አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
493 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#የድንግሊቷየ_አፍቃሪዎች ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ =============== ላዳዋ ይዛቸው ትንሽ እንደተጓዘች ‹‹እሺ ምን ገጠመህ?››ሲል አለማየሁ  የመጀመሪያውን ጥያቄ ጠየቀ፡ አላዛርም‹‹ሰውዬው እየሞተ ነው መሰለኝ….፡፡››ሲል በደፈናው መለሰ፡፡ ሁሉም የአላዛር መልስ አልገባቸውም‹‹የትኛዬው ሰውዬ?››ሲል ሁሴን ጠየቀ፡፡ ‹‹አባት ተብዬው፡፡›› ‹‹በስመአብ..?ማን ነገረህ?››ሰሎሜ…»
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

የማን ይሁን ?

የባሰ! እሾክና መርፌ ተነቅሎ የማይጣል፤ በቅርብ ሳይገፋ ያልተደረሰበት ፤ ከላይኛው የወረደ ዱብዳ ፤ የፈጣሪ የቁጣ ስጦታ፡፡ ለማን ታድርገው? ለማን ትስጠው? ለማንስ አቤት ትበል? ተቆርጦ የማይጣል የጣት ቁስል ሆነባት፡፡

ቀኑ ወደ ጨለማ ተቀየረ፡፡ እንደ ተዳፈነ እሳት ውስጧን አቃጠለው፡፡ እንደ ሰኔ ደመና አረምሞ ገፍቷል፡፡ በአንድ ቀን ስህተት የእግዚአብሔር ስራ እንኳን ባይባልም በመቅሰፍቱ በዲያቢሎስ ቅንብር ሆዷ ውፍረትን መከታ እና ከለላ ተጠቅሞ ሳይታወቃት እየገፋ መጥቷል፡፡

እድላዊት ከወንድሟ ከተመስገን ፀንሳለች፡፡ በአንድ እንዴት ላረግዝ እችላለሁ?፡፡ ስታዝን ስትጨነቅ ዘጠኝ ወር ተቆጥሮ ቦርጩ ወደ ልጅ ተቀየረ፡፡ ወንድ ልጅ ከነ ቃጭሉ ተገላገለች፡፡ ግን ከፊቷ አሁንም የማይገፋ ከዳቢሎስ የተገነባ የጨለማ ተራራ ተጋርዶባታል፡፡

ምንጃር ሸንኮራ አውራጃ ውስጥ ነው፡፡ ጉራንባ ማርያም አካባቢ ያለ ማህበረሰብ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ በእምነታቸው አክራሪና ከእምነት ውጭ ለሚከሰቱ ማንኛውም የክርስትና ጥፋት የፈፀመ ከማህበረሰቡ ይገለላል፡፡ እንደ እድር ፣ ባልትና እና ማህበር የመሳሰሉትን መካፈል አይችልም፡፡ በማህበረሱቡ የተጠላ ፤የማይወደድ ፣ ከሰው እንዳልተፈጠረ ከሰው ውጭ ተደርጎ ይቆጠራል።

እድላዊት እያወቀች ሳይሆን ሳታውቅ ከወንድሟ ከተመስገን መውለዷን ከያሬድ ውጭ ማንም አያውቅም፡፡

የወለደችውን ልጅ ክርስትና የሚነሳው የወላጅ አባት ስም ካልታወቀ መነሳት ፤ መጠመቅ የተወገዘና የተከለከለ ነው፡፡ የእድላዊት ልጅ ባለማወቅ አባት ታዲያ ማን ይሁን ? የማንስ ተብሎ ክርስትና ይጠመቅ ? አክ ተብሎ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥ፡፡ የተመስገን ብትለው ለእሷ አንዴ ሞት ቢሆንም ለዘመዶቿና ለቤተሰቦቿ አስሬ ሞት ብቻ
ሳይሆን ከሰው እንዳልተፈጠሩና ወግ አጥባቂ የክርስትና አገልጋይ እንዳልሆኑ ከሰው ውጭ ተደርገው እንደሚገለሉ የሚታወቅ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ታዲያ እድላዊት ይህ ሁሉ የታዘለባትን የጭንቀት እሳት ማማከር ያለባት ለወንድሟ ለተመስገን እንጅ ለማንም ማማከር እንደ ማይቻል ግልፅ ነው፡፡ ግን አሁንም ሌሊቱ ጨልሞባታል፡፡

"ምን እናድርግ ? የልጁ የክርስትና ቀን እየደረሰ ነው፡፡ እኔ ጨንቆኛል፡፡ የማደርገው ጠፍቶኛል፡፡ ከእንግዴህ ያለኝ አማራጭ መርዝ ጠጥቸ ወይም ታንቄ መሞት ነው፡፡ የወንድሜ ነው ብየ ክርስትና አላስነሳም፡፡ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡

ተመስገን የእህቱ ጭንቀት በሱም ላይ ካደረበት እና ከሰነበተበት ቆይቷል፡፡ ጥሎ እንዳይጠፋ እድላዊትን ተመልሶ ዳግመኛ የማያገኛት መሰለው፡፡

እድላዊት እያለቀሰች መልስ እንኳን ሳይሰጣት ከያሬድ ጋር ደርሸ መጣሁ ብሏት ተነስቶ ወደ ያሬድ ቤት ሄደ፡፡

ተመስገን እንደደረሰ ከያሬድ ጋር የእግዚአብሔር ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ ያሬድ ወደ እርሻ ሊሄድ ሞፈርና ቀንበር እያዘጋጀ ነው፡፡

"ወደ እርሻ ልትሄድ ነው እንዴ ሞፈርና ቀንበር የምታሰናዳው?" አለ ፤ ተመስገን፡፡

"አዎ፤ እንዴው ትንሽ የፋልማ መሬት ከሰም ነበረኝ፡፡ ቧጠጥ አድርጌያት ልምጣ ብዬ ነበር አነሳሴ፡፡ ስተረካከም እዚሁ እረፈደ ብሎ ወደ ቤት ግባ እንጅ አለው፡፡

"ኧረ አልገባም፡፡ አንተ ጋር ነበር የመጣሁት"፡፡

"ምነው በደህና ነው"? አለ ፤ ያሬድ፡፡

"ምን ደህንነት አለ ፤ ገና ስፈጠር የአርባ ቀን እድሌ በእሳት ተሞልቶ የእሳት እረመጡ ወደ ጭስነት ተቀይሮ የመውጭያ በር አጥቶ በቁሜ እያቃጠለኝ፡፡

"ምነው እድላዊት ሰላም አይደለችም እንዴ?፡፡

"አይ! ተወኝ ፤ አሁን የእድላዊት ነገር አስጨንቆኛል፡፡ የልጁ ክርስትና እየደረሰ ነው፡፡ የአባቱ ስም ካልታወቀ ክርስትና እንደ ማይጠመቅ አንተም ታውቃለህ፡፡

የማደርገው ሁሉ ግራ ገብቶኛል፡፡ ወንድሜ እባክህ ከዚህ ጨለማ አውጣኝ፡፡ ያላንተ ማንም የማዋየውና የማማክረው የለኝም አለው፡፡በሃዘን ተሞልቶ ፡፡

"በምን ልርዳህ የማደርገው ጠፍቶኝ እኮ ነው፡፡ እስከ አሁንም ዝም ያልኩህ እንጅ እኔ እንኳን ወደ አዲስ አበባ ይዘናት እንድንሄድ አስቤ ነበር፡፡ ግን ክርስትና ሳታስነሳ ከቤት መውጣት አይቻልም ብየ ነው፡፡ አሁን በምን ላግዛችሁ ? ንገረኝና በተቻለኝ አቅም ልሞክር አለ፡፡

በፊቱ ላይ ወርዶ ቡሃቃ ያስመሰለውን እንባ በለበሰው ፎጣ እየጠራረገ እኔማ ለመጥፋትም አስቤ ነበር፡፡ ግን እድላዊት ጥሎ የሚሄድ አንጄት አጣሁ፡፡ አሁን አንተን የማስቸግርህ ልጁ ክርስትና እስከሚነሳ ድረስ የአባቱን ስም በአንተ እናድርግና ክርስትና ከተጠመቀ በኋላ ፤ የተፈጠረውንና የተደረገውን ባለመተዋወቅ እንደ ሆነ ለቤተሰብ እንነግራለን አለ፤ ተመስገን ፡፡ ደፍሮ በመናገሩ አይኑን ላለማየት አቀርቅሮ መሬት መሬት እያየ፡፡

የልጁ አባት ሆኘ ክርስትና ቢጠመቅ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን የአካባቢያችንን ባህል እንደምታውቀው በሚስቱ ላይ ዲቃላ ወልዷል ተብየ እኔ ከማህበረሰብ እንደምገለል፡፡ ደግሞም ባለቤቴ ይህንን ስሰማ በእኔ ላይ ዲቃላህን ታንጠባጥባለህ ብላ ባዶቤት ዘግታብኝ ትሄዳለች አለ ፤ ያሬድ፡፡

"ያልከው ሁሉም ይገባኛል፡፡ ግን ከወንድሟ ወለደች ቢባል ምን ያህል እንደሚከብድ መገመት አያቅትህም፡፡ ደግሞ አባታችን በዚህ ቦታ ወግ አጥባቂ እንደ ሆነ ታውቃለህ፡፡

እባክህ! ያሬድ ስለፈጠረህ አምላክ! ተለመነኝ ሳላውቅ እንደ ሆነ እሳት ውስጥ የገባሁት አንተም ታውቃለህ፡፡ ሚስጥሩን ለባለቤትህ እንነግራታለን፡፡ መጀመሪያ አንተ ብቻ እሽ በለኝ፡፡ እያለቀሰ ተማፀነው፡፡

ያሬድ የሚለው ሁሉ ጨነቀው፡፡ የእድላዊትና የተመስገን ስቃና መከራ የሱም ሆነ፡፡ ክርስትናው እስከሚያልፍ የልጁ አባት ለመሆን ብቻውን መወሰን አልቻለም፡፡

"ለማንኛውም አበበችን አብረን ሚስጥሩን እናካፍላትና እሷ እሽ ካለች የእኔ አያስቸግርም፡፡ አይቻልም ካለች ግን ምንም ላደርግ አልችልም" አለው

"እሽ አንተ እንዳልክ" ብሎት ወደ ቤት ገቡ፡፡

"ደህና አደርሽ አበበች" ? አለ ፤ ተመስገን፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርክ ተመስገን" ? አለች ፤ አበበች፡፡

ጉንጮቹ አብጠው ገና በጥዋቱ አይኖቹ ቀልተዋል፡፡

ምነው ደህና አይደል ይሆን ? ያለቀሰ ይመስላል፡፡ የሞተ ሰው ይኖር ይሆን ? ያሬድም ደስተኛ አይመስልም፡፡ ዛሬ ምን ተፈጥሮ ይሆን ? አበበች ከውስጧ ሳታወጣና ሳታሰማ የተናገረችው ነበር፡፡

ምን ብሎ እንደሚነግራት ግራ ተጋብቷል፡፡ የቤቱን ጣራ ጣራ እየተመለከተ እንባው በጉንጩ ላይ ይወርዳሉ፡፡ አንገቱን ዞር አድርጎ ለመጥረግ ሞክረ፡፡

አበበች ግን ገና ሲገባ አንስታ እየተመለከተችው ነበር፡፡

"ምነው ደህና አይደለህም እንዴ? የምታለቅሰው" አለች ፤ ለተመስገን፡፡ የተፈጠረውን ለመስማት እየተጨናነቀች፡፡
ተመስገን ከተቀመጠበት ብርጩማ ላይ ተነስቶ ምንም በማታውቀው እና ምንም ባልሰማችው አበበች እግር ላይ ተደፋ፡፡ እባክሽን ከጉድ አውጭኝ ፤ በምትወጅው ልጅሽ ፤ በምትኩ ስም እለምንሻለሁ እያለ ያለቅስ ጀመር፡፡

አበበች ተመስገን ስለምን እንደሆነ የሚያወራው ግራ ተጋብታለች፡፡ ሲለምናትና ሲማፀናት ገና ባልሰማችውና ባላወቀችው ቀላል ነገር መስሏት እሽ፡፡አሁን ተነስ ብላ ካስነሳችው በኋላ፤ ምንድ ነው እሱ የቸገረህ"? አለችው፡፡ ተነስቶ ወደ ነበረበት የብሩጩማ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ አሁንም ከየት መጀመር እንዳለበት ግራ ቢገባውም መንፈሱ ብትጨነቅም ሚስጥሩን ለአበበች ካላካፈለ መፍትሄ ስለማያገኝ ደፍሮ መናገርና መተንፈስ አለበት፡፡ ራሱን አፅናንቶ ለመናገር ወሰነ፡፡
👍524
"አሁን የለመንኩሽና በልጅሽ ስም የተማፀንኩሽ ነገር ብሎ.. የነበረውን ድርጊት ሲያነሳ ውስጡ እንደገና ተረበሸ፡፡ እንባ ሲተናነቀው መናገሩን ትቶ አለቀሰ፡፡

ምን እንደምትረዳው ከአሁን አሁን ሊነግረኝ ነው እያለች ገና ምን እንደሆነ ሳታቅ እሽ በማለቷ ፍራት ፍራት ብሏታል፡፡

"እባክህ ማልቀሱን ተውና ንገረኝ?፡፡ እኔንም እኮ አስጨነከኝ አለች፡፡

ተመስገን ከማልቀሱ መለስ አለ፡፡ በባለፈው ከያሬድ ጋር ድሬ የሄድን እለት እድላዊትን ያገኘናት የሆቴል ሰራተኛ ሆና ነበር፡፡ እኛም በአጋጣሚ እድላዊት የነበረችበት ሆቴል አልጋ ይዘን ስናድር ሳንተዋወቅ ከእድላዊት ጋር አብሬያት አድሬ የተዋወቅነው ጠዋት ነበር፡፡ እና አሁን የወለደችው ልጅ ከእኔ ነው፡፡ የልጁ ክርስትና ስለደረሰ የማን ተብሎ ይነሳ አገሩ ደግሞ የአባት ስም ካልታወቀ ክርስትና መጠመቅ አይችልም፡፡ አሁን የምለምንሽ የልጁ ክርስትና እስከሚያልፍ ድረስ የአባቱ ስም በያሬድ አድርገን ክርስትናው ካለፈ በኋላ ፤ የተፈጠረውንና የተደረገውን እውነቱን አውጥተን የሚሰጠንን የሃጢያት ፍርድ እንቀበላለን ብሎ አይኖቹን የቤቱ ወለል ላይ ተከላቸው፡፡

አበበች የሰማችው ነገር ግራ የሚያጋባ ፤ ለማመን የማይከጀል ፤ በትዳሯ ላይና በሂወቷ ላይ ሰማይ የተደፋባት መስሎ ታያት፡፡ ታዲያ በምትወደው ልጇ በምትኩ ስም ሲማፀናት እሽ ብትልም ባለማወቅ ስለሆነ እሽ ያለችው ነገሩን ስትሰማ ግን ቸኩላ እሽ በማለቷ ተደበላለቀባት፡፡ ደግማ እሽ ሳትለው የባለቤቷ የያሬድን አይን ተመለከተች፡፡

"አንተስ ምን አስበሃል? የምሰማው እውነት ነው?፡፡ የምታቀውስ ነገር አለ? አለች፡፡

"ድርጊቱ የተፈፀመው ባለመተዋወቅ እንደሆነ እኔም አውቃለሁ፡፡ አሁን ተመስገን የጠየቀሽ ግን ለትዳራችንም ይሁን ለሂወታችን ጋሬጣ እንደሚሆን ጥርጥ የለውም፡፡ ነገር ግን ከተመስገንና ከእድላዊት ስቃይና መከራ አይበልጥብንም፡፡ እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር የለምና ለእግዚአብሔር ብለን እንርዳቸው፡፡ ባይሆን ተመስገን እንዳለው ልጁ ክራስትና ከተጠመቀ በኋላ፤ እውነቱን ተናግሮ በስህተት እንደ ሆነ ቤተሰቦቻቸውን አሳምነን ተመስገንና እድላዊት ንሰሃ እንዲገቡ ማድረግ ነው አላት፡፡

አበበች በትዳሯ ላይ ትንሽ የማይባል ነገር ወደ ፊት እንደሚገጥማት ብታስብም የተደበቀው ሚስጥር በቅርብ ቀን ስለሚወጣና ባለቤቷ ያሬድ እንርዳቸው ስላላት ለወደፊት የሚደርስባትን ስቃይና መከራ ወደ ጎን ትታ በባለቤቷ ሃሳብ ተስማምታ አንተ ከተስማማህ እኔ ከአንተ ውጭ አይደለሁም፡፡ ብላ ለተመስገን የሚያስደስት መልስ ሰጡት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113
👍422
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ ልቡ ላይ አዲስ እና ያልተጠበቀ ፍቅር በቅሏል…የአስካለ ምስልም በተለይ ወሬዋና ሳቋ  ከምናቡ ለደቂቃም ሊሰወር አልቻለም፡፡ለዘላለም ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሰው ሊያፍቀር ሚችል አይመስለውም ነበር…ግን ሆነ፡፡እርግጥ ለሁለቱ ያለው ፍቅር ፍፅም ተመሳሳይ አይደለም….ይሄኛው አዲሱ ፍቅሩ የሚያንቀዠቅዝ አይነት ነው፡፡የወሲብ ርሀብ ያለበት የተክለፈለፈ ፍቅር፡፡የሰሎሜ ግን የተረጋጋና ጥልቅ ነው፡፡ስስትና እና ተስፋ ያቆሙት  ዘላለማዊ መሳይ ነው፡፡
ከአስካለ ጋር ባሳለፈ በሁለተኛው ቀን ወደአላዛር ሄደና‹‹አባትህ እንዴት ናቸው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ያው ድኖ አይደል ወደቤት የገባው…ምን ይሆናል?››ሲል ድርቅ ያለ መልስ መለሰለት፡፡
‹‹አሁን እንዴት እንደሆኑ ደውለህ ጠየቅክ?››
‹‹ለምን ብዬ ጠይቃለሁ?››
‹‹በትክክል መጠየቅ ይገባሀል…›››
‹‹የትናንቱንም እንዴት እንዳደረኩት ግራ እየገባኝ ነው››
‹‹እንደውም ተነስ እንሂድና አይተናቸው እንምጣ፡፡››
አላዛር ግራ በመጋባት አፍጥጦ ሲያየው ከቆየ በኃላ፡፡‹‹ሰላም ነህ ግን?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ምነው…ምኔ ነው ሰላም አልመስል ያለህ ?››ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
‹‹ የምናገረው አይገባህም እንዴ? ትናንት በዛ ለሊት ለእሱ ስል ራሴም ተንከራትቼ እናንተንም ሳንከራተት ማደሬ እራሱ እየቆጨኝ ነው ..ጭራሽ ዛሬም ደግሜ ቤት ሄጄ እንድጠይቀው ትፈልጋለህ?፡፡››
‹‹ተወው በኃላ እንዳትፀፀት …ላንተው ብዬ ነው፡፡እኔ አባቴ ጠጪም ሌባም ፤ቁማርተኛም ..ምንም ሆኖ ምንም በህይወት ቢኖርልኝ እንዴት እንደምደሰት ልትገምት አትችልም፡፡በዚህ አለም ላይ እንደቤተሰብ ወሳኝ ነገር የለም፡፡ከፋም ለማም በጨለማ ቀናቶችህ አብረውህ የሚንከራተቱት እነሱ ናቸው፡፡..ቤተሰብ በህይወት መንገድ ወሳኙ አጋር እንደሆነ አውቃለው፡፡የገንዘብ ችግር ቢኖርብህ ቤተሰብ ካለህ ታልፈዋለ…ክፉኛ ብትታመም ቤተሰብ ካለህ ህመምህን ቻል አድርገህ በቀላሉ ማገገም ትችላለህ …ሀገርህ ፈርሳ ስደት ላይ ብትሆን እራሱ ቤተሰብህ ከጎንህ ካለ እንደምንም እየተደጋገፍክ ያንን ክፉ ቀን ታልፈዋለህ፡፡››
‹‹ገባኝ…የእኔ ቤተሰብ እናቴና እህቶቼ ናቸው፡፡በተጨማሪ ደግሞ እናንተ ወንድሞቼ አላችሁልኝ…እርግጥ እናቴ የለችም….ሁለት እህቶቼ ግን አሁንም አሉልኝ..እነሱ በቂዬ ናቸው፡፡ለእኔ አባቴ ከእናቴ ቀድሞ ነው የሞተው…አሁን እሱን ሳይ በድን አካሉ ብቻ ነው ሲንቀሳቀስ የማየው..ነፍሱ ውስጡ የለችም፡፡››
አለማየሁ ሊያሳምነው ስላልቻለ ተበሳጨ‹‹በቃ ቸው..ድሮም አንተ ከጠመምክ  መመለሻ የለህም››አለውና ፊቱን አዙሮ መራመድ ጀመረ፡፡
‹‹ቆይ አትሂድ..ና እንካ››አለና እጁን ወደባንኮኒው በመስደድ ብር በእጁ አስጨበጠው፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹ማኪያቶ ልጋብዝህ ነበር …መውጣት አልቻልኩም..ስለዚህ ብቻህን ጠጣ››አለው፡፡
አለማየሁም‹‹አመሰግናለሁ፡፡››ብሎት የሰጠውን ብር በእጁ እያሻሸ አካባቢውን ለቆ ሄደ ..የእሱ ሀሳብ አላዛርን አሳምኖ አባቱ ቤት አብሮት መሄድ ነበር፡፡፡ያንን የፈለገው ያችን ውብ የጓደኛውን አባት ሚስት ዳግመኛ ለማየት ነው፡፡ከትናንትናው ምሽት ጀምሮ ፈፅሞ ከምናቡ ሊያሸሻት አልተቻለውም፡፡የአላዛር መገገም ግን እቅዱን ሁሉ ገደል ከተተበት፡፡
ከአላዛር ሱቅ ከራቀ በኃላ መዳፉን ፈልቅቆ ሲያየው ድፍን መቶ ብር ነው፡፡ስልኩን አወጣ ..ሰሎሜ ጋር ለመደወል ነው የፈለገው፡፡መቶ ብር ካለው ወይ ይዟት ሲኒማ ቤት ይገባል ወይ ደግሞ አንድ ካፌ ቁጭ ብለው ማኪያቶ እየተጎነጩ  ዘና ይላሉ፡፡እቅዱ እንደዛ ነው፡፡
‹‹ሄሎ ››
‹‹ምነው? አሁን ተለይተሀኝ ሄደህ አሁን ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ውይ ሰው ጠፍቶ አንቺ ትናፍቂኛለሽ…..?ጉረኛ ነሽ››
‹‹እመን …..››
‹‹ለምን ብዬ ነው የማምነው?››
‹‹እሺ ለምን ፈለከኝ?››
‹‹ምን እየሰራሽ ነው…?አመድ በኪሴ ስላለ ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው…››
‹‹አንድ ጥብስ የማይገዛ ብር ይዘህ..ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው ስትል ትንሽ አይሸምምህም?››
‹‹አንቺ ምስጋና ቢስ…ይሄኔ በኪስሽ አምስት ብር የለም…አሁን ትወጪያለሽ ወይስ አትወጪም?››
‹‹አዝናለሁ እቴቴ...ዘመዶቾ ጋር እንሂድ ብላኝ ለመሄድ እየተዘጋጀን ነው፡፡››
‹‹የት ?ሰንዳፋ?››
‹‹አዎ…ምነው መሄድ ትፈልጋለህ እንዴ?››
‹‹አይ ይለፈኝ…ግን ታድራላችሁ እንዴ?››
‹‹አዎ… ነገ ነው ምንመጣው፡፡››
‹‹እሺ መልካም መንገድ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ በጊዜ ወደቤት ግባ …እቴቴ እንዳታዘርፈኝ እያለች ነው ፡፡››
‹‹እሺ …አታስቢ በያት፡፡››ብሎ ስልኩን ዘጋውና ተቀያሪ ሀሳብ ማብላላት ጀመረ…ወዲያው ነው መሳጭ የሆነ ሀሳብ ብልጭ ያለለት‹‹ መንገድ ተሻገረና ወደአትክልት መሸጫ ሱቅ ሄደ ..አንድ ኪሎ ሙዝ ገዛ፡፡ ታክሲ ውስጥ ገባ ፡፡ቀጥታ ወደአላዛር አባት ሰፈር ነው የሄደው፡፡ደረሰና የውጪውን በራፍ አንኳኳ…፡፡
ከተወሰነ ጥበቃ በኃላ ተከፈተለት…
ይህቺን ሴት ለሁለተኛ ጊዜ ሲያያት ይበልጥ አምራና ውብ ሆና ነው የታየችው፡፡አስካለ ፈፅሞ አየዋለሁ ብላ ያልጠበቀችው ስለሆነ በጣም ነው የደነገጠችው፡፡
በዝምታ አፍጥጣ ስታየው ግራ ተጋባና ‹‹ምነው አላወቅሺኝም እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡
በራፉን ጋርዳ እንደቆመች‹‹ይቅርታ እንዲህ በቅርቡ ደግሜ አይሀለው ብዬ ስላልገመትኩ ነው…እንጂማ አንተን እንዴት እረሳሀለው፡››አለችው ፡፡
በጥቁር ፔስታል የያዘውን ሙዝ እንድታይ እያወዛወዘ፡፡‹‹ጋሼን ለመጠየቅ ነው የመጣሁት››አላት፡፡
‹‹ግባ…ና ግባ››አለችና በራፉን ለቀቀችለትና ቀድማው ወደውስጥ መራመድ ጀመረች ፡፡ከኃላዋ ተከተላት፡፡ገቡ፡፡
‹‹ቁጭ በል፡፡››ሙዙን አቀበላትና ፈራ ተባ እያለ ቁጭ አለ፡፡
‹‹አሁን የእውነት ሰውዬው እሷቸውን ልጠይቅ እንደመጣው ያምኑኛል?››ሲል ከዚህ በፊት ያላሰበውን ነገር አሰበ‹‹አይ አላዛር ነው የላከኝ ..ስራ ላይ ስለሆንኩ ሰላም መሆኑን እይልኝ ሳለለኝ ነው የመጣሁት፡፡››እለዋለው ሲል ወሰና ተረጋጋ፡፡ሙዙን ተቀበለችውና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ..ከፊት ለፊቱ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ጋሼ ተኝተዋል እንዴ?››ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
‹‹‹የሉም ስራ ገብተዋል››
በረጅሙ ተነፈሰ‹‹እንደዛ ነው…በደንብ ተሻሏቸዋል ማለት ነው?››
‹‹አዎ በደንብ ተሽሏቸዋል፡፡አተነፋፈስህ ግን ባለመኖራቸው ደስ ያለህ ይመስላል››አለችው፡፡ የውስጡን ስላነበበችበት አፈረ፡፡
‹‹አይ..ያው አለ አይደለ..ከድሮም ጀምሮ እፈራቸዋለው…ለዛ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄን ያህል የሚያጨናንቅህ ከሆነ ለምን መጣህ?››ብላ ሲፈራው የቆየውን ከባድ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አላዛር ስራ ላይ ስለሆነ መጥቶ ሊጠይቃቸው አልቻለም…እይልኝ ብሎ ስላስቸገረኝ ነው››ከደቂቃ በፊት ያቀናበረውን ምክንያት ነገራት፡፡
ፈገግ አለች….
‹‹ምነው?››
‹‹አይ …እኔ ደግሞ እኔን ለማየት የመጣህ መስሎኝ ደስ ብሎኝ ነበር?››ስትል ያልጠበቀውን አማላይ አይነት መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እሱማ ..ያው እግረመንገዴን አንቺንም ማየትና እንዴት እንደሆንሽ ማወቅ ስለፈለኩ ነው የመጣሁት፡፡››ሲል በከፊል  አመነላት፡፡
‹‹ስለመጣህ ደስ ብሎኛል…መጣው ተጫወት›› ብላ ወደውስጥ ገባችና ..ሻይ ጥዳ….ተመለሰች፡፡
ሞባይሉን አወጣና ሰዓቱን ተመለከተ..5፡20 ይላል፡፡‹‹ምሳ ሰዓት እየቀረበ ነው….››አላት፡፡
‹‹አዎ ..ምነው እርቦሀል ላቅርብ እንዴ?››
‹‹አይ!! ማለቴ ጋሼ  አሁን ለምሳ ይመጣሉ ለማለት ነው፡፡››
👍5613
‹‹እ..አይዞህ ዘና በል ፡፡አይመጡም..፡፡ምሳ ይዘው ነው የሚሄዱት…፡፡በጣም ፈጠኑ ከተባለ..ማታ 12 ሰዓት ላይ ነው የሚመጡት፡፡››
በረጅሙ አየር ወደውስጡ ሳበና‹‹እሰከዛ ሰዓት  ታዲያ ብቻሽን ነው የምትሆኚው?››
‹‹ለምን ብቻዬን ሆናለው…?አንተ አለህ አይደል?››
‹‹አይ ዛሬማ አለሁ…ለሌላው ቀን ነው ያልኩሽ፡፡››
‹‹አዎ…ብቻዬን ነው ምሆነው....ግን እንደምታስበው አይከብድም.. ቤት ሳፀዳ ፣እቃ ሳጥብ…ምግብ ሳዘጋጅ…ሳላስበው ነው መሽቶ የሚነጋው፡፡ እኔ የሚከባደኝ ቀን ብቻዬን መዋሉ ሳይሆን ማታ እሳቸው ሰክረው መጥተው ሚረብሹኝ ነገር ነው፡፡ደግሞ እኮ ሁሌም ቤት አልሆንም.. አልፎ አልፎ አስቤዛ ለመግዛት ዋጣ እላለሁ…እህል ላስፈጭ ወፍጮ ቤት ሄዳለሁ….መብራት ልሞላ መብራት ሀይል ሄዳለው……››
ይሁን ..ካሁን በኃላ ግን ብቸኝነት ሲሰማሽ እኔጋር ደውይልኝ›››
‹‹እና ሁሌ ስደውልልህ ትመጣልኛለህ››
‹‹አዎ..ትምህርት ቤት ካልሆንኩ በደቂቃ ውስጥ ነው የምመጣልሽ››
ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደእሱ ጠጋ ብላ ጎንበስ አለችና ጉንጩን በስሱ ሰማው.‹‹ታድዬ››ብላው ወደጓዲያ ገባች፡፡
እሱ በቀኝ እጁ መዳፍ  የሳመችውን ጉንጭ እየዳበሰ እንደፈዘዘ ቀረ፡፡ከደቂቃዎች በኃላ ለሁለቱም ሻይ ይዛ መጣችና አጠገባቸው የነበረች አነስተኛ  ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ ቁጭ አለች፡፡
ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ምሳ አቀረበችና ልክ እንደአዲስ ጎጆ ወጪ ሙሽሮች አይን ለአይን በስስት እየተያዩና እየተጎራረሱ ምሳቸውን በሉ፡፡
‹‹አየሩ ትንሽ ይሞቃል አይደል››አለችው የበሉበትን እቃዎች አነሳስታ እና ጠረጴዛውን አፀዳድታ ፊት ለፊቱ እየተቀመጠች፡፡
‹‹አዎ…እኔን ብቻ ነው እንዴ ሚመቀኝ እያልኩ በውስጤ እያሰብኩ ነበር፡፡››አለና የለበሰውን ጃኬት አውልቆ ከጎኑ ያለው ሶፋ ላይ ጣል አደረገው፡፡እጅጌው ጉርድ በሆነ ጃፖኒ ቀረ፡፡፡ሰውነቱ ፈርጣማ ስለሆነ አይን ይገባል፡፡
‹‹ታዲያ እኔስ ምን ላድርግ ቀሚሴን አላወልቅ?››
ሳቀ….ተሳሳቁ….
‹‹እንደውም አንድ ሀሳብ አለኝ …ከሳሎኑ ይልቅ መኝታ ቤቱ ቀዝቀዝ ይላል…..ና እዛ እንሁን ›› ብላ ቀድማ ተነሳችና እጁን ይዛ ወደመኝታ ቤት ይዛው ገባች፡፡ ለመስዋዕትነት እንደተመረጠ የዋህ በግ ዝም ብሎ ተጎተተላት፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ስትደርስ እጁን ለቀቀችና…የተጫማችውን ነጠላ ጫማ አውልቃ አልጋ ላይ ወጣችና ተጋደመች፡፡
ግራ በመጋባት አፍጥጦ እያያት ነው፡፡በህይወቱ እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሞት አያውቅም….እና አሁን ምን ማድረግ እንዳለበት አላወቀም..‹‹ና ጋደም በል እንጂ…ምነው ፈራህ እንዴ?››አለችው፡፡
‹‹አረ ምን ያስፈራኛል?››አለና እሱም እንደ እሷ ጫማዋን አወልቆ አልጋ ላይ ወጣና አንድን ትራስ ለብቻው ተንተርሶ ከእሷ ሰውነት 20 ሳ.ሜትር ያህል ክፍትት ትቶ ተኛ፡፡ምን ልታወራ ነው ብሎ ሲጠብቅ፡፡
‹‹ይቅርታ …በዚህ ሰዓት ትንሽ ማሸለብ ለምጄለሁ…አንድ አስር ደቂቃ ብተኛ ቅር ይልሀል?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም…ተኚ››አላት
‹‹እሺ..አለችና ወደእሱ ተጠግታ ደረቱ ላይ ተንተራሰችና አይኖቾን ጨፈነች፡፡››
ሳሎኑን ለቆ ወደመኝታ ቤት የመጣው ሙቀቱ እንዲቀንስለት ነበር፤አሁን ግን ይበልጥ ሰውነቱ እየነደደበት ነው፡፡ወደጎን የተዘረጋ እጁን ቀስ ብሎ አነሳና አቀፋት ፡፡ቀስ ብሎ አይኖቹን አጣሞ ሲያያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ የገባች ትመስላለች፡፡ትንፋሿ በአንገቱ አካባቢ ሲበተንበት ልክ ግንቡ እንደተደረመሰ የውሀ ማቆሪያ ግድብ ደሟ እንዳለ ወደታችኛው የሰውነቱ ክፍል ሿሿ እያለ ሲፈስና ብልቱን ሲወጣጥረው እየተሰማው ነው፡፡እንዳቀፋት ገልበጥ አለና ሙሉ በሙሉ ወደእሷ ዞረ፡፡እንደተቃቀፉ ተጣባቁ፡፡አንደኛውን እግሯን አነሳችና ታፋው ላይ ጫነችበት፡፡በዚህ ጊዜ የለበሰችው ቀሚስ ወደላይ ተሰበሰበ…ወደታች ሲያይ የሚያጓጓው ጭኗ ለእይታ ተጋልጦል፡፡የሚንተከተክ የወጣትነት ስሜቱን ይህን አይነት ፈተና ተቋቁሞ እንዲያልፍ አላደረገው፡፡በወቅቱ ስለምንም ነገር የሚያስብበት ሁኔታ ላይ አልነበረም..ቀስ አለና ከንፈሩን ወደከንፈሯ  በማስጠጋት ልክ ውብ ፅጌረዳ አበባ እንደምትቀስም ሰራተኛ ንብ ተጣበቀባት…ቀስ አድርጎ በስሱ ሳማት፡፡መልሳ ሳመችው….ከዛ በኃላ ያለው ነገር ከአእምሮ ስሌት ውጭ ስለሆነ ለመግለፅ እራሱ ከባድ ነበር፡፡መኝታ ቤት አልጋ ላይ  የተጀመረው ፊልሚያ ከ40 ደቂቃ በኃላ  ሳሎን ሶፋ ላይ እርቃን ሆነው ነበር የተገባደደው፡፡ከዛ በኃል ይሄ ድርጊት ማንም ጆሮ ሳይደርስ ለስድስት ወር ለበለጠ ጊዜ ሲደጋገም ነበር፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014
👍566😢1
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አለማየሁና አስካለ ግንኙነት ከጀመሩ ከሰባት  ወር በኃላ
ግንኙነታቸውን ድንገት የሚያከስም  ችግር ተከሰተ፡፡በሁለቱም አእምሮ ያልታሰበበት ቅድመጥንቃቄ ያልተደረገበት አስደንጋጭ ችግር ነው፡፡
ደግሞ ወቅቱ የማትሪክ  ውጤት ከዛሬ ነገ ይለቀቃል ተብሎ እየተናፈሰ ስለሆነ አራቱም  ጓደኛሞች በጉጉት  በምጠበቅበት ወቅት ነበር፡፡ አስካለ ለአላዛር ደወለችለትና በአስቸኳይ እንዲገናኙ እንደምትፈልግ ነገረችው፡፡ከሰፈሯ ብዙም የማይርቅ ካፌ ተቀምጣ ትጠብቀው ጀመር፡፡ብዙም ሳያስጠብቃት እያለከለከ ተገኘ፡፡ እውነተኛ ስሜቱን የሚገልፅ መሸበር ፊቱ ላይ እየታየበት‹‹የእኔ ቆንጆ እንደደወልሽልኝ እየሮጥኩ ነው የመጣሁት.. በአስቸኳይ ፈልግሀለው ስትይኝ ደንግጬ ነበር፡፡››አላት፡፡፡

አስካለ ለእሱ ስሜት እና መሸበር ብዙም ሳትጨነቅ‹‹አዎ …ችግር ተፈጥሯል››አለችው ኩስትርትር እንዳለች፡፡

‹‹የምን ችግር …?ጋሼ ግንኙነታችንን አወቀ እንዴ?››ከፊቷ መኮሳተር እና መገርጣት ከበድ ያለ ነገር እንደተፈጠረ የሚያሳብቅ ነው፡፡ለዛ ነው እንደዛአይነት ጥያቄ የጠየቃት፡፡

‹‹አይ አስከአሁን አላወቀም…››ቅዝዝ እንዳለች መለሰችለት፡፡

‹‹እስከአሁን አላወቀም ስትይ..?ምን ለማለት ነው?››

‹‹ሰሞኑን ሲያዞረኝና ሲያቅለሸልሸኝ ነበር ስልህ ሰምተሀል  አይደል?››

‹‹አዎ !!ምነው ባሰብሽ እንዴ?››

‹‹አይ ..ጤና ጣቢያ ሄጄ ነበር…››

‹‹እና ምን አሉሽ..?መድሀኒት አዘዙልሽ?››

‹‹አይ..አርግዤለሁ››

‹‹ምን ..?አርግዤለሁ››

‹‹አዎ አርግዤለሁ››

‹‹‹ወይኔ ጉዳችን..ከእኔ ነው አይደል?››ሲል እራሱን ይዞ በድንጋጤ አይኖቹን እንዳጉረጠረጠ ጠየቃት፡፡‹‹አዎ ካንተ ነው ያረገዝኩት…››ብትለው ምን እንደሚያደርግ አያውቅም፡፡ይሄ በህይወቱ የጋጠመው እውነተኛው ሰበር ዜና ነው፡፡

እሷ ግን እንደዛ አላለችውም፡፡‹‹እሱ ምን ያደርግልሀል…? የጠራሁህ ልጁ ያንተነው ወይም አይደለም ልልህ አይደለም ››

‹‹እና ለምንድነው?››

‹‹ከዛሬ ጀምሮ  ግንኙነታችን መቀጠል እንደማንችል እንድታውቅ ነው፡፡››ያላሰበውን ሁለተኛ መርዶ ነገረችው፡፡

‹‹ማለት …ምን አጠፋው?አቅጄና ፈልጌ አይደለም እኮ እንድታርዢ ያደረኩሽ››

‹‹እኔም እንደዛ አልልኩም…አንተ ምንም አላጠፋህም..ግን አሁን እንደምታየው ብቻዬን አይደለሁም …በማህፀኔ ልጅ ይዣለሁ…ለራሴ ሳይሆን ለልጄም ደህንነት መጨነቅ አለብኝ፡፡

እስከዛሬ ካንተ ጋር  የቆየሁት ስለማፈቅርህ ነው…ምንም ነገር ቢፈጠር እወጣዋለሁ ብዬ አስቤ ነው…አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል፡፡በልጄ ላይ እንደዛ ማድረግ አልችልም፡››

አለማየሁ ይሄ ቀን ለዛውም እንደዚህ በቅርብ ይመጣል ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር፡፡ይህቺን ሴት በጣም አፍቅሯት ነበር፡፡ከሰሎሜ ቀጥሎ ልቡ የደነገጠባት ሁለተኛዋ ሴት ነች፡፡

ወንድነትን ያጎናፀፈችው  ብቸኛዋ ሴት ነች፡፡በህይወቱ አይቶት የማያውቀውን ፍቅር አስኮምኩመዋለች፡፡ብዙ የደስታ ቀናትን እንዲያሳልፍ አድርገዋለች፡፡ በአለም ተወዳጁና ተፈቃሪው ሰው እንደሆነ እንዲሰማው አድርገዋለች..ይህቺን ልጅ እንዲህ በቀላሉ ‹‹በቃ እሺ እንዳልሺው ግንኙነታችንን እናቁም›› ሊላት አልፈለገም፡፡አዎ እሷ የተናገረቻቸው እያንዶንዷቹ ቃላት ከበሳል ሴት የተሰነዘሩና የፀነሰችውን ልጅ ደህንነት ብቻ ሳይሆን የእሱንም የወደፊት ህይወት አደጋ ላይ ላለመጣል አስባበት ያደረገችው ነው፡፡ለዛም እግሯ ስር ተንበርክኮ ሊያመሰግናት ይገባ ነበር፡፡ግን እንደዛ ማድረግ አልቻለም፡፡እንደውም በተቃራኒው ‹‹እባክሽ…ተረጋግተሸ አስቢበት…እኛ መለያየት የለብንም…ከፈለግሽም ተያይዘን መጥፋት እንችላለን፡፡››ሲል በአይኖቹ ጭምር እየተለማመጠ ተማፀናት፡፡
እሷ ግን የተናገረችውን ሁሉ ለቀናት አስባበት..አውርዳና አውጥታ  የወሰነችው ስለነበር ከአቋሟ ሽብርክ ልትል አልቻለችም‹‹እባክህ የምታፈቅረኝ ከሆነ ያልኩህን አድርግ….ሁለተኛ ቤት እንዳትማጣ… እንዳትደውልልኝ..መንገድ ላይ እንኳን ብታየኝ ልታናግረኝ እንዳትሞክር፡፡››ብላው እንባዋን እያንጠባጠበች…ለጠጡት ማኪያቶ ክፍያ የሚሆን ድፍን መቶ ብር ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ በተቀመጠበት ጥላው ሄደች፡፡

አለማየሁም ጓደኞቹ ግራ እስኪገባቸው ድረስ ለአንድ ወር ነበር ያዘነው፡፡ለሌላ የማይነግሩት የብቻ ሀዘን ደግሞ ውስጥን እንዴት እንደሚበላ የደረሰበት ነው የሚያውቀው፡፡በጣም ነበር የተጎዳው፡፡የሀዘኑ ምንጭ ከእሷ ጋር ያለው ግንኙነት ስለተቋረተ ብቻ አይደለም..እሱንማ ትክክለኛ ቀኑን አይወቅ እንጂ አንድ ቀን እንደሚሆን ከበፊቱ ያውቅ ነበር፡፡በጣም የጎዳው የተፈጠረው ሁኔታ ነው፡፡በመሀከላቸው ልጅ መፈጠሩ….ልጁ በተሳሳተ አባት እጅ ማደጉ….
በጣም የሚገርመው ደግሞ ከገባበት ደባሪ ሀዘን ሳይወጣ በተጨማሪ ሌላ ህይወት መንሸራተት ገጠመው ፡፡ የማትሪክ ውጤት ተነግሮ ከሁሴን በስተቀር እሱን ጨምሮ ሁሉም ጓደኞቹ ዝቅተኛ ውጤት ማምጣታቸው ታወቀ፡፡እርግጥ ከአራቱ ጓደኛሞች ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት  ሁሴን ብቻ ማምጣቱ  ከበፊቱም የሚጠበቅና ሚገመት ነበር፡፡ቢሆንም የቁርጡ ቀን መጥቶ ሁሉም በግልፅ ሲታወቅ ቅሬታ መፍጠሩ አይቀርም፤ቢሆንም ለዚህኛው ሀዘን አብረውት የሚያዝኑ ጓደኞች አሉት፡፡የእሱ  መከፋትን እነሱም ሚከፉት ስለሆነ እርስ በርስ ለመፅናናት ቀላል ነው፡፡እና እንደመጀመሪያው ችግር አልከበደውም፡፡
ሁሴን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ደግሰውና መርቀው ከላኩት በኋላ እነሱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መማከር ጀመሩ..እርግጥ ከበፊቱም ጀምሮ  አላዛር የራሱ ሱቅ ያለውና በንግድ የሚተዳደር ስለሆነ ከእነሱ በተለይ የሚፅናናበት እና ሚመካበት ነገር ስላለው ነገሮች ብዙም አላስጨነቁትም….አንድ ቤት እንደእህትና ወንድም የሚኖሩት አለማየውና ሰሎሜ ግን ምንም አማራጭ የላቸውም..በተለይ አለማየሁ ከገጠመው የፍቅር ስብራት ጋር አንድ ላይ ተጨማምሮ ተራራ የተሸከመ አይነት ስሜት ነበር እየተሰማው ያለው፡፡ ቢሆንም እንደምንም በጓደኞቹ ጎትጓችነት እንደምንም ከቁዘማ ወጥቶ ለገጠሙት ችግሮች መፍትሄ መፈለግ እንዳለበት በማመን መንቀሳቀስ ጀመረ….፡፡

በድንገት ወደህይወቱ ገብታ የፍቅር  አልኮል ስትግተው የሰነበተችው የጓደኛው የአላዛር የእንጀራ እናት ‹‹አርግዤለሁ እና ከአሁን ወዲህ አልፈልግህም ››ማለቷ ከፈጠረበት  ድባቴ መች ሙሉ ለሙሉ ማገገም እንደሚችል አያውቅም ፡፡ፈጽሞ ከአእምሮው ሊፍቀው የሚችል ሁኔታ አልሆነለትም፡፡በ19 አመቱ የልጅ አባት ከመሆኑም በላይ ከባለትዳር ሴት  መወስለቱ  በአሳዳጊው እቴቴ ዘንድ እንዲሁም በሚያፈቅራት በልጇ  ሰሎሜ ዘንድ  ምን አይነት ስሜት እንዲሚፈጥር እያሰበ እየተሳቀቀ ነው፡፡ደግነቱ ልጅቷ ለራሷ ደህንነት ስትል ሚስጥሩን ላለመናገር ወስናለች…በዛም የተወሰነ እፎይታ ተስምቷታል ፡፡ከአስካለ ጋር የነበረው አጭር ግን ደግሞ ጣፋጭ ፍቅር ግንኙነት በአጭሩ እና ባልሆነ መንገድ መቀጨቱ አሳዛኝ ቢሆንም አሁንም ዋናው የህይወት ህልሙ ሰሎሜ ስላለች ለእሷ በቂ ሰው ሆኖ መገኘት እንዳለበት አሰበ….ለዚህም ይረዳው ዘንድ እንደምንም ብሎ ትምህርቱን በመጠኑም ቢሆን ወደፊት መግፋት እንዳለበት ስለወሰነ...ከአላዛርና ከራሷ ከሰሎሜ ጋር በመመካከር ሶስቱም የሞያ ትምህርት ለመማር ተግባረእድ ኮሌጅ ተመዘገቡ…በዚህም የተወሰነ የመንፈስ  መነቃቃት አሳየ ….ትምህርቱ ከዛሬ ነገ ይጀመራል በሚል  ተስፋ መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ግን ደግሞ አንዳንዴ ሕይወት ከፊት ለፊታችን እንቅፋት መደርደር ከጀመረች
👍778👏2🔥1
በቀላሉ አታቆምም ..እኛ ጎንበስ ብለን በብዙ ድካምና ጥረት እንቅፋቱን ባነሳንበት ቅፅበት እሷ ልክ እንደተንኮለኛ ልጅ ከበፊቱ የሚተልቅ ሌላ እንቅፋት ከፊት ለፊታችን አንድ ሜትር ራቅ ትልና ታስቀምጥብናለች፡፡አለማሁም እየገጠመው ያለው ይሄ ነው፡፡እራሱን ለማጠንከር እና ትምህርቱን ቀጥሎ የውስጥ ብሶቶቹን ሁሉ ለመርሳት እየተፈጨረጨረ በሚገኝበት በዚህ ጊዜ  የሰሎሜ እናት እቴቴ‹‹ አለማየሁን እፈልግሀለሁ ፡፡››ብላ ከልጇ ከሰሎሜ ደብቃ ብቻውን ይዛው ወደቤተክርስቲያን ሄደች፡፡
ሁለቱም ተሳልመውና የግላቸውን ፀሎት ፀልየው ከጠናቀቁ በኃላ ቤተክርስቲያኑ ቅፅር ጊቢ ባለ ግዙፉ የዝግባ ዛፍ ስር ጎን ለጎን ተቀምጠው ማውረት ጀመሩ፡፡

‹‹ልጄ ..ለምን እዚህ እንዳመጣሁህ ታውቃለህ?››በልስልስ እናትነት ቃና ጠየቁት፡፡

‹‹እንዴት አውቃለው እቴቴ?››

‹‹ላመሰግንህ ነው..በፈጣሪ ፊት እግዜር ይስጥልኝ ልልህ ነው፡፡››

ያልጠበቀው ነገር ስለሆነ ደነገጠ‹‹እንዴ እቴቴ ምን አድርጌልሽ ነው እኔን ልታመሰግኚኝ የምትፈልጊው?››

‹‹ስላላሳፈርከኝ…የሞች ጓደኛዬን ቃል እንድጠብቅ ስላደረከኝ….››ብለው መለሱለት፡፡

‹‹እቴቴ ምንም እየገባኝ አይደለም››

አቴቴ ቦርሳቸው ውስጥ ገብተው በመሀረብ የተጠቀለለ እቃ  በማውጣት  አቀበሉት፡፡

‹‹ምንድነው?››

‹‹ፍታና እየው፡፡››

ፈታው…ሁለት የጣት ቀለበት..አንድ ጥምዝ ሀብል…አንድ ሴኮ ሰዓት …አንድ እጅ አንባር…ጌጣ ጌቶቹን እጆቹ ላይ እንዳሉ አፍጥቶ አያቸው፡፡

‹‹ምንድነው አቴቴ?››
‹‹የወላጆችህ ነው፡፡እናትህ ነች ከመሞቷ በፊት በአደራ የሰጠችኝ..እርግጥ የተወሰነ ጥሬ ብርም ነበር፡፡ብሩን ግን ወዲያው ነው አጎትህ ወንድምህን ለማሳደግ ሲወስደው ትንሽ እንዲያግዘው ብዬ የሰጠሁት…ይሄ ያንተ ድርሻ ነው፡፡አሁን ክፉና ደጉን የምትለይበት ዕድሜ ላይ ነህ፡፡አሁን ለራስህ መቆምና ችግሮችን መጋፈጥ ትችላለህ…በእነዚህ ጌጣጌጦች ምን ማድረግ እንዳለብህም መወሰን ትችላለህ…ለዛ ነው አሁን ልሰጥህ የወሰንኩት፡፡››

‹‹እቴቴ ምን እንደምልሽ አላውቅም….በጣም አመሰግናለሁ….››

‹‹እኔ ነኝ ማመሰግንህ…እናትህ በጣም ጥሩ ሰው ነች፡፡እንደእህቴ ነበር የምወዳት…እሷ ደግሞ አባትህን እንደነፍሶ ትወደው ስለነበረ ሞቱን መቋቋም አልቻለችም..እና ልትሞት ስትል  ‹‹ልጆቼን አደራ ቢያንስ ትምህርታቸውን እስኪጨርሱ ድረስ ተከታተያቸው ፡፡ባለሽ አቅም አግዢያቸው ››ብላኝ ነበር የሞተችው፡፡ያው ቃሏን ለመጠበቅና ልጆቾን እንደልጆቼ ለመንከባከብ ሙሉ ፍላጎት ቢኖረኝም እንደምታውቀው አቅሜ ግን ውስን ነበር…እና እንደሞተች ሰሞን ምኑን ከምን አድርጌ አንተንና ወንድምህን ማኖር እንደምችል ግራ ገብቶን ስጨነቅ ነበር..በዛ ላይ አያትህ ነበሩ፡፡በኃላ ግን አጎትህን እግዜር ይስጠውና ወንድምህን ወሰደው አያትህም በቃኝ ብለው ገዳም ሲገቡ እንደእኔ የተደሰተ ሰው አልነበረም…ቢያንስ የእናትህን ቃል በከፊልም ቢሆን ማክበር እችላለሁ…አንተን ከልጄ ከሰሎሜ ጋር ማሳደግ አይከብደኝም ብዬ ስላመንኩ…ደስ ብሎኝ የአንተን ኃላፊነት ሙሉ በሙሉ ተቀበልኩ፡፡በእውነት ከገዛ ልጄ እኩል ነው የምወድህ ፤ግን ደግሞ እየጎረመስክና እና እያደክ ስትመጣ በውስጤ አፈራ ነበር…ትምህርቱን ሳይጨርስ አንድ ቀን የሆነ ነገር ጎደለብኝ ወይም በሆነ ነገር አስከፋሺኝ ብሎ ቤቱል ጥሎልኝ ቢሄድስ? የሚል ከፍተኛ ስጋት ነበረኝ…ግን አላደረከውም፡፡ብዙ ነገር ቢጎድልብህም..ግን አንገትህን ደፍተህ ትምህርትህን እስክትጨርስ አብረኸን ቆይተሀል….እና ለጓደኛዬ የገባሁትን ቃል እንዳከብር አድርገህኛል ….አመሰግናለሁ፡፡

‹‹እቴቴ…እንዴት አንቺን ጥዬ ሄዳለሁ..አንቺ እኮ ከልጅሽ ከሰሎሜ እኩል ነው ስትንከባከቢኝ የነበረው…ለሁለታችንም ከምትችይው በላይ እያደረግሽልን ነው ያሰደግሺን…እኔ ምንም ነገር እንደጎደለብኝ ተሰምቶኝ አያውቅም…አንቺ እኮ ማድረግ ስትችይ ሰስተሸ ባታደርጊልን ወይንም ለልጅሽ አዳልተሸ ለእኔ ብታሳንሺ ጉድለት ይሰማኛ ነበር…ግን እንደዛ ሆኖ አያውቅም…ፍቅርሽና ርህራሄሽ ሁሉንም ጎዶሎዎቼን ይሞላልኝ ነበር..አንቺ ሳትሆኚ እኔ ነኝ ማመስገን ያለብኝ…ቤተሰቦቼም በህይወት ቢኖሩ እኮ ከዚህ በተሻለ ሊያሳድጉኝ እንደማይችሉ አውቃለው…እና አንቺ እናቴ ነሽ..አመሰግናለው፡፡የገዛ አያቴ እንኳን ሀላፊነት መሸከም አቅቷት አይደል ጥላኝ ገዳም የገባችው››

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014
👍628
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
==================
ተው በአያትህ አትፍረድ…ማንኛውም በቃኝ መመልኮስ ፈልጋለው ብሎ እራሱን ከአለም ለመለየት የወሰነ ሰው ማድረግ ያለበት ልክ እሷቸው እንዳደረጉት ነው፡፡የምልኩስና ህይወትን ለመንፈሳዊ መንገድ ራስን አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ከአለም ሆነ ከገዛ ዘመድ ምንም ነገር አለመጠበቅ ነው፡፡ከዛም አልፎ ለአለምም ሆነ ለገዛ ዘመድ ምንም አይነት ኃላፊነት አለመቀበል ማለት ነው፡፡አንድ ሰው ከመለኮሰ ልጄ ለምን ሳይጦረኝ ወንድሜ ለምን ሳይጠይቀኝ ብሎ የመጠየቅም ሆነ የመውቀስ  መብት የለውም..በዛውም ልክ እናቴን መጦር ነበረብኝ..ወንድሜን መርዳት ይጠበቅብኛል..የልጅ ልጆቼን መንከባከብ የእኔ ኃላፊነት ነው ከሚለው ማህበራዊ ኃላፊነቶችም ራሱን ነፃ ማድረግ አለበት፡፡
ሙሉ ትኩረቱ መንፈሳዊ ብልፅግና እራስን ማጎልበት ላይ  መሆን አለበት፡፡ለዘመዱም ሆነ ለመላ አለሙ እኩል ፀሎት ማድረግ ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ስለክርስቶስ ፍቅር መትጋት ፤ዳቢሎስ ለመጥላትና ለመርገም ግን ጊዜ ከማባከን መቆጠብ ነው ከእነሱ የምጠበቀው…ምክንያቱም በአንድ ንፅህ ልብ ፍቅርና ጥላቻ እውነትና ሀሰት ክፋትና መልካምነት ተጎራብተው መኖር አይቻላቸውምና፡፡ሁለቱንም አቻችሎ እያኖረ ያለ ልብ የመንፈሳዊ ሰው ልብ ሊባል አይችልም፡፡እና በአያትህ ውሳኔና ድርጊት ቅንጣት ያህል ቅሬታ እንዳያድርብህ ..እንደውም በተቃራኒው በረከታቸው እንዲጠብቅህ ብቻ ነው መመኘት ያለብህ››
‹‹ትክክል ነሽ እቴቴ…ለማንኛውም አንቺን ደጋግሜ አመሰግናለሁ››
‹‹እኔም አመሰግናለው ልጄ….ይሄ ፀባይህ መቼም እንዳይቀየር .አሁን ምን ማድረግ እንዳለብህ የምትወስነው አንተ ነህ…እንደእኔ እንደእኔ ኮሌጅ ገብተህ  የሙያ ትምህርት ለመማር በመወሰንህ በጣም ጥሩ ነው…ሞያ ያለው ሰው ወድቆ አይወድቅም…ቢያንስ የሆነ ተባራሪ ስራ ሰርቶ ወይም የሆነ ነገር ጠጋግኖ የእለት ጉርሱን ያገኛል..ቀስ እያልክ ደግሞ በሂደት የራስህን ድርጅት የማቋቋም እድልም ይኖርሀል….እና እኔ እናትህ  ሁሌም በውሳኔህ አብሬህ ነኝ፡፡››
‹‹አቴቴ አታስቢ ከሰሎሜና ከአላዛር ጋር ተነጋግረን ወስነናል…የሆነ ሞያ እንማራለን ››
‹‹ጎሽ ልጄ እንደዛ ነው…ሰሎሜንም ስለምትንከባከባት አመሰግናለሁ››
‹‹እንዴ እቴቴ እህቴ አይደለችም እንዴ?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…እንደውም ትልቁ ላመሰግንህ የሚገባው እሷን በተመለከተ ነው…እናንተ ላትሰሙ ትችላላችሁ ፡፡ከጎረመሰችና ለአቅመ አዳምና ሄዋን ከደረሳችሁ በኃላ የሰፈሩ ሰው በሰበብ አስባብ እያደረገ…‹‹ይሄ ጎረምሳ ልጇን አስረግዞ ጉድ ያደርጋታል….››ሲሉኝ፡፡‹‹እንዚህ ልጆች እንዳይሳሳቱና አጉል ችግር ውስጥ እንዳይከቱሽ›› እያሉ  ሲመክሩኝ፡፡እኔ ግን ከልጄ ይልቅ በአንተ ላይ ሙሉ እምነት ነበረኝ…አለማየሁማ እኔ እናቱን እንዳፍርና አንገቴን አንቄ እራሴን እንዳጠፋ አያደርገኝም….የገዛ እህቱን  የሆነ ነገር አድርጎ የሰፈርተኛውን ሟርት  እውን በማድረግ እኔ እናቱን ወደመቃብር አይልከኝም››የሚል ፅኑ እምነት ነበረኝ፡፡እናም ቤተክርስቲያን ስሄድ ጌታ ሆይ ለሁለቱም ልጆቼ ልቦና ስጥልኝ ብዬ ከመፀለይ ውጭ በእናንተ ላይ ምንም አይነት ተፅእኖም ሆነ ክትትል አድርጌ አላውቅም ፤ወደፊትም ስለማምናችሁ ስጋት የለብኝም…እና ለዚህም አመሰግናለው፡፡
አለማየሁ አቴቴ ስለእሱና ስለሰሎሜ  እያንዳንዱን ቃላት ከአንደበታቸው አውጥተው በተናገሩት ቁጥር ከልቡ የተወሰነ አካሉ እየተሸራረፈ ሲረግፍ ይታወቀው ነበር..በቃ የአላዛር የእንጀራ እናት ከቀናት በፊት የሰነጣጠቀችው ልቡን አሁን ሙሉ በሙሉ ተሰባበረ፡፡ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለቱም የፍቅር ክንፎቹ ተቆርጦ ሲወድቅበት ..መቋቋም ከሚችለው በላይ ፍፅም ተስፋ  መቁረት ውስጥ ነው የገባው፡፡‹‹እቴቴ ..ይሄን ሁሉ ሰቀቀን ስላሳለፍሽ ቅርታ….አይዞሽ አታስቢ …እኔ ልጅሽ ነኝ ልጅሽም እንደሆንኩ እቀጥላለሁ፡፡››ሲል  ነበር በደመነፍስ ቃል የገባላቸው፡፡
በዚህ ሁኔታ ነበር ሁለቱም ተመሰጋግነውና ተላቅሰው ከቤተክርሰቲያን የተመለሱት፡፡
ከዛ በኃላ ግን አለማየሁ ሁሉም ነገሩ ነው የተመሰቃቀለበት፡፡ማትሪክ ውጤት አይቶ ዩኒቨርሲቲ መግባት እንደማይችል ያወቀ ሰሞን እንኳን እንዲህ መላ ነገሩ አልተተረማመሰም፡፡ከአላዛር እንጀራ እናት በተለያየበት ቀንም የተወሰነ የሚመረኮዘው ተስፋ ነበርው…ከቴቴ ጋር ካወራ በኃላ ግን  በቃል ታስሮል….ከሚወዱትና ከሚያከብሩት ሰው አንደበት የወጣ ቃል ደግሞ ከፖሊስ ካቴና የጠበቀ ቀፍድዶ የሚያስር ነው፡፡አሁን ለአስራዘጠኝ አመት ሲንከባከበውና ሲፋለምለት ከነበረው የፍቅር ሀዲድ ተገፍትሮ ወጥቷል…፡፡የሰሎሜን ፍቅር ከልቡ አውጥቶ በአንደበቱ ማወጅ አይችልም…፡፡እንደዛ ካደረገ እናቷን ማሳዘን አንገት ማስደፋት እንደሆነ ገብቷታል፡፡ከሁለት አንዱን መምረጥ ያለበት ጊዜ ላይ እንደሆነ አውቆል፡፡
ልክ የሀይስኩል ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቀ. ለሰሎሜ ያለውን ፍቅር  ለማፈንዳትና እሷን ከተቀናቃኞቹ ሁሴንና አላዛር ፈልቅቆ ራሱ ለማድረግ የአመታት እቅድ ነበረው…ያ ቀን እስኪደርስ  በመመኘት ብዙ ቀን እንቅልፍ አጥቶል፡፡ በስንት ጣር ቀኑ ሲደርስ ግን እናቷ ያልጠበቀውን ዱብ እዳ ነገሩት፡፡እሱ እንደውም ይሰጋ የነበረው እንዲህ አይነት ነገር ተፈጥሮ ከሰሎሜ ፍቅር ይነጥለኛል ብሎ ሳይሆን  ከአስካለ ጋር የነበረው የድብቅ ፍቅር ሰሎሜ ጆሮ ገብቶ እሷን ያሳጣኝ ይሆን ብሎ ነበር፡፡
ግን ይሄው ጨርሶ ባልጠበቀው መንገድ አሳዳጊ እናቱ እቴቴ እሱና ሰሎሜ በእህት እና ወንድም ስሌት እንዲቀጥሉ እንጂ ፍቅር የሚባል ነገር በመሀከላቸው እንዲበቅል ምንም ፍላጎት እንደሌላቸውና እንደውም እስከሞት ሚያደርስ ሀዘን ላይ እንደሚጥላቸው ግልፅ ባለ አማርኛ ነገርውታል፡፡
እሱ ብቻ ሳይሆን የገዛ ጓደኞቹ አላዛርና ሁሴንም እንደሚያፈቅሯትን  በቅርብ በማንኛውም ጊዜ ፍቅራቸውን እንደሚናዘዙላት ያውቃል፡፡ለዚህ ቃል ኪዳን አላቸው፡፡ሶስቱም እሷን እንደሚያፈቅሮት ስለሚያውቁና እርስ በርስም ለዘመናት ሲነጋገሩና ሲወያዩ በመኖራቸው…‹‹.ስንጠይቃት ለየት ያለ ዝግጅት አዘጋጅተን..ሶስታችንም በአንድ ቃል..ሰሎሜ እኛ ሶስቱ ጓደኞችሽ አንቺን ከልጅነታችን ጀምሮ እናፈቅርሻለኝ… ሶስታችንም የእኛ እንድትሆኚ እንፈልጋለን፡፡አንቺ ከሶስታችንን ማንን ትመርጫለሽ…?በውሳኔሽ እንስማማለን፡፡አስበሽበት ከሶስታችን ማንኛችንን እንደምትመርጪ አሳውቂን ››ብለው ሰርፕራይዝ ሊያደርጓትና  የመምረጡን እድል ለእሷ ሊሰጡ ገና ዘጠነኛ ክፍል እያሉ ነበር ቃል የተገባቡት፡፡

እና ከእቴቴ ጋር ከማውራቱ  ከሳምንት በፊት በሁሴን ሽኝት ላይ ይሄንን ጉዳይ  አንስተው ደግሞው ተነጋገርውበት ነበር፡፡ሁሴንም‹‹በቃ አንድ ሴሚስተር ተምሬ ከጨረስኩ በኃላ በሴሚስተር ዝግ ስመጣ  እንደተባባልነው እናዳርጋለን›› ብሏቸዋል…እነሱም በሀሳቡ ተስማምተው ነበር፡፡ እስከዛ ማንም አፈቅርሻለው ብሎ እንዳይነግራት ተማምለው ከእንደገና ቃላቸውን አድሰው ነበር፡፡እና በዚህ ሁሉ ውይይትና  ንግግር ሰሎሜ አሱን እንደምትመርጥ ከእነሱ በላይ ሰባና ሰማኒያ ፐርሰንት እድል እንዳለው ያምን ነበር..እንደዛ እንዲያስብ ያደረገው ደግሞ ከጓደኝነታቸውም በላይ እንደእህትና ወንድም አንድ ቤት በመኖራቸው..ቀን ብቻ ሳይሆን ምሽትም ለሊትም አንድ ቤት ውስጥ ስለሚሆኑ …ታፋው ላይ ያለውን ጠባሳ ስለምታውቅና ከጡቷ ዝቅ ብሎ ያለውን  የማሪያም ስሞሽ ሰልሚያውቅ…ጭምር ነበር የእሷ ተመራጭ  እሱ እንደሚሆን እርግጠኛ የሆነው፡፡
👍6810
ቢሆንም አለማየሁ ከእዛ ግሩፕ ሳይወድ በግድ እየመረረውም መገንጠል እንዳለበት ወሰነ…ያንን ለማድረግ ደግሞ ከዛን በኃላ ከእሷ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ እየኖረ አብሯት እየወጣ እየገባ መጪዎቹን ሶስት አራት አመታት ማሳለፍ የማይታሰብ ሸክም ነበር የሆነበት….ከዛ ቤት ወጥቶ ደግሞ በዛ ሰፈርም ሆነ በከተማው መኖር አይችልም..አንደዛ ማድረግ ለአመታት ለእሱ ሲሉ የከፈሉለትን መስዋእትነትና የዋሉለትን ውለታ እንደመካድ ነው የሚሆንበት፡፡እና ከዚያ ስፍራ  በሰላም ድምፅን ሳያሰማ ሹልክ ብሎ የሚጠፋበትን መንገድ ማሰላሰል ጀመረ…፡፡መጀመሪያ ወደውጭ መሰደድ የሚል ሀሳብ ነበር ብልጭ ያለለት…ከሀገሩም ከፍቅሩም እስከወዲያኛው መሸሸ..ለዚህ ጉዳይ ሲሯሯጥ ድንገት ለፖሊስ በምክትል መቶ ሀለቅነት  ማዕረግ አሰልጥኖ ለማስመረቅ የወጣ መሳታወቂያ አነበበ…ወዲያው መረጃዎቹን ሰበሰበና ሄዶ ተመዘገበ…
የትምህርት ማስረጃው ብቻ ሳይሆን የእድሜው ለጋነትና ፈረጣማ የሰውነት አቋሙም የሰጠ ስለሆነ በቀላሉ ማጣሪያውን አለፈ፡፡
ከዛ ከእናቱ በውርስ ካገኛቸው ጌጣጌጦች ውስጥ አንድን ሀብል አነሳና ከአጭር መልእክት ጋር ለሰሎሜ ትቶላት  ወደፖሊስ ማሰልጠኛ ተቋም ገባ…
ማስታወሻው ‹‹…ይሄ ከእናቴ የተሰጠኝ ማስታወሻነው..እኔ ደግሞ ለአናቺ ሰጠሁሽ..እቴቴን ተንከባከቢያት እሺ…በዚህ ሁኔታ ስለተለየሁሽ አዝናለሁ…እህቴ አንቺንም ሆነ እቴቴን  በጣም ነው የምወዳቸሁ ››
ይላል..፡፡ሰሎሜ ማስታወሻውን ስታነብ ሰማይ ምድሩ ነው የተገለባበጠባት‹‹እንዴት እንዲህ አይነት ውሳኔ ወሰነ…?እንዴት አስቻለው?ምን አድርጌ ነው ያስቀየምኩት?ነው ከእቴቴ ጋር ተጣልቶ ይሆን?››በእነዚህና በርካታ ጥያቄዎች እራሷን ስታስጨንቅ ከረመች…ከእሷ የተለየ የሚውቁት ነገር ካለ ብላ እናቷንና አላዛርን በተደጋጋሚ ጊዜ በጥያቄ ብታጣድፍቸውም ጠብ የሚል መልስ ማግኘት አልቻለችም፡፡ስልኩ ላይ ደጋግማ ብትደውልም ሊያነሳላት አልፈቀደም፡፡

     💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍515
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አራት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

አይንሽን ላፈር

አይ! ሰው ለሰው ሞት አነሰው ብላ የተረተችው ቀበሮ ወዳም አይደለም፡፡ ለካ ለሁሉም የሚተረትለት ችግሩ በቤቱ ሲደርስበት ኖሯል፡፡ ለነሱ ብዬ ስሜ በማንም አፈኛ በየገብያውና በየቤቱ ይነሳል፡፡ እቤት ተዘፍዝፋ ባሏ ዲቃላ ያንጠባጥባል፡፡ ምን አይነት ግፍንት ነች እየተባልኩ የማንም መሳቂያና መተረቻ ልሁን? ከሰውም ጋር ባይሆንም ከራሷ ሃሳብ ጋር ያወራችው ነበር ፡፡

ስሙን ሳነሳሳና ሳማው መጣ እንዴ? ከውጭ በኩል አበበች የሚል የወንድ ድምፅ ሰምታ ተመስገን መስሏት ነበር፡፡ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወጣች፡፡

ግን ተመስገን ሳይሆን ወላጅ አባቷ አቶ አሸናፊ ነበር፡፡

"ደህና አረፈዳችሁ"? አለ ፤ አቶ አሸናፊ፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አረፈድህ አባባ ፤ ግባ ወደ ቤት" አለች፡፡

ወደ እቤት እየገቡ "ያሬድ የለም እንዴ"? አለ፡፡

"የለም፤ በጥዋት መጣሁ ብሎኝ እንደ ሄደ አልተመለሰም፡፡ የሄደበትንም አልነገረኝም፡፡ ምነው ደህና አይደለህም?፡፡

"እኔስ ደህናነኝ፡፡ ከብቶቹ እፀሃይ ላይ ታስረው ሳይ ለምን አልፈታቸውም ብዬ ነው"፡፡

"እኔም ብዬ አሁን ነበር የሚበላ የሰጠኋቸው፡፡ ውሃ ጠምቷቸው ነው መሰለኝ አልበሉትም፡፡ እሱም ውሃ እንዳያጠጣቸው ብቅታውም ጠፋ፡፡ ወይ እቆያለሁ አጠጫቸው እንኳን አላለኝ፡፡ ቶሎ እንደሚመለስ ሰው ሳይነግረኝ መሔዱ አለች፡፡

"መቼ ጉዳይ ብሎ ነው፡፡ ከብት አጠጥቶ የሚያውቀው፡፡ አንዴ ነጋዴ ነኝ ፤ አንዴ ባለጉዳይ ነኝ
እያለ ፤ መንደር ለመንደርና ከተማ ለከተማ እያሽካካና እየዞረ አላት፡፡

"እንዴው እቤት ካለ ብዬ ነው እንጂ ለማጠጣቱማ አዲስ አይደለሁም፡፡ አሁን ለአንተ ቡና ላፍላና አጠጣቸዋለሁ፡፡

"እኔ ቡና አልጠጣም፡፡ አታፍሊ ፡፡

"ለምን አትጠጣም? ምነው ደህና አይደለህም? እንዴ አለችው፡፡ አባቷ ተኮሳትሮ መናገሩ አስፈርቷታል፡፡

አቶ አሸናፊ በሚወራው የሰፈር ወሬ ማንነቱን ያስደፈረው ይመስላል፡፡ ወደ ልጁ ቤት የመጣው እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ለበጎ ሳይሆን ለነገር እንደመጣ በፊቱ ላይ የሚነበበው የመኮሳተር ምልክት የሚያስይ መሆኑ ጥርጥር የለውም ነበር፡፡

"አንቺ ወራዳ ፤ አንቺ ተዋርደሽ እኔንም አዋረድሽኝ፡፡ ባልሽ አንቺን የቤት ገረድ አድርጎ ዲቃላውን በሔደበት ይፈለፍላል፡፡ ከሰማሽ በኋላ፤ እንኳን ጥለሽ መምጣት አቅቶሽ ነው" አለ፡፡ በዱላ እንደ መምታት ያህል በሚሰማ ንግግር፡፡

አበበች የፈራችው አልቀረም፡፡ በትዳሯ ላይ እሳት ሲለኮስ ታያት፡፡ የአባቷ ንግግር ከያሬድ ጋር እንድትቀጥል የሚፈልግ አይመስልም፡፡ ለተመስገን እሽ ያለችበትን ቀን አምርራ ብትረግምም ያቺን ቀን ግን ተመልሳ ልታገኛት አልቻለችም፡፡ መልስ ሳትሰጥ አይኞቿ በእንባ ተሞሉ፡፡

"አሁን ምንድ ነው ሃሳብሽ ? የባልሽ ገረድ ሆኖ መቀጠል ይሻላል?፡፡ ወይስ ለቆ መውጣት ይሻላል?፡፡ መነፋረቁን ትተሸ ተናገሪ አለ፡፡ አሁንም ቁጣና ንዴት በተቀላቀለበት ንግግር፡፡

"አባባ የማታውቀው ነገር ስላለ እኮ ነው ብላ..

"የማላውቀው ምንድ ነው ባክሽ?፡፡ ከቄስ መልካሙ ልጅ ባልሽ መውለዱን ነው፤ የማላቀው? ወይስ በማንም ጨምላቃ አፍ በየቡና ቤቱ ላይ በአንች የተነሳ ስሜ መነሳቱን ነው የማላውቀው?፡፡ ለነገሩ እኔ የተዋረድኩት ዛሬ ሳይሆን አንቺን የወለድሁ ቀን ነው አላት፡፡

ሚስጥሩን ለአባቷ ለመንገር ብትፈልግም አባቷ ግን ምንም አይነት ምክንያት የሚቀበል አይደለም፡፡

"ትዳሬን እንዴት ባልሰራሁት ለቅቄ እሄዳለሁ?

ልጄን ያለ አባት ማሳደግ አልፈልግም፡፡ ነገ እውነቱ ሲወጣ ጥፋተኛ ማን እንደሆነ ያኔ ታውቃለህ አለች፡፡ ደፍራ በመናገሯ አይኑን ላለማየት ወደ መሬት አቀርቅራ፡፡

አቶ አሸናፊ የባሰ በንዴት ቆሽታቸው አረረ፡፡ አንች ወራዳ አታፍሪም ደግሞ ነገ እውነቱ ይወጣል ስትይኝ?፡፡ አንገታቸውን እየነቀነቁ አይ! አለመታደል ይሄ! ልክስክስ ባልሽ ካዋጣሽ ከዛሬ ጀምሮ! ልጄ! አይደለሽም፡፡ ብሞትም እንኳን ከመቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ፡፡ ብሏት፤ የወለዳትን ልጅ ረግሞ እንዳልወለዳት ልጄ አይደለሽም ብሎ እያለቀሰች ትቷት ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

ታዲያ አበበች ስታለቅስ አይን አይኗን እያዬ የሚቁለጨለጨው ልጇ ለተመለከተው ከሷ ለቅሶ ይልቅ የልጇ አይኖች ሲንከራተቱ ያስለቅሱ ነበር፡፡

"ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው"? አለ ፤ ያሬድ፡፡ ባለቤቱን ጥዋት ትቷት ሲወጣ ደህና ብትሆንም ሲመለስ ግን እያለቀሰች ስላገኛት፡፡ በምን እንደምታለቅስ ግራ ገባው፡፡ ልጁን ከእቅፏ ላይ አንስቶ ታቀፈው፡፡ ባየው ነገር ሆዱ ባባ፡፡ ከየት መጣ ሳይባል እንባ ከአይኖቹ ተንጠባጠቡ፡፡

የተፈጠረውን ለማውቅ ደግሞ "ምንድ ነው የሆሽው? ለምን አትነግሪኝም? አለ ፤ እንደ መቆጣት ብሎ፡፡

አበበች እንባዋን እየጠራረገች አባባ አሁን መጥቶ ነበር አለች፡፡

"ታዲያ ምን አሉሽ ?፡፡

"ምን ይለኛል፡፡ ያው እየፈራን ላደረግነው ነገር አይንሽን ለአፈር አለኝ፡፡ አንቺ የባልሽ ገረድ ሆነሽ ባልሽ ዲቃላውን ይፈለፍላል፡፡ አሁን ባሌ ይሻለኛል ካልሽ ከዛሬ ጀምሮ ልጄ አይደለሽም፡፡ ብሞት እንኳን ከመቃብሬ ላይ እንዳትቆሚ ብሎኝ እያለቀስኩ አሁን ነው ጥሎኝ የወጣው፡፡

"ሚስጥሩን ነገርሻቸው እንዴ"?፡፡

"እኔ ልነግረው አስቤ ነበር፡፡ እሱ ግን የሚሰማኝ ስላልመሰለኝ አልነገርኩትም፡፡

"ድሮም እግዚአብሔርን ብለን እንጅ ይሄ እንደሚመጣ እያወቅን የገባንበት ነው፡፡ አሁን እውነቱ
እስከሚወጣ ድረስ የምናደርገው ምንም አይኖርም፡፡

ሚስጥሩ መውጣት ያለበት የእነሱም ቤተሰቦች የእኛም ቤተሰቦች ተሰብስበው ነው፡፡ እኔም ትላንትና አልነገርኩሽም እንጅ ከገበያ ስመጣ ወንድምሽ ከመንገድ አድፍጦ ሊገለኝ ሲል እሮጨ ነው ያመለጥኩት፡፡ ሁሉም ነገር ጥፋቱ የእኔ እስከሆነ ድረስ በእነሱ የምይዝባቸው ቂም የለኝም፡፡ ከአሁን በኋላ፤ እናትሽም ቢመጡም ሚስጥሩን እንዳትነግሪ፡፡ ምክንያቱም ወሬው በውጭ ከተወራ ተመስገንና እድላዊት ራሳቸውን ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡ እነሱ ከሌሉ ሁሉም ነገር ጨለማ ለብሶ ሳይገለጥ ተዳፍኖ እንዳይቀር ጥንቃቄ ያስፈልገናል፡፡

ወዶዘማች

ወደ ጠጁ ቤቱ ጎራ አለ፡፡ አንድ ብርሌ ጠጅ አዘዘ፡፡ ሁለት አውቶቢስ አንድ ሚኒባስ ከላይዋ ላይ ድምፅ ማጉሊያ ጭና ከፊት ለፊት ቀድማ ትከንፋለች፡፡ የአስረስ ሽለላና ቀረርቶ በከፍተኛ ድምፅ ተለቋል፡፡ የአረርቲ ከተማን ከዳር እስከ ዳርም አናውጧታል፡፡ ታዲያ ሽለላና ቀረርቶው በጥቂቱ እንዲህ ይል ነበር፡፡

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

እንኳን በለው ብለው ልከው ሰደውት፤

ከወገብ ላይ ሆኖ ያኮራል ጥይት፡፡

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ከአፈሙዙ ዘቅዘቅ ከሰደፉ ቀና አድርገው የተኮሱ እንደሆን፤

ጥይት ሰው አይፈራም ምን ደንደሳም ቢሆን፡፡

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ዘሩ የመርዙ ትውልድ፤

አምሶ ይቀብራል እንደ እሳት ሰደድ፤

ኧረ ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ሀገሬ ኢትዮጵያ ኩሪ ይገባሻል፤

የማያስደፍሩ ጀግና ልጅ ወልደሻል፡፡

ኧረ ጎራው ኧረ መርዙ፤

አገሬን ኢትዮጵያ እሳት ይዞረዋል፤

ለመጥፋት ነው እንጅ ምን ይሻገረዋል፡፡

ገዳይ ኧረ ገዳይ፤

ዘራፍ የተጎረፈው በጠመንጃው ፊት ሰው የማያልፈው፤ ሳይነካኳቸው እየደረሱ ይመለሳሉ እየቀመሱ ፤

ታንክ ቢያሽካካ መድፍ ቢያጓራ፤

የሚጋፈጠው በሮ እንደ አሞራ፡፡….

ከአስረስ ሽለላና ቀረርቶ በተጨማሪ ጋዜጠኛ ገረመው ይታያል እሱም እንዲህ ይል ነበር፡፡
👍529
"ሃገራችን ኢትዮጵያን ጥንት አባቶቻችን ፣ የፖርቹጋልንና የጣሊያን ወረራ ያለ ዘመናዊ መሳሪያ ፣ በጦር ፣ በጎራዴ ፣ ተዋግተው ማንነታችንንና ሉዓላዊነታችንን አስከብረዋል፡፡

ዛሬ ደግሞ የመቃብር አፈራቸው እንኳን ሳይሟሽሽ እብሪተኛው የሻቢያ ጠላት ትላንት ከጓዳችን እንዳልወጣ ሉዓላዊነታችንን ለመድፈር ጦርነት አውጆብናል፡፡ እንዴት! የጀግና መፍለቂያ ኢትዮጵያን የመሰለች ሃገርን ይዘን እንደፈራለን?፡፡ እንኳን ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቀን፤ ገና ከሩቅ እንደካሜራ አጉልቶ የሚያሳይ መሪ ይዘን ትጥቃችን ሳይላላ ለመጣብን ጠላት በድንጋይ በዱላ….

የአስረስ ሽለላላ ፣ ቀረርቶ እና የጋዜጠኛ ገረመው ይታያል እልህና ቁጭት የተቀላቀለበት የቅስቀሳ ንግግር እንኳን ቆሞ ለሚንቀሳቀስ ኢትዮጵያዊ አይደለም በእናታቸው መሀፀን ውስጥ ሆነው ለመውጣት የሚፈራገጡ ህፃናትና ከመቃብር ሙታንንም ይቀሰቅስ ነበር፡፡

ሽለላውና ቀረርቶው ልቡን ለሁለት ከፋፍሎት ግራ ተጋብቷል፡፡ ባለቤቱና ልጁን ያለ ዘመድና ያለ አሳዳጊ የቀሩ መሰለው፡፡ የያዛትን አንድ ብርሌ ጠጅ ጨለጣት፡፡ አስተናጋጁን ድገመኝ እስቲ፡፡ ከጠጡ አራት ከመቱም አናት፡፡ እንደሚለው የምንጃር ልጅ አባባል፡፡ አራት እንኳን ባልጠጣም ለጥሩም ለክፉም አንድ አይጠጣምና ሁለት ላድርገው አለ ፤ ያሬድ፡፡ ጠጁን አስደገመ፡፡ ጎንጨትም አለው፡፡ ሃሳቡ ሁሉ ተምታቶበታል፡፡ መወሰን አልቻለም፡፡

"በህይወት እያለሁ አገሬ ኢትዮጵያን ማነው የሚነካት የለም ፡፡ ንብረትና ልጆቸን ነገ አገኛቸዋለሁ፡፡ ከተሰዋሁም ለሃገሬ ነው፡፡ እኔ እንኳን ብሞት ስሜ እስከ ዘላለም አይሞትም፡፡ እየሸለሉና እየፎከሩ አንደኛው አውቶቢስ ውስጥ ዘለው ገቡ፡፡ ከጠጁ ቤት ነበር፡፡ በግምት አንድ ሃምሳ ዓመት ገደማ የሚሆናቸው ሽማግሌ ናቸው ዘለው የገቡት፡፡

እኔስ ከማን አንሳለሁ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም አለ በውስጡ፡፡ የያዘውን ጠጅ ከብርሌው ውስጥ አልጨረሰም፡፡ ተነሳ እናት አገሩን ለማስከበር ኢትዮጵያዊነት ክብሩ ቀሰቀሰው፡፡ ኢትዮጵያዊነት ከምንም በላይ ሆነበት፡፡ አውቶቢሱ ሞልቶ ተጨናንቋል ፡፡ እንደ ምንም ተገፋፍቶ ወደ ባሱ ገባ፡፡ ጉዞውም ወደ ጎጃም ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ሆነ፡፡

ታዲያ ባጋጣሚ ነበር፡፡ ከአጎቱ ልጅ ጋር ገበያ እንደሄዱ ወደ ቤታቸው ለመመለስ የገዙትን እቃ አህያ ላይ ከጫኑ በኋላ፤ ያሬድ እቃ እረስቶ ወደ ገበያ እንደተመለሰ በዛው ወዶ ዘማች የገባው፡፡

በጎጃም ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ለሶስት ወር ስልጠና ሰልጥኖ ተመረቀ፡፡ ማሰልጠኛ ት/ቤቱ ባወጣው ምደባ መሰረት በምዕራብ ትግራይ ፣ በ108ኛ ኮር ፣ በ22ኛ ንስር ክ/ጦር ፣ በ2ኛ ብርጌድ ፣ በ4ኛ ሻለቃ በ3ኛ ሻምበል ፣ በ2ኛ የመቶ እና በ4ኛ ቲም በ1992 ዓ/ም መስከረም ሰባት ቀን

አዲ ሃኪም የሚባል ቦታ ከነባር ታጋይ ሰራዊቶች ጋር የተቀላቀለው፡፡

አዲስ የገቡ የሰራዊት አባላትን ከነባር ሰራዊት ጋር ለማዋሃድ ተጨማሪ የውጊያ ልምምድ ማድረግ ወታደራዊ ሳይንስ ነው፡፡

ያሬድ የብሬን እረዳት ሆኖ ተመደበ፡፡

ከአንድ ሳምንት በኋላ፤ ከአዲ ሃኪም ተነስተው ወደ ደምበ ጨፈቃ ተጓዙ፡፡ ለሁለት ወር ከ15ቀን ከፍተኛ የስልጠና ልምምድ ተደረገ፡፡ ከደምበ ጨፈቃ ወደ አፅርጋ በመጓዝ ለውጊያ የሚያበቃቸውን የመጨረሻ የስልት ልምምድ ተደርጎ አሁንም ከአፅርጋ ወደ ዛግር አቀኑ፡፡ ለተወሰነ ቀን እረፍትና ለውጊያ የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን አዘጋጁ፡፡

በ1992 ዓ/ም ግንቦት ሁለት ቀን እብሪተኛውን የሻቢያን ጠላት ለማጥቃት ከዛግር ተነስተው ጉዞ ወደ ትኩል ተጀመረ፡፡

ግንቦት ሶስት ቀን 1992 ዓ/ም መረብን ሳይሻገሩ ማይ አባይ በሚባል ወንዝ ላይ ተጉዘው አረፉ፡፡ መረብን ተሻግረው ትኩል ላይ ለሚደረገው የማጥቃት ውጊያ ከሌሊቱ 10 ሰዓት እንደሆነ ለሃይል አመራሮች ተነገረ፡፡ የውጊያ ሰዓት እስከሚደርስም ቦታ ቦታቸውን ይዘው እንዲጠብቁ በአራተኛ ሻለቃ ዋና አዛዥ ቀጭን ትእዛዝ ተሰጠ፡፡

ጉዞው አድክሞታል፡፡ በሃሳብ ሰመመን ከባለቤቱና ልጁ ጋር ቅልጥ ያለ ጭዋታ ይዟል፡፡ ምን እንደተባለ አልሰማም፡፡ ያሬድ ከሄደበት የሃሳብ ሰመመን ባነነ፡፡ ግራና ቀኝ ተመለከተ፡፡ ከስሩ የተቀመጡት ሌላ አሃድ ናቸው፡፡ በድንጋጤ ተደናበረ፡፡ ተነስቶ እየተደናበረ ሲሮጥ ሃይሏ አገኛት፡፡ ጋንታ መሪውና ቲም መሪው የት ሄደህ ነው እያሉ ጮሁበት፡፡ ያሬድ ግን በድንጋጤ የተነሳ የጮሁበት አይደለም የተናገሩት አልመሰለውም ነበር፡፡

1992 ዓ/ም ግንቦት ሶስት ቀን ከምሽቱ አምስት ሰዓት የጀመረ ዝናብ ከፍተኛ ጎርፍና ንፋስ እየቀላቀለ ሳያባራ ለአራት ሰዓታት ያክል ዘነበባቸው፡፡ ሌሊት 10 ሰዓት ሬድዮ አመራሮች ተገናኙ፡፡ ማታ በተሰጠው የውጊያ ትእዛዝ መሰረት ጉዞዋቸውን የሻቢያ ጠላት መሽጎበት ወደሚገኘው ትኩል አቀኑ፡፡

ሲዘንብ ያደረው ዝናብ መረብን አፍ እስከ አፍንጫው ሞልቷል፡፡ ሁለተኛ የሻቢያ ጠላት ሆኗል፡፡ ከግራ እና ቀኝ እየተላተመ ይደነፋል፡፡ ለመሻገር የሚያስጠጋ አይመስልም፡፡

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አንተን ፈርተንማ ግዳጃችን አይደናቀፍም፡፡ ብለው ተመሙ፡፡ ለመሻገር ከመረብ ጋር ግብግብ እና ትንቅንቅ ተያያዙት፡፡

የመረብ የውሃ ሙላት የደነፋው አልቀረም፡፡ አንድ ሰራዊት ወሰደ፡፡ ሁለት ሠራዊቶችን ያሬድን ጨምሮ አፈሩን ፣ አሸዋውን እና አንፎርሻውን ተግተው በዋናተኞች ጥረት ህይወታቸው ተረፈ፡፡

በታቀደው መሰረት የትኩል የማጥቃት ውጊያ ከሌሊቱ አስር ሰዓት ከተባለው ትንሽ ዘግይቶ 10፡3ዐ ላይ ከፍተኛ የማጥቃት ፍልሚያ ተጀመረ፡፡

የተጀመረው ውጊያ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ሳያቋርጥ ተካሄደ፡፡ ከፍተኛ መስዋትነት ተከፈለ፡፡ በበላይ ትዕዛዝ መሰረት ቦታ ለመያዝ ማፈግፈግ ተደረገ፡፡ የያሬድ ተኳሽ የነበረው ብሩኬ በጠላት ጥይት ተመትቶ በጠላት መሬት ላይ ወድቋል፡፡ ብሩኬን ከወደቀበት ለማምጣት ወደ ኋላ፤ ተመለሰ ፡፡
የብሩኬን አስከሬን ተሸክሞ ባለው በሌለው አቅም ከጠላት መሬት ይዞ ለመውጣት ሞከረ፡፡ ግን አልቻለም፡፡ ወደ ወገን መሬት ሳይገባ በጠላት ጥይት ተመቶ ወደቀ፡፡

በዛን ጊዜ በጠላት መሬት ላይ ተመቶ የወደቀን ለማንሳት የጠላት የተኩስ ሃይል አይሏል፡፡ እረዳት እና ተኳሽ ተመተው ከወደቁበት ሳይነሱ ሰዓታት ተቆጠሩ፡፡ የጠላት ተኩስ ጋብ አለ፡፡ ቀኑ መሸ፡፡ ተራውን ለምሽት ለቀቀ፡፡

የቆሰሉ እና ህይወታቸው ያለፈ የሰራዊት አባላትን ጨለማውን ተገን በማድረግ ተመተው ከወደቁበት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተነሱ፡፡

ህይወታቸው ያለፈና የቆሰሉ ሰራዊቶች በተመደቡ አግላዮች እየተለዩ የቆሰሉት ወደ ህክምና ሲወሰዱ ለእናት ሃገራቸው የተሰውትን ለመቅበር ወደ ተመረጠ ቦታ ተወሰዱ፡፡

ያሬድ በጥይት ተመቶ ለብዙ ሰዓታት ደም ፈሶታል፡፡ ከወደቀበት ቶሎ አልተነሳም፡፡ ሲነሳ የሞተ እንጂ ህይወቱ ያለ አይመስልም፡፡ ሊቀበሩ ወደ መቃብር ቦታ ከብሩኬ ጋር ተወሰደ፡፡ በደምና
በአቧራ ተጨመላልቋል፡፡ እየተንደፋራ አጓራ፡፡ ውሃ ውሃ ውሃ አለ፡፡ ተወራጨ ፣ ተፈራገጠ፡፡
አግላዮቹ የተማሰው ጉድጓድ ውስጥ ሊቀብሩት ተዘጋጅተዋል፡፡

ኧረ! አለ ፤ ነብሱ አልወጣችም! ተባባሉ፡፡ ከእነህይወቱ ሳይሞት ሊቀብሩት ከወሰዱት የመቃብር ጉድጓድ መለሱት፡፡ በፍጥነት ወደ ህክምና ተወሰደ፡፡

በትኩል የማጥቃት ውጊያ የተሰው የሻለቃዋ አመራሮች በጥቂቱ ፦

“ከ 3ኛ ሻ/ል፦ ፶/አ ቡህ በዛን ጊዜ የሻምበሏ ም/ አዛዥ የነበረ፡፡

፶/አ መላኩ በዛን ጊዜ የሻምበሏ ሎጀስቲክስ የነበረ”፡፡ “ከ4ኛ ሻ/ል፦ ፶/አ ተስፋየ ቡርሳ በዛን ጊዜ የሃይሏ ዋና አዛዥ የነበረ"፡፡
👍366🔥1
በትኩል የማጥቃት ውጊያ ጊዜ ቀላል የማይባል ለእናት ሃገራቸው ህይወታቸውን የገበሩ የሰራዊት
አባላትና አመራሮች እንደነበሩ ሊዘነጋ የማይገባው የምንጊዜም ትውስታ ነው፡፡ በድጋሜ ግዳጅ ተሰጠ፡፡

በአዲኋላ መሽጎ የነበረው የሻቢያ ሰራዊት ላይ በተደረገው ከፍተኛ የማጥቃት ውጊያ ሽንፈቱን ተከናነበ፡፡ ለኢትዮጵያ ትልቅ ድል ተመዘገበ፡፡

ያሬድ ወደ ህክምና እንደሄደ ቶሎ ተሸሎት አልተመለሰም፡፡ በአዲኋላም በተደረገው ውጊያም አልተሳተፈም፡፡

በኢትዮጵያ መንግስት የውጊያ ማቆም ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡ ሰራዊቱ ወደ ኋላ እንዲመለስ ተደረገ፡፡ በራማ አድርገው ሊጓዙ ሲሉ ያሬድ ከህክምና ተመለሰ፡፡ ሳይውል ሳያድር ከእናት አሃዱ ጋር ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ከራማ ወደ ጭላ የነበረው ጉዞ ያለማቋረጥ በእግር አንድ ሳምንት ፈጀ፡፡ ጭላ አካባቢ እረፍት እንዲደረግ ተወሰነ፡፡ በጠላት ላይ የነበረውን የትኩል እና የአዲኋላን የማጥቃት ውጊያ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን ግምገማ ተደረገ፡፡ ግምገማው እንዳበቃ ከጭላ ተነስተው ወደ ሰለክላካ ተጓዙ፡፡ ጉዞው አላበቃም፡፡

የነበረው ጉዞ አሰልች እና አድካሚ ነበር፡፡ አንዳንዴ እረፍት እየተደረገ አንድ ወር የፈጀ የእግር ጉዞ ተደርጎ የፆረናን ምሽግ መቆጣጠር ተቻለ፡፡ በፆረና ምሽግ ወራቶች እንደተቆጠሩ ሀN የሰላም አስከባሪ ሃይል ግንባሩን ተረከባቸው፡፡ ከፆረና ምሽግ ሃያ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀው ገብረ ሰናይ በሚባል አካባቢ አረፉ፡፡

1993 ዓ/ም ወደ 1994 ዓ/ም መግቢያ አካባቢ ከገብረሰናይ ተነስተው ወደ ምዕራብ ጎጃም ቻግኒና አዊአካባቢ እንዲሰፍሩ ታዘዘ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose



ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113
👍272
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አለማየሁ ከተማውን ለቆ በሄደ በ15ተኛው ቀን ለአላዛር  አንድ በስራ ምክንያት የሚያውቀው ሰው የደወለለት፡፡ለረጂም ጊዜ ተደዋውለው ስለማያውቁ ግራ በመጋባት ነበር ስልኩን ያነሳው፡፡
‹‹ሄሎ ሙሳ…በህይወት አለህ እንዴ?››ሲል ጠየቀው አላዛር፡

‹‹አለሁ ባክህ…››

‹‹ከእኛ ሰፈር ከለቀቀክ በኋላ እኮ ተደዋውለን አናውቅም…ውጭ ውጭ ስለምትል የሸመጠጥክ መስሎኝ ነበር››

‹‹አይ እዚሁ ነኝ››

ግራ ገባው ንግግሩ ቀዝቀዝ አለበት…ድሮ ቢሆን ነገሮችን ማግለብለብና ማዳነቅ ይወድ ነበር…የሆነ ነገር እንደሆነ ገባው፡፡

‹‹ሙሳ ሰላም ነው…?እሺ ምን ልታዘዝ?፡፡››

‹‹ባክህ አሁን በአባትህ ሰፈር  እያለፍኩ ነበር…››

የበለጠ ግራ ተጋባ…አባት የሚለውን ቃል  ከእሱ አንደበት አልጠበቀም ነበር‹‹እሺ››

‹‹እኔ እንጃ አባትህ የሆነ ነገር የሆኑ ይመስለኛል…››

‹‹የሆነ ነገር ስትል..?››

‹‹ምን አልባት ተፈንክተው መሰለኝ….ከግንባራቸው ደም እየፈሰሰ ሸሚዛቸው ላይ  ተረጫጭቷል…ከቤታቸው ወጥተው እየሄዱ ነበር..አስቁሜያቸው ላናግራቸው ብል ስለማያውቁኝ መሰለኝ አመናጭቀውኝ ጥለውኝ ሄዱ፡፡››

‹‹ማንም አብሮት የለም?››

‹‹አዎ ብቻቸውን ናቸው …ያ ነው ያሳሰበኝ…ከቻልክ እስኪ ደውልላቸው፡፡››

‹‹እሺ ሙሳ አመሰግናለው…ደውልልሀለው ቻው››ብሎ ስልኩን ዘጋ፡፡በደቂቃ ውስጥ ውስጡ እርብሽብሽ አለበት፡፡‹‹የዚህ ሰውዬ ጣጣ መቼ ነው የሚለቀኝ?››ሲል ተበሳጨ..ስልኩን አወጣና አባቱ ጋር ደወለ…ይጠራል አይነሳም፤መልሶ ደወለ ፤አሁንም አይነሳም…ሶስተኛ ሲሞክር ተዘግቷል፡፡ይሄ ደግሞ ይበልጥ አሳሰበው…፡፡.እቤት የእንጀራ እናቱ ጋር ደውሎ እንዳይጠይቅ ስልክ የላትም…፡፡.በአካል ሄዶ ከማረጋገጥ ውጭ ምንም ምርጫ የለውም፡፡ለአሌክስ ደውሎ ሊነግረውና አብረው እንዲሄዱ ሊጠይቀው አሰበና ስልኩን አንስቶ ለመደወል ከተዘጋጀ በኃላ በራሱ ፈገግ በማለት መልሶ ተወው‹‹አሌክስ ጥሏቸው ከሄደ ሰነባብቷል …ግን ደግሞ እስከአሁን እንደዛ ማድረጉን አምኖ መቀበል አልቻለም፡፡

ዝም ብሎ ተነሳና ላዳ ተከራይቶ ብቻውን ወደአባቱ ቤት ሄደ…ፈራ ተባ እያለ የውጩን በራፍ ገፋ ሲያደርገው ተከፈተለት፡፡አልፎ ወደውስጥ ገባ፡፡በረንዳ ላይ ደረሰ፡፡በስሱ አንኳኳ..መልስ የለም፡፡…አንኳኳ መልስ የለም…፡፡የበለጠ እየፈራና እየተረበሸ መጣ…፡፡በራፉን ገፋ አደረገው፤ ተበርግዶ ተከፈተለት…፡፡ወደውስጥ ገባ….፡፡የሚያየውን ነገር ማመን አልቻለም…፡፡ዛር እንደወረደበት ባለውቃቢ ሰውነቱ ይንዘፈዘፍበት ጀመር…፡፡አረ እንደውም እያቅለሸለሸው ነው….፡፡ተንደርድሮ መልሶ ወደውጭ ወጣ፡፡ በረንዳው ላይ በጉልበቱ ተንበረከከ…፡፡ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት የበላው እራት አንድም ሳይቀር ተዘርግፎ ወጣ….፡፡.እዛው በተንበረከከበት ደንዝዞ ደቂቃዎች አሳለፈ፡፡‹‹እየቃዠው ነው? ወይስ ያየሁት ነገር በእውነት የሆነ ነገር ነው?››በማለት እንደምንም እየተንበረከከ ወደውስጥ ተመልሶ ገባ.፡፡.አዎ ቅዠትም ህልምም አልነበረም…በትክክል ደግሞ እያየው ነው..፡፡ሳሎኑ እንዳለ በደም ፍንጥቅጣቂ ተጨመላለልቋል፡፡እንጀራ እናቱ መሀከል ወለል ላይ እርቃኗን ዝርግትግት ብላ ተኝታላች…ግማሽ ገላዋ ከእንብርቷ በታች ያለው አካሎ በሙሉ በደም ተበክሏል…፡፡.አንጀቷ  ዝርግፍ ብሎ ወጥቷል…፡፡ከአንጀቷ ጋር ደም መሰለ ህጻን ልጅ ይታያል…፡፡ከዛም በታች ያለው አካሏ ተደጋግሞ በጩቤ ይሁን በቢላዋ ተጨቅጭቋል፡፡
እየተንሸራተተ ወደኃላ ተመለሰና ቤቱን ለቆ ወጣ….፡፡ምን ማድረግ እንዳለበት ማሰብም ሆነ መወሰን አልቻለም፡፡ዝም ብሎ ግቢውን ለቆ ወጣ….፡፡ቀጥታ አካባቢው ወዳለው ፖሊስ ጣቢያ ነው የሄደው…፡፡.አዎ ገና ህይወትን በቅጡ ያልኖረችውን ያቺን ምስኪን ነፍሰ ጡር ሴት እንደዛ ብልሽትሽት ያደረጋት አባትዬው ነው፡፡ደግሞ ህይወቱን ያጣው ጮርቃው ህፃን ወንድሙ እንደሆነ ሲያስብ የበለጠ ልቡ ደከመ፡፡ስለዚህ መቀጣት አለበት ሲል ወሰነ …፡፡ለህግ አሳልፎ ይሰጠዋል፡፡ቀሪ ዘመኑን በእስር ቤት ያሳልፋል፡፡አዎ አሁን ለፖሊስ ማመልከትና የተፈጠረውን አሰቃቂ ወንጀል ሄዶ ማሳየት አለበት…፡፡ፖሊስ ጣቢያው ጋር ደረሰ…፡፡አልፎ ወደውስጥ መግባት ግን አልቻለም፡፡እግሩን ካቆመበት መሬት ጋር የማያውቀው ኃይል አስሮ ይዞታል፡፡ፊቱን ወደኃላ ዞረና መራመድ ጀመረ…፡፡ከ2፡30 ጀምሮ እስከ 5፡00 ሰዓት ያለማቆረጥ በደመነፍስ በእግሩ ሲዞር ነበር፡፡ጭው ያለ አስቀያሚ ስሜት እየተሰማው ነው፡፡አሁን አባቱን አይደለም እየወቀሰና እየረገመ ያለው..እራሱንም ጭምር ነው፡፡
‹‹ይህቺ ያለጊዜዋ የተቀጠፈች ሴት እናቴ ወይም እህቴ ብትሆን ምንድነበር የማደርገው…?እዛው  ሬሳዋን ባየሁበት ቅፅበት ጭንቅላቴን ይዤ ኡኡ ብዬ በመጮህ የሰፈሩ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብና ገዳዩም ወዲያው በቁጥጥር ስር እንዲውል አላደርግም ነበር?››እራሱን ጠየቀ…፡፡‹‹አሁን እንዲህ እግሬ እስኪዝል የምኳትነው አባቴን አሳልፎ ላለመስጠጥት ካለኝ ውስጣዊ ፍላጎት የተነሳ ነው…፡፡አዎ ያ ብሽቅ የሆነ አውሬ ሰውዬን ለመከላከል…አዎ ‹‹አባቱን አሳልፎ ፤ለህግ ሰጠ ላለመባል››እርግጥ አባቱን ለፖሊስ አሳልፎ ቢሰጥ እህቶቹ እንደማይደሰቱበት ያውቃል..ግን ደግሞ ተገቢውና ትክክለኛው ነገር ያ ነበር፡፡የሆነ ነገር በአእምሮ ብልጭ አለበት‹‹ቆይ እሱ ግን የት ሄዶ ነው…?ራሱን አሳልፎ ለመስጠት ወደፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ከሆነስ…?መቼስ ትንሽ ሽራፊ አእምሮ ያለው ሰው በደም ፍላትና በንዴት ምንም አይነት ወንጀል ከሰራ በኃላ ትንሽ ሲረጋጋና ደሙ ዚቀዘቅዝ በመጀመሪያ የሚያደርገው ነገር  ቀጥታ ወደህግ ሄዶ የሰራውን ወንጀል አብራርቶ ተናዞ እጅ መስጠት ነው..፡፡እና አባቱም እንደዛ አድርጎ  ሊሆን የሚችልበት እድል ሰፊ እንደሆነ ተስፋ አደረገ እና ወደ አባቱ ቤት ተመልሶ መራመድ ጀመረ…፡፡ደረሰ…፡፡ተስፋ እንዳደረግ ግቢው በሰው ተሞልቶ በአካባቢው ፖሊሶች እየተተረማመሱ  አይደለም…በተቃራኒው ዝምና ፀጥ እንዳለ ነው..፡፡እንደዛ በመሆኑ ደግሞ መላ ሰውነቱ በፍራቻ ተናወፀ….‹‹ብን ብሎ ሀገሩን ለቆ ጠፍቶ ይሆን እንዴ?››ሲል አሰበ…፡፡
‹‹እንደዛ ካደረገ ምንድነው የሚሆነው?›፡፡ቶሎ ብሎ ገብቶ አረጋግጦ ወደደም ጠላም ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ አለበት… ‹‹እስኪጣራ ብለው እኔን እስር ቤት ቢወረውሩኝስ…?አሻራዬ እንደሆነ የውጩም ሆነ የቤቱ በራፍ ላይ ተዝረክርኳል….‹‹አባዬ እድሜ ልኬን ስጠላህ ነው የኖርኩት..አሁንም አምርሬ ጠላሀለው››አለ.

.‹‹ግን እኮ  ሙሳ ደውሎ ነው የጠራኝ..አባቴ በደም የቀለመ ልብስ ለብሶ ከቤቱ ወጥቶ ሲሄድ እንዳየው በስልክ ስለነገረኝ ነው የመጣሁት… ያንን ህግ ፊት ቀርቦ ማስረዳት ይችላል፡፡››ሲል አሰበና ቀላል አለው፡፡ወደ ውስጥ ገባ…የቤቱን  በራፍ ከፍቶ ገባ ፡፡ሌላ የሚያደንዘዝዝ ነገር፡፡‹‹ዛሬ ምን እየተከሰተ ነው?››እራሱን ጠየቀ፡፡ዘለለና መኝታ ቤት ገባ….ማንም የለም፡፡ወደሳሎን ተመለሰ፡፡ሳሎኑ ባዶ ነው..፡፡ወለሉም ንፅህና ፅዱ ነው፡፡ምንም አይነት የተዘረረ እርቃን የሴት ገላ የተዘረገፍ አንጀትና ለአቅመ መወለድ ያልደረሰ ህፃን አይታይም…፡፡‹‹ሰውዬው እንዴት እንዴት አድርጎ ነው እንዲህ ያፀዳው?››ተገርሞ ጠየቀ..፡‹‹፡ሬሳውን የት አደረገው?››ምንም መገመት አልቻለም…፡፡ በፍራቻ የሚንዘፈዘፍ ሰውነቱን እንደምንም ብሎ በራፍ አካባቢ ባለ ደረቅ ወንበር ላይ አሳረፈ፡፡ለምን ቁጭ ማለት እንደፈለገ አያውቅም፡፡ግን ቤቱን ለቆ መውጣት አልቻለም፡፡ከ20 ደቂቃ በኃላ
👍532
የእግር ኮቴ ሰማ…፡፡የሳሎኑ በራፍ ተከፈተ…፡፡በደነዘዘበት እንደተቀመጠ ቀና ብሎ አንገቱን አዞረ..አባቱ ናቸው፡፡በራፍን ከፍተው ገቡን አፈጠጡበት፡፡የልጃቸውን እዚህ መገኘት ያልጠበቁትና የማይፈልጉት ነገርም እንደሆነ በፊታቸው መቋጠርና በአይናቸው መፍጠጥ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
ዝም ብለውት ሄዱና ከፊት ለፊቱ ተቀመጡ፡፡ግንባራቸው ላይ የቁስል ፕላስተር ተለጥፎበታል፡፡እጃቸው እየተንቀጠቀጠ ነው፡፡የሆነ ነፍስ አልባ በድን ነው የሚመስሉት፡፡‹‹ምን ብሎ ማናገር …ምን ብሎ የትኛውን መጠየቅ እንዳለበት ሊገባው አልቻለም፡፡እሳቸውም ምንም ነገር ከአንደበታቸው አላቀው ማውጠት አልቻሉም፡፡ …የሰሩትን ስራ ልጃቸው እንዳየ አውቀዋል…፡፡ እሳቸው ወደቤት በሚመለሱበት ሰዓት ነበር ቤት ገብቶ ወጥቶ የሄደው..እና ከኃላው እየተከተሉት ነበር…፡፡ቀጥታ ወደፖሊስ ጣቢያ ሲያመራም በቅርብ ርቀት እያዩት ነበር…፡፡የሚመጣውን ሁሉ በፀጋ ለመቀበል ወስነው ነበር..፡፡ለዛ ነው ሊያስቆሙት ያልፈለጉት፡፡ግን ሊያደርገው እንዳልቻለ ተመለከቱ፡፡ከፖሊስ ጣቢያው አጥር አካባቢ እንደደረሰ ደንዝዞ ሲቆምና ወደኃላው ተመልሶ ሲሄድ አዩትን ስቅስቅ ብለው አለቀሱ..፡፡‹‹አዎ ልጄ ጨክኖ አሳልፎ ሊሰጠኝ አልቻለም››አሉና እሱን መከተሉን አቁመው ወደቤታቸው ተመለሱ…፡፡ከዛ በኃላ ነው  የአዲሷን ባለቤታቸውንና ያረገዘችውን ልጅ አስከሬን እንዴት አድርገው ማስወገድ እንዳለባቸው ማሰብ የጀመሩት…፡፡እናም ደግሞ ያሰቡትን ያደረጉት፡፡
ከ30 ደቂቃ መፋጠጥ በኃላ አላዛር እየተጎተተ ከተቀመጠበት ተነሳ….፡፡ምንም ሳይናገር ወደመውጫው ተጓዘ..፡፡በራፉን ከፍቶ ወጣ …፡፡ወደቤቱ ሄደና አልጋው ላይ ተዘረረ..፡፡ለአንድ ሳምንት ከመኝታ ክፍሉ መውጣት አልቻለም ነበር፡፡ከአንድ ወር በኃላ ደብዳቤ ደረሰው ፡፡ከአባቱ የተላከ ነው…፡፡አነበበው…፡፡ለምን ሚስታቸውን እንደገደሉ..አሁን እንዴት እንደተፀፀቱ ገልፀው ሀገሩን ለቀው ወደማይታወቁበት ሀገር እንደሄዱና ከቻለ ይቅር እንዲላቸው ገልፀው የተሰናበቱበት ደብዳቤ ነው ፡፡
እሱ ግን እንደአባቱ የሆነ ቦታ ሄዶ ሀገር በመልቀቅ ከተፈጠረው ነገር ህሊናውና ማፅዳት አልቻለም…ያ እርቃን ሰውነት ያየው የእንጀራ እናቱ ሬሳ መላ ህይወቱን ና አመለካከቱን ነው የቀየረበት…ስነ-ልቦናውንና ነው ስብርብር አድርጎ ያደቀቀበት…….ፃረ-ሞት ሁሌ ነው የሚያሳድደው..እረሱ በእጆቹ ጨቅጭቆ እንደገዳላት አይነት ፀፀትና ስብራት ነው ያስከተለበት..ለሰው የማይናገረው ህመም…አልቅሶ ማይወጣለት ፀፀት…..፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍4511😢11😱1
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

የገመሪ ተራራ

የተደበቀው ሚስጥር እንዳይወጣበት ከዛሬ ነገ እያለ እንደሌባ በሩቁ ይሸሻል፡፡ የሱ ጉዳዩ ከተፈፀመለት በኋላ፤ ተመልሶ ወደ ያሬድ ቤት አልሄደም፡፡ ጓደኛው ወደ ውትድርና መግባቱን ሲሰማ ስጋትና
ጭንቀት አላስቀመጠውም፡፡ የአበበችን ዓይን ማየት አልቻለም፡፡

ያለውን ንብረት እንዳይነቃበት በከፊል ሸጠ፡፡ ከእድላዊት ጋር ሃገር ለቀው ለመሄድ ተስማሙ፡፡ ለመንገድ የሚሆን በሶና ቆሎ አዘጋጁ፡፡ ስደትን መርጠዋል፡፡ ልጃቸውንና እናት አባታቸውን ያለጧሪ ፣ ቀባሪ ትተው ለመሄድ ተነሱ፡፡ አንጀታቸው አዘነ፡፡ አይናቸው አነባ፡፡ ልባቸው ግን ጨክኗል፡፡ ቤተሰቦቻቸውን ፀበል ነው የምንሄደው ብለው ዋሽተዋቸዋል፡፡ ጨለማ በተቀላቀለበት ሌሊት በዕለተ ሰንበት ሰው ወደ ቤተክርስትያን ለመሳም  በሚሄድበት ሰዓት እነሱ ወደ አረብ ሃገር ስደት ሆነ፡፡ ከሰም ጅረቱን አቋርጠው በደብረብርሃን አድርገው ወደ ወሎ ባቲ ተጓዙ፡፡

ከሶስት ቀን ጎዞ በኋላ ባቲ ከተማ እንደደረሱ በቀይ ሸራ ወደ ተሸፈነች የሻይ ድንኳን ጎራ አሉ፡፡

በጦስኝ ቅመም የተንቆጠቆጠ የባቲ ሻይ አዘዙ፡፡

አንድ መልከ መልካም ወጣት ወደ ሻይ ቤቷ ገባ፡፡

"ቶሎ በል አንድ ሻይ በዳቦ ስጠኝ ? ሰዎች እየጠበቁኝ ነው አለ ፤ ወጣቱ እየተጣደፈ፡፡

የሻይ አስተናጋጁ "እነማን ናቸው የሚጠብቁህ"? አለ፡፡

ወደ አረብ ሃገር የሚሄዱ ናቸው፡፡ ከመሃመድ ጋር አገናኝቻቸው ልመጣ ነው አለ፡፡ ያዘዘውን ሻይና ዳቦውን ሲበላ ለተመለከተው የቸኮለ ሰው ሳይሆን ከጎሬ የወጣ ጅብ ይመስል ነበር፡፡

ወደ አረብ ሃገር በየት እንደሚኬድ አያውቁም፡፡

"ይሄንን ልጅ እንጠይቀው" ? አለች እድላዊት፡፡ ወጣቱ ስለ አረብ ሃገር ሲያወራ ሰምታ፡፡

ተመስገን ለመጠየቅ ፈራ ተባ አለ፡፡ ኧረ! ለመሄድ ተቻኩሏል ሳይነሳ ጠይቀው አለች ? ደግማ፡፡

"ወንድም" ? አለ ፤ ተመስገን፡፡ ከሻይና ከዳቦ ጋር እየታገለ ያለውን ወጣት፡፡

"አቤት ጠራኸኝ" ? አለ ፤ ወጣቱ፡፡

"አዎ፤ አንድ ነገር ትተባበረኛለህ ?፡፡

አላመነታም፡፡ "ምን ልተባበራችሁ? ወደ አረብ ሃገር መሄድ ትፈልጋላችሁ? ፡፡

"አዎ፤ ለመሄድ ፈልገን ነበር ፡፡

"እኔ ደላላ ነኝ፡፡ ከሚልከው ሰው ጋር እንዳገናኛችሁ፡፡ ከፈለጋችሁ ሁለታችሁም አርባ አርባ ብር ክፈሉኝ ብሎ ለመሄድ ተነሳ፡፡

"እሽ እንከፍልሃለን፡፡ ታዲያ አሁን የት ልትሄድ ነው? አለው፡፡

"ሰው እየጠበቀኝ ነው፡፡ ቼኩያዓለሁ ፤ ከሄዳችሁ ብሩን አምጡና ተነሱ እንሂድ አላቸው፡፡

"እሽ" አሉ፡፡ የያዙትን ገንዘብ ከፍለው ደላላውን ተከተሉት፡፡

ወደ ውጭ ሃገር የሚልኳቸውን የሰዎች ማሰባሰቢያ ቤት ደረሱ፡፡ መሃመድ ለሚባል ደላላ አስረክቧቸው ተመለሰ፡፡

መሃመድ ተቀብሎ ወደ ውጭ ሃገር ሊወስዳቸው ካሰባሰባቸው ስምንት ሴትና አስር ወንዶች ጋር ቀላቅሎ በራሱ መኪና አሳፍሮ አስኢት ከተማ አደረሳቸው፡፡

እሱም ለአስኢት ደንበኛው ለከድር አስረክቧቸው ተመለሰ፡፡

የአስኢት ደላላው ከድር ከመሃመድ ዘጠኝ ሴቶችንና አስራ አንድ ወንዶችን በድምሩ ሃያ ሰዎችን ተቀብሎ ከአስኢት ከተማ ጉዞ በምሽት ጫካ ለጫካ በእግር ወደ የቡኪ ተጀመረ፡፡

የቡኪ የኢትዮጵያ አፋር መሬትን ጨርሶ የጅቡቲ መዳረሻ መሬት ማለት ነው፡፡

ከአስኢት የቡኪ ድረስ በእግር አራት ቀን ይፈጃል፡፡ ወደ ውጭ ሃገር ለመሰደድ የሚጓዙ ወጣቶች ለሚረከቧቸው ደላሎች ሁሉ የያዙትን ገንዘብ በየደረጃው እየሰጡ ነው የሚጓዙት፡፡

ከመካከላቸው አንድ ስደተኛ ይማም ይባላል፡፡ ወደ አረብ ሃገር ከዚህ በፊትም ተሰዶ ሳይሳካለት ከየመን ተመልሷል፡፡ ለእሱ ስደት አዲሱ አይደለም፡፡ በስደት ላይ ምን አይነት ችግሮች እንደሚያጋጥሙ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡

"ገንዘባችሁን ሽፍቶች እንዳይዘርፏችሁ፡፡ ሲፈተሸ በማይገኝበት ቦታ መደበቅ አለባችሁ፡፡ አለ ይማም፡፡ አብረውት ለሚጎዙት ጓደኞቹ ፡፡ ወንዶቹ በልብሳቸው ጠርዝ እና የለበሱትን ሸበጥ በምላጭ በመሰንጠቅ አመሳስለው ሰፉት፡፡

ሴቶቹ ደግሞ እንደ ወንዶቹ የልብስ ጠርዛቸውንና ጫማዎቻቸውን ባይጠቀሙም የያዙትን ገንዘብ በስስ ፌስታል እየጠቀለሉ በብልታቸው ውስጥ ከተቱት፡፡

ከአስኢት እና የቡኪ መካከል ለስደተኛ መቅጫ የተፈጠረ ይመስላል፡፡ የአፋርና የጅቡቲን ሽፍቶች በውስጡ አቅፎ የሚኖር የገመሪ ተራራ፡፡ በጨለማ ለተመለከተው መሬት አልቃ የሰማይ ጥግ የደረሱ ይመስል ነበር፡፡ የገመሪን ተራራ ብቻ በእግር ለመውጣት ከሶስት ሰዓታት በላይ ይፈጃል፡፡ ሃያ የኢትዮጵያ ስደተኞች ተመስገንና እድላዊትን ጨምሮ የገመሪን ተራራ ለመውጣት ትንቅንቅ ገብተዋል፡፡

በውሃ ጥም እና በድካም የሞቱ የስደተኞች አስከሬን በተራራው ፣ በየእንጨቱ ላይ ተንጠልጥሎ ስጋቸው የአሞራ ምሳ ሆኗል ፡፡ ሲያዩት ተደናገጡ፡፡ ከነመፈጠራቸውም አምርረው ረገሙ፡፡ የገመሪን ተራራ በአራት እግራቸው እየዳሁ ስቃይና መከራቸውን አብዝቶታል፡፡

ተንቀሳቃሹ የቁም ስቃይና መከራ የሚያሳዩት የአፋርና የጅቡቲ ሽፍቶች ረሃብ እንደሰነበተበት የበርሃ ጅብ ከፊት ለፊታቸው ድቅን አሉባቸው፡፡

የመሳሪያ አፈሙዝ ደቀኑባቸው፡፡ በበረሃ ልምጭ ገንዘብ አምጡ እያሉ ገረፏቸው፡፡ እግዚአብሔር እባብን ፈጥሮ የአዳም ልጆች ራስ ራሱን እንዲቀጠቅጡት እንደተፈረደበት ተቀጠቀጡ፡፡

በኪሳቸው ያገኙትን ገንዘብ ሁሉ ቀሟቸው፡፡ ሽፍቶቹ በገንዘብ ብቻ አልተመለሱም፡፡ ሴቶችን እየገረፉ አሰቃዩዋቸው፡፡ ልብሳቸውን አስወለቋቸው፡፡

የደበቁትን ገንዘብ እንዳይወሰድባቸው ልብሳቸውን ሲያወልቁ ከፓንታቸው ጋር አመሳስለው በማውለቅ ቢያተርፉትም፡፡ መደፈሩ ግን አልቀረላቸውም፡፡

የጠይም መልከ መልካሟ እድላዊት ለሽፍቶች አለቃ በሞግዚቶቹ ተመርጣ ቀረበች፡፡ አይኖቿ በእንባ ተሞሉ፡፡ ተቁለጨለጨች፡፡ ጨካኙ የሽፍቶች አለቃ አላዘነላትም፡፡ እየረገጠና እያዳፋ ልብሷን አስወለቃት፡፡ እንደ እሳት በሚጋረፈው የገመሪ የፀሃይ ሃሩር እርቃነ ስጋዋን አስቀራት፡፡ አንዴ አፈንድጅ ፣ አንዴ ተገልበጭ እያለ አሰቃያት፡፡ ብልቱ የተለበለበ ማረሻ ይመስላል፡፡ ሊደፍራት ብልቱን አስጠጋ፡፡

እድላዊት ድንገት ከብልቷ የደም ፈሳሽ ፈሰሳት፡፡ እንዳፈነደደች በርግጫ ከመሬት ቀላቀላት፡፡ ወደ ሌሎች ስደተኞች ተመለሰ፡፡

ቅንጣት የሚያክል ርህርሄ የሌላቸው ወንበዴዎች እንደ አስፈለጋቸው የልባቸውን አድርሰው ለቀቋቸው፡፡

ከዘጠኙ ሴቶች አራቱ በደረሰባቸው አስገድዶ መድፈርና ድብደባ ህይወታቸው ወዲያውኑ አለፈ፡፡

የተቀሩት አምስት ሴቶች እድላዊትን ጨምሮ መትረፍ ሳይሆን ለመሰንበት ያክል ነብሳቸው ተረፈች፡፡

በውሃ ጥምና ረሃብ ተሰቃይተው የሽፍታ ዱላ እንደ እናታቸው ጠግበው መሄድ አቅቷቸው በጣረሞት ትንሽ እንደተጓዙ ሁለት ወጣት ወንዶች በመንገድ ላይ ህይወታቸው ተቀጠፈ፡፡ ቢደክማቸውም በእንጨት መሬት ቆፍረው ቀበሯቸው፡፡ ተለቃቅሰው ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡

እድላዊት በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ደከማት፡፡ መሄድ አቅቷታል፡፡ መንገድ ላይ ወደቀች፡፡ አብረዋቸው የነበሩ ጥለዋቸው ሄዱ፡፡ ተመስገን ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ፡፡ የሚያቀምሳት በእጁ ላይ ምንም አልነበረም፡፡ ከቤት ሲወጡ ያዘጋጁትን ስንቅም ሳያስቀሩ የጅቡቲ ሽፍቶች ዘርፈዋቸዋል፡፡ ትንሽ አረፍ እንዳለች ትንፋሿ መለስ አለላት፡፡ እንሂድ ሌላ ሽፍታ ሳይመጣብን አለች፡፡ አብሯት ለቀረው ተመስገን፡፡

የሞት ሞቷን ተነሳች፡፡ ጥለዋቸው የሄዱትን ጓደኞቻቸውን የቡኪ ደረሱባቸው፡፡
👍5410😱2
አድካሚው የእግር ጉዞ ወደ መኪና ተቀይሯል፡፡ ተሳፍረው ወደ ድኬል ፣ ከድኬል ወደ አርታ ፣ ከአርታ ወደ አልሰቢ ፣ ከአልሰቢ ወደ ጅቡቲ

የኢትዮጵያ መኪናዎች ማረፊያ ፣ ከጅቡቲ አቢካዱስ ፣ ከአቢካዱስ አርባ ከመኪና ወደ መኪና እየተገለባበጡ ቀጥለዋል፡፡

አርባ የአበሾች ሰፈር ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያዊና ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩበት አካባቢ ማለት ነው፡፡ ከስደተኞች መካከል አርባ ላይ የቀረው ቀርቶ የተቀሩት ደግሞ ይማም እና እነ ተመስገንን ጨምሮ በአካባቢው አጠራር ቦድ ሃይቅ ተብሎ በሚታወቀው የመሸጋገሪያ ሃይቅ ከአርባ በጀልባ ወደ ተጎሪ አመሩ፡፡

አንድ ጀልባ አሳፍራ ለመሻገር የሚፈቀድላት አርባ ሰው ነው፡፡ ጀልባዋ ግን ከአቅሟ በላይ ስልሳ ሰዎችን ጭናለች፡፡ አልቻለችም ፤ ስትጓዝ ግራና ቀኝ ትዋዥቃለች፡፡ የተሳፈሩት ስደተኞች በቦድ ሃይቅ እየወደቁ የሰው ልጅን ከእነህይወቱ ለአዞ ምሳና እራት እየመገበች መጓዟን ቀጥላለች፡፡

ከአሁን አሁን ገባን እያሉ በስጋት ተውጠዋል፡፡ ተደጋግፈው ፣ እንደሙጫ ተጣብቀው ጀልባዋ ስትዋዥቅ አብረው ይዋዥቃሉ፡፡ የቦድን ሃይቅ ሊጨርሱ ተቃርበዋል፡፡

እንደሙጫ ከተጣበቁበት ተነጣጠሉ፡፡ ተመስገን ራሱን ችሎ ለመቆም ሞከረ፡፡ ጀልባዋ ድንገት ወደ ግራ የፈራው አልቀረም፡፡ እንደጓደኞቹ የቦድን ሃይቅ ለመቅመስ ተገልብጦ ገባ፡፡ እድላዊት ጮኸች ፣ አባረቀች፡፡ ተመስገን ካይኗ ተሰወረ፡፡ ሰከንዶች ከተቆጠሩ በኋላ የገባበት ውሃ ተንቀሳቀሰ፡፡ አንገቱ ብቅ አለ፡፡

እየተንቦጫረቀ ወደ ዳር ወጣ፡፡ እዳር ላይ መግባቱ አጋጣሚ ከቦድ አዞ ሊተርፍ ችሏል፡፡

የቦድን ሃይቅ እንደጨረሱ ተጎሪ ገቡ፡፡ ተጎሪ አላረፉም ፤ ከጀልባ ወደ መኪና ተሳፍረው ጉዟ ወደ ሃዩ ቀጠሉ፡፡

ሃዩ የጅቡቲ መሬት አልቆ የሳውዲ አረብያ የመግቢያ መዳረሻ ከተማ ናት፡፡ ሃዩ እንደደረሱ ሳይውሉ ሳያድሩ ከመኪና ወደ ጀልባ ተዛውረው የመን ፣ ከየመን

ሃሙስ ከተማ ከሃሙስ ከተማ ፣ በመኪና ጅዳ ፣ ከጅዳ መካ መዳረሻቸው ሆነ፡፡

በጅዳም ሆነ በመካ ስራ ለመቀጠር ደላላ ያስፈልጋል፡፡ ወንድም የሚቀጠረው በበረሃ የግመል እረኝነት ሲሆን ሴቶች ደግሞ አበባ ማጠጣት ካልሆነ በስተቀር በከተማ ውስጥ መታወቂያ ስለሌለ

ተንቀሳቅሰህ ስራ መፈለግ አይደለም መታየትም አይቻልም ነበር፡፡

ተመስገን በመካ ጫካ ውስጥ እንድላዊትን ከሌሎች ስደተኞች ጋር አስቀምጦ ከይማም ጋር ስራ ፈልገን እንመጣለን እዚሁ ጠብቁን ብለው በመካ ጫካ ለጫካ አድርገው ወደ ሪያድ ስራ ፍለጋ ተጓዙ፡፡

ይማም በአፋር ክልል ተወልዶ ያደገ ሲሆን በመጠኑም ቢሆን አረበኛ መናገር ይችላል፡፡ በበረሃ የሚያገኙትን እረኞች እያነጋገረ ሪያድ ደረሱ፡፡ ስራ አልተገኘም፡፡ ወደ መካ ተመለሱ፡፡

ታዲያ ጓደኞቻቸው እና እድላዊትን አስቀምጠዋቸው የሄዱበት ጫካ ውስጥ አላገኟቸውም ነበር፡፡

ተመስገን የሚይዘውና የሚጨብጠው አጣ፡፡ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡የመካ ፖሊሶች ይዘዋቸው ወደ እስር ቤት ሄደው ይሆናል፡፡ ማልቀሱን ተውና በዚህ ጋር ወጥተን ሰው እንጠይቅ፡፡ ብሎት ተያይዘው የመካን ጫካ ወጥተው አስፓልት ደረሱ፡፡ በመካ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰዱ፡፡

እድላዊትና ጓደኞቿ በጉዞ ላይ የቆሰለ እግሮቻቸውን እያሻሹ እና እየተለቃቀሱ ነበር፡፡ ከየት እንደመጡ ሳይታወቅ ድንገት እንደ መብረቅ ቁጣ ጡንቻቸው ፈርጣማ ፈርጣማ ገና ሳይጠጉ ከሩቅ የሚያስፈሩ ዘጠኝ ወጣቶች ከተቀመጡበት አስነስተው የወሰዷቸው፡፡

መግባቢያ ቋንቋ አልነበራቸውም፡፡ በምልክት እየተነጋገሩ እድላዊትን ጨምሮ አራት ሴቶችንና ሶስት ወንዶችን ይዘው ወደ አስፓልት የወጡት፡፡ በራሳቸው መኪና አሳፍረው ትንሽ እንደተጓዙ ነበር፡፡ መኪናውን አቆሙት፡፡

ሶስቱን ወንዶች አስወረዱዋቸው፡፡ ያልቆመችውን መኪና እንዲገፉ አዘዙዋቸው፡፡ ሶስቱን የኢትዮጵያ
ለግላጋ ወጣቶች ገና አንድ እንጀራ እንኳን በልተው ያልጠገቡ ፤ ከሃገራቸው ያልፍልናል ብለው በበርሃና በውቅያኖስ አልፈው ፤ ከወንበዴና ከአዞ

ህይወታቸውን አትርፈው ፤ ጓደኞቻቸው ስራ ሊፈልጉ እንደሄዱ ፤ ከአሁን አሁን ይመጣሉ፡፡ እያሉ ሲጠባበቁ ስራ ፍለጋ የሄዱት
ተመስገንና ይማም ሳይመጡ ፤ በመካ ዱርየዎች ታፍነው መኪና ሲገፉ መኪናው እነሱን ትቶ የመካ አስፓልት ላይ ትተው ሄዱ እድላዊትንና ሶስቱን ሴቶች ይዘው ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡

በሪያድ በርሃ እንሰሳት እንኳን በማይፈፅመው ወሲባዊ አፈፃፀም እየተፈራረቁ ደፈሯቸው፡፡ ተዝለፈለፉ ፣ ትንፋሽ አጠራቸው ፤ ደከሙባቸው፡፡ ለሞት ሲጣጣሩባቸው መኪናቸውን አስነስተው ዘጠኙ ወጣቶች ጥለዋቸው ተበታተኑ፡፡

የተፈራረቀባቸው የመንገድ ስቃይ እና ውሃ ጥም ሳያንሳቸው የመካ ዱርየዎች ግብረሰዶም አልቀራቸው ምግብና ውሃ አጥቶ በሚማፀነው አፋቸው የወሲብ መፈፀሚያ ሲያደርጉት ከአራት ሴቶች አንዷ ወዲያውኑ ህይወቷ አለፈ፡፡

ሶስቱ ሴቶች እድላዊትን ጨምሮ ሞት እንዲወስዳቸው በሪያድ በርሃ የጣረሞት ይጮሃሉ፡፡

በአካባቢው የፀጥታ አካላት የሰው ጩኸት ሰምተው ወደ ጫካው ሲገቡ አራቱም ሴቶች በግንድ ስር ለየብቻቸው ተጥለዋል፡፡ አንዷ ህይወቷ አልፋል፡፡

ሶስት ሴቶች ለመሞት ይጣጣራሉ፡፡ ገመናቸውን እንኳን መሸፈን አቅቷቸዋል፡፡ እግራቸው
ተበረጋግዷል፡፡ በተለይ እድላዊት አጥንት ከየቦታው የመለቃቀም ያህል አንስተው ከሪያድ በርሃ በመኪና ጭነው ወደ መካ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዷቸው፡፡

የመካ ፖሊስ ጣቢያ የኢትዮጵያ ስደተኞን መታወቂያ የሌላቸውን ከየቦታው እየለቃቀመ 375 እስረኛ ሴትም ወንድም ጨምሮ ታስረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ሊሞላ 25 ሰው ቀርቶት ተጨማሪ ስደተኛ ይጠባበቃል፡፡

ከአራት ቀን በኋላ፤ 4ዐዐ ሰው የኢትዮጵያ ቦይንግ 777 አውሮፕላን ሞልቶ ከመካ ፖሊስ ጣቢያ ወጥተው ወደ እናት ሃገራቸው በረራ ጀመሩ፡፡

ተመስገንና እድላዊት በመካ ፖሊስ ጣቢያ አንድ ላይ ቢታሰሩም የሴት እና የወንድ ክፍል ለየብቻ ስለነበር አልተገናኙም፡፡ ሃገራቸው ቦሌ አዲስ አበባ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሰውም እንኳን አልተዋወቁም ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር መዝጋቢ የነበረው ይመር በመዝገቡ ላይ ስማቸውን ሲያሰፍር ከ4ዐዐ ስደተኞች መካከል የሁለት ልጆች አባት ስም ተመሳሳይ ሆነበት፡፡ ለማጣራት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተመስገን ብሎ ተጣራ፡፡

"አቤት አለ ተመስገን፡፡

"ከአንተ ጋር አብሮህ የሄደ ቤተሰብ ነበረህ እንዴ"? አለ ይመር ፤

"አዎ ፤ እህቴ እድላዊት የምትባል አብራኝ ሄዳ ፤ እዛው ጠፍታብኛለች ፡ቦሌ አየር ማረፊያ ስደተኞችን ሲቀበሉ ሴትና ወንዶችን ለየብቻ አድርገዋቸው ነበር፡፡ ወንዶቹ ከድብደባ በስተቀር የደረሰባቸው ጉዳት ብዙም አልነበረም፡፡ ከሴቶቹ ቀላል የማይባል ድብደባና
መደፈር የደረሰባቸው ቦሌ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በአፋጣኝ የህክምና እርዳት ሊደረግላቸው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከተላኩት ሰላሳ አምስት ሴቶች መካከል አንደኛዋ እድላዊት ነበረች፡፡

"አብራህ እንደመጣች አታውቅም ማለት ነው"?

"አላውቅም ፤ አብራ ከእኛ ጋር መጥታለች እንዴ" ? አለ፡፡ በተደበላለቀ ስሜት ተውጦ፡፡

"አዎ መጥታለች ፡፡ አሁን ትንሽ ጉዳት ደርሶባት ስለነበረ ህክምና ሄዳለች፡፡ ከህክምና ስትወጣ አብረሃት ትሄዳለህ አለው፡፡

ታዲያ ተመስገን አዲስ አበባ ቦሌ አየር ማረፊያ እንደደረሱ በኢትዮጵያ ፖሊስ ታጅበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ወደሚሰጥበት ጣቢያ ሲገቡ እድላዊትንም ወደ ህክምና ስትሄድ አይደለም ከአየር ስትወርድም ነበር፡፡
👍32😢76
የኢትዮጵያ የስደተኞች ማህበር ለስደተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቶ ገንዘብ ለሌላቸው የገንዘብ ድጋፍ እና ደብዳቤ በመስጠት ወደ መጡበት ክፍለ ሃገርና ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ
ሲደረግ ጉዳት የደረሰባቸው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና ተረድተው በተመሳሳይ የሚደረግላቸውን የመድሃኒት ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመለሱ፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 11ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍241
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ
================

ወንጀሉ በተፈፀመ በ15ተኛው ቀን ለአለማየሁ ደውሎለት ነበር፡፡

‹‹ሄሎ አሌክስ..እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ..አንተስ..?ሰፍር ?እነሰሎሜ ደህና ናቸው?››

‹‹ሁሉም ሰላም ነው….አንተ ጋርስ? ስልጠናው እንዴት ነው?››

‹‹ከባድ ነው.. ግን ያው ስፖርት ስለምወድ…ለእኔ ብዙም አልከበደኝም፡፡››

‹‹ጥሩ…..››

‹‹ምነው የተፈጠረ ነገር አለ እንዴ ?ድምፅህ እኮ ጥሩ አይደለም…ሰሎሜ ምን ሆነች?››

‹‹አይ እሷ ደህና ነች..አባቴ ነው፡፡››

‹‹አባትህ ምን ሆኑ?
አመማቸው?››

‹‹አልታመመም..ግን የሆነ ወንጀል ሰርቷል..ያንን ወንጀል መስራቱን እኔ ብቻ ነኝ ማውቀው..አሳልፌ ለፖሊስ ልስጠው ወይስ ዝም ብዬ ልቀመጥ? ግራ ገብቷኛል…ምክር እንድትሰጠኝ ነው የደወልኩት..በዚህ ጉዳይ ላይ አንተን ብቻ ነው የማምነው፡፡››

‹‹ምን አይነት ወንጀል ?ከባድ ነው?››

‹‹በጣም ከባድ….እጅግ በጣም ከባድ…በእድሜ ልክ ወይም በሞት የሚያስቃጣ ወንጀል፡፡››

‹‹ግን እኮ አላዛር..አባትህ ትልቅ ሰው ናቸው..በዚህ እድሜቸው የእስር ቤትን ህይወት አይችሉም ..ወዲያው ነው የሚሞቱት…ለመሆኑ ወንጀሉ ምንድነው?››

‹‹የእንጀራ እናቴን ታስታውሳታለህ?››

አላዛር ስለእንጀራ እናቱ ሲያነሳ አለማየሁ ጠቅላላ ሰውነት ጆሮ ነው የሆነው፡፡ፈራ ተባ እያለ‹‹አዎ አስታውሳታለው..ምን ሆነች?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹አርግዛ ነበር››
የሚያውቀው ነገር ቢሆንም በተሳሰረና በተወለካከፈ ድምፅ   ‹‹በእውነት….?እሱን አላውቅም ነበር››አለው፡፡

‹‹አዎ እኔም አላውቅም ነበር…እና ያረገዘችው ከሌላ ሰው ነው፡፡››

‹‹ከሌላ ሰው ?ከማን …?›

‹‹እሱን እኔ አላውቅም ..አባቴም የሚያውቅ አይመስለኝም….››

በሚርገበገብ ድምፁ በፍራቻ ‹‹እና ምን ተፈጠረ…?››ሲል ጠየቀው፡

‹‹አባቴ ልጁ የእሱ እንዳልሆነ በምን መንገድ እንደሆነ አላውቅም አወቀና ..እርጉዟን ሚስቱን ገደላት››

‹‹ምን ?ገደላት….››

‹‹አዎ ገድሎ የማላውቀው ቦታ ቀብሮታል….አሁን እሱም ሀገር ጥሎ ጠፍቶል..እና ምን እንዳደርግ ትመክረኛለህ?፡፡››

አለማየሁ በሰማው መርዶ የደነገጠው ድንጋጤ መጠን የሌለው ነው..እናትና አባቱ የሞቱ ሰሞን እንኳን እንደዛ አይነት ፍፅም ቀዝቃዛ ሀዘን አልተሰማውም ነበር ‹‹እሳቸው ሳይሆኑ እኔ ነኝ የገደልኩሽ፡፡››ሲል አሰበ፡፡

ድምፅ የጠፋበት አላዛር‹‹አሌክስ እየሰማሀኝ ነው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አላዛር ይቅርታ ይሄ ጉዳይ ከባድ ስለሆነ ላስብበትና ነገ ልደውልልህ?››አለው፡፡ከንግግሩ ድምፀት  የስሜቱን  መሰባበርን መረዳት ይቻላል፡፡

‹‹እሺ በቃ በደንብ አስብበት..ወንድሜ በጣም ተጨንቄልሀለው፡፡››

‹‹እሺ ጠንከር በል አይዞህ…ቸው፡፡››

አለማየሁ ስልኩን እንደዛጋ ወዲያው ያደረገው ነገር ሲሙ ላይ ያሉትን አድራሻ ወደቀፎው በማስተላለፍ  ስልኩን ከፍቶ  ሲሙን አውጥቶ መሰባበር ነው፡፡
ይሄ የእሱ ጥፋትና መዘዝ ስለሆነ ማንም ላይ ለመፍረድ ሆነ ለማንም ምክር ለመስጠት መብትም ሆነ ብቃት እደሌለው አምኗል፡፡በህይወት ውስጥ ያለውን እድል አሰበና ምርር ብሎ ነበር ያለቀሰው ፡፡መቼም ቢሆን ከማንም ሴት ጋር ፍቅር ፍቅር ላለመጫወትና ረዘም ያለ ግንኙነት ውስጥ ላለመግባት ወሰነ፡፡ከአላዛርም ሆነ ከሰሎሜ ከዛም አልፎ  ከአደገበት አካባቢ ከሚያውቃቸው ሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ አቋረጠ…በብቸኝነት በሶስት ወርም ሆነ በስድስት ወር አንዴ ደውሎ እንዴት ነሽ? ሚለው አሳዳጊ እናቱን  እቴቴን ብቻ ነበር፡፡

አላዛር  ግን ከአለማየሁ ምንም አይነት መልስም ሆነ ምክር ባያገኝም ከፀፀቱ ጋር ህይወቱን ቀጠለ….አባትዬውም በሄዱበት የት እንደገቡ ሳይታወቅ ጠፉ፡፡አላዛር አንገቱን ደፍቶ ትኩረቱን ስራው ላይ አደረገ፡፡በንግዱ ጠንካራ ሰራተኛ ሆነ..፡፡

ከማትሪክ በኃላ  ወደተግባረ እድ የሞያ ማሰልጠኛ ተቋም  ገብቶ የጀመረውን ኮንስትራክሽን ትምህርት አጥብቆ ገፋበት  ..ከሰሎሜ ጋር የነበራቸውም ጓደኝነት ልክ እንደወትሮ ግለቱን እንደጠበቀ ቀጠለ፡፡ እንደውም ከአራት ጓደኛሞች ሁለት ብቻ ስለቀሩ በተሻለ መተሳሰብና በመረዳዳት   ትምህርታቸውን  መማር ብቻ ሳይሆን በህይወትም መተጋገዝና መረዳዳት  ቀጠሉ፡፡እሷ ብቸኛ ስራዋ የጀመረችን የአካውንቲንግ ትምህርት መማር ብቻ ሲሆን እሱ ግን ልክ እንደተለመደው ሁለት ኃላፊነት ነበረበት፤  እየተማረ   ንግዱንም በጎን ማስኬድ ፡፡ ሱቁ እየሰራ..በጎንም ሌሎች ተባራሪ ስራዎች እየሰራ ቀጠለ፡፡እንዲህ እንዲህ እያለ ጊዜ መብረር ጀመረ ፡፡
በዚህ ጊዜ ሁሉ ሁሴን በአመት አንድ ጊዜ እየመጣ በክረምቱ የዩኒቨርሲቲ ዝግ ወቅት  ለአንድ ወር አብሮቸው ያሳልፍ ነበር፡፡በዛን ጊዜ ታዲያ ነገሮች ሁሉ የተለየ ገፅታ ይኖራቸዋል፡፡ከበፊቱ በተለየ አብረው ማሳለፍ..ብዙ መዝናኛ ቦታዎች አብረው  መሄድ ..ሌሎች ለወደፊት ትዝታ የሚሆኑ ኩነቶችን መፍጠር በአጠቃላይ አሪፍ በሚባል  ጣፋጭ ጊዜ ያሳልፈና መልሰው ወደዩኒቨርሲቲ ይልኩታል፡፡

የሆነ የህይወት ጉዞ መጀመር ነው እንጂ ሚከብደው አንዴ ቆራጥ ውሳኔ ወስነው መንገድ ውስጥ ገብተው እግር ማንቀሳቀስ ከጀመሩ  እንቅፋትና ኮረኮንች ከመሀከል ቢያስቸግርም መንገዱ ማለቁና ካሰቡት መዳረሻ መደረሱ አይቀርም ፡፡በተለይ በዚህ ዘመን ሳዕታት እንዴት እንደሚስፈነጠረሩ… ቀናቶች እንዴት እንደሚከንፉ ወርና አመታት እንዴት እንደሚበሩ አይታወቅም፡፡መስከረም፤ጥቅምት….ብለን ሀምሌና ነሀሴ ላይ እንዴት እንደምንደርስ ያስገርማል፡፡ እናም አላዛርና ሰሎሜም የጀመሩትን የኮሌጅ ትምህርት ብዙም ሳይሰላቹና መቼ ባለቀ ሳይሉ ለምረቃት በቁ፡፡ …ሁሴንም እረፍቱን አስታኮ ለምርቃታቸው አዲስአበባ ነው የሚገኘው፡በዛም ምክንያት ምርቃታቸው በጣም ደማቅና በማይረሳ ትዝታ የታጨቀበት ሆኖ እንዲያልፍ ሆኗል…ሶስቱም በየልባቸው አለማየሁም በሆነ ምክንየት ስለምርቃታቸው ሰምቶ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋቸው ሶስት አመት ከተደበቀበት ድንገት ብቅ ብሎ ያስደምመናል ብለው ይጠብቁ ነበር፡፡ያ ምኞታቸው ግን እውነት ሊሆን አልቻለም፡፡በተለይ ሰሎሜ አለማየሁን በተመለከተ  ሙሉ በሙሉ  ተስፋ የቆረጠችበት ወቅት ነበር፡፡‹‹በቃ በዚህ ጊዜ ሊያየን ካልመጣ መቼም ወደህይወታችን ተመልሶ ላለመምጣት ወስኗል ማለት ነው፡››ስትል ደመደመች፡፡…በዛም ምክንያት እሷም እስከወዲያኛው ስለእሱ  ረስታ ህይወቷን ወደፊት መቀጠል እንዳለባት ወሰነች፡፡፡ሁሴን ምርቃታቸውን በደስታና በፈንጠዝያ አብሮቸው አክብሮ ወደዩኒርሲቲው ሊመለስ ቀናቶች ነው ቀሩት፡፡ ከመሄዱ በፊት ግን  ብዙ ጊዜውን ሁለት ጓደኞቹ ጋር ነው የሚያሳልፈው፡፡አሁን በምሽት ከአላዛር ጋር ሆቴል ተቀምጠው እየተዝናኑ ነው፡፡ሰሎሜ አብራቸው የለችም፡፡

‹‹ሁሴኖ በእውነት ምርቃታችንን በጣም ነው ያደመቅክልን….› አለው አላዛር፡፡የተናገረው ከልቡ ነው፡፡እስከአሁን ምርቃታቸውን በተመለከተ ያደረገላቸውን ነገር አንስቶ የማመስገኑን እድል አላገኘም ነበር፡፡

‹‹ምን ነካህ ወንድሜ..አንተም አንተ ነህ..ሰሎሜም ያው የምታውቃት ነች…ቢቻል ለእናንተ…››

‹‹አይዞኝ በሚቀጥለው አመት በዚህን ጊዜ  ያንተን ምርቃት  ደረጃውን በጠበቀና በሚመጥንህ መልኩ ነው የምናከብረው፡፡››

‹‹አይ ..እኔ ተመርቄ የደካማ እናቴ ህይወት ለማስተካከል እንጂ ለምርቃቱ ጋጋታ ምንም አይነት ኢንተረስት የለኝም››ሲል ትክክለኛ ፍላጎቱን ሳይደብቅ ነገረው፡፡
👍6012
‹‹አውቃለሁ…ግን እኛ እያለንልህ ደግሞ ከጓደኞችህ በታች አትሆንም…አሁን እንደምታየው ትምህርት የሚሉት ጣጣ የለብኝም..ሙሉ ጊዜዬም ሆነ ትኩረቴ ወደ ስራ ነው…እና ከአሁኑ ቃል ልግባልህ የሱፍ ምናምን ወጪ እንዳያሳስብህ….ሁሉም በእኔ ነው፡፡››

ሁሴን እንባው ግጥም ብሎ በአይኖቹ ሞላ…‹‹አላዛር አንተ እኮ የተለየህ ሰው ነህ…እስከዛሬ፦ ያደረክልኝ ነገር እኮ መቼም የምረሳው አይደለም…አንተ ባትኖር በአመት አንድ ጊዜ መጥቼ የእናቴን አይን እንኳን ማየት አልችልም ነበር፡፡››

‹‹ባክህ አንተ ደግሞ አታካብድ..ለአንተ ብዬ መሰለህ..ስትናፍቀኝ እኮ ነው… መጥቼ ከማይህ መጥተህ ብታየን ይሻላል ብዬ  ነው የትራንስፖርት የምልክልህ፡፡››

‹‹ተወው በካህ…ለማንኛውም አመሰግናለሁ..በተለይ እኔ በሌለሁበት እናቴን ስለምትንከባከብልኝ የዘላለም ባለውለታዬ ነህ፡››

‹‹ባክህ አሁን ርዕስ ቀይር…በምስጋና ጋጋታ እያስደበርከኝ ነው፡፡››

‹‹እሺ ስለምን እናውራ…?››
‹‹እኔ እንጃ …ያው እንደድሯችን በመሀከላችን ንግስቷ ከሌለች ወሬያችን ስለምንድነው የሚሆነው?››

‹‹የታወቀ ነው ..ስለእሷው ነዋ…››

‹‹እና ስለእሷ ማውራት አትፈልግም?››

‹‹በጣም ፈልጋለው ግን ፈርቼህ ነው…በመሀከላችሁ ያሉ ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ሁሴን አላዛርን ጠየቀው፡፡

‹‹ያው ነገሮች እንደድሮው ባሉበት እንደቀጠሉ ነው…እሷን ከራሴም በላይ ባፈቅራትም ለጓደኝነታችን ታላቅ ክብር አለኝ…እስከአልከው ጊዜ እጠብቃለው…ልክ የዛሬ አመት አንተ ተመርቀህ ስትመጣ ..የዛን ጊዜ በተስማማነው መሰረት የውስጥ ህመማችንን እኩል እንነግራታለን…ከዛ እሷ ትወስናች››

‹‹ጥሩ ነው..ግን የአሌክስ ጉዳይስ?››ዘወትር የሚያሳስበውን ጉዳይ አነሳበት፡፡

‹የአሌክስ ምን?››

‹‹ያው ቃል-ኪዳኑ  የሶስታችንም ነው ብዬ ነው፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነህ..ቃል ኪዳኑ ሶስታችንንም ይመለከታል፡፡ግን  እስከአሁን እንደምታየው አሌክስ ሙለ በሙሉ ከእኛ ጋር ያለውን ግንኙነት ካቋረጠ ሶስት አመት አልፎታል…ምን አልባት አዲስ ነገር ተፈጥሮ በዚህ አንድ አመት ውስጥ የሚመለስ ከሆነ ጥሩ ሶስታችንም ንግስቲቱ ፊት ፍቅሯን ለማግኘት ለተማፅኖ እንቆማለን…እስከዛ እራሱን እንደሰወረ በዛው የሚገፋበት ከሆነ ግን ምን ማድረግ እንችላለን..ተፎካካሪዎቹ እኔና አንተ ብቻ እንሆናለን ማለት ነው፡፡››ሁሴንም በሀሳቡ በመስማማት ‹‹ትክክል ነህ..ሌላ ምን ምርጫ ይኖረናል?››አለው፡፡

‹‹አዎ ማድረግ ምንችለው ያንን ብቻ ነው፡፡››

ሁሴን ፀጉሩን በጣቶቹ አከክ አከክ አደረገና ‹‹ግን አንድ ጥያቄ ጠይቅሀለው እያልኩ..ቆይ አሁን እንደማያት ጭራሽ እየጎመራችና እያማረባት ነው…ሌላ አፈቀርኳት ብሎ ከእጃችን ሊሞጨልፋት የሚሞክር ጩሉሌ የለም እንዴ?››ሲል የዘወትር ስጋቱን ተነፈሰ፡፡

‹‹እሱማ የት ይጠፋል….ግን እንደምታውቀው ስንወጣም ሆነ ስንገባ አንድ ላይ ነው…እኛ ከአንደበታችን አውጥተን ባንናገርም ሰው እንደጓደኛሞች ብቻ አይደለም የሚመለከቱን ስለዚህ አብዛኛው አይኑን የጣለባት ጎረምሳ በሩቁ ተስፋ ቆርጦ ያቆማል..አንዳንዱ አይን አውጣ ቢጤ ገፍቶ ልጠጋት ካለ ደግሞ በዚህም ብዬ በዛ አደብ እንዲገዛ አደርጋዋለሁ፡፡››

‹‹ያ ማለት ጓደኛዋ ብቻ ሳትሆን ቦዲ ጋርዷ ጭምር ነኝ በለኛ››

‹‹አዎ በትክክል ገልፀኸዋል…ምን አልባት ወደፊት ቀኑ ሲደርስ ከእኔ ይልቅ ከሁለት አንዳችሁን ከመረጠች የዚህን ሁሉ አገልግሎቴን ክፍያ መክፈል ይጠበቅባችኃል››

‹‹አዎ ..በእውነት ይሄ ተገቢ ጥያቄ ነው››ብሎ መለሰለት ና ተሳሰቁ፡፡
ከዛ በሶስተኛው ቀን ከሰሎሜ ጋር ሆነው ሁሴንን ወደዩኒቨርሲትው ሸኙት፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 11 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014         
👍5112🎉1
አትሮኖስ pinned «#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ ================ ወንጀሉ በተፈፀመ በ15ተኛው ቀን ለአለማየሁ ደውሎለት ነበር፡፡ ‹‹ሄሎ አሌክስ..እንዴት ነህ?›› ‹‹ሰላም ነኝ..አንተስ..?ሰፍር ?እነሰሎሜ ደህና ናቸው?›› ‹‹ሁሉም ሰላም ነው….አንተ ጋርስ? ስልጠናው እንዴት ነው?›› ‹‹ከባድ ነው.. ግን ያው ስፖርት ስለምወድ…ለእኔ ብዙም አልከበደኝም፡፡›› …»