አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ብሂላዊ #ምክሮች

#ሀሜት:- ያለ መሳሪያ ሰዉን መግደል ነዉ
#ማጉረምረም:- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
#ቁጣ:- ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።
#ብስጭት:- የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የሀጥያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነዉ።
#መርገም:- አቅም ሲያንስ ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
#መሳደብ:- ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸዉ ሰዎች ዱለ ነው።
#ዋዛ #ፈዛዛ:- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።
#ዘፈን:-😕ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ፍላፃ ነው።
#ድንፋታ:- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ
ነው።
#በክፉ #ማንሾካሾክ:- ቀስ ብለዉ ሰዉን የሚገድልበት የአሳባቂዎች ጩህት ነው።
#ነገር:- ማመላለስ የሚዋደዱትን የሚለያዬበት የዲያቢሎስ የግብር ልጆች መሳርያ ነው።
#የአደራ #ገንዘብ #መብላት:- ሳይጥሩ ሳይግሩ የሰዉ ላብ ሲበሉ የሚኖሩበት የሰነፍ ሰዎች መሳርያቸዉ ነው።
#ሰዉን #ማስነወር:- ሰዉ የወደደዉን የተከበረዉን ስም ለማጥፋት የሚቀቡት የምቀኞች ቀለም ነው።
#መሳለቅ:- የማይታይ የቀናተኞች ጦር ነው።
#ተስፋ:- ከማጣት ወደ ማግኘት ለመሸጋገር የሚያገለግል ድልድይ ነው።
#ጠብ:- እሳትን ለማንደድ የሚጫር የነገረኞች የኪስ ክብሪት ነዉ።
#ችኮላ:- የትእግስት ጠላት የፀፀት አባት ነው ልጁም ወይኔ ይባላል።
#ሙከራ:- የስራ ጥልቀትን መለኪያና መመጠኛ ነው።
#የጥበብ #መጀመርያ #እግዚአብሔርን #መፍራት #ነው
ከ ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር መፅሀፍ የተወሰደ በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ
👍2
#ማሂ_ድንግሏ


ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡

ቦይ ፍሬንድ አምሮኛል፡፡

“የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡እስከ ዛሬ ድረስ “
ትምህርቴን በሥርዓት ለመከታተል”፣ “ከአልባሌ ቦታ ለመራቅ”፣ “መቅደም ያለበትን ለማስቀደም” ፤ የከጀሉኝን
በአልገባኝም እየሸወድኩ፣ የጠየቁኝን እምቢ እያልኩ፣ ስንት የተቀበረ
የወንድ ፈንጂ በጥንቃቄ አልፌ ልጃገረድ ሆኜ ቆይቻለሁ፡፡

ኮሌጅ ከገባሁ ጊዜ አንስቶ ግን ከካልኩለስ በላይ ይሄ እየከበደኝ መጣ፡፡ አብሶ ሦስተኛ ዓመት ስደርስ፤ አብሶ 21 ዓመት ሲሞላኝ፣ አብሶ ጓደኞቼ ሁሉ ወሬያቸው በ“እንትና ደውሎልኝ ፣ በ“እንትና ቴክስት ልኮልኝ” ፣ በ“እንትና ስሞኝ” ሲጀምርና ሲያልቅ፤ እኔ ደግሞ ከወሬው መገለል ስጀምር፡፡

እኔ ስልክ የሚደውልልኝ ታላቅ ወንድሜ ብቻ ነው፡፡ ቴክስት
የሚደርሰኝ ከ8100 ብቻ ነው፡፡ ተስሜ የማውቀው አሥራ አንደኛ
ክፍል እያለን አሳስቶ (ለአራት ወራት) በቀመሰኝ ዮናታን ብቻ ነው፡፡

እነሆ! ድንግል መሆኔን ያወቁት የቅርብ ጓደኞቼ የቀልዶች መጀመሪያ ካደረጉኝ ቆዩ፡፡

አንቺ ልጅ ኧረ ተይ...! ኮርማ አምጥተን እናስጠቃሽ እንዴ...?”
“ቱሪዝም ኮሚሽን ስላንቺ ያውቃል...? ከድንቃድንቅ ቅርሶች መሀል
አስመዝግበው ያስጎብኙሽ እንጂ!”
የሆነ አራት ማእዘን የመስታወት ሣጥን ውስጥ አስቀምጠው ሊመረምሩሽ እንዳይመጡ......”

ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡

ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡

የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡ግን ቦይፍሬንድ እንዴት እንደሚገኝ፣ ልጃገረድነት እንዴት
እንደሚሰጥ፣ የኔ ፍቅር ለመባል በየት በኩል እንደሚኬድ አጥርቼ
ስለማላውቅ፤ ጓደኞቼ ሲወጡና ሲገቡ ማጥናት፣ አንዳንዴም ጥያቄ
መጠየቅ፣ አንዳንዴም ዝም ብለው ሲያወሩ ከዝባዝንኬው ፍሬ ነገር
መልቀም ያዝኩ፡፡

ልክ ክፍል ውስጥ ገብቼ ደብተሬ ላይ ዋና ዋናው እንደምጽፈው ፤
ከአፋቸው የሚወጡ ነገሮችን፣ ጆሮዎቼን አፋቸው ስር እንደ ባልዲ ደቅኜ መቅዳት ጀመርኩ፡፡

ብዙ ጊዜ የሚጠቅመኝን ነገር የምታወራው ግን ሰምሃል ነበረች::
ሰምሃል እንደ ኤቲኤም ማሽን?” ለወንዶች ሃያ አራት ሰዓት ክፍት ናት፡፡ በተለይ የሚስጥር ኮድዋን ለሚያውቁ::

የሴቶች ቪያግራ ገንዘብ ነው!” የምትለው ነገር አላት ገንዘብ ካገኘች እንደ ሕዝብ ስልክ ማውራት ትጀምራለች፡፡የተጠየቀችውን ታደርጋላች፡፡

አንድ ቀን ዶርም ለብቻችን ስንሆን ድፍረት አጠራከምኩና፤ "ሰሚ ሰምሃል...” አልኳት፡፡

“እንዳትሥቂ ግን...”

“በምን እሥቃለሁ...?”

“በምጠይቅሽ ነገር”

“ምንድነው.....? የሚያሥቅ ነው...?”

“ኦፋ! አትሳቂ አልኩሽ አይደል...?”

“እሺ.. ጠይቂኝ”

የእግር ጥፍሮችዋን ዐይን የሚያደነቁር ቀይ ቀለም እየቀባች ነው፡፡
ጎንበስ ብሎ ለሞከረ ከአውሮፕላን የሚታይ ይመስለኛል፡፡

“እ... ቦይፍሬንድ... ቦይፍሬንድ እንዴት ነው..... የሚያዘው...?
ማለቴ... መጀመሪያ ምን ማድረግ ነው ያለብኝ...?” አልሣቀችም፡፡

ገረመኝ፡፡

“ማሂዬ! የኔ ቆንጆ... ልብስ እንዴት ነው የሚገዛው...?” አለችኝ
ቀለም ቅቡን ትታ ወደኔ እያየች፡፡

ልብስ ስትገዢ ምንድነው ምታደርጊው...?”

"እለካለሁ!”

ወንድም እንደዛ ነው፡፡ ገበያ ትወጫለሽ፤ ያማረሽን ታነሺያለሽ፤
ትለኪዋለሽ፤ ካልጠበበ ወይ ካልሰፋ በልክሽ የሆነውን በዐቅምሽ ትገዣለሽ፡፡”

ብዙ ጊዜ የምትለው ነገር አይጥመኝም ነበር ይሄ ግን ልክ መሰለኝ፡፡

በልክ መግዛት፡፡ በዕቅም መግዛት፡፡ ግን ልኬ ማነው...? ዐቅሜስ
ምን ያህል ነው ? ወንድን “መለካትስ ምን ማለት ነው.....? ስንት
ምሳ ተጋብዤ እመርጣለሁ? ስንት ከንፈር ቀምሼ አውቃለሁ?
ከስንቱ ጋር ተኝቼ እወስናለሁ...? ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች
ነበሩኝ ግን፤

ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡

ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡

“የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡

ስለዚህ በፈራ-ተባ ቦይ ፍሬንድ ገበያ ወጣሁ፡፡ ምን ያደርጋል!
የምሄድበት ቦታ ሁሉ የኖኅ መርከብ ይመስል ካለ ጥንድ ብቻውን
የቆመ ሰው አጣሁ፡፡ አልፎ አልፎ ብቻውን የቆመ ባገኝም ፤ ለምሳሌ አንዱ መላጣ እና ሾጣጣ ጭንቅላታም ይሆንና፣ “አሁን ይሄ መላጣ፣ ሌላ ፊት አያሰራም?” እያልኩ ስሥቅ የቦይፍሬንድ
ግዢውን እረሳለሁ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያልኩ አቃቂር ሳወጣ ባዶ እጄን እመለሳለሁ፡፡

#ሙከራ_አንድ

ከዕለታት በአንዱ ቀን በሰምሃል አያያዥነት ከአብሥራ ጋር ተዋወቅኩ፡፡ ለነገሩ በፊትም አውቀው ነበር፡፡ “ጓደኝነታችን ሲጠነክርና በግ ተራ እየተቀጣጠርን መገናኘት ስንጀምር፣ የነገሩን አቅጣጫ በመገመት ለሚመጣው መዘጋጀት ጀመርኩ፡፡ የዚያን ጊዜ ነው ሰምሃል የአብሥራም እንደኔ፣ “ልዩና አስደናቂ ወጣት” እንደሆነ የነገረችኝ፡፡ ጎበዝ የማትስ ዲፓርትመንት ተማሪ ስለነበር፣ “በሂደቱ ላይ” ችግር ቢፈጠር መላ መምታት አይከብደውም ብዬ ብዙ አልከፋኝም፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ተከራይቶ የሚኖርበት ቤት ወስዶ፣
“የሚያሳብድ ሙዚቃ” ሊያሰማኝ እንደሚፈልግ ሲነግረኝ በጠዋት
ወጥቼ የውስጥ ሱሪ ገዛሁ፡፡ ቀይ፣ ባለ አበባ፣ የቂጤን አንድ አራተኛ ብቻ የሚሽፍን ሻፋዳ የውስጥ ሱሪ፡፡

እንደ ጎበዝ ተማሪ ባሕሪዬ ፤ ከዚያ በፊት በነበሩት ቀናት ግን ሰምሃልና ሌሎቹ ባሉበት የቅድመ ዝግጅት ጥያቄዬን ልምድ ላካበቱት እነሱ አቅርቤ ነበር፡፡

“ያማል?”

“አዎ ግን አሪፍ ሕመም ነው”

"ካደረግኩ በኋላ ወዲያው መቆምና መራመድ እችላለሁ?”

(ከህብረት ሣቅ በኋላ) “እንዴ! ስልክ እንጨት የምትውጪ መሰለሽ
እንዴ?” ሰምሃል ናት፡፡

ከሱሬ ጋር ካላደረግሽ... ቆመሽ ትሄጃለሽ” ሁሉም ጮኽ ብለው ሳቁ

“ሱሬ ደግሞ ማነው?” ሌላ የማላውቀው ነገር ከጣሪያ በላይ ሲያሥቅ
እኔ ግን መጠየቅ እየሰለቸኝ ጠየቅኩ፡፡

“ሱሬ ቲቪኤስ ነዋ! ሱሬን አታውቂውም?” ሰምሃል ተሽቀዳድማ።

“ሱሬ ማ?”

“ሱሬ ቲቪኤስ!” እንደገና ሣቁ፡፡

“ምንድነው ደሞ ቲቪኤስ?” እያመመኝ ጠየቅኩ፡፡

ሦስቱም በአንድ ጊዜ እንዳጠኑት ሁሉ እኩል “ባለ ሦስት እግር
ተሽከርካሪ!” አሉና እንደገና ሣቁ፡፡

አፍሬም ሥቂም ዝም ብዬ ትንሽ እንደቆየሁ ማክዳ፣ “ለመጀመሪያ
እንኳን ባለማርያም ጣቱን ያድርግልሽ” አለች ከቅድሙ የተረፈ
ይሁን፣ አዲስ ይሆን ያላወቅኩትን ሣቅ ሳታቆም፡፡ ስቄ ዝም አልኩ፡፡

“ባይ ዘ ዌይ..... ክብሩ እንደዛ ነው አሉ!” (ያው እንደምትገምቱት ሰምሃል ናት ይሄን ያለችው)

“ክብሩ..? ክብሩ ሳይኮሎጂ....?” ማክዳ ተሸቀዳድማ ጠየቀች::

“ያ... ሰኒ አብራው አድራ ስትወጣ እንዴት ነበር? ስላት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው?”

“ምን አለች?”

“እሱ ኮንዶም ሲያመጣ እኔ ደግሞ ማይክሮስኮፕ ይዤ መሄድ ነበረብኝ!”

እኔ የሌለሁበት ሌላ የኅብረት ሣቅ፡፡

ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡

ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡

“የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡

ከእነዚህ ልጆች ሣቅ መደመር አምሮኛል፡፡

የአብሥራ፤ ከላይ ጣራዋን፣ ከታች ወለሏን በማዳበሪያ ኮርኒስ የተለበጠች፤ ከትንሽነቷ ብዛት በስፋት ልኬት ልትጠራ የማይገባት
ቤቱ ይዞኝ ሄደ፡፡ ፍራሽና የሲዲ ማጫወቻ ብቻ ነው ያላት፡፡
“ሙዚቃ ልንሰማ... ሃሃ...ያልተበላ ብላ!” አልኩ በሆዴ፡፡

ፍራሽ ላይ ተጣበን ተቀመጠን፡፡ ካሁን ካሁን ወጣብኝ፣ ካሁን ካሁን
ሴት አደረገኝ፣ ካሁን ካሁን ከተተብኝ ብዬ ስጠብቅ በላዬ ላይ ተንጠራርቶ ማጫወቻው ውስጥ የሆነ ሲዲ ከተተ፡፡

ግርማ ይፍራሽዋን መስማት አለብሽ...! ስሚ የምር ሙዚቃ!” አለና
👍7
ጎታታ የፒያኖ ሙዚቃ ከፈተልኝ፡፡ ዝም ብዬ አየዋለሁ፡፡ በግርማይፍራሸዋ ምስጥ ብሏል፡፡ በቁሙ ምስጥ ይብላውና!

#ሙከራ_ሁለት

ሰምሃል ያጣበሰችኝ ሚኪ እየሳመኝ ነው፡፡ ሲስም እንደ ዮናታን አይደለም፡፡ ዮናታን ሲስመኝ ምላሱን የሚያደርግበት ቦታ ጠፍቶት አፌ ውስጥ ይዘፈዝፈው ነበር፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ጥርሴን ይልስበት
ነበር፡፡ እንደዛ እንደዛ ሲደርግ ሊያስመልሰኝ ይደርስ ነበር፡፡

መሳም ለካ እንዲህ ነው!

“ጎበዝ ነህ... መሳም!” አልኩት፣ የትንፋሽ መሰብሰቢያ ዕረፍት ስንወስድ፡፡ ፈገግ አለና ዝም አለ፡፡

“እንዴት... የት ተማርከው በናትህ?”

“መሳም ስሜት እንጂ ሳይንስ የለውም፡፡”

እንደገና መሳሳም ጀመርን፡፡ ዮናታን እግዜር ይይለት፡፡ ሲስመኝ
ሲስመኝ... ሲስመኝ... ነገራችን ከሰሜን ወደ ደቡብ ቢዘልቅ ተመኘሁ፡፡

ባየው አይወርድም፡፡

ባየው አይወርድም፡፡

ከንፈሬን ሙጭጭ ብሎ ቀረ፡ የትራንስፖርት ወጪ ያለበት ይመስል ሰሜን ላይ ሙጭጭ አለ። አቅበጠበጠኝ፡፡ እጁን በእጄ ይዤ ወደ ደቡብ ተጓዝኩ፡፡ ዋናው ከተማ ላይ ከተመ።

ጎሽ!...

በድንገት ግን ባልጠበቅኩት ፍጥነት ዋና ከተማውን ማተራመስ ጀመረ፡፡ ተናወጥኩ፡፡ ደነገጥኩ፡፡

እሱ ሲቸኩል እኔ አዘገምኩ፡፡

እሱ ሲፈላ እኔ ቀዘቀዝኩ፡፡

“ተው!” አልኩና ሸሸሁ፡፡

“ምነው....?” ድምጹ የሱ አይመስልም፡፡ (ድምፃቸውም ይቀየራል እንዴ)

“ሚኪ...ቨርጂን31 ነኝ”

“አውቃለሁ...”

“እንዴት..? ማለት እንዴት አወቅክ?”

“እነ ኀይለኣብ ሲያወሩ ሰምቼ ነው... ሰምሃል ነግራው ነገረችኝ ብሎ ነገረኝ...”

“ምኑን...?”

“ያው ቨርጂን እንደሆንሽ እና 'ዲስቨርጅ' መደረግ እንደምትፈልጊ....”

ራሴ ዞረ፡፡

“ዲስቨርጅ መደረግ እንደምትፈልጊ” በሚለው አባባል ራሴ ዞረ፡፡

ልክ እንደሚፈለጥ ኮብል ስቶን፣ እንደሚፈታ ሳይመልቲኒየስ
ኤኩዌዥን፣ እንደሚተረተር ቱባ ክር መታየቴ ራሴን አዞረው፡፡
የሰዎች በኔ ጉዳይ ተወያይቶ መወሰን፤ ሴራው፣ ቅንብሩ፣ ድርድሩ አዞረኝ፡፡

ሽሽት አልኩ፡፡ ራሴን ለመታረድ ያቀረብኩ ገራገር በግ የሆንኩ መስሎ ተሰማኝና ሽሽት አልኩ፡፡

“ምን ሆነሻል?”

“ምንም... ሬዲ አይደለሁም... እንሂድ...”

ሙከራ ሦስት አልነበረም፡፡ ከሚኪ በኋላ የተረዳሁት ነገር ከተጨማሪ ሙከራ አቀበኝ፡፡

ልጃገረድነት ሰልችቶኛል፡፡

ቦይፍሬንድ አምሮኛል፡፡

የኔ ፍቅር” መባል፤ “የኔ ቆንጆ” ተብሎ መጠራት አሰኝቶኛል፡፡

ግን ፤ ይሄን ሁሉ ስሞክር የነበረው በመገፋቴ እንጂ፣ በመፈለጌ
አልነበረም፡፡

ይሄን ሁሉ ስሞክር የነበረው ተገፍትሬ እንጂ፣ ተራምጄ አልነበረም፡፡ ይህን ሁሉ ስሞክር የነበረው በይ በይ ተብዬ እንጂ፣
በይ በይ ብሎኝ አይደለም፡፡

ነገም ይሆን የዛሬ ዓመት፣ የዛሬ አምስት ዓመት፣ የዛሬ ዐስር ዓመት (ሃሃ እዛስ ድረስ አልቆይም)፣

ድንግልናዬን ማስወሰድ ሳይሆን መስጠት ነው የምፈልገው፡፡

ድንግልናዬን መገላገል ሳይሆን አሽሞንሙኜ መሸኘት ነው የምሻው።

ድንግልናዬን ማስገርሰስ ሳይሆን መጋራት ነው የምመኘው፡፡

💫አለቀ💫
======:=:::======:==::=======

እንዴት ናቹ ውድ ተከታታዮቼ እንደሚታወቀው ትላንት በናተ ምርጫ በቻናላችን በተከታታይ እንዲቀርብ 3 መፅሀፎች አስመርጠን ነበር በዚህም #ሮዛ ከ230 ሰው በላይ ተመርጧል ከነገ ጀምሮ ይዤ እቀርባለው ከናተ ግን በየክፍሉ ከ 200 በላይ Like 👍 እፈልጋለው ምክንያቱም ስለሚያበረታን እና ምን ያህል ሰው እንደሚከታተለን ለማወቅ ይረዳናል

#ሮዛ ቁጥር_አንድ ነገ 12 ሰዓት ይጀምራል
👍4