#ልደት #በኛ #መንደር
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
እንኳን ኬክ ተቆርሶ
ድግስ ተደግሶ
ሻማ ተለኩሶ
ልዩ ልብስ ተለብሶ
"መልካም ልደት" በሚል አንድ ሺ ሙዚቃ
የልደት ቀን ደምቃ
እንኳን ልትከበር
ከና'ካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
.
አሁን የኔ ልደት፣ የተወለድሁበት፣
መቸ እንደነበረ፣ እናቴ ዘንድ ሂደን፣ ንገሪን ብንላት
.
“መንግስቱ ኃይለ ማርያም መንደራችን መጥቶ
በጎበኘ ማግስት
ነበር የወለድሁት፡፡
ይሰማኝ ነበረ፣ የወታደር ሆታ
የተማሪ ጩኸት፣ ያይሴማ እልልታ
ምጥ የያዘኝ ሌሊት፣ ምጥ የያዘኝ ማታ፡፡
ታዲያ በዚህ መሃል፣ ኢሃፓ ተኩስ ከፍታ
የአቶ አበበን ድርቆሽ፣ ባብሪ ጥይት መትታ
የመስቀል ደመራ፣ ሲመስል መንደሩ
ወንዱ ተኩስ ሲገጥም፣ በየ ጉራንጉሩ
ነበር የወለድሁት፡፡
.
በዚያ ጭንቅ ጨለማ
የአካሌን ክፋይ
ጨቅላውን ታቅፋ፣ አዋላጇ ቁማ
'‘ተነሽ መዓት መጥቷል፣ እንውጣ ከዚህ ቤት
ካ'ዲሱ ፍጡር ጋር፣ እንዳይበላን እሳት’'
ስትለኝ ብነሳ፣ ወገቤን አስሬ
በነበልባል እሳት፣ ጠፍታለች መንደሬ
የምጤን ሁኔታ
ያችን የ’ሳት ማታ
ዘወትር እንዲኖር ልቤ እያስታወሰ
የወለድሁትን ልጅ አልሁት እሳቱ ሰ”
ነው ምትልክ
እና...
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
የልደታችን ቀን፣ እንኳን ልትከበር
ከናካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር
፨፨ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን፨፨
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
እንኳን ኬክ ተቆርሶ
ድግስ ተደግሶ
ሻማ ተለኩሶ
ልዩ ልብስ ተለብሶ
"መልካም ልደት" በሚል አንድ ሺ ሙዚቃ
የልደት ቀን ደምቃ
እንኳን ልትከበር
ከና'ካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር፡፡
.
አሁን የኔ ልደት፣ የተወለድሁበት፣
መቸ እንደነበረ፣ እናቴ ዘንድ ሂደን፣ ንገሪን ብንላት
.
“መንግስቱ ኃይለ ማርያም መንደራችን መጥቶ
በጎበኘ ማግስት
ነበር የወለድሁት፡፡
ይሰማኝ ነበረ፣ የወታደር ሆታ
የተማሪ ጩኸት፣ ያይሴማ እልልታ
ምጥ የያዘኝ ሌሊት፣ ምጥ የያዘኝ ማታ፡፡
ታዲያ በዚህ መሃል፣ ኢሃፓ ተኩስ ከፍታ
የአቶ አበበን ድርቆሽ፣ ባብሪ ጥይት መትታ
የመስቀል ደመራ፣ ሲመስል መንደሩ
ወንዱ ተኩስ ሲገጥም፣ በየ ጉራንጉሩ
ነበር የወለድሁት፡፡
.
በዚያ ጭንቅ ጨለማ
የአካሌን ክፋይ
ጨቅላውን ታቅፋ፣ አዋላጇ ቁማ
'‘ተነሽ መዓት መጥቷል፣ እንውጣ ከዚህ ቤት
ካ'ዲሱ ፍጡር ጋር፣ እንዳይበላን እሳት’'
ስትለኝ ብነሳ፣ ወገቤን አስሬ
በነበልባል እሳት፣ ጠፍታለች መንደሬ
የምጤን ሁኔታ
ያችን የ’ሳት ማታ
ዘወትር እንዲኖር ልቤ እያስታወሰ
የወለድሁትን ልጅ አልሁት እሳቱ ሰ”
ነው ምትልክ
እና...
ባደግንበት ቀዬ፣ በኖርንበት መንደር
የልደታችን ቀን፣ እንኳን ልትከበር
ከናካቴው ቀኗስ መች ትታወቅ ነበር
፨፨ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን፨፨
👍1