አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
🎅 ሳንታና ዛፉ 🎄

ባልና ሚሲት ናቸዉ የገና ዛፉን በማስዋብ ላይ ይገኛሉ ምንም የቀረ የለም መብራቱ ጥጡ ሁሉም አለ❗️❗️በድንገት❗️❗️ የሚያስገመግም ድምፅ ተሰማ...ጓ..ጓ..ጓጓጓጓ.ጓጓ..ጓጓጓጓጓጓጓ
ከመቅፅበት ባልየው ከቦታው ጠፋ..😳
ሚስት፦ጥሎኝ ወዴት ገባ?
#ባል፦ነይ ከዛፉ ጀርባ

#ሚስት፦በዚህ በጨለማ ሲደበደብ ይህ በር
አንተ አብረክኝ ባትኖር ምን ይዉጠኝ ነበር
ጓ...ጓጓ..ጓጓጓጓ.........ጓጓጓጓጓጓጓጓጓጓጓጓ

#ሚስት፦አዉጭኝ አደራሽን እማምላክ የዛሬን
ጓጓጓጓጓጓጓጓጓ...

#ባል፦አሁን ባይኔ መጣ በህግ አምላክ በሬን
ሽሽሽሽሽሽ.......

#ሚስት፦በቁም ሸና ይዉልህ ድምፅክን ሲሰማ
ሽሽሽሽሽሽሽሽ

#ባል፦በሲቃ ድምፅ በቃህ ተበላሸክ
መጣዉልክማ

#ሚስት፦በቁም ሸና ይሄዉልክ
ሽሽሽሽሽሽሽ

#ባል፦በል ሽሽ መጣዉልክ ኦኦኦ!! ይላል ባል ካለበት ሳይወጣ በህግ አምላክ ማነክ በሬን የምትመታ የባል አይኖች ላይ እንባ ይታያል

#ሚስት፦እግዞ የኔ ጌታ በሩ ተከፈተ

እህህም...እህህም..

#ባል፦ማናቹ እናንተ ምንድን ነዉ እህህም

ሰባ ሰገል፦እንዴት አይገባክም ሰባ ሰገል ነን ቤተልሄም ድረስ ኮኮብ የመራን
ከግርግሙም ስር ወድቀን የሰገድን
እጣኑን ያጨስን ወርቁን የሰጠን

#ባል፦ ምን መጣብኝ ዛሬ

#ሚስት፦ፍቅሬ

#ባል፦አቤት

#ሚስት፦እባክክ ዉሰደኝ ወደ መኝታ ቤት

#ባል፦ይሄ ነዉ የቀረሽ ልሸከምሽ እንዴ

#ሚስት፦ስሞትልክ ዉዴ ፈራዉ በጣም ፈራዉ አዉጣኝ ከዚ ፍርጃ

#ባል፦ከፈራሽ ተነስቸሽ በገዛ እግርሽ ሂጃ

#ሚስት፦እንዴት ብዬ እኔማ ዝልፍልፍ አለብኝ
እግሬ እንደ ቄጤማ ምክንያቱ ምንድን ነዉ

#ባል፦አይዞሽ ተረጋጊ እዚም እንደዛዉ ነዉ

#ሚስት፦አንተም ደንግጠካል እኔ እኮ አላምንክም

#ሰባ ሰገል፦እህህም እህህም

#ባል፦ምንድን ነዉ እህህም

#ሰባ ሰገል፦እኛ ብንጠይቅህ አንተ መልስ የለክም

#ባል፦መች ተጠየኩና?

#ሰባ ሰገል፦አንተ መልስ ካለክ ጥያቄዉ ይህዉና
በልስቲ ንገረን ምንድን ነዉ ትርጉሙ
በቤትክ ወለል ላይ ይሄ ዛፍ መቆሙ

#ባል፦ያዉ ገና ሲመጣ ብርሀነ ልደቱ
ይህን ዛፍ ያቆማል ሁሉም በየቤቱ

#ሰባ ሰገል፦አጀብ ነዉ ይገርማል ይህ ተረተረት
ህፃኑ ተወልዶ በተኛበት በረት
መች ዛፎች ነበሩ መች ዛፎች ተገኙ
ግልገል በጎች እንጂ አብረዉት የተኙ
ከቤተል ጥድ ከከተማዉ ዝግባ ጨቅላዉን ለማየት ከበረት የገባ አንድ ዛፍ ከሌላ ለምንድን ነዉ ዛሬ ግልገል እና ጥጃ ሙክትና በሬ
ከሰዉ ጆሮ ቀድመው የሰሙትን ወሬ የምታሸክመዉ ለዛፎች ጎፈሬ
መቼስ ግርግም እንጂ ከበጎቹ ጋራ
ጫካ ዉስጥ እዳዉሬ
ዛፍ ላይ እንዳሞራ ጌታ አልተወለደ
ታድያ ይሄ ደማቅ ዛፍ በመብራት ያበደ
ብርሀነ ልደቱን እንዴት ይወክላል

#ባል፦አሁን ጉድ ይፈላል

#ሚስት፦እንዴ!!

#ባል፦ምነዉ ዉዴ?

#ሚስት፦እኔጃ ፈራሁኝ ነገሩ ምነድን ነው? ልቤ ቱር ብሎ ባፌ ሊወጣ ነዉ

#ባል፦አይዞሽ ተረጋጊ እዚም እንደዛዉ ነዉ

#ሚስት፦ይሄን ቢመለከት አገር ጉድ አይልክም
ሰባ ሰገል፦እህህም እህህም

#ባል፦ምንድን ነው እህህም?

#ሰባ ሰገል፦እኛ ብንጠይቅህ አንተ መልስ የለክም

#ባል፦ጥያቄዉን ሳልሰማ

#ሰባ ሰገል፦እንግዳዉ ተጠየቅ መልስ ካለክማ
ንገረን አንተ ሰው በዛፉ ቅጠል ላይ የተነሰነሰዉ
ይህ ጥጥ ምን ይባላል?

#ባል፦ያዉ ያዉሮፓ ክረምት ትንሽ ከበድ ይላል ታድያ ያ ዉሽንፍር ያ ከባድ በረዶ ከጭጋጉ ክምር ተንዶ ተንዶ ቁልቁል ወደ ምድር የወረደ ለታ ይህንን ይመስላል የዛፉ ገፅታ

#ሰባ ሰገል፦ይሄ ሰው ምን ይላል አረ እግዜርን ፍራ
ያላየ ከሚዋሽ የነበርን እናዉራ ያኔ ቤተልሄም ህፃኑ ተወልዶ ባየንበት ምሽት ጥሎል ወይ በረዶ? ነበር ወይ ዉሽንፍር ዛፍ የሚያጨላልም አጥንት የሚቆፍር በርግጥ በዚያ ሌሊት በረዶ ካለማ ሰማዩ ተጋርዶ በጭጋግ ደመና
እንዴት ይታየናል የኮኮቡ ፋና
እንኮን ጥቁር ጭጋግ የለም ስስ ደመና
ሌሊቱ ደስ የሚል ሰማዩ እጅግ ደማቅ
አልተከናነበም ጥቁር ጉም እንደማቅ
ይመስገን ፈጣሪ ረግ ረግ አልዋጠን የበረዶ እቋሪ
ዶፍ አልቀጠቀጠን
ጎርፍ አላጨቀየን
ጥርት ባለ ሰማይ ከወክብት እያየን
ኮከብ እየመራን
መገስገስ ስንጀምር
ከየት መቶ ታየክ የበረዶ ክምር የዉሽፍር ጫናዉ

#ባል፦ይሄ ነዉ ፈተናዉ

#ሚስት፦እንዴ

#ባል፦ማነው ዉዴ?

#ሚስት፦ፈራዉ ለመናገር አንድ ነገር አለ ቀዝቀዝ ያለ ነገር እግሬ ስር የሚሳብ

#ባል፦ከአይምሮሽ አዉጪዉ ይህን የሞኝ ሀሳብ

#ሚስት፦እንጃ እባብ ነዉ መሰለኝ እግሬ ስር የገባዉ

#ባል፦ምንድን ነዉ መቦቅ ቦቅ በረባ ባረባዉ ረጋ በይ እቴ

#ሚስት፦እንኳን ልረጋጋ ሊያመልጠኝ ነዉ ሽንቴ

#ባል፦ አረ ተይ ነዉር ነዉ

#ሚስት፦ምን ላርግ አቃተኛ ምክንያቱ ምንድን ነው

#ባል፦አይዞሽ ተረጋጊ እዚም እንደዛዉ ነው

#ሚስት፦እንዲህ እስትሆን ድርስ አያሳፍርክም

#ሰባ ሰገል፦እህህም እህህም

#ባል፦ምንድን ነው እህህም

#ሰባ ሰገል፦እኛ ብጠይቅክ አንተ መልስ የለክም

#ባል፦ማን ጠየቀኝና

#ሰባ ሰገል፦አንተ መልስ ካለክ ጥያቄዉ ይሄዉና
ማነዉ ይሄ ቁዝር ሆድ ድብልብል ቁመና

#ባል፦ፈረንጅ ሳንታ ክላዉስ ሀበሻ አባ ገና እያለ ይጠራዋል

#ሰባ ሰገል፦ወይ አለማስተዋል እሱማ ከሆነ አባ ገና ማለት ግርግም ለዛ ህፃን ወድቀን ስንሰግድለት የት እንደነበረ ጠይቅል እስኪ
ገናን የማያቀዉ የገና ሰባኪ
ማን እንበለዉ ይሄን የድል አጥብያ አርበኛ ብንጠራም እኛ
ብንደርስም እኛ
ብንሰግድም እኛዉ ነን
በአፍጢም የተደፋን ጌትነቱን አምነን
ይሄዉ ዛሬ ደሞ አጭበርባሪዉ ሳንታ
ገና አባት ነኝ ብሎ ባመጣዉ ጨዋታ
ህዝብ እያታለለ ትዉልድ እያምታታ
እንዴት ገኖ ታየ ካምላክ ልደት በላይ ከኛ ጋር በግርግም ያልነበረ አታላይ

#ባል፦በቃኝ ከዚ በላይ

#ሚስት፦እንዴ

#ባል፦ይበቃሻል ዉዴ ሙግት አተካራ
ይሄንን ዛፍ ጥለን ግርግሙን እንስራ
ደህና ሁን አንተ ዛፍ

#ሚስት፦ደህና ሰንብት ሳንታ

#ሰባ ሰገል፦አሁን ተወለደ እዉነቸኛዉ ጌታ
ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ
ተወለደ ጌታ ተወለደ
ተወለደ አምላክ ተወለደ

#እንኳን #ለጌታችን #ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ #ክርስቶስ #የልደት #በዓል #አደረሳችሁ!
👍11😁1