#እገዛላታለሁ ... !!
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ቆንጆ ማለት ለዓይን የሚማርክ፣ ለጆሮ የሚጥም፣ የሚያምር፣ የሚያስደስት፣ የሚያማልል፣ ሰው፣እንስሳ፣ ሳር፣ ቅጠል፣ አየር፣ ውሃ፣ ቃል፣ ሁኔታ፣ ድርጊት ሌላም መዓት ትርጉም ይኖረዋል፡፡
አሻሚ ነው ቃሉ፡፡ ውብ የሚለው ቃል ግን አያሻማም አያደናግርም፣ “ውብ” ማለት “እናቴ” ማለት ናት ! የእኔ እማማ ብቻ !!
አዎ እናቴ ውብ ናት !! በችግር የማይፈታ ውበት፡፡ ማንም በአድናቆት ቃል በእንቶፈንቶ ድለላ
ውሉን እጁ አስገብቶ የማይተረተረው ነጭ ቱባ ናት እማማ ፤ ፈገግ ስትል ከጥርሶቿ ድል ማድረግ በአካቤቢው ይነዛል፡፡ እንደ እናቴ ፈገግታ ልብ የሚሰነጥቅ ሳቅ አላየሁም፤ የእናቴ ፈገግታ ብርታቴ ነው፡፡ ሰውነቴ በፈገግታዋ ይታደሳል፡፡ የተፈጥሮ ፍልውሃ ነው ፈገግታዋ !!
ሕይወት ወገቧን አስራ ልታስለቅሳት ድንጋይ ስትፈነቅል እናቴ እማምዬ.የኔ ፀሐይ...በአንዲት
የአሽሙር ፈገግታ ትደቁሳታለች ፤ ሕይወት የጨለማ አረሟን በቤታችን ላይ ስትዘራ እናቴ
በፈገግታዋ ትመነጋግለውና የደስታ እና የሐሴት አዝመራ ቤታችን ይዘናፈላል፡፡እዛ ማሳ ውስጥ እኔ እቦርቃለሁ፡፡አውቆም ይሁን ሳያውቅ አባቴ ቤታችንን የምድር ዋልታ ላይ በበረዶ ገነባው፤ እናቴ በፈገግታ ገመድ ጎትታ መሃል አዲስ አበባ፣ አራት ኪሎ፣ ፀሐይ የሞላበት አመጣችው ቤቱን ከነግቢው ከነዛፉ !! እንደዛ ነው የሚሰማኝ፡፡
አባቴ በውትድርና ኤርትራ ሄደ፡፡
“እነከሌ አገር ሊገነጥሉ፣ መሬት ሊሸርፉ ነውና ሄደህ ልክ
አግባቸው!” በሚል ትዕዛዝ ከእኔ ከአንድ ልጁና ከሚወዳት ሚስቱ ተነጥሎ ሄደ :: “.…አቤት
ቁመና ! አቤት የትጥቅ ማማር !” እያለ ጎረቤቱ ሸኘው፡፡ አምሮ ሊገድል፣ አምሮ ሊሞት አባቴ፡፡
ሕፃን ነበርኩ፤ ብዥ ያለ ነው ትዝታዬ፡፡ አባቴ ሄደ፤ (ዘመተ ይሉታል)፡፡ ስልክ የለም፤ ደብዳቤ
የለም፤ ሄደና ጠፋ፡፡
እናቴ ታዲያ በፍፁም ንፅህና
ስድስት ዓመት ጠበቀችው:: ያውም በደጃችን፡ በእናቴ ውበት
መቶ ጀኔራል እየሸለለ፣ ሺ ካድሬ እየቋመጠ፣ ሚሊዩን አብዮት ጠባቂ ምራቁን እየዋጠ !!
"ንፅህናዋን በምን አወቅክ ?” ስድስት ዓመት ሙሉ ማታ ማታ አንዲት ቀን ሳታቋርጥ ፎቶው
ፊት ተንበርክካ ምን እያለች ትፀልይ እንደነበር እናንተ ታውቃላችሁ ? የአባቴን ፎቶ አቧራ ዝር እንዳይልበት በቀን ስንት ጊዜ ትወለውለው እንደነበርስ…?
ከቤታችን ዕቃዎች ውድ የተባለው መደርደሪያ ላይ ምን ይቀመጥ እንደነበርስ ? የአባቴ ፎቶ !! በዛ ናፍቆት በረበበት፣ ምስኪን እናትና ልጅ ምዕመን በሆኑበት፣ የብቸኝነት ቤተ መቅደስ ውስጥ የአባቴ ፎቶ ፅላት ነበር፡፡
አባቴ ፎቶ ጎን ተሳስቼ ደብተሬን ሳስቀምጥ ሳታስደነግጠኝ ቀስ ብላ ታነሳዋለች ፡፡ ቤት ለማዘጋጀት
እንዳይመስላችሁ፣ አባቴ ፎቶ አጠገብ ምንም እንዳይቀመጥ እንጂ !! እማማ የቃል ኪዳን
ቀለበቷን ሽጣ ምን ገዛች? ለኔ ቆንጆ ጫማና ልብስ ፣ ምድረ የትምህርት ቤት ማቲ የቀናበት
የደብተር መያዣ ቦርሳ ፣ ለአባቴ ፎቶ ወርቃማ የብረት ከፈፍ ያለው ባለመስታዋት የፎቶ ማስቀመጫ፤ በተረፈችው የቃል ኪዳን ቀለበቷን የምትመስል አርቴፊሻል ቀለበት ፡፡ በእንቁ ልብና በአርቴፊሻል ቀለበት ቃል ኪዳኗን አጠረች፤ ከእኔ በስተቀር ይሄንን ማንም አያውቅም::ለራሷስ ምን ገዛች?…ምንም !! እች ናት እናቴ!!
ስድስት ዓመት አባቴን ጠበቀችው ይሄ ሊመጣ ይችላል ተብሎ እዛም እዚህም እየተባለ የሚጠበቀው ዓይነት ጥበቃ ሳይሆን 'መቼ ሄደና' ብሎ ክችች የሚሉት አይነት የመንፈስ አብሮነት
በሌሉበት ማከበር !! ..ይሄ የመጀመሪያው ዓመት ላይ “ሄደብኝ የኔ ጌታ የልቤ ቁራሽ የደሜ ጭላፊ…" እያሉ ጎረቤት እንዲያባብል ድራማ መስራት፣ ዓመት በጨመረ ቁጥር 'አሁን ተፅናናች ሰው መቅረብ ጀመረች የሚባለው አይነት መጠበቅ ሳይሆን፣ ትላንትም ዛሬም ዓመታት ጉልበቱን በማይሰልቡት ጥልቅ መሻት ጠበቀችው:: ይህች ናት እናቴ!!
ስለ ኤርትራ በተወራ ቁጥር ኪሎ ስጋ ከአካሏ እየተገነጠለ ጠበቀች :: “ከኤርትራ የመጣ ሰው
በኮተቤ አለፈ" ሲሏት ነጠላዋን አንጠልጥላ ኮተቤ ትገኛለች፡፡” እንዲት ኤርትራዊት ተፈናቃይ
አቃቂ ኪዬስክ ከፈተች” ሲባል ከአራት ኪሎ እየተመላለሰች የስሙኒ ሻይ ቅጠል ለመግዛት
ደንበኛ የምትሆን ሴት ካለች እናቴ ብቻ ነበረች፡፡ እች ናት እማማ!!
እርጋታዋ የእኔ እማማ በእልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል” ተረት እልፍኛቸው ውስጥ ተሳላፊ እንደሚያበዙ ሴቶች አይደለችም ፤ ማንም የቃል ኪዳን መስመሯን አያልፍም፤ አገር ያውቃል፡ቤታችን ቤተ መቅደስ ነው፡፡ የፍቅር ፅላት በቅዱሰ ቅዱሳን እማማ ልብ ውስጥ አለ፡፡ እርጋታዋ ታማኝነቷን ይነግረኛል፡፡ ዓይኗ ከአባቴ ፎቶ ላይ ከተነቀለ ቀጥሎ ማረፊያው እኔ ላይ ነው፡፡
ጆሮዋ ወደ ውጭ አይቀሰርም፡፡ የኔን አርቲ ቡርቲ ወሬ እንደወንጌል በጥሞና መስማት የነፍሷ
እርካታ ነው፡፡ አባባ መጽሐፍ ቅዱስ፣ እኔ ዮሐንስ ራዕይዋ ታነበኛለች፣ ሰባት ቀንድ፣ እስራ
ስድስት ምላስ፣ ምንም ጆሮ የሌላቸው ልዩ ፍጥረቶች መሐል እናቴ ጆሮ ብቻ ሆና ትሰማኛለች ...!!
ጥቁር ፀጉሯ ሲዘናፈል፣ እንደማር የለሰለሰ ቆዳዋ አላፊ አግዳሚ ሲጠራ፣ ረጋ ባለ እርምጃ እንደ
ደመና ስትንሳፈፍ፣ “ፈዛዛ ውበቷን አቀለጠችው” ይሏታል፡፡ “ጎታታ እንደ ኤሊ ስትንቀረፈፍ
እድሜዋን ፈጀች” ይሏታል፡፡ በሌጣ ልባቸው ሮጠው ምናምን ስለቃረሙ የፈጠኑ የመስላቸው
የመንደራችን ከንቱ ሐሜተኞች፡፡ የፍቅር መስቀል ተሸክማ ዳገት የምትወጣ እናቴን ኤሊ ይሏታል፤
አፍ አውጥተው ኤሊ ይሏታል፡፡ የድንጋይ ልባሷ አንደነሱ ቀሚስ የትም ለማንም አለመገለቡ
እያበገናቸው፣ ተኳኩለው የሚጠብቋቸው ወታደር ውሽሞቻቸው ያልተኳኳለች እናቴን እያዩ
«ማናት ይህች ቆንጆ ?” ሲሏቸው እየበሸቁ…::
እማማዬ ስድስት ዓመት ጠበቀችው አባቴን፡፡ “ይኼኔ ባሏ ከአስመራ ቆንጆዎች ጋር አሸሼ ገዳሜ እያለ ነው፣ እሷ እዚህ ጉልበቷን አቅፋ ትጠራሞታለች” እያሏት ጎረቤቶቻችን፤ አስመራ አድረው ጧት አዲስ አበባ የገቡ ይመስል፡፡ “ለታመነልህ ታመን” የቆሸሸ ዲስኩራቸው “በአልታመኑልንም” ሰበብ ባሎቻቸውን እንዲክዱ፣ ፍቅረኞቻቸውን እንዲቀጥፉ መንገድ እየጠረገላቸው፣ ለውስጣቸው ግልሙትና ጥቅስ እየሆነላቸው፣ “የአስመራን ግልሙትና በአዲስ አበባ ግልሙትና መበቀል ፅድቅ
ነው" የተባለ ይመስል እማምዬን “ባልሽ ወንድ ነው አትመኝው” ይሏታል፡፡
እንድ ማለዳ በራችን ተንኳኳ፡፡ እማማ ከፈተች፡፡ ጎረቤቶቻችን አንድ የተጎሳቆለ ወታደር
አስከትለው መጡና “ባልሽ ሞቷል” አሏት :: “በዚህ ወርዶ በዚያ ሂዶ፣ መድፍ ተኩሶ፣ ታንክ
ማርኮ፣ በጀግንነት ሞተ !” አሏት፡፡ ዝም ብላ ሰማቻቸው፡፡ “ሰው ቀጥ ብሎ የማያይ ጨዋ፣ለትዳሩ ታማኝ፣ ወታደሩ ሁሉ እዛና እዚህ ሲል ባልሽ ግን የአንቺን ፎቶ ከደረት ኪሱ ሳይለይ
በየበረሃው ለእዝ ሲፋለም ኖሮ ሞተ” አሏት፡፡ ዝም ብላ ሰማቻቸው፡፡
አባቴ ሲሞት “ከጎኑ ነበርኩ” ያለው ጎስቋላ ወታደር ከአባቴ ሬሳ ኪስ ውስጥ አገኘሁት ያለውን
ፎቶ ሰጣት፡፡ እናቴና አባቴ ጎን ለጎን ሆነው የተነሱት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ነበር፡፡ ልክ መሀላቸው

👍30🔥1👏1
ላይ በጥይት የተቦደሰ ፎቶ እማማ እጅ ላይ እንዳለ በትከሻዋ ተንጠራርቼ ፎቶውን አየሁት፡፡
እንዴ ! በመድፍ ጥይት ነው እንዴ ፎቶውን የበሉት? እና እንዴት አንዲት ጥይት በቤተሰብ
መካከል ይሄን የሚያህል በደም ነጠብጣብም የተከበበ ሽንቁር ትፈጥራለች? ገረመኝ፡፡
“ባለቤትሽ ደረቱ ኪስ ነበር ፎቶውን የያዘው፡፡ ከጠላት የተተኮሰ ጥይት ፎቶ ባስቀመጠበት ኪሱ በኩል ደረቱን መታችው” አለ ድምፁ የሰለለው ወታደር፡፡ እማማ ፎቶውን በትኩረት አየችው፤ ረዥዥዥም ሰዓት ዝም ብላ አየችው፤ አላለቀሰችም፡፡ ፊቷም ላይ ምንም ለውጥ አልታየም፡፡ ከፎቶው ይልቅ ሽንቁሩን የምታይ መሰለኝ፡፡ አንዴ በረዥሙ ተነፈሰችና ፊት ለፊት መደርደሪያው ላይ የተቀመጠውን የአባባን ፎቶ ተመለከተች ፡፡
"አሁን ውሻ ሞት በከፈተው ቀዳዳ ጅብ ወንዶች ዘው ሊሉ አሰፈሰፉ፡፡ “አይዞሽ ሰው መቼስ ዘላለም አይኖር ምናምን…” ብለው በማስተዛዘን ስም ወደ ቤተ መቅደሳችን ዘው ሊሉ፡፡ እናቴ
“ማንም ለቅሶ እንዳይደርሰኝ” አለች፡፡ መንደሩ “ለየላት አበደች…” ብሎ አወራ፡፡
እማማ የእኔ መልአክ እኔንም ግራ አጋባችኝ ፡፡ አባቴ ሞቷል ወይስ አልሞተም ? ቢሞትም
እማማ “አልሞተም” ካለች አልሞተም፡፡
ቀኑ የአባባ መርዶ የመጣበት ሰኞ ነበር፡፡ ረጋ ብላ ቁርስ ሰራችልኝ፤ የሚጣፍጥ ጨጨብሳ
ስኳሩ በዛ ካለ ሻይ ጋር :: እሷ አልበላችም፡፡
በእጇ የያዘቻትን የሻይ ማንኪያ እየነቀነቀች በጥልቀት ታየኛለች፡፡ ዓይን ዓይኔን እያየችኝ ጥርግ
አድርጌ በላሁ፡፡
ጉንጬን ስማኝ ወደ ትምህርት ቤት ሸኘችኝ፡፡ ጉንጬን ነው ያልኩት ? በልምድ ብዙ ወላጆች
“የልጆቻቸውን ጉንጭ ይስማሉ” እንላለን እንጂ እንደ እኔ እናት ከሆነ ግን ወላጆች የልጆቻቸውን
ነፍስ ነው የሚስሙት ፡፡ አዎ እማምዬ ነፍሴን ስማ ነው የምትሸኘኝ!! ብዙ ከሄድኩ በኋላ
ወደ ቤታችን ዞር ስል አረንጓዴ ቢጃማዋን ለብሳ የበሩን ጣውላ ተደግፋ ቆማ እያየችኝ ነበር፡
የደከማት ትመስላለች፡፡ እማማን እንዲህ ከሩቁ ሳያት “ተመለስ ተመለስ.. እቅፍ አድርጋት
ከጎኗ አትለይ…” ይለኛል፡፡ ሁለት ሰው እሆናለሁ፤ እግሬ ወደፊት እየሄደ ልቤ ወደ እማማ
ወደኋላ ይሮጣል ፡፡
ዓይኖቿ ብርታቶቼ ናቸው:: ከኋላዬ ስትቆም እልፍ አእላፍ መላዕክት ከነሰይፋቸው፣ ከነእሳት ሰረገላቸው እኔን ሊጠብቁ የቆሙ ይመስለኛል፡፡ በምድር ላይ ያለ የጦር ሰራዊት ከነመሳሪያው
ያጀበኝ እናትዬ ከኋላዬ ስትቆም ሰማይ ይቀርበኛል፤ ደመና ባጭር የተቆረጠ ፀጉሬን ሲዳስሰኝ
ይሰማኛል፤ የእግዜር እግር ስር የቆምኩ ይመስለኛል፡፡ የምረግጠው ምድር በእግሮቼ ብርታት የሚናጥ፣ ድንጋዮቹ የሚፈነቃቀሉ ይመስለኛል፡፡ የእማማን የዕይታ ጥሩር ከለበስኩ ማንንም አልፈራም ፡፡ተራሮች ምንድናቸው? በእግሬ እንደማንከባልለው የጨርቅ ኳስ ናቸዋ !! ጨጨብሳ ባልበላም በጠረኗ ሺ ዓመት እኖራለሁ፤ በፈገግታዋ ዘላለም!!
እማምዬ የፍቅር ጥግ፣ የእናትነት አልፋና ኦሜጋዬ፡፡ እናንተ “ሴት እናት ናት! ሴት እህት ናት!” የምትሉ በደፈናው ኃይማኖተኛ ሁሉ መነኩሴ ነው እያላችሁ ነውና ይቅር ይበላችሁ፤
ሴትነት እናትነት አይደለም፡፡ “ሴት ከውስጧ የወጣ ገዳም ውስጥ ስትመንን እናት ትሆናለች”
ሴት…“ልጅ” የሚባል መስቀል ተሸክማ የሕይወትን ቀራንዬ ስትወጣ እናት ትባላለች ፤ ሴት
ልጅ የራሷን ዘመን ይቅርብኝ ብላ የልጆቿ የዘመን መስቀል ላይ በፍቅር ስትቸነከር ወደ እናትነት
ከፍታ ታርጋለች፡፡
እማማን ዞሬ አየኋት፡፡ የምትወደው ባሏን መርዶ ቅድም የሰማች ሴት በር ላይ ቆማለች፤ አይገርምም ? እናት የላትም፣አባት የላትም፣…ዘመድ የላትም፣ እኔ ብቻ ነኝ ያለኋት፡፡ የማላውቀው
ስሜት ወረረኝ፡፡ በአንድ ጊዜ ጀግናም ፈሪም ሆንኩ እኩል! “ማንም የላት” እና “እኔ አለሁላት”
የሚሉ ኃሳቦች ተጋጩብኝ፡፡
ትምህርት ቤቴ እስከምደርስ እንባዬ ጉንጮቼ ላይ እየፈሰሰ እንዲህ እያልኩ ለብቻዬ አነበንብ ነበር
“ሳድግ ለእማማ አዲስ አበባ ሱቆች ውስጥ ያሉትን ቀሚሶች ሁሉ እገዛላታለሁ፡፡ ፒያሳ ወርቅ
ቤቶች ወስጥ የተደረደሩትን ያልተ ደረደሩትንም የወርቅ ቀለበቶች ፡ ሃብሎች ጉትቻዎች ሁሉንም
ለእማማዬ እገዛላታለሁ፡፡ ለእናትዬ ትልቅ ቤት እገዛላታለሁ፡፡ ትልቅ ግቢ እገዛላታለሁ ...:
ባለ ሚሊዮን ፎቅ፡ ዛፉ ጨረቃን የሚነካ ሕንፃ እገዛላታለሁ፡፡ በመጨረሻው መስኮት ብቅ ብላ
የአባቴን ፎቶ ከነ ወርቃማ ፍሬሙ ጨረቃ ላይ ታስቀምጠዋለች፡፡ ማንም እንዳይደርስበት !
ሳድግ ለእማምዬ ሰፈራችንን አራት ኪሎን እንዳለ እገዛላታለሁ፡፡ ከነሐውልቱ፡ ከነዩኒቨርስቲው፣
ከነቤተመንግስቱ.…!!
ሳድግ ለእማማ፣ ለእኔ ደግ፣ ለእኔ ሩህሩህ አዲስ አበባን እገዛላታለሁ፡፡ ሳድግ ለኔ ትሁት፣ ለኔ ቃልኪዳን አክባሪ ኢትዮጵያን እገዛላታለሁ !! ከነሕዝቡ፣ ከነኃይማኖቱ፣ ከነቤተ ክርስቲያኑ፡
ከነ መስጊዱ እገዛላታለሁ፡፡
ሳድግ ኢትዮጵያን..ከነተራራው፣ ከነራስ ዳሽኑ፣ ከነሸለቆው፣ ከነጫካው፣ ከነዋልያና ጭላዳው፣
ከነአዋሹ፣ ከነጫሞ እና አብያታው፣ ከነሶፍዑመሩ፣ ከነላሊበላው፣ ከነፋሲለደሱ፣ ከነጣናው፣ ከነአባቱ፣ ከነአክሱሙ እ ገ ዛ ላ ታ ለ ሁ!!
እዎ እገዛላታለሁ !! “አልፈልግም የኔ እንቦቀቅላ ይሄ ሁሉ ምን ያደርግልኛል ?” ብትልም
እልሰማትም፣ እገዛላታለሁ...!!!
ሳድግ…ትልቁ የልቧ ስባሪ፣ የነፍሷ ቀንዲል፣ የፍቅሯ ስር፣ የእኔም አለኝታ እንደቀልድ የወደቀባትን
ምድር
ኤ
ር
ት
ራ
ን
እገዛላታለሁ ! ለ እ ማ ም ዬ !!
✨አለቀ✨

❤27👍24
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሁለት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
....አልፎ አልፎ መስመሩን
የሚዘረጋው ጨረቃና ደፋ ቀና የሚሉት ከዋክብተ አካባቢው ጨርሶ ጨለማ እንዳይሆን ረድተዋል :: ስለዚህ የመሬቱን የሰማዩን ያህል አልጨለመም:: ሆኖም አካባቢው በጣም ያስፈራል፡፡.
ከጉብታውና ከተንጣለለው ሜዳ ላይ ከአንድ ቅርጸ ቢስ ዛፍ ሌላ
ምንም አልነበረም፡፡ ዛፉ መንገደኛው ከደረሰበት ሩቅ አልነበረም:: ሁናቴው ስላላማረው መንገደኛው ወደመጣበት ተመለሰ፡፡
ከምሽቱ ወደ ሁለት ሰዓት ገደማ ሆኖአል፡፡ አካባቢውን ስለማያውቅ
መንገድ እንደመራው ብቻ ዝም ብሎ ተጓዘ፡፡ የከንቲባውን ቤት እንዳለፈ ከትምህርት ቤት አካባቢ ደረሰ፡፡ ትምህርት ቤቱን አልፎ እንደ ሄደ ቤተክርስቲያን አጋጠመው:: ገና ቤተክርስቲያኑን ሲያይ እጁን ጨብጦ ዓይኑን ወደላይ አንጋጠጠ፡፡
ከቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አንድ ማተሚያ ቤት አለ፡፡ ሰውዬው
ድካም አወራጭቶት ስለነበር ከዚህ የተሻለ ሥፍራ ሳይፈልግ ከማተሚያ ቤቱ አጠገብ ከነበረው የድንጋይ አግዳሚ መቀመጫ ላይ ተጋደመ::
ወዲያው እንደተጋደመ አንዲት አሮጊት ከቤተክርስቲያኑ ወጡ፡፡
«ወዳጄ ከዚህ ምን ታደርጋለህ?» ሲሉ ጠየቁት፡፡
«አየሽ የእኔ አዛኝ፤ መተኛቴ ነዋ!» አሊ በቁጣና በድፍረት የማይሆን
መልስ መስጠቱ ሳይታወቀው:: ክብር የሚገባቸው አዛኝዋና ደግዋ ሴት ማዳም ላ ማርኩዚ ይባላሉ::
«እንዴ! ከድንጋይ ላይ!» አሉ፤ «ሌሊቱን በሙሉ ከድንጋይ ላይ
ተኝተህ ሊነጋልህ አይችልም:: ረሃብ እንዳንገላታህና ብርድ እንዳጠቃህ ሰውነትህ ይመስክራል፡፡ የሚያስጠጋ አላገኘህም?»
«ብዙ ቤት ሞከርኩ፤ የየቤቱን ደጃፍ አንኳኳሁ::»
«እና!»
‹‹ሁሉም ሰው ከበራፌ ሂድ አለኝ::
ደግዋ ሴት የሰውዬውን ጀርባ እየመቱ፡ ከአደባባዩ ባሻገር የሚታየውንና ከጳጳሱ ቤት አጠገብ የነበረውን ቤት ጠቆሙት፡፡
«ያንን ቤት ሞክረሃል?» ሲሉ ጠየቁት::
«አዎን::»
«ከዚያ ማዶ ከሚታየው ቤት አንኳኩተሃል?»
«የለም::»
«እዚያ ሞክር እስቲ፡፡»
እናያ ደገ ጳጳስ ከተማ ወስጥ ሲዘዋወሩ በመቆየታቸው ስለደከማቸው ያን እለት ማታ ከክፍላቸው ሳይወጡ ብዙ ቆዩ:: በተጨማሪም ብዙ ስራ
ስለነበራቸው «ሥራዩን ሳልጨርስ አልነሳም» በማለት አእዚያው አመሹ::
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሲሆን እዚያው ሥራቸው ላይ ነበሩ:: በብጣሽ ወረቀትና በማስታወሻ ደብተር ላይ ጉልበታቸውን እያስደገፉ ሲፅፉ
እንደተለመደው አልጋቸው አጠገብ ከነበረው ቡፌ ከብር የተሠራ ሣህን ለማውጣት መዳም ማግልዋር ይገባሉ:: ሴትዬዋ ከተመለሱ በኋላ ጥቂት
ቆይቶ ገበታ እንደቀረበና እህታቸው እንደሚጠብቋቸው በመገመት ጳጳሱ ወደ ምግብ ቤት ሄዱ:: ምግብ ቤቱ፡ የአራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ዓይነት ሆኖ የእሳት ማንደጃ አለው:: ቢፈለግ ወደ አውራ ጎዳናው የሚያስወጣ በርም አለው:: በአትክልቱ በኩል መስኮት አለ፡፡
ማዳም ማግልዋር ገበታውን ሠርተው ከጨረሱ በኋላ ጠረጴዛውን እያስተካከሉ ከመድምዋዚል ባፕቲስታን ጋር ይጫወታሉ:: ገበታው አጠገብ
ሻማ ከትንሽ ጠረጴዛ ላይ ተቀምጦ እየተቀጣጠለ ነው:: ከማንደጃው ውስጥ
የተቀጣጠለው እሳት ፍም ብዛት ስለነበረው ክፍሉ ይሞቃል፡፡ የቤታቸው በር እንዴት መቆለፍ እንዳለበት መዳም ማግልዋር ሲያወሩ ጳጳሰ ይገባሉ፡፡
ማዳም ማግልዋር ለእራት የሚሆን ሸቀጣሸቀጥ ለመግዛት ወደ ገበያ ሄደው ሳለ አንድ መግቢያ ያጣ ማጅራት መቺ ከተማ መግባቱንና ይህ ሰው
በጊዜ ከቤታቸው በማይገቡ ሰዎች ላይ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ሲወራ ይሰማሉ፡፡ ሁለቱ ሴቶች ስለዚሁ ጉዳይ ሲያወሩ ጳጳስ ስለገቡ «አባታችን
መዳም ማግልግር የሚናገሩትን ይሰማሉ?» በማለት ጠየቅዋቸው::
«የምትሉት ነገር ግልጽ ባይሆንልኝም ሰምቼአለሁ» አሉ ጳጳሱ፡፡ከዚያም ፊታቸውን ወደሚነድደው እሳት በማዞርና እጆቻቸውን ከጉልበታቸው
ላይ በማሳረፍ ሠራተኛቸውን እያዩ
«ታዲያስ ፤ ምንድነው ጉዳዩ? የሚያስፈራ ነገር አለ እንዴ?» ሲሉ ጠየቁ፡፡
ይህን ጊዜ መዳም ማግልዌር ሳያስቡት ታሪኩን በማጋነን አዋሯቸው::
«ያለመጫሚያ ባዶ እግሩን የሚጓዝ ማጅራት መቺ፧ ሌባ፤ ቀማኛ ከተማ ገብቷል» አሉ፡፡ «ክዊን ላባር ሄዶ ማረፊያ ቢጠይቅ ባለቤቱ አልፈቀደለትም::
ከመሸ በኋላ ከተማ ውስጥ ሲዘዋወር ታይታል:: ስልቻውን በገመድ አስርና ተሸክሞ ይዞራል:: መልኩ ደግሞ በጣም የሚያስፈራ ነው::
«እውነትሽን ነው?» ሲሉ ጳጳሱ ጠየቁ፡፡
ጳጳሱ በታሪኩ የተመሰጡና ፍርሃትም ያደረባቸው ስለመሰላቸው
መዳም ማግልዋር ታሪካቸውን በኩራት ይቀጥላሉ:: «አዎን አባታችን፤ እውነት ነው:: ዛሬ ማታ ከተማ ውስጥ አንድ ነገር ይሆናል፡፡ ከተማው ሁሉ ይህንኑ ነው የሚያወራው:: መድምዋዜል ባፕቲስታን ደግሞ እንደምትለው...» በማለት ሴትዬዋ ንግግርዋን ስትቀጥል «እኔ» በማለት የጳጳሱ እህት ጣልቃ ገብተው «ያልኩት ነገር የለም» ይላሉ፡፡
ተቃውሞውን እንዳልሰሙ መስለው መዳም ማግልዋር ልፍለፋቸውን ቀጠሉ፡፡
«የዚህ ቤት ደህንነት ይህን ያህል አስተማማኝ አይደለም:: አባታችን
ቢፈቅዱልኝ ሄጄ ቁልፍ ለሚሠሩት ሰወዬ የድሮዎቹን መቀርቀሪያዎች
መልሰው እንዲገጥሟቸው ልንገራቸው:: መቀርቀሪያዎቹ ስላሉ በደቂቃ ይሰርዋቸዋል፡፡ ለዛሬ ማታ ብቻ እንኳን ባይሆን ለወደፊቱም ጥሩ ነው፤
በራችን ጠንካራ መቀርቀሪያ ይግባለት:: በቀላሉ የሚከፈት በር እጅግ አደገኛና አስፈሪ ነው:: አባታችን እንደሆነ ይቅርታ ቢደረግልኝ እኩለ ሌሊት
እንኳን ቢሆን ቤት ለእንግዳ፤ ይግቡ የማለት ልምድ አለብዎት:: ግን መቼም ለዚህ ፈቃድ መጠየቅ እንኳን አስፈላጊ» ሴትዮዋ አሳባቸውን ሳያጠቃልሉ በር በኃይል ይንኳኳል፡፡ «ይግቡ» አሉ ጳጳሱ፡፡
በሩ ተከፈተ:: ኣንድ ሰው ሰዎቹ ከነበሩበት ክፍል ውስጥ ገባ፡፡
ያ የምናውቀው ማደሪያ ፍለጋ ከቤት ቤት ፤ ከሥፍራ ሥፍራ
ይንከራተት የነበረው መንገደኛ ነበር፡፡ ሰውዬው በሩን መልሶ ሳይዘጋ አንድ እርምጃ ወደፊት ተራምዶ ቆም አለ፡፡ ስልቻውን በጀርባው ተሽክሞ ዱላውን
በእጁ እንደያዘ ነው:: የእሳቱ ውጋጋን ከፊቱ ላይ ሲያርፍ ሻካራውና ድካም ያጎሳቆለው ፊቱ የጭካኔ ምልክት እንዳለበት አጉልቶታል፡፡ ሆኖም ያ ስሜት ወደ ውስጥ የተቀበረ እንጂ በግልጽ የወጣ ኣልነበረም:: የመናፍስት
በአካል መታየት ነበር የሚመስለው::
ማዳም ማግልዋር ለመጮህ እንኳን አቅም አልነበራቸውም፡፡ እንደቆሙ እየተንቀጠቀጡ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ፡፡
መድምዋዜል ባፕቲስታን ዞር ሲሉ ሰውዬው ወደ ውስጥ ሲገባ አዩ፡፡
በፍርሃት ተውጠው ከመቀመጫቸው ብድግ አሉ፡፡ ከዚያም ዝግ ብለው ወደሚነድደው እሳት ዞረው ወንድማቸውን ተመለከቱ፡፡ ፊታቸውን ሲያዞሩ ትንሽ መንፈሳቸው ተረጋጋ፡፡
ጳጳሱ ሰውዬውን በጥሞና ተመለከቱት:: ምን እንደሚፈልግ ሊጠይቁት አፋቸውን እንደከፈቱ ለመናገር እድል ሳይሰጣቸው የያዘውን ዱላ በሁለት
እጁ በመመርኮዝ ከዚያ የነበሩትን ሰዎች አንድ በአንድ ከቃኘ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ መናገር ጀመረ::
«ተመልከቱኝ! ስሜ ዣን ቫልዣ ይባላል፡፡ የተፈረደብኝ ወንጀለኛ

👍27
ነኝ:: ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እሥር ቤት ነበርኩ፡፡ ከአራት ቀን በፊት
ተፈታሁ:: ወደ ፓንታልዩ ነው የምሄደው:: የተፈታሁ እለት ከቱሉን ተነስቼ በእግሬ እየተጓዝኩ ዛሬ ከእዚህ ደርሻለሁ:: በዛሬው ቀን ብቻ ወደ 55 ኪሎ ሜትር ያህል ተጉዤአለሁ:: ማምሻውን ወደዚህ ከተማ እንደገባሁ
ወደ ሆቴል ቤት ሄጄ ማደሪያ እንዲሰጡኝ ጠየቅሁ:: ከእሥር ቤት የተሰጠኝ መታወቂያ ብቻ በመያዜ ከዚያ ላድር አልቻልኩም:: ወህኒ ቤት ሄጄ እንዲያሳድሩኝ ብጠይቃቸው ከእዚያም አባረሩኝ:: ከከተማ ወጣ ብዬ ከዛፍ
ስር ለማደር ፈልጌ ነበር፡፡ ሆኖም ጨለማውን ፈራሁት:: ደመናውም
ስላንገበበ ይዘንባል ብዬ ስለሰጋሁና ደግ አምላክ ኖሮም ዝናቡን ያቆማል ብዬ ስላላመንሁ መጠጊያ አገኛለሁ በማለት ወደዚች ከተማ ተመለስኩ፡፡
ከከተማው መካከል ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት ከድንጋይ ላይ ተጋደምኩ፡፡
እንደተጋደምኩ አንዲት ደግ ሴት ቤታችሁን ጠቁማ 'ከእዚያ ቤት አንኳኳ' አለችኝ:: መጥቼም አንኳኳሁ:: ይህ ቤት የማን ቤት እንደሆነ ብትነግሩኝ፡፡
ሆቴል ቤት ነው? ከሆነ ገንዘብ አለኝ:: እሥር ቤት ውስጥ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ሠርቼ 109 ፍራንክና 15 ሱስ ያህል አጠራቅሜአለሁና ሂሣቡን እከፍላለሁ:: በጣም ደክሞኛል:: 55 ኪሎሜትር በአንድ ቀን በእግር መጓዝ ማለት ምን ያህል አድካሚ እንደሆነ ሳትገነዘቡ አትቀሩም:: ደግሞም በጣም ርቦኛል:: ታሳድሩኛላችሁ?»
«መዳም ማግልዋር» አሉ ጳጳሱ፤ «ሌላ ሳህን አምጪ፡፡»
ሰውዬው ጥቂት ራመድ ብሉ ከጠረጴዛው ላይ ተቀምጦ ይነድ
ወደነበረው የሻማ መብራት ጠጋ አለ፡፡ ሰዎቹ ችግሩን ያላወቁለት ስለመሰለው
«ቆዩ» ሲል ጮክ ብሎ በቁጣ ከተናገረ በኋላ «እሱን አይደለም የምለው ፤
ተግባብተናል? የመርከብ ቀዛፊ ባሪያ፤ ወንጀለኛ ነኝ:: ያንን አድካሚ የመቅዘፍ ሥራ ስሠራ ኖሬ ነው የምመጣው:: መታወቂያዩን ተመልከቱ:: የወንጀለኛ መታወቂያ ነው:: ሌላ መታወቂያ ስለሌለኝ የትም ብሄድ ያባርሩኛል::
ወሰዱት! ሰው ሁሉ እንደሆነ አባርሮኛል፡፡ እናንተስ ትቀበለኛላችሁ? ይህ ቤት ለመሆኑ ሆቴል ቤት ነው? የምቀምሰው ነገር ትሰጡኛላችሁ? ማደሪያስ
ትፈልጉኛላችሁ? የፈረሶች ጋጣ እንኳን ቢሆን አልጠየፍም:: ››
«ማዳም ማግልዋር አለ ጳጳሱ፤ «ከእኔ መኝታ ቤት አጠገብ ካለው
ክፍል ውስጥ ያለው አልጋ ይነጠፍ፡፡»
ማዳም ማግልዋር ትእዛዙን ለመፈጸም ወጡ፡፡ ጳጳሱ ፊታቸውን
ወደ እንግዳው አመሩ፡፡
«ልጄ አረፍ በልና ሰውነትህን አማሙቅ፡፡ በቶሎ ገበታ እንቀርባለን፡፡
እራታችንንም እስክንበላ መኝታው ይዘጋጅልሃል፡፡
በመጨረሻ ሰውዬው ገባው:: ያ አስፈሪና ጭጋግ የመሰለው ፊቱ
ተፈታ፡፡ የደስታ ውጋጋን ፊቱ ላይ ያበራ ጀመር፡፡ «እውነትም ሊያሳድሩኝ ይሆን» ሲል ራሱን ጠየቀ:: ከደስታ ብዛት እንደ እብድ ይቀባጥር ጀመር::
«እውነት ነው? እንዴት? ልታሳድሩኝ ነው? ወይስ አታሳድሩኝም?
ወንጀለኛውን! ሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ 'አንተ ውሻ፣ ከዚህ ውጣ' በማለት ፋንታ ልጄ እያሉ በአክብሮት ጠሩኝ እኮ! አሁን ከልብዎ ነው? ከዚህ
እንዳድር ፈቅደውልኛል? ጥሩ ሰዎች ናችሁ:: እኔ ደግሞ ገንዘብ ስላለኝ በሚገባ እከፍላችኋለሁ:: ይቅርታ ብቻ ፤ ድፍረት ባይሆንብኝ፤ የሆቴሉ
ባለቤት እርስዎ ይመስለኛል:: » ስምዎን ልጠይቅ! የጠየቁኝን እከፍላለሁ::
ጥሩ ሰው ነዎት፡፡ የሆቴሉ አስተዳዳሪና ባለቤት ነዎት ወይስ አይደለም?»
«ከእዚህ ቤት የምኖር መነኩሴ ነኝ» አሉ ጳጳሱ በፈገግታ ::
«መነኩሴ» አለ ሰውዩው:: «እህ... ፍጹም መነከሴ! እንግዲያውስ
ገንዘብ አያስከፍሉማ? የተጎዳን የሚረዱ ፤ የተጠቃን የሚያጸናኑ፤ ለነፍስዎ ያደሩ ሰው ነዎታ! አይደለም? የዚያ ትልቅ ቤተክርስቲያን ቄሰ ገበዝ
መሆንዎ ነዋ! አዎን፧ መሆን አለብዎት:: እንዴት ያለሁ ደደብ ሰው ነኝ፤እንዴት ቆብዎን ልብ አላልኩም::
ሰውዩው የባጥ የቆጡን እያለ ስልቻውንና ዱላውን ከአንድ ጥግ
አስቀምጦ መታወቂያውን ወደ ቦርሳው ከመለሰ በኋላ ቁጭ አለ፡፡
«አባቴ፤ ሰብኣዊ ርህራሄና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረብዎት ሰው
ነዎት:: እኔን እንደሌለች ሰዎች አላንቋሸሸኝም:: የካህናት ምሳሌ ነዎት፡፡ እንደ እርስዎም ያለ ካህን ያለ አይመስለኝም:: እንግዲያማ ገንዘብ አይቀበለኝም ማለት ነው?»
«የለም» አለ ጳጳሱ፤ «ገንዘብህን ያው» ካለ በኋላ በኃይል ተነፈሰ፡፡
ሰውየው ልፍለፋውን ቀጠለ፡፡ «አባ፡ ብፁዕ ወቅዱስ ለነፍስዎ ያደሩ ነዎታ! ከእዚያ ከነበርኩበት እስር ቤት እንዳንድ ቀን ትምህርት ይሰጠን ነበር፡፡ አንድ ቀን አንድ ጳጳስ አየሁ:: ሰዎች 'አባታችን' እያሉ ሲጠርዋቸው ሰምቼአለሁ:: ማርሴይ ከተባለ ሥፍራ የመጡ ሲሆን የዚያ አገር ሊቀ ጳጳስ
እንደነበሩ ተነግሮናል:: ጳጳሱ የጳጳሶች ጳጳስ ናቸው ብለውናል:: እዩ እንደት እንደምዘባርቅ:: እኔ እንደሆንክ ምኑንም አልያዝኩም ፧ አልገባኝም ነበር፡፡
ይቅርታ ያድርጉልኝ:: እኛ መሐይሞች እኮ ምንም አናዉቅም:: አንድ ቀን
ከቤተመቅደሱ ውስጥ ሆነው ቀዳሲውን መሩ:: አንድ ሾል ያለና ከወርቅ የተሰራ ነገር ራሳቸው ላይ አጥልቀህ የፀሐይ ጨረር ከላዩ ላይ ሲያርፍ፡በጣም የሚያብረቀርቅ ነገር ነበር:: በሰልፍ፡ እንድንቆም ስለተደረገና ብዙም ብርሃን ስላልነበረ ጳጳሰ በግልጽ አልታዩንም:: ንግግር አድርገውልናል:: ግን በመካከላችን ርቀት ስለነበረ የሚሉትን በግልጽ ለመስማት አልቻልንም::
ጳጳስ ማለት እንግዲህ ይኸው ነው መሰለኝ::»
እንግዳው ሲናገር ጳጳሱ የተበረገደውን በር ዘጉ:: መዳም ማግልዌር ተጨማሪ አንድ ሣህን ይዘው መጥተው ከጠረጴዛ ላይ አኖሩ፡፡
«መዳም ማግልዋር» አለ ጳጳሱ ፤ «አሁን ያመጡትን ሳህን እሳቱ
ከሚነድበት ቀረብ ኣድርገው ቢያኖሩት:: ከዚያም ወደ እንግዳው ዞር ብለው
«የውጪ አየር በጣም ይቀዘቅዛል፤ ሳይበርድህ አልቀረም ልጄ?» አሉት::
ጳጳሱ ረጋ ባለ መንፈስና በሚጋብገዛ ድምፅ ልጄ› ብለው በጠሩት ቁጥር የሰውዬው ፊት ፈገግ ይላል:: የተፈረደበት ወንጀለኛን ልጄ' ብሎ
መጥራት ማለት ባህር ላይ ቁጭ ብሎ በውሃ ጥም ሊሞት ለተቃረበ ሰው አንድ ብርጭቆ ንጹህ ውሃ እንደመስጠት ያህል ነበር፡፡ ሰው የናቀው ክብር ይጠማዋል::
«ፋኖሱ በቂ ብርሃን የለውም» አለ: ጳጳሱ::
መዳም ማግልዋር ገባቸው:: ወደ ጳጳሱ መኝታ ቤት ሄደው ሁለት
ከብር የተሠሩ ረጃጅም የሻማ ማብሪያ አመጡ:: ሻማ ለኩሰው ከሻማ ማብሪያው ላይ ካደረጉ በኋላ ከጠረጴዛው ላይ አስቀመጥዋቸው::
«አባቴ» አለ ሰውዬው፤ «ጥሩ ሰው ነዎት ፤ እኔን አይንቁኝም፤
አያንቋሽሹኝም:: ከቤትዎ ከማስጠጋት አልፈው በትህትና ያናግሩኛል::
ለእኔ ክብር ብለው ተጨማሪ ሻማ እንዲበራ አዘዙ፡፡ እኔም የሕይወት
ታሪኬን ሳልደብቅ ከየት እንደመጣሁና ምን ያህል የተሰቃየሁ መሆኔን
ገለፅኩልዎት::»
ከአጠገቡ ተቀምጠው የነበሩት ሰው ቀስ ብለው እጁን ይዘው
የሚከተለውን ተናገሩ፡፡
«ማን እንደሆንክ እንድትነግረኝ እያስፈልግም:: ይህ የእኔ ቤት
አይደለም፤ የክርስቶስ ቤት ነው:: እርሱ ማንኛውንም ባይተዋር ችግር፧ መከራና ስቃይ እንዳለበት እንጂ ማን እንደሆነ አይጠይቅም:: አንተ መከራን

👍24
ቀምሰሃል፧ ተርበሃል ፤ ተጠምተሃል:: ስለዚህ ቤቴ ቤትህ ነው:: ለዚህም እንድታመሰግነኝ አልፈልግም:: አስጠጋኝም ብለህ አትጠይቀኝ:: ይህ ቤት
ማረፊያ ለሚፈልግ ፤ ለተቸገረ እንጂ የማንም ቤት አይደለም:: ማነው መንገደኛው? ማነው እንግዳ? እመነኝና አንተ ከእኔ ይበልጥ ቤተኛ ነህ::
ከእዚህ ቤት ያለው ነገር ሁሉ ያንተ ነው፡፡ ያንተን ስም ማወቅ ለምን
ያስፈልገኛል? ከዚህም በላይ አንተ ሳትነግረኝ እኔ አውቄዋለሁ::»
ሰውዬው በመገረም አፉን ከፈተ::
«እርግጥ ነው?:: ማን እንደሆንኩ አውቀዋል?»
«አዎን» አሉ ጳጳሱ፤ «
ስምህ ወንድሜ ነው::»
«በቃ…. በቃ አባቴ» ሲል ሰውዬው ጮኸ፡፡ «ከዚህ ቤት ስገባ ጠኔ
ይዞኝ ነበር፡፡ ግን የደግነትዎ ብዛት ይሁን እኔ እንጃ! ምን እንደነካኝ
አላውቅም፧ ምንም ሳልበላ ያ ሁሉ ረሃብ ተወግዶልኛል፡፡»
ጳጳሱ እንደገና አትኩረው ከተመለከቱት በኋላ «ብዙ መከራና ስቃይዐደርሶብሃል» አሉት::
«እወይ! ያቺ ቀይዋ ጥብቆ ፤ የብረቱ ሰንሰለት፧ የእንጨቱ መኝታ!
ሙቀቱ፤ ብርዱ፤ ግርፋቱ፤ ከዚያ የነበሩ ባሮች.. ኧረ ምን ቅጡ፤ አንድ ቃል ቢተነፍሱ የጨለማ ቤቱ ፧ በታመሙ ጊዜ እንኳን ከዚያ ጨለማ ቤት በብረት ሰንሰለት ተጠፍር መኖሩ! ውሾች፧ ውሾች እንኳን ከዚያ የተሻለ ኑሮ ነው የሚኖሩት:: አሥራ ዘጠኝ ዓመት! አርባ ስድስት ዓመቴ ነው።
አሁን ደግሞ መታወቂያዬ የወንጀለኛ ነው:: ይኸው ነው ታሪኩ፡፡»
«ይሁን» አሉ ጳጳሱ፤ «የስቃይና የመከራን ቤት ለቅቀህ መጥተሃል፡፡ አሁን ግን ስማኝ ያንን አስፈሪና አሳዛኝ ቦታ በሰዎች ላይ ጥላቻንና ቁጣን
አሳድሮብህ የምትላቅቀው ከሆነ የሚታዘንልህ ሰው ነህ፡፡ በበጎ ፈቃድ! በጨዋነትና በሰላም የምትለቀው ከሆነ ግን ከሁላችንም ትበልጣለህ፡፡»
በዚህ ጊዜ መዳም ማግልዋር ገበታ መቅረቡን ያበስራሉ፡፡ ከቀረበው
ገበታ ሾርባ፤ ሥጋ፣ አይብና ዳቦ ይገኛል፡፡ የሚወጣ ቪኖም ነበር፡፡
ጳጳሱ የደስታ፣ የእርካታ ስሜትና «እንኳን ደህና መጣህ» የሚል
ፈገግታ እየታየባቸው «እራት ቀርቦአል» አሉ ወደ እንግዳው እየተመለከቱ፡፡
እንግዳወን ከቀኛቸው አስቀመጠት:: መድምዋዚዬል ባፕቲስታን
ከበስተግራቸው ተቀመጡ:: ጳጳሱ ማዕዱን ከባረኩ በኋላ ከሾርባው ለራሳቸው አወጡ፡፡ ሰውዬው ምግቡ ላይ ተረባረበ፡፡
«ገበታው ላይ ኣንድ ነገር የጎደለ መሰለኝ» አሉ ጳጳሱ በድንገት፡፡
መዳም ማግልግር ገበታ ሲያቀርቡ ያዘጋጁት ለጊዜው አስፈላጊ የነበሩትን ሦስት ከብር የተሠሩ ሣህኖችን ብቻ ነበር፡፡ በዚያ ቤት ባህል እንግዳ በመጣ ቁጥር ስድስቱንም ከብር የተሠሩ ሣህኖች ከገበታው ላይ
መደርደር ነበረባቸው:: ለጉራ ሳይሆን ሌላም እንግዳ ቢመጣ ደስ ይለናል በማለት ቸርነታቸውን ለማሳየት ነው::
መዳም ማግልዋር የጳጳሱ አስተያየት ስለገባቸው ወዲያው ከመቅጽበት የተቀሩት የብር ሣህኖች መጥተው ከእያንዳንዳቸው ትይዩ ተቀመጡ፡፡
ከእራት በኋላ ጳጳሱ እህታቸውን ተሰናብተውና አንድ ሻማ ለራሳቸው፣ አንድ ሌላ ደግሞ ለእንግዳው ለመስጠት ሁለት ሻማ ይዘው ተነሱ፡፡
ከዚያም «ልጄ ክፍልህን ላሳይህ» አሉት:: ሰውዬው ተከተላቸው::
ለእንግዳው የተዘጋጀው ክፍል በጳጳሱ መኝታ ቤት አልፎ ነበር
የሚገኘው:: እንግዳው ልክ ከጳጳሱ መኝታ ቤት ሲያልፍ መዳም ማግልዋር
እነዚያ የሚያማምሩ የብር ሣህኖች ከብፁዕነታቸው መኝታ ቤት ውስጥ ይገኝ ከነበረው ቡፌ ውስጥ እያስቀመጡ ስለነበር ዣን ቫልዣ ተመለከተ፡፡ዘወትር ማታ ማታ መዳም ማግልግር ከመተኛታቸው በፊት ሣህኖቹን
አጣጥበው ከቡፌው ውስጥ ነው የሚያስቀምጧቸው::
የእንግዳው አልጋ ከነበረበት ክፍል ደረሱ:: ሰው ያልታኛበት ንጹህ
ነጭ አንሶላ ነው የተነጠፈው:: ሰውዬው ሻማውን አስተካክሉ ከአንዲት አነስተኛ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠ፡፡
‹‹መልካም እንቅልፍ፤ ነገ ጠዋት ከመሄድህ በፊት ላሞች ስላሉን
ትኩስ ወተት ጠጥተህ ትሄዳለህ» አሉ ጳጳሱ::
«አመሰግናለሁ አባታችን» አለ እንግዳው::የምስጋና ቃሉን እንደደረደረ ወዲያው ከመቅጽበት እነዚያ ሁለት ሴቶች ከዚያ ሲኖሩ ውሃ ሊያደርጋቸው ይችል የነበረ ነገር ይናገራል:: ወደ
ጳጳሱ ዞር ብሉና ፊቱን ለዋውጦ በሻከረ ድምፅ ጮክ እያለ «አሁን ጥሩ ነው ፤ ከመኝታ ቤትዎ አጠገብ ነው ያስተኙኝ:: ለመሆኑ በነገሩ አስበውበታል?
ነፍሰ ገዳይ አለመሆኔን ማን ነግሮት?» ሲል ጠየቃቸው::»
«እግዚአብሔር ያውቃል» ሲሉ በእርጋታ መለሰለት::
ከዚያም ምንም ሳይጨነቁና ድምፅ ሳያሰሙ ከራሱ ጋር እንደሚነጋገር ወይም በጥሞና ጸሎት እንደሚያደርስ ሰው ከንፈራቸውን ካነቃነቁና
ሰውዬውን ከባረኩ በኋላ በቀጥታ ወደ ክፍላቸው ሄዱ፡፡
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከዚያ ቤት የነበረ ሰው ሁሉ እንቅልፍ ወሰደው::
እኩለ ሌሊት ላይ ዣን ቫልዣ ነቃ::
💫ይቀጥላል💫

👍34
#ንፋስ_ወዴት_ነህ_ቢሉት_ማርና #ወተት_ወዳለበት
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እማማ አረጋሽ ቤት ሩጫ ልናይ ተሰብስበናል፡፡ ልጃቸው ከውጭ አገር ትልቅ ቴሌቪዥን
ስላመጣችላቸው በሳቸው ቴሌቪዥን ማየት የሩጫ ጥም ይቆርጣል፡፡ መቸስ ቴሌቪዥኑን
ግድግዳ በሉት፡፡ የእማማ አረጋሽ ቤት ከሦስት ግድግዳና ከአንድ ቴሌቪዥን ነው የተዋቀረው
ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ባለቤታቸው አቶ ፈንታው ነፍሳቸውን ይማራቸው ዜና ለምን
በየቀበሌው እንደዞሩ ይሄን ዓለም ሳያዩ ሞቱ፤ ሳያልፍላቸው ሞቱ፡፡ “ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን በማያ ጊዜያቸው ሞቱ” ይላል ጎረቤቱ፡፡
ጀመረ ሩጫው ገንዘቤ ዲባባ፣ አበባ አረጋዊ ቴሌቪዥኑን እየሞሉ ደግሞ ራቅ እያሉ…
እኛም ግንዘብ…ገንዘብዬ…ገንዘባችን ሩጭ አሳያቸው…አይዞሽ” እያልን፣ ያው አበባ አረጋዊ ፈትለክ ብላ ወርቁን ወሰደችው፡፡ ያውም የስዊዲን ማልያ ለብሳ በስዊዲን ባንዲራ ተውባ ! ብዙዎቻችን ቀዝቀዝ ስንል እማማ ወለላ “እልልልልልልልልልልልልልል እሰይ እሰይ” አሉ (ጎረቤት ናቸዉ
“እንዴ ለስዊዲን እኮ ነው የሮጠችው ብንላቸው፣
“ይሁና ልጃችን ናት” አሉ፡፡
እማማ አረጋሽ ታዲያ፣ “አይ ወለላዬ አሁንስ እማማ ፅጌን መሰልሽኝ” አሉ፡፡
ስለ እማማ ፅጌ ለመስማት ጆሯችን ቆመ፡፡
“ማናቸው እማማ ፅጌ ?
እማማ አረጋሽ ስላነሷቸው ሴት ታሪክ አወጉን…
በድሮ ጊዜ እኛ ሰፈር እች አሁን ጋሽ እቁባይ ገፋ አድርገው ያጠሯት ቦታ ላይ አንዲት የእማማ
ፅጌ ድንጋይ የምትባል ጥቁር ድንጋይ ነበረች አጠገቧ ደግሞ የላስቲክ ቤት፡፡ አሁንም አጥሩ
ውስጥ ድንጋዩ አለ፡፡ ታሪክን ሲያጥሩት ያው አጥሩ ውስጥም ሁኖ ቢሆን ይጮሃል፡፡
እማማ ፅጌ አንዲት ልጅ ነበረቻቸው፡፡ መቼስ ቁንጅናዋ አይወራም፡፡ መልአክ፣ መልአክ በሏት፡፡
እንዲት ልጃቸው ናት፣ አባቷ አይታወቅም፡፡ እችው ባልቴት እናቷ እዚህች ድንጋይ ላይ ተቀምጠው
ድንችም ቲማቲምም እየቸረቸሩ አሳደጓት፡፡ በኋላ ህመሙም እርጅናውም ተጫናቸው ግማሽ
ችርችራ፣ ግማሽ ልመና በሆነ ሕይወት ይውተረተሩ ጀመር ::
መቼስ ልጅቱ መንገድ ዳር እየኖረች ልዕልት መሰለች፡፡የመንደሩ ሴቶች ጠርሙስ ሙሉ ቅባት ጨርሰው፣ ያማረ ለብሰው፣ ትኩስ በልተው ጠብ ያላለላቸው መልክ እዚህች መንገድ ዳር
ላስቲክ ከልላ በምፅዋት የምትኖር ልጅ ላይ ፈሰሰ፡፡ ፀጉሯ ተዘናፈለ፣ ዳሌዋ ሞላ ወንዱ ሁሉ
ዓይኑ ይቀላውጣት ጀመረ፡፡
አንድ ምሽት እማማ ፅጌ ኡኡ አሉ፡፡ መንደርተኛው ወደ ላስቲኳ ቤታቸው ተሰበሰበ፡፡ ልጅቱ
የለችም ጠፋች፡፡ መንደርተኛው እማማ ፅጌ ጋር በመሆን ሳምንት ሙሉ ፈለገ፡፡ የለችም፡፡ሀ
ቆንጆዋ፣ ባልቴት እናቷን ትታ ምጥ ትግባ ስምጥ እልም ድርግም አለች፡፡ ጎረቤቱ ተስፋ ቆርጦ
ወደ የራሱ ጉዳይ ሲመለስም ሚስኪኗ ባልቴት ግን ከዛች ቀን ጀምሮ ለአስራ አንድ ዓመታት
ታየች በተባለበት ተንከራተቱ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የቀራቸው ከተማ የተረፋቸው መንደር የለም፡፡
በየደረሱበት የዕለት ጉርሳቸውን እየለመኑ ፅንፍ የለሽ በሆነ የእናት ፍቅር ልጃቸውን ፈለጉ፡፡
በአስራ አንደኛው ዓመት ልጃቸው ውጭ አገር ኖራ እንደተመለሰችና አንድ ባለፀጋ ልታገባ ሰርጉ
እየተደገሰ መሆኑን ከሁነኛ ሰው ሰሙ፡፡ “አይ ልጄ ፈልጋ አጥታኝ ነው” አሉና ወደ አዲሳባ አቀኑ፡፡ አዲሳባ እንደገቡ እንድ ጥግ ላይ ከያዟት ፌስታል ሌት ቀን ብለው ያስቀመጧትንና ላለፉት አስራ አንድ ዓመታት ለብሰዋት የማያውቋትን ቀሚስ አውጥተው ለበሱ፡፡ ራሳቸውን አየት አደረጉና፣ “እመቤት መሰልኩ አይደለም እንዴ፣ ልጄንማ አላዋርዳትም አሉና ፈገግ አሉ፡፡
ልጃቸው አለች ወደተባለበት ቤት ሳያርፉ ጉዞ ጀመሩ፡፡ ቤተ መንግሥት የመሰለው ቤት
በሁለት ዘበኞች ይጠበቃል፡፡ “የልጄ ቤት” አሉ በኩራት ፊት ለፊት ቆመው፤ ከዛም ጠጋ ሲሉ
እግዜር ይስጥሽ አለ አንዱ ዘበኛ፣ እማ ፅጌ ይሄን ቃል ሺ ጊዜ ሰምተውታል የዛሬው ግን
ለየት አለባቸው፡፡
ሳቅ ሳቅ አላቸው፡፡ ይሄ ጥበቃ ከደቂቃዎች በኋላ ጎንበስ ቀና ሲልላቸው ታያቸው፣
“ልጄዋ እኔ እንኳን የመጣሁት ቢጣዬን ብዬ ነው”
“ቢጣ ማናት?”
“ልጄ ናታ እዚህ ቤት እንደምትኖር ነግረውኛል”
“እንደዛ የምትባል ሴት የለችም እዚህ እማማ”
ጠጋ አሉትና፣ “ሙሽራይቱ ማነው ስሟ
“እሜቴ ስማቸው ብሩክታዊት ነው
ግራ ተጋብተው ከግቢው በር እንደቆሙ ቢጣ ከሸበላ ባለቤቷ ጋር ውሃ በመሰለ መኪና ብቅ
አለች፡፡ ራሷ ናት፣ እናትና ልጅ ፊት ለፊት ተፋጠጡ፡፡ እናት ችለው መቆም አልቻሉም ጉልበታቸው ተብረከረከ፣ “ቢጣዬ ያይኔ አበባ " ብለው ወደ መኪናው በእንብርክክ ቀረቡ ልጅ ኮስተር አለች፣ የመኪናውን መስተዋት ዝቅ አደረገች፣ ጥቁር መነፅሯን ወደ ፀጉሯ ከፍ ራሷን መታ አድርጋ ውብ ፀጉሯን ወደ ጎን አለችና፤
“ምንድነው?” አለች ፊቷን አጨፍግጋ፡፡
ቢጣዬ..እናትሽ ስንከራተት ኖሬ ይሄው መጣሁልሽ፡፡ ሄድኩ አይባልም? ሜዳ ላይ ጣል አድርገሽ ማን አላት ብለሽ…"
“ማነህ ወደዛ ውሰዳት! የማንም ወፈፌ እየመጣ…እንሂድ ሃኒ አለች ቢጣ መኪናውን ወደ
ሚያሽከረከረው ሰው ዞር ብላ…፡፡
“ሃሃሃሃሃሃ ሃኒዩ አትበሳጭ አዲሳባ በነዚህ ዓይነት ፈጣጣዎች ነው የተሞላው ነዳጁን ሰጠና
ፈትለክ፡፡ እማማ ፅጌ ተንበርክከው ቀሩ፡፡ ራሳቸውን አይተው “ልጄ እስክትረሳኝ ተጎሳቁያለ
ማለት ነው” አሉ በልጃቸው አልፈረዱም፡፡
እስከሰርጉ ቀን ከግቢው ፊት ለፊት ካለች በረንዳ ላይ ዝናብና ፀሐይ እየተፈራቀባቸው ልት።
መኪና እንደልብስ እየቀያየረች ስትገባና ስትወጣ እየተመለከቱ በልጃቸው ምቾትና ታላቅ ደረጃ
መድረስ የራሳቸውን መከራ ረስተው ቆዩ፡፡ አንድ ቀን እናቴ ብላ እጄን እንደምትዘረጋላቸው
ተስፋ በማድረግ፡፡ (ልጅ ያላየቻቸው እየመሰለች ስታልፍ ቆየች ከአንድ ወር በላይ !!)
የሰርጉ ቀን፣ እናት ያችን ቀሚስ ከፌስታላቸው አወጡና ለበሱ፣ የኖሩባትን በረንዳ ላጠራረጉ
ፌስታላቸው ውስጥ ያስቀመጧትን ትንሽ ብልቃጥ አወጡና በረንዳው ላይ ባለ መስታወት ዓይናቸውን ተኳሉ፡፡
ከሰዓት ሙሽራዋ በነጭ ቀሚስ ተውብ በክፍት መኪና ስትደርስ ጎረቤቱ፡ ሰርገኛው ሲተረማመስ
መሃል መንገድ ላይ ከሰርጉ መኪና ፊት ለፊት እማማ ፅጌ እስከሰታቸውን አወረዱት፡፡
ሁሉ እብድ መስለውት ለአፍታ ትኩረቱን ወደ ባልቴቷ አዞረ፡፡ ከጫጫታው ኮሙዚቃው በላይ
የገዘፈ ድምፅ ከባልቴቷ ወጣ፡፡
መጣችም ሄደችመ ደሟ ከደሜ ስጋዋ ከስጋዬ የተጨለፈ ልጅ ቢጣዬ እቻት እንኳን ደስ ያለሽ በሉኝ ሙሽራው ልጄን አደራ" አሉና ፈታኝውን እዙረው ወደ በረንዳቸው ሄዱ ከኋላቸው የእድምተኛው ሳቅና ፈዝ እየተከተላቸው::
ሌሊቱን ሲጨፈር ሲደለቅ ታድሮ ጧት ያደረው ሰርገኛ ሲወጣ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት
የአስክሬን ማንሻ መኪና ከሰርጉ ቤት ፊት ለፊት ካለ ሱቅ በረንዳ ላይ የአንዲት ባልቴት ሬሳ
ሲያነሱ ታየ፡፡ ሬሳው ከተነሳበት በረንዳ ንፋስ እየገፋ ወደ ሰርግ ቤቱ በር የወሰደው አንድ
ጥቁርና ነጭ ፎቶ ዘበኛው እግር ስር ደረሰ፡፡ እናትና ልጅ የተነሱት ፎቶ ነበር፡፡
ወይ የሰው መመሳሰል.ልጅቱ እትዬን አትመስልም…” አለ ዘበኛው ለጓደኛው፣
እድያ እሱን ወዲያ ጥላህ ይሄን ያዝ!” ብሎ ከሰርጉ የተረፈ ቢራ ሰጠው:: ዘበኛው ፎቶውን
ጥሎ ወደ ቢራው ዞረ፡፡ ነፋሱ ጥቁርና ነጩን ፎቶ ወዳልታውቀ ቦታ እየገፋ ወሰደው::
እኛ ያሳደግናት በማር በወተት" የሰርግ ዘፈን ከግቢው ይሰማል፡፡

👍39❤6👎1😁1
#የመግቢያ_ፈተና
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
አስራ ሁለተኛ ክፍል ተፈትኜ ዩኒቨርስቲ የሚያስገባ ውጤት በማምጣቴ መንደሩ በደስታ አበደ
የበለጠ ወሬውን ያሞቀው ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መመደቤ ነበር፡፡
እሳቷ ኸዋና ከተማው ከባህሩ ዘላ ጥርቅም አለች ተባለልኝ፡፡ ወሬው ሁሉ ስለኔ ሆነ፡፡
“…የእቶ ዘለቀ ልጅ ይንበርስቲ በጠሰ"
“የትኛው"
“ይሄ ባለፈው በሬ ወግቶት የነበረው
“…ኧረረረረረረረ ሰው ሁሉ ሞኛሞኝ መስሎ፤ ለካስ እንዲህ ጥይት ነው ጃል
“ቀለም ዘልቆት ነው ፈዘዝ ያለው አይ…ጎበዝ ነው ከድሮውም አረ፡፡ወሬው ከመንደር መንደር
ተሰራጨ፣ በዛን ሰሞን የመንደሩ ሕፃናት አጥንተን እንሙት አሉ፡፡ ለወትሮው በቅስቀሳ ትምህት
ቤት የሚሄደው ውሪ ሁሉ፣ ሰዓቱ ሳይደርስ ደብተሩን አንጠልጥሉ ቱርርር እያለ ይበር ጀመር፡፡
ሁሉ ነገር ተሰናድቶ ድል ያለ የመሸኛ ግብዣ ተደረገና ቤተሰብ፣ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ ተሰባስቦ ጨዋታው እንደደራ፣ ከከተማ የመጣው አጎቴ ስለሁኔታው ያወጋኝ ጀመረ!
“መላኩ"
“አባት አጎቴ"
"ከሆነስ ሆነና የትኛው ስፍራ ነው የደለደሉህ ስድስት ኪሎ የማባለው ነው የካቲት 12 ሆስፒታል አጠገብ?
አይደለም እጎቴ አምስት ኪሎ የሚባለው ነው በቃ እዛ የአክስቴ ቤት ጎን ከዪኒበርስቲው ጋር ኩታ ገጠም ናቸው እንዲህ አጥር ነው የሚለያቸው አለች ከመንደራችን
ብቸኛዋ አዲሳባን ሁለት ጊዜ ሂዳባታለች የምትባለው አረጋሽ በእርግጥም ወደ አምስት ወር አዲስ አበባ ቆይታ ተመልሳለች አጎቴ ቀጠለ አምስት ኪሎ የት ነው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይቀርባል መላኩ የሚባለው እውነት ነው።
"ኧረ አጎቴ አይደለም"
“ተዉት በቃ አራት ኪሎ ነው” አለች አረጋሽ፡ ቀጠል አድርጋም፡ እዛው ዝቅ ብሎ እኮ ነው! ከዚህ እንደ አቶ አስራት ቤት ቢሆን ነው፡ አጎቴ ጉግሳ ቤቱ እዛው ስር ነው"
"መላኩ፣ ለመሆኑ አራት ኪሎ በመሆኑ ከፍቶኸል?" አለ እጎቱ ፊቴን እያየ ፡ ፡
እናቴ ፊቴ ላይ ያለውን ቅሬታ አንብባ እንዲህ አለች፡
"አይዞህ የኔ አንበሳ፡ እግርህ አዲሳባን ይርገጥ እንጂ ግዴለም ከአራት ጀምረህ አምስትም፡
ስድስትም ሰባትም ኪሎ ትገባለህ፡፡ ስንቅ ነው; እኔ እናትህ እያለሁ አትቸገርም አለች፡፡
"እናትህ እውነቷን ነው! የትም ብትሆን እንዳትሰጋ!” አለ አባቴ ፉከራ በሚመስል ድምፅ፡፡
አጎቴ ቀላል ሰው አይደለም፡ ጊዜው ራቅ ይበል እንጂ አዲሳባ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን
ሰንብቶ መጥቷል፡፡ እናም ባለችው እውቀት ስለ አራት ኪሎ እንዲህ አለ፡ “ኧረረረ ዋናው ጭንቅላቱ ላይ ነህና፣ ቤተ መንግስቱ ውስጥ በለው በቃ አለ ጋቢውን ወደ ትካሻው ከፍ እያደረገ፡፡
ግምታቸው ምርር ስላደረገኝ እንዲህ አልኩ፡ እኔ የተደለደልኩት ኮሜርስ የሚባል ቦታ ነው፡፡
አጉረመረሙ።
"እሱ ደሞ ወዴት ነው? አዲስ አባ ነው…ሲባልም አልሰማሁ” አለ አጎቴ፡፡
እኔም የት እንደሆነ አላውቅም እቴ፡ ብቻ እዛው አዲሳባ ኣንዱ ግድም ነው አልኩ፡፡
በዕርግጥም አራት ኪሎ፡ እምስት ኪሎ፡ ስድስት ኪሎ ካልተባለ ዩኒቨርስቲ ስለማይመስለኝ
ኮሜርስ ባሉት ነገር ከፍቶኝ ነበር፡፡
“ምንድነው የሚያስተምሩት?” አለ አባቴ፡፡
“የንግድ ስራ ይላል ወረቀቱ ላይ" አልኩ፡፡
“መድሃኒዓለም! ንግድ ምን ትምህርት ይላል? ይሄው እኛ ዝም ብለን እያቀላጠፍነው አይደለም!” አለ አባቴ፣ ታዋቂ የእህል ነጋዴ ነው፡፡
“እንዴዴዴዴዴ ባንክ የምትሰራው የአክስቴ ልጅ የተማረችበት ነው፡ ኧረ ጥሩ ተማሪ ቤት ነው ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ሞት ይርሳኝ! ያ በሪሁን፡ የእናቴ የእህት ልጅ፣ ቤቱ እዛው ነው አለች አረጋሽ፡፡
ጋሽ ዘለቀ የመንደራችን አስቂኝ ሽማግሌ፣ “አረጋሽ እንደው ያንች ዘመዶች ሁሉ ዩኒበርስቲ
እጥር ስር ብቻ ነው እንዴ ቤት የሚሰሩት?!” አሉና ሰዉን አሳቁት፡፡
ሁሉም እንደየአቅሙ የሰማውንም ያየውንም ስለእዲስ አበባ ይመከረኝ ጀመረ፡፡
የመጀመሪያው አጎቴ ነው፣
“መላኩ አዲሳባ እንዲህ ቀላል አገር እንዳይመስልህ ባህር ነው
ባህር…በዛ ላይ ሌባው አይጣል፤ ሴት ወንዱ ሞላጫ ነው፡፡ ሱፉን ግጥም አድርጎ መኳንንት
የመሰለው ሰው፣ ጠጋ ብሎ ከኪስህ ገንዘብህን ይከተልብሀል፡፡ ሴቷ ስትውረገረግ ልብህን ትሰልበዋለች፡፡ አንዳች አፍዝ አደንግዝ አላቸው፡፡ ጠንቀቅ ብለህ እንደወታደር ነው መኖር
የኣዲሳባ ሕዝብ ፈዛዛ አይወድም
አጎቴ አዲስ አበባ የሄደው ለሕከምና ነበር፡፡ ታዲያ ከቆየባቸው አርባ አምስት ቀናት
ሰላሳ ዘጠኙን ጥቁር አንበሳ ተኝቶ ነው ያሳለፈው፤ ሁለት ቀን የካቲት 12 ሆስፒታል...
አንድ ቀን ጦር ኃይሎች…ከህመሙ ጋር እየታገለ ስለአዲሳባ ይሄን ሁሉ ማወቁ ግሩም ነው፡፡
ዙሪያሽ ነበረች ቀጣይ መካሪ፣ “ወይ አዲስ አበባ…ሂሂሂሂ…የጉድ አገር እኮ ናት፣ መንገድ
ስትሻገር ነጭ ነጫን እየረገጥክ ነው፣ ሳት ካለህ መኪናው አያፈናፍንም…”
“ይሄ አዲስአባ ሰፊ አገር ነው አልተባለም እንዴ? የምን የማሪያም መንገድ ነው! ነጩን
ጥቁሩን እንዳሻው ይራመድ እንጂ” አለች እናቴ፡፡
ሂሂሂሂሂ ሕግ ነው፤ እንደኛ አገር ያገኙበት መርገጥ የለም እናቴ፣” ብላ አረጋሽ ቀጠለች፣
እና…መላኩ ዋናው ነገር…ዋናው የአዲስአባ ሴቶች አሳሳቾች ናቸው፤ ያንተ ዓይነቱን ሸበላማ
ካዩ ተከትለውህ ነው የሚመጡት፡፡ ኮስተር በል፣ ፊት አትስጣቸው! ኧረ በድንግሏ ሃፍረት የሚባል አያቃቸውም…”
አንድ ቀን የአክስቴ ልጆች ካማሪካ መጡና እራት እንብላ ብለው ሰብስበው ወሰዱን፡፡ ጉድ አየሁ…ጉድ ሴት እና ወንድ፣ ሴትና ወንድ ሁነው ነው የሚቀመጡት፡፡ አንድ ብቻህን ቁሪር ብሎ መቀመጥ ነውር ነው የተባለ ይመስል…፡፡ ሃዲያ አንድ ጊዜ ይጎርሱና መሳሳም፣ ደሞ ይጎርሱና መሳሳም..እማምላክን እህሉን በውሃ ሳይሆ በመሳሳም የሚያወራርዱት ነው እኮ
የሚመስሉት…ሁሁሁሁ” ብላ በሀፍረት ሳቀች፡፡
“ወላዲት አምላከ!ኸምግብ ቤቱ ነው የሚሳሳሙት?
ፈረሰኛው ጊወርጊስ!”
ሁሉም በወሬው ተገርመው ተንጫጩ፡፡
ቀጠለች አረጋሽ፣ “ደሞ ሴቶቹ እንዲቹ እርቃናቸውን ቁራጭ ልብስ ጣል አርገው እንዲቹ
እንደፈጠራቸው ነው የሚመናቀሩት…የቆዳቸው ልስላሴ…መስተዋት ነው የሚመሳስሉት…
አይበርዳቸውም ወይ? እላለሁ እኔማ አለች፡፡ …ገረመኝ!!
እና መላኩ፣ በሌላ ሌላው እንኳን አንተ አትመከርም፣ በሴቶቹ እንዳትፈትን አደራ!" ብላ
ምከሯን ጨረሰች፡፡
እንደጧት አዲሳባ ልሳፈር ሌሊቱን ሲያቃዠኝ አደረ፡፡ እራት እየበላሁ ይመስለኛል፣ የቆዳዋ ጥራት
መስተዋት የመሰለ ሴት እርቃኗን ጎኔ ተቀምጣ አንዴ በጎረስኩ ቁጥር የምትስመኝ ይመስለኛል፤
ልክ እንደማወራረጃ፡፡ ከዚሁ ፈተናው ጀመረኝ፡፡

👍37❤6😁2
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ሶስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
.....ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከዚያ ቤት የነበረ ሰው ሁሉ እንቅልፍ ወሰደው::
እኩለ ሌሊት ላይ ዣን ቫልዣ ነቃ::
ዣን ቫልዣ ገጠሬ ሲሆን የተወለደው ብሬ በመባል ከታወቀ ደሃ ቤተሰብ ነው። በልጅነቱ ትምህርት ቤት ገብቶ የመማር እድል ባለማግኘቱ መሐይም ነው ከአደገ በኋላ ከተማ ውስጥ በአትክልተኝነት ሥራ ጀመረ
ዣን ቫልዣ በተፈጥሮው ለሰው አሳቢ እንጂ አዛኝ አልነበረም፡፡ ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ነው የሞቱት:: እናቱ የሞቱት ታምመው ሲሆን አባቱ ከዛፍ ላይ ወድቀው ነው:: አባቱም እንደ እርሱ አትክልተኛ ስለነበሩ ዛፍ ለመከርከም
ከትልቅ ዛፍ ላይ ወጥተው ሳለ በድንገት ወድቀው ነው ሕይወታቸው ያለፈው:: ከቤተሰቡ መካከል በሕይወት የቀረች ከእርሱ ሌላ አንዲት እህት
ነበረችው:: የእህቱ ባል ሰባት ልጆች ጥሎባት ይጠፋል፡፡ ዣን ቫልዣን ያስጠጋችው እህቱ ስትሆን ባልዋ እስከጠፋ ድረስ ተንከባክባ ነበር ያሳደገችው::
ባልዬው ሲሞት የትልቁ ልጃቸው እድሜ ስምንት ዓመት ሲሆን የመጨረሻው ልጅ እድሜ አንድ ዐመት ነበር፡፡ ዣን ቫልዣ በዚያን ጊዜ 25 ዓመቱ ነበር::
እርሱ በተራው የልጆቹን አባት ተክቶ እህቱንና ልጆችዋን ይረዳ ጀመር::የወጣትነት ዘመኑን አዳጋችና አድካሚ ግን ብዙ ገቢ በማያስገኝ ሥራ ላይ ነበር ያሳለፈው:: በጊዜ ማጣትና ድኅነት ምክንያት በአፍላ ዘመኑ የከንፈር ወዳጅ እንኳን አልነበረውም:: እንዲያውም ከነአካቴው ለፍቅር ጊዜ
አልነበረውም ማለት ይቻላል፡፡
ማታ ማታ ከመሸ በኋላ ከቤቱ ተመልሶ ቃል ሳይናገር ያገኘውን
ይበላል፡፡ አንዳንድ ቀን ያቸን የምስኪን እራቱን ሲበላ እህቱ ከቀረበለት ምግብ ጥቂቱን እንደገና እየወሰደች ለልጆችዋ ትሰጥበታለች:: ይህ ሲሆን
በረጅም ፀጉሩ ፊቱን ሸፍኖ በዝምታ የተረፈችውን ይበላል:: ምንም ነገር እንዳልሆነ በመቁጠር ራሱን ለማታለል ይሞክራል:: ምርጫም አልነበረውም::
ዛፍ በሚገረዝበት ወራት በቀን እስከ 18 ሱስ ያገኛል:: ሥራ ሳይመርጥ ያገኘውን ይሠራል። እህቱም ትሠራለች:: ቢሆንም ራሳቸውን ያልቻለ ሰባት ልጆችን ማሳደግ ቀላል አልነበረም:: ገንዘቡ ስላልበቃቸው ቤተሰቡ
ችግር ቀስ በቀስ እያለ የሚያሳድደው አሳዛኝ ቤተሰብ ሆነ
የአንድ ዘመን ክረምት በጣም የከፋ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ዣን ቫልዣ ሥራ አ፣ልነበረውም:: በዚህ የተነሣ ቤተሰቡ የሚላስ ወይም የሚቀመስ ነገር ያጣል:: አንድ ቀን እሑድ ማታ የአንድ ዳቦ መጋገሪያ ቤት ባለቤት ሊተኛ ሲል የዳቦ ቤቱ መስታወት ሲሰበር ይሰማል፡፡ የሰውዬው መኖሪያ ቅጥር
ግቢው ውስጥ ስለነበር በጊዜ በመድረሱ በተሰበረወ መስታወት በኩል አንድ ሰው እጁን አሾልኮ ዳቦ ሲሰርቅ ያየዋል:: ሌባው ዳቦውን ይዞ ሮጠ፡፡የዳቦ ቤቱ መስታወት የሰበረው በቡጢ ስለነበር እጁ ይደማል:: ስለዚህ
ዳቦው የተወሰደው በሌባ ለመሆነ ሌላ ማስረጃ አላስፈለገም:: ሌባ
ሰውዬ ዣን ቫልገ ነበር፡፡
ይህ የሆነው በ1795 ዓ.ም መጨረሻ ነው:: ዣን ቫልዣ የተዘጋ ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ ሰብሮ ለመስረቅ በመሞከሩ «ወንጀለኛ ነው» ተብሎ ተፈረደበት:: ብያኔው ለአምስት ዓመታት በባርነት የመርከብ ቀዛፊ
ሆኖ እንዲሠራ ነበር፡፡
ዣን ቫልዣ አንገቱ በብረት ሰንሰለት ታስሮ ቱሉን ወደተባለ እስር
ቤት ተወሰደ:: ጉዞው ሃያ ሰባት ቀን ወሰደበት፡፡ የተጓዘው በእንስሳ በሚጎተት ጋሪ ነበር፡፡ ከተወሰነለት ሥፍራ እንደደረሰ ጥብቆ አለበሱት:: ያለፈው ታሪኩ ፤ ስሙ እንኳን ሳይቀር ተለወጠ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ስሙ ዣን ቫልዣ ሳይሆን ቁጥር 24 ሺህ 601 ሆነ::
ከዚያ በኋላ እህቱ ምን ሆነች? ሰባት ልጆችዋስ ምን ደረሱ? ስለዚህ ጉዳይ ራሱን ያስጨነቀ አልነበረም:: ጥቂት የዛፍ ቅርንጫፎች ከትልቅ ዛፍ
ግንድ ሲቆረጥ ማነው ስለቅርንጫፎቹ የሚጨነቀው?
አራተኛ ዓመቱን ሲያገባድድ ዣን ቫልዣ ከእስር ቤት አምልጦ
ነፃነቱን የማግኘት እድል አጋጠመው:: ከእንደዚያ ባለ አስፈሪ ቦታ ያለ ሰዎች ዘወትር እንደሚተባበሩ ሁሉ የእርሱም የሥራ ጓደኞች ረድተውት
አመለጠ፡፡ ለሁለት ቀናት በየጥሻውና በእርሻ ቦታ እየተሽሎከሎከ ቆየ፡፡
በሁለተኛው ቀን ግን ወደማታ እንደገና ተያዘ፡፡ ለ36 ሰዓት ያህል እህል አልቀመሰም:: እንቅልፍም አልተኛም:: ለማምለጥ በመሞከሩ የእሥራት ዘመኑን በሦስት ዓመት ፍርድ ቤቱ አራዘመበት:: በጠቅላላው ስምንት ዓመት ሆነበት ማለት ነው:: በስድስተኛው ዓመት እንደገና ለማምለጥ
ሞክሮ ሳይሳካለት ቀረ:: ማታ ስም ሲጠራ 'አቤት' ሳይል በመቅረቱ
ጥሩምባ ተነፋ፡፡ ማታውኑ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ከመርከብ ስር ተሸሽጎ አገኙት፡፡ ዘበኛው ሊይዘው ሲል ተናነቀው፡፡ ወንጀሉ እጥፍ ሆነ፡፡ ለማምለጥ
በመሞከሩና ዘበኛ በመተናነቁ ለዚህ ጥፋቱ አምስት ዓመት ተፈረደበት::
አሥራ ሦስት ዓመት ሆነ፡፡ በአሥረኛው ዓመት እንደገና ለማምለጥ ሞክሮ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ:: ለዚህም ሙከራው ሦስት ዓመት ተፈረደበት::አሥራ ስድስት ዓመት! በመጨረሻም በአሥራ ሦስተኛ ዓመቱ ይመስለኛል
እንደገና ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ ከአራት ሰዓት በኋላ እንደገና ተያዘ፡፡
ለአራት ሰዓት ከእስር ቤት በመጥፋቱ አሁንም አራት ዐመት ተፈረደበት:: ሃያ ዓመት! ዳቦ በመሰረቁ ከእስር ቤት የገባው በ1796 ዓ.ም ሲሆን ከአሥራ
ዘጠኝ ዓመት እሥራት በኋላ ግን ለማምለጥ ቻለ፡፡
መርከብ ቀዛፊዎች ከሚታሰሩበት ሲገባ እየተንቀጠቀጠና እያለቀሰ
ነበር:: ያን ሥፍራ ሲለቅ ግን ልቡ ደንድኖ ነበር የወጣው:: ከዚያ ሲገባ ተስፋ ቆርጦ ነበር የገባው፧ ሲወጣ ግን ተስፋ ቢስ ብቻ ሳይሆን ጨካኝም ሆኖ ነው የወጣው::
ታዲያ የዚህ ነፍስ ሕይወት ምን ይሆን!
ታሪኩን ለማውሳት እንሞክር እስቲ፡፡ የሰውዬው ችግር በሕብረተሰቡ የተፈጠረ ስለሆነ ይኸው ሕብረተሰብ እነዚህን ነገሮች አጢኖ መመልከት
ይኖርበታል፡፡
ቀደም ሲል እንዳልነው ዣን ቫልዣ አላዋቂ ነው:: ግን ደደብ አይደለም:: በተፈጥሮው ጭምት ነው:: ሰንኳላው እድሉ ደግሞ በይበልጥ እንዲጨምትና
እንዲያስተውል ገፋፍቶታል፡፡ ሲገረፍ፤ በሰንሰለት ሲጠፈር፤ ጨለማ ቤት ሲታሰር ሰውነቱ በድካም ብዛት ዝሏል፡፡ የሌሊት ቁር ሲያቆራምደው፤ የቀን ፀሐይ ሲያወራጨው፤ እንዲሁም ከእንጨት ላይ ተኝቶ ዘወትር
ከአሳብ ውስጥ እየዋኘ ከኅሊናው ጋር ሲሟገት የኖረ ሰው ነው::
ራሱን እንደ ፍርድ ቤት ስለቆጠረ ምርመራውን በመጀመሪያ ከራሱ
ይጀምራል:: ያለ አግባብ የተቀጣ የዋህና ቀና ሰው አለመሆኑን ኅሊናው ያውቃል:: ሕገ ወጥ ተግባር መፈጸሙን አይክድም፡፡ ምናልባት ያንን አንድ ዳቦ ቢለምን ኖሮ አይነፈግም ነበር ይሆናል፡፡ አዛኝ ወይም አሠሪ እስኪያገኝ
ድረስ ደግሞ መታገስ ነበረበት፡፡ ለእነዚያ የትም በትኖአቸው ለቀረው ምስኪኖችም ይኸው ይበጅ ነበር፡፡ ስለዚህ የፈጸመው ተግባር የሞኝ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ አንድ አርቆ ለማየት የማይችል ድሃ ዓለምን በጉልበት
አሸንፋለሁ ብሉ ቢጋፈጥ ወይም ችግሮችን በሌብነት እወጣለሁ ብሎ ቢታለል ስህተተኛነቱን ገሃድ ያወጣል፡፡

👍21❤3
ነገር ግን በአሳዛኝ ታሪኩ ውስጥ ስህተት የፈጸመው ዣን ቫልዣ ብቻ
ነው? እንደ እርሱ ያለ ትጉህ ሠራተኛ ሥራ አጥቶ መንከራተቱና ዳቦ ማጣቱ የሚያሳዝን አይደለም? ስህተት ፈጽሞ ጥፋተኛነቱን ቢያምንም
ቅጣቱ ግን ቅጥ ያጣና የአውሬዎች ብያኔ መሆነ አግባብ ነው? ወንጀለኛ ወንጀል ለመሥራት ካለው ፍላጎት ይበልጥ ሕግን አንተርሶ ቅጣትን የማክረር ባህርይ ትክክል ነው? የቅጣት ክብደት ወንጀልን ለማጥፋትና
በውጤቱ ሁኔታዎችን ለማሻሻል ሳይሆን የተበዳዮችን ስህተት ለማጉላትና በቸልተኞች ስህተት ለመቀየር፤ ወንጀለኞችን ከሚገባው በላይ ለማሰቃየት
አበዳሪን በባለዕዳ ለመለወጥ ከሆነ ይህ ተገቢ ነው?
ዣን ቫልዣ ይህን እያሰላሰለ «እውነቱ ቢወጣ ማነው ጥፋተኛ?» ሲል ራሱን ይጠይቃል፡፡
ሕብረተሰቡ አንድ ጊዜ በምክንያት ባልተደገፈ ግድየለሽነት፤ በሌላ
ጊዜ ደግሞ ርህራሄ በተለየው ዓይን እያየ በአባሎቹ ላይ ተመሳሳይ ፍርድ የመበየን ኃይል ቢኖረውም ሕብረተሰቡ ውስጥ እድል በሚያፈራው ሀብት
እጅግ ዝቅተኛ የሆነ ድርሻ የሚደርሳቸው ምስኪኖችን እጅግ አድርጎ ማሳደድ የጭካኔ አይደለም?
ዣን ቫልዣ እነዚህንና ሌሎችንም ጥያቄዎች እየጠየቀ በሕብረተሰቡ
ላይ ፈርዶ ብያኔ ይሰጣል፡፡ ብያኔው በሕብረተሰቡ ላይ የከረረ ጥላቻን ማሳደር ነበር፡፡ በሕይወት ዘመኑ የደረሰበት ፈተናና ስቃይ የሕብረተሰቡ ውጤት መሆኑን አመነ፡፡ ምናልባት አንድ ቀን እድል ቢገጥመው ሕብረተሰቡን
እንደሚበቀል ለራሱ ቃል ይገባል፡፡
የሕብረተሰቡ አባሎች ሕይወቱን አበላሹበት:: ከቁጡ ፊታቸው ሌላ
ያሳዩት ነገር አልነበረም፡፡ ማንም ቢሆን ለመላላጥ ካልሆነ በስተቀር ፍቅርን አላሳየውም:: ከሕፃንነቱ ማለት ከእናቱና ከእህቱ ከተለየ ጀምሮ ማንም ቢሆን ርህራሄ በተለየው በክፉ ቃል እንጂ በጥሞናና በሰላም ያነጋገረው
የለም፡፡ በስቃይ ላይ ስቃይ እየታከለበት በሄደ ቁጥር ሕይወት ጦርነት መሆኑን አመነ፡፡ በጦርነቱም እርሱ ድል እንደተመታ አወቀ፡፡ ከጥላቻ በስተቀር ሌላ የተማረው ነገር አልነበረም:: እስር ቤት እያለ ይህን ትምህርቱን
ለማጠናከርና ከዚያም ሲወጣ ይዞት እንደሚወጣ ወሰነ፡፡ ዣን ቫልዣ በዚህ ሳይቆም ለስቃዩ ምክንያት የሆነውን ሕብረተሰብ ለፍርድ አቅርቦ በእርሱ ላይ ብያኔ መስጠት ብቻ ሳይሆን ሕብረተሰቡን የፈጠረውንም አምላክ ጭምር አወገዘ፡፡
ዣን ቫልዣ ከታሠረበት ቱሉን ከተባለ ቦታ እንደ እርሱ ያሉ ምስኪኖች የሚማሩበት ትምህርት ቤት ራሳቸውን ለሌሎች መስዋዕት በሚያደርጉት ጥቂት ግለሰቦች ተከፍቶ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ ትምህርትና ንቃት ለተንኮልና
ለክፋት በር የሚከፍቱ ቢሆነም በአርባ ዓመቱ ትምህርት ቤት ገብቶ መጻፍና ማንበብ ተማረ::
እነዚያ 19 የስቃይና የባርነት ዘመን ይህ ነፍስ በአንድ ጊዜ እየሞተና
በሌላ ጊዜ ሕይወት እየዘራ ነው የኖረው:: የሕይወቱ ግድግዳ በአንድ በኩል ብርሃን ሲገባው በሌላ በኩል ጨለማ ቦርቡሮታል፡፡
ዣን ቫልዣ በተፈጥሮው ክፉ ሰው አልነበረም:: ከእስር ቤቱ ሲደርስ
ልቡ ቀና ነገር ነበር የሚያስበው:: እነዚያ ውስጥ እያለ ግን ሕብረተሰብን ጠልቶ እርሱም ክፉ ሰው እንደሆነ አመነ፡፡
አንድ መዘንጋት የሌለብን ነገር አለ:: ይኸውም ዣን ቫልዣ እስር
ቤት ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ በአካል ጥንካሬና ጉልበት እጅግ የላቀ እንደነበረ ነው:: ከባድ ስሪ በመስራት፤ ጠንካራ ሽቦ በመጠምዘዝ ክብደት ያለውን ነገር በማንሳት የአራት ሰዎች ጉልበት አይስተካከለውም አንድ ጊዜ የቤት ጥገና ሥራ እየተካሄደ ሳለ ተንጠልጣይ ግምብን ደግፎ ይዞ የነበረው ብረት ሾልኮ ግንቡ ሊፈርስ ሲል በአጋጣሚ እዚያ
የነበረው ዣን ቫልዣ ሰዎች እስኪደርሰለት ድረስ ብቻውን ግንቡን ደግፎ እንዳቆመ ይነገራል፡፡
ቅልጥፍውና የሰውነቱ መታዘዝ ጉልበቱን የሚያስንቅ ነበር::
የወንጀለኞች የዘወትር ሕልም የማምለጥ እቅድ ማውጣት ሲሆን ይህም አንዳንድ ጊዜ ጉልበት ከችሎታ ጋር ይሰጣቸዋል፡፡ በአእዋፍና በዝንቦች ዘወትር እንደቀኑ የሚኖሩት እስረኞች እንደ እነርሱ መብረር ይፈልጋሉ::
ዣን ቫልዣ የዚህ ዓይነት ቅናት ስላደረበት የማይሞክረው ነገር አልነበረም::ከማዕዘንና ከቋጥኝ ላይ እየዳሁ መውጣት፣ በጀርባ መንሸራተት፤ ከረጅም ከፍታ መዝለልና የመሳሰሉትን መፈጸም ለዣን ቫልዣ የእለት ተእለት
ተግባር ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እርሱ የሚሠራቸው ነገሮች ታምራዊ እንጂ ማንም ሰው የሚሠራው አይመስልም ነበር፡፡ አንዳንድ ቀን እንዴት እንደወጣ ሳይታወቅ ከፎቅ ቤት ጣራ ላይ ወጥቶ ይገኛል፡፡
ብዙ አይናገርም፡፡ ሁልጊዜም እንደተኮሳተረ ነው፡፡ ጥርሱን አሳይቶ አያውቅም፡፡ የእስረኞች የጭንቀት ድምዕ ስሜቱን ይነካው እንደሆነ እንጂ ሌላ ነገር ስሜት አይሰጠውም:: ለተመለከተውና ላጤነው ዘወትር ሳያቋርጥ
በአስፈሪ የአሳብ ባህር የተዋጠ ለመሆኑ ከፊቱ ላይ ይነበባል፡፡
ብቅ ጥልቅ በሚልና ባልተሟላ ሕይወት ታፍኖ በተያዘ እውቀት
አማካይነት በጭላንጭል ለማየት እንደሚሞከር ነፍስ አድን አስፈሪ የሆነ ግዙፍ አካል እንደተጫነው ይሰማዋል፡፡ ከዚያ ይቅርታቢስና አስፈሪ ከሆነው፤ ከተጫነው ነገር ለማምለጥ ኣንገቱን ቀና አድርጎ ዓይኖቹን ለመግለጥ
ሲሞክር ሥልጣኔ ብለን የምንጠራው ነገር ያስገኛቸው ነገሮች ፤ ሕጎች! የሰዎች አስከፊ ገጽታዎችና ሥራቸው ተከማችተውና ከቁጣና ከፍርሃት
ጋር ተደባልቀው በአሳብ ያያቸዋል:: ቀስ በቀስ ግን ከእርሱ እየራቁ ወደላይ አሻቅበው ወጥተው ከፊቱ ሲሰወሩ ይመለከታል፡፡
ዣን ቫልዣ በዚህ ዓይነት ተጨባጭ ዓለም አስፈሪ በሆነ መናፍስት ተሞልቶ ፧ አስፈሪው የመናፍስት ዓለም ደግሞ በእውን ነገር ተተክቶ በቃላት ሊገለጽ በማይችል ሁኔታ በአካሉ ውስጥ እየተቀረጸበት የኖረ ሰው ነው::
አንዳንድ ጊዜ እስር ቤት ውስጥ ሆኖ ድንገት ሥራውን አቁሞ ማሰብ ይጀምራል፡፡ ቀደም ሲል የነበረው ፤ አሁን ግን የዋዠቀው የማመዛዘን ችሎታው ጨርሶ እየጠፋ በእርሱ ላይ የደረሰው ሁሉ ከሥርዓት ውጪ!
በአካባቢው የሚያየው ነገር ሁሉ ያልሆነና የማይሆን ይመስለዋል፡፡ «ይህ ሁሉ ሕልም ነው» እያለ እርስ በራሱ ይነጋገራል:: ከእርሱ ጥቂት ርቆ የቆመውን የእስር ቤት ኃላፊን አተኩሮ ይመለከታል፡፡ ኃላፊው አንድ ዓይነት መንፈስ አንጂ ሰው ሆኖ አይታየውም:: ሆኖም ይህ መንፈስ በድንገት በዱላ ይጠልዘዋል፡፡
ለእርሱ የምናየው ዓለም እውንነት ኣጠራጣሪ ነው:: እንዲያውም
ከአነካቴው ለዣን ቫልዣ «ፀሐይ የለችም ፤ ክረምትና በጋ አይፈራረቁም፤ጠፈር የሚባል ነገር የለም» ቢባል ከእውነት የራቀ አይሆንም፡፡ ለእርሱ የአካሉ መጀመሪያና መጨረሻ የሰው ልጆች ያወጡት ሕግና የሰውን ዘር
በአጠቃላይ መጥላት ሲሆን የዚህም ውጤት ማን፣ ምን ሳይባል በሕይወት ያለን ማንኛውንም ፍጡር የማጥፋት ምኞት ነው:: የዚህ ዓይነቱ ጥላቻ
በተወሰነ ወቅት በመለኮት ኃይል ካልተገታ በስተቀር አደገኛ ነው:: ስለዚህ ዣን ቫልዣን «እጅግ አደገኛ ሰው» ብሎ መናገሩ ስህተት አልነበረም፡፡
ከዓመት ዓመት ይህ ሰው ቀስ በቀስ እያለ በይበልጥ በአደገኛ ሁኔታ እየደነደነና እየጨከነ ሄደ፡፡ ይህም ደንዳና ፍጡር የደረቀ ዓይን ነበረው::
ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እስር ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ኣንድ ቀን እንኳን እንባ አልወጣውም::
💫ይቀጥላል 💫

👍27❤1
#ቆጠራ_ላይ_ስለሆንን_መግባት
#ክልክል_ነው_ኮሚቴው !!
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
“ይሄ የተከበረና የታፈረ ቤተሰብ ተዋርዷል ! ተቃልሏል ! አገር ከመቃጠሉ በፊት አሁኑኑ ይሄን ጉድ አጣርታችሁ ንገሩኝ” አለ እባቴ እኔንና እህቶቼን ሰብስቦ፡፡ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀለው
ብስጭት አቤት ሲያስፈራ፡፡ አባቴ እንዲህ ሲሆን እይቼው አላውቅም፡፡ ጉዳዩን ከሰማን በኋላ ወዲያው ኮሚቴ ተቋቋመ…፡፡
የኮሚቴው አባላት፣
አብርሃም (ቅፅል ስም የለውም)… ትልቅ ወንድም፣ የቤተሰቡ ብቸኛ ወንድ ልጅና የኮሚቴው ሰብሳቢ፡፡
ኖአሚን (ቹቹ)የቤተሰቡ የመጀመሪያ ልጅ ለእረፍት ከአሜሪካ የመጣች፣ የኮሚቴው ጸሐፊ::
ሮዛ (ቢጢቃ)…የአብርሃም ታናሽ እህት የሁለተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ፣ ገንዘብ ያዥ፡፡
መቅደስ(ባርቾ) .…የአክስት ልጅ፣ ለአባቴ ጥሪ ለዚሁ ጉዳይ ከናዝሬት የመጣች…“ሙድ ያዥ እና አባል፡፡
ኮሚቴው በቀጥታ ተጠሪነቱ ለአባቴ ሲሆን፣ የስራ ዘመኑም ይህ ጉዳይ እስኪጣራ ብቻ ይሆናል።
አገር ሊያቃጥል የተፎከረበት ጉዳይ
አባቴ እሁድን የሚያሳልፈው በማንበብና በመፃፍ ነው፡፡ ሁልጊዜ የሚያነበው፣ የደጃዝማች ወንዱ በቀለ የጦር ውሎ የሚል መጽሐፍ ሲሆን የሚፅፈው ደግሞ ማመልከቻ !! ለቀበሌ ለክፍለ ከተማ…ለዕድር…ለጡረታ ሚንስቴር…
አንድ ቀን ታድያ ማመልከቻ ፃፈና ልክ
ፊርማው ላይ ሲደርስ እስክሪብቶው አቋረጠ፡፡
አብራሀም እቲ እስኪሪብቶ እምጣ” አለኝ እየተጣደፈ፡፡
አረ አልያዝኩም አባባ
ኤድያ የተማረ ሰው እንዴት እስኪሪብቶ ከኪሱ ይጠፋል፤ ጠመንጃ የሌለው ወታደር ማለት ነው ብሎ ከተማረረ በኋላ ህፃኗን እህቴን
(ራሴን አሞኝ ስለነበር የከባባ ንዝንዝ አልተመቸኝም፡፡)
ቢጡ እስኪሪብቶ እምጭልኝ አላት::
እሺ ብላ አሻንጉሊቷን ለእኔ አሳቅፋኝ ሮጠች(ፈጣን የኬጂ ተማሪ ነች)፡፡
እሰይ የኔ አንበሳ፡ ካንተ ትሻላለች“ አለ ወደኔ እያየ፡፡
ቆይታ ቆይታ ተመለሰችና፣ “አባባ ቀይ እስክሪብቶ ነው"
የሆነው ይሁን… አላት ስስቅ ወደኔ በብስጭት እያየ፡፡
ቆይታ ቆይታ መጣች፡ “ይሄው…" ያመጣችው እርሳስ ነበር፡፡
አይ…ይሄ ምን ያደርግልኛል? እስከሪብቶ ነው ያልኩሽ” አለ አሁን እሱም ሳቁ መጥቶ ነበር፡፡
ከተሳሳተብህ ታጠፋዋለህ ብዬ ነዋ ! ላጲስ አለው ይኸው::”
"ሂጂ ሀና መኝታ ቤት ፈልጊና አምጪ.አይ ቢጣዬ ፊርማ በላጲስ ቢጠፋ የብድር ሰነድ ላይ የፈረምነውን ስንት ጉድ ፊርማ ባጠፋነውና አገር እፎይ ባለች፡፡”
ቢጡ ወደ ሀና መኝታ ቤት ሮጠች (ሀና የ2ኛ ክፍል ተማሪ እህቴ ነች፡፡ ጨዋ፣ ጎበዝ ተማሪ…)
አቤት አባባ ሲወዳት ሀና ትሙት" ካለ አበቃ !!
ቢጡ የሀናን ቦርሳ ተሸክማ መጣች፡፡
ኤልከፈትም አለኝ አባባ፡፡"
አባባ ቀስ ብሎ ቦርሳውን ከፈተና እስከሪብቶውን ፍለጋ ጀመረ፡፡ ድንገት ትንሽ ፓኬት ነገር እጁ ላይ ዱብ አለች፡፡ ወደ ዓይኑ ጠጋ አድርጎ አያት፡፡ ራቅ ቀረብ…እንደገና ራቅ…
አሃ አብርሃም ! አጠራሩ ከመጥበቁ የተነሳ ስሜ የሚሰበር እስከሚመስለኝ፡፡
“አቤት አባባ"
ሂድ መነፅሬን አምጣልኝ…ቶሎ በል"
እ አልኩ ግራ ገብቶኝ፡፡
መነፅሬን አምጣ እኮ ነው የምለው… ጩኸቱ እስበረገገኝ፡፡
አባባ መነፅርህን እኮ አድርገኸዋል አልኩ፡፡ እጁን ወደ ዓይኑ ልኮ መነፅሩ ዓይኑ ላይ መኖሩን አረጋገጠና፣
“አንቺ ወደ ውስጥ ግቢ…" አላት ቢጡን በቁጣ
“እሺ” ብላ ሮጠች፡፡
“ይሄ ምንድን ነው?”
እኔም ደነገጥኩ፣ የድንገተኛ እርግዝና መከላከያ ፖስት ፒል፣ አባባ አውቆታል፡፡
እኔንጃ ምንድን ነው ?”
“ምን ትጠይቃኛለህ እንብበዋ"
አየት እድጌ፣ “መድኃኒት ነው…ያው ራሷን አሟት ምናምን ሊሆን ይችላል፡፡
“ዝም በል፡፡ እንካ ራሴን አመመኝ ስትል አልነበረም፣ እንካ ዋጠው የራስ ምታት ከሆነ፡፡ እህቶችህን ጥራ አለ በጩኸት፡፡ ሁሉም ተሰባሰቡ፡፡ ሀና የለችም ነበር፣ ላይብረሪ ብላ ሄዳለች
አባባ አጭርና ታሪካዊ ንግግር አደረገ (የሁላችንም ልብ በሐዘን ተነከቶ ነበር፡፡) ይሄን ሁሉ ሴት ሲያሳድግ የዚህ ዓይነት ውርደት ደርሶበት እንደማያውቅ፡፡ በተለይ ይሄን ጉዳዩ ልዩ የሚያደርገው፣ መድኃኒቱ ትልቅ ተስፋ በሚጥልባትና በሚኮራባት ልጁ ሀና ቦርሳ ውስጥ በመገኘቱ
መሆኑን በተጎዳ ድምፅ ከገለፀ በኋላ፣
'በጥብቅ የሀና መኝታ ቤት እንዲበረበር ትዕዛዝ ሰጠን፡፡
አብርሃም እህቶችህ ባሉበት ይሄን ጉዳይ አንተ ራስህ እየመራህ መርምር፤ ባይልልህ ነው እንጂ ቤተሰብ መሪ መሆኛህ ነበር…ወይ ውርደት !” ብሎ ጠረጴዛውን ደቃው፣ እንደ ፍርድ ቤት
መዶሻ የዕለቱ ስብሰባ መዝጊያ ተደርጎ ተወሰደ፡፡
የምርመራ ቡድኑ ከላይ በጠቀስኩት ኮሚቴ በማዋቀር (አባቴ ደውሎ የጠራት የአክስታችን ልጅ በማካተት) ወደ ሀና መኝታ ቤት ዘመተ፡፡ እናቴ የኮሚቴው አባል ልትሆን ብትጠይቅም
የእናት አንጀት በማዘንም ይሁን በሌላ ምክንያት ሊያዳላና የኮሚቴውን ስራ ተዓማኒነት ሊያሳጣው ይችላል በማለት ሳትካተት ቀረች፡፡
ኮሚቴው ገና ከጅምሩ ፀብ ጀምሮ ነበር፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እኔ እንደቀልድ የወረወርኳት ጥያቄ ነበረች፣ “ምናልባት ሀና ቦርሳ ውስጥ ከእናንተ አንድኛችሁ አስቀምጣችሁባት ይሆን? ሁሉተም
ተንጫጩ፡፡ እንደምንም አረጋግቻቸው (የሕዝብና የመንግስት ኃላፊነት ስላለብን) ስራችንን ቀጠልን፡፡
የሀኒ መኝታ ቤት ሲፈተሽ መሳቢያዋ ውስጥ ለቁጥር የሚያዳግቱ የወንድ ፎቶዎች ማግኘት አስደነገጠን፡፡ ጨዋዋ ሀኒ እየዞረች ፎቶ ማንሳት ጀምራ ይሆን ? ሲቀጥል የባሰው መጣ፡፡ " ወላ በጡት ማስያዣ፡ ወላ ከወንዶች ጋር:: ብቻዋን ሀይቅ ዳርቻ ላይ፡፡ ቆይ አዲስ አበባ ሀይቅ
አለ እንዴ ታዲያ የት ሄዳ ተነስታ ነው : በጀልባ ታይታኒከኛ ፎቶ)፡፡ ከቤት ወጥታ የማታውቅ ልጅ በምን ከንፍ በራ ሀይቅ ዳር ተገኘች ? ኧረ ጉድ ጭፈራ ቤት ማታ በሚኒስከርት (ሀናን በሚኒስከርት እየናት ከሚሉኝ፣ አንተን በሚኒስከርት አየንህ ቢሉኝ አምን ነበር ዓይኔ ይሆን መነፀሬ አምጣ አለ አባባ፡፡ እውነቱን ነው፤ ኧረ መነፅሬን አምጡ አለ ያልነው ሲጠፋ ልይበት ሆኖ አረፈው። እኛ ሳሎን ተቀምጠን፣ ዘራፍ የነሉሲ፣ የእነ ማንትስ
ልጆች የመይሳው ደም አባይን ገደብነው ስንል መኝታ ቤታችን፣ የታሪክ የወግና ባህል ግድባችን ፈርሶ አገር ተጥለቅልቋል
ጎበዝ መነፅራችንን ስጡን፡፡ 11፡30 ቤቷ የምትከተት ልጅ ጭፈራ ቤት።
የሀና ላፕቶፕ ተከፈተ (ብልግና ተከፈተ ቢባል ይሻላል፡፡) የወሲብ ፊልም ከአፍ እስከገደፉ፣ በቃ አባባን ካሁኑ መሰናበት አለብን ደም ግፊቱ… ታላቅ ታሪካዊ አደራ የተጣለብኝ ሰው ባልሆን ኖሮ ባለቀስኩ ነበር ግን ስራዬን ቀጠልኩ፤ የወንዶቹ ፎቶ እጅግ ከመብዛቱ የተነሳ ለሪፖርት እዲመች ይቆጠር ብለን መቁጠር ጀመርን፡፡ መኝታ ቤቱ በር ላይ፣ “ቆጠራ ላይ ስለሆንን መግባት ክልክል ነው ኮሚቴው !! የሚል ጽሑፍ ለጠፍን፡፡ ከፎቶዎቹ ኋላ ስማቸው ተፅፎል 43 ዘሩ.…43 ሚኪ 44 ፒተር ፈረንጅ ነው (የአክስቴ ልጅ ምራቋን ስትውጥ ጉሮሮዋ
ሲንገራገጭ ሰማሁት፡፡ ፈረንጁን የዋጠችው ነው የምትመስለው፡፡)
45 ሸምሰዲን (የሰፈራችን ባለሱቅ ) ትልቅ ደንበኛዬ ነው ትላለች ሀኒ፡፡ አይ ሀኒ አዚህ ሚስኪን ቤተስብ ላይ ቅኔ ስትዘርፍበት ነው የኖረችው፡፡ ግዴለም ! 46 ሀውቹባን (ቻይናዊ)፡፡ እቺ ልጅ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ጠርታ ነው እንዴ?
« ዊ መስት ኮል 911 ኢሚዲየትሊ” አለች ለዕረፍት ከአሜሪካ የመጣችው ትልቋ እህታችን ፊቷ በድንጋጤ አመድ መስሎ፣ እንባዋ በዓይኗ ሞልቶ፡፡ …ኮሚቴው በሳቅ ፍርስስስስስ፡፡ ከሳቂታ ኮሚቴ ጋር አብሬ በመስራቴ ኩራት ተሰማኝ፡፡

👍31❤2
ቢጡ ስንስቅ ሰምታን በሩን አንኳኳችና፣ “አብልሽ ኮሚቴው ውስጥ አስገባኝ አለችኝ፡፡ ሳቅ ሁሉ ደስታ የሚመስላቸው ሚስኪኖች ስንቱ ኮሚቴ ውስጥ ገብተው እንደቀለጡ ባወቀች…
"ቢጣ ተመለሽ! ማንበብ ትችይ የለ…የተለጠፈውን አታነቢም ?” አልኳት፡፡
እየጮኸች ማንበብ ጀመረች፣ ቆጠራ…
ላይ….ስ.….ለ…ሆ…ን…ን…አብልሽ እኔም እኮ ቁጥር እስከ መቶ እችላለሁ፡፡ ልቁጠርልህ ? ስማኝ…ዋን…ቱ…ስሪ ፎር ፋይፍ……” የፈረንጁን ፎቶ እያየሁ የቢጣን እንግሊዝኛ ሳዳምጥ፣ “ተከብበናል…" አልኩ ለራሴ፡፡ ምናልክ አብልሽ አልገባህም በአምሀሪክ ልቁጠርልህ ? አንድ…ሁለት…ሶስት…"
ለምሳ ስንወጣ ቢጣ በሩ ስር እንቅልፍ ወስዷት በእንቅልፍ ልቧ ትቆጥራለች፡ “አርባ ሾሽት ባ አራት ባ አምስት እንደገና ኮሚቴው ባሳቅ ፍርስስስስስስ፡፡ የራበው ኮሚቴ ሲስቅ ይደብራል…!

#ክፍል_አራት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
...ለአሥራ ዘጠኝ ዓመት እስር ቤት ውስጥ ሲቀመጥ ኣንድ ቀን እንኳን እንባ አልወጣውም::
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከቤተክርስቲያን አናት ላይ የተሰቀለው ሰዓት ስምንት ሰዓት ሲደውል ዣን ቫልዣ ከእንቅልፉ እንደገና ነቃ፡፡ ከአራት ሰዓት በላይ ጥሩ እንቅልፍ ወስዶት ተኝቷል፡፡ ድካሙ ሁሉ ወጣለት:: ለዚህን ያህል ጊዜ የእረፍት ሰዓት ኣግኝቶ አያውቅም፡፡ ዓይኑን ገልጦ በአካባቢው በሰፈነው ጨለማ
ዘልቆ ለማየት ሞከረ፡፡ ለማየት ባለመቻሉ እንደገና እንቅልፍ እንዲወስደው ዓይኖቹን ጨፈነ፡፡
ቀኑን ሙሉ አእምሮ በብዙ ነገሮች ተበጥብጦ ከዋለና የተለያዩ ነገሮች ከተመላለሱበት አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ጊዜ እንቅልፍ ሊወስድ እንደማይችል
ሁሉ ዣን ቫልዣንም ሊወስደው አልቻለም:: እንቅልፍ መጀመሪያ ሲመጣ ያዳፋል፡፡ ሁለተኛ ግን ቢለማመጡትም በዓይን አይዞርም:: እንደገና እንቅልፍ
ሊወስደው ስላልቻላ ማሰብ ጀመረ::
ብዙ ዓይነት አሳብ ከኀሊናው ውስጥ ገባ፡፡ ግን ሌሎቹን ሁሉ እየዋጠ እርሱ ብቻ እየተመላለሰ ያስቸገረው አንድ አሳብ ነበር፡፡ እነዚያ መዳም ማግልዋር ከጠረጴዛው ላይ የደረደሩዋቸው የሚያማምሩ ስድስት ከብር
የተሠሩ ሣህኖችና ትልቅ የብር ጭልፋ በዓይኑ ዞሩ፡፡ በጣም ወዷቸዋል:: አጠገቡ ከጳጳሱ ትራስጌ በኩል ቡፌ ውስጥ ሴትዬዋ ሲያስቀምጧቸው
አይቶአል፡፡ ከብር የተሠሩ ጥንታዊ ቅርስ በመሆናቸው ከነጭልፋው እስካ 200 ፍራንክ እንደሚያወጡ ያውቃል፡፡
ኅሊናው ከወዲያ ወዲህ እየዋለለ አንድ ሰዓት አለፈ፡፡ በአሳብ እየዋተቱ አንድ ሰዓት ማሳለፍ፤ ያውም ሌሊት በጨለማ ምን ያህል ረጅም እንደሆነ
የደረሰበት ያውቀዋል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ሰዓት ደወል ዘጠኝ ሰዓት መሆኑን አበሰረ:: ዓይኑን በድንገት ገልጦ ከአልጋው ዘልሉ ወረደ:: ስልቻውን በእጁ
እየዳሰሰ ፈለገና እንደያዘው ከአልጋው ጠርዝ ቁጭ አለ፡፡ ሳያውቀው ብዙ ተቀመጠ፡፡ ሰዓቱ በየአሥራ አምስት ደቂቃና ግማሽ ሰዓት ደወል እየደወለ ባይቀሰቅሰውማ እስኪነጋ ድረስ በተቀመጠ፡፡ ደወሉ «አይዞህ፣ በርታ» የሚለው መሰለው::
ተነስቶ ቆመ፤ ለመራመድ ግን አመነታ:: አንድ እርምጃ ወደፊት
ተራምዶ አዳመጠ፡፡ ሁሉም ነገር ጸጥ ብሎአል:: ቀስ ብሎ በጥንቃቄ ወደ መስኮቱ ተጠጋ፡፡ ሌሊቱ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ የተዋጠ ኣልነበረም:: ጨረቃ
በሩቁ ትታያለች:: ሆኖም ደመና ዞሮባታል፡፡ ደመና ጨረቃዋን በጋረዳት ቁጥር ቤቱ ትንሽ ጨለም ይላል፡፡ ውጪው በደምብ ሲታይ እቤት ውስጥ ግን ያንገዳግዳል፡፡ መስኮቱ አጠገብ ደርሶ መስኮቱን ሲመለከት በቀላሉ
እንደሚከፈት ስለተገነዘበ ከፈተው:: ሆኖም ኃይለኛ ብርድ ስለገባ መልሶ ዘጋው:: መስኮቱ መስታወት ስለነበር እንደተዘጋ ግቢውን ቃኘ፡፡ ግቢው
በአነስተኛ ግምብ መከለሉን ተመለከተ:: ከግምቡ ውጭ ረጃጅም ዛፎች ነበሩ፡፡ በሁለት ዛፎች መካከል ያለውን ርቀት ሲያጤን ርቀታቸው ተመሳሳይ
ሆኖ ስላየው ምናልባት ማዘጋጃ ቤቱ የተከላቸው ዛፎች መሆናቸውን በመገመት ከአጥሩ ውጭ ያለው መንገድ አውራ ጎዳና መሆን አለበት ብሎ ደመደመ::
ወደ ውሳኔ አሳብ እንደደረሰ ሰው በቆራጥነት ወደ አልጋው ተመለሰ፡፡ አቆማዳውን አንስቶ ከፈተውና ከውስጠ ምናምን ፈለገ፡፡ ኣንድ ነገር አውጥቶ
አልጋው ላይ አስቀመጠ፡፡ ጫማውን ኪሱ ውስጥ ከተተ፡፡ ኣልጋው ላይ ካስቀመጠው እቃ ሌላ የተቀሩትን እሳስሮ ትከሻው ላይ አኖረ፡፡ ቆቡን አጠለቀና ዱላውን ፈልጎ ከያዘ በኋላ ያሰረውን እቃ ከመስኮቱ ሥር
አስቀመጠው:: ወደ ኣልጋው ተመልሶ ያስቀመጠውን እቃ አነሳ:: እቃው ከአንድ ጫፍ እንደ ጦር የሾለ፣ ከሌላው ጫፍ ቋር ያለው ወፍራም ብረት ነበር፡፡ በዚያ ጨለማ ብረቱ ለምን ሥራ እንደተዘጋጀ ለመለየት አስቸጋሪ
ነበር፡፡ ዱላ ነው ወይስ እቃ ማንሻ? አይታወቅም:: ቀን እንኳን ቢሆን
የማዕድን ሠራተኞች መቆፈሪያ ነው ለማለት ያስችላል፡፡ በዚያን ጊዜ ቱሉን ከተባለ ቦታ አካባቢ በሚገኙ ከፍተኛ ኮረብታዎች ላይ ድንጋይ እንዲፈልጡ
የተፈረደባቸው ወንጀለኞች ይቀጠሩ ነበር፡፡ ወንጀለኞቹ ብዙውን ጊዜ የዚያን ዓይነት ብረት የመሰለ መፍለጫ ይይዛሉ፡፡
ዣን ቫልዣ ያን ብረት በቀኝ እጁ ያዘ፡፡ ትንፋሹን ውጦ በዝግታ
ተራመደ:: ወደ ጳጳሱ መኝታ ቤት አመራ:: ወደ በሩ ሲጠጋ አለመቀርቀሩን ተመለከተ፡፡ «አባታችን በራቸውን ሳይቆልፉ ነው የሚተኙት» አለ በልቡ፡፡
ዣን ቫልዣ ጆሮውን አቅንቶ አዳመጠ፡፡ ድምፅ የሚሉት ነገር
የለም:: በሩን ከፈት አድርጎ ሲፈራ ሲቸር በጣቶቹ ጫፍ ቀስ ብሎ ገፋው::ጥንቃቄው ከድመት ይበልጣል:: በሩ ምንም ድምፅ ሳያሰማና ለመንቀሳቀሱ
እንኳን በሚያጠራጥር ሁኔታ በዝግታ በመገፋቱ ከመጀመሪያው ይበልጥ ጥቂት ከፈት አለ፡
ለጥቂት ጊዜ ከበሩ አጠገብ ቆም አለ፡፡ አሁን ግን በይበልጥ ድፍረቱ
ስለተሰባሰበለት ከቀድሞ በበለጠ ጉልበት በሩን ገፋ አደረገው:: በዚህ ጊዜ የበሩ ማያያገዥ የዛገ ብረት ረዘም ያለ የሚሰቀጥጥ ድምፅ አሰማ፡፡
ልቡ የተሰነጠቀ መሰለው:: እንደ እንጨት ደርቆ ከቆመበት ሐውልት
ይመስል ሳይንቀሳቀስ ለጥቂት ጊዜ ተገተረ:: ለመነቃነቅ አቅም አነሰው ድፍረትም አልነበረውም:: ጥቂት ደቂቃዎች አለፉ:: በሩ ወለል ብሎ ተከፍቷል:: ወደ ክፍሉ ተመለከተ:: የተንቀሳቀሰ ነገር የለም:: አዳመጠ፤ የሚንቀሳቀስ ወይም ድምፅ የሚሰጥ ነገር አሁንም ከጆሮው ኣልገባም::
የበሩ ድምፅ ማንንም አልቀሰቀሰም ማለት ነው::
የመጀመሪያው አደጋ አለፈ:: ልቡ ግን በጣም ፈርቷል ፤ ሆኖም
አላወላወለም:: የፈለገውን ቶሎ ለመጨረስ ቁርጥ አሳብ አደረገ፡፡ በአንድ እርምጃ ከክፍለ ውስጥ ገባ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ጸጥታ ሰፍኖበታል፡፡ ዣን ቫልገዣ ከወንበርና ጠረጴዛ ጋር እንዳይጋጭ እየተጠነቀቀ ወደፊት ተራመደ::ጳጳሱ ክፍለ ውስጥ ጥግ ይዘው ተኝተው በኃይል ሲተነፍሱ አዳመጠ፡፡በድንገት ቆም አለ:: ከጳጳሰ አልጋ አጠገብ ደርሷል፡፡
ቶሉ የደረሰ መሰለው::አንዳንድ ጊዜ ተፈጥሮ የምንሠራውን ሥራ ለማራገብ ከእኛ ጋር ታብራለች:: ለግማሽ ሰዓት ያህል ደመና ጨረቃን በመጋረድዋ አካባቢው
ጨልሞ ነበር፡፡ አሁን ግን ልክ እንደተማከረ ሰው ዣን ቫልዣ ከጳጳሱ አልጋ አጠገብ እንደቆመ ደመና ለጨረቃ ቦታዋን ለቀቀች:: የጨረቃ ብርሃን በመስኮት በኩል ዘልቆ በመግባት ከጳጳሱ የገረጣ ፊት ላይ አበራ:: ጭልጥ
አድርጎ እንቅልፍ ወስዷቸዋል። የሌሊቱ ብርድ ከባድ ስለነበር ወፈር ያለ የሌሊት ልብስ ለብሰው በጀርባቸው ተዘርረው ነው የተኙት፡፡ ስንት ደግ ሥራ የሠራው ታማኙና ነዳያን የሳሙት እጃቸው ካልጋው ጠርዝ አልፎ ወደመሬት ተንጠልጥሎአል፡፡ ሌላው እጃቸው ከደረታቸው ላይ በማረፉ
የጵጵስና ቀለበታቸው ያበራል፡፡ እዚያ ተጋድመው ሲያይዋቸው መላ አካላቸው የተስፋ ፣ የደስታና የእርካታ ማኅደር እንደሆነ ይናገራል:: በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት የማይታይ ብርሃን ከግንባራቸው ላይ አርፎአል፡፡
የጨረቃው በሰማይ ላይ መንጣለል፤ የምድር በከፊል የተኛች መምሰል ፤ የግቢው አትክልት እርጭ ማለትና የቤቱና የዚያች ሰዓት ፀጥታ እኚህ መለኮት የቀረባቸውን ሰው «አክብሩ አትድፈሯቸው» የሚያሰኝ
ነበር፡፡ ዓይናቸውን ጨፍነው እንደተኙ የነበራቸው ግርማ ሞገስና ለተስፋ ምንጭ የሆነውና በጨርቅ ያልተሽፈነው ግንባራቸው ሲያዩት በፍርሃት የሚያርበደብድ ነበር፡፡

👍19❤1
በዚህ የተነሣ ዣን ቫልዣ በፍርሃት ተውጦና ሐውልት መስሎ
ድምፅ ሳያሰማ ከጥላ ሥር ባለቋሩን ብረት ይዞ ከእኚህ ደግ ሰው ፊት ቆሞአል፡፡ በሕይወቱ እንደዚያ ያለ ሁናቴ ገጥሞት አያውቅም፡፡ ይህም በይበልጥ እንዲፈራ አደረገው፡፡ የተብከነከነና የተቅበጠበጠ ሕሊና ክፉ
ተግባር ለመፈጸም ከዚያ ቆሞ ሳለ ንጹሑ ነፍስ እንቅልፍ ወስዶት ከእዚያ ተኝቷል፡፡
ጥቂት ቆሞ ሁኔታውን ከተመለከተ በኋላ በግራ እጁ ቀስ ብሉ ቆቡን
አወለቀ፡፡ ከዚያም ቆቡን ለማውለቅ ያነሳውን እጁን አሁንም በዝግታ አውርዶ እንደገና ዣን ቫልዣ ማሰላሰል ጀመረ:: ቆቡን በግራ እጁ፣ የብረት ዱላውን በቀኝ እጁ ይዟል፡፡ ጳጳሱ ግን ከተኙበት ነቅነቅ አላሉም፡፡
በድንገት ዣን ቫልዣ ቆቡን አጠለቀ፡፡ ከዚያም ወደ ጳጳሱ ሳያይ ከአልጋቸው እልፍ ብሎ ወደ ነበረው ቡፌ ሄደ፡፡ የቡፌው ቁልፍ ከላዩ ላይ ስለነበር ከፈተው:: በመጀመሪያ ያየው እነዚያን ከብር የተሠሩ የሚያማምሩ ሣህኖችን ነበር፡፡ ሳህኖቹን ከነጭልፋው ይዞ ወደ በሩ አመራ:: የእግሬ ኮቴ
ይሰማል በማለት ብዙም ሳይጨነቅ በኃይል እየተራመደ ከክፍሉ ወጥቶ ሄደ፡፡ የብር እቃዎቹን ከአቅማዳው ውስጥ ከተተ:: በኣትክልቱ መካከል
አልፎ ሄዶ ኣጥሩን በመዝለል ከግቢው ከወጣ በኋላ መንገዱን ቀጠለ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በጠዋት ፀሐይ እንደ ወጣች ጳጳሱ ከአትክልት ውስጥ ይንሸራሸራሉ፡፡
መዳም ማግልዋር እየሮጠ መጡ፡፡
«አባታችን ሰውዬው ሄዷል፤ እነዚያ የብር ሣህኖችም ተሠርቀዋል፡፡»
ሴትዮዋ ይህን ሲናገሩ ከአትክልቱ ውስጥ የእግር ኮቴ ተመለከቱ፡፡
ኮቴውን ተከትለው ግምቡን ሲያዩ ከአንድ ፊት መሸረፉን ተገነዘቡ፡፡
«አባታችን አዩ፤ በዚያ በኩል ነው የወጣው:: በአጥር ዘልሉ ነው
የሄደው:: ምን ዓይነት ቀበኛ ነው:: ሣህኖቻችንን ሠርቆ ነው የሄደው፡፡»
ጳጳሱ ለጥቂት ጊዜ ዝም አሉ:: ከዚያም አንገታቸውን ቀና አድርገው ሴትዮዋን እየተመለከቱ «ጥንትም ቢሆን እኮ ሣህኖቹ የእኛ ነበሩ እንዴ?» ሲሉ ጠየቁ፡፡
መዳም ማግልዋር አልመለሱም:: ለጥያቄያቸው መልስ ስላላገኙ
ጳጳሱ ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡
«መዳም ማግልዋር፤ እነዚህን ሣህኖች የነዳያን ሀብት ሆነው ሳለ ለረጅም ጊዜ ያለ አግባብ አስቀመጥናቸው:: ይህ ሰው ማነው? ከነዳያን አንዱ ነው፡፡»
«ይገርማል» አሉ መዳም ማግልዋር፡፡ «እኔም ሆንኩ እህትዎ ግድ የለንም፤ ለእኛ እንደሆነ ሴቶች እንደመሆናችን ለውጥ አያመጣም:: ግን
ለብፁዕነትዎ ገበታ ሲቀርብ አሁን የትኛው ሳህን ሊቀርብ ነው?»
ጳጳሱ በመገረም ሴትዮዋን አተኩረው ተመለከቱ፡፡
«እንዴት እኮ! የቆርቆሮ ሣህን ቢሆን እንኳን! ሌላ ሣህን የለንም
ማለት ነው?» ሲሉ ጠየቁ፡፡
መዳም ማግልዋር ትከሻቸውን ነቀነቁ፡፡
«የቆርቆሮ ሣህን እኮ ሽታ ያመጣል፡፡»
«እንግዲያውማ ከብረት የተሠራ ሣህን ካለ እርሱ ሊሆን ይችላል።»
መዳም ማግልቀር ፈገግ ብለው «እሱም ቢሆን ብረት ብረት ማለቱ
ይቀራል!» አሉ::
«እንግዲያውማ» አሉ ብፁዕነታቸው፤ «የእንጨት ወይም የሸክላ ሣህን መፈለግ ነዋ!»
ከጥቂት ጊዜ በኋላ በአለፈው ሌሊት ዣን ቫልዣ አብሮ ከቀረበበት ጠረጴዛ ላይ ቁርስ ተዘጋጀ:: ቁርስ እየበሉ ምንም ዓይነት አስተያየት ላልሰጡት እህታቸውና ለሚያጉረመርሙት ለመዳም ማግልዋር ዳቦ ሻይ
ውስጥ ነክሮ ለመብላት ማንኪያ ወይም ሹካ የማያስፈልግ መሆኑን በመግለጽ ሳቅ እያሉ ይናገራሉ::: ወዲያው እህትና ወንድም ቀና ብለው ሲተያዩ በር ይንኳኳል::
«ይግቡ» አሉ ጳጳሱ::
በሩ ተከፈተ:: ሦስት የሚያስፈሩና ለቤቱ እንግዳ የሆኑ ሰዎች ገቡ::
ሰዎቹ የአራተኛ ሰው አንገት ጨምድደው ይዘዋል:: ሦስቱ ሰዎች ፖሊሶች ሲሆኑ አራተኛው ሰው ዣን ቫልዣ ነበር፡፡
አዛዡ ወደፊት ቀደም ቀደም ብሎ በወታደር ደምብ መሠረት ለጳጳሱ
የክብር ሰላምታ ሰጠ፡፡
«ብፁዕነትዎ» አለ፡፡
እስከዚያች ደቂቃ ድረስ አኩርፎ ዝም ያለውና ያቀረቀረው ዣን
ቫልዣ ያዛዡን ንግግር አቋርጦ ጣልቃ በመግባት እፍረት እየተሰማው አንገቱን ቀና አደረገ፡፡
«አባታችን፤ የደብር ኣለቃ ብቻ አይደሉማ!» ሲል ተናገረ::
«ዝም በል!» አለ ፖሊሱ፡፡ «አባታችን እኮ ናቸው:: የብፁዕነታቸውን ማዕረግ እንኳን አታውቅም?»
ብፁዕነታቸው እድሜያቸው በፈቀደው መጠን በቶሎ ከገበታው ብድግ ብለው ወደ ሰዎቹ ጠጋ አሉ::
«መጣህ» አሉ ወደ ዣን ቫልዣ እየተመለከቱ፡፡ እንደገና በመገናኘ
ታችን ደስ ብሎኛል፡፡ ግን የሻማ ማብሪያዎችንም ጭምር ሰጥቼህ አልነበረም እንዴ፧ ምነው ተውካቸው? እነርሱም እኮ ከንጹህ ብር የተሠሩ ናቸው:: እስከ 200 ፍራንክ ያወጡልሃል፡፡ ከሣህኖቹ ነጥለህ ምነው አስቀረሃቸው?
ሲሉ ጠየቁት::
ዣን ቫልዣ አፉን ከፍቶ ብፁዕነታቸውን አፍጥጦ ተመለከተ፡፡ የሚሰማው ነገር እውነት መሆኑን ማመን አቃተው::
«አባታችን» አለ አዛዡ፣ «እንግዲያውስ ይህ ሰው ያለው ትክክል ነው ማለት ነዋ? እኛ ስንይዘው እንደገመገምነው የሚሸሽ ሰው ዓይነት መስሎን
ነበር፡፡ ስለዚህ ተጠራጥረን ያዝነው:: እነዚያን የብር እቃዎች መያዙ ደግሞ በይበልጥ አጠራጠረን፡፡»
«እና ተነጋግራችኋላ!» አሉ ጳጳሱ ፈገግ ብለው፤ «ትናንት ሌሊት ካስጠጉት ከአንድ ሽማግሌ መነኩሴ የተሰጠው እቃ ለመሆኑ ገልጾላችኋላ!
እናንተ ግን በመጠራጠር ይዛችሁት መጣችሁ! ተሳስታችኋል፡፡ እቃው
የራሱ ነው፡፡»
«እንዲህ ከሆነማ ሰውዬን በነፃ ልንለቅቀው እንችላለን» አለ አዛዡ፡፡
«ያለ ጥርጥር» ሲሉ ብፁዕነታቸው መለሱ፡፡
ፖሊሶቹ ዣን ቫልዣን ለቀቁት:: ወደኋላ አፈገፈገ፡፡
«አሁን በእርግጥ በነፃ ሊለቁኝ ነው?» ሲል ዣን ቫልዣ እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆነ ድምፅ አጉረመረመ:: ቅዠት መሰለው እንጂ በውኑ እንደሆነ
አላመነም::
«አዎን፥ ልትሄድ ትችላለህ ፤ ነገር አይገባህም» አለ ፖሊሱ፡፡
«ወዳጄ» አሉ ጳጳሱ፤ «ከመሄድህ በፊት እነዚያም የሻማ ማብሪያዎች
የአንተ ስለሆኑ ውሰዳቸው::»
ጳጳሱ ወደ ምግብ ጠረጴዛ ሄደው የሻማ ማብሪያዎችን አምጥተው
ለዣን ቫልዣ ሰጡት:: ሁለቱ ሴቶች ተገርመው ከእዚያው ከገበታ ላይ
አቀርቅረው ቀሩ፡፡ ቃል አልተነፈሱም::
ዣን ቫልዣ ሰውነቱ ርድኦ መቆም ተሳነው:: የሻማ ማብሪያዎቹን
ተቀበለ፡፡ ፊቱ የኣውሬ መሰለ፡፡
«አሁን» አሉ ብፁዕነታቸው በሰላም መሄድ ትችላለህ፡፡» ከዚያም ብፁዕነታቸው ፊታቸውን ወደ ፖሊሶቹ ኣዙረው፤ «ልጆቼ፤ ወደ ሥራችሁ ልትመለሱ ትችላላችሁ» አሉ:: ፖሊሶቹ ወጥተው ሄዱ፡፡
ዣን ቫልዣ ራሱን ስቶ ከመሬት እንደሚዘረር ሰው ተንገዳገደ ፤ ግን አልወደቀም:: ጳጳሱ ወደ እርሱ ጠጋ ብለው ዝቅ ባለ ድምፅ የሚከተለውን ተናገሩ፡፡
«አትርሳ፣ ገንዘቡን እውነተኛና ታማኝ ሰው ለመሆን እጠቀምበታለሁ ብለህ ቃል የገባኸውን እስከ እድሜ ልክህ እንዳትረሳ፡፡»
ዣን ቫልዣ መቼ ቃል እንደገባላቸው ማስታወስ አቅቶት በመደናገር ዝም ብሎ ቆመ:: ጳጳሱ «ቃል የገባኸውን አትርሳ» በማለት አጥብቀው ጠይቀውታል፡: ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡ የእኔ ልጅ ዣን ቫልዣ ፤ ከእንግዲህ
አንተ ለጥፋት ዓለም ሳይሆን ለደግነት የተመረጥህ ነህ:: ነፍስህን ነው የምገዛልህ:: የአንተን ነፍስ የምሰጠው የሁሉም በላይ ለሆነው ለአንድ
አምላክ ነው::»
ዣን ቫልዣ አገር ጥሎ እንደሚሸሽ ሰው እግሬ አውጪኝ በማለት

👍20❤3😁2
ከተማውን ጥሎ ወጣ፡፡ ከተማውን ለቅቆ ገጠር እስከገባ ድረስ እየተጣራ ነበር የሚሄደው፡፡ ወዴት እንደሚሄድ ሳያስተውል መንገድ እንደመራው ዝም እያለ ተጓዘ፡፡ ከነጋ ጀምሮ እህል አልቀመሰም:: ሆኖም የረሃብ ስሜት አልተሰማውም፡፡ ቁጣ ቁጣ ብሉታል፡፡ በማን ላይ ወይም በምን ምክንያት እንደተቆጣ ግን አያውቅም:: የሚቀጥለው ምን ይሆን ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡
የገጠር አየር የልጅነት ጊዜውን አስታወሰው:: የልጅነት ዘመኑን ካስታወሰ በጣም ቆይቶ ነበር፡፡ ከዚያም ብዙ ኣሳቦች ተፈራረቁበት፡፡».....

👍11❤1
#እብድ_እና_ዘመናይ
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
ጓደኛችን አመሃ አበደ !!
ድንገት ነው እንደ ትንታ፣ እንደ ሳል፣ እንደ ንጥሻ እብደቱ ያመለጠው፡፡ እቺ አይምሯችን ግን ከንቱ ናት ለካ! ደርሰን እናሞካሻታለን እንጂ አንዳንዴ እንዲህ ሜዳ ላይ ጣጥላን ትወፍፋለች ለካ፡፡
ሰው ከንቱ !! አይምሯችንን ልንጠብቃት ይገባል፣ አለች ስንላት ገደል ገብታ ገደል ታስገባናለች፣ወይኔ አምሽ! ምነው ሴት ሆኖ ተፈጥሮ በነበር !?..ይሻለው ነበር ! ባንዴ ከማበድ በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ማበድ !
የስነ አእምሮ ጠበብት ሴቶች የማበድ እድላቸው ከወንዶች ጋር ሲነፃፀር በጣም አነስተኛ ነው፤ ምክንያቱም ሴቶች ብስጭታቸውን፣ መከፋታቸውን በእንባ ይሸኙታል፤ በጩኸት ይሸውዱታል፤
ወንዶች ግን አፍነው ስለሚይዙት ውስጣቸው ይጠራቀምና ድንገት ገንፍሎ ጉድ ያደርጋቸዋል ይላሉ፡፡ በነጋዴ ቋንቋ ስንገልፀው ሴቶች የሚያብዱት በችርቻሮ ሲሆን ወንዶች ግን በጅምላ
ነው እንደማለት፡፡
ጓደኛችን አመሃ ኮሌጃችን ውስጥ ወላ ባለባበስ፣ ወላ በትምህርት የሚደነቅ ሲበዛ ዝምተኛ ልጅ ነበር፡፡ ሀይ፣ ባይ ነው ቅፅል ስሙ፡፡ በቃ ስንገናኝ ሃይ ይላል፡፡ አንዲት ቃል ሳይተነፍስ ስንለያይ፣ ባይ ! አምሻ ልዩ ልጅ ነበር፡፡ ምድረ ኩታራ ከየዶርማችን ሱክ ሱክ እያልን ወደ
ክላስ ስንጣደፍ አምሃ ፀዳ ባለ ፓጃሮ መኪናው ከተፍ ይላል፡፡ እንግዲህ እኛ ባየነው ነገር ሰላምን የምንለካ የዋህ ከተሜዎች የአመሃ ተድላ እና ሀብት ተደማምሮ እንኳን እብደት ድብርት
አመሃ አጠገብ ያልፋል ብለን በምን አባታችን ጠርጥረን፡፡ “ፀጉራም ውሻ አለ ሲባል ይሞታል እንዲሉ አበው በሀብት ፀጉር የደለበ የመሰለን አመሃ 'አለ' ስንለው ለቀቀ !!
አመሃ እና እኔ ጓደኞች ነን፡፡ እንደውም አመሃ ሁለት ጓደኛ ብቻ ነው ያለው፤ እኔና ናትናኤል የሚባል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አብረው ሳንፎርድ የተማሩ ልጅ፡፡ በቃ ሌላ ጓደኛ የለውም፡፡ያው ፍቅረኛው እንዳለች ሆና !! ቤቱ ሁሉ ወስዶ ከሞልቃቃ እናቱ ጋር አስተዋውቆኛል፡፡
እንደ አመሃ እናት በጣም አጭር ጅንስ ቁምጣ የለበሰች ወጣት እናት ከዛ በፊትም ከዛ በኋላም አይቼ አላውቅም፡፡ የእግሮቿ አረዛዘም፣ ሰበር ሰካ አረማመዷ ወጣት ይፈትናል፡፡ ከላይ ጣል
ያደረገችው ስስ ቦዲ ነገር የጡት መያዣዋን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ አምሃ ሁለታችንን ትቶን ወደ ውስጥ ሲገባ፣ “የዛሬ ልጆች ቆንጆዎች ናችሁ” አለችኝ፡፡ አነጋሯ እንደ ማስቲካ ይለጠጣል፤
ከአስተያየቷ ጋር ተዳምሮ አድናቆቷ እናታዊ አድናቆት አልመስልህ አለኝ፡፡ የለም የለም እቺ ሴት የእናት ቀለም የላትም፡፡
ፊት ለፊቴ ተቀምጣ አንድ እግሯን ሶፋው ላይ አውጥታ በረዥም የእጁ ጣቶች ጉልበቷን በስሱ እንደማከክ አደረገችው፡፡ ቁምጣዋ ተሰብስቦ የተላጠ ብርቱካን የመሰለ የደላው ሰውነቷን አጋለጠው፡፡ ጥርት ያለ የታፋዋ ቆዳ ላይና የሚያማምሩ የእግሯ ጣቶች ላይ ዓይኔን አለማሳረፍ አልቻልኩም፡፡ በዛ ላይ ውስጥን ሰርስሮ የሚያይ የሚመስል አስተያየቷ “ምነው ባልመጣሁ!"
አስባለኝ፡፡
በምድር ላይ ያሉ እናቶች ሁሉ ሽንሽን ቀሚስ ዩኒፎርማቸው ይመስለኝ ነበር። ያደግኩበት መንደር ሁሉም የሚለብሱት እንደዛ ስለነበረ ሲቀመጡ እንኳን ዘርፋፋ ቀሚሳቸውን እንዴት ሰብሰብ አድርገው እንደሚቀመጡ ሳስብ የዚች “እናት” ነገር ግራ ገባኝ፡፡ መቼም እናት ምን
መምሰል አለባት?” የሚል ጥያቄ ቢነሳ ያው “እናት መምሰል አለባት” ነው መልሱ፡፡ እቺ ሴት ግን ምኗም እናት አይመስልም፡፡ የእናት ለዛ የላትም፤ የእናት የዋህነት፣ ደግነት ፊቷ ላይ ከነአካቴው
የለም፡፡ ዘላ ያልጠገበች የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነው የምትመስለው፡፡
የአመሃ አባት ውጭ አገር በሚገኝ ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው:: እናቱ አብራቸው ። እዛ እንዲኖሩ ብትለመን፣ ብትመከር “በአንገቴ ገመድ ቢገባ አልሄድም!” በማለቷ ሁለቱ ብቻውን
እዚህ በቅንጦት የተምነሸነሸ ቪላ ውስጥ ይኖራሉ፡፡ አባቱ በስድስት ወር አንዴ ብቅ እያሉ ይጎበኟቸዋል ራሱ አመሃ ነው የነገረኝ፡፡ ሁልጊዜም አባቱ ሲመጡ ታዲያ እናትና አባት ዱላ ቀረሽ ንትርክ ውስጥ ናቸው፡፡ ኣባት የሚስታቸውን ባህሪ ያውቁታል፡፡ ሚስትም የባሏን ባልነት
ባትረሳም የትዳሩ ነገር እጅ እጅ ብሏታል፡፡
የሆነው ሆኖ አምሃ አበደ፡፡ ከማበዱ በፊት የሚጠረጥር ዘመድ፣ በጊዜ አፋፍሶ ፀበል የሚወስድ ወዳጅ ዘመድ አጥቶ እንጂ አምሃ ግልፅ የሆኑ ምልከቶች ሲያሳይ ነበር በተለይ ለእኔ፡፡
ምልክት አንድ፡- ህዳር ላይ የሚያብድ፣ መስከረም ላይ ሱሪውን ከፍ ከፍ ያደርጋል ይላሉ እማማ ሩቂያ፣
አንድ ቀን አመሃ (ለይቶለት ከማበዱ አንድ ወር በፊት) ሱሪውን አስር ጊዜ ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡
“ሰፍቶሀል እንዴ ይሄ ሱሪ ? አልኩት፡፡ አይ ቀበቶዬን ረስቼ ሳላረገው ነው የመጣሁት አለኝ፣እንዲህ የምንባባለው ወደ ላይብረሪ እየሄድን ነበር፡፡ ላይብረሪ ውስጥ ጎን ለጎን
ለመቀመጥ ቦታ ስላልነበር በያገኘነው ወንበር ተራርቀን ተቀመጥን፡፡ ድንገት አመሃ ቁጭ ሲል ሸሚዙ ከኋላው
ሰብሰብ አለና ቀበቶ ማድረጉን አየሁ:: ያውም ጥቁር የቆዳ ቀበቶ፡፡ “ቀበቶ አላደረግኩም ማለቱ ገርሞኝ ሰንወጣ እጠይቀዋለሁ ብዬ በዛው ረሳሁት፡፡
ምልክት ሁለት፡- “አላህ ሲቆጣ በትር አይቆርጥም፡ ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም” ይላሉ እማማ ሩቅያ፡ የሰፈራችን አድባር፡
እኔና አመሃ እንድ ታዋቂ ሬስቶራንት ውስጥ ገባንና ምግብ አዘዝን ፒዛ
አምሃ ቀመስ አደረገና አስተናጋጇን ጠርቶ ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ጨው ቤቱ ውስጥ ያለውን ጨው ሁሉ ነው የሞጀራችሁት ?” ብሎ ጮኸባት፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ አመሃ ሲጮህም ሆነ በቁጣ ሲናገር ሰምቼ ስለማላውቅ ከምላሴ ያልቅ አመሃን እምኜው ነበር፡፡ አስተናጋጇ ግን በትህትና፣
“ይቅርታ እኛ ፒዛ ስናዘጋጅ ጨው እንጠቀምም፡ ደንበኛው ራሱ በሚፈልገው መጠን እንዲጠቀም ለብቻ ነው የምናቀርበው" አለች ፈታችን የተቀመጠውን የጨው እቃ እያሳየችን፡፡
“ሂጂ ወደዛ ! ይሄን ልመን እንችን ?” አላት ምላሱን በአስፈሪ ሁኔታ ጎልጉሎ በግራ እጁ ጫፉን በመያዝ በሹካው ጫፍ ለአስተናጋጇ እያሳያት፡ ፒዛውን ትተነው ሌላ ቤት ገባን፡፡ አመሃ ለስላሳ አዘዘ፡፡ አንድ ጊዜ ተጎንጭቶ ፊቱን አጨፈገገና፡ “ቱ " ብሎ ወለሉ ላይ ተፋው፡፡ ፊት ለፊት
ተቀምጠው የነበሩ ወንድና ሴት ፍቅረኛሞች ፊታቸውን አጨፈገጉና ተመለከቱት፡፡ “እንዴት ሚሪንዳ ውስጥ ሎሚ ትጨምራላችሁ ?” ብሎ እዛም ግብ ግብ ፈጠረ፡፡ በቃ ይሄ ልጅ ነገር
ሁሉ አልጥመው አለው፡፡ (ሊያብድ እስር ቀናት ብቻ ነበሩ የቀሩት)
ሦስተኛ ምልክት፡ እብድ
ሌላ ቀን መኪናውን እያሽከረከረ ወደ ማቆሚያው አመራና የዶክተር ታደሰን አሮጌ ዲኤክስ መኪና አርፋ በቆመችበት ከኋላዋ ገጫት፡፡ ድሮም ሆድ የባሳት ነበረች፡፡ ከዛም ሰው ተሰብስቦ ወሬ ሲያይ
አመሃ ረጋ ብሎ ወረደና ልክ እንደ ትራፊክ ፖሊስ ኮስተር ብሎ ግጭቱን ከተለያየ አቅጣጫ አይኑን እያጨነቆረና አንገቱን እየሰበቀ ከተመለከተ በኋላ (ፎቶ የሚያነሳ ነበር የሚመስለው) ወደ ዶክተር ታደሰ ቢሮ ሄደ፡፡ ሳያንኳኳ በሩን በርግዶ ገባና ዶክተሩ ላይ አፍጥጦ፣ “አንተን ብሎ
ዶከተር መኪና እንኳን በስርዓት ማቆም የማትችል…” ብሎ ሙልጭ አድርጎ ሰድቧቸው ወጣ፤
“ይሄ ልጅ እብድ ነው እንዴ ! አሉ ዶክተሩ፡፡
አራተኛው ምልክት፡- ዘመናይ

👍19❤1🤔1
ሄለን የምትባል ዘመናዊ የዲፓርትመንታችን ልጅ አለች፡፡ ምንም ነገር ስትናገር ለነገ የማትል፤
“ውይ እሷ ጣጣ የላትም፣ ፍሪ እኮ ነች” እያለ ለእብደት የቀረበ ዘመናዊነቷን ተማሪው ያባባሰባት፡፡ አመሃ ጋር አንድ ሰፈር ናቸው፡፡ እንደውም ቤተሰብ ናቸው ማለት ይቀላል፡፡
አንድ ቀን አምሃ፣ እኔ፣ እሷ ሆነን ዩኒቨርስቲው መናፈሻ ውስጥ እንደተቀመጥን አንዱ አስተማሪ በፊታችን ሲያልፍ፣ “ይሄ ስድ የሆነ ሰውዬ ባለፈው ቢሮው አስገብቶ ቀሚሴን ሊገልበው…” አለች፡፡
"ምን? ያንቺን ቀሚስ ሊገልብ ይሄ ቆሻሻ ብሎ አምሃ ወደ ሰውየው ሲንደረደር ሲነሳ
እንቅ አድርጌ ያዝኩት መጠርጠር ጀምሬ ነበር አምሽ ለቀቅ እያደረገ እንደነበር፡፡
"ምን ነካህ አምሃ ስትቀልድ እኮ ነው እሷ !" አልኩት፡፡
እየቀለድሽ ነው ? አላት አምሃ ወደ ሄለን ዞሮ፡፡ አዎ እንድትል ጠቀስኳት፣
"አዎ" ከማለቷ፣ አመሃ በጥፊ አጮላት፡፡ አስደንጋጭ ነገር ነበር፡፡ ስድድብ ጀመሩ፤
"ጀዝባ" አለችው፡፡ ሰው ስትሳደብ አይቻት አላውቅም፡፡ መናፈሻው ውስጥ ያለ ተማሪ ሁሉ ወደ እኛ ዞረ፡፡
"ሸርሙጣ" : አላት፡፡ ከአምሃ ይሄ ቃል ይውጣል ብሎ ማንም አይገምትም፡፡
"ቆሻሻ" : አለችው::
“ግማታም!” አላት፡፡
"ስማ አባትህ ቾክ እያቦነነ ባመጣው ገንዘብ ስትሞላቀቅ ጠገብክ !"
"እና እንዳንቺ እናት በመሸርሞጥ ሃብታም መሆን ይሻላል ?” ተማሪ በተሰበሰበበት እብድና ዘመናይ ልክ ልካቸውን ተነጋገሩ፡፡ አመሃ ሊለይለት ሶስት ቀን ቀርቶት ነበር፡፡
ስድስተኛው ምልክት፡- ልበቢስ
የመጀመሪያውን ሴሚስተር ጨርሰን ሁለተኛውን መጀመራችን ነበር፡፡አዲስ ኮርስ የሚሰጡን መምህር ወደ ክላስ ገቡ፡፡ ፀጉራቸው ወደ ኋላ የተደለሰ ህንዳዊ ናቸው፡፡ ስታትስቲክስ
የሚባል ኮርስ ነው የሚያስተምሩት፡፡ ይሄ መምህር ከአንድ የመንግስት የኒቨርስቲ
በተማሪዎቹ የአንፈልጋቸውም ተቃውሞ የተባረሩ ህንዳዊ ቢሆኑም አሁን የምንማርበት ኮሌጅ ግን፣ ከውጭ በመጡ ታዋቂ መምህራን..." እያለ የቴሌቪዥን ማስታወቂያ የሚሰራባቸው የስንፍና ጥግ ናቸው፡፡ ያው እንግዳ ተቀባይ ነንና አከብረን ተቀበልናቸው፡፡
በተኮላተፈ እንግሊዝኛቸው ማስተማር ጀመሩ፤
ስታትስቲክስ ከሌሎች የጥናት መስኮች የሚለየው አንዲት አገር የልብ ምቷን' የምታዳምጥበት መሳሪያ በመሆኑ ነው አሉ በኩራት፡፡
አምሃ ድንገት ብድግ ብሎ "ዝም በል" አላቸው፡፡
“ቲቸርን ከራማቸውን ነው የገፈፈው፡፡ እኛንም እንጂ !
አመሃ በብስጭት ዲስኩሩን ቀጠለ፡፡ “ሁሉም አስተማሪ እየመጣ 'የልብ ምት፣ የልብ ምት ይልብናል፡፡ ኢኮኖሚክስ¨ የአንዲት አገር የልብ ምት የሚለካበት የጥናት መስክ ነው ሕግ የአንዲት አገር የልብ ምት የሚለካበት ፖለቲካል ሳይንስ ሁለንተናዊ የአገር የልብ ትርታን
የሚያዳምጥ የጥናት ዘርፍ ነው… ቆይ የዚች አገር ልብ በስንቱ ነው የሚለካው? ሲጀመር አገራችን ልብ ቢኖራት እንዳንተ አይነቱ ፊት ታስቀምጠን ነበር?
አገራችን ልብ አላት ወይስ የላትም? የሚለውን ሃቅ የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ያስፈልገናል፤ የልብ ትርታ ከመለካታችን በፊት ልብ መለኪያውን ይዞ ከየዩንቨርስቲው በየዓመቱ ወደ ሕዝብ
የሚጎርፈው ሁሉ እዚህ ልብ የለም፣ የምትሄድበት ሄደህ ፈልግ፣ ካልሆነም ልብ ፍጠር እየተባለ ስለ የትኛው ልብ፣ ስለየትኛው ትርታ ነው የምትቀባጥረው ? ሳልፈልግ ብዙ አታስወራኝ ሃሃሃሃሃሃሃ
አመሃ ለየለት !! አፋፍሰን አማኑኤል ወሰድነው፡፡ እዛው ቀረ !! እናቱ ተጠርታ መጣች::ሰውነቷ ላይ ጥብቅ ያለች አጭር ሚኒስከርት ለብሳ ከመኪናዋ ወረደችና ሰበር ሰካ እያለች ወደ እኔ መጣች፡፡
“ምን ሆኖ ነው ” አለችኝ፣
ነገርኳት፡፡
“ድሮም የአባቱ ልጅ ነው፣ ሴታ ሴት፣ ለየለት” አለች በብስጭት፡፡ ምን እንዳበሳጫት አላወቅኩም፤
ከብዙ ጊዜ በኋላ ሄለን አመሃ በእናቱ ምከንያት አዕምሮው እንደተናጋ አወጋችኝ፡፡
"አንድ ቀን አምሃ ሶደሬ ሲሄድ ከሴት ጓደኛው ጋር ቀጠሮ ያዙ፡፡ ታውቃት የለ ያች ሚዳቆ የመሰለች ጓደኛው፡፡ እናልህ ለእናቱም ይሄንኑ ነግሯት መንገድ እንደ ጀመሩ የጓደኛው እናት የደም ግፊታቸው ከፍ ብሎ ጉዟቸው ተሰናከለ፡፡ ሆስፒታል ቆይቶ ወደ ቤቱ ሲመለስ እናቱ
ናትናኤል ከሚባለው ከራሱ ከአመሃ ጓደኛ ጋር ያውም አባቱ አልጋ ላይ…ሂሂሂሂሂሂ”
ሄለን 'ፍሪ ስለሆነች በሚያሳብድ ቃል ነው የነገረችኝ፤ መሳቋ አበሳጨኝ፡፡
“አብርሽ” አለችኝ እየሳቀች፡፡
“ምን ሆንሽ !” አወራሯ አበሳጭቶኝ ነበር፡፡
“ተረኛው አንተ ነህ.…ሂሂሂሂሂ”
ተራዬ ለእብደቱ ይሁን ... አልገባኝም፤ ግን አልጠየቅኳትም፡፡ ምክንያቱም ሄለንም በጅምላ አብዳ ሳይንሱን ጉድ ልታደርገው እየተዘጋጀች ስለመሰለኝ ነበር፡፡

👍25❤5🤔1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
.....ከተማውን ጥሎ ወጣ፡፡ ከተማውን ለቅቆ ገጠር እስከገባ ድረስ እየተጣራ ነበር የሚሄደው፡፡ ወዴት እንደሚሄድ ሳያስተውል መንገድ እንደመራው ዝም እያለ ተጓዘ፡፡ ከነጋ ጀምሮ እህል አልቀመሰም:: ሆኖም የረሃብ ስሜት አልተሰማውም፡፡ ቁጣ ቁጣ ብሉታል፡፡ በማን ላይ ወይም በምን ምክንያት እንደተቆጣ ግን አያውቅም:: የሚቀጥለው ምን ይሆን ሲል ራሱን ጠየቀ፡፡
የገጠር አየር የልጅነት ጊዜውን አስታወሰው:: የልጅነት ዘመኑን ካስታወሰ በጣም ቆይቶ ነበር፡፡ ከዚያም ብዙ ኣሳቦች ተፈራረቁበት፡፡»
ፀሐይ አሽቆልቁላ ገብታ ከአድማስ ውስጥ ልትገባ ስትል ዣን ቫልዣ
እልም ካለ ጫካ ውስጥ ከአንዲት ጉብታ ላይ ቁጭ ብሎአል፡፡ የአልፕስ ተራራ በሩቁ ይታያል፡፡ ከጫካው ወጣ እንዳለ አንድ ቀጭን የእግር መንገድ አለ፡፡
ከዚህ ቁጭ ብሎ ሲያሰላስል ደስ የሚል ድምፅ ይሰማል፡፡ ፊቱን
ሲያዞር ወደ አሥራ ሁለት ዓመት የሚሆነው ልጅ እየዘመረ ወደ እርሱ ይመጣል:: ልጁ በጭንቅላቱ ሣጥን መሳይ ነገር ተሸክሞአል፡፡ ልጁ ጥቂት
ከተራመደ በኋላ ቆም ብሎ በእጁ የያዘውን ሣንቲም ወደ ሰማይ እያጎነ ይጫወታል:: የልጁ ሀብት ምናልባት ይኸው ነጭ ሽልንግ ብቻ ሳይሆን አልቀረም::
ዣን ቫልዣ ከተቀመጠበት ሲደርስ የሰውዬው ከእዚያ መኖር ሳይገነዘብ ቆም አለ፡፡ እንደ ልማዱ ሣንቲሙን ወደ ሰማይ አጎነ፡ ሣንቲሙ አምልጦት
ከመሬት ሊወድቅ ዣን ቫልዣ ወደ ተቀመጠበት በረረ:: ዣን ቫልዣ
ሽልንጉን በእግሩ ረግጦ ያዘበት:: የልጁ ዓይን ሣንቲሙን ተከትሎ ስለሄደ የት ላይ እንዳለ ያውቃል፡፡ ልጁ አልፈራም፤ በቀጥታ ወደ ሰውዬው ሄደ::
«ጌታዬ ገንዘቤን» አለ ልጁ የዋህነትና ድንቁርና በተሞላበት አንደበት::
«ስምህ ማነው?» ሲል ዣን ቫልዣ ጠየቀው::
«ትንሹ ዥራቪ ነው ጌታዬ::»
«ቶሉ ከዚህ ጥፋ» አለው ዣን ቫልዣ ::
«ፍራንኬስ?» ሲል ልጁ ጠየቀ፡፡
ዣን ቫልዣ እንዳቀረቀረ ቀረ::
«ገንዘቤን» አለ ልጁ እምባ እየተናነቀወ :: ሽልንጌን!»
ዣን ቫልዣ ምንም ነገር እንዳልሰማ ሰው ፀጥ አለ፡፡ ልጁ የሰውየውን ሸሚዝ ኮሌታ በአንድ እጁ ያዘ፡፡ በሌላው እጁ ሣንቲሙን ለማስለቀቅ የሰውየውን እግር ለማንሳት ሞከረ::
«ገንዘቤን እፈልጋለሁ ፧ ሽልጌን!» ብሎ ከጮኸ በኋላ ትንሹ ዠራቬ
ማልቀስ ጀመረ:: ዣን ቫልዣ አንገቱን ቀና አደረገ፡፡ ከተቀመጠበት ግን አልተነሳም:: ፊቱ፡ በአሳብ የተዋጠና የተጨነቀ ይመስላል፡፡ በመገረም ልጁን
አትኩሮ አየው:: ዱላውን ሳብ ኣድርጎ «አንተ ማነህ? እህ! ምንድነው የምትፈልገው? እስካሁን አልሄድክም እንዴ» ሲል በሚያስፈራ ድምፅ ጮኸበት:: ሣንቲሙን እንደረገጠ ከመቀመጫው ብድግ ብላ «ራስህን ብትጠብቅ ይሻልሃል» አለው::
ልጁ በፍርሃት ተወጦ ቀና ብላ አየወ:: ሰውነቱ ይንቀጠቀጥ
ጀመር፡፡ ወዲያው ከጥቂት ሰኮንድ መርበትበት በኋላ ልጁ አግሬ አውጪኝ ብሎ ሸመጠጠ፡፡ ዞር ብሎ ለማየት ወይም ጩኸት ለማሰማት እንኳን አልደፈረም፡፡ ሆኖም ጥቂት እንደተጓዘ ትንፋሽ አጥሮት ቆም አለ:: ግን ብዙ
አልቆመም፧ መንገዱን ቀጠለ፡፡
ፀሐይዋ ጠለቀች፡፡ ዣን ቫልዣ ከተቀመጠበት አካባቢ ብርሃን ለጨለማ ሥፍራዋን ለቀቀች:: ቀኑን መሉ ምግብ የሚሉት ነገር አልቀመሰም::ምናልባትም ትንሽ እንደትኩሳት ብጤ ሳይሞካክረው አልቀረም::
ልጁ ከሄደ ጀምሮ ከተቀመጠበት ነቅነቅ አላለም:: በኃይል ነው
የሚተነፍሰው:: ከተቀመጠበት ጥቂት ራቅ ብሎ ከነበረው የሸክላ ስባሪ ገል ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ስለገሉ ይመራመር ጀመር፡፡ ግን በድንገት መላ ሰውነቱ
ተንቀጠቀጠ፡፡ የሌሊቱ ቁር እየተሰማው ሄደ፡፡
ቆቡን ሳብ አድርጎ ግንባሩን ሸፈነ:: የሸሚዙን አዝራር ለመቆለፍ
ጣቶቹ አዝራር ፍለጋ ላይ ታች አሉ:: ብድግ ብሎ ወደፊት ራመድ ካለ ከኋላ መለስ ብሉ ዱላውን ለማንሳት ጎንበስ አለ፡፡
በእግሩ ረግጦ ይዞት የነበረው ሽልንግ በማብረቅረቁ ዓይኑ ወደዚያ ተሳበ፡፡ ኮረንቲ እንደያዘው ሰው ተሸማቀቀ፡፡ «ምንድነው ነገሩ?» ሲል ጥርሱን በማፋጨት ራሱን ጠየቀ:: እንደገና ወደኋላ መለስ ብሉ ሣንቲሙን በእግሩ በመርገጥ ሸፈነው:: ሣንቲሙ ዓይን አብቅሎ የሚያየው መሰለው::
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እግሩን መነጨቀና ጎንበስ ብሎ ሣንቲሙን
አነሳ፡፡ ቀና ብሎ አካባቢውን ተመለከተ:: ጋራውና ሸንተረሩ ሁሉ የሚያየው ስለመሰለው በፍርሃት ተውጦ መወጊያ እንደምትፈልግ ዱኮላ ዓይኑ በፍርሃት ተቅበዘበዘ፡፡ ከቆመበት ተገትሮ ቀረ፡፡
ምንም ነገር አላየም:: ጊዜው እየጨለመና አየሩ እጅግ እየቀዘቀዘ ሄደ:: ሰማዩ በጭጋግ ተሸፈነ፡፡
«ወይ ጣጣ» ሲል ልጁ በሄደበት አቅጣጫ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ አንድ
ሰላሳ - እርምጃ ያህል እንደተራመደ ቆም ኣለ፡፡ አካባቢውን ተመለከቱ።
ምንም ነገር የለም:: ድምፁን እጅግ ከፍ አድርጎ «ዠራቬ» ሲል ተጣራ፡፡ ከዚያም ድምፁ
አጥፍቶ አዳመጠ:: መልስ አላገኘም፡፡
አገሩ ጭር ያለና ጭጋጋም ቢሆንም አካባቢው በግልጽ ይታያል ከዝምታና ከራሱ ጥላ በስተቀር የሚንቀሳቀስ ፍጠር ጨርሶ አልነበረም ዣን ቫልዣ መንገዱን ቀጠለ፡፡ የሚወስደውን እርምጃ ፍጥነት በመጨመር እንደ መሮጥ አለ። አልፎ አልፎ ቆም እያለ በሚያስፈራ ሻካራ ድምፅ «ዠራቬ» ሲል እንደገና ተጣራ፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ልጁ ቢሰማው
እንኳን በፍርሃት ስለሚዋጥ ይደበቃል እንጂ መልስ አይሰጠውም:: ነገር ግን ልጁ በርግጥም በጣም ርቆ ሄዷል፡፡
ዣን ቫልዣ እንደገና ልጁ በሄደበት ኣቅጣጫ መሮጥ ጀመረ
እየተገላመጠ፣ እየጮኸ፣ እየተጣራ ብዘ ተጓዘ፡፡ ግን ማንንም አላገኘም በደረቱ ተንፏቅቆ የሚሄድ ወይም ድምፁን አጥፍቶ ያደፈጠ እየመሰለ ከአንዴም ሁለቴ፣ ከሁለቴም ሦስቴ መንገዱን ለቅቆ ወደ ጥሻው ዞር እያለ
ተመለከተ፡፡ ግን ሰው የመሰለው ነገር ጠጋ ሲል ቁጥቋጦ ወይም ድንጋ ሆኖ ያገኘዋል፡፡ በመጨረሻ ሦስት መንታ መንገዶች ከሚገናኙበት ደረሰ ከመሐል መንገድ ላይ ቆመ:: ጨረቃዋ ብቅ ብላለች:: ለማየት እስከቻለ
ድረስ አርቆ ተመለከተ:: «ዥራቬ፣ ትንሹ ዥራቬ፣ ዠራቬ» በማለት
ሦስት ጊዜ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተጣራ:: ድምፁ የገደል ማሚቶ እንኳ ሳያዕማ ከጭጋጉ ውስጥ ተውጦ ቀረ:: «ትንሹ ዥራቬ» ሲል ዝግ በደከመ ድምፅ አጉረመረመ:: ያ የመጨረሻው ሙከራ ነበር፡፡ በዓይ የማይታይ ኃይል በዱላ እንደመታው ሰው በድንገት እግሩ ተሳስሮ ጉልበቱ እጥፍጥፍ አለበት:: ፀጉሩን በእጁ ጨብጦና ፊቱን ጉልበቱ ላይ አሳርፎ
ከቋጥኝ ድንጋይ ላይ በመቀመጥ «ምን ዓይነት እድለቢስ ሰው ነኝ» አለ ጮኸ፡፡ ልቡ እያበጠ ሄደ፡፡ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ከአሥራ ዘጠኝ ዓመት ወዲህ ሲያለቅስ የመጀመሪያው ነበር:: ዣን ቫልዣ ብዙ አለቀሰ፡፡ ከሕፃኑ መባባትና ከሴቶች መርበትበት ይበልጥ በፍርሃት ተውጦ ከዓይኑ እምባ የወጣ እስኪመስለው ድረስ በማልቀስ አንጀቱን እርር ድብን አደረገ እያለቀሰ ሳለ ከሕሊናው ውስጥ የነበረው ብርሃን እየፈካ ሄደ፡፡
የተለየ ብርሃን ነበር፡፡ ያ ብርሃን አሳደደው፤ አስፈራራው፡፡ ያለፈው የሕይወቱ ዘመን፤ የመጀመሪያው ወንጀሉ፤ የረጅም ጊዜ ስቃዩ ፧ ጨካኙ ዓለም፤ የደነደነው ልቡ ፣ ከእስር ቤት ማምለጡ፤ ከጳጳሱ ቤት በእርሱ ላይ የደረሰው! የመጨረሻው አሳፋሪ ድርጊቱ ፤ ከሕፃን ልጅ ገንዘብ መዝረፉ፤

👍22😁1
ጳጳሱ ይቅርታ ካወረዱለት በኋላ የተፈጸመ አሰቃቂና አስፈሪ ወንጀል መሆኑ፤ ይህ ሁሉ ከዓይነ ልቦናው ውስጥ እየተመላለሰ ከዚያ በፊት ታይቶት በማይታወቅ ዓይነት ቁልጭ ብሎ ታየው:: ያለፈውን የሕይወቱን ምዕራፍ በአሳብ በተመለከተው ጊዜ እጅግ አስቀያሚና አስከፊ መሆኑን
ተረዳ፡፡ የነፍሱንም መኮነን አልተጠራጠረም:: ሆኖም ነፍሱ 'የተስፋ ጭላንጭል ብርሃን ጨርሶ የተለየው አልነበረም:: ቢሆንም ከዚያ የተስፋ
ጭላንጭል ባሻገር ይመለከተው የነበረው የሰይጣን ጥላ ነበር፡፡
ይህም በመሆኑ ከማልቀስ አልተገታም:: ከልቅሶው በኋላ ምን ሆነ? ምን አደረገ? የት ሄደ? ማንም አላወቀም:: ነገር ግን በዚያን እለት ምሽት በዚያ በኩል ያለፈ ባላጋሪ ከእኚያ ደግና ቸር ጳጳስ ቤት በራፍ ከመንገዱ
ጠርዝ ፈቀቅ ብሎ ጥላ ስር ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ተንበርክኮ በስሜት ይጸልይ የነበረ ሰው ማየቱለን ተናግሯል፡፡...

👍12👏2❤1
#ምንዱባን
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ
አንዳንዴ ኃላፊነትን ከመሸከም አሳልፎ መስጠት
በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ፓሪስ አጠገብ ከሚገኘው ሞንትፌርሜ ከተባለ ሥፍራ አንድ አነስተኛ ሆቴል ቤት ነበር፡፡ ዛሬ ግን የለም:: ሆቴል ቤቱ፡ ዘቴናድዬስ የተባሉ ባልና ሚስት ንብረት ሲሆን የሚገኘው በላንገር ከተባለ ቀጭን መንገድ ላይ ነበር፡፡ ከቤቱ በራፍ ላይ ስዕል
ተንጠልጥለአል:: ስዕለ ላይ ሜዳሊያ የተሰካላትና በደም ተበክሎ የተቦጫጨቀ የጄኔራል ልብስ የለበሰ ሰው ሸክም ተሸክሞ ነው የሚታየው::በተጨማሪም ከምስሉ ባዶ ሥፍራ ላይ ጭስ በብዛት አለ:: የሚያመለክተው
የጦር ሜዳን ሳይሆን አይቀርም:: ከምስሉ ስር «የዋተርሉ ጦር ሜዳ
ጀግና የሃምሳ አለቃ» የሚል ጽሑፍ ተጽፎበታል:: ከዚህ ሆቴል ቤት በራፍ ጋሪ ቆሞ ማየት አዲስ ነገር አልነበረም:: ሆኖም «ከዋተርሉ የጦር ሜዳ ጀግናው የሃምሳ አለቃ» ሆቴል ቤት በራፍ
የተሰባበረ ጋሪ መንገድ ዘግቶ ሲቆም ዘወትር የሚታይ ትርኢት አይደለም::ጊዜው የፀደይ ወራት ሲሆን ዓመተ ምህረቱ 1818 ዓ.ም ነው፡፡ የጋሪው መንገድ ዘግቶ መቆም ፤ ያን የመሰለ ስዕል ከዚያ ቤት በራፍ መሰቀል በዚያ
ያለፈ የማንኛውም ሰዓሊ ዓይን የሚማርክ ትርዒት ነበር::
ጋሪው ትላልቅ ግንዲላዎችን ጭኖአል፡፡ ታዲያ ይህ ጋሪ ከዚህ ስፍራ ምን ይሠራ ነበር የሚል ጥያቄ ቢነሳ «ከዚያ የተገተረውማ መንገድ ለመዝጋትና የትጉህ ሠራተኞችን ተግባር ለማደናቀፍ ነው» የሚል ትርጉም
ሊያሰጥ ይችላል፡፡
ከጋሪው የእቃ መጫኛ ሥር የተንጠለጠለው ወፍራም ሰንሰለት መሬት ሊነካ ምንም አልቀረው:: አንዲት ሁለት ዓመት ተመንፈቅ የሚሆናት ልጅ ሌላ ዓመት ከስድስት ወር የሚሆናትን ሕፃን ጭንዋ ላይ አሳርፋ
ከሰንሰለቱ ላይ ተቀምጣለች:: ልጆቹ ጅዋጅዌ ላይ እንደወጡ ደስ ብሎአቸዋል፡፡ አንዲት ሴት አቀማመጣቸውን አይታ «ልጆቼ መጫወቻ አገኘ» በማለት ደስ እንደሚላት ማንኛዋም እናት በማተኮር ታያቸዋለች::አተኩሮ ለተመለከታት አንጀት የምትበላ፧ አንዴ እንኳን ለማየት የምትቀፍና
ኑሮ እጅግ ያጎሳቆላት ሌላ ሴት ከበራፉ አጠገብ ተቀምጣለች፡፡ ልጆቹ ደስ ብሏቸው ሲጫወቱ «ምናልባት ፈረሱ ደምብሮ ይጐዳቸው ይሆን» እያለች
የመጀመሪያዋ ሴት አሁንም እንደማንኛውም እናት ማሰብዋ ኣልቀረም::ሰንሰለቱ በተነቃነቀ ቁጥር ሲጥጥ እያለ ይጮሃል:: ድምፁ ሕፃናቱን አልረሸሻቸወም:: የማታ ጨረር ከልጆቹ ላይ በማረፉ ልብ ብሉ ለተመለከታቸው ዓይንን ይማርካለ::
የልጆቹ እናት በድንገት ድምፅ ትሰማለች:: «እሜቴ ደስ የሚሉ
ልጆች ነው ያሉዎት!»
ከምግብ ቤቱ በራፍ የተቀመጠችው ሌላዋ ሴትም ልጅ ታቅፋ ነበር::ከባድ የሚመስል እቃ በጀርባዋ አዝላለች:: እርስዋም የታቀፈቻት ልጅ ሁለት ወይም ሦስት ዓመት ቢሆናት ነው:: በአለባበስ ከሁለቱ ልጆች
ምንም ያህል አትለይም:: ሻሽ መሳይ ጨርቅ አስራለች:: የተቦጫጨቀ ቀሚስዋ ቀዳዳው እስከጭንዋ ሊደርስ ምንም አልቀረ:: ሆኖም ጤነኛ ነበረች:: መልክዋ ድምቡሽቡሽ ያለ ስለሆነ ንከሰኝ፣ ንከሰኝ ትላለች፡፡ዓይኖችዋ ትላልቅ ስለነበሩ እንቅልፍ ቢወስዳትም ሙሉ ለመሉ
አልተከደነም:: ለስለስ ካለው የእናትዋ ክንድ ላይ ተመችቶአት ስለተኛች እንቅልፍ ሳይጠግብ ሲቀሰቅሱት እንደማይስማው እንደማንኛውም ሕፃን
እርስዋም ቢቀሰቅሱዋት እንኳ አትሰማም::እናትየዋ ሲያዩዋት የተከፋች ምስኪንና ከተማ ስራ ፍለጋ የመጣች የገጠር ሴት ለመሆንዋ ታስታውቃለች:: በእድሜ ልጅ ናት:: ተፈጥሮ
ውበት ቢቸራትም በዚያ ሁኔታዋ ውበትዋ ጎላ ብሎ አይታይም ፀጉርዋ ዞማ እንደሆነ ቢያስታውቅም ተንጨባሮአል:: የተቀዳደደ ሻሽዋ ተፈትቶ
ሊወድቅ ብሎ ከወደኋላዋ ተንጠልጥሎአል፡፡ የደላው ሲስቅ ነጭ ጥርሱን ያሳያል እንጂ የተከፋ ስለማይስቅ ስለጥርሶችዋ ለመናገር አይቻልም:: ለረጅም
ጊዜ ለማልቀስዋ ዓይኖችዋ ይመሰክራለ:: ገርጥታለች፤ ሰውነትዋ በመዛሉ የደከማት ለመሆነ ያስታውቃል፡፡ ምናልባትም ሳትታመም አልቀረችም::ጭንዋ ላይ የተኛችዋን ልጅ አትኩራ በፍቅር ዓይን ትመለከታታለች፡፡ ልጅዋን ደግፋ የያዘችበት እጅ ሲታይ በሥራ ብዛት ለመሻከሩ ጉልህ ነው::
ጠቅላላ ሀናቴዋ ሲታይ ሩህሩህ ልብ ያላቸው ሁሉ የማያልፍዋት
ዓይነት ስለነበረች አንጀት ትበላለች:: በይበልጥ የሚያሳዝነው ግን ማን
ትሁን፤ ከየት ትምጣ ማንም አለማወቁ ነው:: እርስዋም ራስዋ ብትሆን አባትዋና እናትዋ እነማን እንደሆኑ ማለት ማን እንደወለዳት አታውቅም፡፡ስምዋ ፋንቲን ይባላል፡፡ ቤተሰብ ስላልነበራት የአባት ስም የላትም:: የክርስትና
ስምም አልወጣላትም፡፡ ምክንያቱም በዚያ አካባቢ ቤተክርስቲያን ምን እንደሆነ
አይታወቅም:: ፋንቲን ብሎ ስም ያወጣላት በዚያ ሲያልፍ ያገኛት መንገደኛ ነው ይባላል፡፡ ይህ ሰው ይህችን ሕፃን መንገድ ወድቃ ዝናብ ሲዘንብባት ነው ፋንቲን የሚል ስም ያወጣላት:: «ፋንቲን» ማለት ውሃ ወይም ምንጭ
እንደማለት ነው::
ስለዚህች ሴተ ታሪክ ከዚህ ይበልጥ የሚያውቅ ስለሌላ ስላለፈው ታሪክዋ ከዚህ ይበልጥ መናገር አይቻልም:: ሆኖም ፋንቲን ወደዚህች ዓለም ለስቃይ የመጣች በዚህ ዓይነት ነበር ብሎ ለማጠቃለል ይቻላል፡፡ ወደኋላ
እንደተደረሰበት ደግሞ አሥር ዓመት ገደማ ሲሆናት ከከተማ ወጣ ብሎ ወደሚገኝ መንደር ሥራ ፍለጋ ትሄዳለች:: አሥራ አምስት ዓመትዋ አሁንም ሥራ ፍለጋ ወደ ፓሪስ ከተማ ትመጣለች::
በመጨረሻ ጥርሶችዋ ታዩ ፧ እንደወተት የነጡ ነበሩ፡፡ ሌላ ቢጠፋ የእንጨት መፋቂያ አላጣችም ማለት ነው:: ስታገባ የተሰጣት ሳይሆን አይቀርም የሚያማምሩ ጌጣጌጦች አንገትዋ ላይ አስራለች:: ወይም ደግሞ ሥራ ብጤ አግኝታ ትንሽ ከሠራች በኋላ ፤ የገዛቻቸው ይሆናሉ፡፡ ሴት ናትና ማጌጥ አይቀርም:: እርስዋም እንደ ዓቅምዋ ለመኖር ፈልጋ ሥራ
ይዛ ነበር ማለት ነው:: ለመኖር ሆድ እንጀራ እንደሚርበው ሁሉ ልብም ፍቅር ይርበዋልና ልጅዋን እንደዚያ የምታያት የፍቅር ረሃብዋን ለማርካት ነበር፡፡
ያ ስሜት ለሕፃንዋ የእናት ፍቅር ሲሆን ለእናትዮዋ ግን የስሜት
መገንፈል ነበር፡፡ እናትና ልጅ ከተቀመጡበት አቅራቢያ የሚተላለፉ መንገደኞችና ተማሪዎች ቁጥር እጅግ ብዙ ነበር፡፡ ሕፃን ሆና ሕፃን
የታቀፈችዋን ሴት ሁሉም አይቶ አለፋት እንጂ ከመጤፍ የቆጠራት
አልነበረም::
የሕፃንዋ አባት ልጅቱ፡ እንደተወለደች ሚስቱንና ልጁን ጥሎ ከአገር ይጠፋል፡፡ አባት አንዴ ቤተሰቡን ጥሎ። ከሄደ መመለሱ ያጠራጥራል፡፡
ይህም በመሆኑ ልጅትዋ በብቸኝነት ዓለም ውስጥ እየዋዠቀች ስለነበር ተስፋ ከሚፈጥረው ደስታ ርቃለች:: በአንድ ወቅት ተሳሳተች እንጂ
በአፈጣጠርዋ ገራምና ትምክህት የተለያት ለመሆኑ ገፅታዋ ይመሰክራል በፊትዋ ገጽታ ላይ የሚነበብ ገራምነትዋ ብቻ አልነበረም፡፡ ተስፋ
መቁረጥዋን! ቀባሪና ጧሪ የሌላት መሆኑንና ከባድ ችግር ውስጥ
መዘፈቅዋንም ያሳያል፡፡ ሆኖም ፋንቲን ቆራጥና ጠንካራ ሴት ነበረች:: ወደ ትውልድ አገርዋ የመመለስ አሳብ ነበራት፡፡ ምናልባት እዚያ ከሄደን
ድንገት የሚያውቃት ሰው ይኖርና ሥራ ይሰጠኝ ይሆናል የሚል እምነት አድሮባታል፡፡ ነገር ግን የፈጸመችውን ስህተት መደበቅ ስለነበረባት ልብዋ በሀዘን ቢቆስልም ሀሳብዋን ለመፈጸም ቆረጠች፡፡ በሃያ ሁለት ዓመት

👍21❤1