አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ብሂላዊ #ምክሮች

#ሀሜት:- ያለ መሳሪያ ሰዉን መግደል ነዉ
#ማጉረምረም:- ባገኙት በቃኝ ብሎ አለማመስገን ነው።
#ቁጣ:- ከስድብ የሚያደርስ የክፉ አድራጎት መሰረት ነው።
#ብስጭት:- የተበሳጩበትን ነገር ሳይሆን ተመልሶ ራስን የሚጎዳ መርዝ ከክህደት የሚያደርስ የሀጥያት ምንጭ ጭንቀትን የሚያነድ ትንሽ ክብሪት ነዉ።
#መርገም:- አቅም ሲያንስ ወደ ላይ የሚወረወር የደካማ ሰዎች ቀስት ነው።
#መሳደብ:- ህሊናን የሚያቆስል ቁስሉ ቶሎ የማይድን አቅም የሌላቸዉ ሰዎች ዱለ ነው።
#ዋዛ #ፈዛዛ:- በስልት የሚቃኙት የስራ ፈቶች በገና ነው።
#ዘፈን:-😕ለዝሙት የሚያነቃ ልብ የሚወጋ ፍላፃ ነው።
#ድንፋታ:- የጀግኖች ባልትና የሰነፎች ጫጫታ
ነው።
#በክፉ #ማንሾካሾክ:- ቀስ ብለዉ ሰዉን የሚገድልበት የአሳባቂዎች ጩህት ነው።
#ነገር:- ማመላለስ የሚዋደዱትን የሚለያዬበት የዲያቢሎስ የግብር ልጆች መሳርያ ነው።
#የአደራ #ገንዘብ #መብላት:- ሳይጥሩ ሳይግሩ የሰዉ ላብ ሲበሉ የሚኖሩበት የሰነፍ ሰዎች መሳርያቸዉ ነው።
#ሰዉን #ማስነወር:- ሰዉ የወደደዉን የተከበረዉን ስም ለማጥፋት የሚቀቡት የምቀኞች ቀለም ነው።
#መሳለቅ:- የማይታይ የቀናተኞች ጦር ነው።
#ተስፋ:- ከማጣት ወደ ማግኘት ለመሸጋገር የሚያገለግል ድልድይ ነው።
#ጠብ:- እሳትን ለማንደድ የሚጫር የነገረኞች የኪስ ክብሪት ነዉ።
#ችኮላ:- የትእግስት ጠላት የፀፀት አባት ነው ልጁም ወይኔ ይባላል።
#ሙከራ:- የስራ ጥልቀትን መለኪያና መመጠኛ ነው።
#የጥበብ #መጀመርያ #እግዚአብሔርን #መፍራት #ነው
ከ ያለ ጭንቀት የመኖር ምስጢር መፅሀፍ የተወሰደ በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ
👍2
#ገንዘብ_መሆን_የተሳነው_ዕውቀት


#በሕይወት_እምሻው

ከታናሽ ወንድሜ ጋር በዲግሪ ፕሮግራም ተምሮ የተመረቀውን ዳንኤል፣ የኮብልስቶን ሥራን ሲያስተባብር አገኘሁት፡፡

ሻይ ይዘን፤ ስለ የተማሩ ኮብልስቶን ጠራቢና ደርዳሪዎች፤ ተብሎ...
ተብሎ... የተተወውን ክርክር እንደ አዲስ ቀሰቀስነው፡፡

ዳንኤል ፣ “ሥራ አጥተን ቤት ቁጭ ከምንል ገንዘብ እስካገኘን
ብንሠራ ምናለ?” ብሎ ነገሩን ሥራ ከመናቅና ካለመናቅ ጋር አጣብቆት ብዙ ሞገተኝ፡፡

“ሥራ ገንዘብ ማግኛ ነው ፤ ይሄ ደግሞ ገንዘብ ይከፍላል፤ ኀጢአቱ ምንድነው?” ብሎ ተከራከረኝ፡፡

ዳንኤል ልክ ነው፡፡ ድህነት መለዮ ልብሳችን በሆነበት ሀገር ገንዘብ
የሚያስገኝ ነገር ሁሉ እንደ ስኬት እንደሚቆጠር ግልጽ ነው፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ እህል ይሆናል፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ ቤት ኪራይ ይከፍላል፡፡

ምክንያቱም ገንዘብ የታክሲ ይሆናል፡፡

ያን ያህል ቀላል ነው፤ ይገባኛል፡፡ የእኔ ችግር ከአጠቃላይ ክስረቱ ጋር ነው፡፡ የእኔ ችግር እነዚህ ልጆች ለዓመታት "ሲማሩና ሲመራመሩ" ከርመው፤ ያልተማረና ያልተመራመረ ሰው
በሚችለው ሥራ ላይ መሰማራታቸው... የእነዚያን ሰዎች የሥራ ዕድል ከማጣበባቸው ነው፡፡ ለእኔ ይሄ ክስረት ነው።

ሰለዚህ የመንግሥት ሚዲያዎቻችን፣ እነዚህ ልጆች የምርቃት ሱፋቸውን አውልቀው በሥራ ቱታ ድንጋይ ሲፈልጡ መዋላቸውን እንደ ታላቅ ስኬት ሲያቀርቡት አይገባኝም።

“በሥራ ክቡር ነው!” መልካም አባባል፤ ልሽቀታችንን ሲደብቁት ደስ አይለኝም፡፡ ችግሬ ከልጆቹ መሥራት አይደለም፡፡ ከነገሩ አቀራረብና አረዳድ ነው፡፡

ሥራቸው ልጆቹን ሊያሳፍር ባይገባም፤ እንደ ሀገር ግን ሊያኮራን የሚገባ ነገር አይደለም፡፡ ምክንያቱም ልጆቹ ዲግሪ ለማግኘት ብዙ ከፍለዋል፡፡ ሀገሪቷም ካላት ትንሽ ሀብት ብዙ ከፍላለች፡፡

...እና በረጅሙ ስናስበው፣ ዛሬን በልተው ቢያድሩም የትምህርት ሥርዓታችን ክስረት ባንዲራዎች ናቸው፡፡

ዛሬ ትምህርት ላይ ላሉ፣ ማበረታቻ ሳይሆኑ ማስጠንቀቂያ ናቸው፡፡

ያልተማረ ሰው ሊሠራ የሚችለውን ሥራ ተምረው ስለሚሠሩ፣በልተው ቢያድሩም ለሀገር ውድቀቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን፣ ይህ የእነሱ ጥፋት አይደለም፡፡ መብላት አለባቸው፡፡ መኖር አለባቸው፡፡

ስለዚህ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ዕውቀት ልንሰጣቸው ስላልቻልን ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ጉልበታቸውን ተጠቀሙ:: በዚህ ደግሞ ልናፍር እንጂ ልንኩራራ የሚገባ አይመስለኝም፡፡

💫አለቀ💫

ምን ትላላችሁ የቻናሌ ተከታታዎች ይሄ ጉዳይ የሚመለከታችሁም ልትኖሩ ትችላላችሁ እስቲ ሃሳባቹህን አድርሱን

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏