አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጸሎተ #ደቂቃን

አባ ያለህ በሰማይ
አባ አንተ ትልቁ
ከጡቶች ብቻ ሳይሆን
ወተቶች ካ'የር ይፍለቁ...
እንጠጣ ያለ አንዳች እቅፍ
ተይዞ መጥባት ይቅርልን
እየሮጥን የምንጠጣው
እየዳህን የምንረካው
ያ'የር ላይ ጡት ፍጠርልን።
እነኾም አደራ ጌታ
ይቅርልን የቀን መኝታ
ይቅርልን የሌሊት እንቅልፍ
እናቶቻችን አይተኙ
አባቶቻችንም ይንቁ
ደቂቅ ናቸው አይበሉን
ጮርቃነታችን አይናቁ
በገዛ ሕልሞቻችን ላይ
ፍቃድ እንዳለን ይወቁ።
በዛውም አደራ አባ
አባ የሰማያቱ
አልበላችሁም ብለው
አልተኛችሁም ብለው
ቁጠርባቸው ሲማቱ...
በደፋን በገፋን
በሰበርን ቁጥር
የሚዘረጋውን
እጃቸውን ቁጠር።
አባ እንደምታውቀው
ለራስ ልጅ ሲቆርሱ፥ ከቶ አያሳንሱም
ያንተ አባትነት፥ ነውና ለእነሱም
ይቀጡናልና፥ ስናጠፋባቸው
እንዳባትነትህ፥
ጥፋቶቻቸውን፥ አትለፍባቸው።
ረድኤት አ
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች በአጥናፍሰገድ ይልማ የተፃፈውን የበደል ካሳ የተሰኘውን ታሪካዊ ልብ ወለድ መፅሐፍ ያላነበበው ካለ ሙሉውን በPdf ቀርቦላችኋል መልካም ንባብ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ለምን #መጣህ

ለምን መጣህ ትይኛለሽ ለምን እንደሆን እያወቅሽ

ለምን ብለሽ አጠይቂ ይሄንን ብቻ እወቂ

መምጣት ለኔ ያኖረኛል

ከሰፈርሽ እያመሸዉ መዋል ማደር ያረካኛል

ከሰፈርሽ ዉሾች መሀል እኔ ብቻ የምጮህዉ

ሂድ ብለሽኝ ካጠገብሽ ከጥላሽ ስር የማርቀዉ

ጠዋት ማታ ልሳለምሽ ደጅሽ ድረስ የምቆመዉ

ከእልፍ ሰዉ መሀል አንድ የኔ ቸግሮኝ አንችን

ፍለጋ ነዉ ለምን ማለት ምንድን
ለምንስ ምድን ነዉ።

*በባንቻየሁ አለሙ*
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍1
#የገጣሚዉ #ስእል

ከሰአሊዉ ስእል የሚታየው ቀለም
ዉስብስብ አደለም
ዝብርቅርቅ አደለም
ኑሮ ነዉ ህይወት ነዉ የኔና ያንተ አለም
ሰአሊዉ ጀመረ ሽርጡን ታጠቀ
ቀለም ደባለቀ
ሀሳቡ መጠቀ
ከስጋዉ ተለየ ሄደ ካንድ ስፍራ
ህይወት ልታርፍ ነው ከወጠረዉ ሸራ
ተመልከት ስእሉን
አስተዉል ምስሉን
በልቦናህ እይ እድሜዉ ገፋ ያለ አንድ ሽማግሌ ጭቃዉን ይረግጣል
የሚረግጠው ጭቃ በደም ተለዉሶል
እንደዚህ ነው ስእል
እንደዚህ ምስል
ልብ ያለው ልብ ይበል
ከየት መጣ ደሙ
ምንድን ነው ትርጉሙ
የጭቃ ረጋጭን እግር የፈተተ
ከዚህ ብትን አፈር እሾህ ማን ከተተ
የጭቃ ረጋጭን እግር የከፈተ
ከዚህ ልስን ጭቃ ስለት ማን ከተተ
ይሄዉ ነዉ ጥያቄዉ ይሄዉ ነዉ ትርጉሙ ከጭቃዉ መሀል ላይ ለሚላወስ ደሙ
እናም ስእል ማለት ዝብርቅርቅ አደለም
ዉስብስብ አደለም ኑሮ ነዉ ህይወት ነዉ
የኔና ያንተ አለም
ከሰዉ ልጅ በስተቀር ጭቃ ረጋጭ ማነዉ
በደም የሚለዉስ አፈር የሆነን ሰዉ
ደሞም አለ ክፋት ከጭቃዉ ስጋችን
ትጉህ ሰዉ የማይወድ እሾህ ሀሳባችን
ሰአሊዉ ቆም አለ ሽርጡን አጥብቆ
ቀለሙን ደባልቆ
ከማያዉቀዉ አለም በነፍስ እግር ቆሞ
ስእሉን ያይ ጀመር ደጋግሞ ደጋግሞ
ጭቃዉን የሚረግጠዉ ምስኪን ሽማግሌ የራስ ቅሉ ፀጉር ፈትል ጥጥ መሳይ ነው
ልብሱም ቁምጣ ነበር ባጭር የታጠቀው እንደዚህ ነው ስእል እንደዚህ ምስል
ልብ ያለዉ ልብ ይበል
ከህይወት በስተቀር
ከህይወት በስተቀር ምንድን ነው ትርጉሙ
ያጭሩ ቁምጣ ሀዘን ከበዛበት ከሀሳብ ሌላ ምን ታምር ይገኛል ፀጉር የሚያነጣ ከዚህ ሁሉ በላይ ልብህ የሚደማዉ
ዉስጥህ የሚቆስለው
ትንሽ ዝቅ ብለክ በጭድ ተሸፋፍና በደም ተለወሰ ደብዘዝ ብላብህ የአስር ብር ምስል ጭቃዉ ላይ ታያለህ ይሄዉ ነው ህይወቴ ይሄው ነው ህይወትህ ከሰአሊዉ ስእል ላይኔ የሚታየኝ ላይንህ የሚታይህ
ምስኪን ጭቃ ረጋጭ ምስኪን ሽማግሌ በስባሪ ጠርሙስ እግሩ ደምቶ ቆስሎ
አስር ብቻ ነበር የተቀበለዉ ብር ለድካሙ ዉሎ እናም ስእል ማለት ዝብርቅርቅ አደለም
ዉስብስብ አደለም
ኑሮ ነው ህይወት ነው
የኔና የአንተ አለም----
👍1
📕የሼህ ሁሴን ጅብሪልን ትንቢታዊ ግጥሞች በ PDF📙
👇👇👇
#የቅዳሜ #ማስታወሻ
.
.
ልባቸውን አይቶ
እግር የነሳቸው ፣ ቀርፋፋ ቀናቶች
ዘልዛላ ለሊቶች
እንደ ማቱ ሳላ ፣ እድሜ የሚያዘግሙ
ከሰኞ ተነስተው ፣ አርብ እስከሚያከትሙ
በስራ በትምህርት
በስብሰባ ብዛት
በሰበብ ባስባቡ ፣ ሲያቀጥኑኝ አክርረው
እንደ ጠቦት ቆዳ ፣ ሲሰቅሉኝ ወጥረው
በአማራሪ ቀኖች ፣ የማልማረረው
እራሴን ለማጥፋት
ብዙ ጊዜ አስቤ ፣ ሀሳብ ምቀይረው
ለቅዳሜ ስል ነው።
።።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው ፣
አደረች አራዳ ፣ ዘፈን ይለቀቃል
አሳዳሪ አራዳ ፣አልጋቤቱ ያልቃል
እንደጉድ ይጠጣል ፣ ይሰከራል በጣም
ነይና ላሳይሽ
ቅዳሜ የቀረ ፣ ዘላለም አይመጣም።
።።።።
ዛሬ ቅዳሜ ነው
በየመጠጡ ቤት ፣ ገርበብ ያሉ ጭኖች
በየ ጎዳናው ላይ
ቆንጆ ሴት የጫኑ ፣ ጢኒኒጥ መኪኖች
በየ ፋርማሲው ቤት
ፅንስን የሚያመክኑ ፣ እንክብል ኪኒኖች
የሚያዘዋውረው
የሚመነዝረው
የሚያመነዝረው ፣ እንደጉድ ይበዛል
ፌስቡክ ላይ ምታውቂው ፣
በስካር ጠንብዞ
ፖስት የሚያደርገውን ፣ ሚሪንዳ ይገዛል
"ይህች ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው? " ፣ ብሎ ላይኩን ያባዛል።
።።።
ነይና ላሳይሽ
ጨዋ የሚባል ህዝብ ፣ ጠፍቶት ትርጓሜ
ቀሚስ የሚባለው
የት እንደሰረሰ ፣ አጥሮ እንደጷግሜ
የዝች ሀገር ጉዞ
ወዴት እንደሆነ ፣ መልስ አለው ቅዳሜ።
።።።
ነይና ላሳይሽ
የአልኮል ባህር ላይ ፣ የመረብ አጣጣል
መንግስት አልወርድ ያለው
ውስኪ እያወረደ ፣ ሴት ከቦት ይጠጣል
የቢራ ያጣ ሰው
ስለውስኪ አጠጣጥ ፣ አቃቂር ያወጣል
ጭፈራው ለጉድ ነው ፣
ጨፋሪው ብዙ ነው ፣ አያስጥልም ጠጠር
ዝቅ ቢሉ ጭን ነው
ጎንበስ ቢሉ ጡት ፣ ቀና ሲሉ ከንፈር
ነፃ ይታደላል
አንድ የሰከረ ሰው
እቺ ሀገር ወዴት ነው ፣ የምትሔደው ይላል።
።።።
ሁሉ እየተነሳ
ይቺ ሀገር ወዴት ነው
የምትሔደው ብሎ ፣ መጠየቅ ቢወድም
ነይ መልሱን ላሳይሽ
ወደ አልጋ ቤት እንጂ ፣ ወዴትም አትሔድም።
ዛሬ "ቅዳ" ሜ ነው
።።።
ግጥሟም ቅዳሜም ትደገም
።።በላይ በቀለ ወያ።።
#ብሂላዊ #ምክሮች

#ሀሜት:- ያለ መሳሪያ ሰዉን መግደል ነዉ
#ማጉረምረም:- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
#ቁጣ:- ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።
#ብስጭት:- የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የሀጥያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነዉ።
#መርገም:- አቅም ሲያንስ ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
#መሳደብ:- ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸዉ ሰዎች ዱለ ነው።
#ዋዛ #ፈዛዛ:- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።
#ዘፈን:-😕ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ፍላፃ ነው።
#ድንፋታ:- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ
ነው።
#በክፉ #ማንሾካሾክ:- ቀስ ብለዉ ሰዉን የሚገድልበት የአሳባቂዎች ጩህት ነው።
#ነገር:- ማመላለስ የሚዋደዱትን የሚለያዬበት የዲያቢሎስ የግብር ልጆች መሳርያ ነው።
#የአደራ #ገንዘብ #መብላት:- ሳይጥሩ ሳይግሩ የሰዉ ላብ ሲበሉ የሚኖሩበት የሰነፍ ሰዎች መሳርያቸዉ ነው።
#ሰዉን #ማስነወር:- ሰዉ የወደደዉን የተከበረዉን ስም ለማጥፋት የሚቀቡት የምቀኞች ቀለም ነው።
#መሳለቅ:- የማይታይ የቀናተኞች ጦር ነው።
#ተስፋ:- ከማጣት ወደ ማግኘት ለመሸጋገር የሚያገለግል ድልድይ ነው።
#ጠብ:- እሳትን ለማንደድ የሚጫር የነገረኞች የኪስ ክብሪት ነዉ።
#ችኮላ:- የትእግስት ጠላት የፀፀት አባት ነው ልጁም ወይኔ ይባላል።
#ሙከራ:- የስራ ጥልቀትን መለኪያና መመጠኛ ነው።
#የጥበብ #መጀመርያ #እግዚአብሔርን #መፍራት #ነው
ከ ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር መፅሀፍ የተወሰደ በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ
👍2
#ሰማይ_እና_ውዴ

ይሄውልሽ ውዴ
ባይኖቼ አማትሬ ፥ ሰማዩን እያየሁ
ውሎና አዳርሽን
ባፍቃሪ ልቦና ፥ መገመት ችያለሁ።
ሰማይ ፍንትው ሲል
ሰማያዊ መልኩን ፥ በገላው ሲደፋ
ከአድማስ መነሻ
እስከ አድማስ መቋጫ ፥ ሲያውለበልብ ተስፋ
አዋፋት ሳይሰጉ
ሲበሩ ሲቀዝፉት ፥ በላዩ ሲዋኙ
ንስንስ ነጫጭ ጌጦች
የዳመና ገጾች ፥ ገላው ላይ ሲገኙ
አንቺ ተደስተሽ
በፍፁም መፍለቅለቅ ፥ የዋልሽ ይመስለኛል
የሰማዩ ቀለም
ሰማያዊው መልኩም ፥ ምስክሬ ሆኗል።
ደግሞ ሌላ ጊዜ
ሰማይ መልኩን ቋጥሮ ፥ ደርሶ ሲያስገመግም
በመብረቅ ትርኢት
ብልጭ ድርግም ሲል ፥ ጩኸት ሲደጋግም
እዬመላለሰ
አሁንም አሁንም ፥ ሲያምቧርቅ ሲያጓራ
አዋፋት ሸሽተውት
እንሸሸግ ሲሉ ፥ በጎጆቸው ጣራ
ዛሬ ተናደሻል
ግልፍተኛ ቁጣ ፥ ወርሶሻል እላለሁ
የቋጠረ መልኩን
ከጩኸቱ ጋራ ፥ ሰማዩን እያዬሁ።
ደግሞ አንዳንድ ጊዜ
ዳመናን ሰብስቦ ፥ ሰማይ ሲዝረበረብ
ዶፍ ጥሎ በፍርጃ
ምድርን ሲያጨቀያት ፥ ገላዋ ላይ ሲሰንብ
የሀዘንሽ ምክንያት
ምሬትሽ ሳይገባኝ ፥ አለቀሽ እላለሁ
የእንባሽን ክብደት
በዝናቡ መጠን ፥ በዶፉ እለካለሁ።
ይሄውና እንግዲህ
ባፍቃሪ ልቦና
ውሎና አዳርሽን ፥ አይቼ ስመዝን
የውስጥሽን ስሜት
ደስታና ሀዘንሽን ፥ ቁጣሽን ስተምን
ሰማይ ነው ምስክር
በማይነጥፍ መልኩ ፥ የሚያሳዬኝ አንቺን፡፡

--ከሚኪ--
👍1
Re.Post
#ለመለስ #የተፃፈ #ደብዳቤ
፨ ፨
.
.
እንደምን ነህ ጋሼ ፣እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ፣ ቀረህ ሳትመለስ?!
.
እኛማ ይሔውልህ
ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ
በየአደባባዩ ስንል ነበር ዋይ ዋይ
አዎ ትዝ ይለናል
ጀነራልህ ሁሉ ፣ ተኩስ ነው ትእዛዙ
ወገን ይጥል ነበር ፣ የግፍ አፈሙዙ
ለምንድን ነው ስንል? ስምክን አስቀድመው
ከክርስቶስ በላይ ፣ምስልህን አትመው
ቅዱስ መፅሐፍ ይመስል
ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው
ቢረፈርፉንም አላለቅንምና
ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው!
~
የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ
እኛማ ይኸውልህ
ደርሰህ ስትናፍቀን
አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን
መቃብርህን ልንስም ፣አበባ ልናኖር ፣ስላሴ ብንመጣ
ፌደራል ያይሃል ፣ እስረኛ ይመስል ፣ ሾልከህ እንዳትወጣ
መቼም ስላሴ ውስጥ...
ባለስም ነውና ፣ የሚቀበርበት
አንተን አየት አርገን ፣ ዞር ስንል ድንገት
እነፊታውራሪ
ግራ'ዝማች
ቀኝ'ዝማች
ፊተኛ ባለስም ፣ የሆኑት አባቶች
ያለዘብ ቆመዋል ፣ እነ አብዲሳአጋ
ጀግና መሃል ሳለህ ፣ ምነው በድንህ ሰጋ?!
~
የሆነስ ሆነና
ሃየሎም ደህና ነው
እዛም ትግል ይመራል?
እስር ቤት ሰባብሮ ፣ታራሚ ያስፈታል
እዛም ከፊት ሆኖ ፣ ጭቁን ያታግላል
እዛም በጀግንነት ፣ በለኮሳት ሻማ
ነፃ ነኝ ባለባት ፣ ርዕሰ ከተማ
ትንሽ ግሮሰሪ ፣ ይገባ ይሆን ደፍሮ?
እዛስ ጀማል ያሲን ፣ ፈጠረ አምባጓሮ?
ሃየሎምን ሰዋው ፣ በሐሺሽ ናላው ዞሮ?
።።
እኛማ ይኸውልህ
ብዙ ሃየሎሞች ፣ ፈጥረን ስናበቃ
እልፍ ጀማል ያሲን ፣ ይሆናል ጥበቃ
ይኸው ባደባባይ
የጀግኖቻችን ደም ፣ በየቦታው ፈሶ
አለ ጀማል ያሲን ፣ ሞት ሚበይንበት ፣ ፍርድ ቤቱ ፈርሶ!!
~
ግን አንተ ደህና ነህ
አቡነ ጳውሎስስ ፣ብፁው እንዴት ናቸው
እዚያም እንደምድሩ
አንድ አንቀፅ ያክላል ፣ መጠሪያ ስማቸው?
ደረታቸው ግድም "ሽጉጥ" የሚያደርጉት ፣ አለ መስቀላቸው?
።።።
እኛማ ይኸውልህ
ጳጳሳት አስታርቀን ፣ ሾመን በአደባባይ
ቃላቸውን እንጂ ፣ ዘራቸውን ሳናይ
አለን በአንድ ላይ።
የሆነው ሆነና...
አቡነ ጳውሎስ ፣ ጳጳሱ እንዴት ናቸው
ደረታቸው ግድም ሽጉጥ የሚያደርጉት አለ መሥቀላቸው?
እዛም ትውልድ ሲያልቅ
ወገን ደሙ ሲፈስ
እምነትሲተራመስ ፣ አያውቁም ግሳጤ?
እዛም ታጋይ ናቸው?
ቆባቸው የጳጳስ ነብሳቸው የአጤ?
~
እንደምን ነህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ
~
~
~
ከቻልክ ፃፍልን ለደብዳቤያችን መልስ!!
👍1👎1
#ክራር #እና #ፍቅር

ትግስት በሌላት በጨከነች ሌሊት
ወዳጅ ለወዳጁ ደብዳቤ ፃፈላት
ከመፃፉ በፊት ...
ከጥቁር ሰማይ ላይ ሦስት ኮከቦች አየ
ለጥቂት ቅፅበታት ከከዋክብቱ ላይ ሀሳቡን አቆየ
አንደኛዋ ኮከብ እጅግ የደመቀ ብርሃን ትረጫለች
ሁለተኛዋ ግን ደመቅ ትላለች ካንዷ ትሻላለች
ሦስተኛዋ ደሞ እርሱን ትመስላለች
በሁለቱ መካከል ፈዛ ትታያለች
እርሱን ለምትመስለው ብዕሩን አነሳ
ሁለቱን ከዋክብት ልቡን አወረሳ
አሁንም ዳግመኛ ከመፃፉ በፊት
ከአንድ አመት ቀድሞ በርሷ የተፃፈ ደብዳቤዋን አየው
የደብዳቤው ሀሳብ የደም ዕንባ አስነባው
እንባው ማፍቀሯ ነው መፈቀሩም እንባው
የሀሳቧም ሀሳብ ለሁለት ዘላለሞች
አፈቅርሃለሁ ነው
በትንሹ ታምኖ ብዙ ያልወደደ
ስለተፈቀረም ትንሽ ካላበደ
በትንሽነቱም ያልተወላገደ
ፍቅርን እንዴት ያውቃል እንዴት ይረዳዋል
ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
የሆነ መስመር ላይ አስተውለው ብለሽ ከታች ያሰመርሽው
ፊደል እስኪጠፋው እጁን ያሰርሽበት
የፍቅር ቀለማት የማይጠፉ ቃላት
የእውነት መገነዣ ሌላ ያንቺ እውነት
ያንቺ እውነት ፍቅር የርሱ ፍቅር ፊደል
ካፈቀረስ በቀር ፍቅርን ማን ይገልፃል
ማንበብ ክፉ ነገር መፃፍ መገላገል
ይሄ አይደል መታደል
ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
አስተውለው ብለሽ የሆነ መስመር ላይ ከታች ያሰመርሽው
ይልቅ ያን አስታውሰሽ የክራሩን ድምፅ አሰሚኝ
የዜማ ድምፅ ከዚያ ይውጣ
እኔም ክሩን ሆኜ ባንቺ ጣት ልቀጣ
እኔና አንቺ እንዲያ ነን በሁለት አንድነት ዝንት አለም የታሰርን በቅኝት ቢወጣ ጣት እና ክር ነን
ወይም ድምፅ እና ክር
ፍቅርን ጣት አርገነው ባንድነት ምንዘምር
ምን ነበር የፃፍሽው ምንድን ነበር ያልሽው
በፃፍሽው መስመር ላይ መብረቅ ፍቅር አለ
የዝናብ ድምፅ የለም ደመና ግን አለ
ከደመናው በፊት የደብዳቤሽ ቃላት
አንተ ማለት ባህር እኔ ማለት ትነት
በፀሀይ ፈገግታ ጨውን የምንፈጥራት
አንተ ማለት ጸጸት እኔ ማለት መዳፍ
የቀደመ ዕንባህን ካይንህ ላይ የምገፍ
አንተ ማለት ጥማት እኔ ደሞ እርካታ
በበርሀ ንዳድ የምገኝ ጠብታ
ማንበቡን ቀጠለ
የመብረቅ ብልጭታ የዝናብ ድምፅ አለ
በጥቁር ደመና ቀድሞ የታዘለ
ደብዘዝ ያለ ብርሃን የማትታይ ፀሀይ
የተኳረፈ ፍቅር ያረገፈ አደይ
በሁለታችን አዝኖ የተከፋ ሰማይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
መዳፍሽ እርቋል
ጨውነቱም ጠፍቷል
ቃሎችሽ ሰክረዋል
በዚያ ታላቅ ዝናብ ምድር ስትቀጣ
በመብረቅ ብልጭታ ነፍሳችን ስትወጣ
እኮ በምን እግሬ ከደጃፍሽ ልምጣ
አንቺ እንደሆን ንግስት የመኳንንት ልጅ
ህንፃ ፍቅር ልብሽ ጉብዝናን የሚያስረጅ
እኮ በምን ሀይሌ ልርገጠው ያንቺን ደጅ
ማን በምን ጉልበቱ በየት ጀግንነቱ
ዝም ባለ ቅፅርሽ ያንቺ ጉርፊያ ነግሶ
ፊትሽን ፍራቻ ልቦናዬ ፈርሶ
በሳምንት ዘመንሽ ዐይኔ ደም አልቅሶ
እኮ በምን አቅሙ እንዴትስ ተደፍሮ ደጅሽ ይረገጣል
አይኑስ እንዴት ደፍሮ ዕንባውን ጠራርጎ ያንቺን ዐይን ያያል
ምን ነበር የፃፍሽው ወይስ እኔ ፃፍኩኝ
ከፍቅርሽ ላይ ወይን ደብልቄ ጠጣኹኝ
ፍቅር እና ወይን
የሁለት አንድነቱን የጣትና ክሩን
በስልት የተቃኘ ክር ድምፅነትን
ፍቅርን ጣት አርገነው በተነካን ቁጥር
በስሱ ከላይዋ እንደተመታች ክር
በራሳችን ቃና በራሳችን መዝሙር
ለዘላለም እድሜ ባንድ ተገመድን
ወይስ ምንም ሆንን
እውነት ምንም ሆንን
ዜማ ሰጭ ፍቅራችን ተበጠሰ ላላ
የኛ ቅኝታችን በኔነት ተበላ
ያለሙያው ገብቶ ያለመጠን ነክቶ
ያለስልቱስ ቃኝቶ
ክራር ፍቅራችንን ክሩን ማን በጠሰ
በምን አይነት ስልትስ ዜማችን ታደሰ
ከሐሳቡ ነቃ
በራሱ ክር ላይ የራስ ስልቱን ቃኘ
ለደብዳቤዋ መልስ ሊመልስ ተመኘ
ላንተ ያለችውን ላንቺ ብሎ ፃፈ
በራስ የቃል ስልቷ ቃሉን አከነፈ
ረስቶት ነበረ ...
ከጠረቤዛው ስር በፅዋ ተሞልቶ ወይኑ ተቀምጧል
ጥቁር የወይን ደም ከፅዋው አንስቶ አንደዜ ጠጣለት
አንዱን ሳያጣጥም ፅዋዉ ወደቀበት
የፈሰሰው ወይን ልብሱን አረጠበው መሬቱን አራሰው
ፍንጥቅጣቂው ደሞ አይኑን አስለቀሰው
የብርጭቆው ፅዋ አልተሰባበረም
ሁሉም ፈሶበታል የተረፈ የለም
ለመፃፍ ከበደው
ደብዳቤው ቀፈፈው
መሬት አጎንብሶ እጁን ተንተርሶ
ስለሆነው ሁሉ ያስተውል ጀመረ
እንቆቅልሽ
የወደቀ ፅዋ ያልተሰባበረ
የፈሰሰ ወይን ባንድ ጉንጭ የቀረ
ያላለቀ ፅሑፍ በረቂቅ የኖረ
ያኮረፈች ፍቅር ደጇ የታጠረ
አራቱ ሚስጥሮች ሳይተረጎሙ ሳይመረመሩ
ባፍቃሪው ልቦና እንቆቅልሽ ሆነው ለዘላለም ቀሩ
ከኤፍሬም ስዩም
#ተፈጥሮን #ደጅ #ልጥና
" እኔ ልሙትልሽ እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፣ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፣ ታጠበ ሸሚዜ
ገደብ ጫፍ በሌለው፣ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፣ ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፣ ከፎቅ ላይ አልወድቅም
በሀኪሙ ስተት ፣በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፣ ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ፣ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፣ሽጉጤን አልጠጣም።
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ ፣ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፣ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፣ ከመሞት ምን ሊገኝ?
➛ገጣሚ ፦በእውቄ
🎅 ሳንታና ዛፉ 🎄

ባልና ሚሲት ናቸዉ የገና ዛፉን በማስዋብ ላይ ይገኛሉ ምንም የቀረ የለም መብራቱ ጥጡ ሁሉም አለ❗️❗️በድንገት❗️❗️ የሚያስገመግም ድምፅ ተሰማ...ጓ..ጓ..ጓጓጓጓ.ጓጓ..ጓጓጓጓጓጓጓ
ከመቅፅበት ባልየው ከቦታው ጠፋ..😳
ሚስት፦ጥሎኝ ወዴት ገባ?
#ባል፦ነይ ከዛፉ ጀርባ

#ሚስት፦በዚህ በጨለማ ሲደበደብ ይህ በር
አንተ አብረክኝ ባትኖር ምን ይዉጠኝ ነበር
ጓ...ጓጓ..ጓጓጓጓ.........ጓጓጓጓጓጓጓጓጓጓጓጓ

#ሚስት፦አዉጭኝ አደራሽን እማምላክ የዛሬን
ጓጓጓጓጓጓጓጓጓ...

#ባል፦አሁን ባይኔ መጣ በህግ አምላክ በሬን
ሽሽሽሽሽሽ.......

#ሚስት፦በቁም ሸና ይዉልህ ድምፅክን ሲሰማ
ሽሽሽሽሽሽሽሽ

#ባል፦በሲቃ ድምፅ በቃህ ተበላሸክ
መጣዉልክማ

#ሚስት፦በቁም ሸና ይሄዉልክ
ሽሽሽሽሽሽሽ

#ባል፦በል ሽሽ መጣዉልክ ኦኦኦ!! ይላል ባል ካለበት ሳይወጣ በህግ አምላክ ማነክ በሬን የምትመታ የባል አይኖች ላይ እንባ ይታያል

#ሚስት፦እግዞ የኔ ጌታ በሩ ተከፈተ

እህህም...እህህም..

#ባል፦ማናቹ እናንተ ምንድን ነዉ እህህም

ሰባ ሰገል፦እንዴት አይገባክም ሰባ ሰገል ነን ቤተልሄም ድረስ ኮኮብ የመራን
ከግርግሙም ስር ወድቀን የሰገድን
እጣኑን ያጨስን ወርቁን የሰጠን

#ባል፦ ምን መጣብኝ ዛሬ

#ሚስት፦ፍቅሬ

#ባል፦አቤት

#ሚስት፦እባክክ ዉሰደኝ ወደ መኝታ ቤት

#ባል፦ይሄ ነዉ የቀረሽ ልሸከምሽ እንዴ

#ሚስት፦ስሞትልክ ዉዴ ፈራዉ በጣም ፈራዉ አዉጣኝ ከዚ ፍርጃ

#ባል፦ከፈራሽ ተነስቸሽ በገዛ እግርሽ ሂጃ

#ሚስት፦እንዴት ብዬ እኔማ ዝልፍልፍ አለብኝ
እግሬ እንደ ቄጤማ ምክንያቱ ምንድን ነዉ

#ባል፦አይዞሽ ተረጋጊ እዚም እንደዛዉ ነዉ

#ሚስት፦አንተም ደንግጠካል እኔ እኮ አላምንክም

#ሰባ ሰገል፦እህህም እህህም

#ባል፦ምንድን ነዉ እህህም

#ሰባ ሰገል፦እኛ ብንጠይቅህ አንተ መልስ የለክም

#ባል፦መች ተጠየኩና?

#ሰባ ሰገል፦አንተ መልስ ካለክ ጥያቄዉ ይህዉና
በልስቲ ንገረን ምንድን ነዉ ትርጉሙ
በቤትክ ወለል ላይ ይሄ ዛፍ መቆሙ

#ባል፦ያዉ ገና ሲመጣ ብርሀነ ልደቱ
ይህን ዛፍ ያቆማል ሁሉም በየቤቱ

#ሰባ ሰገል፦አጀብ ነዉ ይገርማል ይህ ተረተረት
ህፃኑ ተወልዶ በተኛበት በረት
መች ዛፎች ነበሩ መች ዛፎች ተገኙ
ግልገል በጎች እንጂ አብረዉት የተኙ
ከቤተል ጥድ ከከተማዉ ዝግባ ጨቅላዉን ለማየት ከበረት የገባ አንድ ዛፍ ከሌላ ለምንድን ነዉ ዛሬ ግልገል እና ጥጃ ሙክትና በሬ
ከሰዉ ጆሮ ቀድመው የሰሙትን ወሬ የምታሸክመዉ ለዛፎች ጎፈሬ
መቼስ ግርግም እንጂ ከበጎቹ ጋራ
ጫካ ዉስጥ እዳዉሬ
ዛፍ ላይ እንዳሞራ ጌታ አልተወለደ
ታድያ ይሄ ደማቅ ዛፍ በመብራት ያበደ
ብርሀነ ልደቱን እንዴት ይወክላል

#ባል፦አሁን ጉድ ይፈላል

#ሚስት፦እንዴ!!

#ባል፦ምነዉ ዉዴ?

#ሚስት፦እኔጃ ፈራሁኝ ነገሩ ምነድን ነው? ልቤ ቱር ብሎ ባፌ ሊወጣ ነዉ

#ባል፦አይዞሽ ተረጋጊ እዚም እንደዛዉ ነዉ

#ሚስት፦ይሄን ቢመለከት አገር ጉድ አይልክም
ሰባ ሰገል፦እህህም እህህም

#ባል፦ምንድን ነው እህህም?

#ሰባ ሰገል፦እኛ ብንጠይቅህ አንተ መልስ የለክም

#ባል፦ጥያቄዉን ሳልሰማ

#ሰባ ሰገል፦እንግዳዉ ተጠየቅ መልስ ካለክማ
ንገረን አንተ ሰው በዛፉ ቅጠል ላይ የተነሰነሰዉ
ይህ ጥጥ ምን ይባላል?

#ባል፦ያዉ ያዉሮፓ ክረምት ትንሽ ከበድ ይላል ታድያ ያ ዉሽንፍር ያ ከባድ በረዶ ከጭጋጉ ክምር ተንዶ ተንዶ ቁልቁል ወደ ምድር የወረደ ለታ ይህንን ይመስላል የዛፉ ገፅታ

#ሰባ ሰገል፦ይሄ ሰው ምን ይላል አረ እግዜርን ፍራ
ያላየ ከሚዋሽ የነበርን እናዉራ ያኔ ቤተልሄም ህፃኑ ተወልዶ ባየንበት ምሽት ጥሎል ወይ በረዶ? ነበር ወይ ዉሽንፍር ዛፍ የሚያጨላልም አጥንት የሚቆፍር በርግጥ በዚያ ሌሊት በረዶ ካለማ ሰማዩ ተጋርዶ በጭጋግ ደመና
እንዴት ይታየናል የኮኮቡ ፋና
እንኮን ጥቁር ጭጋግ የለም ስስ ደመና
ሌሊቱ ደስ የሚል ሰማዩ እጅግ ደማቅ
አልተከናነበም ጥቁር ጉም እንደማቅ
ይመስገን ፈጣሪ ረግ ረግ አልዋጠን የበረዶ እቋሪ
ዶፍ አልቀጠቀጠን
ጎርፍ አላጨቀየን
ጥርት ባለ ሰማይ ከወክብት እያየን
ኮከብ እየመራን
መገስገስ ስንጀምር
ከየት መቶ ታየክ የበረዶ ክምር የዉሽፍር ጫናዉ

#ባል፦ይሄ ነዉ ፈተናዉ

#ሚስት፦እንዴ

#ባል፦ማነው ዉዴ?

#ሚስት፦ፈራዉ ለመናገር አንድ ነገር አለ ቀዝቀዝ ያለ ነገር እግሬ ስር የሚሳብ

#ባል፦ከአይምሮሽ አዉጪዉ ይህን የሞኝ ሀሳብ

#ሚስት፦እንጃ እባብ ነዉ መሰለኝ እግሬ ስር የገባዉ

#ባል፦ምንድን ነዉ መቦቅ ቦቅ በረባ ባረባዉ ረጋ በይ እቴ

#ሚስት፦እንኳን ልረጋጋ ሊያመልጠኝ ነዉ ሽንቴ

#ባል፦ አረ ተይ ነዉር ነዉ

#ሚስት፦ምን ላርግ አቃተኛ ምክንያቱ ምንድን ነው

#ባል፦አይዞሽ ተረጋጊ እዚም እንደዛዉ ነው

#ሚስት፦እንዲህ እስትሆን ድርስ አያሳፍርክም

#ሰባ ሰገል፦እህህም እህህም

#ባል፦ምንድን ነው እህህም

#ሰባ ሰገል፦እኛ ብጠይቅክ አንተ መልስ የለክም

#ባል፦ማን ጠየቀኝና

#ሰባ ሰገል፦አንተ መልስ ካለክ ጥያቄዉ ይሄዉና
ማነዉ ይሄ ቁዝር ሆድ ድብልብል ቁመና

#ባል፦ፈረንጅ ሳንታ ክላዉስ ሀበሻ አባ ገና እያለ ይጠራዋል

#ሰባ ሰገል፦ወይ አለማስተዋል እሱማ ከሆነ አባ ገና ማለት ግርግም ለዛ ህፃን ወድቀን ስንሰግድለት የት እንደነበረ ጠይቅል እስኪ
ገናን የማያቀዉ የገና ሰባኪ
ማን እንበለዉ ይሄን የድል አጥብያ አርበኛ ብንጠራም እኛ
ብንደርስም እኛ
ብንሰግድም እኛዉ ነን
በአፍጢም የተደፋን ጌትነቱን አምነን
ይሄዉ ዛሬ ደሞ አጭበርባሪዉ ሳንታ
ገና አባት ነኝ ብሎ ባመጣዉ ጨዋታ
ህዝብ እያታለለ ትዉልድ እያምታታ
እንዴት ገኖ ታየ ካምላክ ልደት በላይ ከኛ ጋር በግርግም ያልነበረ አታላይ

#ባል፦በቃኝ ከዚ በላይ

#ሚስት፦እንዴ

#ባል፦ይበቃሻል ዉዴ ሙግት አተካራ
ይሄንን ዛፍ ጥለን ግርግሙን እንስራ
ደህና ሁን አንተ ዛፍ

#ሚስት፦ደህና ሰንብት ሳንታ

#ሰባ ሰገል፦አሁን ተወለደ እዉነቸኛዉ ጌታ
ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ
ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ

#እንኳን #ለጌታችን #ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ #ክርስቶስ #የልደት #በዓል #አደረሳችሁ!
👍11😁1
#ልደት #በኛ #መንደር

ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
እንኳን ኬክ ተቆርሶ
ድግስ ተደግሶ
ሻማ ተለኩሶ
ልዩ ልብስ ተለብሶ
"መልካም ልደት" በሚል አንድ ሺ ሙዚቃ
የልደት ቀን ደምቃ
እንኳን ልትከበር
ከና'ካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
.
አሁን የኔ ልደት፣ የተወለድሁበት፣
መቸ እንደነበረ፣ እናቴ ዘንድ ሂደን፣ ንገሪን ብንላት
.
“መንግስቱ ኃይለ ማርያም መንደራችን መጥቶ
በጎበኘ ማግስት
ነበር የወለድሁት፡፡
ይሰማኝ ነበረ፣ የወታደር ሆታ
የተማሪ ጩኸት፣ ያይሴማ እልልታ
ምጥ የያዘኝ ሌሊት፣ ምጥ የያዘኝ ማታ፡፡
ታዲያ በዚህ መሃል፣ ኢሃፓ ተኩስ ከፍታ
የአቶ አበበን ድርቆሽ፣ ባብሪ ጥይት መትታ
የመስቀል ደመራ፣ ሲመስል መንደሩ
ወንዱ ተኩስ ሲገጥም፣ በየ ጉራንጉሩ
ነበር የወለድሁት፡፡
.
በዚያ ጭንቅ ጨለማ
የአካሌን ክፋይ
ጨቅላውን ታቅፋ፣ አዋላጇ ቁማ
'‘ተነሽ መዓት መጥቷል፣ እንውጣ ከዚህ ቤት
ካ'ዲሱ ፍጡር ጋር፣ እንዳይበላን እሳት’'
ስትለኝ ብነሳ፣ ወገቤን አስሬ
በነበልባል እሳት፣ ጠፍታለች መንደሬ
የምጤን ሁኔታ
ያችን የ’ሳት ማታ
ዘወትር እንዲኖር ልቤ እያስታወሰ
የወለድሁትን ልጅ አልሁት እሳቱ ሰ”
ነው ምትልክ
እና...
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
የልደታችን ቀን፣ እንኳን ልትከበር
ከናካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር

፨፨ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን፨፨
👍1
🔅ካፑችኖ🔅

ሰዉ ጠልቼ ነበር።ራሴን ከግርግር አግልዬ-ብቸኝነቴን አግዝፌ -ለራሴ እያወራሁለትና በሚደልል ፈገግታ እያወፈርኩት ስኖር- -በሆነ ቀን እሷ ወደ ብቸኝነቴ ዉስጥ ለመግባት መጣች።

ቀኑን <<የሆነ>> ያልኩት- የተረገመ ይሁን የተቀደሰ ለማወቅ ከችሎታዬ በላይ ስለነበር ነዉ።

ካፑቹኖ አዘዘች።እኔም እሱን።ከዛን እለት አንስቶ -አብራኝ ኖረችም አልኖረች -ካፑቹኖ እጠጣለዉ።በጠጣዉ ቁጥር -አብራኝ ኖረችም አልኖረች- ከእኔዉ ጋር እንደሆነች ይሰማኛል።

ካፑችኖና ህይወት አንድ ሆኑ።
ከሌላ ሴት ጋር ሻይ ቡና ለመባባል ከተቀመጥኩ ካፑቹኖ አዝዛለሁ።ሴቶችም ካፑቹኖ ካልጠጡ አምርሬ ነዉ የምጠላቸዉ።

ሞቆኛል።

የከሰአቱ ጠራራ አይደለም የወበቀኝ ።

ያዘዝኩት ካፑቹኖ ምላሴን ተኩሶታል ።የሞቀኝ ግን እሱ ብቻ አይደለም ።እሷ የለችም (የት እንደሄደች ማዉራት የዚህ ታሪክ አላማ አይደለም )።

ብቻዬን ነኝ ።ግን ትሞቀኛለች።

በተደጋጋሚ በተገናኘንባቸዉ ጊዚያት -እሷ ሌላ ነገር ስታዝ እኔ ካፑቹኖ እጠጣለዉ።ስጠጣ ትስቃለች። ስትስቅ ሳቄን ከተሸሸገበት ዋሻ ታወጣዋለች።የሷን ሳቅ ካላየሁ መሳቄ ተራ ማግጠጥ ነው የሚሆኑብኝ።

ቀለሟ ደፍረስ ይላል - - ካፑችኖዉ ላይ የሚነሰነሰዉን ቅመም ትመስላለች - - ፀጉሯ ጥቁር አይደለም - የካፑቹኖዉን ቅመም ነው
የሚመስለዉ።

ሕይወት እንድታምር ደግሞ ቅመም ያስፈልጋታል

እኔ ግን ምን ነካኝ ?

ያለካፑችኖ ሕይወቴ ሰላም ያጣል - - ያለካፑችኖ ዉስጤ ደስታዉን ይነጠቃለል።ያለካፑችኖ ።አለሜ የዝንት አለም ግግር በረዶ ነው።

ዛሬ እሷ የለችም ብያለሁ - - - እሷና እኔ በብዙ ማይሎች ተራርቀናል ። እየተገናኘን ካፑቹኖ የጠጣንባቸዉ - አራት እንደጢንቸል በራሪ አመታት ካለፉ - ስምንት እንደግመል ሽንት የረዘሙ - የተጎተቱ አመታት ተቆጥረዋል ።

እኔ ግን ምን ነካኝ - - - አስራ ሁለት አመት ሙሉ ! ?

ይችኛዋ ሴት ነጭ ። ወተት ግን አላማረኝም - - የናቴም ጡት ትዝ አላለኝም ።

<<ወተት ጠጪ>> አልኳት

<<ለምን?

<<የሆንሽዉን ወይም ለመሆን አቅም ካነሰሽ- የመሰልሽዉን መዉሰድ አለብሽ>>

<<አንተስ ምን ትጠጣለክ ?>>- ለመሳቅ ምከረች ። ሳቆ ግን ሳቄን የማጫር አቅም አልነበረዉም ።

<<እኔ ካፑችኖ ነዉ የምጠጣዉ ። >>

<<ግንኮ ቡና ነዉ የምመስለዉ >>

ተቆጣኋቸ- -ደግሞም ቀፈፈችኝ ወተት መሆኗ ዉበት መስሏታል ። የሚገርመዉ - ይቺ ነጭ ሴት የምመስለዉን እንጂ የሆኑኩትን አታቅም ። መምሰል ደግሞ - በዉስጤ ሞቷል - - በዉስጤ ነፍስ የዘራዉ መሆኑ ነዉ ።

እኔ ካፑችኖ ነኝ ።

እናም ካፑችኖ አዝዤ እጠጣለዉ።

አይኗ በግርምት እላዬ ላይ ተሰንቅሮል ። የወተት እይታ ጠንካራ አይደለም ። ለጋና ስስ ነው ። ግን ለምን ይገርማታል ?

እኔ ካፑችኖ ነኝ።

እኔም ቀኔም በብቻነት የጠቆርን ቡና አደለንም። እኔም ቀኔም ደፍርሰናል - - እኔም ቀኔም ቅመም ተነስንሶብናል - - እኔም ቀኔም ቅመም ሆነናል - - እኔም ቀኔም ሂወት አጣፈጠናል ።

የሰዉ ልጅ መጀመርያ የወደደዉን እንደሆነ ይቺ ወተት ይገባት ይሆን ? "

<<እስቲ ጨዋታ አምጣ ?>>አለችኝ እራሷን ለሰፊ ወሬ እያዘጋጀች ።

<<የመጀመርያሽን መጀመረያ መተዉ ትችያለሸሰ ? >>

<<እንዴት ማለት--->>

<<የመጀመርያሽን መጀመርያ መሆን እንጂ መተዉ የለብሽም>> አልኳት፡

<<ምንድን ነዉ የመጀመርያዉ መጀመሪ
ያ>>

ካፑችኖ ነዉ !!

መጀመረያ ካፑችኖ ነበር - - መለያየት ሳይፈጠር መዋሃድ ስለነበረ- - -ቡና ሆኖ መጥቆር -ወተት ሆኖ መንጣት ኋላ መጥ ነው - -ዉህደት ላይ ሲቀመጡ ቡናም ወተትም መደፍረስን ይመርጣሉ
እናም ቅመም ይነሰነሰባቸዋል - -ሲደፈርሱ ካፑችኖ ሆነዉ ወደ ምንጫቸዉ በመፍሰስ ሕይወትን ያጣፍጣሊ።

እናም -ወተት አያስፈልገኝም ወተትም አልሆንም - - -አረ እንደዉም - ብሄድላት ወይም ብትሄድልኝ መልካም ይመስለኛል ። እኔዉ እራሴ ልሂድላት - - - የማታስፈልገኝን ወተት በ ተ ዘ ፈ ዘ ፈ ች በ ት ስንብቴን ሁሉ ነፍጊያት ወጣሁ።

እኔ የመጀመሪያዬ የሆንኩ - ካፑችኖ ነኝ።

በ ዮሃንስ ሐብተማርያም---
👍3
#እኔ #ላንቺ #ብዬ

ካንበሳ ደቦል ጋር ትግል ገጥሜለሁ

#ነብርን በካልቾ

#ዝሆንን በቡጢ አንከባልያለዉ

አንድ አገር ወጠምሻ ክንዱን አሳብጦ

ሊነካሽ ቢሰለፍ በሰከንድ ዉስጥ ሆኜ ቡጢ ሰንዝሪአለዉ

ጥርሶቹን ማርገፌን አስታዉሰዋለዉ

ብቻ ወ.ዘ.ተ ወ.ዘ.ተ ብዬሽ የነበረዉ
ሰክሬ ነዉ😳

እንደዉ ስታስቢዉ ከአንበሳ ደቦል ጋር
ሊያዉም ላንቺ ብዬ ስታገል የምገኝ

እኔ ታርዛን ነኝ

ማን አባቴ ነኝ

ብዙ ጎርሬአለሁ መቼም ስጋ ለባሽ ትንሽ ከቀመሰ የሚለዉን አያቅም

በይ እዉነቱን ስሚ እድሜዬን በሙሉ ከጠብ የምርቅ ሰው ነኝ

በተቻለኝ አቅም እንኳን ሰዉ ልመታ ነብርን በርግጫ እህ!! ከሩቅ ያየሁ ለታ ሞፋራን ያስንቃል የምሮጠው ሩጫ

አላወቅሽ
ከሁሉም ከሁሉም እኔ የገረመኝ
አንድ አገር ወጠምሻ ክንዱን አሳብጦ
ሊነካሽ ቢሰለፍ በሰከንድ ዉስጥ ሆኜ
ቡጢ ሰንዝሬለዉ ጥርሶቹን ማርገፌ ብዬ የነገርኩሽ እህ!! አይ እኔ..

ምንድን ነዉ እንደዚ ዝም ብሎ መተርተር መለክያ ሲጨበጥ ቲቢት በዝቶ ነዉ ልክ እንደ ህንድ አክተር እኔ ምልሽ

ባረቄ መአበል ልቤን አሳብጄ ጉራዬን ስነዛ
ከቻልሽ አረ ወደዛ
ወይም አረ ትንሽ በዛ

ብሎ እንደመሸሽ ሁሉንም ያመንሽኝ ምን ነክቶሽ ነው ዉዴ

ክሬዚ ነሽ እንዴ
ሰትገርሚ በናትሽ
👍5😁1
#ጅብ #የፃፈው #ግጥም

እንጦጦ ጫካ ውስጥ
የሰከረ ሰይጣን ፣ በልቶ የሰከረ
ብሶቱን ቁጭቱን
በሰው ልጆች ቋንቋ ፣ እያንጎራጎረ
አንድ ሰካራም ጅብ ፣ እንዲህ ሲል ነበረ።
።።
" ስማኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ፍረድ ያገሬ ሰው
እኔ የሀገርህ ጅብ ፣ ከሰው የማልደርሰው
ጫካዬን መንጥረህ
ህንፃ ስትገነባ
ወደሌላ ጫካ ፣ ለመኖር ምፈልሰው
ስሜን ከሰው ተራ
ዝቅ አርገህ አትየው ፣ ክብሬን አትቀንሰው።
የቀን ጅቦች ብለህ
የቀን ሰዎችህን ፣ በኔ ስም አትጥራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ ፣
ብቻ መብላት ማላውቅ ፣ ላካፍል ምጣራ
ማየት የሚቻለኝ ፣ በብርሐንና በጨለማ ስፍራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ
የቀን ሰው ስላልሆንኩ ፣ ኖራለሁ ስኮራ
ክብሬን ዝቅ አድርገህ
ክብረ ቢስ ሰዎችን ፣ በኔ ስም አትጥራ ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ እራስህ ፍረደኝ
እንደውሻ ባልለምድ ፣ እንደበግ ባታርደኝ
በሬ ባልሆንልህ ፣ አስረህ ባትጠምደኝ
አፈንግጬ ብኖር ፣
ላንተ ባልገዛ ፣ ሰው በስሜ አትጥራ
ዝቅ አርገህ አትየኝ ፣ ከቀን ሰዎች ስፍራ
አዎ የቀን ጅብ ነኝ
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀንበቀን ምኮራ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ ፍረድ የኢትዮጵያ ህዝብ
እኔ የሀገርህ ጅብ
እንደ ሰው ጨክኜ ፣ ጅቦችን አልበላም
በዘር ከፋፍዬ ፣ ጅቦች አላጣላም
የጅብ መሰቃያ ፣ እስርቤት አልከፍትም
ትውልዴን እንደ ሰው ፣ አላንኮታኩትም
ከጅቦች ቀምቼ
ለነገ ምበላው ፣ ሀብት አላካብትም
ልክ እንደ ቀን ሰዎች ፣ ሲያገኝ አይሰስትም
ጅብ መሆን ያኮራል
በጋራ ይበላል ፣ ምግብ አያሻግትም
ጮኾ አገኘሁ ይላል ፣ ጠርቶ ያካፍላል
እንዴት ከኔ እኩል
ክብረ ቢስ የቀን ሰው ፣ የቀን ጅብ ይባላል?
ሌላው ሌላው ቀርቶ
ይሞታታል እንጂ ፣ ጅብ ስኳር ይበላል?
ያውም ከነ ስኳር ፣ ፋብሪካ ቆርጥሞ
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
ጅብ ጅብን ይገድላል ፣ በጅቦች ተሹሞ?
ጅብ ህንፃ ይሰራል
ጅብ ጅቦችን ያስራል?
እንዴት ለቀኑ ሰው ፣ ጅብ ስሜ ይጠራል?
።።።።
አዎ የቀን ጅብ ነኝ ፣
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀን በቀን ምመካ
ሰው እንዳይበላኝ ነው
ከቀን ሰው ሸሽቼ ፣ የምኖረው ጫካ!!!

፨፨በላይ በቀለወያ፨፨
👍1
#አለመኖር

"መኖርም የሚጀመረው አለመኖርን ከመፍራት ነው"“
....የሰው ልጆች በመጀመሪያ በውልደት ወደዚህ አለም ስንመጣ፣ የመጀመሪያው ትግላችን ከአለመኖር ጋር መታገል ነው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ስለ ልጅ አወላለድ ሥርዓት ያስተማሯችሁ መምህሮቻችሁ የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከሚቀጥሉት አርባ አመታት በላይ የበለጠ ፋይዳ አለው ብለዋችኋል፡፡ እውነት ነው፡
ምክንያም የመጀመሪያው አንድ ደቂቃ ከመሞት በፊት ያለው ትልቁ የህይወት
ለውጥ ነው፡፡ በእርግጥ መምህሮቻችሁ ይህን ያስተማሯችሁ ህፃን ልጅ ሲወለድ
በአግባቡ አለመተንፈሱ በአንጎሉ ዕድገት ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ ለኔ ግን ከዚያም በላይ ፋይዳ አለው፡፡ ማለትም ሰው ሲወለድ የለመደው በጎ ነገር በጠቅላላ ይቀየራል፡፡
በእናት ሆድ ውስጥ ጥጋብ ነው፣ ረሃብ የለም፡፡ በእናት ሆድ ውስጥ ሙቀት ነው፤
ብርድ የለም፡፡ ከሁሉም በላይ ግን በእናት ሆድ ውስጥ ጣዕር የለም፡፡ መሥራም
የለም፡፡ በምቾት መንፈላሰስ እና በለስላሳ ውሃ ውስጥ መንሳፈፍ ነው፡፡ ይህ ሁሉ
ድሎት በተወለድንበት ቅፅበት ይለወጣል፡፡ መተንፈስ ግድ ይለላ፡፡ ረሃብን
ለማስታገስ መጥባት እንጀምራለን፡፡ ይበርደናል፤ ሙቀት ለማግኘት ከሌላው
እንጠጋለን ለመኖር፡፡ አለበለዚያ መኖር የለም፡፡ መታን፣ በረሃብ አለንጋ መቆላትና
በብርድ ቆርፍዶ መሞት የፍርሃታችን ሁሉ መነሻ ይሆናሉ፡፡ በእናታችን ማህፀን
ውስጥ የምናውቀው መኖርን ብቻ ነው፡፡ መውለድ ግን አለመኖር አመላካች ነው፡፡
ይህ ስጋት ታዲያ በህይወታችን ሙሉ የሚዘልቅ ነው፡፡ በየደረጃው፣ በየእድሜያችን ለአለመኖር ስጋት እንደተጋለጥን እንዘልቃለን፡፡
የምንኖርበት አለም ደግሞ የሰው ልጅ የዘመናት የአለመኖር ስጋን ለማስወገድ
በመመኘት የገነባው የአኗኗር ስርዓት አለው፡፡ ይህም ስርዓት ከመወለዳችን
ይረከብና፡፡ በወላጆች፣ ዘመድ፣ ጎረቤት፣ ሰፈር፣ ብሄር ቋንቋ፣ ባህል፣ ሃይማኖትና
ልምድ ያሉበት ዓለም ከእኛ ቀድሞ ይጠብቀናል፡፡ ይህ ሁሉ ባለበት ዓለም
ተወልደን፣ በእኚህ ቀድመው በተዘጋጁ ስርዓቶች ውስጥ አለመኖርን ሸሽተን
ለመኖር ስንል እንታሰራለን፡፡”
ከአለመኖር መፅሀፍ የተወሰደ።
👍3