#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹አይዞሽ..አይዞሽ››
‹‹ያስፈራል..››
‹‹እኔ ደግፍሻለሁ… ቀስ ብለሽ ዋኚ..››እጆቹ ከስር ሲደግፈኝ በማወቅና ባለማወቅ መካከል ሆኖ አንዴ ጡቶቼን ሲጨፈልቃት..አንዴ ወደጭኑ አካባቢ ሲንሸራተት..እሷም ደግሞ ልክ እንደፕሮፌሽናል ተዋናይ ፍጽም በማስመሰል … አንዴ የፈራች መስላ አንገቱ ላይ በመጠምጠም ከሰውነቱ ስትጣበቅ..አንዴ ከእጁ ሾልካ ውሀ ውስጥ እራሷን በመድፈቅ ስትንደፋደፍ…..በመጋል እና በመቃተት መካከል ሆና ግማሽ ሰዓት ያህል ካለማመዳት በኃላ
‹‹ለዛሬ ይብቃሽ ልወጣ ነው ››አለት…
ቅፅበታዊ ውሳኔው አበሳጫት
‹‹እንዴ ምነው …?በደንብ ሳልችል…?››ኮስተር ብላ..ኮስተር አባባሎን ለተመለከተ ገንዘብ ከፍላው የሚያስተምራትን ሰው የምታወራ ነው የሚመስለው፡፡
መቼም የመልመድ ተስፋ የላትም የሚል በሚመስል ስሜት ‹‹አረ ባክሽ..!!እኛ በስንት አመትና ልፋት የቻልነውን ዋና አንቺ በአንድ ቀን ..ለዛውም በግማሽ ሰዓት መልመድ ትልጊያለሽ……?.››አላት..
የሚያወሩት በጣም ጥልቅ ያልሆነ የገንዳው ጠርዝ አካባቢ ቆመው ነው..ውሀው እሷን ጡቷ አካባቢ እሱን ደግሞ እንብርቱን አካባቢ ድረስ ሸፍኖቸዋል…ከፊል እርቃናቸውን እየታያዩ ፊት ለፊት ተፋጠው ነው የምያወሩት..እሷ ለወሲብ እየጎመዣች..እሱ በትምክት እየጎረረባት
‹‹አረ በናትህ ዋናን እኮ የተለየ ጥበብ አደረከው..›› አለችው..እወነቷን ነበር ያለችውት፡፡
እሷ የደሎ መና ልጅ ነኝ..ዋና እየተስገመገመ በሚጋልበው የያዶት ወንዝ በ3 አመቷ በቀልድ ነው የለመደችው…በዕቃ ዕቃ ጫወታ…ያዶት መዋኘት ለለመደ ሰው ደግሞ እዚህ የረጋ ወሃ ላይ መዋኘት ቀልድ ነው፡፡
‹‹እንግዲህ ጥበብ ካልሆነ ያው ሜዳው…አሳይና››ብሎ አበሳጫት…የጀመረችውን የማጥመጃ ዘዴ በደቂቃ ውስጥ እረስታ ያልሸነፍ ባይነት እና የበላይነት መንፈሷ ከውስጧ ተንቀልቅሎ ገነፈለባት…በቆመችበት ቦታ ድንገት ሰመጠችና ውስጥ ለውስጥ መሹለክለክ ጀመረች … ካለችበት ጫፍ ወደሌላ ጫፍ ተወነጨፈችና በሰካንድ በዛኛው ጫፍ ስትወጣ እሱም እሷን ፍለጋ ሰምጦ ኖሮ በድንጋጤ ከመሀከል አካባቢ ከውሀ ውስጥ ሲወጣ ተመለከተችው..አይኑን ከወዲህ ወዲያ አማተረና እሱ ካለበት በብዙ እርቀት ተስፈንጥራ ከውሀ ውስጥ በሰላም እና በፈገግታ ታጅባ ብቅ ጥልቅ እያለች ሲያያት በመገረም እና በንዴት አፈጠጠባት… በቄንጥና ቲያትራዊ በሆነ ትዕይንት ከላይ እየተንሳፈፈች ፤ እየዋኛችና እየተገለባበጠች ስሩ ደረሰች፡፡
‹‹እያሾፍሽብኝ ነበር..…?እኔ ደግሞ የሰመጥሽ መስሎኝ መደንገጤ››
‹‹ብሰምጥስ ምን ያስደነግጥሀል…?››
‹‹እንዴ ሰው አይደለሽ …? ለምን አልደነግጥ…?››
‹‹ስለተጨነክልኝ አመሰግናለሁ››
‹‹አረ ምስጋናሽን ቀቅለሽ ብይው..በአንቺ ቤት አራዳ ሆነሽ በዘዴ መጥበስሽ ነው?››
‹‹ምን ለማለት ፈልገህ ነው…?››ንግግራቸውን በቅርባቸው የነበሩ ሁለት ሰዎች የሚዋኙ መስለው ግን ጆሮቸውን ወደ እነሱ ቀስረው እያዳመጡ ነው..ደንታም አልሰጣት፡፡
‹‹ሰምተሻል ባክሽ….እኔ ለእንደአንቺ አየነት ጩሉሌ ከምሸነፍ አራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…..
"እኔ ደግሞ በጥቂት ቀን አንተን መጥበስ ካልቻልኩ እራሴን አጠፋለሁ"
"አፍጥጦ አያትና ምንም ሳይናገር ጥሏት ሄደ
እሷም ከገንዳው ወጥታ ወደመኪናዋ ተንደረደረች...
ከፍታ ገባችና በውሀ የራሰውን የዋና ልብሷን አውልቃ ሌላ ልብሷን በመልበስ ከመኪናው ወጣች..ኮፈኑን ተደግፋ ንስሯ ፊት ለፊት ቆማ ማሰብ ጀመረች …. በአካባቢው የሚያልፍ ሰዎች ከንስር ጋር ባልተለመደ ሁኔታ ፊት ለፊት ተፋጣ ሲያዩት በመገረም እየተገላመጡ ሲያልፍ አስተውላለች፡፡
‹‹የሆነውን አይተሀል አይደል…?በቃ ፈልገዋለሁ››የምታወራው ለንስሯ ነው
(ይቅርብሽ የሚል ቃል ወደ አዕምሮዋ ላከላት)
‹‹ አታበሳጨኝ..በቃ ፈለኩት ማለት ፈለኩት ነው …አሁን የሆነ ነገር አድርግልኝ …ሆቴሉ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ቢራ እየተጎነጨው እጠብቅሀለሁ…››
ተነስቶ በረረ……..
እሷም እንዳለችው ወደሆቴሉ በረንዳ በመሄድ ወንበር ይዛ ተቀመጠችና ቢራ አዘዘች….እንግዲህ ያሰበችው እስኪሳካ ሌላነገር ማሰብም አልቻለችም…ቀልቧን ሁሉ ጥቁሩ ልጅ ላይ እንደተጣበቀ ነው…….ጭኗ መካከል ይበላት የነበረው አሁንም እየበላት ነው…. ከመብላቱም አልፎ እያቁነጠነጣት ነው… አሁን እንደዚህ የሚያደርጋት የወሲብ ጥማት ነው…እንጂማ በቅጽበታዊ የፍቅር ፍላፃ ተመታ አይመስልም… ‹‹እንደዛ አይነት ደካማነትማ አይነካካኝም…መጀመሪያውኑስ ፍቅር ምንድነው …...?የፍቅር መነሻውም መድረሻውም አይስማማኝም፡፡ማለቴ በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል ያለው የፍቅር ስሜት መነሻው የተለያየ ቢሆንም መዳረሻው ለምን ተቀራራቢ ወይም ተመሳሳይ ሆነ….ሁል ጊዜ ለምን ፍቅር በወሲብ ልጥ ይታሰራል፡፡ልጡስ ለምን በጋብቻ ሰንሰለት እንዲቀየር ይጠበቃል?ለምን ፍቅር….ወሲብ..መለያት ወይም ፍቅር….ወሲብ ..ጋብቻ ..ልጅ መውለድ….፡፡ሌላስ አማራጭ ለምን አይኖርም…ለምሳሌ ፍቅር …ጓደኝነት….በቃ፡፡እንደዛ ቢሆን ምንም ገደብ አያጨናግፈውም…አንድ ወንድ መቶ ሴት ቢያፈቅር ሚኮንነው ሰው የለም…ምክንያቱም ፍቅር ከዛ ጓደኝነት ነው…ባል ይኑራቸው አይኑራቸው….ወደፊት ያግብ አያግቡ አያስጨንቀውም…፡፡ፍቅር ብቻ…ከልብ ማፍቀር ግን ደግሞ እንዳሻቸው ሲበሩና ሲከንፉ እያዩ መደሰት…ሲያገቡ መጨፈር..ሲወልዱ መሳም….ሲያለቅሱ ጉያ ውስጥ ሸጉጦ ማባበል፡፡ግን ይህ ህልም ብቻ ነው …አጉል ምኞት ፡፡ተፈጥሮም ማህበረሰብም አይፈቅድም፡፡ወንድ አንድን ሴት አፍቅሮ እጆቾን ሲነካ በሰውነቱ እሳተ ጎመራ ይንቀለቀላል…ከንፈሯን መገሽለጥ ጭኖቾን መፈልቀቅ ቀዳሚ ምኞቱ ይሆናል…በቃ ማህበረሰብም ተፋቀሩ ሲል ተኙ መከተል እንዳለበት ያምናል..ፍቅር እና አልጋ…ነገሩ ጥሩ ነው ጤነኝነትም ነው…ፍቅርም ወሲብም ለሰው ልጅ የተሰጡ ደስታቸውን የሚያመርቱባቸው ተፈጥሮአዊ የስሜት እርካታ ፍብሪካዎቻቸው ናቸው፡፡ግን ቢሆንስ ሁሉም ፍቅር ወደወሲብ ሁሉም ወሲብ ደግሞ ወደ ጋብቻ መቀየር አለበት ወይ… ?….አይ ምን እየቀባጠርኩ ነው …አትፍረዱብኝ ምን አልባት ይሄንን አይነት ከሰው ልጅ አስተሳሰብ ውጭ የሆነ ነገር ከአባቴ ዝርያ በደም የወረስኩት ይሆናል፡፡››በማለት ስትብሰለሰል ቆየች
ከ15 ደቂቃ በኋላ ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ንስሯ ተመልሷ መጣና በቅርብ ርቀት ጨለማውን እየሰነጠቃ በአየር ላይ ሲንሳፈፍ ተመለከተችው…ሀሳቧን ሰበሰበችና ከእሱ አእምሮው ጋር አገናኘችት… ያየችውን ወይም አሁን እያየች ያለውን ነገር ለማየት ….
✨ይቀጥላል✨

👍130❤16😁5😱4👎3🔥1🤔1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
ሰውዬው አሁን ያለበት ቦታ ከዚህ እሷ ካለችበት ብዙም በማይርቅ ሌላ ሆቴል ውስጥ ነው..ግን እየጠጣ አይደለም..ቤርጎ ውስጥ ሆኖ ነው የሚታያት፡፡ደግሞ ብቻውን አይደለም..አንድ ቅንጥስጥስ ያለች ለጋ ወጣት ክንዱ ላይ ተዘርራ በፀጉር የተሸፈነ ጥቁር ደረቱን እየዳበሰችለት ነው…..እሱ ከወገቡ በታች ቢጃማ ሱሪ አድርጓል… ልጅቱ ግን በፓንት ብቻ ነች…ደግሞ የሰውነታቸው ቀለም ልዩነት ..እሷ ብጭጭ ያለች ክልስ የምትመስል ሴት ነች….ደግሞ ስዕል የመሰለ ውበት ያለት..
‹‹ይህቺን ይዘህ ነው ለካ በእኔ ላይ የጎረርክብኝ?››ስትል አሰበች....እና ይበልጥ የፉክክር መንፈሷ ተነቃቃ…
‹‹የእኔ ፍቅር አሁንም እንደተበሳጨህ ነው?››ልጅቷ ነች የጠየቀችው
‹‹በጣም እኮ የምታናድድ ሴት ነች..አንተን በዛሬው ቀን ካላወጣሁ እራሴን አጣፋለሁ ትለኛለች?››
(አሁንም ስለእሷ እያወራ መሆኑን ስታውቅ ውስጧ ሞቀ..የሚበላት አካባቢም ጨመረ)
‹‹ታዲያ ጤነኛ ነች ትላለህ?››
‹‹ጤነኛማ አይደለችም››
‹‹ታዲያ ንቀህ ተዋታ..ለምን አትረሳትም .... ?መቼስ አሁን እኔ እቅፍ ውስጥ ነህ…መጠጡም እዚሁ ክፍላችን አለ.. እራቱም እዚሁ ነው የሚመጣልን..እኔን የመሰለች ዘበኛ አለህ እንዴት ብላ ከየት ታገኝሀለች..ነው ወይስ እንደፎከረችው እራሷን ታጠፋለች ብለህ ሰጋህ?››
‹‹ፍግም ትበላ››
‹‹ተው ተው እደዛማ አይባልም…አሁን ለሚሰማህ ሰው አሪፍ ጨካኝ አትመስልም…ሁል ጊዜ እኮ አንደበትህ እና ሆድህ አይገናኝም……….››
‹‹እና እንዴት ነው የሚባለው?››
‹‹አይ ያን ያህል ከወደደችህማ እራሷን ከምታጠፋ አንዴ ብትቸገርላት?››
ገፍትሮ ከደረቱ ላይ አስፈነጠራት ..
እየሳቀች ‹‹አትበሳጭ.. ቀልዴን እኮ ነው›› አለችው ወደአስለቀቃት ቦታ እየተመለሰች
‹‹እንዲህ አይት ቀልድ አይመቸኝም ..ካንቺ ውጭ የሌላ ሴት ገላ ከማቀፍ እኔም እራሴን ባጠፋ ይሻለኛል…››
‹‹በቃ የእኔ ጀግና›› ብላ ወደ ደረቱ ተመለሰችና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀችበት… ገለበጣትና እላዬ ላይ ተከመረባት…መሳሙን ሳያቆም በአንድ እጁ የለበሰውን ቢጃማ ከሰውናቱ መዥርጦ አወለቀ..
በንስራ ታግዛ እያየችው ያለው ገበናቸው የወሲብ ረሀቧን ከምትቆጣጠረው በላይ እንዲሆንባት አደረገው ፡፡
እሷ ልትተኛው የፈለገችው ወንድ ከዕጮኛው ጋር በወሲብ ዳንኪራ እየጨፈረ ነው…እናም ደግሞ በራሱ ታማኝነት እንዴት ተመፃዳቂ እንደሆነ ከንግግሩ ለሁለተኛ ጊዜ መስማቷ የቅድሞውን ብስጭቷን በእጥፍ እንዲጨምር አደረገው…
ሂሳቧን ከፈለችና መቀመጫዋን ለቃ ወደመኪናዋ አመራች ..መኪናዋን አስነሳችና ሰውዬዋ ወዳረፈበት ሆቴል ነዳችው… ንስሯም በሰማዩ ላይ ጭለማውን ሰማይ እየሰነጠቀ ከላይ እየተከተላት ነው፡፡
ንስሯ‹‹ፍቅራቸውን እና መተማመናቸውን አየሽ አይደል…?ተይው በቃ….››የሚል መልዕክት አስተላለፈላት
‹‹አልተውም.. የማታግዘኝ ከሆነ በራሴ እወጣዋለሁ….››መለሰችለት ለንስሯ
‹‹በራስሽማ የበለጠ ጥፋት ታጠፊያለሽ››
‹‹እንግዲያው ዝም ብለህ በቀላሉ ያሰብኩትን እንደሳካ አግዘኛ››
ንስሩ የመስማማት ምልክት አሳያት ..
አሁን ሆቴል ደረሰችና መኪናዋን ቦታ አስይዛ አቆመችና ሞተሩን አጠፋች ….በቀጣይ ምታደርገውን ነገር ግን ገና አላወቀችውም .. መኪናዋ ውስጥ ሆና ትኩረቷን ስብስባ እና ከንስሯ እይታ ጋር እይታዋን በማጣመር ልክ ለስለላ በድብቅ እንደተቀበረ ካሜራ ክፍላቸውን ወደመቃኘቱ ተመሰች
አሁን ፍቅረኛሞቹ ስራቸውን ጨርሰው ሻወር ቤት ግብተዋል…እየታጠቡ ነው ፡፡በመታጠባቸው ውስጥ መተሸሻት ..በመተሻሸታቸው ውስጥ ከወሲባዊ እርካታ በኃላ ያለ ድሪያ አይነት ማሽካካት ይታይባቸዋል….. ታጥበው ከጨረሱ በኃላ ሁለቱም ፎጣ አገልድመው ሻወሩን ለቀው በመውጣት አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አሉ….እሱ ተንጠራራና ፊት ለፊታቸው ካለው ጠራጴዛ የወይን ጠርሙሱን በማንሳት የጎደለውን የወይን ብረጭቆ በመሙላት አንስቶ ሰጣት ..ለራሱም አነሳና ተጎነጨ ….እሷ ግን ጠቀም አድርጋ ተጎነጨችና አፏን ወደእሱ አሞጠሞጠች …ከፈተላት.. በጉንጮቾ ያቆረችውን ወይን በከፈተላት ጉንጩ ውስጥ ገለበጠችለት››ይሄንን ስታይ የሆነ ምቾቷ እየቀነሰ መጣ….ያልተለመደ አይነት ሆነባት፡፡
‹‹አሁን ሰርጋችን ቀን መቼ እናድርገው?››እሱ ነው አይን አይኗን በስስት እያያት የጠየቀው፡፡
‹‹እኔ እንጃ››
‹‹በእኔ በኩል በጣም በቅርብ መሆን አለበት ባይ ነኝ››
‹‹ቅርብ ስትል? ››
‹‹በሚቀጥለው ወር ውስጥ››
‹‹እርግጠኛ ነህ….?እኔ ግን ያለችንን ጊዜ እንደዚሁ በፍቅር ብናሳልፋት ይሻል ይመስለኛል፡፡
‹‹አንቺ ደግሞ ስንት ወር ያወራንበትን ነገር ከእንደገና ወደኃላ ትመልሺዋለሽ ..አድሮ ቃሪያማ አትሁኚ››ኮስተር ብሎ መለሰላት
‹‹የእኔ ፍቀር ላንተው እኮ አስቤ ነው…ከዚህ ጋብቻ መሳቀቅ ብቻ ነው የሚተርፍህ ››
ያንን ጥቁር ፊቱን ይበልጥ አጨልሞ ‹‹ግድ የለም ለእኔ አታስቢ..አንቺ ባለችሽ ጊዜ ቶሎ ቶሎ መኖር መቻል አለብሽ ፡፡.ድል ባለ ሰርግ ማግባት …ልጅ ወልዶ ማቀፍና ማጥባት ላንቺ የሚገቡሽ ነገሮች ናቸው››አላት
‹‹ትቀልዳለህ…..ከዚህ በፊትም ነግሬሀለው …ዛሬም እንደግምልሀለው የማላሳድገውን ልጅ በፍጽም አልወልድም››
‹‹እንግዲህ ነግሬሻለሁ…
ካልወለድሽልኝ አንቺ ጥለሺኝ ስትሄጂ የምጽናናበት ነገር ስለሌለ ያው ከሸኘሁሽ በኃላ እራሴን በማጥፋት እንደምከተልሽ እና በምትቀበሪበት ጉድጓድ አብሬሽ እንደምቀበር አትጠራጠሪ››
‹‹ለምን ታስጨንቀኛለህ?››
‹‹እያስጨነቅኩሽ አይደለም…በትክክል የማደርገውን እየነገርኩሽ ነው…አንቺ ስለመሞትሽ ማሰብን እርሺውና በየቀኑ ማድረግ የምንችለውን እናድርግ.. እንጋባ… ውለጂልኝ..ከዛ በኃላ ያለውን ነገር ለእግዜር እንተወው ..ምን ይታወቃል የሆነ ተአምር ተፈጥሮ በሀኪም ከተቆረጠው የመሞቻ ቀንሽ በፊት ፈውስ የሚሆን መድሀኒት ይገኝ ይሆናል››
ኬድሮን በምሰማው ነገር እየደነዘዘች ነው።

👍110❤9😱5🥰1👏1😢1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ብርጭቆውን አንስታ ተጎነጨችለትና መልሳ በማስቀመጥ መልስ ለመሰጠት ተዘጋጀች….
ኬድሮን በምታየው ነገር በጣም ደንዝዛለች …አላማዋንም ዘንግታ ….የሚበላትንም ነገር ችላ ብላ በምስጠት እየተከታተለችው ነው..በሌላ እይታ…. በሌላ መነጽር
ቀጠለች ልጅቷ‹‹የእኔ ፍቅር በጣም እኮ ነው የምትገርመኝ…. ዛሬም ተስፋ አትቆርጥም፡፡ በቃ እኔን እኮ ከዚህ በሽታዬ ለማዳን ለአመታት ለፋህ..ያለህን ንብረት ጨረስክ ..እስራኤል፤ህንድ፤አሜሪካም ጭምር ወስደህ በአለምአቀፍ ደራጃ አሉ በተባሉ የህክምና ተቋምና ምርጥ ጠቢቦች እድታከም አድርገሀል…በቃ አልተሳካም …እንደውም በአንተ ጥረት ነው የአንድ እና የሁለት አመት ቀሪ እድሜ ማግኘት የቻልኩት..ስለዚህ ይህቺን ባንተ ጥረት ያገኘኋትን ቀሪ ዕድሜዬን እንዳልከው በፍቅር እናጣጥምና ከዛ በሰላም ሸኘኝ …ባይሆን እዛ ጎጆ ቀይሼ መኖሪያ ቦታ አመቻችታ እጠብቅሀላሁ..››አለችና ጉንጩን በመሳም ስሩ ውሽቅ አለችበት..እሱም አጥብቆ አቀፋትና በአንድ እጁን ከአይኖቹ ሚንጠባጠበውን እንባ ማበስ ጀመረ ..
ከዚህ በላይ መቆየትም ሆነ በአላማዋ መግፋት አልቻለችም ….መኪናዋን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው..ተቀጣጥሎ የነበረው የወሲብ ስሜቷ አሁን ከስሟል.‹‹.በዚህ አይነት ፍቅር ውስጥ እንዴት መግባት እችላለሁ?››..ይህቺንስ ሞት ፊት ለፊቷ የቆመባትን ሴት እንዴት መፎካከር ይቻላል… ?ከእሷ መንጠቅ ወይም መስረቅ በየትኛው ሞራል….?
እንደውም ከዚህ በላይ ታሪካቸውን ማወቅ ፈለገች..ልታግዛቸው ፡፡ከቻለች ለመሞከር….ግን ዛሬ አይደለም… ሌላ ቀን …በዚህን ሰዓት በዚህ የጨፈገገ ስሜቷ ውስጥ ሆና ምንም ማድረግ አልቻለችም..አሁን እቤቷ ገብታ ጥቅልል ብላ መተኛት ብቻ ነው የምትፈልገው…መኪናዋን እያከነፈች ነው… ንስሯ ክንፉን እያርገፈገፈ ጨለማውን በመሰንጠቅ ከፊቷ ይከንፋል..ሁኔታው የደስታ ነው….መጀመሪያም አካሄዷ ደስ አላሰኘውም ነበር….ሀሳቧን ቀይራ በቁዘማም ቢሆን ወደቤቷ መመለሷ እሱን እያስፈነጠዘው ነው…፡፡
""""
ምቾት የሌላው ምሽት ነበር ያሳለፈችው….ደግሞ ርዝመቱ እንደተለመደው 11 ሰዓት ከእንቅልፏ ተነሳችና እቤቷ ውሰጥ የተወሰነ የሰውነት እንቅስቃሴ ከሰራች በኃላ ወደበረንዳዋ ወጣች…ንሰሯ አብሯት ነበር የወጣው…..ለተወሰነ ደቂቃ ሀሳቧን ከራሷ ጋር ነበር ያደረገችው.. ኤርፎኗን ጆሮዋ ላይ ሰክታ ከሞባይሏ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ከፍተችና እያዳመጠች ንጽህ የጥዋት አየር ወደ ሳንባዋ እየማገች ነው፡፡
ግን በመረጋጋት ውስጥ ሆና በጽሞና ሙዚቃውን ብቻ ማዳመጡን ቡዙም ልትዘልቀበት አልቻለችም..ሀሳቧ አሁንም ትናንት ላይ እንደተጣበቀ ነው…የብልቷ መብላት ቢተዋትም አዕምሮዋ ግን አሁንም ድረስ እያሳከከት ነው….እሷ እኮ ወንድ ልጅን ለዚህን ያህል ጊዜ ርዝመት በልቧ አዝላ አታውቅም… ፎክራ ስላላሳካችው ዝታ ስላልፈፀመች የመሸነፍ ቁጭት የፈጠረባት መብሰልሰል ይሆናል……….?
አዎ ከንስር ጋር እየኖሩ ሽንፈትን አሜን ብሎ በመቀበል አንገትን መድፋት የማይታሰብ ነው…በምክንያቱም ለንስር መታገል.. ታግሎም ማሸነፍ ተፈጥሮ ያደለው የብቻ ፀጋቸው ነው…ንስር የሞተ እንስሳ ንክች አያደርግም…የሚገድለውን ለማጥመድ ወይም ኢላማውን ለማግኘት መቶ ኪሎ ሜትር ሊያስስ ይችላል ..አስሶ አንዴ ራዳር ውስጥ ካስገባ ግን ንቅንቅ አይልም..ምንም ተአምር አያዘናጋውም…ግዳዩን ሳይጥል ውልፍች የለም…አዎ አድኖ አሳዶና ታግሎ በመጣል የገደለውን ብቻ ነው የሚበላው….፡፡እይታው ጠሊቅና እሩቅ ነው፡ካአለበት ቆሞ በአምስት ኪሎ ሜተር እርቀት ያለ ነገር ላይ ማነጣጠር ይችላል፡፡ልፋቱ የሌለበትን… አሸናፊነቱ የማይዘመርበትን ንክች አያደርግም… …ይህ የሰው ልጅም የህይወት መስመሩን ለማግኘት የተፈጠረበትን አለማ ለመገንዘብ የእድሜውን እሩብ ሊያባክን ይችላል…. ማባከኑም አግባብ ነው..መስመሩን ከያዘ በኃላ ግን አይኑም ቀልቡም መቶ ፐርሰንት መስመሩ ላይ መሆን አለበት፡፡ ትኩረቱም ጥረቱም ወደዛ ወደህይወት ግብ መዳረሻው የሚያደርሰው ሊሆን ይገባል…. የንስር ህይወት ይሄንን ነው የሚያስተምረው…
እሷም የሰለጠንችው በንስራ ስለሆነ ኢላማ ያደረገችበትን ነገር ከግብ ካላደረሰች ያማታል….አሁን እየተሰማት ያለው ስሜት ግን የተለየ ይመስላታል … ምክንያቱም ከባሪያው ልጅ ባልተናነሰ ቀዮ እጮኛውንም ከምናቧ ልታስወግዳት አልተቻለትም፡፡
‹‹አዎ መሞት የለባትም….በዚህ ዕድሜዋ መሞት አይገባትም››…ብላ በውስጧ ደመደመች…መልሳ ደግሞ እራሷን ሞገተች፡፡
‹‹ …በዚህ ዕድሜዋ መሞት የለባትም ስል ምን ማለቴ ነው..
…….?ሰው በስንት አመቱ ነው መሞት ያለበት……….?››ስትል አሰበች፡፡
ወጣት ሆኖ የሞተ ሰው ለምን በዛ ዕድሜዬ ሞትኩ ብሎ ይቆጫል ወይም ፈጣሪውን ይወቅሳል….? አይመስለኝም፡፡.ምን አልባት ይሄኛው አለም እና ከሞት ወዲያ ያለው ያኛው አለም ተብሎ ሚከፈል ዓለም ያለ ቢሆን እንኳን ያኛው አለም በእግዜር ሙሉ ቁጥጥር እና ፍቃድ የሚተዳደር ነው ሚሆነው..እንደዛ ከሆነ ደግሞ ከዚህኛው ዓለም ፍጽም የተሻለ ነው የሚሆነው..ያ ማለት ደግሞ ሞቶ ወደዛኛው አለም የተሸጋገረ ሰው በህፃንነቱም ሆነ በወጣትነቱ ቢሄድ ተገላገልኩ በምድር ከመሰቃየት፤ከመራብ፤ከመጠማት፤ከመጋዝና ከመታሰር እንኳንም በጊዜ ወደዚህ መጣሁ የሚል ይመስለኛል፡፡ሞት ማለት ሙሉ በሙሉ በስጋ መበስበስ እና በነፍስ መክሰም ወይም ወደ ምንምነትም መቀየር ከሆነ ደግሞ ለመፀፀት እና ለምን ቶሎ ሞትኩ …….?ብሎ ለማሰብም የሚያስችል ዕድልም አይኖርም ….ሞች በቋሚው አዕምሮ ሲመዘን ነው በልጅነቱ ተቀጨ..በወጣትነቱ ተቀጠፈ የሚባለው….እና አሁንም እሷ የልጅቷ እሞታለሁ ማለት ለምን ይሄን ያህል እንዳሳሰባት አልገባትም .. …….?ነው ወይስ ለተመኘችው ልጅ ስትል ይሆናል..…….?
‹‹እሱ እንዲያዝንብኝ ስላልፈለኩ ይሆን….?››ስትል እራሷን ትጠይቃለች ..ለጠየቀችው መልስ ከመፈለግ ይልቅ ግን ሌላ ጥያቄ እየጨመረችበት ነው….
እሷ እንደሆነ በመግደልም ሆነ በማዳን አታምንም…እንደእሷ እምነት ሰው የኖረበትን ጊዜ አጭርም ሆነ ረጅም ዋናው የኖረውን ያህል ተደስቶ መኖሩ ነው…..እርግጥ መግደል የእግዜያብሄር የአታድርግ ክልከላ ውስጥ ከሚካተቱ ትዕዛዞች መካከል አንዱ እንደሆነ ታውቃለች፡፡ቢሆንም ህይወት ከመግደልና ከመገደል ውጭ ህልውናዋ ፀንቶ እንደማይቆምም በተግባር አይታለች….ብዙ መግደል የቻለ ብዙ ይኖራል….ለመግደል የሰነፈ በጠንካራው ተገድሎ በሞቱ ለሌላው መኖር ምክንያት ሆኖ ያልፋል፡፡ይሄንን ከህይወት ተምራለች፡፡
ግን እግዚያብሄር አትግደል ሲል ለሰው ብቻ ነው እንዴ የሚሰራው..…….?ሰውን መግደል ብቻ ነው በኃጥያት የሚያስጠይቀው….? ለምን ….?ሰው በእግዜያብሄር ሀምሳል ስለተፈጠረ ልዩ መብት ስላለው….?፡፡ነው ወይስ ሰው የእግዜያብሄር ቤተ መቅደስ ነው የእግዜያብሄርን ቤተ መቅደስ ማፍረስ ደግሞ ያው ቀጥታ እሱን መዳፈር ነው…..ከእሱ ጋር መላተም ነው……ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ ተብሎ ስለሚታሰብ…..? …አትግደል የተባለው ነፍስ ያለውን ሁሉ ከሆነስ ……….?ያማ የማይቻል ከባድ ትዕዛዝ ይሆናል…፡፡ምክንያቱም እንስሳት ነፍስ አላቸው… ተክሎች ነፍስ አላቸው…ለመኖር ደግሞ ህይወት ያለው ነገር ሁሉ መመገብ አለበት..ለመመገብ ደግሞ አንዱ ዝርያ ሌላውን እየበላ ነው ነፍሱን የሚያቆየው…ለመብላት ደግሞ የግድ መግደል

👍93❤6👎6🔥2😁2
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሰላሳ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
‹‹የትናንቶቹን ልጆች ሙሉ ታሪክ ማወቅ እፈለጋለሁ››ለንስሯ ነው እየነገረችው
‹‹ይቻላል››መለሰለት ዛፉ ላይ ሆኖ
‹‹በቃ አሁን ዝናቡ ሊዘንብ ነው …ዝናቡ ሲያባራ ታጣራልኛለህ››
በእሷ በማሾፍ በሚመስል ሁኔታ ክንፉን አርገፈገፈ…እሷ እንዲህ ያለችው ግቢዋ ውሰጥ ያሉ አዕዋፋት ዝናቡን ሽሽት በየዛፎቹ ቅርንጫፎች ሲሸሸጉ እና ወደጎጆቸው ሲገቡ ..ዝንጀሮዋችና ጉሬዛዎቾ ወደመጣለያቸው ሲሸጎጡ አይታ… እሷም ውሽንፍሩን በመፍራት ወደቤት ልትገባ መነሳቷን ከግምት በማስገባት ንስሯም እየዘነበ ካለው ዝናብ ለመጠለል አብሮኝ ተከትሎ ወደቤት ይገባል በሚል ግምት ነው…..በሀሳብ ውስጥ ሆና በዝንጉነት ያሰበችው ሀሳብ
ለካ ንስር ነው…
ንሰሯ አይኖ እያየ ወደላይ ተምዘገዘገ .እያነሰ እያነሰ ደመናውን ሰንጥቆ ከአይኗ ተሰወረ ….አዎ ከደመናው በላይ ብቻ ሳይሆን ከሚዘንበውም ዝናብም በላይ ነው የሆነው..እሷ ዝናብን ስትጠለል ንስሯ ንፍስ የቀላቀለውን ውሽንፍር እየሰነጠቀ በኩራትና በአሸናፊነት ከተዘረጋው ደመና እና ከሚረግፈው ዝናብ በላይ በመምጠቅ ቁልቁል እያየ ሊዝናናበት..
በንስሯ ሁኔታ ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ገባች…..ቁርስ ልታበስል አስባ ነበር …ግን ምንም አይነት የምግብ ፈልጎት ስለሌላት ወደመኝታ ክፍሏ ገባችና መልሳ አልጋዋ ላይ ወጣች..አዎ በዝናብ መኝታ ውስጥ ሆኖ ማሰብ ወይም ሙዚቃ ማዳመጥ የሚያስደስታት ነገር ነው…
‹‹እስቲ ንስሬ ስለትናንቱ ባሪያ ልጅ እና በቅርቡ ሟች ስለምትሆነው ፍቅረኛው ምን አይነት ታሪክ ይዞልኝ ይመጣ ይሆን ……….?የልጅቷስ የማይድነው በሽታዋስ ምን ይሆን….?እንድትሞት ልተዋት ..ወይስ ከንስሬ ጋር ሆኜ ላድናት……….?ቆይ እሱ እንደታሪካቸው ሁኔታ ነው የሚወሰነው….አሁን ንስሬ ከቅኝት ሲመለስ ልክ እንደተካታታይ የሆሊውድ ፊልም ታሪካቸውን ይዘረግፍልኛል….››
ምክንያቱን ባታውቅም ንስሯ ካሰበችው በላይ ቆየባት፡፡
ቆይ ቆይ እስኪ ድምጽ ይሰማኛል………….
ገርበብ ያለው መኝታ ቤት ተበረግዶ ተከፈተ…ሌላ ሰው አይደለም ንስሯ ነው….በራፉን በመንቁሩ ስቦ በመበርገድ በሮ አልጋዋ ላይ ከጎኗ ጉብ ያለው… ክንፎቹን ወደ ውስጥ ሰብስቦ አንገቱን ቀብሮ ሽብልል ብሎ ተኛ…ጥሩ ነገር ይዞላት እንዳልመጣ ገባት…ሁልጊዜ የሆነ ነገር እንዲያጣራላት ልካው ያገኘው መረጃ አና ከምፈልገው በተቃራኒ ከሆነ እንዲህ ነው ዝልፍልፍ የሚለው…ዝልፍልፍ ማለት ደግሞ በእሱ አያምርም፡፡
የንስሯን ሁኔታ ሰለልጁ ታሪክ ለማወቅ ያለቻትን ጉጉት በእጥፍ ጨመረበት..እራሷን አስተካክላ ሀሳቧን ሰብስባ ወደንስሯ አዕምሮ ዘልቃ ገባች..ያየውን ለማየት…ያወቀውን ለማወቅ
//
የትናንትናው ቀልቧን ሰልቧት የነበረው ባሪያው ልጅ መላኩ ይባላል ..እሷ ማለት ከሞት ጋር ቀጠሮ ይዛ በስጋት ኑሮ ላይ ያለችው ፍቅረኛው ስም ደግሞ ሰሚራ ትባላለች…ሁለቱ የተገናኙት ከአራት አመት በፊት ነው….
ንስሯም ስለሁለቱ ፍቅረኛሞች ይዞላት የመጣው ታሪክ መነሻው ከተገናኙበት የዛሬ አራት አመት ወዲህ ያለውን ነው……
አዎ ሰሚራ ነርስ ነች …በአንድ የግል ሆስፒታል ውስጥ በነርስነት በምትሰራበት እና ተረኛ ሆና የስራ ገበታው ላይ በነበረችበት በአንድ ቀን ከ4 ዓመት በፊት ማለት ነው፡፡አንድ ወጣት በሞት እና በህይወት መካከል ተንጠልጥሎ አረፋ ደፍቆ እያቃተተ በአንብላንስ ተጭኖ ይመጣል..
አጋጣሚ ሆኖ በዕለቱ ሰሚራ ተረኛ እንደመሆኗ መጠን ከሌሎች ዶክተሮች ጋር ሆና የመጣውን በሽታኛ ህይወት ለማትረፍ ባለአቅማቸው እና ቴክኖሎጂውን በመጠቀም ይሯሯጣሉ…. ወጣቱ ኃይለኛ ገዳይ መርዝ በመላ ሰውነቱን ተሰራጭቶ አንጀቱን እየበጣጠሰው ነበር ....ከዛ በእነሱ ጥረት የእግዜርም በጎ ፍቃድ ተጨምሮበት ከመሞት ይተራፋል… ግን ጉዳቱ ከፍተኛ ስለነበር ከገባበት ኮማ ለመንቃት አልቻለም ነበር….ስለሆነም የጤናው ሁኔታ በአስተማማኝ ሁኔታ እስኪስተካከል እዛው ሆስፒታል ተኝቶ ክትትል እንዲያደርግ ይወሰናል…
ያ ወጣት ሆስፒታል ከገባበት ቀን አንስቶ አብረውት የነበሩ አንድ ሴት እና አንድ ወንድ ጎልማሶች ነበሩ….ሰሚራ በወቅቱ ከእነሱ ከራሳቸው ጠይቃ እንደተረዳችው ሴቷ የበሽተኛው ፍቅረኛ ወንዱ ደግሞ በአባት የሚገናኘው ግማሽ ወንድሙ …..….በተጨማሪም ፖሊሶችም ገባ ወጣ ይሉ ነበር…የበሽተኛውን መንቃት ተከትሎ የሚሰጠውን ቃል ለመቀበል…
እሷም ምንም እንኳን የስራዋ አንዱ ግዳጅ እና ኃላፊቷ ቢሆንም ግን በማታውቀው ሌላ ተጨማሪ የተለየ ስሜት እየተገፋፋች በከፍተኛ ሁኔታ ስትንከባከበው ትቆያለች…አብረውት የሚያሰትምሙት ቤተሰቦቹ እስኪገረሙባት ድረስ፡፡በሽተኛው እስከ ሶስተኛው ቀን ድረስ ከገባበት ኮማ መንቃት አልቻለም ነበር ፤በአራተኛው ቀን ግን ለ5 ደቂቃ ያህል አይኖቹን መግለጥ እና አንደበቱን ማላቀቅ ቻለ..የመዳን ተስፋው በእጥፍ ጨመረ፤ይሄ ሁኔታ ሰሚራን እና ጓደኞቾን በጣም ቢያስደስታቸውም የመላኩን አሰታማሚ ቤተሰቦች ግን በሚገርም ሁኔታ አለመረጋጋት እና ድንጋጤ ውስጥ ከተታቸው፤ይህንንም ጉዳይ ሰሚራ መታዘብ ስለቻለች ግራ ተጋብታ ትዝብቷን በውስጧ ቀብራ ስትብሰለሰል ትሰነብታለች፤በአምስተኛው ቀን ግን ሰሚራ የእለት ስራዋን አጠናቃ ወደቤቷ ስትመለስ የመላኩ አስታማሚዎች እቤቷ በራፍ ላይ ቆመው ሲጠብቋት አገኘች
ሰሚራም ደንግጣ‹‹ምን ተፈጠረ..….?ምን እግር ጣላችሁ….?››
ሰላም ምትባለው…የመላኩ እጮኛ‹‹ተረጋጊ አንድ ነገር ልናማክርሽ ነው….?››አለቻት፡፡
‹‹ምንድነው ምታማክሩኝ …….?ደግሞስ ሆስፒታል ተገናኝተን አልነበር..እዛው እኮ ልትጠይቁኝ ትችሉ ነበር…?››
የበሽተኛው ግማሽ ወንድም የሆነው ሰሎሞን‹‹አይ እዛማ በስራ ወከባ ላይ ስለሆንሽ የግል ጉዳይ ለማውራት አይመችም ብለን ነው››
ግራ ትጋባና ‹‹የግል ጉዳይ …….?ማለት ስለ መላኩ ጤንነት ማለታችሁ ነው….?›› ብላ ጠየቀች…ሌላ ከእሷ ጋር የሚያገናኘው ጉዳይ አልታይሽ ብሏት፡፡
ሰላም እያቅማማች ‹‹አዎ ግን ካላስቸገርንሽ ወይ እቤትሽ ገብተን ወይ ደግሞ ሌላ ቦታ ሄደን ብናናግርሽ››
ሰሚራ ምታደርገውም ምትናገረውም ግራ ገብቷት ወደ ቤቷ ይዛቸው ትገባለች…ወደቤት ከገቡ በኃላ ለውይይት ያቀረቡላት ርዕስ ከጠበቀችው በጣም የራቀና አስደንጋጭ ነበር…››
የግማሽ ሚሊዬን ብር ቼክ በእጇ ላይ ካስቀመጡላት በኃላ ….‹‹መላኩን እንዳይድን አድርጊልን››ነበር ያሏት፡፡
‹‹እንዴ ለምን…….?ለአንቺ ፍቅረኛሽ ለአንተ ደግሞ ወንድምህ አይደል…….?ነው ወይስ ዋሽታችሁኛል….?፡፡››
‹‹አይ እሱን አልዋሸንሽም…ግን አንቺ ማይገባሽ ብዙ ጉዳዬች አሉ..አሁን ብታድኝው እራሱ ሙሉ ጤነኛ አይሆንም ..አካሉ እንደልብ ላይታዘዝለት ይችላል..ወይም አዕምሮው የማሰብ አቅሙ ተዛብቶ ዘገምተኛ ሆኖ ሊቀር ይችላል….እንደዛ የመሆን እድል እንደሚገጥመው ደግሞ የነገራችሁን እናንተው ናችሁ፡፡››

👍70😱8❤4🥰1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
ለሊቱ ያለእንቅልፍ ነው ያለፈው….የጣር ለሊት…የስቃይ ለሊት…፡፡ደግነቱ ፕሮፌሰሩ ለሊቱን ሙሉ አብረዋት ነው ያሳለፍት…..ይሁን እንጂ እሷ ባዘነች መጠን አብረዋት እያዘኑ ነበር ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም..ግን በታታሪት ሲያዳምጧት እና ደረቅ አልኳል ሲያጣጧት ነበር.. ወፎች የለሊቱን መንጋት የምስራች ሊያበስሩ ሲንጫጩ ድምጻቸው የተሰማው…
ሁለት ጠርሙስ ብላክ ሌብል ጠርሙስ ጨርሰዋል..እሷ አንድ ጠርሙስ ከግማሹን ሳትጨርስ አልቀርም፡፡በንዴት፤ በስጋትና በብስጭት ያወራችው ወሬ ቢቀረብ እና ወደ መጻሀፍ ቢገለበጥ አንድ ደለብ ያለ መጽሀፍ ይወጣዋል፡፡
‹‹ፕሮፌሰር ምን አቀበጠኝና ተክሉን ቀነጠስኩ..….?ምን ቅብጥ አደረገኝ….?››
‹‹እንደነገርሺኝ እኮ ሙሉ በሙሉ ሚያመጣውን መዘዝ አልተረዳሽም ነበር››
‹‹እኮ ረጋ ብዬ ጊዜ ወስጄ ማሰብ ነበረብኝ…ንስሬ እንኳን ሊነግረኝ ባይፈልግ…ጎትጉቼ ሙሉውን መዘዝ መረዳት ነበረብኝ፡፡››
‹‹ግን እርግጠኛ ነሽ ..እንደዚህ ያለ ንስርሽ ለመሄድ እንደምትገደጂ ብታውቂ ኖሮ ተክሏን ከመቀንጠስ ትታቀቢ ነበር….?››
‹‹ይቀልዳሉ እንዴ ፕሮፌሰር..ጭርሽ ለማሰብ እንኳን አልሞክርም…እንዴ ንስሬን ጥዬ እንኳን የማላውቃቸው ..ምን አይነት ፍጡር እንደሆኑ እንኳን እርግጠኛ ወዳልሆንኩባቸው..ይመቹኝ አይመቹኝ መገመት ወደማልችላቸው የአባቴ ዘመዶች ይቅርና እግዚያብሄርም ቢጠራኝ ንስሬን ጥዬ በፍቃደኝነት ለመሄድ አልፈልግም››
‹‹በቃ ተረጋጊ..ያው በሞትም መለየት እኮ አለ››አሏት ፕሮፈሰሩ …በእሳቸው ቤት እሷን የሚያጽናና ቃል መናገራቸው ነው፡፡
‹‹አይ ፕሮፌሰር …ይቀልዱብኛል አይደል?ይሄም እኮ ያው ሞት ነው…ሞት ማለት የራስ ከሆኑ ሰዎችና ከሚኖሩበት ዓለም ለዘላለም ተለይቶ በስጋ ወደመሬት ውስጥ መግባት በነፍስ ደግሞ ወደማይታወቅ አለም መጓዝ ማለት አይደል…?አሁን እኔም ከሳምንት በኃላ የሚገጥመኝ ደግሞ በስጋም በነፍስም ከዚህች ምድርም ሆነ የእኔ ከሆኑት ሰዎች ሁሉ ተለይቼ ለዘላለም ወደማይታወቅ አለም በስጋም በነፍስም መጓዝ ነው…ታዲያ ይሄ እንደውም ሙሉ ሞት አይደለም..….?ማንም ሰው ስናፍቀው እንኳን መቃብሬ ጋር ሄዶ በማልቀስ ወይም አበባ በማኖር ሊያጽናና ዕድሉ አይኖረውም …. ነፍሴንም ስጋዬንም ይዤ ነው የምሄደው…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው››
‹‹አዎ ዋናው ችግር ግን ይሄ አይደለም..ዋናው ንስሬን ጥዬ መሄድ ያለመፈለጌ ነው..እሱን..››ንግግሯን አቋረጧት፡፡
‹‹እኔ እኮ በህይወት እስካለሁ ድረስ ልንከባከብልሽ እችላለሁ፡፡››
‹‹አይ አይችሉም… እርሶ የሚችሉት በስርዓት የቀብር ሰርዓቱን ማስፈፀም ብቻ ነው››
‹‹አልገባኝም..››አሏት ደንግጠው፡፡
‹‹እኔ ጥዬው በሄድኩ ቀን እሱም እደሚሞት ነግሮኛል››
‹‹እንዴት ሆኖ ነው የሚሞተው….?››
‹‹እኔ እንጃ ግን እኔን ከወሰዱኝ በኃላ ለአንድ ቀንም እንኳን በህይወት መኖር እንደማይችል እርግጠኛ ሆኖ ነግሮኛል››
‹‹አይዞሽ ሳምንት እኮ ብዙ ቀን ነው..የሆነ መውጫ መንገድ ልናገኝ እንችላለን..በተለይ ንስርሽ መላ ሚያጣ አይመስለኝም››
‹‹እኔ እንጃ …. እንደዛ ተስፋ አላደርግም …››
‹‹አይዞሽ…ደግሞ ይሄ ጉዳይን እንደመስዋዕትነት ቁጠሪው..ህይወት ለማትረፍ ነው እዚህ ወጥመድ ውስጥ የገባሽው››
‹‹መስዋዕት አሉኝ….መስዋዕትነትማ እንዲህ በቀልድ አይገለጽም..እኔ ከመስዋዕትነት ይልቅ ክስረት ነው የሚሰማኝ…መስዋዕትነት እኮ ለአንድ ክብር አለማ አቅዶና አስቦ ሕይወትንም ጭምር መስጠት ማለት ነው…ህይወትንም ጭምር ቢሆን አጥቶ ሌላውን ለማኖር ቀድሞም አምኖና ወስኖ መተግበር ማለት ነው…
‹‹ልክ እንደ አርበኞቻችን ማለትሽ ነው….?››
‹‹አዎ እንደውም ዛሬ ለሀገር መስዋዕትነት ስለከፈሉ ሰዎች ምስጋና የምናቀርብበት ቀን አይደል…ሀገር ከምትደፈር የእኔ ህይወት ትቀጠፍ ብለው…ለልጆችና ለልጅ ልጆቻችን ባርነትን ከምናወርስ እኛ ዛሬ ደማችንን እረጭተን አጥንታችንን በትነን ነጻነትና ኩራትን እናወርሳቸው ብለው ታሪክ እንደሰሩት አባቶቻችን ነው መስዋዕትነት….ልክ እንደ በላይ ዘለቀ፡፡ ከገዛ አብራክ ልጅ ይልቅ ሀገርን ወይም ህዝብን ማስቀደም ማለት ነው…ለሀገር ክብር እና ለወገን መድህን ሆኖ መውደቅ ማለት ነው…ከስኬት በኃላም ላደረጉት ነገር የተለየ ክብር እና ሹመት አለመፈለግ ማለት ነው..ለሚወዱት ነገር ያለንን ነገር ሁሉ ህይወትንም ጭምር በነፃ መስጠት ማለት ነው….
እንደዛአይነት መስዋዕትነት ሚስጥሩ ከባድ ነው….ከድል በኃላ የበላይን ይሄንን ለሀገሩ በነፃ የሰጠውን መስዋዕትነት ሸፍጠኞቹ እና ባንዳዎቹ አልወደዱለትም ነበር..ምክንያም ስለእሱ ዝናና ታሪክ ሲሰሙ የእነሱን ሆዳምነት እና ትንሽነታቸውን በየጊዜው ስለሚያሳብቅባቸው ከንጉሱ አላትመው በአደባባይ እንዲሰቀል አደረጉት..ከጠላት በክብር የተረፈች ነፍሱ በገዛ ህዝቦቹ ምቀኝነት እና ክፍት ተነጠቀች…ይሄ ነው መስዋዕትነትን መራር የሚያደርገው…ለዚህ ነው መስዋዕትነት የሚለው ቃል ሚያስጠላኝ፡፡
‹‹ትክክል ነሽ ልጄ…ይሄ የበላይ ታሪክ የእንግሊዞች ቢሆን፤ይሄ የበላይ ታሪክ የአሜሪካኖች ቢሆን ኖሮ አንድ ሺ ፊልም እና አስር ሺ መጽሀፍ ተጽፎበት ነበር…?ስንት መንገድ እና ስንት ዩኒቨርሲቲ በስሙ ተሰይሞለት ነበር…?››
እኚህ ለሊቱን ከፕሮፌሰሩ ጋር በመጠጥ እያወራረድ በእሷ ለቅሷ ታጅበው ሲያወሩ ከነበሩት ነጥቦች ጥቂቶቹ ነበሩ..….
አሁን ሰዕቱ ከማለዳ 12፡45 ይላል…ፕሮፈሰሩ በመጠጥ እና በእሷ ወሬ ተዳክመው ይመስላል እዛው የተቀመጡበት ሶፋ ላይ ደገፍ እንደሉ እንቅልፍ ይዞቸው ጭልጥ ብሏል….ንስሯ ያለው መኝታ ቤት ውሰጥ ነው ከእሷ በላይ ትካዜና ቁዘማ ውስጥ ነው…ልትነካካው አልፈለገችም
እየተንገዳገደች እቤቱን ለቃ ወጣችና ወደ መኪና ማቆሚያ አመራች…‹‹ከጠጡ አይንዱ›› የሚለውን የትራፊኮችን ዋና ምክር አዘል መመሪያ ከቁብም ሳትቆጥር መኪናዋን አስነሳችና ግቢው ለቃ ተፈተለከች..ቀጥታ ወደመላኩ ቤት ነው ያመራችው…
እንደደረሰች ወደጊቢው አጥር አስጠጋችና መንገድ እንዳይዘጋ አስተካክላ መኪናዋን ካቆመች በኃላ ሞተሩን በማጥፋት ከመኪናዋ ወረደችና የግቢውን በራፍ መጥሪያ በሰከንድ ሽርፋራፊ ውስጥ ደጋግማ አንጣረረችው ፡፡ከጠበቀችው በፈጠነ ሁኔታ ተከፈተላተት..ከእንቅልፉ የባነነ እና በአንድ እጁ አይኖቹን እያሻሸ በሌላ እጁ የበራፍን እጄታ ይዞ ‹‹ምን ፈለግሽ….? ›› የሚላት ሰው ስትጠብቅ .. ንቁ እንቅልፍ በዓይኑ እንዳልዞረ የሚያስታውቅ..አይ እንደውም እያለቀሰ የነበረ ከዚህ በፊትም ያየችት ዘበኛ ከፈተላትና…ምንም ነገር ሳይጠይቃት እንድትገባ መንገዱን ዞር ብሎ ለቀቀለት …አልፋ ገባችና መንገዷን ቀጠለች ..በፍጥነት ዘግቷ ከኃላዋ ተከተላት፡፡
‹‹ዛሬ ምን አይነት ቀን ነው…….?ሰው ሁሉ ሲያለቅስ እንቅልፍ አጥቶ የሚያድርበት ቀን ነው እንዴ….?››ከዘበኛው ሁኔታ ተነስታ ውስጧን እየጠየቀች ነው… እራሷን ለመቆጣጠር በዚህ በተወለካከፈ እርምጃ አንድ ነገር አደናቅፏኝ እንዳትደፋ እየፈራች ስትራመድ ዘበኛው በታፈነ ድምጽ መናገር ጀመረ
‹‹ጋሼ ደውለውልሽ ነው….?››
‹‹አዎ›› አለችው….ምንም ሳታስብበት
‹‹አይ ቢጨንቃቸው እኮ ነው ..በቃ እኮ 10 ደቂቃም ዕድሜ አይራቸውም …አብቅቶላቸዋል…››
‹‹ማን ነው ያበቃለት ….?››ደንግጣ

👍94❤10🔥1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ስምንት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
የሰው ልጅ ውስጡ ሲጨልምበት እና የመጨረሻ ተስፋው መቁረጥ ላይ ሲደርስ ብስጭቱን የሚያራግፍበት ወይም የሚያላክክበት ሶስት አካላት አሉ…መንግስት፤እግዚያሔር እና እናት ፡፡
የመንግስት እንዝለለው…እግዚያብሄርን ግን ሲከፋን ለምን ፈጠርከኝ….? ብለን እንጠይቀዋለን……መፈጠር ትፈጊያለሽ ወይስ ይቅርብሽ ብለህ ምርጫ ሳትሰጠኝ ለምን ፈጠርከኝ…….?እሺ ይሁን ካለፍላጎቴ ከፈጠርከኝሽ በኋላ ለምን እንደፍላጎቴ ልታኖረኝ አልቻልክም.? ወይም ብትችል እንኳን ለምን አልፈለክም….? ብለን እንጠይቀዋለን…
እሱ በፍቃዱ እኛን መፍጠሩ እና እንደ እኛ ፍቃድ ሳይሆን እንደእራሱ ፍላጎትም የህይወት ጅረታችን የሚፈስበትን መስመር ማስመሩ ስህተት አይመስልም...የሰው ልጅም ሲበሳጭ ፤ተስፋ ሲቆርጥና ሲማረር ለምን ….?ብለን እሱን መጠየቃችንም ስህተት አይደለም….የእግዚያብሄር ዋናው ጥቅም የህይወት ሸክማችንን ከብዶን ስንንገዳገድ ከመውደቅ ታድጎ እንዲያግዘን እና የተሰበረ ተስፋችን እንዲጠግንልን የተንኮታኮተ ሞራላችን እንዲያክምልን ነው….ስለዚህ በከፋን ጊዜ ልንነጫነጭበት የግድ ነው…መነጫነጫችንም ክፋት የለውም፡፡
ከእግዜር ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ የፈረደባት እናት ነች …አራት አመት ሆነን አርባ አመት ሁላችንም ውስጣችን ጨልሞ ነጋችንን ማለም ድክም ሲለን ወደ እናታችን ጉያ ሮጠን መሸጎጥ የመጀመሪያ ተግባራችን ነው፡፡
…እናታችንን በቅርብ አግኝተን የተመኘነውን ማድረግ ባንችል እንኳን ‹‹….እማዬ ለምን ወለድሺኝ….? ››ብለን ባትሰማንም ማማረራችን አይቀርም….በማማረሩ ውስጥ ምስጋና አለው…ለህልውናችን መሰረቷ ሰው ለመሆናችን ዋናዋ ምክንያቷ እሷ ለመሆኗ እየተናገርን ለዛም እውቅና እየሰጠናት ነው…
አሁን እነኬድሮን ያሉት ደሎመና ነው…ትውልድ ሀገሯ፡፡ያሉት ሳር ቤት ውስጥ ግድግዳውን ተደግፎ በተሰራ እና ግዙፍ አጎዛ በተነጠፈበት ትልቅ መደብ ላይ ፤ ንስሯን ከጉያዋ አድርጋ እናቷ እግሯ ላይ ተኝታ እንባዋን እያንጠባጠበች ነው….አሁን ካሉበት የሳር ቤት ፊት ለፊት ባለአራት ክፍል ቢላ ቤት ቢኖራትም እናቷ ግን አትወደውም…በቃ አስገዳጅ ሆኖባት እንግዳ ካልመጣባት በስተቀር ውሎዋ እዛች ሳር ቤት ውስጥ ነው…ምግቡ እዛው ይሰራል እዛው ብና ይፈላል….እዛው ጋደም ይባላል…
‹‹ገራኮ ማል ታቴ….?››(ሆዴ ምን ሆንሽ….?)ትጠይቃለች እናቷ
ድምጽ ያላጀበውን እንባዋን ከማፍሰስ ውጭ መልስ ልትሰጣት አልቻለችም….እርግጥ ሊሆን ያለውን ነገር ለእሷ ልትነግራት እና ልትሰናበታት ነው የመጣችው …ግን እንዲህ በቃላሉ ቃላት ከአንደበቷ ልታወጣ አልተቻላትም፡፡
‹‹ሆማ ኢንታኔ ሀርሜ ኮ..ነገኡማ ›( ….ምንም አልሆንኩ እናቴ…ደህና ነኝ)
‹‹ቀሮ ቲያ .ኢንሶቢን ….? ››(የእኔ ብልጥ አትዋሺኝ….?)
‹‹እማ ጨንቆኛል..በጣም ጨንቆኛል..መልሼ ወደሆድሽ ሁሉ መግባት አምሮኛል››
‹‹እኮ ንገሪኝ …እኔ እናትሽ እያለሁ ለማን ይድላው ብለሽ ትጨነቂያለሽ……?ደግሞ ባንቺ ጭንቀት አያምርም..አንቺ እኮ ለተጨነቀው ሁሉ መፍትሄ ስትሰጪ እንጂ ስትጨነቂ አያምርብሽም››
‹‹እማ አሁን የገጠመኝ ግን ከባድ ችግር ነው››
‹‹እኮ ምንድነው….?››
‹‹ልሄድ ነው››
ፈገግ አለች እናቷ‹‹እንቺ እኮ ገና ከልጅነትሽ ጡት ሳትጥይ ጀመሮ እንደሄድሽ ነው….ያንቺ መሄድ ምን አዲስ ነገር ኖሮት ነው
ሊያስጨንቅሽ የቻለው…….?አይዞሽ ልጄ ንስርሽ ከጎንሽ እስካለ የትም ብትሄጂ ምንም ሀሳብ አይገባኝም..በዛ ላይ የእኔ የእናትሽ ፀሎት እና የአባትሽ መንፈስ በየሄድሽበት ሁሉ ይከተልሻል… ይጠብቅሻል፡፡››
‹‹ሀርሜ…ንስሬ አብሮኝ አይሄድም ….››
ባለማመን አፍጥጣ አየችት..ምክንያቱም ንስሯ ለአንድም ቀን ቢሆን ከእሷ የተለየበትን አጋጣሚ እናቷ አታስታውስም..እንደውም እናቷ ሁለት መንታ ልጇች አሉኝ ብላ ነው የምታወራው…ያው እንደሚታወቀው እናቷ በምትኖርበት አካባቢ በጣም የተከበረችና ሰው ሁሉ የሚፈራት ነች‹‹….አረ ከዳቢሎስ የተወለደች ልጅ አለቻት …አንድ ነገር ብለን ብናስከፋ በልጇ ታስጠፋናለች….አታዩም እንዴ ልጇ እኮ አቅፋ የምትኖረውን ንስር ዳቢሎሱ አባቷ ነው የላከላት›› እያሉ በማንሾካሾክ እንደሚያሟት ታውቃለች……በዛም ምክንያት ሳይወዱ በግዳቸው ይፈሯታል..ስለሚፈሯትም በጣም ያከብሯታል….ግን ይህን ንስሯን የላከላት አባቷ መሆኑን ትጠራጠራለች እንጂ እርግጠኛ አይደለችም እንዴ….….?
‹‹ለምን ልጄ…?ለምንድነው አብሮሽ የማይሄደው….?››
‹‹የምሄድበት ቦታ እሱን ይዤ መሄድ አይፈቀድልኝም….ቢፈቀድልኝ እሱ አዛ መኖር አይችልም…. አየሩ አይስማማውም…››
ከተጋደመችበት ጭኖ ላይ ገፍትራ አስነሳቻትና እንድትቀመጥ አድርጋ ፊት ለፊት አፍጥጣ እያየቻት‹‹እንዴ ቅሪያ…እንዴት እሱን ጥለሽ መሄድ ታስቢያለሽ…….?የህይወት ጉዳይ ቢሆን እንኳን ማድረግ የለብሽም..እሱን ጥለሽ ሄድሽ ማለት እኔንም አሳዝነሽ ሄድሽ ማለት ነው…በዕድሜሽ ለመጀመሪያ ጊዜ አዝንብሻለሁ››
‹‹ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው›ይሏችኋል ይሄ ነው..ከእሷ ባሰች……በጣም ከባዱን ነገር ጭራሽ የበለጠ ጠጣር አደረገችባት፡፡
‹‹ሀርሜ ወዴት እንደምሄድ እኮ አልገባሽም….?››
‹‹ወደ የትም ይሁን አልኩሽ እኮ ..ንስርሽን ጥለሽ የትም መሄድ አትቺይም›› አለችና..ከእቅፌ ንስሬን መንጭቃ ወስዳ ጉያዋ ውስጥ ወሸቀችው…እሱም እጥፍጥፍ ብሎ ተሸጎጠላት፡፡
አፈረጠችው‹‹አባዬ ጋር ነው የምሄደው››
በእድሜዋ ሙሉ እናቷ በዚህ መጠን ስትደነግጥ አጋጥሞት አያውቅም..ሰው እንዴት እየታየ የሰውነት ቀለሙ እየተቀየረ ይሄዳል..?እንዴት እያያችሁት ደም ስሮቹ እየተወጣጠሩ እና ለእይታ ግልጽ እየሆኑ ይታያል….?ሰው እንዴት በሚያግለበልብ ሙቀት ውስጥ ሆኖ የአንታሪቲካ በረዶ ውስጥ እንደጣሉት ጥርሶቹ እርስ በርሳቸው ይንገጫገጫሉ….መልሰው ቃላት ለመለዋወጥ አያሌ ደቂቃዎች ነው ያሳለፈት…..
‹‹እንዴት አድረገሽ ነው የምትሄጂው….?››
‹‹ወገኖቹ ከስድስት ቀን በኃላ መጥተው ይወስዱኝል››
‹‹እሱስ ይመጣል….?››ጉጉት ባሰቃየው እይታ እያየች ጠየቀቻት
‹‹አይ እሱ እንዲመጣ የሚፈቅዱለት አይመስለኝ››
‹‹እሱስ ትክክል ነሽ…ግን እነሱስ እንደሚመጡ በምን አወቅሽ….?››
የሆነውን ሁሉ አስረዳቻት..ቀስ በቀስ በድንጋጤ ወይቦ የነበረው ፊቷ በደስታ እየደመቀ እና እየፈካ መጣ
‹‹እማ እየሳቅሽ እኮ ነው…….?››በገረሜታ ጠየቀቻት ..እያለቀሰችም እየሳቀችም መሆኗ ገርሞት
‹‹አዎ..በጣም ደስ ብሎኝ ነው››
‹‹እንዴ!! እንዴት ደስ ይልሻል..….?ከሄድኩ እኮ አልመለስም››
‹‹አውቃለሁ…ታውቂያለሽ አይደል ትናፍቂኛለሽ …. በጣም ነው የምወድሽ …ግን ወደአባትሽ ነው የምትሄጂው..ደግሞ በአንቺ ዕድሜ ሙሉ ለብቻዬ ተሸክሜው የኖርኩትን እወነቴን ዛሬ አንቺ አረጋገጥሺልኛል… እንዳልተሳሳትኩ አንቺ ልጄ ምስክር ነሽ…እንቡጥ ልጃገረድ ሆኜ ከሌላ አለም የመጣ ሰው መሰል ፍጡር አፍቅሬ እንደነበረ ….ወደእሱ የመኖሬያ አለምም ለአንድ ቀን ወስዶኝ እንደነበረ…የወለድኳት ልጅ አባትም እሱ እንደሆነ ለዘመድም ለጓደኞቼም ሳወራ ነበር የኖርኩት..ግን አውቃለሁ አንድም ሰው አምኖኝ አያውቅም ነበር…እንደውም ነካ እንደሚያደርግኝ ነው የሚስቡት…ዛሬ እወነቴን እንደነበርና ዕድሜዬን ሙሉ ያፈቀርኩት ፍቅር የእውነት እንደነበር አንቺም ተገንዝበኛል…በህይወቴ ሙሉ ከዚህ በላይ ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ሊፈጠር አይችልም››

👍107❤10🥰1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////
ወደሸገር ተመልሰዋል..ማለት እሷ እና ንስሯ ፡፡ለእናቷ በመጨረሻው ቀን ተመልሳ እንደምታያትና ወደአባቷ ዘመዶችም በምትሄድበት ቀን አጠገቧ እንድትሆን እንደምትፈልግ ነግራትና ቃል ገብታላት ነው የመጣችው፡፡
እስከዛው ያሉትን ቀጣዬቹን በስስት እየተሸራረፉ በመርገፍና በማለቅ ላይ ያሉትን ቀሪ 5 የሰቀቀን ቀናቶችን ሸገር ልታሳልፍ ወስናለች….ምን አልባትም አይታውቅም… በመሀል ሀሳቧን ልትቀይር ትችላለች፡፡
ግን አሁን ተረጋግታ እቤቷ መቀመጥ አልቻለችም … ሰዓቱ ከምሽቱ 3 ሰዓት ቢያልፍም ልትቆጣጠረው የማትችለው ከውስጧ ሚመነጭ ስውር ስሜት ውጪ ውጪ ይላት ጀመር….ልብሷን ቀያየረችና መኪናዋን ወዳለችበት መራመድ ከጀመረች በኃላ ሀሳቧን ቀየረችና ስልኳን አውጥታ ደወለች..አዎ ነፃ መሆን ነው የምትፈልገው….ላዳ ያለው የምታውቀው ልጅ ጋር ነው የደወለችው፡፡
‹‹ሄሎ››
‹‹ሰላም ነው… .ፈልጌህ ነበር…የት ነህ ያለኸው?››
‹‹ይቅርታ ዛሬ ስራ ላይ አይደለሁም መኪናዬ ተበላሽታ ገራዥ ነች››
‹‹በቃ አንተ ናልኛ ..የእኔ መኪና ስላለች ትይዝልኛለህ …ጥሩ ስሜት ላይ ስላልሆንኩ መንዳት አልፈለኩም››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር.. ግን ያው ስራ የለኝም ብዬ ከከተማ ወጣ ብያለሁ…..ከፈለግሽ አንድ ጓደኛዬን ልልክልሽ እችላለሁ››
‹‹ደስ ይለኛል››
‹‹በቃ ንገረውና ቁጥርሽን ሰጠዋለሁ…ይደውልልሻል››
‹‹እሺ አመሰግናለሁ››ስልኳን ዘጋችውና ጊቢዋ ውስጥ እየተዘዋወረች እስኪደወልላት መጠበቅ ጀመረች….፡፡
ብዙም ሳይቆይ ስልኳ ላይ የማታውቀው ቁጥር ተንጫረረ …አነሳችው..አናገረችው ….በ15 ደቂቃ እንደሚደርስ ነገራት…..መጠበቅ ጀመረች…..
‹‹አዎ በዚህ ለሊት ምን አልባት ለመጨረሻ ጊዜ ማበድ እፈልጋለሁ..አዎ ብዙ ነገር ማድረግ አምሮኛል…የማሰብ አቅሜን አዳክሞ ጭንቀቴን የሚቀንስልኝን ማንኛውንም ነገር ለማድረግ እፈልጋለሁ…..መጠጣትና መስከር …መቁላላትና መዋሰብ እፈልጋለሁ…መጣላትና መደባደብም ካገኘሁ አልጠላም…››
እግዜር ይስጠው የመኪና ጥሩንባ ድምጽ ሰማች...ጎበዝ ልጅ ነው… በነገረችው ምልክት መሰረት ሳይሳሳት መምጣቱ አስደሰታት… በራፍን ከፈተችና ወጣች…በምልክት ጠራት … የላዳውን በራፍ ከፈተላትና ገባች፡፡
‹‹ወዴት ልውሰድሽ….?››
‹‹መጠጣት ነው የምፈልገው››አለችው፡፡
‹‹መጠጣት›› አላት ግራ ተጋብቶ፡፡
‹‹መጠጣት ስልህ …ብሽቅጥ እስክል መጠጣት ነው የምፈልገው…የፈለከውን ያህል ከፍልሀለሁ እስከንጋትም ቢሆን አብረኸኝ ትቆይና እቤቴ ታስገባኛለህ››
‹‹ይመችሽ ››አላት….
እንዲሁ ወደደችው…አንድን ሰው አይተን በውስጣችን ስለሰውዬው ደስ የሚል ስሜት ሲሰማን ውቃቢዬ ወዶታል የምንለው ነገር አለ አይደል..….? እሷም ይሄን የላዳ ሹፌር እንዳየችው እንደዛ ነው የተሰማት፡፡
‹‹ምርጫሽ የት አካባቢ ነው?››
‹‹የፈለክበት ውሰደኝ ››
‹‹ቺቺኚያ ይመችሻል››
‹‹ይመችህ››
ነዳው….ንስሯ አምኗት እቤት ሊቀር አልቻለም …ከፊት ለፊታቸው በላዳዋ ፍጥነት መጠን ሲበር በመኪናዋ መስታወት አሻግራ አየችው….
ደረሱና መኪናዋን ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀበት ቦታ ፓርክ አድርገው አንዱ ጭፈራ ቤት ገቡ……እሷ ደረቅ አልኮለሏን ስታዝ እሱ ዉሀ አዘዘ..
‹‹ለምን ትንሽ አትሞከርም….? ››
‹‹አይ …የሞያዬ ስነምግባር አይፈቅድልኝም›› ሲል መለሰላት በቀልድ መልክ
..ዝም አለችው… በላይ በላዩ መለጋቱን ቀጠለች….የሙዚቃው ከጣሪያ በላይ ጩኸት…የለሊት ንገስታቶች በገዢ መሳይ ወንዶች ዙሪያ መሽከርከር፤ በስካር የሚናውዙና የሚደንሱ ወንዶችና ሴቶች የሆቴሉን ወለል መሙላት…የሆነ ትርምስምስ ያለ ነገር ነው የሚታየው….በዛ ላይ መብራቱ በአምስት አይነት ቀለም በመፈራረቅ ቦግ ብልጭ ሲል እይታን ብዥ ያደርጋል…….ግን በምትፈልገው መጠን ባይሆንም ተመችቷታል ፡፡ቢሆንም ደስታዋን ሙሉ ማድረግ ፈለገች…
‹‹ሌላ ጓደኛ የለህም….?››ድንገት ከመሬት ተነስታ ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን አይነት….?››
‹‹ሹፌር››..
‹‹ምን ያደርግልሻል….?››
‹‹ያንተን መኪና የሚነዳልን››
‹‹እኔስ….?››አላት በጥያቄዋ ግራ ተጋብቶ
‹‹አይ አንተማ እንድታጣጣኝ ፈልጌ ነው..ብቻዬን ደበረኝ››
‹‹እ ..ቆይ እስኪ ደዋውዬ ልሞክር››አለና ስልኩን እየጎረጎረ ከሆቴሉ ወጣ..ሲወጣ ከጀርባው ሳታየው ነበር…ቁመናው መስጧታል..በቃ የተለመደው ችግሯ እያገረሸባት ነው..ጭኗ መካከል አሳከካት…ምን አይነት መጥፎ አመል ነው…እዛም አባቷ አለም ስትሄድ እንዲህ የሚበላት ነገር ወቅት እየጠበቀ ይፈታተናት ይሆን እንደዛ ከሆነ ምንድነው የምታደርገው….….?
ሀሳቧን ሳትጨርስ መጣና መቀመጫው ላይ ተመልሶ እየተቀመጠ..‹‹ተሳክቶል…ተቀላቅዬሻለሁ››አላት
በደስታ እየፈገገች‹‹ምን ይምጣልህ..?››ሥትል ምርጫውን ጠየቀችው፡፡
‹‹አንቺ የያዝሺውን…››
ሙሉ ጠርሙስ አዘዙ…መጣላቸው…… ይገለብጡት ጀመረ…እየደነሱ እየተቀመጡ …ደግሞ ተመልሰው በመነሳት እየደነሱ ..ውልቅልቃቸው እስኪወጣ ድረስ አስነኩት‹‹ …አቤት ዳንሱ !!ፕሮፌሽናል ነው ፡፡ልቤን ስልብ ነው ያደረገኝ…›አለች በዳንስ ችሎታው ተመስጣ፡፡ይበልጥ ሰውነቱ ላይ ተለጥፋ በተሸሻችው መጠን የጭኗ መብላላ አደብ እየነሳት ነው…በትርምሱ መካከል በዳንስ ስልት በማሳበብ እጣቷን ወደጭኗ በመስደድ ይሉኝታ እስክታጣ ድረስ እያሻሸች ነው..ደግነቱ ሁሉም በመጠጥ የደመቀ እና በመብራቱ ቦግ ብልጭ ብዥ ያለበት መሆኑ በጃት …
ከለሊቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ግን ተዳከሙ…
‹‹ቤት እንቀይር ….?››አለችው… ቤት መቀየር የፈለገችው ሙዳችውንም ጭምር መቀየር ስለፈለገች ነው… ተስማማ ..ሂሳብ ዘግተው ወጡ…
‹‹ጭፈራ ቤት ሳይሆን ዝም ብለን የምንጠጣበት ቦታ ነው የምፈልገው…››
ወደላዳዋ ይዟት ሄደ …ቅድም ተጠርቶ የመጣው ጓዳኛውን ገቢና ቁጭ ብሎ ጫቱን ሲቀመቅም አገኙት..ሁለቱም ተደጋግፈው ከኃላ ገቡ… ላዳዋ ተንቀሳቀሰች… በመስኮቱ አንጋጣ ሰማዮን ሰታይ ንስሯን ቀድሟት ለመብረር ሲያኮበኩብ አየችው…ሰካራሙ ጓደኛው እይታዋን ተከትሎ ወደውጭ በተመሳሳይ ሁኔታ ካየ በኃላ‹‹ አይገርምም ይሄ አሞራ ቅድምም ስንመጣ ከፊት ለፊታችን ሲበር ነበር….እርግጠኛ ነኝ የተለየ ከለር ስላለው አስተውዬው ነበር››አለ
‹‹አሞራ አይደለም..ንስር ነው››አረመችው
‹‹እንዴ.. አዎ ንስር ነው ትክክል ..አንቺ ግን እንዴት አወቅሽ….?››
‹‹የእኔ ነው››በልበ ሙሉነት መለሰችለት፡፡
‹‹የእኔ ነው ስትይ….?››ያዝ ያዝ በሚያደርገው የስካር አንደበት ጠየቃት
‹‹ወንድሜ ነው››
ሁለቱም ተንከትክተው ሳቁ
‹‹..ቀልደኛ ነሽ..ይበልጥ ስትጠጪ ደግሞ ይብልጥ ቀልደኛ የመሆን ተስፋ አለሽ ማለት ነው››አላት፡፡
….አስረድቶ ማሰማንም ሆነ ተከራክሮ ማሸንፈ እንደማትችል ስለተረዳች‹‹ይሁንልህ›› አለችው ፡፡
መገናኛ አካባቢ ደርሱ… ብዙም ትርምስ የሌለበት እሷ የማታውቀው ሁለቱ ግን የሚያውቁት ሆቴል ይዘዋት ገቡ..ሹፌሩ ከላዳዋ አልወረደም…‹‹ጫቴን ብቅም ይሻለኝል›› ብሎ ቀረ …እነሱ ተያይዘው ገቡና የተገነጠለ እና ከታዳሚ የራቀ ወንበር ይዘው ተቀመጡ፡፡

👍86❤11😁2👎1🤔1😱1😢1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
‹‹ለማንኛውም ልድገምልሽ ኤርምያስ እባላለሁ…ለ15 ዓመት ያህል በማንዴላ ሀገር በሆነችው ደቡቡ አፍሪካ ጀሆንስበርግ ኖሬያለሁ… ወደሀገሬ ከተመለስኩ ሁለት ዓመት ከግማሽ ሆኖኛል፡፡የ20ዓመት አፍላ ፍንዳታ ሆኜ ሄጄ የ35 ዓመት ሙሉ ደንዳና ወጣት ሆኜ ተመለስኩ….››
‹‹አሀ ዲያስፖራ ነሀ….?››
‹‹አይ ዲያስፖራ ..!!! ‹ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ ›ትላለች እናቴ… ለማንኛውም እወነቱን ንገረኝ ካልሺኝ … በእነዛ ዓመታት ውስጥ በሰው ሀገር ላይ ስዳክር ..ሞራሌን ከማንቆሻቆሽ…ሰው ሆኜ መፈጠሬን ከመጠየፍ እና ወጣትነቴ ላይ ጢቢ ጢቢ ከመጫወት ውጭ ምንም ያተረፍኩት ነገር አልነበረም…ብዙ ህልም በልቤ ብዙ ምኞት በውስጤ አጭቄ ነበር የተጓዘኩት …እርባነቢስ ሆኜ ባዶ እጄን በሀገሬ ለመሞት ብቻ ብዬ ነበር የተመለስኩት …ይገርማል አይደል?
ሰው እንዴት ለመሞት ብሎ ከደብቡ አፍሪካ ድረስ ኪሎሜትሮችን አቆርጦ ይመጣል ትይኝ ይሆናል..….?ለእኔ ግን ትርጉም ነበረው..››
‹‹ንገረኝ እስኪ ትርጉሙን…››ከሳዕታት ትርኪ ሚርኪ ወሬ እና መዛለል በኃላ ድንገት ምርር ወዳለ የህይወት ታሪክ ሀተታ መግባቱ አስደምሟታል አስደስቷታልም…አሁን እየነገራት ያለውን ታሪክ እሱ ሳይነግራት እንደተለመደው ወጭ እየጠበቀት ያለውን ንስሯን እንዲረዳት አድርጋ በዝርዝር ማወቅ ትችላለች..ግን አልፈለገችም …እንዲሁ እየጓጓችና ቀጥሎ ምን እንደሚናገር እየገመተች ቀጥታ ከራሱ አንደበት መስማቱ የሆነ የተለየ ስሜት ስለፈጠረባት ደስ ብሏታል…
ቀጠለ ‹‹በህይወቴ እያለሁ የመኖር ምኞቴ ሰልበው በድን አድርገውኝ …ወጣትነቴን ከንቱ አስቀርተውብኝ የመጨረሻውን ክስረት ማክሰራቸው ሳይበቃቸው …ከሞቴም በኃላ ክብር ስጋዬን ለሀገራቸው ምድር ልገብር …?አላደርገውም ፡፡ለዘላለም የባዕድ ሀገር አፈር ሆኜ መቅረት አልፈለኩም ..ይህ መልካም አይደለም…ቢያንስ አገሬ እትብቴን በክብር በወርቃማ አፈሯ ውስጥ ቀብራ ከማንነቷ ጋር እንዳወሀደችው ሁሉ ስሞትም በድኔን በክብር ልትቀበለኝ እና ለዘላለም በጉያዋ ልትሸሽገኝ ይገባል..አዎ እንደዛ ነው መሆን ያለበት..በዛ ላይ እናቴን ለመጨረሻ ጊዜ ማየት እፈልጋለሁ… አያየኋት መሰናበት፤ስሮ በመኖር እና እሷን መጦር ችዬ ላስደስታት ባልታደልም… እጇ ላይ ሞቼ አልቅሳ ልትቀብረኝ እና እርሟን ለማውጣት እንድትችል ግን እድሉን ላመቻችላት ይገባል..አዎ ስመጣ እንደዛ ብዬ እና እንደዛ ወስኜ ነበር …
‹‹ከዛስ….?››
‹‹ከደረስኩ ኋላማ … ቆይ ዛሬ ስል …ቆይ ትንሽ ልሰንብት ስል ..የመኖር ጉጉቴ ቀስ በቀስ ከሞተበት እያንሰራራ እና እየተቀሰቀሰ መጣ..ምንም አግኝቼ አልነበረም ..ከእናቴ የማገኘው ተንሰፍሳፊ ፍቅር እና ከጓደኞቼ የማገኘው ማፃናኛ …››
‹‹በጣም አሪፍ ታሪክ ነው ያለህ››
‹‹አዎ መራር የህይወት ገጠመኞች ለሰሚው ወይም ለፅሀፊው ሳቢ ታሪክ ይወጣቸዋል…››
‹‹ከዛስ እንዴት ሀሳብህምን ሙሉ በሙሉ ልትቀይር ቻልክ….?››
‹‹አሁንም ሙሉ በሙሉ አልተውኩትም…አሁንም የመሞት እቅዴ በውስጤ አለ…››
‹‹እሺ እንዴት ልታራዝመው ቻልክ….?››ጥያቄውን አስተካከለችለት፡፡
‹‹እንዴት መሰለሽ….ከዛ ከሰው ሀገር በገንዘብም በመንፈስም ክስርስር ብዬ የመጣሁ ቢሆንም ብዙም ሳልቆይ ሚስኪን የልጅነት ጓደኞቼ አዋጥተው አሁን የምጠቀምባትን ላዳ ገዝተው ሰጡኝ..በቃ የመሞት ሀሳቤን አራዘምኩት ..ለራሴ ሁለተኛ እድል ሰጠሁት..ቢያንስ ለጊዜው ሰርቼ ስጋዬን የማኖርበትን ካገኘሁ አንድ ቀን ምን አልባት ሁለተኛውን የህይወት ምኞቴን በሆነ ተአምር ሊሳካልኝ ይችል ይሆናል…ብዬ ተስፋ አደረኩና መጨረሻውን እስከማይ ሁለት ዓመት ተኩል በሀገሬ ኖርኩ..ዘና ብዬ ለማንም ለምንም ሳልጨነቅ…ባሳኘኝ ሰዓት እየሰራሁ ሲያሰኘኝ ደግሞ እየተኛው..የእናቴን ሽሮ እየበላሁ ተስፋዬን በመጠበቅ እንሆ አለሁልሽ››
‹‹ምንድነው ተስፋህ..ማለቴ ይሳከልኛል ብለህ የምትጠብቀው….?››
‹‹የልጅነት ፍቅሬን… ..አንድ ቀን ቀና ብላ ታየኛለች የሚል ተስፋ..አንድ ቀን ከቄስ ትምህርት ቤት ጀምሮ እንደማፋቅራት እና ዕድሜዬን ሙሉ በልቤ ተሸክሜያት ስዞር እንደኖርኩ ተረድታ በእቅፎ ታስገባኛለች ብዬ ተስፋ በማድረግ..አንድ ቀን እጄ ትገባለች በሚል ተስፋ…..››
‹‹ወየው ጉዴ!!›አለኝች በውስጧ፡ በዚህ ቅርብ ጊዜ ውስጥ የምትቀርባቸውና የምትመኛቸው ወንዶች ሁሉ እንዴት እንዴት ሆኖና ምንስ በሚሉት አጋጣሚ እንደዚህ በፍቅር ስክር ያሉና የታወሩ ሆነው እንደሚገኙ ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም...?‹‹ይሄኛውንስ ዛሬ አልምረውም…በፍጽም፡፡››ስትል ፎከረችው፡፡
‹‹ይቅርታ ሙሉ ታሪኩን እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ….››
‹‹እየነገርኩሽ እኮ ነው …እየተረተርኩልሽ…..ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል አይደል የሚባለው››
‹‹አይ እዚህ አይደለም…እኔ ቤት እንሂድና ተረጋግተን እየጠጣን ታወራልኛለህ….አሁን ሆቴሉም ሊዘጋ መሰለኝ››
‹‹ይቻላል››ይከራከረኛል ወይም ይቃወመኛል ብላ ነበር የጠበቀችው ..ቀድሟት ተነሳ ..ሂሳብ ከፍላ ተከተለችው …. እየተወለጋገድና እርስ በርስ እየተደጋገፉ ላደው ድረስ ሄድ ..ሹፌሩ ተቀብሏቸው እቤት ድረስ አደረሳቸውና የለሊቱን ግዳጅ ጨረሶ ተለያቸው..
እሷም ዛሬ ለዛውም ከመሸ ያወቀችውን ባለ ላዳ ይዛው ወደቤቷ ገባች…..
✨ይቀጥላል✨
#YouTube ቻናሌን አ.ረ.ረ..ረ!!!subscribe እያደረጋቹ😔
👇
https://www.youtube.com/@atronose
#ቻናሉንም ይቀላቀሉ ለሌላም ያጋሩ👇
https://xn--r1a.website/atronosee
Follow my channel on WhatsApp 👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029VaDdoKaJENxsTyh8E43Z

👍122❤11🤔7🔥3😁2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አንድ
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
መኝታ ቤቷ ገብታ ልብሷን ከቀያየረች በኋላ የጀመሩትን አይነት መጠጥ አምጥታ ለሁለቱም ቀዳችና ወደጫወታቸውን እዲመለሱ ተመቻቸች..
‹‹እሺ አሁን ካቆምክበት ጀምርልኝ››
‹‹ምን….? ››አለት ሁሉን ነገር የረሳው ይመስላል
‹‹ታሪክህን እየነገርከኝ ነበር››
‹‹እ..አዎ…ግን የት ላይ ነበር ያቆምኩት….?››
‹‹ስለፍቅረኛህ ጀምረህልኝ ነበር..በህይወት የምትኖርበት ምክንያት እሷን አንድ ቀን አገኛት ይሆናል በሚል ጉጉት ምክንያት እንደሆነ ነግረኸኝ ነበር ያቆምከው››
‹‹አዎ….አይገርምሽም …
እስከጥቂት ቀናት ድረስ እኮ ምንም አይነት ተስፋ አልነበረኝም…››
‹‹ቆይ ጠይቀሀት እንቢ ብላህ ነው….?››
‹‹አረ መጠየቅ…ትቀልጂያለሽ እንዴ ….?ቀና ብዬ እንኳን ሰላምታ ልሰጣት ድፍረቱ የለኝም.››
‹‹ግን እኮ እንደዛ አይነት ሰው አትመስልም..በጣም ደፋር ግልጽ እና በራስ መተማመን ያለህ ሰው ነህ››አለችው ከልቧ..
‹‹እኔም እንደዛ ነኝ ብዬ አምናለሁ..ፍቅር የሚባለው ነገር ግን ዋና ባህሪው ያልሆንሺውን ሆነሽ እንድትገኚ ማድረግ ይመስለኛል…እጅግ ክፉ የነበርሽው ሰው በፍቅር ውስጥ ስትሆኚ ስጋዬን ግፈፉት እስከማለት ድርስ የሚደርስ ደግነት ያጓናጽፍሻል….ደንዳናና ኮስታራ የነበርሽው፤አልቃሽና ተርበትባች ሆነሽ ቁጭ….ፍቅር እንደዛ አይነት በሽታ ነው፡፡››
‹‹ቢሆንም ….ይህን ያህል ካፈቀርካት የሆነ ነገር ማድረግ ነበረብህ ..ለመሆኑ የት ነው የምትኖረው….?››
‹‹የሚገርመው እሱ ነው..በእሷ ቤት እና በእኔ ቤት መካከል ያለሁ እርቀት ግማሽ ኪሎ ሜትር አይሆንም…. ሁለታችንም ሳሪስ በአንድ ሰፍር ተወልደን እዛው አንድ ሰፈር ያደግን ነን…ቤተሰቦቻን የአንድ እድር አባል ሆነው፤አንድ የጽዋ ማህበር መስርተው ዕድሜያቸውን በጉርብትና የኖሩ ናቸው….አንድ ቄስ ትምህር ቤትፊደል መቁጠር ጀምረን .አብረን ኤለመንተር የገባን የእድሜ እኩዬች ነን››
‹‹ይገርማል!!››
‹‹እውነትሽን ነው በጣም ይገርማል…. ከ1ኛ ክፍል አንስቶ እስከ አስረኛ ክፍል አብረን ነበር የተማርነው…በተለይ ዘጠነኛ ክፍል አንድ ወንበር ላይ ነበር የምንቀመጠው…ግን በወቅቱ እኔ ግማሽ ልቤ ነበር ክፍል ውስጥ የሚገኘው… እሷ ደግሞ አካሏም ነፍሶም ትምርቱ ላይ የተጣበቀ ነበር፡፡ግን የሚያመሳስለን አንድ ነገር ቢኖር ሁለታችንም ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ከትምህርት ቤት አንቀርም ነበር..››
‹‹ለምን ….?››አለችው ገለጻው ገርሞት
‹‹እሷ ለትምህርት ባላት ፍቅር የተነሳ እኔ ደግሞ ለእሷ ካለኝ ፍቅር የተነሳ….››
አሳቃት….ብርጭቆውን አንስቶ ከተጎነጨለት በኃላ ቀጠለ
‹‹እሷ እንደማንኛውም የክፍል ጓደኛ ግን ደግሞ ከዛም ትንሽ ከፍ ባለ የሰፈር ልጅነት እና አብሮ አደግነት ነው የምትቀርበኝ…እኔ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ሁለት ሴቶች ብቻ ናቸው ያሉኝ.. እናቴ እና እሷ ብቻ..በቃ..ያኔ አብሬት በምማርበት በዛ ጊዜ ብቻ አልነበረም እንደዛ የሚሰማኝ.. አገር ለቅቄ በስደትም እያለው እንደዛ ነበር እምነቴ…የሆነች ሴት በሆነ ነገሮቾ ትንሽም እንኳን ከእሷ ጋር ካልተመሳሰለችልኝ..የሆነ የእሷን ነገር እንዳስታውስ ካላደረገችኝ አንድ ደቂቃም ላወራት ወይም አጠገቧ ልቀመጥ አይቻለኝም….ከአስር አመት መለያየት በኃላ ከ10 ዓመት ናፍቆት በኃላ እሷን እና እናቴን አንዴ አይቼ ለመሞት ወስኜ ወደሀገሩ ስመጣ…እሷን በተመለከተ ጭራሽ ተስፋ የሚያስቋርጥ ነገር ነው ያጋጠመኝ…፡፡አፍላ ልጃገረድ ገና አጎጠጎጤ ሆና ጥያት የሄድኳት ልጅ አድጋና ፈክታ ሙሉ ሴት ሆና ጠበቀችኝ…፡፡የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሆና የተለየኋት ልጅ ዶክተር ተብላ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ትልቅ ባለሞያ ሆና አገኘኋት..እና የሩቅ ህልሜ የነበረችው ልጅ ጭራሽ መቼም የማትፈታ ቅዠቴ እንደሆነች አሰብኩ…ሳያት በሩቅ መሸሽ ጀመርኩ፡፡ድንገት መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳን ቅንድቤን ከፍ ዝቅ በማድረግ አንገቴን አቀርቅሬ ሰላምታ ለመስጠት ከመሞከር ውጭ እሷ እንኳን ለሰላምታዬ አፀፋውን መመለሷ እና አለመመለሷን እርግጠኛ ሆኜ አላውቅም፡፡ይህቺ ልጅ የእኔ ልጅነቴ ነች….የሩቅ እሩቅ ትዝታዬ …ብዙ ብዙ ለሊቶች በህልሜ ያየኋት… ብዙ ብዙ ታሪክ ያጫወተችኝ….ብዙ ብዙ ነገር ያወጋኋት…ያወጋችኝ..፡፡እንደዛ ብቻ ሳይሆን ደጋግሜ ያገባኋት…ብዙ ብዙ ልጆች የወለደችልኝ…ብዙ የሳምኳት፤ ብዙ የሳመችኝ…ብዙ ያፈቀርኳት፤ብዙ የወደደቺኝ…ግን ሁሉም በህልሜ የሆነ ነበር …››
‹‹ምን አይነት ፍቅር ነው..ስል አሰብኩ ደግሞ ከዚህች ልጅ ጋር የሚያመሳስለኝ አንድ ነገር ይኖር ይሁን .. ….?አዎ መኖርማ አለበት ….እደዛ ቢሆን ነው ይሄን ሁሉ ሰዓት አብሮኝ ያሳለፈው…እቤቴ ድረስ ተከትሎኝ በለሊት የመጣው…አዎ እንደዛ ቢሆን ነው ሚስጥሩን ዘክዝኮ የሚነግረኝ…››ስትል የራሷን ግምት ወሰደች…ግምቷ እውነት ሆኖ እስከአልጋ መዋደቅና መዋሰብ ድረስ ያደርሷቸው እንደሆነ አሁንም በውስጧ እያሳላሳላች ነው ፡
ቀጠለ እሱ…‹‹እና ይገርምሻል ከሶስት ቀን በፊት ያልጠበቅኩት አጋጣሚ ተከሰተ…››
‹‹ምን ተከሰተ….?››
‹‹ወደሀገሬ ከተመለስኩ ከሁለት ዓመት ተኩል በኃላ ትናንት….ድብር እና ጭፍግግ ብሎኝ ሰፈር ላዳዬ አቁሜ እኔም ላዳዬ ውስጥ ወንበሬን ወደኃላ ለጥጬ መፅሀፍ በማንበብ በተመስጦ ላይ እያለሁ...በሀይለኛው የላዳው የኃላዋ በራፍ ሲንኳኳ የሆነ የእብድ ድርጊት መስሎኝ በርግጌ ተነሳሁና አንገቴን በመስኮት አስግጌ ወደ ኃላው ተመለከተኩ…
‹‹እንዴ ሰላም…!!!!!››
‹‹ክፈትልኝ››
‹‹እሺ ››ተረብትብቼ ከፈትኩላት..ተስፈንጥራ ገባች…የሆነ ሰው ከኃላ እያባረራት ይመስላል..ፀጉሯ ሁሉ ጭብርር ብሏል…የአይኖቾ ደም መልበስ ምን አልባት ለቀናት ስታለቅስ እንደቆየች ምስክር ናቸው…..አለባበሶም እንደነገሩ እና ያልታሰበበት ነው….››የአመታት ህልሜ የሆነች ልጅ በእንዲህ አይነት ያልታሰበበት አጋጣሚ ላዳዬ ውስጥ ትገባለች ብዬ እንኳን ማሰብ አልሜ እንኳን አላውቅም…..
‹‹ንዳው ››አለችኝ
ህልም ውስጥ ያለሁ ነበር የመሰለኝ ፡፡ ትዛዞን ተቀብዬ …ሞተሬን አንቀሳቀስኩ እና ነደሁት
‹‹-የትኛው ፖሊስ ጣቢያ እንሂድ….?››ጠየቅኳት
‹‹የምን ፖሊስ ጣቢያ….?›› አለችን ግራ በመጋባት
-‹‹አይ እንዲሁ ነገር ስራሽን ስገመግመው የሆንሽው ነገር ያለ ስለመሰለኝ ነው..››
‹‹ሆኜያለሁ...አዎ የሆነ ነገር ሆኜያለሁ… መች አልሆንኩም አልኩህ …ግን ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ ምን ይፈይድልኛል..….?››አለቺኝ.‹‹ይቅርታ እሺ የት ልወስድሽ..….?››አልኳት
በመለማመጥ..እወነቴን ነው በዛች ላዳ ጆሀንስበርግ አድርሰኝ ብትለኝ እንኳን እድሜ ልክ ይውሰድብኝ እንጂ እንቢ አልላትም…በምን አቅሜ…በእሷ መታዘዝ እኮ ለእኔ እድል ነው…የአለምን ህዝብ አጥፋልኝ ብትለኝ እንኳን ባልችልም ከመሞከር ወደኃላ አልልም፡፡
‹‹እኔ እንጃ የሆነ ሰው እንደእኔ ሲሆን የት ነው የሚሄደው..….?ወይም የት ነው መሄድ ያለበት..››በቀላሉ ልመልሰው የማልችለውን ውስብስብና ግራአጋቢ ጥያቄ ጠየቀችኝ ‹‹እኔ እንጃ ምን አልባት ቤተክሪስትያን ልውሰድሽ….?››ይሻል የመሰለኝን አማራጭ አቀረብኩላት ፡

👍85❤10😁2👏1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አራት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ አራት መአዘን ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል
‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት
‹‹አቤት አባ›››
‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..
‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው
‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡
‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ
‹‹እኔ ነኝ ..››
የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››
‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››
‹‹ምነው በሰላም..?››
‹‹እኔ እንጃ ብቻ ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››
‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››
‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››
‹‹ለምን አይገቡም..?››
‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››
‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት
‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ ወደክፍላቸው ተመለሱ….
‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››
‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››
‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…
‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡
‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››
‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››
‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››
‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››

👍120❤10🥰1👏1🎉1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹ልሄድ ነበር››አላት ሚለው ጠፍቶት..አንዴ ኬድሮንን አንዴ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን መላኩን እያየ
‹‹አይ መኝታ ቤት ተመልሰህ ትጠብቀኝ..አብረን ነው ምንወጣው››
ግር አለው‹‹ይቅርታ አልሰማሁሽም..?››
‹‹እሱን ልሸኝና እመጣለሁ …መኝታ ቤት ተመልሰህ ጠብቀኝ…››
ባለማመን ወደኋላው ዞረና.. ወደመኝታ ቤት ተመለሰ
ከመላኩ ፊት ላይ ግራ የመጋባት ጥያቄ ስላነበበች‹‹ባለቤቴ ነው..?›› አለችና ሳይጠይቃት መለሰችለት….
‹‹እንዴ….ባለቤቴ…ታዲያ እኔን…....?››
‹‹እኔ ለቀልድ ነበር እደዛ ያልኩህ ..የእውነት ታዳርገዋለህ አላልኩም ነበር…..››ከተቀመጠበት ተነስቶ ተንደርድሮ ጉንጯን እያገላባጠ ሞጨሞጫት
‹‹በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ…በቃ ሁለቴ ህይወት ሰጥተሸኝል….ሰሚርን አዳንሺልኝ አሁን ደግሞ ነፃነቴን ስትሰጪኝ››
‹‹አይ ግድ የለም››አለችና ከእቅፉ እየወጣች…ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈትና ሲስማት መተንፈስ አቅቶት ነበር…በቃ በሽታዋ ሁሉ ሊነሳባት እና ሀሳቧን ልትቀይር ትንሽ ነበር የቀራት…..
እንደመደንገጥ አለና ወደመኝታ ቤቱ ገልመጥ በማለት ሲስማት ማንም እንዳላየው ለማጣራት ሲሞክር በቆረጣ አይታ ለራሷ ፈገግ አለች ..‹‹በቃ ልሂድ.. ሌላ ቀን ከሰሚር ጋር መጥተን እንጠይቅሻለን ….በቃ ዘመድ እንሆናለን..››እያለ ይዞ የመጣውን ሻንጣ ይዞ ለመሄድ አንጠልጠሎ ተዘጋጀ፡፡
‹‹ሰላም በልልኝ..ግን እኔን ለመጠየቅ አትልፉ.. ዛሬ ለሊት ወደውጭ ልበር ነው….››ስትል ዋሸችው
‹‹ዉይ !!!ምነው?በሰላም..?››እንደመደንገጥ ብሎ፡፡
‹‹አይ በሰላም ነው …ቤተሰብ እዛ ስለሆነ እዛ ለመኖር ነው››
‹‹እሺ በቃ እግዜር ካንቺ ጋር ይሁን …ዕድሜ ልክ ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታሽ አለብኝ ››እያለ ሳሎኑን ባለማመን ለቆ ወጣ……
‹‹ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈልኩልህ ብታውቃው..ባንተ ምክንያት ይህቺን አለምና ንስሬንም ጭምር እንደአጣሁ ብትሰማ›› ስትል አሰበች
….ይህን ሁሉ ልትነግረው ያልፈለገችው ቢያንስ በስተመጨረሻ ጥሩ ልሁንለት ብላ ነው ….በፀፀት ያልደፈረሰ የፍቅር ህይወት ይገባዋል ብላ ስላሰበች ነው….አሁን የእነሱን ሰሚራ ለማዳን የሆነችውን እና ያጣችውን ዘርዝራ ባታወራው ከማዘን በስተቀር ለእሷ ምንም አይፈይድላትም..በእሱ ህይወት ላይ ግን ቁጭትን ይፈጥርበታል…..ደስታው ላይ ደመና ያጠላል…. ያንን አስባ ነው እውነቱን የደበቀችው፡፡
/////
ሀሳቧን ሰብስባ ቀጥታ ወደመኝታ ቤቴ ሄደች…. ስትደርስ ባዶ ነው..ግራ ገባት….‹‹ እንዴ በጓሮ በር ሾልኮ ፈረጠጠ እንዴ..? ››ብላ ሳታሰላስል ከሻወር ቤት የውሃ መንሾሾት ድምጽ ሰማችና ወደ እዛው ሄደች..ደረሰችና ብርግድ አድርጋ ከፈተችው…. ድንገት መሳሪያ እንደተደቀነበት ምርኮኛ ኩም ብሎ ደነገጠ..እጆቹን የተንዘላዘለ እንትኑ ላይ ሸፈናቸው….
‹‹አረ ልቀቀው ..ለሊቱን እስክጠግብ እኮ ሳየው ነው ያደርኩት››
‹‹እብድ ነሽ..አስደነገጥሸኝ እኮ …››አለና ቀስበቀስ ለቀቀው
‹‹ህፃን ሆነህ እናትህ በቂቤ በደንብ ያሹልህ እና ይጎትቱልህ ነበር እንዴ..? ››
‹‹‹ምን እንዲሆን ነው የምትጎትትልኝ..?››
‹‹እንዲህ እንዲንጀላጀል ነዋ….ሜትር ከምናምን እንዲሆንልህ››
‹‹ትቀልጂያለሽ..ቆይ ማን ነበር ሰውዬው… ውሽማሽ መስሎኝ እኮ ተበላሁ ብዬ ነበር››
‹‹አይደለም ዘመዴ ነው…እንዴት ነው እኔም አወላልቄ ልግባ እንዴ..?››
‹‹ወዴት....?››
‹‹ወደሻወር ነዋ..እጠበኝ ልጠብህ››
‹‹ኸረ በፈጠረሽ..ስወደሽ እንዳታደርጊው››
ሳቋ አመለጠት‹‹እንዴ !!ይሄን ያህል…...?››
‹‹እንዴ…እሳት እኮ ነሽ…እኔ እንጃ የዛሬ ወር ድረስ ተከፍቶ ባገኝ እንኳን ለመክደን አልሞክርም…እንዴት እንዴት አይነት የወሲብ ጥብብ ነው..የሆነ ህልም ውስጥ እኮ ነው ያስገባሺኝ..በአየር ላይ ሁሉ እየተንሳፈፍኩ ይመስለኛል…አሁን ሳስበው ደግሞ እንዴት በአየር ላይ መንሳፈፍ ይቻላል እላለው....?ከግድግዳ ጋር ግን እዳጣበቅሺኝ በእርግጠኝነት አውቃለሁ..ግን አጥንቶቼ ስብርባራቸው ለምን እንዳልወጣ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ…ብቻ ግራ ተጋብቻለሁ.፡፡እኔ በህይወት ፍቅር እንጂ ያጣሁት የወሲብ ችግር ገጥሞኝ አያውቅም….ቁጥራቸውን ከማላስታውሳቸው ሴቶች ጋር ወሲብ ፈጽሜያለሁ..በአንድ ለሊት ስድስት ሰባቴ …ግን ከንቺ ጋር ያደረኩት አንድ ዙር ወሲብ እድሜ ልኬን ከደረኩት ጋር የማይነፃፀር እና የተለየ ነው››
‹‹ወሲብ ደጋግመን የምፈፅመው ለምን እንደሆነ ታውቃልህ..?››
‹‹እኔ እንጃ››
‹‹እኔ ግን ስገምት ..ለኮፍ ለኮፍ ከሆነ ወዲያው ወዲያው ያምርሀል…በሁለት ደቂቃ በራፍ ላይ ደፍቶ ተልኮውን የሚያጠናቅቅ ሰውና በ20 ደቂቃ ውስጠ ውስጥ በርብሮ ግዳጁን ያጠናቀቀ እኩል መልሶ አያሰኛቸውም….ለዛ ነው ››
‹‹ይሁንልሽ ››አለና የሻወሩን ውሃ ዘግቶ… ፎጣውን አገለደመና ከሻወሩ ቤት ወጣ …ተከተለችውና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች፡፡
‹‹እሺ ቁርስ ትጋብዘኛለህ አይደል..?››አለቸው
‹‹አንቺን ለመሰለች ቆንጆ እንኳን ቁርስ አራሴንስ ብጋብዝሽ ቅር አይለኝም..››
‹‹እራስህንማ እንዴት ልትጋብዘኝ ትችላለህ…..?››
‹‹ለምን አልችልም..?››ሲል ጠየቃት ኮስተር ብሎ
‹‹እኔ ልቡን ለሌላ ሰው ጠቅልሎ ያስረከበና ቀፎውን ብቻ ያለ ሰው ምን ያደርግልኛል…....?››
‹‹አይ የምታወሪው ስለ ሰላም ከሆነ ተስፋ ቆርጬያለሁ….አሁን የምፈለገው ምን እንደሆነች ብቻ አውቄ ልረዳት ነው…ያንን ማድረግ ከቻልኩ ይበቃኛል…ካዛ….››
‹‹ከዛ ምን…..?››
‹‹እኔ እንጃ… የላዳ ሹፌር ነው ብለሽ ካልናቅሺኝ በጣም ነው ያፈቀርኩሽ..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ስትል..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ነዋ..በጣም ነው የተመቸሺኝ ….የሆነ የማላውቀውን አለም ነው ያሳየሺኝ…ላጣሽ አልፈልግም….››
‹‹ስለእኔ ምንም እኮ አታውቅም....?››
‹‹ማወቅ አልፈልግም..አንቺ ብቻ እሺ በይኝ እንጂ…..››ንግግሩን ሳይጨርስ ንስሯ እየበረረ የመኝታ ቤቱን በር በርግዶ በመግባት እንደቀናተኛ አባ ወራ አልጋ ላይ ተኮፍሶ ጉብ አለ….
ይሄንን በድንገት ያየው ባለ ላዳው ከተቀመጠበት በርግጎ ወድቆ ነበር..
‹‹አይዞህ አይዞህ…›››ሳቋ እያመለጣት
‹‹አይዞህ….!!›
‹‹የማታው ንስር አይደል..?››
‹‹አዎ ነው››
‹‹ምን ይሰራል እዚህ..?››
‹‹እዚህ ምን ትሰራለህ ..?ብሎ መጠየቅ ያለበት እሱ ነው..ምክንያም እሱ የገዛ ቤት ውስጥ ነው ያለው››
‹‹ማታ የእኔ ነው ያልሺው እወነትሽን ነው እንዴ..?››
‹‹አይ የእኔ አይደለም..እኔ ነኝ የእሱ….››
‹‹እኔ እንጃ ግራ ይገባል..››እያለ ልብሱን መልበስ ጀመረ……..
‹‹ሰላምን እንድትረዳት ልናግዝህ እንችላለን››አልኩት
‹‹ልናግዝህ ስትይ....?አንቺና ማን..?››
‹‹እኔና ንስሬ››
ፈገግ አለ….‹‹ትቀልጂብኛለሽ አይደል..?››
‹‹የምሬን ነው…›
‹‹አንቺ እሺ ይሁን …ይሄ እንስሳ እንዴት አድርጎ ነው የሚረዳኝ..ደግሞስ አንቺስ ብትሆኚ በምን መልኩ ልትረጀኝ ትችያለሽ .. ..?እኔ እንኳን ገና ችግሯን ማወቅ አልቻልኩም››

👍110❤15😁4👏2😱2👎1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/////
ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….
‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›
ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….
‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…
ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት
ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ ….››
‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››
‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ
እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››
‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››
‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››
‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››
‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም ለማለት አቸገራለው….››
‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>
‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ ሲል ሰላም በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….
‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››
‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››
‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው
‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››
‹‹አላውቅም››አለች
‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት ኤልያስ
ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››
‹‹እሺ››
‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››
‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ
ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……
‹‹ልጄ ሰላሜ…››
ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡
‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››
‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››
‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››
‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ ስራ ጣልቃ አትግቢ..››
‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››
‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››
‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››
‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን ድረስ ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››
‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››
እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››
‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››
‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››
‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››
‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››
‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››
‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››
‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››

👍89❤10🥰3👎1🔥1😁1
#ተአምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››
‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት
‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ
‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት
ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…
‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››
‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››
‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››
‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ
ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››
‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ
‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››
‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?››
‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…
መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ እያመሩ ሳለ…
‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት
‹‹ያው ላንተ ስል ነው››
‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››
‹‹ለምን…?››
‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››
‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››
‹‹ምን ለመሆን…?››
‹‹ለመብረር…››
‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››
‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….
እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….
‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››
‹‹ምንም ››
‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ ግን ቅር አሰኝቶኛል››
‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››
‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////
የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…
ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም.. የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ ተክል ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡
‹‹አትመጪም… ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…
‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››
‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡
የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…
‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››
‹‹ውሀ ››
‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል
‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››
‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡
‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች ናቸው…››
‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››
‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና እንከን አልባ ስፍራ ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን ነው፡፡

👍91❤8👏4😢4🔥2🥰2🤔1