አትሮኖስ
279K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
459 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከእዳ_ወደ_የምን_እዳ?

#በእውቀቱ_ስዩም

ጋሻው አዳል የተባለ የምወደው የቆየ ዘፋኝ እንዲህ የምትል ዝነኛ ዘፈን አለችው፥

“ማለዳ ማለዳ
ማለዳ መጥተሽ
አይ ! እህህ
ማለዳ መጥተሽ
እኔን ሳታገኝ ትመለሻለሽ"

ዘፈኑን በሰማሁ ቁጥር ጋሻውን እንዲህ እለዋለሁ”  አባ!  በማለዳ የት ሄደህ ነው የማታገኝህ? ውስጥህ የበቀለውን  ችግኝ ስታጠጣ አምሽተህ በዛው መንገድ ላይ የመሰረት ድንጋይ ተንተርሰህ አድረህ ነው?”

   ሳስበው፥ ጋሻው ይህንን ዘፈን የዘፈነው  ለፍቅረኛው ሳይሆን  ለአበዳሪው ይመስለኛል፤ ብድር ስር ምን ትዝ አለኝ !ኢትዮጵያ ብድር መመለስ ከተሳናቸው አገሮች አንዷ ሆና እንደተመደበች  ሰማችሁ አይደል? እምደንቅ እኮ ነው!

ባለፈው ያሜሪካው ያውሮፓ አበዳሪዎች ከኢትዮጵያ ግምጃ ቤት ሀላፊ ጋር ተገናኝተው በጠረጴዛ ዙርያ እና በጠረጴዛ ስር ተወያይተው ነበር;

በቦታው ተገኝቼ እንደታዘብኩት ውይይቱ ይህንን ይመስላል፥

ያሜሪካው - እዳችንን መች ነው ምትከፍሉን?

የኢትዮጵያው- የምን እዳ?🤔

ያውሮፓው- በቢሊዮን  ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንዳበደርናችሁ ረሳችሁት እንዴ?

የኢትዮጵያው - ስራ ስለሚበዛ እንረሳለን!

የአሜሪካው - እስቲ መፎጋገሩን ትተን በግልጽ እናውራ፤  በኢኮኖሚ ደረጃ  የት ላይ ነው የምትገኙት?

የኢትዮጵያው፤- ማለት?

የአውሮፓው ፤-  እርሙን የበላ ድሀ ናችሁ ? ወይስ ቀን የሚወጣለት ድሀ ናችሁ?

የኢትዮጵያው - የሰው ሀብት አለን ! መቶ አምሳ ሚሊዮን ደርሰናል ! ጠባይ ካላችሁ  አምሳ ሚሊዮኑን  ህዝብ ልንለግሳችሁ እንችላለን !

የአሜሪካው - እያወራን ያለነው ስለገንዘብ ነው !

የኢትዮጵያው - እንዳታባክኑት እኛው ጋ ይቀመጥላችሁ ብለን ነው እንጂ ገንዘቡም ቢሆን አለ!

የአውሮፓው- ሌላው ቢቀር ወለዱን  ክፈሉን

የኢትዮጵያው-   ለጊዜው አይርወለድ እንጂ ወለድ አላዘጋጅንም!
 
የአሜሪካው-- ሌላ ምን መፍትሄ ይኖራል?

የኢትዮጵያው-- ጥቂት የእፎይታ ጊዜ ስጡን!

ያውሮፓው --ምን ያህል ጊዜ?

የኢትዮጵያው- ትንሽ አምሳ አመት ብትታገሱን

ያውሮፓው- በአምሳ አመት ጊዜ ውስጥ ብድሩን የምትከፍሉበት የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ትደርሳላችሁ?

የኢትዮጵያው--አይ እናንተ ብድሩን የማትፈልጉበት ደረጃ ትደርሳላችሁ’

የአሜሪካው -- ከዛሬ ጀምሮ ከዛምቢያ እና ከጋና ቀጥሎ መበደር ከማይችሉ አገሮች ጎን ተመድባችሁዋል!

የኢትዮጵያው-  ይህንን ጨካኝ  ርምጃ ዝም ብለን አናየውም 🙁🙁

የአውሮፓው- ምን ልታደርጉ ትችላላችሁ?

የኢትዮጵያው---ብድር የተነፈጉ አገሮች ማህበር መስርተን እንታገላለን  !

የአሜሪካው- እናያለን !

እዚህ ላይ፥ የኢትዮጵያው በንዴት ተሰናብቶ ከሄደ በሁዋላ እንደገና ተመልሶ መጣና ፥
“አንድ የመጨረሻ  ጥያቄ ነበረኝ ! “ አለ፤

ሁለቱ ሀያላን - ምንድነው?

የኢትዮጵያው፤-

“ዛምቢያን አስይዘን መበደር አንችልም?”



ዩቲዩብ ቻናል በቅንነት  እየገባችሁ #ሰብስክራይብ #እያደረጋቹ ማታ #ትንግርት #ክፍል 8 ይኖራል

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍44😁3311👎2🥰1👏1