#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
////
‹‹ቆይ ዘሚካኤል የት ነበር የጠፋው?፡፡››
‹‹እናቱና እህቱ የሞቱ ቀን ነው የተሰወረው፡፡ሁለቱ በመልክም ሆነ በአመካከት ፍጹም ተቃራኒ የሆኑት ወንድማማቾች ከከተማ ተያይዘው ወደቤት ሲገቡ ..ሳሎኑ ፍፁም ትርምስምስ ብሎ ያያሉ ..ግራ በመጋባት ወደውስጥ ዘልቀው ሲገቡ እናታቸው ልቧ ላይ ነጭ አብረቅራቂ ቢላዋ ተሰክቷባት ወለሉ ላይ ዝርግትግት ብላ ተኝታለች..አባትዬው ስሯ በደም በተጨማለቀው እጇቻቸው ጭንቅላታቸውን ይዘው ደንዝዘዋል….፡፡
‹‹እንዴ አባዬ ምንድነው..?እናቴን ምን አደረካት?›› ብለው ሲጮሁ ከፊት ለፊት ኮርኒሱን ከደገፈው ብረት ላይ በታሰረ ሲባጎ አንገቷ የታነቀው እህታቸው በድኗ 360 ዲግሪ ሲሽከረከረከር ይመለከታሉ፡፡ሁለቱም ወንድማማቸች ወደእህትዬው እየሮጡና ሁለት እግሮቾን አንድ ላይ ይዘው ወደላይ ከፍ ያደርጎታል….‹‹ቶሎ በል ቢላዋ አምጣና ..ገመድን ቁረጥ…››
.ዘሚካኤል ይንደረደርና እናትዬው ደረት ላይ የተሰካውን ቢላዋ ይነቅልና ወንበር ላይ ቆሞ ገመዱን ይበጥሳል…እህትዬው ተዝለፍልፍ ሚካኤል ተከሻ ላይ ታርፋለች… ቀስ ብለው ወለል ላይ አሳርፈው በፍጥነት አንገቷ ላይ ያለውን ገመድ አላቀው ትንፋሿን ቢያዳምጡም በውስጧ የቀረ ምንም እንጥፍጣፊ እስትንፋስ አልነበረም….ከዛ ዘሚካኤል ቀጥታ እህቱ የተንጠለጠለችበትን ገመድ የቆረጠበትን እና እናቱ የተገደለችበትን ቢላዋ ይዞ ወደአባትዬው ሲንደረደር…ሚካኤል በደመነፈስ ሮጠ ይጠመጥበታል…
‹‹ልቀቀኝ..እናቴንና እህቴን ገድሎ እሱ በህይወት አይኖርም››
‹‹አይሆንም….ስለሆነውን ምንም ምናውቀው ነገር የለም››ሲል ይመልስለታል፡፡
‹‹እንዴት አናውቅም..?አታይም እንዴ …?እጁ በደም ተጨማልቆ……ልቀቀኝ ልግደለው›› ሲል ይጋበዛል፡፡
‹‹አባቴንም ማጣት አልፈልግም››
‹‹እንግዲያው ሁለታችሁንም እገድላችኃለው…››ይለውና ድብድብ ይጀምራሉ…ይሄ ሁሉ ሲሆን አባትዬው ደንዝዘው ከተቀመጡበት ቦታ ንቅንቅ አላሉም ነበር….ወንድማማቾቹ አባቴን ልግደል አትገድልም በሚል ጠብ እርስ በርሳቸው ተቦቅሰውና ተደባድበው ሳይለይላቸው ቤቱ በፖሊስ ይሞላል፡፡
አባትዬ እነሱ ከመድረሳቸው በፊት ስልክ ደውለው ሚስታቸውን እንደገደሉ ነግሮቸው ነበር፡፡ፖሊሶቹ ወንድማማቾቹን አገላግለው ሶስቱንም ወደእስር ቤት ከወሰዷቸው በኃላ ሬሳዎቹን አንሰተው ለምርመራ ወደሆስፒታል ይልካሉ..በማግስቱ አባትዬው ሚስታቸውንም ሆነ ልጃቸውን የገደሉት እራሳቸው እንደሆነ ቃል ስለሰጡ በዛ መሰረት ሁለቱ ልጇች ይፈታሉ፡፡
ከአራት ቀን በኋላ የእናትና እህታቸውን ሬሳ ተረክበው ከቀበሩ በሆላ ዘሚካኤል በከተማው አልታየም፡፡‹‹አንተ ያንን አውሬ ሰውዬ ገድዬ የእናቴንና የእህቴን ደም እንዳልበቀል ያደረከኝ ጠላቴ ነህ..ከእሱ በላይ እጠላሀለው ..እና ደግሞ መቼም ቢሆን ይቅር አልልህም፡፡››የሚል ማስታወሻ ለወንድሙ ጥሎ ነበር የጠፋው፡፡ቆይቶ እንደሰማነው ከጓደኞቹ ጋር በቦረና በኩል ወደኬኒያ ከዛም ወደጣልያን ከተሻገረ በኋላ…በፊትም ልጅ እያለ ጀምሮ ይሞካክረው በነበረው ሙዚቃ ገፋበትና በትምህርትም አሳድጎ ጥሩ ሙዚቀኛ ሆነ ፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወት መኖሩን ያወቅነው የዛሬ 3 አመት የሙዚቃ ክሊፑን ሲለቅ ነው፡፡
….የዛን ጊዜ ሚካኤል የተደሰተው መደሰት ያው አንቺም አብረሺን ስለነበርሽ ታውቂዋለሽ፡፡ከዛ በሀገር ውስጥ በጣም ተቀባይነት ስላገኘ ..ጓዙን ጠቅልሎ ገባ፡፡በሙዚቃ ብቻ ሳይሆን በፊልም ትወና ላይ መስራት ቀጠለ…እንግዲህ ባለፉት አምስት አመታት የገነባውን ስምና ዝና እኩል ነው የምናውቀው፡፡››
‹‹ይገርማል….ግን ከመጣ በኃላ ወንድሙን ለማግኘት አልሞከረም…?››
‹‹ወይ ማግኘት..እኔ አንኳን ላገኘው ሄጄ ስለወንድሙ ሳነሳበት እንዴት እንደተንገሸገሽ እስከዛሬ ሳስበው ይዘገንነኛል..አሁንም ጥላቻው እንዳለ ነው፡፡አልፎ አልፎ በድብቅ እየመጣ የእናቱንና የእህቱን መቃብር እየጎበኘ እንደሚሄድ አውቃለው….በዛው ልክ ስለአባቱም ሆነ ስለወንድሙ ምንም መስማት እንደማይፈልግ እና ቢሞቱም ግድ እንደሌለው አውቃለው፡፡››
‹‹ተይ እንደዛ አትበይ…..››
‹‹ወይ አንቺ ልጅ ስንት ነገር ውስጥ አስገባሺኝ..ስለእሱ ለማወቅ ለምንድነው የፈለግሽው?፡››ስትል ዳግመኛ ጠየቀቻት፡፡
‹‹እንደምንም ብዬ በሰርጋችሁ ላይ እንዲገኝ ለማድረግ አስቤለው››
‹‹ምን?››አዲስአለም ክፉኛ ነው የደነገጠችው፡፡
‹‹ምነው መጥፎ ሀሳብ ነው እንዴ?››
‹‹አረ በፍጹም…ግን የሚሳካ እቅድ አይደለም….››
‹‹ከተሳካልኝስ?››
‹‹ከተሳካልሽማ….ለሚካኤል በሰርግ ላይ ሌላ ሰርግ ደገሽለት ማለት ይሆናል….በፊቱንም ይወድሻል በቃ የዘላለም ባለውለታው ነው የምትሆኚው››
ፀአዳ ‹‹ለማንኛውም ጉዳዩ በእኔና አንቺ መሀከል በሚስጥር ይያዝ …..ሚካኤል ሰምቶ ካልተሳካ ቅር እንዲሰኝ
አልፈልግም፡፡››ስትል አስጠነቀቀቻት፡፡
‹‹አታስቢ እኔም ባሌ በሰርጉ ሰሞን እንዲያዝንብኝ ስለማልፈልግ ..አልነግረውም…ለአንቺ ግን እንዲቀናሽ በቻልኩት መንገድ ሁሉ አግዝሻለው፡፡››
በዚህ ሁኔታ ነበር ከአዲስ አለም ስለዘሚካኤል የተወሰነ ነገር ማወቅ የቻለችው..ከዛ ወደ ሶሻል ሚዲያ ሄደችና እና ስለእሱ የተፃፉ የጋዜጣ አምዶችና በተለያየ ጊዜ የሰጣቸውን ቃለ መጠይቆችን ሰብስባ ማንበብና ማዳመጥ ነው የቀጠለችው…ይሄ ሂደት አንድ ሳምንት ነው የፈጀባት፡፡በዚህ ጊዜ በአምስት አመት ውስጥ ያወጣችውን ሶስት አልበሞችና ፤ከስምንት በላይ ነጠላ ዜማዎችን እየደጋገመች ያደመጠች ሲሆን እሱ የተሳተፈባቸውን ስምንት የሚሆኑ ፊልሞችንም በጽሞና መመልከት ችላለች፡፡
እና በዚህ አንድ ሳምንት ውስጥ ለአመታት የምታውቀው የቅርቧ ሰው እንደሆነ እንዲሰማት አድርጎታል..ያንን ስሜት ግራ አጋቢ ነው፡፡‹አይ በጣም የምወደው ወንድሜ የሚካኤል ወንድም ስለሆነ በእሱ እይን እሱንም ማየት ጀምሬለው ማለት ነው..›ስትል ለራሷ ማብራሪያ መስጠት ብትሞክርም ሊያሳምናት ግን አልቻለም፡፡
ደግሞ ስለሴሰኝነቱ..በየጊዜው ስለሚቀያይራቸው ሞዴል መሳይ ሴቶች፤ ከዝነኛ እንስቶች ጋር ስለሚጀምረው የፍቅር ግንኙነትና ስለመለያየቱ …ከስራው እኩል አንዳንዴም ከስራው በላይ ነው ሚያወራው፡፡እና ለእንደዚህ አይነት ሴት አውል የማይጨበጥ ሙልጭልጭ ወንድ ምን አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው….?መልስ የላትም፡፡ግን አሁን ልታገኘውና ልትጋፈጠው ወስናለች..ዝግጅቷንም ጨርሳለች፡፡
///
ፀደይ ባደረገችው ጥናት እና በሰበሰበችው መረጃ መሰረት የሚካኤል መንታ ወንድም የሆነው ዘሚካኤልን ለማናገር አንድ ብቸኛ መንገድ ብቻ እንዳላት ተረድታለች፡፡በሳምንት ሶስት ቀን በሚሰራበት በከተማዋ ታዋቂ ናይት ክለብ ተገኝታ እድሏን መሞከር ፡፡ከእሷ ባህሪ አንጻር እንደዛ አይነት ቦታ ተገኝታ የማታውቀውን ሰው ማናገር በጣም ከባድ የቤት ሰራ ነው፡፡ቢሆንም የግድ ልትወጣው የሚገባ ተግባር እንደሆነ እራሷን አሳምናለች፡፡
ባለፉት ሁለት ቀን ውስጥ የተባለው ናይት ክለብ ውስጥ በውድቅት ለሊት በመገኘት እሱ ሲዘፍን እና በቀበጥ አድናቂዎቹ ሲሞገስና ሲሸለም መመልከት ብትችልም እሱን ተጠግቶ ለማናገር ያደረገችው ሙከራ ግን ሙሉ በሙሉ አልተሳካላትም ነበር፡፡ዛሬ ግን የግድ ሊሳካላት ይገባል..ምከንያቱም ሰርጉ ከአምስት ቀን በኃላ ነው፡፡ዛሬ አግኝታ ካላናገረችው…ወደእዚህ መጥታ ሌላ ሙከራ የምትሞክርበት ሌላ እድል የላትም፡፡

👍62❤13🥰3👏1
ልክ ስምንት ሰዓት አካባቢ ወደ ሽንት ቤት ሄደችና አስባና አቅዳ አስመስላ ያሰፋችውን የቤቱን ሴት አስተናጋጆች ልብስ ለበሰችና ሰሞኑን ባጠናችው መሰረት ሙዚቀኞች ለማረረፊያና ለመዘጋጃ ወደሚጠቀሙበት ከፍል ሄደችና እንደምንም ተሹለክልካ ከጀርባ በኩል አልፋ ስራ እየሰራች በማስመሰል መጠበቅ ጀመረች፡፡
በመድረክ ላይ የሚያቀርበውን ዝግጅት ካጠናቀቀ በኃላ በሁለት ጋርዶች ተጅቦ ሲመጣ ተመለከተች…ፈጠን አለችና በረፉን ከፍታ በመግባት መልሳ ዘግታ ዙሪያ ገባውን ተመለከተች፡፡ተንደረደረችና ከግዙፍ ጥቁር ቆዳ ከለበሰው ሶፋ ጀርባ ሄዳ ተወሸቀች…ብዙም ሳይቆይ የበራፍ መከፈትና የእግር ኮቴ ሰማች….የልቧ ድውድውታ ከእራሷም አልፎ ለእሱ የሚሰማ መስሎ ተሰማትና ሰጋች፡፡
‹‹የአንድ ሰዓት ረፍት አለኝ….ትንሽ አረፍ ልበል…አስር ጉዳይ ላይ ቀስቅሱኝ››ከጋርዶቹ ጋር ነው የሚያወራው፡፡
‹‹እሺ..ተኛ እንቀሰቅስሀለን››
አጮልቃ ስታይ ጋርዶቹ ከውጭ በራፉ ላይ ሲቀሩ እሱ ከውስጥ ሆኖ ዘጋባቸው..በራፉን ቀረቀረና…ከላይ የለበሰውን ጃኬት አወለቀ …ወደክፍሉ መሀል ሄደ…ከዛ የለበሰውን ቲሸርት አወለቀ….በተደበቀችበት ሆና መላ ቁመናውና ተመለከተች…ጠንበልል የሚባል ወንዳወንድ ነው፡፡ከወንዶች ይልቅ የሴቶች የሙዚቃ አፍቃሪዎች በእጥፍ እንደሚወዱት ታውቃለች፡፡ይሄ የሆነው ስርቅርቅ ድምፁ ከወንዶች ይልቅ ሴቶችን የማቅለጥ ተፈጥሮው ስውር ችሎታ ስላለው ሳይሆን የሴቶችን ልብ የማቅለጥ አቅም ያለው ወንዳወንድ ቁመናና አቅልጥ ውበት ስላለው እንደሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ቲሻርቱን ሲያወልቅ ከወገቡ በላይ ርቃኑን ቀረ…ሆዱ በግማሽ በጥቁር ፀጉር የተሸፈነ ነው፡፡በዛ ላይ አብረቅራቂ ሰንሰለት መሳይ ሀብል ስላንጠለጠለበት ቀልብ ይስባል፡፡
በተደበቀችበት ሆና የለበሰችውን የአስተናጋጅ ልብስ አወለቀችና እዛው ስሯ ወለል ላይ ጣለችው፡፡ሱሪውን ለማውለቅ ቀበቶውን መፍታት ሲጀምር ተስፈንጥራ ከተደበቀችበት ወጣችና ከፊት ለፊቱ ተደንቅራ ቆመች፡፡
በከፍተኛ መገረም እነዛ ተንከባላይ ሰማያዊ አይኖቹን ተከለባት፡፡አይኖቹ ልብን በቀላሉ ሰርስረው የሚገቡ አስማታዊ ስለሆኑ መቋቋም ከበዳት፡፡
‹‹አቤት ..እዚህ እንዴት ገባሽ?››የቁጣ ሳይሆን የመደነቅ ቃና ባለው ድምፀት ጠየቃት፡፡
‹‹በብዙ ድካም ….ተደብቄ..››ስትል ድፍን ያለ መልስ ሰጠችው፡፡
አፈቀርንህ ..እራሳችንን እናጠፋለን ..ምናምን የሚሉ በእሷ እድሜም የሆኑ ከእሷ ያነሱ ወጣቶች በየእለቱ የተላያዩ አይነት ገጠመኞችን በመፍጠር ሊያገኙትና ሊዳስሱት ስለሚሞክሩ ይሄንንም ከዛ የተለየ ነው ብሎ አላሳበም…
ፀደይ የሚንደቀደቀውን የልብ ትርታዋን ለመቆጣጠር እየታገለች በቀጣይ ምን ብላ ወደመጣችበት ጉዳይ እንደምትገባ እያሰላሰለች ሳለ…ለግላጋ እጁን በመዘርጋት በቀጭን ወገቧ አዙሮ ያዘትና በኃይል ጎትቶ ግማሽ እርቃን ከሆነ ሰውነቱ ላይ ለጠፋት፡፡
ፈፅሞ ይሆናል ብላ ያልጠበቀችው ስለነበረ …አንገቷን ቀና አደረገችና በልምምጥ ተቁለጭላጭ አይኖቾን በተንከባላይ አይኖቹ ላይ ተከለች፡፡በቁመት ቢያንስ በ40 ሳ.ሜትር ይበልጣታል…ስለዚህ እሷ አንጋጣ ስታየው እሱ ደግሞ አዘቅዝቆ ነው የሚያያት፡፡
.. የገባችበት እውነታ አምኖ መቀበል ነበረበት።አስደናቂ ነበር ። እንዲለቃት ልትጠይቀው በጣም ፈልጋለች..ግን ቃላትቱን ከአንደበቷ ማውጣት አልቻለችም፡፡ ይባስ ብሎ አፉን አሞጥሞጦ ወደታች ዝቅ አለና ከንፈሯን በከንፈሩ ጎረሰው…ሳትወድ በግዷ አይኗን ጨፈነች….‹‹ጌታ ሆይ ድረስልኝ››ስትል በውስጦ ልትፀልይ ሞከረች፡፡እንደክንፍ የተዘረጋውን እጇን ያለፍቃዷ ወደ እሱ ላከችና በወገቡ ዙሪያ ጠመጠመች፡፡ምላሱን ጎልጉሎ አፏ ውስጥ ከተተውና ሲያሽከረከረው..አቃሰተች…ይሄ የመጀመሪያ ጊዜ ገጠመኞ ነው…ገላዋ ከወንድ ገላ ጋር እንዲህ ሲጣበቅና ሲቀልጥ ከስድስት አመት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
የዚህ ዝነኛና ሀብታም ድምጻዊ ሴት አውልነት የታወቀና የየእለት የታብሎይዶችና ዩቲዩቦች ማድመቂ ዜና ነው፡፡ለእሱ በእየእለቱ እንደሚመገበው ቁርስና ምሳ ሴቶችን መቀያየርና በፍቅር በማቅለጥ ከዛም አልፎ ለወሲብ ወደአልጋ ላይ መጎተት ተራና የተለመደ ነገር ነው..ለእሷ ግን ከዛ በጣም የተለየ ነው፡፡ታዲያ አሁን እንዴት ተቃውሞ አልባ ሆነች..?እንዴት ለመሳም ሲያቅፋት ለመታቀፍ እንዲህ ቸኮለች..ሲስማትስ እንዴት መልሳ ሳመችው ?ለአመታት በውስጧ የተዳፈነው የወሲብ ረሀብ ድንገት ገንፍሎ ከቁጥጥር ውጭ ስላደረጋት ይሆን?፡፡‹‹አይ እንደዚህማ ተራ ሴት አልሆንም…. በፍፅም…እንደምንም ታግላ ከንፈሯን ከከንፈሩ አላቀቀች….ከዛ ከእጆቹ ሾልካ ወጣችና አንድ ሜትር ወደኃላዋ ፈንጠር ብላ ቆመችና በእጆቾ ጣቶች ለደቂቃዎች ሲሳማት የቆየውን ከንፈሯን እየነካካች ቆመች ፡፡
እሱም በቆመበት እየተመለከታት ምን እንዳልተመቻት እያሰላሰለ ነው፡፡የሆነ ነገሯ ልቡ በፍጥነት እንዲመታ አድርጎታል፡፡፡ቆንጆ ነች፡፡ግን ደግሞ በእየእለቱ ስዕል ሚመስሉ ብዙ ቆንጆዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ በመልኳ ልታስደምመው አትችልም ፡፡ማንኛዋም ሴት እሱ ፊት ለመቅረብ ስትመጣ ተበድራም ሆነ ተለቅታ ውድ ልብስ ለብሳ ፤ሜካፖን ተለቅልቃና ተቆነጃጅታ ነው፤ይህቺ ፊት ለፊቱ ያለችው ልጅ ግን ዝም ያለ ፍዝ አለባበስ ነው ለበሰችው፡፡ኦሞ ቀለም ያለው ጅንስ ሱሪ ከነጭ ቲሸርት ጋር ለብሳለች፡፡፡አንገቷ ላይ ሮዝ ቀለም ያለው ሻርፕ ጣል አድርጋለች፡፡እና ነጭ ስኒከር ጫማ ተጫምታለች በቃ፡፡በዛ ላይ የለበሰችው ጅንስ ሱሪ ጉልበቱ ላይ ተቦጭቋል…ለፋሽን ተብሎ የተቦጨቀ ሳይሆን ምስማር የቦተረፈው እንደሆነ ያስታውቃል፡፡
ፀደይ ረጅምና ጥልቅ ትንፋሽ ወሰደች። መረጋጋት አለባት። እሷ እዚህ ለትልቅ ተልዕኮ ነው የተገኘችው፡፡በጣም አስፈላጊ ለሆነ ተልዕኮ …. እና በቀላሉ በልብ ድካም ተይዞ ለመዝለፍለፍ ጊዜ አልነበራትም - ይህ የጀመረችው የእብደት አካሄድ በእቅዷ ላይ ከባድ መፋለስ ይፈጥርባታል።የሁለት ጓደኞቾን የስረግ ካርድ ሰጥታው ግብዣዋን ላይ መገኘት እንዳለበት ማሳመን አለባት ፡፡
‹‹ይቅርታ እኔ ለዚህ አልመጣሁም››አለችው፡፡
‹‹ለዚህ ማለት?››በግማሽ መገረምና በግማሽ ፈገግታ ጠየቃት፡፡
‹‹ማለቴ ያው ይገባሀል ..ለመሳሳምና ለ…..››አንጠልጥላ ተወችው፡፡
‹‹እኔ ደግሞ ለዛ መስሎኝ በጣም ተነቃቅቼና ተደስቼ ነበር››አለና ፈገግ አለ፡፡
‹‹ይቅርታ..ስትስበኝ መሳብ..ስትስመኝም መሳም የለብኝም ነበር››
‹‹ግን አድርገሽዋል..እና ሳስበው ደግሞ መጥፎ አይመስለኝም››
‹‹ሊሆን ይችላል…ግን አግባብ ስራ አልነበረም..ይቅርታ…ጊዜህን አልሻማብህ የመጣሁበትን ጉዳይ ልንገርህና ልሂድ››
‹‹ምንድነው..ምን ልርዳሽ?››
የጅንስ ሱሪዋ የኃላ ኪስ ገባችና አንድ ፖስታ አወጣችና አቀበለችው፡፡
‹‹ምንድነው?››እያለ እጁን ዘርግቶ ተቀበላት..ፖስታውን ሲመለከት ወዲያው ወደአእምሮ የመጣለት በሆነ ችግር ለምሳሌ የሆነ ቤተሰብ ታሞባት ለህክምና እርዳታ እየጠየቀች ነበር የመሰለው፡፡
እንደዚህ አይነት ነገር በተለያየ መንገድ ሁል ጊዜ ስለሚደርሱት ብዙም ሚደንቅ አይደለም..በዚህ መንገድ ግን በለሊት ተደብቃና ተሹለክልካ ማረፊያ ክፍሉ ድረስ ገብታ በዚህ መልክ እርዳታ የጠየቀችው ሴት ስለሌለች ተገርሞበታል፡፡
ወደራሱ አስጠግቶ ሲያየው..ከአሰበው የተለየ ጉዳይ ነው፡፡‹‹የምን ሰርግ ነው…ልታጋቢ ነው እንዴ..?ሰርግሽ ላይ እንድገኝ ልትጠሪኝ ነው በዚህ መንገድ በዚህ ሰዓት የተገኘሽው?››

👍67❤7
በተራዋ ፈገግ አለች፡፡‹‹አይ..አይደለም…የጓደኛዬ አዲስአለም እና የወንድምህ የሚካኤል የጋብቻ ስነስርአት በፊታችን እሁድ በአዳማ ይካሄዳል…በዛ ሰርግ ላይ ተገኝተህ ወንድምህን እንድታስደስተውና እንድታስገርመው እፈልጋለው››፡፡
‹‹እና ለዚህ ነው ….ከአዳማ ድረስ መጥተሸ በዚህ ውድቅት ለሊት ክፍሌ የተገኘሽው?››
‹‹አዎ ..አንተን ለማግኘት ያለፉትን ሶስት ቀናት ስመላለስ ነበር..ይሄን ሁሉ የለፋሁት ያንተ ሰርጉ ላይ መገኘት ለወንድምህ ምን ያህል አስደሳች እንደሚሆን ስለማምንበት ነው››
‹‹በእውነት !!በጣም ነው ያስደመምሽኝ..ወንድም የለኝም እንጂ ቢኖረኝና ብገኝ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹ተው እንጂ..እስከማውቀው ድረስ…አንተም ከእሱ በስተቀር እሱም ካንተ በስተቀር ሌላ ዘመድ የላችሁም…ከዚህ በፊት በምንም ሁኔታ ብትጣሉና ብትቀያየሙ ያለፈውን ይቅር ተባብላችሁ ወደፊት መቀጠል አለባችሁ ..ደግሞ ሰርግና ሞት አንድ ነው ይባል የለ….እባክህ!!››
‹‹አዝናለው..ነገርኩሽ ..እውነቴን ነው… እንዳልሽው እኔ ምንም አይነት ዘምድ የለኝም ወንድም ጭምር..ስለዚህ አዝናለው››
‹‹እኔም አዝናለው….በምትዘፍናቸው ዘፈኖች ስለፍቅርና ስለይቅርታ ከደርዘን በላይ ሙዚቃዎችን ተጫውተሀል….ቃላችውን የማይኖሩ ሰዎች ያበሳጩኛል››አለችውና በብስጭት ወደበራፉ መራመድ ጀመረች፡፡
‹‹ይቅርታ ጠብቂኝና የምትሂጂበት ድረስ ሸኝሻለው››
‹‹አይ ይቅርብኝ››አለችና የተቀረቀረውን በራፍ ከፍታ ወጣችና መልሳ ዘግታ በግርምት የሚያዬትን ቦዲ ጋርዶች ገፍትራ ተሰወረች፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍56❤4
🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_20
ዳኛው የሚሰጡትን ውሳኔ ለመስማት ሁሉም ድምጹን አጥፍቶ እያዳመጠ ስለነበር ቤቱ ፀጥ ከማለቱ የተነሳ ውሀ እንኳን ጠብ ቢል መሰማቱ አይቀርም ነበር፡፡ ዳኛው የክርክሩ ጠቅላላ ሂደት እንዴት እንደነበር ካብራሩ በኋላ ይህ ሁሉ ታዛቢ ሰው በጉጉት የሚጠብቀውን የፍርድ ውሳኔ ማሰማት ጀመሩ፤ “አቶ አማረ አስረስ መጋቢት 15 ቀን 1980 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ አዲስ አበባ፣ ሰሜን ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ደብረወርቅ ሆቴል ውስጥ፣ ሰውን ለመግደል አስበውና አቅደው፣ ሟች ወይዘሪት አልማዝ አስፋውን ከእኔ ሌላ ሰው አፍቅረሻል በሚል ምክንያት በቅናት መንፈስ ተገፋፍተው ፍቅረኛቸውን የለምንም ርህራሄ ራሷን እንደገደለች የሚያስመስል ደብዳቤ እንድትፅፍ ካደረጉ በኋላ ገድለው ሰቅለዋታል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ግለሰቡ ይህንን ሁሉ ወንጀል የፈፀሙ ሆነው ሳለ ወንጀሉን አምነው ይቅርታ በመጠየቅ ፋንታ በወንጀላቸው ሳይፀፀቱ ከወንጀሉ ነፃ ነኝ በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ ተከሳሹ ወንጀሉን በቅናት መንፈስ ተነሳስተው መፈፀማቸው በምስክሮችና በማስረጃ ጭምር የተረጋገጠ በመሆኑ፤ ፍርድ ቤቱ ግራና ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ተከሳሹ አቶ አማረ አስረስ ጥፋተኛ ናቸው በማለት ብይን ሰጥቷል፡፡''
ዳኛው የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ አቃቤ ሕግ በተሰጠው የጥፋተኛነት ውሳኔ ላይ የቅጣት አስተያየት ካለው እንዲሰጥ ጋበዙ፡፡ አቃቤ ሕግም የተሰጠውን ዕድል በመጠቀም ምን ያህል ጭካኔ በተሞላው መንገድ ሆን ብዬና ተዘጋጅቼ ግድያውን እንደፈፀምኩ በማብራራት የመጨረሻው ከባድ ቅጣት እንዲበየንብኝ ዳኛውን በሕግ ቃላት ለማሳመን ጥረቱና ትንቅንቁን አጠናከረ፡፡ በተሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ ዕድል የተሰጠው ተረቺው ጠበቃዬ፤ "እኔን ነፃ ለማውጣት ሲከራከር እንዳልነበር ሁሉ አሁን ግን መረታቱን ተቀብሎ፤ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት ወንጀል ሰርቼ እንደማላውቅ በተደጋጋሚ በመጥቀስ የቅጣቱ መጠን እንዲቀልልኝ ተማፀነ፡፡ ዳኛው የቅጣት ማክበጂያና ማቅለያ አስተያቶችን ከሰሙ በኋላ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሚያዚያ 19/1982 ዓ.ም ቀን እንድንቀርብ በማዘዝ አሰናበቱን፡፡ የፍርድ ሂደቱ ይቀጥላል ብዬ ሳስብ እዚሁ ላይ ተጠናቀቀ። ከዚህ በፊት ከስሼም ሆነ ተከስሼ ፍርድ ቤት ቀርቤ ስለማላወቅ የችሎቱ ሂደት የተጠናቀቀበት ሁኔታ ባይገባኝም በአቃቤ ሕግና በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ የማየው የደስታ ሳቅና፣ በኤልሳና በጠበቃዬ ፊት ላይ ያየሁት የመከፋት ስሜት በእርግጠኝነት በእኔ ላይ እንደተፈረደ አመላክቶኛል፡፡ ይሁን እንጂ ፍርዱ የሞት ፍርድ፤ ዕድሜ ይፍታህ፤ ወይም የተወሰነ እስር ዘመን መሆኑን ለይቼ ለመረዳትም ይሁን ለመገመት አለመቻሌ ግራ አጋብቶኛል፡፡ እስር ቤት ተመልሼ እንደገባሁ ግን የጥፋተኝነት ውሳኔ ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሌላ ቀጣይ የፍርድ ሂደት እንዳለ መረዳት ቻልኩ፡፡ እንደእኔ ከሆነ ግን ጥፋተኛ መሆኔ ከታመነበት ጊዜ ሳይፈጁ ፈርደውብኝ ቁርጤን ቢነገግሩኝ ደስተኛ ነበርኩ፡፡ ነገር ግን እንደሚመስለኝ እንዲህ የፍርድ ሂደቱን በማጓተት እስረኛው ምን ይፈረድብኝ ይሆን? ይገድሉኝ ይሆን? ዕድሜ ልክ ይወሰንብኝ ይሆን? ሃያ ዓመት ያስሩኝ ይሆን? ወዘተ.. እያለ ቀን መጨነቁ፣ ሌሊት እንቅልፍ ማጣቱ ከፍርድ በፊት የሚቀጣው ቅጣት ተደርጎ ሳይወሰድ አይቀርም፡፡ የፍርድ ውሳኔ የሚስጥበት ቀን ደርሶ ፍርድ ቤት ቀረብኩ፡፡ ሐሰት በእውነት ላይ የበላይነት አግኝታና የተተበተበው ሴራ ሳይፈታ፣ እጄ ከተያዘበት ዕለት አንስቶ የሃያ ዓመት ጽኑ እስራት ተፈረደብኝ፡፡ ውሳኔውን ስሰማ ጉልበቴ አካላቴን መሸከም እስከሚያቅተው ድረስ መብረክረክ ጀመረ። ንዴትና ፍርሀትም ሰውነቴ ውስጥ ተቀላቅለው በፈጠሩት ትኩሳት የተነሳ መላ ሰውነቴ በላብ ተዘፈቀ፡፡
እንግዲህ እነሆ ያቺ ስጠብቃት የነበረች ውድ ቀን ደርሳ የጠበቅኋት ውሳኔ ባልጠበቅሁት ሁኔታ ተፈረደች:: እኔም ባልሰራሁት ወንጀል ተፈርዶብኝ የታስርኩበት አራት ዓመት ሲቀነስ ለቀጣይ አስራ ስድስት ዓመታት ልታሰር ተወስኖብኛል። እርግጥ ለእኔ ብዙም ለውጥ የለውም። ከአልማዝ ተለይቼ ያሳለፍኳቸው ዓመታት በሙሉ በብረት አጥር ውስጥ ተከልዬ በፖሊስ እየተጠበቅሁና በአንድ ቦታ ተወስኜ አለመኖሬ ካልሆነ በስተቀር ከእሥር የተለዩ ስላልነበሩ ውጪው ዓለም እስከዚህም የሚያጓጓኝና አጥብቄ የምሻው አልነበረም፡፡ ድሮስ ቢሆን ነፃ በመሆኔና እንደልብ በመንቀሳቀሴ መች ተደስቼ አውቃለሁ? ይልቁንም የተሻለ ደስታን ያገኘሁት እሥር ቤት ውስጥ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ውስጤ ይህንን ይቀበለው እንጂ በዓይኔ የማየው ነገር ህሊናዬን እየተፈታተነ ያበሳጨኝ ጀመር። በፖሊስ ታጅቤ ከችሎቱ በመውጣት ላይ ሳለሁ ድንገት ዓይኔን ወደ ኋላ ወርወር አደረግሁ፡፡ ዶ/ር አድማሱ በደስታ እየተፍለቀለቀ አብረውት ከመጡት ጋር ብቻ ሳይሆን አጠገቡ ከቆሙትና ከማያውቃቸው ሰዎችም ጋር እየተቃቀፈ ይሳሳማል፡፡ በእሱ እምነት የፍቅረኛው ገዳይ በሠራው ወንጀል ተገቢውን ቅጣት አግኝቷልና ለምን አይደሰት? ለምንስ አይቦርቅ? ወደ እስር ቤት እንደተመለስኩ እስረኛው ሁሉ የተፈረደብኝን እንደሰማ ክፉኛ አዘነ፡፡ ቀደም ሲል በሌሎች ላይ የሞት ፍርድ ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፍርድ ሲሰጥ እምብዛም የሚያዝን ሰው አልነበረምና ለእኔ ማዘናቸው ገረመኝ:: በተቃራኒው እኔ ከዚህ በፊት የማዝነው እስረኛ ሲፈረድበት ሣይሆን ሲፈታ ነበር፡፡ አለሙና የእሥር ቤቱ ካቦ ሲፈቱ አዝኛለሁ፡፡ ከቤተሰቦቻችን አንድ ሰው ጥሎኝ ወደ ውጪ ሀገር ለዘላለሙ ላይመለስ እንደሄደ ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ከተፈረደብኝ ከአስራ አምስት ቀናት በኋላ ጠበቃዬ አስጠራኝ:: በተፈረደብኝ ፍርድ ተስፋ እንዳልቆርጥ፣ ይግባኝ እንደሚልና እኔን ለማስፈታት የተቻለውን ያህል እንደሚሞክር ቃል ገባልኝ:: ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሳየው ግን ደስ አለኝ፡፡ ምናልባት ሃያ ዓመት እንደተፈረደብኝ ሳውቅ መብረክረኬ አሊያም ጠበቃዬ የሚፈልገውን በማግኘቱ ዳግመኛ አይመጣም ብዬ ገምቼ ስለነበር፣ መምጣቱን እንዳየሁ እውነትም ከልቡ እየተከራከረልኝ ነው ብዬ አስቤ ሊሆን ይችላል፡፡ እርግጥ ፈርቼም ሊሆን ይችላል፡፡ ትንሽ ቆይቼ ይፈቱኛል እንጂ እንዲህ ባልሰራሁት ወንጀል ሀያ ዓመት ይፈረድብኛል ብዬ አስቤ ስላልነበር ውሳኔውን ስሰማ ብፈራ አሊያም ብደናገር የሚደንቅ አልነበረም:: ከዚህ በላይ ደግሞ የመጨረሻው ፍርድ
ሲፈረደብኝ በዶ/ር አድማሱ ፊት ላይ ያየሁትን የደስታ ስሜትና ፈገግታ ላስታውስ መኖርን ፈለግሁ፣ መፈታትንም ተመኘሁ። እስር ቤት ውስጥ እኔና ጠበቃዬ ብቻ በአንዲት ክፍል ውስጥ ፊት ለፊት ተቀምጠን ያንን ሊፈታው ያልቻለውን እንቆቅልሽ መፍታት ላይ እንድረዳው በማሰብ ወደ ኋላ እየተመለሰ ታሪኮቹን በመተረክና በየጣልቃው በዚያው ጉዳይ ላይ ቀደም ሲል የማውቀው ነገር ካለ ይጠይቀኝ ጀመር። ይህም ቢያንስ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችል ነገር ካለ እንዳስታውስ በማሰብ መሆኑ ስለገባኝ በጥንቃቄ እያዳመጥኩ መልስ እሰጠው ነበር።ከምስጠው መልስ ውስጥ የሚጠቅመውን አግኝቶ ይሁን ወይም ለእኔ ትኩረት መስጠቱን ለማሳየት እንደሆነ ባይገባኝም እየመረጠ ከጻፈ በኋላ፤ “አቶ አማረ፤ እንግዲህ ከዚህ በፊትም እንደነገርኩህ የአንድ በሽታ የመጀመሪያው ሀኪም ራሱ በሽተኛው ነው፡፡ መድሀኒቱን ባያውቅ እንኳን የቱ ጋ እንደሚያመው ከሀኪሙ በፊት አስቀድሞ የሚናገረው እሱ ነው:: ከዚያ በኋላ ነው ሀኪሙ እዛ ቦታ ላይ ምርመራውን የሚጀምረውና መድሀኒቱንም የሚያዘው:: ስለዚህ አንተም በበኩልህ በተቻለ መጠን ጠቃሚ ሊሆኑ

👍30❤1👏1
የሚችሉ መረጃዎች ካሉ ለማስታወስ ሞክር፡፡ ማለትም ልትረዳኝ ይገባል“ አለ፡፡ እውነቱን ነው፤ እሱ ያለምንም ክፍያ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ላይና ታች ሲል እኔ ግን ላቀረበልኝ ጥያቄ ብቻ መልስና መረጃ ከመስጠት ውጪ ራሴን ለማዳን ያደረኩት ተጨማሪ ጥረት አልነበረም:: አሁን ሁሉም ነገር ካለቀ በኋላ ደግሞ ላደርገው የምችለው ነገር የለም፡፡ ቢኖርም የፈሰሰ ውሀ ለማፈስ የመሞከር ያህል ሆኖ ተሰማኝ፡፡ እሱ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ ውትወታውን ቀጠለ፡፡ “አቶ አማረ፤ ለሁላችንም እንቆቅልሽ የሆነ ነገር አለ፡፡ ግን ይህንን እንቆቅልሽ መፍታት ያለብህ አንተ ነህ። እኔ በተፈረደው ፍርድ ላይ ይግባኝ ብያለሁ፡፡ ነገር ግን የማቀርበው አዲስ ነገር ስለሌለ በውስጤ ባዶነትና የተሸናፊነት ስሜት ይሰማኛል። ስለዚህ አንድ ከዚህ ቀደም ያልሰማሁትን አዲስ ነገር መስማትና ያላገኘሁትንና ያልደረስኩበትን አዲስ መረጃ ማግኘት እሻለሁ:: ይህ መረጃ ደግሞ ተዳፍኖ ወይም ተደብቆ ይሆናል እንጂ ጠፍቶ ሊቀር አይችልም:: ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያንዣብብኝ እንጂ ከዚህ ድርጊት ጀርባ እውነት ስለመኖሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እውነቱ ደግሞ የጠፋ እስኪመስል ድረስ ተዳፍኗል፡፡ ስለዚህ እኔ ብቻ ሳልሆን አንተም ይህንን ሐቅ በማውጣትና ሐቁን በመፈለግ በኩል ጠንክረህ ልትረዳኝ ይገባል፡፡ አለበለዚያ ይግባኙ ምንም ዓይነት ውጤት አይኖረውም:: በተለይ ዋናው እንቆቅልሽ ያለው አንተና እሷ ልትለያዩ በቻላችሁበት መንስዔ ላይ ነው:: እሷ አንተ ስለከዳሃት እንደተለያያችሁ ስትናገር፣ አንተ ደግሞ እሷ ስለከዳችህ መለያየታችሁን
ገልጸሃል፡፡ ግን ሁለታችሁም ብትሆኑ ለመለያየታችሁ እኔ መንስኤ ነኝ ብላችሁ አልተቀበላችሁም:: ስለዚህ እዚህ አካባቢ የተሰወረው ወይም የተዳፈነው ሐቅ በግልጽ መውጣት አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ አንተ እውነቱን ሳትደብቅ ልትነግረኝ ይገባል፡፡ ሌላው ቢቀር ላልሆነ ነገር እየለፋሁ ከሆነ የእኒ ልፋት ሊያሳዝንህ ይገባል'' አለኝ፡፡ እኔም ባነጋገሩ እጅግ አድርጌ ከውስጤ አዘንኩ:: አሁንም ከብዙ ጊዜ በኋላ እኔ በነገርኩት ነገር አለማመኑን ስረዳም የእሱ ብቻ ሳይሆን የእኔም ልፋት ከንቱ መሆኑን ተረዳሁ:: ስለዚህ ባላመነው ነገር ተከራክሮ ነፃ ያወጣኛል ብዬ መገመት ጅልነት መሆኑንም ተገነዘብኩ:: ግን ምን ማድረግ እችላለሁ? ዕድሌ ሆኖ የምናገረውን የሚያምንም ሆነ ንፁህ መሆኔን የሚቀበል ሰው አላየሁም:: ግን ምን አማራጭ አለ? ወይ እውነቱን ደጋግሞ በመናገር ከተቻለ ማሳመን አለበለዚያ መናገርን ማቆም ነው፡፡ መናገርን ማቆም ማለት ደግሞ ከራሴ በላይ ብዙ የደከመልኝን ጠበቃዬን ጭምር ማስከፋት ነውና ላሳምንበት የምችለው ነገር ካለ ብዬ ማሰላሰሉን ተያያዝኩት:: አእምሮዬ ተንቀሳቀሰ፡፡ ብዙ አወጣሁና አወረድኩ፡፡ ትዝታዎቼን ሁሉ አገላበጥኳቸው፡፡ እሷ የጻፈችው ደብዳቤ ትዝ አለኝ፡፡ ደብዳቤው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኝና ከዚያ ወስዶ እንዲያነበው ስነግረው ልክ ያልጠበቀውን ወሬ የሰማ እስከሚመስል ድረስ ከመቀመጫው ተነስቶ ሳይሰናበተኝ ተጣድፎ ወጣ፡፡ ግራ ተጋባሁ! የሚፈልገውን ነገር በማግኘቱ ተደስቶ ይሁን ወይም _ በአመላለሴ ተበሳጭቶ ይውጣ ግን መለየት አልቻልኩም፡፡ ቢደሰት ኖሮ ቢያንስ ተሰናብቶኝ ይወጣ ነበር፡፡ ምናልባት ከእኔ ብዙ ነገር ሲጠብቅ ቆይቶ እኔ ግን አመላለሴ በአጭሩ ስለነበር የማፌዝ መስሎት ይሆን እንዴ? በማለት ተጠራጠርኩ፡፡ ግን ብዙም አልተጨነቅሁ፡፡ በማይሆን አጉል ተስፋ ተሞልቼ ነፃ እወጣለሁ ብዬ ከማሰብ ይልቅ እውነቱን ተቀብዬ ቀሪ ሕይወቴን እንደምኖር ኖሬ ማሳለፉ ሳይሻል አይቀርም ብዬ ራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ፡፡ ወደ ክፍሌ እንደተመለስኩም በይግባኙ ላይ ተስፋ ቆርጬ የእሥር ዘመኔን መደመርና መቀነስ ጀመርኩ፡፡ አሁን ዕድሜዬ ሰላሳ ሁለት ዓመት ነው፡፡ እዚህ ላይ የታሰርኩበትና የአመክሮ ጊዜ ተቀንሶ ቀሪው አስራ ስድስት ዓመት ሲደመር እሥሬን ስጨርስ አርባ ስምንት ዓመት ይሆነኛል ማለት ነው:: ስለሆነም ከእስራት ስፈታ ቢያንስ ያንን ዶክተር ለመበቀል የሚያስችል በቂ የአካል ብቃት ይኖረኛል ማለት ነው:: ዳሩ ይህንን ማሰቤ ጅልነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ለምን ቢሉ ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነውና በጡንቻ መመካት ድሮ ቀርቷል፡፡ ዛሬ አንዲት ትንሽ ጣት ቃታ ከሳበች ተራራ የሚያክል ሰው ትገነድሳለች::ለዚያች የምትበቃ ጉልበት ደግሞ የሰማንያ ዓመት አዛውንትም ቢሆን አያጡም:: ዋናው ነገር ከአምላክ የተጻፈችልኝ ዕድሜ ከአርባ ስምንት
ዓመት በላይ መሆኗን ማረጋገጥ አለመቻሌ ነው:: ይህንን ደግሞ ማረጋገጥ ስለማይቻል፣ እንዲሆን ከመመኘት ውጪ ሊደረግ የሚችል ነገር ባለመኖሩ አማራጩ እውነታውን ተቀብዬ የተለመደ ኑሮዬን መቀጠል ነው:: ያ ካልሆነ ደግሞ የልቤ ሳይደርስ የተዛባ ፍትሕ ስለባ ሆኜ መቅረቴ የማይቀር ነው:: አንድ ሰኞ ዕለት ስሜ ተጠርቶ ወጣሁ:: ጠበቃዬ ተመልሶ መጥቶ ወይም እጮኛው ያስጠራችኝ መስሎኝ ነበር:: ነገር ግን ሌሎች እስረኞችም እየተጠሩ ሲወጡና እንደተለመደው እጃችን የፊጢኝ እየታሰረ ወደ እስረኛ ማጓጓዢያ መኪና ስንገባ ግራ ተጋባሁ፡፡ ወዴት እንደምንሄድ አጠገቤ የነበረውን እስረኛ ጠየቅሁት:: እስረኛው የሚሄድበትን ቦታ በእርግጠኝነት እንደሚያውቀውና የተማከረ በሚመስል ሁኔታ፤ ''ወዴት ይወስዱናል? ይግባኝ ተብሎልህ ከሆነ ያው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነዋ የሚወስዱህ" አለኝ፡፡ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግቢ በመግባት ላይ ላለሁ ኤልሳና ጠበቃዬ ፈንጠር ብለው ቆመው ሰላምታ ሰጡኝ፡፡ አንድ ነገር ገባኝ፡፡ የመጣሁት ጠበቃዬ ይግባኝ ብሎ መሆኑ ላይ እርግጠኛ ሆንኩ:: ይግባኙ አዲስ ነገር የሚፈጥር ባይሆንም በተስፋ መኖርም ጥሩ በመሆኑ ይግባኝ በመጠየቁ ደስ አለኝ፡፡ ምን ይታወቃል ጠበቃዬ እንደጠረጠርኩት ሳይሆን ከልቡ እየደከመልኝ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ ተጠራጠርኩት እንጂ ያኔ የተፈረደብኝ ዕለት ከፊቱ ላይ የመከፋት እንጂ የተደበቀ የደስታ ስሜት አላየሁበትም ነበር፡፡ ስለዚህ ይህንኑ ተቀብሎ በተስፋ መኖር ተስፋ ከማጣት የተሻለ ነውና እውነቱን ተቀብዬ አብሬው ለመጓዝ ወሰንኩ፡፡ አብረውኝ የመጡ እስረኞች በየተራ ወደ ችሎት እየተጠሩ ደርሰው ይመለሳሉ:: አብዛኞቹ እንደ እኔ ይግባኝ ያሉ ናቸው፡፡ ተራዬ ደርሶ እዚያቹ አለመድኳት ሳጥን ውስጥ ገባሁ:: ጠበቃዬ ከፊት ለፊት ተቀምጦ በፈገግታ ይመለከተኛል፡፡ ተስፋ አትቁረጥ ተስፋ አለን የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የሚሞክር መሰለኝ፤ አዘንኩለት፡፡ እኔ በሌላ ሁኔታ ብጠረጥረውም እሱ ግን አልተወኝም:: ፈገግታው ከልብ የመነጨ ስለነበር በውስጤ የተስፋ ጭላንጭል ጫረብኝ: ፍርድ ቤቱ እንደተለመደው በሰዎች ተሞልቷል:: ዛሬ ግን እነዚያ የመስሪያ ቤት ባልደረቦቼ አልተገኙም፡፡ እንደድሮው እስር ቤት እየመጡም
መጠየቁን ትተውታል:: የእኔ ነገር ማክተሙን ስለተረዱ ያላግባብ መድከም አልፈለጉም :: ከሃያ ዓመት በኋላ ለሚፈታ እስረኛ ማን መድከም ይፈልጋል የፍ/ቤቱና የይግባኝ ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሠረት የኔን ጉዳይ የያዘው ፋይል ተራ እንደደረስ የዕለቱ የችሎት ማብቂያ ሰዓት በመድረሱ ዳኛው ቀጠሮ ለመስጠት አጀንዳቸውን ሲያገላብጡ፣ ጠበቃዬ ነቃና ላቅ ባለ የትሕትና ስሜት፤ “ክቡር ፍ/ቤት፣ ምንም እንኳን አሁን ማስረጃ የማቅረቢያ ወቅት ባይሆንም ተከሳሹ ወንጀሉን አለመፈፀሙን ማረጋገጥ የሚያስችል ማስረጃ እጄ ውስጥ ገብቷል:: በመሆኑም ፍ/ቤቱ ያላግባብ ደንበኛዬ ባልሰራው ወንጀል ሃያ ዓመት እንዳይታሰርና ጉዳዩም በተጓተተ ቁጥር እውነቱ ተደብቆና ተድበስብሶ እንዳይቀር ሲባል መረጃዎቼንና የማቀርበውን ተጨማሪ የሰው ማስረጃ

👍36🥰2🔥1
እንዳቀርብ እንዲፈቅድልኝ በትህትና እጠይቃለሁ" አለ፡፡ ዳኛው ሰዓታቸውን አይተው ይግባኙን እንዲያቀርብ ሲፈቅዱ፣ አቃቤ ሕግ ከመቀመጪያው ተነስቶ፤ “ተቃውሞ አለኝ፣ እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ" አለ:: ዳኛው ተቃውሞውን እንዲያቀርብ ዕድል ሰጡት:: እሱም ቀጠል አድርጎ፤ “ይህ የይግባኝ ሥርዓት እንጂ ማስረጃ የሚታይበት ወቅት ባለመሆኑ ክቡር ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን እንዳይቀበለው እጠይቃለሁ'' አለ፡፡ ዳኞቹ እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩና ከጠበቃዬ የቀረበውን ሰነድ በሥነ- ሥርዓት አስጠባቂ በኩል ተቀበሉ፡፡ ጠበቃዬ ምን አዲስ መረጃ እንዳገኘ ባላውቅም ለእኔ ከድካም ውጪ ሊያስገኘው የሚችል ፋይዳ አልታይህ አለኝ:: ጠቃሚ መረጃ ብሎ ሊያቀርበው የሚችለው ባለፈው መጥቶ በነበረ ጊዜ ከፖሊስ ጣቢያ እንዲወስድ የነገርኩት ደብዳቤ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ ቀደም ሲል የታወቀና በኤግዚቢትነት የተያዘ ስለነበር አዲስ ነው ከተባለ ለእሱ እንጂ ለሌላው አዲስ አልነበረም:: በሌላ በኩል ደግሞ እኔን ነፃ የሚያወጣ የሰው ማስረጃ ተገኘ ከተባለም መሆን ያለበት የገደልኳት እኔ ነኝ የሚል ሰው ከተገኘ ብቻ ነው:: እንዲህ ዓይነት ሰውም ከተገኘ እጅግ በጣም መንፈሳዊ አለበለዚያም ቂል ካልሆነ በስተቀር እሱ የሰራው ወንጀል በተሳካ ሁኔታ ተደብቆለትና ለእሱም ጥፋት ለሀያ ዓመታት የሚታሰርለት እስረኛ ተገኝቶ እያለ እኔ ነኝ ገዳይዋ ብሎ ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል ብሎ የመጠበቅ ያህል ነው:: በመሆኑም ለደስታም ሆነ ለሐዘን አንዳችም ቦታ አልነበረኝም፡፡ ይልቅ የጓጓሁት ዳኞቹ የሚወስኑትን ውሳኔ ለመስማት ነበር።
ጠበቃዬ ያቀረበው ማስረጃ በአባዲና ፖሊስ የምርመራ ክፍል ተመርምሮ ውጤቱ ለመስከረም 5 ቀን 1983 ዓ.ም እንዲቀርብ ወስነው ችሎቱን ተነሳ:: እኔም ክችሎቱ ወጥቼ ወደ እስር ቤቱ መኪና እያመራሁ ላለ ጠበቃዬና ኤልሳ ወደ እኔ እያዩ፤ በእነሱ እይታ በቲ ማስረጃ ስላገኙ ነፃ እንደሚያወጡኝ እርግጠኛ መሆናቸውን በፈገግታ መልዕክት ገለፁልኝ:: በሰማሁት እና ባየሁት ነገር ብዙም ባልደስትም በውስጤ ተስፋ ሰንቂ ወደ እሥር ቤቴ አመራሁ:: ወህኒ ቤት እንደገባሁ ውሎ እንዴት ነበር እያሉ እስረኞች ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ የሆነውን ነገር ሁሉ አንድም ሳላስቀር ነገርኳቸው:: መቼም እስረኛ ሲባል ሌላ "የሕግ ባለሙያ'' ማለት ነው:: እያንዳንዱ አስረኛ እንዴት ራሱን መከላከል፤ የቱን መካድና የቱን ማመን እንዳለበት የሚያማክሩ የእሥር ቤት የሕግ ምሁራን እዚያው ሞልተዋል፡፡ እነዚህ ምሁራን ታዲያ በእኔ ጉዳይ ላይ ባልጠቀምበትም ቀደም ሲል እንዴት መካድ እንዳለብኝ አስረግጠው አስረድተውኛል:: መቼም አውጥተው አይናገሩት እንጂ አንዳቸውም በመግደሌ ላይ ጥርጣሬ አልነበራቸውም:: በዚህም የተነሳ ይመስላል እየደጋገሙ እዚህ እውነት ብትናገር ችግር የለውም፤ ዋናው ነገር ፍርድ ቤት ሲሆን ነው መጠንቀቅ ያለብህ፡፡ ይልቁን ገድለሀት ከሆነ አገዳደልህን በደንብ ብታስረዳን እንዴት ራስህን መከላከል እንዳለብህ ስለምናማክርህ እዚህ መናገርህ ጥቅም እንጂ ጉዳት የለውም" እያሉ "እውነቱን" እንዳወጣ ይጨቀጭቁኝ ነበር። ዛሬም እንደተለመደው በእኔ ጉዳይ ላይ በራሳቸው የሕግ ትንተና ላይ የተመሰረተ መላ ምት መስጠት ጀመሩ፡፡ “እኔ እንደሚመስለኝ፣ አማረ እንዳለው ንፁህ ከሆነ ሊሆን የሚችለው ቀደም ሲል ያልተገኘ የገዳዩን አሻራ ፖሊስ አግኝቷል ማለት ነው" ሲል፡፡ ሌላው የሕግ ምሁር ቀበል አድርጎ፤ “እንዴት ሊሆን ይችላል? ፖሊስ ቀደም ሲል ያላገኘውን አሻራ እንዴት አሁን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ ሊያገኝ ይችላል? አሻራው በሩ ላይ ይኸን ያህል ጊዜ ተለጥፎና ተደብቆ ቆይቶ አሁን ተገኝቶ ይሆናል ልትለን እንዳይሆን?' አለ፡፡ አጅሬ እንዲህ በቀላሉ መረታት ስላልነበረበት፣ “እንዲህ ዓይነት ፍሬከርስኪ ወሬ እያወራሁ አይደለም፡፡ እኔ ማለት የፈለኩት፤ አሻራው በፊት ተገኝቶ ሊሆን ይቻላል፡፡ ግን አሻራው የማን እንደሆነ ሳይታወቅ ቆይቶ አሁን ግን አሻራው የማን እንደሆነ ታውቆ ቢሆንስ? ለዚህም ይመስለኛል እንደገና የአባዲና ምርመራ የተፈለገው'' በማለት መለስ። ሌላኛው "ምሁር" ትራሱን ደገፍ እንዳለ ድምፁን የምሁር ለማስመሰል እያንዳንዷን ፊደል እየቆጠረና በመሀል እ... እ... የሚለውን ድምጽ እየደጋገመ
“እኔ እንደሚመስለኝ እ... እ... ጠበቃው አለኝ ያለው የሰነድና የሰው ማስረጃ እስከሆነ ድረስ እ... እ... አንድ ወንጀሉ ሲፈፀም PP ግለሰብ የአማረ ያላግባብ ተፈርዶበት ወህኒ መውረድ አሳዝኖት ወንጀሉን ማን እንደፈፀመ ማየቱን ገልዖ የፃፈው ደብዳቤ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል፡፡ እ... እ... ደግሞም አቀርበዋለሁ ያለው ማስረጃ ይኼው ግለሰብ የሚሰጠው የምስክርነት ቃል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ ግለሰብ ምናልባት እንደሚመስለኝ ሆቴል ውስጥ ያለ አስተናጋጅ ወይም ዘበኛ ሊሆንና ገዳዩ ገድሎ ሲወጣ አይቶ ሊሆን ይችላል":: ሌላኛው የቀረበውን የሕግ መከራከሪያ ነጥብ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችለውን ሐሳብ ለማፍለቅ ጣራ ጣራ ሲያይ ቆይቶ፤ “ግን እኮ ይኼ ሊሆን አይችልም ባይባልም፣ በፊት መጥቶ ለአማረ ያልመሰከረ ዘበኛ ወይም አስተናጋጅ አሁን እንዴትና ከየት ሊመጣ ይችላል?" በማለት ቢያንስ በጥያቄ መልክ በቀረበው አስተያየት ክርክሩን መሠረት ለማሳጣት ሲሞክር፣ ሌላው ምሁር ቀበል አድርጎ፣ “ይህማ ሊሆን የሚችለው መጀመሪያ ላይ ፈርቶ ቆይቶ በኋላ ግን አላግባብ የአጅሬ መታሰር እረፍት ነስቶትና ተፀፅቶ እ... እ... ወይም ጠበቃው ሁኔታውን ደርሶበት እንዲመሰክር ወይ አግባብቶት አሊያም አስፈራርቶት ሊሆን ይችላል"፡፡ ይኼንን የክርክር ነጥብ ውድቅ ለማድረግ የሚያስችል የመርቻ ሐሳብ የመጣለት ሌላኛው ምሁር፤ “እንዴ! ያበደ ካልሆነ በስተቀር እንዲህማ አያደርግም! ወንጀል ሲፈፀም አይቶ ዝም ማለት በራሱ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እስከአሁን ዝም ብሎ ኖሮ አሁን ሊተነፍስ ቢሞክር ራሱን በገመዱ ማስገባቱ ነው፡፡ ይህንን ያህል ጊዜ ሳይናገሩ መቆየትም በሕግ ያስጠይቃል" ሲል ንግግሩን ቋጨ ፤ “መመስከርማ አለበት እ... እ... እንዲያውም ወንጀል የሚሆነው ከነጭራሹ ደብቆ የኋላ ኋላ የታወቀ እንደሆን ነው:: አሁን ባድራጎቱ ተፀፅቶ በራሱ ተነሳሽነት እውነቱን የሚመሰክር ከሆነማ በሕግ የሚጠየቅ አይመስለኝም' ሲል፤ ሌላው እስካሁን ሳይናገር ክርክሩን ሲያዳምጥ የነበረ እስረኛ፣ “በሕግ መጠየቅማ አለበት፡፡ እስኪ አስቡት፤ እሱ ቀደም ሲል መስክሮ ቢሆን ኖሮ ወንድማችን ይህንን ያህል ጊዜ ባልታሰረና ሊጠግን የማይችል የህሊና ስብራት ባልደረሰበት ነበር፡፡ ስለዚህ ለዚህም በደሉ በሕግ መጠየቁማ
የማይቀር ነው" በማለት በቁጣ የፍርድ ውሳኔ አስተላለፈ:: በመጨረሻም ምሁሩ የማሳረጊያ በሚመስል መልኩ፤ “እ... እ... ምንም ይሁን ምን፤ ጠበቃው የታወቀ ጠበቃ እንደመሆኑ መጠን እንደዚህ እርግጠኛ ሆኖ ማስረጃ ላቅርብ ያለው አንድ ሊረታበት የሚችልበት መረጃ አግኝቶ እንጂ እንዲያው ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ ሊሆን አይችልም፡፡ እ... እ...

👍28❤2👎1🔥1
ደግሞም መረጃው ፋይዳ ቢስ ቢሆን ኖሮ ዳኞቹም ቢሆን በዚህ ወቅት የአሠራር ሥርዓት ስለማይፈቅድ የሚያሳምን ነገር ባያገኙ ኖሮ መረጃውን ተቀብለው ለምርመራ ባልላኩት ነበር። እንደዚህ ከሆነ ደግሞ የአጅሬ ሃያ ዓመት ፍርድ ወደ ሃያ ቀን መለወጡ ነው ማለት ነው" በማለት ውይይቱን ደመደመ:: ከዚህ የተሻለ የመከራከሪያ ነጥብም ሆነ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበ ስላልነበር ክርክሩ በዚሁ ተቋጨ፡፡ ክርክሩ ለእኔ የሚፈይደው ነገር ባይኖርም፣ ቢያንስ ሁሉም የእኔን ንፁህነት ተቀብለው በመከራከራቸው ደስታ ተሰማኝ፡፡ እራሴ የፈጠርኩት ስሜት እንጂ ለካስ በእኔ ንፁህነት የሚያምን ብዙ ሰው ነበር ማለት ነው በማለት በራሴ መፅናናትም ጀመርኩ፡፡ ከሁሉም በላይ የገረመኝ ግን፣ ፍርድ ቤት ቆሜ ጠበቃዬ ሲከራከር፣ ፈገግ ሲልና አይዞህ ተስፋ አለን እያለ ሲያፅናናኝ ምንም ተስፋ አልታይህ እንዳላለኝ ሁሉ እዚህ ግን ምሁራኑ የተለያየ የመከራከሪያ ነጥቦችን እያነሱ ከተወያዩ በኋላ የደረሱበትን መደምደሚያ ስሰማ እውነት የሆነ ያህል ተስፋ በሰውነቴ ውስጥ ተጫረ። በዚህም የተነሳ የቀጠሮ ቀኑ ደርሶ እውነቱን ማወቅና የሚቀርበው ማስረጃም ምን እንደሆነ ለመስማትና ለማየት ጓጓሁ።
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍25
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ዘሚካኤል ተገትሮ በቆመበት የክፍሉ መሀከላዊ ስፍራ እንደደነዘዘ ነው፡፡ልጅቱ አስር ለማይሞሉ ደቂቃዎች ብቻ አብራው ብታሳልፍም….ግን ደግሞ ለቀናት ያህል ያቀፋትና ለሳዕታት ሲስማት የቆየ አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው…‹‹.ለምን ጉዳይ መጣች ምን ሰርታ ሄደች?››ብሎ ሲያስብ ሳይወድ ፈገግ አለ…ከቆመበት ተንቀሳቀሰና እጁ ላይ ያለውን የሰርግ የጥሪ ካርድ የያዘውን ፖስታ በራፉ አጠገብ በሚገኘው ቆሻሻ ማጠረቀሚያ ቅርጫት ውስጥ ጨምድዶ ወረወረው፡፡
ለዛች ስሟን እንኳን ላልነገረችው ሴት ልጅ እንደነገራት በዚህ አለም ምንም አይነት ወንድም ሆነ ቤተሰብ አያስፈልገውም እና ወደ የትኛውም ሰርግ የመሄድ ፍላጎት የለውም። እንደውም ከተቻለው ስለቤተሰብ በውስጡ የቀረውን እንጥፍጣፊ ትዝታ ከልቡ አሟጦ መሰረዝ ነው ፍላጎቱ፡፡
ከወገብ በላይ ራቁቱን መሆኑን ትዝ ሲለው ወደጠረጴዛው ሄደና ያወለቀውን ልብስ መልሶ ለበሰው..መጀመሪያ እቅዱ ቀጣይ የሙዚቃ ማቅረቢያ ሰዓቱ እስኪደርስ ድረስ ሻወር ገብቶ ከተለቃለቀ በኃላ 30 ወይም 40 ደቂቃ መተኛትና እረፍት መውሰድ ነበር፡፡አሁን ግን ሻወር የመውሰድም ሆነ የመተኛት ፍላጎቱ ከውስጡ በኖ ጠፍቷል…ቀጥታ ሶፋው ላይ ሄደና ተቀመጠ፡፡ፊትለፊት ካለው ጠረጴዛ ላይ ያለውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳና ከፍቶ በብርጭቆ ቀድቶ እየተጎነጨ ማሰላሰል ጀመረ….
‹‹ይህቺ ልጅ ምኑን ነክታ እንዴት ስሜቱን ድፍርስርስ አድርጋ እንደሄደች አያውቅም…ወንድሙ ላይ የያዘበት ቂምና የተበሳጨበት ብስጭት አሁንም ትኩስ ነው፡፡
‹‹ግን የዛን ጊዜ ፈቅዶልኝ አባቴን በዛ ቢላዋ ጨቅጭቄ ብገድለው ኖሮስ…?››ሁል ጊዜ እራሱን የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፡፡
አዎ ወንድሙ በድብድብ እና በትግል ባያስቆመው ኖሮ እሱም ይሄን ጊዜ የእድሜ ልክ ፍርድ ተፈርዶበት በአባቱ ምትክ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎበት ተስፋ የሌለው ህይወት ይኖር እንደነበረ…እርግጠኛ ነው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ ሚካኤል ወንድምህ የእድሜ ልክ ባለውለታህ እንጂ ጠላትህ አይደለም?››አለው አእምሮው፡፡
‹‹ለምን..ያማ እውነት አይደለም….እሱ እኮ እንደዛ ያደረገው እኔን ከመከራ ለማትረፍ አስቦ ሳይሆን ለዛ ጨካኝ እና ገዳይ አባቱ ለማገዝ ፈልጎ ነው››
‹‹አይ እሱ የአንተ አእምሮ አንሻፎ የተረጎመው ትርጉም ነው…እንደዛም ቢሆን እንኳን በዛ ታሪክ ውስጥ ዋናው ተጠቃሚ አንተ ነህ፡፡በወቅቱ ዝም ብሎህ ያሰብከውን እንድታደርግ ቢፈቅድልህ ኖሮ ዛሬ በዚህ ጊዜ ዝነኛው ድምፃዊና ተዋናዩ ዘሚካኤል የለም ነበር…ሀመር መኪና የሚነዳው…የተንጣለለ ውድና ውብ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖረው…ከአደባባይ እስከቤተመንግስት የሚታወቀውና የሚጋበዘው የመገናኛ ብዙሀኖች የዜና ማጣፈጫ የሆነው ዘሚካኤል አይኖርም ነበር፡፡››ሲል እራሱን በራሱ በዝርዝር አስረዳ፡፡
የአእምሮው የእርስ በርስ ጭቅጭቅ ከዚህ በላይ ማስቀጠል አልቻለም..ምክንያቱም በንዴትና በቁጭት አእምሮው ብቻ ሳይሆን መላ ሰውነቱ እየጋለበት ነው፡፡ጠረጴዛው ላይ ያለውን ብርጭቆ አነሳና ጠቀም አድርጎ ተጎነጨለት እና መልሶ አስቀመጠው፡፡
ከዛ ስለሌላ ነገር ለማሰብ ሞከረ ..ግን አሁንም አእምሮውን የሞላችው ያቺ ከደቂቃዎች በፊት ከሰውነቱ ለጥፎ ያቀፋትና ለሁለት ሰከንድ ሲስማት የነበረችው ሴት ነች፡፡‹‹ቆይ ይህቺ ልጅ ምን የተለየ ነገር ቢኖራት ነው ከአእምሮዬ ልትወጣ ያልቻለችው ?››እራሱን ጠየቀ…‹‹ከንፈሯ ላይ አስማት አለ መሰለኝ…››አለና ፈገግ አለ….‹‹ምን አለ ስሟን እና የሞባይል ቁጥሯን ብጠይቃት ኖሮ…?››በጣም ተቆጨ፡፡
ደግሞ እሷም እሱን በምንም አይነት ሁኔታ ደግማ የማግኘት ፍላጎት እንደሌላት በሚያሳይ ሁኔታ ነው የመጣችበትን ጉዳይ ተናግራ የጥሪ ካርድን እጁ ላይ አስቀምጣ ነው ውልቅ ብላ የሄደችው፡፡
‹‹ባለትዳር ትሆን እንዴ?››የሚል ሀሳብ በአእምሮ ብልጭ አለበት፡፡
ሀሳብን መቋጫ ሳያበጅለት በራፉ በስሱ ተቆረቆረ…ብርጭቆ ውስጥ የቀረችውን ውስኪ ጨለጠና ሶፋውን ለቆ ወደበራፉ ሄደ ..ቀጣይ ዝግጅቱን የሚያቀርብበት ጊዜ መድረሱን ለማሳወቅ በራፉን እንደቆረቆሩ ያውቀል..በራፉን ከፍቶ ሲወጣ ንቁ ሆነው የሚጠብቁት ሁለት ወጠምሻ ጋርዶች ከግራና ከቀኝ ከበቡት፡፡ ሁለት እርምጃ ከተራመደ በኃላ የሆነ ነገር ወደኃላ ሳበው…መልሶ ፊቱን ዞረና ወደክፍሉ ተመለሰ….ከውስጥ በኩል ከበራፉ በስተቀኝ ወዳለው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ባስኬት አጎነበሰና አጣጥፎ የጣለውን የሰርግ ጥሪ ወረቀት አነሳ ፡፡የሱሪ ኋላ ኪስ ውስጥ ጨመረውና መልሶ ወጣ..ለምን እንዲህ እንዳደረገ ቢጠየቅ ምንም አይነት መልስ የለውም …እንዲሁ በደመነፍስ ያደረገው ነገር ነው፡፡
////
አሁን የዘሚካኤል ምስል ከሙሉ አቋሙ ጋር በአእምሯዋ እየተራወጠ ነው፡፡ሁለቱ ወንድማማቾች ከቁመትና ከፀባይ ውጭ በሌላው ነገር በሚያስደንቅ ሁኔታ ይመሳሰላሉ። የሚካኤል ባህሪያት ከዘሚካኤል ትንሽ ደብዘዝ ያሉ ነበሩ እና የዓይኑ ቀለም ንፁህ ፣ ጠንከር ያለ ሰማያዊ ነበረ ፣ ግን ሁለቱም ሰዎች ተመሳሳይ ውብ ፈገግታ፣ ክብ የፊት ቅርፅ እና ሰልካካ አፍንጫ.. ወተት ከመሰሉ ነጫጭ ድርድር ጥርሶች ጋር አላቸው፤››
እየሾፈረች ያለችውን ቪታራ መኪና ኤክስፐረስ መንገድ ውስጥ አስገብታ ወደ አዳማ እያሽከረከረች ሲሆን አሁንም ስለዛ ዘ-ሚካኤል ስለሚባለው ድምጻዊ ነው የምታሰላስለው፡፡ለሊት 8 ሰዓት ላይ ከእሱ ተለይታ እዛው በአቅራቢያው ወደተከራየችው ፕንሲዬን ሄዳ ለመተኛት ብትሞክርም ምንም እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር እንዲሁ ስትበሳጭና ስትገላበጥ ነው ያደረችው፡፡
ስለእሱ ማሰብ የጀመረችው ቀደም ብላ ታሪኩን ከየጋዜጦችና ከዪቲዩብ ቻናሎች እየሰበሰበች በምታዳምጥበት ጊዜ ነው፡፡እርግጥ ታውቀለች በዩቲዩቭ የቀረበ ዜና ሁሉ በተለይ ስለፍቅርና ፃታዊ ግንኙነት የሚነዙት አብዛኞቹ ተመልካች ለማግኘት የታስቡ…በውሸት የሚፈበረኩ እንደሚሆን ታምናለች..ግን ቢሆንም‹‹ እሳት በሌለበት ጭስ አይጨስም….››በማለት ለሰው ስሜት የማይጨነቅ ጋጠወጥ ወሲባም አድርጋ ስላው ነበር፡፡እና ደግሞ ለሊት እንዳየችው አልተሳሳተችም…በዛ ለሊት እዛ ክፍል ውስጥ ሲያገኛት መጀመሪያ ያደረገው ወደራሱ ስቦ ከንፈሯ ላይ መጣበቅ ነው…..ስለዛች ቅፅበት ስታስብ ከንፈሯ ተንቀጠቀጠባት….የሚያበሳጨው ደግሞ ለማንም ሴት ግርማ ሞገሱንና ውበቱን ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆነ ሰው መሆኑን በራሷ ማረጋገጧ ነው…ባለፉት ስድስት አመታት በጣም ብዙ ከሆኑ ወንዶች በብዙ የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈታተኗት ሞክረው ሾልካና አሳስቃ ..አንዳንዱንም ተኮሳትራና አስፈራርታ እራሷን ማትረፍ ችላለች..ከእሱ ጋር ግን በአንድ እይታ ነው ተዝለፍልፋ እቅፉ ውስጥ የወደቀችው፡፡
እንደምንም ከእቅፉ ወጥታ ለማምለጥ ወደበራፉ በምትራመድበት ጊዜ እንኳን ተንደርድሮ መጥቶ እጇን ይዞ ጎትቶ እንዲያስቀራት እና ተሸክሞ ሶፋው ላይ እንዲጥላት በውስጧ እየተመኘች ነበር፡፡ግን በተመሳሳይ ጊዜ እንደዛ በመመኘቷ እራሷን ስትወቅስና ስትራገም ነበር፡፡

👍61❤6👏1
ባይሰማትም ‹‹ዘሚካኤል አንተ እብሪተኛ እና ጅላጅ ሰው ነህ›› ስትል ተሳደበች፡፡ነገር ግን ነገሩን በጥልቀት ስትመረምረው እሱ ብቻ ጥፋተኛ አልነበረም። እሷም ለተፈፀመው ጥፋት ትልቅ ድርሻ መውሰድ አለባት።
እንዴት እንዲህ ያለ ቸልተኛ እና ኃላፊነት የጎደላት ሴት ልትሆን ቻለች? እንዴት እንዲህ አይነት ውጥንቅጥ ነገር ልትሰራ ቻለች?በራሷ ተግባር በዚህ ልክ ስትበሳጭ ይሄ የመጀመሪያዋ ነው፡፡
ዘሚካኤል አጥብቆ ና ጨምቆ የያዛት ክንዷን አሻሸች… በትክክል እንዴት እንደሆነ ታውቃለች። ልክ እሷን እንዳየ ፣ ከንፈሯን እንደነካ ፣ ጠቅላላ ሰውነቷ ያልተበረዘ የደስታ መጥለቅለቅ ነው ያስተናገደው።
አዳማ እንደገባች ቀጥታ ከአዲስ አለም ጋር ነው ተገናኘችው፡፡እና ሆነችውንና ያጋጠማትን አንድ በአንድ በዝርዝር አስረዳቻት፡አዲስ አለምም አፏን ከፍታ በጉጉት ስታዳምጣት ከቆየች በኃላ
‹‹ታዲያ ምን ያበሳጭሻል …እንደውም በራስሽ መኩራት ነው ያለብሽ››
‹‹ማለት?››
‹‹ቀሽት የሆነ ዜና ነው እኮ እየነገርሺኝ ያለሽው …ወይ ጉድ ››
‹‹ድንገት እኮ ነው የሆነው …ክፍሉ ውስጥ ተደብቄ ገባሁ….›› ትንፋሽ ወሰደች።‹‹አውቃለሁ ግድየለሽ እና ኃላፊነት የጎደለው ነገር ነው ያደረኩት››
አዲስ አለም‹‹ አንቺ የሆነ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ገብተሸ …እኔ አላንም›› ብላ ሳቀች።
‹‹ይህ ደደብ በሰርጉ ላይ እንዲመጣ ላሳምነው ሀሳብ ነበረኝ …እችላለሁ የሚል እምነት ነበረኝ። ››እጆቿን በጭኖቾ መካከል አድርጋ እርስ በርሳቸው ማፋተግ ጀመረ‹‹እርግጥ ..አንቺ እና ሚካኤል እሱን ምን ያህል እንደምትፈልጉት አውቃለሁ..ያደረኩትን ሁሉ ያደረኩት እናንተን ለማስደሰት ካለኝ ምኞት የተነሳ ነው። ››
‹‹እና መጨረሻው እዴት ሆነ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን መጨረሻ አለው..እንደምንም ወደቀልቤ ተመልሼ ራሴን ነፃ አወጣሁና የመጣሁበትን ጉዳይ እስረድቼው ካርዱን ሰጠሁትና ክፍሉን ለቅቄት ወጣው፡፡››ስትል መጨረሻውን ነገረቻት
‹‹ቆይ…. እዚሁ አብረሺኝ እደሪ ምናምና አላለሽም››
‹‹እንዴት እንደዛ ይለኛል..?ትንሽ ጠብቂኝና የምትሄጅበት ድረስ ልውሰድሽ ብሎኝ ነበር..እኔ ግን ከእሱ መሸሽና እሰከወዲያኛው መገላለል ነበር የፈለኩት፡፡››
‹‹እንዴት ነው አሳሳሙ..ቅልጥ ነው አይደል የሚያደርገው?››ጥያቄው የመጎምዠት ስሜት የተጫነው ነው፡፡
‹‹ሴትዬ በቃሽ …ለራሴ በጣም ተናድጄለው ይበልጥ አታናጂኝ››ፀአዳ ተቆጣች፡፡
‹‹ይገባኛል የእኔ ቆንጆ ..ምንም የሚያፀፅት ነገር እኳ አላደረግሽም…መልከ መልካም ና ቆንጆ የሆነውን ሙዚቀኛና ተዋናይ በቀላሉ አግኝተሸ ሳምሽው ..ስለዚህ ያ ድንቅ ነገር ነው..እንደውም ሚያሸልምሽ ጉዳይ ነው።››
‹‹ዝም በይ ባክሽ?›› ፀአዳ ለጓደኛዋ ትችት ወጥመድ ውስጥ እንደገባች ተረዳች፡፡
‹‹ግን ምን አይነት ስሜት እንደተሰማሽ ማወቅ አፈልጋለው።ብቻ ንገሪኝ እስኪ እሱ በፊልሞቹ ላይ እንደሚታየው በሥጋው ውስጥ ሞቃት ሆርሞን የሚራወጥበት አቅልጥ ወንድ ነው?››
‹‹አንቺ ባለትዳር እኮ ነሽ…እንደዚያ ማለት አትችይም። በተግባር ያገባሽ ሴት ነሽ..ለዛውም ወንድሙን ያገባሽ።ስትቁላይ ላየሽ ግን አትመስይም››እንደዚህ ጠንከር ያለ ነገር ተናግራት አፏን ልታዘጋት ፈልጋ በስሌት የሰነዘረችው ዓ.ነገር ነው፡፡
‹‹ምን አጠፋው….አገባሁ እንጂ ሴትነቴን አውጥቼ እኮ አልጣልኩትም ..ውበት ማድነቅ እችላለሁ…አማላይ ወንድ ፈርጣማ ሰውነት በአይኔ ላይ ሲንከባለል አይኔን አልጨፍንም….አንቺ ግን በአጋጣሚ በከፊልም ቢሆን ጾምሽን ፈታሽ ማለት ይቻላል ? እና በህይወትሽ ያለፉትን ስድስት አመታት ስለአንድ ሰው በመብሰልሰል አባክነሽዋል››
‹‹ምን ለማለት እንደፈለግሽ አላውቅም?። ››
‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ቀሚስ የለበሺው መቼ ነው?››
‹‹እኔ ቀሚስ አልወድም። አይመቸኝም››አለች።'
‹‹ለመጨረሻ ጊዜ ሜካፕ የተጠቀምሺውስ መቼ ነው? ወይ ጭፈራ ቤት ገብተሸ የምታውቂው መቼ ነው?ከአንድ ማራኪ ሰው ጋር የመሽኮርመም ስሜት ተሰምቷሽ የሚያውቀው መቼነው?
››አዲስአለም ንግግሯን ለደቂቃ አቆመች…ከዛ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹ ከዘሚካኤል ጋር በመሳሳምሽ ለምን ታፍሪያለሽ? ሰውየው የእያንዳንዱ ሴት የሩቅ ህልም ነው ..አንቺስ ገና የ22 አመት ለግላጋ ወጣት አይደለሽ? ለምን ልትስሚው አትፈልጊም?ነው ወይስ የጤንነት መታወክ አለብሽ..?ይሄ አይነጥላ ምናምን የሚሉት››
‹‹በቃ ተይኝ እስኪ››
‹‹ነው ወይስ አሁንም ያ ወታደርሽ ከለሁበት ፈልጎ ያገኘኛል የሚል ምኞት ውስጥ ነሽ?››
‹‹አረ ተይኝ…ምን ብዬ ነው በቁሜ ገድሎኝ የሄደን ሰው መጥቶ ከሙታን ያስነሳኛል ብዬ የምጠብቀው..ስታይኝ ያን ያህል ጅል እመስልሻለው እንዴ?›››ፀደይ እስከአሁን ከተበሳጨችው በላይ ተበሳጨች፡፡
‹‹እኮ እንደዛ ከሆነ ዘና በያ…ገና ለገና አንድ ሸበላ ወንድ ጋር ተሳሳምኩ ብለለሽ እንዲህ አመድሽ የወጣ.. ሱሪሽን ብታወልቂለት ምን ልትሆኚ ነው?››
‹‹በስመአብ በይ!!!››አማተበች፡፡‹ ስለእሱ የምትቀባጥሪው… ምንም ለውጥ አያመጣም….ይልቅ ትርኪ ምርኪውን ተይና ስለዋናው ነገር እናውራ…እኔን ያናደደኝ ዋናው ጉዳዩ ወደ ሰርግ ለመምጣት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ወንድም የለኝም እያለኝ ማለቱ ነው …እንዴት…..?››ንግግሯን ሳትጨርስ ሚካኤል ድንገት መጥቷ ስለተቀላቀላቸው አፏን እንደከፈተች ቀረች፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe እያደረጋጁ አይደለም 500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ

👍70❤5
#አላገባህም
፡
፡
#ምዕራፍ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
፡
፡
///
‹‹ እንዴት ናችሁ.?.የሴት ወሬ ላይ ነበራችሁ መሰለኝ….በመምጣቴ ምቾት አልተሰማችሁም››አለ፡፡
‹‹እንዴ ባልዬው የሴት ወሬ ደግሞ ምንድነው?››ስትል አዲስ አለም ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው ወንዷችን ማማት ነዋ››ሲል በፈገግታ መለሰላት፡፡
‹‹አንተ እንደዚህማ አትለንም….በዚህ ፀባይህ ላላገባህ እችላለው…የደገስከው ድግስ ብላሽ እንዳይሆንብህ
ፀአዳ ጣልቃ ገባች‹‹አንቺ እንደዛማ አታስፈራሪውም..እስኪ ልብ ይኑርሽና እምቢ በይው….የልጅ እናቷን ሳይሆን ልጃገረዶችን ነው የማንጋጋለት››ስትል መለሰች፡፡
‹‹አንቺ እስስት ለሁለታችንም እኮ ነው እየተሞገትኩ ያለሁት››
‹‹ያንቺን ሙግት አልፈልግም …ይልቅ ሚካኤል… አንተን እና አዲስአለምን ይቅርታ ልጠይቅህ ፈልጌ ነበር። ››አለችው ኮስተር ብላ፡፡
‹‹ምነው ምን ተፈጠረ?››ሚካኤል ብቻ ሳይሆን አዲስአለምም ያልጠበቀችው ስለነበር ግራ ተጋባች፡፡
‹‹ወንድምህን ዘሚካኤል በሰርጋችሁ ቀን እንዲገኝ ለማድረግ የተቻለኝን ጥሬ ነበር…ግን አልተሳካልኝም፣ አሁን የሚመጣበት ምንም ዕድል የለም።››አለችው፡፡
‹‹ለምን ይቅርታ ትጠይቂያለሽ ? እሱ እንደማይመጣ አስቀድመን እናውቅ ነበር፣››በማለት ሚካኤል ተናገረ፡፡
አሁን ግራ የመጋባቱ ተራ የራሷ የፀዳ ሆነ‹‹ቆይ ለመሞከር እንደሄድኩ ታውቅ ነበር እንዴ?››ስትል በጥርጣሬ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡
ፈራ ተባ እያለ በሹክሹክታ‹‹አዎ..አውቅ ነበር››አላት፡፡
ወደአዲስአለም ዞረችና‹‹አንቺ በቃ ሚስጥር የሚባል ነገር አታውቂም..ለዛውም እንዳትነግሪው ብዬ አስጠንቅቄሽ?››
‹‹አንቺ ደግሞ ባልና ሚስት አንድ ሀምሳል አንድ አካል ናቸው ሲባል አልሰማሽም እንዴ? ከገዛ አካሌ ምን ብዬ ነው የምደብቀው?››
‹‹አረ የምትገርሚ ነሽ…ሚኪ ግን በጣም አዝናለው…››
‹‹ምን ያህል እንደሞከርሽና እንደጣርሽ አውቃለው….በእውነት አዲስ በነገረች ቀን እንባ አውጥቼ ነው ያለቀስኩት..ማንም ሰው እዲህ አይነት ነገር ላድርግለህ ብሎኝ አያውቅም ..እህቴ በጣም ነው የምወድሽ …በጣም ነው የማመሰግንሽ››አላት
‹‹እኔም በጣም ነው የምወድህ››አለችና ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችበት፡፡እሱም ተቀብሎ አቀፋት፡፡
‹‹እናንተ እኔንም እኮ አስቀናችሁኝ››አለችና ከተቀመጠችበት ሄዳ ሁለቱንም አንድ ላይ አቀፈቻቸው፡፡
///
መድረስ አይቀርም ለአመታት ሲታሰብበት እና ለወራት ሲለፋበት የነበር የሰርግ ቀን ደርሶ አዳራሽ ሙሉ እድምተኞች ሙሽሮቹን አጅቦ ሽር ብትን እያሉ ነው፡፡ ፀአዳ በህይወቷ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ደስታና ፈንጠዝያ ተሰምቷት አያውቅም?ከሙሽራዋ ጀርባ ሆና በደመቀ ሁኔታ የሚካሄደውን ስነስርዓት እየተከታተለች ነው፡፡በአዲስ አለም የሰርግ ቀሚስ ላይ ያለው የተራቀቀ ዶቃ በመስታወት ላይ ሲያርፍ በተብረቀረቀ ብርሃን አንጸባርቆ መልሶ ወደውስጥ ሲረጭ ስትመለከት በተረት አለም ውስጥ ስላሉ ልዕልቶች እንድታስብ አደረጋት። የአጋቢውን ፓስተር ድምጽ ላይ ለማተኮር ሞክራለች። እሷ ራሷ የለበሰችው ቀሚስ ልዩ አይነት ስሜት እንዲሰማት አድርጓታል…በህይወቷ መቼ ቀሚስ ለብሳ እንደነበረ አታስታውስም፡፡ ምን አልባት ከቤተሰቦቾ ጠፍታ ከወጣች በኃላ ቀሚስ ጨርሱኑ ለብሳ አታውቅም ይሆናል…ሴት መሆኗ እንዲሰማት አትፈልግም…ጠንካራ ታጋይ ሆና ልጇን ማሳደግና ህይወትና ማሸነፍ ብቻ ነው እቅዷ ..ቀሚስ መልበስ ለስላሳ የሚያደርጋት ይመስላታል…በምን ምክንያት እንደዛ ልታስብ እንደቻለች አታውቅም..ግን ደግሞ ትክክል ነበረች፡፡ ይሄው ዛሬ የተለየ ስሜት እየተሰማት ነው…ሴትነቷ ጎልቶ እየበራ ነው…ይሄ ደግሟ ለሚመለከቷት ሰዎች ብቻ ሳይሆን… ለራሷም በደንብ ታውቋታል፡፡ አዲስአለም የሚካኤልን እጅ በመያዝ አጋቢው ፓስተሩ የሚላትን ጥምረታቸውን የሚያበስሩ ውብ ቃላትን ጥርት ባለ ድምፅ ስትደግም ይሰማል… ።
በመከራህም ሆነ በደስታ ጊዜ… ላልለይህ ቃል እገባለው፡፡
በሀዘንህም ሆነ በደስታህ …ጊዜ ከጎንህ ልሆን ቃል እገባለው፡፡
በጤንነትህም ሆነ በህመምህ ጊዜ …ከጎንህ ላልለይ ቃል እገባልው፡፡
ቀላበቱን አውጥቶ አጠለቀላት እሷም አጠለቀችለት፡፡እርስ በርስ እንዲሳሳሙ ተደረገ….ፀደይ በምታየው ነገር ሁሉ አንሳፋፊ አይነት አስካሪ ስሜት እየተሰማት ነው፡፡
እሷ ከረጅም ጊዜ በፊት ነው በደስታ ማመን ያቆመችው፣ ነገር ግን እዚህ ውብ ቦታ ላይ ሆና አዲስአለም እና ሚካኤል ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ባልና ሚስት መሆናቸውን በፓስተሩ ሲታወጅ ስትሰማ ከቁጥጥሯ ውጭ በሆነ ደስታ ተገፋፍታ ከጣሪያ በላይ ‹‹…እልልልልል….›› ስትል አዳራሹን አናጋችው..በዙሪያዋ ያሉ ሚዜዎችና አጃቢዎች ተቀላቀሏት…ዘፈኑና ጭፈራው ቀጠለ..፡፡
///
ዘሚካኤል አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ወንበር ከያዘ ደቂቆች አልፈውታል፡፡በአይኑ እየፈለጋት ነው፡፡‹‹በፈጣሪ ስም ወዴት ሄዳሽ ነው?››አጉረመረመ፡፡
ቢፌ የተዘረጋበትን የተንቆጠቆጠ የድግስ አዳራሽ ውብ ሆኖ ይታያል፣ የሰርጉ ድግስ አሁን በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው እና ወደ ሁለት መቶ የሚጠጉ እንግዶች በግዙፉ አዳራሽ ሽር ብትን እያሉ እና እየተዝናኑ ነበር።
‹‹አንድ ባልና ሚስት እንዴት በዚህ መጠን ብዙ ጓደኞች እና ወዳጆች ሊኖራቸው ቻለ?››ሲል አሰበ ፡፡ እና ደግሞ ሁሉም ወደ እሱ ለመቅረብ እና ከእሱ ጋር ውስን ቃላትን ለመለዋወጥም ፈልገው ሲቁነጠነጡ ታዘበ ። እሱ ግን ቀልቡም አይኑም እየተንከራተተ ያለው አንዲትን ሴት ለማየት ነው ።ድንገት ከመድረክ ላይ ከሙሽሮቹ ጀርባ ሆና ተመለከታት፡፡ ግን ወዲያው ተሰወረችበት ፡፡‹‹ዘሚካኤል አረ እራስህን ሰብስብ ››ሲል ራሱን ገሰፀ…ፊቱን ወደግድግዳ አዞረና በእጁ የያዘውን መጠጥ እየተጎነጨ ዘና ለማለት ሞከረ። ቢያንስ እንደዛ በማድረጉ በአይኖቻቸው ሲያሳድዱት የነበሩትን ጎረምሳ ልጃገረዶችን መገላገል ችሏል ፡፡
‹‹ወደዚህ ተንደርድሬ እንድመጣ ያደረገኝ ምንድን ነው?››እራሱን ጠየቀ፡፡ትላንት አመሻሹ ላይ ወደ ዱባይ የመብረር እቅድ ነበረው፡፡ትኬት ሁሉ ቆርጦ ነበር፡፡ከአምስት ቀን በኃላ የሚጀመርና ለተከታታይ ሶስት ቀን የሚካሄድ የሙዚቃ ድግስ አለው፡፡ከአምስት ቀን አስቀድሞ የሚጎዘው…ቀደም ብሎ ከአካባቢው ሁኔታና የአየር ጻባይ ጋር ለመለማመድና ለዝግጅቱ ትኩረት ለመስጠት ስለፈለገ ነበር፡፡እና በፕሮግራሙ መሰረት ሻንጣውና ሸክፎ ወደቦሌ መጓዝ ጀምሮ ነበር..ግን በመንገዱ ላይ የሚያያቸውን ቢል ቦርዶች ሁሉ የልጅቷን ምስል የያዙ እየመሰሉት ሲደነግጥና ፈፅሞ ሊቆጣጠረው የማይችል ስሜት ውስጡ ሲያሸብረው..ወዲያው ስልኩን አውጥቶ ለኤጀንቱ ነበር የደወለው፡፡
‹‹ሄሎ ይቅርታ ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ስላልሆነ ዛሬ መብረር አልችልም››አለው፡፡
‹‹ምነው..ምን ተፈጠረ?››
‹‹እያመመኝ ነው…አሁን ቦሌ አየር ማረፊያ እየተቃረብኩ ነበር..ግን ወደቤቴ ልመለስ ነው…በረራውን ለሌላ ቀን እንዲሸጋገር አድርግ፡፡››
‹‹ለመቼ ለነገ ላድርገው….?››
‹‹ነገ እንደሚሻለኝ በምን አውቃለው…?ምናልባት ተነገ ወዲያ››
‹‹አውቀሀል …?ዝግጅቱ 5 ቀን እኮ ነው የቀረው››

👍71❤11🥰1
‹‹ሶሪ… ስልኩን ልዘጋው ነው… ከዚህ በላይ ማውራት አልችልም››በማለት ስልኩን ዘጋውና ሹፌሩን ወደቤት እንዲመልሰው አዘዘው፡፡እያደረገ ስላለው ነገር እሱም እየገባው አይደለም…‹ይህቺ ልጅማ የሆነ አስማታዊ ጥበብ ከንፈሯ ላይ አለ፤እንዴት እንዴት እየሆንኩ ነው?››እራሱን ታዘበ….ወደቤት ተመልሶ ለሊቱን ሙሉ ሲገረምና ስለእሷው ሲያስብ አደረ..በጥዋት ተነሳና አምሮና ተሸቀርቅሮ…ልጅቷ የሰጠችውን የሰርግ ጥሪ ካርድ ካስቀመጠበት ቦታ አንስቶ ኪሱ በመክተት ማንም እንዳያገኘው ስልኩን ጠርቅሞ ዘግቶ ግዙፉን ሀመር መኪና እራሱ እያሽከረከረ ወደአዳማ መንዳት ጀመረ፡፡የሆነ ሃይል ሙሉ ልቡን ተቆጣጥሮ አእምሮው የማይፈቅደውን ነገር በግድ እያሰራው እንዳለ ነው እየተሰማው ያለው፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe እያደረጋጁ ቤተሰቦች 500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe እያደረጋጁ ቤተሰቦች 500 መግባት አለበት ይሄ ድርሰት እስከሚያልቅ
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍61❤7
#አላገባህም
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
////
ዘሚካኤል ከሰዓታት በፊት የሰርጉን ስፍራ ለቆ መሄድ ነበረበት። ነገር ግን ከፀአዳ ተለይቶ መራመድ አልቻለም። ከሳምንት በፊት በእንጥልጥል የተወውን ጉዳይ መቋጫ ማበጀት አለበት፡፡በልቡ ጭራበት የሄደችው ሲኦል እሳት እየተንበለበለች መላ ሰውነቱ ትኩሳት እንደለቀቀችበት ነው…እንዴትም አድርጎ እንዴት እሱን ማስተካከል ያስፈልገዋል. ዛሬ ማታ።
ፀአዳ ለዘሚካኤል ቃል በገባችለት መሰረት ወደእሱ ለመሄድ ከውስጥ ወደአዳራሹ በተመለሰች ጊዜ በብዙ ውብና አማላይ ሴቶች ተከቦ ሲያውካካ ተመለከተችውና ከመንገዱ ለመራቅ ወሰነች - ባየችው ነገር ክፍት ነው ያላት…እንደዛ የማድረግ መብት የላትም ..ግን ከማንም ለመፎካከርና እሱን ሻሞ ለመሻማት ምንም አይነት እቅድ የላትም..እና እግሯና ወደኃላ ጎተተችና የአስተባባሪነቱን ስራዋን በትኩረት መስራቷን ጀመረች፡፡እራሷን ማሞኘት አልፈለገችም።
እሱ በእጁ ይዞ የነበረውን ባዶ ብርጭቆ በአጠገቡ በሚያልፈው አስተናጋጅ ትሪ ላይ አስቀመጠና ዓይኑን ወደ ህዝቡ መሀከል አንከራተተ። የሙሽሮቹ ዋና ተጠሪ እንደመሆኗ መጠን መጥፋት አልቻለችም። ግን እሱን ከእይታዋ ለማስወገድ እየሞከረች እንደሆነ ያስታውቅባታል፡፡‹‹እንደዛ እንድታደርጊማ አልፈቅድልሽም››ሲል ፎከረ፡፡ይሄ በእሱ ልምድ አዲስ ተሞክሮ ነበር።አንድ በሆነ አጋጣሚ ከንፈሩን የቀመሰች ሴት መልሳ ልታገኘው መከራዋን ስታይና ስትንሰፈሰፍ ነበር የሚያውቀው፣ከከበቡት ልጃገረዶች በዘዴ ተለየና እሷን ለማግኘት መጣር ጀመረ፡፡
ፀደይ ግራ በመጋባት ያለአላማ ከወዲህ ወዲያ ስትሽከረከር . ድንገት አይን አዲስ ወደእሷ ጠራቻት‹‹እ ምን ፈለግሽ?››
‹‹እኔ ምንም አልፈለኩም… ለምን ከእሱ ትደበቂያለሽ ?››
‹‹ አልተደበቅኩም›› አለች ፀአዳ፡፡
‹‹እሺ እንደዚያ ከሆነ፣ ለምንድነው ከእሱ ጎን ሆነሽ አንድ ብርጭቆ ሻምፓኝ የማትጎነጪው?ምንድነው የሚያስፈራሽ?››
‹‹እንደምታይው እሱ ብቸኛ ሰው አይደለም….ሁሉም ሰው የእሱን እዚህ ሰርግ ላይ ስለመገኘት ነው የሚያወራው -..እና ወደሰርግ አዳራሹ ከገባበት ደቂቃ አንስቶ በሰው በተለይ በሴቶች እንደተከበበ ነው››
‹‹እና ውድድሩን አላሸንፍም ብለሽ ሰጋሽ …?አዎ ከባድ ውድድር እንዳለብሽ እኔም ገምታለው።ግን እኮ ይሄንን ለመሰለ ጠንበልል አማቼ… መፋለም መቻል በራሱ እድል ነው?››
‹‹አረ በካሽ…እኔ ፀደይ ነኝ፡፡ ወንድ ለማግኘት ከሌላ ሴት ጋር የምናጠቀው። እንደው እንዳልሺው ፊልሚያ ውስጥ ልግባ ብልስ እሱ ፍላጎት ከሌለው የሚሆን ይመስልሻል…?እናስ ከእነዛ ከከተመዋ አማላይና ስብር ቅንጥስ ከሚሉ ወዳጆችሽ ጎልቼ በአይኑ የምገባ ይመስልሻል...›› በብስጭት ተንዘረዘረች፡፡
‹‹ገባሽ እኮ ..ቀድመሽ በከንፈሩ ገባሽ….ይልቅ አትንቀርፋፊ..በሰርጌ ቀን ካንቺ ጋር ከዚህ በላይ መዳረቅ አልችልም..ባሌ አየጠራኝ ነው፡፡ቻው››ብላት በቆመችበት ጥላት ሄደች፡፡
ፀደይ ለተወሰነ ደቂቃ ድንዘዝዝ አለች‹‹…ምን ላድርግ?››እራሷን ጠየቀች..፡፡ምንም ያህል ችላ ልትለውና ልትርቀው ብትሞክርም ልቧ ግን ልክ እንደማግኔት ወደእሱ እየጎተታት ነው…ወደአለበት ሄዳ ከሰውዬው ጋር ለመነጋገር ድፍረት አልነበራትም።ፊቷን አዙራም ከእሱ ርቃ ለመሰወር ብትጥርም ከዚህ የበለጠ ተጫማሪ ሳዕታትን ከእሱ ተደብቃ መቆየት እንደማትችል ልቧ ያውቃል፡፡ድንገት ስታየው ብቻውን ሆኖ ስላየችው ወደኋላ ተመለሰችና ቅዱስን ከሞግዚቷ ተቀብላ በማቀፍ እንደምንም እራሷን አደፋፍራ ወደእሱ ሄደች፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…?መምጣትሽን በናፍቆት ስጠብቅ ነበር››ከአንደበቷ የሚወጡት ቃላት ልቧን በቀላሉ ማቅለጥ አቅም ነበራቸው፡፡
‹‹አልደበረህም አይደል?››
‹‹በመጠኑ…ግን በጣም የሚፈልጉትን ነገር ባልተመቸ ሁኔታ ውስጥም ሆነው መጠበቅ የሆነ ደስ የሚል ስሜት አለው….እና አልከፋኝም››አላት፡፡
ዝም አለች…ምን እንደምትል ግራ ተገባች‹‹ከወንድምህ ልጅ ከቅዱስ ጋር ላስተዋውቅህ።››አለችው
ዘሚካኤል በተራው በዝምታ ተዋጠና ህፃኑን በትኩረት ማየቱን ቀጠለ። የሆነ የማያውቀው መከፋት ስሜት ውስጡን ሲያተረማምሰው ተሰማው፡፡ህፃኑን እቅፉ የተንጠለጠሉትን ውብ ጉንጮቹን እያገላበጠ ቢሰመው ደስ ይለው ነበር፤አዎ እንደዛ አይነት ፍላጎት ነበር የተሰማው፡፡ግን ከተቀመጠበት መነቃነቅ ሆነ እጆቹን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡እንዲህ መሆን የለበትም ነበር፡፡እሱ በቤተሰቡ ላይ ያን አይነት መአት ከመድረሱ በፊት በጣም ሰው ወዳጅ በተለይ ዘመድ ለተባለ ሰው ልቡ ትርክክ የሚል በፍቅር የሞላ ልጅ ነበር፡፡ከክስተቱ በኋላ ግን ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ነው የሆነው፡፡ከዘመድ ጋር መነካካት መርዝ እንደመጎንጨት የሚያንገፈግፈው ነገር ሆኖል…ቢሆንም እንዲህ በጮርቃ ህፃን ላይ እንኳን የተለየ አቋም ሊኖረው አይገባም ነበር፡፡
‹‹አይዞህ አትጨናነቅ..በሂደት ጥሩ አጎቱ ትሆናለህ››አለችው፡፡
‹‹ልጁን በተመለከተ እንደጨነቀኝ እንዴት አወቀች?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡
‹‹አሁንም ብቻህን ጥዬህ ልሄድ ነው..ግን አልቆይም..ህፃኑን ለእናቱ አስረክቤ መጣሁ…››
በረጅሙ ተነፈሰ‹‹አዎ እንደዛ ይሻላል..አታስቢ ስለአንቺ እያሰብኩ ጠብቅሻለሁ፡፡››አላት፡፡
ፈገግ አለችለትና ህፃኑን ቅዱስን አቅፋ ተነስታ ሄደች፡፡ከኃላ አይኑን ተክሎ ተመለከታት..አቋሞ ልዩ ነው፡፡ተረከዘ ሎሚ የምትባል አይነት ነች..እንዲህ አይነት እግር ያላት ሴት ከድሮውም በጣም ነው የምትማርከው…ደግሞ ከሁሉም በላይ እሱ ጋር ከሚመላለሱት ሴቶች ተቃራኒ በሆነ መልኩ ምንም አይነት መዋቢያና መኳኳያ አትጠቀምም…ለምን እንደሆነ ሊገባው አልቻለም…ብትጠቀም እኮ የበለጠ ውብ ትሆን ነበር?››ሲል አሰበ፡፡‹‹ግን አንኳንም አልተጠቀመች››ሲል ደመደመ፡፡
ልጁን ለሞግዚቷ አስረክባ ብቻዋን ትመጣለች ብሎ ሲጠብቅ የወንድሙን ሚስት አስከትላ መጣች፡፡
አዲስአለም ‹‹ዘሚካኤል… በመምጣትህ በጣም ደስ ብሎናል … ዛሬ ማታ ቤታችን በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ብትገኝ እንዴት ደስ ይለናል መሰለህ …ግን ምቾት የማይሰማህ ከሆነ እንረዳሀለን….እዚህ ስለመጣህ እራሱ በእውነት በጣም ደስተኛ አድርገሀናል….ሰርጋችንም የማይረሳና የታደመው ሰው ሁሉ መቼም የሚያስታወስው እንዲሆን አድርገሀል ።››
ዘሚካኤል ደቂቃ ወስዶ እንደማሰብ ሲያደርግ ፀአዳ ጣልቃ ገብታ‹‹እባክህ እሺ ብለህ ቆይ…አይዞህ እንደአሁኑ ጣል ጣል አናደርግህም…ቃል እገባልሀለው››አለችው፡፡
ንግግሯን ስታጠናቅቅ አዲስአለምም ሆነች ዘሚካኤል አፍጥጠው እየተመለከቷት ነበር…‹‹ምንድነው የሚያስቀበጥረኝ ?››ስትል በውስጧ እራሷን ወቀሰች፡፡
ዘሚካኤል መናገር ጀመረ‹‹እሺ እቆያለው››ሲል ተናገረ፡፡
አዲስአለም ፊት በደስታ በራ‹‹አመሰግናለው..በቃ አሁን ጥያችሁ ልሂድ …አብረሽው ቆይና ይዘሽውን ነይ››አለችና ተመልሳ ሄደች፡፡
ፀአዳ ከእፍረቷ ሳትላቀቅ በዝግታ ተቀመጠችና፡፡‹‹እሺ ትላለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››አለችው፡፡
‹‹እውነቱን ለመናገር እኔም እሺ እላለው የሚል ግምት አልነበረኝም….ቃልሽን አምኜ ነው እሺ ያልኩት››አላት፡፡
‹‹ማለት የምን ቃል?››
‹‹እንደእስካሁኑ ብቻህን በመተው እንድትደበር አላደርግህም…ከመጀመሪያው እስከፍጻሜው ከጎንህ አልለይም…›ብለሽ የገባሽልኝን ቃል ነዋ››
‹‹አንተ ይሄን ሁሉ መቼ ነው የተናገርኩት.››
‹‹.አሁን ከደቂቃዎች በፊት››
‹‹ይሁን..ለማንኛውም ማትቆጭበት ውሳኔ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለው››

👍63❤9🥰2
‹‹እኔም…አሁን ዝግጅቱ አልተጠናቀቀም እንዴ?..ይሄን ቦታ መልቀቅ ፈልጋለው፡››
‹‹ተጠናቋል …ከ10 ደቂቃ በኋላ እንወጣለን››
‹‹ጥሩ….አንቺ ከፊት ለፊቴ አስካለሽ ከ10 ሰዓትም በሃላ ቢሆን ግድ የለኝም፡፡››
ሳታስበው ‹‹እንደወንድምህ አይደለህም…››አለችው፡፡
‹‹ማለት?››
‹‹እሱ አንደበተ ቁጥብ ነው..በምንም አይነት መንገድ ሰውን በውሸት አይሸንግልም››አለችው፡፡
‹‹በውሸት…ለምን እዚህ የመጣው ይመስልሻል?››
‹‹ይሄ ምን ጥያቄ አለው..የወንድምህ ሰርግ ላይ ለመገኘት ነዋ፡፡››
‹‹ተይ እንጂ….በዛ ውድቅት ለሊት በከንፈርሽ ካደነዘዝሺኝ በኋላ ካንቺ ውጭ ስለሌላ ነገር ማስብ አልቻልኩም..ትናንት ማታ ወደዱባይ መብረር ነበረብኝ ..ትኬት ቆርጬ ወደኤርፖርት ሁሉ መሄድ ጀመሬ ነበር..ከዛ ነው ሀሳቤን ቀይሬ የመጣሁት…ለምን?፡፡››
‹‹በል አሁን ሰው እየተንቀሳቀሰ ነው ተነስ እንሂድ አለችው…..››እንዳለችው የሆቴሉ ዝግጅት አልቆ ሙሽሮቹን ተከትሎ ሰው ሁሉ እየወጣ ነው፡፡ግን የጀመረውን ንግግርም ልታቋርጠው ስለፈለገች ነው አጋጣሚውን ተጠቀመችበት፡፡መቀመጫውን ለቆ ተነሳና ክንዷን ጨብጦ ወደመውጫው መጓዝ ጀመረ….በትክክልም መራመድ አቃታት፡፡ከአዳራሹ ውጭ ወጥተው ወደሀመር መኪናው ሲያመሩ ጎዳናው ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በገረሜታና በመደነቅ ሲያቸው ነበር..አንዳንዱም እጆቻቸውን በደስታ እያውለበለቡ ሰላም ይሉት ነበር፡፡የዘሚካኤል ባለግርማ ሞገስ ሀመር መኪና ከሌሎች መኪኖች መሀከል ሆኖ ጎልቶ ይታያል።፡፡የሙሽሮችን ሊሞዚን ተከትሎ ከኃላ እያሽከረከረ ነው፡፡እሷ ከጎኑ ገቢና ሆና ባልተረጋጋ ስሜት አንዴ የሰርጉን ድባብ ወዲያው ደግሞ በቀጣይ ከእሱ ጋር ስለሚሆነው ነገር ታሰላለስላለች፡፡
እሱ የዚህን ያህል በጣም ታዋቂ እንደሆነ አታውቅም ነበር! እሷ እምብዛም ሙዚቃ አድማጭና ፊልም ተከታታይ አይደለችም፡፡ ስለእሱ ያወቀችው የሚካኤል ወንድም በመሆኑ ነው ..ስለእሱ የተወሰነ መረጃም መሰብሰብ የጀመረችው በዛ ጉዳይ ነው፡፡አሁን ግን እዚህ ሰርግ ላይ ከተገኘ በኋላ እያንዳንዱ ሰው ከህጻናት እስከ አዛውንቶች እሱን ለማየት ሲንጠራሩና ሰላም ለማለት ሲራኮቱበት ስታይ በጣም ነው የተገረመችው፡፡እና ደግሞ በጣምም ነው ያስፈራት፡፡
ቀኝ እጁን ዘርግቶ ትከሻዋን እየነካካ‹‹ቀኑን ሙሉ አልበላሁም እና ርቦብኛል››አለ በረጋ መንፈስ።
‹‹እንዴ ምሳ ግብዣ ኮ ብፌ ነበረ››
‹‹ባክሽ የእኔ ቀልብ አንቺ ማግኘት ላይ ስለነበረ ...በወቅቱ ትዝ አላለኝም..አሁን አንቺን ሳገኝሽ ነው እንደራበኝ ያወቅኩት ››አላት፡፡ ..
ምላሽ ስትሰጠው የድምጻን መንቀጥቀጥ መቆጣጠር አልቻለችም። የአዲስአለምና የሚካኤል መኖሪያ ቤት ለራት ድግስ የተዘጋጀውን ቢፌ ብቻ ሊውጥ ያሰበ አይመስልም …አይነ ውሀውን ስታስተውል ረሀቡ የምግብ ብቻ አይመስልም…፡፡ ለምን እንደዛ እንደተሰማት አታውቅም?
እስከምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ እነ አዲስአለም ቤት የራት ግብዠው ላይ አብረው አሳለፉ…በጣም አስደሳችና ዘና ያለ ምሽት ነው ያሳለፉት ከዛ ሙሽሮቹን በስነስርዓት ተሰናበተና ፀአዳ ሆቴል ድረስ ትሸኘኝ በማለት ይዞት ወጣ..እሷም ያለምንም ማንገራገር ነበር ተከትላው ወጥታ መኪናው ውስጥ የገባችው፡፡ቀጥታ ቀደም ብሎ ወደያዘው ሀይሌ ሪዞርት ነዳው፡፡
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ክፍያችን እሱ ብቻ ነው 500 subscribers Please 🙏

👍107❤6
🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_21
ሕይወትን በወህኒ ቤት ከፖሊስ ጣቢያ የሚለያት ነገር ቢኖር፣ እዚህ ያለው እስረኛ ከጥቂቱ በቁጠሮ ቤት ካለውና ካልተፈረደበት በስተቀር፣ ምን ይፈረድብኝ ይሆን? በዋስ እፈታ ይሆን? ምን ያገኙብኝ ይሆን? ወዘተ ከሚለው ጭንቀት መገላገሉ ነው:: እያንዳንዱ እስረኛ የተፈረደበትን የእስራት ቀናት በልቡ ውስጥ ጽፎ አንድ ቀን በአደረ ቁጥር አንድ ቀን እየቀነስ የመውጪያ ቀኑን ከማስላት ውጪ ሌላ የሚያስጨንቀውና የሚያሳስበው ነገር የለም:: አብዛኛው እስረኛ ትምህርቱን የሚማር ስለሆነ ከዚህ ሲወጣ ስንተኛ ክፍል አጠናቆ እንደሚወጣ ያውቀዋል:: ዩንቨርስቲ አቋርጠው ወይም ዩንቨርስቲ አጠናቀው ሥራ ላይ እያሉ በተለያየ ምክንያት የታሰሩ ምሁራን ምንም ባይከፈላቸውም እስረኛውን ለማስተማር ከልባቸው ይጥራሉ፡፡ ለጥናት የሚሆን ግዜ በሽበሽ ስለሆነ ከልቡ ለመማር ለደፈረ ሰው የሕይወቱን
አቅጣጫ ሊለወጥ የሚችል ዕውቀት አግኝቶ እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም.. ትምህርት ያገኙ ተራ ሌቦች ያገኙት ዕውቀት በመጠኑም ቢሆን በአነጋገራቸውና በባህርያቸው ውስጥ ለውጥ እያመጣ መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ በብዙ መልኩ ከመጣሁበት ፖሊስ ጣቢያ ጋር ሲነፃፀር ብዙ ነገሩ እዚህ ለየት ይላል፡፡ የቤቱ ንጽህና የተጠበቀ ነው፣ ሁሉም ነገር ስርዓት አለው፣ የሚወራው ወሬም ቢሆን ብስለት አለው፡፡ እስረኛውም አብዛኛውን ጊዜውን በማውራት ሳይሆን በመማር፤ በማንበብ፣ የተለያዩ ስራዎችን በመስራትና በመጻፍ ያላልፋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወህኒ ቤት የተለያዩ የሌብነትና የቅጥፈት ባህርያትን ተክኖ ለመውጣት አመቺ ቦታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ራሱን ለውጠ ጥሩ ዜጋ መሆን ለማይፈልግ አሥረኛ በወንጀል ሙያ ለመሰልጠን ምርጥ ኮሌጅ ነው:: በአልባሌ ሰበብ ከሰው ጋር ተጣልቶ ወይም ሳያስበው የሰው ገንዘብ ጠፍቶበት ለተፈረደበት እስረኛ ፍላጎቱ ካለው ሙያውን ለማስፋት ጥሩ የማስልጠኛ ኮሌጅ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እዚህ የማይቻል ነገር የለም:: ውጪ ያለውን ሁሉንም ነገር "ማግኘት ወይም ማድረግ" ይቻላል:: ሌላው ቀርቶ ከሴት ጋር ፍቅር መጀመር ይቻላል:: የኳስ ጨዋታ ወይም ትርዒት በሚቀርብበት ወቅት በሩቅ እየተያዩ መከሳከስ ነው:: መጀመሪያ እንደተያዩ መተፋፈር፣ ቀስ በቀስ በዓይን ሰላምታ መለዋወጥ፣ መሳሳቅና መሽኮርመም ወዘተ የተለመዱ የፍቅር ጨዋታዎች ናቸው:: እንደዚህ ባለ ሁኔታ የተገኘች ፍቅረኛ "አይኑካ ትባላለች፡፡ ታዲያ በአካል ተገኛኝቶ የልብን መወጣት ስለማይቻል የዓይኑካ ፍቅር ከሌላው ፍቅር ይልቅ የጠነከረ ነው፡፡ እኔ ለእንደዚህ ዓይነት ፍቅር ቦታ አልነበረኝም:: የማያት ሴት ስለሌለኝ የሚያዩኝ ሴቶች ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም:: ደግሞ ለእንደኔ ዓይነቱ በፍቅር መነሻ ሃያ ዓመት ተፈርዶበት ወህኒ የተወረወረ እስረኛ፣ ዳግም ላፍቅር ማለት አዲስ እርግማንን ማስተናገድ ነው:: አላርፍ ካልኩ ደግሞ ከዚህ በኋላ ፍቅር ሊያስከትለው የሚችለው መዘዝ በመሬት ላይ የሚያልቅ ሳይሆን ሲዖልም ተከትሎኝ ሊሄድ የሚችል ነውና የምመኘው አልነበረም። ሁለተኛው የይግባኝ ቀጠሮ ብዙም የሚወራለት ነገር አልነበረውም:: ጠበቃዬ ባቀረበው ይግባኝ ላይ የአባዲና የምርመራ ውጤት መምጣቱን ተከትሎ አለኝ የሚለውን ማስረጃ ከሁለት ወር ተኩል በኋላ እንዲያቀርብ በመወሰን አሰናበቱን፡ ዳኞቹ የአባዲናን የምርመራ ውጤት ከተመለከቱ በኋላ የሰው ማስረጃ እንዲያቀርብ በመፍቀዳቸው ጠበቃዬ አንድ ያገኘው ነገር በመኖሩ ነው የሚል ግምት ስላሳደረብኝ ይበልጥ መፅናናት ጀመርኩ፡፡ ጠበቃዬ ለፍ/ቤቱ ያቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት በማግኘቱ ዞር ብሎ እያየኝ ፈገግ ስላለ
መደሰቱን ገመትኩ:: ዳሩ ግን እኔም ሳይታወቀኝ ፈገግ ብዬ ስለነበር መሳቁ አፀፋ ለመመለስ እንጂ በሌላ ላይሆን ይችላል የሚል ስሜትም አደረብኝ፡ በጊዜ ላይ ጊዜ እየጨመረ እነሆ እስር ከተፈረደብኝ ከስድስት ወር በላይ ሆነኝ:: ግን በእነዚህ ወራት ውስጥ ወንጀለኛ አለመሆኔን ሊያረጋግጥልኝ የሚችል መረጃ አለመገኘቱን ሳስብ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያንዣብብብኛል። ዳሩ ምን ያደርጋል! እኔ ውስጥ ያለውን እውነት ለማውጣት ባያዳግተኝም እውነት መሆኑን ለማሳመን ግን አቅሙ ስለሌለኝ ሌላው በእኔ ቦታ ሆኖ እንዲያሳካልኝ ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝምና የቀጠሮ ቀናት በመጡ ቁጥር ዛሬ እውነት ትወጣ ይሆናል እያልኩ ከመጠበቅ በቀር ላደርገው የምችል ነገር አልነበረኝም። ካለፉት ቀጠሮዎች በተለየ መልኩ ዛሬ ተስፋ ያደረኩባት የቀጠሮ ቀን ደርሳ ወደ ፍርድ ቤት ሄድኩ፡፡ ይህቺ ዕለት ከሁሉም በላይ የዘገየችብኝ ቀን በመሆኗ እያንዳንዱ ቀን የወር ያህል ሆኖ ነበር የተሰማኝ። ብዙ ተስፋ የጣልኩባት ቀን በመሆኗ ነው መስለኝ ከፖሊስ መኪናው ላይ ወርጄ ወደ ፍርድ ቤቱ ሳመራ እግሬ መብረክረክ ጀመረ:: ይህቺ ቀን የእኔን የሕይወት አቅጣጫ የምትወስን ከመሆኗም በላይ የመጨረሻ የተስፋዬ ማለምለሚያ ወይም የተስፋዬ መድረቂያ ቀን ነበረች። ማን እንደነገራቸው ባላውቅም ከሌላው የይግባኝ ቀጠሮ ቀን በተለየ መልኩ አንዳንድ የመ/ቤቴ ሠራተኞችም መጥተዋል፡፡ ይህም የመፈታት ተስፋ እንዳለኝ የሚያመላክት ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰውዬ ከተፈታ ይታዘበናል በሚል ስሜት የፍርዱ ሁኔታ ያለበትን ደረጃ ሲስሙ አንዳንዶች ወህኒ ቤት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: መፈታት አለመፈታቴ አንድ ነገር ሆኖ ቢያንስ ለተወሰነች ጊዜ ቢሆን እንኳ ወንጀለኛ አለመሆኔን የሚያምን ሰው ማግኘት ትልቅ ደስታ ፈጠረብኝ:: ዳሩ ድከሙ ቢላቸው ነው እንጂ እኔ ማንንም የምቀየምበት ምክንያት አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም እኔ ለሌላው ሳደርገው ከነበረው አንፃር እያንዳንዱ ስው ለእኔ ያደረገው እጅግ ቢበዛብኝ እንጂ የሚያንስብኝ አልነበረም፡፡ ዛሬ ፍ/ቤት የምቀርበው ሁለት አማራጭ ይዤ ነው፡፡ ጠበቃዬ በእርግጥም ጠቃሚ መረጃ ይዞ መጥቶ ከሆነና ነፃ ካወጣኝ አሰየው፡፡ ነገር ግን እንደጠረጠርኩት እኔን ለተጨማሪ የእስር ዘመን ለመዳረግ ሴራ እየገመደብኝ ከሆነ ግን፣ ጮኬም ሆነ አልቅሼ ውስጤ ያለውን ጥርጣሬ ዳኞች ለጥቂት ደቂቃ እንዲሰሙ በማድረግ፣ ቢቻል ራሴን ነፃ ማውጣት ካልተሳካም *የቻልኩትን ሞክሬአለሁ" በማለት ከወደፊት ፀፀት ራሴን ነፃ ማድረግ ነው፡፡
የቀጠሮው ሰዓት ደርሶ ሣጥኔ ውስጥ ገብቼ ድራማውን እንደተለመደው ለመመልከት በተዘጋጀሁበት ወቅት ዳኛው ጠበቃዬ አለኝ የሚለውን የሰው ማስረጃ እንዲያቀርብ ስለአዘዙ ፖሊሱ “ዶ/ር አድማሱ" ብሎ ሲጣራ ክው ብዬ ደነገጥኩ፡፡ ዶክተሩ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ጥርሱን እየገለፈጠና በጥላቻ ዓይን እየተመለከተኝ ወደ መመስከሪያው ቦታ ሲራመድ ንዴቱ ፈንቅሎ ሊወጣ ደረሰ:: መቼም ይኼ ክፉ ሰው በምንም ዓይነት መንገድ እስሬን ለማጠናከር ካልሆነ በስተቀር እኔን ለማስፈታት የሚሆን ማስረጃ ሊኖረው አይችልም:: ጠበቃዬ ሆን ብሎ ወንጀሌን ለማጠናከር የሚያደርገው መሆኑ ስለገባኝ እጅግ ጠላሁት፡፡ ጠበቃዬ እኔ እንዳልፈታ የሚሸርበው ሴራ ለእጮኛው የሚያበረክተው ገፀ በረከት ነውና ብዙም ባልናደድበት፤ ይህንን ሰውዬ አምጥቶ እኔን ለማናደድ የሚያደርገው ድርጊት ግን እጅግ በጣም አበሳጨኝ:: ያም ሆነ ይህ አንዱ አማራጭ ካልተሳካ ሌላውን መሞከሬ ስለማይቀር ራሴን አረጋግቼ አባላንጣዬ ጋር ፊት ለፊት በጥላቻ ዓይን መተያየቱን ተያያዝነው:: ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ማድረግ የማይታሰብ ነው፡፡ ምንም ያህል ብናደድ ያለኝ አንድ አማራጭ እዚሁ ቆሜ ነድጄ እስከማልቅ ድረስ ውስጥ ውስጡን መቃጠል ነው፡። መሃል ዳኛው ከሁለቱ ዳኞች ጋር

👍37❤5
ከተነጋገሩ በኋላ፣ “ዶ/ር አድማሱ የመጡበትን ምክንያት ያውቃሉ?'' ብለው ሲጠይቁ፣ ዶ/ሩ ኮስተር ብሎ፤ “አላውቅም ጌታዬ" በማለት መለሰ፡፡ እየተርበተበ ጌታዬ ሲል ተገረምኩ፡፡ እሱ እዚያ ዩንቨርስቲ ውስጥ የሁሉም ጌታ ስለነበር ከውስጡ የጌትነት ስሜቱ ጠፍቶ በአንዴ ራሱን ማውረዱ ገረመኝ:: ያ ሁሉ ተማሪ ከእሱ ርህራሄን አግኝቶ ለማለፍ ሲል እሱ እንዳለው ይሆንለታል፤ ይሽቆጠቆጥለታል፡፡ ከተፈተነው ተማሪ ውስጥ ቢያንስ አንድ ሦስተኛው በእሱ ትምህርት መቀጣቱ/መውደቁ/ ስለማይቀር ሲያየው ይበረግጋል፡፡ በእሱ ትምህርት ለማለፍ ትምህርቱን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ በቂ አይደለም:: እያንዳንዷን የተናገራትን ቃልና በመሃሉም አስሎም ከሆነ ይህንኑ ጭምር እየጠቀሱ መጻፍ የግድ ነው:: የተናገራት ቃል ከሌለች፤ "የታለች የእኔ ወርቃማ ቃል Where is my golden word/" በማለት የቅጣት በትሩን ስለሚያሳርፍ የግዴታ እሱ ሲያስተምር ቃላቶች እንዳያመልጡ ሁሉም ተማሪ ጆሮውን አሹሎ ያዳምጣል፡፡ አንድ ነገር ሳያስቀር የተናገረውን በሙሉ ይጽፋል፣ በፈተና ግዜም የተናገረውን በሙሉ በመጻፍ ይመልሳል:: እሱ ሲራራላት የታየች ተማሪ ብትኖር አልማዝ ብቻ ሳትሆን አትቀርም:: ያም ቢሆን ለእሷ አዝኖ ወይም እራርቶ ሳይሆን እኔና እሷን በማለያየት እሷን
ለራሱ ለማድረግ ሲል ያደረገው የመጠቀሚያ ዘዴ ነበር:: ዳኛው ወደ ጠበቃዬ ዞር ብለው፣ “ጥያቄ ካለህ ቀጥል'' አሉ:: ጠበቃዬም፤ “ዶ/ር አድማሱ፤ አቶ አማረን ያውቋቸዋል" ብሎ ጠየቀው:: “ተከሳሹን ማለትዎ ከሆነ አዎ አውቀዋለሁ" በማለት መለሰ፡፡ ጠበቃዬ፤ “እንግዲህ እርሶን የፈለግንዎት አቶ አማረ የተከሰሰበትን ወንጀል አስመልክቶ የምስክርነት ቃልዎን እንዲሰጡን ነው” ሲል፣ ከመቀመጫው በመነሳት፤ አቃቤ ሕግ “ተቃውሞ አለኝ' አለ፡፡ “ምንድነው ተቃውሞህ? ተናገር!" አሉ ዳኛው:: “ክቡር ፍ/ቤት፣ ዶ/ር አድማሱ ቀደም ሲል በዚሁ ጉዳይ ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ስለሆነ አሁን ሌላ የሚለውጡት የምስክርነት ቃል ስለማይኖር ጥያቄውም አግባብ ስላልሆነ ተቀባይነት እንዳይኖረው እጠይቃለሁ" አለ፡፡ ዳኛው ግን ሀሳቡን ስላልተቀበሉት ዶ/ር አድማሱ ጥያቄውን እንዲመልስ አዘዙ፡፡ ጠበቃዬም ቀጠለ፡፡ “ሟቿን ወ/ት አልማዝ አስፋውን ያውቋታል?'' በማለት ጠየቀ። ዶ/ር አድማሱ የተሰላቸ በሚመስል ሁኔታ፤ “አዎ አውቃታለሁ'' አለ፡፡ “ትውውቀችሁ በምን ላይ የተመሰረተ ነበር?” “ይህንን እኮ ቀደም ብዬ ተናግሬዋለሁ፡፡ አሁን ደግሞ መጠየቁ ለምን አስፈለገ?'' በማለት ዶ/ሩ በንዴት መልክ መለሰ፡፡ ዳኛው ጣልቃ ገብተው፤ “ዶ/ር አድማሱ፤ የተጠየቁት ጥያቄ ምንም ያህል ቢደጋገም የመመለስ ግዴታ ስላለብዎ ሳይሰለቹ መልስ ቢሰጡ የተሻለ ነው" አሉ:: ዶ/ር አድማሱ ግን ቶሎ ለመመለስ አልደፈረም፡፡ እርግጥ ይህንን ለመናገር ጉሮሮውን ቢተናነቀው የሚያስደንቅ አልነበረም፡፡ ይህ ኃጢያት እንጂ እንደ ጀብዱ የሚወራ አልነበረምና። እሱ በፈፀመው ስህተት እኔና አልማዝ ተለያየን፡፡ ጣጣው በዚህም ሳያበቃ ለእሷ ሕይወት መጥፋትና ለእኔ መታስር መንስኤ
ሆነ፡፡ ታዲያ ይኼ እንዴት ሆኖ ሳይተናነቅ በቀላሉ ከጉሮሮ ይውጣ? ያም ሆነ ይህ እየተናነቀውም ቢሆን መናገር የግድ ነውና፤ "ቀደም ሲል ተማሪዬ ነበረች፡፡ ትምሀርቷን ከጨረስች በኋላ ደግሞ ፍቅረኛሞች ነበርን" አለ:: ለምን እንደዋሽ ይገባኛል፡፡ ተማሪ ሆና አማገጣት እንዳይባል ጊዜውን ለማራቅ መሞከሩ ነበር። ጠበቃዬም ቀጠል አድርጎ፤ “ሟች የእርሶ ፍቅረኛ ከመሆኗ በፊት የአቶ አማረ ፍቅረኛ እንደሆነች ያውቁ ነበር?' ብሎ ሲጠይቀው ዶ/ር አድማሱ በንዴት፤ “ይህንን እኮ ከዚህ በፊት ተናግሬያለሁ!'' በማለት ሳያስበው በፊት እንዲያርመው የተነገረውን ስህተት ደገመው፡፡ ዳኛው በፊት የተናገሩትን ላለመናገር ፈልገው ሳይሆን አይቀርም ሌላ ቃላት ከመወርወር ይልቅ ዝም ብለው ያዩት ጀመር፡፡ ለአፍታ ያህል ዝም ካለ በኋላ፣ “እውቃለሁ፤ ነገር ግን ይህንን ያወቅሁት ከእሷ ጋር ከተዋወቀን በኋላ ነግራኝ እንጂ ከዚያ በፊት አላውቅም ነበር" አለ፡፡ ምስኪን! ውሀ ውስጥ እንደገባች አይጥ መውጪያ ሲያጣ አዘንኩለት:: ይግባኙ ውጤት ቢኖረውም ባይኖረውም በዚህ ሁሉ ሰው ፊት እንዲህ እንደ ጨው እየሟሟ ሲሄድ በማየቴ ደስ አለኝ:: ጠበቃዬ ቀጠል አድርጎ፤ “መቼም ሟች ይህንን ከነገረችዎት፣ ከአቶ አማረ ጋር እንዴት እንደተለያየች ሳትነግሮት አትቀርምና በምን ምክንያት ነበር የተለያዩት?'' ብሎ ሲጠይቅ፤ አቃቤ ሕግ ትንሽ ትንፋሽ እንዲሰበስብ እረፍት ለመጠየቅ በሚመስል መልኩ፤ “ተቃውሞ" አለ፡፡ ተቃውሞውን እንዲያሰማ ዳኛው ዕድል ሰጡት:: እሱም ጊዜ ለመግዛት በሚመስል መልኩ እየተንቀረፈፈ፤ “ይህ ጥያቄ ተጠያቂውን የሚመለከት ሳይሆን አቶ አማረ ሊመልሰው የሚገባ ጥያቄ በመሆኑ አግባብነት የለውም" በማለት ተቃወመ:: ጠበቃዬም ከተል አድርጎ፤ "ክቡር ፍርድ ቤት፤ የምጠይቀው ጥያቄ ለማቀርበው ማስረጃ አስፈላጊዬ ስለሆነ ጥያቄውን እንዲመልስ ቢፈቀድ" ሲል፣ ዳኛው ተቃውሞውን ውድቅ አድርገው ዶ/ር አድማሱ መልስ እንዲሰጥ አዘዙ። "እኔ የማውቀው ነገር ቢኖር አቶ አማረ ደካማ ተማሪ ስለነበር ለትምህርቱ ትኩረት ሰጥቶ እንዲያጠና በተደጋጋሚ ብትነግረውም ምክሯን ተቀብሎ ውጤቱን ማሻሻል ስለተሳነውና በዚሁ የተነሳ ከትምህርት ቤት
በመባረሩ የተለያዩ ይመስለኛል:: በኋላም እሷ ትምህርቷን መቀጠል ስለፈለገችና እሱም የሚመጥናት ዓይነት ግለሰብ ሆኖ ስላላገኘችው ግንኙነቷን ማቋረጧን ነግራኛለች" በማለት እኔን በማጥላላት በጠበቃዬ ላይ ቁጭቱን ለመወጣት የፈለገ በሚያስመስል መልኩ መልስ ሰጠ፡፡ አነጋገሩም ሆነ አስተያየቱ ሆን ብሎ የእኔን ስሜት ለመጉዳት ያደረገው ስለነበር እጅግ በጣም ተናደድኩ፡፡ ግን ምን ማድረግ ይቻላል? በሕግ ቁጥጥር ሥር ሆኖ መናገር ወይም መማታት በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ስለነበርኩ ልሳደብበት የከፈትኩትን አፌን ቀስ ብዬ ገጠምኩት፡፡ አባቶቻችን "ከወደቁ በኋላ መንፈራገጥ ለመላላጥ" ይሉ የለ! ጠበቃዬ ቀጠል አድርጎ፧ “የሚዋደድ ሰው መቼም በዚህ የተነሳ እስከመጨረሻው መቆራረጥ ስለማይችል ሟች ሌላ ምክንያት ነግራዎት ከሆነ ቢነግሩን" ሲል ጠየቀ፤ “እኔ ይህንን በሚመለከት አንዴ የጠየቅኋት ቢሆንም እሷ ጥያቄውን የመለሰችልኝ በንዴት መልክ ስለነበርና ዳግም ስለእሱ እንዳልጠይቃት ስለነገረችኝ፣ ከዛ በኋላም ጠይቄያት ስለማላውቅ ምንም ልለው የምችለው ነገር የለም'' በማለት መለሰ፡፡ “ማለት እነርሱን በማለያየት እሷን የግልዎ ለማድረግ በእርሶ በኩል አልሞከሩም?" ብሎ ሲጠይቅ፣ ዶ/ር አድማሱ ክው ብሎ ቀረ፡፡ በዚህ ጊዜ አቃቤ ሕግ እንደተለመደው፧ “ተቃውሞ" በማለት ትንፋሽ እንዲሰበስብ ዕድል ሰጠው:: ሲፈቀድለትም፤ “ጥያቄው መስካሪውን በማያውቀው ነገር ሆን ተብሎ እንደጥፋተኛ ለመፈረጅ የተጠየቀና ክብርሩንም የሚነካ ነው፡፡ በመሆኑም ክቡር ፍ/ቤቱ ይህን ጥያቄ እንዳይቀበለው እጠይቃለሁ" አለ:: ዳኛውም አቃቤ ሕጉን ላለማስከፋት በሚመስል መልኩ ጠበቃዬ ሌላ ጥያቄ ካለው እንዲጠይቅ አዘዙ:: ዶ/ር አድማሱ ጥያቄውን ሲጠየቅ የሚናገረው ጠፍቶት መርበትበት ሲጀምር _ አቃቤ ሕግ ጣልቃ ገብቶ ስላስቆመው እጅግ በጣም ተናደድኩ። ለመናገር የፈለገ ቢሆንም አፉን ከፍቶና ደንግጦ ስለነበር የሚመልሰውን መልስ ለመስማት ጓጉቼ ነበር። እኛን ለመለያየት ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረምና በልበ ሙሉነት የሚመልሰው መልስ እንደማይኖረው እርግጠኛ ነበርኩ። ጠበቃዬ ግን ለዚህ ብዙም ሳይጨነቅ የእኔን ጉዳይ ከሚመለከትበት

👍31❤1
ፋይል ውስጥ አንድ ደብዳቤ አውጥቶ ለዳኛው እንዲሰጥለት አደረገ፡፡ ዳኛውና አቃቤ ሕጉ የየራሳቸውን ፋይል እያወጡ ተመለከቱ፡፡የዚሁኑ ደብዳቤ ኮፒ ዶ/ር አድማሱም እንዲያነበው ተሰጠው፡፡ ዶክተሩ ከንፈሩ እየተርበተበተ በጸጥታ አንብቦ ከጨረሰ በኋላ፤
እና ይህ ደብዳቤ ከእኔ ጋር ምን ያገናኘዋል?'' በማለት ጮኸ ተናገረ:: ጠበቃዬ መልስ ሳይሰጥ በተረጋጋ መልኩ ሌላ ደብዳቤ እንዲሰጠው አደረገ፡፡ ዶ/ሩ ወረቀቱን እንደያዘ ጠበቃዬንና ዳኞቹን በየተራ አያቸው:: ፊቲ በላብ ተደፍቆ ደብዳቤውን ማንበብ ተያያዘው:: እንደጨረሰም : “ይህም ደብዳቤ ቢሆን ከእኔ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፣ ይልቁንም መጠየቅ የምትፈልገው ነገር ካለ ለምን በቀጥታ አትጠይቀኝም?" ሲል፣ ጠበቃዬ “ይህ መጀመሪያ ላይ ያነበቡት ደብዳቤ አቶ አማረ ለአልማዝ ከእንግዲህ ወዲህ እሱ ለእሷ ስለማይመጥን በፍቅር መቀጠል እንደማይፈልግና ይልቁንም ቢጤዋን ፈልጋ እንድታገባና የተሻለ ኑሮ እንድትኖር በመመኘት የጻፈውና ለመለያየታቸው መንስኤ ነው የተባለ ደብዳቤ ነው:: ሁለተኛው ደብዳቤ ደግሞ ወ/ት አልማዝ የጻፈችውና ከእሱ ጋር መቀጠል እንደማትችልና ሌላ ሚስት አግብቶ ቢኖር የተሻለ መሆኑን አስመልክቶ ጻፈችው የተባለ ደብዳቤ ነው፡፡ እንዲህ ይላል ብሎ ለችሎቱ ማንበብ ጀመረ፤ “ይድረስ ለውድ ጓደኛዬ ለአማረ አስረስ፡፡ በመጀመሪያ ለጤናህ እንደምን ሰንብተሃል:: እኔ እግዚአብሄር ይመስገን በጣሙን ደህና ነኝ:: ዛሬ የምጽፍልህን ይህን የመጨረሻ ደብዳቤዬን ስታነብ ትንሽም ቢሆን ማዘንህ እንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ:: ነገር ግን የመጨረሻው ሐዘን ይበልጥ ሊከፋ ስለሚችል ከአሁኑ መወሰን ነበረብኝና መወሰኔ አልቀረም:: እንደምታውቀው አብረን ያሳለፍናቸው የፍቅር ዘመናት ለእኔም ሆነ ለአንተ እንዲህ በቀላሉ የሚረሱ አይደሉም:: ግን ይኼ ትዝታ መቆም እንዳለበት ተሰምቶኛል:: እንደምታውቀው እኔ በዚህ አለም ላይ ካንተ የተሻለ ዘመድም ሆነ መከታ ይኖረኛል ብዬ አልገምትም:: ለዚህም ነው አብረን በነበርንባቸው ጊዜያቶች ሁሉ አንተ ሁሌም አጠገቤ ስትሆን ደስታ፣ ስትርቀኝ ሐዘን ይፈራረቅብኝ የነበረው :: ይሁን እንጂ ጊዜ ግዜን እየወለደ ሲሄድ ሕይወትን በአሰብነው መንገድ ልንመራት አልቻልንም:: እሷ በፈለገችው መንገድ እየመራችን ሳንወድ በግድ መለያየታችን ቁርጥ ሆነ:: አሁንም ጊዜ ግዜን እየወለደ ሲሄድ የማይረሳ ነገር የለምና ሁሉም ነገር ሙሉ በሙሉ ባይረሳም እንደጥንቱ ግን ሊሆን አልቻለም። አሁን ስለፍቅር ወይም ስለትዳር ከማውራቴ በፊት ራሴን ማሸነፍ እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው:: መማር አለብኝ፡፡ ብዙ ነገር የማወቅ ፍላጎቴም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መጥቷል፡፡ ከዩንቨርስቲውም በጥሩ ውጤት ተመርቄ የዶ/ር አድማሱ እርዳታና አስተዋፅኦ ተጨምሮበት ዛሬ በትምህርቴ በጥሩ ደረጃ ላይ እገኛለሁ:: ከዚህ የሚበልጥ ትልቅ ነገር የለምና ይህንን
እንደጨረስኩ ለማስትሬቴም ለመማር ወስኜአለሁ:: ግን አንተ እኔን በመጠበቅ ሕይወትህ እንዲበላሽ አልሻም:: የራስህን ሕይወት በሚመስልህ መንገድ ብትመራ የተሻለ ነው፡፡ እኔ ከእንግዲህ ወዲያ አብዛኛውን ጊዜዬን በትምህርት ስለማላልፍ ያንተ ባለቤት ልሆን በምችልበት ደረጃ ላይ አይደለሁም:: የእኔን መጨረሻ እኔ ራሴም አላውቀውም:: ስለወደፊቱ ቃል ገብቼ ቃሌን ልጠብቅ አልጠብቅ እርግጠኛ ሳልሆን ላንተ ቃል መግባቱንም አልሻም:: የወደፊቱን የሚያውቀው ጌታ ብቻ ነውና:: ስለዚህ እኔ የራሴን ውሳኔ ወስኛለሁ:: ውሳኔዬንም በምድር ላይ ሊያስቀይረኝ የሚችል ኃይል ባለመኖሩ በዚህ በኩል እንዳትደክም እመክርሃለሁ:: ለጊዜው ላስከፋህ እንደምችል ባውቅም ወደፊት ግን ጥቅሙን ትረዳለህ ብዬ በማሰቤ በሥራዬ አልተፀፀትኩም:: ሁልጊዜ ላንተ ጥሩ ነገር በማሰቤ ሳላውቅ ላሳዝንህ ብችልም፣ አንተን ለመጉዳት ሆን ብዬ የማደርገው አይደለምና እንዳትቀየመኝ:: ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ደብዳቤ ባትፅፍልኝ ደስ ይለኛል፡፡ የእኔን ሰላማዊ ሕይወት ከመረበሽ ውጪ የሚለውጠው ነገር የለምና አትድከም፡፡ የራስህን ምርጫ በጊዜ ውሰድ። በተረፈ ምን ጊዜም አልረሳህም:: ለአንተ ያለኝ ፍቅር እንዳለ እንዲቆይ ከፈለግህም _ ሃሳቤን ለማስለወጥ አትሞክር፡፡ ሁሌ የማይለይህ አምላክ ክአንተ ጋር ይሁን፡፡ ውድ ጓደኛህ አልማዝ ታፈሰ" ብሎ አንብቦ እንደጨረሰ ጥያቄ ለመጠየቅ ሲዘጋጅ፣ ዶ/ሩ ከአፉ ነጥቆ፤ “ታዲያ ይህ እኔን ምን ይመለከታል? ከእኔ ጋር ባልተያያዘ ነገር ነው ጊዜዬን የምታጠፋው" አለ። በይግባኙ ወቅት አዳዲሶቹ ተጨማሪ ማስረጃዎች ለፍ/ቤቱና ለአቃቤ ሕጉ ቀርበው ስለነበር ወረቀቶቹ እዚያም ቢሆን ተነበው ይዘታቸው ታውቋልና ጠበቃዬ ፈገግ እንደማለት ብሎ፤ "ዶ/ር፧ እርሶም እንዳዩት ሁለቱም ደብዳቤዎች ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው አቶ አማረ ጻፈው በተባለው ደብዳቤ ውስጥ ለመለያየታቸው እንደምክንያት በሟች ዲያሪ ውስጥ የተጻፈው አቶ አማረ ቢጤውን ለማግባት መወሰኑ ሲሆን፤ በዚህ ደብዳቤ ደግሞ ለመለያየታቸው ምክንያቱ ሟች ትምህርቷን መቀጠል መፈለጓ ከመሆኑ በስተቀር ደብዳቤው እምብዛም ልዩነት አልነበረውም። ከዚህ በላይ ደግሞ ሁለቱም ደብዳቤዎች ላይ ያለው የእጅ ጽሑፍ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ደብዳቤዎቹ ያለ ጥርጥር ከእርሶ ውጪ በማንም እንዳልተጻፉ ለእርሶም ሆነ ለማንም ትክክለኛ ጉዳይ አጣሪና ለሐሰት አሳዳጅ ሰው ግልጽ ነው፡፡" ሲል ዶ/ር አድማሱ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ፧
“በፍፁም ሀሰት ነው! ሀስት ነው!' እያለ ጮኸ፡፡ ፍርዱን ሲከታተል የነበረው ሁሉ ያልጠበቀውን ነገር በመስማቱ እርስ በእርሱ የሹክሹክታ ወሬ ጀመረ፡፡ እነሆ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህንን ሁሉ ዘመን ሲያስጨንቀኝ የነበረውና ያንን ሁሉ ገጽ ሳነብ ልፈታው ያልቻልኩት እንቆቅልሽ ተፈታ:: በንዴትም ሳላስበው "ወይኔ! ወይኔ! ወይኔ! ሰውየው፤ ቆይ አገኝሀለሁ!'' ብዬ ጮህኩ፡፡ ሳላስበው ተጨማሪ ወንጀል እየፈፀምኩ መሆኔን እንኳን ማሰብ ተስኖኝ ነበር:: ዳኛው በንዴት ሥነሥርዓት በማለት ጠረጴዛውን በያዙት መዶሻ መታቱት:: ዶ/ር አድማሱ ግን እየደጋገመ “ሀሰት ነው'' አያለ ሲጮህ ጠበቃዬ! “ዶ/ር አድማሱ "አጉል መፍጨርጨር ለመላላጥ ነው" እንደሚባለው እውነቱን ለማስተባበል ባይሞክሩ ጥሩ ነው፡፡ ይኸ የእርሶ የእጅ ጽሑፍ እንደሆነ በአባዲና ፖሊስ ምርመራ ተረጋግጧል” ሲል፣ አቃቤ ሕግ ተስፋ በመቁረጥ አንገቱን ደፋ፡፡ ጠበቃዬ ዶ/ሩ እንዲረጋጋ ይመስላል ጥያቄውን ለአፍታ ያህል ቆም በማድረግ ፋታ ከሰጠውና ፊቱን በመሀረብ ጠርጎ መጨረሱን ከተመለከተ በኋላ ሌላ አንድ ደብዳቤ አውጥቶ በችሎቱ በኩል አሰጠው:: ዶ/ሩ ደብዳቤውን አንብቦ እንደጨረሰ፤ “እና ታዲያ ምን ላድርገው? ይኼ የእኔ የእጅ ጽሑፍ አይደለም፤ የአልማዝ የእጅ ጸሑፍ ነው” አለ፡፡ “አዎ ልክ ነዎት፤ ይህ ጽሑፍ የእርስዎ የእጅ ጽሑፍ ሳይሆን የአልማዝ የእጅ ጽሑፍ ነው:: በዚህ እሷ ጻፈችው በተባለውና እርሶ በጻፉት ደብዳቤ መካከል ያለው ልዩነት ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም እርሶም እያረጋገጡት ነውና ክርክሩን አቁመው ይልቁንም ይህ አልማዝ እራሷን እንደገደለች የሚገልፅውን ደብዳቤ እንዴት እንደጻፈችው ቢገልፁልን የተሻለ ነው” ሲል ጠየቀ

👍36❤4🔥1
። ዶ/ሩ ከዚህ በላይ እውነትን መጋፈጥ እንዳቃተው ፊቱ ላይ ይነበባል፡፡ ወጥመድ ውስጥ የገባች አይጥ ሆኖ ግራ ቀኙን ቢያይ ምንም ማምለጪያ እንደሌለው አወቀ፡፡ ፊቱ ይበልጥ ፍም መሰለ፡፡ ለጥቂት ሴኮንዶች በዝምታ ከተዋጠ በኋላ፣ ንዴት በተናነቀው ሁኔታ ድምፁን ሁሉም እስኪሰማው ከፍ አድርጎ፤ “አዎ ገድያታለሁ" አለ፡፡ ችሎቱ በአንድ ጊዜ በታዳሚው ጫጫታ ታወከ፡፡
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍37❤4😱3