#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================
ከአንድ አመት በኃላ በትዳር ውስጥ ወሲብ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም፡፡ግን ደግሞ ሊቀር የማይችል ከዋነኞቹ አስፈላጊ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡በተጣማሪዎች መካከል የሚከሰትን ማንኛውንም የከረረ ነገር የሚያለዝበው፤ የተጣመመ ስሜታቸውን የሚያቃናው፤የጎበጠ ግንኙነታቸውን የሚያቃናው ወሲብ ነው፡፡
የኑሮ ችግር ቢኖር መፅናኛ..አለመመቸት ቢኖር ማስረሻ ነው..ወሲብ፡፡እናም ባለትዳሮች የኑሮቸውን ኢኮኖሚያው ቀዳዳ ለመድፋት በስራ ደፋ ቀና እንደሚሉት ሁሉ የስሜታቸውን ክፍተት ለመድፈን ስለወሲብ ብቃታቸውና ችሎታቸው እኩል ትኩረት መስጠት አለባቸው፡፡ለዛውም ያልተቆራረጠ ቀጣይነት ያለው ትኩረት ፡፡ምክንያቱም ወሲብ ለፍቅር ተጣማሪዎች ልክ እንደምግብ ነው፡፡ምግቡ ቁርስ ላይ ያበሉት ሆድ ምሳ ላይ አምጡ ብሎ እንደሚጠይቀው ሁሉ ወሲብም ሰኞ እስኪዝለፈለፉ አድርገው እሮብ ላይ ጭንቅላቶትን እስኪያዞሮት ሊያምሮት ይችላል፡፡ይሄ ለምን ሆነ ተብሎ መጠየቅ የለበትም..፡፡እንደውም የሰውነቶትንም ሆነ የአእምሮትን ሙሉ ጤናማነት የሚያሳይ አንድ ምልክት ተደርጎ መወሰድ ነው ያለበት፡፡
በአላዛርና በሰሎሜ ትዳር ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው ስብራት ይህ ነው፡፡ወሲብ፡፡ታዲያ ወሲብ ብቸኛው ችግራቸው ከሆነ እንዴት በመሀከላቸው ያለን አንድ ችግር መፍታት ያቅታቸዋል? በሌሎች ትዳሮች እኮ ከደርዘን በላይ የታጭቁ ችግሮች እያሉ እንኳን ትዳሩን በፀና መሰረት ላይ ማስኬድ ይቻላል፤ታዲያ የእነሱ እንዴት ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ግን ነገሩ ከላይ እንደሚታየው ቀላል አይደለም፡፡ወሲብ ማለት የፍቅር መግለጫ ማህተም ነው….ወሲብ ማለት የአብራክ ክፍይን መተኪያ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ልጆች ደግሞ ለአንድ ትዳር የተለየ ትርጉም የሚሰጡ ፍፅማዊ በረከቶች ናቸው፡፡
ሰሎሜና አላዛር እናትዬውን ለመጠየቅ ኮዬ ፈጬ ከንደሚኒዬም ይገኛሉ፡፡የተለየ ጉዳይ ካልተፈጠረ በስተቀር በ15 ቀን አንዴ እንዲህ እየመጡ እናትዬውን ይጎበኛሉ፡፡ይሄንን በየ15 ቀን የሚደረጉትን ጉብኝት ከእነሱ በላይ እናትዬው ነች የምትናፍቀው፡፡ምክንያቱም እነሱ እንድታገለግላት ከቀጠሩላት አጋዥ ልጅ እግር ሴት በስተቀር ለብቻዋ ነው የምትኖረው፡፡አላዛርም ሆነ ሰሎሜ አብራቸው እንድትኖር ደጋግመው ለምነዋት ነበር፡፡እሷ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡
አላዛርን ሳሎን እንደተቀመጠ ከጎኑ የተቀመጠችው ሰሎሜ ከተቀመጠችበት ተነሳችና .‹‹ማሬ እስኪ እማዬን ኪችን ሄጄ ላግዛት፡፡››አለችው፡፡
‹‹ምነው ልጅቷ የለችም እንዴ?››
‹‹ዛሬ ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ብላ ፍቃድ ተሰጥቶት ሄዳለች.. ››አለችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ እቴቴን ይዘናት ወጣ ብለን ውጭ መዝናናት እንችላለን..ኪችን ገብታ ለእኛ ምግብ ማዘጋጀት የለባትም ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ እቴቴን የማታውቃት ይመስላል…ለማንኛውም መጣሁ…እንዳይደብርህ ሪሞቱ ያውልህ ቲቪውን ክፈተው፡፡››ብላው ወደኪችን ገባች፡፡እናትዬው በእስቶቭ ላይ ጎን ለጎን ሁለት ድስት ጥዳ አንዱን ስታማስል ነበር የደረሰችው፡፡
‹‹መጣሽ ልጄ?››
‹‹አዎ አማዬ…ምን ላግዝሽ?››
‹‹ምንም …በቃ እየበሰለ ነው፤ራባችሁ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም ..አርፍደን ከእንቅልፋችን ስለተነሳን ቁርስ በቅርብ ነው የበላነው፡፡››
በሰጠቻቸው መልስ ባለመደሰት አፋቸውን ወደጎን በማሽሟጠጥ አጣመው‹‹ጥሩ ነው.. እስከአራት አምስት ሰዓት መተኛቱ ጥሩ ነው..ግን ዝም ብሎ መተኛት ምን ረብ አለው?››ሲሉ መለሱላት፡፡
የንግግራቸውን አቅጣጫ እያወቀች ‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?..››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ካንቺ በኃላ ያገቡ ጓደኞችሽ ሁሉ እኮ ወለዱ..ሌላው ይቅር ከአምስት ወር በፊት ያገበችው ቤተልሄም የዛሬ ሳምንት ወልደ ሄጄ ጠየቅኳት፡፡››
‹‹እንዴ እማ …ልጅ በዘጠኝ ወር አይደል እንዴ የሚወለደው?በአምስት ወር እንዴት ማድረስ ቻለች?››
‹‹ቀልጂብኝ…ደግሞ እኮ ስላረገዘች ነው ተካልባ ያገባችወ እያሉ ሲያሟት እኔም አብሬ ማማቴ..ምነው አንቺም ከማግባትሽ በፊት አርግዘሽ ቢሆን ኖሮ…፡፡››
‹‹እቴቴ…. እንተዋወቃለን እኮ..አሁን እደዛ አድርጌ ቢሆን አታዝኚብኝም ነበር..?››
‹‹ልዘና ..የተወሰነ ጊዜ ተነጫንጬ ተወዋለው…ምንም ባዝን አሁን እያዘንኩ እንዳለሁት አላዝንም…ደግሞም እስካሁን በእግሩ ለመሄድ የሚታገል ወፌ ቆመች ወፌ ቆመች የምለው የልጅ ልጅ ይኖረኝ ነበር፡፡››
‹‹አይዞሽ እማዬ… በተከታይ ሶስት አራቱን አንጠባጥብልሻለሁ፡፡››
‹‹ልጄ እናት መሆን እንዲሁ ተራ ነገር አይምሰለሽ..ለህይወትሽ ጥልቅ ትርጉም የሚሰጥሽ እናትነት ነው፡፡እናት መሆን ማለት በህይወት ውስጥ ስርሽን የህይወት እንብርት ድረስ ዘረጋሽ ማለት ነው፡፡እናት ስትሆኚ ለህመም በቀላሉ እጅ አትሰጪም፤እናት ስትሆኚ ብትቸገሪ እራሱ በቀላሉ ተስፋ አትቆርጪም፤እናት ስትሆኚ ለቀናት እህል ባትቀምሺ ራሱ ተዝለፍልፈሽ ለመውደቅ አትሞክሪም፤እናት ስትሆኚ መሞት ብትፈልጊ እንኳን ለመሞት መብት የለሽም፤እኔ አንቺን አጎጉል በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነው የወለድኩሽ..እንደእንቺ በወግ በማአረግ አግብቼ መሰረቱ የፀና ትዳር መመስረት አልቻልኩም፡፡እና ደግሞ አንቺን ስወልድ በደረሰብኝ የማህፀን ጉዳት ሌላ ልጅ ወልጄ ወንድም ወይም እህት እንዲኖርሽ ማድረግ አልቻልኩም…አሁን የምትወልጂያቸው ልጆች ልጆችሽ ብቻ አይደለም የሚሆኑት ወንድምና እህቶችሽም ጭምር ነው የምትወልጂው..ለዛ ነው ቀንና ሌት የምጨቀጭቅሽ፡፡››
‹‹ይገባኛል እቴቴ…አይዞሽ!! ››
ሁል ጊዜ ይሄንን ጥያቄ እናትዬው ባነሳችላት ቁጥር ‹‹አይዞሽ››ከማለት ውጭ ሌላ የምትመልስላት መልስ ኖሯት አያውቅም፡፡አሁን አሁን ግን መልሷ በጣም ከመደጋገሙ የተነሳ ለእናቷ ብቻ ሳይሆን ለእሷም በጣም እጅ እጁ እያላት ነው፡፡ግን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የላትም፡፡
እናትዬው‹‹አይዞሽ ብቻ ምንም አይረባኝም…የምትጠቀሚውን መከላካያ መድሀኒት ዛሬውን አውጥተሸ ሽንት ቤት እንድትጥይው ፈልጋለሁ፡፡፡››አሏት፡፡
‹‹እሺ እኮ አልኩሽ እማዬ..እሺ››
‹‹በይ ወጡ ደርሶል…ታጠቡና ተዘጋጁ፡፡ ››
‹‹እሺ›› ብላ በደፈረሰ ስሜትና በተከፋ ፊት ወደ ባሏ ተመለሰች፡፡ይሄ ጭቅጭቅ ምርር እያደረጋት ነው፡፡ደግሞ የእናቷ ብቻ ቢሆን ምን አለበት..ጠቅላላ የሚያውቋት ሰዎች በተለይ ትንሽ ጠና ያሉ ሴቶች በሙሉ በሆነ አጋጣሚ ፊት ለፊት ሲያገኞት‹‹..እሺ መቼ ነው ገንፎ የምንበላው…?ምነው ሰውነትሽ ጨመረ..?አረገዝሽ አይደል?››በቃ ቋቅ እስኪላት ድረስ ምርር ያደረጎት ጉዳዬች ናቸው፡፡
እናቷ ደጋግማ ስትጠይቃት…‹‹ትንሽ ልቆይ ብዬ ነው..መድሀኒት ስለምጠቀም እንጂ እስከአሁን አረግዝ ነበር ፡፡››የሚሉ መልሶችን ደጋግማ መልሳላቸዋለች፡፡ታዲያ ‹‹አይ እናቴ እስከአሁን ያላረገዝኩት ያገባሁት ባሌ ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም እምቢ ስላለ ነው፡፡እስከአሁን ድንግል ስለሆንኩ ነው ፡፡››ትበላቸው እንዴት ? የዚህ ነገር መቋጫው የት እንደሆነ መገመት እራሱ እየከበዳት ነው፡፡
ምሳ ቀርቦ በልተው ካገባደዱ በኃላ ይዘው የመጡትን ወይን ለሶስቱም ተቀድቶ እሱን እየተጎነጩ በግማሽ ልብ የተከፈተውን ቴሌቭዥን እያዩ በግማሽ ልብ የባጥ የቆጡን ርእስ እያነሱ ሲጫወቱ ቆዩ ፡፡በድንገት ግን ቀልብ የሚስብ ፕሮግራም ወሬያቸውን እንዲያቆሙና ሙሉ በሙሉ ፀጥ ብለው እንዲያዳምጡ አስገደዳቸው፡፡ጣቢያው ኢቢኤስ ነበር፡፡

👍64❤8😢2👏1
ፕሮግራሙ ‹‹ቤተሰብ ፍለጋ›› ነው፡፡አንድ እድሜዋ ሳላሳ አካባቢ የሚገመት ጠይም ቆንጆ ወጣት አንድ ብላክ የወታደር ፎቶ እያሳየች..‹‹ከካናዳ ነው የመጣሁት ..ይሄ በፎቶ ላይ የምታዩት አባቴ ነው፡፡ስሙ ሁሴን ጃርሶ እንደሚባል እናቴ ነግራኛለች…እኔ በተወለድኩ ጊዜ የሚኖረው እዚህ አካባቢ ነበር፡፡አባቴ በህይወት ካለህ አለሁ እዚህ ነኝ በለኝ…እኔ ልጅህ ላገኝህና ላቅፍህ ፈልጋለው….ልንካባከብህና ልወድህ እፈልጋለው…ምን አልባት በህይወት ከሌላም ዘመዶቹ ካላችሁ ብታገኙኝ ደስ ይለኛል፡፡›› እያለች እየተንሰቀሰቀች ትማፀናለች…ጋዜጠኞቹ በየተራ ጥያቄ ይጠይቋታል…ለማታውቀው አባቷ ያላትን ናፍቆትና እሱን ለማግኘት ምን ያህል አመት ስትለፋ እና ስትባክን እንደነበረ ታስረዳለች፡፡
ታሪኩ የእናትና የልጅን ስሜት ወዲያው ነበር ያደፈረሰው…ሰሎሜ ልጅቷ ባለቀሰች መጠን እሷም እያለቀሰች ጉዳዩን ሙሉ በሙሉ ወደራሷ ህይወት ነበር የወሰደችው፡፡አሁን ልጅቷ እየተሰማት ያለው ስሜት በደንብ ታውቀዋለች፡፡እሷንም ለአመታት እየተሰማት የነበረ ስሜት ነው፡‹‹እንደውም እሷ እድለኛ ነች…ቢያንስ የአባቷን ሙሉ ስም እና መልኩ ምን ይመስል እንደነበር ለመገመት የሚያስችል ብላክ ፎቶ አላት፡፡››ሥትል አሰበችና ቀናችባት፡፡ ፕሮግራሙን እሰከ መጨረሻው ለማየት አልቻለችም..እየተንደረደረች ሄደችና እናትዬው መኝታ ክፍል ገባች፡፡ባሏ አላዛርና እናቷ ደነገጡ..እላዛር ምን እየተፈጠረ እንዳለ ምንም አልገባውም..አናትዬው ግን በደንብ ተረድተዋታል፡፡
አላዛር‹‹እቴቴ ..ሄጄ ልያት እንዴ?››ሲል ከአማቱ ፍቃድ ጠየቀ፡፡
እናትዬው‹‹ቆይ እኔ ብሄድ ይሻላል፡፡››አሉና በዝግታ እርምጃ ወደእሷ ለመሄድ ተንቀሳቀሱ፡፡የምትጠይቃቸውን ጥያቄ ከወዲሁ በመፍራት የልባቸው ምት እየተንዷዷ ነው፡፡ወደውስጥ ከገቡ በኃላ መልሰው በራፉን ዘግተው..ሄዳው አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጡ፡፡እሷ በደረቷ ተዘርራ አንገቷን ትራሱ ስር ቀብራ እየነፈረቀች ነው፡፡
እጃቸውን በፈራ ተባ ዘረጉን ፀጉሯ ላይ አሳረፉ፡፡ ቀስ እያሉ ያሻሹላት ጀመር፡፡
‹‹እቴቴ..እኔም እንደልጅቷ የአባቴ ፎቶ ቢኖረኝና ሙሉ ስሙን ባውቅ…እንደልጅቷ እፈልገው ነበር፡፡››
‹‹ ከእዚህ ሁሉ አመት በኃላ ስለእዚህ ነገር ማውራት ጥሩ ነው ልጄ?››
‹‹በንዴት ከተዘረረችበት ተነሳችና ቁጭ ብላ እናቷ ላይ አፈጠጠች…‹‹እማዬ ምናወራው እኮ ስለአባት ነው…አርጅቼም ቢሆን እንኳን አባቴን የማግኘት ፍላጎቴ የሚበርድ ይመስልሻል ? ..አባት እኮ ልክ የተጣሉትን ፍቅረኛ እስከወዲያኛው እንደመርሳት በቀላል ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር አይደለም፡፡››
‹‹ምን ለማለት ነው?››
‹‹ገብቶሻል… አንቺ ፍቅረኛሽ ስለሆነና ጥሎሽ ስለሄደ ቂም ይዘሽበትና ጠልተሸው እስከመጨረሻም ከህይወትሽ በማውጣት እረስተሸው ሊሆን ይችላል..፡፡እንደዛ ለማድረግ መብቱ አለሽ ፡፡ለምን ብዬ አልወቅስሽም፡፡ለእኔ ግን አባቴ ነው፡፡በደም ስሬ ውስጥ የሚራወጠው የአንቺ ደም ብቻ አይደለም የእሱም ደም ጭምር ነው፡፡እኔ እንደአንቺ ከህይወቴ በቀላሉ አስወግጄ ስሙንም ጭምር ልረሳው አልችልም፡፡››
‹‹እና ታዲያ አሁን ምን ይሁን ነው የምትዬው?››
ሰሎሜ በንዴት ከተኛችበት ተነሳች፡፡ ያወለቀችውን ጫማ አጠለቀችና መሀከል ወለል ላይ ቆማ ወደታች አዘቅዝቃ እናቷን እያየች‹‹እንደውም እቴቴ ልብ ብለሽ ስሚኝ..እኔ አባቴን ሳላገኝ..ሞቶም ከሆነ መቃብሩን ጋር ሄጄ አልቅሼ እርሜን ሳላወጣ ልጅ የሚባል ነገር አልወልድም፡፡››
አናትዬው እየሰሙ ያሉትን ማመን አልቻሉም፡፡እራሳቸውን እንዳይስቱ ለራሳቸው ሰጉ‹‹ልጄ ምን እያልሽ እንደሆነ ታውቆሻል?››
‹‹አዎ በደንብ አውቃለሁ፡፡…የአባቴን ሙሉ ስም..ፎቶውን ..የምታውቂውን ነገር ሁሉ…ዘመዶቹ ያሉበትን የምታውቂ ከሆነ ሁሉንም ነገር ትነግሪኛለሽ፡፡.››
‹‹ካላወቅኩስ?››
‹‹አፈላልጊ…የሚያውቁትን ሰዎች ያሉበት ድረስ እየሄድሽ ጠይቂ….ክፍለሀገርም ከሆኑ ግድ የለኝም..ሹፌርና መኪና ሰጥሻለው፡፡››
‹‹ያንን ማድረግ አልችልም፡፡››
‹‹ጥሩ …እንደውም ከአሁን ወዲህ ንገሪኝ ብዬ አልጠይቅሽም ..እራስሽ ለምነሽ እስክትነግሪኝ እጠብቃለው፡፡እንደዛ ማድረግ ካልቻልሽ የልጅ ልጅ የማግኘት ጉጉትሽን ተይው፡፡አንቺም ከአባቴ የማታገናኚኝ ከሆነ እኔም ከልጅ ልጆችሽ እንድትገኛኚ አላደርግም፡››ብላ ከፍፍሉን ከፍታ ወጣች፡፡
ሳሎን እንደደረሰች‹‹ማሬ እንሂድ››አለችው አላዛርን፡፡ሁኔታዋ አላማረውም፡፡አይኖቾ ድፍርስርስ ከማለታቸውም በላይ ከመጠን በላይ እየተርገበገቡ ነው፡፡እንዲህ አይነት ምልክት ደግሞ በጣም ስትደሰትና በጣም ስትበሳጭ የሚከሰት መሆኑን ከልምድ ያውቃል፡፡
‹‹እቴቴስ?››
‹‹እራሴን ትንሽ አሞኛል ልረፍ ብላ ተኝታለች፡፡››ስትል ዋሸችው፡፡
‹‹እና ታዲያ ታማ ጥለናት እንሄዳለን..?ቢያንስ ልጅቷ እስክትመጣላት እንጠብቅ፡፡››
‹‹ ችግር የለውም….መድሀኒት ሰጥቻት ውጣነው የተኛችው…ስትነሳ ሙሉ በሙሉ ትድናለች፤እርግጠኛ ነኝ..ተነስ እንሂድ፡፡ ›› ብላ ቦርሳውን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠልጥላ ቀድማ ወደውጭ መንገዷን ቀጠለች፡፡ግራ በመጋባት ውስጥ ቢሆንም እሷን ተከተላት፡፡
ከእናትዬው ቤት ከወጡ በኃላ ቀጥታ ወደቤታቸው ነው የሄዱት፡፡ እንደደረሱ..እሱ ኳስ አያለው ብሎ ሬሞት ይዞ ሳሎን ሲቀመጥ እሷ ደግሞ ማረፍ ፈልጋለሁ ብላ ወደመኝታ ቤቷ ነበር ያመራችው፡፡ለብሳ የዋለችውን ልብስ ቀይራ ቀለል ያለ ቢጃማ ከለበሰች በኃላ አልጋዋ ላይ ተዘርራ ስለዚህ ውሉ ስለጠፋባት ስለገዛ ትዳሯ ነው ማሰብ የጀመረችው፡፡
ሴት ልጅ ከፍቅረኛዋ ጋር ባላት ግንኙነት ወሲብ ለመፈፅም እምቢ ብትለውና ጥሏት ቢሄድ ..የተዋት ስለማይወዳት አይደለም፤ወሲብን አብዝቶ ስለሚወድ እንጂ፡፡ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ ወንድ ወሲብ ሚፈፅመው ለወሲብ ሲል ሲሆን ሴት ልጅ ደግሞ ወሲብን የምትፈፅመው ለፍቅር ብላ ነው፡፡ወሲብ ለወንድ ልጅ ከመሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ ልክ እንደምግብ ፤ልብስ፤መጠለያ አንድ ነው፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍77❤9
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
በሰሎሜ ላይ እየሆነ ያለው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ወሲብን ሊሰጣት ያልቻለው እሱ ነው፡፡ግን ደግሞ ቢያንስ እስከአሁን ጥላው አልሄደችም፤ቢሆንም በውስጧ የፈጠረባትን ስለልቦናዊ ቀውስ ልትቋቋመው ከምትችለው በላይ እየሆነባት ነው፡፡እንደማንኛውም ሴት በእሷ አረዳድ‹ ከእኔ ጋር ወሲብ የማይፈፅመው ወሲብ የማድረግ ፍላጎት ሳይኖረው ቀርቶ ሳይሆን እኔን ስለማያፍቅረኝ ቢሆንስ?› የሚለው ሀሳብ ሁሌ ነው በአእምሮዋ እየተሰነቀረ የሚያስጨንቃት፡፡
ከወራት በፊት ግን ይሄንን ለማረጋገጥ አንድ ነገር አድርጋ ነበር፡፡‹‹እንዴት አድርጌ የእውነት እንደሚያፈቅረኝ አውቃለሁ?ከእኔ ጋር ወሲብ ማይፈጽመው ሌላ ቦታ በድብቅ የሚሄድባት ሴት ብትኖስ?››በወቅቱ ዋና አላማዋ እነዚህን በእምሮዋ ይጉላሉ የነበሩ ጥያቄዎችን በተግባር ማረጋገጥና ውጤቱን ተከትሎ የራሷን ውሳኔ ለመወሰን ነበር፡፡
ከብዙ መብሰልሰልና መብከንከን በኃላ ምርጥ ያለችውን እቅድ አወጣች፡፡ ለዚህ ተልዕኮ ልትረዳት የምትችል አንድ ጓደኛዋ ትዝ አለቻት፡፡ሀይስኩል አብራት የተማረቻና ስታገባም ሚዜዋ የነበረችውን ሂሩትን ደውላ ቀጠረቻት፡፡
ሂሩት ሰሎሜን ብቻ ሳይሆን አላዛርንም በደንብ ታውቃዋላቸው ….አብረው በመማራቸው የቀረቤታቸው መጠን ይለያይ እንጂ ለሁለቱም ጓደኛ ነች ማለት ይቻላል፡፡ እንደውም ሂሩት ዘጠነኛ ክፍል እያሉ በተወሰነ መልኩ ወደግሩፑ የተቀላቀለችው ለአላዛር ከነባራት የተለየ ፍቅር የተነሳ ነበር፡፡በወቅቱ አማልዬ የራሴ አደርገዋለው የሚል ፅኑ እምነት ነበራት፡፡ለዛም ይረዳት ዘንድ የግሩፑ ብቸኛ ሴት የነበረችውን ሰሎሜን በተለየ ሁኔታ ቀረበቻት፡፡ በኃላ ግን የአላዛር ጉዳይ እንዳሰበችው ባይሳካላትም ከሰሎሜ ጋር ያላትን ጓደኝነት እንደውም ካሰበችው በላይ በጠበቀ ሁኔታ ማስቀጠል ችላለች፡፡ሂሩት ከሰሎሜ ጋር ስትነፃፀር በጣም ልቅም ያለች ቆንጆ ልጅ ነች፡፡በዛ ላይ በጣም ተጫዋችና ቀልጣፋ፡፡
የተቀጣጠሩበት ሆቴል እንደተገናኙ ለወሬ የቸኮለችው ሂሩት ገና በቅጡ ተቀምጠው ያዘዙት መጠጥ እንኳን ሳይቀርብላቸው ‹‹በፈጣሪ… እንዲህ አንገብግበሽ የጠራሺኝ ምን ልትነግሪኝ ነው?፡፡›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ቆይ ተረጋጊ …ነግርሻለው፡፡››
‹‹የጠረጠርኩት ብቻ እንዳይሆን?››
ሰሎሜ ደንግጣ ‹‹ምንድነው የጠረጠርሽው?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ክርስትና እናት ልትሆኚ ነው እንዳትይኝ?››
ሰሎሜ የሄሩትን ያልተጠበቀ ወሬ ስትሰማ ዘወትር ‹‹መቼ ነው አያት የምታደርጊኝ ?››የሚለው የእናቷ ንዝንዝ ትዝ አላት፡፡
‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹አንቺ ደግሞ መቼስ እኔ እያለሁ ልጅሽን ለሌላ ሰው ክርስትና አትሰጪያትም!!››
‹‹የምን ልጅ?››
‹‹ተይ ባክሽ…!!!ገና እንገናኝ ስትይኝ ነው የጠረጠርኩት ..አርግዣለሁ ልትይኝ ነው አይደል…?ስንት ወር ሆነሽ…?መቼስ እናትሽ በአንድ እግራቸው ቆመው ደንሰዋል?››
‹‹ፅድቁ ቀርቶ በቅጡ በኮነነኝ ››አለች እቴቴ፡፡
‹‹ያንቺ እናት ደግሞ ሁሌ የማይገባ ተረት ነው የሚተርቱት…ምን ማለት ነው?፡፡››
ሰሎሜ በማይረባ የጓደኛዋ ግምት ተበሳጨች‹‹አሁን በፅሞና አድምጪኝ …መጀመሪያ አሁን የምነግርሽን ነገር ለማንም እንዳትናገሪ…እንደው ብንጣላ እንኳን ሚስጥር አድርገሽ እስከወዲያኛው በውስጥሽ እንድትቀብሪው እፈልጋለው፡፡››
ሂሩት ፈራች‹‹አረ ችግር የለውም አታውቂኝም እንዴ…?.››
‹‹በእናትሽ ማይልኝ፡፡››
‹‹ይሄን ያህል ምን ቢሆን ነው..?ሰው ገድለሽ ቀብረሽ ነው እንዴ..?ነው ወይስ እንዳቃብርሽ ልትለምኚኝ ነው?በእማሚ ሞት እኔ እንዲህ አይነት ነገር ፈራለሁ፡፡››
‹‹አትቀልጂ!!!... ወይ ማይልኝ ካለበለዚያ አልነግርሽም፡፡›› ኮስተርተር አለቻባት፡፡
‹‹እሺ እማዬ ትሙት…ለማንም አልናገርም፡፡››
‹‹የባልና ሚስቶች ጉዳይ ነው…››
‹‹ማለት..?››
‹‹የእኔ እና የአላዛር ጉዳይ..››
‹‹አንቺና አላዛር ምን ሆናችሁ?››
‹‹እንዴት ብዬ ልንገርሽ …አሳፋሪ ነው፡፡››
‹‹እንደፈለግሽ አድርገሽ ንገሪኝ፡፡ምንድነው እኔ ጓደኛሽ ነኝ እኮ ..በእኛ መካከል መተፋፈር አለ እንዴ..?ለዛውም ካስማልሺን በኃላ ትቅለሸለሻለሽ?ግፋ ቢል ሰረቅኩበት ልትይኝ ነው፡፡›› በማለት ቅድሚያ ወደአእምሮዋ የመጣላትን ሀሳብ ሰነዘረች፡፡
‹‹በስመአብ….አንቺ …አታውቂኝም ማለት ነው..?እንዴት በባሌ ላይ ሰርቃለሁ?››
‹‹ያልሆነ ነገር እንድገምት ካልፈለግሽ… ንገሪኛ፡፡››
‹‹ወሲብን በተመለከተ ነው፡፡››
ሂሩት ይበልጥ ተነቃቃች..‹‹ወሲብ ምን ?አደገኛ ሆኖ አሰቃየሽ….?ምን…. ኩላሊትሽን እያመመሽ ነው?››
ሰሎሜ ከት ብላ ሳቀች..የመገረም ሳቅ…የንዴትና የብስጭት ሳቅ፡፡
አምጣ..አምጣ ‹‹ወሲብ ማድረግ ካቆምን በጣም ቆየን …››ስትል ጉዳዩን አፈረጠችው፡፡
‹‹ቆየን ማለት…?አምስት ቀን….አንድ ሳምንት..ወይስ አንድ ወር?››
በተጎተተ ንግግር ‹‹ስድስት ሰባት ወር አለፈን…..››አለቻት…፡፡
‹ጭራሽ አድርገን አናውቅም እሰከዛሬ ድንግል ነኝ ›› ብላ ልትነግራት አቅም ማግኘት አልቻለችም….እንዴት ከገባሁ አንድ አመት ቢያልፈኝም ባሌ እስከዛሬ ነክቶኝ አያውቅም.. ብላ ከአንደበቷ አውጥታ ትናገር.. ለዚህ ነው ከፊል እውነትና ከፊል ውሸት ደባልቃ ነግራት መፍትሄ ያለችውን ሀሳብ አቅርባላት እንድትተባበራት ለመጠየቅ የፈለገችው፡፡
‹‹ሰባት ወር…!!ምነው ?እናንተ ባለትዳሮች እኮ አንዴ በእጃችሁ አስገብታችሁ እና የራሳችሁ መሆኑኑ ካረጋገጣችሁ በኃላ ችላ የምትሉት ነገር አለ፤እምቢ ብለሽው ነው አይደል?››
‹‹አይ …አኔ አይደለሁም፤እሱ ነው እምቢ ያለኝ፡፡››
‹‹እኔ አላምንም..እንዲሁ አይን አይንሽን አፍጥጦ እያየ ..አፍ አውጥቶ አምቢ እልፈልግም ጠግቤያለሁ..አለሽ?››
‹‹ያው አፍ አውጥቶ እምቢ ባይልም…እናድርግ ብሎኝ ግን ጠይቆኝ አያውቅም፡፡››
‹‹እንዴ ባልሽ አይደለ እንዴ…?እሱ ተዘናግቶ መጠየቅ ካቆመ አንቺ አትጠይቂውም?ብዙ ጊዜ እኮ ብር የሚያሳድዱ የቢዝነስ ሰዎች እንዲህ ናቸው….ሚስታቸውና እና ብራቸውን መለየት ይከብዳቸዋል ፡፡ስለዚህ እሱ ዝም ካለ አንቺ መጠየቅ ነበረብሽ››
‹‹እንዴት ብዬ? ምን ነካሽ ሴት እኮ ነኝ?››
‹‹እንዴ ባልሽን…?ወይኔ እኔ በሆንኩ… ከስር አስተኝቼ ነበር ….በግድ የምደፍረው››
‹‹ባክሽ አትቀልጂ…ወንድ ልጅን ደግሞ እንዴት አድርገሽ ነው የምትደፍሪው?፡፡››
‹‹ለምን አልደፍረውም ..ምነው ጉልበተኛ ስለሆኑ..?እነሱ ጉልበተኛ ቢሆኑም እኛ ደግሞ ከእነሱ የተሻልን ጥበበኞች ነን››
‹‹የጉልበቱ ጉዳይ እንዳለ ሆኖ …እንዴት አድርገሽ ታቆሚዋለሽ››አላቻት እያፈረች፡፡
‹‹ባክሽ ዘዴ አይጠፋም…አሽቼም ሆነ አልቤ እንዲቆም ማድረግ አያቅተኝም፡፡››
‹‹ይሁንልሽ… አሁን ይሄንን ጉዳይ እንድፈታ እንድታግዢኝ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹እንዴት አድርጌ …?በማቆም ነው በመድፈር…?ምን? እጅና እግሩን እንድይዝልሽ ትፈልጊያለሽ?››
‹‹እኔ ተጨንቄ ምሆነው ጠፍቶኛል አንቺ ትቀልጂብኛለሽ አይደል…?በቃ ተይው ተነሽ እንሂድ››ሰሎሜ ተበሳጨች፡፡
‹‹በቃ እሺ ይቅርታ….ንገሪኝ እሺ ምን እንዳግዝሽ ነው የምትፈልጊው?፡፡››
‹‹ምን አልባት ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም ያቆመው ጠልቶኝ ማለቴ ፍቅሩ አልቆ ይመስለኛል..ያንን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡››
‹‹አረጋግጠሸስ?››

👍67❤8
‹‹ካረጋገጥኩማ ….ጥሩ ነው ፍቺ እፈፅመለሁ…እሱስ ለምን ይሰቃይ እኔስ ከማይወደኝ ሰው ጋር ለምን ጊዜዬን አባክናለው፡፡››
‹‹እባክሽ አታሹፊ..አላዛር ነው አንቺን ማፍቀር የሚያቆመው?››
‹‹ምን ይታወቃል.. ሌላ ሴት አፍቅሮ ወይም ለምዶ ከሆነስ?››
‹‹አታስቂኝ…አላዛር ለሌላ ሴት የሚሸነፍ ልብ ቢኖረው እኔ ነበርኩ አሸንፌው ዛሬ ባለቤቴ የማደርገው፡፡ካንቺ ጋር ሳትጀምሩ በፊት እኔ እንዴት አፍቅሬው እንደነበረና ከእሱ ጋር ለመሆን ምን ያህል ጥሬ እንደነበረ ካንቺ በላይ ምስክር የለም፡፡››
‹‹እሱስ አስታውሳለሁ…ግን አሁን እየነገርሺኝ ያለው ከዛሬ አራት አምስት አመት በፊት የነበረ ታሪክ ነው …የሰው ልጅ ደግሞ ሰው ነውና ጊዜ ባለፈና ዘመን በተቆጠረ መጠን ፀባዩም ሆነ አመለካከቱ እየተቀየረ ይሄዳል…..፡፡››አለቻት ፡፡
ሂሩት እንዳለችው….9 ክፍል ሲማሩ ጀምሮ አላዛርን በጣም አፍቅራው መውጫ መግቢያውን እየተከታተለች ስታስቸግረው ነበር፡፡ከእሷ ጋር ጓደኛ እንዲሆኑ ሰበብ የሆናቸውም ያ ገጠመኝ ነው፡፡ቀጥታ ወደ ሰሎሜ ሄዳ‹እባክሽ ጓደኛሽን አፍቅሬዋለው አሳምኚልኝ› ብላ ነበር የተማፀነቻት…የእውነትም ሰሎሜ በወቅቱ ለአላዛር ያለት አመለካከት ልክ እንደአለማየሁና ሁሴን ሁሉ የጠበቀ የልብ ጓደኝነት ስለነበረ ደጋግማ ልታግባባቸውና ልታቀራርባቸው ሞክራ ነበር፡፡እሱ ግን ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ‹እምቢኝ አልፈልጋትም አለ››ለምን ቢባል ምክንቱን ከአንደበቱ አውጥቶ መናገር አልደፈረም…በወቅቱ አለማየሁና ሁሴን ለምን አልፈልጋትም እንዳለ በደንብ ያውቁ ነበር፡፡እያወቁም ስለሂሩት ቁንጅና ማራኪነት አጋናውና አስፋፍተው እየሰበኩት እሺ ብሎ ፍቅረኛው እንዲያደርጋት ደጋግመው ጋፋተውት ነበር፡፡ግግም አለባቸው፡፡እነሱ ያን የህል ጠንክረው የገፋፉት ሂሩት በፍቅር ትጎዳለች ብለው ስላሰቡላት ወይም ለእሱ ስላዘኑ አልነበረም፡፡እሺ ብሎ ከሂሩት ጋር የፍቅር ጓደኛ ቢሆን አንድ ተፎካካሪ እንደሚያስወግዱ ስሌት በማስላት ነበር፡፡ይሄንን ደግሞ ያደረጉት ሳይነጋገሩ ሁለቱም በየራሳቸው ለብቻቸው በማሰብ ነበር፡፡ልክ ሁለት ጠላት አገሮች ሌላ ጠላት ሀገርን ለማዳከም ሳይነጋግሩ በጋራ ለሁለቱም የሚጠቅም የማዳከም ስራ እንደሚሰሩ አይነት፡፡
‹‹አሁን መልሰሽ እንድትፈትኚልኝ ነው የምፈልገው፡፡››
‹‹እንድትፈትኚልኝ ማለት…?ምን ስታይኝ አስተማሪ መስላለሁ?››
‹‹እስኪ በቁም ነገር መሀል አትቀልጂ…እኔ ሁኔታዎችን አመቻቻላሁ፤ ለአዳር ብለሽ ቤት ትመጪያለሽ…እኔ አጉል ሰዓት ላይ ማለት አራት ወይም አምስት ሰዓት ላይ ቤቱን ትቼላችሁ ሄዳለሁ..ከዛ አንቺ ይህንን አማላይ ውበትሽንና ማራኪ ጫወታሽን በመጠቀም የሴትነት ጥበብ ምትይውን አዚም ተጠቅመሽ…ከፈለግሽ እርቃንሽንም ሆነሽ ታማልይዋለሽ..››
‹‹እሺ ካሸነፍኩትና…ልከመርብሽ ካለኝስ?››
‹‹ጥሩ ነዋ…ትወጂው የለ እስከመጨረሻው ፈቅደሽለት ታይዋለሽ፡፡››
ሂሩት በጆሮዋ የምትሰማውን ነገር ማመን አልቻለችም ….‹‹ይህቺ ነችና ልጅት…የምርሽን ነው ግን?››
‹‹ቀልድ ላይ ያለው ይመስልሻል?››
‹‹እሺ አሳሳትኩትና አወጣሁት ይባል…ከዛስ..?ምንም ነገር እንደበፊቱ እንደማይሆን ታውቂያለሽ….?››
‹‹ማለት?››
‹‹ምን ማለት አለው..?አንደኛ እኔ እርግፍ አድርጌ አዳፍኜ የረሳሁትን ፍቅሬን ከተኛበት መቀስቀስ ይሆንብኛል…ከዛ በኃላ እንዴት አድርጌ ወደኃላ መመለስ እችላለሁ?እሱስ ከዛ በኃላ ጣመኝ ድገሚኝ ቢለኝስ..?በምን አንጀቴ አይ ለአንዴ ነበር አይሆንም እለዋለው፡፡አንቺስ ከዛ በኃላስ ከሌላ ሴት ጋር ለዛውም ከጓደኛሽ ጋር መተኛት ፈቅዶ ካንቺ ጋር የሰነፈውን ባልሽን እንዴት ልታደርጊው ነው?እንዴትስ ብለሽ አብረሽው መኖር ልትቀጥይ ትችያለሽ?››
‹‹ይሄን ሁሉ አውጥቼ አውርጄ ደጋግሜ ሳላስብበት ..ጥቅምና ጉዳቱን ሳላሰላ ለአንቺ ለማማከርና እርዳታሽን ለመጠየቅ የደፈርኩ ይመስልሻል?፡፡››
‹‹አይ እሱማ በደንብ እንዳሰብሽበት ያስታውቃል፡፡እኔ ግን እሺ ብሎኝ ብናደርግም እምቢ ብሎ ቢያባርረኝም በሁለቱም እኩል እንደምጎዳ ታውቂያለሽ?ያንን አስበሽዋል?››
‹‹እንዴት?››
‹‹እሺ ብሎኝ ቢሳሳትልኝ…ጊዜዊ ደስታ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡እንደነገርኩሽ ፍቅሩ ሊያገረሽብኝ ይችላል.. ወደኃላ መመለስ ከባድ ሊሆንብኝ ይችላል…ከአንቺና ከእሱ ለመምረጥ እገደድ ይሆናል….እምቢ ብሎ ቢገፈትረኝም እንደዛው ከአመታት በፊት ተሰምቶኝ የነበረውና ለወራት ድባቴ ውስጥ ከቶኝ የነበረው ያለመፈቀር ያለመፈለግ ስሜት ከእንደገና ይቀሰቀስብኝና እሱን ለማስታመምና መልሼ ለማገግም በጣም እቸገር ይሆናል?ብቻ ውስብስብ ነው፡፡››የውስጧን ስጋትን ፍርሀት ዘርዝራ ነገረቻት፡፡
‹‹አውቃለሁ…ለዛ እኮ ነው መስዋዕት ክፈይልኝ የምልሽ፤ደግሞ እሺ ብሎ ከተሳሳተልሽ እና በዛው ለመቀጠል ከተስማማ እኔ ድምፅ ሳላሰማ ሹልክ ብዬ ከመካከላችሁ ወጣለሁ፡፡››
‹‹ባክሽ አታስጎምዢኝ ….ባልሽን ለእኔ ጥለሽ?››
‹‹አዎ…. ያው ከአንቺ ጋር ፈቅዶ ወሲብ ፈፀመ ማለት እኮ ለእኔ ያለው ፍቅር አልቋል ወይም መጀመሪያውኑ መስሎት እንጂ አያፈቅረኝም ነበር ማለት ነው፡፡እናም ከማያፈቅረኝ ሰው ጋር ደግሞ ቀሪ እድሜያን በድባቴ ውስጥ ሆኜ መግፋት አልፈልግም፡፡ ..እፈተዋለሁ…ከፈተሁት ደግሞ ውሎ አድሮ ሌላ አንድ ማላቃትን ሴት ማግባቱ አይቀርም…ያ መሆኑ ካልቀረ ደግሞ ያን እድል አንቺ የምወድሽ ጓደኛዬ ብታገኚው እመርጣለሁ፡፡››
‹‹እውነት ግን እንዲህ ነው የምታስቢው?፡››
‹‹አዎ….አየሽ አላዛር የዛሬ ባለቤቴ መሆኑን ብቻ አትይ ..የልጅነት ጓደኛዬ ጭምር ነው፡፡በባልነቱ እንከን ቢኖርበትም እንደጓደኛ ግን ጉድፍ የማላነሳለት ምርጥ ሰው ነው..እና ያልሆነ ሰው እጅ እንዲወድቅ ፈፅሞ አልፍልግም፡፡ያ ለእሱ አይገባውም፡፡››
‹‹ይሄ ነገር ግን በህልሜ አይደለም አይደል?››ተንጠራራችና ከመቀመጫዋን ለቃ ወደፊት በመቅረብ ጉንጯን ሳመቻት፡፡
‹‹አንቺ እውነትም በህልሜ አይደለም፡፡››
‹እና እሺ አልሺኝ ማለት ነው?››
‹‹በፍፅም እሺ አላልኩሽም…ግን አስብበታለው፡፡››
‹‹አመሰግናለሁ….አስብበታለሁ ካልሽ እንደተስማማሽ ቆጥሬ ዝግጅቴን ጀምራለሁ……በይ ተንሽ እንሂድ››አለችና ሂሳብ ከፍለው ወጡ፡፡

👍78🤔7❤4🥰4
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
===================
አላዛር አልጋ ላይ ተጋድሞ በጥልቀት እያሰበ ነው፡፡ሰሎሜ ቀን ከሂሩት ጋር ያወራችውንና የዶለተችውን ነገር መልሳ በደንብ እያመዛዘነች ስለሆነ ፈጥና ወደመኝታ ቤት ለመግባት አልፈለገችም፡፡ሳሎን ሶፋ ላይ ተዘርግታ አይኖቾን የተከፈተው ቲቪ ላይ በመሰካት በሀሳብ ግን ነጉዳለች፡፡
በተመሳሳይ አላዛርም የባለቤቱን የከረረ የስሜት መለዋወጥ በእራት ሰዓት ስላስተዋለ ጥልቅ ትካዜ ውስጥ ገብቷል፡፡ ‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምቀጥለው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ሚስቱን ያፈቅራታል..፡፡በጣም ነው የሚያፈቅራት፡፡ለመጀመሪያ ቀን ካገባት ቀን ጀምሮ በሙሉ ልቡ እየተንከባከባት ነው፡፡ግን ምንም ያህል ቢጥር ደስተኛ ሊያደርጋት አልቻለም፡፡እስከአሁን እንደወንድሟ ነው አብሯት እየኖረ ያለው፡፡መሆን የሚገባው የሚጠበቅበትም ግን እንደባሏ መሆን ነበር፡፡እንደዛ ቢሆን ልክ እንደተመኘው ሙሉ ደስተኛና ፍልቅልቅ ትሆንለት ነበር፡፡ ያንን ማድረግ ግን አልቻለም…፡፡በጣም እያስጨነቀው ያለው ደግሞ እስከአሁን አለመቻሉ አይደለም..፤ መቼ ሊችል እንደሚችል ፍፁም አለማወቁ ነው፡፡እጅን አንቀሳቀሰ እና ወደቢጃማ ኪሱ ሰደደ..ስልኩን አወጣና ጎግል ከፈተ፡፡ ስንፈተ ወሲብ ብሎ ሰርች ሲያደርግ ብዙ ምርጫዎች መጡለት፡፡
ከመካከላቸው በደመነፍስ መረጠና አንዱን ከፈተው፡፡ትራሱን ቀና አድርጎ አስተካከለና የሆነ የሚጠቅም ነገር ባገኝ በሚል ተስፋ ማንበብ ጀመረ፡፡
ርእሱ ‹‹የስንፈተ ወሲብ አይነቶች ፤ምክንያቶችና መፍትሄዎቹ›› ይላል፡፡
በወንዶች ላይ የሚታዩት የስንፈተ ወሲብ ችግሮችን በሶስት መልኩ ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ አንደኛው የብልት መነሳት ችግር ወይም በሌላ አገላለፅ ስንፈተ ወሲብ እየተባለ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለተኛው እርካታ ደረጃ ሳይደርስ የዘር ፈሳሽ ማውጣት ወይም ገና አካባቢው ጋር እንደደረሱ መርጨት ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ የወሲብ ስሜት አልባነት ወይንም ጭሩሱኑ ወሲብ ለማድረግ ፍላጎት ማጣት ናቸው፡፡
አላዛር ንባቡን ገታ አደረገና ስላነበበው ነገር ማሰላሰል ጀመረ..‹‹ከእነዚህ ሶስት ምክንያቶች መካከል የእኔ ችግር የትኛው ላይ ነው የሚያርፈው?››ሲል እራሱን ጠየቀና
ማሰላሰል ጀመረ፡፡የእሱ ችግር ሙሉ በሙሉ የወሲብ ስሜት ማጣት እንደሆነ ተረዳ፡፡እና ንባቡን ካቆመበት ቀጠለ፡፡
የመጀመሪያውን ስንመለከት የብልት መነሳት ችግር ያለባቸው ሰዎችን በብዛት እናገኛለን፡፡ ይሄ አይነት የወሲብ ችግር በተለያየ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ላይ የሚከሰት ቢሆንም በተደጋጋሚ ወደ ህክምና የሚመጡት ግን ዕድሜያቸው ከስልሳ ዓመት በላይ የሆኑት ሰዎች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ወጣቶችም አልፎ አልፎም ቢሆን የዚህ ጉዳይ ተጠቂዎች መሆናቸውን ሪፖርት ሲያደርጉ ይታያል፡፡
ችግሩ ከየት ይነሳል? ብለን ስንመለከት ሁለት አይነት ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከስነ ልቦና ጋር የተያያዘ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በተለያዩ በሽታዎች በሚፈጥሩ የጎንዬሽ ተፅዕኖ ምክንያት ይከሰታል፡፡ ዋነኛው የስንፈተ ወሲብ መንስኤ ተብሎ የሚጠቀሰው የስነ-ልቦና ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአዕምሮ ውጥረት ፤ ጭንቀት እና የተለያዩ ሀሳቦች ለስንፈተ ወሲብ ችግር ያጋልጡናል፡፡ የአካል ድካም እና መዛልም ሌለኛው ምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ አካሉ በብዙ ስራ ሲንገላታ የዋለ ሰው በግንኙነት ወቅት የብልት መነሳት፣ ስሜት ማጣት አሊያም ለወሲብ ምቹ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሊገኝ ይችላል፡፡
አንድ ሰው የሀሳብ መደራረቦች በአእምሮው እንደታጨቀ ወሲብ ለማድረግ በሚሞክርበት ጊዜ ብልት ትክክለኛው ጥልቀት ላይ ደርሶ ተገቢውን እንቅስቃሴ ከማድረጉ በፊት አስቀድሞ ጥንካሬውን የሚያጣበት ሁኔታ ይከሰታል ፡፡ ይህን በምሳሌ ብንመለከት ከፍቅር ጓደኛው ጋር ወሲብ በሚፈፅምበት ወቅት ነጋዴ ከሆነ ስለተጋረጠበት የንግድ ችግር የመስሪያ ቤት ኃላፊ ከሆነ ስላልተሳኩ የድርጅቱ እቅዶች ካለው ኃላፊነት ጫና የተነሳ በአዕምሮው ሊመላለሱበት ይችላሉ፡፡ ይህም ጥሩ ያልሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳይከውን ምክንያት ይሆነዋል፡፡ግብረስጋ ግንኙነት ደግሞ በባህሪው ሙሉ ለሙሉ ትኩረት የሚሻ የስሜት ተራክቦ ነው፡፡ ሌላው በባልና በሚስት መካከል አለመግባባት እና ቅሬታ በሚኖርበት ጊዜ ተነሳሽነቱ በሁለቱም ወገን ይቀንሳል፡፡……..
እስከአሁን ያነበባቸው የስንፈተ ወሲብ ችግር የሚያጋልጡ ምክንያቶች ለጠቅላላ እውቀት ጥሩ ግንዛቤ የሰጡት ቢሆንም ቀጥታ የእሱን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል መፍትሔ ሚጠቁሙ ሆነው አላገኛቸውም..ቢሆንም ግን ተስፋ ቆርጦ ንባቡን ማቋረጥ አልፈለገም…ትንፋሹን ሰበሰበና ማንበቡን ቀጠለ፡፡
የአንድሮጂን ሆርሞን መመረት ወንዶች ላይ ብዛት ያለው የደም ፍሰት ወደ ብልት እንዲዘዋወር በማድረግ ብልት እንዲነሳ ያደርጋል፡፡ ከላይ የጠቀስናቸው እንደ ጭንቀት፤በስራ መዛል ወዘተ አይነት ምክንያቶች ይህን ሆርሞን በተገቢው መንገድ እንዳይመረት ያደርጋል፡፡በዛም ምክንያት ወደብልት የሚፈሰው የደም መጠን አናሳ ስለሚሆን የብልት በተገቢው ጥንካሬ የመቆም ችግር ያጋጥመዋል፡፡ይሄን ለማካካስ ሲባል በተለይ በወጣቶች የወሲብ ፊልሞች ለማየት ወደመነሳሳት ያዘነብላሉ፣ ይሄም በጫና፣ በሃዘን እና በድካም ላይ ሆነንም የወሲብ ስሜታችን እንዲነሳሳ ያደርጋል፡፡ያ ደግሞ በተለይ ለብልት መነሳሳት አና ለፍላጎት መጨመር ጊዜያዊ መፍትሄ ሆኖ ቢያገለግልም በቆይታ ግን የራሱ የሆነ የጎንዬሽ ጉዳት ማስከተሉ አይቀርም፡፡የፊልም ኢንደስትሪው ሚያመነጫቸው የወሲብ ፊልሞች በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከዛም አልፎ በጎልማሶች ዘንድ በደንብ የሚታዩ ናቸው፡፡እንዚህ ወሲብ ፊልሞች ከላይ ሲታዩ እጅግ ማሪኪ ስሜት ቀስቃሽና መንፈስ አነቃቂ መስለው ቢታዩም በሚያየው ወጣት ላይ የሚያስከትሉት ስነልቦናው ቀውስ ቀላል የሚባል አይደለም፡፡አንደኛ ወጣቱ የአካላዊም ሆነ ስነልቦናዊ ዝግጅት ሳያደርግ ወጣ ያሉ አፈንጋጭ ወሲባዊ ተራክቦ እንዲያደርግ ይወሰውስታል፡፡ያ ደግሞ ለቋሚ የጤና ችግርና ወሲባዊ ችግር ይዳርገዋል፡፡ሁለተኛ በፊልሞቹ የሚደረጉ ወሲባዊ ተራክቦዎች ከሰውኛ ይልቅ ሜካኒካል ገፅታ ያላቸው ከ30 ደቂቃ አስከአንድ ሰዓት የሚዘልቁ አይነቶች ናቸው፡፡
እርግጥ አንድ ሰው በውሲብ ግንኙነት ያንን ያህል ሊቆይ አይችልም ለማለት አይደለም….ግን ከሺ ጥንዶች በአንዶቹ የሚከሰት ነገርን እንደኖርማልና የተለመደ አድርጎ ማቅረብ በአብዛኛው ላይ የሚፈጥረው ስነልቦናዊ ውዥንብር ቀላል የሚባል አይደለም፡፡ለምሳሌ በስንፈተወሲብ ችግር የሚመደበው ቀድሞ መርጨት ችግር የሚባለው አንድ ሰው ወሲብ ጀምሮ ከአንድ ደቂቃ በታች በሆነ የጊዜ ርዝመት ውስጥ የዘርፍሬውን ካፈሰሰ ነው፡፡እንግዲህ ሁለትም ሶስትም አምስትም ደቂቃ ኖርማልና በብዙ ውንዶች የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡ይሄንን ሀቅ ወንዱም ሆነ ሴቷ ማወቅ አለባቸው፡፡ሀያ ..ሰላሳ ደቂቃ መቆየት የቻለም እንደዛው ያንን እንደጀግንነት ማውራት ትርጉመ ቢስ ነው፡፡ዋናው ምን ያህል የጊዜ ርዝመት ቆየ ሳይሆን በቅፅበት ውስጥም ቢሆን ምን ያህል ፍፃማዊ ደስታ ተቀያይረናል…ምን ያህል በአየር ላይ ተንሳፈን ነበር…?ምን ያህልስ ሰዓት አንዳችን በሌላችን ውስጥ ጠፍተን ነበር…?የሚለውን ነው መመዘኛ መሆን ያለበት… እና አንድ ሰው በተቻለው መጠን እነዚህን የምራባዊያን የወሲብ ፊልሞችን ከማየት እራሱን

👍53❤10
ማቀብ አለበት ካልሆነ የእድሜ ልክ ሱስ ነው የሚሆኑበት..ሱሱ ደግሞ ከላይ የተጠቀሱትን ችግሮችን ጨምሮ ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ማስከተላቸው አይቀርም…ምክንያቱም ያንን ፊልም ለመነቃቃትና ዘና ለማለት ብቻ ተጠቅሞ ከተፅዕኖቸው ተጠቂ ላለመሆን ከፍተኛ የሚባል ብስለትና የአእምሮ ጥንካሬ ይጠይቃል…ያንን ደግሞ ሁሉም ሰው የለውም፡፡
አላዛር ከንባቡ እርፍት ወሰደና የወሲብ ፊልሞችን ስለማየት ማሰብ ጀመረ… እሱም ከዚህ በፊት አንድ ሁለቴ ለማየት እና ውጤቱን ለማወቅ ሞክሮ ነበር….ግን ጭራሽ ዘግናኝና የሆረር ፊልም የሚፈጥረውን አይነት አስፈሪና ሰቅጣጭ ምስል ነው በአእምሮ የፈጠረበት፡፡የእሱ ዋና ችግር ርቃን የሴት ገላ ከማየት ጋር ቀጥታ የተያያዘ እንደሆነ ያውቃል፡፡የወሲብ ፊልም ደግሞ እርቃን የሴት ገላ ብቻ ሳይሆን እርቃን የሴት ነፍስም ጭምር የሚታይበት ስለሆነ ለእሱ የሚሆን መፍትሄ ስላልሆነ ወዲያውን ነበር ከአእምሮ የሰረዘው፡፡
ቀጥሎ ማንበብ ደከመው….ለማቋረጥ አለና እንደምንም እራሱን አበረታታ፡፡ አንድ የመጨረሻ አንቀጽ ለማንበብ እስክሮል አደረገና አይኖቹን ንባቡ ላይ ተከለ፡፡
ሁለተኛው የስንፈተ ወሲብ ምክንያት ኦርጋኒክ የሚባለው ሲሆን የተለያዩ ህመሞችን ተከትሎ የሚመጣ የወሲብ ችግር ነው፡፡ ስኳር፣ ደም ግፊትና የአባላዘር በሽታዎች ያለባቸው ሰዎች በስንፈተ ወሲብ ችግር የመጠቃታቸው እድል ሰፊ ነው፡፡ ሌላው የተለያዩ አደገኛ መድኃኒቶች አልኮልና ሀሺሽ የመሳሰሉት ዕፃች የደም ዝውውርን የሚቀንሱ ናቸው፡፡ በግንኙነት ወቅት ብልት እንዲነሳ ካስፈለገ ከፍተኛ የደም ዝውውር ሊኖር ይገባል፡፡ በቂ የሆነ የነርቭ መነቃቃትም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህ ነገሮች የሚያስከትሉት ጫና ደግሞ በወሲብ የመነቃቃትና ትክክለኛውን ኡደት ጠብቆ በሚጠበቀው ደረጃ እርካታ ላይ ለመድረስ እንዳይችሉ እንቅፋት ይሆናል፡፡
እነዚህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉን ህክምናዊ መፍትሄዎች የትኞቹ ናቸው? የሚለውን ስንመለከት በቅድሚያ ወሲባዊ ህይወት እንደ ምስጢር በየሰው አዕምሮ ውስጥ በመቀበሩ ችግሮችን አውጥቶ ከህክምና ባለሙያዎች እና ከትዳር አጋር ወይም ፍቅረኛ ጋር ለመወያየት አለመቻል በራሱ ችግሩን የሚያባብሱ ምክንያቶች ናቸው፡፡ ከህክምናው ጋር የተገናኙትም በትክክል ህክምና ተከታትለው ሲያጠናቅቁ አይታዩም፡፡ በመሆኑም በቀላሉ መፍትሄ ላያገኙ ከሚችሉበት አጋጣሚ በመራቅ ለተለያዩ አላሰፈላጊ የጊዜና ገንዘብ ብክነቶች ይዳረጋሉ፡፡
በመሆኑም መፍትሄው የመጀመሪያው እርምጃ የችግሩን መነሻ ምክንያትን ለይቶ ማወቅ ነው፡፡ እንደመንስኤው የተለያዩ ህክምናዎች እንዲሰጡበት ያደርጋል፡፡ ከስነ-ልቦና ጋር የተያያዘ ከሆነ ያለመድኃኒት ሊስተካከል ይችላል፡፡ ያለውን ችግር ማለትም አካላዊና አዕምሮአዊ ሁኔታ የስነ-ልቦና ድጋፍ በማግኘት በማስተካከል ሊቀረፍ ይችላል፡፡ ከተለያዩ ህመሞች የሚነሳው የስንፈተ ወሲብ ችግር ከመቆጣጠርና ከመከላከል ባሻገር መድኃኒቶችን ለደም የሚገባውን የወሲብ ስሜት መጠበቅ የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ፡፡ በዚህ ውስጥ አልፈን መፍትሄ ካልተገኘ የመጨረሻው አማራጭ ረዳት መድኃኒቶችን ማካተት ይሆናል፡፡
እነዚህ መድኃኒቶች ያላቸው ጥቅም ምንድን ነው? ካልን የደም ዝውውር በመጨመር ነርቮች እንዲነቃቁ የወንዱ ብልት አካባቢ ያሉት ጡንቻዎች እንዲኮማተሩ እና ብልት እንዲጠነክር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ መድኃኒቱም በህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ መሰረት በጥንቃቄ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡ ምክንያቱም አይነትና መጠኑ ሊያውቅ የሚችለው በህክምናው ዘርፍ በቂ ትምህርትና ልምድ ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ተያይዘው ለሚመጡ ተጓዳኝ አሉታዊ ተፅዕኖዎች ተጠንተው ቅድመ እና ድህረ ጥንቃቄ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ችግሩ እንዲቀረፍ 50 በመቶ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡ ከችግሩ አይነትና መጠን ተነስተን ነው መድኃኒቶቹን የምናዘው፡፡መድኃኒቶች ያሏቸውን ጥቅም ያህል ብዙ ጉዳቶችንም ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው የባለሙያ ድጋፍ አስፈላጊነት ሁኔታዎችን በማገናዘብ መድኃኒቶችን ማዘዝ ውጤታቸውንም መከታተል ከተቻለ መድኃኒቱ ያለምንም ጉዳት የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያስመዘግብ ይረዳዋል፡፡
ሰዎች ከተለያዩ ምንጮች ካገኟቸው መረጃዎች ተነስተው መድኃኒቶችን ያለህክምና ትዕዛዝ ይወስዳሉ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ለችግሩ ትክክለኛ መፍትሄ ሊሰጥ ወደሚችለው ባለሙያ ለመሄድ ያለው ተነሳሽነት በጣም ዝቅተኛ መሆን፣ የወሲብ ምስጢራዊነት እሳቤ፣ የመድኃኒቶቹን የጎንዮሽ ችግር ያለመረዳት፤ የጓደኛና የተለያዩ የወሲብ ትዕይንቶች ከሚያስከትሉት ጫና የተነሳ ነው፡፡ ችግሩ ሳይኖር መድኃኒቶችን አፈላልጎ መጠቀም የመቻል አቅምና ድፍረት በተጨማሪ ህገ-ወጥ የመድኃኒት ዝውውር መኖሩ የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል፡፡
ለምሳሌ ቪያግራ የተሰኘውን መድኃኒት በተለያየ መልኩ ማግኘት የቻሉ ሰዎች ዝም ብለው ቢጠቀሙበት ምን ያስከትላል? ስንል የልብ ድካም ያለባቸው ችግር ይገጠማቸዋል፡፡ በተጨማሪም ከልክ ያለፈ የብልት መነቃቃት ሳቢያ ብልት ቆሞ ላይመለስ የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ በተጨማሪም በግንኙነት ወቅት ብልት በጣም ከመወጣጠሩ የተነሳ የብልት ዘንግ ስብራት ሊያጋጥም የሚችላቸው ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፡፡ አንድም ጊዜያዊ ከፍተኛ ህመም፤በተጨማሪም የልብ ስራን የማዛባት ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡
የስንፈተ ወሲብ መድኃኒቶቹን ማግኘት ስለተቻለ ብቻ መጠቀሙ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ብዙ ጊዜ መድኃኒቱ እንደ ችግሩ ሁኔታ ታይቶ በቀን አንዴ ግንኙነት ከማድረጊያ ጊዜ አንድ ሰዓት ቀድሞ እንዲወሰድ የሚታዘዝ ሲሆን በተደጋጋሚ እንዲወሰድ አይመከርም፡፡መድኃኒቱን ደጋግሞ መውሰድ አስቀድመን የጠቀስናቸውን ችግሮችን እንዲባባሱ ያደርጋል፡፡ በተለምዶ የወንዶች ብልት ከተነሳ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ወደ ቀድሞ ቦታው ይመለሳል፡፡ ለረጅም ሰዓት ተነስቶ በሚቆይበት ወቅት እጅግ በጣም ከፍተኛ ህመም አለው፡፡ መልሶ ግንኙነት ማድረግ በሚያስፈልግበት ጊዜም ሊያስቸግር ይችላል፡፡
እኛ አገር ባይኖርም በባለትዳሮች መሀከል የሚደረግ የወሲብ ህክምና በተለያዩ ሀገሮች የሚሰጥ ሲሆን ከትዳር አጋር ጋር በሚያጋጥም የወሲብ አለመጣጣም ችግሮችን በማጥናት መፍትሄ ማስቀመጥ የሚቻልበት ሂደት ነው፡፡ በወሲብ ህይወት ውስጥ ዝግጁነት እና ግልፅነት ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ ነጥቦች ናቸው፡፡ ስለ ወሲብ ከትዳር አጋር ወይም ከፍቅረኛ ጋር በግልፅ መነጋገር ለችግሮቹ መፍትሄ ለመፈለግ ይረዳል፡፡ በዚህ ሳቢያ የሚደርስ የትዳር መፍረሶችን መታደግ ይቻላል፡፡ ተገቢውን ህክምና ማግኘት እና በተለይም ቤተሰባዊ መረዳዳት እና በወሲብ ወቅት ማዘጋጀት፣ እራስን የተረጋጋ፣ ፍቅር የተሞላበት እና መተማመን የሰፈነበት ወሲብ ሙሉ ደስታን ያጎናፅፋል፡፡
መድኃኒቶች ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ጥራታቸው ያልተፈተነ፣ የማዳን አቅማቸው፣ የጎንዮሽ ጉዳታቸው፣ የአወሳሰድ መጠናቸውና ልዩ ጥቅም የሚያስገኝባቸው ችግራዊ መንስኤዎች ስለማይታወቁ ያለሐኪም ትዕዛዝ መውሰዱ ለከፋ ችግር ያጋልጣሉና የጥንቃቄ እርምጃው እየተስተዋለ ሊሆን ይገባዋል፡፡

👍44❤3
ማንበቡን ጨረሰና ሙሉ በሙሉ ስልኩን ዘግቶ ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠ፡፡እስከአሁን ከነበበው ሙሉ በሙሉ ልቡ ላይ ያረፈው ከትዳር አጋር ጋር ስለሁኔታው በግልፅ መነጋገር የሚለው ምክረ-ሀሳብ ነው፡፡ስላለበት የስንፈተ ወሲብ ችግር ከሰሎሜ ጋር በግልፅ ማውራት እና መፍትሄ ማግኘት ይፈልጋል፡፡ለምን የእሷን ጭን ከፍቶ መግባት እንዳቃተው..ለምን ሰውነቷ ከሰውነቱ ሲጣበቅ እንደሚሸማቀቅ ሁሉን ነገር ከልጅነቱ ጀምሮ በጉልምስና ወቅት እስከአጋጠመው ዘግናኝ ገጠመኝ ሁሉንም በዝርዝር ሊነግራት ይፈልጋል፡፡ግን ድፍረቱን ከየት ያምጣው…?ነገሮች ጭራሽ ተስፋ አስቆራጭ ሆነው ቢታዬትስ…?በልቡ የቀበረውን ሚስጥር ዘርግፎ ከነገራት በኃላ ፍፅም ተጠይፋውና ጠልታው ሻንጣዋን ሸክፋ ብትሰወርስ?ፍራቻው ይሄ ነው፡፡ግራ እንደተጋባና በሀሳብ እንደናወዘ. አንድ እልባት ላይ ሳይደርስ የእሷን ኮቴ ሰማ…..የሆነ መጥፎ ነገር ሲሰራ ድንገት እንደያዘችው ነገር ሽምቅቅ አለ፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍44😁5👏1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
================
ሰሎሜና ሂሩት እንደተባባሉት ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል፡፡ .. ሂሩት በሰበቡ እነሱ ቤት እንደምታድር ለአላዛር ነግራው በሰዓቱ እንድትገኝ አደረገች፡፡እራት በልተው መጠጥ እየቀማመሱ ካመሹ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ ከእናትዬው እንደተደወለላትና እንዳመማቸው በመናገር ብቻቸውን ትታቸው ሄደች፡፡ አላዛር ልከተልሽ ቢላትም እምቢ አለችው፡፡ቀጥታ እናቷ ቤት ሳይሆን ቀን ወደዘጋጀችው ከሰፈራቸው ብዙም የማይርቅ ሆቴል ነበር የሄደችው፡፡ቀጥታ የተከራየችው ቤርጎ ገብታ ምን ይፈጠር ይሆን እያለች ስትጨነቅና ስትገላበጥ አደረች፡፡እንቅልፍ በአይኗ ሳይዞር ነበር ንጊቱን የሚያበስሩ የወፎችን ዝማሬ የሰማችው…ሂሩትም ገና ሰማይና ምድሩ በቅጡ ሳይላቀቅ ከለሊቱ 12 ሰዓት አካበቢ ነበር የደወለችላት፡፡ወዲያው ክፍሏን ለቃ ወጣችና የሆቴሉ ፓርኪንግ ጋር ያቆመቻትን መኪና ውስጥ ገብታ ወደነገረቻት ቦታ ተፈተለከች፡፡በወቅቱ የተከፈተ ካፍቴሪያ ወይም ሆቴል ማግኘት ስላልቻሉ ሰሎሜ መኪና ውስጥ ቁጭ ብለው ነበር ያወሩት፡፡
ሶሎሜ ስታገኛት ፈክታና ተፍለቅልቃ አገኛታለሁ ብላ ነበር ያሰበችው..ግን አኩርፋና ለምቦጯን ጥላ ነው ያገኘቻት፡፡ይሄ ደግሞ ይበልጥ አስደነገጣት፡፡‹‹የሆነ ነገር ባይፈጠርማ እንደዚህ አትነፋፋም ነበር፡፡በቃ ተሳክቶላት አሳስተዋለች..በቃ ችግሩ ከእኔ ነው››ብላ ደመደመች፡፡ድምጽ አውጥታ ብትጮህ ወይም እንባዋን ዘርግፋ ብታለቅስ ደስ ይላት ነበር፡፡ግን እንደዛ በማድረግ ሂሩት ፊት ደካማ ሆና መታየት አልፈለገችም፡፡
ከአሁን አሁን አንደበቷን አላቃ የሆነ ነገር ትለኛለች ብላ ብትጠብቅ ዝም ብላ እንዳቀረቀረች የቀኝና የግራ እጇን መዳፎች አንድ ላይ አቆላልፋ እያፍተለተለች ነው፡፡እሷን እንድትናገር መጠበቁ አሰልቺ ሆኖ ስለታያት‹‹እሺ እንዴት ሆነ?››በማለት ቃል አወጣችና ጠየቀቻት፡፡
‹‹በፊትም ተይ ይቅርብኝ ያልኩሽ ይሄን ፈርቼ ነበር…››እንባዋን ዘረገፈችው፡፡
‹‹አይዞሽ ..ምንም የሚያስለቅስ ነገር እኮ የለም..ምንም ነገር ሊፀፅትሽ አይገባም…እኔ እራሴ ፈቅጄና ገፋፍቼ እኮ ነው እንድታደርጊ ያደረኩሽ…አሁን ሁሉ ነገር ግልፅ ሆኖልኛል…… ስለሁሉም ነገር አመሰግናለሁ›› አለቻት፡፡
ከአንደበቷ እየተወረወረ የሚወጣው ቃል ለራሷ እራሱ ሻካራነቱ እየተሰማት ነበር..እስከዛሬ ለሌላ ሰው ከተናገረቻቸው ንግግሮች እጅግ መራሩ ንግግር ነው፡፡እንደውም ንግግር እንዲህ ሊመር እንደሚችል ሲሰማት የመጀመሪያ ቀን የህይወት ልምዷ ነበር፡፡
ሂሩት የሆነ ነገር ትላለች ብላ ስትጠብቅ እሷ ግን እጇን ወደኪሷ ከተተችና ሞባይሏን በማውጣት ከፈተችና ሰጠቻት፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹እይው በቃል ከምነግርሽ በምስል ይሻላል ብዬ አንቺ ከወጣሽ በኃላ ያለውን ትእይንት ሁሉ እሱ ሳያውቅ ቀርጬዋለሁ››
‹‹ምን ሊያደርግልኝ ነው የማየው?‹‹ገና ስታስበው ዘገነናት…የገዛ ባሏ… ቀለበት እጣቷ ላይ አጥልቆ ያጫት፤ ቬሎ ሰውነቷ ላይ አልብሶ ያገባትና አንድ ቀን ጭኗን ፈልቅቆ ማያውቀው ሰው አሁን ፊት ለፊቷ የተቀመጠችውን የገዛ ጓደኛዋን እርቃን ሰውነቷን አቅፎ ፤ቅስር ጡቶቻን እየጠባ…መቀመጫዋን እየጨመቀ…ሲያስጮኸት…እላዮ ላይ ወጥቶ ..ሁለቱም በስሜት እሳት ግለው ነበልባሉ በዙሪያቸው ሲንበለበል በምናቧ ሳላችና ዝግንን አላት..እንደምንም የሰጠቻትን ሞባይል አስጠግታ የተቀረፀውን ማየት ጀመረች፡፡ከጠበቀችው ፈፅሞ ተቃራኒ የሆነ ነገር ነው እያየች ያለችው፡፡
ሂሩት እየደነሳች ተራ በታራ ልብሷን ስታወልቅ…አላዛር ፊቱን ስልኩ ላይ አቀርቅሮ እሷን ላለማየት ሲጠነቀቅና ሲሸማቀቅ…እርቃኗን ሔዳ ስልኩን ከእጁ ነጥቃ ወደሶፋው ወርውራ እላዩ ላይ ለመቀመጥ ስትሞክር፤ከላዩ ላይ ወርውሮ ወለል ላይ ጥሏት እየተንዘረዘረ ሲናገር‹‹አንቺ ምን አይነት ክፉ ሴት ነሽ..ጓደኛሽ አንቺን አምና እኮ ነው ባሏን ጥላልሽ የሄደችው…እኔ እንኳን ልሳሳት ፈቅጄ ባስቸግርሽ አንቺ ትሞክሪዋለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም..ደግሞ ከነዛ ሀሉ ጓደኞቾ አንቺን መርጣ ሚዜ ማድረጓ..?አዝናለሁ..እኔ ሰሎሜን በጣም ነው የማፈቅራት ስልሽ እንዲሁ ተራ ፍቅር መስሎ እንዳይሰማሽ….ነፍስ ካወቅኩበት ቀን ጀምሮ ከእናቴ ቀጥሎ ስወድና ሳፈቅራት.. በየሄደችበት እየሄድኩ ሳጅባት… ስታለቅስ አልቅሼ ስትስቅ ስስቅ እድሜዬን የፈጀሁባት ..የማንነቴ ክፋይ ነች፡፡እሷን ከዳሁ ማለት እራሴን ከዳሁ ማለት ነው፡ያ ከሚሆን ደግሞ ህይወቴን ዛሬውኑ ባጣ ይሻለኛል….በይ ልብስሽን ልበሺና እንግዳ ቤት ገብተሸ ተኚ….ይሄንን ቅሌትሽን እንዳልተፈጠረ እንርሳው…ምክንያቱም የማፈቅራት ሚስቴ በጓደኛዋ መከዳቷን አውቃ እንድታዝና አልፈልግም…››ብሎ ጥሏት አንደኛ ወለል ላይ ወደሚገኘው መኝታ ቤታቸው በመንደርደር ሲወጣ ያሳይና ቪዴዬ ይቋረጣል፡፡
‹‹ታድዬ.!!.ይወደኛል ማለት ነው..?አሁንም ከእኔ ፍቅር እደያዘው ነው››…ተንደርድራ ጉንጯ ላይ ተጣበቀችባትና፡፡ አገላብጣ ሳመቻት‹‹ሂሩትዬ አመሰግናለው….ጋንግሪን ሆኖ ሲበላኝ ከከረመ ጨለማ ጥርጣሬ ነው የገላገልሺኝ››
‹‹ችግር የለውም ..በቃ አሁን ልሂድ››
‹‹እንዴ የት ነው የምትሄጂው.?.የምትሄጂበት ላድርስሽ››
‹‹አይ የመጣሁበት ታክሲ እኮ እየጠበቀኝ ነው››መኪናውን በራፍ ከፍታ ወጣች….፡፡
‹‹ወይኔ በጌታ ቁርስ እንኳን አብረን ሳንበላ?››
‹‹አይ ቤት ሄጄ ልብስ ቀያይሬ ወደስራ መሄድ አለብኝ….ሌላ ጊዜ››
ሰሎሜ ከዚህ በላይ ልትጫናት አልፈለገችም‹‹በቃ ሰሞኑን ደውልልሽና እናወራለን አመሰግናለሁ፡››
ሄሩት ሄደችና ከኋላ ቆማ የነበረችው ታክሲ ውስጥ ገባች፡፡
///
የሰው ልጅ ለህይወት ሚያስፈልጉትን ነገሮች በራሱ ለማድረግ በተደጋጋሚ ልምምድ ይማራል…ለምሳሌ ምግብ እንዴት መመገብ እንዳለበት በወላጆቹ ሶስት አራት አመት እያጎረሱት ያለማመዱታል…ከዛ እንዴት ተጠቅልሎ እና ተዝቆ መብላት እንዳለበት መሞከርና ይጀምራል… ከዛ ይችላል…ግራ ቀኙን ለይቶ በትክክለኛው ጫማ ማድረግም እንደዛለው ሁለት ሶስት አመት ይወስድበታል….
የሰው ልጅ ምንም ሳይማር ቀጥታ ወደማድረግ እንዲሸጋገር የሚጠበቅበት ብቸኛው ለህይወት ወሳኝ የሆነው ነገር ወሲብ ነው፡፡ወሲብ ምን እንደሆነ…?እንዴት መነቃቃት..?እንዴትስ ማነቃቃት እንደሚቻል…?እንዴት መሳም እንዴት መዳበስ እንደሚገባው..?በየት በኩል እንዴት አድርጎ እንደሚያደርግ ማንም የሚያስተምረው የለም፡፡በትምህርት ቤት እንኳን ሚሰጡ ትምህርቶች ወሲብን እንደመራቢያ እና መባዣ መንገድ ብቻ በማየት እና እሱ ላይ ብቻ በማተኮር የሚሰጥ ነው፡፡ለመዋለድ ደግሞ ምንም አይነት የወሲብ ጥበብ አይጠይቅም.. ወጣ ገባ ብቻ በማድረግ ትንሽ ገባ ብሎ ዘር መድፋት ብቻ በቂ ነው፡፡ያ ግን የወሲብ አንዱ ግንጥል ጥቅም ነው፡፡ደግሞ ያ አይደለም የሚገርመው…ያለምንም ልምድ ባገኛቸው ቅንጭብጫቢ ሹክሹክታ መሰል መረጃዋች ብቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሲብ ሲፈፅም ‹‹አይ የመጀመሪያው ስለሆነ ነው ብሎ ለብቃቱ ይቅርታ የሚያደርግለት የለም…በተለይ ወንዱ የዚህ ጉዳይ ተጠቂ ነው፡፡ከመጀመሪያዋ ቅፅበት ጀምሮ ፍፅምነት ይጠበቅበታል ካልተሳካለት እንዲሸማቀቅ ይደረጋል፤ከዛ ህመሙ እየባሰበት ይሄዳል፡፡

👍52❤5👏3
እና እዛ ጋር የሚፈጠር ክፍተት ደግሞ ጠቅላላ የህይወት መስመርና ነው የሚያናጋው፡፡በተለይ በትዳር ውስጥ ጎጆውን አጽንተው ከሚያቆሙት ሶስት አራት ምሰሶዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ወሲብ ነው፡፡ታዲያ እዚህ ጉዳይ ላይ የሚኖር ግንዛቤንና ችሎታን ለማዳበርና ለማበልፀግ እንዴት በቅድመ ጋብቻ ጊዜ ቢያንስ መሰረታዊ ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት ሳይኖሩ..? አላስፈላጊ ስላልሆነ ነው…?የሀይማኖት ተቋማት የሚነሳ ተቃዎሞ ተፈርቶ ነው?ወይስ ሌሎች ምክንያቶች አሉ፡፡
ለምሳሌ ሙሽሮች ቀድመው በሰርጋቸው ላይ እንዴት አይነት ዳንስ እንደሚደንሱ…እንዴት ሻምፓኝ እንደሚጎነጩ ጊዜ ሰጥተው ይለማመዳሉ…ስለወሲብስ?
ሁለት ሰዓት ሆኗል፡፡ሰሎሜ ድብት ስላላት አልጋ ክፍሏ ገብታ ከብርድልብሱ ውስጥ ገባታ ጥቅልል በማለት እያሰበች ነው፡፡ይሄ የዘወትር የተለመደ ተግቧሯ ከሆነ ሰነባብቶል፡፡አላዛር እታች ሳሎን ሆኖ ቴሌቭዥን እያየ ነው፡፡እሷ ደግሞ በሀሳብ እየተንገላታች፡፡
ሰሎሜ ባሏን በሂሩት አማካይነት ከፈተነችው በኋላ ለበርካታ ወራት ለአላዛር ጥሩ ሚስት ለመሆን ከልቧ ስትጥር ነበር …በወጣ በገባ ቁጥር በነገርና በአሽምሩ ከመንቆር ይልቅ በለስላሳ ቃላቷ ታክመውና ..በውብ ፈገግታዋን ትመግበው ጀመር፡፡ከዛም አልፎ እንዴት አድርጋ የወሲብ ፍላጎቱን እንዲቀሰቀስ ልታግዘው እንደምትችል ማሰብና መጨነቅ ጀመረች፡፡
አልጋ ላይ በሚወጡበት ጊዜ እንደድሮ የሆነ ነገር እንዲያደርግ መገፋፋቱና ማሳቀቁን ቀንሳለት ግንኙነታቸው ሁሉ ማራኪ ሆኖ ነበር…ስድስት ወር ሳይሞላው ግን መልሶ ጥርጣሬዋ እያገረሸባት..እስከመቼ የሚለው ጥያቄ ያብሰከስካትና ያመነምናት ጀመር፡፡ያ ደግሞ መልሳ የሆነ ነገር እንዲፈጠር ለማድረግ ከኢንተርኔት ፈልጋ ባገኘችው መረጃ እንዲሁም ከየሰው እንደድንገት የሰማቻቸውን የወሲብ ፍላጎትን ያጎለብታሉ የተባሉትን ዘዴዎች ሁሉ ያለመታከት ተራ በተራ ትፈፅም ጀመረ..
ለምሳሌ አንድ ጊዜ የሆነ ድህረ ገጽ ስትጎረጉር. ስለሀባብ እና ወሲብ ግንኙነት አነበበች፡፡ፅሁፉ በአጭሩ ሲጠቀለል…‹‹ሀባብ በአሚኖ አሲድ የበለፀገ ስለሆነ ኩትሩሊን የተባለ ሆርሞን ያመነጫል።ይህ ሆርሞን የደም ቱቦዎች እንዲነቃቀቁ ያደርጋል።ያ ደግሞ በቂ ደም ወደ መራቢያ አካል እንዲፈስና ለወሲብ ዝግጅ እንዲሆን ያግዛል።ይህ ማለት በሌላ መልክ የቨያግራምን ተግባር ይተካል።››ይላል፡፡ከዛ ወዲያው ቦርሳዋን አንጠልጥላ ሀባብ ፍለጋ ነበር የሄደችው፡፡ከዛ አንድ ወር ያለማቆረጥ እስኪያንገሸግሸውና እንባው እስኪያቀር ድረስ ሀባብ እንዲጠቀም አደረገች…ውጤቱ ግን የእሱን ንጭንጭና ኩርፊያ ከማስተናገድ ውጭ በዜሮ የተባዛ ነበር፡፡
አንድ ጊዜ ደግሞ አንድ ቀበጥ ጓደኛዋ ‹‹ቸኮሌት እና ፍቅር የማይነጣጠሉ ናቸው ።ቸኮሌት መመገብ ሰውነታችን እስቴሮቶኒን ሆርሞን እንዲያመነጭ ያደርጋል… ይህ ሆርሞን ደግሞ ለሰውነታችን የደስታ ስሜትን ያጎናፅፋል፤ ሙድ ያስተካክላል፤እንደዛ ሲሆን ደግሞ የወሲብ ፍላጎት ይጨምራል።ስለዚህ ከወሲብ በፊት ቸኮሌት መጠቀም ይመከራል፡፡››ብላ ነገረቻት፡፡ከዛ ቤቱ ሁሉ በቸኮሌት አይነቶች ተሞላ….ወጤት ዜሮ ነበር፡፡ግን ደግሞ ካዛም በኋላ ተስፋ አልቆረጠችም፡፡
ቀጥሎ ያገኘችው መመሪያ‹‹በዚንክ የበለፀጉ ምግቦች መመገብ የቴስቴስትሮን ሆርሞን በብዛት እንዲመረት ፤የወሲብ ፍላጎት እንዲጨምር ፤ብዛት ያለው እስፐርም እንዲመረት እና እስፐርሙም በፍጥነት የመንቀሳቀስ አቅም እንዲኖረው ያግዛል። በዚንክ ከበለፀጉ ምግቦች ውስጥ ጥቂቶቹ የአሳማ ስጋ ፤ እርጎ ፤ ጥራጥሬዎች የመሳሰሉት ናቸው። ››የሚል ነበር…ለሁለት ወር በዚንክ የበለፀጉ የሚባሉ ምግቦችን እያሳደደች ትጠቀጥቅበት ጀመር….አሁንም ውጤቱ ዜሮ ሲሆን ተሰላቸች፡፡
በዚህ ሁሉ ልፋቷ ምንም አይነት የመሻሻል ፍንጭ አልሰጥሽ ሲላት ንዴቷ ጣሪያ ነካ፡፡ከዛ እሱን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሰበብ አስባብ እየፈለገች ትጨቀጭቀውና ቁምስቅሉን ታሳየው ጀመረች፡፡እንደዛም ሆኖ ግን ጥላው ለመሄድ ..ወይንም ልትፈታው አታስብም፡፡ሁል ጊዜ ነገሮች በጊዜ ሄደት ተስተካክለው በፍቅርና በሰላም ብዙ ልጆች ወልደውና የተሞላ ጠንካራ ቤተሰብ መስርተው የተመቻቸ ኑሮ እንኖራለን የሚል ተስፋ ነው ያላት፡፡እንጂማ ብትፈታው ግማሽ ንብረቱን ይዛ እንደምትወጣ ታውቃለች፡፡የእሱ ግማሽ ሀብት ማለት ደግሞ ከእሷ የእድሜ ልክ ህልሟም የራቀና የገዘፈ ነው፡፡ያንን ሀብት ለእሷ ለመስጠት ህግ እንኳን ባይፈርድላት እሱ እንዳማይከለክላት እርግጠኛ ነች፡፡ግን ያንን አይደለም የምትፈልገው፡፡
እሷ በሲንግል እናት ነው ያደገችው፡፡አባቷ ማን እንደሆነ አታውቅም…፡፡ሰሎሜ ግርማ ተብላ ስትጠራ የሰማ ሰው ሁሉ ግርማ አባቷ ይመስለዋል..እሷም ለረጂም ጊዜ እንደዛ ነበር የምታስበው፡፡በኋላ ግን ግርማ የእሷ ሳይሆን የእናቷ አባት እንደሆነ አና ለእሷ አባቷ ሳይሆን አያቷ እንደሆነ አወቀች፡፡እና የአባትነት ቦታው በአካል ብቻ ሳይሆን በስምም ሽንቅር እንዳለበት ተሰማት፡፡
‹‹እቴቴ…የአባቴ ስም ማን ነው?››
‹‹ግርማ ነዋ››
‹‹ግርማማ የአንቺ አባት ነው..እኔ የራሴን አባት ማለቴ የወለደኝን ነው የጠየቅኩሽ››
‹‹ምን ያደርግልሻል?››
‹‹እንዴ አባቴ አይደለ እንዴ…?አባት ምን ያደረርግልሻል ይባላል…?››
‹‹ለምን አይባልም..እንደእኔ አምጦ ወልዶሻል..?እንደእኔ አዝሎና አቅፎ ጡት እያጠባ አሳድጎሻል..?እንደእኔ ልብስ እየገዛ ትምህርት ቤት ልኮ አስተምሮሻል?››
‹‹አይ እንደዛ አላደረገም..ግን ደግሞ ምንም ባያደርግም አንዴ አባቴ ከሆነ አባቴ ነው…››
‹‹አላውቅም..ስሙ ማን አንደሆነ አላውቅም››
‹‹እንዴ የባልሽን ስም እንዴት አታውቂም?››
‹‹ባልሽ!! የምን ባል…?እኔና አባትሽ አልተጋባንም…ለትንሽ ጊዜ አብረን ነበርን.. ከዛ ጥሎኝ ሄደ….እና ስሙን እረስቼዋለሁ፡፡››
እንደዚህ እያለች ነበር ..ስለ አባቷ ምንም አይነት እውቀት እንዳይኖራት ምታደርገው፤እና አሁን አድጋ የራሷን ትዳር ይዛ እንኳን ስለአባቷ ምንም አታውቅም፤ቢያንስ ስሙን እንኳን አታውቅም፤አሁን አሁንማ በዚህ ጉዳይ ዘወትር ከእናቷ ጋር መጨቃጨቅ እየደበራት ስለመጣ ትተዋለች፡፡የተወችው ስለአባቷ ማንነት ለማወቅ ያላትን ጉጉትና ፍላጎት አይደለም…ስለአባቷ ለማወቅ እናቷን መጨቅጨቅ እንጂ….፡፡
እና እሷ የመሰረተችው ትዳር እሷ እንዳደገችበት ቤተሰብ ያልተሟላና ባለግማሽ ክንፍ አንዲሆን አትፈልግም….ለዛ ደግሞ እስከመጨረሻው አቅሟ እስከቻለበት ጠብታ ድረስ ትታገላለች፡፡

👍75❤10
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አላዛር እጅግ ሸበላ የሚባልና እና የበዛ ውበት አላቸው ተብለው ከሚመደቡ ወንዶች መካከል አንዱ ነው፡፡አብዛኛውን ጊዜ አይደለም ሴቶች ወንዶችም እይታ ውስጥ ለመግባት ለእሱ ዠቀላል ነው፡፡በዚህም የተነሳ የቅርቧም ሆኑ ድንገት ያገኘቻቸው ሰዎች በተለይ ሴቶች እሱን ባሏ ማድረግ በመቻሏ በአለም ላይ ካሉ እድለኛ ሴቶች መካከል አንዷ እንደሆነች በእርግጠኝነት ደጋግመው ይነግሯታል፡፡እሷም በልብ ቁስለትና በፊት ፈገግታ ጥርሷን ብልጭ አድርጋ ምንም አስተያየት ሳትሰጥ ታልፈቸዋለች፡፡
ማታ ከአራት ሰዓት ጀምሮ ነበር ከባለቤቷ ከአላዛር ጋር ደስ ሚል ሙድ ውስጥ የገቡት፡፡ነጭ ወይናቸውን እየተጎነጩ…ጎን ለጎን ተጣብቀዋል፡፡..ጥልቅ የስሜት ትስስር ያለው መላ ሴልን የሚያነቃቃ አይነት ማራኪ የፍቅር ፊልም አብረው ሲያዩ ነው ያመሹት፡፡ወደ መኝታ ቤታቸው ተከታትለው ሲገቡ ከምሽቱ ስድስት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ሰውነቷ ሁሉ ግሏል …አረ ከዛም አልፎ እየተቃጠለች ነው ማለት ይቻላል፡፡‹‹ዛሬ የተለየ ነገር እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ››ስትል በልቧ እያብሰለሰለች ነበር ቧሏን በፈገግታ ተከትላ ወደመኝታ ቤቷ የገባችው፡፡እንደዛ ተስፋ እንድታደርግ ያበረታታት ደግሞ ባለቤቷ ላይ ያየችው ከወትሮ የተለየ መነቃቃትና በፈገግታ የተሞላ አስተያየት ነው፡፡
አልጋ ላይ ቀድሞ ወጣና ብርድልብሱን ገልጦ ከውስጥ ገባ ፡፡ሙሉ ቢጃማውን እንደለበሰ ነበር፡፡እሷም ተቃራኒው አወላለቀችና በፓንት ብቻ ተከተለችውና ከውስጥ ገብታ ተለጠፈችበት፡፡ በጀርባው ነበር የተኛው፡፡ ደረቱን ተንተራሰችና እጆቾን ወደ ሆዱ ላከች፡፡ በስሱ ማሻሸት ጀመረች፡፡ያለምንም እንቅስቃሴ በፀጥታ ላይ ነው፡፡ቀስ አለችና እጆቾን ወደታች አንሸራታ የለሊት ሱሪውን ሰቅስቃ ገባችና ወደታች ወደብልቱ ወረደች…ቀስ እያለች ጨብጣ ማሻሸት ጀመረች፡፡ያው እንደተለመደው ብልቱ ልፍስፍስ እንዳለ ነበር፡፡‹‹እንዴት ነው ግን ይሄንን የመሰለ ዝግባ መሰይ ጠንበለል ሰው እንዲህ አይነት ለንቆሳና ልፍስፍስ ብልት ባለቤት የሆነው?››ሁል ጊዜ ስለእሱ ስታስብ የምትደነቅበት ነገር ነው፡፡ግን አንድ ቀን እንደምንም ጠንካራና የልብ አድርስ ይሆናል የሚል እምነት አላት ፡፡ለዛ ነው ሁል ጊዜ ዘዴዎቾን እየቀያየረች ከመሞከር የማትሰንፈው ..ቀጥላለች….ምንም የሚያበረታታ ነገር እያየች አልነበረም፡፡ይባስ ብሎ እጁን አንቀሳቀሰና የእሷን እጅ ይዞ ቀስ ብሎ በማስለቀቅ እጇን ወደቦታው መለሰ፡፡ከደረቱ ላይ ቀስ ብሎ አንሸራቶ ትራስ ላይ አስተኛትና ፊቱን አዙሮ እንደተለመደው ጀርባውን ሰጣትና ሽብልል ብሎ ተኛ፡፡በወቅቱ ውስጧ ኩምትርትር ብሎ ሲጨማደድ ይታወቃታል…ከውስጥ ከልቧ አካባቢ የሆነ ታፍኖ ሲብላላ የከረመ እሳት ጎመራ ፈንድቶ እቶን እሳት በመላ ሰውነቷ ሲተፋ እየታወቃት ነው፡፡ቃጠሎውን አልቻለችም ነበር፡፡ .ትግስቷ ተሞጠጠ፡፡ካለመቻሉ በላይ ለመቻል የሚያደርገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ይበልጥ አበሳጫት፡፡
ከአልጋዋ ላይ ተፈናጥራ ተነሳች፡፡እጅግ ከፍተኛ የሚባል ንዴት ላይ ነበረች፡፡ተስፈንጥራ ከአልጋዋ ወረደችና እርቃኗን ሆና ቁልቁል አዘቅቃ ታየው ጀመረ፡፡በእውነት ከሆነ ልታንቧርቅበት…ኮመዲኖው ላይ ያለውን የራስጌ መብራት አንስታ ግንባሩን ልትፈረክሰው….ወይንም በጥፍሮቾ ሁለት አይኖቹን ፈጥርቃ ልታፈርጥለት…ብዙ ብዙ ነገር ማድረግ ፈልጋ ነበረ፡፡ግን ሁሉም የስሜት ህዋሳቶቾ ሊታዘዙላት አልቻሉም፡፡አንደበቷ ተላቆ እንኳን የሆኑ ሁለት ሶስት ቃላትን ለማውጣት አልቻለችም፡፡
ባለቤቷ አልአዛር አልጋው ላይ እንደተዘረረ ወደላይ አንጋጦ እየተመለከታት ነበር፡፡አቅፎ ሊያባብላት፤ ስሞ ሊያረጋጋት ይፈልጋል፡፡ግን ደግሞ እንደዛ ማድረግ አይችልም፡፡አዎ ለዛ የሚሆን ወኔ የለውም፡፡ፊት ለፊት ካለ ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቢጃማውን አነሳችና አጠለቀች…ከኮመዲኖ ላይ ያለውን የመኪና ቁልፍ አነሳችና መኝታ ቤቱን ለቃ ወጣች፡፡ተከትሏት ተነስቶ ነበር፡፡ መኝታ ቤቱን ሳይለቅ ወደመስኮት አመራና አንገቱን አስግጎ እስከመጨረሻው ያያት ጀመር፡፡የውጩን በር በርግዳ ስትከፍት፤ወደመኪናው ገብታ ሞተሩን አስነስታ ጊቢውን ለቃ ስትወጣ ሁሉ በዝምታ እየተመለከታት ነበር፡፡
ሳሎሜ በውድቅት ለሊት መኪናዋን አስነስታ ቤቷን ለቃ ወጥታ ወደቄራ መስመር አምስት ኪሎ ሜትር በላይ ስለባሏ ክፉውንም ደጉንም እያሰላሰለ ከነዳች በኃላ ነው ሙሉ በሙሉ ወደቀልቧ መመለስ የቻለችው፡፡ምርር ያለ ንዴት ነበር የተናደደችው፡፡እርግጥ እንዲህ አይነት ንዴት መናደድ የጀመረችው ዛሬ አይደለም፡፤ባለፉት ሁለት አመታት አላዛርን አግብታ እቤቱ ከገባች ጀምሮ አብሯት ያለ ጨለማ ስሜት ነው፡፡የዛሬውን ልዩ የሚያደርገው ከቁጥጥር ውጭ መሆኑ ነው፡፡
‹‹አሁን ወዴት ልሂድ?››ብላ..አሰበችና ተበሳጨች፡፡ብስጭቷን እጥፍ የሚያደርግባት ደግሞ ይሄ ነው፡፡በባሎ ተበሳጭታ ከቤቷ ለቃ ብትወጣም የትም መሄድ አትችልም.፡፡እናቷ ጋር መሄድ አትችልም፡፡ጓደኞቾ ጋርም ፍፅም አይታሰብም….ምክንቱም በምን ተጣላችሁ ተብላ ብትጠየቅ ማስረዳት አትችልም፡፡እንዴት ብላ፡፡እንባዋ ይረግፍ ጀመር፡፡እያለቀሰች በመሆኗ ደስ አላት፡፡አዎ ሁሉ ጊዜ እንዲህ አይነት አስጠሊታ ስሜት ላይ ስትሆን በማልቀስ እና እንባዋን በማርገፍ ነው ቀዝቀዝ ማለት የምትችለው፡›ማልቀስ ባይኖር እንደውም በውስጥ ሀዘኗ ደርቃ የምትሰነጣጠቅና የምትበታተን ነው የሚመስላት፡፡
መኪናዋን አዙራ ወደቤቷ ለመመለስ ወሰነች…መሪዋን ስትጠመዘዝ እየተክለፈለፈ ከሚመጣ ሴኖትራክ ጋር ፊት ለፊት ተጋጠመች፡፡ በ5 ሜትር ርቀት ላይ መሆኗን አየች፤በደመነፍስ ቅፅበታዊ ውሳኔ ወሰነችና መኪናዋን ወደግራ ጠመዘዘች በዚህን ጊዜ ከመንገድ ተፈናጥራ ወጣችና ፊት ለፊቷ ካለ የብሎኬት አጥር ጋር ተላተመች፡፡አጥሩ ተፈረካክሶ ሲረግፋ ና ፍርስራሹ የመኪናዋን አካል ሲያለብስ በሰመመን ታያት፡፡ ለደቂቃዎች እራሷን እንደመሳት አድርጎት ነበር፡፡ነቅታ አይኗቾን ስትገልጥ ግን ከግራና ከቀኝ ሶስት ፖሊሶች መሳሪያ ደቅነውባት በተጠንቀቅ ቆመው ነበር፡፡መጀመሪያ ህልም ውስጥ ያለች መሰሏት ነበር፡፡በጥንቃቄ ከፍተው ጎትተው ሲያወጧት ነው…ሁሉ ነገር ተጫባጭ እውነት እንደሆነ የተረዳችው፡፡..ካልጠፋ የአዲስአበባ አጥር ለዛውም በውድቅት ለሊት የፖሊስ ጣቢያ አጥር ጥሳ መግባቷን ማመን አልቻለችም፡፡ድንዝዝ ነው ያላት፡፡ምን ማሰብ እንዳለባት እራሱ ግራ ተጋብታ ነበር…በመሳሪያ አጅበው ወስደው አንድ ክፍል በመክፈት ከሴት እስራኞች ጋር ቀላቀሏት፡፡
የተኙትን ሰባት የሚሆኑ እስረኞችን እንዳትቀሰቅስ እየተጠነቀቀች..አንድ ኮርነር ላይ ያለች ባዶ ባታ ሄደችና ኩርምት ብላ ቁጭ አለች፡፡በህይወቷ እንደዚህ አይነት ቦታ በስህተት እንኳን ተገኝታ አታውቅም፡፡ከአንድ ሰዓት በፊት ዘመናዊ ቤላ ቤቷ ውስጥ በሞቀ አልጋ ዋ ላይ የቀዘቀዘ ባሏን አካል አቅፋ ተኝታ ነበር ..አሁን ግን ወንጀል ሰርታ ከሌሎች ወንጀለኞች ጋር ታስራ መገኘቷ ፊልም እንጂ እውነተኛ ታሪክ እየመሰላት አይደለም፡፡የሰው ልጅ ህይወት እንዲህ ቅፅበታዊ በሆነ አጋጣም እንዳልሆነ ይሆናል የሚል ግምት ኖሯት አያውቅም ነበር፡፡
‹‹ሰሎሜ አብቅቶልሻል…››ስትል ለራሷ ተናገረች፡፡እንደዚህ ልትል የቻለችው የፖሊሶችን የእርስ በርስ ንግግር ስላዳመጠች ነው፡፡

👍65❤11
‹‹ከጀርባዋ አሸባሪዎች ይኖራሉ…እስረኛ ለማሳመለጥ የተደረገ ኦፕሬሽን ሳይሆን አይቀርም…አከሸፍንባቸው…››ምናምን ሲሉ ሰምታለች፡፡አይ እኔ ፈጽሞ አሸባሪ ሳልሆን በቧሎ ተበሳጭታ በውድቅት ለሊት ከቤት ኮብልላ የወጣች አንድ ሚስኪን ሚስት ነኝ ብትል ማንን ማሳመን ትችላለች?
‹‹ህይወት ግን ለምንድነው ሁሌ ሙሉ የማትሆነው?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡
የልጅነቷ ህይወቷ በጣም አስቀያሚና በድህነት የተከበበ ነበር፡፡አባቷን ጭርሱኑ አታውቀውም፡፡መልኩን አይደለም ስሙን እንኳን አታውቀውም፡፡ሙሉ በሙሉ ጀግና እናቷ ነች በብቸኝነት ያሳደገቻት፡፡ደግሞ የሚገርመው አሁን እዚህ እስር ቤት እንድትገባ ያደረጋት ባለቤቷም አላዛርም ከእሷ ጋር ተቀራራቢ በሆነ ህይወት ያደገ መሆኑ ነው፡፡ሁለቱም በአንድ ዘመን የተወለዱ አንድ ሰፍር ልጆች ነበሩ፡፡እና አሁን ሁለቱም የሚኖሩት ኑሮ ከበፊቱ ኑሮቸው አንጻር በምንም ሊነፃፀር የማይችል አይነት ነው፡፡፡ከ15 አመት በፊት እነሱን የሚያውቅ ሰው በምንም አይነት ሁኔታ ወደፊት እንደዚህ አይነት የተዳላደለ እና የተትረፈረፍ ኑሮ ይኖራሉ ብሎ ሊገምት አይችልም ነበር….እርግጥ ሀብቱ የአላዛር ነው፡፡እሷ የሀብቱ ተቋዳሽ የሆነችው እሱን በማግባቷ ብቻ ነው፡፡
እሱ ደግሞ ከአያቱ ያገኘውን ውርስ በአግባቡ ተጠቅሞ ማሳደግና ስለቻለ ነው፡፡ያንን ያደረገው ደግሞ ለእሷ ሲል ነው፡፡ለሰሎሜ የተሻለ ምቾት ያለው ኑሮ ሊያኖራት..እና እንደእቅዱ ተሳክቶለት በውርስ ያገኘውን ጥቂት ብር እንደመነሻ ተጠቅሞ በብዙ እጥፍ በማባዛት ሀብታም ሆነና ሰሎሜን አሳምኖ አገባት፡፡ይሄንን የተመለከተ የሁለቱም ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶች በጣቅላላ ደስተኛ ሆነው ነበር..የተሳካ ትዳር ፤ደስታ የሚዘንብበት ቤት እንደሚሆን የሁሉም ግምት ነበር፡፡ምክንያቱም ሁለቱም ጥንዶች ከህጻንነታቸው ጀምሮ የሚተዋወቁ… የሚዋደዱና የሚግባቡ ስለሆነ እናም በድህነት ያደጉ በመሆኑና አሁን ያገኙትን ሀብት በምስጋና ማጣጣም ይችላሉ የሚል ግምት በሁሉም ሰው ዘንድ ነበረ ...ግን ህይወት እንዳዛ አይደለችም፡፡ሁሌ ባልተጠበቀ መንገድ ሰውን ሰርፕራይዝ ማድረግ ተክናበታለች፡፡እናም ሰሎሜም ያ ነው የገጠማት፡፡የህይወት ሰርፕራይዝ!!፡፡
በጥቅጥቅ የክፍሉ ጨለማ ላይ አፍጥጣ ቀዝቃዛውን የብሎኬት ግድግዳ ደገፍ ብላ እዚህ ጣጣ ውስጥ የከተተትን የለሊቱን ታሪክ በምልሰት ማመንዠግ ጀመረች፡፡….በሀሳብ እንደባከነች እንቅልፍ በአይኗ ሳይዘር ሰማይና ምድር ተላቀቀ፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronosem

👍50❤7
🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_1
ዱብዕዳ
ከተኛሁ በኋላ የተደወለውን ስልክ ማንሳት ሞት መስሎ ተሰማኝ: ዓይኔን እንደጨፈንኩ መብራት ለማብራት ግድግዳውን ዳበስኩት፡፡ ነገር ግን ማብሪያና ማጥፊያውን ላገኘው አልቻልኩም፡፡ ልማድ ሆኖብኝ ዓይኔን አንድ ጊዜ ከከፈትኩ በኋላ እንደገና እንቅልፍ ስለማይወስደኝ ብዙ ጊዜ እንቅልፌን ካልጨረስኩ ስልክ የማናግረው ዓይኔን እንደጨፈንኩ ነው፡፡ ኮመዲኖ ላይ የነበረውን ባትሪ አብርቼ ማብሪያና ማጥፊያውን ለመፈለግ ስል ዓይኔን ስከፍት ግን ያልጠበኩት ነገር ገጠመኝ፡፡ ምንም የተኛሁ ሳይመስለኝ ነግቶ ቤቱ በብርሀን ተሞልቶ ነበር፡፡ ለካስ ማታ ራሴን እስክስት ጠጥቼ ስለነበር ጫማዬንና ልብሴን ሳላወልቅ ወደ ግርጌ ዞሬ በመተኛቴ ነበር ማብሪያና ማጥፊያውን ማግኘት የተሳነኝ:: ወደ ራስጌ ዞሬ ስልኩን ኮመዲኖው ላይ ብፈልግም ላገኘው አልቻልኩም:: ሁሌ አምሽቼ ከመጣሁና የእረፍት ቀኔ ከሆነ ስልኩ እንዳይረብሽኝ ሳሎን ውስጥ ማስቀመጤ የተለመደ ስለሆነ ማታም እዚያው ወስጄው ኖሯል :: አማራጭ አልነበረኝምና ስልኩን እንድታቀብለኝ "ዓለሚቱ" እያልኩ ተጣራሁ፣ ግን መልስ የለም:: ረስቼው ነው እንጂ ለካስ ዘመድ ጥየቃ ብላ ሄዳለች፡፡ ዘመድ ያላት ሠራተኛ መቅጠር ጣጣ ነው፡፡ "ሴቶች ዘመዱን የጨረሰ ባል ስጠኝ" እንደሚሉት እኔ ደግሞ ዘመዶቿን የጨረሰች ሰራተኛ ስጠኝ እንዳልል ፈራሁ፡፡ ነጠላ ጫማ ፍለጋ አጎነበስኩ፡፡ ከሁሉ በላይ ጫማ መፈለግን የመሰለ ቦርጭን እንደሚያስተጣጥፍ ሥራ እጅግ የሚያስጠላኝ ነገር የለም፡፡ ላገኘው ስላልቻልኩ በባዶ እግሬ ሮጥ ሮጥ እያልኩ እንደምንም ብዬ ስልኩን ለማንሳት ወደ ሳሎን ለመሄድ ስደናበር ተበታትኖ የነበረው ወንበር አደናቅፎ ሊጥለኝ ሲል የመኝታ ቤቱን በር ተደግፌ ቆምኩ፡፡ እንደምንም ሄጄ የስልኩን እጄታ ወደ ጆሮዬ አስጠጋሁና፤ "ሀሎ" አልኩ፡፡ ምንም ድምፅ አልነበረም፡፡ ስደነባበር ደቂቃዎች ፈጅቼ ኖሮ ደዋዩ ሰው ተስፋ ቆርጦ ስልኩን ዘግቶት ነበር፡፡ ሶፋው ላይ ቁጭ ብዬ እንደመሳቅ ቃጣኝ፡፡ መሳቅ የቃጣኝ በሌላ ነገር ሳይሆን "እንዲህ አርበትብቶና አደናብሮ ያውም ለሚዘጋ ስልክ ምን አስሮጠኝ?" የሚለውን ሳስብ ነበር፡፡ እርግጥ በጠዋት የተደወለና ከእንቅልፌ ቀስቅሶ ያስነሳኝ ስልክ ስለነበር ነገሮችን አሰባስቤ ለማስብ ፋታ ባለማግኘቴ፣ አሊያም ዓለሚቱ እደጅ በማደሯ "አንድ ነገር ሆና ይሆን ያለወትሮዋ ደጅ ያደረችው?'' እያልኩ ስጨነቅ
ስለነበር ይኸው ሳይሆን አይቀርም እንዲህ ያሯሯጠኝ፡፡ የራሴ ነገር እየገረመኝ ወደ አልጋዬ ለመሄድ ስነሳ ስልኩ ዳግም አቃጨለ፡፡ ስልኩን አነሳሁና፣ "ሀሎ" አልኩ፡፡ "አቶ አማረ?" አለ በስልክ የሚያናግረኝ ሰው፡፡ "አዎ ነኝ " አልኩ ተጣድፌ፡፡ "ከዚህ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤት ነው':: "ምነው በደህና?" "አይ በደህና ነው፡፡ወ/ሮ አልማዝ አስፋውን ያውቋታል?" ራሴ በአንዳች ነገር የተመታ ያህል አዞረኝና ሶፋው ላይ ተመልሼ ቁጭ አልኩ፡፡ አልማዝንና ፖሊስን ምን አገናኛቸው? አንድ ነገር እንደተፈጠረ ስለተስማኝ ተቻኩዬ እንደማውቃትና ምን እንደተፈጠረ እንዲነግረኝ ጠየቅሁ። እሱ ግን ለጥያቄዬ መልስ ሳይሰጠኝ "ለጥያቄ ስለምንፈልግዎ እባክዎን አዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤት ድረስ ቢመጡልን" አለኝ፡፡ "ምንድነው ችግሩ ለምን አትነግረኝም? " አልኩት፡፡ "ሲመጡ ይደርሳል'' ብሎ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ዘጋብኝ። መብረቅ እንደመታው ዛፍ እተቀመጥኩበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ ምን ተፈጥሮ ይሆን? በሕይወት ትኖር ይሆን ወይስ ሞታለች? ግን እኔ ለምን ተፈለግሁ? እንዴትስ እዚህ ልትመጣ ቻለች? ከሳኝ ይሆን? ሌላ ሌላም ጥያቄ ጭንቅላቴ ውስጥ መመላለስ ጀመረ። ሁሉንም ነገር ማውጣትና ማውረዱ ጥቅም ስለሌለው፣ የሆነው ነገር ሆኗልና ፈጥኜ መድረስ ስላለብኝ እየተንገዳገድኩ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ፡፡ ያጣሁትን ጫማ ለመፈለግ እጄን አልጋው ሥር ሰድጄ ስደባብሰ ሽታው መራኝና አፍንጫዬ ሥር አገኘሁት:: ልብሶቼን ለመልበስ ስፈላልግ ከራስጌዬ አጠገብ ኮሞዲኖው ላይ ከተቀመጠው ከአልማዝ ፎቶ ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ ዓይኖቿ አሁንም ቦግ እንዳሉ ናቸው፡፡ ዘወትር የማይጠፋው ፈገግታዋ አሁንም አለ፡፡ እዚህ ግዑዝ አካል ላይም "ለዘላለም" ተጣብቆ ይኖራል፡፡ አሁን የሌለውና የማይሰማው ነገር ያ አሳዛኝ ድምዕዋ ብቻ ነበር፡፡
"ለምን ፈገግ አለች?" አልኩ፣ ትኩር ብዬ ፎቶዋን እያየሁ:: አስተያየቷንም ሳየው መሰለኝ፡፡ "አይ አንተ ምስኪን፣ አሁንም አለህ?" እያለች የምታፌዝብኝ አይ አልማዝ! አሁንም አይበቃትም? ለምን ሁሌ በእኔ ላይ እየሳቀች ታፌዛለች? በመውደዴ እንደጅል ቆጥራ ለምንስ ትጫወትብኛለች? ምን ይታወቃል፤ የበፊቱ አልበቃ ብሏት አሁን ደግሞ እንደገና እኔኑ ጥፋተኛ አድርጋ አሳኝ ሊሆን ይችላል አልኩ፡፡ ግን ለምን? ከእኔ ከምስኪኑ ምን ለማግኘት? ይኸ ሊሆን የሚችል አይደለም ፡፡ አንድ ነገር ሆና መሆን አለበት እያልኩ ወደ ጭንቀት ባሕር ሰጠምኩ፡፡ ፎቶዋን ደግሜ አየሁት፡፡ አይ አልማዝ! ሁሌ መሳቅ፣ ሲደሰቱም መሳቅ፣ ሲያሞኙም መሳቅ፣ ያኔም እንዲህ ነበረች፡፡ ጥንትም ገና ሳያት ያቀረበኝ ይኸው ሳቋ ነበር፡፡ ትዝ ይለኛል፤ አለማያ ዩንቨርሲቲ እያለን እሷ ለምሳ የምትሰለፈው ከሀረሮች ጋር ነበር፡፡ ያኔ ሁሉም ተማሪ በተለይ በምሳ ሰዓት ድካምና ረሀቡ ፀንቶበት ቢያወራም በሹክሹክታ፣ ቢራመድም በቀስታ ነበር፡፡ የሀረር ልጆች ብቻ ሲከፋቸው አይታይም:: ሁሌ መሳቅ፣ ሁሌ መደሰት ነው፣ ጫት ብቻ አይጥፋ እንጂ! ጫት ተገዝቶ ከተቀመጠ ችኮላው ለሱ ነው፡፡ ሁሌ ቀደም ብለው ሰልፍ የሚይዙት እነሱ ናቸው፡፡ ሁሌ ከሰዓት በኋላ እነሱን ያየ ሰው ደስተኛ መሆናቸውን ያለጥርጥር መናገር ይችላል፡፡ ግን ምን ያደርጋል? ማታ ማታ ብቻ ከምርቃና በኋላ ድብርት ይይዛቸዋል፣ አንደበታቸውንም ይቆልፈዋል፡፡ በዚህ ሰዓት አላርፍ ብሎ ከእነሱ ጋር መቃለድ ወይም አፉን መክፈት የፈለገ ሰው ካለ የሚከተለው ሊሸከመው የማይችል ከእናት ጋር የተያያዘ ስድብ ነው:: መጀመሪያ አካባቢ በተለይ ከወደስሜን የመጣ ሰው እንዲህ ዓይነት ስድብ ሲሰደብ አንቄ ካልገደልኩ ይል ነበር። አንዴ ትዝ ይለኛል አንድ ጎንደሬ ተማሪ በዚህ ስድብ ተናዶ፣ “እኔው እራሴ እምዬን? እሱው ራሱ እንኳን ቢሆን ይሻል ነበር፣ እንዴት ያለ ነውር ነው እናንተ ሆዬ!" በማለት ካልገደልኩ ብሎ ግቢውን እንደበጠበጠ ትዝ ይለኛል፡፡ የአልሚና ጠባይ ግን እንደጫት ቃሚዎቹ ፀሐይ ስትወጣና ልትጠልቅ ስትል አብሮ ሲለዋወጥ አይታይም:: ሁሌ ከፊቷ ላይ ፈገግታ አይጠፋም፡፡ ከሷ ጋር በመልክ ቀለሟ ተቃራኒ ከሆነች የሴት ጓደኛዋ ጋር ማለቂያ የሌለው ወሬ እያወሩ መንከትከት የተለመደ ጠባያቸው ነው፡፡
አልሚና ቀላ ስትል ጓደኛዋ ግን ጠቆር ያለ ግን ውብ ቀለም ያለው ፊት አላት፡፡ የግቢው ሰው በዚሁ ማለቂያ በሌለው ወሬያቸው የተነሳ ቢቢሲ ይላቸዋል፡፡ እነርሱ ቤተመጻሐፍት ውስጥ ካሉ ጥናት የለም፡፡ ሲንሾካሾኩ ድምፃቸው አጠገባቸው የተቀመጠውን ሰው ሁሉ ይረብሻል፡፡ እኔ ግን በድምፃቸው ተረብሼ ካጠገባቸው አልጠፋም፡፡ ብዙውን ጊዜ የታፈነ ሳቃቸው ቀልቤን ስለሚስበው ምን እንደሚያወሩ ለማዳመጥ ጆሮዬን ሳሾል ጥናቴ መና ሆኖ ይቀራል፡፡ ብዙውን ጊዜ የትም ቦታ ቢሆን አልማዝና ኤልሳቤጥ ስለማይለያዩና አፍ ለአፍ ገጥመው እያወሩና እየተሳሳቁ ሲሄዱ ቀልብን ስለሚሰርቁ ግቢው ውስጥ እነሱን የማያውቅ ተማሪ አለ ማለት አያስደፍርም፡፡ አልፎ አልፎ የእርሻ ኢኮኖሚክስ ተማሪ የሆነው ተሾመ የሚባለው ልጅ አብሮ ከእነሱ ጋር

👍45❤11👎1
ከመታየቱ ውጪ ከሌላ ተማሪ ጋር ሲሄዱ ማየት የተለመደ አይደለም፡፡ ተሾመ የአዲስ አበባ ልጅ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ወይ ብቻውን አሊያም ከእነሱ ጋር ብቻ ነው የሚታየው፡፡ እንደሚመስለኝ ከኤልሳቤጥ ጋር ቀደም ብለው የሚተዋወቁና ከአንድ አካባቢ የመጡ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ተሾመ ሽቅርቅር ሲሆን ቀለል ያሉ ልብሶችን በተለይም ቲ-ሸርትና ጂንስ አዘውትሮ ይለብሳል፡፡ ፀጉሩ በአጭሩ እንደተከመከመ ፅድ ያማረ ጎፈሬ ሲሆን ከረዥም ቁመናውና ከሰልካካ አፍንጫው ጋር ተደምሮ ግቢው ውስጥ ካሉ ወንዶች ይልቅ እሱ በሁለንተናው ጎላ ብሎ ይታያል፡፡ ጓደኝነቱ ለሁለቱም ሲሆን ኤልሳቤጥ ከሌለች አብዛኛውን ጊዜ ከአልማዝ ጋር ስለሚታይና ከሁለቱም ጋር ሲሄድም ቢሆን እጁን ሁል ጊዜ አልማዝ ትከሻ ላይ ጣል ስለሚያደርግ አብዛኛው የግቢው ተማሪ "የአልማዝ የፍቅር ጓደኛ ነው" እያለ ያማዋል፡፡ እንዲህ ሆኖ ማየት ስለማልፈልግ ሳይሆን አይቀርም፤ ግቢው ውስጥ የእሱንና የእሷን ፍቅረኛነት የማይቀበል ሰው ቢኖር ምናልባት እኔ ብቻ ሳልሆን አልቀርም፡፡ ቤተመጻሕፍት _ ውስጥ ግን ብዙውን ጊዜ አብረው የሚታዩት አልማዝና ኤልሳቤጥ ብቻ ናቸው፡፡ ተሾመ አብዛኛውን ጊዜ ዶርም ውስጥ ስለሚያጠና ወደ ቤተመጻሕፍት የሚሄደው አልፎ አልፎ ነው፡፡ አልማዝና ኤልሳቤጥ ቤተመጻሕፍት ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ የሚቀመጡት እኔ ብዙውን ጊዜ ከምቀመጥበት መቀመጪያ ፊት ለፊት ነው፡፡ እኔ አዘውትሬ ቤተመጻሕፍት እየሄድኩ "የማጠናው" በእርግጥ ቦታው ለጥናት ከመኖሪያ ክፍላችን የተሻለ ቦታ ሆኖ ሳይሆን፣ አልሚናን አይቼ ለመመለስ ነበር፡፡ ሁል ጊዜ የምቀመጠው ከእርሷ ፊት ለፊት ሲሆን በየመሃሉ ጥናቴ እየተተወ መተያየት የተለመደ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ አቀርቅሬ የማጠና ልምሰል እንጂ ቀልቤም ሆነ ጆሮዬ ያለው እነሱ ሹክሹክታና ሳቅ ላይ ነበር፡፡ መቼም ሰው ትኩረት ከሰጠ የሚያፈቅረውን ሰው መለየት አይሳነውም ብዬ ስለማስብ፣ እኔ
እሷን እንደማፈቅራት ሁሉ እሷም ለእኔ ፍቅር አላት ብዬ በመገመቱ ሳልታክት ፊት ለፊቷ ተቀምጬ ዓይን ዓይኗን ማየት ተያይዤዋለሁ፡፡ እሷም ብትሆን እንደእኔ አታብዛው እንጂ አልፎ አልፎ ሰረት እያደረገች ማየታ አልቀረም፡፡ነገር ግን እኔ ከእዚያ አልፌ እሷን ለማናገር ወኒ ሳላገኝ፤ እነሆ ቀናት በወራት፤ ወራት ደ5ሞ በዓመት ተተኩ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ እንደለመድኩት እሷኑ ለማየት አንገቴን ቀና ሳደርግ አልሚና በፈገግታና በጥቅሻ ተቀበለችኝ፡፡ ጥቅሻው ለኔ ነው ብዬ ስላልገመትኩ ከበስተኋላዬ ሌላ ሰው ይኖራል ብዬ በማሰቤ ወደ ኋላ ዞሬ አየሁ፡፡ የነበረው ግን ግድግዳው ብቻ ነበር፡፡ ለካስ በመደንገጤ ጥግ መቀመጤን ጭምር ረስቼው ነበር፡፡ አስተያየቷ ትዝ ይለኛል፤ ፈገግ ብላ ቅዝዝ ባለ ዓይን የምትመለከተው እኔነ ነበር ፡፡ እፍረቴ ስለመጣ መልስ በመስጠት ፋንታ ቶሎ አንገቴን ሰብሬ የውሸት ጥናቴን ተያያዝኩት፡፡ ግን አላስችል ስላለኝ ትንሽ ቆየት ብዬ ቀና ስል አሁንም ዓይኗ እኔው ላይ እንደተተከለ ነበር፡፡ መልስ ስላልሰጠኋት ደንግጣ ነው መሰለኝ በፊቷ ላይ የሐፍረት ስሜት ይነበብ ነበር፡፡ እኔም ይህንኑ ለማሸነፍ የሞት ሞቴን ፈገግ አልኩ፡፡ የእኔና የአልማዝ የፍቅር ህይወት እዚሁ ላይ በፈገግታ ተጀመረ። ዛሬ የእኔ ፈገግታ በቦታው ባይኖርም ይኸው እሷ ግን አሁንም እንደሳቀች ነው፡፡ ፎቶዋን ወደ ግድግዳው አዙሬ ማታ ለብሼው ያደርኩትን የተጨማደደ ልብስ መቀየር ጀመርኩ፡፡ ከመቸኮሌ የተነሳ ሸሚዜን አዛንፌ፣ ጫማዬን አዟዙሬ እግሬን ለማስገባት ትግል ገጠምኩ፡፡ ጫማዬን እንደምንም ተጫምቼ፣ ልብሴን ለበስኩና ኮቴን ከመስቀያው ላይ አንስቼ እየተጣደፍኩ ወጣሁ፡፡ በሩን ሳልዘጋ ጉዞ ከጀመርኩ በኋላ ልዘጋው ተመለስኩ፡፡ ሠራተኛዬ ቤት ውስጥ እንደሌለች አሁንም ረስቼው ነበር፡፡ ከዚያም ታክሲ ተሳፍሬ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤት ከነፍኩ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ጽ/ቤት ወደ ጎጃም በር በሚያስኬደው መንገድ ከሰሜን ሆቴል ዝቅ ብሎ ይገኛል፡፡ የእኔ ሰፈር ደግሞ የድሮው ቃጫ ፋብሪካ አሁን አዲሱ ኮካኮላ የሚባለው አካባቢ ስለነበር እዚያ ለመድረስ ቢያንስ ከአንድ ሰዓት በላይ ይወስዳል፡፡ በዚሀ ላይ እንደኔ በጭንቀት ለሚጓዝ ሰው አንድ ሰዓት ራሱ እንደ አንድ ቀን ሊረዝምበት ይችላል፡፡ እንደዛሬው ሳይሆን ከልጅነቴ ጀምሮ አለማያ እስከገባሁበት ጊዜ ድረስ ይህንን መንገድ ቢያንስ በሳምንት አንዴ እጓዝበት ነበር፡፡ በተለይ ፊልም ማየት ስለምወድና ጃንሆይ ቢያንስ በሳምንት አንዴ ልዕልት ፀሐይ ሆስፒታል የተኙ ህመምተኞችን ለመጎብኘት ሲመጡ ብር ስለሚሰጡን ከሲኒማ ኢትዮጵያ፣ ከሲኒማ አድዋ፣ ከሲኒማ ኢምፓየር ወይም ከሀገርፍቅርና ከማዘጋጃ ቤት አንዱ ጋ ላልገባ
አልቀርም ነበር፡፡ ለዚህም ካልሄድኩ ማዘጋጃ ቤት ቤተመጻሕፍት ለጥናት ሳልሄድ አልቀርም፡፡ በተለይም አሁን የምሄድበትን ፖሊስ ጣቢያ ድሮ ቋንቋ እማርበት ከነበረው ከጣሊያን ካልቸራል ኢንስቲትዩት አጠገብ እና ደርግ የኢሕአፓና የሌሎች ፖለቲካ ድርጅት አባል የሆኑ የፖለቲካ እስረኞችን እያስቃየ የሚገድልበት ወንጀል ምርመራ እየተባለ የሚጠራው እስር ቤት አካባቢ ስለነበር በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ እንዲያውም ከጣሊያን ካልቸራል ኢንስቲትዩት ቋንቋ ተምረን ስንወጣ እዚያ ስንደርስ መንገድ ተሻግረን ነበር የምንሄደው፡፡ አንዳንዴ የደርግ መርማሪዎች የሚገርፉና የሚያሰቃዩት ሰው ሲያጡና ሲደብራቸው ከአላፊና አግዳሚ ሰው ውስጥ ኢሕአፓ ይመስላል የሚሉትን ያጎፈረ ወጣት ከመንገድ ላይ እየያዙ አስረው ስለሚያሰቃዩ ምንጊዜም በዚያ የምናልፈው በፍርሀት እየተርበደበድን ነበር፡፡ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ስደርስ ልቤ ምቱ ጨመረ። የምን ነገር ነው? የምን ጣጣ ነው? እንዴት ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ እንዲህ ሊሆን ይችላል? ገና መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ነበር፡፡ አሁን መርበትበቱ ምንም ዋጋ የለውምና እውነታውን ለማወቅ ወደ ፖሊስ ጽ/ቤቱ ጉዞ ቀጠልኩ፡፡ በር ላይ ለቆመው ዘብ ተጠርቼ እንደመጣሁ አስረድቼና ተፈትሼ ወደ ቀጠረኝ ሃምሳ አለቃ ቢሮ አመራሁ፡፡ ቢሮዋ ጠባብ ናት፡፡ እዚያቹ ውስጥ ሁለት ፖሊሶች ተቀምጠው ስለነበር የፈለገኝ ሃምሳ አለቃ የቱ እንደሆን ጠይቄ ወደ እሱ ተራመድኩ፡። ሃምሳ አለቃው አንድ ተላልጣ ልታልቅ የደረሰች ጠረጴዛ ላይ አጎንብሶ እየጻፈ ስለነበር አጠገቡ መቆሜን ቶሎ አላየም ነበር። ቀና ብሎ ሲያየኝ ደነገጥሁ፡፡ ጠቆር ያለ ነው፡፡ በፊቱ ላይ በአግባቡ የተቀነባበረ መልክ የለውም፡፡ እግዚአብሄር ካላጣው የውበት ጥበብ በእሱ ላይ አድልዎ ሳይፈፅም አልቀረም፡፡ ፀጉሩ አለ እንዲባል ያህል ብቻ አለፍ አለፍ ብሎ ጣል ጣል የተደረገ ሲሆን፣ ይህም በዛ ተብሎ መመለጥ ጀምሯል፡፡ ዓይኖቹ ከትንንሽነታቸው የተነሳ ትንሽ ጠባብ ጉድጎድ ውስጥ የወደቁ ትንንሽ ብዮች እንጂ ዓይን አይመስሉም፡፡

👍45❤3👎2
ከአፍንጫ እንኳን የተሰጠው ለመተንፈስ እንኳን የምትበቃ ያህል አልነበረም፡፡ አብዝቶ የሰጠው ነገር ቢኖር ጭንቅላት ብቻ ነበር፡፡ የጭንቅላቱ ትልቅነት ከዓይኑ፣ ከከንፈሩና ከአፍንጫው ጋር የሚመጣጠን አልነበረም፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ለማስፈራራት የተፈጠረ ነገር ነበር የሚመስለው፡፡ አጠገቡ ቆሜ እያየኝ እንዳላየኝ ለመምሰል ያቺኑ ፊቱን አጨማዶ ተመልሶ አጎንብሶ ሲጽፍ ጭንቅላቱ ቅቤ የተቀባ ማሰሮ እንጂ የሰው ጭንቅላት አይመስልም፡፡ ትንሸ ቆየት ብሎ ይቀመጡ እንኳን ሳይለኝ፣ “እኔጋ ነው ?'' ብሎ አፈጠጠብኝ::
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
ይቀጥላል...
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍34❤1
🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_2
"አዎ! በስልክ እዚህ እንድመጣ ቀጥረውኝ ነበር፡፡ አልማዝ አስፋውን በተመለከተ ተፈልጌ ነው" አልኩኝ። የረሳውን ነገር ያስታወሰ በሚመስል ሁኔታ፤ በፊት፤ "እ! አቶ አማረ አንተ ነህ ? ተቀመጥ" አለኝ፡፡ እኔ ግን ከመቀመጤ "ምነው ለምን ፈለጋችሁኝ? በደህና ነው? አልማዝ ደህና አይደለችም እንዴ?" በማለት አከታትዬ ጠየቅሁት፡፡ ሃምሳ አለቃው በተረጋጋ መንገድ! "ይቀመጡ አቶ አማረ፤ ስለአልማዝ ሁኔታማ ከእኛ በላይ እርስዎ የሚያውቁ መስሎኝ በማለት አንዴ አንተ አንዴ አንቱ እያለ ጥያቄ አቀረበልኝ፡ እንደተቀመጥኩ፤ “አቶ አማረ፣ ሃምሳ አለቃ አደፍርስ አባላለሁ፡፡ አሁን የፈለግንዎት አልማዝን በተመለከተ ከእርሶ የምንፈልገው መረጃ ስላለ ነው::" “አልገባኝም የምን መረጃ ነው ከእኔ የምትፈልገው?" "መጨረሻ ላይ ስለነበረው ሁኔታ ነዋ"፡፡ "አልገባኝም ሃምሳ አለቃ፤ ግልፅ ብታደርግልኝ'። "እንዴት አልገባዎትም? የሚያውቁትን ነገር እኮ ነው የጠየቅሁዎት ማለትም ስለአልማዝ የሚያውቁትን ነገር ሁሉ አንድባንድ፣ በዝርዝርና በግልጽ እንዲነግሩን እንፈልጋለን፡፡ ይኸውም የት እንደተዋወቃችሁ፣ ግንኙነታችሁ ምን ዓይነት እንደነበርና በኋላም እንዴት እንደተለያያችሁ እያለ ያልጠበቅሁትን ጥያቄ ይጠይቀኝ ጀመር፡፡ እኔም መልስ በመስጠት ፋንታ አልማዝ የት እንዳለችና ምን አዲስ ነገር እንደተፈጠረ መጀመሪያ እንዲነግረኝ ወተወትኩት፡፡ ነገር ግን ይህንን የሚነግረኝ የሚጠይቀኝን ጥያቄ ሁሉ ከመለስኩ በኋላ መሆኑን ነገረኝ፡፡ አማራጭ አልነበረኝምና መልስ ለመስጠት ዓመታት ያስቆጠሩ ትዝታዎቼን ማሰባሰብ ጀመርኩ፡፡ ቤተመጻሕፍት ውስጥ የነበረውን የመጀመሪያ ትውውቃችንን ቆጠብ ባለ ሁኔታ ነገሬው መልስ እንዲሰጠኝ ብጠብቅም፣ ከእኔ ገና በጣም ብዙ መስማት የሚፈልግ መሆኑን ዳግመኛ ስለነገረኝ ሌላ አማራጭ አልነበረኝምና ትረካዬን ልቀጥል ስል፤
“አንድ ነገር ግልጽ ላድርግልዎት ታሪኩ መቀነጫጨብና የምንፈልገውን ቁምነገር የሚያሳጣን መሆን ስለሌለበት፤ ይህ አያስፈልግም ከምልዎት ውጪ ሁሉንም ይግለጹልን፡፡" አለኝ በአጽንኦት፤ "አዎ! ቤተመጻሕፍት ውስጥ በፈገግታ የተጀመረው ትውውቃችን በደጅም ቀጠለ፡፡ ቤተመጻሕፍት እንደተዘጋ እነሱ ፊት ለፊት እኔ ከኋላ ተከታትለን ወጣን፡፡ ተማሪው ሁሉ ወደ ማደሪያው አምርቶ ስለነበር የቀረነው እኛ ብቻ ነበርን፡፡ ከቤተመጻሕፍት ፊት ለፊት በአጫጭሩ ተከምከመው በግራና ቀኝ በተተከሉ ዕዶች የተከበበችውን "ላቭ ስትሪት" ወይም "የፍቅር ጎዳና" ተብላ የምትጠራውን ጠባብ መንገድ ለሁለት ዘግተው እየተሳሳቁ በዝግታ ይሄዱ ስለነበር ከኋላቸው ስደርስ ዝግ ለማለት ተገደድሁ፡፡ ለማለፍ ይቅርታ መጠየቅና መንገድ ማስከፈት ስለነበረብኝ እየፈራሁ በጥግ በኩል "ይቅርታ" ብዬ ለማለፍ ስሞክር ይብስ ተብሎ እሱም ተዘጋብኝ:: በሌላው ዳርቻ ለማለፍ ስሞክርም ለካስ ሆን ብለው የሚያደርጉት ድርጊት ኖሮ ያችንም መልሰው ዘጓት፡፡ ግር ብሎኝ ቆም እንደማለት ስል" "የት ለመሄድ ነው ችኮላው? ለጥናት ከሆነ ያጠናኸው ይበቃሃል። ጥናት ሲበዛ ጥሩ አይደለም፣ ያሳብዳል ይባላል፡፡ ስለዚህ አንዳንዴ እረፍትም ጠቃሚ መሆኑን አትዘንጋ" አለችኝ የኔ መካሪ፡፡ የምመልሰው ጠፍቶኝ ፈዝዤ ቆምኩ፡፡ ሁል ጊዜ እንዴት እንደማናግራት ሳወጣና ሳወርድ እውላለሁ፡፡አንዳንዴም በሕልሜ አገኛትና ከማውራት አልፌ አቅፌ ስስማት ይታየኛል፡፡ ግን አንድም ቀን ደፍሬ በውኔ አንዲት ቃል ትንፍሽ ብዬ አላውቅም፡፡ ከየት የመጣ ትንፍሽ ማለት! ቀና ብዬ እንኳን የማያት ብዙ ርቃ ከሄደች በኋላ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ "ዛሬስ የመጣው ይመጣል እንጂ ሳላናግራትማ አልመጣም" ብዬ ቆርጬ እወጣና በምታልፍበት መንገድ ላይ ስጠብቃት እውልና አጠገቤ ስትደርስ፣ "ኤጭ! ከጓደኞችዋ ጋር ነች፣ ያ ሴታ ሴት ተሾመ አጠገቧ አለ፣ ወይም ወደ ሆነ ቦታ ለመሄድ ስለቸኮለች አሁን ቀልቧን ሰብስባ አታናግረኝም™ እያልኩ ሰበብ ፈጥሬ እመለሳለሁ:: አንዳንዴ ደግሞ ብቻዋን ከወጣች እንደነገሩ ከተል እልና ባጋጣሚ ዞር ካለች አቅጣጫዬን ለውጬ እሄዳለሁ፡፡ ዛሬ ግን እሷው ቀድማ ስታናግረኝና መንገዱ ወለል ብሎ ሲከፈትልኝ የምናገረውና የማደርገው ጠፍቶኝ ፈዝዤ መቆሜ ምን ይባላል? አሁን ወደድኩም ጠላሁም ልወጣው ከማልችለው እውነታ ጋር ተፋጥጫለሁና መልስ መስጠት ስለነበረብኝ፣ "እ... እ.... አልቸኮልኩም " ብዬ በነበርኩበት ፈዝዤ ቆሜ ቀረሁ።
መፍራቴን እንዳወቁና እንዳዩ በሳቅ መንከትከት ጀመሩ፡፡ ሳቃቸውን ስሰማማ መላ ሰውነቱን ድንጋጤ ወረረው ::ይባስ ብሎም ጉልበቴ መብረክረክ፣ ላቤም በፊቴ ላይ ችፍፍ ማለት ጀመረ፡፡ አይገርምም! ላብ በጭለማ ያውም በብርድ ወቅት፡፡ እፍረቴን ለማስወገድ በሚመስል መልኩ እጇን ዘርግታ፣ "እንተዋወቅ፤ አልማዝ እባላለሁ፣ እሷ ደግሞ ኤልሳቤጥ ትባላለች" አለችኝ፡፡ አልማዝ ስልክክ ያለች ቆንጆ ነች ማለት ባይቻልም የደስ ደስ ያላትና ያያት ሁሉ የሚወዳት፣ ፊቷ የሚማርክ የቀይ ዳማ ነች፡፡ ኤልሳቤጥ ጠቆር ስለምትል የእሷን ቅላት ታጎላዋለች እንጂ ቀይ የምትባል አልነበረችም:: ከሁለመናዋ እኔን የሚስቡኝ ግን ጎላ ጎላ ያሉት ዓይኖችዋ እና ከፍልቅልቅ ሳቅዋ ጀርባ የተደበቁት ሳቅ አድማቂዎቹ ነጭ ሰልፈኛ የሚመስሉት ጥርሶቿ እንዲሁም ውብና ተመጥኖ የተሰራው ከንፈሯ ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ ቀጠንና ረዘም ያለች ሆና ከወደ ዳሌዋ ሰፋ ያለች ናት፡፡ አልማዝ ምንም እንኳን ለውበትዋ ብዙም የማትጨነቅ፤ መኳኳልና መሽቀርቀር የማታበዛ ብትሆንም፣ እንደነገሩ እንኳን ለባብሳ ስትወጣ መላ ሰውነቷ ውበትን ይላበሳል፡፡ እኔ በተለይ እሁድ እሁድ ልብስ ለማጠብ እንደነገሩ ሆና ስትወጣ ማለትም ለአለባበስዋም ሆነ ለመልኳ ብዙም ሳትጨነቅ ሳያት በጣም ታምረኛለች፡፡ ፀጉርዋ ዞማ ሆኖ ጀርባዋ ላይ አይተኛ እንጂ ሉጫ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሌላው እኔን የሳበኝ የድምፅዋ ቃና ነው፡፡ ቤተመጻሕፍት ውስጥ ስትንሾካሾክም ሆነ መንገድ ላይ ስታወራ ስሰማት የሙዚቃ ቃና ያለው ድምፅዋንና አወራሯን ተከትለው ወደ ላይና ወደ ታች የሚንከባለሉት ዓይኖችዋ ማንንም የማማለል ችሎታ አላቸው፡፡ ምንም እንኳን ባጠቃላይ ከግቢው ተወዳጅ ሴቶች ውስጥ ብቸኛዋ ባትሆንም ከዋናዎቹ ቆንጆዎች ጎራ የምትመደብ ነበረች፡፡ለእኔ ግን ከሁሉም በላይ የቆንጆ ቆንጆ ነበረች::" ሃምሳ አለቃው ለዛ ቢስ ፈገግታውን እያሳየኝ፤ "የሚገርም ነው! ለምን ሰዓሊ ወይም ደራሲ አልሆንክም? በጣም ጥሩ ገለፃ ነው፡፡ እስኪ አሁን ደግሞ እንዴት እንደተዋወቃችሁ በዝርዝር ንገረን" አለኝ በትዕዛዛዊ ስሜት፡፡ አነጋገሩ የለበጣ ቢመስልም አማራጭ አልነበረኝምና ትረካውን ቀጠልኩ፡፡ "እዚያ የፍቅር ጎዳና ላይ ቆሜ ፈራ ተባ እያልኩ ስሜን ተናገርኩ፡፡ ጊዜው ቢርቅም ትክክለኛ ስሜን የተናገርኩ ይመስለኛል፡፡ ድንጋጤውም ቀስ በቀስ እየለቀቀኝ በመሄዱ በእነሱ ጨዋታ አምጪነት የቆጥ የባጡን መቀባጠር ጀመርን፡፡ እኔም ብዙም ቁም ነገር ያለው ጨዋታ ባላመጣም የተቻለኝን ያህል አወጋሁ፡፡ በመጨረሻም ወደ ፊት አብረን ለማጥናት ተነጋግረን ተለያየን፡፡

👍37❤5
ለመጀመሪያ ጊዜ ላናግራት በመቻሌና ህልሜ እውን በመሆኑ ዝጅግ ተደሰትኩ። ወደ መኖሪያ ክፍሌ ስሄድም የምራመድ ሳይሆን የምንሳፈፍ ነበር የመሰለኝ። ክፍሌ እንደገባሁም እየሙህኩ አልጋው ላይ ዘልዬ ወደቅሁ። ጓደኞቼ ደብተራቸውን ይዘው እያጠኑ ስለነበር ሁሉም ደንግጠው ምን እንደሆንኩ ይጠይቁኝ ጀመር:: አሁንም ሰው መረበሼ እንኳን ሳይታወቀኝ፣ “አናገርኳት! ተዋወቅን!" እያልኩ መጮህ ጀመርኩ። ጓደኞቼ ድንጋጤው ለቀቃቸውና በሳቅ ተንከተከቱ:: ማንን እንዳናገርኩ ግን መጠየቅ አላስፈለጋቸውም:: ሁሌ ፉከራዬ “ዛሬስ አናግሬያት ካልመጣሁ ወንድ አይደለሁም!" የሚል ስለነበር ማንን አናገርክ ለሚለው ላይጨነቁ፤ “እንዴት አናገርካት? ምን አለችህ?'' እያሉ ሁሉም ይጠይቁኝ ጀመር፡፡ እኔም አንበሳ እንደመጣ አዳኝ ገድሎ ወዲህና ወዲያ እየተንጎራደድኩ፣ ሳልጠይቅ መጠየቄን እያጎላሁ ትረካዬን ተያያዝኩት፡፡ መቼም በዚያች ጊዜ አለመኖራቸው እንጂ በዚያች ጨለማና ብርድ እንዴት በፊቴ ላይ ላብ ችፍፍ እንዳለ ቢያዩ ኖሮ ምን ይውጠኝ ነበር? ይሁን እንጂ የዘወትር ፉከራዬ በመጨረሻ በመሳካቱ ያልተደሰተ አልነበረም፡፡ ሲያጠና ሰው እንዳይረብሽው የአልጋውን ዙሪያ በነጠላ ጋርዶ የሚያጠናው አስጨናቂ እንኳን ሳይቀር የፉከራዬ በመጨረሻ እውን መሆን አስደንቆት ነጠላውን ከፈት አድርጎ፤ “ከዚያስ፣ ከዚያስ" እያለ በመጠየቁ ጓደኞቼ በሙሉ ከእኔ በላይ ይጨነቁ እንደነበር ገባኝ::" ሃምሳ አለቃው በትረካዬን መሀል ገብቶ፤ "ጥሩ አሟሟቂ ጓደኞች ነበሩህ ማለት ነው! እሺ በል መጨረሻችሁን በደንብ አሰማኝ" ብሎ በረጅሙ የፌዝ ሳቅ ሳቀብኝ፡፡ ምን እንደነካኝ ባላውቅም ተርክ ተርክ፤ ቀጥል ቀጥል የሚል ስሜት ስለተሳማኝ ካቆረጥኩበት በመቀጠል፤ “የመኖሪያ ክፍላችን ጠበብ ያለች ብትሆንም በተደራረበ አልጋ ላይ እየተኛን ለስድስት እንኖርባታለን:: ከእኔ በላይ ተሰማ፣ ከፊት ለፊቴ እታች ካለው አልጋ ላይ ሁሌ ጋቢውን ጋርዶ የሚያጠናው አስጨናቂ፣ ከሱ በላይ ስለሞን ይተኛሉ:: ሁለተኛዋ የማጥኛ ክፍላችን ውስጥ አፈወርቅ የተባለ የሲዳሞ ልጅ እና ወንድይፍራው በተደራራቢ አልጋ ላይ ይተኛሉ፡፡ አብዛኞቻችን የአዲስ አበባ ልጆች ስንሆን ከሌላ አካባቢ የመጡት ደግሞ ከሲዳሞ አፈወርቅ፣ ከጎጃም አስጨናቂ ብቻ ናቸው:: ወደ ዩንቨርስቲ
የመጣነው በአንድ አውቶቡስ ስለነበርና ስለተግባባንም የአካባቢያቸውን ልጆች ትተው ከእኛ ጋር አንድ የመኖሪያ ክፍል ውስጥ ገብተዋል። አፈወርቅ ከሁሉም በላይ ለእኔ የተለየ ፍቅር ነበረው፡፡ ቀደም ሲል መናገሬን እየረሳሁት የምደጋግማቸውን ታሪኮችን ሳወራ ምንጊዜም ሳይስለች እያዳመጠ ሁሌም ይስቃል:: እኔም ብሆን በሴት ፊት ወኔ ባይኖረኝም ወንድ ብቻ በተሰበሰበበት ቦታ ከሆነ ጥሩ ተጫዋች ስለሆንኩ የሚያስቅ ነገር አላጣም:: ለእኔ ካለው ፍቅር የተነሳ ገንዘብም ካገኘ ለእኔ ሲጋራ ለመግዛት አይሰስትም፡፡ በሌላ በኩል ተሰማ ራሱን የሚጠብቅ፣ መዘነጥና መተረብ የሚያዘወትር ነበር:: እኔ አንዳንዴ እየረሳሁ የነገርኳቸውን ታሪክ ደጋግሜ ከተናገርኩ የሰማበትን ድግግሞሽ ሳይረሳ "ሁለተኛ" ፣ "ሶስተኛ" እያለ ሲቆጥር ስሰማ ስለሚያሳፍረኝ ሁሌ እናደድበታለሁ፡፡ ይሁን እንጂ እሱም እንደ አፈወርቅ ለእኔ የተለየ ፍቅር አለው:: ሆኖም ያስቀመጠው ዕቃ ያለ እሱ ፈቃድ ከቦታው ከተነሳ ከእኔም ሆነ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ይጣላል። በዚህ የተነሳ “ሚ/ር ጥንቃቄ' እያልን እንጠራዋለን፡፡ እኔ ከሁሉም በላይ መጫወትና ማብሸቅ የምወደው ሰለሞንን ነበር:: የቤቱ ሰው ሁሉ የሚዝናናው በእኔና በእሱ ብሽሽቅ ነው፡፡ ታዲያ እሱም ቢሆን ለጊዜው ብቻ ይበሽቅ ይሆናል እንጂ በነጋታው ግን የተናገርኩትን ነገር እራሱ እያነሳ ይስቃል እንጂ አይቀየምም፡፡ እኔም ብሆን ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የማካፍለው ሚስጥር ካለኝ የማወራው ለእሱ ነው:: የልብ ጓደኛዬ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለትምህርት በጣም የሚጨነቅ ቢሆንም የጥናት ፕሮግራም ግን አልነበረውም፡፡ አንዳንዴ ሌሊቱን በሙሉ ሲያጠና ያድርና በነጋታው ቀኑን በሙሉ በየዶርሙ ስለሚዞር፤ አንዱ ላጥናበት እያለ ሲያባርረው ሌላው ጋ እየሄደ ሲያወራ ይውላል:: አንዳንዴ ልተኛ ብሎ ጋደም ይልና፤ ተመልሶ እኛ እያጠናን መሆኑን ሲያይ ደንግጦ ተነስቶ ማጥናት ይጀምራል:: ታዲያ አንዴ ትዝ ይለኛል፣ ከምሽቱ 3፡30 አካባቢ ልተኛ አለና 4፡00 ላይ እንድቀሰቅሰው _ ነግሮኝ ጋደም አለ፡፡ እኔም እንዳይተኛ የተለያዩ ነገሮችን እያነሳሁና እየተበሻሸቅን እያለ አራት ሰዓት ስለሆነ ከአልጋዬ ላይ ወርጄ ወደ እሱ በመሄድ መቀስቀስ በሚመስል መልኩ እየነቀነኩት፤ “ሰለሞን፡ ሰለሞን ተነስ አራት ሰዓት ሆኗል" እያልኩ ቀሰቅሰቅው፤ ምን ሊለኝ ነው ብሎ አይኑን አፍጥጦ እየጠበቀኝ ነበርና በመገረም መልክ ሰዓቱን ተመልክቶ፤ “ከይሲ! የጥናት ሰዓቴን ያቃጠልከው ሳያንስ ዓይኔ እያየ ትቀሰቅሰኛለህ" ብሎ ሊመታኝ ዘሎ የወረደው ትዝ ይለኛል::
ወንድይፍራው ለትምህርት ብዙም የማይጨነቅ ሆኖ ሳለ በጥናት እኛን ብቻ ሳይሆን የእርሻ ምህንድስና ተማሪዎች በሙሉ ያቃተንን የሂሳብ፣ የፊዚክስና ሌሎች ሂሳብ ነክ የሆኑ ትምህርቶችን የሚያስጠና ጎበዝ ተማሪ ነው፡፡ ብዙ ሰው የሚያውቀው በትምህርት ጉብዝናውንና በዝምተኛነቱ ቢሆንም በመኖሪያ ክፍል ውስጥ ግን ቀስ እያለ ተንኮል አዘል ቀልዶችን በመጣልና በማብሸቅ የሚታወቅ ነበር። በተለይ እኔና ሰለሞን ስንበሻሸቅ መስማትና መሳቅ ስለሚወድ በተቻለ መጠን ነገር እየለኮስ ያጣላናል፡፡ በዚህ ጠባዩ የተነሳ "ልዝቡ ሰይጣን" እንለው ነበር፡፡ ከመካከላችንም ብዙ ጊዜ ገንዘብ የሚላክለት እሱ ስለነበር ከደግነቱ የተነሳ እንደፈለግን ገንዘብ ከኪሱ ብንወስድም ቅር አይለውም ነበር።ከሁላችን የተለየ ጠባይ ያለውና ለማንኛችንም ጨዋታ ብዙም ደንታ የሌለው አስጨናቂ ነው:: እሱ በጥናት ጉዳይ ቀልድ አያውቅም :: ቀኑን በሙሉ ሲያጠና ቢውል ደስታው ነው፡፡ በጥናት መሀል ለማረፍ በማለት መጫወት ከጀመርንም፤ “እረ እናንተ ሰዎች አትረብሹኝ ላጥናበት፡፡ ጥናት ጨርሳችሁ ከሆነ ለምን ወደ ክበብ ሄዳችሁ አትጫወቱም?" እያለ ይነጫነጫል:: በዚህ ላይ ምንጊዜም የማልረሳት አንድ የብረት ሳጥን ነበረችው፡፡ ብዙውን ጊዜ ከሳጥኑ ውስጥ የሚፈልገው ነገር ካለ ሳጥኑን ከአልጋ ሥር ስቦ ሲያወጣ ጩኸቱ ሁላችንንም ከየእንቅልፋችን ይቀሰቅስናል፡፡ ታዲያ ዛሬ በዚህ ድርጊቱ ብንጣላውም ነገ ተመልሶ ማድረጉ ግን አይቀርም፡፡ ሆን ብሎ እኛን ለመቀስቀስ ወይም ለማናደድ የሚያደርገው ነገር ሳይሆን በዝንጋታ የሚያደርገው ስለነበር እሱን ከማኩረፍ ይልቅ፤ "ባቡሩ ባልሆነ ሰዓት መጥቶ ቀሰቀሰኝ፣ ወይም እንዴት ነው ዛሬስ ባቡሩ በዚህ አላለፈም?' እያልን በረባሹ የብረት ሳጥን ድምዕ እንቀልዳለን፡፡ ታዲያ ዛሬ እንዲህ ጓጉቶ ምን እንደተፈጠረ ሲጠይቀኝ መገንዘብ የቻልኩት የማይሰማ መስሎ ሲያዳምጥ እንደነበርና እሱም እንደ ሌሎቹ የእኔን መጨረሻ ለማወቅ መጓጓቱን ነው፡፡ ሃምሳ አለቃው መስማት የሚፈልገውን ታሪክ ትቼ ወደ ሌላ ጉዳይ በመግባት ስቀባጥርና ማእበል እንደሚያንገላታው መርከብ ከወዲያና ወዲህ ስወዛወዝ በማየቱ ሣይናደድ አልቀረም፡፡ በመሆኑም በንግግሬ መሀል ጣልቃ ገብቶ አቋረጠኝና ጥያቄና ቁጣ በተቀላቀለበት ሁኔታ፤ "አቶ አማረ እኔ የጠየቅሁህ ስለአልማዝ እንጂ ስለ ጓደኞችህ አይደለም:: ይልቅ የማይሆን ወሬ እያወራህ ውድ ጊዜዬን ከምታባክንብኝ ከአልማዝ ጋር ስለነበራችሁ ጓደኝነት እና ስለተፈጠረው ሁኔታ ብትነግረኝ ጥሩ ነው፡፡ ማለቴ ከአልማዝ ጋር በጓደኝነታችሁ ቀጠላችሁበት? ጓደኝነታችሁስ እስከ ምን

👍34❤3👏1
ድረስ ነበር? ለመጨረሻ ግዜ አልማዝን ያየሃት
መቼ ነው? በማለት ኮስተር ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እኔም ንዴት በተቀላቀለው ሁኔታ "ሃምሳ አለቃ አደፍርስ፣ እኔም ብሆን እዚህ የመጣሁት የእኔንና የአልማዝን የሕይወት ታሪክ በማውራት ውድ ጊዜዬን ለማቃጠል ሳይሆን አልማዝ ምን እንደሆነች ወይም ምን እንዳጋጠማት ለማወቅ ነው፡፡ በሕይወት አለች ወይስ ሞታለች? ይልቅ ስለሱ ብትነግረኝ ይሻላል" አልኩት:: ፊቱን ቅጭም አድርጎ በአግራሞት እየተመለከተኝ "አቶ አማረ፣ እርስዎ የመጡት ስለአልማዝ ለማወቅ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ነው እንበል፡፡ ነገር ግን ወደ እዚህ የመጡት እርስዎ ራስዎ ፈልገውና ጠይቀው ሳይሆን እኛ ጠርተንዎት ነው፡፡ እኛ ወደ እርስዎ ፍላጎትና ጥያቄ ከመግባታችን በፊት ከእርስዎ ማግኘት የምንፈልጋቸው ብዙ ጠቃሚ መረጃዎች ስላሉ የእርስዎን ጥያቄ አዘግይተው እኛ ለምንጠይቃቸው ጥያቄዎች ብቻ መልስ በመስጠት ቢተባበሩን መልካም ነው" አለኝ፡፡ ለየትኛው ጥያቄ መልስ እንደምሰጠው ግራ ገባኝ፡፡ የጠየቀኝ ጥያቄ እንዲህ በትንሽ ሰዓት ውስጥ የሚመለስ አይደለም፡፡ ይህ ታሪክ ከዓመታት በፊት ምንም ሳያምርበት የተጠናቀቀ ማሰሪያ የሌለው ታሪክ ነው፡፡ ይህ ታሪክ የእኔና የአልማዝ የሕይወት ታሪክ ነው፡፡ የሕይወት ታሪክ ደግሞ ከመወለድ ይጀምርና በሞት ይጠናቀቃል፣ ለታደለው፡፡ የእኔ ቢጤው ግን እንደዚህ ሳያምርበት ባጭሩ ይቀጫል፡፡ የፈለገው ጉዳይ አቅጣጫ የያዘለት የመስለው ሃምሳ አለቃ ያንን የቁጣ መፍለቂያ የመስለ ፊቱን በግድ በተገኘ ፈገግታ ፈታ አደረገው፡፡ ትኩረት ሰጥቶ መስማት የሚፈልገው ይህንን ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ የሕይወት ታሪክ ነው፡፡ ይህንን ታሪክ እንኳን ላወራው ቀርቶ ልሰማው እንኳ ባልፈልግም አማራጭ አልነበረኝምና ታሪኩን ለመጀመር ስል በሩ ተንኳኳና አንድ የአስር አለቃ ሰላምታ ሰጥቶ፤ "ጌታዬ የፖሊስ አዛዡ ይፈልጉዎታል " ብሎ ወጣ፡፡ ለግዜው ቢገላግለኝም፣ መጨነቄ ግን አልቀረም፤ "ምን ይሆን? ይህን የተጠራሁበትን ጉዳይ የሚመለከት ይሆን?" አልማዝ ምን ሆና ይሆን? ግራ ገባኝ፡፡ በዚያች ጠባብ ክፍል ውስጥ ሀሳብ ባህር ውስጥ ገብቼ የሕይወቴን ውጣ ውረድና የመከራዬን መብዛት ማጠንጠን ጀመርኩ፡፡ የሸሸሁት የአልማዝ ታሪክ አሁንም ደስታን ሳይሆን ይኸው ጭንቀትና መከራን ይዞልኝ መጥቷል፡፡ እንደ ሃምሳ አለቃው አያያዝ ከሆነ ከዚህች ክፍል በሰላም እንደማልወጣ ታውቆኛል፡፡ "ግን ለምን የእኔ ሕይወት
የመከራ ሕይወት ብቻ ሆነ? ለምን ሕይወቴ በሙሉ ደስታ የተነፈገው ሆነ? ለሰው ላወራው የምችል ጥሩ ታሪክ ስርቼ እንዳልፍ ምነው ጌታ አልፈቅድ አለ?" አዎ! ትዝ የሚለኝና በሰላም ተጀምሮ ተጠናቀቀ የምለውና መኩራሪያ የሚሆን ታሪክ አለኝ ካልኩ ያው የልጅነቴ ታሪክ ብቻ ነው፡፡ "ተኖረና ተሞተ" እንደሚባለው "ታሪክ ተሆነና ተነገረ" ካልተባለ፡፡

👍43❤3🔥2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
ማንኛውም የሰው ልጅ መላ አቆሙን እንቅስቃሴውንና ንግግሩን ትኩር ብለው ሲያዩት ከሆነ እንስሳት ጋር ይመሳሰላል፡፡ለምሳሌ አንዳንድ ሰው ከታች ከእግሮቹ ቀጭን ይሆንና ወደላይ ሲሄድ እየሰፋ እየሰፋ ይሄዳል..ትከሻው ከሰውነቱ ባልተመጣጠነ ሰፊ ሲሆን በመጠኑ ጎበጥ ያለ ይሆናል..አንገቱ ደልዳላና አጭር ሆኖ ወደታች ዘንበል ያለ ነገር ሲሆን ከጎሽ ጋር ይመሳሰላል..በቃ በአራት እግሩ ቆሞ የሚሄድ ጎሽ ነው የሚመስላችሁ፡፡ሌላው ደግሞ አላ ረጅም መለሎ ነው ግን ከስር እስከ ላይ ወጥ ነው..ሁሉ ጊዜ ለመጋለብ የተዘጋጀ ይመስላል…እናም ከፈረስ ጋር ይመሳሰላል፡፡ሌላው ደግሞ አለ ስልክክ ያለ ቆንጆ ነው..ፀጉሩ ከግራና ከቀኝ ገባ ብሎ ከፊት ለፊት ወደፊት የወጣ ነው..አይኖቹ ትንሽ የሆኑ ጥልቅ ጥርት ያሉና ተቁለጭላጭ ናቸው…ደረታቸውና ነፍተውና ቀና ብለው በመወጣጠር ነው የሚሄዱት፡፡አይን ያሰብራሉ እንጂ አይን አይሰብሩም..አነዚህ ልክ እንደ አንበሳ ነው የሚመስሉት ፡፡አሉ ደግሞ ሌሎች ሙልጭልችና ስብርብር ያሉ… ተንኮለኞችና ተናዳፊዎች..ልክ እባብን የሚመስሉ፡፡
ሰሎሜ ደግሞ ሲያዬት ሁሌ በራ አበባ ላይ ለማረፍ ክንፏን እያማታች ያለች ቢራቢሮ ነው የምትመስለው፡፡መላ ሰውነቷ ላይ አይነግቡ ደማቅ ቀለማት የተበተኑባት ነው ምትመስለው፡፡ለዛ ነው ጓደኖቾ አልፎ አልፎ ቢራቢሮ እያሉ የሚጠሯት ፡፡
አላዛር ባለቤቱን በመስኮት ቁልቁል አዘቅዝቆ እያያት በጭንቀት‹‹በፈጣሪ በዚህ ውድቅት ለሊት ይህቺ ቢራቢሮ ወደየት ነው የምትበረው ?››ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹በቃ ወደ እናቷ ቤት ልትሄድ ነው፡፡››ሲል በመገመት ነበር እርግጠኛ የሆነው…ተከትሏት መሄድ እንደማይችል እርግጠኛ ነው፡፡ማድረግ የሚችለው ከአንድ ሰዓት በኃላ እናቷ ጋር ደውሎ በሰላም መድረሷን መጠየቅ ነው፡፡ቢጃማውን ደረበና ወደውጭ ወጣ፡፡የተበለቀጠውን የውጭ በራፍ መልሶ ዘጋና ወደሳሎን ተመልሶ ቁጭ አለ ፡፡ደግሞ ተነሳና ከመደርደሪያው ውስኪ ጠርሙስ ከብርጭቆ ጋር ይዞ ወደመቀመጫው ተመለሰ፡፡መጀመሪያ የቀዳውን በአንድ ትንፋሽ ነው የጨለጠው፡፡በዚህ ውድቅት ለሊት የልጅነት ጓደኛው የእድሜ ዘመን ፍቅሩና የቤቱ ዋልታ ሚስቱ ጥላው ስለሄደች በእሷ አልተበሳጨም፡፡ ፈፅሞ በእሷ ለመበሳጨት መብት እንደሌለው ያውቃል፡፡ .በራሱም አልተበሳጨም….ግን ደግሞ በእድለ ቢስነቱ በጣም አዝኗል፡፡
‹‹እንዲህ አይነት አፀያፊ ጉድለት በእኔ ላይ እንዴት?እግዚያብሄር በየትኛው ሀጥያቴ ነው የፈረደብኝ?››መልስ የሌለውን ጥያቄ እራሱን ጠየቀ፡፡እና አባቱን አስታወሰነ ምን አልባትም በህይወት ዘመኑ ለአንድ ሺኛ ጊዜ ከአንጀቱ ረገመው፡፡
አባት ልጅን ሲረግም የተለመደ ነው፡፡ወደኃላ ተመልሶ ልጅ አባትን ሲረግም ግን ነገሩ ውስብስብ ነው፡፡
ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡እናቷ ጋር ነው የደወለው፡፡ይጠራል..ግን ደግሞ አይነሳም፡፡‹‹ሳይለንት ላይ አድርገውት ይሆናል፡፡››አለና በቤት ስልክ ደግሞ ሞከረ፡፡፡አሁንም ይጠራል የሚያነሳ የለም..ይበልጥ ግራ ተጋባ፡፡ ….ደግሞ ደወለ…ይግረምህ ብሎ ተዘጋበት፡፡መልሶ ደወለ፡፡አይሰራም፡፡
‹‹በቃ ደርሳለች ማለት ነው፡፡.በዚህ ለሊት ልጄን እንዴት አባረራት ብለው ስለተበሳጩብኝ ነው ስልኬን የማያነሱት….››ሲል ደመደመ፡፡‹‹በቃ ጥዋት በማለዳ እቤታቸው ሄጄ አያታለው..ቢገላምጡኝም እችለዋለሁ››፡፡አለና ብርጭቆ ውስጥ የነበረውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠና አዛው የተቀመጠበት ሶፋ ላይ ኩርምትምት ብሎ ተኛ፡፡እና ማሰብ ጀመረ ፡፡ይህቺን ፍቅሩን ነፍስ ካወቀበት ቀን አንስቶ በልቡ አለች፡፡እሷን ማግባት ይፈልግ የነበረው ገና ማግባት እራሱ ምን መሆኑን ሳያውቅ በፊት ነው፡፡በእሷም ምክንያት መስዋዕትነት መክፈል የጀመረው በጮርቃ እድሜው ጀመሮ ነው፡፡ትዝ ይለዋል…
ሰሎሜ በ5 ወር ትበልጠዋለች፡፡ያደጉት በአንድ ሰፈር ውስጥ በሚገኝ ከመንገድ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ በትይዩ በሚገኙ ቤቶች ውስጥ ነው፡፡ጭቃ ተጋግዘው አቡኩተዋል…አፈር በአንድ ላይ በትነው ተጫውተዋል፡፡በተቀዳደደ አሮጌ ካልሲ ውስጥ ላስቲክ ጠቅጥቀው ኳስ በመስራት አብረው ጠልዘዋል፡፡ሌባና ፖሊስ…ለኪ ለኪቾ… መሀረቤን ያያችሁ ..ሁሉንም ሀገርኛ የጫወታ አይነቶችን ተጫውተው ተደስተዋል፡፡ከሁሉ በላይ ግን የማይሰለች ጫወታቸው ዕቃ ዕቃ ነበር፡፡የአባትነት ብቃት የእናትነት ኩራት.. የፖሊስነት ስልጣን ወዘተ የሚያጎናፅፋቸው፡፡ በህይወት ባህር ላይ በትንሹ አእምሯችው የታዘቡትን እና የኮረጅትን …ወደፊት የሚገጥማቸውን የህይወት ውጣ ውረድ ባዩትና እና በገባቸው ልክ የሚለማመድበት ድራማ መሳይ የጫወታ አይነት ነው..ዕቃ ዕቃ፡፡
ያው እቃ እቃ ካለ ደግሞ ባልና ሚስት የግድ ይኖራል፡፡ ማንኛውም ህፃን በቅድሚያ ምኞቱ ወንዱ አባቱን መተካት ሴቷ ደግሞ እናቷን መተካት ነው፡፡ወጣት እየሆኑና ለአባትና እናትነት እየቀረብ ሲሄድ ግን ሸክሙ ምን ያህል እንደሚያጎብጥ ስለሚረዱ በተቃራኒው ፈሪና ድንጉጥ በመሆን ስለጋብቻ በተነሳ ቁጥር በርጋጋ ይሆናሉ)
ታዲያ ብዙውን ጊዜ በተለይ ብቻችውን ሲሆኑን ባልና ሚስት ሆነው መተወን የየእለት ድርጊታቸው ነበር፡፡
ትዝ ይለዋል አንድ ቀን አለማየሁና ሁሴን ተነጥለው በቦታው አልነበሩም፡፡እሱና ሰሎሜ ብቻ ነበሩ፡፡ በወቅቱ ሁለቱም የስድስት ወይም የሳባት አመት እንቡጦች ነበሩ፡፡በእለቱ ታዲያ ዘወትር እንደሚያደርጉት እቃ እቃ ለመጫወት ቅራቅንቦ ኮተታችውን ሰብስበው ከእነሶሎሜ ቤት ጀርባ ወደሚገኝ ቦታ ተያይዘው ሄድ ፣ስብርባሪና የተጣሉ እቃዎችን ደረደሩና ልክ እቤት እንደሆነ ካዘጋጁ በኋላ ያው አላዛር እንደባልነቱ ውጭ በመውጣትና ስራ በመስራት ብር ማምጠት ስላለበት ‹‹ ስራ መሄዴ ነው›› በማለት ተሰናብቷት ይወጣና ዞር ዞር ብሎ ይመለሳል፡፡
‹‹እባክሽ ደክሞኛል.. እራት አልደረሰም እንዴ?››ልክ እንደአባቱ ጅንን ብሎ ይጠይቃል፡፡
‹‹መጣሁ ደርሷል ቁጭ በል፡፡;››ንግግራቸው ሆነ ድርጊታቸው ከሁለቱም ቤት ከእየእለት ክንውን የተቀነጨበ እና የተቀዳ ነበር፡፡ሰሎሜ በቆርኪ ክዳን እጁን እንዲታጠብ አደረገችና በሰባራ ሸክላ ላይ ቅጠል አንጥፋ በላዩ ላይ በውሀ የተለወሰ ጭቃ አድርጋበት(ወጥ መሆኑ ነው)አቀረበችለት፡
‹‹ብላ››
‹‹ነይ እንጂ እንብላ….ልጆቹንም ጥሪያቸው፡፡››
‹‹ልጆቹ በጊዜ በልተው ነው የተኙት….››
በወቅቱ ተደብቆ የሚሰማቸው ሰው ቢኖር መቼም ሳይገረም አይቀርም ‹‹የመአድ ስርዓቱ ከተጠናቀቀ በኃላ አላዛር ‹‹ጥዋት ስራ ገቢ ነኝ ..ልተኛ›› አለ፡፡
ትንሿ ሰሎሜም ‹‹ቆይ አልጋውን ላንጥፍ ››ትላለች፡፡
አላዛርም ልክ የገዛ አባቱ እናቱን በሚያናግርበት የድምፅ ቃና ጠንከር ብሎ‹‹እስከአሁን አልጋው አልተነጠፈም…?በየመንደሩ እየዞርሽ ቡናሽን ስታንቃርሪ ምን ጊዜ አለሽ?በጅራፍ ጀርባሽን መለጥለጥ ነበር››
ሰሎሜ‹‹እንግዲህ ጭቅጭቅህን ጀመርክ ››በማለት የለበሰችውን የእናቷን ፎጣ ከተከሻዋ ላይ ገፋ መሬት ላይ አነጠፈችና ‹‹ያው ተኛ ››ብላው ፊቱ ስትገተር ቀድሟት ተኛና እሷንም ጎትቶ አስተኛት፡፡ከዚያም ትንሹ አላዛር ስለሚቀጥለው ትዕይነት አሰላሰለ፡፡ እናትና አባቱ ወደሚተኙበት እውነታኛ አልጋ በምናብ ተጓዘ ..ትዝ አለው፡፡
‹‹እንትን እናድርግ፡፡››የሚል ሀሳብ አቀረበላት፡፡
‹‹ምን?››ግራ በመጋት ጠየቀችው፡፡
‹‹እናትና አባቴ ሲተኙ እንደሚያደርጉት››

👍52❤10😁6