አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
579 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቀርና_በቀል


#ክፍል_ስድስት


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


"ከከሰረ ጠቢብ የከሰረ ነጋዴ ይሻላል…በገንዘብ ስትከስር
ቁስ ነው ምታጣው…በአዕምሮው ስትከስር ግን ሙሉ
ስብዕናህ ነው ሚወድመው፡፡››


ፕሮፌሰር አብረሀም ጋር እሄድኩ ነው፡፡ፕሮፌሰር የሚኖሩት
ከሩት ጋር ነው፡፡እሳቸው ቤት ሄድኩ ማለት እግረ-መንገዴን
የሩትን ቤት አወቅኩ ማለት ነው፡፡በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ
ይሏችሆል እንደዚህ ነው፡፡አሁን በዚህን ሰዓት እሷን
እንደማላገኛት እርግጠኛ ነኝ፡፡ምክንያቱን በዚህ ሰዓት እዛው
የተለመደ ቦታዋ ነው የምትገኘው፡፡
ደረስኩና የውጪ በራፍ ጋር ቆሜ ደወልኩላቸ፡፡እራሳቸው
መጥተው ከፈቱልኝ እና ወደ ውስጥ አስገቡልኝ፡፡ያው ወደ
ዕድሜ ጠገቡ ቪላ መኖሪያቸው ነው ይዘውኝ የገቡት፡፡
ሳሎናችው ያው የተደራጀና በዕቃ የተሞላ ቢሆንም የሆነ
የመዝረክረክ አይነት ሁኔታ ይታይበታል፡፡ ተከተለኝ አሉና ወደ
ውስጠኛው ክፍል ቀድመውኝ ሄዱ.. ተከተልኳቸው..አንድ
ክፍል ከፍተው ገቡ…እኔም ተከተልኳቸው..ወደ መኝታ
ቤታቸው ይዘውኝ እየገቡ ነበር የመሰለኝ፡፡ግን አንድ
በመጽሀፍት ቁልል ወደተሞላ ክፍል ነበር የገባነው፡፡ እነስተኛ
ጠረጵዛ ግድግዳውን ተደግፎ ይታያል፡፡ግድግዳው በሶስት
አቅጣጫ በመጽሀፍ መደርደሪያ የተሞላ ነው…በተጨማሪም
ወለሉ ላይ ተደርድረውና ተዝረክርከው ያሉ መጽሀፎች ቁጥር
ስፍር የላቸውም፡፡እሳቸው አልፈው ወንበሩ ላይ ተቀመጡ…
እኔም ከፊት ለፊታቸው ያለ ወንበር ስቤ ተቀመጥኩ፡፡
ዓይኖቼን ክፍሉ ውስጥ አሽከረከርኩ….አይኔ ላይ የገቡትን
መጽሀፍት ርዕሶችን ለማንበብ ሞከርኩ .. ከአዳዲሶቹ
መጽሀፍት ይልቅ ዕድሜ ጠገቦቹ መጽሀፎቹን በቁጥር
ይበልጣል››
‹‹ጋሼ በእውነት ያሎት መጽሀፍት ስብስብ ይገርማል››
‹‹ምን ዋጋ አለው?››አሉ እንደመተከዝ ብለው….አፍንጫቸውን
ላይ የተንጠለጠለውን መነጽራቸውን በእጃቸው ከፍ ዝቅ
እያደረጉ
‹‹ለምን ዋጋ የለውም..…? ‹ሀገር የምትገነባው
ከመጽሀፍቶች ተበርብሮ ከሚገኘ ዕውቀት ነው…›ብለው
ያስተማሩኝ እኮ እርሶ እራሶት ነበሩ››
‹‹አይ ልጄ ማስተማርማ ቀላል ነው… ያስተማሩትን መኖር ነው
ከባዱ…የታደሉት ጥቂት ጠቢባን ከእነዚህ መጽሀፍት በትጋት
በቀሰሙት ጥበብ ትውልድ ይገነቡበታል …ሀገር ያንጹበታል…
የሰውን ህይወት ኑሮ የሚያቀል በረከት ያመርቱበታል፡፡..እኔ
ግን የከሰርኩ ነኝ፡፡ከከሰረ ጠቢብ ደግሞ የከሰረ ነጋዴ
ይሻላል…በገንዘብ ስትከስር ቁስ ነው ምታጣው…በአዕምሮው
ስትከስር ግን ሙሉ ስብዕናህ ነው ሚወድመው፡፡ ›› አሉኝና…
ጠረጵዛው ላይ ከተቆለሉት መጽሀፍቶች ጎን ያለውን የአረቄ
ጠርሙስ አንስተው አንዴ ጠቀም አድርገው ተጎነጩለትና ልክ
የኮሶ መድሀኒት እንደተጎነጨ ህጻን ፊታቸውን አኮሳትረው
ተንገሸገሹ፡፡‹‹ጋሼ አንዴት ከስሬያለው ብለው ሊያስቡ
ይችላሉ.? እርሶ እኮ ለዚህ ሀገር ባለውለታ ኖት..የእርሶን
መጽሀፍቶች እኮ ትውልድ እየታነጸባቸው ያሉ የመንፈስ
ሀብቶቻችን ናቸው…. እርሶ ከስሬያለው ካሉ እኛ ደግሞ
ምን ልንል ነው?››
‹‹ልታፅናናኝ አትሞክር…አየህ ይሄን ሁሉ መጽሀፍት ለዚህ ሁሉ
አመታት አንብቤና ብዙ ተመራምሬ ብዙ ነገር ጽፌያለው…ግን
በተግባር ምን የሰራውት ነገር አለ…?የእኔ የግሌ የሆኑትን ትተን
ሁለት ነፋሶችን የተመሰቃቀለ ህይወት የማቃናበት መንገድ
በዚህ ሁሉ አመት ካላገኘው ታዲያ ከመክሰር ውጭ ይሄንን
ምን ይገልፅዋል?፡፡የግል ችግሮችህን ምትፈታበት አቅም
ከሌለህ የጋራ ለሆነ ነገር እንዴት ልትፋለም ትችላለህ…..?
ቤተሰቡን ማስተዳደር ያቃተው ሰው ሀገር እመራለው ብሎ
የፓለቲካ ፓርቲ ቢያቋቁም ምፀት አይሆንም…..?›››
‹‹ጋሼ ከምንም በላይ እኮ ቤተሰብን መምራት ነው
የሚከብደው…
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ ግን አሁን አሁን የእነዚህን ሁለት
ልጆች ስቃይ በእየእለቱ መመልከት አድክሞኛል፡፡››
‹‹ግን ጋሼ …የማንኛቸው ትክክለኛ አጎት ኖት?››
‹‹የሁለቱም ሊሆን ይችላል..ግን ለጊዜው ይሄንን ጥያቄ
ዝለለው?››
‹‹እሺ ጋሼ…. አሁን ሙሉ በሙሉ ጡረታ ወጥተዋል
አይደል..? ሌላ ሚሰሩት ነገር አለ..?››
‹‹በደንብ አለ እንጂ ..ቀን ቀን አነባለው ፤እጠጣለው፤
ሲደክመኝም ጋደም እላለው..እንዳንዴም ኃይሌ ጋር ሄጄ ዘና
ብዬ እመለሳለው››
‹‹ማታ ማታስ?››
‹‹ማታ ማታማ ሩት እስክትመጣ መጠበቅ ነው ስራዬ
..ስትመጣ ጠብቄ ጫማወን አወላልቄ ልብሷን ቀያሬ
ማስተኛት መደበኛ ስራዬ ነው…በደህና እንደወጣች በሰላም
ወደ ቤቷ መመለሷን ማረጋገጥ ነው ስራዬ…?.አሁን ያው ሌላ
አላማ የለኝም…. ዐላማዬ እሷን መንከባከብ ነው..ዓላማዬን
ኃይሌን መንከባከብ ነው..››
‹‹ቆይ ግን እንዳየውት ሩት ወደ ቤት ምትመጣው ከለሊቱ
አምስት እና ስድስት ሰዓት ነው፣እርሶ የሚቀበሏት ደግሞ
እዚሁ ጠብቀው ከበራፍ ላይ ነው..ታዲያ ከተክለኃይማኖት
ተነስታ እዚህ እስክትደርስ የሆነ አደጋ ያጋጥማታል ብለው
አይሰጉም..?››
‹‹አልሰጋም››
‹‹ለምን?››
‹‹ከዛ እዚህ እስክትደርስ የሚሸኞት ኃይልዬ የቀጠራቸው
ልጆች አሉ..ሁሌ ስራቸውን በትጋት እና በንቃት ነው
የሚወጡት ..እርግጥ እሷ ይሄንን አታውቅም ….. ግን
በየሄደችበት ቀንም ሆነ ለሊት በፈረቃ በሚስጥር እየተከታተሉ
ይጠብቋታል…አየህ ከጤናዋ ጋር በተያያዘ ድንገት ምንም
ነገር ልታደርግ ትችላለች….ከሰው ልትጋጭ
ትችላለች..ሰዎች ሊተናኮሏት ይችላሉ..ድንገት ተነስታም
ከሚበር መኪና ጋር ልትላተም ትችላለች…ለዚህ ነው በቅርብ
እንዲከታተሏት ያደረገው ››
‹‹ይገርማል አልኩ› እውነት ገርሞኝ ‹‹መምህር ቆይ እሩትና
ኃይሌ በየቀኑ ይገናኛሉ …በየቀኑ ይተያሉ... አንድም ቀን ግን
ሲነጋገሩ አይቼ አላውቅም...?
‹‹ትክክል ነህ …ቃላት ከተለዋወጡ ስምንት አመት
አልፎቸዋል››
‹‹ስምንት ዓመት …?››
‹‹አዎ ከተፋቱ ቡኃላ ይተያያሉ እንጂ
አይነጋገሩም….ይቀራረባሉ እንጂ አይነካኩም….››
‹‹እንዴ !!!ተጋብተው ነበር እንዴ ?››
‹‹አዎ ሶስት አመት በጋብቻ አሳልፈዋል..እርግጥ ጋብቻ ስልህ
ቤተሰብ ፈቅዶ ሠርግ ተደግሶ..መዘጋጃ ተፈራርመው
አይደለም፡፡ግን ቢሆንም ከአዲስ አበባ ጠፍተው ከቤተሰብ
ሸሽተው ከሶስት አመት በላይ በጋብቻ አሳልፈው ነበር….›
›‹‹ቆይ ትሁት ማን ነች?››በውስጤ ሲጉላላ የነበረውን ጥያቄ
ድንገት ጠየቅኮቸው
‹‹ትሁትማ የሩት ልጅ ነች?››
‹‹የእሷ ልጅ እንደሆነችማ አውቃለው…ልጠይቆት የፈለግኩት
አባቷስ ማን ነው
የሚለውን ነው?››
‹‹ያው የኃይሌ ናታ..ሌላ የማን ትሆናለች..?››
‹‹ኃይሌ !!!1…….እና ለእሱም ልጁ ነቻ?››
‹‹አዎ..የሁለቱም የጋራ ልጅ ነች››
‹‹እና ልጄን ነጠቁኝ ብላ ነግራኝ ነበር..ኃይሌ ነው እንዴ
የነጠቃት....?የነጠቃት ስል ከጤንነቷ የተነሳ ልጁን ለብቻው
ወስዶ እያሳደገ ነው ወይ ልሎት ነው?››
‹‹ይሄንን ጥያቄ እራሱኑ ብትጠይቀው የተሻለ መልስ
ታገኛለህ››ብለው ከነጥያቄዬ ተውኝ፡፡
‹‹ለምንድነው ግን እንዲህ እየተዋደድ የተፋቱት….?››
‹‹መፋታቱ የኃይሌ ውሳኔ ነው..ግን በቂ ምክንያት አለው››
‹‹እሷስ? ››
‹‹እሷማ ፈጽሞ የምትቀበለው ውሳኔ አልነበረም…..ለዛም
ነው ከህሊናዋም የተጣላቸው..ለዛም ነው በራሷ መንገድ
እሱን እየተበቀለችው ያለችው››
‹‹እየተበቀለችው..እንዴት አይነት በቀል?››
‹‹የምታየውን አይነት በቀል ነዋ…ለምን መሰለህ ምርጫ
እንደሌላት አንድ ሴተኛ አዳሪ አስፓልት ላይ ወጥታ
ከማታውቀው ወንድ ጋር በገንዘብ እየተደራደረች
ምትሄደው..? እሱን ለመበቀል ነው…፡፡ለምን ይመስልሀል
ቤት አልባ እንደሆነ ጎዳና ተዳዳሪ በረንዳ ላይ እራሷንም
እሱንም በብርድ
👍2
#ፍቀርና_በቀል


#ክፍል_ሰባት


ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


"እናትህ ምንም ልታደርግልህ ባትችልም በህይወት አጠገብህ
መኖሯ ብቻ በራስ መተማመንህ እንዲጨምር እና ደህንነት
እንዲሰማህ ያደርጋሀል…. ጠረኗን መማግህ ብቻ ከናርዶስ
ሽቶ ሚሊዬን ጊዜ እጥፍ በልብህ ውስጥህ የደስታ ነውጥን
እና የስሜት መነቃቃትን ይፈጥርልሀል፡፡"


ዛሬ እንደ በቀደምለታው አይነት መሰናክል አልገጠመኝም፡፡
በሰዓቱ ተገኝቼ ፊት ለፊቷ ተቀምጬያለው፡፡ኃይሌም
የካሻሪውን ቦታ እንደያዘ ነው፡፡
‹‹እሺ ሩት ካቆምንበት እንቀጥል?››
‹‹አይ አንተ ሰው!!! ካቆምንበት ምንም የምንቀጥለው ነገር
የለንም…እኔ የጀመርኩትን ነገር ሳልጨርስ አላቆምም ..፡፡
በጅምር ካቆምኩም ደግሞ በቃ አቆምኩ ነው….መልሼ
መቼም አልጀምርም፡፡ምክንያቱም በማግስቱ ካአቆምኩበት
ለመቀጠል ስል ወደኃላ ተመልሼ በማሰብ እራሴን
አላሰቃይም..፡፡እኔ በየቀኑ ተወልጄ በየቀኑ የምሞት …በየቀኑ
ሞቼ ደግሞ በየቀኑ የምወለድ ሰው ነኝ፡፡››
‹‹ ይሄንን ጉዳይ ከዚህ በፊትም ነገረሺኝ ነበር..፡፡ለመሆኑ
ኃይሌን ማፋቀር የጀመርሽው መቼ እንደሆነ
ታስታውሺያለሽ?››ያለ መንደርደሪያ ወደ ጥያቄዬ ገባው፡፡
‹‹እኔ እንጃ››አጭር መልስ
‹‹እንዴት እኔ እንጃ?››
‹እኔ እንጃ ማለት.. ያው እኔ እንጃ ነዋ…. ኃይልሻን
ከመወለዴም በፊት የማፈቅረው ይመስለኛል… ምድር
ከመፈጠሯ በፊትም አፈቅረው ነበር….አዎ እርግጠኛ ነኝ
እንደዛ ነው››
‹‹አንድ ቤት አብራችሁ ስላደጋችሁ ለረጅም ጊዜ እንደ እህትና
ወንድም ትተያዩ እንደነበር እገምታለው ..ያው ከጎረመሳችሁ
ቡኃላ ቀስ በቀስ ወደ ፍቅር የገባችሁ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ግምትህ ትክክል አይደለም ..፡፡የትኛውን ዘመን እንደ
ወንድሜ… የትኛወን ዘመን እንደፍቅረኛዬ … የትኛውን ደግሞ
እንደጠላቴ እሱን አየው እንደነበረ በጊዜ ስሌት ሸራርፌ እና
ከፋፍዬ መናገር አልችልም፡፡አሁን አስበሽ ንገሪኝ ካልከኝ ግን
..ከመጀመሪያው ጠብታ ጀምሮ ሁሌ ወንድሜ እንደነበረ…
ሁሌም ፍቅረኛዬ እንደነበረ…ሁሌም ደግሞ ጠላቴም እንደነበረ
ነው የሚሰማኝ…፡፡ አሁንም አንዳዛው እንደሆነ ነው
የሚሰማኝ፡፡ለዛ ነው በየቀኑ እዚህ ተጎልቼ ወንድሜን ምንም
እንቅፍት እንዳይነካው የምጠብቀው፡፡ለዚህ ነው በየቀኑ
እዚህ ቁጭ ብዬ ፍቅሬን በስስት ዓይን ዓይኑን የማየው…
ለዚህ ነው ጠላቴን በየቀኑ ፊት ለፊቱ እየጠጣው ..ፊት ለፊቱ
እየሸረሞጥኩ የምበቀለው…፡፡ ወንድምነት ፤ፍቅርና በቀል.ደስ
አይልም?››
‹‹እኔ እንጃ….!!! ግን…..!!››
‹‹ምንም ግን የለም..፡፡አንድን ሰው በተመሳሳይ የጊዜ ክበብ
ውስጥ በእኩል መጠን ለማፍቀር እና በእኩል መጠን
ለመጥላት በእኔ ቦታ መሆንን ይጠይቃል፡፡ግን ከፈለክ ጽታዊ
ስለሆነው ነገር መቼ ማሰብ እንደጀመርኩ ልነግርህ
እችለለው፡፡ጊዜው እኔ 7ተኛ ክፍል ኃይልሻ እና ወንድሜ
ደግሞ የ9ነኛ ክፍል ተማሪዎች እያለን ነበር፡፡ትዝ ይለኛል ቀኑ
ደማናማና የሚጨፈግግ ነበር ….ወይንም እኔን ብቻ
ጨፍግጎኝ ይሆናል፡፡ልደታ ማርያም ምትነግስበት ዕለት
ስለነበር ነጭ የሀበሻ ልብሴን ለብሼ ነበር ወደ ትምህርት ቤት
የሄድኩት፡፡ያው እንደነገርኩህ በእለቱ ቢጨፈግገኝም
ከጎደኞቼ ላለመነጠል በእረፍት ሰዓት አብሬአቸው
ነበርኩ..እንደወትሮው እየተሯሯጥን እና እየተባረርን መጫወት
ላይ ነበርን…..ግን ድንገት ሰውነቴ እየጋለብኝ እና እየደከመኝ
መጣ...፡፡
ያው በጫወታው ተመስጬ ብዙ ስለተሯሯጥኩ ይሆናል ብዬ
በማመን አንድ ቦታ በመቆም ከጫወታው እራሴን አግልዬ
ለመረጋጋት ሞከርኩ ፡፡ወዲያው ጭኔን ሲሞቀኝ ተሰማኝ…
ደግሞ እዛው አካባቢ ቀዘቀዘኝ…..ግራ ተጋባው…፡፡ ምን
ነክቶኝ ነው…?፡፡ በቆምኩበት እግሮቼን አጣመርኩ፡፡…..
ወዲያው የሆነ ሰቅጣጭ እና አሸማቃቂ የጩኸት ድምጽ
ከኃላዬ ሰማው፡፡ አንድ ልጅ እጣቱን ወደመቀመጫዬ ቀስሮ‹‹
ወይኔ ደም …ወይኔ ደም..›› እያለ ልክ እንደተአምር አዋጅ
አስነገረ… ወድያው ምድረ ውሪ ሁሉ ተቀባበለው …ከበቡኝ፡፡
እኔ በድን ሆንኩ…፡፡ ካላውበት ቦታ በፍጥነት ለቅቄ መሮጥ
ይኑርብኝ ወይስ ባላውበት ልቀመጥ መወሰን ቸገረኝ..፡፡
ሳለስበው ወሰንኩ… ቁጢጥ ብዬ ተቀመጥኩ …አንገቴን ወደ
መሬት ደፋው፡፡ ከዛ ከየት እንደመጡ አላውቅም ኃይልዬ እና
ወንድሜ ክብን ሰንጥቀው ከፊት ለፊቴ ቆመው አየዋቸው፡፡
ኃይልሻ ኩርምትምት ብዬ ሲያየኝ ‹‹ ምን ሆነሽ ነው..?›› ምን
አገኘሽ..?››በማለት በድንጋጤ እና ግራ በመጋባት ዙሪያዬን
እየዞረ ጠየቀኝ….
‹‹ደም…. !!!ቀሚሷ ደም በደም ሆኗል››በህብረት መለሱለት…
‹‹ማን መታት..?››ማን ነው የፈነከታት?››
‹‹ኸረ ማንም አልነካት… እንትኗ መጥቶባት ነው..የወር
አበባዋ››መለሱለት፡፡
በዚህ ጊዜ ወንድሜ ደንዝዞ ከተገተረበት እንደመባነን አለና
እግሮቹን አንቀሳቀሰ ……ፊቱን አዞረና ለሩጫ በቀረበ እረምጃ
ከቦታው ተፈተለከ…‹‹ወይኔ ጉዴ.. ኃይልዬም ሊከተለው
ነው..›› ብዬ በስጋት ስቃትት እሱ እቴ…. ጭራሽ የለበሰውን
ጃኬት አወለቀና እጄን ይዞ ቁጢጥ ካልኩበት በማስነሳት ልክ
እንደ ሽርጥ ከወገቤ በታች አሸረጠልኝና የሚታየው ደም
ከእይታ እንዲሸፈን አደረገ፡፡ከዛ ብኃላ አንድ እጄን እንደያዘ
እየጎተተና የከበቡኝን አብሻቂ ልጆች በኃይል እየገፈታተረ
ከቦታው ይዞኝ ተሰወረ ..፡፡ ወደቤት ፡፡
ግቢ ስንደርስ ያው እንደነገርኩህ የሰፈራችን ደብር የሆነችው
ልደታ ማሪያም
የምትነግስበት ቀን ስለነበረ ሰው አልባ ነበር..ከእናቱ ጋር ወደ
ሚኖሩበት ክፍል ወሰደኝ..፡፡ተረጋግቼ እንድቀመጥ ካደረገኝ
ብኃላ ወሀ በማስታጠቢያ ሞላልኝ…ሳሙናም ካለበት ፈልጎ
አመጣልኝና ‹‹በይ ልብስሽን አወላልቂና ገላሽን ታጠቢ
….እስከዛ የምትቀይሪው ልብስ ከትልቁ ቤት ላምጣልሽ››
ብሎ ክፍሉን ጥሎልኝ በመውጣት በራፍን ገርበብ አድርጎልኝ
ሄደ…..
‹‹…ያገለደምኩትን የኃይልዬን ጃኬት አወለቅኩና አየውት …
የተወሰነ ደም አቅልሞታል…ልብሴን አወለቅኩና በተዘጋጀልኝ
ውሀ እራሴን አፀዳዳው….ከዛ የእቴቴን ጋቢ ከአልጋ ላይ
አንስቼ በመልበስ ላይ ሳለው..ኃይልዬ በራፉን ገፋ አድርጎ
ገባ…. ምን እንደነካኝ አላውቅም እጆቼ አቅመቢስ
ስለሆኑብኝና ጋቢው አመለጠኝና ከላዬ ላይ ተንሸራቷ ወለሉ
ላይ ወደቀብኝ..እና እርቃኔን ቀረው.... ቶሎ ብዬ ሁለት
የእጆቼን መዳፍ በማነባበር ብልቴን ለመሸፈን ሞከርኩ…
ኃይልሻ ግን ምንም አልመሰለው…‹‹ምን እየሆንሽ ነው..?
መታፈሩ ነው…...? ለነገሩ አሁን ብታፍሪም ይገባሻል….
ማደግሽን ዛሬ አስመስክረሻል››አለኝና ይዞልኝ የመጣውን
ልብስ አልጋው ላይ አስቀመጧ መጀመሪያ ጋቢውን ከወለሉ
ላይ በማንሳት ረገፍ ረገፍ በማድረግ አለበሰኝ፡፡ ከዛ ‹‹ፓንትሽን
አድርጊው…‹›› ብሎ አቀበለኝ ፡፡ተቀበልኩትና አደረግኩ…፡፡
ቀጥሎ ቀሚሴን ሰጠኝ …ጋቢውን ከላዬ እንስቼ ቀሚሴን
ለበስኩ ..ከዛ ምን እንዳደረገ ታውቃላችሁ …ከልብሶቼ ጋር
አንድ ላይ ይዞ የመጣውን የአንገት ልብሴን ቀደደው..ክው
ነው ያልኩት
‹‹ምን እየሰራህ ነው?››››
‹‹የምሰራውንማ ልታይው አይደል?››አለና ልክ የህፃን ልጇን
ሽንት ጨርቅ እንደምታዘጋጅ እናት ቆራረጣው....ከዛ አንዱን
አነሳና በስነስርአት አመቻችቶ ካጣጠፈ ብኃላ ‹‹እንቺ›› ብሎ
ወደ እኔ ዘረጋልኝ ግራ ገብቶኝ ‹‹ምን ላድርገው?››በማለት
ጠየቅኩት
ፈገግ እንደማለት ብሎ‹‹ይሄንን ከፓንትሽ ስር አመቻችተሸ
አድርጊው የሚፈሰውን ደም ወደ ውጭ እንዳይወጣ መጦ
እዛው ያስቀርልሻል.ከዛ አንቺ በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ጨርቁን
ትቀይሪያለሽ አየሽ ቅድም እንደዛ የሆነብሽ ስላልተዘጋጀሽና
እንዲህ አይነት
👍3
#ፍቀርና_በቀል


#ክፍል_ስምንት


ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


"ብዙውን ጊዜ ከእውናዊው ህይወታችን ይልቅ በህልማዊው
ቅኝታችን ውስጥ የተሸሉ ፍትሀዊና ምክንያታዊ ድርጊቶች
ሲከወኑ እንታዘባለን...በዛም ምክንያት በህልማችን እንደ
ውስጣዊ ምኞታችን የምንኖርበትን እና ጣፋጭ ደስታም
የምናገኝበት የተሻለ ምቾት ያለው ዓለም እናገኝበታለን፡፡ለዛም
ነው ብዙውን ጊዜ ህልማችንን የምንወደው፡፡ለዛም ነው
በእውኑ ሕይወታችን የተነፈግነውን ነገር በህልማችን
ለማግኘት የምንዳክረው፡፡"



……ያው በፕሮግራሜ መሰረት ኃይሌ ቤት ተገኝቼያለው፡፡
በተለመደ መስተንግዶው ተቀበለኝ :: ትናንት ከሩት ጋር
ያደረግኩትን ውይይት ሰጠውት፡፡ አንብቦ እስኪጨርስ
ጠበቅኩት››እንደጨረሰ ትንሽ ሽራፊ ፈገግታ ፈገግ አለና
ወረቀቱን መለሰልኝ፡፡
‹‹ይገርማል !!!ይሄንን ታሪክ ዘንግቼው ነበር ..፡፡ማለቴ ስለወር
አበባዋ ያወራችህን…. ደግሞ በሌላ ጊዜ እንኳን አንሰተነው
አናውቅም፡፡ግን አሁን አስታወስኩት… ያሸረጥኩላትን ጃኬት
ሳይቀር አስታውሰዋለው፡፡በጣም የምወደውና እቴቴ
ለእንቁጣጣሽ የገዛችልኝ ጃኬት ነበር፡፡ እና እሷ እንዳለችህ
እቤት ከደረሰች ብኃላ ጃኬቱን ስናየው ልክ እንደቀሚሷ ሁሉ
እሱም የተወሰነ ክፍሉ በደም ቀልሞ ነበር ፡፡እርግጥ
በማግስቱ እራሷ አጥባልኝ ነበር ግን በደንብ ባለመልቀቁ
ምልክቱ ለረጅም ጊዜ እላዩ ላይ ታትሞ እንደቀረ
አስታውሳለው፡፡ እንደዛ በመሆኑ ቅሬታ ተሰምቶኝ አያውቅም
ነበር፡፡ለምን ብትለኝ ..?አላውቅም…፡፡ ግን በዛ የልጅነት
ጊዜዬ ባየውት ቁጥር የሆነ ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ
ያደርገኝ ነበር..ያ ስሜት ለእሷዋ ያለኝ ፍቅር ነው ልልህ
አልችልም… ፡፡ በምንም አይነት በዛን ወቅት ስለፍቅር ላስብ
አልችልም ነበር…፡፡ለዛውም እሷን …...?ምን ነካህ!!! አንድ
ቤት ስላደግን አይደለም..እንደእህቴ አያት ስለነበረም
አይደለም…ዋናው ምክንያት የጋሼ ልጅ ስለሆነች ነበር እሷን
ማፍቀር የምፈራው፡፡
ልጃቸውን እንዳፈቀርኩ በወቅቱ ቢሰሙ እናቴ ጥዋት ጥዋት
ለቁርስ ብላ ለእሳቸው ገንፎ የምታገነፋበት ማሰሮ ወስጥ
ከታትፈው ጨምረውኝ የሚቀቅሉኝ እና ስጋዬንም ለኩቲ
የሚሰጡት መስሎ ነው የሚሰማኝ….፡፡እንዴ ጭራሽ
በውስጤ እንኳን አስቤው አላውቅም፡፡ ፍቅር..!!! እንደድንገት
ልብስ ስትቀይር አጎጠጎጤዋን ያየዋት እለት ወይንም የሆነ
ድብቅ ሰውነቷን በቆረጣ የሾፍኳት ቀን እንዴት ስደነብር እውል
እንደነበር እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ይሁን እንጂ አንድ የማልክደው
ነገር ቢኖር እንዲሁ አይምሮዬን ሞልታ ያለችው እሷ
ነበረች….፡፡
‹‹የሆነ ነገር አደናቅፎኝ ስወድቅ ዙሪያዬን ቶሎ ብዬ
የማማትረው እሷ ከሆነ ቦታ በራ በመምጣት ታነሳኛለች ብዬ
ነው….ሲርበኝ አይን አይኗን የማየው ከቤታቸው የተትረፈረፈ
መሶብ ቆረስ አድርጋ እንደምታጎርሰኝ ሁሌ እርግጠኛ
ስለነበርኩ ነው፡፡ሲከፋኝ የማለቅሰው ከየት መጣች ሳልላት
እጎኔ ተገኝታ እንደምታጽናናኝና አብራኝ እንደምታለቅስ ከልምድ
ስለማውቅ ነው፡፡እንዲያም ሆኖ ግን በወቅቱ ፍቅረኛዬ
ብትሆን ብዬ አስቤ አላውቅም.. ሽማግሌው ተግባሬን
አይደለም ምኞቴን እራሱ ከጭንቅላቴ ሚያነብ ነው
የሚመስለኝ፡፡ስለዚህ እሷ ፍቅር ጀመረኝ ባለችበት ወቅት እኔ
አልጀመረኝም ነበር፡፡ወይም ጀምሮኝ እኔ ግን አዳፍኜው
ነበር..አኔ እንጃ አላውቅም፡፡››
በተለይ ህልም ስላለችው ልንገርህ..በጣም የሚገርም ነገር
ነው፡፡ እንዴት እንዳረሳችው አላውቅም፡፡የወር አበባው ታሪክ
ከተከሰተ ከአምስት ወራት ቡኃላ ይመስለኛል፡፡አስፈሪ እና
አስደንጋጭ ህልም አየው፡፡ህልሙ ያን ያህል አስፈሪ ሆኖ
አይደለም ፡፡እኔ ግን ማየት የሌለብኝን ህልም ያለምኩ
መስሎኝ በጣም ተፀፅቼ ነበር.፡፡ያየውትን ህልም እንዳላይ
እራሴን መቆጣጠር እንደነበረብኝ አስብ ነበር፡፡ ህልሙ
እንዲህ ነው…..ሰላሜ(ሩት) ወደተኛውበት ክፍል በለሊት
እርቃኗን ትመጣብኛለች፡፡ ደንግጬ እኔም እርቃኔን
ከተኛውበት መኝታ አወርድና ከፊቷ ተገትሬ እቆማለው‹‹..ምን
ሆንሽ....?ለምን መጣሽ..?››
‹‹ምን አይነት ጥያቄ ነው የምትጠይቀኝ…..?ይሄ እኮ ለእኔም
እቤቴ ነው..አልጋውም የጋራችን ነው››አለችኝ ፈርጠም ብላ
‹‹እንዴት ቤቴ ስትይ..?››
‹‹እረሳሀው ተጋብተናል እኮ፡፡››
‹‹እኔ እና አንቺ..?››
‹‹አዎ እኔ እና አንተ›› ብላ እርቃኗን ይበልጥ ወደ እኔ
ታስጠጋለች..እንደቆመች
ትለጠፍብኛለች…ከዛ የሁለት እጆቾን ትከሻ እይዝና ከራሴ
የተወሰነ አርቄያት በትኩረት አያታለው‹‹..እንዴ!!! ጡቶችሽ
ከመቼ ወዲህ ነው እንደህ ያደጉት..? ›› እጠይቃታለው፡፡
ከማውቀው በላይ ገዝፎ የሚታዩኝን ጡቾቿን
እያስተዋልኩ…፡፡ ከዛ ወደታች አያለው… ወደ ብልቷ…..፡፡‹‹እንዴ ልሙጥ ሜዳ አልነበረም እንዴ ..?ይሄ
ሁሉ ጭገር ከየት አመጣሽው…...?እኔ እንኳን የለኝም፡፡››
‹‹የለህም…!!! ይሄ ታዲያ ምንድነው..?›› ብላ እጇን ወደ
ብልቴ አካባቢ ልካ ጭገሬን ጨምድዳ ትይዘዋለች..
‹‹እንዴ!!!ይገርማል የእኔም እንዲህ አድጓል..?››ይገርመኛል..
‹‹እንዴት እንዲህ እስኪያድግ ድረስ ሳለየው ››ብዬ መገረሜን
ሳላቆርጥ… ተያይዘን እንተኛለን….እኔ ከስር እተኛላተለው እሷ
ከላዬ ትሆናለች… ከዛ ከዛ ከማህጸኖ በሚወጣ ደም
እታጠባለው… ግንኙነት አድርገን ስንጨርስ ትቆማለች…
የምትቆመው እግሮቾን አንፈርክካ እኔ ከማሀከል እንዳለው
ቁልቁል እያየችኝ ነው፡፡እና ቆማም ከማህፀኗ የሚወጣው
ደም አይቋረጥም ….እንደውም መጠኑ እየጨመረ እየጨመረ
ጎርፍ ይሆንና እኔን ያንሳፍፈኛል….
ከዛ ጠርጎኝ ይዞኝ ይፈሳል… ግን እየወሰደኝም ከእሷ ጋር
አልተለቀቅኩም..የእሷ ጭገር ከእኔ ጭገር ጋር አንድ ላይ
ተቋጥሮ ነበር..እኔ በደሙ ታጥቤ በራቅኩ ቁጥር እሱም አብሮ
ይሳባል ..አይበጠስም…፡፡ ብቻ ዝም ብሎ ይሳባል፡፡
መጨራሻውን ሳለውቅ ነቃው…
ብዙውን ጊዜ ከእውናዊው ህይወታችን ይልቅ በህልማዊው
ቅኛታችን ውስጥ የተሸሉ ፍትሀዊና ምክንያታዊ ድርጊቶች
ሲከወኑ እንታዘባለን...በዛም ምክንያት በህልማችን እንደ
ውስጣዊ ምኞታችን የምንኖርበትን እና ጣፋጭ ደስታም
የምናገኝበት የተሻለ ምቾት ያለው ዓለም እናገኝበታለን፡፡ለዛም
ነው …ብዙውን ጊዜ ህልማችንን የምንወደው፡፡ለዛም ነው
በእውኑ ሕይወታችን የተነፈግነውን ነገር በህልማችን
ለማግኘት የምንዳክረው፡፡እና የእኔም ህልም ከዚህ የተነሳ
የተፀነሰ..ከዚህ የተነሳ የተወለደ ይመስለኛል፡፡ ቢሆንም
በጣም በፍራቻ ተተብትቤ ነበር፡፡እቤቱንም ሀገሩንም ጥዬ
ለመጥፋት ሁሉ አስቤ ነበር…እንዴት እንዲህ ይሆናል…?
እንዴት እንዲህ አልማለው….? ጥዋት ነግቶ እሷን እስካያት
ጣር ሆኖብኝ ነበር…. ግን ፊት ለፊት ላገኛት አልፈለግኩም
...እሷን ፈራዋት…. እራሴንም ፈራውት…..ሶስት ቀን
እየተሸለኮለኩ ከእሷ ለመራቅ ሞከርኩ… ለሊት ከቤት
እየወጣው አምሽቼ ወደ ቤት እመጣለው፡፡በሶስተኛው ቀን
ግን ከለሊቱ አስራ ሁለት ሰዓት አካባቢ አድፍጬ ከቤት
ስወጣ ነጠላዋን ለብሳ ከግቢው ውጭ አገኘዋት… በርግጌ
ስፈተለክ ተከተለችኝ… ደረሰችብኝ እና አነቀችኝ፡፡
‹‹ምን አድርጌህ ነው››
‹‹ምን አደረግሽኝ? ››
‹‹ለምንድነው ያኮረፍከኝ? ››
‹‹መች ነው ያኮረፍኩሽ? ››
‹‹ይሄው ሶስት ቀን ሙሉ ትሸሸኛለህ››
‹‹አንቺን እንደምሸሽ በምን አወቅሽ? ››
‹‹ለምን አላውቅም አውቃለው፡፡.ንገረኝ ? ››ምን ልበላት…
መንገዱን ለቀቅኩና ሸሸግ ብሎ ከሚታየኝ ድንጋይ መቀመጫ
ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ..ተከትላኝ መጣችና ከጎኔ ተቀመጠች፡፡
‹‹ንገረኛ ምን አደረግኩህ? ››
‹‹ፈርቼሽ ነው››
‹‹ለምንድነው

የፈራሀኝ?
👍2
#ፍቀርና_በቀል


#ክፍል_ዘጠኝ


ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ



"በራስ ጥፋት መቀጣት ተገቢም ፍትሀዊም ነው…ወላጆች
በሰሩት ያለፈና የተዳፈነ ስህተት ምክንያት ልጆችን መቅጣት
ግን ከበደልም የከፍ ግፍ ነው፡፡"


ባለፋው ፕሮግራማችን ከኃይሌ ጋር ያደረግነውን ውይይት
ሙሉ በሙሉ አላቀርብኩላችሁም ነበር…ስለዚህ ካቆምንበት
እንቀጥላለን፡፡…ኃይሌ ቀጥሏል
‹‹ከዛ ያው የእኔ እና የሰላሜ ግንኙነት ሳይታወቀው ቀን ከቀን
እያደገና እተጠነከረ መጣ››
‹‹የለየለት መቼ ነው..?››ጠያቂው እኔነኝ
‹‹የለየለት ስትል.?››ግራ በመጋባት መልሶ ጠየቀኝ
‹‹ወደ እውነተኛው ግንኙነት ጠልቃችሁ
የገባችሁት..ፍቀረኛሞች የሆናችሁት? ››ያው በተደጋጋሚ
ጊዜ እኔም ሆንኩ ሰላሜ እንደነገርንህ የሩት እናት በትክክል
ወልዳ አጥብታ ያሰደገችው ግርማን ብቻነው፡፡ሰላሜን እና
ትእግሰትን ግን ከመወለድ በስተቀር ተንከባክባ ፤ አዝላ እና
አጥብታ ያሳደገቻቸው የእኔው እናት እቴቴ ነች፡፡በተለይ እሩት
እናቷን ብዙም አትቀርባትም ነበር…..እንደ እናት የምትመለከታት
እቴቴን ነው ፡፡እቴቴ እስክትሞት እሩት ከጉያዋ አልወጣችም፡፡
እቴቴ ሁል ጊዜ ስታወራ እሰማ እንደነበረው…ልክ እኔ ተወልጄ
በሁለተኛው አመት አካባቢ ነው ሩት የተወለደችው…እና ጡት
ያስጣለችኝ እሷ ነች፡፡በህፃንነታችን ሰላም ( እሩት) አንዱን
የእናቴን ጡት ጎርሳ እየጠባች እኔ ሌላውን ጡት አቅፌ
እየተከዝኩ ነበር የምንተኛው…. ሰላሜ በግራ እናቴ መሀከል
እኔ በቀኝ አንድ መኝታ ላይ ስምንት አመት ሙሉ ተኝተናል፡፡ከዛ
ቡኃላ ነው በዲክታተሩ አባቷ ትዕዛዝ ወደትልቁ ቤት መኝታ
ተመቻችቶላት የተለየችን፡፡ እንደዛም ቢሆን ግን ወይ ማታ
ሹልክ ብላ መጥታ አንድ ሰዓት ወይም ግማሽ ሠአት እናቴ
ጉያ ውስጥ ውሽቅ ብላ ተኝታ በእናቴ እጆች ፀጎሯን ተዳብሳ
….በእናቴ ጣቶች ሰውነቷን ታሽታ .በእናቴ ከንፈሮች ግንባሯን
እና ጉንጮቾን ተስማ ስትጠግብ ወይም ስትረካ
እንደአመጣጧ ሹልክ ብላ ትሄዳለች፡፡…. ወይም ለሊት አስር
ወይም አስረአንድ ሰዓት….አንዳንዴም ስምንትና ዘጠኝ ሰዓት
የጨነበሱ አይኖቾን እያሻሸች‹‹እቴት እንቅልፍ እንቢ አለኝ››
ብላ በራፉን ታንኳኳለች..እኔም እሷን እጠብቅ ይመስል
በርግጌ እነሳና እከፍትላታለው፡፡‹‹ምን ሰውን ትረብሺለሽ
››እያልኩ በማጉረምረም…እናቴ የውሸቴን መሆኑን አይገባትም
‹‹አንተ ምናባክ ታርግህ…. ማን ክፈትላት አለህ ….?ልጄን
አትናገርብኝ… አኔ እራሴ ከፍትላታለው..››ትልና ጎትታ ጉያዋ
ውስጥ ትከታታለች… እኔም ቅናት ብጤ ውርር ያደርገኛና ፊቴን
ወደ እናቴ ጀርባ እዞርና እጆቼን አንገቷ ላይ አዙሬ አቅፋታለው
…ተልዕኮዬ ግን እናቴን ማቀፍ ብቻ አይደለም… ተሸግሬ
ሰላሜንም በተደራቢነት ለማቀፍ ነው..እንዲህ ስሆን እናቴን
አንዳንዴ አሳዝናታለው መሰለኝ ወደእሷ የዞረው ፊቷን
ትመልስና ባይመቻትም በጀርባዋ ትተኛለች… እኔን በቀኝ እጇ
አቅፋ ቀኝ ደረቷ ላይ ታስተኘኛለች እሷን በግራ እጇ አቅፋ ግራ
ደረቷ ላይ ታስተኛታለች…. የሁለታችን ግንባር ይገጣጠማል…
የሁለቱም እጆቾ ጣቶች ሁለታችንንም ጸጉር ውስጥ ገብተው
በፍቅር ያርመሰምሱልናል..ተራ በተራ ግናባራችንን
ትሰመናለች..በዛው ጭልጥ ያለ የሰላም እንቅልፍ
ይወስደናል..
ይሄ ድርጊት እስከእናቴ ህልፈት ድረስ ያልተቋረጠ ነበር…
እናቴ ሁሌ ለሁለታችንም መልካሙን እንደተመኘችልን
ነው‹‹እደጉልኝ ልጆቼ ክፉ አይንካችሁ..ሩቴ መቼም ቢሆን
ወንድምሽን እንዳትረሺው..እሱን ከረሳሽው እኔ እናትሽ
እቀየምሻለው..አንተም አለሜ እህትህን ምንም
እንዳትሆንብህ መጠበቅ ያንተ ሀላፊነት ነው ፡፡ሁል ጊዜ
ተረዳዱ… ተደጋገፉ››ትመክረናለች ትመርቀናለች፡፡
ትሰመናለች፤ ታቅፈናለች፡፡
የዛን ጊዜው ትዝታ እስከዛሬ ድረስ በሁለታችንም ውስጥ
ተቀብሮ ይገኛል፡፡
በነገራችን ላይ እቴቴ ስትሞት እኔ የ12ኛ ክፍል ማትሪክ ተፈታኝ
እሷ ደግሞ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ለፈተና ሁለት ወር
ሲቀረው ነው የሞተችው… እኔ ከሀዘኔ አገግሜ ፈተናዬን
መፈተን ስችል ሰላሜ ግን እቴቴን የማጣቱን ሀዘን መቋቋም
አቅቷት ትምህርቷንም አቋርጣ ከስምንት ወር በላይ የአልጋ
ቁራኛ ሆና ነበር….ወደተነሳውበት ጉዳይ
ልግባልህና..ከህልሙ ጣጣ ከሁለት ወር ቡኃላ ይመስለኛል
… ዛሬም ቀኑ በጣም ጥርት እና ፍንትው ብሎ ነው
የሚታወሰኝ……ወሩ ጭጋጋማው ሀምሌ ነው….ለሊቱን ሙሉ
ዝናቡ ሲወቃው ነው ያደረው…የደራራብኩት ብርድልብሥ
ከቅዝቃዜው አላድን ብሎኝ እናቴ ጉያ ውስጥ ተወሽቄያለው…
አዎ የእሷ ትንፋሽ ራሱ የአምስት ብርድልብሥ ያህል ሙቀት
ይሰጣል….፡፡
ይገርማል በዛ ቅዝቃዜ …በዛ ለሊት በራፋችን ተንኳኳ ፣ያው
ማን እንደሚያንኳኳ የተወቀ ነው…. ከእናቴ እቅፍ ተስፈንጥሬ
ወጣውና ከአልጋዬ ወርጄ በራፍን ከፈትኩላት ….ገፍትራኝ
ወደ ውስጥ ገባች፡፡ከመንሰፍሰፌ የተነሳ መብራቱን እንኳን
ያበራውት ወደውስጥ አልፋ ከገባች ቡኃላ ነበር…ብስብስ
ብላለች..በዛላይ ብርዱ አነጀቷ ገብቶ እየተንቀጠቀጠች
ነው፡፡
‹‹አይ አንቺ ልጅ !!!ምነው በዚህ ዶፍ ልጄ ….?ብርድ ቢመታሽስ…..?››
‹‹እይ እቴቴ ልጅ እና ፊት ብርድ አይመታውም ትይ የለ
››መለሰችላት
‹‹ልበልሻ ተዲያ!!! እንዲህ በዶፍ ዝናብ ተቀጥቀጪ
አልኩሽ….? በይ የለበሽውን ልብስ አውልቂና የእኔን ቀሚስ
ልበሺ…››እንዳለቻት ወዲያው የለበሰችውን ማውለቅ
ጀመረችና… አቋረጠች… ነቄዋ እቴቴ ለምን ማውለቋን
እንዳቋረጠች ገባትና‹‹..ምን ተገረትረህ ታፈጥባታለህ ….?
ተነስ ተኛ፡፡ ››አለችኝ ..ያው ትዕዛዞን አክብሬ አልጋዬ ላይ
ወጣውና ፊቴን ወደግድግዳው አዙሬ በመተኛት
ተከናነብኩላት…ብዙም ሳትቆይ ቶሎ ቀያይራ ወደአልጋው
ወጣች
‹‹…ወይ ልጄን እንዴት ቀዝቅዘሻል..››እለች ጭኖ ውስጥ ከታ
እያሻሸቻት
‹‹…እንቅልፍ እንቢ ስላለኝ እኮ ነው …ዝናብ ደግሞ ፈራለው
ታውቂያለሽ አይደል.?››
‹‹እሱስ አውቃለው…እንደውም እኔም ስላአንቺ እያሰብኩ
አልወስድ ብሎኝ ነበር›››…ከዛ ቀስ እያለ ዝናቡ ወደ ካፊያነት
እየተቀየረ መጣ… አስራ ሁለት ሰዓት ሊቃረብ ሲል ድንገት
የእድር ጡሩንባ ነፊው የአቶ ደበሳይ አዎጅ ተሰማ
‹‹የልደታ እድር አባላት በሙሉ…ወይዘሮ ዘነቡ ጎበና ስላረፉ
ለቅሶ ድረሱ
ተብላችኃል……..››እቴቴ በርግጋ ከመሀከላችን ተነሳች‹‹……
ምነው እቴት.?ምን ሆንሽ?›› ሁለታችንም ከልዩ እንቅልፋችን
ስላባነነችን እየተነጫነጭን…
‹‹ዘነቡ ሞተች ወይኔ እህቴን ወይኔ….››ተረብተበተች….
ማልቀስ ጀመረች… ከአልጋዋ ወረደች..ወይዘሮ ዘነቡን እኔም
ሰላሜም የምናውቃቸው የሰፈራችን ቀደምት ኖሪና የእቴቴ
የቆዩ ወዳጅ ናቸው…እቴቴ በፍጥነት ልብሷን እንደነገሩ
ለባበሰችና ነጣላዋን አዘቅዝቃ በመልበስ ለካፊያው ምንም
ትኩረት ሳትሰጥ በራፍን ከፋታ መልሳ በላያችን ላይ በመዝጋት
ጥላን ሄደች፡፡ሁለታችንም ባለንበት አድፍጥ ዝም አልን
….ደቂቃዎች አለፉ..ከዛ ዝናቡ ከእንደገና አገርሸበት… ዶፍን
ለቀቀው፡፡ በዚህ ጊዜ ሰላም ተስፈንጥራ ተለጠፈችብኝ …
እኔም ተለጠፍኩባት…. እቅፍቅፍ ብለን የአንዳችንን ፍርሀት
ለአንዳችን እያጋራን፤የአንዳችንን ሙቀት ለአንዳችን እያካፈልን
…ሳናውቀው መሳሳም ጀመርን..፡፡ይሄ እንግዲህ የመጀመሪያ
መሳሳማችን ነበር…እርግጥ እንደነገርኩህ ከወራት በፊት
ጉንጬን ስማኝ ነበር..በዛን ጊዜ ግን አድርገን ያማናውቀውን
በወሬ ብቻ የምናውቀውን ከንፈር ለከንፈር መሳሳም
ጀመርን…. ግንኙነታችንን ከሀሳብ እና ምኞት ለመጀመሪያ ጊዜ
ወደ ተግባር የተቀየረበት ቀን ነበር..

በዛን ወቅት ጋሼ ሞገሴ ትዝ አላሉኝም ነበር.....ኧረ ምን
👍1
#ፍቀርና_በቀል


#ክፍል_አስር


ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ


"የስሜት ህዋሳቶቻችን አንድ ላይ ቢቀናጁ እንኳን እውነትን
ለመዳኘት ያላቸው ብቃት ሙሉ አይደለም፡፡ለዚህ ነው
አንዳችን ጋር እውነት ነው ብለን የደመደምነው ክስተት
በሌላው ሰው ውስጥ ተቃራኒውን ገጽ ይዞ የሚናገኘው፡፡
ይሄም ነው ያለማግባባታችን መሰረታዊ መነሻ ምክንያት
ሚሆነው….ምክንያቱም ሁለችንም በራሳችን ውስጥ እውነት
ነው ብለን ላመንበት ጉዳይ ስለምናዳላ….ለዛም ጥብቅና
ቆመን እስከመጨረሻም በጭፍን ስለምንፋለም፡፡"


ለተለመደው አይነት ውይይት በቀጠሮችን መሰረት
የፕሮፌሰሩ የጥናት ክፍል ስደርስ ብቻቸውን አልነበሩም..አንድ
ደልደል ያሉ በእሳቸው ዕድሜ አካባቢ የሚገኙ… ግን በተሸለ
ይዞታ ላይ ያሉ ሰው አብሮቸው ነበሩ….ሰላምታ ሰጥቼ ወደ
ውስጥ እንደዘለቅኩ‹‹ተዋወቀው ዬሴፍ ይባላል.. አብሮ አደግ
ጓደኛዬ ነው‹››አሉኝ ፕሮፌሰሩ
በአክብሮት አንገቴን ሰበር አድርጌ እጄን ለሰላማታ በመዘርጋት
ስሜን ተናገርኩ…..ሰውዬውም በተመሳሳይ አክብሮት
የዘረጋውትን እጅ እየጨበጡ‹‹ዩሴፍ እባላለው..››አሉኝ ..ቦታ
ይዤ እንደተቀመጥኩ‹‹ ..በሉ ትቼያችሁ ልሄድ ነው..ቡኃላ
ደውልልሀላው›› ብለው ፕሮፈሰሩንም እኔንም ተሰናብተው
ወጥተው ሄዱ….እንግዳው፡፡
ፕሮፌሰርም ለመጠጣት እንዲመቻቸው ጠርሙሱን አንስተው
አረቄውን ወደ ብርጭቆው እያንደቀደቁ‹‹የልጅነት ጓደኛዬ
ነው…አሜሪካዊ ሆኗል..ከረጅም አመት የስደት ቆይታ ቡኃላ
ነው ሰሞኑን የመጣው..በጣም ጥሩ እና ልበ-ቀና ሰው
ነው››በማለት ለእኔ ባያስፈልገኝም ተጨማሪ ማብራሪያ
ሰጡኝ
‹‹አይ ጥሩ ነው›› አልኩ ሌላ ምንም ማለት ስላልቻልኩ…ከዛ
አስከተልኩና‹‹ጋሼ ዛሬ ስለ ሩት እናት እንድናወራ ነው
የምፈልገው››አልኳቸው፡፡
‹‹ስለእሷ ምን…?››
‹‹ከእሷ ጋር ያሎትን ግንኙነት በተመለከተ…መቼስ በጣም
ጠበቅ ያለ ይመስለኛል..?ተሳሳትኩ?››
‹‹አልተሳሳትክም …ቤተሰብ እኮ ነን !ማለቴ የታላቅ ወንድሜ
ሚስት ነበረች..››
‹‹አይ ያን ማለቴ አይደለም …ልጅ ሆናችሁ አንድ ሰፈር ነው
አይደል ያደጋችሁት?››
‹‹ አዎ የእኔ ወላጆች ቤት እና የእሷ ወላጆች ቤት አንድ ሰፈር
ነበር…ከእኛ ቤት ግቢ ወጥተህ ቀጥታ መንገድን
እንደተሸገረክ....ፊት ለፊት የምታገኘው የእነሱን ቤት
ነው..ከዛ ጎን ደግሞ የእነ ዮሴፍን ቤት..ዬሴፍ ማለት አሁን
አንተ ስትመጣ የወጣው አብሮ አደግ ጎደኛዬ ያልኩህን ››
‹‹ስለዚህ በደንብ ትግባቡ ነበር ማለት ነው?››
‹‹በትክክል …እርግጥ ከእኔ ይልቅ ከዬሴፍ ጋር እጅግ በጣም
የሚግባቡና የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ….ግን ምንም እንኳን
የእነሱ ቅርርብ የጠነከረ ቢሆንም የእኔ የተለየ ነበር››
‹‹የተለየ ነበር ሲሉ?››
‹‹በጣም ነበር የማፈቅራት ..በጣም ነበር ላገባት እፈልግ
የነበረው ..የልጆቼ እናት
እንድትሆንም እፈልግ ነበር ››
‹‹‹ይሄንን ነግረዋት ያውቁ ኖሯል?››
‹‹ከሚሊዬን ጊዜ በላይ ነዋ…አጋጣሚውን ሁሉ ባገኘው
ቁጥር ከመንገር እና ከማስረዳት ቦዝኜ አላውቅም››
‹‹የእሷስ ምልስ በወቅቱ ምን ነበር?››
‹‹ያው እሷ በጣም አይናፍር እና ስሜቷን አውጥታ መግልፅ
የማትችል አይነት ሰው ነበረች…ሁሉ ነገር በሆዷ ነው..ሁል
ጊዜ ስንገናኝና ስነግራት በፈገግታ እና በዝምታ ታዳምጠኝ
ነበር..ያ ደግሞ ለእኔ ትልቅ ተስፋና ጉጉት ውስጥ እንድገባ
አድርጎኝ ነበር››
‹‹ታዲያ እንዴት ወንድሞት ሊያገባት ቻለ?››
‹‹ምን መሰለህ …በዛ ወቅት ጋብቻን በተመለከተ ወሳኞቹ
ሁለቱ ጥንዶች ሳይሆኑ ወላጆቻቸው ነበሩ… ወንድሜ እንዲሁ
ወንድሜ ልበለው እንጂ የአባት ያህል ነበር በዕድሜ
የሚበልጠኝ..በጣም ትልቅ በሀብትም የተትረፈረፈው..
በንጉሱ ጊዜ ትልቅ ባላባት የነበረ ሰው ነው..በዛም ምክንያት
ማንም ቤተሰብ ከእሱ ጋር መዛመድ እንደክብር እና እንደትልቅ
ዕድል ነው የሚቆጥረው ….እኔ ደግሞ በዛን ወቅት ገና
ከቤተሰቦቼ ድጎማ ራሱ ያልተላቀቅኩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ
ነበርኩ..እና ወላጆቾ ከእኔ ወላጆች ጋር ተደራድረው እና
ተመሳጥረው አንስተው ሲሰጧት ከመንፈራገጥ፣ ከማዘን እና
ከማልቀስ ውጭ ምንም ላደርግ አልቻልኩም.. ማስጣሉን
ተወው በግልፅ በአደባባይ ወጥቼ እንኳን ቤተሰቦቼ ወይም
ቤተሰቦቾ ፊት ለፊት ቀርቤ ‹የእኔ ፍቅረኛ ነች… የብዙ አመት
ምኞቴ እና የረጅም አመት ተስፋዬ ነች ..ማንም ሊነጥቀኝ
አይችልም› ብዬ ለመጋፈጥ ድፍረቱም ብቃቱም አልነበረኝ…፡፡
ምክንያቱም ቤተሰቦቼ በንግግር አና በውይይት የማያምኑ
በጣም ወግ አጥባቂዎች ከመሆናቸውም በተጨማሪ
እንድፈራቸው አድርገው ነበር ያሳደጉኝ፡፡ …ደግሞ በእሷ እና
ወንድሜ መጋባት የእኔ ልብ ብቻ አልነበረም የተሰበረው..
ዬሴፍም በጣም አዝኖና ሚሆነው ነገር ጠፍቶት ነበር..በዛም
ብስጭት ነው አገር ጥሎ ወደሱዳን የተሰደደውና ከብዙ ውጣ
ውረድ ቡኃላ ወደአሜሪካ መግባት የቻለው ፡፡
‹‹እሱ ደግሞ በምን ምክንያት?››
‹‹ነግሬሀለው እኮ ..ምንም እንኳን የማፈቅራት እና ላገባት
የምፈልገው እኔ ብሆንም እሱ ከእኔ በላይ በጣም
የሚቀርባትና የሚወዳት ጓደኛው ነበረች..ታዲያ ዕድሜውን
ለጨረሰና ለማታፈቅረው ሰው ስትዳር እንዴት
አይበሳጭ..እንዴት አይናደድ›› አልተዋጠልኝም..ቢሆንም
ስሜቴን ለእሷቸው በግልጽ ማሳወቅ አልፈለኩም…. ዝም
ብዬ ጥያቄዬን ቀጠልኩ‹‹እሺ ለመሆኑ እርሶስ ካገባች ቡኃላ
ፍቅሩ ቀነሰሎት?››
‹‹ቀነሰሎት…!!! ምን መቀነስ ጭራስ በብዙ እጥፍ ጨመረ
እንጂ››
‹‹እሷስ?››
‹‹የእሷን እርግጠኛ ሆኜ ልነግህ አልችልም..ወንድሜን
በማግባቷ ግን ተከፍታ
ነበር..ዕድሜ ልኳንም ደስተኛ አድርጎት እንደማየውቅ
በርግጠኝነት መናገር እችላለው…››
‹‹ስትታመም እርሶ ውጭ ነበሩ… ከዛ ወስደው አሳከሞት?››
‹‹አዎ… ያ ወቅት በህይወቴ በምሉዕነት የኖርኩበት ብቸኛው
ጊዜ ነበር …እነዛ ወደ አሜሪካ መጥታ አብረን ያሳለፍናቸው
አመታት ፍጽም የማይዘነጉ ገነታዊ ወዘና የነበራቸው
ነበሩ….እና እሷን በማሳከሜ እና በዛ በመከራዋ ወቅት
አብሬያት ከጐኗ በመሆኔ አሁንም ድረስ እራሴን እንደእድለኛ
ነው የምቆጥረው….እርግጥ ለህክምና የወጣው ወጪ
በጣም ብዙና ከእኔ አቅም በላይ ስለነበረ ብዙውን እጅ
የሸፈነው ዩሴፍ ነበር..እሱም ያው እንደነገርኩህ በወቅቱ
እዛው አሜሪካ ነበር የነበረው..እንደእኔ ለትምህርት ሄዶ
ሳይሆን አንደኛውን እዛው ነበር የሚኖረው..ዜግነቱንም ቀይሮ
የተደላደለ ኑሮና አቅም ስለነበረው በዛ ላይ የእኔም ሆነ የእሷ
የልብ ወዳጅ ስለነበረ ያለማንገራገር በደስታ ነበር የረዳን…ለዛ
ነው ቅድም በጣም ጥሩ ሰው ነው ያልኩህ››
‹‹ይገርማል!! እና እዛ እርሶ ጋር ሆና በምትታከምበት ጊዜ
በመሀከላችሁ የተፈጠረ ምንም ነገር የለም?››
‹‹መፈጠር የነበረበት ነገር ሁሉ ተፈጥሯል..እዛ ሆነን ምንም
አይነት የቤተሰብ ፍራቻ ..የሰው ሀሚት… የባህል ተጽዕኖ
ስልልነበረብን የምኞታችንን በሙሉ መከወን ችለን ነበር፡፡››
‹‹እና ታዲያ ለምን ተመለሰች.?.በዛው ጠፍታችሁ በመቅረት
ለዘላለም ህይወትን አብራችሁ መቀጠል ትችሉ ነበር››
‹‹አዎ እንችል ነበር ..የእኔም ፍላጎት እንደዛ ነበር:: ግን ያው
የእናት ነገር ሆኖ የልጆን የደረጄን ናፍቆት መቋቋም
አልቻለችም ..በዛ ላይ ሌላ የምትመለስበት ምክንያት ነበር››
‹‹የምን ምክንያት?››
‹‹ፀንሳ ነበር?››
‹‹ፀንሳ ሲሉ..!!ከማ?››
‹‹ያው ሌላ ከማን ይሆናል ከእኔ ነዋ ››
‹‹ይገርማ…ታዲያ ከእርሶ መፀነሷ እንዴት ወደሀገር ቤት
ለመመለስ ምክንያት ሊሆናት ይችላል…?፡፡እንደውም
ይበልጥ እዛው ለመቅረት እንድትወስን ያስገድዳታል
👍3