#ሁቱትሲ
፡
፡
#በኢማኪዩሌ_ኢሊባጊዛ_እና_ስቲቭ #ኤርዊን
፡
፡#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች፡
፡
#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ
፡
#ቀዳሜ_ቃል
ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ ከስቲቭ ኤርዊን ጋር በመተባበር የጻፈችው #ሁቱትሲ የተሰኘው መጽሐፍ ምናልባት ስለ ሩዋንዳ ከተጻፉት መጻሕፍትም ሆነ ከታዩት ፊልሞች በላይ የፍጅቱን አሰቃቂነትና ዘግናኝነት ገላጭ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም መጽሐፉ ከሰሚ ሰሚ የወረደ ታሪክ ሳይሆን እጅግ ከሚዋደዱ ከስድስት ቤተሰብ አባላት ከግድያው የተረፈችው አንዲት ቱትሲ ወጣት ከአንድ ቁምሣጥን በማይበልጥ መጸዳጃ ቤት ከሰባት ቱትሲ ጓደኞቿ ጋር ከአሁን አሁን ተገደልኩ እያለች እየተጨነቀች የሃይማኖት ጽናቷ እንዴት ለሦስት ወር በሕያውነት እንዳኖራትና በኋላም እንዴት ነጻ ወጥታ ወልዳ ለመሳም የበቃች መሆኗን የሚተርክ ታሪክ ነው፡፡ የሩዋንዳ የዘር ፍጅት ተዋንያንን ፍርድ ቤት እንዳቀርብ በተባበሩት መንግስታት በከፍተኛ የሕግ አማካሪነት ተቀጥሬ በሠራሁበት ጊዜ ከሰማኋቸው በላይ ልብን ሰቅዞ የሚይዝና አእምሮን የሚያናውጥ ታሪክ ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ መጽሐፍ አጋጥሞኛል፡፡
ስሜታዊነት አይነካኝም፣ መንፈሴ በሚያየውና በሚሰማው የማይረበሽ ጠንካራ ሰው ነኝ ባይ ይህንን መጽሐፍ በሚያነብበት ጊዜ ከአንዴም ሁለቴ ዓይኖቹ በእንባ ችፍ ችፍ ማለታቸው አይቀርም፡፡
የኢማኪዩሌ ታሪክ ምንጩ ወይንም የስቃይዋ ምክንያት የተወሳሰበ አይደለም፡፡ መንስኤው ርህራሄ የሚወልደውን የሰብአዊ ስሜትን ደምስሶ ከጥላቻ በላይ ጥላቻ ወልዶ ሰውን ከአውሬነት በታች የሚያውለው የዘር ጥላቻ ነው፡፡
የዘር ጠላቻ አንድ ሰብዓዊ ፍጡር ለሌላው ሰብዓዊ ፍጡር ሊኖረው የሚገባውን ሐዘኔታና ርህራሄ ከሰው ልብ ፈልቅቆ አውጥቶ ከአውሬ በባሰ ጭካኔ ይተካዋል፡፡ በሩዋንዳው የዘር ፍጅት የተፈጸመውን አራዊት ከሚያደርጉት ጋር ማወዳደር የአራዊትን ስም ማጥፋት ይሆናል፡፡ የትኛው አውሬ ነው ሕጻናትን ከታትፎ እንደ ጌሾ በሙቀጫ የሚወቅጠው? የትኛው አውሬ ነው በኢማኪዩሌ ወንድም ላይ እንደተፈጸመው የሰውን አካላት ቆራርጦ ክምር ላይ የሚጥል? የትኛው አውሬ ነው የሰውን ጭንቅላት በገጀራ ለሁለት ሰንጥቆ ሰውዬውን በዝግታ እንዲሞት የሚያደርገው? የትኛው አውሬ ነው የአምስት ልጆችን እናት በልጆቿና በባሏ ፊት ደፍሮ ፊቷ አምስቱንም ልጆቿንና ባሏን አንድ በአንድ የሚከትፈው? ከአክራሪ ሁቱዎች በስተቀር የትኛውም አውሬ አያደርገውም፡፡
የሩዋንዳ የዘር ፍጅት የሰው ልጅ ጭካኔ ልክ የታየበት ነው፡፡ ተመሳሳይ ፍጅትና ጭካኔ የተፈጸመባቸው የናዚዎችና የአርመኖች እልቂቶች እንደሩዋንዳው መንስኤአቸው የዘር ጥላቻ ነበር፡፡
ኢማኪዩሌ በመጽሐፏ የጠቀሰችው የዘር ፍጅቱ ቀስቃሽና ዋና አስተባባሪ ኮሎኔል ቲዩኔስት ባጎስራ ፍርድ ቤት አቅርቤው ዳኞቹ ክሱን አንብበውለት ጥፋተኛ ነህ
አይደለህም ብለው ሲጠይቁት ፈገግ እያለ ‹‹ጥፋተኛ አይደለሁም›› ሲል ፈገግታው እንደ ጦር ይዋጋ ነበር፡፡
መጽሐፉ ከእንግሊዝኛ የተተረጎመ ሲሆን፤ ምናልባትም የአማርኛው ትርጉም ድርጊቶቹን ከእንግሊዝኛው በተሻለ ይገልጻቸዋል ማለት ይቻላል፡፡ ተርጓሚው የሥነጽሑፍ ምሁር እንደመሆናቸው መጠን አገላለጹ ከኢማኪዩሌ በልጦ ቢገኝ አይገርምም፡፡ የቃላቱ ገላጭነት፣ የአረፍተ ነገሮቹ አሰካክ፣ የቋንቋው አወራረድና በጠቅላላው የአማርኛው ውበት ከታሪኩ መሳጭነት ጋር ሆኖ መጽሐፉን ማንበብ ከተጀመረ መልሶ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡፡
ይህ መጽሐፍ የብሔር ጥላቻ የሚፈጥሩ ፖሊሲዎችን ለሚቀርጹና በብሔረሰብ ስም ህዝብን ከፋፍለው ጥላቻ ለሚያስፋፉ ሰዎችም ሆኑ መዋቅርት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ መጽሐፉ ጥላቻ የሚያስከትለውን ሰቆቃ በግልጽ ስለሚያሳይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያነበው በአጽንኦት ስማጠን በዓይኔ በብረቱ ካየሁት ተነሥቼ ነው፡፡
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም
በተባበሩት መንግስታት የቀድሞ የሩዋንዳ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የሕግ አማካሪ
#መግቢያ
ኢማኪዩሌ እባላለሁ
ገዳዮቹ ስሜን ሲጠሩ ሰማኋቸው፡፡
እኔ በግንቡ በአንደኛው በኩል ስሆን እነሱ ደግሞ በሌላኛው አቅጣጫ ናቸው፤ አንድ ጋት የማይሞላ ውፍረት ያለው ጭቃና ዕንጨት ብቻ ይለያየናል፡፡ ንግግራቸው ጭካኔ የሚንጸባረቅበትና ቆርጠው መነሳታቸውን የሚያሳይ ነው፡፡
‹‹እዚህ ነች… እዚህ የሆነ ስፍራ እንዳለች እናውቃለን፡፡ …. ፈልጓት-ፈልጓት ኢማኪዩሌን፡፡››
አካባቢው በሁካታ ተሞላ፡፡ ብዙ ገዳዮች መጥተዋል፡፡ በአእምሮዬ ይታዩኛል - ሁልጊዜ በፍቅርና በደግነት ሰላምታ ይሰጡኝ የነበሩ የቀድሞ ወዳጆቼና ጎረቤቶቼ በቤቱ ውስጥ ጦርና ገጀራ ይዘው ስሜን እየጠሩ ይዘዋወራሉ፡፡
‹‹399 በረሮዎችን ገድያለሁ›› ይላል አንደኛው ገዳይ፡፡ ‹‹ኢማኪዩሌ 400 ታደርግልኛለች፡፡ ይህን ያህል ከገደልኩ ምን እፈልጋለሁ!››
በትንሿ ምስጢራዊ መታጠቢያ ቤታችን ጥጋት አንድስ እንኳን የሰውነቴን ክፍል ሳላላውስ ተሸሽጌያለሁ፡፡ እንደኔው ሕይወታቸውን ለማትረፍ እንደተደበቁት ሌሎች ሰባት ሴቶች ሁሉ ገዳዮቹ ስተነፍስ እንዳይሰሙኝ ትንፋሼን ውጫለሁ፡፡ ድምጻቸው የሠራ አከላቴን ገማመሰው፡፡ በከሰል ፍም ላይ እንደተኛሁ፣ እሳትም ላይ እንደተጣልኩ ተሰማኝ፡፡ መላ ሰውነቴ የሕመም ውርጅብኝ ወረደበት፡፡ ሺህ የማይታዩ መርፌዎች ተቸከቸኩብኝ፡፡ ፍርሃት እንደዚህ የሚያርበደብድ ስጋዊ ሥቃይ ያስከትላል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡
ለመዋጥ ሞከርኩ፤ ጉሮሮዬ ግን ተዘግቷል፡፡ ምራቅ አልነበረኝም፤ አፌም እንደ ኩበት ደርቋል፡፡ ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው፤ ራሴንም ለመደበቅ ሞከርኩ፤ ንግግራቸው ግን እየጎላ መጣ፡፡ ምንም ዓይነት ምኅረት እንደማያደርጉልኝ አውቃለሁ፤ በአእምሮዬም አንድ ሐሳብ ያስተጋባ ጀመር - ከያዙኝ ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ
ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ ይገድሉኛል…
ገዳዮቹ በራፉ ላይ አሉ፤ በማንኛዋም አፍታ እንደሚያገኙኝ አውቃለሁ፡፡ ገጀራው ቆዳዬን አልፎ ሲገባና አጥንቴ ድረስ ሲቆራርጠኝ የሚሰማኝ ስሜት ምን እንደሚመስል አሰብኩት፡፡ ወንድሞቼና ወላጆቼም ትዝ አሉኝ፤ ሞተው ወይንም በሕይወት እየኖሩ እንደሆነ፣ በገነት ከአፍታ በኋላ እንገናኝም እንደሆነ አለምኩ፡፡
እጆቼን እርስ በርሳቸው አጣመርኳቸው፤ የአባቴን መቁጠሪያም ጥብቅ አድርጌ ያዝኩ፤ በለሆሳስም መጸለይ ጀመርኩ - እባክህ እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ እርዳኝ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ እንድሞት አታድርገኝ፣ እንደዚህ አይሁን፡፡ እነዚህ ገዳዮች እንዲያገኙኝ አታድርግ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስህ ከጠየቅን እንደሚሰጠን ትነግረናለህ… እንግዲህ ጌታዬ እየጠየኩህ ነው፡፡ ወይ በለኝ፡፡ እባክህን እነዚህን ገዳዮች ወዲያ እንዲሄዱ አድርጋቸው፡፡ ኧረ በዚህ መታጠቢያ ቤት እንድሞት አታድርገኝ፡፡ እባክህ፣ እግዚአብሔር፣ እባክህ፣ እባክህ፣ እባክህ አድነኝ፡፡
ገዳዮቹ ከቤቱ ወጥተው ሄዱ፡፡ እኛም እንደገና መተንፈስ ጀመርን፡፡ ሄደዋል፤ ሆኖም ግን በቀጣዮቹ ሦስት ወራት ውስጥ ብዙ ጊዜ ይመላለሳሉ፡፡ ሕይወቴን እግዚአብሔር እንዳተረፋት አምናለሁ፤ ሆኖም ቁምሣጥን በምታክል መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ከሰባት ሌሎች ሰዎች ጋር በፍርሃት እየተርበደበድኩ ባሳለፍኳቸው 91 ቀናት መትረፍ ከመዳን በጣም የተለየ አንደሆነ እማራለሁ… ይህ ትምህርትም ለዘለቄታው ለውጦኛል፡፡ ይህ ትምህርት በጅምላ ጭፍጨፋ ውስጥ የሚጠሉና

👍3❤2