አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#በኢማኪዩሌ_ኢሊባጊዛ_እና_ስቲቭ_ኤርዊን


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ

#ክፍል_አንድ


#ክፉ_ቀን_ዳር_ዳር_ሲል

#ምዕራፍ_አንድ

የዘላለማዊ ፀደይ ምድር
የተወለድኩት በገነት ነው፡፡ስለ ትውልድ ሀገሬ በልጅነት ዘመኔ የሚሰማኝ ይህ ነበር፡፡ሩዋንዳ በመካከለኛው አፍሪካ እንደጌጥ ጣል የተደረገች ትንሽ ሀገር ነች፡፡ በጣም ማራኪ ውበት ስላላት፣ በለምለም ሸንተረሮቿ፣ ጭጋግ በሸፈናቸው ተራሮቿ፣ በአረንጓዴ ሸለቆዎቿና በአንጸባራቂ ሐይቆቿ ተማርኮ ለምስጋና ወደ አምላክ አለማንጋጠጥ የማይታሰብ ነው፡፡ ከተራሮቿ ቁልቁል የተለያየ ዝርያ ወዳላቸው የጽድ ጫካዎቿ የሚወርደው ነፋሻ አየር በልዩ ልዩ አበቦች መዐዛ የተሞላ ነው፡፡ የአየሩም ሁኔታ ዓመቱን ሙሉ በጣም ተስማሚ በመሆኑ በ19ኛው ክፍለዘመን መጨረሻ አካባቢ ወደ ስፍራው የመጡት የጀርመን ሰፋሪዎች ሀገሪቱን ‹‹የዘላለማዊ ፀደይ ምድር›› ብለው ሰየሟት፡፡
ውድ ሀገሬን በደም ጎርፍ እንድትታጠብ ያደረጓት ለጅምላ ጭፍጨፋ መነሻ የሆኑት ርኩሳን ሃይሎች በልጅነቴ ተሰውረውብኝ ነበር፡፡ በልጅነቴ የማውቀው ነገር የከበበኝን አማላይ መልከዓምድር፣ የጎረቤቶቼን ደግነት፣ የወላጆቼንና የወንድሞቼን ጥልቅ ፍቅር ነበር፡፡ በቤታችን ዘረኝነትና ምክንያት የለሽ ጥላቻ በፍጹም አይታወቁም፡፡ ሰዎች የተለያየ ጎሳና ዘር እንዳላቸው እንኳ ግንዛቤው አልነበረኝም፤ ቱትሲና ሁቱ የሚሉትን ቃላትም ቢሆን ትምህርት ቤት እስከገባሁበት ጊዜ ድረስ አልሰማኋቸውም፡፡
በሰፈሬ ትንንሽ ልጆች ከቤት ወደ ትምህርት ቤት ብቻቸውን ጭር ባለው አሥራ ሦስት ኪሎሜትር መንገድ ሲመላለሱ ወላጆቻቸው ልጄ ይጠለፍብኛል ወይንም በማናቸውም መንገድ ይጎዳብኛል ብለው አይጨነቁም፡፡ ልጅ ሆኜ በጣም የምፈራው ነገር በጨለማ ብቻዬን መሆንን ሲሆን፤ ከዚያ በስተቀር ግን ሰዎች የሚከባበሩበት፣ የሚተሳሰቡበትና ደስተኛ ይመስለኝ በነበረ መንደር ውስጥ ከደስተኛ ቤተሰብ ጋር የምኖር በጣም ፍልቅልቅ ልጅ ነበርኩ፡፡
የተወለድኩት በምዕራብ ሩዋንዳዋ የኪቡዬ ክፍለ-ሀገር፣ በማታባ መንደር ነው፡፡ ቤታችን ከኪቩ ሐይቅ ትይዩ በሚገኝ ኮረብታ ላይ ያለ ሲሆን፤ ሐይቁም ከፊታችን እስከ ዓለም ጠርዝ የተዘረጋ ይመስላል፡፡ ጠዋት ሰማዩ ከጠራ በሐይቁ በሌላኛው ጠርዝ በጎረቤት ሀገር ዛየር፣ በአሁኑ አጠራሩ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ያሉትን ተራሮች አያለሁ፡፡ ከቤታችን ወደ ሐይቁ የሚወስደውን አስቸጋሪ ቁልቁለት መውረድ ከአስደሳች የልጅነት ትዝታዎቼ አንዱ ነው፡፡ የማለዳው ጤዛ በንጋቷ ጸሐይ ተኖ የሚያልቅበት ጊዜ ሲቃረብ ከአባቴና ከወንድሞቼ ጋር ወደ ዋና እወርዳለሁ፡፡ ውሃው ሞቃት፣ የአየሩ ቅዝቃዜ ውርር የሚያደርግና ከሐይቁ ዳርቻ ያለው የቤታችን እይታ ዘወትር አማላይ ነበር፡፡
አቀበቱና በእግራችን የምንረግጠው አሳሳች ልል አፈር ወደ ቤት የምናደርገውን የመልስ ጉዞ አስፈሪም አስደሳችም ያደርጉታል፡፡ ብዙውን ጊዜ ስለሚያንሸራትተኝ ገደል ገብቼ ሐይቁ ውስጥ እንዳልወድቅ እፈራለሁ፡፡ አባቴም ሁልጊዜ ስፈራ ስለሚያውቅ እቤት እስክንደርስ ድረስ በእጁ ይደግፈኛል፡፡ ትልቅና ጠንካራም በመሆኑ በእነዚያ ትላልቅ እጆቹ በመያዜ ደህንነት ይሰማኛል፤ እንደተወደድኩም ይገባኛል፡፡ እንደዚያ በፍቅር ጢል መደረግ ደስ ያሰኘኛል፡፡ ለዚህም ምክንያት የሆነው በተለይ አባቴ ምንም እንኳን እንደሚወደን ብናውቅም በዘልማዳዊው መንገድ የሚያምን፣ ስሜቱን ብዙውን ጊዜ አውጥቶ የማያሳይና ወንድሞቼንም ሆነ እኔን እንደሚወደን የማይነግረን በመሆኑ ነው፡፡
ከዋና ስንመለስ ቆንጆዋ እናቴ በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ከመሄዳችን በፊት የምትመግበንን ትኩስ የሩዝና የፎሶሊያ ቁርስ እየሠራች በኩሽና ስትባትል እናገኛታለን፡፡ ብርታቷ እኔን ከማስደነቅ ቦዝኖ አያውቅም - እማማ ሁልጊዜ ከቤተሰባችን አባላት ሁሉ ከእንቅልፍ ለመነሳት የመጀመሪያዋና ወደ መኝታ ለመሄድ የመጨረሻዋ ነበረች፤ ቤቱን እንደሚጠበቀው ለማሠጋደድ፣ ልብሶቻችንን ለማስተካከል፣ መጻህፍታችንንና በትምህርት ቤት የሚጠበቁብንን ጉዳዮች ለማዘገጃጀትና የአባቴን የሥራ ወረቀቶች ለማደራጀት ከሁላችንም በፊት ቀድማ እየተነሣች ትለፋለች፡፡ ልብሶቻችንን ሁሉ እሷው በልካችን ትሰፋለች፣ ጸጉራችንን ትቆርጣለች፤ ቤቱንም በእጅ ሥራዎች ጌጦች ታሸበርቀዋለች፡፡ ለቁርሳችን የምትሠራው ፎሶሊያ የሚለማው እኛ ጠዋት ከመኝታችን ሳንነሳ እማማ በምትንከባከበው በጓሮ አትክልት ማሳችን ነው፡፡ እህሉን ቃኝታ ለቀን ሠራተኞቹ የእርሻ መሣሪያዎች ታከፋፍልና ላሞቻችንና ሌሎቹ እንስሶቻችን እንዲቀለቡና እንዲታጠቡ ታደርጋለች፡፡ እነዚህን የማለዳ ሥራዎቿን ከጨራረሰች በኋላ እኛን ወደ ትምህርት ቤት ትሸኝና በእግሯ ቁልቁል መንገዱን ይዛ የሙሉ ጊዜ የማስተማር ሥራዋን ለመጀመር በአቅራቢያችን ወዳለው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትሄዳለች፡፡
ወላጆቼ መምህራን ነበሩ፡፡ ድህነትንና ርሃብን ብቸኛው መመከቻም ትምህርት እንደሆነ በጽኑ ያምናሉ፡፡ በቆዳ ስፋቷ ከሞላ ጎደል ጂቡቲን የምታክለው ሩዋንዳ ከአፍሪካ ትናንሽ ሀገራት አንዷ ብትሆንም በአህጉሩ በከፍተኛ የሕዝብ ጥግግት ተጠቃሽና ከዓለምም ደሃ ሀገራት አንዷ ነች፡፡ እናቴና አባቴ ከየቤተሰቦቻቸው የመጀመሪያዎቹ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቁ ሰዎች ሲሆኑ ልጆቻቸው እነርሱ ከደረሱበትም በላይ እንድንደርስላቸው ቆርጠዋል፡፡ አባባ ጠንክሮ በመሥራትና በሕይወቱ ሙሉ በማጥናት አርዓያ ሆኖናል፡፡ በሥራ ሕይወቱ ብዙ ክብሮችንና ዕድገቶችን ያገኘ ሲሆን፤ በአጭር ጊዜም ከአንደኛ ደረጃ መምህርነት ወደ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርነት አድጓል፡፡ በኋላም በአውራጃችን ላሉት ለሁሉም የካቶሊክ ትምህርት ቤቶች ዋና አስተዳዳሪ ሆኖ ተሾሟል፡፡ በሩዋንዳ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ልዩ የሆነ መጠሪያ ስም አለው፡፡ ለእያንዳንዱ ልጅ ወላጆች ልጁ ሲወለድ እናቱ ወይንም አባቱ መጀመሪያ ባዩት ጊዜ የተሰማቸውን ስሜት የሚያንጸባርቅ ስም ይሰጡታል፡፡ ኪንያሩዋንዳ በሚባለው ያገራችን ቋንቋ የኔ ስም (ኢሊባጊዛ) ትርጉሙ ‹‹መንፈሰ-ብሩህና ግሩም ጸዳል ያላት›› ማለት ነው፡፡ ይህን ስም ያወጣልኝ አባቴ ከተወለድኩባት ቅጽበት ጀምሮ ምን ያህል እንደሚወደኝ ስሜ ሁልጊዜ ሲያስታውሰኝ ይኖራል፡፡
የአባቴ ስም ሊኦናርድ፣ የእናቴ ደግሞ ማሬ ሮዝ ሲሆን፤ እናቴን ባልንጀሮቿ ሮዝ እያሉ ይጠሯታል፡፡ በ1963 ክረምት በአንደኛዋ የአክስቴ ልጅ ቤት ወላጆቼ ወደጋራ ጓደኛቸው ሰርግ ሲሄዱ ይገናኛሉ፡፡ ሲተዋወቁ አባቴ ጸጉሩ አድጎ እንደነገሩ ስለነበር እናቴ አየት አድርጋው ከንፈሯን መጠጠችለት፡፡
‹‹ጸጉርህ እንደዚህ ሆኖ ሰርግ ልትሄድ ነው?›› በማለት በቁጭት ጠየቀችው፡፡ አባቴ ጸጉር አስተካካይ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጾ ‹ምን ላድርገው ብለሽ ነው› በሚል ስሜት ትከሻውን ነቀነቀ፡፡ ወዲያውኑ እዚያው እናቴ መቀስ ፈልጋ አባቴን አመቺ ስፍራ አስቀመጠችና ጸጉሩን ማስተካከል ጀመረች፡፡ ጸጉር ቆረጣውን እንዳሳመረችው አይጠረጠርም - ከዚያ ጀምሮ አልተለያዩምና፡፡ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ታጋብተው አባቴ ከዚያ በኋላ እናቴ እንጂ ሌላ ማንም ሰው ጸጉሩን እንደማያስተካክለው አረጋገጠ፡፡
ወላጆቼ በማስተማር ሥራቸውና አያቴ የሰጣቸውን መሬት በማረስ (ባቄላ፣ ሙዝና ቡና እያመረቱ ይሸጡ ነበር) ከሚያገኙት ገቢ ትንሽ ገንዘብ መቆጠብ ቻሉ
3👍3