#ታምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡
፡
////
እየሄደች ነው… ልታናግረው…፡፡ ለምን እሱን ማናገር እንደፈለገች አታውቅም፡፡ ምን አልባት ዳግመኛ አጠገቡ ልትቆምና ያንን ወንዳወንድ ቁመናው እና ቆንጅዬ ባሪያ የሆነ መልኩን በቅርበት ለማየት ፈልጋ ሊሆን ይችላል….ናፍቋትም ሊሆን ይችላል፡፡
ንስሯ የት እዳለ በነገራት መሰረት ቀጥታ ቤቱ ነው የሄደችው..የውጩን የጊቢ በር መጥሪያ ስትጫን ዘበኛው ነበር የከፈተላት…‹‹ከመላኩ ጋ ቀጠሮ ነበረኝ ቤት እየጠበኩሽ ነው ብሎ ደውሎልኝ ነበር..?››ብላ ቀላመደች… ዘበኛው ያልተለመደ ነገር ሆኖበት .. ግራ እንደመጋባት አለና በመጠኑ ካቅማማ በኃላ እንድትገባ ፈቀደላት…
ቀጥታ ቤተኛ እንደሆነ ሰው የተንጣለለውን ግቢ ሰንጥቃ ባለአንድ ፎቅ ከሆነው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት በረንዳው ላይ ደረሰች… የሳሎኑን በር ገፋ ስታደርገው ተከፈተ…የቀኝ እግሯን አስቀድማ ግራዋን አስከትላ ወደውስጥ ከገባች በኃላ ወደኃላ ዞሯ በራፉን አንኳኳችው…
‹ከገቡ በኃላ ማንኳኳት ከገደሉ በኃላ ማዘን አይነት አይደለም እንዴ…..?››እራሷው በራሷ ነው የጠየቀችው
መላኩ የሳሎኑ መአከላዊ ስፍራ ላይ ካለችበት ወደውስጥ 4 ወይም 5 ሜትር ያህል ርቆ በመገረም አፍጥጦ እያያት ነበር….
ማንኳኳቷን ስትቀጥል
‹‹አቤት››የሚል ድምጽ አሰማ
‹‹መግባት ይቻላል..?››
‹‹ገብተሻል እኮ ››
‹‹እሺ ካልክ›› ብላ ቀጥታ የሳሎኑን በር መልሳ ዘግታ ወደእሱ አቅጣጫ አመራች ….በተገተረበት ስለማንነቷ በመመራመር ይመስለል ፈዞ እንደቆመ በስሩ አልፋ ልክ እንደቤተኛ ሶፋው ላይ ዘና ብላ ተቀመጠች….መጣና ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ
‹‹አውቅሻለሁ ልበል..?››
‹‹እኔን የመሰለች ቆንጆ ልጅ እንዴት ልትረሳ ትችላለህ..?››
‹‹ማለት..?››
‹‹ጎበዝ የዋና ተማሪህ ነበርኩ ብዬ ነዋ››
…ድንገት እንደበራለት ሰው በመደነቅ ‹‹እንዴ አንቺ እብድ ..እቤቴን ደግሞ ማን አሳየሽ..?›› አለት ‹‹ቀላል ሰው አይደለሁም ብዬህ ነበርኮ..?››
‹‹አረባክሽ.. ፉከራሽን እኮ አየነው..እኔማ አንተን ማሳሳት ካቀተኝ እንጠለጠላለው ብለሽ ስለነበረ..በቃ ይቺ ልጅ አልሆንላት ሲል እራሷን አጥፍትለች ማለት ነው..ምን አይነት ለቃሏ ታማኝ ልጅ ነች ብዬ ሳደንቅሽ ነበር የሰነበትኩት፤ለካ ዝም ብለሽ ጉረኛ ነገር ነሽ..?››
‹‹አንተን ማውጣት አቅቶኝ ሳይሆን አሳዝነኸኝ ነው የተውኩህ ››
ግድግዳውን ሰንጥቆ በመውጣት ውጭ ድረስ ለመሰማት ኃይል ባለው አይነት አንቧራቂ ሳቅ ሳቀ‹‹አሳዘንኩሽ…..?ቀልደኛ ነሽ››
‹‹ቀልድ አይደለም…የዛን ቀን የሄደክው ከፍቅረኛህ ጋር ወደሆቴል አልነበር…..?ስለ ጋብቻ ስታወሩ አልነበር....?እንድታገባህ ስትለምናት አልነበር…..?እሷ መጋባቱ ቀርቶባችሁ እስክትሞት ድረስ የቀራትን ህይወት እንደዚሁ እንድታሳልፉ ስትለምንህ አልነበር…..?ከመሞቷ በፊት ካላገባችህ እና መጽናኝ የሚሆን ልጅም ካልወለደችልህ በሞተች ቀን አብረሀት እንደምትሞት እየነገርካት ስትላቀሱ አልነበር……..?››
ይሄንን ስትነግረው እነዛ የኮከብ ክፋይ የሚመስሉ ደማቅ አይኖቹን ከወዲህ ወዲያ በመገረም እያሽከረከራቸው ነበር…..
‹‹አንቺ ክፍል ውስጥ ተደብቀሽ ስታዳምጪኝ ነበር እንዴ..?››በንዴት ጡንቻው ውጥርጥር ሲልና … ልነቃት አልነቃት እያለ ከውስጡ ጋር ሙግት እንደገተመ ከሁኔታው ያስታውቃል….
‹‹አይደለም …ክፍል ውስጥ አልነበርኩም…ግን በአካል ባይሆንም ክፍል ውስጥ ገብቼ እናንተን ምታዘብበት ሌላ ዘዴ ነበረኝ››
‹‹ምን ..?ካሜራ ..?››
‹‹አይደለም…ምንነቱን ቀስ ብዬ ነግርሀለሁ…አሁን ወደመጣሁበት ጉዳይ እንግባ››
‹‹ወደመጣሁበት ጉዳይ .. ..?በይ ሳትዋረጄ በመጣሽበት እግርሽ ሹልክ ብለሽ ቤቴን ለቀሽ ውጪ..››ከመቀመጨው ቀድሞ ተነሳ…
‹‹ሁለተኛ እንኳን እቤቴ እኔ ባለሁበት አካባቢ በድንገት ባገኝሽ እወነቴን ነው አጠፋሻለሁ…ሲጥ አድርጌ ነው የምገልሽ….››
ዘና ብላ እንደተቀመጠች መልስ መመለሷን ቀጠለች ‹‹ዝም ብለህ አትፎክር…በቁጣ እያንቧረቁ መናገር እና ፊትን ማጨማደድ የምትለውን አይነት ጭካኔ እንዲኖርህ አያግዝህም››
‹‹ምን ማለት ነው..?››
‹‹እንኳን እኔን ምንህም ላይ ያልደረስኩትን ልጅ ይቅርና ሰላምን እንኳን እንደዛ በድላህ ፍቅህን ረግጣ የገዛ ወንድምህን በማግባት ስታወድምህ ለህግ አሳልፎ ከመስጠት ውጭ ምንም ልታደርጋት አቅም አላገኘህም፡፡››
ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና ተንበርክኮ አንገቷን በማነቅ እያረገፈገፋ‹‹ማነሽ …....?አንቺን ማነው የላከብኝ....?ማነው ንገሪኝ..?››
‹‹ማንም …ምን አልባት የምታመልከው አምላክ ሊታረቅህ ፈልጎ ይሆናል…ምን አልባት እስዛሬ የፀለይከው ፀሎት አምላክ መንበር ደርሶ መልስ የማግኛህ ጊዜ ደርሶም ሊሆን ይችላል…››
፣እጁን ከአንገቷ ላይ መንጭቃ በማላቀቅ ገፈተረችውና …ዝርፍጥ ብሎ ወለሉ ላይ በቂጡ ቁጭ አለ …እዛው ባለበት አፍጦ እሷን ከማየት በስተቀር ለመነሳት አልሞከረም
‹‹ሰሚራን ባድንልህ ምን ታደርግልኛለህ..?››
‹‹ምን እየቀባጠርሽ ነው…...?ደግሞ በእሷ ልትቀልጂብኝ ነው..?››
‹‹አይደለም ..ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኝለህ..?››
‹‹ቅጠል አሽተሸ በመቀባት የምታድኚው ቁስል… ምች መድሀኒት ወይንም ጅንጅብል ጨቅጭቀሽ ከሻይ ጋር አፍልቶ በመጋት የምታድኚው ጉንፋን በሽታ ያመማት መሰለሽ እንዴ..?››
‹‹አውቃለሁ…ለአመታት በጭንቅላቷ ቆይቶ የነበረው ጥይት እና የጭንቅላት እጢ ተከትሎ…….››
አላስጨረሳትም ‹‹…በፈጠረሽ ማን ነሽ ?ምንድነው ምትፈልጊው....?ይሄን ሁሉ ገበናችኝን ስንት አመት ብትሰልይን ነው ማወቅ የቻልሺው..?››
ጥያቄውን ችላ በማለት የራሷን ጥያቄ ደግማ ጠየቀችው
‹‹ካዳንኩልህ ምን ታርግልኛለህ..?››
‹‹ እኮ እንዴት ነው የምታዲኚያት…..?የጀርመንና አሜሪካ ጠበብቶች ያቃታቸውን አንቺ እንዴት ብለሽ..?››
‹‹እኔ የተለየ መንፈሳዊ ስጦታ አለኝ …››
‹‹አላምንሽም››
‹‹እንድታምነኝ…አንድ አንተ ብቻ የምታውቀው ታሪክ ልንገርህ…እንደውም ለምን ዛሬ ያየኸውን ህልም አልነግረህም ..…››
ንገሪኝም ተይው ማለት አቅቶት በግራ መጋባት ስሜት እየዋለለ ዝም ብሎ እንዳፈጠጠባት ፈዞ ቀረ…
ጣና ሀይቅ መሀል ላይ ያለች ትንሽ ደሴት ትመስልሀለች….እሷን ከብዙ የሀገሪቷ ሀብታሞች ጋር ተወዳደረህ በጫረታ በማሸነፍ ትገዛና …በጣም ውብ የሆነ በባህላዊ መንገድ እጽብ ድንቅ ተደርጎ የታነፀ ቤት ትሰራበታለህ…በዛች ደሴት ላይ አንተ ከሰራሀት ቤት ውጭ ምንም አይነት ሌላ ቤት የለም፤ደሴቱ ሙሉውን በቡና ተክል፣በሙዝ፣በብርቱካን፣በመንደሪን፣በአፕል እና በመሰሰሉት የሚበሉ ፍራፍሬዋች የተሞላች ነች…አዕዋፍት እና የዱር እንስሳትም ከደኑ ጋር ስመም ፈጥረው ተፈጥሮን አድምቀው እና በተፈጥሮም ደምቅው የሚኖርበት ቦታ በመሆኑ ልዩ ድስታ ተሰምቶህ ይሄንን ስጦታ ላዘጋጀህላት ለሰሚራ ትሰጣታለህ…
‹‹ሰሚርዬ ቀሪ ህይወትሽን ምንም እንኳን አጭር ብትሆንም በደስታ የተሞላች እድትሆን ፈልጋለሁ…በዛ ላይ እዚህ ከእኔ እና ከተፈጥሮ ውጭ ምንም አይነት የሰው ልጅ ወደ ሌለበትና ወደማይኖርበት ቦታ ሳመጣሽ ቀሪ ዘመንሽን የብቻዬ ብቻ እንድትሆኚ በመፈለግ እና በመሰሰት ነው…ይቺ ስፍራ የእኔ እና የአንቺ ገነት ነች››ትላታለህ፡

👍76❤6😁3🥰2
እሷም በመፍለቅለቅ እና ስጦታህን ከልቧ በደስታ በመቀበል‹‹የእኔ ውድ….እዚህ ሰፍራ ከንተ ጋር አንድ ሳምንት እንኳን መኖር ዘላለም የመኖር ያህል ጣዕም ይሰጠኛል.. አፈቅርሀለው››ትልሀለች
‹‹ካፈቀርኝማ አግቢኝ››ትላታለህ
‹‹እንዲህ አድረገህልኝማ እንዴት እንቢ ልልህ እችላለሁ…..?ዛሬውኑ አገባሀለሀ…እዚህም ደሴት ላይ ምታምር ልጅ ወልድልሀለሁ… ስሟንም ዘሀራ ትላታለህ ..ትርጉሙም አበባ ማለት ነው››ትልህና ያልጠበቅከውን የምስራች ነግራህ ታስፈነድቅሀለች፡፡አንተም በሰማሀው ነገር ሰክረህ ጮኸህ ስትጠመጠምባት‹‹..አረ አነቅከኝ …ምነካህ …››ብላ ከጎንህ የተኛችው የእውነቷ አለም ሰሚራ ቀስቅሳ ነው ከእንቅልፍህም ከህልምህም ያፋታችህ…
ከተዘረፈጠበት ወለል..ዝልፍልፍ እንዳለ እየተጎተተ ተነሳና ሶፋው ላይ ተቀመጠ..ድክምክ ባለ እና እጅ የሰጠ በሚመስል የተሸነፈ ድምጽ‹‹ይህንን እኮ ለሰሚራዬ እንኳን እ
አልነገርኳትም… ለብቻዬ አልሜ በውስጤ ብቻ ቀብሬ አስቀርቼው የነበረ ፍቺውን በማብሰልሰል ላይ የነበርኩት ጣፍጭ ህልሜ ነበር….እንዴት ልታውቂ ቻልሽ?››
‹‹ዋናው ማወቄ ነው…..አሁን እንዳድንልህ ትፈልጋለህ..?››
‹‹በጣም…አትቺይም እንጂ ከቻልሽ በጣም እድታድኚልኝ እፈልጋለሁ….››
‹‹ካዳንኩልህ ምን ታደርግልኛለህ…..?››መልሳ ወደ መነሻ ጥያቄዋ
‹‹ህይወቴንም ከፈለግሽ..አንገቴን ቀንጥሼ ለመስዋዕትነት በሰሐን እንዲቀርብልሽ አደርጋለሁ ››
‹‹ጥሩ ስጦታ ነው…..ግን አንገትህን አልፈልግም››
‹‹እሺ ሙሉ ንብረቴን ምንም ቤሳ ቤስቲ ሳትቀር ሰጥሻላሁ››
‹‹እሱንም አልፈልግም….እኔ በንብረት የምደሰት አይነት ሰው አይደለሁም››
‹‹እሺ ምን ትፈልጊያለሽ..?››
‹‹ሰሚራን ከዳነች በኃላ ትተዋታለህ..ትተዋት እና እኔን ታገባለህ››
‹‹ዝም አለ…በቃ ዝም …..በድን የሆነ የሚጮህ ዝምታ….ድምፅ ያለው ዝምታ…..››
‹‹እ ምን አልከኝ..?››አለችው ዝምታው በውስጧ የፈጠረውን ስቃይ መቋቋም ሲያቅታት ልትረብሸው ፈልጋ…
✨ይቀጥላል✨
#አደራ በዛውም YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ አያስከፍልም👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቻናሉም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://tttttt.me/atronosee

👍83❤12👏6😢6👎5🥰1
👁🍃በ'ነሱ ቤት🍃👁
🍃ክፍል አስራ ዘጠኝ🍃
❤🍃❤🍃❤🍃❤
ሰመረ የጌታነህ ልምምጥ ገርሞታል እውነት አብ ላካትን ወዷት ነው ለማለት በፍፁም አልቻለም ምክንያቱም አብላካትን የመጀመሪያ ጊዜ ተቸግራ ያገኟት ጊዜ ያን ያክል ለጌታነህ ልዩ የምትሆን ሴት ሆና አልነበረም ። ይልቁንም ጌታነህ በአለባበስም ሆነ በኮንፊደንስ የሚንቀቸው የሚጠየፋቸው አይነት ሰው አይነት ነበረች ።የአብላካት ብቸኛ እና የሚያስመካ ነገር አላት ከተባለ ቁንጅናዋ ነበር እናም ልጅነቷ ። ታዲያ ጌታነህ እስካሁን ድረስ አብላካትን የሚጨቃጨቃት ለምንድነው ? ከዛንቀን በዋላ አይቷት አያውቅም በስልክ ሊያማልላት ቢሞክርም አልተሳካለትም ።እና ለምን አይተዋትም ነው ከ'ኔ ጋር እልህ እየተጋባ ነው ? ' ብሎ አሰበ ሰመረ የጌታነህ ጓደኝነት ሲበላሽበት ታየው ።
"ሰሙ ታውቃለህ እቺ ትንሽ ልጅ በጣም አስቸጋሪ ነች ኪኪኪኪ ነገር ግን በስልክ ስለሆነ ነው እንጂ በአካል ያገኘዋት ለት የአስር ደቂቃ ስራ ነች ኪኪኪ "ብሎ ሳቅም ቀልድም አስከተለ
"አልጠየኩህም !ስለዚ ምንም ነገር ለኔ ለማስረዳት አይጠበቅብህም "አለው ሰመረ በውሃ የተሞላውን ብርጭቆ አንስቶ ለመጠጣት እየተዘጋጀ
"ኪኪኪኪ አታስመስል ያቺ ልጅ እንድትነካብህ አትፈልግም ያልገባኝ እሷ ላይ ያለህ ፍላጎት ነው"አለው እንየውም እንዲያግዘው እየነካካው
"እኔ በአንዲት ትንሽ ልጅ ላይ ምን ፍላጎት ይኖረኛል አንተን አደረከኝ "አለው። ውስጡ ደሞ ሌላ ወሬ አወራው እውነት አብላካት ቅድም እንዳየዋት ትንሽ ልጅነት ይታይባታል ።በጭራሽ ቀልቤን ገፋው አይደልእንዴ ።በአስተናጋጁ ሰሚርስ አልቀናውም ነበር ።ብሎ አስቦ መልሶ በራሱ እንደማፈር አለ ።ወይጉድ ማፊ 'ወንድ ልጅ 'ጅብ ነው ያገኘውን ነው የሚበላው 'ያለችው ትዝ አለው ።
"ተወው እኔን አያድርግህ ኪኪኪኪ እኔን ለመሆን ዳግም መፈጠር አለብህ እኔ ለሴቶቹ መዳኒት ነኝ ኪኪኪ ፈዋሽነቴን መደበቅ አይሆንልኝም ለሁሉም አለውላቸው ለሚያቁኝም ለማያቁኝም ።አቢ ደሞ የማታውቀው ዓለም አለ እሱን የማሳየት የኔ አላፊነት ነው ።ታያለ በዚ እሷ በጭራሽ አትከፋም የሚያስፈልጋት ገንዘብ ነው እንዳየውት ከሆነ ።እና እሷ እንትን ትሰጠኛለች እኔ ገንዘብ እሰጣታለው አለቀ ኪኪኪኪኪ"ብሎ አሽካካ ።እንየው አብሮ አሞቀ
"አይ አንተ የተመታህ እኮ ነህ ! ችኮቹ አሳዘኑኝ ኪኪኪኪ"ብሎ እንየውም ሳቀ። ሰመረ ወሬው አልተመቸውም ከጌታነህ ጋር መነጋገር የባስ መቃጠል ሆኖበታል ።አብላካትን ካገኙ ጀምሮ ጓደኝነታቸው ብሽሽቅ የሞላበት ሆኗል ።
ምሽታቸው ብዙም ውበት አልነበረውም ።ጌታነህ ሲያሽካካ እንየው ሲያሽቃብጥ ።ሰመረ ሲቆስል ነበር ያሳለፉት ። በመጨረሻ ሰመረ እንደተለመደው ተሰናብቷቸው ከሆቴሉ ሲወጣ ቅሬታቸው ጨመረ ።ከአስተሳሰባቸውና ከአመለካከታቸው ጋር ባለመሄዱ ሰመረን ማማት ጀመሩ ። ማነኝ ብሎ ነው፣ እሱኮ እንዲ ነው ፣እንዲያነው ፣እንትንም ብዙ አይደለም ፣ ማፊ እየተጫወተችበት ነው፣ አልቻላትም ፣ስራላይም ብዙ አይደለም የቤተሰቡ ሀብት ባይኖር ኖሮ ባዶ ጭንቅላት እኮ ነው፣ ምናምን ምናምን .....እያሉ ሰመረን ማማታቸውን ቀጠሉ .......
👁አብላካት ሰመረን ማሰቧን አላቆመችም ።ዳግም ካየችው ጀምሮ ከአይምሮዋ ሊወጣላት አልቻለም ።ስራም ላይ ሆና ስትተኛም ሰመረን አለማሰብ አልቻለችም ቁመናው እርጋታው ድንገት ቱግ የሚለው ነገር ይመላለስባታል ። በራሷ ተገርማለች በቀን በቀን ባገኘው ምን ልሆን ነው ትላለች ለራሷ ። የሰመረን ስልክ አለመጠየቋም ይቆጫታል ።ደሞ እሱ ስልኳን አለመጠየቁም ትዝ ይላትና ።ምናልባት ንቆኝ ከሆነስ ብላ እዝን ትላለች ።ለነገሩ እኔ ማነኝና ነው ያንን የሀብታም ልጅ የምመኘው እሱ ከኔ በጣም የላቁ ሴቶችን እንደልብ ማግኘት ይችል የለ ። አጉል ምኞት ብላ ትተክዛለች ።
አስተናጋጁ ሰሚር የአብላካት ፀባይ እየተቀየረበት ሲመጣ ይታወቀዋል እንደበፊቱ በቀላሉ አትስቅለትም መተከዝ አብዝታለች ። በሆነ ባልሆነው ድንገት ትቆጣለች ።በዚ ሁኔታዋ ግር ቢሰኝም ።አንዳች ነገር እንዳለ ግን ጠርጥሯል ስለዚህም ።በተለያየ አጋጣሚ የሰመረን ስም እያነሳ እየፈተሻት ነው ።እውነትም የሰመረ ስም ከተነሳ ጆሮዋን አቅንታ ታዳምጠዋለች እናም ። ስለሷ ፈራላት ፍቅር ይዟት ከሆነ ምን ሊፈጠር ነው ......
ይቀጥላል......
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

👍100🥰14❤8👏3😁2🤔1😱1
#ታምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
‹‹ግን ምን አይነት ዳቢሎስ ነሽ..?››ሙትት ባለ ድምጽ
‹‹ዳቢሎስ እንኳን አይደለሁም…. ምን አልባት የዳቢሎስ ልጅ ልሆን እችላለሁ…ግን የምትወዳትን ልጅ ላድንልህ እኮ ነው እያልኩህ ያለሁት .. ..?እንደዚህ አይነት በጎ ተግባር ዳቢሎስ ያሰኛል እንዴ..?››
‹‹አዎ ዳቢሎስ ፍቅር አያውቅም..ፍቅር የማያውቅ ደግሞ ምንም ነገር በነፃ መስጠት አይችልበትም፤ለሰጠሸ ጥሩ የሚመስል ነገር ሁሉ ተመጣጣኝ የሆነ መከራና ስቃይ ያስከፍሉሻል…››
‹‹አልገባኝም..?››
‹‹ለምሳሌ …ያለፋሽበትን ገንዘብ ተመኝተሸ ስጠኝ ብትይው በደስታ ነው የሚሰጥሽ፤የገንዘብን ባለቤት ግደይና ነጥቀሺው ውስጂ ብሎ መንገድን እና ብልሀቱን ያሳይሻል…ከዛ ትገድይና ገንዘብን ታገኚያለሽ ሀብታም እና በፀፀት የሚሰቃይ ሰው ትሆኚያለሽ፡፡አንቺም ፍቅረኛህን ላድንልህ..እና ልንጠቅህ እያልሺኝ ነው…፡፡ያው እኮ ነው በስጋ ከመሞት ታድኛታለሽ ከዛ ፍቅርን በመንጠቅ በመንፈስ ትገያታለሽ…እኔንም እንደዛው፤ታዲያ አንቺ ዳቢሎስ ካልሆንሽ ማን ይሆናል....?››አላት ምርር ባለ የመጠየፍ ንግግር፡
‹‹እሺ እንግዲያው ይቅርብህ…ሁለተኛ አረብሽህም፤ደህና ሁን››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና እንደ አመጣጧ ሳሎኑን ሰንጥቃ በርፍን ከፍታ ወጣች እና መልሳ ዘግታ መንገዶን ቀጠለች…የግቢው አማካይ ስፍራ ስትደርስ ነበር የበር መከፈት እና ‹‹ማን ነበር ስምሽ..?››የሚል ከሙታን መንፈስ የወጣ የሚመስል ድምጽ ከጀርባዋ የተሰማው
እርምጃዋን ገታችና ቀኝ ኋላ ዞራ ‹‹ሶፊያ››ስትል መለሰችለት
‹‹ከቻልሽ አድርጊው..አድኚልኝ ፤ተስማም..ቼ…ያ….ለሁ››አላትና ከእሷ ምንም አይነት መልስ ሳይጠብቅ ፊቱን መልሶ ወደውስጥ በመግባት በራፉን በመዝጋት ከእይታዋ ተሰወረ ..
‹‹እውነትም ዳቢሎስ ነገር ነኝ እንዴ..?….ምን እያረግኩ ነው…...?››ስትል አሰበች፡፡ቅድም እዚህ እሱ ጋር ስትመጣ ይሄንን ለማድረግ አልነበረም…ዝም ብላ ፍቅረኛው እደምታድንለት ልትነግረው እና በተስፋ ልታስፈነጥዘው ብቻ ነበር ፍላጎቷ…ያደረገችው ግን ተቃራኒውን ነው..በደስታ እና ሀዘን መካከል ነፍሱ ተንጠልጥላ እዲሰቃይ ፈረደችበት …
‹‹የእውነት ግን ያልኩትን አደርገዋለሁ…..?እሷን አድኜ እሱን ነጥቄያት አገባዋለሁ…..?.ማግባትስ በእውነት እኔ የምፈልገው ነገር ነው....?ወይስ በስቃዩ ለመደሰት…..?››ብላ ተደራራቢ ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡
ለማንኛውም ዛሬ ማታ ከንስሯ ጋር ለመብረር አቅዳለች….ለልጅቷ የሚሆን መድሀኒት የት እደሚገኝ ፍንጩን አግኝታለች ….ቦረና ባሌ መካከል መዳ ወላቡ አካባቢ ነው ለሰሚራ ፈውስ የሚሆነው መድሀኒት ሚገኘው….፡፡
የየትኛውም ሀገር አቨዬሽን የማይቆጣጠረው በረራ ላይ ነች፡፡ግን ደህንነቱ ፍፅም የተረጋገጠ በረራ ….ከየትኛውም አይሮፕላን ጋር እጋጫለሁ ወይም አሞራና ወፎች ተላትመውብን አቅጣጫ ያስቀይሩናል…ነዳጅ አልቆ ወይም ሞተር ጠፍቶ ችግር ላይ እንወድቃለን ብላ የማትሰጋበት ዥዋዝዌ የመጫወት ያህል ዘና የሚያደርግ በረራ…. ይሄን አይነት በረራ ሳታካሂድ ሶስት ወራት ስላለፋት ናፍቆት ነበር…
እየሄድ ያለው ከአዲስ አበባ ወደ መዳወላቡ ነው ፡፡መዳወላቡ የት እንደምትኝ መገመት ካቃታችሁ..ኬንያ ድንበር አካባቢ ብትሉት አካባውን ለመገመት ይቀላችኋል ፡፡እየበረሩን ያለነው ከንስሯ ጋር ነው…፡፡እሱ ክንፎች መሀከል ዘና ብሎ ቁጭ ብላለች….
ከመሬት ያሉበትንን ከፍታ ገምታ ለመናገር አትችልም ..…ግን ትንሽ ግልፅ ለማድረግ ምሳሌ ለመስጠት ያህል በዚህ ሰዓት ( ከምሽቱ ሶስት ሰዓት አካባቢ ነው) ሻሸመኔ ከተማ አካባቢ ደርሰዋል..እላይ ባሉበት ከፍታ ላይ ሆነው ከተማዋ ቁልቁል ስያዮት ከእሷ ቤት ጊቢ ብዙም ሰፍታ አይታያትም….ጭልጭል የሚሉ አንድ ቦታ የተሰበሰቡ መብራቶች ናቸው እንደምልክት የሚታዩት..
የሚፈልገበት ቦታ ላይ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነው የደረሱት…ከአውሬ ድምጽ እና ከጥቅጥቅ ጨለማ በተጨማሪ ብዙ ድምጽ ይሰማል..የደረቁ ቅጠሎች በንፋስ ተገፍተው ከዛፍ ሲወድቁ ይሰማል…..ካረፍበት ተራራ ወገብ ላይ እየፈለቀ ቁልቁል ወደ ታች እየተምዘገዘገ የሚወርድው አረፋ ደፋቂ ፏፏቴ ድምጽ በጣም ይሰማል…የብዙ አውሬዎች መጣራራት እና ማስካካተ ድምጽ ይሰማል…. ….
‹‹የቱ ነው መድሀኒቱ….?››ጠየቀችው ንስሯን
አንድ ከእሷ ቁመት ብዙም የማትበልጥ ቋጥኝ ላይ ዘና ብሎ ቁጭ በማለት ዝም አለት
የሚያስበውን ማወቅ ስለፈለገች..‹‹አዕመሮህን ክፈትልኝ…..….?››ስትል ጠየቀችው… ቁልፍ አደረገና ችላ አለት ..አንዳንዴ እንዲህ ግግም ብሎ ያስቸግራታል..
‹‹ምን እያሰብክ ነው… ….?ለሊቱን እዚሁ ጫካ ውስጥ ከአውሬ ጋር እናሳልፍ እንዴ…….?››ጠየቀችው
አዕምሮው ውስጥ ሰርስሯ እንዳትገባ እንደከረቸመባት በሹፈት መልክ አንገቱን አሸከረከረባትና ጀርባውን ሰጣት…በቃ ምንም ማድረግ አልችለችም …እስኪለቀው ድረስ መጠበቅ እንዳለባት ስለተረዳች እራሷን አረጋጋች..የሆነ የሚጠብቀው ወይም ለጊዜው ያልጣመው ነገር አለ ማለት ነው ስትል አሰበች..ተወችውና አካባቢውን በመቃኘት ዘና ማለት ጀመረች..
ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ ስታይ.. በአካባቢው በቅርብ ርቀት ከሚገኙ የገጠር መንደሮች ጭል ጭል የሚሉትን የኩራዝና የፍኖስ መብራቶችን ..ወደ ላይ አንጋጣ የዘወትር አጫዋቾን ጨረቃን ስትመለከት ሰዓቱ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ሆነ …ንስሯ ፀባይ ላይ ምንም የተለወጠ ነገር የለም …አሁንም የነበረበት ቋጥኝ ላይ በተመስጦ… አረ እንደውም የፀሎት በሚመስል ሁኔታ ያለእንቅስቃሴ አንገቱን ወደጨረቃዋ አንጋጦ ተደምሟል ..
የተቀመጠችበት የወደቀ የግንድ ጉማጅ ቂጧን ስላሳመመት ተነሳችና ቀስ እያለች እሾህ እንዳይቧጭራ እና አውሬ ጉድጋድ ውስጥ ተንሸራታ እንዳትገባ እየተጠነቀቀች ወደ ፏፏቴው ተራመደች… እንደደረሰች ሙሉ ልብሷን ፓንቷንም ሳታስቀር ውልቅልቅ አድርጋ ገባችበት… ፏፏቴው ከላይ ከአለቱ እየተላተመ መቶ ጭንቅላቷ ላይ ሲያርፍ ያለውን ኃይል መቋቋም አቅቶት ልትወድቅ ነበር.. ለጥቂት ነው በአቅራቢያዋ የጋጠማትን የግንድ ቅርንጫፍ ይዛ የተረፈችው‹‹..ደግሞ ውሀው እንዴት አባቱ ይሞቃል…….?››አለችና ድክም እስኪላት ድረስ ሰውነቷን እየተገለባበጠች አስመታችውና ወጥታ ልብሷን ለብሳ ወደ ንስሯ ተመለሰች፡፡
ስሩ እንደደረሰች ከፊት ለፊቱ ቆማ በትኩረት አየችው…መልኩ ተለየባት… የሆነ አመድ ላይ የተንከባለለ አህያ መስሏል..እንዴ ምን ላይ ተንከባሎ ነው….?..እዚህ ሰውነት ላይ ነው እንዴ ተጭኜ የመጣሁት…….?ነው ወይስ እኔ ውሀ ውስጥ ሳለው የሆነ ነገር ከሰማይ አመድ ነፋበት..….?አረ አመድ ብቻ አይደለምል አንገቱንም መሸከም አቅቶታል…››ስለንስሷ ቴና ሀሳ ገብቷት መነብሰልሰል ጀመረች
‹‹ምን ሆንክ….?››
አዕምሮውን ቀስ እያለ ከፈተላት፡፡እሷም እንደምንም እራሷን ለማረጋጋት ሞከረችና ወደአዕምሮው ገባች…አዎ መድሀኒቷን አየቻት …እሷ ካለችበት በ5 ሜትር ያህል ርቀት ላይ ትገኛለች…የተለየች አይነት ልዩ ተክል ነች ….?የአንድ ሰው የማህል ጣትን ነው የምታክለው…የበቀለችው ሌላ ትልቅ የብሳና ዛፍ ላይ ጥገኛ ሆና ነው….የሆነ ሀመራዊ አይነት የተለየ ብርሀን ትረጫለች…

👍71❤12😁1
‹‹እንዴ ታዲያ እንዲህ ምን ዝልፍልፍ አደረገህ..….?ሄጄ ቀንጥሼ ልምጣና የመልስ ጉዞችንን እንቀጥላ.››
አዕምሮዋ ላይ መልዕክት አስቀመጠላት..‹‹ልክ ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ ነው መቀንጠስ ምትችይው….›››
ሞባይሏን አወጣችና አብርታ ሰዓቷን አየች..5፡20 ይላል
‹‹እና ገና 40 ደቂቃ መጠበቅ አለብን….?››
‹‹ የግድ ነው››
‹‹በቃ እንጠብቃለን…አንተ ግን ምነው እንዲህ አዘንክ ደስ አለለህም….….?››
‹‹መዳኒቱን ጥለን እንሂድ››አለት..ያልጠበቀችው ምክረ-ሀሳብ ነው
‹‹እንዴ ለምን….? እዚህ ድረስ በዚህ ለሊት የለፋነው ለመድሀኒቱ አይደል እንዴ….? ››
‹‹አዎ ቢሆንም ጥለነው እንሂድ››
‹‹እንዴ ምን ነካህ .. ….?በዚህ አይነት ሁኔታ እስከዛሬ ብዙ ሰዎች አድነናል…አይደለም ከኢትዬጵያ ሱዳን ኤደን ባህረሰላጤ.. ኢራቅ ድረስ እኮ ሰውን ለማዳን የሚሆን መድሀኒት ፍለጋ ሄደን በስንት ልፋትና ጥረት አግኝተን ብዙ ሰው አድነን እናውቃለን..መድሀኒትን ያለበት ቦታ በእንደዚህ ሁኔታ ቀርበን ግን አንድም ቀን ትተነው እንመለስ ብለሀኝ አታውቅም››
‹‹ይሄ የተለየ ስለሆነ ነው››
‹‹ምንድነው የተለየ..….? ልጅቷን አያድናትም….?››
‹‹ያለምንም ጥርጥር ያድናታል…. ››
‹‹እና ታዲያ..….?ገባኝ ልጅቷን ከዳንኳት በኃላ ባሏን ስለምወስድባት አሳዝናህ ወይም እኔ ያልሆነ ነገረ እንዳልሰራ
ለመካላከል ነው አይደል..….?››
‹‹አይደለም….….?ይሄ ተክል የአባትሽ ዘመዶች በምድር ላይ የበተኑት ተክል ነው…ይሄንን ያየሽውን ተክል ማንም ሰው በዓይኑ ማየት አይችልም..››
‹‹እኔ እኮ እያየሁት ነው..››
‹‹አንቺ ያየሽው የአባትሽ ደም በውስጥሽ ስላለ ነው››
አባተሽ የሚለውን ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ሲደግመው ነው ያስተዋለችው
✨ይቀጥላል✨
#አደራ በዛውም YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ እያደረጋቹ አይደለም አያስከፍልም እባካቹ እያረጋቹ ለሚለቀቁት ታሪኮች እንደክፍያ ቁጠሩት👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቻናሉንም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇

👍93❤13👏6😱4🥰2🔥1
#ታምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
‹‹የአባትሽ ዘመዶች ነው ያልከው….?››
‹‹አዎ የአባትሽ ወገኖች … ይሄንን ተክል በምድር ላይ እንዲበቅል አድርገው ሲበትኑት ለመድሀኒትነት እንዲሆን አስበው አይደለም…››
‹‹እና ለምድነው….?››
‹‹አንቺን ለማግኘት….››ብሎ ጭራሽ ግራ አጋባት
‹‹እንዴት አድርገው ነው እኔን የሚያገኑኝ…….?ደግሞ የት ናቸው….?››
‹‹የት እንዳሉማ ታውቂለሽ….››
‹‹እና እንዴት ነው የሚያገኙኝ ….?››
‹‹ልክ ያቺን ተክል ስትቀነጥሺ ቀጥታ መልእክቱ እነሱ ጋር ይደርሳል››
‹‹እወነትህን ነው….?››ውስጧ ፈነጠዘች..አባቷ የማግኘት ምኞት ሳታስበው አዘለላት..የእናቷን እውነት የማረጋጋጥ ፍላጎት…
‹‹እና አሪፍ ነዋ..ያለሁበትን ካወቁ ይመጣሉ አይደለ..….?አባቴም ይመጣል አይደል….?››ጠየቀችው
‹‹አይ አባትሽ በጥብቅ እስር ላይ ስላላ መምጣት አይችልም.. ወደዚህ ምድር በመጣ ጊዜ ሳይፈቀድለት ከሰው ጋር በፍቅር በመቆራኘትና አንቺን ስለወለደ ይሄው ባንቺ እድሜ ሙሉ እንደታሰረ ነው››አንጀቷ ተላወሰ..በምድር ላይ ታስሮ ቢሆን ኖሮ የፈጀውን ያህል ይፍጅ እንጂ መንግስትንም ገልብጣ ቢሆን አባቷን ታስፈታው ነበር
‹‹እና ታዲያ ዘመዶቹም ቢሆን ይምጡ ምን ችግር አለው….?››
‹‹ሚመጡት አንቺን ለመውሰድ ነው››
ደስ አለት..ደነገጠችም ‹‹ወዴየት ነው የሚወስድኝ….?››
‹‹ወደራሳቸው አለም….››
‹‹እኔ መሄድ ካልፈለኩስ….?››
‹‹ፈለግሽም አልፈለግሽም ይወስዱሻል …ምንም አይነት ምደራዊ ኃይል አንቺን ከመውሰድ አያግዳቸውም….››
ለአምስት ደቂቃ በትካዜ ውስጥ ገባች…ሌላ አለም የማየት ፍላጎት… አባቷን እና ዘመዶቹን የማወቅ ፍላጎት..ደግሞ ይህቺን ምድርስ….?
‹‹ቆይ ሄጄ ሁሉን ነገር ካየሁ በኃላ ተመልሼ ወደምድር መምጣት አልችልም….?››
‹‹አይመስለኝም… ብትመለሺም እንደዚህ ሆነሽ አይደለም…ሙሉ በሙሉ ተቀይረሽ.. ሙሉ በሙሉ እነሱን ሆነሽ..የእነሱን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው ሚሆነው.ያ በእነሱ ፍቃድ ላይ የተመሰረተ ነው.ከፈለጉ እስከወዲያኛው ዳግመኛ ምድርን ላትረግጪ ትችያለሽ፡፡››
‹‹በቃ ይሁን.. ለእኛም እዛ መኖር ይሻለናል..የተለየ ዓለም እኮ አሪፍ ነው..ይቺን ዓለም እንደሆነ በተቻለ መጠን በርብረናታል…ምን ይቀርብናል….?››
‹‹እና ወሰንሽ››
‹‹አዎ ባክህ እንደውም አሪፍ እድል ነው››
እንግዲያው ተዘጋጂ… ከአምስት ደቂቃ በኃላ ሄደሽ መቀንጠስ ትችያለሽ..ከቀነጠስሽ በኃላ ግን አንድ ሳምንት ብቻ ነው በምድር የመቆየት እድል የሚኖርሽ… ልክ የዛሬ ሳምንት በዚህን ሰዓት ካለሽበት ቦታ መጥተው ይዘውሽ ይፈተለካሉ››
‹‹አንድ ሰምንት..አንድ ሳምንት ፈጠነ..ግን ቢሆንም ቀላል ቀን አይደለም….ብዙ ነገር እንሰራበታለን…እናቴን ሄደን እንሰናበታለን..የልጅነት ጎደኞቼን እሰናበታለሁ… አሪፍ ነው..አንድ ሳምንት ይበቃናል..››አለችና ወደተክሏ ተራመደች..
ደረሰችና ልክ ድፍን 6 ሰዓት ሲሆን ከብሳናው ዛፍ ቅርንጫፎች መካከል እጇን ዘረጋችውና ጨበጠችው… ቀነጥሰዋለሁ ስትል በእጇ ሟሞና እንደቅባት ተሙለጭልጮ ወደሰውነቷ ሲገባ ታወቀት… ደነገጠች የቀነጠስችው መስሏት ነበር… እጇ ላይ ግን ምንም ነገር የለም… እጇ የተለየ ቀለም እያመጣ ነው ..ሀመራዊ እሳት መሰል ቀለም… በመላ ሰውነቷ እየተራወጣ ከተዳረሰ በኃላ አንዘርዝሮና አንቀጥቅጦት በአፏ የቴንስ መጫወቻ የምታክል ድብልብል እሳት ብልቅ ብሎ በመውጣት እንደሮኬት ተተኩሶ ወደሰማይ ተምዘገዘገ ..እያየችው አየሩን ሰንጥቆ ተሰወረ..ግራ ጋባት …እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከረች ወደንሰሯ አዕምሮ ተመለስችና ‹‹ምን እየሆነ ነው….?››ጠየቀችው
‹‹በቃ ጨርሰናል እንሄድ››
‹‹እንዴ መቀንጠስ አልቻልኩም እኮ ..እጄ ላይ ምንም የለም….?››
‹‹እጅሽ ላይ ምን ያደርግልሻል …ተክሉ እኮ በመላ ሰውነትሽ ገብቶ ተዋሀደሽ..አሁን መዳኒቱ ተክሉ ሳይሆን አንቺ ራስሽ ነሽ..በዚህ የሳምንት ጊዚ ውስጥ የፈለግሽውን ማዳንም የፈለከግሽውን መግደልም ትችያለሽ..››
‹‹ደስ ሲል ››
‹‹ደስ አይልም…››አለና ከመጣ ጀምሮ ተዘፍዝፎበት ከነበረው ቋጥኝ ላይ ክንፉን አርገፍግፎ ተነሳን ማጅራቷን ይዞ ወደሰማይ ተምዘገዘገ ….ወደጀርባዋ ዞረና ተጣበቀባት… ወደ አዲስአባ ተመልሰው እቤታችን ሲደርሱ ከምሽቱ 8 ሰዓት አልፎ ነበር… …
‹‹ወይኔ ድክም ብሎኛል..ግን መድሀኒቱን ስላገኘን ከአባቴ ወገኖችም ጋር ልንገናኝ ስለሆነ ደስ ብሎኛል…አንተስ ደስ አላላህም….?››ለመተኛት ወደ አልጋዋ እያመራች ነበር ምትናገረው
‹‹በጣም ከፍቶኛል››አላት ንስሯ
ደነገጠች‹‹ለምን….?››
‹‹ከንቺ ጋር የምኖረው ..በህይወትም የምቆየው ለሳምንት ብቻ ስለሆነ››
በህይወቷ እንደዚህ አይነት ድንጋጤ ደንግጣ አታውቅም.‹‹.እንዴ የእኔ ንስር ሟች ፍጡር ነው እንዴ…….?›ብላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰበችብት ጊዜ ነው
‹‹ጥዬህ የምሄድ መስሎህ ነው..አብረን እኮ ነው የምንሄደው››
‹‹ይዘሺኝ መሄድ አትቺይም››
‹‹ለምን….?››
‹‹እኔ መጀመሪያም ከዛ ነው የመጣሁት…ለአባትሽ ብዬ እና አሁን ተመልሼ ለመሄድ ፍፅም አይፈቀድልኝም፡፡››
‹‹በቃ ይቀራላ ..እስከዛሬ ካንተ ጋር እንጂ ከእነሱ ጋር አልኖርኩ.. ምን ያደርጉልናል እነሱ መቅረት ይችላሉ››
‹‹እሱማ ጊዜው አለፈ..ቅድም ከአፍሽ የወጣችው እሳት አነሱ ጋር መልዕክት ይዛ የምትሄድ ነች…ወደድሽም ጠላሽም አንቺን ይወስዱሻል..እኔ ደግሞ ካለአንቺ ህይወት የለኝም …ተነጥለሺኝ እንደሄድሽ ወዲያው በዛኑ ሰዓት እሞታለሁ..››
‹‹እንዴ እሞታለሁ ማለት ምን ማለት ነው….?ይሄንን ታዲያ ተክሉን ከመቀንጠሴ በፊት ለምን አልነገርከኝም….?››
‹‹ውሳኔሽ በእኔ ላይ እንዲመሰረት ስላልፈለኩ ››
‹‹ያምሀል እንዴ . ….?.ካንተ ሚበልጥብኝ ነገር አለ…….?
ህይወቴ እኮ ነህ..››አበደች ጮህች ፕሮፌሰሩ ከእንቅልፋቸው ባነው በራፏን እስኪያንኮኩ ድረስ ግቢውን አተረማመችው …፡፡
✨ይቀጥላል….✨

👍111😢31❤20🔥5👏5🥰4
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
ለሊቱ ያለእንቅልፍ ነው ያለፈው….የጣር ለሊት…የስቃይ ለሊት…፡፡ደግነቱ ፕሮፌሰሩ ለሊቱን ሙሉ አብረዋት ነው ያሳለፍት…..ይሁን እንጂ እሷ ባዘነች መጠን አብረዋት እያዘኑ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም..ግን በታታሪት ሲያዳምጧት እና ደረቅ አልኳል ሲያጣጧት ነበር.. ወፎች የለሊቱን መንጋት የምስራች ሊያበስሩ ሲንጫጩ ድምጻቸው የተሰማው…
ሁለት ጠርሙስ ብላክ ሌብል ጠርሙስ ጨርሰዋል..እሷ አንድ ጠርሙስ ከግማሹን ሳትጨርስ አልቀርም፡፡በንዴት፤ በስጋትና በብስጭት ያወራችው ወሬ ቢቀረብ እና ወደ መጻሀፍ ቢገለበጥ አንድ ደለብ ያለ መጽሀፍ ይወጣዋል፡፡
‹‹ፕሮፌሰር ምን አቀበጠኝና ተክሉን ቀነጠስኩ..….?ምን ቅብጥ አደረገኝ….?››
‹‹እንደነገርሺኝ እኮ ሙሉ በሙሉ ሚያመጣውን መዘዝ አልተረዳሽም ነበር››
‹‹እኮ ረጋ ብዬ ጊዜ ወስጄ ማሰብ ነበረብኝ…ንስሬ እንኳን ሊነግረኝ ባይፈልግ…ጎትጉቼ ሙሉውን መዘዝ መረዳት ነበረብኝ፡፡››
‹‹ግን እርግጠኛ ነሽ ..እንደዚህ ያለ ንስርሽ ለመሄድ እንደምትገደጂ ብታውቂ ኖሮ ተክሏን ከመቀንጠስ ትታቀቢ ነበር….?››
‹‹ይቀልዳሉ እንዴ ፕሮፌሰር..ጭርሽ ለማሰብ እንኳን አልሞክርም…እንዴ ንስሬን ጥዬ እንኳን የማላውቃቸው ..ምን አይነት ፍጡር እንደሆኑ እንኳን እርግጠኛ ወዳልሆንኩባቸው..ይመቹኝ አይመቹኝ መገመት ወደማልችላቸው የአባቴ ዘመዶች ይቅርና እግዚያብሄርም ቢጠራኝ ንስሬን ጥዬ በፍቃደኝነት ለመሄድ አልፈልግም››
‹‹በቃ ተረጋጊ..ያው በሞትም መለየት እኮ አለ››አሏት ፕሮፈሰሩ …በእሳቸው ቤት እሷን የሚያጽናና ቃል መናገራቸው ነው፡፡
‹‹አይ ፕሮፌሰር …ይቀልዱብኛል አይደል?ይሄም እኮ ያው ሞት ነው…ሞት ማለት የራስ ከሆኑ ሰዎችና ከሚኖሩበት ዓለም ለዘላለም ተለይቶ በስጋ ወደመሬት ውስጥ መግባት በነፍስ ደግሞ ወደማይታወቅ አለም መጓዝ ማለት አይደል…?አሁን እኔም ከሳምንት በኃላ የሚገጥመኝ ደግሞ በስጋም በነፍስም ከዚህች ምድርም ሆነ የእኔ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ ተለይቼ ለዘላለም ወደማይታወቅ አለም በስጋም በነፍስም መጓዝ ነው…ታዲያ ይሄ እንደውም ሙሉ ሞት አይደለም..….?ማንም ሰው ስናፍቀው እንኳን መቃብሬ ጋር ሄዶ በማልቀስ ወይም አበባ በማኖር ሊያጽናና ዕድሉ አይኖረውም …. ነፍሴንም ስጋዬንም ይዤ ነው የምሄደው…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው››
‹‹አዎ ዋናው ችግር ግን ይሄ አይደለም..ዋናው ንስሬን ጥዬ መሄድ ያለመፈለጌ ነው..እሱን..››ንግግሯን አቋረጧት፡፡
‹‹እኔ እኮ በህይወት እስካለሁ ድረስ ልንከባከብልሽ እችላለሁ፡፡››
‹‹አይ አይችሉም… እርሶ የሚችሉት በስርዓት የቀብር ሰርዓቱን ማስፈፀም ብቻ ነው››
‹‹አልገባኝም..››አሏት ደንግጠው፡፡
‹‹እኔ ጥዬው በሄድኩ ቀን እሱም እደሚሞት ነግሮኛል››
‹‹እንዴት ሆኖ ነው የሚሞተው….?››
‹‹እኔ እንጃ ግን እኔን ከወሰዱኝ በኃላ ለአንድ ቀንም እንኳን በህይወት መኖር እንደማይችል እርግጠኛ ሆኖ ነግሮኛል››
‹‹አይዞሽ ሳምንት እኮ ብዙ ቀን ነው..የሆነ መውጫ መንገድ ልናገኝ እንችላለን..በተለይ ንስርሽ መላ ሚያጣ አይመስለኝም››
‹‹እኔ እንጃ …. እንደዛ ተስፋ አላደርግም …››
‹‹አይዞሽ…ደግሞ ይሄ ጉዳይን እንደመስዋዕትነት ቁጠሪው..ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ወጥመድ ውስጥ የገባሽው››
‹‹መስዋዕት አሉኝ….መስዋዕትነትማ እንዲህ በቀልድ አይገለጽም..እኔ ከመስዋዕትነት ይልቅ ክስረት ነው የሚሰማኝ…መስዋዕትነት እኮ ለአንድ ክብር አለማ አቅዶና አስቦ ሕይወትንም ጭምር መስጠት ማለት ነው…ህይወትንም ጭምር ቢሆን አጥቶ ሌላውን ለማኖር ቀድሞም አምኖና ወስኖ መተግበር ማለት ነው…
‹‹ልክ እንደ አርበኞቻችን ማለትሽ ነው….?››
‹‹አዎ እንደውም ዛሬ ለሀገር መስዋዕትነት ስለከፈሉ ሰዎች ምስጋና የምናቀርብበት ቀን አይደል…ሀገር ከምትደፈር የእኔ ህይወት ትቀጠፍ ብለው…ለልጆችና ለልጅ ልጆቻችን ባርነትን ከምናወርስ እኛ ዛሬ ደማችንን እረጭተን አጥንታችንን በትነን ነጻነትና ኩራትን እናወርሳቸው ብለው ታሪክ እንደሰሩት አባቶቻችን ነው መስዋዕትነት….ልክ እንደ በላይ ዘለቀ፡፡ ከገዛ አብራክ ልጅ ይልቅ ሀገርን ወይም ህዝብን ማስቀደም ማለት ነው…ለሀገር ክብር እና ለወገን መድህን ሆኖ መውደቅ ማለት ነው…ከስኬት በኃላም ላደረጉት ነገር የተለየ ክብር እና ሹመት አለመፈለግ ማለት ነው..ለሚወዱት ነገር ያለንን ነገር ሁሉ ህይወትንም ጭምር በነፃ መስጠት ማለት ነው….
እንደዛአይነት መስዋዕትነት ሚስጥሩ ከባድ ነው….ከድል በኃላ የበላይን ይሄንን ለሀገሩ በነፃ የሰጠውን መስዋዕትነት ሸፍጠኞቹ እና ባንዳዎቹ አልወደዱለትም ነበር..ምክንያም ስለእሱ ዝናና ታሪክ ሲሰሙ የእነሱን ሆዳምነት እና ትንሽነታቸውን በየጊዜው ስለሚያሳብቅባቸው ከንጉሱ አላትመው በአደባባይ እንዲሰቀል አደረጉት..ከጠላት በክብር የተረፈች ነፍሱ በገዛ ህዝቦቹ ምቀኝነት እና ክፍት ተነጠቀች…ይሄ ነው መስዋዕትነትን መራር የሚያደርገው…ለዚህ ነው መስዋዕትነት የሚለው ቃል ሚያስጠላኝ፡፡
‹‹ትክክል ነሽ ልጄ…ይሄ የበላይ ታሪክ የእንግሊዞች ቢሆን፤ይሄ የበላይ ታሪክ የአሜሪካኖች ቢሆን ኖሮ አንድ ሺ ፊልም እና አስር ሺ መጽሀፍ ተጽፎበት ነበር…?ስንት መንገድ እና ስንት ዩኒቨርሲቲ በስሙ ተሰይሞለት ነበር…?››
እኚህ ለሊቱን ከፕሮፌሰሩ ጋር በመጠጥ እያወራረድ በእሷ ለቅሷ ታጅበው ሲያወሩ ከነበሩት ነጥቦች ጥቂቶቹ ነበሩ..….
አሁን ሰዕቱ ከማለዳ 12፡45 ይላል…ፕሮፈሰሩ በመጠጥ እና በእሷ ወሬ ተዳክመው ይመስላል እዛው የተቀመጡበት ሶፋ ላይ ደገፍ እንደሉ እንቅልፍ ይዞቸው ጭልጥ ብሏል….ንስሯ ያለው መኝታ ቤት ውሰጥ ነው ከእሷ በላይ ትካዜና ቁዘማ ውስጥ ነው…ልትነካካው አልፈለገችም
እየተንገዳገደች እቤቱን ለቃ ወጣችና ወደ መኪና ማቆሚያ አመራች…‹‹ከጠጡ አይንዱ›› የሚለውን የትራፊኮችን ዋና ምክር አዘል መመሪያ ከቁብም ሳትቆጥር መኪናዋን አስነሳችና ግቢው ለቃ ተፈተለከች..ቀጥታ ወደመላኩ ቤት ነው ያመራችው…
እንደደረሰች ወደጊቢው አጥር አስጠጋችና መንገድ እንዳይዘጋ አስተካክላ መኪናዋን ካቆመች በኃላ ሞተሩን በማጥፋት ከመኪናዋ ወረደችና የግቢውን በራፍ መጥሪያ በሰከንድ ሽርፋራፊ ውስጥ ደጋግማ አንጣረረችው ፡፡ከጠበቀችው በፈጠነ ሁኔታ ተከፈተላተት..ከእንቅልፉ የባነነ እና በአንድ እጁ አይኖቹን እያሻሸ በሌላ እጁ የበራፍን እጄታ ይዞ ‹‹ምን ፈለግሽ….? ›› የሚላት ሰው ስትጠብቅ .. ንቁ እንቅልፍ በዓይኑ እንዳልዞረ የሚያስታውቅ..አይ እንደውም እያለቀሰ የነበረ ከዚህ በፊትም ያየችት ዘበኛ ከፈተላትና…ምንም ነገር ሳይጠይቃት እንድትገባ መንገዱን ዞር ብሎ ለቀቀለት …አልፋ ገባችና መንገዷን ቀጠለች ..በፍጥነት ዘግቷ ከኃላዋ ተከተላት፡፡
‹‹ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው…….?ሰው ሁሉ ሲያለቅስ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድርበት ቀን ነው እንዴ….?››ከዘበኛው ሁኔታ ተነስታ ውስጧን እየጠየቀች ነው… እራሷን ለመቆጣጠር በዚህ በተወለካከፈ እርምጃ አንድ ነገር አደናቅፏኝ እንዳትደፋ እየፈራች ስትራመድ ዘበኛው በታፈነ ድምጽ መናገር ጀመረ
‹‹ጋሼ ደውለውልሽ ነው….?››
‹‹አዎ›› አለችው….ምንም ሳታስብበት
‹‹አይ ቢጨንቃቸው እኮ ነው ..በቃ እኮ 10 ደቂቃም ዕድሜ አይራቸውም …አብቅቶላቸዋል…››
‹‹ማን ነው ያበቃለት ….?››ደንግጣ

👍94❤10🔥1
‹‹እትዬ ሰሚራ ናቸዋ… ስንት ነገር ሲታሰብ… ለሰርጋቸው ሲዘጋጁ እንዲህ ባጭር ይቅሩ..….?ውይ ጋሼ በጣም ነው አንጀቴን የበሉት ..ተሳቀቁ፤እትዬስ አንዴ ለይቶላቸው ሊገላገሉ ነው እሷቸው ግን ጤነኛ ሰው የሚሆኑ አይመስለኝም፡፡››
ይህን ሁሉ እያወራ ሳሎኑ በራፍ ድረስ አደረሰታ እና የሳሎኑን በራፍ ከፍቶ አስገብቶ ወደኃላ ተመለሰ….ሳሎኑ ውስጥ በግምት ከ10 ያላነሱ ፎጣ የለበሱ፤ ጋቢ የደረቡ ፤ የተቀመጡ፤ የሚንጓራደዱ ሰዎች ይታያሉ……
‹‹ዋው !!!ምን አይነት ሰዓት ደረስኩ….?››ስትል እራሷን ጠየቀች…በአይኗ መላኩን ብፈልግ ላየው አልቻልኩም ….እቤቱን ከዚህ በፊት በደንብ እደሚያውቅ ሰው ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ የመቁጠር ያህል በዝግታ እየረገጠች ቀስ እያለች ሀንድሪሉን በአንድ እጇ ተደግፋ ወጣች….፡፡
ተራራ የመውጣት ያህል ደከማት…. ስትደርስ መኝታ ቤቱ በራፍ ላይ ሁለት ወጣት ሴቶች ወገባቸውን በሻርፕ ጥፍንግ አድርገው አስረው በእንባ በመታጠብ እህህህ…. እያሉ በኮሪደሩ ላይ ይሽከረከራሉ…ዝም ብላ ችላ አለቻቸውና መኝታ ቤቱን ከፍታ ገባች…
ደረቷ ላይ ተደፍቶ ሲንሰቀሰቅ ነበር የደረሰችው…እሷ በቃ የለችም አምልጣቸዋለች….አንጀቴን በላኝ…‹‹አይዞህ›› ስለው ከተደፋበት ቀና ብሎ አየኝና
‹‹አይዞህ?ምን አይዞህ አለው…….?ጥላኝ ሄደች እኮ…ጨከነችብኝ..ብዙ ቃል ገብታልኝ ነበር..በቅርብ ቀን ድል ባለ ሰርግ ልንጋባ ቃል ገብታልኝ ነበር…ልጅ እደምተወልድልኝ ቃል ገብታለኝ ነበር..ቢያንስ 2 ዓመት እንደምትኖር ዓምኜ ነበር..ሀኪሞቹም እንደዛ ብለውኝ ነበር…››
‹‹አይዞህ… በቃ ተረጋጋ››
‹‹ተረጋጋ አትበይኝ…አንቺም እኮ ቃል ገብተሸልኝ ነበር…ግን ይሄው እሬሳዋን ከታቀፍኩ በኃላ ልታፌዥብኝ መጣሽ››
‹‹እስቲ ዞር በልልኝ››አለችው፡፡
የልጅቷን መሞት እና የእሱን ሀዘን በማየቷ ምክንያት ስምታ ይዛው የመጣችው ስካር በግማሽ ፐርሰንት በረደላት፡፡
‹‹ልነሳ….?ምን …በመገነዝ ልትተባበሪኝ ነው..….?››ተነሳና ስሯ ቆሞ አፈጠጠባት፡፡
ገፍትራው እሱ በተነሳበት ቦታ ተተካችና ተቀመጠች ..እጇን ጭንቅላቷ ላይ አኖረችና አዕምሮዋን በመክፈት ትኩረቷን ሰብስባ እጇን ግንባሯ ላይ አድርጋ የሚሆነውን መጠበቅ ጀመረቸ… ከ30 ሰክንድ በኃላ የእጇ ቀለሙ መቀየር እና ለሊት መዳወላቡ ላይ ተክሏን ስትቀነጥስ እዳጋጠማት ሀመራዊ አይነት ቀለም ከውስጧ መፍለቅ ጀመረ ..
ከእሷ እጅ የፈለቀው ወደ ልጅቷ ጭንቅላት ሲገባና የእሷም በተመሳሳይ ሲቀየር ታየ…በዚህ አይነት ሁኔታ ለሁለት ደቂቃ ያህል ከቆየ በኃላ ጥቁር ጭስ የመሰለ ትነት ከጭንቅላቷ እየበነነ ወደቤቱ ኮርኒስ በመስገምገም በኖ መጥፋት ጀመር…ከዛ ህይወቷ ያለፈና በድን የነበረችው ልጅ መንቀጥቀጥና መንዘፍዘፍ ጀመረች…ታአምር ተከሰተ…..
ከደቂቃዎች ቆይታ በኃላ ልክ ከቀናት እንቅልፍ እንደናቃ ሰው አይኖቾን ገለጠችና አካባቢዋን መቃኘት ጀመረች…ፈገግ አለችና ቀና ብላ እንደሀውልት የተገተረውን መላኩን ተመለከተችው..አፉን እደከፈተና እነዛ ብርሀን የሚረጩ አይኖቾን እንደበለጠጣቸው በገረሜታ እያፈራረቀ ሲመለከታት አየችው…
‹‹የእኔ ፍቅር ምንድነው እየሆነ ያለው….?››አለችና በፍፅም ንቃት ከመኝታዋ ተነስታ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጠች…..ሶፊያ በጥርጣሬ እያየች‹‹አላወቅኩሽም ይቅርታ….?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹አይ አታውቂኝም..ትንሽ አሞሽ ነበር…››
‹‹አረ ምንም የህመም ስሜት አይሰማኝም…እንደውም እንደዚህ ፍጽም ሰላማዊ የሆነ ስሜት ከተሰማኝ ዓመት አልፏታል ››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ለማንኛውም እኔ ሀኪምሽ ነኝ..አሁን ስራዬን ስለጨረስኩ ልሂድ››ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ፊት ለፊቱ ተገትራ ቆመች…..ምን እንዳዛ እንዳስቆማት አታውቅም…
‹‹አደረግሺው..እንደፎከርሽው አደረግሽው››ብሎ በመፍለቅለቅ ተጠመጠመባት…እንደዛ ሲያደርግ ፍቅረኛዬ ምን ታስብ ይሆን….? ብሎ እንኳን መጨነቅ አልፈለገም….
እሷም እንዳቀፋት ጆሮው ላይ ተለጠፋችና በማንሾካሾክ‹‹አዎ አድርጌዋለሁ…..ዛሬውኑ ወደሀኪም ቤት ውሰዳትና አስመርምራት…ሙሉ በሙሉ መዳኗን ካረጋገጡልህ ያው በተስማማነው መሰረት በሶስት ቀን ውስጥ ቃልህን እንድትተገብር እፈልጋለሁ..የእቤቴ አድራሻ …››አለችና ከለበሰችው ጂንስ ሱሪዬ ኪስ ውስጥ ቢዝነስ ካርዷን አውጥታ የለበሰው ጃኬት ኪስ ውስጥ ከተተችለት…፡፡
በዝግታ ከእቅፉ አወጣትና በመገረም አፍጥጦ ያየት ጀመር….እሷም አይኖቾን ሳትሰብር አፍጥጣ አየችው …ደስታው በኖ በአንዴ አመድ ነፋቶበታል…እንደደነዘዘ ባለበት ቆመ፡፡
..‹‹ሰሚራም ምንድነው እየተካሄደ ያለው ….?››ብላ በጥርጣሬ የተለወሰ ጥያቄዋን ስትደረድር እና እየተካሄደ ስላላው ነገር ይበልጥ ለማወቅ በጥያቄ ሁለቱንም ስታፋጥጥ… ሶፊያ ከቆመችበት ስፍራ እግሮቾን በማነቃነቅ የተዘጋውን የመኝታ ቤት በራፍ ከፍታ ወጣች…..
ስትመጣ ከነበራት በተሻለ ፍጥነት ደረጃውን እየተንደረደረች ወርዳ ሳሎኑን ሰንጥቃ በመውጣት የግቢው የውጭ በራፍ ጋር ስትደርስ ቅልጥ ያለ የእልልታ ድምጽ እቤቱን ሲያደበላልቀው ሰማች……ፈገግ አለች..
‹‹ይህ የእነዚህ ሰዎች ደስታ እኔን ምን እንዳስከፈለኝ ቢያውቁ እንዲህ እልል አይሉም ነበር…ግን ምንድነው ለመላኩ ብዬው የመጣሁት?አሁን አስቲ ምን ማድረጌ ነው ….?››ስትል እራሷን ታዘበች፡፡በተስማማነው መሰረት በሶስት ቀን ውስጥ ትከፍለኛለህ ማለቷን ማመን አልቻለችም፡ ..በዛ ላይ እኮ የቤቷን አድርሻ ጭምር ሰጥታዋለች‹‹..እስቲ ይሄ ደስታው ለዛሬ እንኳን ሙሉ ቢሆንለት ምን ነበረበት..….?ገና ለገና እኔ ስቃይ ውስጥ ነኝ ብዬ ሌላውን ሰውም እንዲሰቃይ ማድረግ ነበረብኝ..….?ደግሞ ለሳምንት ዕድሜዬ እንደዚህ ክፉ መሆን ምን የሚሉት ልበ ጠጣርት ነው ….….?››እራሷን በራሷ ገሰፀች
የመኪናዋን ሞተር በማስነሳት ከአካባቢው በፍጥነት ተፈተለከቸ….
✨ይቀጥላል✨
#YouTube ቻናሌን subscribe ያደረጋቹ በጣም ጥቂት ናችሁ ምንም አያስከፍልም እያደረጋቹ ለሚለቀቁት ታሪኮች እንደክፍያ ቁጠሩት ዛሬ ብዙ ታደርጋለቹ ብዬ እጠብቃለው
👇

👍101👏22❤15😁2🤔2
👁❤በ'ነሱ ቤት❤👁
🍃ክፍል ሃያ🍃
❤🍃❤🍃❤🍃❤
አንድ ቀን አስተናጋጁ ሰሚር ከስራ ወጥቶ እየተጣደፈ ወደ ቤቱ ሲሄድ ሳለ ከወደዋላው የመኪና ትላክስ ድምፅ እየተከተለው ሲጮኽ ሰማና ፊቱን ቢያዞር የሰመረ መኪና መሆኑን ልብ አለ እናም ባለበት ቆሞ ጠበቀው ።ሰመረ አጠገቡ ደርሶ ከመኪናው በመውረድ እጁን ለሰላምታ ዘረጋለት ።አስተናጋጁ ሰሚር ትንሽ ግር አለው ቀኑ ቅዳሜ ቢሆንም እንደተለመደው ሰመረን ከጓደኞቹጋር ሬስቶራንቱ ውስጥ አላየውም ። ከዚበፊት ተነጣጥለው ስለማያውቁ የዛሬው ለየት ብሎበታል ።ይበልጥ ደሞ አሁን ሰመረ ተከታትሎ ሲያስቆመው ። የነዚ ልጆች ጉድ አያልቅም ደሞ ምን ሊለኝ ነው በሚል እያየው እጁን ጨበጠው። ሰመረ ሰላምታ ከተለዋወጡ በዋላ
"እንዴት ነህ አስተናጋጅ "አለው
"ሰሚር ጅላሉ "አለው እየከፋው
"ይቅርታ ስምህ ጠፍቶኝ ነው "አለው
"አይ ችግር የለም እእ ምን ፈልገኽኝ ነው?"አለው አስተናጋጁ ሰሚር
"አዎ እእ ምን መሰለህ አንድ ነገር ላይ እንድትረዳኝ ፈልጌ ነበር እእ እንዴት ብዬ ልንገርህ ጉዳዩ ትንሿን ጓደኛህን የሚመለከት ነው "አለው ሰመረ ጭንቅ እያለው። አስተናጋጁ ሰሚር 'ይኽዋ እንደፈራውት ሁሉም አይናቸውን ጥለውባታል በቃ በነሱ ቤት ሀብታም ስለሆኑ ሁሉም ነገር እንደሚገባቸው ነው የሚያስቡት ኤጭ 'አለ በውስጡ።
"ምን መሰለህ ጓደኛዬ በሷላይ ያለው ፍላጎት ደስ አላለኝም እና አንተ በተቻለህ መጠን እንዳትታለል ምክር እንድትሰጣት ነው ያው አብረሃት ስለሆንክ "አለው ከየት ወደየት እንደሚያወራ ግራ እየገባው
"እእ ጓደኛህ ማለት ያ ወፍራሙ "አለው አስተናጋጁ ሰሚር እንደማያውቅ ሆኖ ።
"አዎ ጌታነህ ነው ። ለማንኛውም ስልክ እየደወለ ወደራሱ ሊስባት ጥረት እያደረገ ነው እሷ ታዳጊ ስለሆነች ብዙም ስለወንዶች ባህሪ ላታውቅ ትችላለች ስለዚህ አንዳች ስህተት ውስጥ እንዳትገባ ጠብቃት እባክህ! ከራስህም ጭምር ! እንዴት ስለጓደኛው እንዲ ይናገራል ብለህ እንደምታስብ አውቃለው ነገር ግን ጓደኛዬ የሚይሆን አካሄድ እየሄደ ስለሆነ እሱን ባልጠላውም ድርጊቱን መቃወም ስላለበኝ ነው በዛላይ ለምን እንደው አላውቅም ያቺልጅ ታሳዝነኛለች እንድትጎዳ አልፈልግም "አለው ፀጉሩን ወደዋላ ወደዋላ በጣቶቹ እያበጣጠረ
"እም.... ገ..ገባኝ እሷም ብትሆን እኮ የዋዛ አደለችም በቀላሉ የምትሸነፍ አይመስለኝም "አለው አስተናጋጁ ሰሚር
"ምን ማለት አንተ ሞክረሃት ባልሆነ!?"አለው ሰመረ ኮስተር ብሎ
"ኧረረ እኔ ሰሚር እንዴ እሷ እኮ በጣም ታናሼ ናት ።በጭራሽ አላስበውም ታውቃለህ ዜይነብ የምትባል ብቸኛ እህት አለችኝ ክፍልሃገር ነው የምትኖረው ቡታጅራ እእ እና ልክ በሷ ዕድሜ ናት እሷን ነው የምታስታውሰኝ ።የሷ ሁኔታ ካንተም በላይ ያሳስበኛል ።ልልህ የፈለኩት እሷ በጣም ጠንካራ ልጅ ናት ነው"አለ አስተናጋጁ ሰሚር
"እእ በነገራችን ላይ ስልኬ ካስፈለገህ ያዘው "አለው ቁጡሩን እየነገረው ። አስተናጋጁ ሰሚር በፍጥነት ስልኩን ያዘው ።ምን ሀልባት አብላካት በዚው ከቀጠለች የሰመረ ስልክ ሊያስፈልጋት ይችላል ብሎ በማሰብ ።
ስልክ ከተለዋወጡ በዋላ። ሰመረ አንዳች ችግር በሷ ዙሪያ ከተፈጠረ አሳውቀኝ አደራ ብሎት ሲሄድ። አስተናጋጁ ሰሚር ፈገግ ብሎ በቃ በነሱ ቤት ያለነሱ ችግር የሚፈታ ያለ አይመስላቸውም አሂሂሂ አይ ሀብታም አይ ገንዘብ ደረጃ መዳቢ ሆንክብን እኮ አለ ።ሰመረ መኪናውን አስነስቶ ሲሄድ ጠብቆ ። ወደቤቱ ሊሄድ የነበረውን አሳብ በመተው ወደ አብላካት ቤት መጓዝ ጀመረ .........
👁

👍97❤12😁9🔥3
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
የሰው ልጅ ውስጡ ሲጨልምበት እና የመጨረሻ ተስፋው መቁረጥ ላይ ሲደርስ ብስጭቱን የሚያራግፍበት ወይም የሚያላክክበት ሶስት አካላት አሉ…መንግስት፤እግዚያሔር እና እናት ፡፡
የመንግስት እንዝለለው…እግዚያብሄርን ግን ሲከፋን ለምን ፈጠርከኝ….? ብለን እንጠይቀዋለን……መፈጠር ትፈጊያለሽ ወይስ ይቅርብሽ ብለህ ምርጫ ሳትሰጠኝ ለምን ፈጠርከኝ…….?እሺ ይሁን ካለፍላጎቴ ከፈጠርከኝሽ በኋላ ለምን እንደፍላጎቴ ልታኖረኝ አልቻልክም.? ወይም ብትችል እንኳን ለምን አልፈለክም….? ብለን እንጠይቀዋለን…
እሱ በፍቃዱ እኛን መፍጠሩ እና እንደ እኛ ፍቃድ ሳይሆን እንደእራሱ ፍላጎትም የህይወት ጅረታችን የሚፈስበትን መስመር ማስመሩ ስህተት አይመስልም...የሰው ልጅም ሲበሳጭ ፤ተስፋ ሲቆርጥና ሲማረር ለምን ….?ብለን እሱን መጠየቃችንም ስህተት አይደለም….የእግዚያብሄር ዋናው ጥቅም የህይወት ሸክማችንን ከብዶን ስንንገዳገድ ከመውደቅ ታድጎ እንዲያግዘን እና የተሰበረ ተስፋችን እንዲጠግንልን የተንኮታኮተ ሞራላችን እንዲያክምልን ነው….ስለዚህ በከፋን ጊዜ ልንነጫነጭበት የግድ ነው…መነጫነጫችንም ክፋት የለውም፡፡
ከእግዜር ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ የፈረደባት እናት ነች …አራት አመት ሆነን አርባ አመት ሁላችንም ውስጣችን ጨልሞ ነጋችንን ማለም ድክም ሲለን ወደ እናታችን ጉያ ሮጠን መሸጎጥ የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡
…እናታችንን በቅርብ አግኝተን የተመኘነውን ማድረግ ባንችል እንኳን ‹‹….እማዬ ለምን ወለድሺኝ….? ››ብለን ባትሰማንም ማማረራችን አይቀርም….በማማረሩ ውስጥ ምስጋና አለው…ለህልውናችን መሰረቷ ሰው ለመሆናችን ዋናዋ ምክንያቷ እሷ ለመሆኗ እየተናገርን ለዛም እውቅና እየሰጠናት ነው…
አሁን እነኬድሮን ያሉት ደሎመና ነው…ትውልድ ሀገሯ፡፡ያሉት ሳር ቤት ውስጥ ግድግዳውን ተደግፎ በተሰራ እና ግዙፍ አጎዛ በተነጠፈበት ትልቅ መደብ ላይ ፤ ንስሯን ከጉያዋ አድርጋ እናቷ እግሯ ላይ ተኝታ እንባዋን እያንጠባጠበች ነው….አሁን ካሉበት የሳር ቤት ፊት ለፊት ባለአራት ክፍል ቢላ ቤት ቢኖራትም እናቷ ግን አትወደውም…በቃ አስገዳጅ ሆኖባት እንግዳ ካልመጣባት በስተቀር ውሎዋ እዛች ሳር ቤት ውስጥ ነው…ምግቡ እዛው ይሰራል እዛው ብና ይፈላል….እዛው ጋደም ይባላል…
‹‹ገራኮ ማል ታቴ….?››(ሆዴ ምን ሆንሽ….?)ትጠይቃለች እናቷ
ድምጽ ያላጀበውን እንባዋን ከማፍሰስ ውጭ መልስ ልትሰጣት አልቻለችም….እርግጥ ሊሆን ያለውን ነገር ለእሷ ልትነግራት እና ልትሰናበታት ነው የመጣችው …ግን እንዲህ በቃላሉ ቃላት ከአንደበቷ ልታወጣ አልተቻላትም፡፡
‹‹ሆማ ኢንታኔ ሀርሜ ኮ..ነገኡማ ›( ….ምንም አልሆንኩ እናቴ…ደህና ነኝ)
‹‹ቀሮ ቲያ .ኢንሶቢን ….? ››(የእኔ ብልጥ አትዋሺኝ….?)
‹‹እማ ጨንቆኛል..በጣም ጨንቆኛል..መልሼ ወደሆድሽ ሁሉ መግባት አምሮኛል››
‹‹እኮ ንገሪኝ …እኔ እናትሽ እያለሁ ለማን ይድላው ብለሽ ትጨነቂያለሽ……?ደግሞ ባንቺ ጭንቀት አያምርም..አንቺ እኮ ለተጨነቀው ሁሉ መፍትሄ ስትሰጪ እንጂ ስትጨነቂ አያምርብሽም››
‹‹እማ አሁን የገጠመኝ ግን ከባድ ችግር ነው››
‹‹እኮ ምንድነው….?››
‹‹ልሄድ ነው››
ፈገግ አለች እናቷ‹‹እንቺ እኮ ገና ከልጅነትሽ ጡት ሳትጥይ ጀመሮ እንደሄድሽ ነው….ያንቺ መሄድ ምን አዲስ ነገር ኖሮት ነው
ሊያስጨንቅሽ የቻለው…….?አይዞሽ ልጄ ንስርሽ ከጎንሽ እስካለ የትም ብትሄጂ ምንም ሀሳብ አይገባኝም..በዛ ላይ የእኔ የእናትሽ ፀሎት እና የአባትሽ መንፈስ በየሄድሽበት ሁሉ ይከተልሻል… ይጠብቅሻል፡፡››
‹‹ሀርሜ…ንስሬ አብሮኝ አይሄድም ….››
ባለማመን አፍጥጣ አየችት..ምክንያቱም ንስሯ ለአንድም ቀን ቢሆን ከእሷ የተለየበትን አጋጣሚ እናቷ አታስታውስም..እንደውም እናቷ ሁለት መንታ ልጇች አሉኝ ብላ ነው የምታወራው…ያው እንደሚታወቀው እናቷ በምትኖርበት አካባቢ በጣም የተከበረችና ሰው ሁሉ የሚፈራት ነች‹‹….አረ ከዳቢሎስ የተወለደች ልጅ አለቻት …አንድ ነገር ብለን ብናስከፋ በልጇ ታስጠፋናለች….አታዩም እንዴ ልጇ እኮ አቅፋ የምትኖረውን ንስር ዳቢሎሱ አባቷ ነው የላከላት›› እያሉ በማንሾካሾክ እንደሚያሟት ታውቃለች……በዛም ምክንያት ሳይወዱ በግዳቸው ይፈሯታል..ስለሚፈሯትም በጣም ያከብሯታል….ግን ይህን ንስሯን የላከላት አባቷ መሆኑን ትጠራጠራለች እንጂ እርግጠኛ አይደለችም እንዴ….….?
‹‹ለምን ልጄ…?ለምንድነው አብሮሽ የማይሄደው….?››
‹‹የምሄድበት ቦታ እሱን ይዤ መሄድ አይፈቀድልኝም….ቢፈቀድልኝ እሱ አዛ መኖር አይችልም…. አየሩ አይስማማውም…››
ከተጋደመችበት ጭኖ ላይ ገፍትራ አስነሳቻትና እንድትቀመጥ አድርጋ ፊት ለፊት አፍጥጣ እያየቻት‹‹እንዴ ቅሪያ…እንዴት እሱን ጥለሽ መሄድ ታስቢያለሽ…….?የህይወት ጉዳይ ቢሆን እንኳን ማድረግ የለብሽም..እሱን ጥለሽ ሄድሽ ማለት እኔንም አሳዝነሽ ሄድሽ ማለት ነው…በዕድሜሽ ለመጀመሪያ ጊዜ አዝንብሻለሁ››
‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው›ይሏችኋል ይሄ ነው..ከእሷ ባሰች……በጣም ከባዱን ነገር ጭራሽ የበለጠ ጠጣር አደረገችባት፡፡
‹‹ሀርሜ ወዴት እንደምሄድ እኮ አልገባሽም….?››
‹‹ወደ የትም ይሁን አልኩሽ እኮ ..ንስርሽን ጥለሽ የትም መሄድ አትቺይም›› አለችና..ከእቅፌ ንስሬን መንጭቃ ወስዳ ጉያዋ ውስጥ ወሸቀችው…እሱም እጥፍጥፍ ብሎ ተሸጎጠላት፡፡
አፈረጠችው‹‹አባዬ ጋር ነው የምሄደው››
በእድሜዋ ሙሉ እናቷ በዚህ መጠን ስትደነግጥ አጋጥሞት አያውቅም..ሰው እንዴት እየታየ የሰውነት ቀለሙ እየተቀየረ ይሄዳል..?እንዴት እያያችሁት ደም ስሮቹ እየተወጣጠሩ እና ለእይታ ግልጽ እየሆኑ ይታያል….?ሰው እንዴት በሚያግለበልብ ሙቀት ውስጥ ሆኖ የአንታሪቲካ በረዶ ውስጥ እንደጣሉት ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው ይንገጫገጫሉ….መልሰው ቃላት ለመለዋወጥ አያሌ ደቂቃዎች ነው ያሳለፈት…..
‹‹እንዴት አድረገሽ ነው የምትሄጂው….?››
‹‹ወገኖቹ ከስድስት ቀን በኃላ መጥተው ይወስዱኝል››
‹‹እሱስ ይመጣል….?››ጉጉት ባሰቃየው እይታ እያየች ጠየቀቻት
‹‹አይ እሱ እንዲመጣ የሚፈቅዱለት አይመስለኝ››
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ…ግን እነሱስ እንደሚመጡ በምን አወቅሽ….?››
የሆነውን ሁሉ አስረዳቻት..ቀስ በቀስ በድንጋጤ ወይቦ የነበረው ፊቷ በደስታ እየደመቀ እና እየፈካ መጣ
‹‹እማ እየሳቅሽ እኮ ነው…….?››በገረሜታ ጠየቀቻት ..እያለቀሰችም እየሳቀችም መሆኗ ገርሞት
‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኝ ነው››
‹‹እንዴ!! እንዴት ደስ ይልሻል..….?ከሄድኩ እኮ አልመለስም››
‹‹አውቃለሁ…ታውቂያለሽ አይደል ትናፍቂኛለሽ …. በጣም ነው የምወድሽ …ግን ወደአባትሽ ነው የምትሄጂው..ደግሞ በአንቺ ዕድሜ ሙሉ ለብቻዬ ተሸክሜው የኖርኩትን እወነቴን ዛሬ አንቺ አረጋገጥሺልኛል… እንዳልተሳሳትኩ አንቺ ልጄ ምስክር ነሽ…እንቡጥ ልጃገረድ ሆኜ ከሌላ አለም የመጣ ሰው መሰል ፍጡር አፍቅሬ እንደነበረ ….ወደእሱ የመኖሬያ አለምም ለአንድ ቀን ወስዶኝ እንደነበረ…የወለድኳት ልጅ አባትም እሱ እንደሆነ ለዘመድም ለጓደኞቼም ሳወራ ነበር የኖርኩት..ግን አውቃለሁ አንድም ሰው አምኖኝ አያውቅም ነበር…እንደውም ነካ እንደሚያደርግኝ ነው የሚስቡት…ዛሬ እወነቴን እንደነበርና ዕድሜዬን ሙሉ ያፈቀርኩት ፍቅር የእውነት እንደነበር አንቺም ተገንዝበኛል…በህይወቴ ሙሉ ከዚህ በላይ ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ሊፈጠር አይችልም››

👍106❤10🥰1
‹‹እማ እኔ እኮ የምታወሪውን ነገር አንድም ቀን ተጠራጥሬሽ አላውቅም…››
‹‹አመሰግናለሁ ልጄ…..….››ጎትታ ግንባሯን ደጋግማ ሳመቻት፡፡
‹‹ልጄ ለአባትሽ መልዕክት ታደርሺልኛለሽ….?››
‹‹አዎ.. ምን ልበልልሽ?››
‹‹ዕድሜዬን ሙሉ እሱን ብቻ ሳፈቅር እንደኖርኩ ንገሪልኝ…አንተ የከፈትከውን ጭኔን ሌላ ሰው እዲከፍተው ፈቅጄ በመሀከላችን የነበረውን ቅዱሱን ፍቅራችንን ላሳንሰው ስላልፈለኩ እስከዛሬ በስምህ መልኩሼ እየኖርኩ ነው በይልኝ….እንደዛም በማድረጌ ከደስታ ውጭ አንድም ቀን ከፍቶኝ እንደማያውቅ ነግሪልኝ…ደግሞ ቆንጆና ብልህ ልጅ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ…መልሼ ለአንተ ስልክልህም ደስ እያለኝ ነው በይልኝ፡፡››
የእናትዬው ንግግር አንጀቷን አላወሰው‹‹…እሺ ያልሺኝን ሁሉ እነግረዋለሁ››አለቻት፡፡
መቼስ እሷ ብቻ ሳትሆን እሱም በእሷ እድሜ ሙሉ መስዋዕት እየከፈለ እንደሆነ እና በወገኖቹ እንደጥፋተኛ ተቆጥሮ እስራት ላይ እንደሚገኝ ባታውቅም ይሄንን ነግራት ደስታዋን ልታደፈርሰው እና እሷ ከሄደችም በኃላ ያለውን ህይወቷን ወደ ትካዜና ሀዘን ልትቀይረው ስላልፈለገች አሳዛኙኝ የታሪክ ክፍል ደበቀቻት..፡፡
‹‹ልጄ››እናቷ ጠራቻት፡፡
‹‹ወይ ሀርሜ››
‹‹አይዞሽ አታስቢ ንስርሽን እኔ እንከባከበዋለሁ..ማለቴ በአንቺ ፋንታ እኔን ይንከባከበኛል››
‹‹እስቲ እናያለን››አለቻት ..አዎ እናቷ እንዳለቸው ቢሆን እሷም ደስ ይላት ነበር..ግን እንደዚህ አይነት ተስፋ ከንስሯ አላየችም….እና አሁን በዚህ ሰዓት እናቷን ይሆናልም አይሆንምም ልተላት አልደፈረችም፡…..
✨ይቀጥላል✨
#YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ አትስጉ አላስከፍልም😁 ዛሬ ብዙ subscriber እጠብቃለሁ

👍83❤19🥰8😁1
👁በ'ነሱ ቤት👁
🍀ክፍል ሃያ አንድ🍀
❤❤❤🍃❤❤❤
❤❤❤🍃❤❤❤
የናይት ክለቡ ሙቀት ለየት ያለ ነው ። የሙዚቃው ከፍታ የድምፅ መጠኑን የጠበቀ አይደለም ከጩኽቱ የተነሳ የዘፈኑን ይዘት ለማወቅ እንኳ ያስቸግራል ።ነገርግን ማን ለዚ ይጨነቃል ? በክለቡ ውስጥ ያሉ ሁሉም በራሳቸው ሙድ ውስጥ ናቸው ።ገሚሱ በናይት ክለቡ ለስራ የወጡ ከሚመስሉ ብጣቂ ጨርቅ በሚባል ደረጃ ሰውነታቸው ላይ ጣል ያረጉ ሴቶች ጋር ይደንሳሉ ።ገሚሶቹ ጥግ ይዘው ለምሽቱ ካጠመዷት ሴት ጋር ከንፈር ለከንፈር ይላላሳሉ ። ሌሎች ወንዶች ጮክብለው ያወራሉ ቦታው ለወሬ የተመቸ ይመስል ። ይህች ክለብ የነ ጌታነህ የሁልጊዜ መደበቂያ ናት ። ስፋቷ ያን ያክል ባለመሆኑ ትጨናነቃለች ወጣቶች በጣም ተጠጋግተው ይቀመጣሉ ተጠጋግተው ይጨፍራሉ ።አንዱ ያንዱን ገበና ያያል ።ምንም ቢያደርግ ማንም ከማንም አይሰወርም ። ሁሉም ወንዶች እዚ የሚመጡት የሴት መቀመጫላይ ለማፍጠጥ ነው ። ሴቶቹም ይህን ያውቃሉ ለዚህም ይመስላል መቀመጫዋ ተለቅ ያለችዋም አነስ ያለችዋም ይወዘወዛሉ ከዋላ የወንዶቹን አይን እንደሚይዙ እርግጠኛኞች ናቸው። መጥጥ ይዘው ለማስተናገድ ወዲወዲያ እያሉ ዳሌያቸውን ያውረገርጋሉ። አንዳንዴ ሞቅ ባለው ወንድ ቸብ ይደረጋሉ ላመል ያክል ተገላምጠው ዘወር ይላሉ ።
ጌታነህ እና እንየው አንዳንድ ሴት ጭናቸው ላይ አስቀምጠው ያወራሉ ።ወሬያቸው በጋራ ቢሆንም አንዳቸውም የወሬው መነሻና መድረሻ አልገባቸውም ዝምብለው ከአንዱ ወደ አንዱ ይዘላሉ ሴቶቹ በሚያስቀውም በማያስቀውም እኩል ይስቃሉ ።ጌታነህ እራሱን እንደ ጨዋታ አዋቂ ቆጥሮ ይለፈልፋል ቀልድ የሚመስል ነገር ጣል ያደርጋል እንየውን ጨምሮ ሴቶቹ እኩል ያሽካካሉ ። ጌታነህ ጭኑ ላይ ያስቀመጣትን ሴት በጫወታው መሃል ቆንጠጥ ያደርጋታል በዚጊዜ 'ወይኔ በናትህ እጅህን 'ብላ ትወራጫለች ስትንቀሳቀስ ደስ ደስ ይለዋል ።እንየው በጓደኛው ከመሳቅ ውጪ እንደሱ ለመሆን ያልተፈቀደለት ይመስል ጭኑ ላይ ያስቀመጣትን ሴት ከማጫወት ይልቅ የጌታነህን ሁኔታ በመከታተል ይስቃል ። ምሽቱ እየተጋመሰ ሲመጣ ጌታነህ አቅበጠበጠው እናም እንየውን ልጅቷን ይዞ ሊሄድ መሆኑን ነገረው ።እንየው ያለ ጌታነህ ኮንፊደንስ ስለሌለው ተጨነቀ ፡ እሱ ከሌለ እዛ ናይት ክለብ ውስጥ እየተጫወተ የመቆየቱ ነገር ከበደው ።ጌታነህ ቅሬታውን በግልፅ ስላየበት "ምነው ደበረህ እንዴ ?ካልሆነ ለምን ከኔጋር መምጣት ትችላለህ አልተመቸችህም እንዴ ?"አለው ለልጅቷ ሞራል ሳይጠነቀቅ ።እንየው መልስ ሳይሰጠው ወደሌላ አቅጣጫ ሲመለከት ጌታነህ አንድ አሳብ የመጣለት ይመስል ፈገግ እንደማለት ብሎ"ለምን አብረን አንሆንም አራታችንም እእ በቃ ምን ችግር አለው ! ባካቹ ፈታ እንበል አንድ ላይ ለየት ያለ ነው የሚሆነው እእ ለየት ያለ ነገር አላማራችሁም "አላቸው ።ሴቶቹ እርስ በእርስ ተያይተው በምንቸገረኝ ትከሻቸውን ከፍ ዝቅ አደረጉ ።እንየው እንደተለመደው በጌታነህ አሳብ በመገረም ፈገግ አለ ።ጌታነህ ብዙ የመቶብር ኖቶች አውጥቶ ለሴቶቹ ቅድመክፍያ ብሎ ሰጣቸው። ሴቶቹ አሽካኩ ።እናም ጌታነህን ተከትለው ሦስቱም ተነስተው ወጡ እሱ ወደ ሚወስዳቸው ቦታ ተነዱ ። እንየው በጓደኛው አሳብ ተደስቶ አንድ ላይ በሚያደርጉት ነገር የተለየ ነገር እንደሚያገኝ ሁሉ ጓጓ.......ጌታነህ ሁሉንም በመኪናው አጭቆ ማረፊያ ፍለጋ ተጓዘ ............
👁አስተናጋጁ ሰሚር እነ አብላካት ቤት ሲደርስ በሩን አንአንኳኳ ያለወትሮው በጊዜ በሩ ስለተዘጋ ደሞ አሳሰበው ።ሌላ ጊዜ ካልመሸ በስተቀር መሳይ በሩን ዝግ አታደርገውም አላፊ አግዳሚ ጎረቤቶቿ ሰላም ሲሏት ሰላም ስትል የሚሰጣት እርካታ አለ ።ጎረቤቶቿን ወዳድ ነች እነሱ የሷን ያክል አሳቢ ባይሆኑም እሷ ሲጠፉ እንኳ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጤናቸውን ትጠይቃለች ። ወይም አብላካትን ልካ ሰላማቸውን ታረጋግጣለች ።
ሰሚር ደግሞ ሊያንኳኳ ሲል በሩ ተከፍቶ አብላካት ብቅ አለች ።
"እንዴ አንቺ እውስጥ ሆነሽ ነው እንዲ እጄ እስኪዶለዱም ዝም የምትይኝ"አላት እጁን ጨብጦ እያሳያት ።አብላካት ፈገግ ለማለት እየሞከረች.....
"ተኝቼ ነበር እኮ!ደሞ አታካብድ ብዙ አላንኳኳህም "አለችው እያዛጋች
"ኧረ ባክሽ ከዚ የበለጠ ጣቶቼ መቆረጥ አለባቸው "አለ አስተናጋጁ ሰሚር እየቀለደ
"እሺ በቃ ናግባ እንዴ ጭቅጭቅ ።ደሞ እንደምትመጣ ሳትነግረኝ ነው የመጣኽው !ጉሊት መሳዬ ጋር ብሄድስ ልታለቅስ ነበር ።"አለችው እየተቀመጠች ።ሰሚር ዱካላይ ተቀመጠ ና ትክ ብሎ ሲያያት ቆይቶ "በጣም የደበረሽ ትመስያለሽ ምነው?"ብሎ ጠየቃት
"እንጃ! እመስላለው ?ምን አልባት ተኝቼ ስለተነሳው ነው ።ከስራ በጊዜ ነበር የወጣውት "አለችው
"ይሆናል ።እኔማ ዛሬ የሚገርም ወሬ አግኝቼ በአካል ሄጄ ልንገራት ብዬ ነው የመጣውት "አላት ።
"ምንድነው እሱ "አለችው አብላካት እያዛጋች
"ኧረረ አፍሽ ይሰፋል አንቺ ልጅ "ብሎ ሳቀ።
"ሂድ እዛ አሁን የምትነግረኝን ንገረኝና ቡና ላፍላ ተነስቼ የምሳዬም መምጫ ደርሷል "አለችው
"መሳይ እንዴት ናት ግን"አላት ሰሚር
"ደና ነች "አለችው እየተነሳች
"እህ ወዴት ነው ልነግርሽ እኮ ነው"አላት
"በዋላ ትነግረኛለህ"አለችው ማንደጃውን እያስተካከለች፡የከሰል መቆንጠጫ እያነሳች
"ሰመረን አግኝቼው ነበረ"ሲላት የከሰል መቆንጠጫው አመለጣትና ወደቀ ።አስተናጋጁ ሰሚር ሳቀ ........

👍116❤17😁6👎1😱1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////
ወደሸገር ተመልሰዋል..ማለት እሷ እና ንስሯ ፡፡ለእናቷ በመጨረሻው ቀን ተመልሳ እንደምታያትና ወደአባቷ ዘመዶችም በምትሄድበት ቀን አጠገቧ እንድትሆን እንደምትፈልግ ነግራትና ቃል ገብታላት ነው የመጣችው፡፡
እስከዛው ያሉትን ቀጣዬቹን በስስት እየተሸራረፉ በመርገፍና በማለቅ ላይ ያሉትን ቀሪ 5 የሰቀቀን ቀናቶችን ሸገር ልታሳልፍ ወስናለች….ምን አልባትም አይታውቅም… በመሀል ሀሳቧን ልትቀይር ትችላለች፡፡
ግን አሁን ተረጋግታ እቤቷ መቀመጥ አልቻለችም … ሰዓቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ቢያልፍም ልትቆጣጠረው የማትችለው ከውስጧ ሚመነጭ ስውር ስሜት ውጪ ውጪ ይላት ጀመር….ልብሷን ቀያየረችና መኪናዋን ወዳለችበት መራመድ ከጀመረች በኃላ ሀሳቧን ቀየረችና ስልኳን አውጥታ ደወለች..አዎ ነፃ መሆን ነው የምትፈልገው….ላዳ ያለው የምታውቀው ልጅ ጋር ነው የደወለችው፡፡
‹‹ሄሎ››
‹‹ሰላም ነው… .ፈልጌህ ነበር…የት ነህ ያለኸው?››
‹‹ይቅርታ ዛሬ ስራ ላይ አይደለሁም መኪናዬ ተበላሽታ ገራዥ ነች››
‹‹በቃ አንተ ናልኛ ..የእኔ መኪና ስላለች ትይዝልኛለህ …ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ መንዳት አልፈለኩም››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር.. ግን ያው ስራ የለኝም ብዬ ከከተማ ወጣ ብያለሁ…..ከፈለግሽ አንድ ጓደኛዬን ልልክልሽ እችላለሁ››
‹‹ደስ ይለኛል››
‹‹በቃ ንገረውና ቁጥርሽን ሰጠዋለሁ…ይደውልልሻል››
‹‹እሺ አመሰግናለሁ››ስልኳን ዘጋችውና ጊቢዋ ውስጥ እየተዘዋወረች እስኪደወልላት መጠበቅ ጀመረች….፡፡
ብዙም ሳይቆይ ስልኳ ላይ የማታውቀው ቁጥር ተንጫረረ …አነሳችው..አናገረችው ….በ15 ደቂቃ እንደሚደርስ ነገራት…..መጠበቅ ጀመረች…..
‹‹አዎ በዚህ ለሊት ምን አልባት ለመጨረሻ ጊዜ ማበድ እፈልጋለሁ..አዎ ብዙ ነገር ማድረግ አምሮኛል…የማሰብ አቅሜን አዳክሞ ጭንቀቴን የሚቀንስልኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ እፈልጋለሁ…..መጠጣትና መስከር …መቁላላትና መዋሰብ እፈልጋለሁ…መጣላትና መደባደብም ካገኘሁ አልጠላም…››
እግዜር ይስጠው የመኪና ጥሩንባ ድምጽ ሰማች...ጎበዝ ልጅ ነው… በነገረችው ምልክት መሰረት ሳይሳሳት መምጣቱ አስደሰታት… በራፍን ከፈተችና ወጣች…በምልክት ጠራት … የላዳውን በራፍ ከፈተላትና ገባች፡፡
‹‹ወዴት ልውሰድሽ….?››
‹‹መጠጣት ነው የምፈልገው››አለችው፡፡
‹‹መጠጣት›› አላት ግራ ተጋብቶ፡፡
‹‹መጠጣት ስልህ …ብሽቅጥ እስክል መጠጣት ነው የምፈልገው…የፈለከውን ያህል ከፍልሀለሁ እስከንጋትም ቢሆን አብረኸኝ ትቆይና እቤቴ ታስገባኛለህ››
‹‹ይመችሽ ››አላት….
እንዲሁ ወደደችው…አንድን ሰው አይተን በውስጣችን ስለሰውዬው ደስ የሚል ስሜት ሲሰማን ውቃቢዬ ወዶታል የምንለው ነገር አለ አይደል..….? እሷም ይሄን የላዳ ሹፌር እንዳየችው እንደዛ ነው የተሰማት፡፡
‹‹ምርጫሽ የት አካባቢ ነው?››
‹‹የፈለክበት ውሰደኝ ››
‹‹ቺቺኚያ ይመችሻል››
‹‹ይመችህ››
ነዳው….ንስሯ አምኗት እቤት ሊቀር አልቻለም …ከፊት ለፊታቸው በላዳዋ ፍጥነት መጠን ሲበር በመኪናዋ መስታወት አሻግራ አየችው….
ደረሱና መኪናዋን ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀበት ቦታ ፓርክ አድርገው አንዱ ጭፈራ ቤት ገቡ……እሷ ደረቅ አልኮለሏን ስታዝ እሱ ዉሀ አዘዘ..
‹‹ለምን ትንሽ አትሞከርም….? ››
‹‹አይ …የሞያዬ ስነምግባር አይፈቅድልኝም›› ሲል መለሰላት በቀልድ መልክ
..ዝም አለችው… በላይ በላዩ መለጋቱን ቀጠለች….የሙዚቃው ከጣሪያ በላይ ጩኸት…የለሊት ንገስታቶች በገዢ መሳይ ወንዶች ዙሪያ መሽከርከር፤ በስካር የሚናውዙና የሚደንሱ ወንዶችና ሴቶች የሆቴሉን ወለል መሙላት…የሆነ ትርምስምስ ያለ ነገር ነው የሚታየው….በዛ ላይ መብራቱ በአምስት አይነት ቀለም በመፈራረቅ ቦግ ብልጭ ሲል እይታን ብዥ ያደርጋል…….ግን በምትፈልገው መጠን ባይሆንም ተመችቷታል ፡፡ቢሆንም ደስታዋን ሙሉ ማድረግ ፈለገች…
‹‹ሌላ ጓደኛ የለህም….?››ድንገት ከመሬት ተነስታ ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን አይነት….?››
‹‹ሹፌር››..
‹‹ምን ያደርግልሻል….?››
‹‹ያንተን መኪና የሚነዳልን››
‹‹እኔስ….?››አላት በጥያቄዋ ግራ ተጋብቶ
‹‹አይ አንተማ እንድታጣጣኝ ፈልጌ ነው..ብቻዬን ደበረኝ››
‹‹እ ..ቆይ እስኪ ደዋውዬ ልሞክር››አለና ስልኩን እየጎረጎረ ከሆቴሉ ወጣ..ሲወጣ ከጀርባው ሳታየው ነበር…ቁመናው መስጧታል..በቃ የተለመደው ችግሯ እያገረሸባት ነው..ጭኗ መካከል አሳከካት…ምን አይነት መጥፎ አመል ነው…እዛም አባቷ አለም ስትሄድ እንዲህ የሚበላት ነገር ወቅት እየጠበቀ ይፈታተናት ይሆን እንደዛ ከሆነ ምንድነው የምታደርገው….….?
ሀሳቧን ሳትጨርስ መጣና መቀመጫው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ..‹‹ተሳክቶል…ተቀላቅዬሻለሁ››አላት
በደስታ እየፈገገች‹‹ምን ይምጣልህ..?››ሥትል ምርጫውን ጠየቀችው፡፡
‹‹አንቺ የያዝሺውን…››
ሙሉ ጠርሙስ አዘዙ…መጣላቸው…… ይገለብጡት ጀመረ…እየደነሱ እየተቀመጡ …ደግሞ ተመልሰው በመነሳት እየደነሱ ..ውልቅልቃቸው እስኪወጣ ድረስ አስነኩት‹‹ …አቤት ዳንሱ !!ፕሮፌሽናል ነው ፡፡ልቤን ስልብ ነው ያደረገኝ…›አለች በዳንስ ችሎታው ተመስጣ፡፡ይበልጥ ሰውነቱ ላይ ተለጥፋ በተሸሻችው መጠን የጭኗ መብላላ አደብ እየነሳት ነው…በትርምሱ መካከል በዳንስ ስልት በማሳበብ እጣቷን ወደጭኗ በመስደድ ይሉኝታ እስክታጣ ድረስ እያሻሸች ነው..ደግነቱ ሁሉም በመጠጥ የደመቀ እና በመብራቱ ቦግ ብልጭ ብዥ ያለበት መሆኑ በጃት …
ከለሊቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ግን ተዳከሙ…
‹‹ቤት እንቀይር ….?››አለችው… ቤት መቀየር የፈለገችው ሙዳችውንም ጭምር መቀየር ስለፈለገች ነው… ተስማማ ..ሂሳብ ዘግተው ወጡ…
‹‹ጭፈራ ቤት ሳይሆን ዝም ብለን የምንጠጣበት ቦታ ነው የምፈልገው…››
ወደላዳዋ ይዟት ሄደ …ቅድም ተጠርቶ የመጣው ጓዳኛውን ገቢና ቁጭ ብሎ ጫቱን ሲቀመቅም አገኙት..ሁለቱም ተደጋግፈው ከኃላ ገቡ… ላዳዋ ተንቀሳቀሰች… በመስኮቱ አንጋጣ ሰማዮን ሰታይ ንስሯን ቀድሟት ለመብረር ሲያኮበኩብ አየችው…ሰካራሙ ጓደኛው እይታዋን ተከትሎ ወደውጭ በተመሳሳይ ሁኔታ ካየ በኃላ‹‹ አይገርምም ይሄ አሞራ ቅድምም ስንመጣ ከፊት ለፊታችን ሲበር ነበር….እርግጠኛ ነኝ የተለየ ከለር ስላለው አስተውዬው ነበር››አለ
‹‹አሞራ አይደለም..ንስር ነው››አረመችው
‹‹እንዴ.. አዎ ንስር ነው ትክክል ..አንቺ ግን እንዴት አወቅሽ….?››
‹‹የእኔ ነው››በልበ ሙሉነት መለሰችለት፡፡
‹‹የእኔ ነው ስትይ….?››ያዝ ያዝ በሚያደርገው የስካር አንደበት ጠየቃት
‹‹ወንድሜ ነው››
ሁለቱም ተንከትክተው ሳቁ
‹‹..ቀልደኛ ነሽ..ይበልጥ ስትጠጪ ደግሞ ይብልጥ ቀልደኛ የመሆን ተስፋ አለሽ ማለት ነው››አላት፡፡
….አስረድቶ ማሰማንም ሆነ ተከራክሮ ማሸንፈ እንደማትችል ስለተረዳች‹‹ይሁንልህ›› አለችው ፡፡
መገናኛ አካባቢ ደርሱ… ብዙም ትርምስ የሌለበት እሷ የማታውቀው ሁለቱ ግን የሚያውቁት ሆቴል ይዘዋት ገቡ..ሹፌሩ ከላዳዋ አልወረደም…‹‹ጫቴን ብቅም ይሻለኝል›› ብሎ ቀረ …እነሱ ተያይዘው ገቡና የተገነጠለ እና ከታዳሚ የራቀ ወንበር ይዘው ተቀመጡ፡፡

👍86❤11😁2👎1🤔1😱1😢1
ሙሉ ጠርሙስ ጎርደን ጅን አዘዙ
‹‹አረ ልባችን ትፈነዳለች››አላት
አልመሰለችለትም …መጠጡ መጥቶም ለተወሰኑ ጊዜ ከዲጄው የሚለቀቀውን ለስለስ ያለ ሙዙቃ በተመስጦ እያዳመጡ እና ከራሳቸው ሀሳብ ጋር እየተብሰለሰሉ ቆዩ…. ሰላሳ የሚሆኑ ደቂቃዎች በየራሳችን ዝምታ ወስጥ ቆይተዋል..ግን ድንገት ስትባንን መጠጡ ግማሽ ጠርሙስ ተጋምሷል..ደነገጠች ….እሷ የተቀዳላት ብርጭቆ ግማሹን እራሱ አላጋመሰችም ..አጅሬ ላካ እየለጋው ነበር..‹‹ወይ ከእኔ የባሰ መጠጥ የራበው ነው እንዴ የገጠመኝ .….?››ስትል አሰበች፡፡ደግሞ ሲያዩት ገና ብዙ የመጠጣት አቅሙ እንዳለው ያስታውቃል….እንግዲህ ምንም ማድረግ አይቻልም አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ናቸው..፡፡ለእሷ እንዲህ መጠጡን መሳቡ ተመችቶታል..ብቻ እራሱን እስከመሳት ደርሶ ሰውነቱን ማዘዝ አያቅተው እንጂ ህሊናው እስኪቆለፍ ድረስ መጠጣቱ አሪፍ ነው ብላ አሰበች…‹‹እበላዋለሁ…ሌላ ተጽዕኖ ወስጥ ሳልከተው በራሱ ፍላጎት አብሮኝ እንዲያድር ማደረግ እፈልጋለሁ…እንደማንኛዋም ተራ ሴት ሆኜ ላሸነፈው ነው የምፈልገው……ሰውኛ ማሸነፍ እንዲሆን …›ስትል እቅድ አወጣች፡
ድንገት ከመሬት ተነስታ‹‹ተጫወት›› አለችው፤
እሱም እንደመባነን አለና ‹‹እሺ …ባይዘወይ ኤርሚያስ እባላለሁ..››አላት
‹‹አሪፍ ስም ነው ..እኔን ሰፊ በለኝ ››..
‹‹አይገርምም ማን ልበል ሳትይኝ እንዲሁ ከምድር ተነስቼ ኤርሚያስ አባላለሁ በማለት ከበሮ መደለቅ ምን የሚሉት እራስ ወዳድነት ነው..ኤርሚያስ ልባል ሚኪዬስ ለአንቺ ምን ይረባሻል፡፡ግን ያው ትረጂኛላሽ ብዬ አስስባለሁ…በመጀመሪያ እኔ በዚህች አለም ላይ ያለኝን ውክልና ለማሳወቅ ከስሜ መጀመር የግድ ይለኛል..ከስሜ ቀጥሎ ነው ወደ ሌላ ጫወታ መግባት የምችለው ››
‹‹አረ ትክክል ነህ.. እንደውም እኮ ገና እንደተገናኘን ነበር ስም መቀያየር የነበረብን ››
✨ይቀጥላል✨
#YouTube ቻናሌን subscribe እያደረጋቹ አትስጉ አላስከፍልም😁 ዛሬ ብዙ subscriber እጠብቃለሁ
👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቻናሉንም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://tttttt.me/atronosee
Follow my channel on WhatsApp 👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029VaDdoKaJENxsTyh8E43Z

👍75❤9🤔6🥰3
Forwarded from ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘 (Tsi 🦋)
🍀🍀በ'ነሱ ቤት🍀🍀
❤ክፍል ሃያ ሁለት❤
🍃❤🍃❤🍃❤🍃
አስተናጋጁ ሰሚር አብላካት የያዘችውን መቆንጠጫ ስትለቀው ። ፈገግ አለ አብላካት አፈር ብላ የጠለችውን አንስታ እራሷን ለማረጋጋት ሞከረች ።
"አቢ ምንድነው እሱ ነገር ያሟልጫል እንዴ"አላት የፊቱ ፈገግተ ሳይከስም
"እህህ አንዳንዴ"አለችው በሽሙጥ ነገሩ ስለገባት
"ተይውና ቁጭበይ መሳይ ስትመጣ ጉድጉድ ትያለሽ "አላት
"እእም እሺ መክሰስ ነገር ላቅርብ "አለችውና ወደውስጥ ገባ አለች
"ተይው አልኩሽ እኮ ነይ ይልቁንስ ሰመረ ምን እንዳለ ልንገርሽ "አላት ። አብላካት ግድ የሌላት አስመስላ
"እሺ አንተ ካልክ ምንድነው ግን እንዲ ሲያስሮጥ ያመጣህ የሰመረ ጉዳይ ?"ብላ ወንበር ላይ ቁጭ አለች
"ከስራ እንደወጣው ወደቤት ሄጄ እረፍት ለማድረግ ፈልጌ ነበር ።ነገር ግን መንገድ ላይ ሰመረ በመኪናው ተከትሎኝ ኖሮ ድንገት አስቆመኝ ከዛ ..."ብሎ ሁኔታዋን ለማጥናት አያት በጉጉት እያዳመጠችው ነው
"ከዛ ምን ?"
"ከዛ ስለ አንቺ አወራኝ ማለት....."
"ስለ እኔ !ስለእኔ ምን አለህ?"አለች ጆሮዋን አቅንታ
"አንቺን ከጌታነህ እንድትጠነቀቂ እንድነግርሽ እና ..."
"ምን እኔ ከጌታነህ እንድጠነቀቅ በቃ? ይሄ ምን ማለት ነው ?እሱ ምን አሳሰበው ?እሺ ካሰበስ እራሱ ለምን?....."ብላ ዝም አለች ።እንዴ ምን እያልኩ ነው ?ደሞስ ምን አናደደኝ? ምን አልባት ጌታነህ ለኔ ስልክ የሚደውልልኝ በጓደኞቹ ፊት ይሆናል ።ስለዚ እሱ የኔና የሱን ጉዳይ አካብዶ ነግሯቸው ይሆናል ።ለዚህም ሊሆን ይችላል የማስጠንቀቂያ መልህክቱ ።ብላ ተረጋጋች
"እኔ እንጃ ግን ጌታነህ ሲጎርር ስለ አንቺ ብዙ ሳያወራ አይቀርም ።ሰመረ ደሞ እንዳያታልልሽ ፈርቶ ነው ለኔ የነገረኝ ። በጣም የሚገርምሽ እኔን እንኳ አስጠንቅቆኛል ስለ አንቺ ። "አላት ሰሚር በቅሬታ
"አንተን ኪኪኪኪ ለምን ?"
"እንዴ ኮስተር ብሎ ከጌታነህ እንድትጠነቀቅ ንገራት ።በተቻለ መጠን እንዳያታልላት ጠብቃት ገና ታዳጊ ልጅ ናት ከራስህም ጭምር ጠብቃት አላለም "አላት ትንሽ ጨመርመር አርጎ እየነገራት ።አብላካት በጣም ተገርማለች ።ማንነቷን ሳያውቅ የዚን ያክል የሚያስብላት ለምንድነው ። በትክክል እንኳ ተቀምጠው አውርተው አያውቁ ።እና እሱስ ከሷ ምን ፈልጎ ነው እንዲ የሚሳሳላት የሰመረ አካሄድ አልገባ አላት ። እራሷስ ብትሆን ከባለፈው ጊዜ ጀምሮ ልቧ ለሱ ለምን መምታት ጀመረ ።ለምን ስሙ ሲነሳ እንዲ ያደርጋታል ። ለምን ድጋሚ ልታየው ፈለገች ለምን ለምን ????
"በነገራችን ላይ ስልኩ ካስፈለገሽ እሰጥሻለው ።ትንሽ ላቆየው ነበር ነገርግን ሳይሽ ልታዋሪው የምትፈልጊ ትመስያለሽ "አላት አስተናጋጁ ሰሚር እያጠናት
"በእውነት ለኔ ስጣት ብሎህ ነው ?"አለችው ደስ ደስ እያላት
"አይ እሱ እንኳ በሷ ዙሪያ አንዳች ችግር ከተፈጠረ አሳውቀኝ ብሎ ነው "አላት ፈገግ እያለ
"እሺ እዚም ተደርሷላ ምን አስቦ ነው ።እኔን የመጠበቅ ፍላጎት ካለው ለምን በቀጥታ አይመጣም ።በሰው በሰው ከሚያስጠብቀኝ ሆሆሆ"አለች ውስጥ ውስጡን ግን ደስ ብሏታል ።ስልኩን በማግኘቷ ። አስተናጋጁ ሰሚር ።ለመናገር አፉን ሲከፍት በሩ ተንኳኳ አብላካት ለመክፈት ተነሳች በዛውም የሞባይል ስልኳን ቁጥሩን እንዲፅፍ እያቀበለችው ....

👍65❤4👎1🔥1👏1
Forwarded from ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘 (Tsi 🦋)
🌺🍃በ'ነሱ ቤት🍃🌺
🌻ክፍል ሃያ ሦስት🌻
❤🍀❤🍀❤🍀❤
አብላካት በሩን ከፍታ ስታይ እናቷ መሳይ በኩርቱ ፌስታል እቃ ይዛ ድክም ብሏት አየች ፡ ይሄ ሁኔታዋ ሁሌም አንጀቷን ቢበላትም ምንም ማድረግ ስለማትችል ዋጥ ታደርገዋለች ። የእናቷን ድካም ጨርሶ ማጥፋት እንኳ ባትችል ብትቀነስላት በወደደች ፡።
"የኔ ትንሽ አበባ ምነው በሩን ዘጋሽው የቀረ ሰው የለም "ብላት ፈገግ አለች
"ውይ እናቴ በሩን መዝጋቴን እንኳ ልብ አላልኩትም ሰሚር በወሬ ልቤን ውልቅ ሲያደርገኝ እኮ ...."ብላ ዝም አለች ።ምን አልባት ደሞ ሌላ ነገር እንዳይመስላት ፡ ብላ አሰበች። መሳይ ግን ወደዛ ያሰበች አትመስልም እየሳቀች ወደ ውስጥ ገብታ ሰሚርን ጨበጠችው"አንተ ለምንድነው ልጄን በወሬ ልቧን የምታወልቀው በል መልሰህ ልቧን ትከልላት"አለችው
"ኧረረ መሳዬ ዝም በያት እሷ ነች እንጂ እንግዳ መጣ ምግብ ይቅረብ የለ ቡና ላፍላ የለ በወሬ ጠምዳ ያዘችኝ "ብሎ የውሸት ኩርፍ አለ
"አንቺ እንዲ አደርገሽ ነው..."ብላ መሳይም የውሸት ቆጣ አለች
"አንተ ምን አይነት ውሸታም ወቶሃል !ምግብ ላቅርብ ስልህ አልበላም አላልክም ሆሆሆ ደሞኮ እሳት እንኳ እንዳላያይዝ ቁጭበይ ብሎ ....."ብላ ዝም አለች የሰመረ ወሬ ትዝ አላት ።ሰሚርን ጠቀሰችውና ስልኳን በአይኗ አሳየችው ። ሰሚር ጭንቅላቱን ነቅንቆ ስልኳን ሰጣት ።ስልኳን ተቀብላ አየችው የሰመረን ቁጥር መመዝገቡን ቼክ ካደረገች በዋላ አመሰግናለው አለችው ።እና ወደ መንደጃው ስትሄድ እናቷ ተይው አለቻት ።አብላካት ግን አይሆንም ብላ ማንደጃውን ይዛ ለመውጣት ተጣደፈች ራመድ እናዳለች ግን ባልተለመደ ሁኔታ አቃስታ ወደቀች ።የአብላካት እናት 'ልጄን'ብላ ጮኽች አስተናጋጁ ሰሚር ተወርውሮ ከመሬት አነሳት አብላካት ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ "ደደና ነነኝ ት ን ሽ አ ዙሮኝ ነው.."አለች
"ሰሚ ልጄን ምንድነው ምምንድነው እስኪ አምጣት እዚ አስተኛት ..የኔ ትንሽ አበባ ምንው እኔ ድፍት ልበል "አለች መሳይ እያለቀሰች በጣም ተደናግጣለች ።
"እማ እእማ ደደና ነኝ እኮ ድድንገት ስለዞርኩ ነው"አለች እያቃሰተች ከወደ ጎኗ አንዳች ውጋት እንዳላት እየተሰማት ። ሰሚር ከድንጋጤው መለስ ሲል አብላካትን አፍጥጦ እያየ "ምንድነው ህመም እየተሰማሽ ነበር "አላት
"አአይ ማለት ራስ ምታት ነበረብኝ"አለችው አልጋውላይ ጋደም እንዳለች ።
"ማለት ዛሬ ነው ወይስ ቆይቶብሻል"አላት
"ዶክተር በቃ ደና እኮ ነኝ "ብላ ፈገግ ለማለት ሞከረች
"እየቀለድኩ አይደለም አቢ ሰሞኑን ያምሽ ነበር"አላት ኮስተር ብሎ
"እንዴ ወንድሜ ሰው እኮ አልፎ አልፎ ይታመማል አይደል እንዴ እንደውም አንድ መፀሐፍ ላይ እንዳነበብኩት ፣ይሄ የኔ እድሜ የተለያዩ ለውጦች ስለሚደረግ ህመም ሊኖር ይችላል እንደ እራስምታት ያለ ድብርት ምናምን..."አለችና ተነፈሰች
"እሺ እሺ የኔ አበባ በቃ እረፍት አድርጊ ።ጭንቀትም ይሆናል እኮ እንዲ የሚያደርጋት ።የኔ ውድ እኔ እሆናለው በሽታዋ ።እባክሽ ስለ እኔ ድካም ደጋግመሽ አትጨነቂ ።እኔ እኮ ያን ያክል ያረጀው ሰው አይደለውም አንቺ እኮ የልጅነት ልጄ ነሽ እኩያ ልጄ ።ልክ እንደ ደከማት አሮጊት አይተሽኝ ለኔ መጨነቅ አይገባሽም "አለቻትና ፀጉሯን ከግንባሯላይ እየመለሰች በፍቅር አየቻት ።አብላካት ልትናገር ስትል አፏን በጣቷ ያዝ አድርጋ ዝም ብለሽ እረፍት አድርጊ አለቻት ።ሰሚር ግን ነገሩን በቀላሉ የጭንቀት ብቻ ነው ብሎ ሊያልፈው አልቻለም የሆነ ህመም እማ አላት ። በቅርቡ መታየት ነው ያለበት ብሎ ከራሱ ጋር አወራ

👍102❤12🥰2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
‹‹ለማንኛውም ልድገምልሽ ኤርምያስ እባላለሁ…ለ15 ዓመት ያህል በማንዴላ ሀገር በሆነችው ደቡቡ አፍሪካ ጀሆንስበርግ ኖሬያለሁ… ወደሀገሬ ከተመለስኩ ሁለት ዓመት ከግማሽ ሆኖኛል፡፡የ20ዓመት አፍላ ፍንዳታ ሆኜ ሄጄ የ35 ዓመት ሙሉ ደንዳና ወጣት ሆኜ ተመለስኩ….››
‹‹አሀ ዲያስፖራ ነሀ….?››
‹‹አይ ዲያስፖራ ..!!! ‹ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ ›ትላለች እናቴ… ለማንኛውም እወነቱን ንገረኝ ካልሺኝ … በእነዛ ዓመታት ውስጥ በሰው ሀገር ላይ ስዳክር ..ሞራሌን ከማንቆሻቆሽ…ሰው ሆኜ መፈጠሬን ከመጠየፍ እና ወጣትነቴ ላይ ጢቢ ጢቢ ከመጫወት ውጭ ምንም ያተረፍኩት ነገር አልነበረም…ብዙ ህልም በልቤ ብዙ ምኞት በውስጤ አጭቄ ነበር የተጓዘኩት …እርባነቢስ ሆኜ ባዶ እጄን በሀገሬ ለመሞት ብቻ ብዬ ነበር የተመለስኩት …ይገርማል አይደል?
ሰው እንዴት ለመሞት ብሎ ከደብቡ አፍሪካ ድረስ ኪሎሜትሮችን አቆርጦ ይመጣል ትይኝ ይሆናል..….?ለእኔ ግን ትርጉም ነበረው..››
‹‹ንገረኝ እስኪ ትርጉሙን…››ከሳዕታት ትርኪ ሚርኪ ወሬ እና መዛለል በኃላ ድንገት ምርር ወዳለ የህይወት ታሪክ ሀተታ መግባቱ አስደምሟታል አስደስቷታልም…አሁን እየነገራት ያለውን ታሪክ እሱ ሳይነግራት እንደተለመደው ወጭ እየጠበቀት ያለውን ንስሯን እንዲረዳት አድርጋ በዝርዝር ማወቅ ትችላለች..ግን አልፈለገችም …እንዲሁ እየጓጓችና ቀጥሎ ምን እንደሚናገር እየገመተች ቀጥታ ከራሱ አንደበት መስማቱ የሆነ የተለየ ስሜት ስለፈጠረባት ደስ ብሏታል…
ቀጠለ ‹‹በህይወቴ እያለሁ የመኖር ምኞቴ ሰልበው በድን አድርገውኝ …ወጣትነቴን ከንቱ አስቀርተውብኝ የመጨረሻውን ክስረት ማክሰራቸው ሳይበቃቸው …ከሞቴም በኃላ ክብር ስጋዬን ለሀገራቸው ምድር ልገብር …?አላደርገውም ፡፡ለዘላለም የባዕድ ሀገር አፈር ሆኜ መቅረት አልፈለኩም ..ይህ መልካም አይደለም…ቢያንስ አገሬ እትብቴን በክብር በወርቃማ አፈሯ ውስጥ ቀብራ ከማንነቷ ጋር እንዳወሀደችው ሁሉ ስሞትም በድኔን በክብር ልትቀበለኝ እና ለዘላለም በጉያዋ ልትሸሽገኝ ይገባል..አዎ እንደዛ ነው መሆን ያለበት..በዛ ላይ እናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ማየት እፈልጋለሁ… አያየኋት መሰናበት፤ስሮ በመኖር እና እሷን መጦር ችዬ ላስደስታት ባልታደልም… እጇ ላይ ሞቼ አልቅሳ ልትቀብረኝ እና እርሟን ለማውጣት እንድትችል ግን እድሉን ላመቻችላት ይገባል..አዎ ስመጣ እንደዛ ብዬ እና እንደዛ ወስኜ ነበር …
‹‹ከዛስ….?››
‹‹ከደረስኩ ኋላማ … ቆይ ዛሬ ስል …ቆይ ትንሽ ልሰንብት ስል ..የመኖር ጉጉቴ ቀስ በቀስ ከሞተበት እያንሰራራ እና እየተቀሰቀሰ መጣ..ምንም አግኝቼ አልነበረም ..ከእናቴ የማገኘው ተንሰፍሳፊ ፍቅር እና ከጓደኞቼ የማገኘው ማፃናኛ …››
‹‹በጣም አሪፍ ታሪክ ነው ያለህ››
‹‹አዎ መራር የህይወት ገጠመኞች ለሰሚው ወይም ለፅሀፊው ሳቢ ታሪክ ይወጣቸዋል…››
‹‹ከዛስ እንዴት ሀሳብህምን ሙሉ በሙሉ ልትቀይር ቻልክ….?››
‹‹አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተውኩትም…አሁንም የመሞት እቅዴ በውስጤ አለ…››
‹‹እሺ እንዴት ልታራዝመው ቻልክ….?››ጥያቄውን አስተካከለችለት፡፡
‹‹እንዴት መሰለሽ….ከዛ ከሰው ሀገር በገንዘብም በመንፈስም ክስርስር ብዬ የመጣሁ ቢሆንም ብዙም ሳልቆይ ሚስኪን የልጅነት ጓደኞቼ አዋጥተው አሁን የምጠቀምባትን ላዳ ገዝተው ሰጡኝ..በቃ የመሞት ሀሳቤን አራዘምኩት ..ለራሴ ሁለተኛ እድል ሰጠሁት..ቢያንስ ለጊዜው ሰርቼ ስጋዬን የማኖርበትን ካገኘሁ አንድ ቀን ምን አልባት ሁለተኛውን የህይወት ምኞቴን በሆነ ተአምር ሊሳካልኝ ይችል ይሆናል…ብዬ ተስፋ አደረኩና መጨረሻውን እስከማይ ሁለት ዓመት ተኩል በሀገሬ ኖርኩ..ዘና ብዬ ለማንም ለምንም ሳልጨነቅ…ባሳኘኝ ሰዓት እየሰራሁ ሲያሰኘኝ ደግሞ እየተኛው..የእናቴን ሽሮ እየበላሁ ተስፋዬን በመጠበቅ እንሆ አለሁልሽ››
‹‹ምንድነው ተስፋህ..ማለቴ ይሳከልኛል ብለህ የምትጠብቀው….?››
‹‹የልጅነት ፍቅሬን… ..አንድ ቀን ቀና ብላ ታየኛለች የሚል ተስፋ..አንድ ቀን ከቄስ ትምህርት ቤት ጀምሮ እንደማፋቅራት እና ዕድሜዬን ሙሉ በልቤ ተሸክሜያት ስዞር እንደኖርኩ ተረድታ በእቅፎ ታስገባኛለች ብዬ ተስፋ በማድረግ..አንድ ቀን እጄ ትገባለች በሚል ተስፋ…..››
‹‹ወየው ጉዴ!!›አለኝች በውስጧ፡ በዚህ ቅርብ ጊዜ ውስጥ የምትቀርባቸውና የምትመኛቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት እንዴት ሆኖና ምንስ በሚሉት አጋጣሚ እንደዚህ በፍቅር ስክር ያሉና የታወሩ ሆነው እንደሚገኙ ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም...?‹‹ይሄኛውንስ ዛሬ አልምረውም…በፍጽም፡፡››ስትል ፎከረችው፡፡
‹‹ይቅርታ ሙሉ ታሪኩን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ….››
‹‹እየነገርኩሽ እኮ ነው …እየተረተርኩልሽ…..ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል አይደል የሚባለው››
‹‹አይ እዚህ አይደለም…እኔ ቤት እንሂድና ተረጋግተን እየጠጣን ታወራልኛለህ….አሁን ሆቴሉም ሊዘጋ መሰለኝ››
‹‹ይቻላል››ይከራከረኛል ወይም ይቃወመኛል ብላ ነበር የጠበቀችው ..ቀድሟት ተነሳ ..ሂሳብ ከፍላ ተከተለችው …. እየተወለጋገድና እርስ በርስ እየተደጋገፉ ላደው ድረስ ሄድ ..ሹፌሩ ተቀብሏቸው እቤት ድረስ አደረሳቸውና የለሊቱን ግዳጅ ጨረሶ ተለያቸው..
እሷም ዛሬ ለዛውም ከመሸ ያወቀችውን ባለ ላዳ ይዛው ወደቤቷ ገባች…..
✨ይቀጥላል✨
#YouTube ቻናሌን አ.ረ.ረ..ረ!!!subscribe እያደረጋቹ😔

👍121❤11🤔7🔥3😁2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
መኝታ ቤቷ ገብታ ልብሷን ከቀያየረች በኋላ የጀመሩትን አይነት መጠጥ አምጥታ ለሁለቱም ቀዳችና ወደጫወታቸውን እዲመለሱ ተመቻቸች..
‹‹እሺ አሁን ካቆምክበት ጀምርልኝ››
‹‹ምን….? ››አለት ሁሉን ነገር የረሳው ይመስላል
‹‹ታሪክህን እየነገርከኝ ነበር››
‹‹እ..አዎ…ግን የት ላይ ነበር ያቆምኩት….?››
‹‹ስለፍቅረኛህ ጀምረህልኝ ነበር..በህይወት የምትኖርበት ምክንያት እሷን አንድ ቀን አገኛት ይሆናል በሚል ጉጉት ምክንያት እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር ያቆምከው››
‹‹አዎ….አይገርምሽም …
እስከጥቂት ቀናት ድረስ እኮ ምንም አይነት ተስፋ አልነበረኝም…››
‹‹ቆይ ጠይቀሀት እንቢ ብላህ ነው….?››
‹‹አረ መጠየቅ…ትቀልጂያለሽ እንዴ ….?ቀና ብዬ እንኳን ሰላምታ ልሰጣት ድፍረቱ የለኝም.››
‹‹ግን እኮ እንደዛ አይነት ሰው አትመስልም..በጣም ደፋር ግልጽ እና በራስ መተማመን ያለህ ሰው ነህ››አለችው ከልቧ..
‹‹እኔም እንደዛ ነኝ ብዬ አምናለሁ..ፍቅር የሚባለው ነገር ግን ዋና ባህሪው ያልሆንሺውን ሆነሽ እንድትገኚ ማድረግ ይመስለኛል…እጅግ ክፉ የነበርሽው ሰው በፍቅር ውስጥ ስትሆኚ ስጋዬን ግፈፉት እስከማለት ድርስ የሚደርስ ደግነት ያጓናጽፍሻል….ደንዳናና ኮስታራ የነበርሽው፤አልቃሽና ተርበትባች ሆነሽ ቁጭ….ፍቅር እንደዛ አይነት በሽታ ነው፡፡››
‹‹ቢሆንም ….ይህን ያህል ካፈቀርካት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብህ ..ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው….?››
‹‹የሚገርመው እሱ ነው..በእሷ ቤት እና በእኔ ቤት መካከል ያለሁ እርቀት ግማሽ ኪሎ ሜትር አይሆንም…. ሁለታችንም ሳሪስ በአንድ ሰፍር ተወልደን እዛው አንድ ሰፈር ያደግን ነን…ቤተሰቦቻን የአንድ እድር አባል ሆነው፤አንድ የጽዋ ማህበር መስርተው ዕድሜያቸውን በጉርብትና የኖሩ ናቸው….አንድ ቄስ ትምህር ቤትፊደል መቁጠር ጀምረን .አብረን ኤለመንተር የገባን የእድሜ እኩዬች ነን››
‹‹ይገርማል!!››
‹‹እውነትሽን ነው በጣም ይገርማል…. ከ1ኛ ክፍል አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል አብረን ነበር የተማርነው…በተለይ ዘጠነኛ ክፍል አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው…ግን በወቅቱ እኔ ግማሽ ልቤ ነበር ክፍል ውስጥ የሚገኘው… እሷ ደግሞ አካሏም ነፍሶም ትምርቱ ላይ የተጣበቀ ነበር፡፡ግን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ቢኖር ሁለታችንም ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ከትምህርት ቤት አንቀርም ነበር..››
‹‹ለምን ….?››አለችው ገለጻው ገርሞት
‹‹እሷ ለትምህርት ባላት ፍቅር የተነሳ እኔ ደግሞ ለእሷ ካለኝ ፍቅር የተነሳ….››
አሳቃት….ብርጭቆውን አንስቶ ከተጎነጨለት በኃላ ቀጠለ
‹‹እሷ እንደማንኛውም የክፍል ጓደኛ ግን ደግሞ ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ የሰፈር ልጅነት እና አብሮ አደግነት ነው የምትቀርበኝ…እኔ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው ያሉኝ.. እናቴ እና እሷ ብቻ..በቃ..ያኔ አብሬት በምማርበት በዛ ጊዜ ብቻ አልነበረም እንደዛ የሚሰማኝ.. አገር ለቅቄ በስደትም እያለው እንደዛ ነበር እምነቴ…የሆነች ሴት በሆነ ነገሮቾ ትንሽም እንኳን ከእሷ ጋር ካልተመሳሰለችልኝ..የሆነ የእሷን ነገር እንዳስታውስ ካላደረገችኝ አንድ ደቂቃም ላወራት ወይም አጠገቧ ልቀመጥ አይቻለኝም….ከአስር አመት መለያየት በኃላ ከ10 ዓመት ናፍቆት በኃላ እሷን እና እናቴን አንዴ አይቼ ለመሞት ወስኜ ወደሀገሩ ስመጣ…እሷን በተመለከተ ጭራሽ ተስፋ የሚያስቋርጥ ነገር ነው ያጋጠመኝ…፡፡አፍላ ልጃገረድ ገና አጎጠጎጤ ሆና ጥያት የሄድኳት ልጅ አድጋና ፈክታ ሙሉ ሴት ሆና ጠበቀችኝ…፡፡የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የተለየኋት ልጅ ዶክተር ተብላ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ትልቅ ባለሞያ ሆና አገኘኋት..እና የሩቅ ህልሜ የነበረችው ልጅ ጭራሽ መቼም የማትፈታ ቅዠቴ እንደሆነች አሰብኩ…ሳያት በሩቅ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ድንገት መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳን ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ አንገቴን አቀርቅሬ ሰላምታ ለመስጠት ከመሞከር ውጭ እሷ እንኳን ለሰላምታዬ አፀፋውን መመለሷ እና አለመመለሷን እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ይህቺ ልጅ የእኔ ልጅነቴ ነች….የሩቅ እሩቅ ትዝታዬ …ብዙ ብዙ ለሊቶች በህልሜ ያየኋት… ብዙ ብዙ ታሪክ ያጫወተችኝ….ብዙ ብዙ ነገር ያወጋኋት…ያወጋችኝ..፡፡እንደዛ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ ያገባኋት…ብዙ ብዙ ልጆች የወለደችልኝ…ብዙ የሳምኳት፤ ብዙ የሳመችኝ…ብዙ ያፈቀርኳት፤ብዙ የወደደቺኝ…ግን ሁሉም በህልሜ የሆነ ነበር …››
‹‹ምን አይነት ፍቅር ነው..ስል አሰብኩ ደግሞ ከዚህች ልጅ ጋር የሚያመሳስለኝ አንድ ነገር ይኖር ይሁን .. ….?አዎ መኖርማ አለበት ….እደዛ ቢሆን ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት አብሮኝ ያሳለፈው…እቤቴ ድረስ ተከትሎኝ በለሊት የመጣው…አዎ እንደዛ ቢሆን ነው ሚስጥሩን ዘክዝኮ የሚነግረኝ…››ስትል የራሷን ግምት ወሰደች…ግምቷ እውነት ሆኖ እስከአልጋ መዋደቅና መዋሰብ ድረስ ያደርሷቸው እንደሆነ አሁንም በውስጧ እያሳላሳላች ነው ፡
ቀጠለ እሱ…‹‹እና ይገርምሻል ከሶስት ቀን በፊት ያልጠበቅኩት አጋጣሚ ተከሰተ…››
‹‹ምን ተከሰተ….?››
‹‹ወደሀገሬ ከተመለስኩ ከሁለት ዓመት ተኩል በኃላ ትናንት….ድብር እና ጭፍግግ ብሎኝ ሰፈር ላዳዬ አቁሜ እኔም ላዳዬ ውስጥ ወንበሬን ወደኃላ ለጥጬ መፅሀፍ በማንበብ በተመስጦ ላይ እያለሁ...በሀይለኛው የላዳው የኃላዋ በራፍ ሲንኳኳ የሆነ የእብድ ድርጊት መስሎኝ በርግጌ ተነሳሁና አንገቴን በመስኮት አስግጌ ወደ ኃላው ተመለከተኩ…
‹‹እንዴ ሰላም…!!!!!››
‹‹ክፈትልኝ››
‹‹እሺ ››ተረብትብቼ ከፈትኩላት..ተስፈንጥራ ገባች…የሆነ ሰው ከኃላ እያባረራት ይመስላል..ፀጉሯ ሁሉ ጭብርር ብሏል…የአይኖቾ ደም መልበስ ምን አልባት ለቀናት ስታለቅስ እንደቆየች ምስክር ናቸው…..አለባበሶም እንደነገሩ እና ያልታሰበበት ነው….››የአመታት ህልሜ የሆነች ልጅ በእንዲህ አይነት ያልታሰበበት አጋጣሚ ላዳዬ ውስጥ ትገባለች ብዬ እንኳን ማሰብ አልሜ እንኳን አላውቅም…..
‹‹ንዳው ››አለችኝ
ህልም ውስጥ ያለሁ ነበር የመሰለኝ ፡፡ ትዛዞን ተቀብዬ …ሞተሬን አንቀሳቀስኩ እና ነደሁት
‹‹-የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ….?››ጠየቅኳት
‹‹የምን ፖሊስ ጣቢያ….?›› አለችን ግራ በመጋባት
-‹‹አይ እንዲሁ ነገር ስራሽን ስገመግመው የሆንሽው ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው..››
‹‹ሆኜያለሁ...አዎ የሆነ ነገር ሆኜያለሁ… መች አልሆንኩም አልኩህ …ግን ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ምን ይፈይድልኛል..….?››አለቺኝ.‹‹ይቅርታ እሺ የት ልወስድሽ..….?››አልኳት
በመለማመጥ..እወነቴን ነው በዛች ላዳ ጆሀንስበርግ አድርሰኝ ብትለኝ እንኳን እድሜ ልክ ይውሰድብኝ እንጂ እንቢ አልላትም…በምን አቅሜ…በእሷ መታዘዝ እኮ ለእኔ እድል ነው…የአለምን ህዝብ አጥፋልኝ ብትለኝ እንኳን ባልችልም ከመሞከር ወደኃላ አልልም፡፡
‹‹እኔ እንጃ የሆነ ሰው እንደእኔ ሲሆን የት ነው የሚሄደው..….?ወይም የት ነው መሄድ ያለበት..››በቀላሉ ልመልሰው የማልችለውን ውስብስብና ግራአጋቢ ጥያቄ ጠየቀችኝ ‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ቤተክሪስትያን ልውሰድሽ….?››ይሻል የመሰለኝን አማራጭ አቀረብኩላት ፡

👍85❤8😁2👏1