#ጅብ #የፃፈው #ግጥም
እንጦጦ ጫካ ውስጥ
የሰከረ ሰይጣን ፣ በልቶ የሰከረ
ብሶቱን ቁጭቱን
በሰው ልጆች ቋንቋ ፣ እያንጎራጎረ
አንድ ሰካራም ጅብ ፣ እንዲህ ሲል ነበረ።
።።
" ስማኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ፍረድ ያገሬ ሰው
እኔ የሀገርህ ጅብ ፣ ከሰው የማልደርሰው
ጫካዬን መንጥረህ
ህንፃ ስትገነባ
ወደሌላ ጫካ ፣ ለመኖር ምፈልሰው
ስሜን ከሰው ተራ
ዝቅ አርገህ አትየው ፣ ክብሬን አትቀንሰው።
የቀን ጅቦች ብለህ
የቀን ሰዎችህን ፣ በኔ ስም አትጥራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ ፣
ብቻ መብላት ማላውቅ ፣ ላካፍል ምጣራ
ማየት የሚቻለኝ ፣ በብርሐንና በጨለማ ስፍራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ
የቀን ሰው ስላልሆንኩ ፣ ኖራለሁ ስኮራ
ክብሬን ዝቅ አድርገህ
ክብረ ቢስ ሰዎችን ፣ በኔ ስም አትጥራ ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ እራስህ ፍረደኝ
እንደውሻ ባልለምድ ፣ እንደበግ ባታርደኝ
በሬ ባልሆንልህ ፣ አስረህ ባትጠምደኝ
አፈንግጬ ብኖር ፣
ላንተ ባልገዛ ፣ ሰው በስሜ አትጥራ
ዝቅ አርገህ አትየኝ ፣ ከቀን ሰዎች ስፍራ
አዎ የቀን ጅብ ነኝ
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀንበቀን ምኮራ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ ፍረድ የኢትዮጵያ ህዝብ
እኔ የሀገርህ ጅብ
እንደ ሰው ጨክኜ ፣ ጅቦችን አልበላም
በዘር ከፋፍዬ ፣ ጅቦች አላጣላም
የጅብ መሰቃያ ፣ እስርቤት አልከፍትም
ትውልዴን እንደ ሰው ፣ አላንኮታኩትም
ከጅቦች ቀምቼ
ለነገ ምበላው ፣ ሀብት አላካብትም
ልክ እንደ ቀን ሰዎች ፣ ሲያገኝ አይሰስትም
ጅብ መሆን ያኮራል
በጋራ ይበላል ፣ ምግብ አያሻግትም
ጮኾ አገኘሁ ይላል ፣ ጠርቶ ያካፍላል
እንዴት ከኔ እኩል
ክብረ ቢስ የቀን ሰው ፣ የቀን ጅብ ይባላል?
ሌላው ሌላው ቀርቶ
ይሞታታል እንጂ ፣ ጅብ ስኳር ይበላል?
ያውም ከነ ስኳር ፣ ፋብሪካ ቆርጥሞ
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
ጅብ ጅብን ይገድላል ፣ በጅቦች ተሹሞ?
ጅብ ህንፃ ይሰራል
ጅብ ጅቦችን ያስራል?
እንዴት ለቀኑ ሰው ፣ ጅብ ስሜ ይጠራል?
።።።።
አዎ የቀን ጅብ ነኝ ፣
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀን በቀን ምመካ
ሰው እንዳይበላኝ ነው
ከቀን ሰው ሸሽቼ ፣ የምኖረው ጫካ!!!
፨፨በላይ በቀለወያ፨፨
እንጦጦ ጫካ ውስጥ
የሰከረ ሰይጣን ፣ በልቶ የሰከረ
ብሶቱን ቁጭቱን
በሰው ልጆች ቋንቋ ፣ እያንጎራጎረ
አንድ ሰካራም ጅብ ፣ እንዲህ ሲል ነበረ።
።።
" ስማኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ፣ ፍረድ ያገሬ ሰው
እኔ የሀገርህ ጅብ ፣ ከሰው የማልደርሰው
ጫካዬን መንጥረህ
ህንፃ ስትገነባ
ወደሌላ ጫካ ፣ ለመኖር ምፈልሰው
ስሜን ከሰው ተራ
ዝቅ አርገህ አትየው ፣ ክብሬን አትቀንሰው።
የቀን ጅቦች ብለህ
የቀን ሰዎችህን ፣ በኔ ስም አትጥራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ ፣
ብቻ መብላት ማላውቅ ፣ ላካፍል ምጣራ
ማየት የሚቻለኝ ፣ በብርሐንና በጨለማ ስፍራ
አዎን የቀን ጅብ ነኝ
የቀን ሰው ስላልሆንኩ ፣ ኖራለሁ ስኮራ
ክብሬን ዝቅ አድርገህ
ክብረ ቢስ ሰዎችን ፣ በኔ ስም አትጥራ ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ እራስህ ፍረደኝ
እንደውሻ ባልለምድ ፣ እንደበግ ባታርደኝ
በሬ ባልሆንልህ ፣ አስረህ ባትጠምደኝ
አፈንግጬ ብኖር ፣
ላንተ ባልገዛ ፣ ሰው በስሜ አትጥራ
ዝቅ አርገህ አትየኝ ፣ ከቀን ሰዎች ስፍራ
አዎ የቀን ጅብ ነኝ
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀንበቀን ምኮራ።
።።።።
ስማኝ የሀገሬ ሰው ፣ ፍረድ የኢትዮጵያ ህዝብ
እኔ የሀገርህ ጅብ
እንደ ሰው ጨክኜ ፣ ጅቦችን አልበላም
በዘር ከፋፍዬ ፣ ጅቦች አላጣላም
የጅብ መሰቃያ ፣ እስርቤት አልከፍትም
ትውልዴን እንደ ሰው ፣ አላንኮታኩትም
ከጅቦች ቀምቼ
ለነገ ምበላው ፣ ሀብት አላካብትም
ልክ እንደ ቀን ሰዎች ፣ ሲያገኝ አይሰስትም
ጅብ መሆን ያኮራል
በጋራ ይበላል ፣ ምግብ አያሻግትም
ጮኾ አገኘሁ ይላል ፣ ጠርቶ ያካፍላል
እንዴት ከኔ እኩል
ክብረ ቢስ የቀን ሰው ፣ የቀን ጅብ ይባላል?
ሌላው ሌላው ቀርቶ
ይሞታታል እንጂ ፣ ጅብ ስኳር ይበላል?
ያውም ከነ ስኳር ፣ ፋብሪካ ቆርጥሞ
ደግሞ
ደግሞ
ደግሞ
ጅብ ጅብን ይገድላል ፣ በጅቦች ተሹሞ?
ጅብ ህንፃ ይሰራል
ጅብ ጅቦችን ያስራል?
እንዴት ለቀኑ ሰው ፣ ጅብ ስሜ ይጠራል?
።።።።
አዎ የቀን ጅብ ነኝ ፣
በቀን ጅብነቴ ፣ ቀን በቀን ምመካ
ሰው እንዳይበላኝ ነው
ከቀን ሰው ሸሽቼ ፣ የምኖረው ጫካ!!!
፨፨በላይ በቀለወያ፨፨
👍1