🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_21
ሕይወትን በወህኒ ቤት ከፖሊስ ጣቢያ የሚለያት ነገር ቢኖር፣ እዚህ ያለው እስረኛ ከጥቂቱ በቁጠሮ ቤት ካለውና ካልተፈረደበት በስተቀር፣ ምን ይፈረድብኝ ይሆን? በዋስ እፈታ ይሆን? ምን ያገኙብኝ ይሆን? ወዘተ ከሚለው ጭንቀት መገላገሉ ነው:: እያንዳንዱ እስረኛ የተፈረደበትን የእስራት ቀናት በልቡ ውስጥ ጽፎ አንድ ቀን በአደረ ቁጥር አንድ ቀን እየቀነስ የመውጪያ ቀኑን ከማስላት ውጪ ሌላ የሚያስጨንቀውና የሚያሳስበው ነገር የለም:: አብዛኛው እስረኛ ትምህርቱን የሚማር ስለሆነ ከዚህ ሲወጣ ስንተኛ ክፍል አጠናቆ እንደሚወጣ ያውቀዋል:: ዩንቨርስቲ አቋርጠው ወይም ዩንቨርስቲ አጠናቀው ሥራ ላይ እያሉ በተለያየ ምክንያት የታሰሩ ምሁራን ምንም ባይከፈላቸውም እስረኛውን ለማስተማር ከልባቸው ይጥራሉ፡፡ ለጥናት የሚሆን ግዜ በሽበሽ ስለሆነ ከልቡ ለመማር ለደፈረ ሰው የሕይወቱን
አቅጣጫ ሊለወጥ የሚችል ዕውቀት አግኝቶ እንደሚወጣ ጥርጥር የለውም.. ትምህርት ያገኙ ተራ ሌቦች ያገኙት ዕውቀት በመጠኑም ቢሆን በአነጋገራቸውና በባህርያቸው ውስጥ ለውጥ እያመጣ መሆኑን መመልከት ይቻላል፡፡ በብዙ መልኩ ከመጣሁበት ፖሊስ ጣቢያ ጋር ሲነፃፀር ብዙ ነገሩ እዚህ ለየት ይላል፡፡ የቤቱ ንጽህና የተጠበቀ ነው፣ ሁሉም ነገር ስርዓት አለው፣ የሚወራው ወሬም ቢሆን ብስለት አለው፡፡ እስረኛውም አብዛኛውን ጊዜውን በማውራት ሳይሆን በመማር፤ በማንበብ፣ የተለያዩ ስራዎችን በመስራትና በመጻፍ ያላልፋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ወህኒ ቤት የተለያዩ የሌብነትና የቅጥፈት ባህርያትን ተክኖ ለመውጣት አመቺ ቦታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ራሱን ለውጠ ጥሩ ዜጋ መሆን ለማይፈልግ አሥረኛ በወንጀል ሙያ ለመሰልጠን ምርጥ ኮሌጅ ነው:: በአልባሌ ሰበብ ከሰው ጋር ተጣልቶ ወይም ሳያስበው የሰው ገንዘብ ጠፍቶበት ለተፈረደበት እስረኛ ፍላጎቱ ካለው ሙያውን ለማስፋት ጥሩ የማስልጠኛ ኮሌጅ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እዚህ የማይቻል ነገር የለም:: ውጪ ያለውን ሁሉንም ነገር "ማግኘት ወይም ማድረግ" ይቻላል:: ሌላው ቀርቶ ከሴት ጋር ፍቅር መጀመር ይቻላል:: የኳስ ጨዋታ ወይም ትርዒት በሚቀርብበት ወቅት በሩቅ እየተያዩ መከሳከስ ነው:: መጀመሪያ እንደተያዩ መተፋፈር፣ ቀስ በቀስ በዓይን ሰላምታ መለዋወጥ፣ መሳሳቅና መሽኮርመም ወዘተ የተለመዱ የፍቅር ጨዋታዎች ናቸው:: እንደዚህ ባለ ሁኔታ የተገኘች ፍቅረኛ "አይኑካ ትባላለች፡፡ ታዲያ በአካል ተገኛኝቶ የልብን መወጣት ስለማይቻል የዓይኑካ ፍቅር ከሌላው ፍቅር ይልቅ የጠነከረ ነው፡፡ እኔ ለእንደዚህ ዓይነት ፍቅር ቦታ አልነበረኝም:: የማያት ሴት ስለሌለኝ የሚያዩኝ ሴቶች ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም:: ደግሞ ለእንደኔ ዓይነቱ በፍቅር መነሻ ሃያ ዓመት ተፈርዶበት ወህኒ የተወረወረ እስረኛ፣ ዳግም ላፍቅር ማለት አዲስ እርግማንን ማስተናገድ ነው:: አላርፍ ካልኩ ደግሞ ከዚህ በኋላ ፍቅር ሊያስከትለው የሚችለው መዘዝ በመሬት ላይ የሚያልቅ ሳይሆን ሲዖልም ተከትሎኝ ሊሄድ የሚችል ነውና የምመኘው አልነበረም። ሁለተኛው የይግባኝ ቀጠሮ ብዙም የሚወራለት ነገር አልነበረውም:: ጠበቃዬ ባቀረበው ይግባኝ ላይ የአባዲና የምርመራ ውጤት መምጣቱን ተከትሎ አለኝ የሚለውን ማስረጃ ከሁለት ወር ተኩል በኋላ እንዲያቀርብ በመወሰን አሰናበቱን፡ ዳኞቹ የአባዲናን የምርመራ ውጤት ከተመለከቱ በኋላ የሰው ማስረጃ እንዲያቀርብ በመፍቀዳቸው ጠበቃዬ አንድ ያገኘው ነገር በመኖሩ ነው የሚል ግምት ስላሳደረብኝ ይበልጥ መፅናናት ጀመርኩ፡፡ ጠበቃዬ ለፍ/ቤቱ ያቀረበው ማስረጃ ተቀባይነት በማግኘቱ ዞር ብሎ እያየኝ ፈገግ ስላለ
መደሰቱን ገመትኩ:: ዳሩ ግን እኔም ሳይታወቀኝ ፈገግ ብዬ ስለነበር መሳቁ አፀፋ ለመመለስ እንጂ በሌላ ላይሆን ይችላል የሚል ስሜትም አደረብኝ፡ በጊዜ ላይ ጊዜ እየጨመረ እነሆ እስር ከተፈረደብኝ ከስድስት ወር በላይ ሆነኝ:: ግን በእነዚህ ወራት ውስጥ ወንጀለኛ አለመሆኔን ሊያረጋግጥልኝ የሚችል መረጃ አለመገኘቱን ሳስብ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ያንዣብብብኛል። ዳሩ ምን ያደርጋል! እኔ ውስጥ ያለውን እውነት ለማውጣት ባያዳግተኝም እውነት መሆኑን ለማሳመን ግን አቅሙ ስለሌለኝ ሌላው በእኔ ቦታ ሆኖ እንዲያሳካልኝ ከመጠበቅ ውጪ ሌላ አማራጭ አልነበረኝምና የቀጠሮ ቀናት በመጡ ቁጥር ዛሬ እውነት ትወጣ ይሆናል እያልኩ ከመጠበቅ በቀር ላደርገው የምችል ነገር አልነበረኝም። ካለፉት ቀጠሮዎች በተለየ መልኩ ዛሬ ተስፋ ያደረኩባት የቀጠሮ ቀን ደርሳ ወደ ፍርድ ቤት ሄድኩ፡፡ ይህቺ ዕለት ከሁሉም በላይ የዘገየችብኝ ቀን በመሆኗ እያንዳንዱ ቀን የወር ያህል ሆኖ ነበር የተሰማኝ። ብዙ ተስፋ የጣልኩባት ቀን በመሆኗ ነው መስለኝ ከፖሊስ መኪናው ላይ ወርጄ ወደ ፍርድ ቤቱ ሳመራ እግሬ መብረክረክ ጀመረ:: ይህቺ ቀን የእኔን የሕይወት አቅጣጫ የምትወስን ከመሆኗም በላይ የመጨረሻ የተስፋዬ ማለምለሚያ ወይም የተስፋዬ መድረቂያ ቀን ነበረች። ማን እንደነገራቸው ባላውቅም ከሌላው የይግባኝ ቀጠሮ ቀን በተለየ መልኩ አንዳንድ የመ/ቤቴ ሠራተኞችም መጥተዋል፡፡ ይህም የመፈታት ተስፋ እንዳለኝ የሚያመላክት ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰውዬ ከተፈታ ይታዘበናል በሚል ስሜት የፍርዱ ሁኔታ ያለበትን ደረጃ ሲስሙ አንዳንዶች ወህኒ ቤት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል:: መፈታት አለመፈታቴ አንድ ነገር ሆኖ ቢያንስ ለተወሰነች ጊዜ ቢሆን እንኳ ወንጀለኛ አለመሆኔን የሚያምን ሰው ማግኘት ትልቅ ደስታ ፈጠረብኝ:: ዳሩ ድከሙ ቢላቸው ነው እንጂ እኔ ማንንም የምቀየምበት ምክንያት አልነበረኝም፡፡ ምክንያቱም እኔ ለሌላው ሳደርገው ከነበረው አንፃር እያንዳንዱ ስው ለእኔ ያደረገው እጅግ ቢበዛብኝ እንጂ የሚያንስብኝ አልነበረም፡፡ ዛሬ ፍ/ቤት የምቀርበው ሁለት አማራጭ ይዤ ነው፡፡ ጠበቃዬ በእርግጥም ጠቃሚ መረጃ ይዞ መጥቶ ከሆነና ነፃ ካወጣኝ አሰየው፡፡ ነገር ግን እንደጠረጠርኩት እኔን ለተጨማሪ የእስር ዘመን ለመዳረግ ሴራ እየገመደብኝ ከሆነ ግን፣ ጮኬም ሆነ አልቅሼ ውስጤ ያለውን ጥርጣሬ ዳኞች ለጥቂት ደቂቃ እንዲሰሙ በማድረግ፣ ቢቻል ራሴን ነፃ ማውጣት ካልተሳካም *የቻልኩትን ሞክሬአለሁ" በማለት ከወደፊት ፀፀት ራሴን ነፃ ማድረግ ነው፡፡
የቀጠሮው ሰዓት ደርሶ ሣጥኔ ውስጥ ገብቼ ድራማውን እንደተለመደው ለመመልከት በተዘጋጀሁበት ወቅት ዳኛው ጠበቃዬ አለኝ የሚለውን የሰው ማስረጃ እንዲያቀርብ ስለአዘዙ ፖሊሱ “ዶ/ር አድማሱ" ብሎ ሲጣራ ክው ብዬ ደነገጥኩ፡፡ ዶክተሩ ከፊት ለፊቴ ሆኖ ጥርሱን እየገለፈጠና በጥላቻ ዓይን እየተመለከተኝ ወደ መመስከሪያው ቦታ ሲራመድ ንዴቱ ፈንቅሎ ሊወጣ ደረሰ:: መቼም ይኼ ክፉ ሰው በምንም ዓይነት መንገድ እስሬን ለማጠናከር ካልሆነ በስተቀር እኔን ለማስፈታት የሚሆን ማስረጃ ሊኖረው አይችልም:: ጠበቃዬ ሆን ብሎ ወንጀሌን ለማጠናከር የሚያደርገው መሆኑ ስለገባኝ እጅግ ጠላሁት፡፡ ጠበቃዬ እኔ እንዳልፈታ የሚሸርበው ሴራ ለእጮኛው የሚያበረክተው ገፀ በረከት ነውና ብዙም ባልናደድበት፤ ይህንን ሰውዬ አምጥቶ እኔን ለማናደድ የሚያደርገው ድርጊት ግን እጅግ በጣም አበሳጨኝ:: ያም ሆነ ይህ አንዱ አማራጭ ካልተሳካ ሌላውን መሞከሬ ስለማይቀር ራሴን አረጋግቼ አባላንጣዬ ጋር ፊት ለፊት በጥላቻ ዓይን መተያየቱን ተያያዝነው:: ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ማድረግ የማይታሰብ ነው፡፡ ምንም ያህል ብናደድ ያለኝ አንድ አማራጭ እዚሁ ቆሜ ነድጄ እስከማልቅ ድረስ ውስጥ ውስጡን መቃጠል ነው፡። መሃል ዳኛው ከሁለቱ ዳኞች ጋር