🍁🍁ዲያሪው 📝
ደራሲ ፍስሐ ተክሌ
#ክፍል_22
“አዎ ገድያታለሁ!" አለ፡፡ ችሎቱ በአንድ ጊዜ በታዳሚው ጫጫታ ታወከ፡፡ እኔ ፍጹም ያልጠበቅሁትን ነገር በመስማቴ በቁሜ ደረቅሁ፡፡ ዳኛው በመዶሻቸው ፀጥታውን አስከበሩ፡፡ ጠበቃዬም፤
"ይህንንማ አውቄዋለሁ፤ ግን ለምን?" ሲለው፡፡ ፊቱ ላይ አንዳችም የመፀፀት ስሜት ሳይታይበት፤ "ለእሷ ሞት ያንሳት እንደሆነ እንጂ የሚበዛባት አይደለም:: አሁንም ሁለተኛ ተነስታ ዳግመኛ ብገድላት እንኳን በእኔ ላይ የፈፀመቺውን በደል የሚያካክስ አይደለም:: ከሁሉ አስበልጬ እየወደድኳት፣ እሷን አጥቼ መኖር እንደማልችል እያወቀች፣ ፍቅሬን ረግጣው ለመሄድ ሞከረች:: ከራሴ በላይ እሷን የተሻለች ሰው ለማድረግ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ለጥሩ ነገር ላበቃት ብችልም የእኔ ድካም፣ የእኔ ውለታ፣ ለእሷ ምንም አልነበረም:: ሁሌ ጊዜ ከእኔ ይልቅ የምትናፍቀው ይህንን ደደብ ነበር:: ዳሩ ግን እሷ የእናትነትና የአባትነት ፍቅርን አይታ ስለማታውቅ ለፍቅር ስለፍቅር የሚያስብ ህሊና አልነበራትምና አልፈርድባትም:: እኔ ግን ተስፋ ሳልቆርጥ አንድ ቀን ታፈቅረኝ ይሆናል እያልኩ የቻልኩትን ሁሉ ብጥርም እሷ ግን ለእኔ በድኗን እንጂ መንፈሷን ሳትሰጠኝ ለሶስት ዓመታት በአንድ ቤት ውስጥ አብረን የይስሙላ ህይወት ኖርን:: ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አንድ ቀን ትወደኝ ይሆናል፣ ልጅ ስንወልድ ታፈቅረኝ ይሆናል እያልኩ ተስፋ ሳልቆርጥ በእሷ የምወደድበትን ቀን በናፍቆት መጠባበቁን ተያያዝኩት:: ግን ምን ያደርጋል! ልፋቴ ሁሉ የእምቧይ ካብ ነበር፡፡ ምንም ያህል ብጥር፣ ምንም ያህል ጥሩ ነገር ብሰራ ሕሊናዋ ውስጥ አልገባ አልኩኝ። በእሷ አባባል እኔን በወንድምነት እንጂ በፍቅር ሊቀበል የሚችል ልቦና አልነበራትም፡፡ ወሬዋ ሁሉ ስለአማረ ነበር፡፡ ዓይኖችዋ ማየት የሚፈልጉትና የሚመኙት እኔን ሳይሆን በእኔ ውስጥ አሻግረው የሚያዩት እሱኑ ነበር። ሌላው ቀርቶ አልጋ ላይ በፍቅር ጨዋታ ወቅት የምትጠራው የእኔን ስም ሳይሆን የእሱን ስም ነበር፡፡ የእኔ የራሴ ብቻ ላደርጋት የወስንኩትን ሁሉ እንደፈላ ውኃ አተነነችው፡፡ይህ ደግሞ እጅግ በጣም አተከነኝ:: ስለዚህ ቀናሁ፡፡ ለዚህ ደግሞ ብቸኛው መፍትሄ አሷን ከእሱ ጋር ማለያየት ብቻ ነው ብዬ ስላሰብኩ ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ አንድ መላ ፈጠርኩ። በመጀመሪያ ቢያንስ እሷ ደብዳቤ እየጻፈችለት እሱ መልስ የማይሰጥ ከሆነ ተስፋ ቆርጣ ትተወው ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ አማረ የሚጽፋቸውን ደብዳቤዎች ከፖስታ ቤት ሳጥናችን ውስጥ ቀድሜ እያወጣሁ ማቃጠሉን ተያያዝኩት፡፡ በተቻለ መጠንም እንዳይደርሳት አደረኩ፡፡ እሷ ግን ተስፋ ባለመቁረጥ ትጽፍለት ነበር፡፡ "ባይመቸው ነው እንጂ ሲመቸው ይጽፍልኝ ይሆናል" እያለች በተደጋጋሚ ትሞክር ነበር። በመጨረሻ ግን ሌላ አማራጭ መፈለግ ነበረብኝና እነዚህ የምታሳየኝን ሁለቱም ተስፋ ያስቆርጣሉ ያልኳቸውን ደብዳቤዎች ጽፌ በእሱና በእሷ ስም በተለያየ ጊዜ አሽጌ ላኩኝ፡፡ ይህንንም እንዳታውቅብኝ የተቻለኝን ሁሉ
አደረኩ፡፡ ይኸ በእርግጥ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተሳክቶልኛል፡፡ እሷም ሆነች እሱ ድርጊቱን በእውነትነት ስለተቀበሉት ሁለቱም ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህም ቢሆን ሊዘልቅ አልቻለም፡፡ እንዴት ልታውቅ እንደቻለች ባይገባኝም ወደ መጨረሻ አካባቢ ሁለቱም ደብዳቤዎች በእኒ እንደተጻፉ በማወቋ ይበልጥ ጠላችኝ፡፡ ይህንን ሁሉ ያደረግሁት ለፍቅሯ ስልና እጅግ በጣም ስለምወዳት ነበር። እሷን ለማንም ቢሆን አሳልፌ መስጠትን ህሊናዬ የሚቀበለው ጉዳይ አልነበረምና እውነታውን ተቀብዬ አርፌ መቀመጥ አልቻኩም:: ልቤን ሰብሮ እጅግ ተስፋ ያስቆረጥኝ ግን ዘወትር በምታነበው መጽሐፏ ውስጥ ያገኘሁት የደብዳቤ ረቂቅ ነበር፡፡ ተጽፎ ያልተላከውን ለጓደኛዋ ኤልሳ የተጻፈውን ደብዳቤ እንዳነበብኩ ክፉኛ አንቀጠቀጠኝ፤ አሁንም ቢሆን ያንገሸግሸኛል፡፡ ኮፒውን አስቀርቼ ደጋግሜ ስላነበብኩት በቃሌ አጥንቼዋለሁ ማለት ይቻላል፡፡ እንዲህ እኳ ነው ያለችኝ፡፡ "ዶ/ር አድማሱ ራስ ወዳድ ነው፡፡ እኔ ለእሱ ከወንድምነት ያለፈ ፍቅር እንደሌለኝና መቼም ቢሆን የእሱ ዘላቂ ፍቅረኛ ልሆን እንደማልችል እያወቀ ለእኔ ደስታ ሳያስብ ለራሱ ፍላጎት ብቻ በመጨነቅ የእኔ ሕይወት አበላሽቶ በእኔ መደሰት መፈለጉን ሳስብ ይበልጥ እንድጠላው ያደርገኛል:: እኔ ለአማረ፣ አማረ ለእኔ ምን ያህል ፍቅር እንዳለን እያወቀና በሚያደርገው እኩይ ተግባር ሁለታችንም ምን ያህል ልንጎዳ እንደምንችል እየተገነዘበ፣ በሁለታችን ደስታ ማጣት የራሱን ደስታ ለመግዛት ሲሞክር ማየት ምንጊዜም ቢሆን የሚያናድድ ተግባር ነው:: በዚህም የተነሳ ለእኔ ከእሱ ጋር ተመልሶ አብሮ መኖር ቀርቶ ማሰቡም ሆነ መሞከሩ ራሱ የማይቻል ሁኔታ ነው፡፡ እርግጥ ነው ዶ/ር አድማሱ፣ ለእኔ ያለውን ፍቅርና በዚህም የተነሳ ያደረገልኝን ነገር ሁሉ ምንግዜም የምረሳው አይደለም:: በልቤ ውስጥ ትልቅ ቦታ አለው:: አንድ የምተማመንበት ዘመዴ እሱ ነው ብዬ ስላመንኩ ሳላቅማማ ያለኝን ሁሉንም ነገር አሳልፌ ልሰጠው ሞከርኩ፡፡ ግን ገላዬን እንጂ ጥልቅ ፍቅሬን ልሰጠው አልቻልኩም፡፡ ውጪያዊ አካሌ እንጂ ነፍሴ ከሱ ጋር ልትሆን አልቃጣችም:: በተለይ አሁን ከአማረ ጋር እንዴት እንደተለያየን ካወቅሁ በኋላና ያለ በደሉ በደለኛ አድርጌ መለያየቴን ስገነዘብ ፀፀቱ በፍጹም አላስቀምጥ አለኝ፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እስካሁን አላግባብ ሳብጠለጥለው መኖሬን ሳስብና ከሁሉም በላይ ደግሞ ዶ/ር አድማሱ ያደረገውን ነገር ሁሉ እያወቅሁ፣ በምንም ተአምር ተመልሼ የእሱ ፍቅረኛ ሆኜ ልኖር እንደማልችል ይታየኛል፡፡ አርግጥ እሱ ለእኔ ካለው ፍቅር የተነሳ ያደረገው መሆኑን ስለማውቅ ጥፋቱን ሁሉ ይቅር ልለው እችላለሁ፣ ሆኖም እላይ
በጠቀስካቸው ምክንያቶች የተነሳ ዳግም የእሱ ፍቅረኛ ለመሆን ግን በምንም ሁኔታ አይቻለኝም:: የበደልኩትን ፍቅረኛዬን ፈልጌና እግሩ ላይ ወድቂ ይቅርታ ለመጠየቅ ወደ አንቺ እየመጣሁ ነው:: ቢያንስ ዳግም ባያፈቅረኝ እንኳ ይቅር ካለኝ ይበቃኛል" ይላል፡፡ ይህንን ደብዳቤ እንዳነበብኩ ራሴን መቆጣጠር ተሳነኝ፡ ከጽሑፉ ምሬት የተነሳ ሳልወድ በግድ ደጋግሜ አነበብኩት፤ በቃሌም አጠናሁት፡፡ ይህን በሕልሜም በውኔም ይሆናል ብዬ ያልጠበኩትን ነገር በራሷ የእጅ ጽሑፍ ሳነብ ውስጤ እሳት የተለኮሰበት ያህል ነደደ፡፡ ግን መጨከን አልቻልኩም፡፡ በዚሁ የተነሳ ጥላኝ ለመሄድ በተነሳችበት ዕለት ጨክኜ ላሰናብታት አልቻልኩም፡፡ ጽኑ ፍቅሬን እየገለጽኩላትና የወደፊቱን አስደሳች የሚሆን ሕይወታችንን በልዩ ልዩ መልክ እያብራራሁላት እንድትቀር ለመንኳት፡፡ እሷ ግን እምነቴንና ተስፋዬንም በእሷ ላይ ማሳደሬን በተደጋጋሚ ነግሬያት ሳለ ታደርገዋለች ብዬ በሙሉ ልቤ ሳላምን ጥላኝ ሄደች፡፡ ይህንን ሁሉ ውለታና ለእሷ ያለኝን ፍቅር ከምንም ሳትቆጥር ጥላኝ ወደ እዚህ እርኩስ ለመሄድ ወሰነች:: ለመንኳት፣ እግሯ ላይ ተንበርክኬ ቅሪ እያልኩ እያለቀስኩ ተማፀንኳት፣ ከእሷ ወዲያ ሕይወት ለእኔ ትርጉም እንደሌለው እና በእኔ ላይ በምትፈፅመው ነገር የኋላ ኋላ ከምትፀፀት ብትቀር እንደሚሻል ደጋግሜ ነገርኳት፡፡ አንጀት ካላት በማለት እንድትራራልኝ ጣርኩ፡፡ ለእሷ ግን ይህ ሁሉ መማፀን ምንም ዋጋ አልነበረውም:: እነዚህ ሁለት ደብዳቤዎች በእኔ መጻፋቸውን በማወቋ እጅግ አድርጋ ጠላቺኝ:: አፍ አውጥታ ለምን ይህንን እንዳደረኩ ግን ልትጠይቀኝ አልፈለገችም፡፡ ነገር ግን ይህ ድርጊቴም ቢሆን በእኔ ላይ እንዲህ የከፋ ጥላቻን ሊያስከትል የሚችል መሆን አልነበረበትም:: ምንም