አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
የሚያሳድዱኝን እንዴት መውደድ እንዳለብኝ - ቤተሰቤን ያረዱትንም ሁሉ እንዴት እንደምምር ዕውቀት የቀሰምኩበት ነው፡፡
ስሜ ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ነው፡፡ ይህ በታሪክ ብዙ ሕዝብ ካለቀባቸው ጭፍጨፋዎች በአንዱ እግዚአብሔር እንዴት እንደተገለጠልኝ የሚያሳይ ታሪክ ነው።
=======

ይሄን ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ዘወትር ከሰኞ አስከ ቅዳሜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በ #አትሮኖስ ቻናል ብቻ ያገኙታል እንድትከታተሉ ስጋብዛቹ በደስታ ነው ከናንተ ከውድ የቻናሉ አባላቶች የምጠብቀው #MUTE ያደረገችሁን #UNMUTE እንድታደርጉንና ዘወትር ማንበብን ነው ያበረታናል እና Like 👍 እንድታደርጉልንም ነው።
ማታ #አንድሰአት እንገናኝ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ።
#ሮዛ-2

#ብጥስጣሽ_የእለት_ማስታወሳዎች

#ከባለታሪኳ_ግርድፍ_ማስታወሻዎች #የተዋቀረ

#መግብያ

መግቢያ ጥሩ ነው። ያግባባል። ብዥታን ያጠራል። መግቢያ እንኳን ለመጽሐፍ ለ“ሾርት”ም ያስፈልጋል። እነ ሮዚ
ለምሳሌ ወንድ አቻኩሎ ወደ መኝታ ሲነዳቸው ይከፋቸዋል። ጋብዞ፣ አግባብቶ፣ አጫውቶ፣ አቅፎና ደግፎ
ሲሆን ግን ቅልል ይላቸዋል። ለዚህ መጽሐፍ አጭር መግቢያ እንዲኖር የፈለኩትም ለዚሁ ነው።
ሮዚን እስኪ በሞቴ ትንሽ መግቢያ ነገር ጻፊያ ብላት፤ እኔ መዉጫ እንጂ መግቢያ አላውቅልህም”ትለኛለች።አንባቢ እንደሚረዳው “መዉጫ” ማለት ሮዚና ባልደረቦቿ ከሚሠሩበት ቡና ቤት ለአዳር ሲወጡ የሚከፍሉት የኮቴ ግብር ነው። ታዲያ እሷን ከማስቸግር ለምን ራሴ አልሞከረውም?

አንዳንድ የተኖረ ሕይወት ለልቦለድነት የቀረበ ነው። ለምሳሌ የሮዚ ዓይነት ሕይወት። ለዚህም ነው ይህን
መጽሐፍ እውነተኛ ታሪክ” በሚል ሼልፍ ላይ ማስቀመጥ የሚጎረብጠው። “ኩሽተኛ ታሪክ” ቢባል ደግሞ
ትክክል አይሆንም። ደግሞ ልቦለድም አይደለም፣ ባይሆን የተቀባባ፣ በልቦለድኛ የተለወሰ፣ ግን ደግሞ ድብን
ተደርጎ የተኖረ ታሪክ ብንለው ይቀላል።
ስንትና ስንት ግሩም ድንቅ ታሪኮች በጥሩ ሁኔታ ስላልተጻፉ ብቻ ከአንባቢ ሳይደርሱ በትነት መልክ
ይጠፋሉ! እነዚህን ታሪኮች አርታኢ አደምኖ ወደ ሕዝብ ካላዘነባቸው ማን አላቸው!? የሴተኛ አዳሪ ታሪኮች
ደግሞ ጥሎባቸው በአግራሞት የተሞሉ ናቸው። ለመሆኑ እንደነሱ ሕይወትን እስከነንፍጧ የሚያሳየን ሌላ
ፍጥረት አለ? ለዚህ ይመስለኛል ብዙ ሰዎች ለእንዲህ አይነት ታሪኮች ቶሎ የሚሳቡት።

ይህንን መጽሐፍ ትውልድ እንዲማርበት ነው በዚህ መልክ ያዘጋጀሁት እያልኩ መታበይ አልፈልግም። መጽሐፉ
ትውልድ የማነጽም ሆነ ትውልድ የማባለግ ግብ ይዞ አልተነሳም። ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲባል ከታዳጊዎች ይልቅ
አዋቂዎች ቢያነቡት ደስ ይለኛል። አዋቂዎችም ቢኾኑ "ሳማት ሳመችው”፣“አወቃት-አወቀችው፣ •
ተኛችው” ከሚሉት ትዕይንቶች ባሻገር ያሉ ሕይወቶች ላይ ቢያሰላስሉ ይበልጥ ደስ ይለኛል። ጨዋነትም ሆነ
ራስን መጠበቅ በማፈር ላይ ሳይሆን በማወቅ ላይ፣ በመሸፋፈን ሳይሆን በመገላለጥ ላይ፣ በድብቅነት ሳይሆነ
በግልጽነት ላይ፣ መሬት ላይ ያለን ተጨባጭ ሀቅ በማበል ሳይሆን እውነታን በመቀበል ላይ፣ በማስመሰል ላይ .
ሳይሆን በመሆን ላይ ሲመሰረት ቶሎ አይናድም።
ገና ወደፊት በስልጣኔ መስኮት ሾልከው ከሚገቡ ስንትና ስንት ጣጣዎች ጋ እንደምንላተም ሳስብ ካሁኑ ይደክመኛል።

ድሮ የሞራል አስተማሪዎቼን ማታ መስመር ላይ ሳገኛቸው ከነርሱ በላይ እኔ በሐፍረት እከሳ ነበር። ከነ ሮዚ ጋር
እየዋልኩ እያደርኩ ብዙ ጉድ የሚያሰኙ ታሪኮችን ስሰማ መገረም ማቆም እንዳለብኝ ተሰማኝ።ብዙ ሰው ግን አሁንም መገረም አላቆመም መሰለኝ።

ባለታሪኳን የማውቃት አገር ቤት ሳለሁ ነው፤መስቀል ፍላወር በአንድ ተራ ሺሻዊ” አጋጣሚ ይህ የባለስልጣን ፊርማ የመሰለ ሕይወቷን የቸከቸከችበት የማስታወሻ ደብተር እጄ ውስጥ ገባ። አነበብኩት። በጊዜው በነበራት
ብሩህ አእምሮ ተደመምኩ። ያኔ ኮሌጅ የበጠሰ ሸሌ ለኔ ብርቅ ነበር። የመስቀል ፍላወር ጓደኞቼ እንትን ስጪኝ እያሉ ደጅ ሲጠኗት እኔ ደግሞ በተቃራኒው”ዳያሪሽን ስጪኝ እያልኩ አስጨነቅኳት።ተሳካልኝ
ከብዙ ወራት በኋላ ደግሞ በተራዋ

“ዳያሪዬን መልስልኝ!” እያለች ጨቀጨቀችኝ።

ጭቅጭቋ ሰለቸኝ። በኋላ በአንድ የስካር ሞቅታ ተገናኘንና እንዳትጨቀጭቀኝ ፈርቼ አፌ እንዳመጣልኝ
“መጽሐፍ አደርገዋለሁ! ስላት ሳቀችብኝ። ሮዚ ስትስቅ እንዴት ታምር እንደነበር! አልነግራችሁም።

እነሆ ከስንትና ስንት ዓመት በኋላ በቃሌ ስገኝ።

ፍጹም ብርሃኔ አራጌ (አርታኢ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ያው እንግዲህ የ #አትሮኖስ ቻናል ተከታታዮች ቃል በገባሁትና በናንተም ምርጫ መሰረት #ሮዛ-ቀጥር-2 ይዤላችሁ መጥቻለው #ሮዛ-ቁጥር-1 ለመጀመርያ ጊዜ በኛ ቻናል አቅሪቤላችሁ(ማለቴ ታሪኩ በኛ ከቀረበ በኋላ በብዙ ቻናሎች ላይ copy paste ተደርጎ ስለምታገኙት ማለቴ ነው) እንደተመቻቹ በቃላቱም ወጣ ማለት ደንገጥ ብላችሁ አስተያየት የሰጣችሁኝ ብዙ ተከታዎቼ አላችሁ ለሁሉም መልስ ግን ከላይ #መግቢያው ላይ ያለውን እኔም እጋራዋለሁ።

ዛሬ በተለመደው ሰዓት #ሮዛ-ቁጥር-2ትን ይዤላችሁ እቀርባለው እናንተም ወድያው እንዲደርሳቹ ቻናሉን #MUTE ያደረጋችሁ #UNMUTE በማድረግ ተባበሩን አብሮነተችሁን #Like 👍 በማድረግ አሳውቁን።
👍141