አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አድካሚው የእግር ጉዞ ወደ መኪና ተቀይሯል፡፡ ተሳፍረው ወደ ድኬል ፣ ከድኬል ወደ አርታ ፣ ከአርታ ወደ አልሰቢ ፣ ከአልሰቢ ወደ ጅቡቲ

የኢትዮጵያ መኪናዎች ማረፊያ ፣ ከጅቡቲ አቢካዱስ ፣ ከአቢካዱስ አርባ ከመኪና ወደ መኪና እየተገለባበጡ ቀጥለዋል፡፡

አርባ የአበሾች ሰፈር ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩበት አካባቢ ማለት ነው፡፡ ከስደተኞች መካከል አርባ ላይ የቀረው ቀርቶ የተቀሩት ደግሞ ይማም እና እነ ተመስገንን ጨምሮ በአካባቢው አጠራር ቦድ ሃይቅ ተብሎ በሚታወቀው የመሸጋገሪያ ሃይቅ ከአርባ በጀልባ ወደ ተጎሪ አመሩ፡፡

አንድ ጀልባ አሳፍራ ለመሻገር የሚፈቀድላት አርባ ሰው ነው፡፡ ጀልባዋ ግን ከአቅሟ በላይ ስልሳ ሰዎችን ጭናለች፡፡ አልቻለችም ፤ ስትጓዝ ግራና ቀኝ ትዋዥቃለች፡፡ የተሳፈሩት ስደተኞች በቦድ ሃይቅ እየወደቁ የሰው ልጅን ከእነህይወቱ ለአዞ ምሳና እራት እየመገበች መጓዟን ቀጥላለች፡፡

ከአሁን አሁን ገባን እያሉ በስጋት ተውጠዋል፡፡ ተደጋግፈው ፣ እንደሙጫ ተጣብቀው ጀልባዋ ስትዋዥቅ አብረው ይዋዥቃሉ፡፡ የቦድን ሃይቅ ሊጨርሱ ተቃርበዋል፡፡

እንደሙጫ ከተጣበቁበት ተነጣጠሉ፡፡ ተመስገን ራሱን ችሎ ለመቆም ሞከረ፡፡ ጀልባዋ ድንገት ወደ ግራ የፈራው አልቀረም፡፡ እንደጓደኞቹ የቦድን ሃይቅ ለመቅመስ ተገልብጦ ገባ፡፡ እድላዊት ጮኸች ፣ አባረቀች፡፡ ተመስገን ካይኗ ተሰወረ፡፡ ሰከንዶች ከተቆጠሩ በኋላ የገባበት ውሃ ተንቀሳቀሰ፡፡ አንገቱ ብቅ አለ፡፡

እየተንቦጫረቀ ወደ ዳር ወጣ፡፡ እዳር ላይ መግባቱ አጋጣሚ ከቦድ አዞ ሊተርፍ ችሏል፡፡

የቦድን ሃይቅ እንደጨረሱ ተጎሪ ገቡ፡፡ ተጎሪ አላረፉም ፤ ከጀልባ ወደ መኪና ተሳፍረው ጉዟ ወደ ሃዩ ቀጠሉ፡፡

ሃዩ የጅቡቲ መሬት አልቆ የሳውዲ አረብያ የመግቢያ መዳረሻ ከተማ ናት፡፡ ሃዩ እንደደረሱ ሳይውሉ ሳያድሩ ከመኪና ወደ ጀልባ ተዛውረው የመን ፣ ከየመን

ሃሙስ ከተማ ከሃሙስ ከተማ ፣ በመኪና ጅዳ ፣ ከጅዳ መካ መዳረሻቸው ሆነ፡፡

በጅዳም ሆነ በመካ ስራ ለመቀጠር ደላላ ያስፈልጋል፡፡ ወንድም የሚቀጠረው በበረሃ የግመል እረኝነት ሲሆን ሴቶች ደግሞ አበባ ማጠጣት ካልሆነ በስተቀር በከተማ ውስጥ መታወቂያ ስለሌለ

ተንቀሳቅሰህ ስራ መፈለግ አይደለም መታየትም አይቻልም ነበር፡፡

ተመስገን በመካ ጫካ ውስጥ እንድላዊትን ከሌሎች ስደተኞች ጋር አስቀምጦ ከይማም ጋር ስራ ፈልገን እንመጣለን እዚሁ ጠብቁን ብለው በመካ ጫካ ለጫካ አድርገው ወደ ሪያድ ስራ ፍለጋ ተጓዙ፡፡

ይማም በአፋር ክልል ተወልዶ ያደገ ሲሆን በመጠኑም ቢሆን አረበኛ መናገር ይችላል፡፡ በበረሃ የሚያገኙትን እረኞች እያነጋገረ ሪያድ ደረሱ፡፡ ስራ አልተገኘም፡፡ ወደ መካ ተመለሱ፡፡

ታዲያ ጓደኞቻቸው እና እድላዊትን አስቀምጠዋቸው የሄዱበት ጫካ ውስጥ አላገኟቸውም ነበር፡፡

ተመስገን የሚይዘውና የሚጨብጠው አጣ፡፡ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡የመካ ፖሊሶች ይዘዋቸው ወደ እስር ቤት ሄደው ይሆናል፡፡ ማልቀሱን ተውና በዚህ ጋር ወጥተን ሰው እንጠይቅ፡፡ ብሎት ተያይዘው የመካን ጫካ ወጥተው አስፓልት ደረሱ፡፡ በመካ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰዱ፡፡

እድላዊትና ጓደኞቿ በጉዞ ላይ የቆሰለ እግሮቻቸውን እያሻሹ እና እየተለቃቀሱ ነበር፡፡ ከየት እንደመጡ ሳይታወቅ ድንገት እንደ መብረቅ ቁጣ ጡንቻቸው ፈርጣማ ፈርጣማ ገና ሳይጠጉ ከሩቅ የሚያስፈሩ ዘጠኝ ወጣቶች ከተቀመጡበት አስነስተው የወሰዷቸው፡፡

መግባቢያ ቋንቋ አልነበራቸውም፡፡ በምልክት እየተነጋገሩ እድላዊትን ጨምሮ አራት ሴቶችንና ሶስት ወንዶችን ይዘው ወደ አስፓልት የወጡት፡፡ በራሳቸው መኪና አሳፍረው ትንሽ እንደተጓዙ ነበር፡፡ መኪናውን አቆሙት፡፡

ሶስቱን ወንዶች አስወረዱዋቸው፡፡ ያልቆመችውን መኪና እንዲገፉ አዘዙዋቸው፡፡ ሶስቱን የኢትዮጵያ
ለግላጋ ወጣቶች ገና አንድ እንጀራ እንኳን በልተው ያልጠገቡ ፤ ከሃገራቸው ያልፍልናል ብለው በበርሃና በውቅያኖስ አልፈው ፤ ከወንበዴና ከአዞ

ህይወታቸውን አትርፈው ፤ ጓደኞቻቸው ስራ ሊፈልጉ እንደሄዱ ፤ ከአሁን አሁን ይመጣሉ፡፡ እያሉ ሲጠባበቁ ስራ ፍለጋ የሄዱት
ተመስገንና ይማም ሳይመጡ ፤ በመካ ዱርየዎች ታፍነው መኪና ሲገፉ መኪናው እነሱን ትቶ የመካ አስፓልት ላይ ትተው ሄዱ እድላዊትንና ሶስቱን ሴቶች ይዘው ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡

በሪያድ በርሃ እንሰሳት እንኳን በማይፈፅመው ወሲባዊ አፈፃፀም እየተፈራረቁ ደፈሯቸው፡፡ ተዝለፈለፉ ፣ ትንፋሽ አጠራቸው ፤ ደከሙባቸው፡፡ ለሞት ሲጣጣሩባቸው መኪናቸውን አስነስተው ዘጠኙ ወጣቶች ጥለዋቸው ተበታተኑ፡፡

የተፈራረቀባቸው የመንገድ ስቃይ እና ውሃ ጥም ሳያንሳቸው የመካ ዱርየዎች ግብረሰዶም አልቀራቸው ምግብና ውሃ አጥቶ በሚማፀነው አፋቸው የወሲብ መፈፀሚያ ሲያደርጉት ከአራት ሴቶች አንዷ ወዲያውኑ ህይወቷ አለፈ፡፡

ሶስቱ ሴቶች እድላዊትን ጨምሮ ሞት እንዲወስዳቸው በሪያድ በርሃ የጣረሞት ይጮሃሉ፡፡

በአካባቢው የፀጥታ አካላት የሰው ጩኸት ሰምተው ወደ ጫካው ሲገቡ አራቱም ሴቶች በግንድ ስር ለየብቻቸው ተጥለዋል፡፡ አንዷ ህይወቷ አልፋል፡፡

ሶስት ሴቶች ለመሞት ይጣጣራሉ፡፡ ገመናቸውን እንኳን መሸፈን አቅቷቸዋል፡፡ እግራቸው
ተበረጋግዷል፡፡ በተለይ እድላዊት አጥንት ከየቦታው የመለቃቀም ያህል አንስተው ከሪያድ በርሃ በመኪና ጭነው ወደ መካ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዷቸው፡፡

የመካ ፖሊስ ጣቢያ የኢትዮጵያ ስደተኞን መታወቂያ የሌላቸውን ከየቦታው እየለቃቀመ 375 እስረኛ ሴትም ወንድም ጨምሮ ታስረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ሊሞላ 25 ሰው ቀርቶት ተጨማሪ ስደተኛ ይጠባበቃል፡፡

ከአራት ቀን በኋላ፤ 4ዐዐ ሰው የኢትዮጵያ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ሞልቶ ከመካ ፖሊስ ጣቢያ ወጥተው ወደ እናት ሃገራቸው በረራ ጀመሩ፡፡

ተመስገንና እድላዊት በመካ ፖሊስ ጣቢያ አንድ ላይ ቢታሰሩም የሴት እና የወንድ ክፍል ለየብቻ ስለነበር አልተገናኙም፡፡ ሃገራቸው ቦሌ አዲስ አበባ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሰውም እንኳን አልተዋወቁም ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር መዝጋቢ የነበረው ይመር በመዝገቡ ላይ ስማቸውን ሲያሰፍር ከ4ዐዐ ስደተኞች መካከል የሁለት ልጆች አባት ስም ተመሳሳይ ሆነበት፡፡ ለማጣራት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተመስገን ብሎ ተጣራ፡፡

"አቤት አለ ተመስገን፡፡

"ከአንተ ጋር አብሮህ የሄደ ቤተሰብ ነበረህ እንዴ"? አለ ይመር ፤

"አዎ ፤ እህቴ እድላዊት የምትባል አብራኝ ሄዳ ፤ እዛው ጠፍታብኛለች ፡ቦሌ አየር ማረፊያ ስደተኞችን ሲቀበሉ ሴትና ወንዶችን ለየብቻ አድርገዋቸው ነበር፡፡ ወንዶቹ ከድብደባ በስተቀር የደረሰባቸው ጉዳት ብዙም አልነበረም፡፡ ከሴቶቹ ቀላል የማይባል ድብደባና
መደፈር የደረሰባቸው ቦሌ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በአፋጣኝ የህክምና እርዳት ሊደረግላቸው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከተላኩት ሰላሳ አምስት ሴቶች መካከል አንደኛዋ እድላዊት ነበረች፡፡

"አብራህ እንደመጣች አታውቅም ማለት ነው"?

"አላውቅም ፤ አብራ ከእኛ ጋር መጥታለች እንዴ" ? አለ፡፡ በተደበላለቀ ስሜት ተውጦ፡፡

"አዎ መጥታለች ፡፡ አሁን ትንሽ ጉዳት ደርሶባት ስለነበረ ህክምና ሄዳለች፡፡ ከህክምና ስትወጣ አብረሃት ትሄዳለህ አለው፡፡

ታዲያ ተመስገን አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በኢትዮጵያ ፖሊስ ታጅበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ወደሚሰጥበት ጣቢያ ሲገቡ እድላዊትንም ወደ ህክምና ስትሄድ አይደለም ከአየር ስትወርድም ነበር፡፡
👍327😢7
የኢትዮጵያ የስደተኞች ማህበር ለስደተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቶ ገንዘብ ለሌላቸው የገንዘብ ድጋፍ እና ደብዳቤ በመስጠት ወደ መጡበት ክፍለ ሃገርና ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ
ሲደረግ ጉዳት የደረሰባቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና ተረድተው በተመሳሳይ የሚደረግላቸውን የመድሃኒት ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመለሱ፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 11ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍241
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

ወንጀሉ በተፈፀመ በ15ተኛው ቀን ለአለማየሁ ደውሎለት ነበር፡፡

‹‹ሄሎ አሌክስ..እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ..አንተስ..?ሰፍር ?እነሰሎሜ ደህና ናቸው?››

‹‹ሁሉም ሰላም ነው….አንተ ጋርስ? ስልጠናው እንዴት ነው?››

‹‹ከባድ ነው.. ግን ያው ስፖርት ስለምወድ…ለእኔ ብዙም አልከበደኝም፡፡››

‹‹ጥሩ…..››

‹‹ምነው የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ ?ድምፅህ እኮ ጥሩ አይደለም…ሰሎሜ ምን ሆነች?››

‹‹አይ እሷ ደህና ነች..አባቴ ነው፡፡››

‹‹አባትህ ምን ሆኑ?
አመማቸው?››

‹‹አልታመመም..ግን የሆነ ወንጀል ሰርቷል..ያንን ወንጀል መስራቱን እኔ ብቻ ነኝ ማውቀው..አሳልፌ ለፖሊስ ልስጠው ወይስ ዝም ብዬ ልቀመጥ? ግራ ገብቷኛል…ምክር እንድትሰጠኝ ነው የደወልኩት..በዚህ ጉዳይ ላይ አንተን ብቻ ነው የማምነው፡፡››

‹‹ምን አይነት ወንጀል ?ከባድ ነው?››

‹‹በጣም ከባድ….እጅግ በጣም ከባድ…በእድሜ ልክ ወይም በሞት የሚያስቃጣ ወንጀል፡፡››

‹‹ግን እኮ አላዛር..አባትህ ትልቅ ሰው ናቸው..በዚህ እድሜቸው የእስር ቤትን ህይወት አይችሉም ..ወዲያው ነው የሚሞቱት…ለመሆኑ ወንጀሉ ምንድነው?››

‹‹የእንጀራ እናቴን ታስታውሳታለህ?››

አላዛር ስለእንጀራ እናቱ ሲያነሳ አለማየሁ ጠቅላላ ሰውነት ጆሮ ነው የሆነው፡፡ፈራ ተባ እያለ‹‹አዎ አስታውሳታለው..ምን ሆነች?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አርግዛ ነበር››
የሚያውቀው ነገር ቢሆንም በተሳሰረና በተወለካከፈ ድምፅ   ‹‹በእውነት….?እሱን አላውቅም ነበር››አለው፡፡

‹‹አዎ እኔም አላውቅም ነበር…እና ያረገዘችው ከሌላ ሰው ነው፡፡››

‹‹ከሌላ ሰው ?ከማን …?›

‹‹እሱን እኔ አላውቅም ..አባቴም የሚያውቅ አይመስለኝም….››

በሚርገበገብ ድምፁ በፍራቻ ‹‹እና ምን ተፈጠረ…?››ሲል ጠየቀው፡

‹‹አባቴ ልጁ የእሱ እንዳልሆነ በምን መንገድ እንደሆነ አላውቅም አወቀና ..እርጉዟን ሚስቱን ገደላት››

‹‹ምን ?ገደላት….››

‹‹አዎ ገድሎ የማላውቀው ቦታ ቀብሮታል….አሁን እሱም ሀገር ጥሎ ጠፍቶል..እና ምን እንዳደርግ ትመክረኛለህ?፡፡››

አለማየሁ በሰማው መርዶ የደነገጠው ድንጋጤ መጠን የሌለው ነው..እናትና አባቱ የሞቱ ሰሞን እንኳን እንደዛ አይነት ፍፅም ቀዝቃዛ ሀዘን አልተሰማውም ነበር ‹‹እሳቸው ሳይሆኑ እኔ ነኝ የገደልኩሽ፡፡››ሲል አሰበ፡፡

ድምፅ የጠፋበት አላዛር‹‹አሌክስ እየሰማሀኝ ነው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አላዛር ይቅርታ ይሄ ጉዳይ ከባድ ስለሆነ ላስብበትና ነገ ልደውልልህ?››አለው፡፡ከንግግሩ ድምፀት  የስሜቱን  መሰባበርን መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እሺ በቃ በደንብ አስብበት..ወንድሜ በጣም ተጨንቄልሀለው፡፡››

‹‹እሺ ጠንከር በል አይዞህ…ቸው፡፡››

አለማየሁ ስልኩን እንደዛጋ ወዲያው ያደረገው ነገር ሲሙ ላይ ያሉትን አድራሻ ወደቀፎው በማስተላለፍ  ስልኩን ከፍቶ  ሲሙን አውጥቶ መሰባበር ነው፡፡
ይሄ የእሱ ጥፋትና መዘዝ ስለሆነ ማንም ላይ ለመፍረድ ሆነ ለማንም ምክር ለመስጠት መብትም ሆነ ብቃት እደሌለው አምኗል፡፡በህይወት ውስጥ ያለውን እድል አሰበና ምርር ብሎ ነበር ያለቀሰው ፡፡መቼም ቢሆን ከማንም ሴት ጋር ፍቅር ፍቅር ላለመጫወትና ረዘም ያለ ግንኙነት ውስጥ ላለመግባት ወሰነ፡፡ከአላዛርም ሆነ ከሰሎሜ ከዛም አልፎ  ከአደገበት አካባቢ ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋረጠ…በብቸኝነት በሶስት ወርም ሆነ በስድስት ወር አንዴ ደውሎ እንዴት ነሽ? ሚለው አሳዳጊ እናቱን  እቴቴን ብቻ ነበር፡፡

አላዛር  ግን ከአለማየሁ ምንም አይነት መልስም ሆነ ምክር ባያገኝም ከፀፀቱ ጋር ህይወቱን ቀጠለ….አባትዬውም በሄዱበት የት እንደገቡ ሳይታወቅ ጠፉ፡፡አላዛር አንገቱን ደፍቶ ትኩረቱን ስራው ላይ አደረገ፡፡በንግዱ ጠንካራ ሰራተኛ ሆነ..፡፡

ከማትሪክ በኃላ  ወደተግባረ እድ የሞያ ማሰልጠኛ ተቋም  ገብቶ የጀመረውን ኮንስትራክሽን ትምህርት አጥብቆ ገፋበት  ..ከሰሎሜ ጋር የነበራቸውም ጓደኝነት ልክ እንደወትሮ ግለቱን እንደጠበቀ ቀጠለ፡፡ እንደውም ከአራት ጓደኛሞች ሁለት ብቻ ስለቀሩ በተሻለ መተሳሰብና በመረዳዳት   ትምህርታቸውን  መማር ብቻ ሳይሆን በህይወትም መተጋገዝና መረዳዳት  ቀጠሉ፡፡እሷ ብቸኛ ስራዋ የጀመረችን የአካውንቲንግ ትምህርት መማር ብቻ ሲሆን እሱ ግን ልክ እንደተለመደው ሁለት ኃላፊነት ነበረበት፤  እየተማረ   ንግዱንም በጎን ማስኬድ ፡፡ ሱቁ እየሰራ..በጎንም ሌሎች ተባራሪ ስራዎች እየሰራ ቀጠለ፡፡እንዲህ እንዲህ እያለ ጊዜ መብረር ጀመረ ፡፡
በዚህ ጊዜ ሁሉ ሁሴን በአመት አንድ ጊዜ እየመጣ በክረምቱ የዩኒቨርሲቲ ዝግ ወቅት  ለአንድ ወር አብሮቸው ያሳልፍ ነበር፡፡በዛን ጊዜ ታዲያ ነገሮች ሁሉ የተለየ ገፅታ ይኖራቸዋል፡፡ከበፊቱ በተለየ አብረው ማሳለፍ..ብዙ መዝናኛ ቦታዎች አብረው  መሄድ ..ሌሎች ለወደፊት ትዝታ የሚሆኑ ኩነቶችን መፍጠር በአጠቃላይ አሪፍ በሚባል  ጣፋጭ ጊዜ ያሳልፈና መልሰው ወደዩኒቨርሲቲ ይልኩታል፡፡

የሆነ የህይወት ጉዞ መጀመር ነው እንጂ ሚከብደው አንዴ ቆራጥ ውሳኔ ወስነው መንገድ ውስጥ ገብተው እግር ማንቀሳቀስ ከጀመሩ  እንቅፋትና ኮረኮንች ከመሀከል ቢያስቸግርም መንገዱ ማለቁና ካሰቡት መዳረሻ መደረሱ አይቀርም ፡፡በተለይ በዚህ ዘመን ሳዕታት እንዴት እንደሚስፈነጠረሩ… ቀናቶች እንዴት እንደሚከንፉ ወርና አመታት እንዴት እንደሚበሩ አይታወቅም፡፡መስከረም፤ጥቅምት….ብለን ሀምሌና ነሀሴ ላይ እንዴት እንደምንደርስ ያስገርማል፡፡ እናም አላዛርና ሰሎሜም የጀመሩትን የኮሌጅ ትምህርት ብዙም ሳይሰላቹና መቼ ባለቀ ሳይሉ ለምረቃት በቁ፡፡ …ሁሴንም እረፍቱን አስታኮ ለምርቃታቸው አዲስአበባ ነው የሚገኘው፡በዛም ምክንያት ምርቃታቸው በጣም ደማቅና በማይረሳ ትዝታ የታጨቀበት ሆኖ እንዲያልፍ ሆኗል…ሶስቱም በየልባቸው አለማየሁም በሆነ ምክንየት ስለምርቃታቸው ሰምቶ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋቸው ሶስት አመት ከተደበቀበት ድንገት ብቅ ብሎ ያስደምመናል ብለው ይጠብቁ ነበር፡፡ያ ምኞታቸው ግን እውነት ሊሆን አልቻለም፡፡በተለይ ሰሎሜ አለማየሁን በተመለከተ  ሙሉ በሙሉ  ተስፋ የቆረጠችበት ወቅት ነበር፡፡‹‹በቃ በዚህ ጊዜ ሊያየን ካልመጣ መቼም ወደህይወታችን ተመልሶ ላለመምጣት ወስኗል ማለት ነው፡››ስትል ደመደመች፡፡…በዛም ምክንያት እሷም እስከወዲያኛው ስለእሱ  ረስታ ህይወቷን ወደፊት መቀጠል እንዳለባት ወሰነች፡፡፡ሁሴን ምርቃታቸውን በደስታና በፈንጠዝያ አብሮቸው አክብሮ ወደዩኒርሲቲው ሊመለስ ቀናቶች ነው ቀሩት፡፡ ከመሄዱ በፊት ግን  ብዙ ጊዜውን ሁለት ጓደኞቹ ጋር ነው የሚያሳልፈው፡፡አሁን በምሽት ከአላዛር ጋር ሆቴል ተቀምጠው እየተዝናኑ ነው፡፡ሰሎሜ አብራቸው የለችም፡፡

‹‹ሁሴኖ በእውነት ምርቃታችንን በጣም ነው ያደመቅክልን….› አለው አላዛር፡፡የተናገረው ከልቡ ነው፡፡እስከአሁን ምርቃታቸውን በተመለከተ ያደረገላቸውን ነገር አንስቶ የማመስገኑን እድል አላገኘም ነበር፡፡

‹‹ምን ነካህ ወንድሜ..አንተም አንተ ነህ..ሰሎሜም ያው የምታውቃት ነች…ቢቻል ለእናንተ…››

‹‹አይዞኝ በሚቀጥለው አመት በዚህን ጊዜ  ያንተን ምርቃት  ደረጃውን በጠበቀና በሚመጥንህ መልኩ ነው የምናከብረው፡፡››

‹‹አይ ..እኔ ተመርቄ የደካማ እናቴ ህይወት ለማስተካከል እንጂ ለምርቃቱ ጋጋታ ምንም አይነት ኢንተረስት የለኝም››ሲል ትክክለኛ ፍላጎቱን ሳይደብቅ ነገረው፡፡
👍6013
‹‹አውቃለሁ…ግን እኛ እያለንልህ ደግሞ ከጓደኞችህ በታች አትሆንም…አሁን እንደምታየው ትምህርት የሚሉት ጣጣ የለብኝም..ሙሉ ጊዜዬም ሆነ ትኩረቴ ወደ ስራ ነው…እና ከአሁኑ ቃል ልግባልህ የሱፍ ምናምን ወጪ እንዳያሳስብህ….ሁሉም በእኔ ነው፡፡››

ሁሴን እንባው ግጥም ብሎ በአይኖቹ ሞላ…‹‹አላዛር አንተ እኮ የተለየህ ሰው ነህ…እስከዛሬ፦ ያደረክልኝ ነገር እኮ መቼም የምረሳው አይደለም…አንተ ባትኖር በአመት አንድ ጊዜ መጥቼ የእናቴን አይን እንኳን ማየት አልችልም ነበር፡፡››

‹‹ባክህ አንተ ደግሞ አታካብድ..ለአንተ ብዬ መሰለህ..ስትናፍቀኝ እኮ ነው… መጥቼ ከማይህ መጥተህ ብታየን ይሻላል ብዬ  ነው የትራንስፖርት የምልክልህ፡፡››

‹‹ተወው በካህ…ለማንኛውም አመሰግናለሁ..በተለይ እኔ በሌለሁበት እናቴን ስለምትንከባከብልኝ የዘላለም ባለውለታዬ ነህ፡››

‹‹ባክህ አሁን ርዕስ ቀይር…በምስጋና ጋጋታ እያስደበርከኝ ነው፡፡››

‹‹እሺ ስለምን እናውራ…?››
‹‹እኔ እንጃ …ያው እንደድሯችን በመሀከላችን ንግስቷ ከሌለች ወሬያችን ስለምንድነው የሚሆነው?››

‹‹የታወቀ ነው ..ስለእሷው ነዋ…››

‹‹እና ስለእሷ ማውራት አትፈልግም?››

‹‹በጣም ፈልጋለው ግን ፈርቼህ ነው…በመሀከላችሁ ያሉ ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ሁሴን አላዛርን ጠየቀው፡፡

‹‹ያው ነገሮች እንደድሮው ባሉበት እንደቀጠሉ ነው…እሷን ከራሴም በላይ ባፈቅራትም ለጓደኝነታችን ታላቅ ክብር አለኝ…እስከአልከው ጊዜ እጠብቃለው…ልክ የዛሬ አመት አንተ ተመርቀህ ስትመጣ ..የዛን ጊዜ በተስማማነው መሰረት የውስጥ ህመማችንን እኩል እንነግራታለን…ከዛ እሷ ትወስናች››

‹‹ጥሩ ነው..ግን የአሌክስ ጉዳይስ?››ዘወትር የሚያሳስበውን ጉዳይ አነሳበት፡፡

‹የአሌክስ ምን?››

‹‹ያው ቃል-ኪዳኑ  የሶስታችንም ነው ብዬ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነህ..ቃል ኪዳኑ ሶስታችንንም ይመለከታል፡፡ግን  እስከአሁን እንደምታየው አሌክስ ሙለ በሙሉ ከእኛ ጋር ያለውን ግንኙነት ካቋረጠ ሶስት አመት አልፎታል…ምን አልባት አዲስ ነገር ተፈጥሮ በዚህ አንድ አመት ውስጥ የሚመለስ ከሆነ ጥሩ ሶስታችንም ንግስቲቱ ፊት ፍቅሯን ለማግኘት ለተማፅኖ እንቆማለን…እስከዛ እራሱን እንደሰወረ በዛው የሚገፋበት ከሆነ ግን ምን ማድረግ እንችላለን..ተፎካካሪዎቹ እኔና አንተ ብቻ እንሆናለን ማለት ነው፡፡››ሁሴንም በሀሳቡ በመስማማት ‹‹ትክክል ነህ..ሌላ ምን ምርጫ ይኖረናል?››አለው፡፡

‹‹አዎ ማድረግ ምንችለው ያንን ብቻ ነው፡፡››

ሁሴን ፀጉሩን በጣቶቹ አከክ አከክ አደረገና ‹‹ግን አንድ ጥያቄ ጠይቅሀለው እያልኩ..ቆይ አሁን እንደማያት ጭራሽ እየጎመራችና እያማረባት ነው…ሌላ አፈቀርኳት ብሎ ከእጃችን ሊሞጨልፋት የሚሞክር ጩሉሌ የለም እንዴ?››ሲል የዘወትር ስጋቱን ተነፈሰ፡፡

‹‹እሱማ የት ይጠፋል….ግን እንደምታውቀው ስንወጣም ሆነ ስንገባ አንድ ላይ ነው…እኛ ከአንደበታችን አውጥተን ባንናገርም ሰው እንደጓደኛሞች ብቻ አይደለም የሚመለከቱን ስለዚህ አብዛኛው አይኑን የጣለባት ጎረምሳ በሩቁ ተስፋ ቆርጦ ያቆማል..አንዳንዱ አይን አውጣ ቢጤ ገፍቶ ልጠጋት ካለ ደግሞ በዚህም ብዬ በዛ አደብ እንዲገዛ አደርጋዋለሁ፡፡››

‹‹ያ ማለት ጓደኛዋ ብቻ ሳትሆን ቦዲ ጋርዷ ጭምር ነኝ በለኛ››

‹‹አዎ በትክክል ገልፀኸዋል…ምን አልባት ወደፊት ቀኑ ሲደርስ ከእኔ ይልቅ ከሁለት አንዳችሁን ከመረጠች የዚህን ሁሉ አገልግሎቴን ክፍያ መክፈል ይጠበቅባችኃል››

‹‹አዎ ..በእውነት ይሄ ተገቢ ጥያቄ ነው››ብሎ መለሰለት ና ተሳሰቁ፡፡
ከዛ በሶስተኛው ቀን ከሰሎሜ ጋር ሆነው ሁሴንን ወደዩኒቨርሲትው ሸኙት፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 11 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍5113🎉1
አትሮኖስ pinned «#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ ================ ወንጀሉ በተፈፀመ በ15ተኛው ቀን ለአለማየሁ ደውሎለት ነበር፡፡ ‹‹ሄሎ አሌክስ..እንዴት ነህ?›› ‹‹ሰላም ነኝ..አንተስ..?ሰፍር ?እነሰሎሜ ደህና ናቸው?›› ‹‹ሁሉም ሰላም ነው….አንተ ጋርስ? ስልጠናው እንዴት ነው?›› ‹‹ከባድ ነው.. ግን ያው ስፖርት ስለምወድ…ለእኔ ብዙም አልከበደኝም፡፡›› …»
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

የተዳፈነ እሳት

ከሁለት አጉል ሆነች፡፡ እንደ ባህር ላይ ኩበት ተንሳፈፈች፡፡ ከባለቤቷ ወይም ከቤተሰቦቿ ሳትሆን ቀረች፡፡ ባለቤቷ ለገበያ እንደሄደ ወደ ውትድርና መግባቱን ሰማች፡፡ የመኖር ተስፋዋ እንደ ተዳፈነ እሳት ውስጧ ተንቦገቦገ፡፡ የጨለማ ተከናነበ፡፡ ከባለቤቷ ጋር ሰርታ የመለወጥ ተሰፋዋ ከማህል ተቀጨ፡፡ የኑሮዋ መሻሻል ከጨለማ የመውጫ መንገድ ሳይሆን የጨለማ መግቢያ ሆናት፡፡ ቤተሰቦቿ ባላወቁት ጉዳይ አይንሽን ላፈር አሏት፡፡

ታዲያ አበበች አስቀድማም እንደሚገጥማት ብገምትም ለሰው መልካም ነገር ማድረግ ግን እንደዚህ የእሳት እረመጥ ይሆንብኛል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡ አንዴ ያደላትን የመከራ ፅዋ ተጎንጭታ፡፡ ገና እናትና አባቱን እንኳን በደንብ ካለየ ህፃን ልጇ ጋር ያለ ዘመድና ያለ አይዞሽ ባይ ባዶ ቤት ለመኖር ተገደደች፡፡ ስታለቅስ ውላ ስታለቅስ ብታድርም ከልጅዋ በስተቀር አብሯት የሚያለቅስ ሰው አይደለም ወደ ቤቷ ዝር ብሎ አይዞሽ የሚላት እንኳን አልነበረም፡፡

ከእለታት አንድ ቀን የያሬድ አጎት አቶ አስፋው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የኔነሽ ጋር ቡና አፍልተው እየጠጡ ነው፡፡

"እንዴው ያችን የያሬድ ባለቤት ሳንጠይቃት ምን ትለን ይሆን ? ቤተሰቦቿም እደጃችንም እንዳትደርሽ ብለዋታል አሉ፡፡ ያሬድም ብቻዋን ባዶ ቤት አዳፍኖባት ወዶ ዘማች መሄዱ የሚገርም ነው" አሉ፡፡ አቶ አስፋው ፤ በጉንጫቸው ላይ የወረደውን ረጃጅም ፂማቸውን በእጃቸው እየደባበሱ፡፡

"ምን ተጠየቀች አልተጠየቀች ምን ጎሎባታል፡፡ ያለውን ንብረት ጥሎላት ነው የሄደው፡፡ እሷን ደግሞ ማን ይጠይቃታል፡፡ እቤት ተቀምጣ ባሏን ሳይሞት በቁሙ የገፋች ገፊ" አሉ፡፡ ምንም አዘኔታ እንኳን ሳይታይባቸው፡፡ ግን የአበበችን በደልና ስቃይ ቢያውቁ ኖሮ እንደዚህ ባልተናገሩ ነበር፡፡
አቶ አስፋው በሰል ያሉና ብዙ ውጣ ውረዶችን በትንሹም ቢሆን መከራና ስቃይን ያሳለፉ በመሆናቸው ለተጎዳ ሰው የሚያስቡና ትህትና ያላቸው ማለፊያ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው፡፡ የባለቤታቸው ንግግር አልተዋጠላቸውም፡፡

አይ! አንች ከንቱ መሆንሽ ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ የችግርን ነገር ስለማታውቂው አይፈረድብሽም፡፡

የአንች ነገር በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት እንደ ሚባለው ነው፡፡ በአንች ላይ ቢደርስብሽ ያኔ በደንብ ታውቂው ነበር አሉ፡፡

ምን የተባለውንና የተወራውን ነው፡፡ የተናገርኩት በእሷም የተነሳ አይደለም እንዴ፡፡ ወንድሟ ያሬድን ለመግደል እያደፈጠ ሲስተው የነበረው፡፡ ታዲያ ይህ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው አይደለም አሉ፡፡ ስኒ አጣጥበው እረከቦት ላይ እያደረጉ፡፡

"ዝም ብለሽ በማታውቂው ነገር ትዘላብጃለሽ፡፡ ያሬድ የተሳሳተው በራሱ ልክስክስነት እንጂ በአበበች ጥፋት አይደለም፡፡ እሷ ምን አጠፋች ባሌ ዲቃላ ቢወልድም እሱ ይሻለኛል፡፡ ስላለች አይደለም አባቷ አይንሽን ላፈር ያሏት፡፡ ለማንኛውም ምንም ቢሆንዐተዋልደናልና የእሷ ቤተሰቦች እንኳን ቢጠሏት ደግሞ በራሳችን ጥፋት ልንሸሻት አይገባም፡፡

ደግመውም ሌላ ንግግር ሳይነጋገሩ በይ እስቲ አሁን በቁሜ ቢሆን ደረስ ብዬ ልምጣ ብለው ዘንጋቸውን ይዘው ተነስተው ወደ አበበች ቤት ሔዱ፡፡

ቤቱ ተዘግቶ በግቢው ውስጥ ሰው አይደለም ከብትም አላገኙም፡፡ አቶ አስፋው፡፡ ወዴት ሔዳ ይሆን ? ቆይታ ይሆን ከሄደች ? እያሉ ግራ በመጋባት ከራሳቸው ሐሳብ ጋር እየተሟገቱ ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡

አበበች ልጇን አዝላ ውሃ ቀድታና ከብቶቿን አጠጥታ ከወንዝ ስትመጣ ከአቶ አስፋው ጋር እመንገድ ላይ ተገናኙ፡፡

"ደህና ዋልሽ አበበች" ? አሏት አቶ አስፋው፡፡

እግዚአብሔር ሰላም ዋሉ ? አለች፡፡ አይኗን ወደ አቶ አስፋው አትኩራ እየተመለከተች፡፡

"እኔ እኮ እቤት ሄጄ ቤቱ ተዘግቶ ሳይ የት ሄደች ብየ ስመለስ ነው ያገኘሁሽ" አሉ፡፡

"ምን ላድርገው አንዴ ያደለኝን ከብት እንኳን የሚያጠጣልኝ ሰው አጣሁ፡፡ ችግር ሲደርስብኝ እንኳን ዞር ብሎ የሚያዬኝ ጠፋ፡፡ እግዚአብሔርም ጨከነብኝ አለች፡፡

"እኔም ዛሬ ነገ እያልኩ ሳልመጣና ሳልጠይቅሽ ቀረሁ፡፡ ብትቀየምም ዛሬ አይቻት ልምጣ ብዬ ነው የመጣሁት፡፡ ሰው በቁሙ ካልተረዳዳ ከሞተ በኋላ ዋይ ዋይ ቢሉት ተመልሶ አይመጣም፡፡ እንዴው ሰራተኛ አላገኝሽም ኖሯል? አሉ፡፡

አይ! ጋሸ አስፋው የት አገኛለሁ ሰራተኛ የሚገኘው ከሰው ሲገናኙ ነው፡፡ እኔ ከሰው አልገናኝ፡፡ ዘመዶቸም ጠልተውኛል፡፡ አሁን ደግሞ አዝመራ እየደረሰ ነው፡፡ ማሳውን ማን እንደሚያርስልኝ ጨንቆኛል፡፡ ብን ብየ እንዳልጠፋ ይሄን ጨቅላ ልጅ አቅፌ መሄዱ ከበደኝ፡፡… ልማደኛው እንባዋ ተናንቋት አለቀሰች፡፡

በቃሽ አታልቅሽ ተይ፡፡ አንች እያለቀስሽ ምንም የማያቀውን ህፃን አታስለቅሽ፡፡ ያሬድም እንደሆነ ይመጣል፡፡ ወዶ ዘማች የሄደ ሁሉ አይሞትም፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ዛሬ ቢጨልምም ነገ መንጋቱ አይቀርም፡፡ አይዞሽ፡፡ አዝመራውም ይዘመራል፡፡ ነገ ወደ ሸንኮራ ዮሃንስ መሄዴ ስለማይቀር ሰራተኛ እዠልሽ እመጣለሁ፡፡

ደግሞም የሚቸግርሽ ነገር ካለ እኔም ቢሆን እየመጣሁ አግዝሻለሁ፡፡ በነጋ በጠባ ቁጥር ማልቀስ ጥሩ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርም አይወድም፡፡ እባክሽን ለልጅሽ ስትይ አታልቅሽ፡፡ አንችም ያለ እድሜሽ በሽታ ላይ ትወድቂያለሽ፡፡ ብለው አፅናንተዋት ተነስተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ትንሽ የነበረባት የጭንቀት ጨለማ ፈገግ ያለ መሰላት፡፡ አቶ አስፋው አይዞሽ ብለዋት ሲሄዱ፡፡ ባለቤቷ ወዶ ዘማች በመግባቱ መልሳ በህይወት የምታገኘው ግን አልመስል አላት፡፡ ፈገግ ብሎ የነበረው የጨለማ ብርሃን መልሶ ይጨልምባታል፡፡

አበበች ሁለተኛ ልጇን መፀነሷን የታወቃት ያሬድ በሄደ በሁለተኛው ሳምንት የወር አበባዋ ሲቋረጥ ነበር፡፡

አቶ አስፋው ለአበበች በገቡላት ቃል መሰረት ሰራተኛ አግኝተው ቀጠሩላት፡፡ ባለቤቷ ያሬድ እንደነበረው ጊዜ የተደላደለ ህይወትን ባትኖርም በባዶ ቤት ሆና ከምታለቅሰው የተሻለ ህይወት መኖር ጀመረች፡፡
የቤተሰቦቿ መጥላት ሳያንሳት የተመስገን እናት ወ/ሮ አሰገደች ሲወጡና ሲገቡ የባልሽን ዲቃላ አሳዳጊ አደረግሽኝ ፡፡ ባልሽም ዲቃላውን እንዳይወስድ የሰራው ስራ አሳፍሮት አገር ለቆ ጠፋ፡፡ እያሉ አላስገባ አላስወጣ አሏት፡፡ አበበች ግን አልቅሳ ዝም ከማለት ውጭ ምንም ምላሽ አልነበራትም፡፡

ጉልላት የተባለው የአበበች ሰራተኛ ትንሽ ጠና ያለና ነብስ አወቅ ያደረገ ነው፡፡ አበበች ስታለቅስና ስትበሳጭ አይዞሽ እያለ እያፅናና ያበረታታል፡፡

ጉልላት ለሁሉ ታዛዥ ቅን ሰው ለመሆኑ ደከመኝ ሰለቼኝ ሳይል ሲያገለግላት ላየውና ለተመለከተው የእናት ልጅ እንኳን እንደሱ አድርጎ የሚሰራ አይመስልም ነበር፡፡

አበበች ባለቤቷ ያሬድ ከሄደ ከዘጠኝ ወር በኋላ አንድ ቀን በእለተ ሐሙስ በጥዋት ተነሳች፡፡ የሚሸጥ ስንዴ ቋጠረች፡፡ ለጉልላት ገበያ ልልከው አስባለች፡፡ ይሔን ስንዴ ሽጥና አንዳንድ ነገሮችን ግዛልኝና ና፡፡ እኔም ቀኔ ደርሷል ብላ የሚገዙትን የእቃ ዓይነቶች ነግራ ቁርሱን አብልታ ወደ ገበያ ላከችው፡፡
👍533
ወገቧን እየቆረጠማት መነሳትና መቀመጥ አልቻለችም፡፡ ከብቶቹን ወደ ወንዝ ወስዳ ውሃ ለማጠጣት አቅሟ አልፈቀደም፡፡ ጉልላትም ቶሎ ከገበያ ሳይመጣ ቆየባት፡፡ ለከብቶቹ ለቤት የመጣላትን ውሃ አውጥታ ሰጠቻቸው፡፡ የገበያውን መንገድ ስትመለከት ቆይታ ወደ ቤት ገባች፡፡ ህመሟ ባሰባት፡፡ እቤቱ ወለል ላይ የበግ ምንጣፍ ነጠል አድርጋ ደገፍ አለች፡፡ ሰውነቷን ጨፈጨፋት ፤ ቆረጣጠማት፡፡ ዘጠኝ ወር በሆዷ ውስጥ ተሸክማ የኖረችው የማይቀረው ምጥ መጥቶባታል፡፡ የሚያዋልዳት ከዘመድ ቢሉ ዘመድ ፣ ከጎረቤት ቢሉ ጎረቤት እንኳን የላትም፡፡ ጭንቅ መጣ፡፡ ማንን ትጥራ ብቻዋን ማማጥ የግድ ሆነባት፡፡ ልጇ ምትኩ አይኖቹ ተንከራተቱ ፡፡ እማዬ እማዬ እያለ ሲያለቅስ የሚሰማ ጎረቤት ቢኖር ይደርስ ነበር፡፡ ያለ አዋላጅ ወንድ ልጅ ተገላገለች፡፡ ግን እትብቱን ማን ይቁረጥላት ሰው አጣች፡፡ ነብስ ግቢ ነብስ ውጭ ሆነ፡፡

ጉልላት ከገበያ ተመልሶ ከቤት አካባቢ ደርሷል፡፡ የልጅ ጩኸት ሰማ፡፡ እየሮጠ ወደ ቤት ገባ፡፡ አበበች የቤቱ ወለል ላይ ተዘርራለች፡፡ የፈሰሳት ደም የቤቱን ወለል አጥለቅልቆታል፡፡ የእግር መርገጫ እንኳን አልነበረም፡፡ ገዝቶት የመጣውን እቃ በቁሙ
ዘረገፈው፡፡ ምላጭ ከደረት ኪሱ አወጣ፡፡ እትብቱን በጠሰላት፡፡ ህይወቷ ከሞት አፋፍ ላይ ሊተርፍ ቻለ፡፡ ሰው እንኳን ቢጠላትም እግዚአብሔር የወለደውን አይጥልምና ደረሰላት፡፡ ሴትም ወንድም ሆኖ የሚሰራ ሰራተኛ ጉልላትን ስለሰጣትም አብዝታ እግዚአብሔርን አመሰገነች፡፡ በጉልላት እጅ ታርሳ የልጇን ክርስትና አወጣች፡፡ የልጁም ስም ሁሉባንተ ተባለ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose



#ZOO  የX-Empire ፕሮጀክት...9 ቀን ብቻ ቀረው
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113
👍354
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር  በግንባታ ሰሎሜ ደግሞ በአካውንቲንግ በሌቭል 3 ከተመረቁ ወራቷች ተቆጠሩ፡፡   ሰሎሜ  ስራ ለመቀጠር መባከን ብትጀምርም አላዛር ግን ለመቀጠር  ሙከራ አላደረገም፡፡ቀጥታ  ስራውን ነው አስፋፍቶ የቀጠለበት፡፡
ከምረቃው ከሶስት ወር በኃላ ሰፈራቸው በኮሪደር ልማት ምክንያት እንደሚነሳ ተነገራቸው ፡፡በአንድ ወር ውስጥ ኮዬ ፈጬ ኮንደሚኒዬም ምትክ ቤት ተሰጣቸውና ወደእዛው እንዲዘዋወሩ ተደረገ፡፡ለሁለቱም ቤተሰቦች የተሰጣቸው ቤት አንድ ህንፃ ላይ ከመሆኑም በላይ አንድ ፍሎር ላይ ነው፡፡ሰሎሜና እናቷ ይሄ አጋጣሚ በመፈጠሩ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የተሰማቸው፡፡ የሚኖሩበት ቤት በየወሩ ኪራይ የሚከፈልበት የቀበሌ ቤት ቢሆንም ግን ደግሞ በተለይ ሰሎሜ እድሜ ልኳን የኖረችበት ሙሉ ትዝታዋ ያለበት.. የሳቀችበት.. ያለቀሰችበት የታመመችበት የዳነችበት የህይወቷን ጠቅላላ ታሪክ ተፅፎ የታተመበት ቤት በመሆኑ ስሜቷን ድፍርስርስ ነው ያደረገባት… ቢሆንም ግን አሁን በምትክ የተሰጣቸው ቤት የተሻለ ጥራት ያለው በመሆኑ  እንደማካካሻ ቆጥራ በፀጋ ተቀበለችው፡፡
ለአላዛር ግን ልክ እንደሎተሪ ነው የቆጠረው፡፡ግድ ሆኖበት እንጂ ያንን ተወልዶ ያደገበትን ቤት አይወደውም..ከዛ ቤት ጋር በተያያዘ ካለው አስደሳች ትዝታ በእጥፍ ሀዘኑና ቁጭቱ ይበዛል፡፡በተለይ ቀጥታ አባቱን ስለሚያስታውሰው  ሁሌ እንደቀፈፈውና የመቃብር ቤት አይነት ስሜት እንዲሰማው እንዳደረገው ነው፡፡እንደውም ከእዚህ ቤት ለመገላገል ሲል የራሱን የሆነ ቤት ለመግዛት የተለየ የባንክ ደብተር ከፍቶ ብር ማጠራቀም ከጀመረ አመት አልፏታል …፡፡ስለሆነም ዜናውን በደስታ ነው የተቀበለው፡፡ከዛ   ቀጥታ ያደረገው የሱቅ ስራውን ላለማቋረጥ እዛው አካባቢ ሌላ ሱቅ በመከራየት እቃውን ወደእዛ ማዘዋወረና እቤቱን በደስታ አስረክቦ ወደኮዬ ፈጬ ጠቅልሎ ገባ፡፡በጣም አሪፉ አጋጣሚ  ደግሞ በዛው ሰሞን በጣም የሚወዱት   አያትዬው ህይወታቸው ስላለፉ ከበፊት ጀምሮ የልጅ ልጃቸውን  ጥረቱና ትጋቱን ያዩ ስለነበረ ጠቀም ያለ የውርስ ገንዘብ ትተውለት ሞቱ ፡፡ከዛ ደረጃ 6 የኮንትራክተርነት ፍቃድ አወጣና የግንባታውን ዘርፍ ተቀላቀለ፡፡
///
ወደኮዬፌጬ ተዘዋውረው መኖር ከጀመሩ ከሁለት ወር በኃላ ነው፡፡
ስራ ውሎ ድክም ብሎት ወደ እቤት ገብቶ ሶፋው ላይ ጋደም እንዳለ በሩ ተቆረቆረ…በቅልጥፋና ሄዶ ከፈተው..እንደገመተው  ሰሎሜ ነበረች፡፡

‹‹ግቢ›› አላትና በራፉን ክፍት ትቶላት ወደ ውስጥ ተመለሰና ሶፋው ላይ ተቀመጠ፡፡

በራፉን ዘጋችና ወደውስጥ ዘልቃ ዘላ ሶፋው ላይ በመውጣት ከጎኑ ተወሸቀች፡፡

ስሩ በመቀመጧ እና ሰውነቷ ከሰውነቱ በመነካካቱ በውስጡ እርካታ እየተሰማው በአንደበቱ ግን

‹‹ካልጠፋ ሶፋ ለምን ታጨናንቂኛለሽ?››አላት ፡፡

እንደማኩረፍ ብላ‹‹ጉረኛ ..አግኝተህ ነው?››አለችው ፡፡

‹‹አረ ባክሽ….?ለመሆኑ እንዲህ በተለየ ሁኔታ እየተፍለቀለቅሽ ያለሽው በምን ምክንያት ነው?››

‹‹ውይ በእቴቴ ሞት ያስታውቅብኛል እንዴ?››

‹‹በደንብ ነዋ…አንቺ እኮ ነሽ… ደስታሽም ሆነ ሀዘንሽ በግልፅ ነው ፊትሽ ላይ የሚፃፈው…ለመሆኑ ምን ተገኘ…?ብቻ ስራ አገኘሁ እንዳትይኝ?››

‹‹አንተ ደግሞ…እንዴት ብዬ ነው ስራ ማገኘው…ያው እዛው ካፌ እየሰራሁ ነው፡፡››

‹‹እና ምንድነው?››

‹‹ፍቅር ያዘኝ››

‹‹ምን?›› ብሎ በመደንገጥ ከጉልበቱ ላይ አሽቀንጥሮ አስነሳትና  እግሮቹን ከሶፋው አውርዶ  ቁጭ ብሎ አፈጠጠባት፡፡

አደነጋገጡ አስደነገጣት‹‹እንዴ ምን ያልኩህ መስሎህ ነው….?ፍቅር ያዘኝ እኮ ነው ያልኩህ››

‹‹ሰማሁሽ እኮ!!››

‹‹አይ አልሰማኸኝም.ኤሌክትሪክ ያዘኝ እንዳልኩህ እኮ ነው አደነጋገጥህ?››

‹‹እንዴ ምን ነካሽ? ኤሌክትሪክ ቢይዝሽ ይሻላል …አሁን ኤሌክትሪክ ቢይዝሽ ቆጣሪው አውቶማቲክ  ስለሆነ ቶሎ ያጠፋል… ለጊዜው ተንዘርዝረሽ ወዲያው ታገግሚያለሽ…ፍቅር ግን ለዛውም በዚህ እድሜሽ!!››

‹‹በዚህ እድሜሽ….!ምን ለማለት ነው?››

‹‹ምን አስቸኮለሽ ለማለት ነዋ››

‹‹ሰውዬ..ስንት አመቴ ነው ታውቃለህ?››

‹‹እኔ እንጃ …ሀያ መሰለኝ››
‹‹አይደለም ሀያ ሶስት….ከእናንተ ጓደኛ ተብዬዎች ጋር ስንዘላዘል ተላልፎብኛል…››

‹‹እሺ ለመሆኑ አውቀዋለሁ….ማነው?››

‹‹ታውቀዋለህ….እስራኤል ነው››

‹‹እስራኤል …እስራኤል?››

‹‹ኮሌጅ እያለን አስተማሪያችን የነበረ፡፡››

‹‹እ እሱ ነው››አለ ቀዝቀዝ ብሎ ፡፡ተማሪ እያሉም አይኑን ይጥልባት እንደነበረ ታዝቧል…አሁን ኮሌጁን ሙሉ በሙሉ ለቀው ከተለዩ በኃላ በየት ዞረው እንደተገናኙ ምንም ሊገባው አልቻለም…፡፡

‹‹እና ምን ትላለህ?››
‹‹ምንም…በዚህ ዘመን አስተማሪ  ማግባት ግን ጥሩ ነው?››አላት፡፡ይህን ያላት አስቦበት ሳይሆን ድንገት የሆነ ነገር ብሎ ጉዳዩን መቃወም ስላለበት ነው አፉ ላይ የመጣለትን የተናገረው፡፡

‹‹ምን ለማለት ነው ..?አስተማሪ ሰው አይደለም እንዴ…?.ደግሞ አፈቀርኩት አልኩህ እንጂ ላገባው ነው አልኩህ እንዴ?፡፡››

‹‹ያው ነው..ዛሬ ካፈቀርሺው ነገ ላግባው ማለትሽ ይቀራል?››

‹‹እና ብልስ ምን ችግር አለው?››

‹‹አይ ምንም ችግር የለውም..ከነጭ ድህነት ወደ ጥቁር ድህነት መሸጋገር ነው የሚሆንብሽ ብዬ ነው፡፡››

‹‹ብሽቅ የሆንክ ነገር ነህ፡፡ሰው ሁሉ አንደአንተ ብራም መሆን አለበት…?ፍቅር ደግሞ በገንዘብ አይገዛም››

‹‹ባክሽ እሱ ጊዜ ያለፈበት የድሮ አባባል ነው..በዚህ ዘመን  ፍቅር ድብን አድርጎ በገንዘብ ይገዛል..እናም ደግሞ ድህነት የነበረን ፍቅር አባሮ ከልብ ያስወጣል፡››

‹‹እሱ ያንተ እምነት ነው..ለማንኛውም አፍቅሬዋለው.. ስላፈቀርኩትም በጣም ተደስቼለሁ..ደግሞ እኮ አንተም በእኔ መደሰት በጣም የምትደሰት መስሎኝ ነበር ዜናውን ላበስርህ እየበረርኩ የመጣሁት፡፡››አለችው በቅሬታ፡፡

..አፍቅሬዋለሁ እያለች ስታወራ ፊቷ ላይ ያለው ብርሀን ልዩ ነው፡፡‹‹ምን አለ እኔን አፍቅረሽ አብረን እንዲህ በደስታ ብናብረቀርቅ››ሲል በውስጡ አጉረመረመ፡፡እና እንደምንም እራሱን አረጋጋና ለእሷ ንግግር መልስ ይሰጥ ጀመረ‹‹ደስታሽ እንደሚያስደስተኝ አንቺም  ታውቂያለሽ…ግን ደግሞ ለአንቺ የምመኝልሽ ዘላቂ ደስታ ነው…ዛሬ ለሳቅሽ ምክንያት የሆነ ነገር ነገ ሀዘን ላይ እንዲጥልሽ ለአልፈልግም….ለዛ ነው ሁሉን ነገር በጥንቀቃቄ እና በእርጋታ እንድትይዥው የምፈልገው፡፡››

እሷም ለስለስ አለችና ‹‹ለእኔ አስበህ እንደሆነ እኮ አውቃለው…ግን አታስብ እጠነቀቃለሁ…በል አሁን ቤት ስራ አለብኝ..እቴቴ ሳትጠራኝ ልሂድ››አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጩን ስማ ወደውጭ መራመድ ጀመረች…፡፡

አይኖቹ አብረዋት ተንከራተቱ….፡፡በሰማው መርዶ የዛለ ሰውነቱን እንደምንም ጎትቶ ከተቀመጠበት ተነሳና በራፉን ከውስጥ ቀርቅሮ ወደቦታው ተመለሰ፡፡30 ለሚሆኑ ደቂቃዎች በድንዛዜ አሰበ….ከዛ የሆነ ነገር አድርጎ ይሄንን ጉዳይ ማኮላሸት እንዳለበት ድምዳሜ ላይ ደረሰና .ስልኩን አነሳ፡፡ አንዳንድ ጉዳዬችን የሚያስፈፅምለት ልጅ ጋር ደወለ ስልኩ ተነሳ‹‹‹እንዴት ነህ…ከመሸ ደወልኩ ይቅርታ››

‹‹ሰላም ነኝ አላዛር ….ችግር የለውም….ምን ልታዘዝ?››

‹‹ለአንተ የሚሆን አንድ ስራ ነበረኝ፡፡››
‹‹ምንድነው?››
👍5211👎1
‹‹እኔ የተማርኩበትን ኮሌጅ ታውቀዋለህ አይደል..?እዛ የሚያስተምር እስራኤል የሚባል አስተማሪ አለ…ፎቶውን አሁን በቴሌግራም ልክልሀለው…እና ሙሉ ታሪኩን ታጠናልኛለህ….በተለይ የሰራቸው ያልሆኑ ነገሮች ካሉ እነሱ ላይ ትኩረት አድርግ….፡፡››
‹‹እሺ..አደርጋለሁ፡፡››
‹‹በቃ..ዝርዝሩን ነገ ተገናኝተን እናወራለን..አደራ በጣም አስፈላጊ ስራ ነው…ጥሩ ከፍልሀለው፡፡››
‹‹አረ ችግር የለውም… አላዛር ለአንተ ማንኛውንም ስራ በደስታ ነው የምሰራው ፡፡››
አልአዛር ስልኩን ዘጋና ቀጥታ ወደአልጋው ነው የተጓዘው፡፡
‹‹እርግጠኛ ነኝ ማንኛውም ሰው የሆነ ጊዜ እና የሆነ ቦታ የሰራው አንድ ስህተት አይጠፋውም..ያንን ማንም እንዲያውቅበት የሚፈልገውን ድብቅ ገበናውን አገኘሁ ማለት ….በቀላሉ ከሰሎሜ ህይወት አስወግደዋለው ማለት ነው››ሲል አሰበ፡፡
መተኛት ከወሰነ በኃላ ሀሳቡን ቀየረና ስልኩን ካስቀመጠበት መልሶ አነሳው ..ደወለ….
‹‹እሺ ሁሴን ..መቼስ በዚህ ሰዓት ተማሪ አይተኛም ብዬ ነው የደወልኩልህ፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነህ አልተኛሁም….እያጠናሁ ነው፡፡››
‹‹የሆነ ነገር ልነግርህ ነበር….››
መደንገጡን በሚያሳብቅ ድምፅ ‹‹ምነው እናቴ ምን ሆነች?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አረ እሷቸው ሰላም ናቸው›››
‹‹አይ ሰሞኑን ስደውልላት እያመመኝ ነው ስለምትለኝ ምን ተፈጥሮ ይሆን ብዬ ደንግጬ ን››ሲል አብራራለት፡፡
‹‹አይ ቢራቢሯችንን የተመለከተ ወሬ ልነግርህ ነበር››
‹‹እሺ እየሰማሁህ ነው..እሷን በተመለከተ ምን ተፈጠረ?››
‹‹አሁን ቤት መጥታ ነበር…..እና  አንተ መስማት የማትፈልገውን ነገር ነግራኝ ነው የሄደችው››
‹‹ምን? አፈቅርሀለው አለችህ እንዴ?››አለው በድንጋጤ፡፡
‹‹አይ እኔን ቢሆንማ በደስታ አብድ ነበር..››
‹‹ታዲያ አንተን ካልሆነ ማንን ነው?››
‹‹አንድ ኮሌጅ ያስተምረን የነበረን አስተማሪ ነው፡፡››
‹‹አንተ ምን አይነት ነገር  ነው እየነገርከኝ ያለኸው….እሺ ምን ይሻለናል?፡፡››
‹‹እንዲህ አሳድገን ለማንም ጩሉሌ አሳልፈን የምንሰጣት ይመስልሀል?››
‹‹እኮ ምን ልታደርግ አሰብክ?››ሲል ደግሞ ጠየቀው፡፡
‹‹ለእኔ ተወው..የደወልኩልህ እንዲሁ መረጃውን እንድታውቀው ነው….በሆነ መንገድ ከፊታችን ገለል እንዲል አደርጋለሁ፡፡››
‹‹ጥሩ …ያንን በመስማቴ ደስ ብሎኛል..ለነገሩ ከአራት ቀን በኃላ ቅዳሜና እሁድን አስታክኬ ለአንድ ለአራት ቀን መምጣቴ አይቀርም፡፡››
‹‹ምነው በሰላም?››
‹‹አይ ሰላም ነው ..የእማዬ ጉዳይ አሳስቦኛል..በአይኔ ካላየኋት ተረጋግቼ መማር አልችልም፡፡››
‹‹‹ጥሩ…ታዲያ መሳፈሪያ ልላክልህ፡፡››
‹‹አይ መምጫ አለኝ…ባይሆን መመለሻውን አስብበት፡፡››
‹‹አብሽር…..አንተ ብቻ በሰላም ና፡፡››
‹‹እሺ ደህና እደር፡፡››
‹‹ደህና እደር››ብሎ ስልኩን ዘጋውና ቀለል ብሎት ለመተኛት መብራቱን አጠፋፋና አንሶላውን ተከናነቧ አይኑን ጨፈነ፡፡
ከአራት ቀን በኃላ ሁሴን ከዩኒቨርሲቲ መጥቶ ተቀላቀላቸው… .ግን እንደጠበቁት ጥሩ ጊዜ አላሳለፉም፡፡በመጣ በሁለተኛው ቀን ታመው የነበሩት እናቱ አረፉ፡፡ያልተጠበቀና አሳዛኝ  ክስተት ነበር፡፡ሁሴን ከሚገባው በላይ ነው የተሰባበረው፡፡እናትዬው በህይወቱ ውስጥ ያሉ ብቸኛ  ዘመዱ ነበሩ፡፡በህይወት የሚያጋጥመውን ሁሉ ችግርና መካራ በእናቱ ፍቀር ነበር እየታገለ ሚያሸንፋቸው፡፡በትምህርቱ ከፍተኛ ትጋት  አንድ ሴሚስተር እስኪቀረው ድረስ አንድ ቢ ብቻ ሲገባበት በኤ ጀምሮ በኤ ሊጨርስ ከጫፍ የደረሰው  ‹‹በምድር ላይ ለእናቴ ልዩ ገነት እገነባላታለሁ..እድሜ ዘመኗን ያሳለፈችውን ችግርና የስቃይ ህይወት ጭራሽ እስክተዘነጋው ድረስ አንደላቅቄ አኖራታለሁ›› በሚል ምኞት ነበር፡፡አሁን ግን እጅግ ቅስም ሰባሪ ሀዘና አጋጠመው…‹‹ቢያንስ ምን አለ ለዘመናት ስትጓጓለት የነበረውን የመመረቂያ ቀኔን እንኳን ብታይ…እንዴት ተጨማሪ ሶስት ወራት መቆየት ያቅታታል?››የሚለውን ጥልቅ ድረስ እያሰበ የተሰቃየበት ጉዳይ ነበር፡፡
እነአላዛርን ጨምሮ የሰፈሩ ሰው ተሯሩጠው አስቀበራቸው፡፡ሰሎሜም ሆነች አላዛር ከስሩ ሳይለዩ ለአራት ቀን አብረውት ሲያስተዛዝኑትና ሲያፅናኑት ቆዩ፡፡በ5ተኛው  ቀን‹‹  በቃኝ ልሂድ›› ብሎ ተነሳ፡፡አላዛር አብሬህ ተከትዬህ ልሸኝህ ብሎት ነበር፡፡ሁሴን ግን ፍቃደኛ ሊሆን አልቻለም፡፡‹‹ከአሁኑ በጥንካሬ መቆምና ከሁኔታው ጋር ራሴን ማለማመድ አለብኝ..እሰከመቼ ትከተለኛለህ››በማለት እምቢ አለው፡፡ከዛ አላዛርና ሰሎሜ አብረው  ቦሌ ድረስ በማጀብ  በፕሌን ሸኙት፡፡ሲሸኙት ሁለቱም ለምርቃቱ እንደሚመጡና እንደሚያስመርቁት ቃል ገብተውለት ነበር፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 9 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍60😢84
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ሚስጥሩ

ከአራት ዓመት ከውጊያ በኋላ፡፡ እንደ ማንኛውም የሰራዊት አባላት ዓመታዊ የወር ፍቃድ ደረሰው፡፡ የታጠቀውን የመንግስት መሳሪያ ለቅርብ አመራሩ አስረከበ፡፡ የፍቃድ ወረቀት ተቀበለ፡፡ የትግል አጋሮቹ ወደ ቤተሰቦቹ ሸኙት፡፡

የወርሃዊ ፍቃድ የተሰጠው እለት አራት አመታትን እንዳልቆየ ባለቤቱንና ልጁን ቶሎ ደርሶ ለማየት አንድ ቀን ሌሊት አልነጋ አለው፡፡ ካሳለፈው አራት ዓመታት በላይ በአይኑ ላይ እንቅልፍ የሚባል እንኳን ሳያልፍ ፍጥጥ ብሎ አነጋ፡፡ የሌሊቱ እንቅልፍ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ ከመኪና ወንበር እያወዛወዘ ያላትመዋል፡፡

ያሬድ ከሁለት ቀን የመኪና ጉዞ በኋላ፤ አመሻሽ ላይ የትውልድ ቀየው ደረሰ፡፡ ሰፈሩ ሁሉ ዓዲስ ሆነበት፡፡ አካባቢው ተቀያይሯል፡፡ ተገረመ ፤ ከቤቱ አካባቢ
ዳገቱ ላይ ሻንጣውን አውርዶ አረፍ አለ፡፡ አይኖቹን በእሱ ቤት ላይ ተከላቸው፡፡ የእሱ ቤት ሰርቶት እንደሄደ አላገኘውም፡፡ የጣራው ሳር እረግፏል፡፡

የግቢውም አጥር ወላልቋል፡፡ በውስጡ ሰው ያለበት አይመስልም፡፡ ቤተሰቦቹን የሚያገኝ አልመስል አለው፡፡ ሆዱ በፍራት ተዋጠ፡፡ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ ወደ ወላለቀውና ፈራረሰው ቤቱ ተጠጋ፡፡

ከቤቱ ደጅ ላይ ሁለት ወንድ ህፃናት ልጆች እየቦረቁ ይጫወታሉ፡፡ አትኩሮ ተመለከታቸው፡፡ አንደኛው ህፃን ትልቅ እና ሰውነቱ ለወጥወጥ ቢልበትም የራሱ ልጅ ምትኩ እንደሆነ አልተጠራጠረም ነበር፡፡

ሁለተኛው ህፃን ግን የማን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ ወደ ሚጫወቱት ህፃናት ተጠግቶ ልጁን ምትክ ምትኩ? ብሎ ተጣራ፡፡ ህፃኖቹ የራስ የራሳቸውን እየተጨዋወቱ ከስራቸው ተጠግቶ የቆመውን ያሬድን አላዩትም ነበር፡፡ ህፃን ምትኩ መጫወቱን ትቶ ቀና አለ፡፡ በሰውነቱ ግዙፍ የሆነ ሰው አዬ፡፡ አባቱ እንደሆነ አያውቅም፡፡ ፈርቶ የወንድሙን የሁሉባንተን እጅ እየጎተተ ሸሽተው ወደ ቤት ገቡ፡፡
ምን ሁናችሁ ነው የምትሮጡት? ውሻ አባረራችሁ እንዴ ? አለች አበበች፡፡ ልጆቿ እየሮጡ ሲገቡ ደንግጣ፡፡

"ህፃን ምትኩ በተቆራረጠ ትንፋሽ ውሻ አይደለም ፤ መጥቷል" አላት፡፡

"የማን ሰው ነው የመጣው" ?፡፡

"አላውቀውም ሲያዩት ያስፈራል፡፡ ውጭና እይው እውጭ ቁሟል አላት፡፡ ውጭ ውጭውን እየተመለከተ፡፡

አበበች ውጭ እና እይው ሲላት የባሰ ድንጋጤ ጨመረባት፡፡ የሚያስፈራ ሰው ደግሞ ከየት መጣብኝ፡፡ እንዲያው አምላኬ ምን ልታሰማኝ ይሆን? ቤቴን ሰው አያውቀው፡፡ እንዲያው ሰርታ በላች ብለው ሊጨርሱኝ ይሆን? ከሰው ጋርም ባይሆን ከራሷ ጋር ያወራችው ነበር፡፡

ወደ ውጭ ብቅ አለች፡፡ እውነትም የሚያስፈራ ሰው ነው፡፡ የውጩን በር ከፍቶ ገባ፡፡ ሰውነቷ ተርበተበተ፡፡ የሚያስፈራው ሰውየ እየቀረባት መጣ፡፡
ለአራት አመታት የተለያት ባለቤቷ ያሬድ ነው፡፡ ማመን አቃታት፡፡ለመራመድ እግሮቿ ተሳሰሩ፡፡ አይኖቿ ያሬድ ላይ እንደተተከሉ በናፍቆት እንባ ተሞሉ፡፡

አበበች በደረሰባት ስቃይና መከራ ተጎሰቋቁላለች፡፡ የሃያ አምስት አመት ወጣት መምሰሏ ቀርቶ የአምሳ አመት አሮጊት ሆናለች፡፡ ያሬድ አዘነ፡፡ እያለቀሰ ተጠመጠመባት፡፡ ቤቱ ከሃዘን እንባ ወደ ደስታ እንባ ተቀየረ፡፡ አበበች የደረሰባትን ስቃይና መከራ እንዲሁም ባለቤቷ ያሬድ ከሄደ ስለወለደችው ልጅ ሁሉባንተ አጫውታው ልጁም የራሱ እንደሆነ ነግራው አምኖ ተቀብሏት ፡፡ ያሳለፉትን ናፍቆትና ትዝታ እያስታወሱ ሲለቃቀሱና ሲያወሩ ቢቆዩም ስለተደበቀው ሚስጢር ምንም ነገር ሳያወሩ አድረው በማግስቱ ጥዋት ነበር፡፡

ቡና ተፈልቶ "እንዴት አደረግሽው ያንን ነገር ያላት ?

"የቱን ነገር ? አለች ጥያቄው ግራ አጋብቷት፡፡

"ሚስጢሩን ነዋ አላት"፡፡

"አይ! ምነው ሁሉንም ነገር ለማንም እንዳትነግሪ ብለኸኝ በባዶ ቤት ያለቤተሰብና ያለ ዘመድ አዳፍነህብኝ ሄደህ ፤ እንዴት ነው ሚስጢሩ የሚወጣው?፡፡ ይኸው ከዛን እለት ጀምሮ ተመስገን እኔ ደጀም አልደረሰም፡፡ እስካሁንም አላየሁት፡፡ ብላ የነበረውን ሁኔታ ስታነሳሳ ውስጧ ተረበሸ፡፡ የብሶት እንባ አለቀሰች፡፡

ያሬድ የሚለው የሚናገረውን ቢያጣ ግራ ቢገባውም፡፡ ከተመስገን ያልተገናኛችሁት እዚሁ እያለ ነው ወይስ ከሃገር ለቆ ነው? አለ፡፡

በፊቷ ላይ የሚወርደውን እንባ በፎጣዋ ጠረግ ጠረግ እያደረገች "እዚሁ እያለ ሲሸሸኝ ፣ ሲሸሸኝ ቆይቶ እህቱን እድላዊትን ወደ ፀበል ልወስዳት ነው፡፡ ብሎ ቤተሰቦቹን አታሎ ወደ ተባለበት ፀበል ሳይወስዳት ወደ አረብ ሃገር ተሰደው ምን እንደደረሰባቸው እንጃ እድላዊትም ከመጣች አንስታ ከአልጋ ላይ አልተነሳችም አሉ"፡፡

"ማን ነገረሽ ? እነሱ ቤት እንደማትደርሽ ነግረሽኝ ነበር"::

እድላዊት በጠና መታመሟን የነገረኝ ጉልላት ነው፡፡ እኔማ ከቤትም ስወጣ ሰው ሁሉ እንደ ዕብድ ውሻ ይሸሸኛል፡፡ አለች የፈላውን ቡና እየቀዳች፡፡

"ለዚሁ ሁሉ ስቃይና መከራ ያበቃሁሽ እኔ ነኝ፡፡ እንደበደልኩሽም አውቃለሁ፡፡ ግን ወድጀ አይደለም፡፡ የሃገር ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡ ጥየሽ የሔድኩት ፤ ብዙ አትፍረጅብኝ ሃገር ሰላም ካልሆነች እኛም ሰላም እንደማናገኝ አንችም ታውቂያለሽ" አለ ፤ ያሬድ፡፡

"እግዚአብሄር እንኳን ከእሳት አትርፎህ ለአይነ ስጋ እንድንገናኝ አበቃን እንጂ ያለፈው አልፏል፡፡ አሁንም አንተ ከመጣህ ጊዜው አይርቅም፡፡ የተደበቀው ሚስጢር ይውጣና እኔም እናቴ ናፍቃኛለች፡፡ ይሄው ካየኋት፤ አራት አመታትን ጨርሰን አምስተኛ አመታችንን ልንይዝ ነው፡፡ ምንም ቢሆን የእናት ክፉ የለውም፡፡ ባላወቀችው ነገር እንደጠላችኝ አውቃለሁ አለች፡፡ የቀሉ አይኖቿን እያሻሸች፡፡

እድላዊት በደረሰባት ጉዳት የተነሳ የአልጋ ቁራኛ ሆናለች፡፡ እህል እንኳን መቅመስ አቅቷታል፡፡

ተመስገን የቁም ስቃይና መከራ እያየ ባለበት ሰዓት ሞቷል እየተባለ የተወራለት ያሬድ መምጣቱን ሲሰማ

ወደ አረብ ሃገር ሲሰደድ ሶስት ሰዓት የፈጀበት የገመሪ ተራራ እፊቱ ላይ የተጋረጠበት ያክል መስሎ ተሰማው፡፡

ከአምስት ቀን እረፍት በኋላ፤ የተደበቀውን ሚስጢር ለማውጣት ይመለከታቸዋል የተባሉትን ዘመድና ሽማግሌዎች ለማነጋገር በጥዋት ተነሳ፡፡ የውጭ በሩን ከፍቶ ሳይወጣ ከቤቱ ማዶ ላይ አንድ ነጭ ጋቢ የለበሰ ሰው አየ፡፡ ወደ እሱ ቤት እየመጣ ይመስላል፡፡ ወደ አሰበበት መሄዱን ተወት አድርጎ ወደ እሱ የሚመጣውን መጠባበቅ ጀመረ፡፡

በጥዋት ጋቢያቸውን ተከናንበው ወደ ያሬድ ቤት የሚመጡት ቄስ አሻግሬ ነበሩ፡፡

"ደህና አደርህ ያሬድ" ? አሉ ቄስ አሻግሬ፡፡ እስሩ ደርሰው፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደሩ ቄስ አሻግሬ"?፡፡

"እንኳን ለሃገርህ አበቃህ" ፡፡

ልጆች ደህና ናቸው ?፡፡

"ደህና ናቸው ፤ እንዲያው አንተ ለጤናህ ደህናነህ ?

ደህና ነኝ፡፡ ወደ ቤት ይግቡ ? ቄስ አሻግሬ አለ፡፡

አይ! አልገባም ቸኮል እላለሁ፡፡ እንዲያው በጥዋቱ ተነስተህ ኖሯል፡፡ የምትሄድበት አለ እንዴ ? አሉ፡፡

አዎ፤ የምሄድበት ነበረኝ፡፡ ከማዶ ስትመጡ ሳይ ጊዜ ነው፡፡ ወደ እኔ መምጣትዎን ሳውቅ የጠበኩዎት፡፡ ብሎ ምን ነው ደህና አይደሉም እንዴ? አለ፡፡

አይ! እኔስ ደህና ነኝ፡፡ እንዲያው እኒያ ቄስ መልካሙ ወደ አንተ ልከውኝ ነበር፡፡ የመጣሁት አሉ፡፡

ምን ነው በሰላም ነው? አለ ያሬድ፡፡ እድላዊት ምን ሆነች ብሎ እየተጠራጠረ፡፡

ልጁን ወይም ማሳደጊያ ይክፈለን እኛም አቅማችን እየደከመ ነው፡፡ እድላዊትም በሽተኛ ሆናለች፡፡ አንድ ነገር ያድርግልን ብለው ነው የላኩኝ አሉ፡፡
👍443🎉2
አይ! ደህና ነው፡፡ ለመርዳትም ሆነ ልጁን ለመውሰድ የምንነጋገረው ስላለ ነገ እነ ተመስገን ቤት አብረው ይጠብቁኝ፡፡ እኔም የራሴን ሽማግሌዎች ይዠ እመጣለሁ ብሏቸው ቄስ አሻግሬን አሰናብቷቸው ሊሄድ ወደ አሰበበት ሄደ፡፡

በነጋታው ጠዋት በቀጠሮው መሰረት የግድ ሚስጢሩ መውጣት ስላለበት በነ እድላዊት ቤት ይመለከታቸዋል የተባሉ ቤተሰብና ዘመድ ተሰብስበዋል፡፡ ሚስጥሩ ሊወጣ ቡና ተፈልቶ ጨዋታው ደምቋል፡፡

ያሬድ የአልጋ ቁራኛዋን እድላዊትን ለመጠየቅ ወደ ተኛችበት አልጋ ተጠጋ፡፡ ከአንገቷ ቀና በማድረግ በቀኝ እጁ ደገፍ አድርጎ እንዴነሽ አላት፡፡

እድላዊት አይን አይኑን አትኩራ አየችው፡፡ መልስ ለመስጠት አልቻለችም፡፡ አንደበቷ ተሳሰረ፡፡

በአይኖቿ እንኳይ የሚመስሉ የእንባ ጠብታ ግራና ቀኝ በጉንጮቿ ላይ ፈሰሱ፡፡

አይዞሽ አታልቅሽ ? አለ ያሬድ፡፡ ግራና ቀኝ በጉንጮቿ ላይ የሚወርደውን እንባ በእጁ መዳፍ ጠራረገላት፡፡

ምን እንደነደፈው ሳይታወቅ ድንገት ግቢው ውስጥ ውሻው ጩኸቱን አባረቀው ፤ እንደ መርዶ ነጋሪ አላዘነ ፡፡

ተመስን ተነስቶ ወጣ ፤ እቤቱ በር ላይ የወደቀ ገመድ አንስቶ ውሻውን እያባረረ ወደ ጓሮው ዘለቀ፡፡ ተመስገን ውሻውን ሊያባርር እንደወጣ ዘገዬ፤

የተሰበሰቡት ሽማግሌ እና ዘመዶቹ በመቆየቱ ግራ ተጋቡ

አንድ ሰው እስኪ ጥራው አሉ ፤ ቄስ አሻግሬ ፡፡

የአምስት ዓመቱ የእድላዊት ልጅ ባለማወቅ እኔ ልጥራው ብሎ እየሮጠ ወጣ ፡፡

ተመስን..ተመስገን..እያለ ተጣራ ፤ የሚሰማው አላገኘም ፡፡ ግቢውን እየዞረ ወደ ጓሮ ሲዘልቅ ተመስን እጓሮው ውስጥ ያለው የዋንዛ ዛፍ ላይ በአንገቱ ገመድ አጥልቆ ተሰቅሏል ፡፡ ይሄ ሚስጥር ሲወጣ ከምሰማ ብሎ የዚችን ዓለም ኑሮ ዳግም ላያያት እስከ ወዲያኛው አሸልቧል፡፡

ባለዋወቅ ወደ ቤት እየሮጠ ተመለሰ ፤ በተሰበሰበው ሰው መሃል ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ተመስገን ገመድ አንገቱ ላይ አድርጎ ዛፍ ላይ ወጥጧል አለ፡፡

እድላዊት ታንቆ መሞቱን ስሰማ በድንጋጤ ቀስ ቀስ እና ፈርገጥ ሳትል በያሬድ ክንድ ላይ እንዳለች ከተመስገን የመሽቀዳደም ያህል ለአንዴ እና ለመጨረሻ ይህችን ዓለም በሞት ተሰናበተቻት ፡፡ ሚስጥሩም ሳይወጣ ተዳፍኖ ቀረ😳

ተ ፈ መ ፀ

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 6 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍26😢174🔥3
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================

ሁሴን ወደዩኒቨርሲቲው  ከተመለሰ ከአስራ አምስት ቀን በኋላ…
አላዛር እንደተለመደው  ስራ ውሎ ቤት እንደገባ  በራፉ ከልክ በላይ ተቆረቆረ..በድንጋጤ ሄደና ከፈተው፡፡ሰሎሜ ነች..፡፡አይኖቾ በለቅሶ ብዛት ደም ለብሰዋል፡፡በዛ ላይ አባብጣለች፡፡ወደውስጥ ጎትቶ አስገባትና በራፉን መልሶ ዘግቶ ‹‹ምን ሆንሽ?››ሲል ጠያቃት..ልትመልስለት ሞከረች ግን ሳግ እየተናነቃት ማውራት አልቻለችም፡፡ተንደርድራ ሄዳ ሶፋው ላይ ወጥታ እጥፍጥፍ ብላ ተኛች፡፡ለምን እንደዚህ እንደሆነች በደንብ ያውቃል፡፡ቢሆንም አሳዘነችው፡፡ቢቻለው ይሄንን ጉዳይ እሷን ቅንጣትም ሳያሳዝን በፀጥታ ማጠናቀቅ ነበር ምኞቱ…ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም‹‹ካለመስዋዕትነት የሚገኝ ውጤት የለም››ብሎ በማሰብ እራሱን ለማፅናናት ሞከረ፡፡በጣም አሳዘነችው፡፡በዝግታ ሄዶ ፈራ ተባ እያለ ስሯ ተቀመጠ፡፡

‹‹ሶል ምን ሆንሽ?››

‹‹ያ ደደብ..ቺት ሲያደርግብኝ ነበር ለካ፡፡››

‹‹እንዴ ማን?›

‹‹እስራኤል ነዋ.. ሌላ ማን ይሆናል?››

‹‹እንዴ ገና ከመጀመሪያችሁ..አረ የተሳሳተ ወሬ ደርሶሽ እንዳይሆን?››ከመጋረጃ ጀርባ ያለውን  እውነተኛ ሙሉ  ታሪኩን  ቢያውቅም በማስመሰሉ ቀጠለበት፡፡

‹‹ኸረ ባክህ…››አለችና ከተጋደመችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከጃኬቷ ኪስ ውስጥ ፎቶዎችን አወጣችና ጠረጴዛው ላይ ዘረገፈችለት፡፡

ልክ ፎቶውን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየው በማስመሰል በመደነቅና  በመገረም እያቀያየረ ይመለከታቸው ጀመር፡፡

‹‹ልጅም አለው ማለት ነው?›

‹‹አይገርምም..ምን አይነት ጅል ኖሪያለው?››

‹‹እንዴ አንቺ እንዴት ልታውቂ ትችያለሽ?››

‹‹አይደል …ልስልስ ብሎሰ ሲቅለሰለስ እኮ መላአክ ነው የሚመስለው፡፡.

ፎቶውን እንዴት እንዳገኘችው በደንብ እያወቀ‹‹ለመሆኑ ይሄን መረጃ እንዴት አገኘሽው?››ሲል ጠየቃት፡፡

..ካፌ አስተናጋጅነት ስራ ጀምሬለሁ አላልኩህም…ሽፍቴን ጨርሼ ወደቤት ለመምጣት ታክሲ እየጠበቅኩ ሳለሁ ነው የሆነ ህፃን ልጅ  የሰጠኝ…የሆነች ሴት ነች የላከችልሽ››ነው ያለኝ…በወቅቱ ግራ ተጋብቼ ስለነበር ከዛ በላይ ማጣራት አልቻልኩም፡፡››

‹‹እራሷ ሚስቱ ትሆናለች፡፡››

‹‹አዎ መሰለኝ ከፎቶው ጋር አብሮት የሆነ ማስታወሻ ነበረበት

..‹እባክሽ የልጄ አባት ባሌን ተይልኝ……ትዳራችንን አትበጥብጪ› ይላል››

‹‹ይገርማል…ታዲያ እሱን አላናገርሽውም?››

‹‹ምን አባቱና ነው የማናግረው…..ወዲያውኑ ነው ስልኩን ብላክ ሊስት ውስጥ የጨመርኩት ፣  ብቻ እግዜር ነው የተፋኝ፡፡››

‹‹እንዴት ማለት?››

‹‹ምን እንዴት አለው..?አንድ ተጨማሪ ወር ቆይተን ቢሆን ኖሮ ሌላ ነገር ውስጥ ልንገባ እንችል ነበር››

‹‹ሌላ ነገር ማለት?››

‹‹አንተ ደግሞ በረዶ ነጭ ነው ካለሉህ አይገባህም….››አለችው በብስጭት፡፡
በረጅሙ ተነፈሰ….‹‹አለመነካካታችሁም አንድ ነገር ነው…አይዞሽ ቀስ እያልሽ ትረሺዋለሽ››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡

‹‹አይ አካላችን አለመነካካቱን አትይ …ልባችን ተነካክቶ ነበር..በተለይ ልቤ ልቡ ላይ ተለጥፎ ነበር….ልብን ከተለጠፈበት መንጭቀህ ስታላቅቀው ደግሞ ተቦጭቆ የሚቀር ነገር አለ..የሚቆስልና የሚቆጠቁጥ…ያማል…..››
ጭንቅላቷን እያሻሸ‹‹አይዞሽ…!!.››አላት፡፡

‹‹አላዛር››ስትል ድንገት ጠራችው፡፡

‹‹ወዬ ሰሎሜ››

‹‹ቆይ እኔ አስጠላለሁ እንዴ?››

‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው?››

‹‹ጓደኛዬ ከሆንክ በታማኝነት መልስልኝ..እኔ አስጠላለሁ ወይ?››

‹‹አንቺ ማለት ድቅድቅና ጭለማ በሆነ  አለም ውስጥ ቦግ ብለሽ በድምቀት የምታበሪ ጨረቃ ነሽ…አንቺ ውብ ካልሆንሽ..ውብ ሚባል ነገር ጭራሽ በዚህ አለም የለም ማለት ነው››አላት ከአንጀቱ፡

‹‹አንተ ደግሞ ከፊክሽን ያነበብከውን ውብ የፍቅር ውዳሴ አሰማኝ አላልኩህም እኮ….ንፅህ ስሜትህን ነው የጠየቅኩህ››

‹‹እኔም የነገርኩሽ ስለአንቺ የሚሰማኝን ነው..ፊክሽን ማንበብ እንደማልወድ ደግሞ ታውቂያለሽ፡፡››

‹‹ታዲያ እንደምትለው ከሆነ ..ለምን ፍቅርን በተመለከተ ስኬታማ መሆን አቃተኝ..?››

‹‹አንቺ ብቻ እኮ አይደለሽም ..እኛም ጓደኞችሽ እስከአሁን ይሄነው የሚባል የፍቅር ታሪክ የለንም፡፡ያ ማለት ወደፊት አይኖረንም ማለት አይደለም….ከፊታችን ገና ብዙ ብሩህ እድሎችና ተስፋዎች እንዳሉን አምናለው፡፡ደግሞ እንዳትረሺ ውቧች ሁሉ  ሁሌ  በፍቅር ውጤታማ መሆን አለባቸው የሚል ህግ የለም ፡፡ .››

‹‹ይሁን እስኪ እንደአፍህ ያድርግልን…..ምን አልባት ሁለችንም ጓደኛሞች ልጆች ሆነን ጀምሮ ተንኮል ስንሰራ ስላደግን የሆነ ሰው ‹ፍቅር  በልባችሁ አይደር…ካደረም አይሰንብት› ብሎ እረግሞን ይሆናል….›› ብላ  ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቆመች፡፡

‹‹ምነው ልትሄጄ ነው እንዴ?››

‹‹እና ልደር?››

‹‹ምን ችግር አለው…?

‹‹በል ይሄን ያህል ካለቃቀስኩብህ ይበቃኛል ..አመሰግናለው..ትንሽ ቀለል ብሎኛል››

‹‹በይ እሺ ደህና እደሪ››አለና በራፉ ድረስ ሸኛት፡፡በራፉን እንደከፈተ ቆሞ በራፏን ከፍታ እስክትገባ  ተመለከታት…ከዛ በእፎይታ እና በእርካታ በራፉን ዘጋና ወደመኝታው አመራ፡፡
////
አላዛር እና ሰሎሜ ለሁሴን ምርቃት ለመሄድ እየተዘጋጁ ባሉበት ወቅት ያልገመቱት አስደንጋጭ እና ያልተጠበቀ ግን ደግሞ አስደሳች ተብሎ ሊታሰብ የሚችል ዜና ደረሳቸው፡፡
መጀመሪያ ለአላዛር  ነው መልእክት የተላከለት፡፡
ሰሎሜ እና አላዛር ወንድሜ እኔን ለማስመረቅ ወደእኔ ለመምጣት ምታደርጉትን ዝግጅት አቁሙ..አስፈላጊ አይደለም፡፡ልትልክልኝ ያሰብከውን  ገንዘብም አትላክልኝ …እስከዛሬ ከበቂ በላይ ረድተኸኛል…አመሰግናለሁ፡፡ለምን እንደዛ እንዳልኩህ  ዝርዝር ምክንያቱን ሰሞኑን ኢሜል አደርግልሀለው፡፡››ይላል፡፡
ገና ሰሞኑን ጠብቆ ኢሜል እስኪልክለት መጠበቅ አልችልም.፡፡ለምን እንደዛ እንዳላቸው ለማወቅ..ስልክ ደወለለት …አይነሳም፡፡ደጋግሞ መከረ…፡፡በማግስቱ እንደውም ጭሩሱን ስልኩ አይሰራም ፡፡ጥሪ አይቀበልም ይላል፡፡
ለሰሎሜም ሁኔታውን ነግሯት አብረው መጨነቅ ጀመሩ፡፡
እሷም ከእሱ በላይ ተጨንቃ

‹‹ታዲያ ምን ይሻላል ትላለህ?››ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹እኔ እንጃ …ምን አልባት እኛን ማስቸገር ከብዷት እንዳይሆን››

‹‹ይመስለኛል…ማለቴ አንተን ማስቸገር ከብዶት ነው የሚሆነው››ስትል በሀሳቡ ተስማማች፡፡

‹‹ምን ማለት ነው..?ጓደኛቹ አይደለን እንዴ..?በእንደዚህ አይነት ጊዜ ከጎኑ ካልሆን ጥቅማችን ምኑ ላይ ነው፡፡››ተበሳጨ፡፡
‹‹ያው ሁሉም ጓደኛ እኮ አንተ እንደምታደርገው አያደርግም››

‹‹እንዴት? ››

‹‹እኛ እርስ በርስ ጓደኛሞች ብቻ አይደለንም የእድሜ ልክ ትስስር ያለን ወንድምአማቾች ነን››

‹‹ይሄ ገለፃ አሌክስንም ያጠቃልላል?››ሲል መልሶ ሌላ ጥያቄ ጠየቃት፡፡

ፊቷ ቅይርይር አለ…አሌክስ የሚባለውን ስም መስማት የማትፈልገው ስም ከሆነ ከራርሟል ፡፡መኮሰታተሯን አይቶ‹‹እሺ አትበሳጪ..እንዳልሺው ሊሆን ይችላል፡፡አሁን ዋናው ነገር  ምን እናድርግ የሚለው ነው?›› ሲል ምክረ ሀሳቧን ጠየቀ፡፡

‹‹እኔም ግራ ገባኝ እኮ…፡፡›

‹‹ዝም ብለን  ወደ ጎንደር እንሂድ እባክሽ››ሲል ቅፅበታዊ ውሳኔውን ነገራት፡፡

‹‹መቼ….?››

‹‹በቃ ነገ እንዘገጃጅና ተነገ ወዲያ እንሂድ፡፡››

‹‹ግን አውቀሀል… ለምርቃቱ ገና አስር ቀን ይቀረዋል…ደርሰን እንመለሳለን ወይስ  እንዴት እናደርጋለን?››
👍504
‹‹አንቺ ብቻ እቴቴን አስፈቅጂያት…..እንሄዳለን…..ምን ላይ እንዳለ እናይና ያለበትን ችግር በመቅረፍ ወደሙዱ ከመለስነው በኃላ ቀኑ አስኪደርስ እዛ አካባቢ ያሉ የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን እንጎበኛለን፡፡ውቧን ባህርዳርን እናያለን፤ወደ ላሊበላ እንዘልቃለን፤ከፈለግሽ አክሱም ፀዬን ድረስ መሄድ እንችላለን፤እንደውም ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡››
‹‹አንተ እያስጎመዠሀኝ ነው….ለመሆኑ ይሄን ሁሉ ስፖንሰር መሆን ትችላለህ?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ …አንቺ ብቻ ከእቴቴ ፍቃድ አግኚ እንጂ ለወጪው አትጨነቂ፤አሁን እኮ ሀብታም እየሆንኩ ነው፡፡በዛ ላይ በራሳችን መኪና ነው የምንሄደው…ወጪያችን የነዳጅና የሆቴል ምናምን ነው፡፡››

‹‹ውይ እረስቼው….ለካ ባለመኪና ነህ፡፡››

በዚህ ተስማሙና ተለያዩ….
በማግስቱ ግን  አላዛር ከሁሴን የተላከው  የኢሜል መልዕክት ደረሰው ፡፡

ይድረስ ለምወድህ ወንድሜ እና ለሰሎሜ
ይሄንን ጉዳይ ለእናንተ እንዴት አድርጌ መንገር እንዳለብኝ ስላላወቅኩ ለብዙ ቀን ከራሴ ጋር ስወዛገብ ነበር የከረምኩት፡፡ግን የግድ ነው፡፡የምነግራችሁ ዜና አስደሳች ይሁን አሳዛኝ አላውቅም፡፡አስኮላርሽፕ አግኝቼ ወደእንግሊዝ በርሬያለሁ፡፡ይሄንን ደብዳቤ በምታነቡበት ጊዜ ምን አልባት አውሮፕላኑ አኮብኩቦ አየር ላይ ይሆናል..ምን አልባትም የኢትዬጵያን ድንበር ለቆ ባህሩን አዘቅዝቆ እያየ የጠራውን ሰማይ እየሰነጠቀ ሊሆን ይችላል፡፡ብቻ ሄጄያለው፡፡
እስከዛሬ ስለሰጣችሁኝ የጓደኝነት እንክብካቤ እና የወንድምነት ፍቅር በጣም አመሰግናለው፡፡ሁል ጊዜ ባሳፈለጋችሁኝ ጊዜ ሁሉ ከጎኔ ነበራችሁ፡፡ከልጅነቴ ጀምሮ በስኬቴ ከእኔ በላይ እንደፈነጠዛችሁ ይበልጥ ውጤታማ እንድሆን እንዳበረታታችሁኝ ነው፡፡የእኔ እዚህ መድረስ በጥረቴና በጭንቅላት ብቃቴ ብቻ የሆነ አይደለም..የእናንተ ግፊትና ማበረታቻ አለበት፡፡የኤሌመንተሪ ተማሪ እያለን  ጀምሮ በትምህርቴ አንደኛ ደረጃ ስወጣ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለእናንተም ጭምር የወጣው ነበር የሚመስለኝ…እንደዛም ፊል እንዳደርግ ያደርገኝ የነበረው  በእኔ ውጤት እናንተ ከእኔ በላይ ስትጨፍሩና ስትፈነጥዙ ስለማይ ነበር..ብቻ አመሰግናለው፡፡እርግጠኛ ነኝ ከሁለት አመት በኃላ የሄድኩበትን የትምህርት ጉዳይ ያው እንደተለመደው በድል አጠናቅቄ እመለሳለሁ፡፡የዛን ጊዜ ሁሉን ነገር ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡እስከዛው እርስ በርሳችሁ ተደጋገፉ..ከተቻላችሁ አለማየሁንም ፈልጋችሁ አግኙትና ወደቡድኑ መልሳችሁ ቀላለቅሉት፡፡የሆነ ከባድ ችግር አጋጥሞት እንጂ በእኛ ጨክኖ ይሄን ሁሉ ጊዜ  አይሰወርም ነበር፡፡
በአጠቃላይ በጣም ነው የምወዳችሁ፡፡ እንግሊዝ ደርሼ እንደተደላደልኩ ያለሁበትን ሁኔታ በዝርዝር ፅፍላችኃላው… ፡፡በአካል አግኝቼያችሁ ሳልሰናበታችው ስለሄድኩ ቅር ካሰኘዋችሁ ይቅርታ..እድሉ ድንገት ስለመጣና ፕሮሰሱም የተዋከበ ስለነበረ ነው እንደዛ ማድረግ ያልቻልኩት፡፡ከጎንደር አዲስ አበባ በገባን በአንድ ሰዓት ልዩነት ነው ወደእንግሊዝ የሚበረው ፕሌን ውስጥ የምገባው…ለዛ ነው ምንም ማድረግ ያልቻልኩት ፡፡በሉ  ቸው፡፡
አላዛር አንብቦ እንደጨረሰ ድንዝዝ ነው ያለው ..ከፋውም ተደሰተም፡፡ የከፋው…ሌላ ተጨማሪ ጓደኛውን ስላጣ ነው፡፡ድሬደዋ የከተመውን አለማየሁ ተመልሶ ሊጠይቃቸውና ሊያገኛቸው ካልፈለገ ባህር የተሻገረው ሁሴንማ  ጭራሽ ማይመስል ነገር ነው የሆነበት፡፡ቢሆንም ግን የተሻለ እድል ስላገኘ  ተፅናንቷል…ቆየት ብሎ ሲያስበው ደግሞ  ሁለቱም በየተራ የእሱን የልብ ስቃይ  ሰሎሜን እሱ እጅ ላይ ጥለውለት  መሄዳቸውን ሲያስተውል ፈገግ አለ፡፡
‹‹ከአሁን ወዲህ ማንንም አልጠብቅም››ሲል ካራሱ ጋር አወራ፡፡አሁን በማንኛውም ጊዜ ሰሎሜን እንደሚያፈቅራት ቢነግራት ምንም አይነት ፀፀት አይሰማውም…ምክንያቱም ቃልኪዳናቸውን ያፈረሱት እሱ ሳይሆነ እነሱ ናቸው፡፡ በመጀመሪያ‹‹ ሶስታችንም አንድ ላይ ሆነን እንደምናፈቅራት እንነግራትና እሷ እንድትመርጥ እናደርጋለን›› የሚል ስምምነት ነበራቸው፡፡ በአለማየሁ ድንገት መሰወርና ከተማውን ጥሎ መጥፋት የተነሳ ተሰናከለ፡ ፡የቀሩት እሱና ሁሴን ከእንደገና ቃል ኪዳናቸውን አድሰው ነበር፡፡ሁሴን ልክ ተመርቆ እንደመጣ እሷን ከፊት ለፊታቸው ቁጭ አድርገው ሁለቱም እኩል እንደሚያፈቅሯት እና ከሁለት አንዳቸውን እንድትመርጥ ውሳኔውን ለእሷ እንደሚተው ስምምነት ነበራቸው፡፡ይሄው ቀኑ ሲደርስ  ሁሴን ስለጉዳዩ ምንም ሳይለው ጭራሽ ባህር አቋርጦ ሄዶል….ስለዚህ አሁን እሱ ብቻ ነው ያለው፡፡፡
‹‹አዎ..አሁን ጊዜው እየመጣ ነው፡፡ብቸኛው እጩ አፍቃሪ እኔ ብቻ ነኝ..ከዛሬ ቀን ጀምሮ እሷን እንዴት አድርጌ የእኔ እንደማደርጋት ማሰብና ለዛም ጠንክሬ መዘጋጀት አለብኝ›› ሲል ወሰነ፡፡
በማግስቱ ሁሴን የጻፈውን የኢሜል መልዕክት ለሰሎሜ አስነበባት፡፡ልክ እሱ መጀመሪያ ሲያነብ የተሰማውን አይነት ስሜት ነው የተሰማት..እንደውም ከዛ አልፋ ተንሰቅስቃ ሁሉ አልቅሳለች፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 9 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍673👏1
አትሮኖስ pinned Deleted message
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ከአመት በኃላ
አላዛር በግንባታው ዘርፍም በፍጥነት እየቀናውና እያደገ ሄዶ  በሁለት አመት  የኮንስትራክሽን ስራው ደራጃ -4 መድረስ ቻለ፡፡በስራ ዓለም ብቻ ሳይሆን እህቶቹንም በማገዝ የተዋጣለት ነበር …አንደኛዋን አህቱን ደግሶ ጥሩ የሚባል ትዳር ሲያሲዛት  ሌለኛዋን ደግሞ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ  እያስተማራት ነው፡፡

…በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ ሰሎሜን አግቢኝ ብሎ ለመጠየቅ በተሻለ ብቃት ድፍረቱን ማሰባሰብ የጀመረው፡፡እንደውም ይሄንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በጣም ቆይቶል፡፡ከአመት በፊት ሁሴን ጨርቄን ማቄን ሳይል ወደውጭ እንደሄደ ነበር ወዲያው ሊያደርገው የወሰነው፡፡ግን  ቆይ ከዛሬ ነገር ሲል…መጀመሪያ ይህቺን ነገር ላሞላ ብሎ ከራሱ ጋር ሲሟገት ከአመት በላይ ጊዜ ፈጀበት፡፡አሁን ግን አግቢኝ ብሎ ሰሎሜን ለመጠየቅ  ከመቼውም ጊዜ በላይ  ሁኔታዎች ጠቅላላ ለእሱ ያደሉ እየሆኑ ነው ፡፡
እስከአሁን በዋናነት የያዘው ከበፊት ጀምሮ ሰሎሜን ካገባው በኃላ አኖርበታለሁ ብሎ ያልም የነበረውን አፓርታማ እስኪገዛ ድረስ ነበር፡፡ያንን ለማድረግ ለሶስት አመት ያህል ወገቡን አስሮ  ገንዘብ ማጠራቀም ነበረበት ..አሁን ግን ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ገንዘቡም ሞልቶለት ውብ የሆነ አፓርታማ ገዝቶ በእጁ አስገብቷል፡፡
አሁን እዛ ኮንደሚኒዬም ቤት ውስጥ የሚኖረው ከእሷ ላለመለየት ብቻ ብሎ እንጂ በቅርብ የገዛውን አፓርታማ ቤት የሚስተካከለውን ነገር ቶሎ አስተክሎ ወደዛው መዘዋወር ይችል ነበር፡፡ ፡፡ለጊዜው ግን አፓርታማውን ባለበት አቆይቶ  የእሷ ጎረቤት ሆኖ መኖሩን ቀጥሏል፡፡
ሁለተኛ እሷን እንዲጠይቃት ገፊ ምክንያት  ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ እሷን የራሳቸው ለማድረግ አብረውት ሲፎካከሩት የነበሩት የእሱም የእሷም ምርጥ ጓደኞች በከተማው አለመኖር ነው፡፡
ሁሴን ለትምህርት ከአገር ውጭ የወጣበት አለማየሁ ደግሞ ፖሊስ ሆኖ ተመርቆ የት እንኳን እንደተመደበ የማያውቅበት ጊዜ ላይ ነበር፡፡እናም በዚህ ጊዜ እነዚህ ሁለት ተፎካካሪዎቹ እስከወዲያኛው ከመንገዱ ገለል እንዳሉ እርግጠኛ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ በእነዚህና ሌሎች ምክንያቶች የእሷ ብቸኛ ጓደኛ ሆኖ የሚገኝበት አጋጣሚ ላይ  በመገኘቱ ክፍተቱን ለመጠቀም ትክክለኛው ጊዜ አሁን እንደሆነ አእምሮውም ሆነ ልቡ በእኩል ተስማምተው እየጨቀጨቁት ነው፡፡

ሌላው እሱ ቢዝነሱ ሁሉ መስመር ይዞ በኢኮኖሚ ጠንክሮ የካማፓኒ ባለቤት እና የብዙ ንብረት ባለቤት  መሆን ችሏል ፡፡  በተጨማሪም  እሷ   ስራ አጥታ  ካፌ በአስተናጋጅነት እየሰራች ብስጭት የምትልበት   ጊዜ ላይ በመሆኗ ግራ ቀኙን አመዛዝኖ እሺ እንድትለው የሚያግዙትን ሌሎች እርምጃዎችን ቀድሞ ለማድረግ  መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡
ሁለት ጥንዶች ወደጋብቻ ከሚገብባቸው ዋነኛው ምክንያት መካከል አንድ   በመካከላቸው የተፈጠረውን ጓደኝነት እድሜ ለመስጠት እና በመካከላቸው የበቀለውንም ፍቅር አድጎና አብቦ ፍሬ እንዲያፈራና እንዲጎመራ ለማድረግ ነው፡፡በዚህ ሰበበ-ምክንያት ጥንዶቹ  ወደጋብቻ ከገቡ በኃላ አንዳቸው ለአንዳቸው ረጅም ጊዜ ይሰጣጣሉ፤ስሜታቸውን በተሻለ ግለት ይጋራሉ፤ በጋራ ስቀው በጋራ ያለቅሳሉ፡፡ለዚህም ሲሉ በጋብቻ እቅፍ ውስጥ አንድ የፍቅር ብሉኮ ለሁለት ለብሰው ህይወት በመደጋገፍ ይስኬዱታል፡፡

ሌላው ጥንዶች ወደጋብቻ የሚገቡበት ሁለተኛው ምክንያት ለህጋዊ ጉዳዬችና ለጥቅማ ጥቅም ሲሉ ነው፡፡ሁለት ጥንዶች ፤ከመንግስት ለሚያኙት ጥቅማ ጥቅም ሲሉ፤ለሚያገኙት ውርስ ሲሉ፤ከፖለቲካ ለሚያገኙት ተርፍና ክብር ሲሉ ወደጋብቻ ሊገቡ ይችላሉ፡፡በሶስተኛ ደረጃ ለጋብቻ ምክንያት ተደርጎ የሚወሰደው ልጆችና ቤተሰብ ለማፍራት ሲባል ነው፡፡አንዳንድ ተጣማሪዎች በግላቸው በነበራቸው ጉዞ  በህይወት ሁሉ ነገር ይሳካላቸውና ግን ደግሞ ዘራቸውን ተክተው ለማለፍ ወይም ያላቸውንን ንብረት ወይም ሌጋሲያቸውን ሚወርስ ልጅ እንደሚያስፈልጋቸው ትዝ ሲላቸው..ያንን ለማግኘት አቅደው ወደጋብቻ ይገባሉ፡፡ ልጆች ለመውለድና ቤተሰብ ለመሰረት ሲሉ፡፡በአራተኛ ደረጃ እንደምክንያትነት የሚጠቀሰው ደግሞ ለሀይማኖታዊ ወይም ባህላዊ ጉዳዬች ሲባል የሚደረግ ጋብቻ ነው፡፡ሁለት ተመሳሳይ ሀይማኖት ወይም ባህላዊ እሴት የሚጋሩ ጥንዶች ምንም እንኳን በመካከላቸው ወደትዳር አንደርድሮ የሚከት የፍቅር መሳሳብ ባይኖርም በሀይማታዊ ጉዳዬች ምክንያት ወይም በባህላዊ መንገድ በቤተሰቦቻቸው ፍቃድ ብቻ ወይም በጎሳ መሪዎቻቸው ልዩ ትዕዛዝ ወደጋብቻ ሳያቅማሙ የሚገብበት አጋጣሚ አለ፡፡በአሁኑ ዘመን በብት የሚተገበረው አምስተኛው ምክንያት ደግሞ
እራስን ለማሻሻል የሚደረግ የጋብቻ አይነት ነው፡፡ውጥረት በበዛበት በዘመናዊው አለም በተለይ በተጨናነቁ ዋና ከተሞች የሚኖሩ ጥንዶች በመካከላቸው የተወሰነ መግባባት ከተፈጠረ..አስቸጋሪውን የኑሮ ዳገት ተጋግዞ ለመግፋትና ወደፊት ትንሽ ፈቅ ለማድረግ ሲሉ ወደጋብቻ የሚገቡበት አጋጣሚ የተለመደና በቁጥርም ቀላል የሚባል  አይደለም…የቤት ኪራይ ወጪ ለመጋራት…የቤት ውስጥ የስራ ጫናን ለመተጋገዝ፤አብሮ በመረዳዳት ወደተሻለ ህይወት ለመሸጋገር ሲባል በመነጋገርና በመደራደር ወደጋብቻ ተያይዞ ይገባል፡፡
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ለጋብቻ ገፊ ከሆኑ ምክንያቶች ውስጥ ዋና ዋኖቹ ናቸው እንጂ ብቸኞቹ አይደሉም..ደግሞም አንድ ሰው ለአንዱ ምክንያት ሲል  ወደጋብቻ ሲገባ ሌሎቹን ፈፅሞ አይፈልጋቸውም ወይም አያገኛቸውም ማለት ሳይሆን ዋና ትኩረቱንና ከጋብቻው ጥምረት በዋናነት ሊያተርፍ የሚፈልገውን ነገርን ለመግለጽ ነው፡፡ለልጆች ብሎ ወደጋብቻ የገባ ሰው..ልጁንም ፤በሂደት ደግሞ ከመቀረረብ ብዛት ፍቅርንም…ከዛም አልፎ ተጋግዞ ከመስራትና ተሳስቦ ከመኖር  ብዛት የተሻለ ህይወትንም ሊያገኝ ይችላል፡፡
አላዛርም ሰሎሜን ሊያገባ የፈለገበት ዋናውና አንገብጋቢው ምክንያት ለእሷ ያለውን ፍቅር ለዘላለም ለመንከባከብና ለመጠበቅ ሲል ብቻ ነው፡፡በዋናነት በአእምሮው ያለው ምክንያት ያ ነው፡፡ቢሆንም ግን ከእሷ ምርጥና ተወዳጅ ልጆችን ማግኘትም ይፈልጋል…እሱ ከቤተሰቡ ያለገኘውን ፍቅርና እንክብካቤ ከእሷ ጋር ለሚመሰርተው አዲስ ቤተሰብ መስጠትና ለልጆቹ  ምርጥና ተወዳጅ አባት ለእሷ ደግሞ ተንከባካቢ እና አፍቃሪ አባወራ  መሆን መቻሉን ማረጋገጥ ይፈልጋል….በኑሮ እንድትረዳውና እንድትደግፈው ፍጽም አይፈልግም…ይልቅ በተቃራኒው ለዘላለም እንደንግስት ሊንከባከባትና ሊያቀማጥላት ነው ምኞቱ፡፡አዎ ሊያነግሳት ነው የሚያገባት፡፡
አዎ በእቅዱ መሰረት ቅድሚያ የሚደረጉ ነገሮችን አድርጎ እንደሚያፈቅራት ነግሯት እንድታገባው ቢጠይቃት .. ምንም እንኳን ለተወሰነ ጊዜ ልታቅማማ ብትችልም ጨክና እምቢ ልትለው እንደማትችል ጠንከር ያለ እምነት አድሮበታል፡፡…

ሰሎሜን ደወለና ቀጠራት፡፡አዲሱ ሰፈራቸው የሚገኝ በብዛት አዘውትረው የሚጠቀሙበት ካፌ ቁጭ ብሎ ስለእሷው እያሰበ ስክትመጣ እየጠበቃት ነው፡፡ከመንገድ ማዶ  በሩቁ ወደእሱ ስትመጣ ሲያያት ነው ውስጡ በደስታ የተተራመሰው፡፡እንደቀረበችው ከመቀመጫው ተነሳና ጉንጭ ለጉንጭ ተሳስመው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች፡፡እሷ ፊት ለፊቱ ስትቀመጥ የጥዋት ፀሀይ ወጥታ ሰውነቱን እየዳበሰችው እንዳለ ህፃን መላ ሴሎቹ ይነቃቃሉ፡፡አላዛር  ሰሎሜን ዛሬ እንዲህ አብባ እና አሽታ ሲያያት ይደንቀዋል፡፡እንደልጅነታቸው ሊቀርባት ሊያቅፋት ሊስማት ሁሉ ይመኛል፡፡ግን ደግሞ ይፈራል፡፡በዚህም ረጅም ብስጭት ይሰማዋል፡፡
👍529
‹‹እሷ ባትኖር ህይወት እንዴት አስጠሊታ ነበረች ?››ሲል በውስጡ አሰበና..ፈገግ አለ፡፡
በተቀመጠችበት ቀና ብላ እየተመለከተችው‹‹ብዙ አስጠበቅኩህ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ችግር የለውም …ሀያ ደቂቃ ብቻ ነው የጠበቅኩሽ››
‹ይቅርታ …..ስራ ይዤ ነበር››
‹‹ስራ ባትይዢም ማርፈድሽ አይቀርም ነበር….እድሜ ልኬን አንቺ ስታረፍጂ እኔ ስጠብቅሽ ነበር….እናም የዛሬው የተለየ አይደለም…ይልቅ የሆነ ነገር እዘዢ››አላት፡፡
ማኪያቶ አዘዘች…
‹‹ኬክ ወይም ፒዛ ይምጣልሽ?››
‹‹ተው ትጎዳለህ?››
‹‹ግድ የለም እዘዢ››
አዘዘች…
ሁል ጊዜ በእሱ መጋበዝ እንደሰለቻት በሚያሳብቅ የድምፅ ቅላፄ‹‹እኔም አንድ ቀን  ደህና ስራ እይዝና እጋብዝህ ይሆናል››አለችው ፡፡
‹‹ስራእኮ ነበረሽ..ግን ጋብዘሺኝ አታውቂም››
አስተናጋጅነቱን ማለትህ ነው፡፡ደሞዙ ከግል ወጪዬ አያልፍም እኮ..በዛ ላይ ስሙ አስተናጋጅ ሆነ እንጂ እየሰራሁ ያለሁት አነስተኛ ካፌ ነው….ለዛውም ደስ ይበልህ ለቅቄዋለው፡፡››
‹‹በእውነት ይሻላል?››
ስራውን በመልቀቋ ደስ ነው ያለው፡፡መስማት የሚፈልገውን ዜና ነው ያሰማችው፡፡
‹‹እኔ እንጃ..አላውቅም…ግን ትቼዋለው››
‹‹በቀደም የተመዘገብሽው ስራስ እንዴት ሆነ ..አልጠሩሽም እንዴ?››
‹‹ጠርተውኝ ፈተናውን ወስጂ ነበር ..ለሀያ ምናምንኛ ጊዜ ተጠባባቂ ሆኜ ወደቅኩ…አሁንስ ምርር ብሎኛል››አለችው የእውነትም መማረሯን በሚያሳብቅ ድምፀት፡፡
‹‹ደሞዙ ስንት ነበር?››
‹‹ሶስት ሺ ብር ነበር..ለደሞዙ ግድ የለኝም.. ከዛም በታች ቢሆን እሰራ ነበር…በአሁኑ ጊዜ የምፈልገው እስከአሁን ስሰራው  ከነበረ ትንሽ የተሻለ  ስራ ማግኘት ብቻ ነው፡፡››
‹‹እንደዛ ከሆነ ለምን እኔ አልቀጥርሽም…ከዚህ በፊትም ኮንስትራክሽን ሳይቱ ጋር ስሪ ብዬሽ እምቢ ብለሻል…አሁን ግን በወር ሶስት ሺ ብር እከፍልሻለሁ››አላት፡፡ዜናው ለእሷ ድንገቴና አስደንጋጭ ቢሆንም ለእሱ ግን ተረጅም ጊዜ ያሰበበትና እሷን እስከወዲያኛው የራሱ ለማድረግ ከሚወስዳቸው እርምጃዎች አንዱ ነው፡፡
‹‹ቀልድብኝ››አለችው የተናገረውን ባለማመን፡፡
‹‹እውነቴን ነው…ደግሞ ሳት ላይ እንድትሰሪ አይደለም እየጠየቅኩሽ ያለሁት…በአሁኑ ጊዜ ከአያቴ ባገኘሁት  በውርስ  የጀመርኩት የግንባታ ስራ  በጣም ውጤታማ ሆኖልኛል.... የሱቁን ስራ ሰው ቀጥሬ ማሰራት ከጀመርኩ አመት እንዳለፈኝ ታውቂያለሽ…አሁን ግን የሚሰራው ልጅ  ሰራውን ስለለቀቀ የግድ የሚተካው ሰው ማጋኘት አለብኝ….››ሲል አብራራላት፡፡
‹‹እና››
‹‹በቃ የማይደብርሽ ከሆነ ሱቁን ተረከቢኝና እዛ ስሪ…በመሀከል የተሻለ ስራ ካገኘሽ ትተይዋለሽ››
የልቧ ምት ጨምሮ‹‹የእውነትህን ነው እንዴ?››ስትል አፈጠጠችበት፡፡
‹‹አዎ የእውነቴን ነው››
ከመቀመጫው ተንደርድራ ተነሳችና ጉንጩን ሳመችው….ደስ ስላላት እሱም በጣም ደስ አለው፡፡እንዲህ ትፈነጥዛለች ብሎ አላሰበም ነበር፡፡
‹‹በእውነት አንተ ጓደኛዬ ስለሆንክ እድለኛ ነኝ….ጥሩ ሰራተኛ እንደምሆን ልትተማመንብኝ ትችላለህ››
‹‹አዎ..በደንብ እተማመንብሻለው…ልጁ ሰራውን ለቃለሁ ሲለኝ በመጀመሪያ ያሰብኩት እቃውን ጠቅላላ በጅምላ አሰረክቤ ሱቁን ለመዝጋት ነበር፡፡ምክንያቱም ለሱቅ ስራ ለቁጥጥርም አስቸጋሪ ስለሆነ በማንኛውም  ሰራተኛ የምታሰሪው ስራ አይደለም…ለዛ ነበር ሙሉ ለሙሉ መዝጋት የፈለኩት፣..በኃላ ግን አንቺ ትዝ ስትይኝ ሀሳቤን ቀየርኩ…እንዴ ይህቺን የመሰለች እንደራሴ የማምናት ጓደኛ እያለችኝ ሱቁን ለምን ዘጋለሁ ብዬ አሰብኩ..አንቺም አላሳፈርሺኝም››
በንግግሩ ልቧ ተነካ‹‹በእውነት ከራስህ እኩል ታምነኛለህ?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን እንኳን አጋንኜው ነው…ማለት እራሴን ያንቺን ያህል አላምነውም….››
‹‹የሆነ ስህተት ሰርቼ እንደማላከስርህ ተስፋ አለኝ››አለችው
‹‹ምንም አትሳቀቂ.. ስራ ላይ ምንም ይፈጠር ምንም ለአንቺ ያለኝን አመለካከት አይቀይረውም…ደግሞ በስራአለም መክሰርና ማትረፍ ያለ ነው…ለማንኛውም ስራ ስላገኘሽ የሆነ ቦታ እንሂድና ምሳ ጋብዢኝ››አላት፡፡
‹‹ችግር የለውም…ግን እንደምታውቀው ደሞዝ ምቀበለው ገና ከ30ቀን በኃላ ነው…ባለ ሆቴሎቹ ዱቤ የሚሰጡኝ ከሆነ ጋብዝሀለው….ካልሆነ  ግን አንድ ወር መጠበቅ የግድ ይልሀል››
‹‹እሺ ተነሽ እንሂድና የዱቤውን ጉዳይ እናጣራ››አላትና ሁለቱም በደስታ  እየተሳሳቁ ተያይዘው ወጡ፡፡
ሰሎሜ  በማግስቱ 2 ሰዓት ሲሆን አላዛር ሱቅ በራፍ ላይ ቆማ ደወለችለት፡፡ከቤቱ በፍጥነት መጥቶ ሙሉ ሱቁን ከነቁልፉ አስረከባት፡፡ስራውን በደንብ እስክትለምድ ለአንድ ወር ገባ ወጣ እያለ እንደሚያግዛት ነግሯት. ስራ አስጀመራ፡፡
ይሄ ስራ ሰሎሜን ብቻ ሳይሆን እናትዬው እቴቴንም በጣም ነው ያስደሰታቸው፡፡አንድና ብቸኛ ልጇቸው ለ3 አመት ኮሌጅ ተምራ ከተመረቀች በኃላ ምንም የረባ  ስራ ሳታገኝ በመንከራተቷ  በጣም አበሳጭቷቸውና አሳስቧቸውም ነበር…ባለሰቡት መንገድ ግን በአላዛር የተሰጣትን ስራ ሁለቱም በምስጋና ነው የተቀበሉት፡፡
ከሁለቱም በላይ ግን አላዛር ነበር ደስተኛ፡፡ይህንን ለአመታት ሲሰራበትንና ቤተሰቦቹን ሲረዳበት እህቶቹን ያስተማረበትን ሱቅ ሲያስረክባት በፍፁም ደስተኝነት ነው፡፡ይህ ደስተኝነት ሱቁን የበለጠ ትርፋማ ታደርግልኛች ወይም በፊት ከነበሩኝ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን ትስብልኛለች በሚል ስሌት አይደለም….እንደውም ከአሁን ወዲህ ከዛ ሱቅ ስለሚገኘው ገቢ ግድ የለውም….ኪሳራ ውስጥም ቢወድቅ ቅር አይለውም..የእሱ አላማ ከልጅነት ጓደኛውና ከእድሜ ልክ ህልሙ ሰሎሜ ጋር ይበልጥ ለመቀራረብና በየሰበብ አስባቡ እንደልቡ ለመገናኘት ሲለሚያግዘው ነው፡፡ከዛም አልፎ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስለሚያቀርብላት የፍቅር ከዛም አልፎ የጋብቻ ጥያቄ የወርቅ ድልድይ ይሆነኛል ብሎ ስሌት ስለሰራ ነው፡፡
እንዳሰበውም በቀን ውስጥ አምስት ስድስት ሰዓት አንዳንዴም ሌላ ስራ በሌለው ጊዜ ቀኑን ሙሉ ሱቅ ውስጥ አብሮት ማሳለፍ ቻለ..ማታ አንድ  ሰዓት ሱቅ ይዘጉና ወደሆቴል ጎራ ብለው እራት በልተው አንድ ላይ ኮዬ ፈጬ የሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ይሄዳሉ…ከዛ እሷ የእናቷን በራፍ ስታትንኳኳ እሱ ደግሞ በተቃራኒው አቅጣጫ  ያለውን የራሱን የወንደላጤ ቤት ከፍቶ ይገባል፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 4 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍7510👎1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
==================

ሰሎሜ አላዛር ሱቅ መስራት ከጀመረች ከከስድስት ወር በኃላ
እለቱ ሰኞ ነው፡፡የሳምንቱ መጀመሪያ፡፡አላዛር ድንገት ተከሰተና ሱቁን ዘግተው እንዲወጡ አደረገ፡፡ቀጥታ ወደ መዝናኛ ቦታ ወስዳት፡፡ሲዝናኑ አመሹና አረፍ ብለው እየተጫወቱ ሳለ፡፡
‹‹አንድ ሰዓት ሆነ እኮ ወደቤት አንሄድም እንዴ?፡፡››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹ወደቤት ስትይ?››
‹‹እንዴ ምኑ ነው ያልገባህ…?ወደየቤታችን ነዋ!!››
‹‹ቤት እንደገዛው ነግሬሻለሁ አይደል?››አላት
‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኛል..በአጭር ጊዜ ስኬታማ እየሆንክ ነው..ጠንካራ ሰራተኛ ስለሆንክ ይገባሀል፡፡››
‹‹አይ ጠንካራ ሰራተኛ ስለሆንኩ ብቻ አይደለም የተሳካልኝ..እድለኛም ጭምር ስለሆንኩ ነው፡፡አያቴ ያወረሰቺኝ ገንዘብ …ቀላል አልጠቀመኝም..ይሄንን የኮንስትራክሽን ስራ ከጀመርኩ በኃላ ደግሞ አሪፍ የተባሉ ሶስት ፕሮጀክቶችን አገኘሁ…ረጅም አመት በስራው የቆዩ ኮንትራክተሮች እንኳን ይሄንን ያህል ስራ በቀላሉ አያገኙም፡፡››
‹‹ቢሆንም ያገኙትን እድልም በስርአት መጠቀምና ውጤታማ መሆንም እኮ ትልቅ የጥንካሬ ምልክት ነው፡፡››
‹‹እዛ ላይ እንኳን ትክክል ነሽ…ያገኘሁትን እድል ላለማባከን የተቻለኝን ሁሉ ከማድረግ አልሰንፍም››አላት በእርግጠኝነት፡፡
‹‹አዎ…ታዲያ እቤቱን መች ነው የምታሳየን?››
‹‹አሁን ጥቂት የሚስተካከሉ ነገሮች ስላሉ እያሳደስኩት ነው…እንዳለቀ ወስጄ አሳይሻለሁ››ሲል ቃል ገባላት፡፡
‹‹እና ሲያልቅ ጎረቤታችንን ልናጣ ነዋ፡፡››አለችው
‹‹ማለት?››
‹‹ያው ኮንደሚኒዬሙን ለቀህ ..አዲሱ ቤትህ ስትገባ ጓረቤት መሆናችን ይቀራል ማለቴ ነው››
‹‹አይ ..እንደዛ እንኳን አላደርግም..እሺ ካልሺኝ አብረን እንገባበታለን…ካልሆነም እሱን አከራይቼ እዛው ጎረቤትሽ ሆኜ መኖሬን ቀጥላለሁ፡፡››ብሎ ያልጠበቀችውን ነገር ነገራት፡፡
‹‹አልገባኝም…እኔ ደግሞ ለምንድነው አብሬህ የምገባው?››
‹‹አንድ ወንድና ሴት አንድ የጋራ ቤት ውስጥ ለምንድነው አብረው የሚገቡት?››ሲል መልሶ ጠየቃት፡፡
‹‹ቆይ ቆይ…..እየጀነጀንከኝ ነው እንዴ?››
‹‹ከተሳካልኝ አዎ››
‹‹ይገርማል ከዚህ ሁሉ አመት መጓተት በኃላ ድንገት ምን ተፈጠረ?››
ወደልቡ በሌባ ጣቱ  እየጠቆመ ‹‹ሁሌም ሀሳቡ እዚህ ውስጥ ነበር ..ልዩነቱ አሁን ከአንደበቴ ምውጣቱ ነው››አላት፡፡
‹‹ቀልድ ጨምርሀል…ባይሆን አንዷን ጥበስና ደግሼ ልዳርህ!››
‹‹አይ ይቅርብኝ ..እኔ አንቺን ማግባት ካልቻልኩ እስከወዲያኛው መመልኮስ ነው የምፈልገው፡፡››
በድንጋጤ አፏን በመክፈት አፍጥጣ አየችው›‹‹እየቀለድክብኝ ነው እንዴ?››
‹‹አረ የምሬን ነው››
‹‹እኔን ጓደኛህን ማግባት ትፈልጋለህ?››
‹‹አዎ በደንብ፡፡››
‹‹ለምን? ››
‹‹ስለማፈቅርሽ ነዋ!!››
‹‹ከመቼ ጀምሮ››
‹‹እኔ እንጃ …ነፍስ ካወቅኩበት ጊዜ ጀመሮ አንቺን እንደማፈቅቅር ነው የማውቀው››
‹‹ይሄኔ ነው መሸሽ….እና እስከዛሬ ለምን ሳትነግረኝ?››
‹‹ስለምፈራሽ..ዛሬ እራሱ እንዴት እንደነገርኩሽ አላውቅም…››
ዝም አለችው…ምን እንደምትለው ምንም ሀሳብ አልመጣላትም..አስባበት ስለማታውቅ በእሷ በኩል ለእሱ ተመሳሳይ ስሜት ይኑራት ወይስ አይኑራት ማወቅ አልቻለችም፡፡
‹‹በል… አሁን ተነስ እንሂድ፡፡››
‹‹እሺ›› ብሎ …ከተቀመጠበት ተነሳ ና ተከተላት፡፡
ለሶስት ወር ያህል በጉዳዩ ላይ መልሰው በማንሳት አልተነጋሩበትም ነበር…
ከሶስት ወር በኃላ ሱቅ ስራ ላይ እያለች ስምንት ሰዓት ላይ መጣና ‹‹ሱቁን እንዝጋውና ..የሆነ ቦታ እንሄዳለን››አላት፡፡
‹‹የት?››
‹‹ሰርፕራይዝ ነው፡፡››
ተስማማችና ሱቁን አብረው ዘጋግዘው  በፒካፕ መኪናው ተያይዘው ሄዱ…ወደ ላፍቶ ነው የወሰዳት ፡፡አዲስ የገዛው አፓርታማ ቤት ውስጥ ነው ይዞት የገባው……ሙሉ ዕቃው የተሞላ እጅግ ውብ ቤት ነበር፡፡
‹‹ይሄ የእኔ ቤት ነው እንዳትለኝ?››አለችው በመደነቅ ፈዛ፡፡
‹‹አይ የእኔ አይደለም የእኛ ቤት ነው፡፡››
‹‹በጣም እኮ ነው የሚያምረው፡፡››
‹‹ስለወደድሽው ደስ ብሎኛል፡፡››
‹‹ትቀልዳለህ እንዴ ..?እንዴት ላልወደው እችላለሁ? ቤተ መንግስት እኮ ነው የሚመስለው፡፡››
‹‹እንግዲህ እንዳልሺው ቤተ መንግስት ከሆነ ንግስት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡››
‹‹እሱን ጫወታ ለጊዜው ትተን ሁሉንም ክፍል እየዞርን እንየው፡፡››
‹‹ይቻላል››ብሎ እየመራ ወደፎቁ ይዞት ወጣ፡፡ንግግሩን ጠንከር ብላ ስላልተቃወመችው ደስ ብሎታል፡፡ፈፅሞ ጥያቄው  እስከወዲያኛው ላለመቀበል ወስና ቢሆን ኖሮ ቁርጥ አድርጋ ምንም አንደበቷን ሳያደናቅፋት ‹‹አይሆንም ››ትለው ነበር፡፡አሁን ግን …ለጊዜው  እንተወው ››ነው ያለችው፡፡
//
እቤቱን ወስዶ ካስጎበኛት ከ15 ቀን በኃላ ድንገት‹‹በሚቀጥለው ሳምንት እቴቴ ጋር ሽማግሌ ልልክ ነው››ብሎ አስደነገጣት፡፡
‹‹ምን?››
‹‹አዎ …ሽማግሎዎችን አነጋግሬ አዘጋጅቼዋለሁ..በኃላ አዲስ እንዳይሆንብሽ ብዬ ነው አሁን የነገርሽው፡፡››
‹‹ያምሀል እንዴ…?እኔ መች እሺ አልኩህና ነው ሽማግሌ የምትልከው?፡፡››
‹‹ችግር የለውም…ሽማግሌ እልካለሁ…የማትፈልጊ ከሆነ ከእናትሽ ተማክረሽ ለሽማግሌዎች አይ አልፈልገውም ማለት ትቺያለሽ፡፡››
‹‹እንደዛ ብል እና በሽማጊሌዎች ፊት መዋረድ አይሆንብህም››
‹‹ግድ የለኝም….ዋናው አንቺን ለማግኘት ከልቤ መሞከሬ ነው፡፡››
‹‹ከዛ በኃላ ግን እዚህ  መስራት አልችልም…››
‹‹እ ..እሱን በተመለከት በውሳኔሽ ተፅእኖ እንዳያሳድርብስሽ ስለፈለኩ ቅድመ ዝግጅት አድርጌለሁ፡፡››
‹‹የምን ቅድመ ዝግጅት?››
ፊት ለፊቱ ያለውን አጀንዳ አንሳና…‹‹ይሄንን ዝርዘር ተመልከችው..እዚህ ሱቅ ውስጥ ያለው እቃ  ነው፡፡ይሄ ደግሞ ውል ነው..ይሄንን ሱቅ ከአሁን ወዲያ አልፈልገውም….ሁሉንም ዕቃ ትረከቢኝና ቀስ እያልሽ በሁለት አመት ውስጥ ትከፍይኛለሽ…ይሄ ማለት ይሄንን ውል ከፈረምሽ በኃለ የእኔ ሰራተኛ አይደለሽም ማለት ነው፡፡የራስሽን ንግድ ፍቃድ አውጥተሸ በራስሽ መስራት ትቀጥያለሽ ማለት ነው፡፡እናም ያ ማለት እንደከዚህ ቀደሙ በፈለኩ ጊዜ ወደሱቅሽ ዘው ብሎ መምጣትና ወደውስጥ ዘልቆ መግባት አልችልም ማለት ነው….እና ሽማግሌዎች ሲመጡ አሺ አገባዋለሁ ብትይም አላገባውም ብለሽ ብትነግሪያቸውም፤ከዚህ ሱቅና ከስራሽ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡በይ ቸው››ብሏት ጥሎት ወጥቶ ሄደ፡፡
እንዳለው በሳምንቱ ሽማግሌ ላከ ….በሚቀጥለው እሁድ ተመልሰው እንዲመጡና መልሳቸውን የዛን ጊዜ እንደሚያገኙ ተነገራቸው፡፡የሰሎሜ እናት እቴቴ አንድ ብቸኛ ልጇን አስቀምጣ ጠየቀቻት፡፡
‹‹ልጄ ለመሆኑ ከአላዛር ጋ መቼ ነው የጀመራችሁት?››
‹‹ምንድነው የጀመርነው?››
‹‹ሽማጊሌ ልኮ እያየሽ ምን ትይኛለሽ እንዴ?››
‹‹አይ እቴቴ..እንደሚወደኝ ነገረኝ እንጂ ምንም የጀመርነው ነገር የለም …መልስ እንኳን አልሰጠሁትም፡፡››
‹‹ለምን?››
‹‹እኔ እንጃ እያሰብኩበት ነበር፡፡››
‹‹ምንድነው የምታስቢው…አትወጂውም?››
‹‹እኔ እንጃ… የምወደው ይመስለኛል፡፡››
‹‹አዎ ..እኔም ምትወጂው ይመስለኛል፡፡››
ሰሎሜ በእናቷ ንግግር ተገርማ‹‹እንዴት የምወደው ሊመስልሽ ቻለ?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ባትወጂውና ባትፈልጊው ኖሮ ወዲያውኑ ነበር አልፈልግም ብለሽ መልስ ምትሰጪው….እንደሚወድሽ ከነገረሽ ቀን አንስቶ እስከዛሬ ጉዳዩን እያብላላሽውና  እያሰብሽበት ከሆነ ሌላ ምንም ትርጉም ልሰጠው አልችልም፡፡››
👍6514😁8
‹‹እሺ ..እንዳልሽ››
‹‹ጥሩ …ስለዚህ እሁድ ሽማግሌዎቹ ሲመጡ ተስማምተናል የሚል መልስ ነው የምንሰጣቸው ማለት ነው፡፡››
‹‹ምን ትያለሽ..እኔ እንጃ ..አንቺ የፈለግሽውን መልስ ስጪያቸው፡፡››
‹‹እንዴ…እኔን እኳ አይደለም ለትዳር የጠየቁኝ….››
‹‹አውቃለሁ…ግን አንቺ እናቴ ነሽ..ለእኔ የሚሆነውን ከእኔ በላይ ታውቂያለሽ…አላዛርን ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ እሱንም ሆነ ቤተሰቡን ጠቅላላ ታውቂያቸዋለሽ…ለመወሰን አይከብድሽም …ለእኔ እራሴ ከምወስን ይልቅ አንቺ ብትወስኚልኝ ነው ጥሩ የሚሆነው፡፡››
‹‹የእኔ ጅል..ያንቺ ዘመን ልጆች ወላጆቻቸውን በህይወቴ ጣልቃ አትግቡ ብለው ነው ጦርነት የሚያስነሱት..አንቺ ግን እናትሽን ባል ምረጪልኝ ብለሽ ችግር ውስጥ ትከቻታለሽ…በኃላ በምወስነው ውሳኔ ብትበሳጪና ብትነጫነጪ ማንም አይሰማሽም፡፡››
‹‹እሺ እቴቴ..አልነጫነጭም›› ብላ …ከተቀመጠችበት ተነስታ የእናትዬውን ጉንጭ ሳመች፡፡
‹‹በቃ ሽማግሌዎች ይምጡ..የዛ የሰካራም ልጅ ለአንዲቷ ውብ ልጄ  እንዳማይመጥን ነግራቸዋለሁ፡፡››
ሰሎሜ‹‹እንደፈለግሽ እልኩሽ እኮ››ብላ እናትዬውን ተለይታ ቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ግን ደግሞ በእናትዬው የመጨረሻው ዓ.ነገር ሳምንቱን ሙሉ ስትጨነቅ ነበር ያሳለፈችው፡፡‹‹እውነት እንዳለችው ልጄን አልሰጥም ብትልስ? እውነት አላዛርን ማግባት ልፈልግም?››እኚንና መሰል ጥያቄዎችን እራሷን በመጠየቅ ስትብሰለሰልና ስትተክዝ ነበር ያሳለፈችው፡፡
እሁድ ሱቅ ከፍታ በመሸጥ ላይ ሳለች..3 ሰዓት አካባቢ አላዛር መጣና ከፊት ለፊት ወንበር ስቦ ተቀመጠና ያወራት ጀመር፡፡
‹‹ምነው የተጨናነቅክ ይመስላል?››አለችው የራሷን መጨናነቅ በውስጥ አፍና፡፡
‹‹ያው ታውቂያለሽ አይደል..ሽማግሌዎች እቴቴ ጋር ሄደዋል፡፡››
‹‹አዎ አውቃለው….ታዲያ ምን ያስጨንቅሀል…?እሺ ወይም እምቢ ነው የምትባለው››
‹‹እንዴ..እምቢ የሚለውን መልስ እንዲህ በቀላሉ የምቀበለው ይመስለሻል…በጣም ነው የሚሰብረኝ…፡፡››
‹‹አይዞኝ…..ቆንጆና መለሎ ነህ…በዛ ላይ ሀብታም ነህ…..እንደዚህ አይነት ወንዶችን በራሳቸው አሳደው የሚያገቡ ደግሞ በሺ የሚቆጠሩ ሴቶች አሉ፡፡ከመሀከላቸው አንዷን እድለኛ አፈፍ አድርገህ ታገባለህ፡፡››
‹አይ እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ለራሴ ቃል የገባሁት ገና ልጅ ሆኜ ነው …ምርጫዬ  አንድ አንቺ ብቻ ነሽ…አንቺን ማግኘት ካልተሳካልኝ በቃ..ትዳር እጣ ክፍሌ አይደለም ማለት ነው፡፡››
‹‹አይ… ይህቺማ ፖለቲካ ነች፡፡››
‹‹እማዬ ትሙት እውነቴን ነው….ግን ለምን አሁን አንቺ መልሱን ነግረሺኝ አትገላግይኝም፡፡››በልምምጥ ጠየቃት፡፡
‹‹መልሱን ምትሰጠው እናቴ ነች እንጂ እኔ አይደሁም፡፡››
‹‹እኮ እናትሽ የአንቺን ፍላጎት  ጠይቃሽ የለ..በዛ መሰረት መሰለኝ ለሽማግሌዎች መልስ ምትሰጠው….አንቺ ምን አልሻት..? ፈልጋለሁ ነው አልፈልግም?፡፡››
‹‹ሁለቱንም አላልኳትም››
በመልሶ በጣም ደነገጠ፡፡ሳምንቱን ሙሉ ሲጨነቅ ከነበረው በእጥፍ ተጨነቀ….አፉን ከፍቶ የሆነ ነገር ሊላት እየተዘጋጀ ሳለ..ስልኩ ተንጫረረ…፡፡ ንግግሩን ተወውና ስልኩን አየው…ሽማግሌዎች ናቸው፡፡
በተቀመጠበት ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ…እንደምንም ብሎ አነሳው‹‹ለአስር ሰክንድ ያህል ደዋዩን ሽማግሌ የሚናገሩትን አዳመጠ›፤ምንም መልስ ሳይሰጥ ስልኩን ጆሮቸው ላይ ጠረቀመባቸውና ድንዝዝ ብሎ ተቀመጠ…
ሁኔታውን ስትከታተል የነበረችው ሰሎሜም ተመሳሳይ ስሜት ውስጥ ገባች፡፡እንደምንም እራሷን አበረታታችና‹‹አላዛር አይዞህ….እቴቴን መልሼ አናግራታለሁ፡፡››
‹‹ምንድነው የምታናግሪያት..?››ብሎ ከተቀመጠበት ተነሳ፤ወደውስጥ የሚያሸጋግረውን በራፍ ከፍቶ ወደሱቅ ውስጥ ገባ …ተጠጋትና ተጠመጠመባት…በአየር ላይ አንጠለጠላትና አሽከረከራት‹‹እንዴ ምን እየሆንክ ነው…?ምን ተፈጠረ?››
‹‹ባልሽ ልሆን ነው….እሺ ተብያለሁ…እሺ ተብዬለሁ››ለእንቁጣሽ አዲስ ልብስ እንደተገዛለት የድሮ ልጅ በአየር ላይ እስኪንሳፈፍ ድረስ ፈነጠዘ፡፡
በመከራ ተላቀቃት‹‹‹እንዴ… መንግስተ ሰማያት ትገባለህ የተባልክ እኮ ነው የምትመስለው፡፡››
‹‹በይው..ለእኔ መንግሰተ ሰማዬ ካንቺ ጋር አንድ ላይ መኖር ነው፡፡በይ አሁን ዝጊው…የሆነ ቦታ ሄደን ይሄንን ታላቅ የምስራች በፈንጠዝያ እናክብረው፡፡
‹‹ሰውዬ ተረጋጋ እንጂ…በቀደም ያስፈረምከኝን ወረቀት ዘነጋው እንዴ..ብዙ እዳ ያለብኝ ሰው እኮ ነኝ፡፡››
‹‹ታሾፊያለሽ እንዴ.. አንቺን ለማግባት እሺ ተባልኩ እኮ እያልኩሽ ነው…ሚስቴ ሆንሽ ማለት ያ የፈረምሽው ወረቀት ጥቅም አልባ ነው ማለት ነው...የእኔ የሆነው ሁሉ ያንቺ ነው..በባልና ሚስቶች መካከል ብድርና እዳ ብሎ ነገር አይሰራም..ይልቅ በቃ ውጭ፡፡››
አክለፍልፎ ከሱቅ ይዟት ወጣ..ቀኑን ሙሉ እስከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲዝናኑና ሲደሰቱ አመሹ…ከወር በኃላ ሆቴል ውስጥ በተደረገ 100 ሰዎች በተሳተፉበት እጥር ምጥን ያለ ሰርግ ተሰረገና ባልና ሚስት ሆነው አንድ ቤት ገቡ፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 2 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍8714
አትሮኖስ pinned «#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ ================== ሰሎሜ አላዛር ሱቅ መስራት ከጀመረች ከከስድስት ወር በኃላ እለቱ ሰኞ ነው፡፡የሳምንቱ መጀመሪያ፡፡አላዛር ድንገት ተከሰተና ሱቁን ዘግተው እንዲወጡ አደረገ፡፡ቀጥታ ወደ መዝናኛ ቦታ ወስዳት፡፡ሲዝናኑ አመሹና አረፍ ብለው እየተጫወቱ ሳለ፡፡ ‹‹አንድ ሰዓት ሆነ እኮ ወደቤት አንሄድም እንዴ?፡፡››ስትል…»
አትሮኖስ pinned Deleted message