የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ሶስት፦ ጠባቂ መልአክ (1)
ሁለት ጋዤጠኞች ያወራሉ ፦ ቲቪው ላይ። አንድ ወንድና ሌላ ሴት። እኔም እንባዬ አቅርሮ፣ በሃዘን ቆዝሜ አያለሁ፦ ቲቪውን። እሰማለሁ፦ የሚሉትን፣ የሚያወሩትን።
“…እንዲህ አይነት … ምን አይነት መስዋእትነት ነው? …” ወንዱ ጋዜጠኛ ይጠይቃል።
“…ፈጽሞ አይቼ አላውቅም። በ‘ንዲህ አይነት ሁኔታ፣ ነፍስን በሚያስጨንቅ ቀውጢ ወቅት ሁሉም ህይወቱን በደመ ነፍስ ለማዳን ነው የሚሮጠው።…እዚህ ቪድዮ ምስል ላይ የሚታየው ግን አዲስ ነገር ነው። …” ሴቷ ጋዜጠኛ ትመልሳለች።
“…እንዲህ አይነት ፍቅር አይተሽ ታውቂያለሽ?...”
“…ይህን ያየሁት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። እጅግ ለማመን የሚከብድ አስደናቂ መሰጠት ወይም መስዋእትነት ነው …በቃላት ለመግለጽ ይከብዳል ….በተግባር የታየው ….ይህ ወጣት የፍቅረኛውን ህይወት በህይወቱ ሲለውጥ ነው። ሲያድናት፣ ሲጋርዳትና ሲጠብቃት ነው።…እጅግ የሚያስደንቅ የሁለት ወጣቶች ፍቅር …. ሊታመን የማይችል የአንድ ልጅ መስዋእትነትን ይህንን ቪዲዮ በመመልከት ማየት ይቻላል።….” ጋዜጠኛዋ በስሜት፣ ሲቃ እየተናነቃት ታወራለች፣ በቲቪው ላይ።
እኔም አያለሁ።
ጋዤጠኞቹ እያወሩ ያሉት ሰለ ዳሪክና ሳሌም ነው። የሚወያዩትም በአምስተኛው አቬኒዩ ካፌ ከሰኪሪቲ ካሜራ ላይ ከተገኘው ቪድዮ ምስል ነው። ከካፌው የሰኩሪቲ ካሜራ ምስል ነፍሰ ገዳዩ ግለሰብ ሲገባና ሰዎቹ ላይ ሲተኩስ የነበረው ትዕይንት የጠዋቱ የዜና መነጋግሪያ ሆኗል። ከሁሉም በላይ ደሞ የጠዋቱ የሰባ ትኩስ ዜና ዳሪክ ሳሌምን ለማዳን ያደረገው፣…. የከፈለው ክፍያ ነው።
በምስሉ ላይ እንዲህ ይታያል፦…ግለሰቡ ካፌው ውስጥ ገባና ሽጉጡን አውጥቶ ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ ያገኘው ሰው ላይ መተኮስ ጀመረ። …. ወደ ሳሌም ዞሮ ሲተኩስ ዳሪክ በፍጥነት ሊጋርዳት ሲሞክር ይታያል። ነገር ግን አልቻለም። ምናልባት በመጀመሪያ የተተኮሱት አንድ ወይም ሁለት ጥይቶች ሳሌምን በደረቷ አካባቢ ያገኛት ይመስላል። ሳሌም በተቀመጠችበት ወደ ኋላ ስትዘረር፣… ዳሪክ የራሱን ነፍስ ማዳን ትቶ … ሳሌምን ሲያቅፋትና እንደ መጋረጃ፣ ሙሉ በሙሉ በሰውነቱ ሲጋርዳት፣ ሲሸፍናትና አብሯት ካላዯ ላይ ሲወድቅ ይታያል። …ከዛ ቡሃላ የተተኮሱት ጥይቶች (አራት ወይም አምስት ይመስለኛል) ሁሉም በዳሪክ ጀርባና አንገት አካባቢ ሲሰገሰጉ በምስሉ ላይ ይታያል። ተኳሹ ግለሰብ ጥይቱን ሲጨርስና ለማምለጥ እየሮጠ ሲወጣ በምስሉ ላይ ሲታይ …. ግለሰቡ ብዙም ሳይርቅ በፖሊሶች ቁጥጥር ስር ገብቷል።
በምስሉ ላይ ለሚታየው ትዕይንት ዓለምን ቢያስገርም አይገርመኝም። ቢያስደንቅ አይደንቀኝም። እውነትና ፍቅር ሲዋሃዱ የሚሆነው ይህ ነው። የሁለቱ ውህደት ውጤት እውነተኛ ፍቅርን ያመጣል። ይህ ፍቅር ደሞ የጌታ ፊት ስስ ነጸብራቅ ነው። ያስደንቃል። ያስገርማል። ዳሪክና ሳሌምን ሳያቸው የማየው ይህን ነበር። የምመለከተው የእውነትንና የፍቅርን ውህደት ነው። በቃ የማየው ልብን የሚሰረስር፣ ነፍስ ውስጠት ደረስ የሚገባ የእውነት ከልብ የሆነ ፍቅርን ነው። ይህን ፍቅርን ሳይ ለሁለት አመት ስለቆየሁ ዛሬ ዜናና ትልቅ ወሬ የሆነው ይህ የዳሪክ መሰጠትና መስዋእትነት ብዙም አልገረመኝም።
ዳሪክ ከልቡ፣ ከነፍሱ፣ ከእውነቱ ሳሌምን ይወዳል። ከፍቅሩ ጥልቀትም የተነሳ ከሷ ህይወት ወጪ የህይወቱ ስትንፋስ ሲተነፍስ፣ የነፍሱ ትርታ ሲመታ አይታየውም … አይታሰበውም። ስለዚህ ፍቅሩን ለማዳን ሰውነቱን እንደ ጥይት መከላከያ ልብስ አድርጎ በሳሌም ፊት ቆመ። ፍቅር የራሱን አይፈልግም … ህይወቱን እንኳን ቢሆን የራሱን አይሻም። የሚወደውን ሰው እንጂ። በሌላ አነጋገር ዳሪክ የራሱን አይፈልግም … የሳሌምን እንጂ። እውነት፣ የሆነውም ዳሪክ ያደረገውም ይህን ነው። ይህ ለፍጥረት አእምሮ ከባድ ነው። በፍቅር መርህና ቀመር ውስጥ ግን ይሆናል … ይደረጋል። ዳሪክ ይህንን አድርጏል።
ራሴን የምጠይቀው ግን አንድ ጥያቄ ነበር። ጥያቄው ይህ ነው። እንዴት እንዲህ ሊዋደዱ ቻሉ? እንዴት ነፍሳቸው አንድ ስኪመስል ድረስ ተፋቀሩ? እንደምንስ ያንዱ ህይወት ከሌላው መነጣጠል ሳካይችል ተጣበቀ? አንድ ቀን እድሉን ባገኝ ሁለቱን አጠገቤ አስቀምጬ አይን አይናቸውን እያየሁ ብጠይቅ …አቤት ደስታዬ፣… ይህ ጸሎቴ ነው።
…ታዴ ወደኔ ሲመጣ ከሩቅ ሳየው ከተጋደምኩበት አግዳሚ ሶፋ ላይ ተነሳሁ። ሊነጋጋ ሲል እንቅልፌ ሲበረታ በሆስፒታሉ አንድ ጥግ ላይ ካለ ማረፊያ ስፍራ አረፍ ብዬ ነበር። የቲቪው ወሬና የሚዋዥቀው ሃሳቤ ረፍት ነሳኝ እንጂ። ሆኖም ረዥሙ ሌሊት አልፏል። የማይገፋው ውድቅት ነግቶ ጸሀይ ወጥታለች። አሁንም ግን የዳሪክና የሳሌም መልካም ወሬ እየጠበቅን ነው። የዳሪክም ኮድ ብሉ ከሰማንበት ጊዜ ቡሃላ ከሃኪሞቹ ምንም የሰማነው ነገር የለም። መልካምም ክፉም ወሬ የለም። አሁንም ምጥ ላይ ነን።
“…ምን አዲስ ነገር አለ?” አጠገቤ ሲደርስ ታዴን ጠይቅኩኝ።
“…አሁንም ምንም አልነገሩንም። በሮቹ ሁሉ ዝግ ናቸው።…”
“…ሁሁሁሁሁሁሁሁ…” በረጅሙ ተነፈስኩ። “…እንጠብቃለን፣ ሁሉም መልካም ይሆናል…”
ታዴ የሰማኝ አልመሰለኝም። ሃሳቡ በግድግዳው ላይ ወደተሰቀለውና ሳየው ወደ ነበረው ቲቪ ሄዿል።
“…የሚገርም መስዋእትነት፣ አስደናቂ ጀግንነትና ፍቅር …” ቲቪው ላይ ያለው ጋዜጠኛ ያወራል።
ታዴ በዜናው ላይ የሚታየው ምስል እንዳይረብሸው ብዬ “…እዛው እንግዳ መቀበያው አካባቢ ሄደን ሃኪሞቹን እንጠብቅ…” ስለው
ዞር ብሎ አየኝና “…ዜናውን ያላየሁት መስሎሽ ከሆነ አይቼዋለሁ...” አለኝ
በምስሉ ላይ የሳሌም አወዳደቅ የዳሪክም እሷን ለማዳን ያደረገው ነገር ልብን የሚሰብር ነው። ለታዴ ምን ማለት እንዳለብኝ ስለጠፋኝ … ዝም ብለን ወደ እንግዳ መቀበያው ክፍል ማምራት ጀመርን።
እየሄድን ታዴ መናገረ ጀመረ “..ሳሌም ሁሌም የምትለው ነገር ነበር። ምን እንደ ሆነ ታውቂያለሽ?...”
“…ምንድን ነው?...” አይን አይኑን እያየሁ ጠየቅኩት።
© hassed agape fiker
ይቀጥላል....
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️

👍69❤10👏3
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ሶስት:- ጠባቂ መልአክ(2)
“…ምንድን ነው?...” አይን እይኑን እያየሁ ጠየቅኩት
“…ዳሪክ ጋርዲያን ኤንጅሌ (ጠበቂ መልአኬ) ነው ትላለች። እንዴት እንደዛ ላስብና ላምን እንደቻልኩ ልነገርህ ስትለኝ በቁም ነገር ጊዜ ሰጥቺያት ሰምቺያት አላውቅም። አንቺ ደሞ ታበዢዋለሽ፣ ጓደኛሽ ነው፣ ትወጂዋለሽ በቃ ይኸው ነው እያልኩ እቀልድ ነበር።…”
ታዴ ትክ ብሎ አይን አይኔን እያየኝ በሃሳቡ እልም ብሎ ሄደ “….ግን ዳሪክ ያደረገውን ነገር ስመለከት፣ ያለችኝን አንድ ልጄን ህይወቷን ለማትረፍ ሲሸፍናት፣ ራሱን አሳልፎ ሲሰጥ ሳየው፣ ይህን ፍቅር ስመለከት ልጄ ሳሌም ትክክል ናት ብዬ አሰብኩኝ ። ምናልባትም ይህ ልጅ ለልጄ እንደ ጠባቂ መልአክ ነው የሆነላት ብዬ አመንኩኝ ። አስቢው እስኪ ዳሪክ ያደረገውን ባያደርግ ኖሮ እኮ፣ ባይሸፍናት፣ ባይጋርዳት፣ ባይቆምላት ኖሮ እኮ ይሄኔ የልጄን አስክሬን ይዤ ነበር ያለሁት…ዛሬ እኮ የሱ ልብ ቆሞ፣ የልጄ ልብ ትር…ትር የሚለው …እሱ ትንፋሽ አጥቶ የኔ ልጅ የምትተነፍሰው ዳሪክ በከፈለላት ዋጋ ነው።…” ታዴ እንባው በአይኑ ውስጥ ሞላ
እየታገለ ማውራቱን ቀጠለ “…እኔ እንኳን የወልድኳት አባቷ እንኳን ይህን ዳሪክ ያደረገውን መሰጠትና ፍቅር ለልጄ ማደረግ የምችል አይመስለኝም፣….” የአይኑን ከረጢቶች አልፎ እንባው ሲወርድ በእጁ ጠራረገ።
ጥቂት አረፈና ትንፋሹን ሰበሰበና “…ደሞ እኮ ስለዚህ መልካም ልጅ ዳሪክ የማውቀው ምንም ነገር የለም። እዚህ ሃገር እንዴት እንደመጣ፣ ዘመድ ቤተሰብ እንዳለው ራሱ አላውቅም። አንድ የማውቀው ነገር ልጄ ሳሌም አብዝታ እንደምትወደው ነው።…”
“…ሆስፒታል የመጣ ዘመድ ሰው የለውም?...” ደንግጬ ጠይቅኩኝ ከነበረው ሰው መካከል የዳሪክ ቤተሰብና ዘመድ ይኖራል ብዬ ነበር የጠበቅኩት።
“…አንድስ እንኳ የለም።…” ተክዞ መለሰልኝ “…አንዲት ነፍስ ሊጠይቀው አልመጣም። ለህክምናው መደረግ ያለበትን ነገር በሙሉ እንደ ወላጅ ወስኜ የፈረምኩት እኔው ነኝ።…
ያን ማድረጉ አልከፋም። ስለ ራሴ ልጅ ብዙ አውቃለሁ። ስለ ልጄ የልብ አፍቃሪ፣ ነፍሱን አሳልፎ ስኪሰጣት ደረስ ሰለወደዳት ስለዚህ ልጅ ምንም የማውቀው ነገር የለም። የማውቀው ከጥቂት አመታት በፊት እዚህ ሃገር መምጣቱን፣ ልጄን ደሞ በብዙ እንደምትወደውና እንደምታፍቀረው ።ይህን አውቃለሁ። እውቀቴ ይህ ነው።….”
“….ጊዜ ስላልሰጠኸውና ስላላውቅከው አትጸጸት…” አልኩት “…ለነገሩ ልጅህ ሳሌም ራሷ በሞትና በህይወት መካከል ሆና አንተ ስለ ዳሪክ ማሰብህ በራሱ መልካም ልብ እንዳለህ ያሳያል። ደሞ እኮ እነዚህ የፍቅር ርግቦች አይሞቱም። በእርግጠኝነት እልሃለሁ አይሞቱም። ልቤን የሞላው ይህ ነው። ርግቦቹ በህይወት ይኖራሉ።…”
ታዴ ደስ ብሎት ፈገግ ብሎ አየኝ “…እምነትሽ ይገርማል። ትልቅ ነው…”
እኔም ፈገግ አልኩኝ “…እኔ ራሴ እየገረመኝ ነው። እንዲህ አምኜ አላውቅም። የመጀመሪያዬ ነው። ግን አንድ ነገር አውቃለሁ። የነዚህ ፍቅር ርግቦች ፍቅር የሆነ ካፌ ውስጥ ድፍት ብሎ የሚቀር አይደለም። ገና ብዙዎቹን ያነጋግራል። ለብዙዎች ብርታት ይሆናል። በየቤቱ ይገባል። ፍቅራቸው ፈውስ ይሆናል። የሺዎችን ሙት ፍቅር ህይወት ይዘራበታል። እግዚአብሄር በዚህ መንገድ ውስጥ ሲያሳልፋቸው አላማ አለው።…”
ዝም ብሎ ለደቂቃዎች በእንግዳ መቀበያው መስኮት ውስጥ ብቅ ያለችውን ጸሐይ እያየ ቆየና ዞር አለ ወደ እኔ “…የፍቅር ርግቦች …..እንዴት ደስ የሚል ስም ነው የሰጠሻቸው ባክሽ?...”
ሳቅኩኝ። “…እኔና ጓደኞቼ እንደዛ ነበር የምንጠራቸው?...”
ሳቄ ታዴንም በደንብ ፈገግ አስደረገው። በዚህ የፈተና እለት ሁለታችንም ትንሽ የሳቅነው ….የተኮሳተረው ፊታችን የተፈታው፣ ፈገግ ያልነው አሁን ገና ነው።
ጥቂት ቆይቶም....
“…ልጅ ሳዬ…”
“…አቤት …”
“…አይገርምሽም?...”
“…ምኑ?...”
“…የሁለቱ ፍቅር። ማለቴ ….እነዚህ ሁለት ብላቴኖች እንዴት እንዲህ በንጽህና ሊፋቃሩ ቻሉ?...”
“…ይህ የኔም ጥያቄ ነው። አንድ ቀን ሁለቱንም ቁጭ አድርጌ የምጠይቃቸው ጥያቄ…”
እውነቴን ነበር። የዳሪክና ሳሌም መዋደድና ፍቅር ብዙ ያለተነካ፣ ያልሰማነው፣ ገና የምናየው ብዙ ታሪክ እንዳለው አምኛለሁ። ፍቅራቸው እንደ አንድ ታላቅ ግዙፍ ተራራ ነው። እኛም ያየነው ገና ከተራራው ላይ የወደቀችን ሽራፊ ጠጠር ነው።
ከዛ ዝም ተባባልን።
ዝም ስንል ..ቅድም የሰማሁትን በልቤ ማሰብ ጀመርኩኝ። ስለ ሳሌምና ዳሪክ። ሳሌም ዳሪክን በሰው መልክ ያለ ‘ጠባቂ መልአኬ’ ትለው ነበር።
ለአንዳንዶች ልጆች አሏቸው …
አንዳንዶች ወንድሞች አላቸው …
አንዳንዶች እህቶች አላቸው …
አንዳንዶች እናቶች አላቸው…
ጠባቂዬ፣ የሚቆሙልኝ የሚሏቸው….ጌታ በዚህ ምድር ስጦታ አድርጎ የሰጣቸው። ሳሌም ግን የተሰጣት ዳሪክ ነበር።
ሳሌምም ዳሪክን እንዲህ ትለዋለች … ‘ጠባቂ መልአኬ’...
የእውነትም በሰውነቱ...በስጋው፣ በአጥንቶቹ፣ በቆዳው ....ባለው ነገር ሁሉ ስኪከልላት ድረስ፣ ስኪጋርዳት ድረስ በሞትና በሳሌም መካከል ዳሪክ ቆሞ ነበር። ይህን ያህል ዳሪክ ለሳሌም ሆኗል።
ከምናቤ፣ ከሃሳቤ ባንንኩኝ። ከሃሳቤ ያወጣኝም የቀዶ ጥገናው በሮች መከፈታቸው ነበር።
ውሃ ሰማያዊ ጋውን የለበሱ፣ የቀዶ ጥገና ኮፍያና የፊት መሸፈኛ ያደረጉ ድክም ያላቸው ሃኪሞች ወጡና “…የሳሌምና የዳሪክ ቤተሰቦች..” ብለው ተጣሩ።
ታዴ ተነስቶ ወደ በሩ ሲጣደፍ
“…ልምጣ ታዴ?...” ጠይቅኩት።
ራሱን በአውንታ ሲነቀንቅልኝ ሳላመነታ ተከተልኩት።
ከእንግዳ መቀበያው ቀጥሎ ባለው የሃኪሞች ቢሮ ውስጥ አስገብተውን ተቀመጥን። ልቤ ከውስጤ የሚወጣ ያህል በድንጋጤና በፍርሃት ሲደልቅ ይሰማኛል።
ከሁለቱ ሃኪሞች አንደኛው መናገር ጀመረ። “…ሁለት ዜናዎች አሉኝ። አንዱ መልካም ነው። አንዱ ደግሞ መጥፎ ነው። ….”

👍54❤7🔥1
#ከእዳ_ወደ_የምን_እዳ?
#በእውቀቱ_ስዩም
ጋሻው አዳል የተባለ የምወደው የቆየ ዘፋኝ እንዲህ የምትል ዝነኛ ዘፈን አለችው፥
“ማለዳ ማለዳ
ማለዳ መጥተሽ
አይ ! እህህ
ማለዳ መጥተሽ
እኔን ሳታገኝ ትመለሻለሽ"
ዘፈኑን በሰማሁ ቁጥር ጋሻውን እንዲህ እለዋለሁ” አባ! በማለዳ የት ሄደህ ነው የማታገኝህ? ውስጥህ የበቀለውን ችግኝ ስታጠጣ አምሽተህ በዛው መንገድ ላይ የመሰረት ድንጋይ ተንተርሰህ አድረህ ነው?”
ሳስበው፥ ጋሻው ይህንን ዘፈን የዘፈነው ለፍቅረኛው ሳይሆን ለአበዳሪው ይመስለኛል፤ ብድር ስር ምን ትዝ አለኝ !ኢትዮጵያ ብድር መመለስ ከተሳናቸው አገሮች አንዷ ሆና እንደተመደበች ሰማችሁ አይደል? እምደንቅ እኮ ነው!
ባለፈው ያሜሪካው ያውሮፓ አበዳሪዎች ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ሀላፊ ጋር ተገናኝተው በጠረጴዛ ዙርያ እና በጠረጴዛ ስር ተወያይተው ነበር;
በቦታው ተገኝቼ እንደታዘብኩት ውይይቱ ይህንን ይመስላል፥
ያሜሪካው - እዳችንን መች ነው ምትከፍሉን?
የኢትዮጵያው- የምን እዳ?🤔
ያውሮፓው- በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዳበደርናችሁ ረሳችሁት እንዴ?
የኢትዮጵያው - ስራ ስለሚበዛ እንረሳለን!
የአሜሪካው - እስቲ መፎጋገሩን ትተን በግልጽ እናውራ፤ በኢኮኖሚ ደረጃ የት ላይ ነው የምትገኙት?
የኢትዮጵያው፤- ማለት?
የአውሮፓው ፤- እርሙን የበላ ድሀ ናችሁ ? ወይስ ቀን የሚወጣለት ድሀ ናችሁ?
የኢትዮጵያው - የሰው ሀብት አለን ! መቶ አምሳ ሚሊዮን ደርሰናል ! ጠባይ ካላችሁ አምሳ ሚሊዮኑን ህዝብ ልንለግሳችሁ እንችላለን !
የአሜሪካው - እያወራን ያለነው ስለገንዘብ ነው !
የኢትዮጵያው - እንዳታባክኑት እኛው ጋ ይቀመጥላችሁ ብለን ነው እንጂ ገንዘቡም ቢሆን አለ!
የአውሮፓው- ሌላው ቢቀር ወለዱን ክፈሉን
የኢትዮጵያው- ለጊዜው አይርወለድ እንጂ ወለድ አላዘጋጅንም!
የአሜሪካው-- ሌላ ምን መፍትሄ ይኖራል?
የኢትዮጵያው-- ጥቂት የእፎይታ ጊዜ ስጡን!
ያውሮፓው --ምን ያህል ጊዜ?
የኢትዮጵያው- ትንሽ አምሳ አመት ብትታገሱን
ያውሮፓው- በአምሳ አመት ጊዜ ውስጥ ብድሩን የምትከፍሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ትደርሳላችሁ?
የኢትዮጵያው--አይ እናንተ ብድሩን የማትፈልጉበት ደረጃ ትደርሳላችሁ’
የአሜሪካው -- ከዛሬ ጀምሮ ከዛምቢያ እና ከጋና ቀጥሎ መበደር ከማይችሉ አገሮች ጎን ተመድባችሁዋል!
የኢትዮጵያው- ይህንን ጨካኝ ርምጃ ዝም ብለን አናየውም 🙁🙁
የአውሮፓው- ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ?
የኢትዮጵያው---ብድር የተነፈጉ አገሮች ማህበር መስርተን እንታገላለን !
የአሜሪካው- እናያለን !
እዚህ ላይ፥ የኢትዮጵያው በንዴት ተሰናብቶ ከሄደ በሁዋላ እንደገና ተመልሶ መጣና ፥
“አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ነበረኝ ! “ አለ፤
ሁለቱ ሀያላን - ምንድነው?
የኢትዮጵያው፤-
“ዛምቢያን አስይዘን መበደር አንችልም?”
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍44😁33❤11👎2🥰1👏1
#አባሮሽ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
አብረን ያየን ሰው ሁሉ “አፈስሽ አፈስሽ” እያለ ያወራል፡፡
ቆንጀ ፣ ሎጋ፣ ረጋ ያለና ዝምተኛ ነው፡፡ የወንድ ልጅ አማላይነት
የተሠራው ከእነዚህ ተንኮለኛ ንጥረ ነገሮች አይደል?
በፍቅር መውደቅ ከገደል እንደመውደቅ ያማል? በፍቅር መያዝ
እንደ ተስቦ ያማቅቃል?
አዎ፡፡ ቢሆንም እያመመኝ እወደዋለሁ፡፡ እየማቀቅኩ አፈቅረዋለሁ፡፡
እኔ እወደዋለሁ ፤ እሱ ግን እንደ ሁሉም ሰው በግብረ ሥጋ ሳይሆን
ከመላእክት ተዳቅሎ እንደተፈጠረ ይለጠጥብኛል፡፡ ይንበላጠጥብኛል፡፡
ቢሆንም ስሜቴ ለእርሱ ባሪያ ነው፡፡ ሲያወድሰኝ ብቻ የማብብ -
ሲኮንነኝ የምጠወልግ ፤ ሲመለከተኝ የማምር - ፊቱን ሲያዞርብኝ
የማስቀይም፤ እስከሚመስለኝ ድረስ እወደዋለሁ፡፡
ይሄን ዐውቃለሁ፤ ፍቅሬ አቅብጦታል፡፡ መውደዴ አቀማጥሎታል፡፡
ብዙ ጊዜ ደህና ስንጫወት እንውልና በድንገት ያኮርፈኛል፡፡
ይኮፈሳል፡፡ ዐይኔን ማየት ይጠላል፡፡ ያን ጊዜ ሁሉ ነገር
ይዞርብኛል፡፡ ሣቄ ይከስማል። የልቤ ሱረቃ በሐዘን አታሞ ይተካል፡፡
ይገርመኛል፡፡ በስሜቴ ላይ እንዲህ እንዲሰለጥን ከመፍቀዴ በፊት ፤
እሱን ከማግኘቴ በፊት፤ በምን ነበር የምቀው? በምንስ ነበር የምደሰተው?
“ምን ሆንክብኝ?” እለዋለሁ፡፡ ልክ እንደዚያ ሲሠራው::
“ምንም አልሆንኩም.. ተይኝ ላንብብበት።” ለዚህች ለዚህች ጊዜ
ተዘጋጅታ የምትቀመጥ፣ መዥረጥ አድርጎ የሚያወጣት .
የዘወትር መልሱ ናት፡፡
"ኤሊ..."
“እ...” (ከልቡ ሳይሆን)
“ሻይ በጦስኝ ላፍሳልህ?”
(ሻይ በጦስኝ ስለሚወድ)
“አልፈልግም”
“ፍሬንድስን ልክፈትልህ?” (ፍሬንድስን አይቶ ስለማይጠግብ)
“አላሰኘኝም”
“ቶሎ ሃያ ሁለት ሄጄ የፀሐይን ሽሮ ይዤልህ ልምጣ?” (ከትግሬ ሽሮ ሌላ በዓለም ላይ ደህና ምግብ ያለ ስለማይመስለው)
“አልራበኝም...”
“እሺ ምንድነው ምትፈልገው?»
“ተይኝ ላንብብበት...”
ይሄኔ ነው፣ የአዳም ረታን አንዱን መጽሐፍ አውጥቶ ጥሎኝ
የሚሄደው፡፡ ይሄኔ ነው፣ የራሱን ክብ ዓለም ፈጥሮ አንዱን መጽሐፍ አውጥቶ ጥሎኝ አፈናጥሮ የሚያስወጣኝ።ያን ጊዜ ማውራት መቀጠሌ ለሬሳ መድኀኒት ከመስጠት እንደማይለይ ስለማውቅ ጥዬው ለመሄድ እሰናዳለሁ፡፡
መጽሐፉ ላይ ተተክሎ አንዴ የላዘዘ ፈገግታ ሲያሳይ፣ አንዴ ጮህ ብሎ ሲስቅ
ከዚያ እንደማልቀስ ሲሠራው፤ በእሱ ስሜት ላይ
በሠለጠነው ብቸኛው ሰው አዳም ረታ እቀናለሁ፡፡ አንዳንዴም የምወደውን ልጅ ስለነጠቀኝ እያልጎመጎምኩ በልቤ እረግመዋለሁ፡፡
“ብዕርህ ይንጠፍ... እጅህን ቁርጥማት ይዘዝበት...” ዓይነት ነገር፡፡
“ልሄድ ነው ቻው” እለዋለሁ፣ ጫማዬን አጥልቄ ስጨርስ፡፡
እሺ... ቻው...” ይለኛል ቦግ ቦግ ያሉ ዐይኖቹን ከመጽሐፉ
ሳይለይ፡፡ ስሜቱን ከአዳም ረታ ገጸ ባሕርያት ሳያላቅቅ፡፡
ያን ጊዜ ከእንባዬ እየታገልኩ ወደ ቤቴ!
።።።።።።።።።
ስምንት ወር አብረን ስንወጣ፤ “ስንተኛ ስንነሳ” ፤ ስንገባ፣ ስንወጣ
ብረት አሎሎ ልቡን አልፈታልኝም፡፡ ስለ አለፈ ሕይወቱ አይነግረኝም፡፡ ስለወደፊቱ አያወራኝም፡፡ ከቤተሰብ - ጓደኛ
አያስተዋውቀኝም፡፡
እየቆየ የትርፍ ሰዓት ሥራው መሆኔ ሲገለጽልኝ፣ ጭምቷ ልጅ
ላብድ ደረስኩ፡፡ ተዉኩት ስል እያገረሽ በሚያስቸግረኝ አስቀያሚ
ፍቅሩ ብሸነፍም ቁርጤን ማወቅ እንዳለብኝ አመንኩ፡፡
አንዱን ቅዳሜ ስገሰግስ ቤቱ ደረስኩ። ከሰዐት ዘጠኝ ሰዐት ቢሆንም፣
አብዝቶ የሚለብሰውን፣ እህቱ ከካናዳ የላከችለትን ፒጃማ አድርጎ
ሶፋው ላይ ተጋደም ያነባል፡፡ ማንን? ያንን በየዓመቱ መጽሐፍ የሚያመርተውን አዳም ረታ፡፡
“ስማ ኤልያስ...? እኔ እንደዚህ መቀጠል አልችልም... ማውራት
አለብን...” አልኩ፣ ቦርሳዬን አንዱ ሶፋ ላይ ወርውሬ አጠገቡ
እየተቀመጥኩ፡፡
.
“እ... ?” አለኝ፣ መጸሐፉን ሳይዘጋ ቀና ብሎ እያየኝ፡፡
“ኣመልህ ሊገባኝ አልቻለም... እኔ እወድሃለሁ... ግን የማትወደኝ
ከሆነ... ማለቴ ልብህን የማትሰጠኝ ከሆነ...”
ሳልጨርስ አቋረጠኝ፡፡
“ምንድነው የምትፈልጊው?” ተናዶም በማይለወጠው እርጋታና ግዴለሽነቱ ጠየቀኝ፡፡
.
መጽሐፉን ዘጋ፡፡ ጉዳዩ “ሲሪየስ" ነው!
“እኔ?”
“አዎ አንቺ...! ምንድነው የምትፈልጊው?”
ምንድነው የምፈልገው? እንዴትስ ብዬ ነው የምጠይቀው...?
ከአንጀቱ - እንዲህ በትኩረት እያየኝ ይጠይቀኛል ብዬ አስቤ
ስለማላውቅ፣ እያሰብኩ ያንን ውብ ፊቱን አየሁት፡፡
ጢሙ እንደምወደው አድጓል፡፡ ጠጉሩ ጨብረር ብሏል፡፡ መከረኛ
ቢጃማው እጅጌና አንገቱ ጋር መንችኳል፡፡
ብም ብሎ ያየኛል፡፡ ብዙ ጊዜ ይሄን ያህል ጊዜ ሰጥቶ አያየኝም፡፡
አንሶላ መሀል ገብተን ወንድና ሴት . ድርና ማግ ስንሆን እንኳን፣
እያስበው ዐይኖቹን በዐይኖቼ ስይዘው፣ ዐይኖቹ ላይ ትኩረትና ፍቅር
አላይም፡፡ አንዳንዴ እንደውም ውስጤ መቆየት የሰለቸው... ገላዬ
ውስጥ ዘለዓለም የከረመ ያህል፣ የታከተው የሚመስል ነገር ዐይኖቹ
ላይ አነባለሁ፡፡
እንዲህ ዐይቶኝ አያውቅም፡፡
በማውራት ይሄን ያልተለመደ ክስተት ላቋርጥና ላበላሽ ስላልፈለግኩ፣ ካለሁበት ሶፋ እየተሳብኩ ተጠጋሁት፡ ማየቱን ቀጥሏል፡፡ ደርሼ አንገቴን አንገቱ ውስጥ ቀብሬ በጥልቀት
አሽተትኩት፡፡ ጦስኝ ጦስኝ ይላል፡፡ የምወደው ልጅ በጦስኝ፡፡ልቤ እንደሰም ሲቀልጥ፣ መንፈሴ በስሜት ማዕበል ሲታመስ እንኳን፤ የማወራው የማስበው ነገር ከአንጎሌ ሲተን...
“እህስ ምንድነው የምትፈልጊው?” አለኝ፣ ከአንገቱ ውስጥ በእጁ ጎትቶ እያወጣኝ፡፡
“ምንም...”
“ምንም አትፈልጊም?”
“ኤሊ... እንድትወደኝ... እንድትወደኝ ነው የምፈልገው:: ይከብዳል?” ወደ ኣንገቱ ሥር ተመልሼ ልወሽቅ ስል፣ አሁንም
መልሶ አወጣኝና በእነዚያ አሸባሪ ዐይኖቹ እያየኝ..
“መች ጠላሁሽ...?” አለኝ፡፡
"እንደማትጠላኝ ዐውቃለሁ... ግን አንድ ቀን እወድሻለሁ ብለኸኝ አታውቅም፡፡ እ... ከመሬት ተነስተህ ታኮርፈኛለህ:
ታበሻቅጠኛለህ."
“ምንድነው የምትፈልጊው? በሥርዓት ቁጭ ብለን ይሄን ነገር
እንቋጨው...” አለኝ፡፡ ለስብሰባ እንደተቀመጠ ሰው መጽሐፉን
እንደተከፈተ ሶፋው ላይ አስቀምጦ፤ እጆቹን አጣምሮ፡፡ .
ቀና ብዬ ተቀመጥኩ፡፡
“ልብህን... ልብህን ነው የምፈልገው፡፡”
እጆቹን አመሳቀለና ሣቀ፡፡
ተበሳጨሁ፡፡
“ያስቃል?”
“ሃሃ... አዎ... እዚህ መጽሐፍ ላይ ያለው... አንዱ የአዳም ካራክተር' ምን አለ መሰለሽ... ልቤን ለሴት ከምስጥ ለጎረቤት ድመት ብሰጥ ይሻለኛል...”
ዝም ብዬ ዐየሁት፡፡
“ምን ታይኛለሽ... ካ'ንጀቴ እኮ ነው እውነቴን ነው፡፡”
አሁንም ዝም ብዬ ዐየሁት...
ጨረስን? ወደ መጽሐፌ ልመለስ?”
እየቀለድክ አይመስለኝም።
አልኩ፣ | በተቀመጥኩበት እየተቁነጠነጥኩ፡፡
“አይደለም አልኩሽ እኮ...”
“የአንድ ሥራ ፈት ደራሲ ተረት ተረት እና ቅዥት እያነበብክ
የእኛን ሕይወት ማበላሸት አለብህ?”
“አዳም ስለማይገባሽ አልፈርድብሽም...”
“እሱን ተወው... ዝባዝንኬ አይገባኝም... ድመት ምናምን...ሰውየው የሚያወራውን አያውቀው ... ግን አንተ ምነው ለልብህ
እንደዚህ ሣሣህ? ልብህን ስጥተኸው የጎዳህ ሰው ነበር እንዴ?”
እየተቁለጨለጭኩ ተጠየቅኩት፡፡
ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆየና...
“ለምን ጦስኝ ሻይ አታፈይልኝም?
ጠዋት የጠጣሁ ነኝ” አለኝ፣
መጽሐፉን እያነሳ..
“ለምን አትመልስልኝም...?
ለምንድነው እንደዚህ ፍቅርን የምትፈራው?”
“በናትሽ ሻዩን... እያዛጋኝ ነው...”
የምናብ ደጁ ሊዘጋብኝ ነው። ለዛሬ

👍60❤11👏2😁1
ከዚህ በላይ ሊያናግረኝ
አልፈቀደም፡፡ ለሻዩ ወደ ኩሽና መንገድ ጀመርኩና መለስ ብዬ ዐየሁት
“ኤሊ...”
“እ...?” (ከልቡ ሳይሆን)
“ልቤን ለሴት ከምሰጥ፤ ለድመት ብሰጥ ይሻለኛል ነው ያልከኝ አይደል..?”
“እ...አዎ...”
የኩሽና መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ሻይ ጀበናውን በውሃ ሞልቼ ምድጃው
ላይ ጣድኩ፡፡ ጦስኙን አዘጋጀሁ፡፡
ኤልዬ... የምወደው ልጅ እንዲወደኝ....
የእሱን ልብ እንዳገኝ ሰውነቱ ቀርቶብኝ፤ ምነው ለአንዲት ቀን ድመት ቢያደርገኝ?
የማፈቅረው ልጅ መልሶ እንዲያፈቅረኝ፤ ምነው ለአንድ ሌት
ሚያው ባስባለኝ?
ሚያው....
ሚያው....
💫አለቀ💫
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
አልፈቀደም፡፡ ለሻዩ ወደ ኩሽና መንገድ ጀመርኩና መለስ ብዬ ዐየሁት
“ኤሊ...”
“እ...?” (ከልቡ ሳይሆን)
“ልቤን ለሴት ከምሰጥ፤ ለድመት ብሰጥ ይሻለኛል ነው ያልከኝ አይደል..?”
“እ...አዎ...”
የኩሽና መንገዴን ቀጠልኩ፡፡ ሻይ ጀበናውን በውሃ ሞልቼ ምድጃው
ላይ ጣድኩ፡፡ ጦስኙን አዘጋጀሁ፡፡
ኤልዬ... የምወደው ልጅ እንዲወደኝ....
የእሱን ልብ እንዳገኝ ሰውነቱ ቀርቶብኝ፤ ምነው ለአንዲት ቀን ድመት ቢያደርገኝ?
የማፈቅረው ልጅ መልሶ እንዲያፈቅረኝ፤ ምነው ለአንድ ሌት
ሚያው ባስባለኝ?
ሚያው....
ሚያው....
💫አለቀ💫
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍47❤12👎8😢5😁3
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አራት፦ ትንሹ ተዐምር (1)
“..ይሄኛው ምንድን ነው?...” እኔ እጠይቃለሁ
“…ይህ ቼስት ቲዩብ (Chest Tube) ነው። በደረቱ አካባቢ የተከማቸውን የፈሰሰ ደም ለማስወገድ ይረዳዋል። …”
“…ይሄኛውስ?...” በአጠገቡ ያለውን በዝግታ የሚጮህ ማሽን ፣ከማሽኑ ተያይዞ የሚሄድ ሌላ ሰፋ ያለ ትቦ፣ አፉ ላይ ሄዶ ይገጥማል።
“ …ይሄ ሰው ሰራሽ ቬንትሌተር (Vent) ነው። በሳንባው ቦታ ሆኖ ለመተንፈስ ያግዘዋል። በአሁን ሰዐት ሙሉ በሙሉ በሰው ሰራሽ የመተንፈሻ ትቦዎች ነው እየተነፈሰ ያለው።….”
ውስጤ በሃዘን ስብርብር ብሎ ደሞ ጥያቄዬን እቀጥላለሁ። “...እነዚህስ?...” ሌሎች ከጀርባው አካባቢ የሚወጡ ቀጫጭን ቱቦዎች።
“... እነሱ ደሞ ከሰርጀሪው ቁስሎችና ስፌት ስፍራ የሚወጡትን ሌሎች አላስፈላጊ ፈሳሾች መጦ ለማወጣት የተሰኩ ናቸው።…”
ይህ በኔና በዳሪክ ሃኪም መከካል እየተደረገ ያለ ንግግር ነው። እኔ እጠይቃለሁ። የዳሪክ ዋና ሃኪም በትህትና በሚገባኝ ቋንቋ ሳይሰለቸው ያስረዳል።
….ጥቅጥቅ ያለ ጥቁር ከርዳዳ ጸጉር፣ ጠይም ረዘም ያለ ፊትና ሳቅ፣ ሳቅና ደሞ ሌላ ሳቅ… ይሄ ደሞ ዳሪክ ነው።
አሁን ግን ይህ ዳሪክ የለም። ይህ ዳሪክ ነበር። አሁን እሱን፣ ዳሪክን የሚመስል አንድም ነገር የለም። ጸጉሩ ሙሉ በሙሉ ተላጭቷል። ጭንቅላቱ ሙሉ በሙሉ በፋሻ ተጠቅልሏል። በሰውነቱ ውስጥ ያልገባ አይነት የህክምና ትዩብ የለም። ለመተንፈስ ጎማ የመሰለ ቱቦ፣ በደረቱ ላይ የተጠራቀመ ፈሳሽ የሚያወጣ ሌላ ፣ ሰርጀሪ ከተደረገበት የጀርባው የተለያዩ የሚወጡ ሌሎች ቀጫጭን ቱዩብስ … የተለያየ ፈሳሽ፣ እንዲሁም ያጣውን ደም እየተተካ ያለበት አይ ቪ (Intravenous) ሰውነቱ ላይ ተሰክተው፣ ግማሽ አካሉ በተለያዩ ድሬሴንጎች ተጠቅልሎ በቃ ዳሪክ ዳሪክን አይመስልም። እጅግ በጣም እጅግ ያሳዝናል። …በጉልበት፣ በስቃይ አየር ይስባል። ደሞ አረፍ ይላል። የጭንቁን እንደገና ይስባል። ለመተንፈስ የሚረዳው ቬንትሌተር ማሽን ቢኖርም ከፍተኛ ህመም እንዳለው ያስታውቃል።
… ደስ የሚሉ ትላልቅ አይኖች፣ ቀይ እንቡጥ የመሰሉ ከናፍርት፣ ጽድትና ጸጥ ብሎ ጸጥ ያለ ፊት ሳሌም ናት።
ሳሌምም እንዲህ ነበረች። አሁን ግን ሳሌምና የሳሌም መልክ የለችም። ቀይ ፊቷ ከህመሙ ብዛት ጠቁሯል። ትላልቅ አይኖቿ ተከድነዋል። ውብ ከንፈሮቿ ከሰል መስለው ደርቀዋል። ለሳሌምም ….ቼስት ትዩብ በቀኝ በኩል ተገጥሞላታል፣ ደምና የተለያዩ አይ ቪ (IV) ፈሳሾች፣ የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ያለ ማቋረጥ እየተሰጣት ነው።
ሁለቱንም ለመጀመሪያ ጊዜ ለማየት እድሉን ሳገኝ ያየሁት ይህንን ነው። በአካላዊ ሁኔታቸው ዳሪክና ሳሌም ተለውጠዋል። ፈጽሞ የሉም። እነዛ ፍቅር ብቻ ሲፈስባቸው የሚታዩ፣ ፍቅር ፍቅር የሚሉ፣ የፍቅርን መዐዛ ለሁላችን የሚያቋድሱ የፍቅር ልጆች፣ ሰላምን ብቻ የሚያውቁ ሰላማዊ ታዳጊዎች … ከህመምና ከስቃይ በቀር ፊታቸው ላይ የማይታይባቸው ሳሌምንም ዳሪክንም የማይመስሉ ሌሎች ልጆች ሆነዋል።
አየሩ የማይበቃቸው የሚመስሉኝ የፍቅር ርግቦች፣ ህዋው ተንሳፈውበት የሚያጥራቸው ሚመስሉኝ የመውደድ ከዋክብት በነዚህ ትንናሽ የሆስፒታል ክፍሎች ውስጥ በብዙ ቱቦዎች ተይዘው፣ የህክምና መሳሪያዎች ተሰካክቶባቸው፣ በፋሻዎች ተጠቅልለው አሉ።
አሁን ….
ጥላቻ ደረቱ አብጧል።
ፍቅር አጎንብሷል።
ጥላቻ ይስቃል።
የፍቅር አይን እንባ አቅርሯል።
ሳያቸው በአይኔ ውስጥ እንባ መሙላቱ አልቀረም። ሃዘን፣ እልህ፣ ንዴት፣ ቁጭት የተደባላለቀ የነዚህ ሁሉ ስሜት በውስጤ ሲመላለስና ልቤ “…ጮኺ … አልቅሽ …” ሲለኝ ይሰማኛል። የማይጮሁበት ሁኔታና ቦታ ሆነ እንጂ።
…. ከቀዶ ጥገናው ቡሃላ … ከሁለቱ ሃኪሞች አጠር ያለ ሪፖርት ቡሃላ …ዳሪክና ሳሌምን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማግኘት እድሉን ሳገኝ እያየሁ የነበረው ነገር ይህን ነው። የተሰማኝም ስሜት ይኸው ከላይ እንደተጠቀሰው።
ከስላሳ ደቂቃ በፊት እንዲህ ነበር ሃኪሙ ያለው።
“…ሁለት ዜናዎች አሉኝ። አንዱ መልካም ነው። አንዱ ደግሞ መጥፎ ነው። …።”
አይናችንን በድንጋጤ ከመፍጠጡ በስተቀር እንደ በድን ፊት ለፊቱ ቁጭ ያልነውን ታዴንና እኔን አየና ቀጠለ “…መልካሙ ዜና የሁለቱንም ህይወት ለጊዜው ማትረፍ መቻላችን ነው። በተለይ ሳሌም በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው። ሁኔታዋ በሙሉ ተስፋ የሚሰጥ ነው።…”
ጎሮሮን አጸዳዳና ቀጠለ ሃኪሙ “…መጥፎ ዜና ብለን ደሞ ልንናገር የምንችለው የዳሪክ ሁኔታ ነው። እውነቱን ለመናገር ከነበረበትና ካለበት ሁኔታ አንጻር ህይወቱ ራሱ መትረፉ ተዐምር ነው። እንደ ሃኪምነታችን ተዐምር ብዙም አያጋጥመንም። የዚህ ልጅ ሁኔታና የመትረፉ ሚስጥር ግን ተዐምር ነው ለማለት እደፍራለሁ። አይደለም እንዴ?...” ሲል ወደ ሌላኛው ሃኪም ዞሮ
ጠየቀው።
“…እስማማለሁ…” ሌላኛው ሃኪም መለሰ “…በጣም ብርቱ ልጅ ነው። አልሞትም ብሎ የሚታገል ነው የሚመስለው። ኦፕራሲዮን እየተደረገ ለሶስት ጊዜ ያህል ልቡ ቆሞ ነበር። በተለይ ለሶስተኛ ጊዜ ልቡ መምታት ሲያቆም የመጨረሻው መጨረሻ ነበር የሚመስለው። ከሰላሳ አምስት ደቂቃ በላይ ሲፒአር (CPR) ተስጥቶት በብዙ ትግል ነው ልንመልሰው የቻልነው።….”
“…የሆኖ ሆኖ …” የመጀመሪያው ሃኪም ነበር “….የሆነ ሆኖ ህይወቱ ተርፏል። ዛሬን አብሮን አለ። ግን የወደፊቱን ስናስብ የምናየው ነገር አስቸጋሪ ነው።…” ሃኪሙ የሚቀጥለውን ነገር ለመናገር የፈራ ይመስል ለአፍታ ንግግሩን ቆም አደረገ።
“…ምኑ ነው አስቸጋሪ? ምኑ ነው መጥፎ ዜና … ንገሩኝ?...” እስካሁን ዝም ብሎ ሲያድምጥ የነበረው ታዴ ነበር በድንጋጤ የጠየቀው
*

👍41❤8
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
....‹‹እምትገርሚ ነሽ፡፡ እንደምታውቂው አንድ ዓመት ሙሉ አንድ ቤት አብረን ሠርተናል፡፡ ምርጥ ጓደኛሞችም የነበርን ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ያህል ደደብ ኖሬያለሁ፡፡ በእውነት በራሴ አፍሬያለሁ፡፡ እኔ እኮ ስለራሴ አንድም ሚስጥር ሳልሸሽግ ነበር ዘርግፌ የምነግርሽ፡፡.....
ለማንኛውም ስታጃጅይን የኖርሽ መስሎ ስለተሰማኝ ትንሽ እንደተቀየምኩሽ ልደብቅሽ አልፈልግም፡፡ ቢሆንም በስራሽና በእውነተኛ ማንነትሽ በጣም ኮርቼብሻለሁ፡፡
እኛን በተመለከተ የሠራሻቸው ስዕሎች ኖረሽ ያየሻቸው የእውነተኛ ገጠመኞችሽ ውጤት በመሆናቸው ሕያው ናቸው፡፡ ውስጤንም ነክተውኛል፡፡ ብቻ ብዙ ማውራት ፈልጌ ነበር ግን ድብልቅልቅ ያለ ስሜት እየተሰማኝ ስለሆነ አልቻልኩም፡፡ በአጠቃላይ ድንቅ ነሽ፡፡ በቅርብ ታላቅ ሠዓሊ እንደምትሆኘ እርግጠኛ ነኝ፡፡››
ሌላዋ ሴት..
‹‹... እማዬ ትሙት ስላስገደድሽኝ እንጂ እኔ መፃፍ አይሆንልኝም፡፡ ስለ ሥዕል ብዙም ባላውቅም ሥዕሎችሽ የሚያምሩ ይመስለኛል፡፡ ግን አይገቡም ወይም እኔ ደደብ ስለሆንኩ ይሆናል፡፡ ውይ በእማዬ ሞት በቃ አንድ ቀን በርጫ ይዤ መጥቼ ከመረቀንኩ በኋላ የተሠማኝን በቀላሉ አወራልሻለሁ፡፡ ግን እማዬ ትሙት የዛን ቀንም በፅሁፍ እንዳትይኝ፡፡ ከፈለግሽ ስናገር መቅዳት ትቺያለሽ፡፡››
ሠለሞን...
‹‹ካየሁሽ ቀን ጀምሮ ተራ ሴት አለመሆንሽን
እንደለፈለፍኩ ነው፡፡ ይሄ ደደብ ጓደኛሽ እንኳን
አያደምጠኝም ነበር፡፡ አንዳንዴ ደራሲ...ሌላ
ጊዜ ደግሞ ወሮበላ...አልፎ አልፎ ደግሞ ከፍልስፍና ት ቤት በመመረቂያ ወቅት
የተባረርሽ ተማሪ ትመስይኝ ነበር፡፡ ይሄንን ለማጣራት ሠላይ ሁሉ ቀጥሬ ላሠልልሽ ያሰብኩበት ጊዜም ነበር፡፡በኋላ ምን
አስጨነቀኝ ብዬ ተውኩት፡፡ ግን እግዚአብሔር ቸር ነው፡፡ በቀኑ ባላሰብኩት ሁኔታ ገለፀልኝ፡፡ ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ ልግባና ስለ ሥዕሎችሽ ትንሽ ላውራሽ ... እንደውም ምንም አላወራሽም፡፡ ብቻ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ኤግዚብሽን እንድታዘጋጂ እፈልጋለሁ፡፡ ወጪው ጠቅላላ እስፖንሰር እምሆንሽ እኔ ነኝ፡፡ ጠቅላላ ሴቶች ትርኪ ምርኪ ነገር
ሲከውኑ ዕድሜያቸውን የሚያበክኑ አድርጌ
እቆጥር ነበር፡፡ ለካ እንዳንቺ አይነቷ ከወንድ የምታስንቅ ጀግና ከጎኔ ኖራለች፡፡ እታች ሸለቆ ውስጥ አዘቅዝቄ ስመለከትሽ እላይ ከጨረቃ ጎን ተንሳፍፈሽ አገኘሁሽ፡፡ የኤግዚብሽኑን ነገር እንዳትረሺ፡፡ በአገሪቱ ላይ ስምሽ እንዲነግስ እፈልጋለሁ፡፡ ጋዜጠኞች አንቺን ለማነጋገር እና ታሪክሽን ለመፃፍ ሲተረማመሱ ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ድንቅ ነሽ!፡፡››
ሁሴን...
‹‹ደደብነቴ እንደዛሬ ፍንትው ብሎ ተገልፆልኝ አያውቅም፡፡ በከፍተኛ ጥረት የሠበሠብኳቸው ሁለት ዲግሪዎች ባዶ ሆነው ታዩኝ፡፡ ታውሬ ነበር ማለት ነው፡፡ በእኔ ጅልነት አጠገቤ ያሉ ነገሮች ሚስጥር ሆነው ሲቆዩብኝ እበሽቃለሁ፡፡
ለነገሩ አንዳንድ ጊዜ አጠገብሽ ካለ ነገር ይልቅ
እሩቅ ስላለ ነገር የበለጠ ዕውቀት ይኖርሻል፡፡
ምናልባት እንዲህ የታወርኩት በዛች ድብቅ
ደራሲ የተነሳ ይሆናል፡፡ ውስጤን ተቆጣጥራዋለች፡፡ የማሰብ አቅሜም ተዳክሟል፡፡ ለማንኛውም ፍቃደኛ ከሆንሽ ስለ
ሕይወትሽ ታሪክ፣ስለ ስራዎችሽ እናም ስለ አጠቃላይ ማንነትሽ ተከታታይ ታሪክ በጋዜጣዬ ላይ መፃፍ እፈልጋለሁ፡፡ የፈለግሽውን ያህል ብር ልከፍልሽ ፍቃደኛ ነኝ፡፡ ስዕሎችሽን በተመለከተ አድናቆቴን በቃላት ልገልፅልሽ ያዳግተኛል፡፡ግን አንድ ውለታ እንድትውይልኝ እፈልጋለሁ፡፡ የደራሲዋን ስዕል ሳይልኝ፡፡ በተለያየ ጊዜ ስለሷ የማውቀውን ሁሉ ነግሬሻለሁ፡፡ባንቺ ምናብ ምን እንደምትመስል ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ቢያንስ መፅናኛ ይሆነኛል፡፡ ለማንኛውም ለሊት ደውልሻለሁ፡፡ ላወራሽም እፈልጋለሁ፡፡ ያንቺው አክባሪና አፍቃሪ ነኝ፡፡››
ማስታወሻ ደብተሯን አሽቀንጥራ ወለሉ ላይ ወረወረችው፡፡ ‹‹ስሜት አልባ እመስለዋለሁ እንዴ?ዛሬም በዚች ልዩ ቀኔ ስለእኔ ምን እንደምታስብ ንገረኝ ስለው እሱ ምንም ሳያውቃት ስላፈቀራት ሴት ይደሰኩርልኛል? ለምንድነው ግን የሠው ልጅ ሲባል ካየነው ነገር ይልቅ ያላየነው ከዳሠስነው ይልቅ ያልነካነው ከአገኘነው ይልቅ ያጣነው ነገር ይበልጥ ዋጋ ያለው መስሎ የሚሠማን? በእጃችን ላይ ያለው እንቁ ለምን ድንጋይ መስሎ ይታየናል?፡፡ >> መዓት ጥያቄዎችን እራሷን ጠየቀች፡፡ መልስ ሳታገኝ እንቅልፍ ይዟት ጥርግ አለ፡፡
።።።።።።።።።
ሁሴን ዛሬ ቤቱ የገባው በጊዜ ነው፡፡ እራሱን በመጠኑ ስላመመው በእንቅልፍ እንዲያልፍለት ሳሎን ሶፋ ላይ ጋደም ቢልም እንቅልፍ ግን አልወሰደውም፡፡ሰሞኑን መደበት ውስጥ ተነክሯል፡፡እንዲሁ ምክንያቱ ባልገባው ነገር ይጨናነቃል..በማያበሳጭ ነገር ይበሳጫዋል፡፡ብቻ መላ ፀባዩ ቅይርይር ብሏል፡፡ፎዚያ ከጓዳ በር ብቅ አለች፡፡
‹‹ትምህርት ቤት አልሄድሽም እንዴ?››ጠየቃት፡፡
አትኩራ እያየችው‹‹ ዛሬ የለንም ..ምነው አንተ ጠቋቆርክ?››አለችው፡፡
‹‹ደህና ነኝ፡፡ ትንሽ ብቻ ተጫጭኖኛል፡፡››
‹‹ቡና ላፍላልህ?››
‹‹ስራ ከሌለሽ ደስ ይለኛል፡፡››
‹‹ኧረ የለኝም፡፡›› በማለት እየተንደረደረች ወደ ኩሺና ገባች፡፡
ሁሴን ስለ ፎዚያ ሲያስብ ይገርመዋል፡፡ አንድ ላይ መኖር ከጀመሩ ሦስት ዓመት አልፎአቸዋል፡፡ አንድም ቀን አስከፍታው ወይንም የማያስደስተውን ነገር ለመስራት ሞክራ አታውቅም፡፡ በመጀመሪያ የተገናኙበት አጋጣሚ ትዝ አለው፡፡ ትክክለኛ ቀኑንና ወሩን አያስታውሰውም ብቻ ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ቢሮ አምሽቶ ጨለምለም ሲል በዝግታ እየነዳ ወደ ቤቱ እያመራ ሳለ ሲጋራ አሠኘውና ኪሱን ቢዳብስ ማግኘት አልቻለም፡፡ መኪናውን ጥግ አሲዞ አቆመና ወደ ኪዎስክ ጎራ አለ... ሲጋራ፡፡ ገዝቶ ሲመለስ ግን ዓይኖቹ አንድ ነገር ላይ አረፉ፡፡ የመብራት ምሰሶ ስር አንድ የትምህርት ቤት ዩኒፎርም የለበሰች ልጅ እግር ወጣት ሴት ቁጭ ብላ ታለቅሳለች...ያረጀ ሻንጣ አጠገቧ አለ፡፡ ሻንጣው ላይ የተወሰኑ ደብተርና መጽሀፎች ይታያሉ፡፡ አልፏት እንዳይሄድ የሆነ የማያውቀው ስሜት ሰቅዞ ያዘው፤ አቅጣጫውን ቀየረና ወደእሷ በማምራት
ተጠጋት፡፡ ቀናም ብላ አላየችውም፡፡ እንባዋ በቀጥታ ከአይኖቿ ወደ መሬት ይንጠባጠባል.. ጠብታዎቹም ሲደጋገሙ መሬቱን እያጎደጎድት ነው..ጥቃቅን የብሶት ኩሬ እየፈጠሩ..፡፡
‹‹ምን ሆነሽ ነው የእኔ እህት?›› ጠየቃት፡፡
…ዓይኖቿን ወደ ላይ በልጥጣ ተመለከተችው፡፡
ጎንበስ አለና ቀኝ እጁን ትከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ‹‹ከቤት ተጣልተሽ ነው?›› ሁለተኛ ጥያቄ ጠየቃት፡፡
በደከመና በተጎተተ ድምፅ‹‹አ...ዎ›› ስትል መለሠችለት፡፡
‹‹ታዲያ ጎዳና ላይ ምን ትሠሪያለሽ? ጎረቤት ወይም ዘመድ ጋር ለምን አትሄጅም? ያስታርቁሻል፡፡››
‹‹ዘመድ የለኝም፡፡››
‹‹እናትና አባት ብቻ ነው ያለሽ?››
‹‹እናትም አባትም የለኝም፡፡ አንድ አክስት ብቻ ነበር ያለችኝ እሷው ነች ያ.ባ..ረ..ረ..›› ሳግ ስለተናነቃት ንግግሯን መቋጨት አልቻለችም፡፡ ከኪሱ ሶፍት አወጣና ፊቷ ላይ የተረጨ እንባዋን አበሠላት፡፡ ትንሽ ካረጋጋት በኋላ እጇን ይዞ አስነሳት፡፡ በጥርጣሬ እያየችው በዝግታ ተነስታ ቆመች፡፡
‹‹ይኸውልሽ አሁን መሽቷል፡፡ ለዛሬ እኔ ቤት ታድሪና ነገ የሚሆነውን ነገር እንነጋገራለን፡፡ በዚህ ሁኔታ ላይ የዱርዬ መጫወቻ እንድትሆኚ ጥዬሽ ልሄድ አልችልም፡፡››

👍97❤12😁6👎2
እንደተገተረች አፍጥጣ አየችው፡፡ ምን መወሠን እንዳለባትም ግራ ገብቷታል፡፡ የማታውቀውን ሠው ተከትላ መሄድ ጨነቃት፡፡ እምቢ ብላም ከጨለማው ጋር መፋጠጥም ይበልጥ አስጨናቂ ሆነባት፡፡
ሁሴን ፍራቻዋ ስለገባው ስለ ራሱ ያብራራላት ጀመር፡፡ ‹‹እኔ ሁሴን ሙሀመድ እባላለሁ፡፡ የፍኖተ ጥበብ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነኝ፡፡
ጋዜጣውን ታውቂዋለሽ ብዬ እገምታለሁ፡፡››በማለት መታወቂያውን አውጥቶ ዘረጋላት፡፡ አልተቀበለችውም.. አላየችውምም፡፡
‹‹አውቅኩህ፤ማለት በአጋጣሚ ጋዜጣው እጄ ሲገባ አንዳንዴም ከጓደኞቼ በመዋስ የማንበብ ዕድል ገጥሞኛል፡፡ በጣም የምወደው ጋዜጣ ነው፡፡ አሁን ጋዜጣው ላይ ያየሁት ፎቶም ትዝ አለኝ›› በማለት ጎንበስ ብላ ደብተሯንና መፅሀፍቿን አስተካክላ በቀኝ እጇ ይዛ በግራ እጇ ሻንጣዋን ልታነሳ ስትሞክር እሱ ቀደሟት አነሳውና ወደ መኪናው ጉዞ ጀመረ... ከኋላው ተከተለችው፡፡
ቀጥታ ወደ ቤት ከመሄዳቸው በፊት ወደ ሬስቶራንት ጎራ ብለው እራት በሉ፡፡ ስለተለያዩ ነገሮች እያወራት ትንሽ ዘና እንድትል ካደረጋት በኋላ ወደ ቤት ይዟት ገባ፡፡
ሳሎን አረፍ ብለው ትንሽ ካወሩ በኋላ …‹‹ለመሆኑ ስምሽ ማን ይባላል?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ፎዚያ
‹‹እሺ ፎዝያ..ደክሞሻል መሠለኝ፤ እዛ ጥግ የሚታይሽ ክፍል ገብተሸ ተኚ፡፡ ምንም ነገር አትፍሪ፡፡ እንደቤትሽ ቁጠሪው፡፡ ዘና በይ፡፡ የእኔ ክፍል ይሄኛው ነው፡፡ የምትፈልጊው ነገር ካለ አንኳክተሸ ልትጠይቂኝ ትችያለሽ፡፡ ሽንት ቤት ወይም ሻወር ከፈለግሽ ከክፍልሽ ፊት ለፊት ያለው ክፍል ነው፡፡ ምን እንዳጋጠመሽ ጥዋት በዝርዝር ትነግሪኛለሽ›› አላት፡፡እሷ ግን ይሄንን የታመቀ ብሦቷን ለሊቱን ሙሉ አፍና መቆየት አልፈለገችም፡፡ መተንፈስ፤ማውራት ፈልጋለች፡፡ እንኳን እንዲህ ችግሯን ሊረዳላት የሚችል ሠው አግኝታ ይቅርና እንሠማሻለን ካሏት ለግኡዞቹ ለጨረቃና ለከዋክብቶችም ብታወራላቸው ደስታዋ ነው፡፡
‹‹እኔ እንኳን አልደከመኝም፡፡ ከፈለክ አሁን ልነግርህ እችላለሁ፡፡ >> አለችው፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ ቀጥይ እኔም እንዳላጨናንቅሽ ብዬ ነው እንጂ ችግርሽን አሁኑኑ ብሠማ ደስ ይለኛል፡፡››
ማውራት ጀመረች ‹‹እናትና አባቴ ከአምስት አመት በፊት ነው በሚጓዙበት መኪና ላይ
በደረሠ የመገልበጥ አደጋ በአንድ ላይ የሞቱት፡፡ በወቅቱ የእናቴ ታናሽ እህት
የሆነችው ይህቺ አክስቴ እኛ ጋር ነበር የምትኖረው፡፡ ከእሷ በስተቀር ሌላ የሥጋ
ዘመድ አላውቅም፡፡ ስለዚህ ከእሷው ጋር አብሬ መኖር ቀጠልኩ፡፡ ወላጆቼ ከተወሠነ ቁሳቁስ እና ጥቂት ብሮች በስተቀር የረባ ነገር ጥለውልኝ አላለፉም፡፡ የምንኖርበትም ቤት እንኳን ሳይቀር የኪራይ ነበር፡፡ያው ያለንበትን ችግር ለመቋቋም ይመስለኛል ብዙም ሳይቆይ አክስቴ በዕድሜ በጣም የሚበልጣትን አንድ
አስተማሪ አገባች፡፡ይሄ አስተማሪ ይጠጣል፣ ያጨሳል፣ይረብሻል፣ ይደባደባል፡፡በቃ ፀባዩ መላ ቅጥ የሌለው ነው፡፡
ከቆይታ በኋላ ግን የእሱ ብቻ ሳይሆን የእሷም ፀባይ እየተበላሸ መጣ፡፡ በተለይ ልጆች ከተወለዱ በኋላ በጣም ትጨክንብኝ ጀመር...
ስቃዬ በዛ፡፡ ትምህርት ቤት ከምሄድበት ቀን ይልቅ የማልሄድበት ይበልጥ ጀመር፡፡ የልጆቹን ልብስ አጥባለሁ፣ለቤተሰብ ምግብ አበስላለሁ፣ቤት አፀዳለሁ፤ የማልሠራው ስራ የለም፡፡ እንዲያም ሆኖ ሠላም የለኝም፡፡
ከስድስት ወር ወዲህ ደግሞ ነገሮች በጣም እየከፉብኝ መጡ፡፡ የአክስቴ ባል አዲስ ፀባይ አመጣ፤ የአክስቴን ወጣ ማለት እየጠበቀ መቀመጫዬን ይመታኛል፣ጡቴን ሳላስበው ጨምቆ ያስለቅሰኛል ፤ ፀያፍ ቃላቶች ይናገረኝ ጀመር፣በቃ ጣሬን አበዛው፡፡ ምን ልሁን ለአክስቴ እንዳልነግራት ምን ብዬ፡፡
በኋላ እያደፈጠ ሊደፍረኝ መሞከር ጀመረ፡፡ ሁለት ሦስት ቀን በመከራ አመለጥኩት፡፡ የዛሬውም ችግር መነሻው ይሄው ነበር፡፡ አስራ አንድ ሠዓት ከትምህርት ቤት ሲመጣ ቤት ያለሁት እኔ ብቻ ነበርኩ፡፡ አክስቴ ትንሿን ልጅ አዝላ ጎረቤት ለቅሶ ሄዳለች፡፡ ትልቁ ልጅ ደግሞ ጎረቤት ለመጫወት ሄዶ ነበር፡፡ እንደመጣ አለመኖሯን ጠይቆ ካረጋገጠ በኋላ ‹ውሃ
ጠምቶኛል ስጪኝ› አለኝና ወደ መኝታ ቤት ገባ፡፡ ውሀውን በብርጭቆ ቀድቼ በራፍ ላይ ቆሜ ሳንገራግር ... <ጠምቶኛል እኮ ነው የምልሽ አምጪ እንጂ›በማለት ሲጮህብኝ በድንጋጤ ተርበትብቼ ወደ ውስጥ ዘለኩና ስሰጠው ብርጭቆውን ትቶ እጄን ለቀም አደረገው፡፡ ሳላስበው ብርጭቆ ከእጄ ሾለከና ወለሉ ላይ ተከሠከሠ፡፡ ባለችኝ ጉልበት እጄን አስለቅቄ ለማምለጥ መታገል ጀመርኩ፡፡ እሱ ግን ባለ በሌለ ኃይሉ ተሸክሞኝ አልጋ ላይ ወረወረኝና ተከመረብኝ፡ታገልኩት፤ ታገልኩት፤እስኪደክመኝ ታገልኩት፤ በጥፊ መታኝና በቦክስ ደገመኝ፡፡ እኔን ለማድከም የቻለውን ሁሉ አደረገ፤በመጨረሻ ኃይሌ ተሟጠጠ፤ተስፋ ቆረጥኩ፤ እያለከለከ ሱሪውን አውልቆ ቀሚሴን በመግለብ ጭኔን ሲፈለቅቅ አክስቴ ልጇን እንደታቀፈች ዘው ብላ መኝታ ቤቱ መሀል አይኗን አጉረጥርጣ ታየን ጀመር፡፡እሱ ሲያያት አልደነገጠም፡፡ ተበሳጨ እንጂ፡፡ ‹ምን አይነት ምቀኛ ነሽ› በማለት ያወለቀውን ሱሪ በእጁ እንደያዘ ገፍትሯት መኝታ ክፍሉን ለቆ ወጣ፡፡ እሷም እንደመደንዘዝ ካለችበት ነቃችና መጮኽ ማልቀስና መራገም ጀመረች፡፡እንደምንም እየተጎተትኩ ከአልጋው ላይ ተነሳሁና በተዳከሙ ቀጫጫ አግሮቼ ወለሉ ላይ ቆምኩ፡፡
‹‹አንቺ ሸርሙጣ የልጆቼን አባት...› ብላ ጮኸችብኝ፡፡ ግራ ገባኝ፤ የተበደልኩት እኔ፣የተደበደብኩት እኔ፣ልደፈር የነበረው እኔ፣ጥቃት የደረሰው እኔው ላይ፣እርግማኗንም የምታወርደው በእኔ ላይ፡፡
‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡ >> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡
በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡.....
✨ይቀጥላል✨
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች በአንድ ፖስት 10 ሰው #Subscribe ካደረገ በየቀኑ #ትንግርት ይለቀቃል

👍124❤21🥰3
#የአልጋ_ላይ_ዱካ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
ትላንት ማታ ክፉ ነገር ተፈጠረ፡፡
መልከ መልካሙና ገራገሩ እጮኛዬ ላይ ማገጥኩበት፡፡
ያች በልጣጣ ጓደኛዬ ትዕግስት ናት፣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የከተተችኝ።
ሁሌም ለሰኔ ሚካኤል ቤቷ ድል ያለ ድግስ ታዘጋጃለች፡፡ የምታውቀውን ሰው ሁሉ ትጋብዛለች፡፡ ከልክ በላይ
ታበላለች፡፡ ከመጠን በላይ ታጠጣለች፡፡ አንድ ውስኪ ለሦስት ሰው እየቀረበ፣ በረዶ አንሷል እየተባለ ውስኪ እንደተፈጠረ በጉሮሮ ሲንቆረቆር፣ ሰዉ ሁሉ ከማያውቀው ሰው እንደ አብሮ አደግ ይሣሣቃል፣ ያሽካካል፡፡ ምስጢር ይጋራል፡፡ ይሟዘዛል፡፡ የትዕግስት
ፓርቲ እንዲህ ነው፡፡ ነጠላ
ሆኖ የመጣን፣ ጥንድ አድርጎ
ይሸኛል፡፡ አይተው ከማያውቁት ሰው አደጋግፎ፤ አስተቃቅፎ፣አልጋ ድረስ ያጓትታል፡፡
ውስኪዋ ውስጥ ትንሽ ቅንዝር ጠብ፣ ብዙ የፍትወት ፍላጎትና የመማገጥ ዓላማ ሙጅር ታደርግበት ይመስል፤ በየዓመቱ የሚወራ የወሲብ ገድል መነሻ ይሆናል፡፡
ለስድስት ዓመታት ይሄንን የተቀበረ የመጠጥ ፈንጂ አልፌ፤ ዘንድሮው ግን ረገጥኩት፡፡
እርግጥ አድርጌ ብ......ው......
አደረግኩት፡፡ አጀማመሩ እንዲህ ነበር፡፡
ጥሬና ጥብሱን ሥጋ፣ ከዚህ በኋላ ለሳምንት አትበሉም የተባልን ያህል ተስገብግበን ጎስረን፣ ጎስረን፣ “እሰቲ አወራርዱት... እስቲ ጥረጉት” እያለች የምታስተናብረውን ትዕግስት እየሰማን፣ ሁለት ጠርሙስ ውስኪያችንን በጉሮሯችን እያንቆረቆርን ስድስት ሆነን
አንድ ጠረጴዛ ላይ ተሰይመናል፡፡
ከለብታ አልፎ ሞቅታ፣ ከሞቅታ አልፎ ስካር ሲጀማምረኝ ትዕግስት
ወደ ጠረጴዛችን መጥታ፣ “አወራርዱት” ባለች ቁጥር፤ የሞት ሞቴን የብርጭቆዬን አፍ በእጆቼ ለመክደን ብሞክርም፣ ልክ ትንኝ እንደምታባርር ሁሌ እጄን ጧ እያደረገች ታስከፍተኝና በውስኪ
ሞልታው ትሄዳለች፡፡
ቺርስ ባሉ ቁጥር እጠጣለሁ፡፡
“አትጨምሪልኝ... በቃኝ” እያልኩ በእጄ ብርጭቆውን ለመዝጋት እሞክራለሁ፡፡
እጄን ጧ አድርጋ፣ ብርጭቆዬን አስከፍታኝ ሞልታው ትሄዳለች፡፡
ቺርስ ባሉ ቁጥር እጠጣለሁ፡፡
እንደገና “አትጨምሪልኝ... በቃኝ” እያልኩ በእጄ ብርጭቆውን ለመዝጋት እሞክራለሁ፡፡
እጄን ጧ አድርጋ፣ ብርጭቆዬን አስከፍታኝ ሞልታው ትሄዳለች፡፡
ይሄ አዙሪት ለዐሥራ ምናምን ጊዜ እንደቆየ ሳሙኤል ከፊቴ ተከሰተ፡፡ ያንን ሰንደቅ የሚያስቅል ቁመቱን፤ የቀይ ዳማ የደስ ደሳም ፊቱን፣ ቦርጭ አልባ ሰውነቱን ይዞ፣ ሳሙኤል ከፊቱ ተከሰተ፡፡ ያውም አንዴ ሁለት፣ አንዴ አራት፣ አንዴ ስድስት
ሆኖ... ሞቅታዬ አብዝቶት፣ ስካሬ አባዝቶት የቀድሞ ፍቅረኛዬ ሳሙኤል ከፊቴ ተከሰተ።
ሲቀመጥ ትዝ አይለኝም፡፡ እጆቼን ሲያሻሸኝ ግን ትዝ ይለኛል፡፡
መጀመሪያ ሲስመኝ ትዝ አይለኝም፡፡ አፌን አፉ ውስጥ ሳገኘው ግን ትዝ ይለኛል።
መኪናው ላይ ስሳፈር አላስታውስም፡፡ አልጋው ውስጥ መግባቴ ግን ውል ይለኛል፡፡ ልብሳችንን ስናወልቅ ትዝ
አይለኝም፡፡ ዕራቁት ሰውነቱን በስሜት ስቧጭር ግን በደንብ ትዝ ይለኛል።
ከንፈር እየተሻማን ስንቃበጥ፣ አንገቴን ሲልስም፣ ሲስምም፤ ኋላም ሴትነቴን በወፍራም ወንድነቱ ሲከድን፣ መሀሉ መሀሉ ጭለማ በገባበት ሁኔታ ትዝ ይለኛል፡፡
ይሄው ነው፡፡
ጠዋት ላይ፣ አልጋው ውስጥ አናት ከሚፈልጥ ራስ ምታት ጋር
ስነቃ፣ ትላልቅ ድፍርስ ዐይኖቹ ተቀበሉኝ፡፡
ራሴን በሁለት እጆቼ ካልደገፍኩ ቷ ብሎ የሚፈነዳ ስለመሰለኝ፣በቀኝም በግራም እጆቼ ጭንቅላቴን ይዤ፣ ከወገቤ በላይ ብድግ አልኩና፣
“ምንድነው ...! ምንድነው ያደረግነው?” ብዬ ጮኽኩ፡፡ ሳሙኤል
ትላልቅ ዐይኖቹን ፊቱ ላይ እያንጎማለለ ሲያየኝ፣ የራሴ ጩኸት ራስ ምታቴን እያባሰው ከወገቤ በታች ዐየሁ፡፡ እንደፈጠረኝ ነኝ፡፡
“ሳሙኤል... እዚሀ እንዴት መጣሁ...? ምንድነው ያደረገገው...?”አልኩ በአንሶላው ተጠቅልዬ ከአልጋው የመሸሽ ያህል እየወጣሁ:ከአልጋው ፈንጠር ብሎ ወጣ፡፡ ቁምጣ ከሚያህል ቡራቡሬ የውስጥ ሱሪ ሌላ ምንም አላደረገም፡፡
“ሆሆሆ! ምንድነው ያደረግነው? ካርታ ስንጫወት ነዋ ያደርነው”አለኝ፣ እየሣቀ፡፡ ጥርስህ ይርገፍ፡፡
ዝም ብዬው ልብሶቼን ፍለጋ ጀመርኩ፡፡
ሮዝ ጡት ማስያዣዬን አልጋው ግርጌ፣ ጥብቅ ያለው ቀይ የድግስ ቀሚሴን ከአልጋው በስተቀኝ መሬት ላይ አግኝቼ፣ በሰማያዊው ለስላሳ አንሶላ እንደተጠመጠምኩ ወደ ማውቀው መታጠቢያ ቤት ገብቼ ፊቴን ሳልታጠብ መስታወቱ ፊት ቆምኩ፡፡
ምንድነው የሠራሁት?
ምን ነካኝ?
እሺ ለብ ይበለኝ፡፡ እሺ ሞቅ ይበለኝ፡፡ እሺ ልስከር፡፡ እሺ እጄን እንዲይዝ ልፍቀድለት፡፡ እሺ ሲስመኝ ልሳመው፡፡ እሺ ትንሽ ልቃበጥ፡፡ ግን ምንስ ያህል ብጠጣ ከትዕግስት ቤት ወጥቼ፣
መኪናው ውስጥ ገብቼ፣ ከብስራተ ገብርኤል ሰሚት ድረስ ንፋስ እየመታኝ መጥቼ፣ እቤቱ ሄጄ፣ መኝታ ቤቱ ገብቼ፣ አልጋው ጋር ሄጄ፣ አልጋው ውስጥ ገብቼ፣ ልብሴን አውልቄ፣ ራቁቴን ሆኜ፣
እጮኛ (ያውም የሰው ጥግ) እያለኝ፤ ከቀድሞ ፍቀረኛዬ ጋር ስዳራ
ማደሬ ልክ ነው?
ለመልአክ ሩብ ጉዳይ በሆነ እጮኛዬ ላይ
መልከስከሴ ግፍ አይደለም?
ቢሰማ አያብድም?
ቢያውቅ ራሱን አያጠፋም?
ፊቴን በቅጡ ሳልታጠብ፣ ከመታጠቢያ ቤቱ ወጥቼ በጥድፊያ ጫማዬን አድርጌ፣ ቦርሳዬን አነገብኩና... “ስሚኝ...” ምናምን...የሚለኝን ሳሙኤል ሙሉ በሙሉ ዘግቼ እግሬ በፈቀደልኝ ፍጥነት
ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፡፡
የኮንዶሚኒየሙን ደረጃ እየወረድኩ ስልኬን አወጣሁ፡፡
.
ዐሥራ ዘጠኝ ያመለጡኝ ጥሪዎች፡፡ ሰባት የጽሑፍ መልዕክቶች፡፡ከፈትኩት፡፡
ዐሥራ ስድስቱ የእጮኛዬ ጥሪ ነው፡፡ ስማግጥ ያልመለስኳቸው 16
ጥሪዎች፡፡ እርምጃዬን አቁሜ እጄ እየተንቀጠቀጠ መልዕእክቶቹን
ከፈትኳቸው፡፡ ሁሉም ከእሱ ናቸው፡፡
“ማሬ ስልክ አታነሺም” ... “በሰላም ነው...?”... “ኧረ ተጨነቅኩ”...
.
“በደህናሽ ነው?”... “እባክሽ ደውይልኝ... “ትዕግስትም አላነሳ አለችኝ ... “በናትሽ ደውይልኝ” ....
ኮንዶሚኒየሙ ጣራ ላይ ወጥቼ መፈጥፈጥ አማረኝ፡፡
ልደውልለት ግን ጉልበት አጣሁ፡፡ እሱን ትቼ ትዕግስት ጋር ደወልኩ፡፡ በሁለተኛው ዙር ከአራት ጥሪ በኋላ አነሳች፡፡
ሰላምም ሳልላት፣ “አንቺ ማታ ምንድነው የተፈጠረው?” ብዬ ጮኽኩባት፡፡
“እንዴ እኔ ምናባሽ አውቅልሻለሁ... የት ሆነሽ ነው...?” አለችኝ።ድምፅዋ፣ ቤተክርስትያን ሲያስቀድስ አድሮ የመጣ ሰላማዊ ሰው እንጂ፤ አሸሼ ገዳሜ ሲል ያደረ አይመስልም፡፡
“ምን የት ነሽ?” ትይኛለሽ... ሳሚ ጋር ነበርኩ... እንዴት እንዲህ
ዓይነት ነገር ሲደረግ... እዚህ ሲያመጣኝ ዝም ትያለሽ?” አልኩ፣ ቱግ ብዬ እርምጃዬን እያፈጠንኩ፡፡
“እንዴ... ኧረ ቀስ...! አንቺ አይደለሽ ስንት ሆነን ስንለምንሽ፣ ከእሱ በስተቀር ከማንም ጋር አልሄድም እያልሽ፤ እንደ
እባብ ስትጠመጠሚበት ያመሸሽው?” አለችኝ ቆጣ ብላ፡፡
ወሬውን በስልክ መቀጠል ስላልፈለግኩ፣ ቤት መሆኗን አረጋግጬ ራይድ ጠራሁና ስበር ቤቷ ደረስኩ፡፡
በስልክ የጀመረችልኝን አጠናክራ፣ ለያዥ ለገናዥ ማስቸገሬን፤ ያየኝ ሰው ሁሉ ሲሥቅ እንደነበር፤ መጨረሻ ላይ እንደፈለጋት ትሁን ብለው እንደተዉኝ በሚያም ዝርዝር ነገረችኝ፡፡
ያቀረበችልኝን ቁርስ ሳልነካ ሻዩን ብቻ እየማግኩ፣
“ቲጂ...” አልኳት፡፡
“ወይ...” አለች፣ ዐይን ዐይኔን እያየች፡፡
“ደሬ የሚሰማ ይመስልሻል...? ማለቴ ሰው ቢነግረውስ?” አልኳት፡፡
“እ...ህ አይመስለኝም... ደግነቱ እንደዛ ስታብጂ የነበረው አብዛኛው ሰው ከሄደ በኋላ ነው...ማሐቴ ሳሙኤል ካልተናገረ" አለችኝ።
ሳሙኤል ካልተናገረ!
በተቀመጥኩበት መርዶ እንደተረዳ ሰው

👍70❤7😱3🔥2👏1
ከወገቤ በላይ ወደፊትና
ወደኋላ ሄድ መለስ እያልኩ፣ አፌን በእጆቼ እየያዝኩ፣ የተመሳቀለ ጸጉሬን እየፈተልኩ፣ አፍጥጨ እያየኋት ጠየቅኳት፡፡
“ቲጂዬ ሳሙኤል የሚነግረው ይመስልሻል?”ድምፄ እየተንቀጠቀጠ፡፡
ነገሩን አልኩሽ እንጂ የት ተገናኝተው ይነግረዋል...?”
እፎይታ ተሰማኝ፡፡
የምሆነው ጠፋኝ፡፡ ተንስቼ አንዴ ወዲህ፣ አንዴ ወዲያ በጭንቀት ስንጎራደድ ዝም ብላ ታየኛለች፡፡
“ኩኩዬ በቃ ረጋ በይ... ዋናው እኮ፣ ይሄ ወሬ ከሳሙኤል ወደ ደሬ የሚደርስበትን መንገድ ካላ ማሰብ ነው፡፡ ማለቴ የወሬውን መንገድ ማጥፋት፤ አለ አይደል፣ ዱካ ማጥፋት” አለችኝ፡፡ ትንሽ ቆየት ብላ፡፡
በግርምት ዐየኋት። ልክ ናት። በጣም ልክ ናት።
ቶሎ ብላ፡፡
ቲጂ ከመርዛማ ውስኪ ውጪ የፖሊስ ጭንቅላት ነው ያላት፡፡
የውስልትና ዱካዬን ለማጥፋት፣ አብሬው በወሰለትኩት ሳሙኤልና በእጮኛዬ መካከል ያለውን የግንኙነት መሥመር
ማሰብ የመማገጤን ወሬ ወደ እጮኛዬ ደሬ ሊያደርስ የሚችለውን መንገድ
ማሰላሰል ጀመርኩ፡፡
ኦኬ... ሳሙኤል... ሳመኤል ጋር መደወል አለብኝ፡፡
ባለሁበት እየተንቆራጠጥኩ ደወልኩለት፡፡
“ሄሎ ሳሙኤል ...የት ነህ?”
“ሄሉ...ቢሮ ነኝ... ምነው? እንደዛ ቻው እንኳን ሳትይኝ በናትሽ...?”
“በናትህ ሳሙኤል ጊዜ የለኝም... ስማ ይልቅ...”
“እ...?”
“ስለ ተፈጠረው ነገር ለማንም አላወራህም አይደል? በናትህ ለማንም
እንዳትናገር፡፡”
“ህም... ካሁን በኋላ አልናገርም እሺ” ሣቀ፡፡
“ሳሙኤል በማርያም! አታሹፍ፤ እጮኛ እንዳለኝ ታውቃለህ፡፡
በናትህ ለሰው ነገርክ እንዴ?”
“ዌል... ለዳጊ ኦሬዲ ነግሬዋለሁ
ሃሞቴ ፈስሰ፡፡ ውሃ ልኬ ተዛባ፡፡
ትንፋሽ ሰብስቤ፣
“ማነው ዳጊ... ዳጊ ማነው?”
እንዴ...! ዳግምን ረሳሸው እንዴ... የዛሬ ወር ኣካባቢ ሮሃ ምግብ ስንበላ አግኝተሽኝ ያስተዋወቅኩሽ የቢሮ ጓደኛዬ ትዝ አይልሽም...?”
“እህህ... እንዴ... አብሮህ የሚሰራው ቀዩ ልጅ ባልሆነ... አብሮህ የሚሰራው ያ ቀዩ ጸጉረ ሉጫው ልጅ ነው?” እንደ ጉድ
ተርበተበትኩ፡፡ እንደ ጉድ ተንተባተብኩ፡፡
መሆኑን አረጋገጠልኝ፡፡
ዳግም ሰማ አልስማ፣ ጉዳይ ኖሮኝ አይደለም መርበትበቴ፡፡ ብርክ
የያዘኝ ዳግምን አንድ ሁለቴ ከእጮኛዬ ደሬ እህት ጽዮን (በማላቀው
ምክንያት አምርራ ትጠላኛለች) ጋር ካፌ ቡና ሲያንቃርር ስላየሁት ነው፡፡
ተበጠበጥኩ፡፡
“ሳሙኤል... በናትህ የዳጊን ቁጥር ስጠኝ... ልደውልለት...” አልኩ፣
በድንጋጤ በሰለለ ድምፄ፡፡
“እ... ኦኬ... ቴ ክስት አደርግልሻለሁ” አለኝ፣ በፍጹም ግዴለሽነት፡፡
ስልኩን ዘግቼ ወዲህ ወዲያ እየተራመድኩ፣ ባሏ እንደሞተባት
ባልቴት ወገቤን ይዤ እያረገድኩ ቁጥሩን ስጠብቅ፤ ማን ደወለ? ጽዮን፡፡
“ኦህ... ማይ ... ጋድ!
የማደርገው ጠፍቶኝ
ስልኩን፣ አንዴ ቲጂን እያየሁ
ስርበተበት አንደኛው ጥሪ አበቃ፡፡ የሚካሄደው ነገር ያልገባት ቲጂ ፣
“ንገሪኝ እንጂ... ምንድነው እሱ...?" እያለችኝ ጽዮን እንደገና ደወለች፡፡ እነሳሁት፡፡
“ሄሎ..." አልኩ አሁንም በሰላላ ድምፄ
“አንች ሽርሙጣ! ድሮም አውቄው ነበር ..እይ ኔቨር ላይክድ ዩ
ለኔ ወንድም እንደማትመጥኚ አውቀው ነበር... ሽ...ር...ሙ..ጣ
ነገር ነሽ"
አለቀልኝ፡፡
✨ጨርሰናል✨
አንባብያን በንደዚች ያለች አጋጣሚ ፎንቃችሁን ያጣችሁ እስኪ እጅ እያወጣቹ ባይመለስም ትምህርት ነውና ንገሩን እስቲ ።
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች ለናንተ ቀላል ነው ለኛም ማበረታቻ።

👍71❤5👎3👏3
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አራት:- ትንሹ ተዐምር (2)
የታዴን ጥያቄ ተከትሎ ሃኪሙ መናገሩን ቀጠለ “…ዳሪክ ያለበት ሁኔታ እንዲህ ነው። ከደረሰበት ጉዳት፣ ህይወቱን ለመመለስ፣ ከተደረጉትም ከፈተኛ ኦፕራሲኖች የተነሳ ኢንድዩስድ ኮማ ውስጥ ልናስገባው ግድ ነበር። አሁን በደንብ ለማየት ባንችልም ይህ ልጅ እስከ መጨረሻው ያለመንቃት እድል አለው። የምንችለውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን። ነገር ግን አሁንም ህይወቱ የማለፍ፣ ኮማ ውስጥ ለረዥም ጊዜ ወይም እስከ ህይወቱ ፍጻሜ የመቆየት፣ ወይም ቢነቃም ለከፍተኛ አካል ጉዳት የመጋለጥ እድሉ በጣም ከፍተኛ ነው። እጅግ በጣም አዝናለሁ …ግን በህክምና እይታ የምናየው ይህ ነው። ….”
ያስደነግጣል። ሃኪሙ የሚነግረን ልብን ያርዳል። ግን አንድ ነገር አለ። ሃኪሙ እንዳለው ይህ የህክምና እይታ ነው። የሰዎች እውቀት ጥግ ነው ይህን እያለ ያለው።
“…ዶክተር አንድ ጥያቄ ልጠይቅ?...” አልኩት
“…በሚገባ!...” ዶክተሩ ወደኔ ዞሮ እያየኝ
“…መትረፉ ራሱ ተዐምር ነው ብለሃል አይደል?...”
“…አዎ ብያለሁ…”
“..ስለዚህ ዋናው ህይወቱ መትረፉ ነው ….” አልኩኝ “ …የወደፊቱን የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ህይወቱን ያተረፈው ተዐምር ላያኖረው አልጀመረም።….ተዐምሩ ሊቀጥል ይችላል።…. አሁን ካላስቸገርን ማየት እንችላለን ዳሪከና ሳሌምን?....” ጠየቅኩኝ… በእውነትም ለማየት ጓጒቼ ነበር።
“…ልክ ነሽ…” አለ ሃኪሙ “…ህይወቱ መትረፉ ለኔ ከ አእምሮዬ ልክና መጠን በላይ ነው። ተዐምር ነው። ነገር ግን በህክምና እይታ ወደፊት ሊሆን የሚችለውን የመናገር ሃላፊነት አለብን። ማየት እንችላለን ወይ ብለሽ ለጠይቅሽ አዎ። የሁለቱንም ሁኔታ በቅርብ ወደ ምንከታተልበት ወደ ICU ተውሰድዋል። በፈለጋችሁ ጊዜ ማየት ትችላላችሁ …” አሉንና ተለያየን።
*
*
መጀመሪያ ታዴና ሌሎች የነበሩ የቅርብ ሰዎች ሳሌምንና ዳሪክ እየገቡ ጎበኙ። በመጨረሻም እኔ እድሉን አገኘሁ።
….እንግዲህ መጀመሪያ ሳሌምን ቀጥሎም ዳሪክን ስመለከት፣ ሳይ ያየሁት ይህንን ነው። ሳሌም ሳሌምን አትመስልም። ዳሪክም ሌላ ዳሪክ ሆኗል።
በተለይ ዳሪክ ያለበት ሁኔታ ያሳዝናል፣ ያንሰፈስፋል። አሁንም አየዋለሁ፦ ዳሪክን። ሳቅ የሚፈስበት ጠይም ፊቱ ጸጥ ብሏል። ፊቱ ላይ የሚታየው ስቃይ ከሱ አልፎ ለሌላ ሁሉ የሚሰማ ነው።
እጠይቃለሁ፦ እኔ።
ይመልሳል፦ ሃኪሙ።
“…ፊቱ ሲታይ ያመመው ይመስላል። ህመም ላይ ይሆን?....” ጠይቅኩኝ
“…ያለማቋረጥ የህመም ማስታገሻ መደሃኒት እየተሰጠው ነው።…” የተሰቀለውን መድሃኒት አሳየኝ “…ግን የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ ህመም አለው። ስለዚህ ህመም ቢኖርበት አይገርመኝም። ቅድም እንዳልኩት መትርፉ በራሱ ተዐምር ነው።… ኦ አር (OR) የነበረው ሁኔታና የሃኪሞችን ሪፖርት ሳነብ በቃ ይሄ ልጅ ከዚህ ዓለም እንዳይሄድ የሆነ ሃይል እየጠበቀው ያለ ነው የሚመስለው። በእንደ እዚህ አይነት ነገር ብዙም አላምንም። ነገር ግን ሶስት ጊዜ የልብ ትርታው ቆሞ የተመለሰም ሰው አይቼ አላውቅም። በቃ ነፍሱ በሁለት ሃይላት ጦርነት ውስጥ ያለች ነው የመሰለኝ። አንዱ ሊያድነው ሌላው ደሞ ሊወስደው የሚታገሉ ያህል ነው የሆነው።….”
ሃኪሙ ፈገግ አለ “…ዳሪክ በእድሜ ትንሽ ነው፣ በተክለ ሰውነቱም ትልቅ አይደለም። ግን እንደ ትንሽነቱ አይደለም። ‘…አልሞትም፣ ቀኔ ዛሬ አይደለም…’ ብሎ ታግሎ ያሸነፈ ነው የሚመስለው። ስለዚህ … ‘ትንሹ ተዐምር’…” ብለነዋል።
…ሌሊቱን ሳልተኛ በማሳለፌ ወደ ቤት ሄጄ አረፍ ከማለቴ በፊት ….የዛን ለት ጠዋት ይህን ያህል ነው ያየኋቸው፦ ሳሌምና ዳሪክን። ወደ ቤቴ እየሄድኩኝ ማሰብ ጀመርኩኝ። በአንድ በኩል የሁለቱ ሁኔታ የሚያሳዝን፣ ልብን የሚስብር ነው። በሌላ በኩል ደሞ በዚህ ሁሉ ሁኔታ ውስጥ አልፈው በህይወት መትረፋቸው እጅግ በጣም ትልቅ ድልና እድል ነው።
ተስፋ አለ። እምነት፣ ተስፋና ፍቅር ቤተሰቦች ናቸው። ተስፋ ካለ፣ እምነት አለ። ሁለቱን ደሞ የሚያያዝው ታላቅ ወንድም ፍቅር ነው። አሁንም ለርግቦቹ ተሰፋ አለ። እምነት ይህን ተስፋ ያያል። ህይወት ይሆናል። በመጨረሻ ፍቅር ደሞ ሁሉንም አያይዞ ያስራል። ….ተስፋ አለ። በእምነት አይን ይህ ተስፋ ሲታይ ህይወትን ይሰጣል። ከህይወት ቡሃላ ደሞ ዳግመኛ ያ ታላቅ ፍቅር ለዳሪክና ሳሌም ይሆናል። አሁንም ቢሆን እነዚህ ሁለት ፍቅሮች እንደገና አይን ለአይን እየተያዩ አለምን የሚረሱበት፣ እጅ ለእጅ ተያይዘው እየተሳሳቁ በዙሪያቸው ያሉትን ሁሉ በደስታ የሚያሰክሩበት፣እስከ ፍጻሜያቸው ላይለያዩ በመውደድ ሰንስለት የሚቆራኙበት ቀን ቅርብ ነው። እንኳንም በህይወት ኖሩልን። እንኳንም ተረፉልን። ጌታ ይመስገን።
ዳሪክን ሃኪሞቹ ‘ትንሹ ተዐምር’ ብለውታል። ትክክል ስም ነው። መልካም ስም ነው። ይገልጸዋል። ትንሹ ተዐምር ጀምሯል። ተዐምሩም ላያልቅ አልጀመረም። ትንሹ ተዐምር ትልቅ ሊሆን፣ ሊሰፋ፣ ሊያድግ፣ ሊወርስ ዛሬ ጀመረ።
ልቤ እርፍ አለ። ቤት ሄጄ ለሚቀጥሉት ብዙ ሰዐታት ተኛሁ።
… የተረፈውን ቀንም … ሌሊቱንም በሚገባ አርፌ በሚቀጥለው ቀን በማለዳ እንደገና ዳሪክና ሳሌምን ላይ ሄድኩኝ። ትላንትና ቀኑን ለጥቂት ሰዐታት አርፎ ሌሊቱን ያደረው ታዴ ድካም ይታይበታል። እሰከ ከሰዐት እኔ ልቆይ እንደምችል ነገሬው ቤት ሄዶ እንዲያርፍና እንዲመለስ ሃሳብ ሳቀርብ አላመነም። “…ተባረኪ ልጄ…” ብሎ ወዲያውኑ ሄደ።
ሁለቱን ፍቅሮች ላያቸው ስገባ ዳሪክ ያለበት ሁኔታ ለውጥ የሌለው ነው፣ ሳሌም በሌላ በኩል ወደ ራሷ ወደ መልኳ መለስ ብላለች። ብቅ እያለች ነው።
አንዴ ዳሪክ ክፍል ሌላ ጊዜ ደሞ ሳሌም ጋር እየተመላለስኩ ሳያቸው፣ ያሉበትን ሁኔታ ስከታተል አረፈድኩኝ።
ወደ እኩለ ቀን አካባቢ ሳሌም ክፍል ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ ሙቪ እያየሁ ነበር።
ያላመንኩት፣ያልጠበቅኩት ነገር ሆነ።
ድክም ያለ ድምጿን ሰማሁት። በተሰባበሩ ቃላት፣ ድምጿ እየተጎተተ “…የ.. ት ..ነው ያ.. ለ.. ሁ ት?...”
ወደ ሳሌም ዞር ስል፣ ትላልቅ አይኖቿ ሽፋናቸው ገርበብ ብለው ተከፍተዋል።

👍67❤11🤔1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
...‹‹ስሚ አሁኑኑ ጨርቅሽን ይዘሽ ከቤቴ እንድትወጪልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ልጆቼን ላሳድግበት፡፡ ከፈለግሽ ሽርሙጥና ቤት ግቢና እንደፈለግሽ ሁኚ፤አልፈልግሽም፡፡>> በማለት ጨርቄንና ደብተሮቼን ሠብስባ አስታቅፋኝ እየገፈተረችኝ ከቤቷ አውጥታ አባረረችኝ፡፡
በእንደዚህ ሁኔታ ነበርሰ ታሪኳን ያስረዳችው፡፡ ከዛም እንደ እህቱ አድርጎ ተቀበላት፡፡."
ትምህርቷንም እንድትቀጥል አደረጋት፡፡ በወቅቱ እሱ ጋር ስትመጣ የአስረኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ አሁን በዲፕሎማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሦስተኛ አመት ተማሪ ነች፡፡
....ሁሴን የሀሳብ ውቅያኖስ ተንፈራግጦ ሲወጣ እቤቱ ሞቆና ተጫጭሷ ነበር፡፡ ፎዚያ ቅድም የለበሠችውን ልብስ አውልቃ ድርያ ለብሳለች፡፡ ብዙውን ጊዜ የምትሸፍነውን ፀጉሯን በነፃነት ለቃዋለች፡፡ አጭር ቢሆንም ሉጫ ስለሆነ ለውበቷ ልዩ ድምቀት ለግሷታል፡፡
‹‹እሺ ፎዚያ ትምህርት እንዴት ነው?›› አላት፡፡
‹‹አሪፍ ነው፡፡አሁንማ ልጨርስ አራት ወር ብቻ ቀረኝ እኮ!››
‹‹በጊዜ ስራ ፈልጉ ማለትሽ ነው?››
‹‹ለስራው እንኳን ብዙም ጉጉት የለኝም፡፡ ዋናው ተምሬ እዚህ ደረጃ መድረሴ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ ዕቅዴ አንተን በተሻለ መንገድ መንከባከብ ነው፡፡››
‹‹እንዴት ባክሽ? እኔን ለመንከባከብ እኮ ሦስት ዓመት ሙሉ ኮሌጅ ገብቶ መማር አያስፈልግሽም ነበር
‹‹...እንዲህ ብለህ አታሳምነኝም...አንተ ለእኔ ምርጥ ወንድሜ ብቻ ሳትሆን አባቴም ጭምር ነህ ፡፡ብዙ ነገር አድርገህልኛል፡፡አላህ አንተን ባይጥልልኝ ኖሮ ዛሬ ዕጣ ክፍሌ የሰው ቤት ግርድና ካልሆነም ሽርሙጥና ነበር፡፡ስለዚህ የእኔ አንተን ለመንከባከብ መወሰን ያንስብሀል እንጂ አይበዛብህም፡፡››
‹‹...ፎዚ ለእኔም እኮ ምርጥ እህት ሆነሽኛል፡፡ ይሁን እንጂ እህትም አንድ ቀን የታለቅ ወንድሟን ቤት ጥላ የራሷን ቤት ትገነባለች፡፡ የወንድም ኃላፊነት ደግሞ እህቱ እዚህ ደረጃ እንድትደርስለት ማበረታታትና መደገፍ ነው፡፡ እርግጥ ነገሮች ቀላል አይደሉም፡፡ እኔም እኮ አንድ ቀን ስራ ይዘሽ ፣የፍቅር ጓደኛ አበጅተሸና ትዳር መስርተሸ ጥለሺኝ እንደምትሄጂ ሳስብ በጣም ይጨንቀኛል፤ ቢሆንም ግን የግድ መቀበል እንዳለብኝ አምናለሁ፡፡
የፈላውን ቡና በመቅዳት ስኳር ጨምራ በማማሰል አቀበለችውና ለራሷም ቀድታ ንግግሯን ቀጠለች፡፡
‹‹እንግዲህ ውሳኔዬ የማይቀየር ነው፡፡ ምን አልባት አግብተህ ባለቤትህ ቤቱን ከተረከበችኝና ከልብ እንደምትንከባከብህ እርግጠኛ ከሆንኩ.. ያኔ ያልከውን አደርግ ይሆናል፡፡›
‹‹ዝም ብለን በባዶ ሜዳ እኮ ነው የምንጨቃጨቀው፡፡>>
‹‹እንዴት ማለት?›› ሁሴን ሊላት የፈለገው ምን እንደሆነ ስላልገባት ጠየቀችው፡፡
‹‹እኔ አሁን በቅርብ የማገባ ይመስልሻል? >>
‹‹ለምንድነው የማታገባው?››
‹‹ማን ነች ፍቃደኛ ሆና እኔን ልታገባኝ የምትችለው?››
‹‹በጣም ዕድለኛዋ ሴት ነቻ፡፡›› ፎዚያ ከምሯ ነው እውነተኛ ስሜቷን የምታወራው፡፡
‹‹አይምሰልሽ .. በዙሪያዬ ያሉ ሴቶች ሁሉ በፍቅር እንጂ ትዳርን ለሚያህል ቁም ነገር ብቁ እንዳልሆንኩ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡››
‹‹ይሄ አንተን በተመለከተ ትክክለኛ ምልከታ ነው ብዬ አላስብም፡፡›› አለች ቅሬታን በዛለ ድምፅ፡፡
‹‹እንዴት ... ? ሌላው ይቅር በአንቺ አመለካከት እኔ ለትዳር የምሆን ግለሠብ እመስልሻለሁ?›› ሲል ጠየቃት ፡፡
‹‹እውነቱን ልንገርህ?›› በታፈነ ድምፅ ጠየቀችው፡፡
‹‹አዋ!.. ንገሪኝ ... ትክክለኛ ስሜትሽን ንገሪኝ፡፡››
‹‹እንግዲያው እኔ ሙሉ በሙሉ ያንተ አይነት ወንድ እስከማገኝ ትዳር ሚሉት ነገር አልሞክርም፡፡››
ደነገጠ፡፡ እንደምትወደው ያውቃል፡፡ ይሄን ያህል ተፅዕኖ ውስጥ እንደከተታት ግን ልብ ብሎ አስተውሎት አያውቅም፤ ውይይታቸው ከወትሮው በመጠኑም ቢሆን ጠንከር እያለ ስለመጣበት ርዕስ ለመቀየር ተገደደ፡፡
‹‹ኦ! ይሄ ቡናሽ ልዩ ነው፤ ከደባሪው እራስ ምታቴ ገላገለኝ›› አላት፡፡
‹‹ስለተሻለህ ደስ ብሎኛል፤በነገራችን ላይ ቀን ትንግርት መጥታ ነበር፡፡››
‹‹እንዴት ሳትደውልልኝ መጣች ..…?››
‹‹እኔ እንጃ፡፡ ሁኔታዋ ግን ከወትሮው የተለየ ሆነብኝ፡፡ ሁሉ ነገሯ ወደ ኖርማል ተመልሷል... አገባች እንዴ?›› የገረማትን ነገር ጠየቀችው፡፡
‹‹አይመስለኝም.. ስራ ግን ቀይራለች›› መለሠላት፡፡
<<ለማንኛውም የሆነ ዕቃ አምጥታልሃለች፡፡ >>
‹‹ምን አይነት ዕቃ? >> ለማወቅ በተጣደፈ ስሜት ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ እንጃ ሥዕል መሠለኝ፤ታሽጓል፡፡ መኝታ ቤት አስቀምጬልሀለሁ፡፡››
ተስፈንጥሮ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ፡፡ በግምት ሠማንያ በስልሳ የሚሆን በፍሬም የተወጠረ፤ በስጦታ ወረቀት የተጠቀለለ ሸራ አገኘ፡፡ በጥድፊያ ልባሱን አነሳው፡፡የሚያፈዝ ስዕል ነው፡፡ የጥንት ንግስቶች የሚለብሱትን አይነት አብረቅራቂ ወርቀዘቦ ልብስ የለበሠች እንስት ትታያለች፡፡ እግሮቿ መሬት አይረገጡም፡፡ በአየር ላይ የምትራመድ ትመስላለች፡፡ ፀጉሯን ንፋሱ እያንሳፈፈው በአየር ላይ ተበታትኖ ሲታይ ሰማይ ጠቀስ ማማ ላይ የተሰቀለ የታላቅ ሀገር የተከበረ ባንዲራ ይመስላል የእጆቿ ጣቶች ውበታቸው የገነት ደናግሎችን አይነት ነው፡፡ በቀኝ እጇ ዓይነ ሥውሮች የሚጠቀሙበትን አቅጣጫ መጠቆሚያ ነጭ ዘንግ ይዛለች፡፡ ፊቷ የተለየ ነው፡፡ እንደ ሠው ዓይን፣ አፍንጫ፤ ከንፈር ሳይሆን በቦታው የሙሉ ጨረቃ ቅርፅ ይታያል፡፡ በጨረቃዋ ዙሪያም በህብረ ቀለም የደመቀ የብርሃን አምድ ያንፀባርቃል፡፡የሥዕሉ ጥልቀትና ምጥቀት... ውስጡ የተዳፈነውን የፍቅር እቶን ቀሠቀሠበት፡፡ የናፍቆት እሳት መላ ሰውነቱን ሲለበልበው ተሠማው፡፡
ትንግርት መጽናኛ የሚሆነውን ውድ ስጦታ ስላበረከተችለት ከልብ አመሠገናት፡፡ ፊት አልባ ሥዕል የተሳለላት ድብቋ ደራሲ ግን በምን ተአምር በአካል ሊያገኛት እንደሚችል ከመቼውም ጊዜ በላይ ግራ ገባው፡፡ ስዕሉን እንደታቀፈ ወደ አልጋው ሄደና በጥንቃቄ ተኛ፡፡ የቀለሙ ሽታ ከደራሲዋ ሰውነት የሚመነጭ መግደላዊት ማሪያም የክርስቶስን እግር ያጠበችበትን የአልባስጥሮስ ሽቶ አይነት እንደሆነ ሁሉ በረጅሙ ስቦ ወደ ውስጡ ማገው.. የስሜቱ ጥጋ.. ጥግ ድረስ ገብቶ ለውስጡ ሀሴት እንዲሰጠው በመመኘት ፡፡ በስዕሏ ፋንታ ዋናዋንም አንድ ቀን በአካል አግኝቷት እዚሁ አልጋው ላይ እንዲህ አቅፎት በእጆቹ እየዳበሳት..በከንፈሮቹ እየመጠጣት. በትንፋሹ እያጋላት... በሙቀቱ እያቀለጣት... በፍቅሩ እያሰከራት አብሯት እንደሚተኛ ተስፋ በማድረግ…፡፡...
✨ይቀጥላል✨
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች በባለፈው #ፖስት 10 ሰው ብዬ 2 ሰው ብቻ ነው #ሰብስክራይብ ያደረገው 10 ሰው #ሰብስክራይብ አድርጉና ቀን በቀን እንልቀቅ

👍116👏15❤13👎2😁1
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አምስት፦ ስስ ፈገግታ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
“..ሙሉ ስምሽን ንገሪኝ?...”
“…ሳሌም ታደሰ ሃይሉ…”
“…ያለንበትን አመተ ምህረት ንገሪኝ?...”
“…ሁለት ሺ አስር…”
“…ያለንበትን ወር ታስታውሻለሽ?...”
“…ጁላይ …”
“…የሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ማነው?....”
“…ባራክ ኦባማ….”
እዚህ ጋር ሳሌም ትንሽ የተናደደች መሰለች “… ይህን ሁሉ ጥያቄ የምጠየቀው ለምንድን ነው? …” የሚጠይቃት ሃኪም ላይ በትላልቅ አይኖቿ አፈጠጠች። “…የት ነው ያለሁት ንገሩኝ….”
( ….ቅድም … መጀመሪያ እይኖቿ ገርበብ ብለው ተከፈቱ ፦ የሳሌም። በሰከንዶች ውስጥም ሙሉ በሙሉ ተከፍተው ታይ ጀመር። አዎ ሆኗል። አዎ ተደርጏል። አዎ ተፈጽሟል። ሳሌም ነቅታለች። እንዲህ በፍጥነት መሆኑ ሃኪሞችን ቢያስደንቅም ሳሌም ተመልሳለች። አሁን ይኸው እያወራች ነው ፦ ከሃኪሟ ጋር። እኔም በግርምት፣ በድንቅ ሳሌምን አያለሁ። ወሬውን እሰማለሁ።…)
“…ሳሌም ስሚኝ… በደንብ ስሚኝ…” ሃኪሙ ቀረብ ብሎ አይን አይኗን እያየ “…ያለሽው ሆስፒታል ነው። ርዳታ እየተደረገልሽ ነው። ለምጠይቅሽ ጥያቄዎች መልስ መስጠት አለብሽ። የማስታወስ ችሎታሽን እንዳልጠፋ ወይም እንዳልቀነሰ ለማወቅ ያስችለኛል።….”
ሃኪሙ 'ሆስፒታል' ሲል ሳሌም ግራ በመጋባት አይነት አየችውና የተኛችበትን ክፍል ዙሪያውን መመልከት ጀመረች።
“…ሳሌም እይኝ። ወደ እኔ ተመልከች። ፎከስ …. ለመጨረሻ ጊዜ የምታስታውሽውን ንገሪኝ። የት ነበርሽ? ምን እያደረግሽ ነበር? ከማን ጋር ነበርሽ?...” ጥያቄውን ቀጠለ።
ሳሌም አሁንም ግራ በመጋባት ማየት ቀጠለች። ለጥቂት ጊዜ አይኗን ክፍት ክድን አደረገችና “…ት/ቤት ነበርኩኝ መስለኝ …. አይደል?.....” ጥያቄውን በጥያቄ መለሰች
“…እርግጠኛ ነሽ?....”
“…አይደለም!...” ሳሌም የሆነ ነገር ያገኘች ይመስል በደስታ “…ከክላስ መልስ….ካፌው … ካፈው ውስጥ ነበርኩኝ። ከ ‘ዲ’… ጋር ‘ከኔ መልዐክ’ …ጋር ነበርኩኝ….” ከዛ ቡሃላ ፊቷ ተቀየረ። በድንጋጤ፣ በጭንቀት ለሰከንዶች ጸጥ አለችና ጮኸች “…ዳሪክ…ዳሪክ…ዳሪክ… የኔ መልዐክ የት ነው ያለው?...ላየው እፈልጋለሁ። የት ነው ያለው?...ዳሪክ!…ዳሪክ!...ዳሪክ!...” ስሙን እየጠራች ከአልጋው ላይ ለመነሳት መጣጣር ጀመረች። ነገር ግን አቅሙም፣ ሃይሉም አልነበራትም። የሰውነቷም ህመም ሊያንቀሳቅሳት አልቻለም።
ከሁኔታዋና ከጩኸቷ የሆነውን ነገር ሁሉ እንዳስታወሰች ታስታውቃለች።
“…ሳሌም እንድትረጋጊ እፈልጋለሁ። ተረጋጊና ስሚኝ።…” ሃኪሙ ሊያረጋጋት እየጣረ።
ሳሌም ግን የምትረጋጋበት ሁኔታ ላይ አልነበረችም “…ዳሪክ!.. ዳሪክ!... የኔ መልዐክ!... የኔ ፍቅር!... ዳሪክ !... ዳሪክ!.... ላይህ እፈልጋለሁ፣… አይኑን ማየት እፈልጋለሁ…. አሳዩኝ? ልየው እባካችሁ?...እባካችሁ?...እባካችሁ? …. አይኑን ብቻ ልየው?... ልየው?...በህይወት እንዳለ ብቻ፣ ሲተነፍስ ብቻ ልየው?... የኔ መልዐክ፣ የኔ ቆንጆ፣ የማፈቅርህ፣… ልይህ አንድ ጊዜ….” እንባዋ እየወረደ፣ እያለቀሰች መለመን ጀመረች።
እንደገና ከተኛችበት ለመነሳት መታገል ጀመረች። ስትታገል ሰውነቷ ላይ የተሰካው አይቪ ና ሌሎች የህክምና መሳሪያዎች ሊነቀሉ ሆነ።
ሃኪሙ ጥብቅ አድርጎ ያዛት።
“…ዳሪክ!... የኔ መልዐክ!... በህይወት አለ ብቻ በለኝ? አይኑን ብቻ አሳዩኝ? ዳሪክ!...ዳሪክ!...” በሳግ ድምጿ እየተቆራረጠ
“…ሳሌም ስሚኝ… ተረጋጊና ስሚኝ። ዳሪክ አለ። በህይወት አለ። አልሞተም።…”
“…አልሞተም? በህይወት አለ?...” ማልቀሷን አቁማ በጉጉት ጠየቀች
“…እህ…” በአውንታ ነቀነቀ
“…የት ነው ያለው?...”
“…እዚሁ ሆስፒታል ውስጥ ነው ያለው። …ተጎድቷል ግን በህይወት አለ። …”
“…ላየው እችላለሁ? ልየው? … እባክህን?.. እባክህን?.. እባክህን?…” የሃኪሙን አይን አይን እያየች መለመን ጀመረች።
“…..የተኛበት ክፍል ድረስ ሄደሽ ብታይው ደስ ይለኛል። ችግሩ ግን አሁን ባለሽበት ሁኔታ አንድ ርምጃ እንኳን የመራመድ አቅም የለሽም። ከጥቂት ቀናት ቡሃላ ….”
“…ጥቂት ቀናት ?....” ሳሌም ደንግጣ ጠይቀች። ድንጋጤዋ ለሚቀጥለው ሰከንድ የምትተነፍሰውን አየር የተቀማች፣ ጸሃይ በአይኗ ፊት ለዘላለም እንዳትወጣ የተከለከለች ያህል ነው።
“….ቀናት ቀርቶ ደቂቃዎች መቆየት አልችልም። …. ‘ዲ’ ዬን፣ ‘የኔን መልዐክ’፣ ‘የኔን ውድ’፣… በየደቂቃው ‘የምወድሽ’… ብሎኝ የማይጠግበውን ሳላይ ከዚ በላይ አንድ ደቂቃ መቆየት አልችልም።…” ሳሌም እንደገና እንባዋ መውረድ ጀመረ። “…አልገባህም እኮ ዶክተር እወደዋለሁ እኮ! …. አፈቅረዋለሁ እኮ!... እኔ እኮ በጣም አብዝቼ፣ ከልቤ፣ ከነፍሴ እወደዋለሁ እኮ!.... እወደዋለሁ እኮ!... ፊቱን ማየት እፈልጋለሁ፣ አንድ ጊዜ ብቻ….”
ሳሌም አንድ ጊዜ ሃኪሙን፣ ሌላ ጊዜ ነርሷን፣ ደሞ እኔን በተማጽኖ እያየች፣ እንባዋ ከትላልቅ አይኖቿ እንደ ጉድ እየፈሰሰ ድምጿ እየተቆራረጠ
“..እ..ወ..ደዋለሁ እኮ!”
“..አፈ ..ቅ..ረ..ዋ..ለሁ እኮ!"
“…እ.ወደ..ዋለሁ እኮ!...”
“…እ..ወ..ደ..ዋ..ለ..ሁ እኮ!...”
“… ‘የምወድሽ’ ይለኛል እኮ …. ሲጠራኝ እኮ ‘የምወድሽ’…. እያለ ነው እኮ …. ማየት እፈልጋለሁ …. ‘የኔን መልዐክ’ ማየት አለብኝ…. ‘የምወድሽ’… ሲለኝ መስማት እፈልጋለሁ። እወደዋለሁ እኮ!... ፊቱን ማየት እፈልጋለሁ፣ አንድ ጊዜ ብቻ ….”
ሳሌም ተማጽኖዋ፣ አለማመኗ፣ የቃላት አወጣጧ በጣም ያሳዝን ነበር። ሃኪሙም ነርሷም የሚያደርጉት አጥተው፣ ግራ ተጋብተው ሲተያዩ ሃሳብ መጣልኝ። የዛን ሰሞን የተጀመረው ፌስ ታይም (Face Time)።
“…እኔ አንድ ሃሳብ አለኝ…” አልኩኝ
ሳሌምም ሌሎቹም ዞር ብለው ተመለከቱኝ።
“….እንዲተያዩ ማድረግ እንችላለን። ‘ፌስ ታይም’ በመጠቀም። የምፈልገው ሌላ ‘አይፓድ’ ወይም ‘አይፎን’ ነው አልኩኝ…” ስልኬን እያወጣሁ።
ሃኪሙና ነርሷ ዝም ብለው ሲያዩኝ እንዳልገባቸው ስለተረዳሁ የፈስ ታይም አጠቃቀምን አጠር አድርጌ አስረዳሁ።
“…በጣም ጥሩ ሃሳብ…” አለች ነርሷ “…የኔን ስልክ መጠቀም እንችላለን…”ብላ ስልኳን አቀበለችኝ።
የሳሌም ፊት በደስታ አበራ።
ርግቦቹን በ‘ፌስ ታይም’ እንዲተያዩ ለማድረግ የፈጀው ደቂቃዎች ነበር።
ሳሌም ለመጀመሪያ ጊዜ ዳሪክን ስታየው ዳሪክ ያለበት ሁኔታ የሚያስደነግጣት፣ ልቧን በሃዘን የሚሰብረው ነበር የመስለኝ። ግምቴ ግን በትልቁ ስህተት ነበር። የሆነው ተቃራኒ ነው።
ሳሌም አላለቀሰችም።
ሳሌም አላዘነችም።
ይልቅስ በእንባዋ ታጥቦ በቀላው ፊቷ ላይ የበቀለው የፈገግታ ዘር ነው ፦ ‘ስስ ፈገግታ’።
ቀና ብላ በእፎይታ አየችኝና “… በህይወት አለ፣ የኔ መለዐክ አልሞተም።….” የስልኩን መስታወት ቀስ ብላ በእጇ እየዳሰሰች
… ከዛ ቡሃላ አልተናገረችም፣ ቃል አልወጣትም። ዝም ብላ ታየው ጀመር። ያኔ ካፌው ውስጥ ቁጭ ብላ ስታየው እንደነበረው፣ ዝም.. ጸጥ ብላ በፈሻ ተጥቅለሎ ዳሪክ የማይመስለውን ዳሪክን ፊቱን በፍቅር፣ በመውደድ፣ በስስት ታየው ጀመር። ... ታየው ጀመር። ትክ ብላ …ውስጡን ሰርስራ፣ በዐጥንቶቹና በጅማቶቹ ላይ ተንሸራታ፣ በደም ባንቧዎቹ ውስጥ ዋኝታ፣ በልቡ ትርታዎች ላይ ተሰፈንጠራ ፦ አዎ ነፍሱ ላይ ነፍሷ ላይ የምትደርስ ‘ስኪመስል ታየው ጀመር።

👍47❤4
ስታየው፣....ስታየው፣...ስታየው፣ ….ስስ ፈገግታዋ ከናፍርቷን አልፎ እየሰፋ ጉንጮቿን፣ አይኗን እየሞላ ፊቷ ላይ ፈሰሰ። እርጋታዋ መጣ። ጸጥታዋ ሆነ። ሳሌም ተመልሳ ሳሌም ሆነች። ሳሌም ተመልሳ ‘ሳሌም፣ሳሌም’ አለች።
በሳሌም ፊት ላይ የሚታየው ያ ‘ስስ ፈገግታ’ ዋጋው የማይገመት፣ የከበረ የፍቅር ብርሃን ነው።
ስስ ፈገግታዋ … ውበት ነው። በጸደይ ወቅት በሰፊ ሜዳ ላይ በብዛት አንድ ላይ ከፈነዱ እንቡጥ አበባዎች የበለጠ ቁንጅና ነበረው። ውብ ነው። ያምራል። ይስባል።
ስስ ፈገግታዋ … ብሩህ ነው። ፈገ ግታዋ ከሳሌም አንባ ቡሃላ ብቅ ሲልና እየሰፋ ሲሄድ ከድቅድቅ የክረምት ጨለማ ላይ የማለዳ ጸህይ ብሩህ ሆና ብቅ ስትልና ብርሃኗ እየጨመረ ሲሄድ ያህል ነው።
ስስ ፈገግታዋ … የእውነት ነው ህይወት አለው። በቀለማት መስመር ክንፎቹ ያማረ ቢራቢሮ ከታሰረበት ቅርፊቱ ተላቆ፣ ነጻ ሲወጣ ህይወት ሲዘራ፣ ሲበር፣ ክብ እየዞረ ሲጨፍር፣ ሲደንስ …. ይህንንም ከማየት ይበልጣል።
ስስ ፈገግታዋ …. የሳሌም!
*
*
ይቀጥላል....
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
በሳሌም ፊት ላይ የሚታየው ያ ‘ስስ ፈገግታ’ ዋጋው የማይገመት፣ የከበረ የፍቅር ብርሃን ነው።
ስስ ፈገግታዋ … ውበት ነው። በጸደይ ወቅት በሰፊ ሜዳ ላይ በብዛት አንድ ላይ ከፈነዱ እንቡጥ አበባዎች የበለጠ ቁንጅና ነበረው። ውብ ነው። ያምራል። ይስባል።
ስስ ፈገግታዋ … ብሩህ ነው። ፈገ ግታዋ ከሳሌም አንባ ቡሃላ ብቅ ሲልና እየሰፋ ሲሄድ ከድቅድቅ የክረምት ጨለማ ላይ የማለዳ ጸህይ ብሩህ ሆና ብቅ ስትልና ብርሃኗ እየጨመረ ሲሄድ ያህል ነው።
ስስ ፈገግታዋ … የእውነት ነው ህይወት አለው። በቀለማት መስመር ክንፎቹ ያማረ ቢራቢሮ ከታሰረበት ቅርፊቱ ተላቆ፣ ነጻ ሲወጣ ህይወት ሲዘራ፣ ሲበር፣ ክብ እየዞረ ሲጨፍር፣ ሲደንስ …. ይህንንም ከማየት ይበልጣል።
ስስ ፈገግታዋ …. የሳሌም!
*
*
ይቀጥላል....
ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍46❤2
#ፍንጣሪው!
#አሌክስ_አብርሃም
የሆቴሉ በረንዳ ላይ አራት ሰዎች እየጮሁ ፖለቲካ ያወራሉ፣ እዚህ ጋ ብቻየን ቡና እየጠጣሁ ለተቀመጥኩ እኔ ሳልፈልግ ወሪያቸው ይደርሰኛል። በወሪያቸው መሀል አንዱ ጮክ ብሎ ...
"ያኔ ቦንብ ተወርውሮበት የሳቱት ጊዜ ..." አለ
ሌላኛው አቋርጦት "አልሳቱትምኮ" አለ። ዞር ብየ አየሁት፤ ምን እኔ ብቻ የሆቴሉ ሰው በሙሉ ወደተናጋሪው ዞረ። ደልደል ያለ ወዛም ጎልማሳ ነው። እኔም እንደሳቱት ነበር የማውቀው! የዚህ አገር ዜና ምኑ ይታመናል ብየ ጆሮየን አቆምኩ! አንዱ ከጥግ በማያገባው ገብቶ " ካልሳቱት እንዴት የምስራቹን (ማለቴ መርዶውን) እስካሁን ደበቁን? " አለ።
"ስተውታል እንጅ! ወዲያው መግለጫ ሰጥቶ የለም እንዴ?!" ሌላኛው በክርክር ድምፅ መለሰ።
" ምናለ እኔን ብትሰሙኝ ዓመት አላወራ ፤ ደብቀውን ነው እንጅ አልሳቱትም፣ 'የቦንቡ ፍንጣሪ እሱን ጭንቅላቱ ላይ ምክትሉንና አማካሪዎቹን ደግሞ ልባቸውን አግኝቷቸዋል ብሎ አንድ የታሪክ ምሁር ነግሮኛል" አለ፤ ጋባዢ ነው መሰል ማንም አልተከራከረውም!
"ለዛ ነዋ በሶስት ቀን ሰላሳ ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪ ያስጨፈጨፈው" አለ ከመካከላቸው በዝምታ የቆየው ሰውየ!
"ማን?" አለ ያ በማያገባው የሚገባው ሰውየ ግራ ገብቶት።
"ግራዚያኒ ነዋ !" አለው ደልዳላው እና ወዛሙ ሰውየ! ሁሉም ጉጉቱ ረገብ ብሎ ወደየራሱ ጨዋታ ዞረ። እኔ ደግሞ ፖለቲካ መስሎኝ ለካስ ታሪክ ነው የሚያወሩት! በነሞገስ አስገዶም ቦንብ ስለተወረወረበት ግራዚያኒ ምናምን። ድሮም ጮክ ብለው ሲያወሩ መጠርጠር ነበረብኝ።
ቡናየን ፉት አልኩና ቀና ብየ ወደሰማይ አየሁ ፤ ሰው አልባ የመንገደኞች አውሮፕላን በዝግታ የሚንሳፈፉበት ደመናማ ቀን ነበር። እስቲ ቡና ድገሚኝ!
ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች

👍36😁27🔥4❤3
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ስድስት፦ የሳሌም ሰሌዳ
©ሃሴድ አጋፔ ፍቅር
የኔ መልዐክ… የኔ ቆንጆ፣ የልቤ ግማሽ ዳሪክ ፦
ዛሬ ጃንዋሪ 15, 2011 ሲሆን ቀኑ ደሞ ቅዳሜ ቀን ነው። ያለኸው ኤቨረት (Everett) ከተማ ውስጥ የሚገኝ የህሙማን እንክብካቤ ማዕከል ነው። ስትነቃ አጠገብህ ከሌለው አትደንግጥ እኔ በፍጥነት እመጣልሃለሁ።
ያንተ ብቻ ሳሌም!
ይህ ጹህፍ የሰፈረው ዳሪክ የተኛበት ክፍል ውስጥ ግድግዳ ላይ በተሰቀለ ትንሽ ነጭ ሰሌዳ ላይ ነው። በቀላሉ በዳስተር ወይም በእጅ ዳሰሳ መጥፋት በሚችል የተለያየ ቀለማት ባላቸው ማርክሮች መልዕክቱ ተጽፏል። ሳሌም ይህንን መልዕክት በየቀኑ፣ በጥንቃቄ አስውባ ትጽፋለች። መሽቶ ሲነጋ የወሩን ቀን ትቀይራለች። የሳምንቱን ቀን ታድሳለች፦ ሰሌዳው ላይ። ማዕከሉ ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ነርሶች ይህንን Salem’s Board (የሳሌም ሰሌዳ) ብለው ሰይመውታል።
ይህ የሳሌም መልዕክት ብቻ የሚጻፍበት የሳሌም የፍቅር ሰሌዳ ነው። ዳሪክ ከገባበት ሰመመን ሲወጣ፣ አይኖቹን ሲከፍት፣ ሲነቃ ምናልባት ሳሌም አጠገቡ ከሌለች እንኳን እንዳይደነግጥ፣ እንዳይሸበር …ሰሌዳው ላይ የተጻፈውን መልዕክት አይቶ እንዲረጋጋ በሳሌም ታስቦ የተዘጋጀ የሳሌም የፍቅር ቦርድ ነው።
ሰባት ወራት አልፈዋል…
ሳሌም በሆስፒታሉ ውስጥ ከነቃች ቡሃላና ዳሪክ በህይወት መኖሩን ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ ከ አደጋው ለማገገም የወሰደባት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ነበር። በአስደናቂ ፍጥነት ሙሉ በሙሉ ድና ተነሳች። ሃኪሞች፣ ነርሶች፣ የሆስፒታሉ የአካል ብቃት ባለሙያዎች (Physical Thearapists) የሚሉትን፣ ከአደጋው ለማገገም የሚሰጡትን መመሪያና ልምምድ ተግታ ስትሰራ ለሆነ ተልዕኮ እየተዘጋጀች ያለች ነበር የምትመስለው። የትጋቷም ፍሬ ሲታይ ጊዜ አልፈጀም። ሳሌም ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተነስታ፣ ወደ ድሮ አካላዊ ማንነቷ ተመለሰች።
ዳሪክ ግን ያው …ከአደጋው ቡሃላ ያለው ዳሪክ ነው። አሁንም አይኖቹ እንደተከደኑ ነው። በማሽን ርዳታ ይተነፍሳል። በሆዱ ላይ ባለ አነስተኛ ቀዳዳ በአነስተኛ ቱቦ በማሽን ምግብ ይሰጠዋል። ዳሪክ አሁንም ጥልቅ ሰመመን ውስጥ ያንቀላፋል። ሆስፒታሉ ውስጥ ለስድስት ሳምንታት ያህል ሲረዳ ከቆየ ቡሃላ አሁን ወደ ሚገኝበት፣ ተመሳሳይ ታካሚዎች ርዳታና እንክብካቤ ወደሚያገኙበት ማዕከል ተዘዋወረ። ሰባት ወራት… ዳሪክ አሁንም ዝም ብሎ በሰላም ተኝቷል። ሰባቱ ወራቶች ለዳሪክ አልጋ በአልጋ አልነበሩም።ሰባቱ ወራት መኝታ፣ ሰመመንና እንቅልፍ ብቻ አልነበሩም። ሶስት ጊዜ በተለያዩ ኢንፌክሽኖች ሆስፒታል ገብቶ ታክሞ ወጥቷል።
ባለፉት ሰባት ወራት በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ሳሌም ሁሌም ከዳሪክ ጎን ናት። ሳይጋነን ሃያ አራት ሰዐት አጠገቡ ነበረች። ምናልባት ወደ ቤተ ከሄደች ልብስ ለመቀየርና፣ ሻወር ለመውሰድ ነው። ዳሪክ በተኛበት አነስተኛ ክፍል ውስጥ ቀኑን ሙሉ አብራው ነች። ሌሊት ደሞ ከአልጋው አጠገብ አነስተኛ የምትታጠፍ አልጋ ዘርጋታ ትተኛለች። ሁሉን ነገር ትታ ጊዜዋን በሙሉ ሙሉ በሙሉ ዳሪክን ለመንከባከብ ሰጥታ ነበር።
በጸሀያማ ቀን … ሳሌም ከዳሪክ ጋር ናት።
በዝናባማ ውሽንፍር ቀን … ሳሌም ዳሪክ አጠገብ ነች።
በረዶ ለቀናት ሳያቋርጥ ቢወርድ …ሳሌም ከዳሪክ ጎን አልሄደችም።
ከሰኞ እስከ አርብ … ሳሌም ከዳሪክ ጋር አብራው ነበረች።
ቅዳሜና እሁድ ሳሌም ….ዳሪክን ብቻውን አልተወችውም።
ሳሌም በትላልቅ ውብ አይኖቿ የተከደኑትን የዳሪክ አይኖች እያየች፣ እንደ አጥር ዙሪያውን ከብባው አብራው ነበረች። ሳሌም ዳሪክን ለ አፍታ መለየት አልቻለችም።
ባለፉት ወራት እኔና ሳሌም ከመቀራረባችን የተነሳ እንደ እህቶች ሆነናል። ባለኝ ጊዜ በሙሉ፣ ከሳምንቱ አብዛኛውን ቀን ከሳሌምና ዳሪክ ጋር አሳልፋለሁ። ሁለቱን ከማየት የበለጠ ደስ የሚል ነገር ምን አለ? የሁለቱን ፍቅር ማየት በራሱ ህይወት ነው። ፍቅር የለም ትለኛለህን? መውደድ ሞተ ትይኛለሽን? እነዚህን ወጣቶች ማየት ግን፣ እነዚህን ልጆች መመልከት ግን ፍቅር ዛሬም መኖሩን ህያው ማረጋገጫ ነው።
ዳሪክን ለመንከባከብ ከሳሌም ጋር ብዙ ሌሊቶች አሳልፌያለሁ። ሳሌም ሌሊት ስትተኛ አንድ አይኗን ብቻ ጨፍና የምትተኛ ነው የምትመስለኝ። አንዳች ኮሽታ ከሰማች፣ ዳሪክ የሚተነፍስበት ማሽን ትንሽ ድምጽ ካወጣ፣ የነርሶች ኮቴ ከተሰማ…ሳሌም ተነስታ ቁጭ ብላለች። የዳሪክ ነገር ፈጽሞ፣ ፈጽሞ አይሆንላትም።
ሳሌም ትነቃለች ፦ እጅግ ማልዳ። ተነስታ የዳሪክን እጆች ይዛ ትጸልያለች። ቀኑን በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፋ ትሰጣለች። በመቀጠል የመጀመሪያ ስራዋ የሳሌም ሰሌዳ ላይ የተጻፈውን ነገር አጥፍታ እንደገና አሳምራ መጻፍ ነው። ቀኑን ሰሌዳው ላይ ትቀይራለች። መልዕክቱን በተለያዩ ቀለማት አሳምራ ስትጽፍ፣ ጥንቃቄዋ የሆነ ውስብስብ ጥበብ …አርት የምትሰራ ነው የምትመስለው።
አንድ ማለዳ በሰሌዳው ላይ በጥንቃቄ ስትጽፍ ገርሞኝ አያታለሁ። “…ሴሌምዬ ትገርሚኛለሽ እኮ አጻጻፍሽ፣ጥንቃቄሽ …”
ሳሌም ፈገግ አለች “…አየሽ ሳዬ…. የኔ መልዐክ፣ የኔ ቆንጆ የሚነቃበት ጊዜን አላውቀውም። ምናልባት ምግብ ለማምጣት ወይም ባዝ ሩም በሄድኩበት ቅጽበት ቢነቃ … የት ነው ያለሁት? ቀኑ መቼ ነው? ብሎ ሊደነግጥ አይገባውም።…”
ሳሌም መጻፏን ቀጠለች።
ሳሌም እንግዲህ እንዲህ ናት። ለዳሪክ ያላት ሃሳብ ይህን ያህል ነው። አጠገቡ በሌለችበት ጥቂት ደቂቃዎች ቢነቃ እንኳን ብላ እስክታስብለት ድረስ። ብዙዎች እኮ እኔን ጨምሮ ይህ ልጅ እስከ መጨረሻው ላይነቃ ይችላል ብለን አምነን ሊሆን ይችላል። ለሳሌም ግን የዳሪክ ከዚህ ከገባበት ሰመመን መውጣት፣ መንቃት ጥያቄ አይደለም። እንደሚነቃ አምናለች። እንደሚነቃ አይታለች። እንደሚነቃ እርግጠኛ ነች። የጸሀይን መውጣትና መግባት ያህል የዳሪክ መንቃት ለሳሌም የረገጠ ሃቅ ነው። የሷ ጥያቄ … መቼ ነው የሚነቃው የሚለው ነው? የማታውቀው ያ ዳሪክ አይኖቹን የሚከፍትበትን እለት ነው። የሳለም ዝግጅትም ለዛች እለት ነው።
ቦርዱ ላይ መጻፍ ያለባትን ከጻፈች ቡሃላ ሳሌም ዳሪክን ንጽህና ትጀመራለች። ጸጉሩን ታበጥራለች። ፊቱንና ጥርሱን ታጸዳለች። ጥፍሩ መቆረጥ ካለበት በጥንቃቄ ትቆርጣለች። የመኝታውና አንሶላና አልጋ ልብስ ትቀይራለች ወይም ነርሶቹ እንዲቀይሩ ትጠይቃለች። ክፍሉ ውስጥ ያሉትን ጠረጴዛዎች ወንበሮች አጽድታ ታዘጋጃለች።…የዳሪክ ክፍል ሁሌም ስንዱ፣ ጽድት ያለና የተዋበ ነው።
ይህን ሁሌ ለምን እንደምታደርግ ስት ጠይቅም …መልሷ “…የኔ ፍቅር ሲነቃ ምስቅልቅል ያለ ቤት ውስጥ ራሱን ማግኘት የለበትም…” በአጭሩ መልሷ ይህ ነው።
ሳሌም ለዳሪክ የሳምንቱን ቀናት መርሃ ግብር አውጥታለች።
ሰኞ፦
…የሙቪ ቀን ነው። ሳሌም ከዳሪክ ጋር ቁጭ ብላ፣ እጁን ይዛ ሙቪ ታያለች። ብዙ ጊዜ ሁለቱም የሚያዩት የፍቅር ሙቪ ነው። ዲር ጆን፣ ዘ ኖት ቡክ ከቆዩትም ታይታኒክና ስሊፕለስ ኢን ሲያትል የሚሉትን ፊልሞች ሳሌም ስታይ ደርሼ አውቃለሁ።
ማክሰኞና አርብ ፦
… ጠዋት የመጻህፍት ቀን ነው። ሳሌም ዳሪክ የሚወዳቸውን የተለያዩ የአማርኛና የእንግሊዝኛ መጻህፍት ለዳሪክ ድምጿን ልስልስ አድርጋ ታነብለታለች። ከሰዐት ቡሃላ ደሞ ቀስ እያለች የእግሮቹንና የእጆቹን ጡንቻዋች ነርሶቹ ያሳዯትን ስፖርት ታሰራዋለች። ይህም በመኝታ ብዛት አካሉ እንዳይመነምን ይረዳዋል።

👍40🥰6❤4👏2