አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከቡስካ_በስተጀርባ
#ድንግል_ውበት


#ክፍል_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ባኞ ቤቱ ውስጥ ጠብ ጠብ ከሚለው የውኃ ድምፅ በተጨማሪ ላይ ላይ የምትተነፍስ ሴት ድምፅ ይሰማል" የመታጠቢያ ገንዳው ውኃ እስከ ወገቡ የደረሰ ሲሆን ካርለት ውኃው ውስጥ ጋደም ብላ
ቀኝ እግሯን ገንዳው ከንፈር ላይ በማስቀመጥ ከግርጌዋ ያለውን የውኃ ማሞቂያ በተመስጦ ትመለከታለች" ከውኃ ገንዳው በስተቀኝ የእጅ መታጠቢያው ከፍ ብሎ ደግሞ በክፍሉ ሙቀት ሳቢያ የሚያዠው መስተዋት አለ የመታጠቢያ ክፍሉ ጠበብ ያለ ቢሆንም ንጹሕና ዘመናዊ ነው ከመግቢያው በር በስተግራ ካለው የቆሻሻ ልብስ ማጠራቀሚያ ቅርጫት ካኔተራ፣ ሱሪና ጃኬት ተቀምጧል። ከሱ በላይ ሰፋና ረዘም ያለ በነጭና ሐምራዊ ቀለም የተዥጎረጎረ ፎጣ
ተንጠልጥሏል።

ካርለት የገንዳውን ውኃ ቀይራ ሰውነቷን በንጹሕ ውኃ ከተለቃለቀች በኋላ ከገንዳው ውስጥ ወጥታ በጥቁርና ነጭ ቀለም
የአጥር ሥዕል ከተሣለበት ጸጕራማ ምንጣፍ ላይ ቆመች" እርጥቡ ጸጕሯ ትከሻዋና ደረቷ ላይ ተለጥፏል" ከጸጕሯ ወደ ግንባሯ እየተንኳለለ የሚወርደው ውኃ በቅንድቧ ሥር እየሰረገ ተለቅና
ሰርጐድ ያለውን ዓይኗን ያራጥባል” በደረትና ትከሻዋ አካባቢ ቁጥር ቁጥር ያለ የውኃ እንክብል ከመታየቱም ባሻገር ከሴት ብልቷ ላይ ካለው ስስ ጸጕር ላይ ደግሞ በውርጭ ሰሞን ሳር ላይ የሚታየውን የመሰለ ትንንሽ የውኃ ነጠብጣብ ይታያል"

ካርለት ወደ መስተዋቱ ቀረብ እንዳለች ገፅታዋ ከሚያዠው መስተዋት ውስጥ ተከፋፍሎ ታያት። መስተዋቱን ተወት አድርጋ
በእጆቿ ጡቶቿን ጨበጥ ጨበጥ አደረገቻቸው" ቀኝ እጇ ቀኝ ጡቷ ላይ ሲቀር ግራ እጇ ግን ወደ ታች እየተንከላወሰ ጕዞ ጀመረ ወደ ሴት ብልቷ" እጇ የደረሰበትን በዓይኗ ተመለከተችው
ከሰፊው የመስተዋት መስኮትና ላዩ ላይ ከተንጠለጠለው ነጭና
ቡና ዓይነት መጋረጃ አልፎ አልፎ ዧ ብሎ የሚያልፍ የመኪና ድምፅ ይሰማል" ክፍሉ ውስጥ ካሉት ሁለት አልጋዎች መካከል አንድ
ኮመዲኖ አለ። ኮመዲኖው ላይ «ሶኒ» የሚል ምልክት ካለበት ሬዲዮ ካሴት ውስጥ ከዛሬ ሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበረው ፒያኖ ሶናታ የሙዚቃ ስልት ድምፁን ሰለምለም
ሞቅ ሞቅ ሰለምለም...እያደረገ ይንቆረቆራል ከመስኮቱ ጠርዝ አካባቢ ሁለት ሶፋና አንድ ጠረጴዛ ያለ ሲሆን ጠረጴዛው ላይ ከግማሽ
በላይ የተጠጣለት የማር አረቄ ይታያል"

ስቲቭ ማርቲን የአደረው «የዞረ ድምር» ዓይኖቹን ከርቸም ያለ እንቅልፍ አጋድሞታል በአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል
በተዘጋጀው የቡፌ ግብዣ ላይ ሦስት ወንበር እንዲያዝላቸው በማዘዝ ሁለቱ የፍቅር ጓደኛሞች ከከሎ ሆራ ጋር በመሆን ምሽቱን ከምግብ ጕዝጓዙ በኋላ መጎንጨቱንና በአፍሪቃውያን ሙዚቃ መውረግረጉን
እስከ እኩለ ሌሊት ሲያስኬዱት ቆይተው ነው ሁለቱ ፍቅረኛሞችና
ከሎ ሆራ «መሥመርህን ለይ» የተባባሉት"

ካርለት እና ስቲቭ የሥራ ቦታቸው በጣም የተራራቀና
የትራንስፖርትም ችግር ያለበት በመሆኑ ተመልሶ ለመገናኘት ቢያንስ የሦስት ወር ጊዜ ያስፈልጋቸዋል" በፍቅር አባዜ ለተያዙት ለእነዚህ ወጣቶች ደግሞ ጊዜው የትየለሌ ነው ሩቅ። ስለ መለያየታቸው እንጂ ስለ መገናኘታቸው የማይተማመኑት ፍቅረኛሞች በወሲብና በፍቅር ጨዋታ ሰዓታቸውን በሚገባ ለመጠቀም በአንድ ወጥ ስሜት ጥረዋል" ድብቅነት በሌለው ንጹሕ የፍቅር ጨዋታ ልባቸውን
ስልትና ቃናው በሚጣፍጥ ቅላፄ እያስጨፈሩ ራሳቸውን በመሆን በፍቅር ባሕር ከመዋኘት አልፈው ዘቅጠውበት አድረዋል።

ካርለት እንደምንም በድኗን ከስቲቭ እቅፍ መንጭቃ ተነሥታ ወደ ባኞ ክፍሉ በመሄድ ገላዋን ተጣጥባ ስትጨርስና በፎጣ ገላዋን
ስታደራርቅ ከስቲቭ ረዘም ላለ ጊዜ የመለየቷን፣ የፍቅርና ወሲብ ጥመኛ የመሆኗን ትርዒት በእዝነ ልቦናዋ ስትቃኝ ፍርሃትና ጭንቀት መንፈሷን ሰንገው ያዙት ተፈጥሯዊ ስሜቷ መኪና አይቶ እንደማያውቅ ፈረስ አእምሮዋን ጥሎ በረገገባት"
አንገቷን ዘንበል በማድረግ መጀመሪያ ጡቶቿን ከዚያም
እምብርቷንና ሰርጓዳ ወገቧን፣ ለስላሳ ጭኖቿን ስትመለከት ስሜቷን
በአእምሮዋ ለመቆጣጠር ተሳናት" ካርለት ስሜቷን ልትጫነው ስላልፈለገች በግዴለሽነት የመታጠቢያ ከፍሉን በር በርግዳ ስትወጣ ስቲቭ ቀኝ እግሩን አጠፍ አድርጎ ጭኖቹን በመበርገድ ተንጋሎ ተኝቷል።

ካርለት ስቲቭን ስታየው የሆነ ስሜት በመላ አካሏ ቅጽበታዊ መተረማመስ ፈጠረና ፍቅር አመንጭ ሕዋሳቶቿ ተከፋፍተው ወደ ፊት ገፈተሯት አእምሮዋም በስቲቭ አካል ላይ ቀስቱን ደገነ የልግጠም፣ ይውጋኝ ፍልሚያ። «ግንኮ የስቲቭ ስሜት እንደኔ ላይሆን ይችላል? ስሜቴን መቆጣጠር መቻል አለብኝ" ሊደከመውም እኮ ይችላል!» ብላ አሰበች" ታስብ እንጂ መንቀሳቀሷን አላቆመችም የሚገፋፋት ስሜት ወደፊት አዳፋት ተጠጋችው» ካርለት ያሰቡትን ለማድረግ መወሰን የሚሳንበት ወቅት መሆኑ ገብቷታል"

«ስቲቭ» አለች የእጅ ጣቶቿን ወደ ቡናማው ጸጕሩ እየሰገሰገች።
ቦንብ ቢፈነዳ እንኳን የሚነቃ የማይስለው ፍቅረኛዋ የእሷን ውብ ድምፅ ሰምቶ ዓይኖቹን ሲገልጥ የሚወደው ምስል እርቃነ ሥጋውን ከአጠገቡ ቆሞ ሲያይ፣ «ኦ...» ብሎ ዓይኖቹን ገለጠ።

«ፍቅር የሚጣፍጠው ሲልሱት ሳይሆን ሲግጡት፣ ኩርሽምሽም አድርገው ሲውጡት፣ ከአካል ጋር ሲዋሐድ፣ የተፈጥሮ ቦታውን
ሲይዝ፣ ደባቂና ተደባቂ ሲሆን እንጂ በቃላት ድርደራ አይደለም»ብላ የምታምነው ካርለት ለስቲቭ፣ «ና» የሚል ምልክት በእጇ አሳየችው ያ እጇ ሁሌም ከሚያስደስተው አካሏና ውስጣዊ እሷነቷ
እንደሚያደርሰው ያውቃልና ተከተለው።

በጣም ደክሞታል፤ ከካርለት እጆችና የፈገግታ ኃይል ግን ራሱን ሊለይ አልተቻለውም። ስለዚህ ወደ ተጠራበት አቅጣጫ ተጓዘ ጒዞው ራቀበት ከተጠራበት አካል ቶሎ ደርሶ ለመደሰት በጣም ጓጕቷል ካርለት ባኞ ቤት ውስጥ እንደገቡ ገፍትራ ለብ ካለው ውኃ
ውስጥ ከተተችው ሣቀ ሣቀች ሁለመናቸው ተሣሣቀ
ጭኖቿን ተመርኵዞ አንጋጦ ሲያይ የገነትን በር ያየ መሰለው ታዲያ የዚያን ውብ ስፍራ በር ከፍቶ የማይገባ ማን አለ? በየጅማቱ ሥር ተበታትኖ የነበረው ኃይል ዘቅዝቆ ወደ ብልቱ ሲንዶለዶል
ተሰማው" ያ የተበታተነ ኃይል እንኳን የተፈቀደለትን፣ ሌላ ጠንካራ በር እንኳ ጥሶ የሚያስገባ ኃይል እንዳለው አመነ።

«እወድሃለሁI ፍቅርህን አልጠግብምI ስግብግብ ነኝ እንድትለቀኝ አልፈልግም...» የሚል ድምፅ የሰማ መሰለው
የቃላት ምልልስ ወቅቱ አለመሆኑን በመረዳቱ ግን እግሮቿን እየዳሰሰ
ተነሣ ሁለቱ አካሎች ተዋሐዱ ፍጡር ካለ ክንፍ ወደሚንሳፈፍበት ወደ ሰማየ ሰማያት ተነጥቆ የገነትን ውበት ወደሚጎበኝበት ማራኪ መዓዛ ውብና እንከን የለሽ ተፈጥሮ ወደሚታይበት፣
እውነተኛ የፍቅርና የደስታ ዜማ ወደሚዜምበት ዓለም ተያይዘው ነጐዱI በሩ ተከፍቶ ተዘጋ።

።።።።።።።።።።።
ካርለት አልፈርድ በኦhስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በሶስዮሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ በዩኒቨርሲቲው የአንትሮፖሎጂ
ዲፓርትመንት አባል በመሆን በወቅቱ ታዋቂ በነበሩት አንትሮ ፖሎጂስቶች የተዘጋጁትን ጽሑፎችና ዲስኩሮች ተከታትላለች።

ከአሥራ አምስተኛው ክፍለ ዘመን በተለይም ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ እመርታን ካሳየበት ከዛሬ መቶ ሃምሳ ዓመት ወዲህ እየተዋጡ
የመጡት ቅርሶች፣ የተናቁት ባህሎችና ለከፍተኛ ውጤት ሊያበቁ የሚችሉት የአርኪዮሎጂና የሌሎችም ጥናቶች የምሁራኑን አእምሮ ይበልጥ በመሳባቸው እንደ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ አሜሪካና ጃፓን የመሳሰሉት ምሁራን ትኵረት እንደ ሰጡት እንግሊዛውያንም ምሁራንም በመስኩ እጅግ ተስበው ነበር"
👍46
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሁለት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከኢትዮጵያ ጥናትና ምርምርና ከሌሎች ተቋማት ለጥናቷ
አስፈላጊ የሆኑትን ውጤቶች ካነበበችና ከግለሰቦች ጋር ሐሳብ
ለሐሳብ ከተለዋወጠች በኋላ እግረ መንገዷን ሊረዳት የሚችል የክልሉ ተወላጅ አድራሻ፣ የጥናትና የጕዞ ፈቃድ አውጥታ ወደ
ጥናት ቦታዋ ከመጓዟ በፊት ምሽቱን በአዲስ አበባው ሒልተን እንግሊዝ ኤምባሲ ከሚሠራውና ለተወሰኑ ወራት በአዲስ አበባው
ቆይታዋ ጠረኑን ከለመደችው ጓደኛዋ ጋር እቅፉ ውስጥ ስትንቀሳቀስ
አድራ እንደገና ገላዋን ታጠበችና ልብሷን ለባብሳ ወጣች"

በአስተሳሰቧ፣ በግልጽነቷና በውበቷ የነሆለለው ስቲቭ
አለባበሷን፣ ከሰዓታት በፊት ፍቅር አመንጪ የነበረው አካሏ ተለውጦ ለሥራ መዘጋጀቷን ሲያይ እሱ ፍቅር ከፈጠረው የደስታ
ዓለም ከነበረበት ፈጽሞ ሳይንቀሳቀስ እሷ ግን ገስግሳ ወደ ገሐዱ
ዓለም በመመለሷ በፍጥነቷ ተደንቆ በተመስጦ ሲመለከታት ቆየና፣

«የኔ ቆንጆ አሁንም ታምሪያለሽ» አላት።

«ማማሬን እርሳው» አለችው።

«ለምን?»
«ከጥቂት ሰዓታት በፊት እኔም እረስቸዋለሁና።»

«የኔ ቆንጆ፣ ታዲያ ምን እንድልሽ ትፈልጊያለሽ?»

«የጉጉትን ዘዴ፣ የንስርን ማስተዋል፣ የአንበሳን ልብ፣ የኢዮብን ትዕግሥት፣ የአባትሽን ተስፋ አይቆርጤነትና አእምሮ ይስጥሽ በለኝ» ብላ፣ ጉንጩን ሳም አደረገችው"

ስቲቭ አስተያየቱን ጠለቅ አድርጎ ሲያስተውላት ቆየና፣ «አሁን አንችን የመሰለ ውብ ከእነዚያ ዘላኖች...» ሊናገር የፈለገውን ሳታስጨርሰው አፉን በአመልካች ጣቷ ከደነችው።
«ማፍቀር ያለብህ እኔን ብቻ ሳይሆን ፍላጎቴንም እንዲሆን እፈልጋለሁ" ትልቁ ውበት ደግሞ ሥራ መሆኑን አትዘንጋ» አለችውና ሌላ ቃል ሳይለዋወጡ ለቁርስ ክፍሉን ቆልፈው ወጡ"
  ።።።።።።።።።።።።።
ፈርጠም ያለ፣ የቀይ ሽንኩርት ቅርፅ መሳይ አፍንጫ ያለው! ዳጐስ ብሎ ቀላ ያለውን ከንፈሩን ሲገልጥ ነጫጭ ፍልጥ ጥርሶቹ የሚያማምሩና ከሸበላው ቁመናው ጋር የተስተካከለ አቋም ያለው
ከሎ ሆራ ለየት ያለ ባሕርይ ይታይበታል።

ቁጥብነቱን፣ ጅንንነቱን፣ ጥርጣሬውንና ብቸኝነት መውደዱን ያዩ ጓደኞቹ፣ «ነብሮ» ይሉታል የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቹ" ቀልድ፣
ቧልት ከጀመሩለት እንደ ቆሰለ ጎሽ በንዴት ጦፎ ይፎገራል" ከሰው ጋር ደጋግሞ እንደ መጣላቱ ግን ኃይሉን ተማምኖ ተማቶ
አያውቅም" ሁለቴ ሦስቴ ቃጥቶ ቃጥቶ ማንም በማይገባው ቋንቋ
አኩተምትሞ ዘወር ይላል" ታዲያ ብዙዎቹ አዳልጧቸው ቀልድ ብጤ ጀማምረው በዚያ ፈርጣማ ጡንቻው በሰነዘረ ቁጥር ጠረመሰን
እያሉ አንዴ ከተሳቀቁ፣ «እርም» ብለው ይሸሹታል" ስለዚህ ምን እንደሚያበሽቀው ያለፈው ሕይወቱ ምን እንደሚመስል፣
ብቸኝነቱ ከመቼ ወዲህ እንደ ጀመረው ከፍቶ ማየት የሚችል ሰው አልተገኘም ግለቱ ስላላስቀረበ"

የተማሪን ቆብ አውላቂ መምህራን በለመዱት ቧልት «ጢብ ጢብ» ሊጫወቱበት ይዳዳቸውና እንደ ከለመዳሪ የሚነፋውን
ከንፈሩንና እሳት ተፊ ትናንሽ ዓይኖቹን ሲያዩ በተለይም
በአንቀሳቀሰው ቁጥር እንደ አሎሎ የሚንከባለለውን ጡንቻውን ሲመለከቱ! «በቸር አውለኝ» ብለው አቅጣጫቸውን ሲቀይሩ
ዓመታት ተቈጠሩ“

ከሎ ሆራ የአራተኛ ዓመት የሶሲዮሎጂ ትምህርቱን ሊያጠናቅቅ በተቃረበበት ወቅት በቀጭን ወገቧ ጂንስ ሱሪዋን በቀላል «ቲሸርት» አስተካክላ ለብሳ፣ የተጐነጐነ ረዥም ጸጕሯን ወገቧ ላይ እያላጋች፣ ቶሎ ቶሎ በመራመድ ጫማዋን ቀጭ ቋ ቀጭ ቋ እያደረገች የምትገሰግሰው ወጣት ከዩኒቨርሲቲው ፖስታ ቤት ወረድ ብሎ ከሚገኘው ኮሪደር ጫፍ ላይ ቁጭ ብሎ እግሩን እያወዛወዘ!
ጠጠር ወደሚወረውረው ጥቁር ወጣት ተጠግታ፣ «ይቅርታ ከሎ ሆራ ነህ አይደለም?» ብላ ጠየቀችው፣ በእንግሊዝኛ"

«አዎ ነኝ» አለ ከሎ፣ ከተቀመጠበት ሳይንቀሳቀስ"

«ካርለት አልፈርድ እባላለሁ" እንግሊዛዊት አንትሮፖሎጂስት
ነኝ" ስለ ሐመር ሴቶች ጥናት ለማድረግ ዓላማ አለኝ" አንተም የሐመር ተወላጅ መሆንህን ከዲፓርትመንትህ ኃላፊ ጠይቄ አረጋግጫለሁ» አለችና ንግግሯን በመግታት ትኵር ብላ ተመለከተችው
ከሎ ሆራ፣ የመርበትበት ስሜት አሳየና ከተቀመጠበት ፈጥኖ ተነሣ
ላብ ከወደግንባሩና ቅንድቡ አካባቢ ችፍፍ ችፍፍ ሲል ከንፈሩ አመድ የነሰነሱበት መሰለ።

«ሶ ለምን ፈለግሽኝ?» አላት በተቆራረጠ ድምፅ
«እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ» አለችው፣ በዓይኗ እየመረመረችው
«እንድትረዳኝ እፈልጋለሁ?» ብሎ አባባሏን ደገመና ለትንሽ ጊዜ የመመሰጥ ሁኔታ አሳይቶ፣

«አዝናለሁ፣ ልረዳሽ አልችልም» አላት"

ካርለት፣ የከሎ ሰውነት ሲለዋወጥና ከብስጭቱ ጋር ሲታገል ያስተዋለች መሰላት ስለዚህ ወጣቱ ከሷ ያለበለዚያም ራሱ ከራሱ
ጋር ያልተግባቡት ወይንም ለእሷ ግልጽ ያልሆነላት ሌላ ምክንያት እንዳለው በመረዳቷ ተጨማሪ ጥያቄ ሳታነሣ፣ «አመሰግናለሁ“ ነገ
ግን ጊዜ ወስደህ ካሰብክበት በኋላ ሐሳብህን ከቀየርክ አይ.ኢ.ኤስ
ልታገኘኝ ትችላለህ ካለዚያም ስልክ ቁጥሬን ልሰጥህ እችላለሁ» ብላ፣ ፍጹም ልብ በሚነካ ፈገግታ የአድራሻዋን ካርድ ሰጥታው
«ደህና ሁን» እያለች፣ እጇን አውለብልባለት ሄደች"

ከሎ ሆራ ወደ መቀመጫው ሲመለስ፣ የሚሰበቀውን ወገቧንና ጀርባዋ ላይ ከብለል  ከብለል የሚለውን ጉንጉን ጸጕሯን ሲመለከት
ሐሳቡ ሸፈተበት" ከዓይኑ እስክትሰወር ድረስ በመደመም ሲመለከታት ቆየና ከጥቂት ደቂቃ በፊት የነበረበትን ድንገተኛ ሁኔታ ለማስታወስ ሞከረ» «ሐመር ጥናት ውብ እንግሊዛዊት የሐሳብ
ፍጥጫ፣ የተዳፈነ እሳት ጭረት.እሳት ጫሪ አንትሮፖሎጂስት...ወጣትና ውብ...ዳሚት» አለ፣ እጆቹን ከተቀመጠበት ደረጃ
ጋር እያላተመ።
  ።።።።።።።።።።።።።
ልቡ የአዶከበሬ አታሞ ይመስል እየተነረተ፣ ሰውነቱ ፀሐይ እንዳቆረናው የበረሃ ባልጩት ድንጋይ እያተኮሰ፣ እንቅልፍ ሲመኝ ግን ሲነቃ፣ ዕረፍትን ሲሻ፣ ሲንጠራወዝ፣ ሲገለባበጥ፣ በሐሳብ
ሲድህና ፎቀቅ ፎቀቅ ሲል አድሮ ዋለ"

ብዙ አወጣ አወረደI ያለፈ የልጅነት መጥፎ ትዝታውንም አስታወሰ" አሁን ሊያደርግ የማይፈልገውን እንዲያደርግ ግብዣው
ቀርቦለታል" ሌላው ቀን አልፏል። ለዛሬ ሥሩ ትናንት ነው" ትናንት ደግሞ እሱ የመከራ ጽዋውን የጨለጠበት ወቅት ነው" ዳግመኛ ሬት ሊያወርድ የሚችል ጉሮሮ የለውም” ስለዚህ በትናንት ቂም ያረገዘው አእምሮው አጓርቶና ድብልቅልቁ ወጥቶ እንዲሟሟና እንዲተን
ይፈልጋል" ችግሩ እንዳሰበው ለማድረግ አቅሙ አለ ወይ ነው።

የልጅነት ጊዜው መጥፎ ትዝታ ጥርሱን አግጥጦ፣ ጥፍሩን በማሾል፣ የታባክ ይለዋል“ ይኸኔ እንደ ልጅነቱ ልጅ ይሆንና በጭንቀት እየተንቦራቸ ይርበተበታል" ሊጮህ ይፈልግና ድምፁ
አልወጣልህ ይለዋል" ትናንት ከገደል ውስጥ ወጥቷልI ዛሬ ግን ወደ
ገደል ተገፍቶ ለመግባትና ለመሞት ዝግጁ አይደለም" መሞትም አይሻም ለምን?

እንግዲህ ችግሩ ያለው በትናንትናና በዛሬ መካከል ነው" ልጅ ከነበረው ከሎና አሁን በአካልና በአእምሮ ካደገው ከሎ መካከል
አንዱ ሽሽቱን ማቆምI አለበለዚያም፣ «በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ» እንዲሉ፣ በፍርሃት ላይ የጅብን ፍርሃት እያከለ ወደ ኋላ ሳያይ የሕይወትን ሩጫ መሸምጠጥ አለበት።

ትንሹ ከሎ ማምለጥ፣ መሸሽ ይፈልጋል ከሐመር። ትልቁ ከሎ ደግሞ ልቡ ከሁለት ቦታ ተንጠልጥሎበታል" ከሎ ውሳኔው ሲከብደው ካርለት ከተወችለት ካርድ ላይ በብዕር የተጻፈውን ስልክ
ቁጥር ተመልክቶ ስልክ ደወለ" «ሔሎ ከሎ» አለችው እንደ ሕፃን
ተቁነጥንጣ።

«...ደህና ነኝ» አላት"
«ምነው ልትገልጽልኝ የምትፈልገው ጉዳይ አለ?» አለችው።

«ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ» አለ ከሎ።
👍29
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሦስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሁለት ሳምንት አለፈው ካርለትና ከሎ የየራሳቸውን የጕዞ ዝግጅት ሲያደርጉ ሰነበቱ። ከሎ ሐመር ሲሄድ የሚያነባቸው ልብወለድና
ታሪክ ነክ የአማርኛ መጻሕፍት፣ መጽሔቶች፣ በእንግሊዝኛ የተጻፉ
ልብወለድና የሳይንስ መጻሕፍትን እየገዛ ከፊሉንም እየተዋሰ
አዘጋጀ"

በተለይም ካርለት ኮተቷ በዛ" በማስታወሻዋ በዝርዝር ከያዘችው
አስፈላጊ የምግብ ዓይነቶች የታሸገ የዓሣ፣ የአሳማ፣ የከብት ሥጋ የድንች የዱባ፣ ያጃ ሾርባI የፓፓያ፣ የብርቱካን፣ የአናናስ
ጭማቂ ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር የበዛበት ብስኩት ደረቅ ብስኩት የቆርቆሮ ቢራ ወዘተ ከመድኃኒ ዓይነትም ክሎሮኪን፣ ፓልዱሪን፣ ኒቫኩይን ለወባ መከላከያI ሌሎች፣ «አንቲባዮቲክስ» መድኃኒቶችንና የመጀመሪያ ሕክምና ኪት ኮዳክ ፊልሞችI ባትሪ
ድንጋዮችI ሶፍቶች ወዘተ. በአራት የፕላስቲh ሣጥኖች ደረደረች" ካኖንና ፔንታክስ ካሜራዋንና የተለያየ መጠን ያላቸውን ሌንሶች
በእጅ በሚንጠለጠለው ቦርሳዋ ካኪ ሱሪዎች፣ ካኔትራ፣ ውስጥ
ሱሪ ፎጣ፣ ጡት ማስያዣ፣ ስሊፒንግ ባግ፣ ግራጫ  መልክ ያለው ሹራብ በአየር የሚሞላና ሌላ ተጣጣፊ ፍራሽ፣ ሳሙና፣ ኦሞ፣
ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በፊት በሞዛርት የተቀነባበሩ የፒያኖ ሶናታና የፒያኖ ኮንቸቶ የቤቶቪን ሲንፎኒ ከሦስት ጊዜ በላይ
የወርቅ ዲስክ አሸናፊው ድምፃዊ የቢሊ ጆይል፤ ከሦስት መቶ ዓመት
በፊት የነበረውና የሲንፎኒ አባቱ የሃይደን እንዲሁም ሌሎቹን የባሮክ
ክላሲካል፣ ሮማንቲክና ዘመናዊ የሙዚቃ ካሴቶችን፣ ማስታወሻ፣
ብዕር መጻሕፍትና መጽሔቶች በአራት ማዕዘኑ የብረት ሣጥን
ውስጥ ከተተች" ለሽፍን ላንድ ክሩሰር ቶዮታ መኪናዋም በሁለቱም
ታንከር ነዳጅ ሞላች“ አምስት ጀሪካን ናፍጣም ለመጠባበቂያ ያዘች
ካርለት ለሦስት ወራት የሚያስፈልጋትን ቁሳቁስ ካሟላች በኋላ
ቀሪውን ዕቃዋንና ገንዘቧን ስቲቭ በሰጣት ክፍል ውስጥ
አስቀመጠች» ለአንዳንድ ወጪ ብላ የያዘችውን ሦስት ሺህ አምስት
መቶ የኢትዮጵያ ብርም በሹራቧ ውስጥ በሰፋችው ስውር ኪስ፣
አንገቷ ላይ በምታንጠለጥለው የጨርቅ ቦርሳና ብረት ሣጥኑ ውስጥ
አhፋፍላ ያዘች
ሰኞ ጠዋት ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ላይ አራት ኪሎ ሞቢሉ
ጎን ካለው ሱቅ በር ላይ በቀጠሯቸው ተገናኙu ካርለት ልጥፍ የኋላ
ኪስ ያለው ካኪ ሱሪ፣ ተረከዙ ፕላስቲክ የሆነ ሽፍን ባለማሰሪያ
ማ፣ ቡና ዓይነት ቲ–ሸርት ለብሳ፣ አንገቷ ላይ አነስ ያለ ነጭ ፎጣ
ጣል አድርጋ፣ ከመኪናው በመውረድ የከሎን «ዩኤስኤ» የሚል
ወስፋት የነፋው የሕፃን ሆድ መስሎ የተወጠረ ቦርሳ የኋላ በሩን ከፍታ
በዕቃ ከሞላው መኪና ውስጥ በአንድ በኩል ባለው ክፍት ቦታ
አስገባችና ወደ መኪናው ውስጥ ገቡ" ካርለት የውኃ ኮዳዋን፣ ዳቦ
የያዘ ላስቲኳን አቀረበችና ከከሎና እሷ መካከል ካለው የካሴት ሣጥን
የሞዛርትን ፒያኖ ሶናታ ወደ መኪናው ቴፕ አስገብታ ማስታወሻዋን
በማውጣት የተነሡበትን ሰዓት መዘገበች" ከዚያም ፈገግ ብላ
«መሄድ እንችላለን?» አለችው።

«ኢ ህ» አላት ከሎ፣ ዝግጁ መሆኑን አንገቱን በማወዛወዝ እየገለጸ። ካርለት፣ ቀኝ እጇን ማርሹ ላይ በማስቀመጥ፣ በግራ እግሯ ፍሪሲዮኑን እረግጣ፣ የመኪናውን መስተዋት አየትየት በማድረግ
በአራት ኪሎው የድል ሐውልት ወደ ቀኝ ታጥፈው፣ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት አድርገው ቁልቁል ወደ መስቀል አደባባይ ወረዱ።
ከዚያም በደብረ ዘይት መንገድ ወደ ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ዱከም ተጕዘው ደብረ ዘይት ከተማ ሲደርሱ ወደ ግራ ታጥፈው ሁለት ኪሎ ሜትር በመጓዝ ዠመኪናዋን ሆራ ሆቴል አቁመው ለቁርስ ወደ ውስጥ ገቡ" በስተጀርባ፣ ከሐይቁ ትይዩ የመርከብ ላይ መናፈሻ ከሚመስለው ስፍራ ሆነው የተለያዩና ቱር ቱር እያሉ በመዘመር
የሚበሩ አዕዋፍን እያዩ ቁርሳቸውን ተመግበው ወጡ" ካርለትና ከሎ
ሆራ በሞጆ ታጥፈው፣ ወደ ሻሸመኔ ጕዟቸውን ተያያዙ“ ካርለት፣በመንገዱ ግራና ቀኝ የግራር፣ የጥድ፣ የኮሶ፣ የዝግባ...ዛፎችንና
የተለያዩ ቀለም ያላቸውን እፅዋት እያየች፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ከሚኙት ከሃያ በላይ አዕዋፋት ውስጥ የምታያቸውን በመልክና
በቅርፃቸው ለማወቅ በጆን ጂ ዊሊያምስና በኖርማን አርሎት የተጻፈውን የአዕዋፍ ምስል፣ ቀለም ባሕርይና የሚገኙበትን አካባቢ እያየች ተጓዙና ለምሳ በስምጥ ሸለቆ ካሉት ሐይቆችና የመናፈሻ ቦታዎች አንዱ ወደሆነው ወደ ላንጋኖ ከመንገዱ ወደ ግራ ታጥፈው ገቡ"

ላንጋኖ ሆቴል ምግብ ቤት ብዙ የውጪ ሀገር ዜጎች፣ አፍሪቃውያንና ኢትዮጵያውያን ክብ እየሠሩ በመጫወት ይመገባሉ። ከሆቴሉ ውጪ በቀላል ድንኳን ጥግ፣ በዋና ውስጥ ሱሪና ጡት ማስያዣ
ሆነው የፀሐይ ክሬም ሰውነታቸውን የሚቀቡና ሐይቁ ዳር ለዳር
የሚዋኙ ሴትና ወንዶች ይታያሉ" ጥቁርና ነጭ ሕፃናትም በመዋኛ
ፕላስቲክ ውኃውን በማንቦራጨቅ እየተንጫጩ ይጫወታሉ ከሎና ካርለት ከምግብ ቤቱ ትይዩ የፀሐይ ጃንጥላው ውስጥ
ተቀምጠው ቡናቸውን ሲጎነጩ ቆዩና ካርለት የሐይቁን ዳር ትርምስ
አሸጋግራ ስትቃኝ ቆይታ፣ «ሐይቅ ዳር ስሆን እረካለሁI አገሬ ውስጥ ከጓደኞቼና ቤተሰቦቼ ጋር ያለሁ ስለሚመስለኝ የደስታ ስሜት ይሰማኛል" በአውሮፓ፣ ብዙዎች መዝናኛዎች የሚገኙት ባሕር ዳርቻ ነው" ብቻ...» ካርለት ከሎ ሆራን በጎን ተመለከተችው“


«ኢ ህ» አላት እግሮቹን ወደፊት በመዘርጋት ሰውነቱን ለጥጦ" ካርለት የከሎ ሆራ ጠባይ ደንቋታል ግን አልከፋትም" በቀላሉ ከምትግባባቸው ሰዎች ይልቅ አስቸጋሪ ባሕርይ ያላቸውን ታከብራለች" ሁሉም ሰው ሊረዳው የሚችል ባሕርይ ያላቸው ሰዎች ለሷ አያረኳትም" እረቀቅ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ግን አእምሮዋን
አስደንሳ መላ ፈጥራ፣ የተለያየ ስልት በመጠቀም እንደ ግል ሬዲዮና መከፈት መዝጋት እንደ መቻል
የምትረካበት ነገር የለም።
ለዚህም ካርለት «ዘመናችን የሚርጠው ልዩና ውስብስብ አስተሳሰብ ያላቸውን ነው" ምክንያቱም የነገው ፈጠራና ብሩህ
ሕልም ህላዊነት በመዳፋቸው መሃል ያለው ከእነዚህ ዓይነት ግራ
አጋቢ ባሕርይ ካላቸው ሰዎች ነው» ብላ ታምናለች።

ከሎ ቅንና ተባባሪ ሰው መሆኑን፣ ነገር ግን ይህን ባሕሪውን የሚገልጽ የቃላት ድርደራ ችሎታ የሚጎድለው መሆኑን ተገንዝባለች" ካርለት ከሎን የተለያዩ ነገሮችን እያወራች
እየጠየቀች የቱ እንደሚያስደስተው፣ የቱ አፍንጫውን እንደሚ
ያስነፋውና ጥንካሬውን ከደካማ ጎኑ ለመለየት ምርምሯን ስለ ቀጠለች
አንድ ወጥ በሆነው የሥውር ባሕርይው ዋሻ ለመግባት ትልቁ
የድንጋይ መዝጊያ ማንቀሳቀስ ጀምራለች።

«አዎ የከሎ ባሕርይ ራሱ መጠናት የሚገባው ነው" እሱን ለማጥናት ግን አስፈላጊውን ቁልፍ ማዘጋጀት አለብኝ» አለች
ካርለት፣ ከሻሸመኔ ከተማ ወጥታ የአርባ ምንጭን መንገድ ስትይዝ"
ከሻሸመኔ ትንሽ ራቅ ብለው የአስፋልቱ ጐዳና አልቆ ኮረኮንቹን መንገድ ሲጀምሩ ግን መኪናዋ እየተገጨች ስትንሰጠሰጥና ከፊት
ለፊቷ ያሉትን መኪናዎች ስታልፍና ከእሷ ተቃራኒ የሚያልፉት መኪናዎች የሚያነሡት አቧራ መኪናዋ ውስጥ እየገባ ማፈን
ሲጀምር፣ ካርለት መኪናዋን አቁማ፣ ጸጕሯን በመሸብለል፣ ቆብ
ደፋችበትና መኪናዋን በማንቀሳቀስ ከመሪው ጋር መታገል ጀመረች"
👍20🔥1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አራት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ከሎ ከተቀመጠበት ስፍራ ላይ ጕልበቱን ሰብሰብ አድርጎ በመታቀፍ ከንፈሩን እያኘከ የሚተነፍገውን የወይጦ በረሃ የእፅዋት
ሽታ ይምጋል ከየጉድባው ወጥተው ድብልቅልቅ በሚያደርግ ድምፅ የሚያገሱት አንበሶች፣ በቀጭንና ወፍራም ድምፅ ጨለማን ተገን አድርገው ድምፃቸውን በነፃነት የሚያስተጋቡትን የአራዊት
ትርምስ እያዳመጡ ሁለቱም በሐሳብ ተውጠው ቆዩ"

ከዋክብት ሰማዩ ላይ ሆጨጭ ብለው ብርሃናቸውን ብልጭ
ድርግም ሲያደርጉ፣ ገና የተወለደች ጨረቃ ካለአቅሟ ግዙፉን
ጨለማ ከዝሆን ጋር እንደሚታገል ዝንብ በብርሃን ድል ለማድረግ
ከተራራው አናት ወደ መሃል ሰማይ ስትገሰግስ፣ በበረት የታጎሩት ከብቶች እያመነዠኩ ሲያቃስቱ፣ ካርለትም ሆዷ እየተሸበረ፣
በምትፈጥረው ወኔ ግን እራሷን እየደለለች እንደ ከብቶች ላይ ላይ
እየተነፈሰች ታቃስታለች።

የወይጦ በርሃ በተለይም በቀትር ላይ ሙቀቱ እንደ ደመራ እሳት ይጋረፋል" የአራዊቱና የእፅዋቱ አካል ሳይቀር በሙቀቱ ስለሚቀረና አካባቢው ለየት ባለ ሽታ ይታፈናል" በዚህ ወቅት እንግዳ ሰው እንደ
ውሻ እያለከለከ የሚስበው አየር ፍለጋ አፍንጫውን እንደ አንቴና አቁሞ ያንጋጥጣል። ሆኖም ግን የፀሀይ ማኅበረሰብ፣ ሰጎን፣ አንበሳ፣ የሜዳ ፍየል፣ ጉርኑክና የመሳሰሉት እንስሳት በደስታ ተዝናንተው
ይኖሩበታል።

የወይጦ በረሃ ግለት እየቀነሰ ሲመጣ የፀማይ ማኅበረሰብ አባላት
ከማሳ፣ ከወንዝ፣ ከከብት ጥበቃ፣ ከአደን፣ ከማር ቆረጣ፣ከመንገድ...
ወደየመንደሩ ሲከት፣ ከተለመደው ውጭ ነጭ መኪና፣ ጸጕሯ ረዘም ያለ ነጭ ሴት፣ ልብስ የለበሰ ጠይም ከተሜ መንደራቸው
ውስጥ ድንኳን ከትመው አገኛቸው" በዚያን ወቅት፣ ድፍን የፀማይ ኗሪ ስልክና ሌላ መገናኛ ባይኖርም የሰማው ላልሰማው መልእክቱን በቃል እያስተላለፈ፣ ቤት ለቤት የሚውሉ ሽማግሌና ባልቴቶች ሳይቀሩ «ነጭ በቆሎ» የመሰለችውንና ብልጭልጭ ቅራቅንቦ
የተቀረቀበባትን መኪና፣ ለማየት ጎረፉ።

በካርለት ጸጕርና እጅ ላይ ብዙ የፀማይ «ተመራማሪ» እጆች አረፉበት እንደ አንበሳ ጐፈሬ የለሰለሰ ጸጕር፣ እንደ እብነ በረድ የነጣና የለሰለሰ ገላ፣ የትንባሆ አጢያሽ የመሰለ ጥርስ ሲመለከቱ፣
«ይህች ሰው ምንድ ናት?» ብለው ሲደነቁ ቆዩ። ከመካከል አንዱ፣
«ፈረንጅ ናት» አለ፣ ነቃ ያለው።

«ፈረንጅ...ኡ» አሉ፣ በአድናቆት አፋቸውን እየያዙ“

«አሃ ፈረንጅማ ከሆነች ያች በፍየልና ማር ከነጋዴ
የምንለውጣት የሽጉጥ ጥይት የመሰለችው የፈረንጅ መድኃኒት ትኖራለች» ተባባሉ እርስ በእርሳቸው ከሎ ሆራ ፀማይኛ አይችልም
አንዳንድ ፀማዮች ግን ሐመርኛ ስለሚችሉ መድኃኒቷን እንድትሰጠን
ጠይቅልን አሉት፥ ለምልክት አንድ የ«ቴትራሳይhሊን» እንክብል እያሳዩት" ፀማዮች ካርለትና ከሎ ቋንቋቸውን ባለመቻላቸው በተለይ
ሴቶችና ጎረምሶች ግራ ገብቷቸዋል፣ «ሆሆይ ለካ እናንተዬ ፀማይኛም የማይችል ሰው አለ!» ብለው ተሳልቀዋል።

በዚህ መልክ ራቁታቸውን የሆኑ ሕፃናት፣ ጎረምሳና አዋቂ ወንዶች ግልድም ያገለደሙ፣ ከወገባቸው በታች የለበሱት ቆዳ
መሬት ለመሬት የሚጎተት ትንሽ እንጨት ያለበት ሴቶች ካርለትን እንደ ጉድ ተመለከቷት እሷም እነሱን በተመስጦ እየተመለከተች
የሁለት ወገን ጉዶች ካለ ቋንቋ በጥቅሻ ሲነጋገሩ፣ አንዱ ሌላውን ለመግባባት ሲጣጣር ቆይተው የምሽቱ የአራዊት ትርምስና ጨለማ
ሳያሸብራቸው በየአቅጣጫው በመሄድ ቀስ በቀስ ተበታተኑባት"።

ካርለት፣ hአዲስ አበባው ሒልተን ሆቴል ወደ አርባ ምንጩ በቀለ ሞላ ሆቴል፣ ከአርባ ምንጩ ሆቴል ወደ ድንኳን አዳር እየወረደች
የምትበላውም መጠኑና ዓይነቱ በጣም እየቀነሰ
ቢመጣም፣ በጣም የተቸገረችበት ጉዳይ ሌላ ነበር። እስከ አሁን
እንዳስተዋለችው ፀማይ መንደር ውስጥም ሆነ መንገድ ላይ ሽንት ቤት አላየችም። ለመጸዳዳት ወደ ጫካ ሲገቡ ተመልhታለች" እሷ ደግሞ ጫካ ሄዳ መጸዳዳቱን ሕሊናዋ ሊቀበለው አልቻለም" በጕዞዋ ባሳለፈችው ቆይታ በሶፍት እየተጸዳዳች በማቃጠል፣ እየተጠቀመች
ነው። ሐመር ስትሄድ ግን በዚሁ መልክ መቀጠል የሚቻላት አይሆንም" ሽንት ቤት አስቆፍራ እንዳትጠቀም ለአካባቢው እንግዳ ሁኔታ በመፍጠሯ መልካም ግንኙነት ላይኖራት ነው“ ስለዚህ ሊታይ
በማይችልና መጠነኛ ጥልቀት ባለው ጉድጓድ መጠቀሙን እያሰበችበት ነው።

በእርግጥ እንኳን ካደጉበት ባህል ውጭ ላተወሰነ ጊዜ
ከተከታተሉት ባህልን ለየት ወዳለ ሲገባ የመጨነቅ ስሜት መፈጠሩ
የነበረ ነውና ካርለትም የኢንግላንድ ዘመናዊነት፣ የለንደን ከተማ፣
ማንችስተር የሚገኙት አያቶቿ፣ የወንድና ሴት ጓደኞቿ፣ መዝናኛዎች፣ የጭፈራ ቦታዎች ቀርተው ራቁታቸውን ከሚሄዱ ጥቋቁር ሰዎች፣ ከከብቶች በረት፣ ከፍየልና በጎች ጋጥ አካባቢ መሆንዋ
ሕልም እንጂ እውን ሊመስላት አልቻለም።

ካርለት ወደ ኢትዮጵያ ለጥናት ከመምጣቷ በፊት የአገር ቤቱን ሕይወት ለመለማመድ ወደ ስፓኝ በመሄድ «የስፓኝ በር» ተብላ በምትታወቀው የሁልቫ ከተማ የበጋ መዝናኛዋን በማድረግና ከወንድ ጓደኛዋ ጋር በብርቱካንና የሱፍ ማሳ አቅራቢያ ተቀምጣ ፀሐይ ላይ ብዙ መቆየት፣ ብርድና፣ ብቸኝነትን ለመለማመድ ሞካክራ ነበር።ያን ጊዜ የወደፊት የጥናት ቦታዋ በአሥር እጅ ከዚያ ሊለይ
እንደሚችል ብትገምትም አሁን ግን ዘጠና ዘጠኝ እጅ ያላሰበችውና
ያልገመተችው ዓይነት ሆነባት"

ካርለት እንዲህ በሐሳብ ጉና ስትንጨዋለል፣ እያንቋረረ
የሚከፈተውን የከሎን ጕሮሮ ስትሰማ ከሰመመኗ ተመለሰች።ከዚያም ዓይኗንና ሕሊናዋን ወደ እሱ መለሰች።፣

እስከ አሁን ከከሎ ጋር ባደረገችው ቆይታ ካላናገሩት የማይናገረው ጥቁሩ ወጣት በራሱ ፍላጎትና አነሳሽነት፣ ሊያወጋት መዘጋጀቱ ሳያስደንቃት አልቀረም።
«ሚንጊ ነኝ» አለ ከሎ ድንገት።

«ምን?» አለች ካርለት፥ የጠቀሰው ቃል አልገባሽ ብሏት

«ሚንጊ ማለት በሐመር ቋንቋ ገፊ ማለት ነው» አሁንም የባሰ ተደነጋገረችI ስለዚህ፣ እንዲግባቡ ለማድረግ ገለጻውን ሰፋ አድርጎ ጀመረ።

«ሕፃን ልጅ በሽማግሌዎች ፈቃድ ይወለዳል።»

«ካለ ሽማግሌ ፈቃድ መውለድ አይቻልም? ለመውለድ የሽማግሌዎችን ፈቃድ እንዴት ይጠየቃል? ሽማግሌ የተባሉት ልዩ
ችሎታ ያላቸው ሰዎች ናቸው?» ካርለት ልጅ ለመውለድ ሲያስፈልግ የሐኪም፣ ካስፈለገም የሥነአእምሮ ጠቢብ ምክር
ሊጠየቅ እንደሚችል ታውቃለች" ይህም ቢሆን ችግር ያለባቸውና
በማኅበራዊ ጠንቅ ውስጥ እንዳይዘፈቁ የሰጉ ሰዎች የሚፈጽሙት እንጂ ለማንኛውም ዜጋ የተደነገገ ሕግ አይደለም" ሆኖም፣ ሽማግሌ የተባሉት ለየት ያለ ችሎታ ያላቸው ይሆናሉ ብላ ገመተች።

«አንችን ለማስረዳት ለኔ ከባድ ነው" በኋላ ቀስ በቀስ
ልታውቂው ትችያለሽ ሽማግሌ የተባሉት ግን በዕድሜና በልምድ
ተደማጭነት ያላቸው ሲሆኑ ማንም የሐመር ማኅበረሰብ ሴት ባሏ ጥሎሽ ጥሎ እሱ ዘንድ ካመጣት በኋላ አንድ ቅል አሸዋና አንድ ቅል
ወተት ይዛ ወደ ክልሉ ሽማግሎች ዘንድ ትሄድና ትመረቃለች"ከዚያም ወተቷን ትሰጥና አሸዋውን የያዘውን ቅል ቤቷ አምጥታ
ግርግም ላይ ታንጠለጥለዋለች" ከዚያ፣ ከባሏ ጋር የግብረሥጋ
ግንኙነት አድርጋ ፅንስ ከፀነሰች፣ ወደ ሽማግሎች ሄዳ መፀነሷን ታስታውቃለች። አንዴ መፀነሷን ሽማግሎች ከሰሙ፣ ባሏና እሷ
ፅንሱ አድጎ ከተወለደ በኋላ ጥርስ ማብቀል እስኪጀምር ድረስ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አይፈጽሙም።»
👍30
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_አምስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


...ካለ ሽማግሌ ፈቃድ የተወለደ ግን እንደ እርኩስ ስለሚቈጠር የማደግ ዕድል አያገኝም" የማስወረድ ዘዴውም ልምድ ያላቸው ሰዎች በማኅፀን ውስጥ ያለውን ፅንስ  ጭንቅላት ከውጭ በኩል በመዳሰስ ሲያገኙ ጭንቅላቱን በሁለት አውራ ጣታቸው ውስጥ ደጋግመው በመጭመቅ..» ሲል ካርለት ፊቷ በስሎ የተበላሸ ቲማቲም መሰለ፣ ከንፈሮቿ ተንገረበቡ፣ መላ አካሏ ራደ"

ከሎ ግን ንግግሩን ቀጠለ፣ «...እድታስወርድ ይደረጋልI ከተወለደም ሕፃኑ ጫካ ይጣላል። ስለዚህ አንድ የሐመር ሴት በሽማግሎች ፈቃድ ማርገዟ ከታወቀ በኋላ ከባሏ ጋር ግንኙነት ሳታደርግ ፅንሱ አድጎ መውለጃዋ ሲደርስና ምጥ ቢይዛት በአካባቢዋ የሚኖሩ
ሴቶች ይሰበሰቡና እጅና እግሯን ጥፍር አድርገው ይዘው፣ አፍዋን ያፍኗታል" ይህም ልጁ የእናቱን ማኅፀን ለቆ ተፈትልኮ
እንዲወጣ ይረዳል» ሲል ካርለት ፍርሃት መላ አካሏን አንገጫገጨው። እሷም እንደታፈነች ሁሉ ልቧ ዘለለባት።

«ውልጃ ባፈና? በምጥ ላይ ሌላ ምጥ? » ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ።

«እንግዲህ እንደ ነገሩ ታርሳ ራቁቱን ለተወለደው ሕፃን መታቀፊያ፣ ፎጣ፣ ሙቀት፣ ጂኒ ጃንካ ሳያስፈልገው የቡና ውኃ በማጠጣት
አቀባበል ይደረግለታል። ልጁ ቁሩንና ሙቀቱን ተቋቁሞ አደግ እያለ
ሲመጣ ግን እናቱ ከማማጡ በላይ ትጨነቃለች አባትም ውስጥ
ለውስጥ ይሳቀቃል።

የሚጮኸው ጅብ ሆድ ዕቃዋን፣ የከሎ ወሬ ደግሞ ሕሊናዋ አተረማመሰባት። ትሰማዋለችI የምትሰማው ግን ለማወቅ ሳይሆን
በቃ ከአቅሜ በላይ የሆነ ‹አስፈሪ ነው ብላ መናገር ተስኗት ነው ደንታ ቢሱ ከሎ ግን ጨዋታውን ቀጠለ"

«በሐመር ማኅበረሰብ ላም፣ በሬ፣ በግ...ጥርስ የሚያበቅሉት በታችኛው ድዳቸው ስለሆነ ‹ቅዱስ› ሲባሉ አህያ፣ ፈረስ፣ ጅብ...
ጥርስ የሚያበቅሉት በላይኛው ድዳቸው በመሆኑ እርኩስ ይባላሉ"
የሰው ልጅም የመጀመሪያውን (የወተት ጥርስ ማብቀል የሚገባው
እንደ ቅዱሳን እንስሳት በታችኛው ድዱ መሆን ሲኖርበት፣ እንደ እርኩሳን እንስሳት በላይኛው ድዱ ካበቀለ ከእርኩሳን እንስሳት እንደ አንዱ ስለሚቆጠር ለማኅበረሰቡ አይበጅም ቢያድግም አባቱ
የሚጋፋ፣ የሚገድል፣ የሚበጠብጥ ስለሚሆን ገፊ ወይንም በአካባቢው አጠራር «ሚንጊ» ተብሉ ይጣላል።
«ጥርስ እንደማብቀሉ ሁሉ መውለቁ ላይም በቅድሚያ መውለቅ የሚገባው በታችኛው ድድ የበቀለው ጥርስ መሆን ሲገባው፣
በላይኛው ድዱ የበቀለው ጥርስ ቀድሞ ከወለቀ ሚንጊ ነው ተብሎ
አሁንም ይጣላል ከዚህ በተጨማሪም፣ ሕፃኑ የታችኛው ጥርሱ ከመውለቁ በፊት በአጋጣሚ እንኳ ወድቆ ወይንም በሌላ መንገድ
የላይኛው ጥርሱ ቢወልቅ ሚንጊ ተብሎ ከማኅበረሰቡ እንዲወገድ ይደረጋል» ከሎ ሆራ «ኢ ህ አለና፣

«እና እኔም እንደነገርኩሽ ሚንጊ ነኝ» አላት"

«ታዲያ አንተ ‹ሚንጊ ነህ› ተብለህ ተጥለህ ነበር?» ካርለት፣ ካለማብራሪያ መልሱን በአሉታ ወይንም በአወንታ እንዲመልስላት
በሕሊናዋ እየተማጸነች ጠየቀችው"

«አዎ!» ብሎ፣ ጭንቅላቱንና ትከሻው ላይ በጦር የተወጋውንና በድንጋይ የተፈነከተውን አሳያት" ከዚያ ቀና ብሎ ጨለማውንና
ከዋክብቱን ተመለከተና እንዴት አድርገው እንደ ጣሉት ጨዋታውን
ሲቀጥል ካርለት በሕሊናዋ «ከሎ ለእኔም የሚያዝን አንጀት ይኑርህ እንጂ» በማለት፣ እየተብሰከሰከች የማይቀርላትን ጨዋታ ለመስማት ጉንጯን በጣቶቿ ደግፋ፣ ዓይኖቿን በማፍጠጥ ዓይን ዓይኑን
ተመለከተችው"

«እኔ የተወለድኩት ሐመሮች ተሰባሰቡበት ከሚባለው የቡስካ ተራራ ስር ላላ ከተባለው መንደር ነው" እናቴ በንቲ ኃይሎ ትባላለች" አባቴ ደግሞ ሆራ ሸላ ይባላል። እናቴ ለአባቴ አምስተኛ ሚስት ስትሆን፣ አምስት ልጆችም ወልዳለታለች" እናቴ፣ በልጅነቴ ሁል ጊዜ በምትለብሰው ቆዳ ሸፈን አድርጋ ከሰውነቷ ጋር ትለጥፈኝና ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ቆይታ፣ «ጨዋንዛ» በሚባል ሸካራ ቅጠል
ጥርሴን ትሞርድልኝ ነበር" በወቅቱ ባይገባኝም ኋላ ኋላ ግን የተጣልሁበትን ምክንያት ስሰማ የጥርስ አበቃቀሌ በትክክለኛው መንገድ ማለትም መጀመሪያ በታችኛው ድዴ፣ ቀጥሎ በላይኛው ድዴ ነበር አሉ የበቀለው" ይሁን እንጂ፣ አንድ ጊዜ ጥጃ
ለመመለስ ስሮጥ ወድቄ የላይኛው ጥርሴ አንዱ ወለቀ፣ አንደኛው
ተሸረፈ። እንዳበቃቀሉ ሁሉ፣ በቅድሚያ የታችኛው ድዴ ላይ የበቀለው ጥርስ መውለቅ ሲገባው፣ የላይኛው ጥርሴ ቀድሞ
በመውለቁ፣ ለአደጋ ተጋለጥሁ" እናቴ፣ በሸካራው የጨዋንዛ ቅጠል
ጥርሴን ስትሞርድልኝ የነበረው ለካ የታችኛው ድዴ ጥርስ ቀድሞ የወለቀ ለማስመሰል ኖሯል"

«ይሁን እንጂ፣ ጥረቷ ከንቱ ነበር" ወድቄ ሳለቅስና ጥርሴ ወልቆ ያዩኝ ሰዎች ለሽማግሎች መንገራቸው አይቀሬ ነበር" እናም አንድ
ቀን አባቴ ባልነበረበት ወቅት፣ ሚንጊ የተባሉ ልጆችን የሚጥሉ
ሽማግሎች ወደ እኛ ጎጆ መጡ" እናቴ፣ ከርቀት እንዳየቻቸው ሰውነቷ እየተንቀጠቀጠ ሰውነቴን እንቦሳዋን እንደምትልስ ላም እየሳመችና እየላሰች አለቀሰች።

«ከእናቴ ጋር በተለያየ አጋጣሚ እንለያይ ነበር ከብቶች በድርቅ ጊዜ እርቀው ሲሄዱ፣ ወደ ማሳ፣ ለገበያ ወዘተ.ስትሄድ ሁለትና ሦስት ቀናት፣ አልፎ አልፎ ደግሞ ከዚያም በላይ እንለያያለን ታዲያ ስንለያይ እናቴ ታለቅሳለች እኔ ግን የእሷ ሁኔታ ቢረብሸኝም
ተሎ ወደ ጨዋታዬ እመለስ ነበር። የዛን ቀን ሽማግሎች፣ «ጥርሱ
አስወልቀን እናምጣው» ብለው፣ በጠንካራው እጃቸው ትንሿን እጄን በጨመቁ ቁጥር ግን እንባዬ ሳያቋርጥ ይንዠቀዠቅ ነበር"
«እናቴ ሽማግሎች ጥርሱን አስወልቀን እናምጣው ብለው ሲጠይቋት ካለምንም ተቃውሞ ገፋ አድርጋ አሳልፋ ብትሰጠኝም! ትከሻዋን በሁለት እጆቿ አቅፋ፣ ድምፅዋን አጥፍታ፣ አምርራ
ስታለቅስ ለአደገኛ ሁኔታ እንደተጋለጥኩ ገመትሁ" ሆኖም ግን ምን እንደሚደርስብኝና ለምንስ እንደምቀጣ አላወቅሁም ነበር"

«ሁለቱ ሰዎች ከመንደራችን እያራቁ ሲወስዱኝ እናቴ እጇ
እያርገበገበች ስታለቅስ ትታየኝ ነበር። እንዲያውም እስከ አሁን ድረስ እንኳ ሰው እንደ እሷ ስፍስፍ ብሎ ሲያለቅስ አይቼ
አላውቅም"

«ከመንደራችን ብዙ ርቀን ወደ ጫካው ውስጥ እስክንገባ ሽማግሎች ምንም ሳያወሩኝ ሄድንና የሆነ ገደል አጠገብ ስንደርስ ከፊለፊታቸው ወደነሱ ሳልዞር እንድቆም ነገሩኝ" እኔ ግን፣ ያሉኝን
ለመፈጸም ስላልተቻለኝ ዘወር ስል፣ አንደኛው ሽማግሌ ጦሩን ወደ
ትከሻዬ ሲሰድ ተመለከትኩኝ" ከዚያ በኋላ ሰውነቴን ሲወጋኝና
ለመጮህ ስሞክር፣ ገፍትረው ወደ ገደሉ ከተቱኝ ገደሉ ውስጥ የነበረው ድንጋይ ደግሞ እራሴን ተረተረኝ፤ ደም ፊቴን አለበሰው የሞት ሞቴን ግን የእናቴን፣ የወንድሜን፣ የአባቴን...ስም እየጠራሁ
ጮሁኩ" የደረሰልኝ ግን አልነበረም።

«ስለዚህ፣ ጉድጓድ ውስጥ እንደሆንኩ ስጓጉር ውዬ አድሬ፣ ጠዋት ላይ ድምፄ ተዘጋ። ረፈድፈድ ሲል የሰው ድምፅ ሰማሁ"
የሰማሁት ድምፅ ግን የሰው ቢሆንም ቋንቋው የማውቀው ሐመርኛ
አልነበረም" ለመጣራት ብሞክርም ድምፄ እምቢ አለኝ።

«የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ፣ አንዷ በልቅሶ የተዘጋውን ድምፄን ሰምታ ኖሮ፣ አብረዋት ከሐመር ቆቄ ከተማ የመጡትን ሴቶች ጠርታ በድንጋጤ ተያይዘው ሄዱ መሰለኝ ድምፃቸው ጠፋብኝ" ብዙ ቆይቼ
ግን፣ እንደገና የወንዶችና ሴቶች ድምፅ ተሰማኝ ከወላጆቼ ጋር ሳለሁ፣ እነዚያን መሳይ ሰዎች ወደ መንደራችን ሲመጡ፣ በፍርሃት ፈርጥጬ እሮጥ ነበር" ሆኖም ግን፣ የማልፈራቸው የኔ ወገኖች
ስለጨከኑብኝ መሰለኝ፣ አለባበሳቸውንና ቋንቋቸውን የማላውቃቸው ሰዎች ከጉድጓድ ውስጥ አውጥተው የሚበላ ሲሰጡኝና ሲያሳክ
ሙኝ፣ አንድም ተቃውሞ አላሰማሁም"
👍23
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስድስት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ዲመካና ቱርሚ ሁለቱም የሐመር አውራጃ የገጠር ከተሞች ናቸው" ለቆላማው የሐመር ክፍል ቱርሚ፣ ለደጋማው ደግሞ ዲመካ
አማካዮች ሲሆኑ፣ ሁለቱም ደረቅና ቁጥቋጦ የበዛበት መሬት ያላቸው ናቸው። ቱርሚ መንገድ ዳር ያለ ከተማ ሲሆን፣ ከዲመካ ይልቅ ሁለት ትናንሽ ምግብ ቤቶች፣ ወደ አምስት የሚደርሱ ሻይና ቂጣ
መሸጫ ቤቶች፣ ሁለት በመጠን ከፍ ያሉና ትናንሽ ሳሙና፣ ባትሪ ድንጋይ፣ ክብሪት...የሚሸጥባቸው መንገድ ላይ የሚዘረጉ ሱቆች አሉ። በተለይም በገበያ ቀን ከተማዋ ደመቅዐመቅ ብላ ትታያለች
ገበያ ውስጥ ለመጠጥ ቦርዴና የአበሻ አረቄ፣ ግልድም የሚሆን ከጥጥ
ተሠርቶ ከኮንሶ በነጋዴዎች የሚመጣ ሳዳጎራ፣ ጨሌና አንባር፣በቆሎና ማሽላ ዓይነተኛ ሸቀጦች ናቸው" ቱርሚ፣ በከብት እርባታና
በቁፋሮ ምርት ለሚተዳደረው የሐመር ሕዝብ ድል ያለች ከተማ፣
ታምሮና ተውቦ የሚታዩባት፣ ጐረምሳና ሴቱ አብሮ መሸታ ገብቶ የሚደባበስባት፣ የተጣላ የሚታረቅባት፣ ሽማግሎች ተሰባስበው
የሚመክሩባት፣ ብርቅዬ ከተማ ናት ለሐመሮች።

ዲመካ ግን፣ ከዋናው መንገድ ወጣ ብላ፣ ሰቀላ ቤቶች በአራት ማዕዘን ተሰትረው የሚታዩባት ከተማ ናት። በየሰቀላ ቤቶች ፊት ለፊትና በስተኋላ የግራር፣ የብርብራ.ዛፍ ያለ ሲሆን ከከተማው ግርጌ፣ ከወንዙ ጥግ በሚስዮናውያኑ የተተከለ በፀሐይ ብርሃን በሚንቀሳቀስ መስኖ የለማ የፍራፍሬ፣ የበቆሎና ሌሎችም ወቅታዊ
አዝርእቶች የሚታይ ሲሆን፣ ከጎን በኩልም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንፃና ጋራዡ፣ ዲመካን አንድ ዓይና ከመሆን አድኗታል"የገበያ ቀን፣ በየሰቀላ ቤቱ ጠጅ የሚሸጥ ሲሆን፣ ምግብ ቤት ግን ከናካቴው የለም" ደግነቱ፣ እንግዳ ብርቅ በመሆኑ ጋባዡ ብዙ ስለሆነ
እግር የጣለው ሰው ሕቅ ብሎ ሲያዝን አይሰማም" በተረፈ ገበያ ውስጥ ያለው ሸቀጥ ከቱርሚ ጋር ተመሳሳይ ነው ሁለቱንም ከተሞች ቡስካ ስር ካሉት ላላና ሻንቆ እስከ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዳ
መንደር ድረስ የሚያገናኛቸው የማኅበረሰብ ሕይወት የሆነው የከስኪ ወንዝ ነው ከብቱ፣ ፍየሉ፣ በጉ፣ ሰው፣ አዕዋፍ...ሁሉም ጥሙን
ይቈርጥበታል።

ካርለትና ከሎ ሆራ ከዲመካ ወጣ ብላ ከምትገኘው የሻንዛ መንደር መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራት አለፋቸው የክልሉ ኗሪዎ
ከሎ ሆራን እንዳዩ፣ «የሆራ ሻላ ልጅ» እያሉ፣ ሰላምታና ስጦታ አጐረፉለት ቆዳ ለባሽ እናቱና እኅቶቹም ደረታቸውን በመድቃት
የደስታ እንባ እያነቡ አስተናገዱት።

ካርለት፣ በቆይታዋ የተለያዩ ልምዶችን አገኘች። ከዘመናዊ ሕይወቷ እንደ ባንዲራ ወርዳለችI ይህን አጋጣሚዋን ግን በግላዊ
ትርጕሟ እንደ መጥፎ ከመውሰድ ይልቅ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰዷ የሚሰማት ስሜት የደስታ ስሜት ነው። ይህ ደግ
ማኅበረሰቡን ለመቅረብና ለመርዳት እንድትጣጣር አድርጓታል ስለዚህ፣ ካርለት የከሎ ሆራን እናትና እኅቶች፣ የአካባቢው ሴቶችና ወንዶች ለመቅረብ የቋንቋ ትምህርቷን በማጠናከር ልትግባባ ሞክራለች ቢሆንም ግን፣ በወደፊቱ ጥናቷ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት
እየሆነባት የመጣው በሴቶች ላይ ያለው ባህላዊ ተፅዕኖ እንደ ጋለ ብረት ምጣድ አላስጠጋሽ አላት"¸

በማኅበረሰቡ፣ ሴት ሣቂታ ወንድ ኰስታራ ነው" ሴት በልጃገረድነቷ የአባቷ፣ ባል ካአገባች ደግሞ የባሏ ጥገኛ ናት" ስለዚህ
በልባዊ ኵራት የተሞሉት የሐመር ወንዶች ካርለት ሴት ሆና እንዴት ባሏን ወይንም አባቷን ጥላ ወደ እነሱ እንደ መጣች በጣም
አስገርሟቸዋል" ሽማግሎች እንዲያውም፣ «ይእ! እሷ ምን ታድርግ? አባቷ ወይም ባሏ፣ ብቻዋን መልቀቃቸው ከቶ ምን ያሉ ነፈዞች ቢሆኑ ነው» ብለው አውግዘዋል"
ስለሆነም፣ ካርለት የጥናት ኮተቷን ይዛ ለጥያቄ ቀረብ ባለቻቸው ቍጥር የደስታ ገጽ ስለማታይባቸው ለተወሰነ ቀን ግራ ተጋብታ
ነበር" አንድ ቀን ግን ወንዶች ሊያደርጉት ባሰቡት ስብሰባ ለመካፈል ሄደች። ገላጣ ስፍራ ላይ ካለ ትልቅ ግራር ጥላ ሥር፣ የሻንቆ መንደር
ሽማግሌ፣ አባወራ፣ ጐረምሶች ተሰብስበዋል" ከወገብ በላይ ራቁት
ሆነው፣ ቆዳቸው የተሸበሸበ፣ ጸጕራቸው ገለል ብሎ ሽበት ጣል
ጣል ያደረገበት አዛውንት በሁለት ወገን ጦር የተሰካበት ብትር ይዘው፣ መሬቱን ወጋ ነቀል እያደረጉ ወዲያ ወዲህ እየተንቀሳቀሱ
ንግግር ሲያደርጉ ሁሉም ጸጥ ብሎ በተመስጦ ሲያዳምጥI ካርለት
ስብሰባውን ለመካፈል ጓጕታ ቀስ እያለች ተጠግታ ልትቀመጥ ስትል
ሁሉም ዘወር ብለው አይዋትና በስብሰባው መካፈል እንደማትችል
ነገሯት"

ካርለት፣ ወንዶችን ለመቅረብ አለመቻሏ ብቻ ሳይሆን፣ ሴቶችም
ምሥጢራቸውን ሊገልጹላት ባለመቻላቸው ግራ ተጋብታ ቅር ተሰኘች" በተለይ ደግሞ፣ ለመሳተፍ ጓጕታለት በነበረው የወንዶች
ስብሰባ ልትካፈል ባለመቻሏ ጥልቅ ኀዘን ከመስማት አልፎ ለወደፊቱ አደርገዋለሁ ብላ የደከመችለት ጥናት ሊሳካ አይችልም ብላ ሠጋች"
ስለዚህ፣ ዓይኗ ቁንዶ በርበሬ መስሎ እስኪቀላ ድረስ እያለቀሰች፣ «ከሎ! ለምን ወንዶች ጥያቄዎቼን ለመመለስ ፈቃደኛ
አይሆኑም? ለምንስ በስብሰባቸው እንዳልካፈል ይከለክሉኛል? በዚህ
ዓይነት ጥናቴንስ እንዴት ማድረግ እችላለሁ? » ብላ ጠየቀችው።

«በሐመር ማኅበረሰብ ሴት ወንድን ለመርዳትና ለማገልገል የተፈጠረች ጸጋ ናት። ለወንዶች ትንባሆ ታዘጋጃለች ልጃገረድ
ከሆነችም ታርሳለች፤ የከብቶችን በረት ታጸዳለች ሕፃናትን ትንከባከባለች ምግብ ታበስላለች.እንጂ ከወንድ ጎን ተቀምጣ ስለ
ማኅበረሰቡ ችግር በመነጋገርና በመምከር መፍትሔ መፈለግና ጦርነት
መግጠም አትችልም።

«ካርለት፣ አንቺ ወንድ ብትሆኚ ኖሮ ምንም ችግር ላያጋጥምሽ ይችል ነበር" ሆኖም ግን አንቺ ሴት ነሽ። ለሐመር ሴቶች የወጣው
ደንብ ማንኛዋንም ሴት ያጠቃልላል፣ ብለው ስለሚያምኑ በስብሰባቸው እንድትካፈይ አለመፍቀድ ብቻ ሳይሆን፣ የምትጠይ
ቂያቸውንም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ ፈቃደኛ አይሆኑም" እኔም
ይህ ችግርሽ እጀ ሰባራ ሊያደርግሽ እንደሚችል እየተሰማኝ መጥቷል" ምናልባትም ችግሩ ግልጽ ከሆነልሽ የግልሽን መፍትሔ
ውሰጂ» አላት"

ካርለት ፈጽሞ ያልጠበቀችውን መልስ በማግኘቷ በባህላዊ
ልዩነቱ በጣም ተሸማቀቀች በአሁኑ የጥናት አያያዟ በእርግጥ ለመቀጠል አለመቻሏ ቁልጭ ብሎ ታያት በአእምሮዋ አውጥታ
አውርዳ የወሰነችው ውሳኔ፣ እስከ አሁን ያደረገችው ጥረትና ጒዞ ጥሩ የድንጋይ ምት እንዳረፈበት መስተዋት ከሽ ብሎ ሊሰበር
የተቃረበ መስሎ ታያት። ያ ችሎታዋንና ጥንካሬዋን የሚያስመሰክረው፣ ማንነቷን የሚያረጋግጠው፣ ብቃቷን ማያዋ መስተዋት
እንዲሰበር ግን ጭራሽ አትፈቅድም። በዚህም ተባለ በዚያ የጀመረችውን ከግቡ ለማድረስ ሕሊናዋ እሷን ወደፊት መግፋት
አለበት" ሰዎች ከጎሪላና ከእፉኝት፣ ከአንበሳና ከተኩላ ጋር በሐሩርና
በረዶ መኖር መቻላቸውን አስመስክረዋል" እሷም ዓላማዋን ከግቡ
ለማድረስ ተጣጣፊና ጠንካራ ለመሆን ከራሷ ጋር ተማማላች" ግን ምን መላ ትምታ? ለተወሰነ ቀን ካለ ዕረፍት በዚህ ጉዳይ ላይ ስታስብ ከቆየች በኋላ ምንም እንኳ የችግር ኮተቱን ዓይኗን ጨፍና አላይም
ብትልም፣ የሚያጋጥማት ሥቃይ ከባድ መሆኑን አውቃ ቀበቶዋን አጠበቀች

ከዚያም፣ ያሰበችውን መላ ለመጀመር ያስችላት ዘንድ ባል አለማግባቷን የሚገልጽ ወሬ ለአገኘችው ሁሉ አወራች" ወሬው ተዛምቶ በየመንደሩ መዳረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ጐረምሶች፣ ወጣት
ባለትዳር ወንዶች፣ ያላገቡና ባለ እጮኛ ልጃገረዶች ምሽትን ተገን አድርገው ወደሚቦርቁበት የምሽት ጭፈራ «ኢቫንጋዲ» ለመካፈል ነኢማ ከምትባለው የከሎ ሆራ እኀት ጋር ስትሄድ ምንም ተቃውሞ ሳይደርስባት ቀረ።
👍271
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ሰባት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


ሦስት ወራት አለፈ" ካርለት በሐመር ቆይታዋ ብዙ ልምድ አካበተች ያልጠበቀችውንም እርካታ አገኘች ካርለት ከሎን ወደ ዲመካ፣ ቱርሚና ጂንካ ከተማ ሲሄዱ እግረ መንገዷን መኪና ማሽከርከር ስላስለመደችው መረዳዳት
ጀምረዋል" ካርለት በሐመር ኑሮዋ ዕቃዋን፣ ገንዘቧን ለማስቀመጥ የምትተማመነው በመኪናዋ ውስጥ ነው፤ በተለይም ሙዚቃ ለማዳመጥ መኪናዋ ከፍተኛ ጥቅም ትሰጣታለች" በነዳጅ በኩል እስከዚያ ወቅት ድረስ ችግር አላጋጠማትም፤ ካስፈለጋት ግን ጂንካ ከተማ ናፍታ ማግኘት እንደምትችል ተረድታለች።

የሐመር ሰማይ ጥርት ያለና አልፎ አልፎ ብን ያለ የጥጥ ባዘቶ መሳይ ዳመና ይታይበታል” የዝናቡ ወቅት፣ እምብዛም የሚያስተማምን ባይሆንም፣ ድንገት እያጓራ የሚያጋሽብ ጥልመት ዳመና ከታየ «አህያ» የማይችለው ዝናብ፣ መዓቱን ያወርደዋል" በዚህ
ወቅት የዕጽዋት ቅጠሎች እንደ በረዶ ብን ብን እያሉ ሲወድቁ ከብቶች ጅራታቸውን ሸጒጠው፣ ጆሮአቸውን ይጥላሉ።

በዚህ ወቅት፣ የከሰኬ ወንዝ ከአሸዋ በላይ ዛፍ ቅጠሉን እያተራመሰ፣ ባሕርይውን ይቀይርና በመደንፋት፣ እየተነሣ ይፈርጣል"
በዚያን ጊዜ ከሰኬ ወንዝና የሐመር ማኅበረሰብ፣ ከብቱ፣ ፍየሉ፣ ይኰራረፋሉ «አትድረስብኝ» አንመጣብህም ይባባላሉ"
አንድ ጊዜ፣ ካርለትና ከሎ መዝነቡን ሳያውቁ ከጂንካ ወደ ሻንቆ ሲሄዱ፣ ከሰኬ ወንዝን በመኪና ገብተው ሊሻገሩ ሲሉ መኪናዋ
በአሸዋው ተያዘች እነሱም ከመኪናቸው ወርደው በዶማና አካፋ
ለማውጣት ሲሞክሩ «ፉ..ፉ..ፉ.» የሚል ድምፅ ሰሙ። ቀና ሲሉ ደረቱን ገልብጦ፣ የሚጣደፍ ደራሽ ውኃ ተመለከቱ። ካርለትና ከሎ ብርክ ይዟቸው እንደ ሕፃን ልጅ ተንቦራቹ። ውኃው ግን ገሰገሰ ካርለትና ከሎ ዳር ላይ ሊደርሱ ሲሉ ውኃው ሲያጠናግራቸው
ተንገዳገዱ፤ ሳያስቡት እጅ ለእጅ መያያዛቸው ግን በጃቸውና ለትንሽ
አመለጡ። ደራሽ ውኃው መጀመሪያ መኪናዋን እያነቃነቀ ፈተሻት፣
ቀጥሎ በጎኗ፣ ከዚያም በጭንቅላቷ አቆማት።
«አምላኬ!» አለች፣ ካርለት መኪና የሚያገለባብጠው ውኃ እነሱን ቢያገኝ እንዴት ብትንትናቸውን እንደሚያወጣቸው እያሰበች።

ዛፉ «ቋ..ቀሽ.."ቀሽቀሽ...» ይላል፤ ግንድና ቅጠሉ ብቅ–ጥልቅ ይጫወታሉ፤ ውኃው፣ ሣር ቅጠሉን ያግበሰብሳል" መኪናዋ ጎማዋ ሲታይ ቆይታ በጎኗ ተጋደመች። ደራሽ የውኃ ሙላቱ ግን ለማንም
በሚያስገርም ሁኔታ እየቀነሰ፣ እየቀነሰ መጣና ጸጥ አለ። ካርለትና
ከሎ መኪናዋን ማውጣት ባለመቻላቸው፣ በየቦታው የተገነደሰውንም
ግንድ ለብቻቸው ማነቃነቅ የማይሞከር በመሆኑ፣ የሻንቆን መንደር
ኗሪ በእግር ሄደው ጠርተው፣ በስንት ችግር መኪናዋን ሊያወጡ
ቻሉ" ስለዚህ፣ ሐመር ላይ ዝናብ ሲዘንብ ከስኬ ሰው፣ ከብት፣ መኪና ሳይቀር ስለሚወስድና ስለሚያሰምጥ ምሱን አያጣም፤ ከብቱን፣ አራዊቱን፣ ሰውን...ድንገት ጠልፎ በመዋጥ የቆየ ልምድ አለው። ካርለትና ከሎ በቆይታቸው የተለያዩ ዕጽዋትንና ጥቅማቸውንም ተረድተዋል። ወንዴና ሴቴ ቃጫ ለገመድና ቤት ሥራ፣
ጠዬ ለዱላ፣ ሌልሜ ለቤት ሥራ፣ ፌጦ ለመፋቂያ፣፣ ኩንኩሮ ለተለያየ ጥቅም፣ ፊላና ሰንበሌጥ ለቤት ሥራ እንደሚውሉ ተረድተዋል።
በተረፈ ጨው ሊንባ፣ እንኮይ፣ ዘምባባ፣ አጋም፣ ጨዋንዛ፣ ግራር
ወዘተ የሐመርንና የአጐራባቾችን መሬቶች አስውበው ሲመለከቱ፣
ከመንፈስ እርካታው በተጨማሪ አንዳንዶቹን መጠቀም ችለዋል።
ካርለትና ከሎ ሻንቆ፣ ላላ፣ ወሮ፣ ዴንባይቴ፣ ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ሚኖ፣ ሚርሻ፣ ሜን፣ አንጉዴ...መንደሮች ሲዘዋወሩ ከማኅበረሰቡ
አባላት ጋር ከሚገናኙበት አንዱ ሸፈሮ ቡና (የቡና ገለባ) የሚፈላበት
ወቅት ነው። የሐመር ቡና የሚፈላው በጀበና ሳይሆን በትልቅ እንስራ ነው ቡናው የሚጠጣው ንጋት ላይ ጀምሮ እስከ ረፋዱ ድረስ
ሲሆን፣ ያደረሰው ሁሉ መጠጣት ይችላል። አንድ ጊዜ ታዲያ፣ ካርለትና ከሎ ሻንቆ መንደር ለመጀመሪያ
ጊዜ ቡና ሊጠጡ ሄደው፣ ኦይጊ የተባለችው የመንደሩ ኗሪ ቤቷ ለመጡት እንግዶች በሾርቃ ከትልቅ ቅል ላይ በተከፈለ መጠጫ
ለሁሉም እንግዳ ስታድል፣ ለሁለቱም ሰጠቻቸው" ካርለት አንዱን
ሾርቃ እንደምንም ጨርሳ ‹ተገላገልኩ› ብላ፣ ሾርቃውን ለአይጊ አቀበለቻት በሐመር ባህል ሾርቃውን ቡናውን ለምትቀዳው ካቀበሉ
ድገሚኝ እንደማለት በመሆኑ፣ ኦይጊ ቡናውን በሾርቃ ሞልታ ለካርለት ሰጠቻት፤ «አምላኬ!» አለች ካርለት የመጀመሪያው ቋቅ
ሊላት ደርሶ፣ ሁለተኛውን ስታስታቅፋት።

ካርለት፣ ቡናውን መጠጣት ከበዳት። ቁጭ አድርጋ ትታ
እንዳትሄድ፣ ባህሉን መናቅ እንዳይሆንባት ሠግታ ስትጨነቅ ቡናውን
በያዘው ሾርቃ ላይ ዝንቦች እየገቡ ተንሳፈፉ። ካርለት፣ «ጥሩ አጋጣሚ» ብላ፣ እየሣቀች፣ «ዝንብ ገባበት» በላቸው አለችው ከሎን!
«ድፊው» ይሉኛል ብላ። እነሱ ግን፣ «ጠጭው ምንም አይልሽም፣
ይሄ የወተት እንጂ፣ የቆሻሻ ዝንብ አይደለም» አሏት። ካርለት፣ ሌላ አማራጭ ስላልነበራት የሚንሳፈፉትን ዝንቦች «እፍ» እያለች
ቡናውን ጠጥታ ጨረሰች።

ካርለት በሐመር ኑሮዋ በጣም የከበዳት ችግሯ ግን የሐመሮች የጊዜ ዕውቀት አለመኖር ነው። ካለፕሮግራሟ በተለይ በገበያ ቀን ዲመካ፣ ቱርሚ፣ ቀይአፈርና ጂንካ በመኪናዋ እንድትወስዳቸው
ይጠይቋትና መኪናዋ ውስጥ ዱቄት፣ ፍየል፣ በግ፣አረቄ፣ ማርና ቅቤ
ሰለሚጭኑ ሁሌ ትሳቀቃለች" አንዳንዴም አፍ አውጥታ! «አልሄድም» ትላለች።

ካርለት ምግብ፣ ደብዳቤ፣ መጽሔት፣ ከቤተሰብ ጋር የስልክ ግንኙነት ለማድረግ አዲሳባ ስትሄድም በጕዞው ከሎ ሆራ መኪና
ማሽከርከር ቢረዳትም ወንዝ እየሞላ፣ ጭቃ ሲይዛቸው ትማረራለች።

ካርለትና ከሎ ወደ አዲሳባ ሲሄዱ አልፎ አልፎ የሚላኩት መልእክት የተወሰነ ሲሆን አቡጀዲ፣ የላስቲክ ጫማ፣ ሸፈሮ ቡና
ሽጉጥ መሳይ መድኃኒት «ቴትራሳይክሊን ወይም ክሎሮፌኒኮል”ዋነኞቹ ናቸው"

ካርለት ሐመር ሦስት ወር ቆይታ አዲሳባ እንደሄደች፣ ከስቲቭ ጋር ተገናኙ። ስለ ሐመር ሕይወቷ፣ ስላየቻቸው ነገሮች፣ ስላጋጠማት ችግርና ስለ ወሰደችው የመፍትሔ እርምጃ አጫወተችው
ስቲቭ ከነገረችው ሌላ፣ ካርለት አንገቷና እጇ ላይ ያለውን ነገር ከማየቱም ባሻገር፣ ሳታቋርጥ ስታክ ተመለከታት» ከዚያም፣ «የኔ
ፍቅር፣ ይህን ያህል ለምን ራስሽን ለችግር ታጋልጫለሽ?» አላት
ስቲቭ"

«ችግር ስትል ምን ማለትህ ነው?»

«ይህ ደረሰብኝ እያልሽ ያወራሽኝ ሁሉኮ ጋሪ ላይ የተጫነ ጭነት ሳይሆን፣ አንች የተሸከምሽው ችግር ነው?» አላት"

«ስቲቭ፣ አንድ ሰው የምኖረው ትርጕም ያለው ሥራ ለመሥራት ነው ካለ፣ ሕይወቱም ትርጕም ያለው ይሆናል" ሌላው ደግሞ
(ምኖረው ለመሞት ነው› ካለ በውስጡ እውነትነት አለው” ሕይወቱ ግን፣ ትርጕም አልባ ይሆንበታል"

«ማንኛውም አጋጣሚ በየግላችን አእምሮ አመዛዝነን፣ መክረን፣
እናወጣ እናወርደዋለን፣ ቀጥሎ ጥሩ ወይም መጥፎ ትርጕም እንሰጥና ተግባሩ ላይ ያን አጋጣሚ እንጠላዋለን ወይም እንወደዋለን።

«አንዱ መኖርን ጥሩ ሥራ ለመሥራት እንደሆነ ተረድቶ ሲጥርI ሌላው ደግሞ መኖሩ ለመሞት መሆኑን አውቆ ተስፋው ይኰሰምናል"
👍25🥰2
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ስምንት


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

..ደልቲ ገልዲ በራሱ የሚተማመን ጀግና በመሆኑ በዚህ ዓለም ላይ
ከእሱ በላይ ሰው ያለ አይመስለውም" ስለሆነም፥ የሚፈልገውን አጣለሁ የሚል ቅንጣት ታህል ጥርጣሬ የለውም" በስሙ ሲዘፈንና ሲዘመር ጥርሱን እየፋቀ በርኳታው (መቀመጫው) ላይ ቁጭ ብሎ ወይንም ጋደም ብሎ መዝናናት ነው;

ጀግንነት ከሀብት ጋር ገና ዕድሜው ሳይገፋ፥ «ቤት ለእንቦሳ» ሲል «እንቦሳ እሠር» ብሎ፥ ተቀብሎታል" በእርግጥ እያንዳንዱ
የሐመር ጓዳ ላጠቃላይ ማኅበረሰቡ ግልጽ ነው። ተካፍሎ መመገብ፥
ተሰባስቦ መጨፈር፥ ተከባብሮ መኖር፥ ጠላትን በጋራ ማጥቃትና
መደናነቅ የማኅበረሰቡ ወግና ልማድ ነው። ደልቲ ገልዲም የዚህ ባህላዊ ኑሮ ተሳታፊና ተገዥ በመሆኑ ኃይሉን ተማምኖ ሌላውን የሐመር አባል ማጥቃትም ሆነ ንብረት መቀማት ክብሩን ለውርደት፥ ሀብቱን
ለጥፋት ስለሚያበቃ ከልጅነቱ ጀምሮ ክብርንና መብትን በጥንቃቄ
መያዙንና ተከባብሮና ተመካክሮ መኖርን ሊዘነጋ አልቻለም።

ደልቲ ገልዲ፥ በዚያን ሰሞን ወደ መንደራቸው የመጣችውን እንግዳ የተመለከታት በኲራት ነበር" የለበሰችውን ጨርቅና
የምትሸተው ቃና ከአካባቢው ልጃገረዶች ጠረን የተለየ በመሆኑ ራቅ
ብሎ ነው ያስተዋላት።

«እንደ ሐመር ሴቶች ቆዳ የማትለብሰውና ጭኖቿን የማታሳየው ምናልባት የሚያሳፍር ነገር ቢኖርባት ይሆናል» ብሎ፥ከመገመቱም
በላይ የሴትነት ጠረኗን የዋጠው ሽታ አስጠልቶት ነበር በተደጋጋሚ
ቀናት እንዳያትም በሚኰርፍ ነገር መተጣጠቧ ብልግናዋን ከማረጋገጡም በላይ መጥፎ ጠረኗን ለማጥፋት መሆኑን አምኖበታል"

የሐመር ልጃገረዶች በውኃ አይታጠቡም። «ብልታቸውን ውኃ ከነካው መካን ይሆናሉ» ስለሚባል፣ በጣም ነውር ነው" ይህችኛዋ እንግዳ ግን አልፎ አልፎ ብቻ ሳይሆን ዘወትር ስትተጣጠብ ያያታል" «መካንነቷ መቼም የማይቀር ነው" ግን ሴት ሆና ስትተጣጠብ
የማታፍር ምኒቱ ባለጌ ናት?» እያለ ኮንኗታል። ሌላውም እንደሱ
በድርጊቷ ጠልቷታል"

ሆኖም እሱ የጀግኖች ጀግና ነው፤ እንዲህ ዓይነቷን ባለጌ ልክ የማግባቱ ኃላፊነት ከሱ ትከሻ ላይ የወደቀ ነው" ስለዚህ፣ እንግዳይቱን በግርፋትም ቢሆን ሥነ ሥርዓትን ሊያስተምራት ይችላል"
ይህን ለማድረግ ደግሞ፣ እሷን ማግባት አለበት" ካለበለዚያ ዝንቧንም እሽ ማለት ላይችል ነው ደግሞኮ የሱ ሚስቶች በመልካቸው ጥቋቁሮች ናቸውI ስለዚህ ነጭ ሚስት ያስፈልገዋል" ሀብቱ
እንደሆነ የትየለሌ ነውI ሦስት በረት ከብት፣ በየጋጡ ብዛት ያለው ፍየል፣ በየጫካው ለቍጥር የሚታክት ቀፎ አለው" በዚያ ላይ የቀጭኔ፣ የጎሽ፣ የአንበሳና የሰው ገዳይ ነው።

ስለዚህ፣ ይህችን ባለጌ ለማረቅ እንዲችል እሷን የራሱ የሚያደርግበት በቂ ሀብት አለው። እና፣ የሚጠየቀውን ጥሎሽ ከፍሎ የሱ ንብረት ካደረጋት በኋላ ቢቀጣት ጠያቂ የለበትም። ለዚህ ሁሉ
ግን፣ ሚስቱ እንድትሆን ማድረግ እንዳለበት አመነ። አብሯት የመጣው ከሎ ሆራ እንደሆነ ምኗም እንዳልሆነ አረጋግጧል"

አንድ ቀን ካርለትና ከሎ ሆራ ሲጨዋወቱ ደልቲ ገልዲ
«ነጋያ» ብሎ አጠገባቸው ለመቀመጥ ይዞት በሚዞረው በርኮታ ላይ
መሣሪያውን ጭኖቹ መሃል አድርጎ ተቀመጠ" ከዚያም፣ «ባል  አለሽ?» ብሎ በቋንቋው ጠየቃት" ይሉኝታና ፍርሃት የሐመርን
ተወላጅ ሲያልፍም አይነካካውም" ደግሞስ ሰው ሰው ነው" ያውም
እሱ ጀግናው። ከሎ ሆራ ያለውን ለካርለት ተረጐመላት።

«የለኝም» አለችው" ካርለት በቀኝ እጇ ግንባሯ  ላይ
የተበታተነውን ጸጕር ወደ ኋላዋ እየመለሰች።

«አባትሽ ስንት ከብት አለው?» አላት፣ ደልቲ።

«ከብት የለውም፣ ፕሮፌሰር ነበር" ስለዚህ ደመወዙ…»
ፕሮፌሰር፣ ደመወዝ ያለችው ሊገባው አይችልም። ከባለጌ የሚጠበቅ
ተራ የተራ ነገር ይሆናልና ስለሱ ማሰብ አያስፈልግም።

«ቀፎና ፍየልስ?» ጠየቀ ደልቲ።

«የለውም» አለች" አባቷ ደሃ ቢሆን ነው ማለት ነው ወደዚህ የላካት ብሎ አዘነላት" በሐመር ማኅበረሰብ ሀብት ማለት ከብት፣ ፍየል፣ ቀፎ ነው። ከዚህ ውጭ ደመወዝ፣ ቪላ፣ መኪና ብሎ ሐተታ፣
የሚገባው የለም። ደልቲ ገልዲ በክልሉ የሀብት ሁሉ ባለቤት አባወራው እንደሆነ
አሳምሮ ያውቃል" ስለዚህ፣ እንግዳዋን ስለ እናቷ
አያስፈልግም" ደግሞ ሴትን፣ «ሀብት አላት ወይ?» ብሎ መጠየቅ ነውር ነው። የእንግዳዋን አባት ሁኔታ እንደሆነ ጠይቆ፣ ድህነቱን
ተረድቷል

ደልቲ ገልዲ በእሱና በእንግዳዋ አባት ሀብት መካከል ያለው ልዩነት የሰማይና የምድር ያህል ሰፍቶ ታየው" ለምግብ ማቅረቢያ፣ ለመኝታ የምትጠቀምበት፣ በተለይም ማታ ማታ «ፋ» የምታደርገው መብራትና ብልጭልጭ ቅራቅንቦዋ፣ ከሱ ንብረት አንፃር ሲታይ
ጠጠርና ተራራን ማወዳደር ቢሆንም፣ አባቷ ሀብቱን ለምን ለእሷ እንደተወላት ግራ ገብቶታል። የሱ ወገን የሆኑት የሐመር ሴቶች የግሌ የሚሉት ሀብታቸው የሚለብሱት ቆዳ፣ ጨሌና አንባራቸውን ብቻ
እንደሆነ ጥርት አድርጎ ያውቃል።

ያም ሆነ ይህ ግን፣ እንግዳዋን አግብቶ በግርፋት መግራት እንዲችል ሊያገባት መፈለጉን ለሽማግሎች ማማከር አለበት ሽማግሎች የሚሉት ባይታወቅም ብልግናዋን ገልጾ ሊገራት እንደሚፈልግ
ሲነግራቸው እነሱም ይህን ስለሚረዱ ተቃውሞ እንደማይኖራቸው
ተማምኗል" አንድ ግን ግራ የገባው ጉዳይ አለ" ጋብቻውን ሽማግሎች ቢቀበሉት «ልጅቱን ለማግባት፣ አባቷ የት ተገኝቶ በሽማግሎች
ይጠየቃል? ጥሎሹንስ እንዴት ወስዶ ከችግሩ ይላቀቃል?» ብሎ
አሰበ።

ይህ ከሆነ በኋላ ግን፣ ብዙም ሳይቆይ ደልቲ ገልዲና ካርለት በምሽት ጭፈራ ተገናኙ ካርለት ያ አስደናቂ ጥያቄ ሲጠይቃት
የነበረው ወላንሳ እየዘለለና እያሸበሸበ ሲደንስና ሲሥቅ፣ ደጋግማ
ስታየው ሁሉን ነገር በተለይም ስለሱ የሚባለውን ሁሉ አስታወሰች። ስለዚህ፣ ዛሬ ይህን ስሙ በሐመር ሰማይ ላይ የሚንሳፈፍ ሰው ማንነት ማወቅ አለባት"

ያም ሆኖ ግን ካርለት ስሜቷ ለሁለት ተከፈለባት" በአገሯ ምን ዓይነት ውበትና ጠባይ ያላቸው ወንዶች በሴቶች እንደሚፈቀሩ፣ ከሞላ ጎደል ታውቃለች። እሷም ብትሆን በአፍላው የወጣትነት ጊዜዋ የነበራት የስሜት ቅብጥብጥነትና በምታፈቅረው ወንድ ላይ

ታጠምደው የነበረውን መረብ አስታወሰች" ሆኖም ይህ ሰው እዚ
ከምታውቃቸው ሰዎች በብዙ መልኩ ይለያል ለነገሩ የደልቲ ውበት
ጭጋግ ለብሶ ይታያልI ያውም ይኖራል ብላ ያልገመተችው ውበ
የሐመር ልጃገረዶችን ሕሊና ያማልላል ተብሎ የሚደነቀውን ልበ ሙሉ ወንድ ጭጋጉን በታትና ሥነ ውበቱን በትክhል መቁጠር አለባት" የለንደኑ፣ የቦኑ፣ የማንቸስተሩ..ወጥመዷ ያለውን የመያዝ ችሎታም መፈተን ይኖርባታል"

እንደ ባልጩት ድንጋይ የለሰለሰውን ገላውንና በጨረቃ የሚያንፀባርቁት ጥርሶቹን ባሰበች ቍጥር ጥርት ጎላ እያሉ ታይዋት
ስለዚህ፣ ማራኪውና የመጨረሻ ዓይነት የጭፈራ ምት መጀመሪያው ጊዜ መቃረቡን ስታውቅ፣ ሐሳቧን ተግባራዊ ለማድረግ ለሩጫ
እንደሚዘጋጅ ሯጭ አደፈጠች።

ያን የወቅቱን ወላንሳና ቀብራራ ሐመር ጠብቃ ለዳንስ ስትጋብዘውና እያኮበኮበ፣ አየሩን በመቅዘፍ ቀርቦ ጥቁሩ ጭኑ ከነጩ ጭኗ ሲተሻሽ፣ ሸካራና ጠንካራ እጆቹ ትከሻዋን ሲይዙ፣ ስሜቱ
በስሜቷ ውስጥ ሲሟሟ፣ ያለችበትን ቦታና ሰዎችን በመዘንጋት የሚያቃጥል፣ የሚነዝርና በሰመመን የሚያሰጥም ስሜት እንደ
ተሰማት፣ ከራሷ ቍጥጥር ውጭ ሆነች" ስለዚህ፣ ሁሉን ነገር ዘንግታ
ተንጠራርታ አንገቱን በማቀፍ ከንፈሯን ከከንፈሩ ጋር ለማላተም
ተጣጣረች ደልቲ ግን፣ በጠንካራ እጆቹ እጇን ያዝ አድርጎ፣ የዳንሱን ቦታ ጥሎ፣ ወደ ጫካ ይዟት ገባ፤ ጥቁሩና ነጭ አባይ ጫካ መሃል ተገናኙ።
👍24👎1
#ከቡስካ_በስተጀርባ
   #ድንግል_ውበት


#ክፍል_ዘጠኝ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

የሐመር ዕጽዋት ለምልመው፣ ንቦች ከአበባ ወደ አበባ እየተዘዋወሩና እየዘመሩ ሲቀስሙ፣ ከብቶች ጨሌ ሳራቸውን እያመነዠኩ ሲያገሱ፣ እንቦሶች ቃጭላቸውን እያቅጨለጨሉ ሲቦርቁ፣
ልጃገረዶችም ማሳውን እያረሱ ሲያዜሙ፣ ልጆች እራቁታቸውን ሆነው በቀስት ጫካ ለጫካ ተሪ ለመግደል ሲሯሯጡ በሚውሉበት፣
ጎረምሶች ሹልሹላ፣ ሹርባ...ጸጕራቸውን እየተሠሩ «አኖ» በተባለው አፈር ሰውነታቸውን በማዥጐርጐር ለማታው ጭፈራና ድሪያ ሲዘጋጁ፣ የብልታቸውን ጸጕር እየተላጩ በመኸር ጊዜ የሚዘፍኑትን ዘፈን ሲያዜሙ በሚውሉበትና ሐመር የክቱን የተፈጥሮ ሕይወት
ለብሳ ኗሪዎቿን በምታስፈነጥዝበት ወቅት ድንገተኛ ሁኔታ ታየ።

ካርለት አልፈርድ ሰቀላ ቤት አሠርታ መኖር ከጀመረች ዘጠኝ ወር አለፋት። ከሷ በስተግራ ከሃያ ሜትር ላይ የከሎ ክብ ጎጆ አለ።
በግቢያቸው የዱር አበባ፣ ቦዬ፣ ጉደሬ በቅሏል። ከነሱ ግቢ ራቅ ብሎ አለፍ አለፍ በማለት የሐመሮች መኖሪያ ይታያል። ካርለት ቤቷ ሆና
ፀሐይ ስትወጣ ከፊት ለፊት፣ ስትገባ ደግሞ ከበስተኋላ ሆና ልታያት
ትችላለች"

በእርግጥ በፖስት ካርድ ፀሐይ ስትወጣና ስትገባ አስደናቂ ፎቶዎችን ተመልክታለች። ሕይወት ያላት የሐመሯ ፀሐይ ግን ምሽት ላይ በተለያዩ ቀለማት ተውባ እንደ ዕንቁ እያንፀባረቀች አካባቢውን
ቀይ፣ ቢጫ ሐምራዊ ድብልቅልቅ ቀለማትን ስትለዋውጥ ስታያት
ግን በሕይወቷ ካየችው ውብ ነገር ይልቅ፣ በሐሳቧ የቀረፀችው የገነት
ውበት ይታያታል።

ታዲያ፣ በጣም ተመስጣ የአካባቢውን ውበት ስትመለከት ውበትን በትክክል ለማስቀመጥ፣ መጨመር የምትፈልገውንም
ጨምራ ለመርካት፣ ከአንትሮፖሎጂስትነቷ ይልቅ ባለቅኔ ወይንም
ሠዓሊ መሆን ያምራታል
ካርለት ያጣችው ነገር የለም አይባል" የዋና ቦታ አላገኘችም ኑሮዋ ዘመናዊ አይደለም" ያም ሆኖ ግን በሚያውዳት የተፈጥሮ
መዓዛ፣በስሜት በምትውረገረገው የምሽት ጭፈራ፣ ባየችውና
በቀረበችው ቍጥር ጥልቅ እሳቤን የሚጠይቃት የተፈጥሮ ምሥጢር፣ በንጹሕ ሕሊና የምታነባቸው መጻሕፍት የደስታ ሚዛኗን
ይጠብቁላታል።

አሸጋግራ የምታየው የሐመር ሰንሰለታማ ተራራ፣ መሸት ሲል ከየዋሉበት ብቅ ብቅ የሚሉት ሰዎችና እንስሳት፣ ስታንቀላፋ
የዋለችው መንደር፣ ሞቅ ሞቅ ደመቅ ስትል፣ ሁሉም ከፀሐይ ውበት ጋር ውሕደት፣ ቅንብር ሲፈጥሩ ስሜቷ ይረካል» እንዲያውም ከዚህ
ለየት ላለ ያልተበረዘ ተፈጥሮ ያላት ፍቅር «ምነው እናቴ፣ ወንድሜ፣ እኅቴና ስቲቭ ይህን ባዩ» ብላ፣ ቅን ሐሳብ እንድታልም
ያደርጋታል"

አንድ ቀን ግን፣ የተለመደ ትርዒቷን ስትመለከት፣ በግምት የአሥራ አምስት ዓመት ልጃገረድ፣ ከጥቁር ፍየል ለፍቶ የተሠራውን
ቆዳ ዙሪያዋን በነሐስና ጨሊ አስጊጣ ለብሳ፣ አንገቷ ላይ በደረደረችው ጨሌ ራሷን አሰማምራ፣ ዳሌዋንና ቀጥ ብለው ግጥም ያሉ ማራኪ የእግር ቅርፅዋን ስታይ ካርለት አፏን በአድናቆት ከፈተች
«በእርግጥ በጣም ቆንጆና ለየት ያለች ነች መቼም አይቻት እንደማላውቅ እርግጠኛ ነኝ» እያለች በባለ ሌንሱ ካሜራዋ ደጋግማ
ከርቀት አነሣቻት" ልጃገረዷ ካለምንም ሥጋት ወደ ካርለት ሰቀላ ቀርባ ሰላም ብላ ካርለትን ቆም ብላ ካየቻት በኋላ ጸጕሯን በጣቶቿ እሷም በተራዋ እየነካካች አድናቆቷን በሣቋ ገልጣ ልትሄድ ስትል
ካርለት «ወይ አምላኪ፣ አምላኬ! ኧረ ጥርሶቿስ እንዴት ያምራሉ!» አለችና እንድትቀመጥ ጋበዘቻት" ልጃገረዷ ግን፣ ካርለትን የቤት ውስጥ ሁኔታ አንገቷን አስገብታ ቃኝታ በድጋሜ
ፈገግ ብላ፣ «ደህና ሁኝልኝ» ብላ ሄደች"

ከሎ ሆራ የሐመሯን ውብ ቀደም አድርጎ ይመለከታት ነበርና ውበቷ ደንቆታል" በተለይ ወደ እሱ ቤት አቅጣጫ ስትመጣ ልቡ
መዝለል፣ ሐሳቡ መተረማመሱን ጨመረ። ከሎ ሆራ እስh ዛሬ
ታይቶበት የማያውቅ መርበትበትና ድንጋጤ ታየበት"

ልጃገረዷ፣ «ደህና ዋልህ» ብላው፣ ከተከፈተው የጎጆ ቤት መስኮት ላይ ተንጠልጥላ ስታይ እግሮቿ፣ ጭኗ፣ ዳሌዋና የሚሳበው
| ወገቧ ከሎን በሲቃ አፈኑት። ልጃገረዷ፣ የሚተኛበትን መኝታና
ዕቃዎቹን ተመልhታ ስትወጣ የሱም ልብ አብሮ ተከተላት እሷ እንደምታውቀው በማንኛውም የሐመር ቤት የሚገኝ ለመተኛ ቁርበት፣ ለመመገቢያና ለመጠጫ ሾርቃ (ከቅል የተሠራ)
እንስራ (ለሸፈሮ ቡና ማፍያ) ነው" ከነጯ ቤትና እንደ ሐመሮች መልክ ያለውና ጨርቅ ለባሹ ቤት ግን አይታው የማታውቀው ዕቃ
አለ" በኮተቱ ብዛት ትገረም እንጂ አልተደነቀችም“ እንዲያውም ለሰው ልጅ አስፈላጊ የሆኑት ቁርበት፣ ሾርቃ፣ እንስራ ቤታቸው
ውስጥ ባለመኖሩ ተደንቃለች።

ከሎ ቤቱ በር ፊት ለፊት ሆኖ ጠበቃት በሐመር ባህል ደንብ ልጃገረድ ከቡር ናት ካለፍላጎቷና ሳያግባባ መታገል የውርደት
ውርደትና ነውር ነው" ልጃገረድ እንደሚሰበር ዕቃ የሚጠነቀቁላት፣ እንደ ሕፃን ልጅ ፍላጎቷን የሚያከብሩላት መሆን ይገባል"ልጃገረድ የምትፈልገውን ወንድ ቀጠሮ ትሰጠዋለች" ያውም
ከተመቻት ነው" ካለበለዚያ፣ ካለ እሷ ትብብር አፈቀርኩ፣ ወደድኩ፣ በዚህ ወጥቶ በዚያ ወርዶ፣ ምን ሲባል ያን አይተሽ፣ እያሉ መሟዘዝ በባህሉ አይታወቅም
በሐመር ማኅበረሰብ ልጃገረድ ቀሳሚ ንብ፣ ወንዶች አበባ ናቸው" ባል ካገባች በኋላ ግን ሴት የባል ዕቃና ንብረት ናት።

ስለዚህ ልጃገረዷ ካለፍላጎቷ የሚደርስባት ችግር እንደሌለ
ስለምታውቅ ከሎን አልፈራችውም ከሎ ሆራ ግን ድንገት «እጅ ወደ ላይ» እንደተባለ ሰው ደንዝዟል" ካርለት የሁለቱን ሁኔታ
ከርቀት በጕጕት ትመለከታለች" ልጃገረዷ ሰላምታ አቅርባለት
መንገዷን ሰትቀጥል፣ ከሎ በባህሉ ኰራ ብሎ መታየት ሲገባው ተርበተበተ"

ሰንበት ብሎ ሲያስበው ራሱን ቢታዘብም በሕይወቱ በጣም አደገኛ ወጥመድ ላይ የወደቀበት ጊዜ ያ መሆኑን ራሱ ለራሱ አመነ"
ልጃገረዷ ግን ዳግመኛ ወደ መንደሩ አልተመለሰችም።

ሆኖም ከሎ፣ «ከየትኛው መንደር ይሆን የመጣችው? እጮኛ አላት ይሆን?» እያለ፣ በሐሳቡ መዋለሉ አልቀረም።

«...የሐመር ወንዶች ቢያፈቅሩም ፍቅራቸውን በግልጽ ማሳየት
ነውር ነው። ቢሆንም ልጃገረድን መዳራት ነውርነት የለውም» ብሎ፣
ከሎ የነገራትን ካረለት አስታወሰች"

ከሎ ሲቆዝምና ሐሳብ ሲያበዛ፣ ካርለት በፍቅር ሰመመን መዋጡን በመረዳቷ፥ «ከሎ ያችን ልጃገረድ እውን አፍቅሮ ይሆን? ፍቅሩንስ በምን መልክ ይገልጽ ይሆን? ባህላዊውን ወይስ ዘመን
አመጣሹን ይሆን የሚጠቀመው? ኧረ ኅብረተሰቡስ ምን ይሰማው
ይሆን?» በማለት፣ ካርለት በጥንቃቄና በተመስጦ ማሰቧን ቀጠለች።

«ምን ዓይነት ድንቅ ነገር ነው!» ሁሉም ነገር ምሥጢር ሆኖባት
ተገረመች። ስሜት ረቂቅ ነው፤ አይጨበጥም። ስሜት በአካባቢ ላይ
ተፅዕኖ ቢኖረውም፣ አካባቢም በስሜት ላይ ጫናው ከባድ ነው"
ማፍቀርና መፈቀር ተፈጥሯዊ ነውና ማንም ከዚህ ስበት ሊያመልጥ
አይችልም" ችግሩ ከፍቅር ቀጥሉ ግንኙነቱ በምን መልክ መሆን ይኖርበታል ነው። እኒህ ሁለት ሥረ ግንዳቸው አንድ የሆኑ፣ አካባቢያቸው ግን ለውጥ ያለው ሰዎች እውነት እንዳሰቡት ቢፋቀሩስ?»

አዲሱን ምርምሯን በተለያዩ መንገዶች ተጠቅማ ማወቅ
ይኖርባታል" «ከሎ ከልጃገረዷ ጋር ፍቅር ቢይዘው ልብስ በመልበሱ
ትንቀው ትችል ይሆን? አውሬ ወይንም የጎሳው ጠላት የሆነውን ሰው አልገደለም ከብት የለውም ስለዚህ ዘመናዊዋም ሆነች ቆዳ ለባሿ ሴት ክብርና ዝናን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ፈላጊ ስለሆነች
ላትቀርበው ትችላለች"»

«ከሎም ቢሆን ልጃገረዷን ለማግባት ኡክሊ ሆኖ በየዘመዶቹ መዞር፣ ከብት መዝለልና ለኮይታ (ጥሎሽ) የሚሰጠው ከብት፣
ፍየል፣ በግና ማር ማግኘት አለበት"
👍30😁3