#ፍቀርና_በቀል
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
✍ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
"የስሜት ህዋሳቶቻችን አንድ ላይ ቢቀናጁ እንኳን እውነትን
ለመዳኘት ያላቸው ብቃት ሙሉ አይደለም፡፡ለዚህ ነው
አንዳችን ጋር እውነት ነው ብለን የደመደምነው ክስተት
በሌላው ሰው ውስጥ ተቃራኒውን ገጽ ይዞ የሚናገኘው፡፡
ይሄም ነው ያለማግባባታችን መሰረታዊ መነሻ ምክንያት
ሚሆነው….ምክንያቱም ሁለችንም በራሳችን ውስጥ እውነት
ነው ብለን ላመንበት ጉዳይ ስለምናዳላ….ለዛም ጥብቅና
ቆመን እስከመጨረሻም በጭፍን ስለምንፋለም፡፡"
ለተለመደው አይነት ውይይት በቀጠሮችን መሰረት
የፕሮፌሰሩ የጥናት ክፍል ስደርስ ብቻቸውን አልነበሩም..አንድ
ደልደል ያሉ በእሳቸው ዕድሜ አካባቢ የሚገኙ… ግን በተሸለ
ይዞታ ላይ ያሉ ሰው አብሮቸው ነበሩ….ሰላምታ ሰጥቼ ወደ
ውስጥ እንደዘለቅኩ‹‹ተዋወቀው ዬሴፍ ይባላል.. አብሮ አደግ
ጓደኛዬ ነው‹››አሉኝ ፕሮፌሰሩ
በአክብሮት አንገቴን ሰበር አድርጌ እጄን ለሰላማታ በመዘርጋት
ስሜን ተናገርኩ…..ሰውዬውም በተመሳሳይ አክብሮት
የዘረጋውትን እጅ እየጨበጡ‹‹ዩሴፍ እባላለው..››አሉኝ ..ቦታ
ይዤ እንደተቀመጥኩ‹‹ ..በሉ ትቼያችሁ ልሄድ ነው..ቡኃላ
ደውልልሀላው›› ብለው ፕሮፈሰሩንም እኔንም ተሰናብተው
ወጥተው ሄዱ….እንግዳው፡፡
ፕሮፌሰርም ለመጠጣት እንዲመቻቸው ጠርሙሱን አንስተው
አረቄውን ወደ ብርጭቆው እያንደቀደቁ‹‹የልጅነት ጓደኛዬ
ነው…አሜሪካዊ ሆኗል..ከረጅም አመት የስደት ቆይታ ቡኃላ
ነው ሰሞኑን የመጣው..በጣም ጥሩ እና ልበ-ቀና ሰው
ነው››በማለት ለእኔ ባያስፈልገኝም ተጨማሪ ማብራሪያ
ሰጡኝ
‹‹አይ ጥሩ ነው›› አልኩ ሌላ ምንም ማለት ስላልቻልኩ…ከዛ
አስከተልኩና‹‹ጋሼ ዛሬ ስለ ሩት እናት እንድናወራ ነው
የምፈልገው››አልኳቸው፡፡
‹‹ስለእሷ ምን…?››
‹‹ከእሷ ጋር ያሎትን ግንኙነት በተመለከተ…መቼስ በጣም
ጠበቅ ያለ ይመስለኛል..?ተሳሳትኩ?››
‹‹አልተሳሳትክም …ቤተሰብ እኮ ነን !ማለቴ የታላቅ ወንድሜ
ሚስት ነበረች..››
‹‹አይ ያን ማለቴ አይደለም …ልጅ ሆናችሁ አንድ ሰፈር ነው
አይደል ያደጋችሁት?››
‹‹ አዎ የእኔ ወላጆች ቤት እና የእሷ ወላጆች ቤት አንድ ሰፈር
ነበር…ከእኛ ቤት ግቢ ወጥተህ ቀጥታ መንገድን
እንደተሸገረክ....ፊት ለፊት የምታገኘው የእነሱን ቤት
ነው..ከዛ ጎን ደግሞ የእነ ዮሴፍን ቤት..ዬሴፍ ማለት አሁን
አንተ ስትመጣ የወጣው አብሮ አደግ ጎደኛዬ ያልኩህን ››
‹‹ስለዚህ በደንብ ትግባቡ ነበር ማለት ነው?››
‹‹በትክክል …እርግጥ ከእኔ ይልቅ ከዬሴፍ ጋር እጅግ በጣም
የሚግባቡና የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ….ግን ምንም እንኳን
የእነሱ ቅርርብ የጠነከረ ቢሆንም የእኔ የተለየ ነበር››
‹‹የተለየ ነበር ሲሉ?››
‹‹በጣም ነበር የማፈቅራት ..በጣም ነበር ላገባት እፈልግ
የነበረው ..የልጆቼ እናት
እንድትሆንም እፈልግ ነበር ››
‹‹‹ይሄንን ነግረዋት ያውቁ ኖሯል?››
‹‹ከሚሊዬን ጊዜ በላይ ነዋ…አጋጣሚውን ሁሉ ባገኘው
ቁጥር ከመንገር እና ከማስረዳት ቦዝኜ አላውቅም››
‹‹የእሷስ ምልስ በወቅቱ ምን ነበር?››
‹‹ያው እሷ በጣም አይናፍር እና ስሜቷን አውጥታ መግልፅ
የማትችል አይነት ሰው ነበረች…ሁሉ ነገር በሆዷ ነው..ሁል
ጊዜ ስንገናኝና ስነግራት በፈገግታ እና በዝምታ ታዳምጠኝ
ነበር..ያ ደግሞ ለእኔ ትልቅ ተስፋና ጉጉት ውስጥ እንድገባ
አድርጎኝ ነበር››
‹‹ታዲያ እንዴት ወንድሞት ሊያገባት ቻለ?››
‹‹ምን መሰለህ …በዛ ወቅት ጋብቻን በተመለከተ ወሳኞቹ
ሁለቱ ጥንዶች ሳይሆኑ ወላጆቻቸው ነበሩ… ወንድሜ እንዲሁ
ወንድሜ ልበለው እንጂ የአባት ያህል ነበር በዕድሜ
የሚበልጠኝ..በጣም ትልቅ በሀብትም የተትረፈረፈው..
በንጉሱ ጊዜ ትልቅ ባላባት የነበረ ሰው ነው..በዛም ምክንያት
ማንም ቤተሰብ ከእሱ ጋር መዛመድ እንደክብር እና እንደትልቅ
ዕድል ነው የሚቆጥረው ….እኔ ደግሞ በዛን ወቅት ገና
ከቤተሰቦቼ ድጎማ ራሱ ያልተላቀቅኩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ
ነበርኩ..እና ወላጆቾ ከእኔ ወላጆች ጋር ተደራድረው እና
ተመሳጥረው አንስተው ሲሰጧት ከመንፈራገጥ፣ ከማዘን እና
ከማልቀስ ውጭ ምንም ላደርግ አልቻልኩም.. ማስጣሉን
ተወው በግልፅ በአደባባይ ወጥቼ እንኳን ቤተሰቦቼ ወይም
ቤተሰቦቾ ፊት ለፊት ቀርቤ ‹የእኔ ፍቅረኛ ነች… የብዙ አመት
ምኞቴ እና የረጅም አመት ተስፋዬ ነች ..ማንም ሊነጥቀኝ
አይችልም› ብዬ ለመጋፈጥ ድፍረቱም ብቃቱም አልነበረኝ…፡፡
ምክንያቱም ቤተሰቦቼ በንግግር አና በውይይት የማያምኑ
በጣም ወግ አጥባቂዎች ከመሆናቸውም በተጨማሪ
እንድፈራቸው አድርገው ነበር ያሳደጉኝ፡፡ …ደግሞ በእሷ እና
ወንድሜ መጋባት የእኔ ልብ ብቻ አልነበረም የተሰበረው..
ዬሴፍም በጣም አዝኖና ሚሆነው ነገር ጠፍቶት ነበር..በዛም
ብስጭት ነው አገር ጥሎ ወደሱዳን የተሰደደውና ከብዙ ውጣ
ውረድ ቡኃላ ወደአሜሪካ መግባት የቻለው ፡፡
‹‹እሱ ደግሞ በምን ምክንያት?››
‹‹ነግሬሀለው እኮ ..ምንም እንኳን የማፈቅራት እና ላገባት
የምፈልገው እኔ ብሆንም እሱ ከእኔ በላይ በጣም
የሚቀርባትና የሚወዳት ጓደኛው ነበረች..ታዲያ ዕድሜውን
ለጨረሰና ለማታፈቅረው ሰው ስትዳር እንዴት
አይበሳጭ..እንዴት አይናደድ›› አልተዋጠልኝም..ቢሆንም
ስሜቴን ለእሷቸው በግልጽ ማሳወቅ አልፈለኩም…. ዝም
ብዬ ጥያቄዬን ቀጠልኩ‹‹እሺ ለመሆኑ እርሶስ ካገባች ቡኃላ
ፍቅሩ ቀነሰሎት?››
‹‹ቀነሰሎት…!!! ምን መቀነስ ጭራስ በብዙ እጥፍ ጨመረ
እንጂ››
‹‹እሷስ?››
‹‹የእሷን እርግጠኛ ሆኜ ልነግህ አልችልም..ወንድሜን
በማግባቷ ግን ተከፍታ
ነበር..ዕድሜ ልኳንም ደስተኛ አድርጎት እንደማየውቅ
በርግጠኝነት መናገር እችላለው…››
‹‹ስትታመም እርሶ ውጭ ነበሩ… ከዛ ወስደው አሳከሞት?››
‹‹አዎ… ያ ወቅት በህይወቴ በምሉዕነት የኖርኩበት ብቸኛው
ጊዜ ነበር …እነዛ ወደ አሜሪካ መጥታ አብረን ያሳለፍናቸው
አመታት ፍጽም የማይዘነጉ ገነታዊ ወዘና የነበራቸው
ነበሩ….እና እሷን በማሳከሜ እና በዛ በመከራዋ ወቅት
አብሬያት ከጐኗ በመሆኔ አሁንም ድረስ እራሴን እንደእድለኛ
ነው የምቆጥረው….እርግጥ ለህክምና የወጣው ወጪ
በጣም ብዙና ከእኔ አቅም በላይ ስለነበረ ብዙውን እጅ
የሸፈነው ዩሴፍ ነበር..እሱም ያው እንደነገርኩህ በወቅቱ
እዛው አሜሪካ ነበር የነበረው..እንደእኔ ለትምህርት ሄዶ
ሳይሆን አንደኛውን እዛው ነበር የሚኖረው..ዜግነቱንም ቀይሮ
የተደላደለ ኑሮና አቅም ስለነበረው በዛ ላይ የእኔም ሆነ የእሷ
የልብ ወዳጅ ስለነበረ ያለማንገራገር በደስታ ነበር የረዳን…ለዛ
ነው ቅድም በጣም ጥሩ ሰው ነው ያልኩህ››
‹‹ይገርማል!! እና እዛ እርሶ ጋር ሆና በምትታከምበት ጊዜ
በመሀከላችሁ የተፈጠረ ምንም ነገር የለም?››
‹‹መፈጠር የነበረበት ነገር ሁሉ ተፈጥሯል..እዛ ሆነን ምንም
አይነት የቤተሰብ ፍራቻ ..የሰው ሀሚት… የባህል ተጽዕኖ
ስልልነበረብን የምኞታችንን በሙሉ መከወን ችለን ነበር፡፡››
‹‹እና ታዲያ ለምን ተመለሰች.?.በዛው ጠፍታችሁ በመቅረት
ለዘላለም ህይወትን አብራችሁ መቀጠል ትችሉ ነበር››
‹‹አዎ እንችል ነበር ..የእኔም ፍላጎት እንደዛ ነበር:: ግን ያው
የእናት ነገር ሆኖ የልጆን የደረጄን ናፍቆት መቋቋም
አልቻለችም ..በዛ ላይ ሌላ የምትመለስበት ምክንያት ነበር››
‹‹የምን ምክንያት?››
‹‹ፀንሳ ነበር?››
‹‹ፀንሳ ሲሉ..!!ከማ?››
‹‹ያው ሌላ ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ ››
‹‹ይገርማ…ታዲያ ከእርሶ መፀነሷ እንዴት ወደሀገር ቤት
ለመመለስ ምክንያት ሊሆናት ይችላል…?፡፡እንደውም
ይበልጥ እዛው ለመቅረት እንድትወስን ያስገድዳታል

👍3
እንጂ …
ነው ወይስ
ጽንሱን አስወረደችው?›››
‹አይ ከጤንነቷ ጋር ተያይዞ ማስወረድ አደጋ ስለነበረው
እንድትሞክረው አልፈቀድኩላትም››
‹‹ታዲያ እንዴት አደረጋችሁ?››
‹‹በቃ ወደ ሀገር ቤት ተመልሳ ወለደቻ….››
‹‹ወለደች ..!!!እንዴት …ማንን?››
››ሩትን ..ሩት የእኔ ልጅ ነች››
ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳው… እጆቼን አፌ ላይ
ከደንኩ…ከዛ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ተመልሼ
ተቀመጥኩ
‹‹ቆይ ወንድሞትስ…?እኔ በታሪክም ቢሆን እንደሰማውት
በጣም ኃይለኛ እንደሆኑ ነው..በደልን አሜን ብለው የሚቀበሉ
አይነት ሰው አይደሉም..ታዲያ..?››
‹‹ጉዳዩን በሚስጥር ነበር የያዝነው… ሩት በሰባት ወር
እንደተወለደች ነው የሚታወቀው..እወነታው ግን እንደዛ
አልነበረም..በትክክለኛው ዘጠኝ ወሯን ጠብቃ ነው
የተወለደችው…ወንድሜ ከእሱ ያለጊዜዋ እንደተወለደች ነው
ሚያውቀው.. ከአሜሪካ ወደሀገር ቤት ስትመለስ የሁለት ወር
ጽንስ በሆዷ ይዛ ነበር››
‹‹እሷስ ….ማለት ሩት አጓቷ ሳይሆነ አባቷ እንደሆኑ
ታውቃለች?››
‹‹አታውቅም››
‹‹አሁንም?››
‹‹አሁንም አታውቅም..ይሄ የእኔ እና የእናቷ የብቻችን ሚስጥር
ነበር… አሁን እናቷ የለችም ስለዚህ የብቻዬ ሚስጥር
ነው..አሁን አንተ ከማወቅህ በስተቀር ማለት ነው››
‹‹ታዲያ መቼ ሊነግሯት አሰቡ?››
‹‹እኔ እንጃ ..አንድ ቀን ወኔና ብርታቱን እግዚያብሄር የሰጠኝ
ቀን..ወይንም እስትንፋሴ ልትቋረጥ ስትል እና ማጣጣር
ስጀምር በንዛዜ መልክ…››
‹‹አንድ ሌላ ጥያቄ ልጠይቆት ጋሼ?››
‹‹ጠይቀኝ››
‹‹ሚስት አግብተው ያውቃሉ..?ሌላስ ልጅ የሎትም?››
‹‹አየህ እኔ እና ልጄ ሩት አንድ አይነት ባህሪ ነው ያለን ..ምን
አልባት አንድ አይነት ደም በውስጣችን የሚራወጥ አባት እና
ልጅ ስለሆነ ይሆናል…በህይወታችን ሙሉ አንድ ሰው ብቻ
እንድናፈቅር ነው የተፈቀደልን፡፡ሞዛዛ የምንባል አፍቃሪዎች ነን
፡፡ ወጣት ሆኜ የእሷን እናት በልቤ አስገባው ..አሁንም ድረስ
ያው እሷው ላይ ነኝ…አግብታም አልተውኳት..ወልዳም
አልተውኳት…ሞታም ልረሳት አልቻልኩም፡፡ ልክ ልጄ አሁን
ኃይሌን አፍቅራ ህይወቷን ሙሉ ድራማዊ በሆነ ውጥንቅጥ
ትዕይንት እየመራች እንዳለች ሁሉ እኔም ያው እንደእሷ በሜዳ
ላይ ትዕይንት እና በአደባባይ ተውኔት የውስጤን እሳት
መግለጽ አልቻል እንጂ በሚስጥር እና በስውር በጓዲያዬ
ውስጥ ጨርቄን ጥዬ እንዳበድኩና እንደተኮራመትኩ ይሄው
ዕድሜዬ አለቀ… አየህ ልጄ አሁን ያለችበት ስቃይና መሳቀቅ
እኔ በምረዳላት መጠን ማንም ሊረዳላት አይቻልም..ልረዳት
የቻልኩት ልጄ ብቻ ስለሆነች አይምሰልህ..እኔም ጋር ያለው
ህመም ተመሳሳይ ስለሆነ ነው፡፡ ምላሻችን ይለያ እንጂ
ህመማችን ተመሳሳይ ነው፡፡ እኔ ሽንፈቴን ተቀብዬ እራሴን
ብቻ በመቅጣት ስኖር እሷ ግን ፍቅር እና በቀልን አዳቅላ
እራሷንም ያፈቀረችውንም ሰው በመከራ እየለበለበች ነው፡፡
እኔ ያፈቅርኳትን ሴት በተቻለኝ መጠን የእኔ ባትሆንም
እንኳዋን ባገኘውት አጋጣሚ እየተንከባከብኮት እና
ስትቸገርም አይዞሽ እያልኳት ነው የኖርኩት … ልጄ ግን
ያፈቀረችውን ኃይሌን በውስጧ በተፈጠረው እሳት
በመለብለብ ከልቧ ሳታወጣው ግን በበቀሏ እያደማችው
ትገኛለች፡፡
.ውይይታችንን ዘግተን የፕሮፌሰሩን የጥናት ክፍል ለቅቄ
ስወጣ ሩትን ሳሎን መሀል ላይ ቆማ አገኘዋት..ሽቅርቅር ብላ
ለብሳለች
‹‹እሺ እንዴት ነህ?››አለቺኝ ገና እንዳየችኝ ፈገግ ብላ
‹‹አለውልሽ… አንቺስ?››
‹‹ያው እኔም እንደምታየኝ ሰላም ነኝ››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው …በጣም አምሮብሻል ››አልኳት
ደግሞም እውነቴን ነው በጣም ዝንጥ ብላለች
‹‹አመሰግናለው..ወደውጭ እየወጣው ነው አብረን እንሄድ››
‹‹ደስ ይለኛል››አልኳት… ተያዘን ሰሎኑን አልፈን ግቢውን ትተን
ወጣን ..የተወሰነ መንገድ በዝምታ ተጉዘን የእነሱን ሰፈር
ከለቀቅን ቡኃላ መለያያችን ደረሰ ብዬ ሳስብ‹‹ጊዜ
ይኖርሀል..ማኪያቶ ልጋብዝህ ?››አለችኝ
‹‹አረ አለኝ… በጣም ደስ ይለኛል››ፈጠን ብዬ በደስታ
መለስኩላት
‹‹እሺ ና ››ብላኝ ቀኝ እጄን ይዛ እየጎተተችኝ ከአቅረቢያው
ከሚገኝ አንድ መለስተኛ ካፌ ይዛኝ ገባች..ቁጭ አልንና
ማኪያቶ አዘዝን… ፈጠን ብሎ መጣልን..እየጠጣን ወሬ
ጀመርን
‹‹እንዲ ዝንጥ ብለሽ ወዴት እየሄድሽ ነው?››ሳላስበው
የጠየቅኳት ጥያቄ ነበር
‹‹ያው የተለመደው ቦታ ነዋ ..ኃይልሻ ጋር››መለሸችልኝ
‹‹ግን እስከመቼ ነው እንዲህ ሚቀጥለው..?››
‹‹እስከመጨረሻው ነዋ››
‹‹ጥሩ ይመስልሻል… ?››
‹‹ጥሩ ይሁን አይሁን እኔ ምን አገባኝ››
‹‹ያው ሁለታችሁም እየተሰቃያችሁ ነው ብዬ እኮ
ነው..የሁለታችሁም ህይወት እየባከነ ነው..በአንድነት
መቀጠል ካልተቻለ እኮ ተለያቶም በተናጠል የራስን ህይወት
መቀጠል ይቻላል››
‹‹አይ እኛ ጋር እንዲህ አይሰራም..መላያየት ብሎ ነገር
የለም…አብረን መኖር ካልቻን አብረን እንሞታታለን እንጂ
ለየብቻ የሚባል ታሪክ የለም››
‹‹እሱም እኮ በጣም ያፈቅረሻል ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹አዎ እንደሚያፈቅረኝ ስለማውቅማ ነው ለየብቻ የሚባል
ነገር የለም የምልህ››
‹‹እኮ ሁለታችሁም ትፋቀራላችሁ… በመሀከላችሁ ያለው
ሚስጥር ነው ለጋብቻችሁ እንቅፋ የሆነው..ኃይሌም አምኖ
የተቀበለው ሚስጥሩ ትዳራችሁን ለማፍረስ አሳማኝ ምክንያት
ስለሆነ ነው..እርግጠኛ ነኝ አንቺም ሚስጥሩን ብታውቂ
ተመሳሳዩን ውሳኔ ነው የምትወስኝው››
‹‹ሚስጥሩን ንገረኝ እስኪ?››
‹‹እይ እኔ እንኳን እስከአሁን አላውቀውም..ግን አጎትሽ
ወይም ሃይሌ እንዲነግሩሽ ላሳምናቸው እችላለው››
‹‹ተወው ባክህ… ምንም እርባን የለውም?››
‹‹እርባንማ አለው…ሚስጥሩን ሳታውቂው እንዴት እርባን
የለውም ብለሽ መደምደም ትችያለሽ?››
‹‹እነሱ ከማወቃቸው ከሶስት አመት በፊት ሚስጥሩን
አውቀው ነበር››
‹‹ምን!!?››
‹‹አዎ ሚስጥሩን ከሁሉም ቀድሜ አውቀው ነበር..ከኃይልሻ
ከመጋባታችን በፊት አውቀዋለው ነበር››
‹‹እንዴት… ?ማን ነገረሽ?››
‹‹እቴቴ የኃይልሻ እናት….. ልትሞት ስትል ነግራኛለች….
ከሞተች ቡኃላ ለልጇ አዋዝቼ እንድነግርላት ነበር
የነገረቺኝ….እኔ ግን ኃይሌ እንደእኔ ስላልሆነ ሚስጥሩን ካወቀ
ፍቅራችንን ያፈራርሰዋል ህልማችንንም ያጨለመዋል ብዬ
ስለሰጋው በውስጤ ቀበርኩት..እናም እሱን ይዤ ከአገር
ጠፋው …አገባውት፡፡ ከሶስት አመት በላይ ጣፋጭ የጋብቻ
ህይወት አሳለፍን ፡፡..ብኃላ ያ አባቴ ጣር ላይ እያለ
ሚስጥሩን ለራሱ ለሀይሌ በመንገር ድብልቅልቁን አወጣው
እንጂ ……
..ለምንድነው ግን የሀገራችን ሰዎች በዕድሜ ልክ የሰሩትን
እና አዳፍነው ያኖሩትን አስጠሊታ ታሪካቸውን ሊሞቱ ሲሉ
የሚዘከዝኩት…?››
‹‹ለመሆኑ ሚስጥሩ ምንድነው?››
‹‹ሚስጥሩ?››
‹‹አዎ ሚስጥሩ››
‹‹ኃይሌን ጠይቀው…››ብላ እጇን ወደቦርሳዋ አስገባችን
የማኪያቶውን ሂሳብ አውጥታ ጠረጵዛ ላይ በማስቀመጥ
በተቀመጥኩበት ጥላኝ ሄደች… እያየዋት ታክሲ ውስጥ
ገባች፡፡ ለመሆኑ ይህቺ ጉደኛ እንስት እስከመቼ ድረስ ነው
እኔን የምታስደምመኝ…? ለመሆኑ ያ አውቀዋለው ያለችው
ሚስጥር ምን ይሆን..? ፕሮፌሰሩስ አጎቷ ሳይሆኑ ወላጅ አባቷ
መሆናቸውን ቀድማ አውቃ ይሆን?ይገርማል …የስሜት
ህዋሳቶቻችን አንድ ላይ ቢቀናጁ እንኳን እውነትን ለመዳኘት
ያላቸው ብቃት ሙሉ አይደለም፡፡ለዚህ ነው አንዳችን ጋር
እውነት ነው ብለን የደመደምነው ክስተት በሌላው ሰው
ውስጥ ተቃራኒውን ገጽ ይዞ የሚናገኘው፡፡ይሄም ነው
ያለማግባባታችን መሰረታዊ መነሻ ምክንያት
ሚሆነው….ምክንያቱም ሁለችንም በራሳችን ውስጥ እውነት
ነው ብለን
ላመንበት ጉዳይ

👍2
ስለምናዳላ….ለዛም ጥብቅና
ቆመን እስከመጨረሻም በጭፍን ስለምንፋለም፡፡አዎ በዛሬው
ቀን ከሁለቱ ሰዎች ጋር ካደረግኩት ውይይት የተገነዘብኩት
አንድ ሀቅ ቢኖር ይሄንን ነው፡፡
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
ቆመን እስከመጨረሻም በጭፍን ስለምንፋለም፡፡አዎ በዛሬው
ቀን ከሁለቱ ሰዎች ጋር ካደረግኩት ውይይት የተገነዘብኩት
አንድ ሀቅ ቢኖር ይሄንን ነው፡፡
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#ፍቅርና_በቀል
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
✍ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
"ፍቅር ከበጎነት ማህፀን እንጂ ከፍራቻ ጉያ ሊመነጭ
አይችልም።"
‹‹ዛሬ አንድ ነገር እንድትነግረኝ ነው የምፈልገው….. ትዳር
እንዴት ነው የመሰረታችሁት?›› ከኃይሌ ጋ እንደተገናኘን
የጠየቅኩት የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር ‹‹ያው ፍቅራችን ከዚህ
በፊት ባጫወትኩህ ቅደም ተከተል በየጊዜው እያደገ እያደገ
ከሰውም መደበቅ የማንችልበት ደረጃ ስንደርስ እና ወሬው
ቀስ በቀስ መዛመት ሲጀምር ስጋት ውስጥ ወደቅን››
‹‹የምን ስጋት?››
‹‹አባቷ ጀሮ ይደርሳል ብለን ነዋ… አባቷ ከሰሙ መቼስ
ጭንቅላቴን በገጀራ ከመቀንጠስ እንደማይመለሱ ሁለታችንም
እርግጠኛች ነበርን፡፡››
‹‹የእውነት ይገድሉኛል ብለህ ታስባለህ?››
‹‹ወሬውን በሰሙበት ቅፅበት ፊት ለፊታቸው ካገኙኝ
እንደሚያደርጉት እርግጠኛ ነኝ፡፡››
‹‹ታዲያ እንዴት አደረጋችሁ?››
‹‹ተመካከርንና ለመጥፋት ተስማማን… እሷ ከአባቷ አንድ ሺ
ብር ሰርቃ…..በአንድ ሻንጣ የሁለታቸንንም ልብስ ከተን
በለሊት ማንም ሳያየን ሹልክ ብለን ጠፋን››
‹‹ግን እንጥፋ ስትላት ሩት ምንም አላንገራገረችም?››
‹‹የመጥፋቱ ሀሳብ እኮ የእሷነው…እኔንም ጨቅጭቃና ለምና
ያሳመነችኝ እሷው ነች››
‹‹ታዲያ እንዴት አደረጋችሁ..ማለቴ ወደየት ጠፋችሁ?››
‹‹እንዳልኩህ በጠፍ ጨረቃ ከቤት ወጣንን አቶቢስተራ
ደረስን….ዝም ብለን ነው
ከተኮለኮሉት የክፍለሀገር አውቶቢሶች መካከል አንድ ውስጥ
የገባነው፡፡ ዋናው አላማችን ከሽማግሌው መራቅ እንጂ
ወደየትም ብንሄድ ግድ አልነበረንም… ይሄኛው አቅጣጫ
ከዚህኛው አቅጣጫ ይሻላል…ይሄኛው ከተማ ከዛኛው ከተማ
ይመቸናል ብለን ለመምረጥ ዝግጁነቱም ዕውቁም
ልነበረንም፡፡
‹‹እሺ በስተመጨረሻ ወደ የት የሚሄድ መኪና ውስጥ
ገባችሁ?››
‹‹ወደደቡብ…አርባምንጭ ነበር የወሰደን..፡፡ አርባምንጭ
በጥሩ ሁኔታ ነበር የተቀበለችን፣ሲቀላ ላይ ነበር
የከተምነው..እዛው ነው የተጋባነው፣ እዛው ነው በባልና
ሚስትነት ሶስት አመት ያሳለፈነው…እዛነው ደሳሳ ከሆነች
አንድ ክፍል የኪራይ ቤት ጀምረን የራሳችንን ቤት
እስከመስራት የደረስነው…፡፡ በመጀመሪያው አንድ አመት
ህይወት በጣም ፈታኝ ነበረች.. ሊስትሮ ሰርቼያለው፤
ተሸካሚም ሆኜ ነበር፤ኮንስትራክሽን ውስጥም በቀን
ስራተኝነት ሰርቼያለው..እሷም እንደዛ..፡፡
ያ ሁሉ ሆኖ ግን ህይወታችን የምሬት አልነበረም… ምክንያቱም
በዓለም ላይ ከሚገኙ ነገሮች በጣም ውዱ ሀብት በጎጆችን
ነበረ…ሰማየሰማያት ለማረግ የሚያስችለን ኃይል ያለው ፍቅር
በቤታችን ነበረን….…
ከሁለተኛ ዓመት ቡኃላ ግን እንደአጋጣሚ ጠርቀም ያለ ብር
እጄ ላይ ስለገባ ንግድ ጀመርኩ …ያው ብልህ ስለሆንኩ
ሳይሆን እንዲሁ እጣ ክፍሌ ሆኖ መሰለኝ ንግድ በጣም
ይሳካልኛል… በመጀመሪያ መለስተኛ የኮንቲነር ቤት
ተከራይተን የዓሳ ጥብስ እና ሾርባ መሸጥ ጀመርን… ያው
መቼስ ዕድሜ ለአባያ እና ጫሞ ሀይቅ ይሁንና አርባምንጭ
በዓሳ ምርቷ የበለፀገች እና የተትረፈረፈ ምርት ያለባት
ሀብታም ከተማ ነች… እና ያንን ተጠቀምንበት ..፡፡ገበያው
ሲደራልን ንግዳችንን አሳፋፋነው…የተሸለ ቤት ቀየርን..ከዛ
በቃ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሁለት እግራችን ቆምን …በደንብ
ተደራጀን፡፡መሬት ገዝተን እቤት እስከመስራት ደረስን..ይሄ
ሁሉ ሲሆን ግን ከአዲስ አበባ ጋር ያለን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ
እንደተቋረጠ ነበር፡፡ሁለታችንም በየውስጣችን እንዴት ሆነው
ይሆን?ብለን ማሰባችን እና መጨነቃችን የማይቀር ቢሆንም
በግልፅ ግን እርስ በርሳችን አንስተን ተወያይተንበት አናውቅም
ነበር፡፡ ሰላሜ ትሁትን ካረገዘች ከስድስት ወራት ቡኃላ ግን
መረበሽ ጀመረች…በህልሜ አባቴን አየውት….ወንድሜ
እንዲህ ሆነ ..የእናቴን እና የእቴቴን የሙት መንሰፈስ
አገኘው..የማትለው ነገር አልነበራትም፡፡..ተለከፈች እንዴ?
ብዬ እስክጠራጠር ድረስ…በየቀኑ መተከዝና ማልቀስ ቋሚ
ስራዋ ሆነ ..ግራ ገባኝ፡፡
የማደርገው ስለጠፋኝ ወሰንኩ…ከሶስት አመት ቡኃላ ወደ
አዲስአበባ ደወልኩ…የማውቀው የሰፈር ሰው ጋር…
እውነትም የሰላሜ ህልሞች ከአባቷ የጭንቀት መንፈስ
የተበተኑ እውነተኛ መልዕክቶች ነበሩ….ሽማግሌው በጠና
ታመው በሞት እና በህይወት መካከል መቃተት ከጀመሩ
ሳምንት እንዳለፋቸው ነገሩኝ..በተጨማሪም ልጆቼን ካሉበት
ፈልጉልኝና አይናቸውን አይቼ፤ይቅርታቸውን አግኝቼ ልሙት
እያሉ ወዳጅ ዘመድን ሁሉ እያስጨነቁ ነው ብለው
ነገሩኝ….ግራገባኝ…፡፡ይሄንን ጉዳይ ከሰላሜ ልደብቃትም
አስቤ ነበር….ግን ቡኃላ ተረጋግቼ አሰብኩበት …ቢሞቱስ!!
መታመማቸውን ሰምቼ እንደደበቅኳት ያወቀች ቀን እስከ
መጨረሻው እንደምትጠላኝ ሳስብ የሰማውትን ሁሉምንም
ሳላስቅር ነገርኳት..ያዙኝ ልቀቁኝ አለች.. በማግስቱ ብን ብለን
ተያይዘን አዲስአበባ ገባን፡፡
‹‹እና ስትደርሱ የእውነት ታመው ነበር?›››
‹‹አዎ በመጨረሻው የህይወታቸው ምዕራፍ ላይ ነበሩ….››
‹‹እና እንዴት ተቀበሏችሁ?››
‹‹እኛን ከጠበቅነው በተቃራኒው በፍጽም ሰላም እና ፍቅር
ነበር የተቀበሉን››
‹‹ታዲያ ሌላ..?››
‹‹ሌላውማ ትዳራችንን ነው…በመጀመሪያ የማይረባ ምክንያት
እና ሰበብ እየፈጠሩ ነበር መፋታት አለባችሁ ያሉን…ቡኃላ
ግን ያ እንደማያዋጣችው ሲረዱ መሰለኝ ለብቻዬ አናገሩኝ››
‹‹ምን ብለው?››
‹‹ያው እውነተኛ ምክንያታቸውን አስረዱኝ..አስረዱኝ እንኳን
ማለት ይከብደኛል…ከዛ ይልቅ አረዱኝ ብል ይቀላል››
‹‹ምን አሉህ?››አልኩት ሚስጥሩን ለመስማት ቸኩዬ …
‹‹የእለቱ ትዕይንት ዛሬም ልክ በሆሊውድ መንደር እንደተቀረጸ
ፊልም ጥርት ብሎ ይታየኛል፡፡ አልጋው ውስጥ ተዘርረው
ተኝተው ነበር….ሁለት ትራስ ተደራርቦላቸው በመጠኑ ቀና
እንዲሉ ተደርጓል…እና በሚንቀጠቀጥ አንደበታቸው
‹‹ልጄ አባትህ ጣሰው አይደለም ››አሉኝ
‹‹እንዴ እርሶ እራሶት አይደሉ እንዴ ያኔ ገና በልጅነቴ ጣሰው
ነው ያሉኝ?››
‹‹ዋሽቼሀለው››
‹‹እሺ እርሶስ ይዋሹኝ…እሱ ግን እኮ አባትህ ነኝ ብሎ
ተቀብሎኛል...አባትህ ነኝ ብሎ ወዷኛል ....አባትህ ነኝ ብሎ
ይሄው እስከዛሬ ሳይተወኝ ይንከባከበኛል…››
‹‹አውቃለው..እንዳዛ ያደረገው እኔ አባቱ ሁን ስላልኩትና
ስለሚፈራኝ ነው….››
‹‹በፍፅም…እሺ እርሶ እንዳሉት ፈርቶ አባትህ ነኝ
ይበለኝ..ፈርቶ እንዴት ሊወደኝ ይችላል…››
‹‹ጣሰው በጣም በጎና መልካም ሰው ስለሆነ ነው…
እውነትህን ነው ፍቅር ከበጎነት ማኅፀን እንጂ ከፍራቻ ጉያ
ሊበቅል አይችልም››
‹‹እንደዛ እሟገታቸው የነበረው ፈርቼነው..ብቸኛ እንዳያደርጉኝ
ፈርቼ….ልጅ ሆኜ አባት አልባ መሆን እንዴት እንደነበር
አቅቃለው…እስከዛም ጊዜ ድረስ ስሜቱ ከውስጤ አልጠፋም
ነበር..ያንን እጦት…ያንን መሳቀቅ ያጠፋልኝ እና ያስወገደልኝ
አባቴ ጣሳው ነው..አሁን አባቴ ካልሆነ ተመልሶ ያ አስቀያሚ
ስሜት ሊሰማኝነው….ፍራቻዬ ያ ነበር….ሙግቴን
ቀጠልኩ‹‹እኔ እንጃ አይመስለኝም..ደግሞ ግድለኝም ..አባቴ
ነው ብዬ አንዴ አምኜያለው በቃ አበቴ ነው››
‹‹ትክክል ነህ…ወላጅ አባትህ ግን አኔ ነኝ››
‹‹ምን!!! ?››
‹‹አዎ ወላጅ አባትህ ..እኔ ..ነኝ››አስጠሊታ የተሰባበረ እና
የተቆራረጠ ድምጽ ወደጆሮዬ እየተንጠባጠበ ገባ
‹‹እንዴት ተደርጎ?››
‹‹ያው እናትህ እኔ ጋር ለረጅም ጊዜ እንደኖረች
ታውቃለህ….የደረጄ እናትን ከማግባቴ በፊት ለብዙ አመታት
በቤቴ የነበረች መልካም ሴት ነበረች..ያው በድብቅም ቢሆን
ግንኙነት ነበረን..ማለቴ ጾታዊ ግንኙነት››
‹‹ግንኙነት ነበራችሁ…ወይስ ጌታዋ ነኝ ብለው እያስገደድ
ይተኟት ነበር?››››

👍2🥰1
እሱ ምንይረባሀል…ዋናው ወላጅ አባትህ መሆኔን
ማወቅህ ነው?››
‹‹ይሄ ቀልድ መሆን አለበት..እርሶ የእኔ አባት በፍጽም ሊሆኑቸ
አይችሉም በጣም ነበር እኮ የሚጠሉኝ..››
‹‹አልጠላህም ነበር…ልጄ ለምን እጠላሀለው..እርግጥ
ከሌሎቹ ልጆቼ እኩል
አላቀረብኩህም ይሆናል…ግን አልጠላህም››
‹‹ኸረ በደንብ ነው የሚጠሉኝ…በጣም ነበር
የሚያመነጫጭቁኝ..በጣም ነበር
የሚጠየፉኝ…በጣም ነበር የሚያሰቃዩኝ…፡፡እርግጥ
ይገባኛል…ከገረድ ወለዱ ቢባሉ ክብሮት በጣም ዝቅ ይላል…
እንዴት ተደርጎ!!የእርሶ ወርቅ የዘር ፍሬ ገረድ መህፀን ውስጥ
ገብቶ እኔን የመሰለ የተረገመ ዲቃላ ሊያፈራ ይችላል..
በፍጽም….፡፡.ልንገሮት በጣም እራስ ወዳድ የሆኑ እርጉም
ሰው ኖት…. ምን ያህል እንደምፈራዎት ያውቃሉ …?እናቴ
ስለጭራቅ እና ቡልጉ አስፈሪ ተረት ስትነግረኝ እኔ
የሚመጣብኝ የእረሶ አስፈሪ ገጽ እና የተቋጠረ ጨለማ ፊት
ነበር…ህጻን ሆኜ ወደ ውጭ ስወጣ ጅቡ ይበላሀል እያሉ
ሲያስፈራሩኝ እሮጬ ወደቤት የምገባው ይሄ አውሬውን ጅብ
ፍርቼ ሳይሆን እርሶ ከጭለማ ውስጥ ወጥተው ያንቁኛል ብዬ
በመፍራት ነበር..እና ምን ያህል እንደምፈራዎት እና
እንደምጠላዎት ገባዎት…የልጅነት ጊዜዬንስ ምን ያህል
ጨለማ አድርገውት እንደነበረ ተረዱ..››
‹‹ይቅር በለኝ ልጄ..ይቅርበለኝ››
‹‹እርሶን….ይቅር ማለቴ ገነት የሚያስገባኝ ብቸኛው በጎ
ድርጊት ቢሆን እንኳን
አላደርገውም..እርሶን ይቅር ብዬ ገነትን ከምወርስ ….እንዲሁ
ከነፀፀቶት ወደ ቀጣዩ አለም ሸኜቼዎት እኔም ሲኦልን ብገባ
እመርጣለው››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..በደሌ ይቅርታ የሚያሰጠኝ
አይደለም..ግን ያው ይሄ እውነታውን አይቀይረውም ….እኔ
ወላጅ አባትህ ነኝ..ሩትም የአብራኬ ክፋይ ልጄ ነች..ስለዚህ
እህትህ እንጂ ሚስትህ ልትሆን አትችልም››እስከዛን ደቂቃ
ድርስ እየነገሩኝ ያለውን ቀፋፊ ታሪክ ከሩቴ ጋር አላየያዙኩትም
ነበር…ለካ የበለጠው የታሪኩ ቆሻሻው ገጽ ገና ነበር‹‹ሚስቴ
መሆን አትችልም..ምን ነክቶሀል..ነች እኮ…ከተጋባን ሶስት
አመት አልፎናል እኮ››ከንዴቴ ብዛት ከአንቱታ ወደ አንተ
ወረድኩት….
‹‹ቢሆንም መፍረስ አለበት…ያንን ያደረጋችሁት በእኛ ስህተት
ነው…ሚስጥሩን
ስላላወቃችሁ ነው…፡፡አሁን ግን አውቃችሆል …ስለዚህ
ልትፋቱ ግድ ይላል…ያው ከባህላችን ያፈነገጠ
በሀይማኖታችን የተከለከለ ነውር ድርጊት ነው››
‹‹ባህል ሀይማኖት ህግ ስለሚሏቸው ነገሮች እኛ
አያገባንም…ነውርም ላሉት ነውሩን የሰራችሁት እናንተ ወላጅ
ተብዬዎች ናችሁ እንጂ እኛ አይደለንም.. በመጀመሪያ
ድርጊቱን እንደዚህ ባለ ሁኔታ እስዲወሳሰብ ማድረግ
አልነበረባችሁም ..እንደዛ መሆኑ ያጋጣሚ ጉዳይ እና
ከቁጥጥራችሁ ውጭ ሆኖባችሁ ቢሆን እንኳን ቀድማችሁ
ለእኛ መናገር ነበረባች..ዛሬ አንዲህ ነገሮች ሁሉ ብልሽትሽት
ከሉ ቡኃላ ሳይሆን ከብዙ አመት በፊት…..እና አስረግጬ
ልነግሮት የምፈልገው ነገር ቢኖር የእኔ እና የሰላም መጋባት
የእኛ ስህተት አለመሆኑን ነው››
‹‹ቢሆንም መፋታታችሁ የግድነው››
‹‹ይቀልዳሉ …እርጉዝ እኮ ነች››
‹‹አስወርዱት››ፈርጠም ብለው
‹‹አስወርዱት..ስድስት ወሯ ውስጥ እኮ ነው ያለችው››
‹‹ቢሆንም መውለድ የለባትም..ይሄ በዘራችን ተሰምቶ
የማይታወቅ ትልቅ ነውር ነው…ሰው ጆሮ ከደረሰ የቤተሰባችን
ክብር ገደል ገባ ማለትነው…እዚህ መጋባታችሁን የሚያውቅ
ማንም ሰው የለም…ከሌላ ሰው አርግዛ እንደነበረ እና
እንዳስወረዳት ማስወራት ትችላላችሁ››
‹‹ስታስወርድ ልትሞት ትችላለች››
‹‹ወልዳ የሰው ምላስ በቁሟ ከሚለበልባት ..ስታስወርድ …››
‹‹ስታስወርድ ምን .. ?እንዳይጨርሱት…›› በማለት
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እየተራገምኩ ና እየተሳደብኩ
በግማሽ ንዴት እና በግማሽ ዕብደት ጥያቸው ወጣው፡፡
ከሰው ራቅኩ… ከአካባቢው ራቅኩ አሰብኩበት..እረጅም
ሰዓት በእንባ እየታጠብኩ አሰብኩ..ምንም መወሰን አቃታኝ…
ሲቸግረኝ ደራጄ ጋር ደወልኩና የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኩት…
ከጠበቅኩት በላይ እሱንም አስደነገጠው…..ያው
የአባትዬውም ሁኔታ ተስፋ የሌለው በመሆኑ የእኛው ሁኔታ
ስላሳሰበው መሰለኝ ፈጥኖ መጣ…..
ሁኔታውን በድጋሚ አስረዳውት..ተነጋግረን ተጨቃጭቀን
ስምምነት ላይ ደረስን…፡፡የልጄን ነፍስ ማትረፍ ብችልም
ጋብቻችንን ግን መታደግ አልሆነልኝም…..፡፡ሰላሜን ዝም ብዬ
በደፈናው አልፈልግሽም አልኳት….ከአሁን ወዲህ ባልና
ሚስት አይደለንም አልኳት…በፍፁም ልትቀበለው
አልቻለችም…. ከአዕምሮዋ ውጭ ሆነች … በአዕምሮ
ህክምና ክትትል ስር ሆና ነው ለመውለድም የበቃችው ..
ከዛ በስምምነታችን መሰርት ትሁትን እንደተወለደች ገና
በጨቅላነቷ ደረጄ ወሰዳት ..ይዞት ወደ ስደት ሀገር ገባ…..እኔ
እና ሰላሜ ይሄው በምታየው ሁኔታ ላይ አለን፡፡ ይገርምሀል
ሳልነግርህ የዘለልኩት ሽማግሌው የዘመን ሀጥያቱን ተናዞ
ከሀጥያቱ የመነጨውን መከራ ወደ እኛ አሸጋግሮ ሲሞት
የሀብቱን ግማሽ ለእኔ ነበር ያወረሰው..ከዛ የተቀረውን ግማሽ
ለዋና ልጆቹ ለደረጄ እና ለሰላሜ አካፈላቸው፡፡ይሄ ሰውን ሁሉ
ግርም እንዲለው ያደረገ ኑዛዜ ነበር..አልዋሽህም እኔንም
አስደምሞኛል…..፡፡አሁን የምኖርበት ቤት እና ሆቴሉም ከውድ
አባቴ በውርስ ያገኘውት ንብረት ነው…እርግጥ በተወሰነ
መልኩ አሳድሼዋለው፤አስፋፍቼዋለው..ግን ያው በውርስ
ያገኘውት ነው››
‹‹እሺ ወንድሟ መሆንህን ለሩት ለምን አልነገራችሆትም
ታዲያ?››
‹‹እንዴት ብለን ..እንኳን እሷ እኔም መቋቋም አልቻልኩም››
‹‹ግን እርግጠኛ ናችሁ ይሄን ሚስጥር አታውቅም?››አልኩት
በቀደም ሩት የነገረችኝ ትዝ ብሎኝ
‹‹ኸረ አታውቅም…››እነደምታውቅ ቢያውቅ ምን ይሰማው
ይሆን ?ብዬ አሰብኩ፡፡
‹‹ታዲያ አሁን መንገሪያው ጊዜ አይመስልህም?››
‹‹አዎ በቀደም ከአጎቴ ጋር ስንነጋገርበት ነበር…አብረን ሆነን
በቅርብ ልንነግራት አስበናል….››
‹‹በቅርብ መቼ? ››
‹‹የፊታችን አርብ …አንተም ብትገኝ ደስ ይለኛል››
‹‹ካልረበሽኮችሁ በጣም ነው ደስ የሚለኝ››
‹‹በቃ አርብ ስምንት ሰዓት እኔ ቤት እንዳትቀር››
‹‹ኸረ አልቀርም….እንዴት እቀራለው››አልኩ አውነቴን ነበር
እንዲህ አይነት አጎጊ ጉዳይ ተገኝቶ እንዴት እቀራለው..
‹‹ግን ፈርቼያለው..››አለኝ ድንገት ውይይታችን ጨርሰን
ተሰናብቼው ለመሄድ በዝግጅት ላይ እያለው፡፡
‹‹እንዴት..ምኑ ያስፈራህል?››
‹‹ላለፈት ስምንት አመታት እኮ ከሰላሜ ጋር አውርተን
አናውቅም….ከሌላ ሰው ጋር ስታወራ ድምጽን እሰማለው
እንጂ ከእኔ ጋር የሆነ ነገር ብላኝ..የሆነ ነገር መልሼላት
አላውቅም እና አሁን ፊት ለፊት ተቀምጠን ቃላት
እንደምንለዋወጥ ሳስበው…በጣም ፈራው››
‹‹አይዞህ….ግን እሷ ተስማምታለች?››
‹‹እንግዲህ አጎቴ ነው ተስማምታለች ያለኝ…ሁለታችንም
ላለፉት ወራቶች ካንተ ጋር ማውራታችን እና ያለፈ ታሪካችንን
መከለሳችን እርስ በርስ ለመናጋገር እንድንወስን ሳይረዳን
አልቀረም….እመሰግናለው››አለኝ…ከእሱ ምስጋና ማግኘት
ያልጠበቅኩት ነው፡፡ደስ አለኝ፡፡ ለማኝኛውም ተሰናብቼው
ከቤቱ ወጥቼያለው..

.:
#ፍቅርና_በቀል
፡
፡
#ክፍል _አስራ_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)
፡
፡
✍ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
፡
፡
-- -
"አንዳንዴ መውጫ በሌለው ጭለማ ዋሻ ውስጥ ተጥለን
በረሃብ ሰውነታችን
ቢጠወልግ..በውሀ ጥም ጉሮራችን ቢሰነጣጠቅ….ፀጉራችን
ቢረግፍ …አይናችን
ቢደበዝዝ…. ተስፋችን ግን መጨለም የለበትም ..ምክንያቱም
እስትንፋሳችን ልትቋረጥ በመጨራሻዋ ሽራፊ ደቂቃ
የሚታደገን ተአምራዊ መላአክ ከምናመልከው አምላካችን
ሊላክልን ይችል ይሆናል…"
የጊዜን ስሌት ንጻሬን በተመለከተ ትክለኛው ትርጉም ግልጽ
ብሎ የገባኝ በእነዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ነው፡፡ይህቺ አርብ
የምትባለው ቀን አልደርስ ብላኝ እንዴት ቃትቼ እዚህች ሰዓት
ላይ እንደደረስኩ እኔ ነኝ የማውቀው…. ለማንኛውም አሁን
ወደ ኃይሌ ቤት እየሄድኩ ነው፡፡ ደርሼ የአጥሩን በራፍ
መጥሪያ ስጫን እንደበፊቱ የከፈተልኝ ጋሽ ጣሰው ሳይሆን
ሌላ ወጣት ዘበኛ ነው››አልፌ ገባው…. የሳሎኑ በራፋ ክፍት
ነው. ፡፡
ቀድሜ የምደርሰው እኔ እንደምሆን ነበር
የገመትኩት….ምክንያቱም ገና ሰዓቱ ለስምንት እሩብ ጉዳይ
ነበር፡፡ግን የመጨረሻው ሰው ነበርኩ… ሁሉም ቀድመውኝ
ሳሎኑን ሞልተውታል፡፡ እስኪ ስለሳሎኑ ድባብ የተወሰነ ነገር
ልበላችሁ….ልክ ስገባ በግራ በኩል በፊት ያልነበረ ሰፊና
ግዙፍ ጠረጴዛ ይታያል..በዛ ግዙፍ ጠረጴዛ ላይ በግምት
ከሰላሳ የማያንሱ ወጣ ወጥ..ጥብሳ ጥብስ…
አትክልቶች..የተቆራረጡ ዳቦዋች.. እንጀራ..ቆጮ…ምንም
የምግብ ዘር የቀረ አይመስልም…. ተደርድሯል ..ከዛ
አልፋችሁ አይናችሁን ወደ መሀል ስትልኩ ግዙፉ ሶፋ በሰዎች
ተከቧል..ጋሽ ጣሰው..ፕሮፌሰር…ሩት..ኃይሌ እና አንድ
ያልጠበቅኩት ሰው…..ፕሮፌሰሩ ጓደኛዬ ብለው ያስተዋወቁኝ
ሰውዬ..አቶ ዮሴፍ…፡፡
ለሁሉም በየተራ ሰላምታ ሰጥቼ ተቀላቀልኳቸው….እንግዲህ
ያንተን መምጣት ነበር የምንጠብቀው አሁን ከሁሉም በፊት
ምሳችንን እንብላ አለና ከተቀመጠበት ቀድሞ ተነሳ…ኃይሌ፡፡
ዛሬ የተለየ አይነት አለባበስ ነው የለበሰው..እርግጥ ሁሉም
ከወትሮ የተለየ እና የደመቀ አለባበስ ነው የለበሱት….የኃይሌ
ግን እኔን በተለየ ሁኔታ አስደምሞኛል…..ከሱፍ በስተቀር ሌላ
ልብስ ለብሶ ሳየው ዛሬ የመጀመሪያዬ ነው…ነጫ የባህል
ልብስ …በላዩ ላይ ጃኖ ነጠላ ጣል አድርጎበታል…በግራ እጁ
ጭራ ይዞ ይታያል..በእሱ መሪነት ወደ ምግብ ጠረጵዛው
ተንቀሳቀስን ….እንግዲህ ስለምሳው ሂደት
አልነግራችሁም..ምክንያቱም በዚህ ሰዓት ጥጋብ ላይ
ያላችሁ.. ብርቅ ነው እንዴ ታዲያ እንዳትሉኝ…
እየሞረሞራችሁ ያላችሁ ደግሞ ምነው እራባችንን
ታባብስብናለህ ብላችሁ እንድታማርሩኝ ስለምፈልግ
ዘልዬዋለው፡፡
።
9፡30 ላይ ሁሉም መመገቡን አጠናቆ እጆቹን አጸዳድቶ
የመረጠውን መጠጥ ፊት ለፊቱ በማስቀመጥ ለእለቱ ዋና
ፕሮግራም ዝግጁ ሆኗል፡፡
የመድረኩ ዋና መሪ ፕሮፌሰሩ ናቸው..ጀመሩ ‹‹…ሁላችንም
እዚህ ቦታ ለምን እንደተሰበሰብን በመጠኑም ቢሆን
ግንዛቤው አላችሁ ብዬ አስባለው… እኔ፤ ሩቴ፤ ኃይሌና አቶ
ጣሰው በዚህ…ዛሬ በምናወራው ታሪክ ዙሪያ የራሳችን ድርሻ
ያለን ሰዎች ነን…››ወደ እኔ ዞሩና….‹‹አንተ ደግሞ ይሄንን የኛን
ታሪክ ለወራት ስትከታተልና ስታጠና የነበርክ እና ሁላችንም
የምናከብርህ ልጃችን እና ወንድማችን ስለሆንክ እዚህ ቦታ
ላይ መገኘት ይገባሀል ብለን ስላሰብን ነው የጋበዝንህ…
ጓደኛዬ ዬሴፍ ደግሞ የቤተሰቡ የረጅም ጊዜ ወዳጅ
እንደመሆኑ መጠን እንደ ታዛቢም እንደ መካሪም ቢኖር
መልካም ነው ብለን ነው የጋበዝነው..ስለዚህ ወደ ዋናው
ጉዳይ እገባለው፡፡
ዛሬ ሁላችንም ለዘመናት በውስጣችን ደብቀን እና ሸሽገን
ያኖርነውን ሚስጥር በግልጽ እንነጋገራለን…ይሄ ዛሬ አንዳችን
ለአንዳችን የምንነገራው ሚስጥር ምን አልባት በቀጣይ
ህይወታችን ላይ ምን አይነት ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል
በሂደት እናየዋለን…እና መጀመሪያ የመናገሩን ዕድል
የምሰጠው ለኃይሌ ነው›› ብለው መድረኩን ለቀቁለት..
ኃይሌ ከተቀመጠበት ተነሳ…ጉሮሮውን አፀዳዳ
‹‹ምን አልባት ይሄንን ነገር መናገር ያለብኝ ከብዙ ጊዜ በፊት
ነበር..ግን ፈርቼም ይሁን በተለያዩ ሌሎች ምክንያቶች
እስከዛሬ በውስጤ አፍኜ ስቃጠል እና ስለበለብ
ኖሬያለሁ….››አለና ንግግሩን ገታ አድርጎ ወንበሩን ለቆ
ተንቀሳቀሰ…ወደ ሩት ተጠጋ…ስሯ ሲደርስ ተንበረከከ..ግን
አልነካትም…ቅርበቱ ክፍተት ነበረው .. እሷ ፈጣ በመገረም
እየተመለከተችው ነው… እኛም እንደዛው‹‹ሰላሜ ትዳራችንን
ያፈረስኩት ስለጠላውሽ ወይም ካንቺ ጋር መኖር በቅቶኝ
አልነበረም››
‹‹እናስ?››አለችው ፍርጥም ብላ
‹‹ወላጆቻችን ሰርተውት በነበረ ስህተት የእኛ ትዳር መቀጠል
ስለማይችል ነበር››
‹‹ፈሪ ስለሆንክ እንጂ…የእኔ እና አንተን ትዳር ለማፍረስ
የሚችል..ምንም በቂ ምክንያት በዚህ ምድር ላይ ሊኖር
አይችልም..ምክንያቶች ሁሉ ከእኛ ፍቅር በላይ ጥንካሬ
ሊኖራቸው አይችልም››
‹‹የእኔ እመቤት…አልገባሽም…እኔ የጣሰው ልጅ
አይደለውም..፡፡ማለቴ እርግጥ ጣሰው አሁንም የምወደው
አባቴ ነው…ግን በስጋ የወለዱኝ አባትሽ ናቸው… አባትሽ
የእኔም አባት ናቸው….እህቴ የመሆንሽን እውነታ ሳውቅነው
ትዳራችንን ላፈርስ የቻልኩት››….ይሄንን ሲነግራት ከእኔ
በስተቀር እቤት ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ ሀይለኛ
ማዕበል፤ትልቅ ነውጥና ከፍተኛ ድንጋጤ ጠብቀው ነበረ…ሩት
ግን ምንም የሰማች አትመስልም..ምንም አይነት የስሜት
ለውጥ አልታየባትም፡፡
‹‹ያልኩሽን ሰምተሺኛል…….ሰላሜ እኔ ወንድምሽ ነኝ››
‹‹ወንድሜም ሁን አጎቴም..ሲፈልግህ አባቴም ሁን….ምኔም
ብትሆን ግድየለኝም… የእኔ ፍቅር ከዚህ ሁሉ በላይ ነው..ግን
..አንተ ባሌነህ…ልትተወኝ አትችልም››
‹‹አንቺም ሚስጥሩን በወቅቱ ብታውቂ ኖሮ እኔ የወሰንኩትን
ውሳኔ ነበር የምትወስኚው››
‹‹አይ አልወስንም ነበር››
‹‹ተይ ትወስኚ ነበር››
‹‹እኔ አንተ ከማወቅህ ከሶስት አመት በፊት ወንድሜ
እንደነበርክ አውቅ ነበር…
ከመጋባታችን…ከአዲስአበባ ከመጥፋታችን በፊት ጀምሮ
አውቅ ነበር›› አፈረጠችው ‹‹እ..!!!ምን…?››አልጨረሰውም
ኃይሌ… ፊት ለፊቷ እንደተንበረከከ እራሱን መቆጣጠር
አቃተው መሰለኝ ሸርተት ብሎ ወላሉ ላይ ተዘረፈጠ…..ቶሎ
ብዬ በአቅራቢያው ስለነበርኩ እንዳይወድቅ ደገፍኩት
..ፕሮፌሰር ጣልቃ ገብተው መናገር ጀመሩ
‹‹የእውነት ከማጋባታችሁ በፊት ታውቂ ነበር?››
‹‹አዎ አውቅ ነበር፡፡››
‹‹እና ነገሮች ሳይወሳሰቡ ማቆም እኮ ትቺይ ነበር ››
‹‹እኔ ነገሮች ተወሳሰቡ አልተወሳሰቡ ጉዳዬ አይደለም….እኔ
ከኃይልሻ ጋር በአንድ ጎጆ ውስጥ ኖሬ በአንድ አልጋ ላይ ማደር
እስከቻልኩ ድረስ ምድር ጠቅላላ ለምን ገሀነም አትሆንም
ጉዳዬ አይደለም..››….ኃይሌን እንደምንም ከተዘረፈጠበት
ደግፌ አስነሳውትና ሶፋው ላይ ተረጋግቶ እንዲቀመጥ
አደረግኩት…
‹‹ሩቴ ትክክልም አልሰራሽ››አሉ ፕሮፌሰሩ በቅሬታ
‹‹ቆይ ከፍቅሬና ከወንድሜ የቱ ይበልጥብኛል….እኔ ወንድሜ
የሆነውን ኃይሌን ገድዬ ፍቅሬ የሆነውን ኃይሌን አርነት
ማውጣት ነው የምፈልገው››
‹‹እሺ ይሁን ..አሁን ደግሞ የእኔ ተራ ነው…ያው መቼስ ይሄን
አሁን የምንግራችሁን ነገር ለመናገር ለአመታ አስቤያለው
ተጨንቄያለው….ግን አልቻልኩም ነበር..ዛሬ ግን የቁርጡ ቀን
መጥቷል ..እሩቴ ያው እንደምታውቂው እናትሽ አባትሽን
ስታገባ በዕድሜ በጣም ልጅ ነበረች….. ያገባችውም
በቤተሰቦቾ ግዳጅ እንጂ በእሷ ፍቃድ አልነበረም…ግን አንድ
ሚስጥር ልንገራችሁ እናትሽ አባትሽን ከማግባቷ በፊት ጀምሮ
በጣም አፈቅራት ነበር››
‹‹ምን….?አንተ….አጎቴ የእኔን እናት?

👍4😱1
››
‹‹አዎ
በጣም ነበር የማፈቅራት…. ለዚህ ደግሞ የሁለታችንም
ልጅነት ጓደኛ የነበረው እና አሁንም በመሀከላችን
በእንግድነት የሚገኘው ዬሴፍ ምስክር ነው…አባትሽን
ስታገባው በጣም ተበሳጭቼ ነበር….ሰርጉ ላይም
አልተገኘውም ነበር…››
‹‹እሺ!!!››አለች..ገርሟት
በዚህ መሀከል የኃይሌ ሞባይል ተንጫረረችና ሁላችንንም
ከተመሰጥንበት
አናጠበን..ኃይሌም ከደነዘዘበት እንደመባነን አለና
የሚጠራውን ስልክ ሳያነሳው ዘግቶት ከመቀመጫው
ተነሳ…‹‹ይቅርታ አጎቴ ለተወሰነ ደቂቃ ላቆርጥህ ነው..››አለና
በቅርብ ርቀት ካለ ጠረጽዛ ላይ የሚታየውን ላፕቶፕ አነሳና
ወደ እኛ ተመለሶ ከፈተው…አንተርኔቱን ኮኔክት አደረገና
ስካይፒ ከፈተ..ላፕቶፕን ለሁላችን እንዲታይ አስተካከለው…
ወዲያው አንድ ወጠምሻ መሳይ ጠይም ጎልማሳ ሰው
የላፕቶፑን ስክሪን ሞላው
‹‹….ወይኔ ወንድም ጋሼ››አለች ሩት ወደ እስክሪኑ ይበልጥ
እየተጠጋች
‹‹ሀይ ሲስተር…እንዴት ነሽ..?አጎቴ ኃይልሻ..ጋሽ ጣሰው
ሁላችሁንም ሰላም እያልኩ ነው››
ሁላችንም እጃችንን እያወዛወዝን ለሰላምታው አጻፋውን
መለስን..
ሩት ቀጠለች‹‹ወንድሜ በጣም ነው የናፈቅከኝ…በጣም››
‹‹አይዞሽ ልመጣልሽ ነው››
‹‹የእውነት?››ደስታዋን ልትቆጣጠረው አልቻለችም
‹‹ከአስር ቀን ብኃላ እንመጣለን››
‹‹እንመጣልን..ወንድም ጋሼ ትሁቴስ?››
‹‹አብረን እንመጣለን.››አለና… ፊትን ወደ ጎኑ መለሰ‹‹..ነይ
ዘመዶችሽን አናግሪ..››
…አንድ የአረብ ልጅ የምትመስል ድንቡሽቡሽ ታዳጊ ልጅ
ከደረጄ ፊት እስክሪኑን ሞላችው..
‹‹ልጄ የእኔ ልጅ …እንዴት አድገሻል…ልጄ…›› የምትሆነውና
ምትናገረው ጠፋት…ከመቀመጫዋ ተንሸራታ ወለሉ ላይ
ተንበረከከችና ወደ እስክሪኑ ይበልጥ ተጠጋች….መዳፎን ወደ
እስክሪኑ ልካ የልጇን ፊት ለመዳበስ ሞከረች..እንባዋ
ያለፍቃዷ ይንጠባጠባል
‹‹አክስቴ ለምን ታለቅሺያለሽ…?››
‹‹እኔ ይወድሻል…አጎቴንም ይወዳል….ሁሉም ይወዳል
››አለች በተኮለታተፈ አማርኛ
‹‹እኔ እናትሽም በጣም እወድሻለው››
‹‹አንቺ አክስቴ….አኔ እመጣለው..አንቺ ጋር››
‹‹ነይልኝ ልጄ..ነይልኝ››
‹‹አጓት..››አለች ወደ ኃይሌ እይታዋን አስተካክላ…
‹‹ሀይ ትሁቴ››
‹‹እኔ ስመጣ..ሀገር ያስጎበኛል አይደል…?ሁሉ ነገር ያሳያል
አይደል?››
‹‹አንቺ ብቻ ነይ እንጂ ሁሉንም አሳይሻለው…ጠቅላላ
ኢትዬጵያን አስጎበኝሻለው የእኔ ጣፋጭ ››አላት
‹‹እሺ ባይ››አለች እጆቾን ለስንብት እያውለበለበች …..ሩት
ልትሰናበታት አቅሙ አልነበራትም…እየተንሰቀሰቀች
ከተንበረከከችበት ተነስታ ወደመታጠቢያ ክፍል
ገባች…….ተረጋግታ ለመመለስ ከአስር ደቂቃ በላይ ፈጅቶባት
ነበር…..ሌሎቻችንም እሷ እስክትመጣ እና እስክትቀላቀለን
በዝምታ ስንጠብቃት ነበር…
ተረጋግታ እና ፊቷን ተጣጥባ በመመለስ ቦታዋን ይዛ
ከተቀመጠች ቡኃላ‹‹..አየህ አይደል ኃይልሽ…ይሄ ሚስጥር
ብለህ ለምትለፈልፍለት የማይረባ ታሪክ ብለህ ይህቺን
የመሰለች ልጄን እንዳሳጣሀኝ..ለመሆኑ የገዛ ልጅህ አጎቴ
ስትልህ ምን ይሰማሀል….?እኔ በበኩሌ አክስቴ ስትለኝ የሆነ
ጦር በጉሮሮዬ የሰነቀሩብኝ አይነት ስሜት ነው የሚሰማኝ፡፡››
ሃይሌ በሀዘን ግንባሩን ወደ ምድር አቀርቅሮ የምትለውን
ከመስማት በስተቀር ምንም መልስ ሊመልስላት አልደፈረም..
‹‹እንግዲህ ወደ ውይይታችን እንመለስና ካቆምኩበት
ልቀጥል..››አሉ ፕሮፌሰሩ..በቤቱ ያረበበው የመደበት ስሜት
ወደሌላ አቅጣጫ ለመመለስ.
‹‹ቀጥል….አጎቴ ቀጥል››አለች ሩት
ቀጠሉ‹‹….ቅድም እንዳልኳቹሁ እናትሽን አፈቅራት ነበር….
ያው ከዛ ነገሮች በዛ አይነት ለረጅም አመት ከቆዩ ብኃላ እኔ
ለትምህርት አሜሪካ በሄድኩበት ጊዜ መታመሞን
ሰማው..በዚህም በዛም ብዬ አባትሽን አሳምኜ ወሰድኳት…
በወቅቱ ያንን ያደረግኩት ምንም አስቤ አልነበረም ..ያው
ከውስጤ አፈቅራት ስለነበረ እንድትሰቃይብኝ ስለማልፈልግ
ነበር…ግን እኔ ጋር በቆየችበት ረጅም ጊዜ ወስጥ አንድ ላይ
አንድ ቤት ስንኖር በተፈጠረ መቀራረብ በስተመጨረሻም
ቢሆን ፍቅር ጀመርን››
‹‹ፍቀር ጀመርን ስትል?››
‹‹ያው ፍቅር ጀመርና ..የልጅነት ፍቅሬን አባትሽ እንደቀማኝ
ነበር የማስበው…ቂም ይዥበት ነበር..ከዛ አጋጣሚውን ሳገኝ
መልሼ ነጠቅኩት…ተበቀልኩት››
‹‹እናቴ ድሮም ማንም በቀላሉ ሚወስዳት እና ሚጥላት ደካማ
መሆኗን አውቃለው››
‹‹በፍጽም እናትሽ ደካማ አይደለችም ..እናትሽ ብልህና ድንቅ
ሴት ነች..እና በግንኙነታችን አንቺን ፀነሰች..ወደ ሀገር ቤት
ስትመለስ የሁለት ወር እርጉዝ ነበረች…አንቺን በማህፀኖ ይዛ
ነበር››
‹‹‹እኔን?እንዴት…..?አንተ አባቴ ነህ?››ጠየቀች
‹‹አዎ ልጄ…እኔ አባትሽ ነኝ››…ከተቀመጠችበት ተነስታ
ቆመች….ከት ብላ ሳቀች›‹‹ኪ..ኪ..ኪ……የሚገርም ቤተሰብ
ነው ያለን….!!!የሚገርም!!!፡፡ ግን ለውጥ
የለውም…..››መልሳ ተቀመጠች
‹‹እንዴት ለውጥ የለውም››
‹‹አንተ እስከ ዛሬ አጎቴ ነበርክ...አጎቴም ሆነህ በጣም
እንደምወድህ ታውቃለህ..ዛሬ አባቴ እንደሆንክ ስለተረዳው
ይበልጥ ላፈቅርህ አልችልም…..››
‹‹ይሁን ልጄ››
‹‹ግን እናቴን ይበልጥ ጠላዋት ..እንዴት እንዲህ…?.››
‹‹ተይ አንቺ..እናትሽንማ እንዲህ ልትወቅሺያት አትችይም››
እስከ አሁን ምንም
ያልተናገሩትና በዝምታ ሲታዘቡ የነበሩት አቶ ዬሴፍ ናቸው
ጣልቃ ገብተው በንዴት የተናገሩት››
‹‹ለምን አልችልም?››መለሰች የፈጠጠ ዓይኖቾን
አተኩራባቸው
‹‹እናትሽ እንደምትያት አይነት ሰው አይደለችማ….እናትሽ
ላንቺና ለወንድምሽ ስትል በህይወቷ ምን መስዋትነት
እንደከፈለች ማንም አያውቅም..ማንም››
‹‹አርሶስ ያውቃሉ?››
‹‹እንዴ ሩቴ ዬሴፍ እኮ ለእናትሽ ከህጻንነቷ ጀምሮ የልብ
ጓዳኛዋ ነው……ሚስጥረኛዋ››ድጋፍ ሰጡ ፕሮፌሰሩ
‹‹አይ ጓደኛዋማ አይደለሁም… እኔ ለእናሽ የዕድሜ ዘመን
ፍቅረኛዋ ነኝ…..እናትሽ በዕድሜ ዘመኗ ሁሉ ከእኔ እና ከልጆቾ
በስተቀር ሌላ ሰው አፍቅራ አታውቅም›› በዚህ ጊዜ እቤት
ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በድን ነበር የሆነው ..የሆነ መብረቅ
ነው ፊት ለፊታችን የፈነዳው….. ከሁሉም በላይ የፕሮፌሰሩን
መደንዘዝ የሚስተካከል የለም…
‹‹አልገባኝም ..ምን እያልክ ነው..ዬሴፍ?››
አቶ ዬሴፍ ጎናቸው የነበረ ቀድመን ማናችንም ያላስተዋልነውን
ተለቅ ያለ ቦርሳ ወደራሳቸው በመሳብ ከፈቱና መአት በቀላሉ
ለመቁጠር የሚያስቸግሩ አሮጌ ና የተሻሹ ፓስታዎች
አወጡ…..
እነዚህ ምታያቸው ፖስታዎች የእኔና የሩት እናት በዕድሜ ልክ
የተለዋወጥናቸው የፍቅር ደብዳቤዎች ናቸው…በቁጥር 153
ናቸው….105ቱን እኔ ለእሷ የጻፍኮቸው ደብዳቤዎች ሲሆኑ
48 እሷ ለእኔ የጻፈቻቸው ናቸው፡፡ ልትሞት አንድ ወር ሲቀራት
ነው ሰብስባ የላከችልኝ…እዚህ ላይ የፍቅራችን ጥልቀት ምን
ያህል እንደሆነ…ያሳለፍናቸውን የፍቅር
ጊዜያቶች..ናፍቆታችንን ህመሞቻችንን..አንቺን
የተመለከተ..ሙሉ ታሪካችን ያለበት ደብዳቤዎች ናቸው…፡፡
ይቅርታ ዛሬ ሁላችንም አንዳችን ካንዳችን፣ብሎም ከራሳችን
የደበቅነውን ሚስጥር የምናፈርጥበት ቀን ነው..አብረሀም
ይሄ ታሪክ ከሁሉም ሰው በላይ አንተን ይጎዳሀል ብዬ
አስባለው….ለዚህም ይቅርታ እጠይቃለው..የሩት እናትንም
ምን ያህል ታፈቅራት እንደነበረ አውቃለው..እውነቱን ልንገርህ
እሷ ግን አፍቅራህ አታውቅም፡፡
‹‹ምን እየቀባጠርክ ነው››
‹‹እየቀባጠርኩ አይደለም…››ወንድምህ የቀማው ያንተን
ሳይሆን የእኔን ፍቅር ነበር…እኛ በዛን ወቅት ብዙ ብዙ ነገር
ቃል ተግባብተን ነበር…ብዙ ብዙ የፍቅር ቃል ኪዳን
ተለዋውጠን ነበር..በየአድባራቱ ሄደን በምናመልከው አምላክ

አልተውህም ተባብለን ተማምለን
ነበር..ይሄንንም ማረጋገጥ የፈለገ እነዚህን ደብዳቤዎች
አንብቦ መረዳት ይችላል፡፡ግን ያ ወንድምህ እነደዛ
ሲያደርግ..ሁለት ምርጫ ነበር የመጣልኝ..ወይ እራሴን
ማጥፋት.. ወይ ደግሞ ብን ብዬ ከሀገር
መጥፋት…..ሁለተኛውን አደረግኩ፡፡
በስደት አለም እሷን የረሳው መስዬ በየቀኑ እያለምኳትና
እየናፈቅኳት ለአመታት ኖርኩ…ከዛ ዕድሜ ላንተ ይሁንና ወደ
አለውበት አሜሪካ አምጥተህ አገናኘሀን….ትዝ ይልሀል አንተ
በወቅቱ እየሰራህ የነበረው እና የምትማረው እኔ በማርፍበት
ሰአት ነበር…እና የተነጠቅነውን ፍቅር በነጻነት እንቋደስ ነበር
..ህይወት ለዘመናት የበደለችኝን በጥቂት ጊዜ ውስጥ
ለማካካስ የተቻለንን ያህል ጣርን…ግን ሳናስበው ችግር
ተከሰተ..ፀነሰችብኝ…ግራ ገባን፡፡
ልናሰወርድም ሞክረን ነበር… ግን ለህይወቷ አደገኛነው ሲሉን
ተውነው…ከዛ በቃ ሁሉንም ነገር ትታ ከእኔ ጋር
እንድትኖር..እንድንጋባ ለመንኳት››
አቶ ዩሴፍ ያወራሉ እቤቱ ኮሽታ አልባ ሆኗል…ሁሉም በያሉበት
ሀውልት መስለው እና አፋቸውን ከፍተው ነው በድንዛዜ
እያዳመጡ ያሉት
‹‹…እናትሽ አልተስማማችም…ለእኔ ስትል መላ አለምን
ልትተው እንደምትችል.. ግን ደግሞ ልጇ ደረጄን
እሰከመጨረሻው ልትተወው እንደማትችል አስረድታ እንቢ
አለችኝ…..እኔ የማደርገው ጠፍቶኝ ነበር..እሷ ግን አንድ ሀሳብ
አለኝ አለችና ከሳምንት ቡኃላ ያደረገችውን ነገር ነገረችኝ…››
‹‹ፕሮፌሰር ከሩት እናት ጋር ግንኙነት የፈጸማችሁት ለሁለት
ቀን ብቻ ነው …አይደል?››በተሰበረ ልብ ግንባራቸውን
በመነቅነቅ ትክክል እንደሆነ ፕሮፌሰሩ አረጋገጡለት
‹‹ከዛ ከሁለት ሳምንት ቡኃላ አረገዝኩ አለች..?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ››
‹‹ከዛ በሁለተኛው ወር ወደ ሀገር ቤት ላካት…እኛ ማርገዞን
ያወቅነው በአስራአምስተኛው ቀን ለሌላ ህክምና ወደ
ሆስፒታል ይዤት በሄድኩበት ጊዜ ነበር….ካንተ እንዳረገዘች
ለማስለመሰል ለምን እንደፈለገች አልገባኝም..ምን አልባት
ነገሮች ወደ ሀገር ቤት ስትመለስ ወንድምህ አውቆ ችግር
ከተፈጠረ ያው የገዛ ወንድምህ ነው ብላ አፍ ለማስያዝም
አስባ ይመስለኛል..››
‹‹እና አሁን የዚህ ታሪክ ማጠቃለያ ምንድነው?››ሩት ነች
በጉጉት እና በስጋት ተቀስፋ የጠየቀችው..
‹‹የዚህ ታሪክ ዋናው አስኳልማ አንቺ የእኔ ልጅ መሆንሽ
ነው…አባትሽ እኔ ነኝ…›› ይሄ አረፍተ ነገር ከሰውዬው አንደበት
እንደ ወጣ ኃይሌ ከመቀመጫው ሲነሳ ሩትም ከዛኛው ጥግ
ተነስታ ተመሳሳዩን ስታደርግ….አንደኛቸው ወደ አንደኛቸው
ሲሮጡ …….
አዎ አንደኛው በሌለኛው እቅፍ ገቡ…ከስር እግሮቾን አንድ
ላይ አጣምሮ ያዘና ወደ ላይ አንጠላጠላት… በፍቅር አንገቱ
ስር ተሸጎጠች..ፀጉሯን አንድ ላይ ይዞት የነበረ ጨርቅ
ተንሸራቶ ተፈታና ጸጉሯ ብትንትን ብሎ ትከሻው ላይ ተዘረገፈ››
‹‹የእኔ ፍቅር አየህ ወንድሜ አይደለህም››አለቻ በሹክሹክታ
‹‹ስለዚህ መልሰሽ ታገቢኛለሽ?››
‹‹መጀመሪያውስ አንተነህ እንጂ እኔ መች ፈታውህ››አለችው
እንባዋ ኩልል እያለ….
💫ተፈፀመ💫
ስለነበረን ቆይታ እጅግ አመሰግናለሁ🙏

#ሁቱትሲ
፡
፡
#በኢማኪዩሌ_ኢሊባጊዛ_እና_ስቲቭ #ኤርዊን
፡
፡#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች፡
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
#ቀዳሜ_ቃል
ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ከስቲቭ ኤርዊን ጋር በመተባበር የጻፈችው #ሁቱትሲ የተሰኘው መጽሐፍ ምናልባት ስለ ሩዋንዳ ከተጻፉት መጻሕፍትም ሆነ ከታዩት ፊልሞች በላይ የፍጅቱን አሰቃቂነትና ዘግናኝነት ገላጭ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉ ከሰሚ ሰሚ የወረደ ታሪክ ሳይሆን እጅግ ከሚዋደዱ ከስድስት ቤተሰብ አባላት ከግድያው የተረፈችው አንዲት ቱትሲ ወጣት ከአንድ ቁምሣጥን በማይበልጥ መጸዳጃ ቤት ከሰባት ቱትሲ ጓደኞቿ ጋር ከአሁን አሁን ተገደልኩ እያለች እየተጨነቀች የሃይማኖት ጽናቷ እንዴት ለሦስት ወር በሕያውነት እንዳኖራትና በኋላም እንዴት ነጻ ወጥታ ወልዳ ለመሳም የበቃች መሆኗን የሚተርክ ታሪክ ነው፡፡ የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተዋንያንን ፍርድ ቤት እንዳቀርብ በተባበሩት መንግስታት በከፍተኛ የሕግ አማካሪነት ተቀጥሬ በሠራሁበት ጊዜ ከሰማኋቸው በላይ ልብን ሰቅዞ የሚይዝና አእምሮን የሚያናውጥ ታሪክ ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ መጽሐፍ አጋጥሞኛል፡፡
ስሜታዊነት አይነካኝም፣ መንፈሴ በሚያየውና በሚሰማው የማይረበሽ ጠንካራ ሰው ነኝ ባይ ይህንን መጽሐፍ በሚያነብበት ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ዓይኖቹ በእንባ ችፍ ችፍ ማለታቸው አይቀርም፡፡
የኢማኪዩሌ ታሪክ ምንጩ ወይንም የስቃይዋ ምክንያት የተወሳሰበ አይደለም፡፡ መንስኤው ርህራሄ የሚወልደውን የሰብአዊ ስሜትን ደምስሶ ከጥላቻ በላይ ጥላቻ ወልዶ ሰውን ከአውሬነት በታች የሚያውለው የዘር ጥላቻ ነው፡፡
የዘር ጠላቻ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ለሌላው ሰብዓዊ ፍጡር ሊኖረው የሚገባውን ሐዘኔታና ርህራሄ ከሰው ልብ ፈልቅቆ አውጥቶ ከአውሬ በባሰ ጭካኔ ይተካዋል፡፡ በሩዋንዳው የዘር ፍጅት የተፈጸመውን አራዊት ከሚያደርጉት ጋር ማወዳደር የአራዊትን ስም ማጥፋት ይሆናል፡፡ የትኛው አውሬ ነው ሕጻናትን ከታትፎ እንደ ጌሾ በሙቀጫ የሚወቅጠው? የትኛው አውሬ ነው በኢማኪዩሌ ወንድም ላይ እንደተፈጸመው የሰውን አካላት ቆራርጦ ክምር ላይ የሚጥል? የትኛው አውሬ ነው የሰውን ጭንቅላት በገጀራ ለሁለት ሰንጥቆ ሰውዬውን በዝግታ እንዲሞት የሚያደርገው? የትኛው አውሬ ነው የአምስት ልጆችን እናት በልጆቿና በባሏ ፊት ደፍሮ ፊቷ አምስቱንም ልጆቿንና ባሏን አንድ በአንድ የሚከትፈው? ከአክራሪ ሁቱዎች በስተቀር የትኛውም አውሬ አያደርገውም፡፡
የሩዋንዳ የዘር ፍጅት የሰው ልጅ ጭካኔ ልክ የታየበት ነው፡፡ ተመሳሳይ ፍጅትና ጭካኔ የተፈጸመባቸው የናዚዎችና የአርመኖች እልቂቶች እንደሩዋንዳው መንስኤአቸው የዘር ጥላቻ ነበር፡፡
ኢማኪዩሌ በመጽሐፏ የጠቀሰችው የዘር ፍጅቱ ቀስቃሽና ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ቲዩኔስት ባጎስራ ፍርድ ቤት አቅርቤው ዳኞቹ ክሱን አንብበውለት ጥፋተኛ ነህ
አይደለህም ብለው ሲጠይቁት ፈገግ እያለ ‹‹ጥፋተኛ አይደለሁም›› ሲል ፈገግታው እንደ ጦር ይዋጋ ነበር፡፡
መጽሐፉ ከእንግሊዝኛ የተተረጎመ ሲሆን፤ ምናልባትም የአማርኛው ትርጉም ድርጊቶቹን ከእንግሊዝኛው በተሻለ ይገልጻቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ ተርጓሚው የሥነጽሑፍ ምሁር እንደመሆናቸው መጠን አገላለጹ ከኢማኪዩሌ በልጦ ቢገኝ አይገርምም፡፡ የቃላቱ ገላጭነት፣ የአረፍተ ነገሮቹ አሰካክ፣ የቋንቋው አወራረድና በጠቅላላው የአማርኛው ውበት ከታሪኩ መሳጭነት ጋር ሆኖ መጽሐፉን ማንበብ ከተጀመረ መልሶ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡፡
ይህ መጽሐፍ የብሔር ጥላቻ የሚፈጥሩ ፖሊሲዎችን ለሚቀርጹና በብሔረሰብ ስም ህዝብን ከፋፍለው ጥላቻ ለሚያስፋፉ ሰዎችም ሆኑ መዋቅርት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ መጽሐፉ ጥላቻ የሚያስከትለውን ሰቆቃ በግልጽ ስለሚያሳይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያነበው በአጽንኦት ስማጠን በዓይኔ በብረቱ ካየሁት ተነሥቼ ነው፡፡
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም
በተባበሩት መንግስታት የቀድሞ የሩዋንዳ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሕግ አማካሪ
#መግቢያ
ኢማኪዩሌ እባላለሁ
ገዳዮቹ ስሜን ሲጠሩ ሰማኋቸው፡፡
እኔ በግንቡ በአንደኛው በኩል ስሆን እነሱ ደግሞ በሌላኛው አቅጣጫ ናቸው፤ አንድ ጋት የማይሞላ ውፍረት ያለው ጭቃና ዕንጨት ብቻ ይለያየናል፡፡ ንግግራቸው ጭካኔ የሚንጸባረቅበትና ቆርጠው መነሳታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
‹‹እዚህ ነች… እዚህ የሆነ ስፍራ እንዳለች እናውቃለን፡፡ …. ፈልጓት-ፈልጓት ኢማኪዩሌን፡፡››
አካባቢው በሁካታ ተሞላ፡፡ ብዙ ገዳዮች መጥተዋል፡፡ በአእምሮዬ ይታዩኛል - ሁልጊዜ በፍቅርና በደግነት ሰላምታ ይሰጡኝ የነበሩ የቀድሞ ወዳጆቼና ጎረቤቶቼ በቤቱ ውስጥ ጦርና ገጀራ ይዘው ስሜን እየጠሩ ይዘዋወራሉ፡፡
‹‹399 በረሮዎችን ገድያለሁ›› ይላል አንደኛው ገዳይ፡፡ ‹‹ኢማኪዩሌ 400 ታደርግልኛለች፡፡ ይህን ያህል ከገደልኩ ምን እፈልጋለሁ!››
በትንሿ ምስጢራዊ መታጠቢያ ቤታችን ጥጋት አንድስ እንኳን የሰውነቴን ክፍል ሳላላውስ ተሸሽጌያለሁ፡፡ እንደኔው ሕይወታቸውን ለማትረፍ እንደተደበቁት ሌሎች ሰባት ሴቶች ሁሉ ገዳዮቹ ስተነፍስ እንዳይሰሙኝ ትንፋሼን ውጫለሁ፡፡ ድምጻቸው የሠራ አከላቴን ገማመሰው፡፡ በከሰል ፍም ላይ እንደተኛሁ፣ እሳትም ላይ እንደተጣልኩ ተሰማኝ፡፡ መላ ሰውነቴ የሕመም ውርጅብኝ ወረደበት፡፡ ሺህ የማይታዩ መርፌዎች ተቸከቸኩብኝ፡፡ ፍርሃት እንደዚህ የሚያርበደብድ ስጋዊ ሥቃይ ያስከትላል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡
ለመዋጥ ሞከርኩ፤ ጉሮሮዬ ግን ተዘግቷል፡፡ ምራቅ አልነበረኝም፤ አፌም እንደ ኩበት ደርቋል፡፡ ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው፤ ራሴንም ለመደበቅ ሞከርኩ፤ ንግግራቸው ግን እየጎላ መጣ፡፡ ምንም ዓይነት ምኅረት እንደማያደርጉልኝ አውቃለሁ፤ በአእምሮዬም አንድ ሐሳብ ያስተጋባ ጀመር - ከያዙኝ ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ
ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ ይገድሉኛል…
ገዳዮቹ በራፉ ላይ አሉ፤ በማንኛዋም አፍታ እንደሚያገኙኝ አውቃለሁ፡፡ ገጀራው ቆዳዬን አልፎ ሲገባና አጥንቴ ድረስ ሲቆራርጠኝ የሚሰማኝ ስሜት ምን እንደሚመስል አሰብኩት፡፡ ወንድሞቼና ወላጆቼም ትዝ አሉኝ፤ ሞተው ወይንም በሕይወት እየኖሩ እንደሆነ፣ በገነት ከአፍታ በኋላ እንገናኝም እንደሆነ አለምኩ፡፡
እጆቼን እርስ በርሳቸው አጣመርኳቸው፤ የአባቴን መቁጠሪያም ጥብቅ አድርጌ ያዝኩ፤ በለሆሳስም መጸለይ ጀመርኩ - እባክህ እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ እርዳኝ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ እንድሞት አታድርገኝ፣ እንደዚህ አይሁን፡፡ እነዚህ ገዳዮች እንዲያገኙኝ አታድርግ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስህ ከጠየቅን እንደሚሰጠን ትነግረናለህ… እንግዲህ ጌታዬ እየጠየኩህ ነው፡፡ ወይ በለኝ፡፡ እባክህን እነዚህን ገዳዮች ወዲያ እንዲሄዱ አድርጋቸው፡፡ ኧረ በዚህ መታጠቢያ ቤት እንድሞት አታድርገኝ፡፡ እባክህ፣ እግዚአብሔር፣ እባክህ፣ እባክህ፣ እባክህ አድነኝ፡፡
ገዳዮቹ ከቤቱ ወጥተው ሄዱ፡፡ እኛም እንደገና መተንፈስ ጀመርን፡፡ ሄደዋል፤ ሆኖም ግን በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ብዙ ጊዜ ይመላለሳሉ፡፡ ሕይወቴን እግዚአብሔር እንዳተረፋት አምናለሁ፤ ሆኖም ቁምሣጥን በምታክል መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ከሰባት ሌሎች ሰዎች ጋር በፍርሃት እየተርበደበድኩ ባሳለፍኳቸው 91 ቀናት መትረፍ ከመዳን በጣም የተለየ አንደሆነ እማራለሁ… ይህ ትምህርትም ለዘለቄታው ለውጦኛል፡፡ ይህ ትምህርት በጅምላ ጭፍጨፋ ውስጥ የሚጠሉና

👍3❤2
የሚያሳድዱኝን እንዴት መውደድ እንዳለብኝ - ቤተሰቤን ያረዱትንም ሁሉ እንዴት እንደምምር ዕውቀት የቀሰምኩበት ነው፡፡
ስሜ ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ነው፡፡ ይህ በታሪክ ብዙ ሕዝብ ካለቀባቸው ጭፍጨፋዎች በአንዱ እግዚአብሔር እንዴት እንደተገለጠልኝ የሚያሳይ ታሪክ ነው።
=======
ይሄን ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ዘወትር ከሰኞ አስከ ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በ #አትሮኖስ ቻናል ብቻ ያገኙታል እንድትከታተሉ ስጋብዛቹ በደስታ ነው ከናንተ ከውድ የቻናሉ አባላቶች የምጠብቀው #MUTE ያደረገችሁን #UNMUTE እንድታደርጉንና ዘወትር ማንበብን ነው ያበረታናል እና Like 👍 እንድታደርጉልንም ነው።
ማታ #አንድሰአት እንገናኝ
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።

#በኢማኪዩሌ_ኢሊባጊዛ_እና_ስቲቭ_ኤርዊን
፡
፡
#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
#ክፍል_አንድ
፡
፡
#ክፉ_ቀን_ዳር_ዳር_ሲል
#ምዕራፍ_አንድ
የዘላለማዊ ፀደይ ምድር
የተወለድኩት በገነት ነው፡፡ስለ ትውልድ ሀገሬ በልጅነት ዘመኔ የሚሰማኝ ይህ ነበር፡፡ሩዋንዳ በመካከለኛው አፍሪካ እንደጌጥ ጣል የተደረገች ትንሽ ሀገር ነች፡፡ በጣም ማራኪ ውበት ስላላት፣ በለምለም ሸንተረሮቿ፣ ጭጋግ በሸፈናቸው ተራሮቿ፣ በአረንጓዴ ሸለቆዎቿና በአንጸባራቂ ሐይቆቿ ተማርኮ ለምስጋና ወደ አምላክ አለማንጋጠጥ የማይታሰብ ነው፡፡ ከተራሮቿ ቁልቁል የተለያየ ዝርያ ወዳላቸው የጽድ ጫካዎቿ የሚወርደው ነፋሻ አየር በልዩ ልዩ አበቦች መዐዛ የተሞላ ነው፡፡ የአየሩም ሁኔታ ዓመቱን ሙሉ በጣም ተስማሚ በመሆኑ በ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ አካባቢ ወደ ስፍራው የመጡት የጀርመን ሰፋሪዎች ሀገሪቱን ‹‹የዘላለማዊ ፀደይ ምድር›› ብለው ሰየሟት፡፡
ውድ ሀገሬን በደም ጎርፍ እንድትታጠብ ያደረጓት ለጅምላ ጭፍጨፋ መነሻ የሆኑት ርኩሳን ሃይሎች በልጅነቴ ተሰውረውብኝ ነበር፡፡ በልጅነቴ የማውቀው ነገር የከበበኝን አማላይ መልከዓምድር፣ የጎረቤቶቼን ደግነት፣ የወላጆቼንና የወንድሞቼን ጥልቅ ፍቅር ነበር፡፡ በቤታችን ዘረኝነትና ምክንያት የለሽ ጥላቻ በፍጹም አይታወቁም፡፡ ሰዎች የተለያየ ጎሳና ዘር እንዳላቸው እንኳ ግንዛቤው አልነበረኝም፤ ቱትሲና ሁቱ የሚሉትን ቃላትም ቢሆን ትምህርት ቤት እስከገባሁበት ጊዜ ድረስ አልሰማኋቸውም፡፡
በሰፈሬ ትንንሽ ልጆች ከቤት ወደ ትምህርት ቤት ብቻቸውን ጭር ባለው አሥራ ሦስት ኪሎሜትር መንገድ ሲመላለሱ ወላጆቻቸው ልጄ ይጠለፍብኛል ወይንም በማናቸውም መንገድ ይጎዳብኛል ብለው አይጨነቁም፡፡ ልጅ ሆኜ በጣም የምፈራው ነገር በጨለማ ብቻዬን መሆንን ሲሆን፤ ከዚያ በስተቀር ግን ሰዎች የሚከባበሩበት፣ የሚተሳሰቡበትና ደስተኛ ይመስለኝ በነበረ መንደር ውስጥ ከደስተኛ ቤተሰብ ጋር የምኖር በጣም ፍልቅልቅ ልጅ ነበርኩ፡፡
የተወለድኩት በምዕራብ ሩዋንዳዋ የኪቡዬ ክፍለ-ሀገር፣ በማታባ መንደር ነው፡፡ ቤታችን ከኪቩ ሐይቅ ትይዩ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ያለ ሲሆን፤ ሐይቁም ከፊታችን እስከ ዓለም ጠርዝ የተዘረጋ ይመስላል፡፡ ጠዋት ሰማዩ ከጠራ በሐይቁ በሌላኛው ጠርዝ በጎረቤት ሀገር ዛየር፣ በአሁኑ አጠራሩ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ያሉትን ተራሮች አያለሁ፡፡ ከቤታችን ወደ ሐይቁ የሚወስደውን አስቸጋሪ ቁልቁለት መውረድ ከአስደሳች የልጅነት ትዝታዎቼ አንዱ ነው፡፡ የማለዳው ጤዛ በንጋቷ ጸሐይ ተኖ የሚያልቅበት ጊዜ ሲቃረብ ከአባቴና ከወንድሞቼ ጋር ወደ ዋና እወርዳለሁ፡፡ ውሃው ሞቃት፣ የአየሩ ቅዝቃዜ ውርር የሚያደርግና ከሐይቁ ዳርቻ ያለው የቤታችን እይታ ዘወትር አማላይ ነበር፡፡
አቀበቱና በእግራችን የምንረግጠው አሳሳች ልል አፈር ወደ ቤት የምናደርገውን የመልስ ጉዞ አስፈሪም አስደሳችም ያደርጉታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ስለሚያንሸራትተኝ ገደል ገብቼ ሐይቁ ውስጥ እንዳልወድቅ እፈራለሁ፡፡ አባቴም ሁልጊዜ ስፈራ ስለሚያውቅ እቤት እስክንደርስ ድረስ በእጁ ይደግፈኛል፡፡ ትልቅና ጠንካራም በመሆኑ በእነዚያ ትላልቅ እጆቹ በመያዜ ደህንነት ይሰማኛል፤ እንደተወደድኩም ይገባኛል፡፡ እንደዚያ በፍቅር ጢል መደረግ ደስ ያሰኘኛል፡፡ ለዚህም ምክንያት የሆነው በተለይ አባቴ ምንም እንኳን እንደሚወደን ብናውቅም በዘልማዳዊው መንገድ የሚያምን፣ ስሜቱን ብዙውን ጊዜ አውጥቶ የማያሳይና ወንድሞቼንም ሆነ እኔን እንደሚወደን የማይነግረን በመሆኑ ነው፡፡
ከዋና ስንመለስ ቆንጆዋ እናቴ በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ከመሄዳችን በፊት የምትመግበንን ትኩስ የሩዝና የፎሶሊያ ቁርስ እየሠራች በኩሽና ስትባትል እናገኛታለን፡፡ ብርታቷ እኔን ከማስደነቅ ቦዝኖ አያውቅም - እማማ ሁልጊዜ ከቤተሰባችን አባላት ሁሉ ከእንቅልፍ ለመነሳት የመጀመሪያዋና ወደ መኝታ ለመሄድ የመጨረሻዋ ነበረች፤ ቤቱን እንደሚጠበቀው ለማሠጋደድ፣ ልብሶቻችንን ለማስተካከል፣ መጻህፍታችንንና በትምህርት ቤት የሚጠበቁብንን ጉዳዮች ለማዘገጃጀትና የአባቴን የሥራ ወረቀቶች ለማደራጀት ከሁላችንም በፊት ቀድማ እየተነሣች ትለፋለች፡፡ ልብሶቻችንን ሁሉ እሷው በልካችን ትሰፋለች፣ ጸጉራችንን ትቆርጣለች፤ ቤቱንም በእጅ ሥራዎች ጌጦች ታሸበርቀዋለች፡፡ ለቁርሳችን የምትሠራው ፎሶሊያ የሚለማው እኛ ጠዋት ከመኝታችን ሳንነሳ እማማ በምትንከባከበው በጓሮ አትክልት ማሳችን ነው፡፡ እህሉን ቃኝታ ለቀን ሠራተኞቹ የእርሻ መሣሪያዎች ታከፋፍልና ላሞቻችንና ሌሎቹ እንስሶቻችን እንዲቀለቡና እንዲታጠቡ ታደርጋለች፡፡ እነዚህን የማለዳ ሥራዎቿን ከጨራረሰች በኋላ እኛን ወደ ትምህርት ቤት ትሸኝና በእግሯ ቁልቁል መንገዱን ይዛ የሙሉ ጊዜ የማስተማር ሥራዋን ለመጀመር በአቅራቢያችን ወዳለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትሄዳለች፡፡
ወላጆቼ መምህራን ነበሩ፡፡ ድህነትንና ርሃብን ብቸኛው መመከቻም ትምህርት እንደሆነ በጽኑ ያምናሉ፡፡ በቆዳ ስፋቷ ከሞላ ጎደል ጂቡቲን የምታክለው ሩዋንዳ ከአፍሪካ ትናንሽ ሀገራት አንዷ ብትሆንም በአህጉሩ በከፍተኛ የሕዝብ ጥግግት ተጠቃሽና ከዓለምም ደሃ ሀገራት አንዷ ነች፡፡ እናቴና አባቴ ከየቤተሰቦቻቸው የመጀመሪያዎቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ሰዎች ሲሆኑ ልጆቻቸው እነርሱ ከደረሱበትም በላይ እንድንደርስላቸው ቆርጠዋል፡፡ አባባ ጠንክሮ በመሥራትና በሕይወቱ ሙሉ በማጥናት አርዓያ ሆኖናል፡፡ በሥራ ሕይወቱ ብዙ ክብሮችንና ዕድገቶችን ያገኘ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜም ከአንደኛ ደረጃ መምህርነት ወደ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርነት አድጓል፡፡ በኋላም በአውራጃችን ላሉት ለሁሉም የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ዋና አስተዳዳሪ ሆኖ ተሾሟል፡፡ በሩዋንዳ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ልዩ የሆነ መጠሪያ ስም አለው፡፡ ለእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች ልጁ ሲወለድ እናቱ ወይንም አባቱ መጀመሪያ ባዩት ጊዜ የተሰማቸውን ስሜት የሚያንጸባርቅ ስም ይሰጡታል፡፡ ኪንያሩዋንዳ በሚባለው ያገራችን ቋንቋ የኔ ስም (ኢሊባጊዛ) ትርጉሙ ‹‹መንፈሰ-ብሩህና ግሩም ጸዳል ያላት›› ማለት ነው፡፡ ይህን ስም ያወጣልኝ አባቴ ከተወለድኩባት ቅጽበት ጀምሮ ምን ያህል እንደሚወደኝ ስሜ ሁልጊዜ ሲያስታውሰኝ ይኖራል፡፡
የአባቴ ስም ሊኦናርድ፣ የእናቴ ደግሞ ማሬ ሮዝ ሲሆን፤ እናቴን ባልንጀሮቿ ሮዝ እያሉ ይጠሯታል፡፡ በ1963 ክረምት በአንደኛዋ የአክስቴ ልጅ ቤት ወላጆቼ ወደጋራ ጓደኛቸው ሰርግ ሲሄዱ ይገናኛሉ፡፡ ሲተዋወቁ አባቴ ጸጉሩ አድጎ እንደነገሩ ስለነበር እናቴ አየት አድርጋው ከንፈሯን መጠጠችለት፡፡
‹‹ጸጉርህ እንደዚህ ሆኖ ሰርግ ልትሄድ ነው?›› በማለት በቁጭት ጠየቀችው፡፡ አባቴ ጸጉር አስተካካይ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጾ ‹ምን ላድርገው ብለሽ ነው› በሚል ስሜት ትከሻውን ነቀነቀ፡፡ ወዲያውኑ እዚያው እናቴ መቀስ ፈልጋ አባቴን አመቺ ስፍራ አስቀመጠችና ጸጉሩን ማስተካከል ጀመረች፡፡ ጸጉር ቆረጣውን እንዳሳመረችው አይጠረጠርም - ከዚያ ጀምሮ አልተለያዩምና፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ታጋብተው አባቴ ከዚያ በኋላ እናቴ እንጂ ሌላ ማንም ሰው ጸጉሩን እንደማያስተካክለው አረጋገጠ፡፡
ወላጆቼ በማስተማር ሥራቸውና አያቴ የሰጣቸውን መሬት በማረስ (ባቄላ፣ ሙዝና ቡና እያመረቱ ይሸጡ ነበር) ከሚያገኙት ገቢ ትንሽ ገንዘብ መቆጠብ ቻሉ

❤3👍3
በምዕራቡ ዓለም ደረጃ ልከኛ ሊባል የሚችለውና በመንደራችን በጣም የቅንጦት የሚባለው ቤታችን አባቴ ንድፉን አውጥቶ የገነባው ነው፡፡ ማእድ ቤት፣ መመገቢያ ክፍል፣ የየራሳችን መኝታ ቤቶች፣ የእንግዳ ቤትና የአባቴን የግል ሥራ ማከናወኛ ክፍልን ያጠቃልላል፡፡ የራሱ በር ያለው የቀን ሠራተኞቻችን የሚያሳልፉበት ተቀጥላ ግቢና ለእንስሶቹም ራሱን የቻለ ከግቢው የተለየ በረት ስለነበረን ላሞቹ ከኛ ጋር እቤታችን ውስጥ አይተኙም፡፡ አባቴ በቤታችን ጣራ ላይ የሚያርፈውን የዝናብ ውሃ ያጠራቅመው ስለነበር ከኪቩ ሐይቅ ድረስ ውሃ መጎተት ቀርቶልናል፤ የገጠማቸውም የጸሐይ ብርሃንን ቀን ቀን አምቀው ይዘው ማታ ለመብራት የሚጠቅሙ ዕቃዎች ምሽት የአንድ ሰዓት ብርሃን ይሰጡናል፡፡
እኛ እንኖርበት በነበረው የሩዋንዳ ክፍል ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሁለት ተሽከርካሪዎች ነበሩን፡፡ አባቴ የሩቆቹን ገጠራማ ትምህርት ቤቶች ለመጎብኘት የሚንቀሳቀስበት ቢጫ ዶቅዶቄና በሰንበት ቤተክርስቲያን ለመሳምና ዘመዶቻችንን ለመጠየቅ የምንጠቀምባት ትንሽ ተሽከርካሪ ነበረችን፡፡ አንዳንድ የሰፈራችን ሰዎች ሃብታም ባንሆንም ናችሁ ይሉናል፤ አባቴንም ሙዙንጉ ማለትም ‹‹ፈረንጅ›› ወይንም
‹‹ሃብታም›› (ለአብዛኞቹ ሩዋንዳውያን ተመሳሳይ ናቸው) ይሉታል፡፡ በመንደራችን ማንም ሌላ ሰው ዶቅዶቄ አልነበረውም፡፡ ከዚህም የተነሣ እናቴ ሁልጊዜ አባቴ ጭር ባለ ተራራ ሲሄድ በሽፍቶች እንዳይጠቃ ትጨነቃለች፡፡ ስለቤተሰቧ መጨነቅ ልማዷ ሲሆን፤ ከአንድ ምሽት በላይ ከቤት ስንርቅ ሁልጊዜ ማታ ማታ በሬድዮ የሚነገረውን የሐዘን መግለጫ እስከመከታተል ትደርሳለች፡፡ ከቶ ላይሳካልኝ ‹‹እማማ ስለ መጥፎ አጋጣሚ አብዝተሸ ከምትጨነቂ እስኪ ደግ ደጉን ተመኚ›› እላታለሁ፡፡
‹‹አይ ኢማኪዩሌ አንድ ሰው ከልጆቼ አንዱን ወይንም አባትሽን እንዲህ ያለ ክፉ ነገር ደረሰበት ብሎ በሩን ቢያንኳኳብኝ እኮ አልችለውም፡፡ ከማንኛችሁም በፊት እንድሞት ነው ጸሎቴ፡፡›› ለጤናችንና ለደህንነታችን ያለማቋረጥ ትጸልያለች፡፡ ወላጆቼ ጽኑ የሮማ ካቶሊካውያን የነበሩ ሲሆን፤ እምነታቸውንም ለኛ አስተላልፈውልናል፡፡ እቤት የምሽት ጸሎት ማድረስ ልማዳችን እንደሆነው ሁሉ የእሁድን ቅዳሴም አናስታጉልም፡፡ እኔ በበኩሌ ጸሎት ማድረስ፣ ቤተክርስቲያን መሄድና ከአምላክ ጋር የሚያገናኝን ማናቸውንም ነገር ማድረግ እወዳለሁ፡፡ ድንግል ማርያምን ከገነት ሆና የምትጠብቀኝ ሁለተኛዋ እናቴ እንደሆነች በማመን በተለየ ሁኔታ ስወዳት እኖራለሁ፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም መጸለይን እወደውና ያስደስተኝ ነበር፡፡ በእርግጥ በጣም ያስደስተኝ ስለነበር በአሥር ዓመቴ አንድ ቀን ከጓደኛዬ ከዣኔት ጋር ከትምህርት ቤት የቤተሰባችን ጥሩ ወዳጅ የነበሩትንና እንደ አያቴ የማያቸውን ብልህ አረጋዊ ቄስ አባ ክሌሜንትን ለመጠየቅ ጠፍቼ ሄድኩ፡፡ ዣኔትና እኔ አባ ክሌሜንት ዘንድ ለመድረስ በእግራችን አሥራ አንድ ኪሎሜትር ሜዳና ጫካ ተጓዝን፤ ወንዝም አቋረጥን፡፡ ሞቅ አድርገው ሰላም ያሉን ቢሆንም መኖሪያቸው ጋ ስንደርስ በጣም ደክሞን፣ እያለከለክን፣ ረጥበንና ቆሽሸን ስለነበር ሐሳብ ገብቷቸዋል፡፡ ሲቀበሉን ዠቅ ያለውን ነጭ ልብሰ-ተክህኗቸውን ለብሰው፣ እጆቻቸውን ዘርግተውና የሚያምር መቁጠሪያ ባንገታቸው አድርገው ልክ መልአክ መስለዋል፡፡‹‹ምንድነው ልጆቼ? ምን ልርዳችሁ?›› ሲሉ ጠየቁን፡፡
‹‹አባ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር መስጠት እንፈልጋለን›› አለች ዣኔት፡፡
‹‹ልክ ነው አባ›› ስል ተስማማሁ፡፡‹‹አስበንበታል፣ መመንኮስ እንፈልጋለን፡፡›› ምንም እንኳን ሳቃቸውን እንደደበቁ እርግጠኛ ብሆንም ‹‹መመንኮስ? እህ›› አሉ ራሳቸውን በመስማማትና በቁምነገር እየነቀነቁ፡፡ እጆቻቸውን ራሶቻችን ላይ አድርገው ልዩ ቡራኬ ሰጡን፡- ‹‹እግዚአብሔር ሆይ፣ እነዚህን ውድ ልጆች ባርካቸው፤ ከክፉ ጠብቃቸው፤ በዕድሜ ዘመናቸውም ሁሉ ካጠገባቸው አትለይ፡፡›› ከዚያም አየት አደረጉንና ‹‹አሁን ወደየቤታችሁ ሂዱ፡፡ ከ18ኛ ዓመት ልደታችሁ በኋላ ተመልሳችሁ ኑ፤ የዚያን ጊዜም የመመንኮሱ ሐሳብ የሚኖራችሁ ከሆነ እንነጋገራለን፡፡››
ወላጆቼ ጽኑ ካቶሊኮች የነበሩ ሲሆን፤ ክርስቲያንነታቸው እውነተኛ ነው፡፡ ‹‹ሰዎች ለእናንተ ሊያደርጉላችሁ እንደምትፈልጉት አድርጉላቸው›› በሚለው በወርቃማው ሕግ ስለሚያምኑ ጎረቤቶቻችንንም በደግነትና በአክብሮት እንድንቀርብ ያስተምሩናል፡፡ ከመንደራቸው ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንዳላቸው ስለሚሰማቸው የበለጸገና ስሙር ማኅበረሰብ ለመፍጠር በሕይወት ዘመናቸው ሙሉ ግረዋል፡፡ አባቴ ብዙ ሰንበቶችን የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ ያሳልፍ የነበረ ሲሆን፤ ለአብያተክርስቲያናት ቤቶችን መገንባትን የመሳሰሉ ሥራዎችን ወጭዎቹን ከኪሱ እየሸፈነ ያሠራል፡፡ ለደሃ ሕፃናት የትምህርት ዕድል የሚሰጥ ተቋም አቋቁሞ ከሩዋንዳ ጥቂት የቡና አምራቾች ሁለገብ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አንዱን በመመስረት ደርዘን የሚደርሱ የቡና ገበሬዎችን ከትርፋቸው ትንሽ ገንዘብ ለተቋሙ እንዲሰጡ ከተስማሙ በራሱ መሬት ላይ ከኪራይ ነጻ ያሠራል፡፡ መርሃ-ግብሩ በጣም ስኬታማ ስለሆነለት በተወሰነው ገንዘብ የማኅበረሰብ ማእከል መመስረት፣ ለወጣቶች የእግር ኳስ ሜዳ መሥራትና ለትምህርት ቤቱ አዲስ ጣራ ማልበስ ችሎ ነበር፡፡
እናቴም ብትሆን በብዙ መልካም ሥራዎቿ ትታወቃለች፡፡ የተቸገረን ሰው አታልፍም፤ ቀን ጎድሎባቸው ወድቀው በእግራቸው መቆም እስኪችሉ ድረስ መቆያ ቤት የሚፈልጉ ሰዎችን ሁልጊዜ በቤታችን ታኖራለች፡፡
እናቴ የዕለት ሥራዋን ከጨረሰች በኋላ ተማሪዎችን በነጻ ታስጠናና ዕድሜ ልኳን ለሴት ተማሪዎች የደንብ ልብስ ለመስፋት ግብዓቶችን ትገዛ ነበር፡፡ አንዴ ጎረቤታችን ለልጇ የሙሽራ ልብስ መግዛት አለመቻሏ አሳስቧት ለእናቴ ስታዋያት ሰማሁ፡፡
‹‹ሮዝ፣ የገዛ ልጄን በአሮጌ ልብስ ወደ አዲሱ ሕይወቷ የምልካት እንዲያው ምን ዓይነት እናት ብሆን ነው?›› ስትል ሴትዮዋ አዋየቻት፡፡ ‹‹የሚሸጥ ፍየል ቢኖረኝ በሰርጓ ዕለት መልበስ የነበረባትን ልብስ ላለብሳት እችል ነበር፡፡››
እናቴ በፈጣሪ ዕምነት ካላት እንደሚሰጣት በመግለጽ እንዳትጨነቅ ነገረቻት፡፡ በቀጣዩ ቀን እናቴን ከወርሃዊ ደሞዟ ላይ የቆጠበችውን ገንዘብ ስትቆጥር አየኋት፡፡ ወደ መንደሩም በእግሯ ሄዳ እጆቿ በአብረቅራቂ ብትን ጨርቆች ተሞልተው ወደ ቤት ተመልሳ መጣች፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ተቀምጣ ለሴትዮዋ ልጅና ለሁሉም ሚዜዎች
ቀሚሶቹን ስትሰፋ አደረች፡፡
እናቴና አባቴ መንደሩን በሙሉ እንደ ዘመዳችን ስለሚያዩ መንደርተኞቹም በበኩላቸው ብዙውን ጊዜ እንደ ወላጆቻቸው ነበር የሚያዩአቸው፡፡ ለምሳሌ አባቴ በክልሉ የተማረ፣ አስተዋይና ፍትሃዊ ሰው ተብሎ ይታሰብ ነበር፡፡ ስለሆነም ሰዎች በቤተሰብ ጉዳይ፣ በገንዘብ ችግርና በንግድ ሐሳቦች ላይ ምክሩን ፈልገው ብዙ ርቀት ተጉዘው ይመጣሉ፡፡ ግጭቶችን እንዲፈታላቸውና ባለጌ ልጆቻቸውን
እንዲያርምላቸውም ይፈልጉታል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ በሰፈራችን ያለ ችግር የእኛን በር በማንኳኳትና በሚከተለው ልመና ይታጀባል - ‹‹ሊኦናርድ ልትረዳን ትችላለህ? ምክርህን እንፈልጋለን፡፡ ምን ብናደርግ ይሻላል ሊኦናርድ?››
አባቴ ሰዎችን ወደ ቤት በማናቸውም ሰዓት ላይ ይጋብዝና ችግሮቻቸው መፍትሔ እስኪያገኙ ድረስ ያዋያቸዋል፡፡ ጥሩ ሽማግሌና ሰዎች የራሳቸውን ችግር በራሳቸው እንደፈቱ ያህል እንዲሰማቸው የሚያደርግ ሰው ነው

እናቴም ከባሎቻቸው ጋር ችግር ውስጥ በሚገቡ ሴቶች ለምክር ትፈለጋለች፡፡ ባሳለፈቻቸው ዓመታት በሙሉ ከጎረቤቶቻችን ብዙዎቹ በአንድ ወቅት ተማሪዎቿ ስለነበሩ አብዛኛዎቹ መንደርተኞች መምህርት ይሏት ነበር፡፡ ወላጆቼ ለመንደራቸው ኃላፊነት እንደሚሰማቸው ሁሉ በእርግጠኝነት ለልጆቻቸውም ያስባሉ - በተቻላቸውም መጠን ከኛ ጋር ብዙ ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡ አባቴ አንድ ምሽት ሥራ ቦታ በማምሸት መጠጥ ለመጠጣት ከጓደኞቹ ጋር ሄዶ ወደ ቤት ሲመጣ ተኝተን ይደርሳል፡፡ ትንሽ ሞቅ ቢለውም በፍቅር ተሞልቶ ‹‹ልጆቼ የታሉ? የምወዳቸው ልጆቼ የታሉ?›› ብሎ ይጠይቃል፡፡
እናቴ ‹‹ተኝተዋል፤ ሊኦናርድ፣ መተኛት ስላለባቸው፤ ልታያቸው ከፈለግህ በጊዜ መምጣት ነበረብህ፡፡›› ብላ ትቆጣዋለች፡፡ ‹‹በቃ ራት ብቻዬን አልበላም›› ይልና ቀስ ብሎ ሁላችንንም ከመኝታችን ያስነሳናል፡፡ እሱ ራት ሲበላና ስላዋዋሉ ሲነግረን የሌሊት ልብስ ለብሰን በጠረጴዛው ዙሪያ እንቀመጣለን፡፡ አቤት እያንዳንዷን ደቂቃ እንዴት እንዳጣጣምናት!
አባታችን ራቱን በልቶ ከጨረሰ በኋላ ሁላችንንም ሳሎን ያንበረክከንና የምሽት ጸሎታችንን እንድናደርስ ያደርገናል፡፡
‹‹ጸሎታቸውን እኮ አድርሰዋል ሊኦናርድ፡፡ ነገ እኮ ትምህርት አለባቸው!››
‹‹ምን እነርሱ ብቻ፣ እኔስ ብሆን? እንደምታውቂው ነገ ሥራ አለብኝ፣ ሮዝ፡፡ በይ ኢማኪዩሌ፣ ብዙ ጸሎት ማድረግ የለብሽም፡፡ ልክ ነኝ?››
‹‹አዎን አባባ›› እላለሁ አፍሬ፡፡ አባቴን አመልከው ስለነበር እንደዚህ ዓይነት ወሳኝ ጥያቄ ስለጠየቀኝ ደስታ ተሰማኝ፡፡
የአባቴ ኮስታራ መሳይ ገጽታ የማይኖርባቸውና የእርሱን ፍቅር ማየት ለኛ ቀላል የሚሆንባቸው እንደዚህ ያሉ አስደናቂ ጊዜያት ነበሩን፡፡
በቤተሰባችን ውስጥ አራት ልጆች ነበርን - እኔና ሦስት ወንድሞቼ፡፡ ትልቁ፣ ወላጆቼ ከተጋቡ ከአንድ ዓመት በኋላ በ1965 የተወለደው፣ ኤይማብል ነው፡፡ ልጅ ሆኖ እንኳን ኤይማብል ከቤተሰባችን በጣም ኮስታራው ነበር፡፡ ጸጥ ያለና የሚብሰለሰል ስለነበረ የቤተሰቡ ቄስ እያልን እንቀልድበታለን፡፡ እናታችን የበኩር ልጇ በመሆኑ ከሁላችንም አስበልጣ ብትወደውም ኤይማብል ግን እናታችን በምታደርግበት ተጨማሪ ትኩረት ራሱን ዝቅ ዝቅ ለማድረግ፣ ዓይናፋር ለመሆንና ለመሸማቀቅ በቃ፡፡ ለሰው የሚመች ስብዕና አለው፤ ረብሻንም አምርሮ ይጠላል፡፡ ሌሎቹ ልጆች ቤቱን ሲረብሹና እርስ በእርሳቸው ሲጣሉ በመካከላቸው ይገባና ይገላግላል፡፡
አባታችን በማይኖርበት ጊዜ ኤይማብል የእርሱን ቦታ በመተካት የቤት ሥራችንን መሥራታችንን፣ የማታ ጸሎታችንን ማድረሳችንንና በሰዓቱ መተኛታችንን ያረጋግጣል፡፡ ከዚያም በኋላ አምሽቶ በሮቹ መቆለፋቸውንና ቤቱ ሌሊቱን አስተማማኝ መሆኑን ይቆጣጠራል፡፡ ሰውነቱ ከዕድሜው በላይ ቢያስመስለውም እኔን ግን ስለ አዋዋሌ ለመጠየቅ የማይቦዝን፣ በትምህርቴ እንዴት እየገፋሁ እንደሆነና ጓደኞቼ በደኅና ይቀርቡኝ መሆኑን የሚጠይቀኝ አፍቃሪ ወንድሜ ነበር፡፡ በእኔና በኤይማብል መካከል የ5 ዓመታት የዕድሜ ልዩነት ሲኖር እንደ ልጆችነታችን እርስ በርስ ለመተዋወቅ ችግር ፈጥሮብናል፡፡
ወንድሜ ወደ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሄድ የሰባት ዓመት ልጅ ስሆን ከዚያም በኋላ እርስ በርስ የምንተያያው በበዓላት ቀንና በድግሶች ጊዜ ሆነ፡፡ ከቤት የሄደ ዕለት ግን የሚያስጨንቅ የሆድ ህመም ያዘኝ፡፡ ትምህርት ቤቱ የሚገኘው በአቅራቢያችን ባለች ከተማ ቢሆንም ለኔ ግን ወንድሜ ወደ ጨረቃ የሚሄድ መሰለኝ፡፡ የምወደውን ሰው በማጣቴ አካላዊ ህመም ሲሰማኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ እኛን ልጆቹን አባቴ ለኤይማብል ደብዳቤ እንድንጽፍለት ሲያደርገን ማለት የቻልኳቸው ሁለት ነገሮች ነበሩ፡፡ በትላልቅ ቅጥልጥል ፊደላት የሚከተለውን ጻፍኩ - ውድ ኤይማብል፣
እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ፤ እናፍቅሃለሁ፤ እወድሃለሁ… እናፍቅሃለሁ!!!!! እወድሃለሁ፣ ኢማኪዩሌ የቀረ ነገር አለ፤ ይኸውም - እናፍቅሃለሁ ነው!
አባቴ ሲያነበው ሳቀ፡፡ ‹‹የአያትሽን ቤት እንደጎበኘሽ ወይንም ወንድሞችሽ እንዴት እንደሆኑ ምንም የገለጽሽው ነገር የለም ኢማኪዩሌ፡፡ ትንሽ ወሬ ጨመር አድርገሽና እወድሃለሁና እናፍቅሃለሁ የሚለውን ቀንሰሽ እንደገና ለመጻፍ ሞክሪ እንጂ›› ሲለኝ፤
‹‹ግን የሚሰማኝ ያ ነው እኮ አባባ›› በማለት መለስኩ፡፡
ወንድሜን ከዚያ አሳንሼ እንድወድ እንዴት እንደፈለገ ሊገባኝ አልቻለም - እና አባቴ ስለዚያ ደብዳቤ እያነሳ ሁልጊዜ ይቀልድብኛል፡፡
ኤይማብል ከተወለደ ከሁለት ዓመታት በኋላ ሌላኛው ታላቅ ወንድሜ ወደ ዓለም መጣ፡፡ ስሙ ዳማሲን ሲሆን፤ ጎበዝ፣ ተጫዋች፣ ቀልደኛ፣ ደግ፣ በማይታመን ሁኔታ ለሰው አሳቢና መቋቋም በማይችሉት መንገድ የሚወዱት ነው፡፡ በየቀኑ ያስቀኛል፤ ሳለቅስ እንዴት እንደሚያስቆመኝ ሁልጊዜ ያውቅባታል፡፡ ዳማሲንን እስከዛሬ ድረስ ፈገግ ሳልል ወይንም ሳላለቅስ ስሙን መጥራት አልችልም፡፡ በሦስት ዓመታት ቢበልጠኝም እንደመንትያዬ አየዋለሁ፡፡ የቅርብ ጓደኛዬና ነፍሴ ነበር፡፡ ሲከፋኝ ዳማሲን ደርሶ መንፈሴን መልሶ ያነቃቃዋል - ልክ እናቴ ወንዶቹ ልጆች እግር ኳስ እየተጫወቱ ግቢውን እንዳጸዳ ትዕዛዝ ሰጥታኝ እንደተናደድኩባት እለት፡፡ ዳማሲን ጨዋታውን ትቶ፣ ጓደኞቹን ረስቶ እኔን ሊያግዘኝ ወሰነ - ቀሚስ ለብሶ!
‹‹የሴት ሥራ መቼም አያልቅ›› እያለ ድምጹን ከፍ አድርጎ የቁም መጥረጊያውን ያዝ አድርጎ ሲዘፍን እስኪደክመኝ አሳቀኝ፡፡ ከሰዓት በኋላም ከኔ ጋር ሲለፋ ዋለ፡፡ አልፎ አልፎ አስቸጋሪ ጸባይ ቢታይበትም ሁኔታዎች በደግ ማለቃቸው የተለመደ ነበር፡፡ የ12 ዓመት ልጅ ሳለ በምስጢር የአባባን ተሽከርካሪ ‹‹ተውሶ›› ራሱን በራሱ አነዳድ ለማስተማር ሞከረ፡፡ እንደ ወትሮው ቢሆን ኖሮ አባቴ ለጥፋቱ ክፉኛ ሊቀጣው ሲገባ ጉዳዩን ባወቀ ጊዜ ግን ይብሱኑ ልጁን አቀፈው፡፡ እናቴ አስሟ በድንገት በተነሣባት ወቅት አባቴ ለሥራ ጉዳይ ከአካባቢያችን ርቋል፡፡ በከፊል ራሷን
ስታና ለመተንፈስ ተቸግራ መሬቱ ላይ ትወድቃለች፡፡ ዳማሲን ትከሻው ላይ አውጥቶ ተሸክሟት፣ ተሸከርካሪው ጋ ወስዶ፣ በጥንቃቄ ከኋላ ወንበር አስቀምጧት፣ 15 ኪሎሜትር ነድቶ ወደ ቅርቡ ሐኪም ቤት ይወስዳታል፡፡ በመንገድ ላይ ከሁለት ላሞች፣ ሦስት ፍየሎችና ከብዙ ጎረቤቶቻችን ጋር ሊጋጭ ምንም አልቀረውም ነበር፤ ግን ልክ በሰዓቱ ደረሰ፡፡ ሐኪሙ እናቴ በደረሰችበት ሰዓት ሐኪም ቤት ባትደርስ ሟች ነበረች ብሎ ነበር፡፡
ዳማሲንን ያገኘው ሁሉ ይወደዋል - ማራኪ ፈገግታውና ተግባቢ ስብዕናው ከያዙ አይለቁም፡፡ ተጫዋች ቢሆንም በትምህርት ቤቱ በቋሚነት ጥሩ ደረጃ ከሚይዙ ተማሪዎች ተርታ የሚሰለፍ ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ በዚሁም በመቀጠል በመላው ክፍለ ሀገራችን የማስተርስ ዲግሪ በማግኘት በዕድሜ ትንሹ ለመሆን ችሏል፡፡ ያለማቋረጥ የሚያጠና ቢሆንም በካራቴ ቡናማ ቀበቶ ለማግኘት፣ የሁለተኛ ደረጃ

ትምህርት ቤቱና የዩኒቨርሲቲው የቅርጫት ኳስ ቡድኖች አምበል ለመሆን፣ ብሎም ቤተክርስቲያናችንን ለማገልገል ጊዜውን አብቃቅቷል፡፡ ቤታችንን ለቆ ወደ አዳሪ ትምህርት ቤት ሲሄድብኝ ለሳምንት ስላለቀስኩ ዳግመኛ የማልስቅ ያህል ተሰምቶኝ ነበር፡፡ዳማሲን የሕይወቴ ብርሃን ነበር፡፡
የቤተሰቡ ሕጻን፣ ትንሹ ወንድሜ ቪያኒ ሲሆን የተወለደው ከኔ ሦስት ዓመት ዘግይቶ ነበር፡፡ እንደኔ አስተያየት ቪያኒ የባቄላ አበባ መሳይ ዓይን፣ እርጋታና የሰው መውደድ ያለው፤ ግን ሁሉም ታናሽ ወንድሞች እንደሆኑት ሁሉ አስቸጋሪ ነው፡፡ አድጎ ቆንጆ፣ ግዙፍና በቁመት ከኔም በላይ ቢሆንም በኔ ዓይን ቪያኒ ሁልጊዜ ሕፃን ወንድሜ ነው፡፡ እሱን መጠበቅ ኃላፊነቴ መሆኑን ማሰቤን አቁሜ አላውቅም፡፡ እንደ ቡችላ በየሄድኩበት የሚከተለኝ ውድ ልጅ ነው፡፡ ቋሚ ጓደኝነቱን በጣም ተላምጄው ካጠገቤ ሆኖ ካላስቸገረኝ ይናፍቀኛል፡፡
እኔ ሦስተኛዋና ብቸኛዋ ሴት ልጅ ነኝ፡፡ ወንድ የበላይ በሆነበት ማኅበረሰባችን ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ልጅ መሆኔ ተጨማሪ ግፊት አሳድሮብኛል፡፡ በሩዋንዳ ባህል ‹‹ጥሩ ስም›› ይዞ መገኘት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በመሆኑም ወላጆቼ ብቸኛዋ ሴት ልጃቸው እንከን - የለሽ ስም ይዛ እንድታድግ ይጥሩ ነበር፡፡ ከወንድሞቼ ይልቅ በኔ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ነበረብኝ - ብዙ የቤት ሥራ በመስጠት፣ በጣም ጥብቅ የሰዓት እላፊ በመጣል፣ ልብሴን በመምረጥ፣ ጓደኞቼን በማጽደቅና አይሆኑሽም በማለት ወላጆቼ ተቆጣጥረውኛል፡፡ በትምህርት እንዲሳካልኝና አእምሮዬም እንዲጎለብት ይገፋፉኝ የነበረ ቢሆንም ቅሉ በጣም ወግ አጥባቂ በነበረው ማኅበረሰባችን ውስጥ እንደምትኖር እንደማንኛዋም ወጣት ሴት እንድታይ እንጂ እንድሰማ አይጠበቅብኝም ነበር፡፡ እኔ የቤተሰባችንን ታሪክ እነግር ዘንድ መትረፌ ታዲያ ምንኛ ይገርም!
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
የቤተሰቡ ሕጻን፣ ትንሹ ወንድሜ ቪያኒ ሲሆን የተወለደው ከኔ ሦስት ዓመት ዘግይቶ ነበር፡፡ እንደኔ አስተያየት ቪያኒ የባቄላ አበባ መሳይ ዓይን፣ እርጋታና የሰው መውደድ ያለው፤ ግን ሁሉም ታናሽ ወንድሞች እንደሆኑት ሁሉ አስቸጋሪ ነው፡፡ አድጎ ቆንጆ፣ ግዙፍና በቁመት ከኔም በላይ ቢሆንም በኔ ዓይን ቪያኒ ሁልጊዜ ሕፃን ወንድሜ ነው፡፡ እሱን መጠበቅ ኃላፊነቴ መሆኑን ማሰቤን አቁሜ አላውቅም፡፡ እንደ ቡችላ በየሄድኩበት የሚከተለኝ ውድ ልጅ ነው፡፡ ቋሚ ጓደኝነቱን በጣም ተላምጄው ካጠገቤ ሆኖ ካላስቸገረኝ ይናፍቀኛል፡፡
እኔ ሦስተኛዋና ብቸኛዋ ሴት ልጅ ነኝ፡፡ ወንድ የበላይ በሆነበት ማኅበረሰባችን ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ልጅ መሆኔ ተጨማሪ ግፊት አሳድሮብኛል፡፡ በሩዋንዳ ባህል ‹‹ጥሩ ስም›› ይዞ መገኘት ወሳኝ ነገር ነው፡፡ በመሆኑም ወላጆቼ ብቸኛዋ ሴት ልጃቸው እንከን - የለሽ ስም ይዛ እንድታድግ ይጥሩ ነበር፡፡ ከወንድሞቼ ይልቅ በኔ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ነበረብኝ - ብዙ የቤት ሥራ በመስጠት፣ በጣም ጥብቅ የሰዓት እላፊ በመጣል፣ ልብሴን በመምረጥ፣ ጓደኞቼን በማጽደቅና አይሆኑሽም በማለት ወላጆቼ ተቆጣጥረውኛል፡፡ በትምህርት እንዲሳካልኝና አእምሮዬም እንዲጎለብት ይገፋፉኝ የነበረ ቢሆንም ቅሉ በጣም ወግ አጥባቂ በነበረው ማኅበረሰባችን ውስጥ እንደምትኖር እንደማንኛዋም ወጣት ሴት እንድታይ እንጂ እንድሰማ አይጠበቅብኝም ነበር፡፡ እኔ የቤተሰባችንን ታሪክ እነግር ዘንድ መትረፌ ታዲያ ምንኛ ይገርም!
💫ይቀጥላል💫
Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
#ሁቱትሲ
፡
፡
#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
፡
#ምዕራፍ_ሁለት
#ከመቀመጫችን_ሲያስነሡን
‹‹ቱትሲዎች ከመቀመጫችሁ ተነሡ!››
አንድ ቀን አራተኛ ክፍል ሆኜ እማርበት በነበረው መማሪያ ክፍል ውስጥ ስድስት ልጆች ከመቀመጫቸው ተስፈንጥረው ሲቆሙ ግማሽ ደርዘን ወንበሮች ወደ ኋላ ተንጓጉ፡፡ ከዚያ በፊት ሁልጊዜ እናቴ በምታስተምርበት አነስተኛ ትምህርት ቤት ውስጥ እማር ስለነበር ምን እየተከሰተ እንደነበር ልገምት አልቻልኩም፡፡ በዚያን ወቅት አሥር አመቴ ስለነበርና ትንሽ አደግ ላሉ ልጆች የሚሆን ትምህርት ቤት ውስጥ ስማር የመጀመሪያ ቀኔ በመሆኑ የልጆቹ መራበሽ ግራ አጋብቶኛል፡፡ ከዚያ በፊት አስተማሪ የዘውግ ጥሪ ሲያካሂድ በፍጹም አይቼ አላውቅም፡፡
‹‹ቱትሲዎች በሙሉ ከመቀመጫችሁ ተነሡ!›› መምህራችን፣ ቡሆሮ፣ አምባረቀ፡፡ በትልቅ እርሳስ ከዝርዝሩ ላይ ከተማሪዎች ስም አጠገብ ምልክት እያደረገ ነበር፡፡ ከዚያም አቆመና በቀጥታ እኔ ላይ አፈጠጠ፡፡
‹‹ኢማኪዩሌ፣ ሁቱ ስል አልተነሣሽም፤ ትዋ ስል አልተነሣሽም፤ አሁንም ቱትሲ ብል ልትነሺ አልቻልሽም፡፡ ለምንድነው?›› ቦሆሮ ፈገግ እያለ ቢሆንም ድምጹ ግን ክፋቱን ያሳብቅበታል፡፡
‹‹አላውቅም መምህር፡፡››
‹‹ምን ዘውግ ነሽ?››
‹‹የት አውቃለሁ፣ መምህር?››
‹‹ሁቱ ነሽ ቱትሲ?››
‹‹እኔ - እኔ አላውቅም፡፡››
‹‹ካላወቅሽ ውጪያ! ከዚህ ክፍል ውጪ፤ እና ምን እንደሆንሽ ሳታውቂ ተመልሰሽ አትምጪ!››
መጻሕፍቴን ሰበሰብኩና በሃፍረት አንገቴን ደፍቼ ክፍሉን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ ገና ያልታወቀኝ ቢሆንም በሩዋንዳ የዘውግ ክፍፍል ላይ የመጀመሪያዋን ትምህርቴን
ተማርኩ፤ ይህም ክው ነበር ያደረገኝ፡፡
ወደ ትምህርት ቤቱ ጓሮ ሮጬ ወንድሜ ዳማሲን የዕለቱን ትምህርት እስኪጨርስ ድረስ ከቁጥቋጦ ጀርባ ተደብቄ መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ እንባዬን ማቆም ተስኖኝ ሰማያዊ የትምህርት ቤት የደንብ ልብሴ እስኪረጥብ ድረስ ነፈረቅሁ፡፡ ምን እንደተከሰተ ስላልገባኝ ወደ ክፍል ሄጄ የቅርብ ጓደኛዬን ዣኔትን ጉዳዩን ታብራራልኝ ዘንድ ለመጠየቅ በጣም ፈለግሁ፡፡ መምህሩ ሁቱ የሚለውን ስም ሲጠራ ተነሥታለች - ምን አልባትም መምህሩ ለምን እንዳመናጨቀኝ ታውቅ ይሆናል፡፡ በቁጥቋጦው ውስጥ ተኮራምቼ ዳማሲን እዚያ እስኪያገኘኝ ድረስ እንባዬን ሳዘራ ቆየሁ፡፡
‹‹ማን መታሽ ኢማኪዩሌ?›› ሲል ታላቅ ወንድሜ ባለችው የ13 ዓመት ሥልጣን ጠየቀኝ፡፡ አለኝታዬ ዳማሲን አንድ ሰው ጫፌን ከነካኝ ለመፋለም የተዘጋጀ ልጅ ነው፡፡ ቡሆሮ ያለኝን ነገርኩት፡፡
‹‹ቡሆሮ ጥሩ ሰው አይደለም›› አለ ወንድሜ፡፡ ‹‹ቢሆንም አትጨነቂለት፡፡ ሌላ ቀን ስም ሲጠራ እኔ የማደርገውን አድርጊ፤ ከጓደኞችሽ ጋር ተነሺ፡፡ ጓደኛሽ ዣኔት ስትነሳ ተነሺ፡፡››
‹‹ዣኔት ሁቱ ብሎ ሲጠራ ነበር የተነሣችው፡፡››
‹‹በቃ እንደዚያ ከሆነ ሁቱ ሲሉ ተነሺ፡፡ ጓደኞቻችን የሆኑት ያንን ከሆነ መቼም እኛም የምንሆነው እንደዚያው መሆን አለበት፡፡ ሁላችንም አንድ ሕዝብ ነን፣ አይደል?››
በዚያን ወቅት የማውቅበት መንገድ አልነበረኝም፤ ዳማሲንም እንደኔው በሩዋንዳ ስለነበረው ዘውገኝነት ግንዛቤ አልነበረውም… ይህም በአካባቢው በጥሩ ሁኔታ ይማሩ ከነበሩት ልጆች ውስጥ ከመመደባችን አንጻር እንግዳ ነገር ነው፡፡ በየዕለቱ ከትምህርት መልስ ወንድሞቼና እኔ ወደ ቤታችን በእናታችን ተቆጣጣሪነት የቤት ሥራችንን እንድንሠራ ከመጠራታችን በፊት የ90 ደቂቃ የእረፍት ጊዜ ነበረን፡፡ አባታችን ከራት በፊት የትምህርት ቤታችንን ሰሌዳዎች የምታክል ጥቁር ሰሌዳ በቤታችን መካከል አድርጎ ከአንድ ሰዓት ለሚበልጥ ጊዜ ያስጠናናል፡፡ የሒሳብ፣ ሰዋስውና መልክዓምድር ጥናት ጠመኔ እየሰጠ ያለማምደናል፡፡
ይሁን እንጂ ወላጆቻችን ስለራሳችን ታሪክ አላስተማሩንም፡፡ ሩዋንዳ የሦስት ዘውጎች፣ ማለትም የሚበዛው ሁቱ፣ አናሳ ቱትሲዎችና በጣም ትንሽ ቁጥር ያላቸው በጫካ ውስጥ የሚኖሩት ትዋዎች ስብስብ እንደሆነች አላስገነዘቡንም፡፡ የጀርመን ቅኝ ገዥዎችና ከእነርሱ በኋላ የመጡት ቤልጅየሞች የሩዋንዳን ነባር ማኅበራዊ አወቃቀር ማለትም ሩዋንዳን ለምዕተ-ዓመታት ሰላምና ስምምነት የሰጣት ቱትሲ ንጉሥ የሚመሩትን ዘውዳዊውን ሥርዓት በአግላይ ዘውግ-ተኮር የመደብ ሥርዓት ቀይረውት እንደነበር አልተማርንም፡፡ ቤልጅየማውያኑ የቱትሲውን ገዥ መደብ ደግፈውና በመሪነት ደረጃ ያለውን አስተዋፅኦም ተቀብለው፣ አገሪቱን በተሻለ መንገድ ለማስተዳደርና ለቤልጅየማውያኑ ከፍተኛ ትርፍ ለማስገኘት ያግዝ ዘንድ ቱትሲዎች የተሻለ ትምህርት እንዲያገኙ አድርገዋል፡፡ ቤልጅየሞች በሁቱና ቱትሲ መካከል ፈጥረውት የነበረውን ክፍተት በማባባስ ሁለቱን ዘውጎች በቀላሉ ለመለየት የዘውግ መታወቂያ ደብተር አስተዋውቀዋል፡፡ እነዚያ የማይረቡ ስህተቶችም በሁቱዎች ዘንድ ዘላቂ ቁጭት በመፍጠር ለዘር ጭፍጨፋ መሠረት ለመጣል አገዙ፡፡ ቱትሲዎች የተሻለ ነጻነት በጠየቁ ጊዜ ቤልጅየማውያኑ በጠላትነት አዩአቸው፡፡ በ1959 ደም-አፋሳሽ የሁቱ አመፅን ደግፈው ዘውዳዊው ሥርዓት እንዲገረሰስ አደረጉ፡፡ ከ100 000 በላይ ቱትሲዎች በበቀል በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ተገደሉ፡፡ በ1962 ቤልጅዬም ከሩዋንዳ ለቃ ስትወጣ የሁቱ መንግሥት አንቀጥቅጦ በመግዛት ላይ ሲሆን ቱትሲዎችም በሁቱ አክራሪዎች ማሳደድ፣ ሽብርና ግድያ የሚፈጸምባቸው ሁለተኛ ዜጎች ለመሆን በቁ፡፡ በብዙ አሥር ሺህዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎች ግድያዎች የዕለት ከዕለት ክስተት በነበሩባቸው አሥርት ዓመታት ውስጥ ሞቱ፡፡ የሽብር ዑደቱ ተጧጡፎ መድሎ መፈጸሙ ቀጠለ፡፡ የሁቱው መንግሥት ከቤልጅየሞች የአገዛዝ ዘመናት የወሰደው የዘውግ መታወቂያ ደብተር አሠራር መድሎውን የበለጠ ይፋና ቀላል አደረገው፡፡
ወላጆቻችን እኔና ወንድሞቼ ቢያንስ በልጅነታችን እንዳንማራቸው ያልፈለጓቸው የታሪክ ትምህርቶች እነዚህ ነበሩ፡፡ ስለ መድሎም ሆነ ስለ ግድያ ዘመቻዎቹ፣ ስለ ዘር ማጽዳቱም ሆነ የዘር መታወቂያ ካርዶቹ አላወሩንም - እነዚህ ነገሮች ፈጽሞ የልጅነቴ አካል አልነበሩም፡፡
ዘርን፣ ሃይማኖትን ወይንም ዘውግን ከግምት ውስጥ ሳናስገባ በቤታችን ማንንም ሰው በደስታ እንቀበላለን፡፡ ወላጆቼ የእርስዎን ሁቱ ወይንም ቱትሲ መሆን ከስብዕናዎ ጋር አያገናኙትም፡፡ ጥሩ ጸባይ ካለዎትና ገራገር ከሆኑ እጆቻቸውን ዘርግተው ሰላምታ ያቀርቡልዎታል፡፡ ወላጆቼ ራሳቸው ግን በሁቱ ጽንፈኞች የደረሱባቸው የተወሰኑ አሰቃቂ ችግሮች ነበሩ … እንዲያውም አንደኛውን ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ፡፡ ያኔ የሦስት ዓመት ልጅ ነኝ፡፡ ነፍስ ባለማወቄ ምን እየተከሰተ እንደነበር አልገባኝም፡፡ የምሽቱን ሰማይ እሳት ሲንቦገቦግበት፣ እናቴም በእጆቿ ጥብቅ አድርጋ ታቅፋኝ ከቤታችን ስትሮጥ ይታወሰኛል፡፡ ይህ የሆነው ብዙ ቱትሲዎች በተሳደዱበት፣ ከቤቶቻቸው በተነዱበትና በየመንገዱ በተገደሉበት የ1973ቱ መፈንቅለ-መንግሥት ወቅት መሆኑ ነው፡፡ በኛ ክፍለሀገር ሁቱ ጽንፈኞች የቱትሲዎችን ቤቶች በየተራ አቃጥለዋል፡፡ እሳቱ ወደኛ ሽቅብ ሲገሰግስ መላው ቤተሰቤ አብሮ ቆሞ ወደ ኪቩ ሐይቅ ቁልቁል በማስተዋል ላይ ነበረ፡፡ ሩታካሚዜ ወደተባለው ጥሩ ሁቱ ወዳጅ ጎረቤታችን ቤት ሸሸን፡፡ እርሱም ግድያዎቹና ቃጠሎው እስኪያቆሙ ድረስ ሸሸገን፡፡ ወደ ቤታችን ስንመለስ የሚጫጫስ

👍2❤1