አትሮኖስ
284K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
521 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍83
#ትንግርት


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በማግስቱ ሁሴን ገና በጊዜ አንድ ሰዓት ላይ ነበር ወደቤቱ የገባው፡፡ ቀኑን ሙሉ በአንድ ሀሳብ አይምሮው ተጠፍንጎ ስለ ምስጢር ሲያስብ ነው የዋለው፡፡ እንደገባ ያረፈበት ለወትሮው ምቾትን የሚለግሠው የቤቱ ሶፋ ዛሬ ቆረቆረው፡፡ ሞባይሉን ከኪሱ አወጣና መጎርጎር ጀመረ፡፡ ቀን ደውላለት ነበር... ያደረጉትንም የስልክ ልውውጥ ቀድቶታል... ከፈተው፡፡ ደጋግሞ ሲያዳምጠው ይሄ ለ13ተኛ ጊዜ ነው፡፡ እያንዳንዷን ከአንደበቷ የወጡትን ቃላቶች ሸምድዳቸው ተብሎ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተላለፈበት ፍርደኛ ይመስላል፡፡ ሞባይሉ ማውራት እሱ ማዳመጥ ጀመረ፡፡

‹‹ከየት ነው ምትደውይው?››

‹‹ከየትስ ቢሆን ምን ይፈይድልሀል?.ይልቅ ለምን ደወልሽ?የሚለው ጥያቄ አይቀልም?››

‹‹እንደዛ ብዬ እንኳን አልጠይቅሽም፤ ዋናው መደወልሽ ነው እንጂ የደወልሽበት ምክንያት ብዙም አያስጨንቀኝም፡፡››

‹‹የውክልናው ወረቀት ደረሠህ?›› ቀጭን ማራኪ ድምፅ፡፡

‹‹አዋ>>

ደርሶኛል...ታደርጊዋለሽ ብዬ ግን አላመንኩም ነበር፡፡››

«ለምን?»

‹‹እኔ እንጃ፤ይሄን ያህል እንዴት ልታምኚን ቻልሽ... ?ግራ የሚገባ ነገር ነው፡፡ በነገራችን ላይ እስከ አሁን በእኛ ጋዜጣ ላይ ከታተሙልሽ ሃያ ሰባት የሚሆኑ አጫጭር ልብወለዶች መካከል አስራ ሁለቱን መርጬ አንብበው አስተያየታቸውን እንዲሠጡኝ ለሁለት ታዋቂ ደራሲያን ሠጥቼያቸው ነበር...፡፡ >>

ጉጉት በማይታይበት የቀዘቀዘ ድምፅ‹‹ጥሩ ነው።>>

‹‹አንደኛው ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? ‹ይሄ ድርሠት በአማተር ፀሀፊ ተጻፈ ብትለኝ ፍፁም አላምንህም፤ እርግጠኛ ነኝ ፀሀፊው አንተ ራስህ ነህ፤ በስምህ ላለማሳተም መቼም በቂ ምክንያት ይኖርሀል፤ ምስጢር የሚለውን የብዕር ስም ግን ለምን መጠቀም እንደፈለክ ፍፁም አልገባኝም ፡፡ ›ነበር ያለኝ፡፡

‹‹ታዲያ ለምን በራስህ ስም አታሳትመውም?››

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ?››

‹‹እውነቴን ነው፡፡››

‹‹ቀልዱን አቁሚ... በዚህ ወር መጨረሻ መፅሀፍሽ ይታተማል፤ የምረቃ ፕሮግራም ለማዘጋጀት አስቢያለሁ፤ዝግጅቱ ላይ መቼም ትገኚያለሽ?››

‹‹ኪ...ኪ..ኪ.›› ከት ብላ ሳቀች፡፡ደነገጠ፡፡ ሣቋ ከሆነ ከሚያውቃት ሴት ሳቅ ጋር ተመሳሰለበት፡፡

‹‹ምን ያስቅሻል?››

‹‹አታስብ አልመጣም፡፡››

‹‹ኦ! ....ኧረ በፈጠረሽ ልታቀውሽኝ ነው? ስራዬን በትክክል መስራት እንኳን እየተሳነኝ ነው እኮ፡፡››

‹‹የማይመስል ነገር፤ በአካል እኮ አታውቀኝም::>>

‹‹ምንም ሁኚ ምንም አፈቅርሻለሁ፤ፍፁም ልረሳሽ አልችልም... ነፍስሽን ነው ያፈቀርኳት፤እስቲ በፈጠረሽ ስለ ራስሽ ጥቂት ንገሪኝ...?>>

‹‹ስለ አቋሜ ማለትህ ነው?››

«ይቻላል አዎ::>>

‹‹እንግዲህ እኔ ሦስት አይነት ሰው ነኝ፤እንደ አያቴ፣እንደ ጓደኞቼ እና እንደ አፋቃሪዎቼ...>>

<<ብታብራሪልኝ?>>

‹‹አያቴ ነፍሷን ይማርና የእኔ መላአክ ነበር የምትለኝ፤እሷ ስታደናንቀኝ ክንፍ ሁሉ ያበቀልኩ መስሎ ይሰማኝ ነበር፤ እንደሷ ምልከታ እንከን አልባ አይነት ነኝ፡፡እንደ ጓደኞቼ ደግሞ ቆንጆም ያልሆንኩ ፤ የማላስቀይምም እንደው በድርባቡ አርገው ነው የሚገልፁኝ፡፡ አፍቃሪዎቼ ደግሞ አያቴ እንደምትለው መላአክ ነበርሽ ይሉና፤ ዳሩ ምን ያደርጋልን!! ይጨምሩበታል፡፡››

‹‹ምን ማለት ፈልገው ነው?››

‹‹ቆንጆ መሆኔን አረጋግጠው ...አይነ ስውር በመሆኔ የተሰማቸውን ቅሬታ ለመግለፅ ፈልገው ..››ንግግሩ ተቋረጠ፡፡

<< ትሁን...አይነስውር ትሁን፤ከፈለገች በዊልቸር ትሂድ፤የፈለገችውን ትሁን፤እወዳታለሁ….አፈቅራታለሁ፡፡ከራሱ ጋር ሲያወራ በእጁ ያንከረፈፈው ሞባይሉ ጮኸ፡፡ ኤደን ነበረች፡፡

‹‹ደህና ዋልሽ?››

‹‹ደህና ነኝ..ምነው ጠፋህ?››

‹‹ስራ በዝቶብኝ ነው፡፡››

«የት ነህ?>>

‹‹ቤት ነኝ፡፡››

<<እየመጣሁ ነው፡፡››

<<ወዴት?>>

<<አንተ ጋር ነዋ>>::»

‹‹የተጨናነቀ ስራ ላይ ነኝ፤ብቻዬን መሆን ነር የምፈልገው፡፡››

‹‹ናፍቀኸኛል እኮ!!››

‹‹ከናፈቅኩሽ ነገ እንገናኛለን... ከደበረሽ ደግ ጓደኞችሽ ጋር መሄድ ትችያለሽ፤ እኔን ግን ተይኝ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ...

ቻው፡፡››ብሎ ስልኩን ጆሮዋ ላይ ጠረቀመባት፡፡ እንዲህ አዕምሮው በተጨናነቀበት ወቅት ከኤደን ጋር መገናኘት ፍፁም አይፈልግም፡፡ በጭቅጭቋ ይበልጥ ታበግነዋለች‹‹ ቅራቅንቦ ጥያቄዎቿን መመለስ ከቀን ስራ በላይ ይከብዳል፡፡›› ይላል፡፡

‹‹ምን ሆነሀል?ምነው ጠቆርክ?...ከማን ተጣለህ?.. ካመመህ ሀኪም ቤት እንሂድ፡፡›› ወዘተ፤ሳይለያዩ ይሄን ሁሉ ዘመን እንዴት አብረው ሊቆዩ እንደቻሉም ግርም ይለዋል፡፡ ስለ አብሮነታቸው ዘውትር እቅድ እንዳወጣች ነው፡፡ አንድም ጊዜ ግን ተሳክቶላት አያውቅም፤ያም ሆኖ ግን ተስፋ አትቆርጥም፡፡ ከተቀመጠበት ተነሳና ሳሎን ውስጥ ተንጎራደደ፡፡ አዕምሮው ፍፁም ሊረጋጋለት አልቻለም፡፡ ወደ ውጭ ሊወጣ ፈለገ፡፡ ሠዓቱን ተመለከተ ፤ሁለት ሠዓት ተኩል ይላል፡፡ ሀሳቡን ቀየረና ስልኩን ደወለ፤ ዘና የሚያረገው ሰው ፈለገ፡፡

‹‹ሄሎ... ትንግርት፡፡››

‹‹እሺ የኔ ፍቅር፡፡››

‹‹አለሁልሽ .. የት ነሽ?››

‹‹ቤተ መንግስት የራት ግብዣ ላይ ነኝ፡፡››

ፈገግ አለ ‹‹ከምሬ ነው፡፡››

‹‹አንድ ደንበኛዬ ጭን ላይ ቁጭ ብዬ እያጋልኩት ነው፡፡››

‹‹መምጣት አትችይም?>>

‹‹ቢዝነስ እኮ ተነጋግሬአለሁ>>

<<ስንት?>>

‹‹የዛሬው ዋጋዬ አራት መቶ ሃምሳ ነው..... ከትላንቱ ትንሽ ረከስ ብያለሁ፡፡››

‹‹ወደ ትላንቱ ዋጋሽ ልመልስሻ ..እኔ ጋር ነይ::>>

‹‹ቀነዘረብህ እንዴ?››

‹‹ብዙም አይደል፤ ብቻ አስፈለግሽኝ... ያቺን ደራሲ ለሠዓታትም ቢሆን እንድታስረሽኝ እፈልጋለሁ፡፡››

<ኦ! ... ምን አይነት እድለኛ ነች ባክህ ... ቀናሁባት፡፡ ለማንኛውም መጣሁ፡፡ የተሻለ ዋጋ ከከፈልከኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቴ በሸርሙጦች መተዳደሪያ ደንብ የተከበረ ነው፡፡››

‹‹በሙሉ ሰርዥው›› አለ ቆጣ ብሎ፡፡ በከፊል ስትል ምን ማለት እንደፈለገች ገብቶታል፡፡ ደንበኛዋ እንዳይቀየማት አንዴ ከውጥረቱ እንዲረግብ ረድታው ለመምጣት ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ለሁሴን አይመቸውም፡፡ ቢያንስ እሱ ጋር በምታድርበት ቀን የሌላ ወንድ ጠረን ይዛበት እንድትመጣ አይፈልግም፡፡ተሠነባበቱና ስልኩን ዘግቶ ወደ ሶፋው ተመለሰ፡፡

ሪሞቱን ከጠረጴዛው ላይ አነሳና ቴሌቪዢኑን ከፈተ፡፡ ምን አይነት ፕሮግራም እየተላለፈ እንደሆነ ለማሰብ ሳይጨነቅ ወደ ሀሳቡ
ተመልሶ ተዘፈቀ፡፡ ረዥም ቆንጆ ውብ ወጣት በአየር ላይ እየተንሳፈፈች ወደ እሱ ስትመጣ ይታየዋል፡፡ በግራ እጇ አቅጣጫ መጠቆሚያ ዘንግ ይዛለች፡፡ በቀኝ እጇ ደግሞ አዲስ የፈነዳ እምቡጥ ፅጌሬዳ አበባ ይታየዋል፡፡አይኖቿ አይታዩም፤በጥቁር መነፅር ተሸፍነዋል፡፡ ፈገግ እያለች አበባውን እንዲቀበላት ትማጸነዋለች፡፡ እሱ ደግሞ አበባውን ከመቀበሉ በፊት ከአይኖቿ ላይ የሚያስጠላውን ጭለማ መነፅር አውልቃ እንድትጥለው .. የማያዩትን አይኖቿን ቀጥታ ማየት እንደሚፈልግ እየነገራት ሳለ የሳሎኑ በር ተንኳኳ፡፡ ከጣፋጭ ሀሳቡ ነቅቶ ተነስቶ ከፈተ፡፡
👍11012😁2👎1🔥1😢1
የመጣችለት ሲጠብቃት የነበረችው ትንግርት አልነበረችም.... ኤደን እንጂ፡፡ ወደ ውስጥ ተመልሶ ሶፋው ላይ ተዘረፈጠ፡፡ኤደን ተሽቀርቅራለች፡፡ ከታች ሠማያዊ ጅንስ ሱሪ፣ከላይ በቀይና በጥቁር ቀለም የተዥጎረጎረ ሹራብ ለብሳለች፡፡ ወርቃማ ሉጫ ፀጉሯን ትከሻዋ ላይ ነስንሳዋለች፡፡ በንዴት የመነጨው ላቧ ጠይም ፊቷ ላይ ወዝ ረጭቶ
ተጨማሪ ውበት ለግሷታል፡፡ የለበሰችው ሹራብ ሰውነቷ ላይ ጥብቅ ስላለ ጡቶቿ ወደ ፊት ቀድመው አይን ውስጥ ይመሠጋሉ፡፡ የቁመቷን ማጠር ባደረገችው ባለ ተረከዝ ጫማ አካክሰዋለች፡፡

‹‹ቴሌቪዥን ላይ ለማፍጠጥ ነው አትምጪ ያልከኝ?›› በመውረግረግ ወደ ምትቀመጥበት ቦታ እያመራች የመጀመሪያ ጥያቄዋን ሠነዘረች፡፡

‹‹አይደለም፡፡›› አላት ሪሞቱን ተጠቅሞ ቴሌቪዥኑን እያጠፋ፡፡ አበሳጭታዋለች፡፡ካለ ባህሪዋ እንደ ችኮነቷ የሚያማርረው የለም፡፡ ‹‹ነገሮችን ከራሷ ፍላጎት አንፃር እንጂ ከሌሳ ሠው ፍላጎት አንፃር መዝኖ ማገናዘብ ፍፁም አልፈጠረባትም›› ሲል ሁሌ ይወቅሳታል፡፡››

<<እና?>>>

‹‹ቀጠሮ ስላለብኝ ነው፡፡››

‹‹ቀጠሮ? .... የምን ቀጠሮ? ... ከማን ጋር ?››

‹‹ከትንግርት ጋር፡፡››

‹‹ኧረ! .. ከሸርሙጣዋ ጋር ቀጠሮ!››

‹‹ሁላችንስ ሸርሙጦች አይደለን? እሷ ሸርሙጣ መሆኗን በአዋጅ ያስነገረች የአደባባይ ሸርሙጣ ስትሆን እኔ እና አንቺ ደግሞ ጓሮ ለጓሮ ከሠው ተሸሽገን በሚሥጥ የምንወሰብ ሸርሙጦች ነን፡፡ አሁንም እኮ የመጣሽው እንድንሸረሙጥ ፈልገሽ መሠለኝ >>

ሠውነቷ ተንቀጠቀጠባት፣የጨጓራዋ ቁስለት ሲለበልባት ይሰማታል፡፡ በትንግርት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ለቀናቶች በተደጋጋሚ ተኮራርፈውም ያውቃሉ እስከአሁ የተለወጠ ነገር ባይኖርም፡፡ ብዙ ጊዜ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ታስብና መሸነፍ ደግሞ ያስጠላታል.... እልህ ትገባለች፡፡‹‹እና ተመልስ እንድሄድልህ ትፈልጋለህ?››

‹‹እንደፈለግሽ፡፡››...

ይቀጥላል


ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ   አደለም ከ 100,000 በላይ አባላት ውስጥ ቢያንስ ይሄን የምታነቡ እንኳን subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ።
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1128🥰7🤔1
Forwarded from Rihrahe Diabetes Healthcare
ርህራሔ የስኳር ጤና ክብካቤ

አገልግሎት ለማግኘት እና ለማንኛውም መረጃ:

Subscribe Our Telegram Channel
> https://tttttt.me/Rihrahe

Join Our Telegram group
> https://tttttt.me/rihrahe_DM

Visit our Website:  
> http://rihrahe.com

Email:   info@rihrahe.com
Contact us   0995-440344
                       0947-964189

#diabetes #prediabetes
#rihrahe #healthcare

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፣

¤ የስኳር ጤና ራስ አገዝ ስልጠና / ትምህርት
¤ ሀሳብዎን በእኛ ላይ የሚጥሉበት ሁለንተናዊ የመደበኛ ክትትል እና አባልነት አገልግሎት
¤ 24 ሰዓት የማስታመም አገልግሎት
¤ የነርሰ አገልግሎቶች፣
¤ መሰረታዊ የጤና ቅድመ ምርመራ
¤ የላብራቶሪ አገልግሎት
¤ መደበኛ የጥርስ እጥበት
¤ የቤት ለቤት የፊዝዮቴራፒ አገልግሎት
¤ ስኳር መከላከል ኘሮግራም
¤ የስነ ምግብ ስልጠና
¤ ማህበራዊ አገልግሎት
¤ እና ሌሎች ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎቶችን ያሉበት ድረስ መጥተን እንሰጣለን።



Office Address Addis Ababa
Jemo, Kafdem Mall, F-306
👍152
#ትንግርት


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


.....‹‹ሁላችንስ ሸርሙጦች አይደለን? እሷ ሸርሙጣ መሆኗን በአዋጅ ያስነገረች የአደባባይ ሸርሙጣ ስትሆን እኔ እና አንቺ ደግሞ ጓሮ ለጓሮ ከሠው ተሸሽገን በሚሥጥ የምንወሰብ ሸርሙጦች ነን፡፡ አሁንም እኮ የመጣሽው እንድንሸረሙጥ ፈልገሽ መሠለኝ >>

ሠውነቷ ተንቀጠቀጠባት፣የጨጓራዋ ቁስለት ሲለበልባት ይሰማታል፡፡ በትንግርት ጉዳይ ብዙ ጊዜ ተጨቃጭቀዋል፡፡ ለቀናቶች በተደጋጋሚ ተኮራርፈውም ያውቃሉ እስከአሁ የተለወጠ ነገር ባይኖርም፡፡ ብዙ ጊዜ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ታስብና መሸነፍ ደግሞ ያስጠላታል.... እልህ ትገባለች፡፡‹‹እና ተመልስ እንድሄድልህ ትፈልጋለህ?››

‹‹እንደፈለግሽ፡፡››...

መሄድ አልፈለገችም፡፡ የምትወደውን ገላ፣በፍቅር የምትሰቃይለትን ሠውነት፣የምትራብለትን ትንፋሽ አይኗ እያየ አለሌ ለምትላት ትንግርት አስረክባ ወደ ቤት ሄዳ የሠላም እንቅልፍ እንደማትተኛ ስለገባት እዚሁ ቆይታ እውነታውን በመጋፈጥ ለመፋለም ወሰነች፡፡በዚህ ቅፅበት ነበር መለስ ብሎ የነበረው የሳሎን በር በድንገት ተበርግዶ የተከፈተው፡፡

እንደመንገዳገድ ብላ ቆመች ትንግርት ነች፡፡ ከላይ ከደረቷ እስከ እምብርቷ  ከስር ደግሞ ከመቀመጫዋ ብዙም የማይረዝም እራፊ ጨርቅ እላይዋ ላይ ጣል አድርጋለች፣ ከትከሻዋ አልፎ ወደ መቀመጫዋ የሚጠጋውን እንደ ሀር የሚጠቁረ ፀጉሯን በትግሬዎች ባህላዊ ሹሩባ አሰራር ተሰርታ አሽሞንሙናዋለች፡፡ ጎላ ጎላ ያሉ አይኖቿን በኩል ይበልጥ ደምቀዋል፡፡ በተረፈ ፊቷ ንፁህ ነው፡፡ በሜካፕ አልተጨማለቀም፡፡ በአጠቃላይ እርቃኗን የቀረች ክንፍ አልባ በሰው አካል ውስጥ ሰርጋ የምትንቀሳቀስ መንፈስ መስላለች፡፡

ሁሴን አስተውሏት ምራቁን ዋጠ፡፡ ትንግርት ሁለቱንም በደከሙ አይኖቿ እያፈራረቀች አየችና ፍርፍር ብላ ሳቀች፡፡ ‹‹ኪ.ኪ.. ኪ...
እንደምንም ተረጋግታ መናገር ጀመረ፡፡‹‹ጋሼ ጋዜ..ጠኛው፤ ዛሬ ደግሞ ሁለታ..ችንም በአንድ ጊዜ አሠኘንህ?›› አለች በተኮለታተፈ አንደበት፡፡

ከዚህ በፊት ሁለቱ በአካል ተገናኝተው ባያውቁም አንደኛዋ ስለሌላዋ ታሪክ በደንብ ያውቃሉ፡፡ ትንግርት ኤደንን በሩቅ አይታት ታውቃለች፡፡ ኤደን ግን የትንግርትን መልክ ስታይ የመጀመሪያ ጊዜዋ ነው፡፡ ደነገጠች..ዘወትር ሸርሙጣ ብላ የምታንቋሽሻት ጣውንቷ የዚህን ያህል አፍዛዥ ውበት አላት ብላ ገምታ አታውቅም ነበር፡፡

ሁሴን‹‹ቁጭ በይ›› አላት፡፡ተንደርድራ ከጎኑ ሄዳ ተቀመጠችና ጉንጩን ሳመችው፡፡ ኤደን ላለማየት ፊቷን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞረች፤

እራሷን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ

‹‹እሺ እህት... ደህና ነሽ?›› ትንግርት ነበረች የሽሙጥ ይሁን የትህትና ባለየለት ቃና ሠላምታ ለኤደን የሠነዘረችው፡፡ አልመለሠችላትም፡፡

የኋላ በር ተከፈተና ፎዚያ ገባች፡፡ ግራ በተጋባ ሁኔታ እንግዶቹን እያፈራረቀች ከቃኘች በኋላ በመርበትበት ለሁለቱም ሠላምታ አቀረበች፡፡ ሁለቱ በአንድ ቀን በአንድ ላይ ሲመጡ ስትመለከት ይሄ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኟ ነው፡፡

‹‹ሃይ..›› አለቻት ትንግርት፡፡ ኤደን በዝምታዋ እንደቀጠለች ነው፡፡

ፎዚያ‹‹እራት ላቅርብ?››ብላ ወደ ሁሴን በመዞር ጠየቀች፡፡

‹‹አቅርቢ፡፡›› መለሰላት፡፡

‹‹ጋዜጠኛው.... ሳልጠግብ ነው የመጣሁት፤ መጠጥ እፈልጋለሁ፡፡›› ትንግርት ነች ጠያቂዋ፡፡

‹‹ኦኬ›› በማለት ከተቀመጠበት ተነሳና ሙሉ የውስኪ ጠርሙስ ከሦስት ብርጭቆ ጋር ይዞ በመምጣት በየተራ ለሁሉም እስከ ድርበብ ቀዳላቸው፡፡ ለሁለቱ ሴቶች አድሎ ለራሱም ይዞ ወደ መቀመጫው ተመለሰ፡፡ ቀድማ መጠጣት የጀመረችው ኤደን ነበረች፡፡ በአንድ ትንፋሽ ግማሹን ማገችው፡፡

ትንግርት በመገረም‹‹እንዴ...?››. አለች፡፡

‹‹ምን ሆነሻል?›› በግልምጫ ጠየቀች ኤደን፡፡

‹‹የቤት ልጆችም እንዲህ ትጠጣላችሁ እንዴ?››

‹‹ከሸርሙጦች ነው የተማርኩት፡፡›› የመልስ ምት ሠነዘረች፡፡

‹‹ሠካራምነቱ ብቻ ነው… ወይስ ሽርሙጥናውንም? ፡፡››

ኤደን ሌላ መልስ ለመመለስ ስታሞጠሙጥ ፎዚያ የምግብ ሠሀኖችን ይዛ ገባችና ጠረጴዛ ላይ ኮለኮለችው፡፡ ትንግርትም ከተቀመጠችበት ሶፋ ተንደርድራ በመነሳት ወደ ምግብ ጠረጴዛው እየሄደች ‹‹ጋዜጣኛው... ካልበላሁ ለሊቱን በደንብ ላስደስትህ አቅም አይኖረኝም›› አለችው፡፡

ምንም አልመለሰላትም፡፡ የእንካ ሠላምታው ተሳታፊ ላለመሆን ወስኖ በዝምታ እንደተሸበበ ወደ ምግብ ጠረጴዛው ቀረበ፡፡

‹‹እመቤት እንብላ እንጂ፡፡›› አለቻት ትንግርት ወደ ኤደን በፈገግታ እየተመለከተች፡፡

ከግልምጫ ውጪ መልስ አልመለሰችላትም፡፡ ይልቅስ መጠጡን ከብርጭቆ አጋባችና ሁለተኛውን ሞልታ ቀዳች፡፡

‹‹እራት አትበይም እንዴ?›› ሁሴን ጠየቃት፡፡

‹‹ነገር አጥግቦኛል›› መለሠችለት፡፡

‹‹የእኔ እህት አንድ ምክር ልለግስሽ.. ለዘመኑ ወንድ እንዲህ በግነሽ አትችይም፡፡ ወንዱ ሁሉ ንፋስ ሆኗል፡፡ እንደ አነፋፈሱ አብረሽ ካልነፈስሽ ዕድሜሽ አጭር ይሆናል፡፡ የሠብለወንጌልና የበዛብህ አይነት በድንግልና እስከ መቃብር ድረስ ተማምኖ የመዝለቅን አይነት ፍቅር በዚህ ዘመን እየፈለግሽ ከሆነ በእውነት አንቺ ገና ከእንቅልፍሽ ያልነቃሽ ህልመኛ ነሸ፡፡››

‹‹ይሄንን ፍልስፍና…ማስተርስሽን በሽርሙጥና ስትሰሪ ነው ያስተማሩሽ?››

‹‹ይሆናል .. አንቺን ከማስረዳት በእርግማን የፈራረሰችውን ባቢሎን መልሶ መገንባት ይቀላል፤አርፌ እራቴን ብበላ ይበጀኛል፡፡›› በማለት መብላቱ ላይ አተኮረች፡፡

ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኃላ ሁሴንና ትንግርት ምግባቸውን ተመግበው ወደ በፊት መቀመጫቸው በመመለስ መጠጡን
ተያያዙት፡፡ ትንግርትና ኤደን በመጠጥ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚፎካከሩ ይመስላል፡፡ ሁሴንም በተመስጦ እየኮመኮመ ይመለከታቸዋል፡፡ በመሀከል ኤደን መተኛት እንደምትፈልግ መጠጥ ባሠከረውና በተኮላተፈ አፏ ተናገረች፡፡

‹‹ያው ግቢና ተኚ ››በማለት ከሱ መኝታ ክፍል ቀጥሎ ያለውን ሌላ መኝታ ክፍል ጠቆማት፡፡

‹‹ምን ማለትህ ነው?››

‹‹እንዴት ምን ማለት?››

ትንግርት ሳቅ አፈናትና እጆቿን አደራርባ አፏን ከደነች፡፡

‹‹አንተስ?››ኤደን ነች አሁንም ጠያቂዋ፡፡

‹‹እኔማ መኝታ ክፍሌ ተኛለሁ፡፡››

‹‹እንዴ ነችና ልጅት! ... እሷስ?››

‹‹እሷ ደግሞ ካንቺ ፊት ለፊት ካለው መኝታ ቤት ትተኛለች፡፡››

ትንግርት ጣልቃ ገባች፡፡ ‹‹ብሬን ግን ከች ነው፡፡››

እጁን ወደ ኪሱ ሠደደና ድፍን አምስት የመቶ ብር ወረቀቶች አውጥቶ ሠጣት፡፡

‹‹እግዜር ይስጥልኝ የእኔ እህት፡፡ ማታ አንዱ ጎረምሳ ስብርብሬን አውጥቶኝ ስለነበር ድክም ብሎኝ ነበር፡፡ አንቺ ባትመጪ ደግሞ ጋሼ ጋዜጠኛው በእዛ በምታውቂው ጠንካራ ዕቃው ሲሠነጣጥቀኝ ነበር የሚያድረው፡፡››
በማለት የሠጣትን ብር ጨምድዳ ቦርሳዋ ውስጥ ከታ እየተወላገደች ወደ ተመደበላት መኝታ ክፍል አመራች፡፡ በራፉ ላይ እንደደረሰች የረሳችው ነገር እንዳለ ፊቷን መልሳ ‹‹አንተ ጋዜጠኛ… ለምን ግን ያቺ ደራሲህንም ሳትጠራት? ሦስት ብንሆን ደግሞ ቤትህ ይበልጥ ይደምቅልህ ነበር!››
‹‹ጠርቼያታለሁ...እሷ እዚህ ውስጥ ነው ያለችው፡፡›› አላት በጣቱ ወደ ልቡ እየጠቆመ፡፡

‹‹ታድላለች....ልብህ ውስጥ ካለችማ እሷ ነች ማለት ነው አብራህ የምታድረው፡፡ እመቤት ኤደን አየሽ.. እኔ እና አንቺ ስንፎካከር ሌላዋ ጩልሌ ቀማችን፡፡ ለምን ግን ተስማምተን ለሁለት አናገባውም?››
👍10214😁11🥰3👏3👎1
ኤደን በንዴት ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ወደ ክፍሏ በረረች፡፡‹‹እውነቴን ነው... ሁለታችንም ከምናጣው ብንካፈለው ጥሩ ይመስለኛል... ለእኔ ይመቸኛል፡፡ አንቺ ግን ምን አልባት የቤት ልጅ ስለሆንሽ ...›› ንግግሯን ሳትጨርስ ፊትዋን መልሳ ወደ ክፍሏ ዘልቃ አልጋው ላይ ከነልብሷ ተዘረረች፡፡

ሁሴንም ዝግ ባለ እርምጃ ወደ መኝታ ክፍሉ ለብቻው አዘገመ፡፡ መጨረሻ የተዝረከረከውን ክፍል ወግ አስይዞ ማስተካከል እና በራፎቹን መዘጋጋት የፎዚያ ስራ ነበር፡፡...

ይቀጥላል


ድርሰቱ ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ  ዩቲዩብ ቻናል እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ አበረታቱን 5 10 ሰው እንኳን ቀለላል አደለም አስቡት ከ 100,000 ሰው ነው 10 5 ሰው Subscribe እንዲያደርግ የምንጠይቀው
አሁንም በቅድምያ
ስለመልካምነታችሁ ከልብ አመሰግናለሁ
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍1017👏3😱1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ .....‹‹ሁላችንስ ሸርሙጦች አይደለን? እሷ ሸርሙጣ መሆኗን በአዋጅ ያስነገረች የአደባባይ ሸርሙጣ ስትሆን እኔ እና አንቺ ደግሞ ጓሮ ለጓሮ ከሠው ተሸሽገን በሚሥጥ የምንወሰብ ሸርሙጦች ነን፡፡ አሁንም እኮ የመጣሽው እንድንሸረሙጥ ፈልገሽ መሠለኝ >> ሠውነቷ ተንቀጠቀጠባት፣የጨጓራዋ ቁስለት ሲለበልባት ይሰማታል፡፡ በትንግርት ጉዳይ ብዙ ጊዜ…»
#ትንግርት


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለታደሉ ጋብቻ ገነታዊ ደህንነት የተላበሰ የደስታ ቅፅር ይሆንላቸዋል ለሌላው ደግሞ በእቶን እሳት የታጠረ ሲኦላዊ የግዞት ቦታ ነው…፡፡

ከሠዓት በኋላ ወደ ማተሚያ ቤት መላክ ያለባቸውን የጋዜጣ ፅሁፎችን ለመጨረሻ ጊዜ ተመልክቶ ጨረሰና በድካም ስሜት ወደ ኋላው ተንጠራራ፡፡ለወትሮ ለአስራ ስድስት ሠዓት ያለዕረፍት ሲሠራ የድካም ስሜት የማይሠማው ሠውዬ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሁለት እና ሦስት ሰዓት ስራም ያዝለው ጀምሯል፡፡

‹‹ኢንጅነር ሠሎሞን ዛሬ ደግሞ ምነው ይበልጥ አጠርክ?›› ድንገት በራፉን ከፍቶ ወደ ቢሮው እየገባ ያለውን ጓደኛውን በተረብ ተቀበለው፡፡

‹‹ዓይንህ ነው››

‹‹አይመስለኝም፡፡ ኧረ ይሄንን ቦርጭ ቀንስ፡፡ የድሮዎቹ ኢንጅነሮች ኪሳቸውን ብቻ ነበር የሚቆዝሩት፤ያሁኖቹ ደግሞ ሆዳችሁንም ሳይቀር በስብ ትቆዝራላችሁ፡፡››

‹‹ባክህ አትጨቅጭቀኝ፡፡›› በማለት ወንበር ስቦ ፊት ለፊቱ ተቀመጠ ፡፡

‹‹ፕሮጀክትህን ለማየት ባህርዳር የሄድክ መስሎኝ ነበር?››

ቀረሁ ባክህ ከሶስት ቀን በኋላ የልጆቼ ልደት ነው፤ ዘንግቼው ነበር ሄዳለሁ ያልኩህ፡፡››

‹‹ኦ ..! መንታዎቹ ስምንተኛ ዓመታቸው መሆኑ ነው? >>

‹‹አዋ! ደረሱልኝ፡፡ ብቻ ለአቅመ ሄዋን ሲደርሱ እንደአንተ አይነቶቹን አዳሞች ከምድር ሚጠራርግልኝ ነገር ቢፈጠር ፍቃዴ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ባክህ?›› ሁሴን በገረሜታና በፈገግታ ጠየቀው፡፡

‹‹ምን እንዴት ትለኛለህ...በሄዋኖች ላይ እየተጫወትክ፤ ደግሞ በቀደም ምንድነው የሠራኸው?››

«...ምን ሰራው?»

‹‹ሁለቱን ሴቶች በአንድ ላይ ጠርተህ ልታቧቅሳቸው ነው ወይስ ልታሳስማቸው?››

‹‹ኧኧ .. ማን ነገረህ ደግሞ?››

‹‹ኤደን ደውላልኝ ተገናኝተን ነበር፡፡ የእሷ ልጅ እምባ ከፀረ አርያም የደረሠ ቀን ምን እንደሚውጥህ እኔ አላውቅም፡፡ ቆይ ምን እያስነካሀቸው ነው እንደሙጫ ተጣብቀው እኝኝ የሚሉብህ?›› ግርምት በተቀላቀለ ስሜት ነው የሚጠይቀው፡፡

‹‹እሱን እራሳቸውን ብትጠይቃቸው አይሻልም ..ቆይ ምን ሆንኩ አለችህ?››

‹‹እሷማ በእሱ ያልሆንኩት ነገር የለም ነው የምትለው...እኔም እውነቷን ነው እላለሁ፡፡ እንደውም ምን እንዳልኳት ታውቃለህ፡፡ይሄን ያህል ከተንገሸገሺበት ተይው፤ እኔም በሚስቴ ተማርሪያለሁ፤ ስለዚህ ልፍታትና እንጋባ፤ሁለት ብሶተኞች ቢገናኙ የደስታ ኑሮ ሊገጥማቸው ይችል ይሆናል፡፡ ››አልኳት፡፡

‹‹ድንቅ መፍትሄ ነው፤እንደተስማማች እገምታለሁ፡፡››

‹‹ምን ትስማማለች፡፡ እኔ በቁም ነገር ችግሬን ሳዋይህ አንተ ታሾፋለህ አለችኝ፡፡ አልተረዳችኝም እንጂ እኔስ ከአንጀቴ ነበር፡፡ ያቺን የመሠለች መልዐክ ከእንዳንተ አይነቱ ነጂስ ባድናት እርግጠኛ ነኝ ከፃድቃን ተርታ ያሰልፈኛል፤እኔም ከዛች መሠሪ ሚስት ተብዬ እገላገል ነበር፡፡››

‹‹መስሎሀል... ያህቺ አሁን መልዐክ የመሠለችህ ወደ ትዳር ይዘሀት ስትዘልቅ የባሰች ሠይጣን ልትሆን ትችላለች፡፡

ከማግባትህ በፊት ለየውብዳር እንዴት
ትንሰፈሰፍላት እንደነበር ዘነጋኸው? የፍቅር
ግንኙነትና የጋብቻ ጥምረት ፍፁም የተለያዩ ሂደቶች ናቸው፡፡አየህ በፍቅረኝነት ሃያ ሠላሳ ዓመት ጣፋጭ የስምምነት ህይወት መኖር
እምብዛም የሚከብዱ አይደለም፡፡ ምክንያቱም
የተወሰነ ክፍተት .. መፈናፈኛ ቦታ .. ነፃነት
እንዲሁም እኔ እና እሱ የሚል ልዩነት አለና፡፡

በጋብቻ ውስጥ ግን ከተወሰኑ ዓመታት በላይ
ፍቅርን ከእነ ጣዕሙና ወዙ ማቆየት ለጥቂቶች ብቻ ነው የሚቻለው፡፡ እኔ እና እሷ የሚለውን ቃል ፍፁም ደምስሶ እኛ በሚለው ቃል
ለመተካት ጥረት ይደረጋል፡፡ ዳሩ ግን ሃያ ሰላሳ ዓመት በተለያየ የኑሮ ዘየ በተለያየ ቤተሰብ ውስጥ የኖሩ ሁለት የተለያዩ ግለሰቦች አንድ
ይሆናሉ ብሎ ማሰብ በራሱ እብደት ነው፡፡

የፍቅር ተቋም ከጋብቻ ተቋም ፍፁም የተለየ
ነው፡፡አየህ አብዛኞቹ በምድራችን የተከሰቱ
የፍቅር ታሪኮች (ልብ ወለዶቹ ሳይቀሩ)
የሚያረጋገረጡት ይህንን ሀቅ ነው፡፡

የሼክስፒሮቹ ሮሚዮና ጁልዮት፤ የአዲስ አለማየሁ በዛብህና ሠብለ ወንጌል ሁሉም በመከራ እንጂ በጋብቻ አልተፈተኑም፡፡ምን ' አልባት ተሳክቶላቸው ከዛ ሁሉ የህይወት ፈተና በኋላ ወደ ጋብቻ አምርተው ቢሆን ኖሮ ዛሬ ታሪካቸው ሌላ መልክ ይይዝ ነበር፤በፍቺም ሊጠናቀቅ ይችል ነበር፡፡ፈተና ለፍቅረኞች ብርታት ነው፣ ወኔ ነው፣አቅም ነው፡፡ በተለይ ሁለቱን ለመነጣጠል የሚደረግን ማንኛውንም አሻጥርን ለመበጣጠስ ያላቸው እምቅ ጉልበት ከኒውክሌር ይስተካከላል፡፡ ጉልበታቸው የሚመነጨው ከፍቅራቸው ብቻ ሳይሆን ከመከልከላቸው ውስጥ ነው፡፡ መከልከል ከሠው ልጅ የስነ ልቦና ታሪክ ጋር ትልቅ ትስስር አለው፡፡››

‹‹ገባኝ፡፡ ያንተዋ ኤደን ቢጤ ማለት ነው፡፡ ይሄኔ ላግባሽ እያልክ ብትለምናት ኖሮ ጉዳዩ ተቃራኒ ይሆን ነበር፡፡›› ሠሎሞን ነው ቦርጩን እያሻሸ በመሀከል ገብቶ ሀሳብን የሠነዘረው፡፡

ሁሴን ንግግሩን ቀጠለ ‹‹በተወሰነ መልኩ ትክክል ነህ፡፡ የሠው ልጅ የተከለከለውን ነገር
ለመጨበጥ ቀን ከሌት ይጥራል፡፡ እስኪሳካለትም እረፍት አልባ ይሆናል፡፡ ስለ ግብ አይጨነቅም፡፡ የተከለከለውን በእጁ ካላስገባ ደካማ ነኝ ብሎ ያስባል እንጂ ነገሩ ለእኔ ምን ያህል ያስፈልገኛል፤ ከውስጣዊ ፍላጎቴስ ጋር ምን ያህል ትስስር አለው? ብሎ መጨነቅ ብዙ አይስተዋልበትም፡፡ የአብዛኞቻችን የፍቅር ታሪክም ይህን መሠል ነው፡፡የፍቅር ጉዞ ይጀመራል... በጉዞ ውስጥ እንቅፋት ይደነቀራል.... በዚህ ወቅት ፍላጎት በእጥፍ ይጨምራል፡፡ እንቅፋቱን ለማስወገድ የዓመታት ፍልሚያ ይጀምራል፡፡ በፍልሚያው ሜዳ ላይ  የሚከፈለው የመስዋዕትነት መጠን የፍቅር መጠን መለኪያም ተደርጎ ይወሠዳል፡፡ የታገለ ማሸነፉ ወይም መሸነፉ አይቀርምና በመጨረሻ በስኬት ከተጠናቀቀ ቀጥታ ፍቅር ወደ ጋብቻ ይሸጋገራል፡፡ክፍተት የሌለበት ውህደት፤ አንዱ የሌላው የግል ንብረት ይሆናል፡፡ታዲያ ሲሰነባብት ጀብዱ የለ...ትግል የለ...ግራ መጋባት ይከሰታል፡፡ከውጭ የሚታገላቸው ሲያጡ ፊታቸውን ወደ ጋብቻ




ተጣማሪያቸው ያዞራሉ፤እርስ በርስ ፍትጊያ ይጀመራል…፡፡ ውጫዊ ትግል በውስጣዊ ጭቅጭቅና አንባጓሮ ይተካል፡፡ እሱ እሷ ላይ ይጮኸል…እሷም እሱ ላይ ታንቧርቃለች፡፡ በስተመጨረሻም ውጤቱ ሁለት ይሆናል፤ አንድም የትግሉ ውጤት በመሸናነፍ ይጠናቀቅና ‹ጨዋታ ፈረሠ ዳቦ ተቆረሠ› ተብሎ ትዳሩ ይፈርሳል፤ሁለተኛው ደግሞ ለይሉኝታ ሲባል .. በመሀከል ለተፈጠሩ ልጆች ሲባል ወይም በጋራ ላፈሩት ቁሳዊ ሀብት ሲባል ጋብቻው የዕድሜ ልክ የፍልሚያ ሜዳ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

ጥቂት በነፃነት ላይ የተመሠረተ ፍቅር ግን በእጮኝነትም ሆነ በጋብቻ ጊዜ ተመሳሳይ አንድምታ ሊኖረው ይችላል፡፡ከተለያዩ ሁለት ቤተሰብ የመጣን ሁለት የተለያየን ሠዎች ስለሆንን በሁሉ ነገር ላይ መስማማት አይጠበቅብንም፤በሚያስማማን ነገር ላይ እንስማማለን፤አንዳችን የሌላችንን የተለየ ፍላጎትም እናከብራለን፡፡›› በማለት ተግባብተው ከፍቅር ዘለው ወደ ጋብቻ የዘለቁ
ጥቂቶች ችግር አልባ የሆነ ጣፋጭና ምቹ ህይወት ለመምራት ይታደላሉ፡፡ >>

‹‹ፍልስፍና መዘባረቅና ህይወትን ቀጥታ መኖር ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ምን አለበት የእኔን ትዳር ለሦስት ወር ብትሞክረው እሳቱ እንዴት እንደሚያቃጥል ትረዳልኝ ነበር፡፡››

‹‹ያንተን ሳይሆን የራሴኑ እሞክረዋለሁ፤ደራሲዋን ሳገባ፡፡ ግን እስቲ ንገረኝ አሁን የውብዳር ፍታኝ ብትልህ ትፈታታለህ?»

<<እኔንጃ>>

‹‹እንዴት እኔ እንጃ?››
👍1107😢2😁1
‹‹እነዛ እርግብ የመሠሉ ልጆቼ ክንፋቸው ሲሰበር ይታይህ፡፡ እሷ ጋር ቢሆኑ እኔ አጣቸዋለሁ... እነሱም ያጡኛል፡፡እኔ ብወስዳቸው ደግሞ እሷን ያጧታል፡፡ መቼስ ጥሩ ሚስት ባትሆንም ጥሩ እናት መሆኗን መካድ አልችልም፡፡››

‹‹እሺ አብረሃት የምትኖረው ለልጆችህ ሞግዚት እንድትሆንላቸው ብቻ ነው ወይስ ሌላም ምክንያት አለህ?››

‹‹አንድ ተጨማሪ ምክንያት አለኝ፡፡ አሁን ብፈታት ስንት ብር ይዛ እንደምትሄድ ታውቃለህ? ቢያንስ አስራ አምስት ሚሊዮን ብር ይደርሳታል፡፡ ይታይህ አስራአምስት ሚሊዮን ብር ሙሉ ታቅፋ ሄዳ ለማን እንደምታስረክበው ታውቃለህ? ለእንዳንተ አይነቱ አማላይ አለሌ ወንድ! እኔ በየበረሃው ተንከራትቼ ስንት ጉድጓድ ቧጥጬና ድንጋይ ፈንቅዬ ያከማቸሁትን ብር እሷ እዚህ መሀል አዲስ አበባ በአሜሪካ ኮስሞቲክስ እያብረቀረቀች ፤በፈረንሳይ ሽቶ እየታጠበች ስታውደለድል ከርማ እንደቀልድ አስራ አምስት ሚሊዮን ብር!››

ሁሴን ደነቀው ‹‹በእውነት ስግብግብ ነህ፡፡››

‹‹ለምን አልስገበገብ፤ትርኪ ምሪኪ ወሬና አሉባልታ ለቃቅሜ በወረቀት አስፍሬ በመበተን አይደለም እኮ ንብረት ያፈራሁት፡፡››

‹‹አውቃለሁ አውቃለሁ .. ጥቂቱን ሰርተህ አብዛኛውን ደግሞ ከሙሰኞች ጋር በመተባበር ዘርፈህ መሆኑን በሚገባ አውቃለሁ፡፡›› ተረቡን በተረብ መለሠለትና ሌላ ጥያቄ አስከተለ፡፡ ‹‹ትቀናባታለህ አይደል? ለነገሩ የውብዳር ማንም ሊገምጣት የሚጓጓባት ኬክ ነች።

‹‹ኡፍ… ስንት ሸንቃጣዎች በሞሉበት ከተማ እሷ አገር ስታሳስትና ስታስጎመዥ ታየኝ!!!›› የውስጥ ስሜቱንና የዘወትር ድርጊቱን ለመደበቅ የሠነዘረው ቃል ነው እንጂ ሠሎሞን በየውብዳር መቅናቱን ከወዳጅ እስከ ጠላት የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ አለባበሷ ያበሳጨዋል፣ የሚደወልላት የስልክ ብዛት ያበግነዋል፣የምታርከፈክፈው ሽቶ መዓዛ ያጥወለውለዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በነገር ይጎነትላታል፤ እሷም በእጥፍ ትመልስለታለች፡፡ እንዲህ እንዲህ እያሉ ነገሮች ይባባሳሉ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የደባል በሚመስሉ ኑሮ ውስጥ ነው የከረሙት፡፡ ሁለቱም በየፊናቸው ያቅዳሉ፣ያሻቸውን ይከውናሉ፡፡ሁለቱም የየራሳቸው የገቢ ምንጭ ስላላቸው ማንም ማንንም ገንዘብ አይጠይቅም፡፡ መሳሳም አቁመዋል፤ አልጋም ለይተዋል፡፡ ዘመድ አዝማድ በእንግድነት እቤታቸው ሲመጣ ወይም እነሱ ተጋብዘው ሠርግና ግብዣ ቦታ ሲሄዱ ግን ለይምሰል ጎን ለጎን ተጣብቀው በሞተ ፈገግታ እየተያዩ፡፡

‹‹ምትገርም ነህ፡፡››አለው ሁሴን የእውነትም ገርሞት፡፡

‹‹ ካንተ አልብስም..ይልቅ አሁን ተነስ ወደ ቤት እንሂድ፡፡››

<<ለምን>>

‹‹እየነገርኩህ እንድታማልደኝ ነዋ…መቼስ እሷም እንዳንተ ንክ ስለሆነች ትግባባላችሁ ብዬ ነው፡፡››ብሎ ከመቀመጫው ተነስቶ ቢሮውን ለቆ ወጣ..ሁሴንም ተከተለው፡፡ ሁለቱም በየራሳቸው መኪና ውስጥ ገብተው ተከታትለው 22 አካባቢ ወደሚገኘው የሰሎሞን ቤት ጉዞ ጀመሩ …እስጢፋኖስ ጋር እንደደረሱ ግን ሰሎሞን መሪውን ጠመዘዘና የፒያሳን አቅጣጫ ያዘ…ሁሴን መኪናውን ሳያቆም ስልኩን አነሳና ደወለለት ‹‹ምነው.. ሀሳብህን ቀየርክ እንዴ?››

‹‹አይ ድንገተኛ ጉዳይ አጋጥሞኝ ነው፤ መዘጋጃ አንድ ፕሮጀክት ክፍያ ነበረኝ... አሁን ደርሶል ብለው ደውለውልኝ ነው፡፡››

‹‹ታዲያ ሌላ ጊዜ አይደርስም እንዴ?››

‹‹አይ አይደርስም ..ገንዘቤ መንግስት ጋር ብዙ ሲቆይ ይጨንቀኛል.. አንተ ወደ ቤት ሂድና ጨርስልኝ .. ባይሆን ማታ የተለመደው ቦታ እንገናኝ….፡፡››

‹‹እሺ..ግን ከክፍያው ላይ በደንብ ዘገን አድርገህ ይዘህ ና፡፡››

‹‹እንዳልክ አደርጋለሁ፡፡ ››ሁለቱም ጉዞቸውን በየፊናቸው ቀጠሉ፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰብ

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍79🥰114🔥1👏1
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አንድ፦ መነሻው (1)

   ደስ ይላል፦ፍቅርን ማየት። ያረካል፦ ውብ የሆነ፣ ልብን  አልፎ፣ ነፍስ ውስጠት ድረስ የሚገባን ፍቅር ማጣጣም። አይንና ልብን ያበራል፦ ፍቅርን መልመድ። ተጽፏል፦ ብዙ ስለፍቅር…አያሌ ጸሀፍት፣ ገጣሚያን ብዙ ብለዋል። ተሞዝቋል፦ ብዙ ስለ መውደድ…እልፍ የሙዚቃ ቀማሪያን ተጠበውበታል፦…የፍቅርን ቁንጅናና ውበት ለመግለጽ።  ፍቅረኛችንን ወይም ትዳር አጋርን እንወድበት ዘንድ ከጌታ የተሰጠን ፍቅር እንዴት ድንቅ ነው?

   ህይወት ያለው፣ በአርኪ መዐዛ የተሞላ እንዲህ አይነት ፍቅር የት አየሽ ቢሉኝ? መልሴ አጭር ነው። ዳሪክና ሳሌም አይን ውስጥ።

   ከአመታት በፊት በአምስተኛው አቬኒዩ ላይ ባለው ስታር ባክስ ካፌ እሰራ ነበር። ያኔ ገና የሃይ ስኩል ተማሪ ነኝ። ከት/ቤት መልስ በሳምንት ለተወሰኑ ቀናት፣ ለተወሰኑ ሰአታት እዛ አሳልፋለሁ። ካፌው በቃ ካፌ ነው። ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ የቡና ማሽን፣ የኬክ መደርደሪያ ያለበት ተራ ካፌ። ካፌው ካፌ ነበር፦ ሳሌምና ዳሪክ እስከሚመጡ ድረስ።

   አንድ ቀን ሳሌምና ዳሪክ አምስተኛው ጎዳና ላይ መጡ። ቁመታችው ተመጣጣኝ ለጋ ወጣቶች። ሁለቱም ቦርሳ ይዘዋል። የኮሌጅ ተማሪዎች ይመስላሉ። ሳሌም ረጅም ቀሚሷ የበለጠ ረጅም አስመስሏታል። ደስ የሚሉ ትላልቅ አይኖች፣ ቀይ እንቡጥ የመሰሉ ከናፍርት፣ ጽድትና ጸጥ ብሎ ጸጥ ያለ … ፊት ሳሌም ናት። ጥቅጥቅ ያለ ጥቁር ከርዳዳ ጸጉር፣ ጠይም ረዘም ያለ  ፊትና ሳቅ፣ ሳቅና ደሞ ሌላ ሳቅ… ይሄ ደሞ ዳሪክ ነው።

   እንግዲህ ዳሪክና ሳሌም መጡ፦ ከሰአት ቡሃላ አስር ሰዐት አካባቢ። ከየት መጡ?እንዴት መጡ? ማንም አያውቅም። መጥተው በካፌው ውስጥ በአንድ ጥግ ባሉት ወንበሮች ላይ ተቀመጡ።

ሳሌም ሻይ አዘዘች።
ዳሪክ ካርሜል ማኪያቶ።

ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት ሳያሳልሱ በሳምንቱ ውስጥ አብዛኛው ቀናት አምስተኛው ጎዳና ላይ … ስታርባክስ መጡ። መጥተው ለአንድ ሰአት ያህል ቆይተው ይሄዳሉ። መጥተው ሄዱ። መጥተው ሄዱ። በብዙ መጥተው በብዙ ሄዱ።

   የፍቅር ወፎች ናቸው ፦ ዳሪክና ሳሌም። የማይለያዩ… በአየር ላይ፣  ከደመናት በላይ ተንሳፈው ማንም በማይደርስበት አየር ክልል የሚበሩ ወፎች። አሁን በአየር ላይ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ዙሪያችውን አያዩም። አካባቢውን አይሰሙም። እሱ እሷን ያያል። እሷ እሱን ታያለች። እሱ እሷን ይሰማል። እሷ እሱን ትሰማለች።  ካፌው ውስጥ ተስተናጋጅ ቢጣላ (ቢንጫጫ)፣ ብርጭቆ ቢከሰከስ፣ ወንበር ቢሰባበር፣ ማንኪያ ወድቆ ቢንኳኳ (ኳኳኳኳ…ኳኳ...ኳ.ኳ.ኳ.ኳ…ኳ) እያለ  መሬት ለይ ቢሄድ) እነሱ ግን በራሳቸው አለም ውስጥ ናቸው።

  ደሞ የፍቅር ከዋክብቶች ናቸው፦ ዳሪክና ሳሌም። ሰፊ በሆነው የፍቅር ህዋ ውስጥ ከተለያዩ ‘ጋላክሲዎች’… የተገናኙ በራሪ የመዋደድ ከዋክብቶች። ሁለቱም ሲበሩ አንድ ቀን ተገናኙ።  …ተገናኙ …. ተያዩ … መተያየታቸውንም ሊያቆም የሚችል ነገር ጠፋ። እሷ… እሱን … እሱ…. እሷን ብቻ ለማየት የተፈጠሩ ይመስል ይተያያሉ። አሁን በህዋ ውስጥ ያሉት እነሱ ብቻ ናቸው። ሰው ቢሮጥ፣መኪና ቢበር፣ባቡር በድምጹ ቢያንባርቅ፣ የፖሊስ መኪና ሳይረን (ኡኡኡ…ኡኡኡኡኡ..ኡኡኡ….ኡኡ……) እያለ ቢከንፍ አይሰሙም፣ አያዩም።

…የእነሱ አለም ሶስት ማዕዘን ነው።

አንደኛ ጎን፦ ዳሪክ
ሁለተኛ ጎን ፦ ሳሌም
ሶስተኛ ጎን፦ አምስተኛው ጎዳና

…ደሞ ሌላ ሶስት ማዕዘን ነው።

ካፌው ፦ የፍቅራቸው መቅደስ
ጥግ ያሉት ወንበሮች፦ የፍቅራቸው ቅድስት
ሻይና ማኪያቶ፦ የፍቅራቸው ቅመም ነው

…ደሞ ሌላ ሶስት ማዕዘን ነው።

የዳሪክ አይኖች፦ ሳሌምን ያያሉ
የሳሌም አይኖች፦ ዳሪክን ያያሉ
የኔ አይኖች፦  ደሞ ሁለቱን ያያሉ

ሳያዩኝ አያቸዋለሁ፦ የፍቅር ዋኖሶችን፣ የፍቅር የዋህ እርግቦችን። የተለየ ነገር አላቸው። የበራ፣ የጠራ፣ የነጠረ አፍላ ፍቅር።

© hassed agape fiker

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍729👎2🥰2
"የሴቶች ፓንት ከነ... በ20 ብር ብቻ!”

በአንድ የሥራ ቀን ጠዋት ፤ ታክሲ የምጠብቅበት ቦታ ፤ መንገድ ላይ ዕቃ
ዘርግተው ከሚሸጡ ነጋዴዎች መካከል አንዱ ጆሮ ገብ ማስታወቂያ
ሲሠራ ሰምቼ ዞር ብዬ አሁት ።

“የሴቶች ፓንት ከነቂጡ በ20 ብር ብቻ”

በበእውቀቱ ስዩም አባባል ፣"ማቄት ለተሳናቸው" ሴቶች  የተሰራውን፤
እንዲህ ያለውን "ግልገል ሱሪ" ካየሁት ሰነባብቻለሁ ። እንዲህ ሲሸጥ
ግን ሰምቼ አላውቅምና ሣቅኹ።

የጊዜአችን ሴቶኝ ፤ጸጉራችን፤  ጡታችን፣
አሁን አሁን አሁን ደግሞ ፣መቀመጫችን ሳይቀር ከመንገድ ላይ የሚገዛ መሆኑ አስገራሚ ነው።

ስለ እነዚህ በገላችን ላይ ስለምናኖራቸው ባዕድ ነገሮች የምናወራው ወሬም
የዚያኑ ያህል ግር የሚያጋባ እየሆነ ነው።

ለምሳሌ አስቧት አንዷን፣ ከባሏ ጋር እንዲህ ስትባባል....

"የኔ ቆንጆ እንውጣ ፤ ረፈደ” ይላታል እሱ

“እሺ... እስቲ ከዚያ ከኮመዲናው ላይ
ጸጉሬን አቀብለኝ።

ይሰጣታል።

"ባለ ስፖንጁን ጡት መያዣዬን አይተኸዋል?"  ያቀብልና ፣

“እር በናትሽ እንውጣ በቃ!” ይላክ :

"ጨረስኩ እኮ…. አንዴ ብቻ ፣ ይህን ቂጤን ላስተካክለው! ተቀምጨበት
ተጨማዱል!”

አጃኢብ ነው!

ድሮ ድሮ ፣ “እገሊትማ ቂጧን የጣለች ዱርዬ ናት” ይባል ነበር ።
በዚህ አያያዛችን፣ አሁን አሁን ሴቱ ሁሉ ቂጡን፣ እየጣለም ሊተኛም አይደል?

🔘ሕይወት እምሻው🔘
😁77👍464👎2🥰1
ሃሴድ አጋፔ ፍቅር:
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል አንድ - መነሻው (2)

   ካፌው ውስጥ አንዳቸው ቀድመው ደርሰው … ከዛ ሲገናኙ ማየት ነው፦ የፍቅር ዋኖሶችን። ሳይገናኙ በፊት ክረምት ነው፦ በሁለቱም ፊት ላይ። ዶፍ ዝናብ የሚዘንብበት፣ በረዶና ጠል የሚወርድበት፣ ቅዝቃዜው ጆሮን የሚቆርጥበት፦ ድቅድቅ ክረምት። ሳይገናኙ ለሁለቱም ጨለማ ሃምሌ ነው። ሲገናኙ ጸሐይ በፊታቸው ላይ ትወጣለች። የፊታቸው ሰማይ ጭጋጉ ይጠፋል። ይጠራል። ሰማያዊ ይሆናል። ሲተያዩ ጸሐይ ነው፦ ብርሃን፣ ደስ የሚል የፍቅር ብርሃን በሁለቱም ፊት ላይ ያለማቋረጥ ይወርዳል።

   የፍቅር ዋኖሶቹ ፍቅር ሲገላለጹ ንጹህ ናቸው። በዚህ “ፍቅር” የሚለው ቃል ትርጉም ሚዛኑ ተንጋዶ በራስ ወዳድነትና በእኔነት በሚገለጽበት አለም ላይ እንዴት እነሱ በታላቅ ንጽህና መዋደዳቸውን አሳዩ? እኔ አንጃ። እኔ አላውቅም።

አንዳንድ ቀን …

ዳሪክ ያወራታል ሳሌምን። ሳሌም ትስቃለች። አይኗ፣ ፊቷ፣ጥርሷ ይስቃል። በሳቋ የሚያምሩት የእጆቿ ጣቶች አብረው የሚደንሱ፣ እግርቿ የሚያጅቡ ይመስላሉ። እንባዋ እስኪፈስ ትስቃለች። ስትስቅ ጸጥ ያለው ፊቷ የበለጠ ይበራል። ጸጥ ያለ ውቂያኖስ ላይ ጸሐይ በማለዳ ብቅ ስትል የምትሰጠውን ውበት ያህል ፊቷ ይውባል፣ ይበራል።
 
ዳሪክ ፈርዶበት ሳቂታ ነው። ሳሌም ስት ስቅ ደግሞ  የዳሪክ ሳቅ ሞልቶ፣ በዝቶ ይትረፈረፋል። መናገር የፈለገውን ነገር መናገር ስኪያቅተው ድረስ ይስቃል፣…. ይስቃል። ከርግቦቹ ንጹህ ፍቅር የሚፈሰው የደስታ ዝናብ  በሳቆቻቸው ድምጽ ተሳፍሮ ለኛም ልብ ካፊያው ይደርሳል። የነሱ ደስታና ሳቅ በዙሪያችን ያለነውን የእኛን ነፍስ ሳይቀር ፍስሃ ይሆንላታል። .ሳያውቀው ልባችን ጮቤ ይርግጣል። ሳናውቀው ጥርሶቻችን ከከናፍርቶቻችን መሃል ብቅ ይላሉ ይላሉ … ፈገግ።

አንዳንድ ቀን…

ዝም ይላሉ። በቃ ዝም ብለው ይተያያሉ። ሰው ዝም ብሎ፣ ቃል ሳያወጣ ይነጋገራል? አዎ። ዳሪክ የሳሌም አይን፣ ሳሌም ደሞ የዳሪክን አይን በስስት ይመለከታሉ። ያያታል፣ ያያታል ደሞ አሁንም ያያታል። አይኗን አልፎ፣ ውስጧን ሰርስሮ፣ በዐጥንቶቿና በጅማቶቿ ላይ ተንሸራቶ፣ በልቧ ትርታዎች ላይ ተሰፈንጠሮ ፦ አዎ ነፍሷ ላይ፣ ነፍሷ ላይ የሚደርስ ‘ስኪመስል ያያታል።

   …ታየዋለች፣ታየዋለች፣ አሁንም ደግማ ታየዋለች። አይኑ ውስጥ የማያቋርጥ ውብ ትዕይንት እንዳለ፣ አይኑ የበጋ ላይ የውቂያኖስ ውብ ውሃ፣የአይኑ ብሌን በውቂያኖሱ ላይ የምትጠልቀውን ቆንጆ ጸሀይ እስኪመስለኝ ድረስ ታየዋለች። ሻይና ማኪያቶ ይረሳል። ይቀዘቅዛል። የፍቅር ዋኖሶች በመተያየት ያወራሉ፣ በመተያየት ይጫወታሉ፣ በመተያየት ይግባባሉ።

አንዳንድ ቀን…

ዳሪክ እጁን ዘርግቶ ሳሌምን ይዳስሳታል፣እጇን ይዞ በዝግታ እየደሳሰ ጣቶቿን በታላቅ ቀስታ ይንካካቸዋል። አደሳሱ፣ አነካኩ አዲስ ሙዝቃን አዲስ በተገኘ ፒያኖ የሚጫወትን ዘማሪ ያህል ነው። እኛ ደሞ ታዳሚዎች ነን።

….ሳሌም በተመሳሳይ እጁን ትነካካዋለች፦ በዝምታ፣ በስሱ ። ውብ ጣቶቿን በአይበሉባው፣ በቆዳው ላይ በርጋታ ስታስኬድ.. ከአልማዝ፣ ከእንቁና ከሩቢ ውህድ የተሰራ በአለም ያለታየ አዲስ የከበረ ድንጋይ ያህል (…የኔ ብቻ እጅ… የኔ ብቻ…) እያለች የምትነካካው የምታየው ይመስለኛል።

ረጅሙ መንገድ!....

   ረጅሙ መንገድ….ለሁለቱ የፍቅር ርግቦች ረጅሙ መንገድ የትኛው ነው? ምን ያህል ነው? ከሃምሳ ሜትር የሚበለጥ አይመስለኝም። ከካፌው እስከ አውቶቢስ ፌርማታው ያለው ነው። ሃምሳ ሜትር ለ‘ነሱ ሃምሳ ጊዜ የምድርን ክበብ የመዞር ያህል ነው። ርግቦቹ የአለምን ግማሽ ያህል የሚሄዱ ይመስል ያዘግማሉ። በብዙ ግፊያ ውስጥ የሚሄዱ ይመስል እርምጃቸውን ይቆጥራሉ። በጫማቸው ልክ ይራመዳሉ። እጅ ለእጅ ተያይዘው ይቆማሉ፣ ደሞ ዝግ ብለው (…ኤሊን “…ደሞ ከኔ የባሳም አለ እንዴ?...” ) ብላ በሚያስደምማት አይነት ጉዞ ይጓዛሉ። ለምን? እንዳይለያዩ እኮ ነው።

አይደረስ የለም ባስ ፌርማታው ላይ ሲደርሱ ደሞ ይቆማሉ።

በመስመሩ ላይ የሚመጣው አንድ አውቶቢስ ነው። ባስ መጥቶ ይቆማል። ሹፌሩ ያያቸዋል።

የሚሄዱ ይመስላሉ። ትንሽ በትዕግስት ይጠብቃል። ።

“…ትሄዳላችሁ?...” ሹፌሩ ይጠይቃል

ዳሪክና ሳሌም አይሰሙም። ቆመው ያወራሉ። ወይም ዝም ብለው ቆመው ይተያያሉ። አንዳንድ ጊዜ ሳስበው ወሬ የሚመጠላቸው፣ በጥልቅ መተያየት የሚፈልጉት በዚህ በመለያያቸው አስራ አንደኛ ሰአት ላይ ይመስላል።

ጥሏቸው ይሄዳል። ሌላ ባስ ይመጣል። ይሄዳል። ሌላ ይመጣና ይሄዳል። ደሞ ሌላ ይመጣል።

ሳሌም ወደ ባሱ መንገድ ትጀምርና ዳሪክ ደሞ ሊያወራት ይጀምራል። ትመለሳለች። ደሞ እንደገና ተያይዘው፣ ቆመው ወሬ ይጀምራሉ። ተለያዩ ሲባል፣ ሲሳሳቡ፣ ሲያወሩ ረዥም ጊዜ አልፎ በመጨረሻ ሳሌም አውቶብሱ ውስጥ ገብታ ጉዞ ይጀምራል።

ዳሪክ ቆሞ ሳሌም የገባችበትን ባስ ያያል። ህጻን ልጇን ላይመለስ እንደተወሰደበት ወላጅ፣ ለመጨረሻ ጊዜ እንደምትታይ መቼም ተመልሳ እንደማትመጣ የጸህይ ጥልቀት ቆሞ ያያል። አውቶብሱ ከዐይን እስኪሰወር አሻግሮ ይመለከታል። ከዛ በተቃራኒው አቅጣጭ ቀስ እያለ መጓዝ ይጀምራል። ቀኑ መሽቷል። ጸሐይም ጠልቃለች።

ረጅሙ ጊዜ!...

ረጅሙ ጊዜ የትኛው ነው? ፍቅሮቹ ተለያይተው እስከሚገናኙ ድረስ ያለው ነው።
 
  …ሲለያዩ ሰአታት ይቆጠራሉ፣ ደቂቃዎች ይመነዘራሉ፣ ሰኮንዶች ይሸራረፋሉ። የናፍቆት ምጥ ይጀምራል። በሚቀጥለው ቀጠሮ የሚገናኙበትን ጊዜ ዋኖሶቹ መራብ ይጀምራሉ። አሁን ሲለያዩ
ሰኔ ነው። እሱ ጸደይ ነው፦ እሷ ደሞ አበባ። ጸደይ አበባን፣ አበባም ጸደይን እንደሚናፍቁ የዋኖሶቹም ናፍቆት እንዲሁ ነው። አሁን ሲለያዩ ጥቅምት ነው። እሱ መስከረም ነው ፦እሷ ደሞ የመስቀል ወፍ። መስከረም የመስቀል ወፍን፣ የመስቀል ወፍም መስከረምን እንዲናፍቁ የእነሱም ናፍቆት እንዲህ ነው።

እኔና የስራ ጓዶቼ ላቭ በርድስ (የፍቅር ርግቦች) እንላቸዋለን። ስማቸውን አናውቅም። ለግማሽ አመት ተመላልሰው መጥተው እዛ ካፌ ውስጥ ሳያቸው ምንም ብለምዳቸው፣ በጣም ደስ ቢሉኝም አናግሬያቸው አላውቅም። ሌሎቹም ሰራተኞች ቢሆኑ ከሰላምታ ያለፈ ብዙም አያወሯቸውም።

አንድ ቀን ግን ወሰንኩና ሄድኩ። ላናግራቸው አጠገባቸው ቆምኩ።

“…ብዙ ጊዜ እዚህ ካፌ አያችዋለሁ። አበሾች ናችሁ?...”

ቀና ብለው ተገርመው አዩኝ፦ ሁለቱም። አማርኛ ሲሰሙ ነው መሰለኝ።

“…አዎ…”  አለች ሳሌም   “…አበሾች ነን…”

“…በጣም ደስ ትላላችሁ …ብንተዋውቅ ደስ ይለኛል…” ብዬ ስሜን ነገርኳቸው።

“…ሳሌም…” አለችኝ በትህትና ከተቀመጠችበት ተነስታ

“…ዳሪክ…” አለኝ እሱም

ተዋወቅን።

ከዛ ዝም ብለው ያዩኝ ጀመር። ግራ ግብት ብሏቸው… “…የፍቅራችን የጊዜ ማር ላይ ያረፍሽ ዝንብ…” በሚል አይነት። የፍቅር ጊዚያቸው የከበረ ነው። ለኔ የሚያጋሩኝ ቅጽበተ ሰከንድ አልነበራቸውም።

ምንም ሳይሉኝ፣ ቃል ሳይተነፍሱ የፈልጉት ገባኝ። ስለ ተዋውቁኝ አመስግኜ ተጫወቱ ብዬ ተለየኋቸው። 

ከዛ ቡሃላ ሰላምታ እንሰጣጣለን። ለአመት ከመንፈቅ ያህል ሲመጡ ይኸው ነው። ሰላምታ ብቻ። ስለ ፍቅር ዋኖሶቹ የማውቀው ዳሪክና ሳሌም መሆናቸውንና የጠለቀ ፍቅራቸውን ብቻ ነው።

አንድ እለት…
👍523😁2😱1
…ስራ ባልሄድኩበት አንድ ምሽት እራቴን ይዤ ከቲቪው ፊት ለፊት ተሰይሜያለሁ። የምወደውን ሾው ፍለጋ ቻናሎችን ወደ ላይ ወደ ታች ሳሳልፍ ድንገት እየተላለፈ ያለ ሰበር ዜና ቀልቤን ሳበው። ዜናውን ማየትና መስማት ስጀምር ግን አይኖቼ ተከፍተው ቀሩ፣ እጄ ላይ ያለው ሳህን ወድቆ ተከሰከሰ፣ ቤቱ በላዬ ላይ ሲዞርብኝና ልወድቅ ስል የሶፋውን ጠርዝ ይዤ ተረፍኩ….

© hassed agape fiker

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍23
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ሁለት፦ ረጅሙ ሌሊት (1)

   ይዋኛሉ። ቀስ እያሉ፣ አንዳንዴ ደሞ በፍጥነት፣ ሌላ ጊዜ ደሞ ለውድድር ‘የሮጡ ይመስል። የተለያየ መጠን አላቸው። ውበት የፈሰሰባቸው፣ በቀለማት ቅብ ያማሩ…  ጥቂቶቹ ሃምራዊ፣ ሌሎቹ ደማቅ አረንጓዴ፣ ከፊሎቹ ቀይ፣ ደሞ ሰማያዊ፣ ቢጫ  ....ይዋኛሉ፣ ….  አሳዎቹ በዚች ትንሽ አለማቸው፣ በሆስፒታሉ እንግዳ መቀበያ ጥግ ላይ ባለው በጥቂት ሜትሮች ወርድና ቁመት በተዘጋጀላቸው ገንዳ በሞላው ውሃ ውስጥ ይዋኛሉ፣ ይሮጣሉ። በዝች በተሰጠቻቸው ትንሽ ሳጥን አለም ውስጥ ይደሰታሉ ይቦርቃሉ። ስለምን እኛ እጅግ ሰፊ አለም ተስጥቶን …ምድርንና ሞላዋን ግዙ ተብለን….. መስማማት አቃተን? ፍቅራችን ቀዘቀዘ? ጥላቻን አብዝተን ፈገግታችን ጠፋ?

   በእንግዳ መቀበያው ጥግ ላይ ባለው ትንሽ ገንዳ ውስጥ አሳዎቹ ይዋኛሉ፣ …..  የእንግዳ መቀበያው መግቢያ ላይ ያለውን ኮሪደር ተሻግሮ ባሉት፣ የተዘጉ ቀዶ ጥገና  ክፍሎች ውስጥ ናቸው ፦ ሳሌምና ዳሪክ። በነዛ በተዘጉ ክፍሎች ….ሃኪሞች፣ ነርሶች፣ የከተማው ስፔሻሊስቶች እየተረባርቡ ነው፦ የሁለቱን ልጆች ነፍስ ለማትረፍ። 

   ዝምታ ነው ፦ ድባቡ። ጸጥታ ነው፦ አካባቢው።  ምናልባትም  ከአሳዎቹ ሰው ሰራሽ ገንዳ ውስጥ ከሚመጣው የማያቋርጥ (ሽሽሽሽሽሽሽሽ….) የሚል ድምጽ በስተቀር የሚሰማ ድምጽ የለም። ሁላችንም ትንፋሻችን ጸጥ ብሏል።

    ቀደም ብሎ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም እየመሸ ሲሄድ፣ ሌሊቱ መውደቅ ሲጀምር ብዙዎች መልካሙን ተመኝተው፣ በጸሎት ወጣቶቹን እንደሚያስቡ ነግረውን ቀስ እያሉ ወጥተው ሄዱ። አሁን የቀረነው የሳሌም አባት ታዴ፣… ጥቂት የቅርብ ሰዎችና…. ያው እኔ ነኝ። እናም  ዝም ብለናል። ግን ዝምታችን ድምጽ አለው። ጸጥታችን ይጮሃል… “…ኤሎሄ… ኤሎሄ…” ይላል። ። ጩኸቱም አንድ ነው …. በዝምታችን ውስጥ የምንለው፣ የምንማጸነው የሁለቱን ወጣቶች ደህንነት ነው። የህይወታችውን መትረፍ ነው።

    አንዳንዴ ሳስበው ….ለኛ ለሰው ልጆች ፍቅር ስራችን ነው። መዋደድ ግንዳችን ነው። የሰው ልጆች ስንሰራ፣ ስንፈጠር እንዲህ ነው። ፍቅር ነን። በጊዜና በቦታ የማያቋርጥ ጉዞ ውስጥ አንዳንዴ ጥላቻ የሚባል አረም ግንዱ ላይ ይበቅላል። ፍቅርንም ሊዋጋ፣ ሊቃወም ይነሳል። ይህ የጥላቻ ብቅል እድሉን ካገኘ የመዋደድን ግንድ ሊቆርጥ የሚነሳ የሳለ ምሳር ነው። ፍቅር ባለበት በፍቅር ጥላ ውስጥ፣ በጥላው ጥቁረት መሃል ….በጥላው ጽልመት ስር ተደብቆ የሚያደባ፣ ፍቅርን ሊንድ ሊገል የሚወጣ ጥላቻ አለ። ጥላቻ እንደ ጥላ ይከተላል። ጥላቻ አድጎ፣ ተመንድጎ ጣሪያውን ሲነካ ደሞ ሰው የማያውቃቸውን ንጹሃን፣ ሰላማዊ ሰዎችን ሊገድል፣ ሊያርድ ሽጉጥ፣ ሾት ገን፣ ክላሽን ኮቭ ይዞ ይወጣል። ዛሬ የሆነውም ይህ ነው። አንድ በልቡ ውስጥ የጥላቻን ዘር ዘርቶ፣ኮትኩቶ ያሳደገ ግለሰብ አምስተኛው አቬኒዩ ላይ መጣ። ካፌው ውስጥ መሰስ አለ። ለማንም ምንም ሳይናገር፣ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ አይቷቸው የማያውቃቸው ታዳሚዎች ላይ ጥይት ማርከፍከፍ ጀመረ። ሰዎች ወደ ኋላቸው ወደቁ። በጊዜና  በቦታ የማያቋርጥ ጉዞ ውስጥ ሳሌምና ዳሪክ እዚህ ስፍራ ከጥላቻ ጋር ተፋጠጡ። ባልሆነ ጊዜ ላይ፣ ያልሆነ ስፍራ ተገኙ። የጥላቻ ሰላባዎችም ሆኑ።

   ቤት ሆኜ የሰማሁት ሰበር ዜና ጆሮዬ ውስጥ ይጮሃል። ልቤ ውስጥ ይሰማኛል። አምስተኛው አቬኒዩ ላይ ያለው ስታር ባከስ … Active Shooter … አክቲቭ ሹተር (ዝም ብሎ ከመሬት ተነስቶ ሰዎችን በጥይት ተኩሶ የሚፈጅ ግለሰብ) ባደረሰው ጥቃት አንድ ሰው ገድሎ ሌሎች አራት ሰዎችን አቁስሏል። ከቆሰሉት ሁለቱ ህይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ወደ …..ሆስፒታል ተወስደዋል።

በዜናው ድንጋጤ ልቤ ራደ። በጄ ላይ ያለው ሳህን ወድቆ ተከሰከሰ። ቤቱ ጣሪያ ግድግዳው ዞረብኝ። ለተወሰነ ጊዜ  የምለው፣ የማደርገው ጠፍቶኝ ዝም ብዬ ቁጭ ብዬ ቲቪው ላይ አፍጥጬያለሁ። አይኖቼ ተከፍተዋል። እጄ ይንቀጠቀጣል። … የማውቀው ሰው ተጎድቶ ይሆን? አብረውኝ የሚሰሩት ወደጆቼ ከሞቱት ውስጥ ይኖሩ ይሆን?  ስራ ይሆናሉ ብዬ የማስባቸው ጋር ሁሉ ብደውል ስልኩን የሚያነሳ የለም።

   ቆይቼ ራሴን አረጋግቼ ካለማቋረጥ የሚተላለፈውን ዜና መከታተል ጀመርኩኝ። የበለጠ መረጃ ሲሰበሰብና ፖሊሶች የሟቾቹንና የተጎጂዎችን ማንነት ሲገልጹ  የፈራሁት አልቀረም የማውቃቸው ሁለት ወጣቶች በቲቪው ላይ ብቅ አሉ። ሳሌምና ዳሪክ ፦ ለህይወታቸው አስጊ በሆነ ሁኔታ ከተጎዱት …. ሁለቱ ናቸው። ዜናው እጅግ ልቤን ቢሰብረው፣ ሰላሜን ቢያሳጣኝ እነዛ ከነፍሴ የወደድኳቸው የፍቅር ርግቦች፣ የዋህ ነፍሶች የደረሱበትን፣ ያሉበትን ሁኔታ ለማየት ይኸው መጥቻለሁ። ሆስፒታሉ ውስጥ ዝም ብዬ፣ ጸጥ ብዬ ከፊት ለፊቴ ባለው ስው ሰራሽ ፊሽ ታንክ ውስጥ የሚዋኙትን አሳዎች እመለከታለሁ። …ጥቂቶቹ ሃምራዊ፣ ሌሎቹ ደማቅ አረንጓዴ፣ ከፊሎቹ ቀይ፣ ደሞ ሰማያዊ፣ ቢጫ …. አሳዎች  በሰላም ይዋኛሉ፣ ይሮጣሉ፣ ይቦርቃሉ። ከአሳ የተሻልን ነን የምንል እኛ ደሞ በሰፊው አለም ላይ እንጣላለን፣ እንፋጃለን፣ እንገዳደላለን።


© hassed agape fiker

ይቀጥላል....

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍424😁1
#ትንግርት


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በዓይናችን ዓይተን ከወደድነው ነገር ይልቅ በምናባችን ቀርፀን ደጋግመን የተመኘነው ነገር ወደ ጣኦትንት የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ነው፡

የውብዳር ለብ ባለ ውሃ ሠውነቷን ተለቃልቃና ፎጣ አገልድማ ፓንቷን በእጇ ይዛ ከባኞ ቤት በመውጣት ወደ መኝታ ቤቷ ልትገባ በእርምጃ ላይ ሳለች ሁሴን የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ፡፡

‹‹እኔ አላምንም፡፡ ቤቱን ማን አሳየህ?›› ወደ እሱ እየተራመደች ነበር የምትናገረው፡፡

ጉንጭ ለጉንጭ ከተሳሳሙ በኋላ ግማሽ እርምጃ ራቅ በማለት አስተዋላት፡፡ ድንቡሽቡሽ ያለች የምትበላ ብስል ቀይ ወይዘሮ ነች፡፡ ያገለደመችው ሮዝ ቀለም ያለው ፎጣ ከወገቧ እስከ ጉልበቷ ሸፍኗታል፡፡ ሌላው አካሏ እንደተጋለጠ ነው፡፡ ጡቶቿ አሁንም እንደልጃገረድነቷ እንዳጎጠጎጡ ናቸው፡፡ የቆዳዋ ጥራትም አስደምሟታል፡፡

‹‹ምን ያፈዝሀል? ቁጭ በል እንጂ›› አለችው፡፡ በእሷ ውበት መደመሙን ስታስብ ውስጧን የንዝረት ስሜት ተሰማት፡፡

‹‹ለምን አልፈዝ፡፡ ጓደኛዬ ለካ ይሄንን ሠውነት እንደ አሞሌ ጨው ሲልስ እያደረ ነው እንዲህ

‹‹ኡ . ኡ . ቴ <ቅጡም የምንኩስና ነው› አለች አክስቴ.... ለማንኛውም ልብሴን ለብሼ ልምጣ.... የሚጠጣ ከፈለክ ፍሪጁን ከፈት አድርግ፡፡›› በማለት እየተውረገረገች ወደ መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡

ሁሴን ፍሪጁን ከፍቶ ቢራ አወጣና እየተጎነጨ ማሠብ ጀመረ፡፡ ስለ ሰሎሞን ነበር የሚያስበው፡፡ በመጀመሪያ የውብዳርን ያፈቀራት ጊዜ ጨርቁን መጣል ነበር የቀረው፡፡ እሷን ማግባት ካልቻለ በህይወት መኖር
እንደማይችል ደጋግሞ ሲምል ነበር፡፡ በወቅቱ ደግሞ የእሷ ቤተሠቦች ፍቃደኞች አልነበሩም፡፡ ይሁን እንጂ የእሱ ፍቅር ብርታትና መስዋዕትነት የመክፈል ፅናቱ እሷንም ሙሉ በሙሉ በፍቅሩ እንድትጠመድና ከቤተሠቦቿ ፍቃድ ውጭ አሻፈረኝ ብላ እቤቱ እንድትገባ አስገደዳት፡፡ እናም ትዳራቸው በእንደዛ አይነት ሁኔታ በጽኑ ቁርጠኝነትና በከፍተኛ ደስታ ተጀመረ፡፡ ንብረት መጣ፣ልጆች ተወለዱ፣ሁሉ ነገር የሰመረ መሰለ፡፡ዳሩ ግን ውሎ አድሮ አካል ሲቀራረብ ፍቅር ቀስ በቀስ ከመሀከል ሾልካ ተነነች፤አንዳቸው ለአንዳቸው የወዳጅ ጠላት ሆኑ፡፡

‹‹እሺ አቶ ሁሴን... ደህና ነህ?›› እስከተረከዟ የሚደርስ ረጅም አብረቅራቂ ጥቁር ቀሚስ ለብሳለች፡፡ ዊግ የተቀላቀለበት ሹሩባዋ ያምራል፡፡ የሁለት ጡቶቿ አካፋይ የስምጥ ሸለቆ ስንጥቅ መስሎ በከፊል ይታያል፡፡ የተቀባችው ሽቶ የሳሎኑን አየር በሠከንድ ነበር የቀየረው፡፡

‹‹አለሁልሽ... ከውዱ ባለቤትሽ ጋር ነበር የመጣነው ግን ከበራፍ ተመለሰ፡፡››

‹‹ምነው ውሽማው ጠራችው እንዴ?›. ግዴለሽ በሆነ አሽሞጣጭ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ! ውሽማው ጋር ነው የሄደው፤ወይዘሪት ገንዘብ ጋር ።

‹‹እነ ዕፀ-ህይወት ትምህርት ቤት ናቸው እንዴ? ... የጫወታውን አቅጣጫ ወደ መጣበት ጉዳይ እንዲያመራላት ነበር ጥያቄውን የሠነዘረው፡፡››

<<አዋ>>

‹‹ልደታቸው ደረሠ አሉ፡፡ ለምን ዝግጅቱ በእናንተ ወጪ እኔ ቤት አይሆንም? በዛውም እኔ አገባበታለሁ፡፡ ‹ብልጥ ዝንጀሮ በሞኝ ክምር ያገባል› አይደል የሚባለው፡፡›› ፈገግ አለች... ስለመጨቃጨቃቸው እንደሰማ እርግጠኛ ሆነች‹‹ሀሳብህ ጥሩ ነው፤ ቢያንስ ከጓደኛህ ይሻላል፡፡››

‹‹የእሱ ሀሳብ እንዴት ነው?››

‹‹እንደነገረህ ነዋ ..! ሆቴል ይዘጋጅ ነው የሚለው፡፡ አሁን አሁን ምን እያሠብኩ እንደመጣሁ ታውቃለህ፤ ለእሱ ስል ይሄንን ሳሎን ወደ ሆቴልነት በመቀየር በመጠጥ ሞልቼ ለእሱ እንዲመች ማድረግ… ፡፡››

‹‹እንግዲያው ከጓሮ ያሉትን ሰርቪስ ክፍሎችም ወደቤርጎ ቀይሪልን፤ እኔም አንዳንዴ ሴቶችን ሸጎጥ አድርጌ መጣና አረፍ እልበታለሁ።

‹‹ምን አንተስ የእሱ ጓደኛ አይደለህ፡፡››

‹‹ከእሱ በፊት እኮ የአንቺ ጓደኛ ነበርኩ…ኧረ እንደውም የዕቃ ዕቃ ባልሽ አልነበርኩ እንዴ?››

ፊቷ ቀላ፡፡ የውብዳር ሁል ጊዜ ስለ እሷ እና ስለ ሁሴን የልጅነት ታሪክ ስታስብ የሠውነቷ ሙቀት ይጨምራል፡፡ በተቀራራቢ ጊዜ አንድ ሠፈር ውስጥ ከማደጋቸው አንፃር ጣፋጭ የሆነ የልጅነት፤ ከዛም ዘሎ እስከ አሁን የዘለቀ የጓደኝነት ቁርኝት በመሀከላቸው አለ፡፡ ከሠሎሞን ጋር እንዲገናኙ መሠላል የሆናቸውም እሱ ነበር፡፡

ካለፈ ትውስታቸው እንደመባነን አለችና ‹‹አዋ እሱማ ለእኔም ጓደኛዬ ነህ፡፡ካንተ ጓደኝነት ያተረፍኳቸው ሦስት ትላልቅ ነገሮች ምን እንደሆኑ ታውቃለህ? ምርጥ ተወዳጅ ልጆች፣ብዙ ብር እና የምሁር ደደብ የሆነ ባል ናቸው፡፡ እና ላማርርህም ሆነ ላመሠግንህ ግራ ይገባኛል፡፡ ባይገርምህ ወደ ኃላ ተመልሼ ሳስብ የዛን ጊዜ ከእሱ ይልቅ አንተን ለምን እንዳልጠበስኩህ ድንቅ ይለኛል፡፡ እንደ ቤተሰብ ሆነን አብረን ማደጋችን እንደወንድምና እህት እንድንተያይ ተፅዕኖ ያሳደረብኝ ይመስለኛል፡፡ ግን እንደ አሁኑ በሳል
ሆኜ ቢሆን ኖሮ መቶ ጊዜ ደጋግሜ አንተን ነበር የምጠብሰው

‹‹ድሮም ሆነ አሁን ዱርዬ እንደሆንኩ እኮ ደጋግመሽ ነገርሽኝ ነበር››፡›› ሁሴን የድንጋጤ ንግግር ነበር የተናገረው፡፡ የውብዳር ስለ እሱ እንደዚህ አይነት ስሜት እንደሚሰማት ገምቶ አያውቅም፡፡

‹‹ዱርዬማ ዱርዬ ነህ፡፡ ግን ንፁህ ዱርዬ ነህ፡፡ አፍቃሪም ነህ፡፡ ከተረጋጋ ማህበራዊ ሕይወት ይልቅ በማዕበል የሚናወጽ ግን በደስታ የተጥለቀለቀ ሕይወት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ደስታ በሕይወት ለመኖር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው የምትረዳው ባጣኸው ጊዜ ነው፡፡ ፍቅር አልባ ሕይወት እኮ በቃ..… ንብ አልባ ባዶ ቀፎ ማለት ነው፤ንብ የሌለበት ባዶ ቀፎ ደግሞ ማር ሊመረትበት አይችልም፡፡ ብር ምን እንደሚያደርግልህ ታውቃለህ፡፡ ቁሳዊ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያስገኝልሀል፡፡ ውጫዊ ችግሮችህን ሁሉ በቀላሉ ታስወግዳለህ፡፡ ሀብታም ሆነህ ሳለ የፍቅር ካዝናህ ባዶ ከሆነ ግን ..በቃ ቀንና ሌት ስለ እሱ ብቻ ታስባለህ፡፡ ሌሎች ፍላጎቶችህ ሁሉ ስለተሟሉ ሌላ የምትጨነቅበት ጉዳይ አይኖርማ፡፡ ስለዚህ ይበልጥ በፍቅር እጦትህ እንድትሠቃይ ትሆናለህ፡፡››

‹‹ቆይ ይሄንን ያህል እስክትማረሩ ድረስ ምን
ትሠራላችሁ፡፡ ለምን አትነጋገሩም?፡፡ የተከሰቱ
ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት ጥረት ለምን
አታደርጉም ? ፍቅር እኮ ዘላለማዊ ነገር አይደለም፡፡ ይወለዳል .. ያድጋል .. ይሞታል፡፡በልጅነቱ .. በወጣትነቱ አልያም አርጅቶ ሊሞት ይችላል፡፡ የዕድሜውን ርዝመት የሚወስነው ግን ሁለቱ ፍቅረኛሞች ስለፍቅር ባላቸው ግንዛቤና ለፍቅራቸው በሚያደርጉለት
እንክብካቤ መጠን ነው፡፡ እናንተም አያያዙን
ያወቃችሁበት አይመስለኝም፡፡ ሲጋቡ
አይታችሁ ተጣድፋችሁ ተጋባችሁ፤ ይሄው
ጀርባ ለመሠጣጣትም ብዙ አልዘገያችሁም፡፡ለማንኛውም በዚህ ጉዳይ ላይ ሌላ ጊዜ በእርጋታ ቁጭ ብለን በሠፊው እንነጋገርበታን፡፡

አሁን ወደ መጣሁበት ጉዳይ እንመለስ
መግባባት ስላቃታችሁ የልጆቹ የልደት ዝግጅት ጉዳይ….፡፡››

‹‹እንዳልክ እሺ፡፡መቼስ አንተ ጠይቀኸኝ ምንም ነገር እምቢ ማለት እንደማልችል ስለሚያውቅ ነው የላከህ፡፡ ከዛ በፊት ግን ስለራበኝ የሚበላ ነገር እንድታመጣ ሠራተኛዋን ልዘዛት›› በማለት ወደ ማብሠያ ክፍል አመራች፡፡

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍13113👏5🔥3🎉2🤔1😢1
አትሮኖስ pinned «#ትንግርት ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በዓይናችን ዓይተን ከወደድነው ነገር ይልቅ በምናባችን ቀርፀን ደጋግመን የተመኘነው ነገር ወደ ጣኦትንት የመቀየር ዕድሉ ሰፊ ነው፡ የውብዳር ለብ ባለ ውሃ ሠውነቷን ተለቃልቃና ፎጣ አገልድማ ፓንቷን በእጇ ይዛ ከባኞ ቤት በመውጣት ወደ መኝታ ቤቷ ልትገባ በእርምጃ ላይ ሳለች ሁሴን የሳሎኑን በር ከፍቶ ገባ፡፡ ‹‹እኔ አላምንም፡፡ ቤቱን…»
‼️‼️
ኢትዮጵያ🇪🇹በቅርቡ ግብረሰዶማዊነት🏳️‍🌈፣የጾታ መቀየር፣ውርጃና ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትን የመሳሰሉ እኩይ አጀንዳዎች በሰብዓዊ መብት ሽፋንና በሌሎች አሳሳች ሀረጎች ተሰውረው የቀረበን ሰነድ
ፈርማለች። 😭
ይህም ሰነድ በዚህ አንድ ወር
ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ ይጠበቃል።🤯
ለዚህም መቃወሚያ Petition በትንሹ 50,000 ፊርማዎችን ለማሰባሰብ በዚህ Link እንሳተፍ።
🇪🇹Say NO!!
ታሪክ የማይረሳውንና  እስከትውልድ ጥግ  በመልካሞቹ የሚዘከረውን ይህን movement በደስታ ተቀላቀሉ!!!

🛑Petition ለመፈረም
https://keap.page/gq193/.html
👍42👎21😁1
የፍቅር 'ርግቦች
ክፍል ሁለት:- ረጅሙ ሌሊት(2)

….ምጥ ነው!.... ያለንበት ሁኔታ። ስለ ወጣቶቹ ሁኔታ ምንም መረጃ የለም። የ(OR) …ኦ አር በሮች ለሰዐታት ተዘግተዋል። በፍርሃት የሚረዱ ልቦች፣ በሮቹ ከአሁን አሁን ተከፈቱ ብለው የሚጠብቁ ጉጉ ነፍሶች እዚህ እንግዳ መቀበያው ውስጥ ቁጭ ብለን እናምጣለን። 

አልፎ አልፎ

“…እህህህህህህ …”  የሳሌም አባት በረጅሙ ይተነፍሳል።

ደሞ እንደገና ለረጅም ጊዜ ፊቱን በሁለት እጆቹ ውስጥ ቀብሮ አርቆ  ያስባል።

አንዳንዴ ተነስተው በዝግታ ወደ ተዘጉት በሮች ይሄዱና ይመለሳል። ከተዘጉት በሮች ውስጥ ሳሌምን ጎትቶ፣ ዳሪክን ስቦ የሚያወጣ  ወይም ደሞ በግድግዳው ውስጥ አሻግሮ የሚደረገውን የማየት ችሎታ ያለው  ይመስል በሮቹ ላይ ግድግዳውን ለረጅም ጊዜ ይመለከታል።

ከዛ በተረፈ ዝምታ ነው። ረጅም ጸጥታ።

ሌሊቱ እየገፋ ቢሄድም የሳሌምንና የዳሪክን መጨረሻ ሳላይ ከዚህ አካባቢ ላልንቀሳቀስ ለራሴ በልቤ ምያለሁ። ለእናቴም ያለሁበትን ሁኔታ ነግሬ  አዳሬ እዚሁ ሊሆን ስለሚችል እንዳትጠብቀኝ ነግሬ… ይኸው አለው ምጥ ላይ፣ ... አለሁ መጠበቅ ላይ።

“…የሳሌም ጓደኛ ነሽ የኔ ልጅ?....”

ጥያቄውን ሰምቼ ቀና ስል የሳሌም አባት ታዴ ፊት ለፊቴ ቆሟል።

ያልጠበቅኩት ጥያቄ።…አሰብኩኝ። …የማን ጓደኛ ነኝ? የማን ጓደኛ አይደለሁም?  የሁለቱም …ነኝ…ወይም የሁለቱም አይደለሁም። ግን ለምንድን ነው እዚህ የመጣሁት። ሳሌምና ዳሪክን በቅጡ እንኳን የማላውቅ ልጅ ነኝ። ታዲያ እዚህ የወጣቶቹ የቅርብ ሰው ይመስል ምን አስመጣኝ? በውድቅት ሌሊት ምን አስቀመጠኝ? …ማሰብ፣ ማምሰልሰል ጀመርኩኝ።  ባስብም ለጊዜው መልስ አልነበረኝም።

“…ጥያቄዬን ሰማሽኝ?....” ታዴ መልሶ ሲጠይቀኝ ከሃሳቤ ወጣሁ።

“….አይ ብዙም የቅርብ ጓደኛ አይደለሁም። ግን ሁለቱንም  በሩቅ አውቃቸዋለሁ። …”

ታዴ ፈገግ ብሎ አየኝ ። “…ት/ቤት ነው የምትተዋወቁት? አንድ ላይ ተምራችኋል?...”

“….አይ..አልተማርንም …” አልኩኝና ሳላስበው መናገር ጀመርኩኝ በልቤ የሞላውን “… እንዳልኩት ብዙ አላውቃቸውም። ግን ደሞ በብዙ የማውቃቸው ያህል ይሰማኛል። ፍቅራቸውን በቅርበት ለማየት እድል አግኝቻለሁ። ፍቅራቸው የሆነ እምቅ ሃይል አለው። ሁለቱ ሲታዩ፣ በፍቅር አለም ላይ ስፍፍፍፍ… ሲሉ …የሚያያቸውን ሁሉ ፈገግ የሚያስብል፣ ድባቴን ከሰዎች ላይ የሚገፍ የሆነ ድብቅ ጉልበት አላቸው። የሁለቱ ፍቅር፣ በአይናችው የሚለዋወጡት ቋንቋ፣ ሲገናኙ የሚያሳዩት ንጹህ መዋደድ በቃ የሆነ ፈውስ ይመስልኛል። የሁለቱ ፍቅር አለማችንን ለሞላው የጥላቻ፣ ማን አልብኝነት፣ እኔነት ወረርሽኝ እጸ -ፈውስ ይመስለኛል። ከነሱ ፍቅር ናሙና ወሰደን ለጥላቻ ፍቱን ክትባት ለጥልና ጸብ ምርጥ መድሃኒት የምናገኝ መስሎ ይታየኛል። ….እና ዛሬ ሳሌምና ዳሪክ ክፋት አገኛቸው ሲባል፣ ጥላቻ አደናቀፋቸው ተብሎ ሲወራ  ….ለማየት ነው የመጣሁት። ምን ለማየት መጣሽ ብለህ ጠይቀኝ። ...”

ታዴ አተኩሮ፣ ተገርሞ እያየኝ ጠየቀኝ  “…ምን ለማየት መጣሽ?...”

“…..ፍቅር ጥላቻን ድባቅ ሲመጣ ለማየት ነው የመጣሁት። መውደድ ጥልን ራሱን ቀጥቅጦ ሲቀጣው ለመመልከት ነው እዚህ ያለሁት። እምነቴ ይህ ነው። ሳሌምና ዳሪክ ምንም አይሆኑም። አይሞቱም። ያሸንፋሉ። ሲያሸነፉ ደሞ በቦታው ላይ ሆኜ ማየት እፈልጋለሁ። ድል ሲነሱ በነዚህ ሁለት አይኖቼ ማየትን እሻለሁ።….” በሁለት ጣቶቼ አይኖቼን አሳየሁት።

ታዴ ዝም ብሎ ሲያየኝ ጥቂት ቆየ። ጭፍግግ ያለው ሃዘን የወረረው ፊቱ ቀስ በቀስ ሲበራ አየሁት።

“…ስምሽ ማነው የኔ ልጅ?...”

ሰሜን ነገርኩት  “… ሳዬ …”

እሱም ስሙን ነገረኝ በአንቱታ ለጠራው ስጀምር ግን አቋረጠኝ “…አባትሽ ነኝ። ሳሌም አንተ ብላ እንደምትጠራኝ እንዲሁ አንቺም …አንተ በይኝ የኔ ልጅ። አንዳንዴ ከልጆች አፍ ብዙ ትማሪያለሽ። እግዚአብሄር ልባቸውን ተጠቅሞ ይናገራል። ….ዛሬ ብዙዎች አዋቂዎች  ካሉኝና ከነገሩኝ የማጽናናት ቃል ይልቅ አሁን አንቺ ያልሽኝ የእምነት ቃልና ንግግር ከፍ ያለ ብርታት ሰጠኝ። ተባረኪ …. ይሄ ክፉ ጊዜ አልፎ ስለ የሳሌምና ዳሪክን ፍቅር ከጅምሬው ብትስሚው ብዙ የሚያስተምር፣ የሚያንጽ ነገር አለው። እኔ ራሴ ለነሱ ማስተማር ሲገባኝ ከነሱ ብዙ ተምሬያለሁ። ፍቅራቸው ተስፋን ሰጥቶኛል … ለካስ ዛሬም በሰዎች ልብ ውስጥ እውነተኛ ፍቅር አለ የሚልን ተስፋ።….”

ወሬያችንንና ጨዋታችንን የሚያቋርጥ ድምጽ …..

በሆስፒታሉ የውስጥ ለውስጥ ድምጽ ማጉያ አንዲት ሴት ማውራት ጀመረች።

    “ Code blue OR. ER Doctor please respond!”

    “ Code blue OR. ER Doctor please respond!”

    “ Code blue OR. ER Doctor please respond!”

ጸጥ ባለው ሌሊት ድምጹ ሲጮህ፣ የቀዶ ጥገናው ክፍል በሮች ሲከፈቱ፣ ሃኪሞች፣ ነርሶችና ሌሎች...
የህክምና ባለሙያዎች ከሌሎች ሆስፒታሉ ክፍሎች  እየሮጡ ሲመጡ አካባቢው ቀውጢ ገበያ መሰለ።

በድንጋጤ ሁላችንም …. ተነስተን ወደ ተከፈቱት በሮች አመራን።

ታዴ የሚገቡትና የሚወጡትን የህክምና ባለሙያዎች “ …ምንድነው ነገሩ? ምን ተፈጠረ? እባካችሁ ንገሩን ….” ቢማጸንም ሁሉም ጥድፊያ ላይ ነበሩ የሚሰማው ሰው የለም።

በግርግሩ መሃል  ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል ልትገባ ያለች አንዷን ነርስ እጇን አንቄ ያዝኳት።ከቅድም ጀምሮ ስትገባ ስትወጣ አይቻታለሁ። “…ስሚኝ ወንድሜና እህቴ ናቸው …እዚህ ውስጥ ያሉት ወንድሜና እህቴ ናቸው። ምን እንደተፈጠረ ልትነግሪኝ ይገባል። እባክሽን ንገሪኝ … ነገሪኝ..."  እንባዬ አይኔን ሞልቶ ጠይቅኳት።

እንደ ማመንታት አለችና ነገረችኝ።  “….የዳሪክ የልብ ትርታ ሙሉ በሙሉ ቆሟል። ትንፋሽም የለውም። የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው።  …..”

እጇን ለቀቅኩት። ፍዝዝ ብዬ እያየኋት ... ተጣድፋ የቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ ገብታ በሩን ዘጋችው።

© hassed agape fiker

ይቀጥላል....

Code Blue … በሆስፒታሎች ውስጥ ኮድ ብሉ (Code Blue) የአንድ በሽተኛ ልብ ትርታ ወይም ትንፋሽ ሲቆም ርዳታ ለማግኘት የሚጠራ ጥሪ ነው።

ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን  ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
♥️♥️♥️♥️♥️❤️❤️
👍575🔥1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


...በሱስ እና በወንጀል ወደ ተጨማለቀ የህይወት ማጥ መግባት ቁልቁለትን ተንደርድሮ የመውረድ ያህል ቀላልና አዝናኝ መሰል ነው ከአዙሪቱ መውጣት ግን ቀጥ ያለ ሰማይ ጠቀስ አቀበትን የመውጣት ያህል ፈታኝና ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ ቢሆንም አሸናፊዎች በጥረታቸው ያሳኩታል፡፡

የዛሬው ቀን ለትንግርት ልዩ ነው፡፡ የክርስቲያኖችን ገና.. የሙስሊሞችን መውሊድ... የደርግን መስከረም 2፣ የወያኔን ግንቦት 2ዐ፣የኢትዮጵያውያንን እንቁጣጣሽ ዓይነት ነው፡፡ ሦስት ዓመት ከተንቦጫረቀችበ የሕይወት አዘቅት ወጥታ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር የምትንደረደርበት የዳግም ውልደት ቀን፡፡ ይህንን የመሸጋገሪያ ቀን ደግሞ በልዩ ሁኔታ ልታከብረው ወስናለች፡፡ሳሪስ የሚገኘዉ ባለ ሦስት ክፍል ቤቷ በልዩ ሁኔታ አምሯል፡፡ ይሄንን ቤት ውጭ የሚገኙት ሁለት
ወንድሞቿና አንድ እህቷ አዋጥተው ነው የገዙላት፡፡ እናትና አባቷ ሳይቀሩ የሚኖሩት ካናዳ ነው፡፡ ከቤተሠቡ ውስጥ ብቸኛዋ አገር ቤት ኗሪ እሷ ነች፡፡ ብዙ ጊዜ ኢትዮጵያን ለቃ እነሱ ጋር እንድትመጣ ጨቅጭቀዋታል፤ ለምነዋታልም፡፡ ግን አልተሳካላቸውም፡፡ ይሄ ሁኔታ ደግሞ አሜሪካን እንደምድራዊ ገነት በሚያስብና በእውኑም በህልሙም ምድሪቷን ለመርገጥ በሚኳትን ሸፋታ ልብ ካለው ትውልድ መከከል ተፈጥራ አብራ እየኖረች የተለየ እምነት መያዟ ከእሷ በስተቀር ሰሚውን ሁሉ ያስገርማል ፡፡

‹‹ይህቺ መስኮት እንደሌለው ቤት በመከራ የምታፍን ነጻነት አልባ ሀገር ....››

‹‹ይህቺ ጥቂቶች ድራማ የሚሰሩባት..ብዙሀኑ በፍዘት የሚመለከቱባት ሀገር.... >>

‹‹ይህቺ በተረት የተሞላች...የምንቸገረኝ ሀገር.....>>

‹‹ይህቺ ማማት እንጂ ..አብሮ መስራት የማይሳካላቸው ጭንጋፍ ልጆች የሞሉባት ሀገር...>>

‹‹ይህቺ ባለውለታዎቾን የማታከብር... ባንዳዎችን የምትሾም የሽፍቶች ሀገር....››

‹‹ይህቺ ነበርኝ እንጂ አለኝን የማታውቅ ሀገር....>>

‹‹ይህቺ ዘረኞች የወረሯት...የጎጠኞች ሀገር...>>

‹‹ይህቺ ......>>በተለያየ ጊዜ ከተለያዩ የቅርቧ ሰዎች ወደ ስደቱ ዓለም እንድትበር ለማበረታቻ የተሰነዘረላት ‹‹..ብትሄጂ ተገላገልሽ እንጂ ምንም አታጪም›› የሚለውን ሀሳብ ለማስረገጥ ከተነገሯት ንግግሮች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ያሉት ነገር ሁሉ ትክክል ቢሆንም ባይሆንም…ለእሷ ግን ከሀገር ለቆ ለመሰደድ ምክንያት አይሆናትም..… እሷ በቃ የሀገሯ ቋሚ ልጅ ነች፡፡ሀገሯ ለእሷ ተመቸቻትም ጐረበጠቻትም በቃ ሀገሯ ነች፤ልትከዳትም.. ልትሸሻትም አትሻም…. ‹‹ሀገሬ ብቻ እኮ አይደለችም ለእኔ ያልተመቸችኝ ..እኔስ ለሀገሬ መች ተመቸዋት?›› የሚል አባባል አላት፡፡በዚህ ምክንያት ዛሬም በውጣ ውረድ ህይወት እየተርገበገበችም ቢሆን ይሄው እዚሁ አለች፡፡ የሀገሯ እንብርት የሆነችው አዲስአበባ ላይ፡፡ የዛሬውን ልዩ ቀኗን ከወዳጆቿ ጋር ልታከብር እየተዘጋጀች፡፡

ሳሎኑ መሀከል ባለ ጠረጴዛ ላይ ሦስት ነጫጭ ሻማዎች ሳይለኮሱ ይታያሉ፣ደብዛዛ ሰማያዊ ቀለም የተቀባው የሳሎኑ ግድግዳ መስኮቱ ላይ ከተዘረጋው መጋረጃ ጋር ስምምነት ፈጥሯል፣ ሻማዎቹ የተቀመጡበትን ጠረጴዛ ስድስት በሚሆኑ በምርጥ ባለሙያ መሠራታቸው በሚያስታውቁ ደረቅ ወንበሮች ዙሪያውን ተከቧል፤በአንድ ጥግ ማዕዘን ላይ መካከለኛ መጠን ኖሮት ሠማያዊ ጨርቅ በለበሰ ጠረጴዛ ላይ የተለያዩ የወጥ ዓይነቶች የያዙ ሣህኖች.... የተቆረጠ እንጀራ ይዞ በነጭ ዳንቴል የተሸፈነ ትሪ.... ኩኪሶችና ብስኩቶች ሲገኙ፣ከአንድ ጥግ ደግሞ የተለያዩ መጠጦች የያዙ ጠርሙሶች ተደርድረዋል፡፡ለግብዣው የተጠሩት ሁሴን፣ ሰሎሞንና ሌሎች ሁለት የቡና ቤት ጓደኞቿ ናቸው፡፡ ድግሱ ግን አስር ያህል ሰዎችን ዘና ባለ ሁኔታ የማስተናገድ አቅም አለው፡፡

የሶኒ ምርት ከሆነው ቴፕ ሪከርደር በስሱ የተለቀቀው የአስቴር አወቀ ዘፈን ለቤቱ
ተጨማሪ ድባብ ለግሶታል፡፡ ግንባሯን ቀና አድርጋ የግድግዳ ሠዓቷን ተመለከተች፡፡ ስድስት ሠዓት ሊሞላ አስር ደቂቃ ነው የቀረው፡፡ የእንግዶቹ መምጫ ሰዓት ደርሷል፡፡

ሁለቱ ሴት ጓደኞቿ እቤቷን ቢያውቁትም ሠሎሞንና ሁሴን ግን ፍፁም አያውቁትም፡፡

ቤት እንዳላት እንኳን ያወቁት ከሦስት ቀን በፊት ስለ ዛሬው ቀን ዝግጅት ስትነግራቸው ነበር፡፡

ሁለቱም በአግራሞት ነበር ያፈጠጡባት፡፡እንደመሠሎቿ በምትሠራበት ቡና ቤት ውስጥ ምትኖር ነበር የሚመስላቸው፡፡ ሌላው ይቅር ለዓመታት አንሶላ የተጋፈፋት... ደጋግሞ ጠረን የተጋራት ሁሴን እንኳን ግምት አልነበረውም፡፡ ትንግርት በሌሎች ነገሮች ግልፅ የመሆኗን ያህል የግል ህይወቷን በተመለከተ ለማንም በጣም ድብቅ ነች፡፡

በተሠጣቸው ምልክት ታግዘው በመጀመያ
ቤት የደረሱት ሁሴንና ሠሎሞን ነበሩ፡፡
ሠሎሞን ጥቁር ሱፍ ከነጭ ሸሚዝና ቀይ መደብ ካለው ክራባት ጋር ለብሷል፡፡ አለባበሱ የቦርጩን መጠን አተልቆበታል፡፡ ሁሴን
እንደወትሮው ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው፡፡ ሠማያዊ ጅንስ ሱሪ ነጣ ካለ ሹራብ ጋር ለብሶ ከታች ስኒከር ጫማ ተጫምቷል፡፡ሁለቱም ፊት ለፊታቸው
ለተገተረችው ትንግርት ሠላምታ መስጠት ዘንግተው የቤቱን ዙሪያ ገባ በአግራሞት ይቃኙ ጀመር፡፡የቤቱ ስፋትና ጥራት ብቻ ሳይሆን የትንግርት ከወትሮ የተለየ አለባበስ ጭምርም
ነበር ያፈዘዛቸው፡፡ እሷ የሆነ ገፀ ባህሪ ተላብሳ የምትተውንበት ቲያትር ቤት የገቡ ነው የመሠላቸው፡፡ ተረከዟ ድረስ የሚረዝም..
ባማረ ጥልፍ ያሸበረቀ የአገር ባህል ቀሚስ ለብሳ ነጭ አንገት ልብስ አንገቷ ላይ ጣል አድርጋለች፡፡

ድሮም የፈረስ ጭራ የሚመስለው ፀጉሯ ሹርባ ተሠርቶ ጀርባዋ ላይ ተነጥፏል፡፡

‹‹እውነትም ትንግርት ነሽ›› ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡ በዝግታ እርምጃ ወደ እሷ ተጠግቶ ደረቱ ላይ ልጥፍ አድርጎ እያቀፋት፡፡

‹‹በዶላር ነበር እንዴ ስትሰሪ የከረምሽው?›› እጁን ለሠላምታ እየዘረጋላት ሠሎሞን እደዛ ያላት፡፡

‹‹አይ..በዩሮ ነው፡፡ ለማንኛውም ቁጭ በሉ፡፡›› በማለት ወደ ወንበሩ መርታ አስቀመጠቻቸው፡፡ በዛው ቅፅበት ሌሎች ተጋባዥ እንግዶቿም እጅ ለእጅ ተያይዘው ገቡ እና ተቀላቀሏቸው፡፡ ጨዋታው ደራ፣ ሳቁ ደመቀ፤ ሁሉም የምርጫቸውን እያነሱ ምሳቸውን ተመገቡ፡፡ ያሻቸውንም የመጠጥ ዓይነት እየመረጡ መጎንጨት ጀመሩ፡፡ ሻማዎቹ ተለኮሱ፡፡ እቤቱ
ደመቀ፡፡ ትንግርት በመሀከል ጨዋታቸውን
አቋረጠቻቸውና በተቀመጠችበት ሆና ንግግሯን ጀመረች፡፡ እንግዶቿም በፀጥታ ያዳምጧት ጀመር፡፡

‹‹ጥሪዬን አክብራችሁ እቤቴ ስለመጣችሁ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ቀን ለእኔ ልዩ ነች፡፡ ልክ የዛሬ አምስት ዓመት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በዲግሪ ስመረቅ የተሠማኝን ዓይነት የደስታ ስሜት ነው ዛሬም እየተሰማኝ ያለው›

‹‹በዲግሪ ስመረቅ ...?›› ሠሎሞን ነበር ፡፡

‹‹አዎ ምነው በሶስዮሎጂ ተመርቄያለሁ፡፡ ያንን ያህል እኮ ትልቅ ነገር አይደለም፡፡ እና ወደ ነገሬ ልመለስና ባለፉት ሦስት ዓመታት የቡና ቤት ሕይወቴ ሁለተኛ ዲግሪዬን ስማር እንደቆየሁና ዛሬ በእናንተ ፊት የምረቃ በዓሌን እያከበርኩ እንዳለሁ አርጋችሁ ቁጠሩት፡፡ እውቅና የሚሠጠኝ አካል ባይኖርምC ብዙ ተዓምር የሚያሠኙ የሕይወት ውጣ ውረዶችን አሳልፌያለሁ፡፡ መዓት ዓይነት ወንዶች
አጋጥመውኛል፡፡ ልምዱ የሌለው ጀማሪ….ያጎበደደ ሽማግሌ… አምስት አስር ልጆች ያሉት ባለትዳር... በስንፈተ ወሲብ የሚሰቃይ ጎልማሳ…ከወሲብ ጥማቱ በቀለሉ የማይረካ ጎረምሳ፣ደግ፣ንፉግ፣ተጫች፣ ዝጋታም፣ተደባዳቢ፣ኧረ ስንቱ…፡፡
👍1069👎4🔥4😁3👏1🎉1
ከዚህ በተለየ መልኩ ደግሞ ሱስ አስያዥ የተባሉትን ነገሮችን ሁሉ በየተራ ሞክሬያቸዋለሁ፡፡
ጫት፣ሲጋራ፣ሺሻ፣ሐሺሽ፣ መጠጥ በየዓይነቱ
ወዘተ…እየደጋገምኩ ወስጄያቸዋለሁ ፤ ጣዕማቸውንም እስኪበቃኝ
አጣጥሜያቸዋለሁ፡፡
ተፈቅሬያለሁ፣ተጠልቼያለሁ፣የተደበደብኩባቸው ቀናቶችም አሉ፣ታስሬም አውቃለሁ፣አንድ ሁለቴም በቡድን የመደፈር ሙከራ ተደርጎብኛል፡፡

በቃ በአጠቃላይ አንድ የቡና ቤት ሴት የሚያጋጥማት ችግርና ደስታ አጋጥሞኛል፡፡

የእኔን ለየት የሚያደርገው ግን እንደሌላው ተቸግሬ፣ ምርጫ አጥቼ ወይንም ስለ ሕይወቱ ያለኝ ግንዛቤ አናሳ ሆኖ አልነበረም ፡፡በሙሉ ፍላጎቴ አውቄ.. ሕይወቱ ምን እንደሚመስል ለመፈተሸ፣ስሜቱ እንዲሰማኝ፣ህመሙ እንዲያመኝ፣ቁስሉም እንዲቆጠቁጠኝ፣በአጠቃላይ ህይወቴን ለማጨማለቅ ስለፈለኩ የገባሁበት ኑሮ ነው፡፡

እናም በሦስት ዓመታት ሂደት ውስጥ ከጠበቅኩት በላይ ሸርሙጪያለሁ፡፡ ከጠቅበኩት በላይ እያንዳንዱን የቡና ቤት የሕይወት ፈርጅ ፈትሼ ቀምሼ አጣጥሜ ስለጠገብኩ.. እነሆ በዛሬዋ ቀን ይህንን ምዕራፍ ዘግቼ ወደ ሌላ የህይወት ገፅ ለመሸጋገር ወስኜ የመዝጊያውን ክብረ በዓል በማክበር ላይ እገኛለሁ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ከቃረምኳቸውና ካካበትኳቸው ታላላቅ የሕይወት ልምዶች በተጨማሪ እናንተን የመሠሉ በህይወቴ ትልቅ ቦታ የምሠጣቸው ወዳጆች ያገኘሁበት ቦታ ስለሆነ በገጠሙኝ ነገሮች ሁሉ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ በነገራችን ላይ ከሽርሙጥና ስራዬ በሚተርፈኝ ጥቂት ጊዜ በመጠቀም ጫር ጫር ያደረኳቸው የተወሰኑ ስዕሎች አሉኝ፡፡ እና እናንተ የተከበራችሁ እንግዶቼ እግረመንገዳችሁን ብትጎበኙልኝ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡›› ከእነሱ አስተያየት ሳትቀበል አፋቸውን በአድናቆት ከፍተው እያዳመጧት ሳለ ከተቀመጠችበት ተነስታ እንዲከተሏት ከጠየቀች በኋላ ከተዘጉት ሁለት ክፍሎች አንዱን ከፍታ ወደ ውስጥ ዘለቀች፡፡ ሌሎችም በየተራ ተከተሏት፡፡

ማንም ከአንደበቱ ድምጽ ማውጣት የቻለ የለም፡፡ መጠነኛ ስፋት ያለው ክፍል ግድግዳው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በተለያዩ የሸራና የቆዳ ላይ ስዕሎች ተሞልቷል፡፡

ከሁሉም በተለየ ሁኔታ... ሁሴን ጋዜጠኛ እንደመሆኑ መጠን በሕይወቱ ብዙ አስገራሚና አስደማሚ ክስተቶች አጋጥሞት ያውቃል፡፡ የዛሬው ግን የተለየ ነው የሆነበት፡፡ እንዴት ብሎ ስጋዋን ስትቸረችር የሚያውቃት አንዲት ሴት እንዲህ ድንቅ ሠዓሊ ትሆናለች ብሎ ሊገምት ይችላል?በፍፅም እንግዳ ነገር ነው የሆነበት፡፡ሁሉም በተመስጦ ድባብ ውስጥ ሠምጠው እያንዳንዱን ስዕል እየተዟዟሩ የሚገባቸውንም የማይገባቸውንም እየተመለከቱ ነው፡፡ትንግርትም የእያንዳንዱን የስሜት ለውጥ... የእጅ እንቅስቃሴያቸውን፤ የፊታቸውን መቋጠርና መፍታታት በፀጥታ እያስተዋለች ምን እየተሰማቸው እንደሆነ የራሷን ግምት ትገምታለች፡

ሁሴን ካስደመሙት ስዕሎች ውስጥ ግንባር ቀደሙ ‹‹ማነው ሸርሙጣ?›› የሚል ርዕስ የሰጠችው ነው፡፡ስዕሉ እንዲህ ይነበባል አንዲት እራፊ ጨርቅ በሠውነቷ አጋማሽ አካባቢ ጣል ያደረገች ለግላጋ ወጣት ሽበት የወረረው ሽማግሌ ጭን ላይ ተቀምጣለች፡፡ የቀኝ እጇን በትከሻው አዙራ ሽማግሌው ደረት ኪስ ውስጥ በመግባት ብር ስትመዝ በግራ እጇ ደግሞ በረሀብ የተጣበቀ የሚመስለው ሆዷን ጨምድዳ ጨብጣለች፡፡ ሽማግሌው ደግሞ በአንድ እጁ ቢራ ጨብጦ በሌላው
እጁ የጉብሊቷን ጭን ያሻሻል፡፡ ከሽማግሌው ፊት ያደፈ ልብስ ለብሳ እራፊ ነጠላ እላይዋ ላይ የጣለች ሴት በንዴት ፀጉሯን አንጨፍርራ ወደ ሰውዬው እየተንደረደረች ስትመጣበት ይታያል.... ከሴትዬዋ ኋላ አራት የደረሱ ሴቶችና ሦስት ወንድ ልጆች አጅበዋታል፡፡ ከሴቶቹ መሀከል ሁለቱ ህፃን ልጆች ታቅፈዋል፡፡ በአትኩሮትና በፅሞና ተመለከተው፡፡ ትርጉሙ ከአንድ ሙሉ መፅሐፍ በላይ ገዘፈበት፡፡ ሌሎች ስዕሎቿንም በየተራ ቃኛቸው፡፡ ‹አፍቃሪዋ ሸርሙጣ› ‹የፈረሰው መንደር› ‹መብረቅ› ‹ትኩሳት› ከስዕሎቹ መሀል የተወሰኑ ናቸው፡፡

ሁለቱ ሴቶች ለስዕል ያላቸው ግንዛቤ የተወሰነ ቢሆንም መደመማቸው ግን አልቀረም ነበር፡፡ በውስጣቸውም የተወሰነ መረበሽ ተፈጥሮባቸዋል፡፡የገዛ ሕይወታቸውን መለስ ብለው እንዲገመግሙ ተገደዋል፡፡‹‹እኛስ የተለየ ምን ነገር አለን…? ተናገሩ ቢሉን የምንናገረው .. አሳዩን ብንባል የምናስጎበኘው፡፡›› ብለው እንዲጠይቁ የትንግርት ስራ አስገድዷቸዋል፡፡

ከሠዓታት ተመስጦ በኋላ ሠሎሞን መናገር ጀመረ፡፡ ‹‹በፊትም ተዓምረኛ መሆንሽን ቀልቤ ይነግረኝ ነበር፡፡አሁን አረጋገጥኩ..በይ አሁን አስተያየቴን ልስጥሽ ተቀበይ….፡፡››

‹‹አይቻልም...በቃል መስማት አልፈልግም፡፡ ማስታወሻ ደብተሬ ላይ የተሰማችሁን በየተራ በፅሁፍ ታሰፍሩልኛላችሁ... ብቻዬን ሆኜ በተመስጦ ደጋግሜ እያነበብኩ ማጣጣም ፈልጋለሁ፡፡››
እንግዶቿን ከሸኘች በኋላ የተዝረከረከ ሳሎኗን አስተካክላ ማስታወሻ ደብተሯን ይዛ ተዘግቶ ወደዋለው መኝታ ክፍሏ ገባች፡፡ ባለ ሜትር ከሃያ ሞዝቦልድ አልጋ ከወደ አንዱ ጥግ መስኮቱን ታኮ ተዘርግቷል፡፡ ሌላውን ግድግዳ ተደግፎ ትልቅ የመፅሀፍ መደርደሪያ ይታያል፡፡ መደርደሪያው አምስት ዘርፎች አሉት፡፡

የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ረድፍ አናት ላይ
ልብ-ወለድ የሚል ሀመግለጫ ተለጥፎበታል፡፡ ሦስተኛው ረድፍ ላይ ሥነ ግጥም ይላል፡፡ አራተኛው ረድፍ ሳይኮሎጂ እና ፍልስፍና ሲሆን የመጨረሻው ረድፍ ደግሞ ልዩ ልዩ የሚል ፅሁፍ ተለጥፎበታል፡፡ ከአልጋው ፊት ለፊት ባለ ባዶ ቦታ ላይ በሚገኝ አንድ ጠረጴዛ ላይ ላፕቶፕ ይታያል፡፡ የመኝታ ቤቷን በራፍ ዘግታ ተንደርድራ አልጋዋ ላይ ተፈናጠጠች፡፡ ድክምክም ቢላትም ውስጧ በልዩ ደስታ ተጥለቅልቋል፡፡ የተሰጧትን አስተያየቶች ለማንበብ ያላት ጉጉት ትንፋሽ ሊያሳጣት ትንሽ ነው የቀራት፡፡ ለማንበብ ተዘጋጀች.. ለመጀመር የፈለገችው ከሴቶቹ ነው፡፡

አንደኛዋ ሴት ...

‹‹እምትገርሚ ነሽ፡፡ እንደምታውቂው አንድ ዓመት ሙሉ አንድ ቤት አብረን ሠርተናል፡፡ ምርጥ ጓደኛሞችም የነበርን ይመስለኝ ነበር፡፡ ግን ምን ያህል ደደብ ኖሬያለሁ፡፡ በእውነት በራሴ አፍሬያለሁ፡፡ እኔ እኮ ስለራሴ አንድም ሚስጥር ሳልሸሽግ ነበር ዘርግፌ የምነግርሽ፡፡.....

ይቀጥላል

ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ቤተሰቦች 200 አስገቡት

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍8917👏6