኛዋ ውሽማ ሊሆን እንደሚችልም ገመተች፡፡
በሩን አልፋ ወደውስጥ ስትገባ የቤታቸው ሰራተኛ አለም ‹‹እንኳን በደህና መጣሽ!!›› ብላ በታላቅ ፈገግታ ተቀበለቻት፡፡
‹‹አመሰግናለው…አለም››
‹‹ እናትሽ ኩሽና ውስጥ ነች..››
‹‹…ለጥቆማው አመሰግናለሁ ።እማዬ ምን አይነት ምግብ እንደሰራች ልትነግሪኝ ትችያለሽ?››
አለም ሚስጥራዊ የሆነ ፈገግታ ፈገግ እያለች‹‹ ላንቺ እና ለእንግዳቸው የበለጠ ባህላዊ ነገር የሚያዘጋጁ ይመስለኛል…ከስጋ ጥብስ እና ክትፎ ሲኖር ሌላው ጠቅላላ የጎሯ ምርት የሆነ ቅጠላቅጠል ነው….››የሚል መልስ ሰጠቻት፡፡
ራሄል‹‹አይ እማዬ እና ቅጠላ ቅጠል መች ይሆን የሚለያዩት!!››አለችና ያንን አስጠሊታ ሞተር ሳይክል እያከነፈ የመጣው ሰው ማን እንደሆነ ሳትጠይቃት ወደ ቤቱ ጀርባ ሄደች። ራሄል የፊት ለፊት ክፍል ግድግዳ ላይ የተንጠለጠለው መስታወት ውስጥ የራሷን ምስል ነጸብራቅ ተመለከተችና ቆም አለች፡፡ በመጠኑ የተዘበራረቀውን ፀጉሯን ለማስተካከል ትንሽ ጊዜ ወሰደባት፡፡ መላ አካሏ ንፁህ እና የተስተካከለ እንደሆነ አሰበች ። በጠባቡ ኮሪደር በኩል ወደ ኩሽና አመራች፡፡ እናቷ በዘመናዊው ኩሽና ውስጥ እንደ ደሴት የሚያገለግለው ግዙፉ መደርደሪያ ላይ ቆመው አትክልት ሲከትፉ አገኘቻቸው፡፡ ብርቱካናማ ልቅ ሽርጥ አድርጋገዋል፡፡ ወ.ሮ ትርሀስ ልጇቸውን ስያዩ ቢላዋዋን አስቀምጠው በሽርጣቸው ዙሪያ እጆቻቸውን እየጠራረጉ, ራሄልን እቅፏቸው ውስጥ አስገብተው አገላብጠው በመሳም ሞቅ ባለ ስሜት ተቀበሏት ‹‹በሰዓቱ በመምጣትሽ በጣም ደስ ብሎኛል ። ››
ራሄል እናቷን ሀዘን ባጠላባቸው አይኖቿ ተመለከተቻቸው።
‹‹ትንሽ የገረጣሽ ትመስያለሽ …ውዴ።?››
ራሄል ግልጽ ባልሆነ ምልክት እጇን አነሳችና ።‹‹ ስራ በዝቶብኝ ነበር..ሰሞኑን በቂ እንቅልፍ አላገኘውም…ለዛ ነው››
ለፀጋ ያመጣችውን ስጦታ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠች። እናቷ ማስጠንቀቂያቸውን አጠንክረው ቀጠሉበት ‹‹ራስህሽን መንከባከብ አለብሽ …ሰውነታችን የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ነው …እግዚአብሔር በምድር ላይ ሥራውን ለመሥራት ጤናማ አገልጋዮች ያስፈልጉታል።››አሏት፡፡
ራሄል በእናቷ የተለመደ አይነት ንግግር ፈገግ አለች። በእግዚአብሔር ጉዳይ ላይ ከእናቷ ጋር ለመወያየት አልፈለገችም።ላለፉት ስምንት አመታት እግዚአብሔርን ከህይወቷ አስወጥታለች ወይም ለማስወጣት ሞክሯለች። የዚህም ምክንያት ‹‹ከእግዚአብሔር ፀሎቴን ቀብሮታል.. ህልሜን አክስሞታል…››ብላ ስለምታስብ ነው።እናቷ እጇቸውን በራሔል ትከሻ ላይ አድርገው ወደ ባንኮኒው ወሰዷት።
‹‹እኔና አባትሽ አንድ ደስ የሚል አስገራሚ ነገር አለን።የፀጋ ሐኪም መጥቶ እንዲጎበኘን ጋብዘነዋል።››
‹‹አሁን እዚህ አለ?››
እናትዬው በአውንታ ግንባራቸውን ነቀነቁ
‹‹ማለት ሞተር ሳይክ እየነዳ ቀድሞኝ የገባው ሰውዬ እንዳይሆን?››
‹‹አዎ››እናትዬው አረጋገጡላት፡፡‹‹አንቺም እሱን ለማግኘት ትፈልጊ ይሆናል ብዬ አሰብኩ››በማለት አከሉበት፡፡
እናትዬው በዘዴ ከዶ/ሩ ጋር ፊት ለፊት ከመጋፈጧ በፊት ስለሰውዬው የተወሰነ ግንዛቤ ሊያስጨብጧት እየሞከሩ እንደሆነ ገብቷታል፡፡
‹‹በሞተር ሳይክል ላይ ሳየው ግን ሞኝ መስሎ ነው የሚታየው›› ስትል ተናገረች፡፡

❤68👍6
‹‹ራሄል እንደዚህ አይነት ቃላትን መጠቀም የለብሽም።በተለይ እንደ ኤሊያስ ላለ ድንቅ ሰው።››
ራሄል እናቷ የሁለት ዓመቷን ፀጋን በማደጎ ልጅነት ወደቤታቸው ስትመጣ ለልጅ ልጆች ያላቸውን ሥር የሰደደ ፍላጎት እንደምታረካላቸው ተስፋ አድርጋ ነበር።እናም እሷን አግቢ ..ውለጂና የልጅ ልጅ አሳይን ብለው በየእለቱ የሚጨቀጭቋትን ጭቅጭቅ እንደሚያቆሙላት ትጠብቅ ነበር፡፡ አሁን እንደምታው ግን ያ ሽንቁር አሁንም እንዳለ መሆኑን ነው የገባት፡፡
‹‹አዝናለሁ እማዬ፣ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ማንም ሞተር ሳይክል የሚነዳ ሰው ኃላፊነት የሚሰማውና የሚተማመኑበት ሰው ይሆናል ብዬ አላምንም።ለዛውም የሕፃናት ሐኪም ሆኖ…ሞተር ሳይክል መንዳት።››ራሄል በጠረጴዛው ላይ ከተቀመጠው ጎድጓዳ ሳህን ውስጥ አንድ አነስ ያለ ካሮት ወሰደች እና ገመጠች።
እናትዬው ልጇቸው ስለሞተር ሳይክል አንስታ ስታወራ ምን ለማለት እደፈለገች ስለገባቸው ምንም ሊመልሱላት አልፈለጉም፡፡
ራሄል ‹‹አባዬ የት ነው ያለው?››ስትል ጠየቀች፡፡
‹‹እሱ እና ዶ/ር ዔሊያስ ከፀጋ ጋር ሆነው ወደ አትክልት ስፍራ ወጥተዋል።እስከአሁን ተመልሰው እየመጡ እንደሆነ አምናለሁ።››
ራሄል ግቢውን ለማየት ወደ መስኮቱ ዞረች፣የመጨረሻውን የካሮት ቁርጭ አፏ ውስጥ ከታ እየኮረሸመች መመልከቷን ቀጠለች፡፡ በበር ኤሊያስ ከአባቷ ጋር ብቅ አለ፣ እጁን ዘርግቶ የፀጋን ፀጉር ከፊቷ ላይ ገልጦ ወደኃላ እያስተኛላት በለስላሳው ፈገግ አለ።ፀጋ በሩቅ ስታያት ሳቀችላት እና ወደ አባቷ ተጠጋች።ራሄል ከፊትለፊቷ ከአባቷ ጎን ያለውን ሰውዬ የእህቷ ዶክተር ይሆናል ብላ በአእምሮዋ ከቀረፀችው ፎቶ ጋር ምስሉን ማጣመር አልቻለችም።
‹‹ሞተር ሳይክሉን እየነዳ የነበረው ሰውዬ ማን ነበር?።››ራሷን ጠየቀችና ከመስኮቱ ዞር ብላ ወደእነሱ ተጠጋች፡፡
ራሄል አባቷ ወደ ክፍል ሲገባ ተመለከተች። ወደ ፊት ተንቀሳቀሰችና አባቷ እቅፍ ውስጥ ገባች …ትንሹን ሴት ልጁን በሌላኛው ክንድ ላይ አስተካክሎ አቀፋት..።‹‹ሰላም አባዬ››።
‹‹የእኔ ውድ ስላየሁሽ ደስ ብሎኛል››ፀጋን በጨረፍታ ተመለከተቻት፣ ወደ እሷ በመመልከት ሣቅች፣ የተጠማዘዘ ቡናማ ፀጉሯ እና የልብ ቅርጽ ያለው ፊቷን አስተዋለች፡፡ ሮዝ ቲሸርት እና ሰማያዊ ጂንስ ቱታ ለብሳለች። የእናቷን የልብስ ጣዕም ግምት ውስጥ በማስገባት የተለመደ አለባበስ ነው ስትል አሰበች.፡፡እሷም ልጅ እያለች ተመሳሳይ አይነት አለባበስ ታዘወትር ነበር፡፡
ራሄል በፈጣን ፈገግታ የእህቷን ትከሻ እየዳበሰች‹‹ሄይ፣ እህቴ››አለች ።ፀጋ ሚዛናዊ ሆና እጆቿን ወደ ራሄል ዘረጋች። ራሄል ወደ አባቷ እቅፍ መለሰቻት እና አንድ እርምጃ ከእነርሱ ርቃ ቆመች። ፀጋ ቆንጆ እና አፍቃሪ ሴት ነበረች። ራሄል ግን ለእሷ ያላትን በጎ ስሜት አሳይታት ስለማታውቅ ትንሽ ትጨነቃለች።ራሄል የወላጆቿን ልብ የማረከችውን ትንሽ መልአክ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ስታያት መተንፈሻ መሳሪያ ተገጥሟላት ፣ ከ IV እና ከሌሎች ማሽኖች ጋር ተሳስራና እራሷን ስታ ነበር ። ፀጋ ሴሬብራል ፓልሲ የሚባል በሽታ ነበረባት፡፡በዚህ የተነሳ እንቅስቃሴ ማድረግ በጣም የምትቸገር..አጥንቶቾ ያልጠነከሩና የተልፈሰፈሰች..ከዛም በላይ ብዙ ተያያዥ ችግሮች ያሉባት ህፃን ነበረች፡፡እና በወቅቱ የወላጆቾን ውሳኔ ደፍራ ለመቃወም ባትደፍርም በጣም ያሳሰባትና ያስጨነቃት ነበር፡፡አሁን ግን በብዙ የህክምና ክትትልና የመድሀኒት እገዛ ቀስ በቀስ ከበሽታዋ እያገገመች ነው።ከብዙ ጊዜ በፊት ወላጆቿ ልጅ ተቀብለው ለማሳደግ ለማደጎ ተቋም አመልክተው ነበር ፀጋን ሲያዬት ግን እሷን ለማሳደግ እንደሚፈልጉ በመናገር የራሔልን አስተያየት ጠየቋት። በሰዓቱ ራሄል ጋንዲ ሆስፒታል ተኝታ የነበረችውን ፀጋን ልታያት ስትሄድ ለሆስፒታሎች ያላትን ጥላቻ ማሸነፍ እንደምትችል አስባ ነበር፣ ነገር ግን ከአምስት ደቂቃ በላይ ከጸጋ አልጋ አጠገብ መቆም አልቻለችም ነበር ። የመተንፈሻ አካሉ ጩኸት እና በአየሩ ላይ የተንሰራፋው የጸረ-ተባይ ጠረን በውስጦ የተዳፈነውን ቀፋፊ ትዝታ ነበር የቀሰቀሰባት፡፡ከዛም አልፎ በማቅለሽለሽ ማዕበል ተመታች።ለወላጆቿ መልካም ምኞቷን በመግለፅ ሆስፒታሉን ለቃ ወጣች…ከዛ ፀጋ የተወሰነ የጤና መሻሻል አሳይታ ወደቤት ከመጣች በኃላ ነው ያየቻት፡፡ ።ይሁን እንጂ አሁን ድረስ ልጅቷን ስታያት አቅመቢስነት እና ጣር የታከለበት ህመም እና ቀፋፊ የሆስፒታል ምስል ነው የሚታያት ።በዛ ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ከአጠገቧ ለመቆየት ምቾት አይሰማትም።
ራሔል‹‹ ታንሿ እህቴ እነሆ ስጦታ አመጣሁልሽ።›› በማለት ለፀጋ የተጠቀለለውን እሽግ ሰጠቻት።
‹‹ምን ትያለሽ ማር?››አባቷ ቸርነት ፀጋን ስለስጦታው ምን እንደተሰማት ጠየቋት።
በኮላታፈ እና በሚጎተት አንደበቷ ‹‹አመሰግ…ና..ለው›› አለች፡፡
✨ይቀጥላል✨

❤77👍8