አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ .....የሚያንቀጠቅጥ ሀሳብ መጣብኝı ኬሪ ወይም ኮሪ የሆነ ነገር ሊሰብሩ ቢችሉ ቅጣቱ ምን ሊሆን እንደሚችል!. እናታችን ቃሏን በመጠበቅ መንትዮቹ ከተኙ በኋላ ወደ ክፍላችን መጣች::በጣም ቆንጆ ከመሆኗ የተነሳ ልቤ በኩራት፣ በአድናቆትና በትንሹ በቅናት አበጠ የለበሰችው ልብስ ጆሮዎቿ ላይ በረጅሙ ከተንጠለጠሉትና ከሚያበሩት…»
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

...“ ኧረ እኔ እንጃ ጌታዬ እኔ ካፒቴን ቶርንን አንድ ጊዜ ብቻ ስለ ነበር ያየሁት አሁን ዐውቀዋለሁ ለማለት አልደፍርም " ይኸን ሰውዬ ላየውም ስለዚያኛው ሰውዬ የመጣልኝ ትዝታ የለም " ሰዉዬውን ሳየው ምንም አይቸው የማውቅም አልመሰለኝም "

ስለዚህ ሚስተር ካርላይል ከጆይስ ምንም ጠቃሚ ፍንጭ አላግኘም በበነጋው ኦትዌይ ቤተልን ፈልጎ አግኘው "

"ያ ከሔርበርት ቤተሰብ ጋር ያለፈው ካፒቴን ቶርን የሚባለውን ስው ደኅና አድርገህ ታውቀዋለህ ? አለው

“ አዎን! ሁለት ሰዓት ያህል ከሱ ጋር መቆየት በደንብ ለመተዋወቅ የሚበቃ ከሆነ በቀደም ሔርበርት ዘንድ ሔጄ ሳለ ሰውየው መጣ እዚያ ስናወጋ ብዙ ቆየን ግን ለምን ጠየቅኽኝ ?”

“ ያ አፊ ሆሊጆንን ያሳድድ የነበረው ቶርን የሚባለው እሱ ነው ከፈለግህ እውነቱን ልትነግረኝ ትችላለህ " "

ቤተል ድርቅ ብሎ ቀረ “ እንዴት ያለ እግር ያወጣ ውሸት ነው ! አለ
ቆይቶ ቆይቶ “ ይኸ ያ አይደለም አይደለም እንዴ የማን ቶርን ነው እሱ ?”

“ ዐውቀህ እያምታታህ ነው ቤተል " ከሆሊጆን ግድያ ጋር የተያያዘው ቶርን የሚባለው ሰው ይኸው አይደለም ?

ምን ሆንክብኝ ... ሚስተር ካርላይል እኔ ከአፊ ጋር የሚተዋወቅ ቶርን
የሚባል ሰው መኖሩን እንደማላውቅ ነግሬህ ነበር " ለምንድነው ቃሌ የማይታመነው? እኔ ቶርንን ከበቀደም በቀር አይቸው አላውቅም ካስፈለገ እምላለሁ” ብሎት ጥሎት ሔዶ

ቤተል የቶርንና የአፊ ስም ሲነሣበት ከዚህ በፊት እንዳዶፈደረግው ሁሎ አሁንም
መልኩ ተለዋወጠ አንድ ዐይነት ጭንቀት ሲፈጠርበት ታየ " ከዚህ ስምና ግድያ ጋር የተሳሰረ ምስጢር መኖሩን ለሚስተር ካርላይል ተሰማው " በግምት ምንም ማድረግ አልቻለም " የቤተል መልስም ፍንጭ አልሰጠውም » ከዚያ እሱም ወደ
ቢሮው ሲሔድ ቶም ሔርበትን አገኘውና ቶርን ከነሱ ጋር ብዙ ይሰነብት እንደሆነ ቢጠይቀው : ወዴፊት ካልመጣ በቀር ለአሁኑ ግን መሔዱን ነገረው "

ሚስተር ካርላይል ለራት ወደ ቤቱ ሲሔድ ሚስዝ ሔርን ለመጠየቅ አስመስሎ ወደ ዐፀዱ ጐራ አለ » ባርባራ የሚስተር ካርላይልን መልስ ለመስማት ልቧ ተንጠለጠለ ። ሚስዝ ሔርን አነጋግሮ ሲወጣ ተከትላው ወጣች ።

“ ምን ፍንጭ አገኘህ ?

“ ምንም የሚረባ ነገር አልተገኘም ሰውየውም ሒዷል ”

“ ሔደ! "

ባለፈው ምሽት ባርባራ ወደ ቤቷ እንደ ተመለሰች ሰውየውን ከቶም ሔርበት ጋር እንዴት ወደ ቤቱ እንደ ወሰዳቸው ኋላም ቶም ሔርበትን አግኝቶት ምን እንዳለውና ከቤተል ጋርም መነጋገሩን ሁሉ አጫወታት

“ምናልባት የነገሩን አዝማሚያ በመገመት ፈርቶ ይሆን የሔደው? አለችው "

አይመስለኝም መጀመሪያውንስ ለምን ይመጣ ኖሯል ?

ግን የተጠረጠረ መሆኑን የሚጠቁም ቃል አለመናገርህን እርግጠኛ ነህ ?

ምንም አልተናገርኩም ፡

ሰውየው ግን ምንድነው ?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ጥቂት ዓታት ዐለፉ

ሰማህ ሚስተር ካርላይል እስኪ ቦታ ትለውጥ ለምላሌ ወደ ቤልጅግ ወይም ወደ ፈረንሳይ
ሊረዳት ይችላል ባሕር ጠረፎች ብትወስዳት ፡ በባሕሩ ውሃ ስትታጠብ በጣም ሊረዳት ይችላል።

“ ከቤት ርቃ መሔዱ ለሷ ደኅና ይመስልሃል ? ”

“ አዎን ይመስለኛል " አየህ ይህ ነው የምትለው የአካል ቀውስ ካለ 'በሕክምና መከታተል ስለሚገባ ቦታ መለወጡ ፡ አየር መቀየሩ ሁሉ አይታየኝም"ክስዊስ ተራሮች ቢወጡ ወይም ከዴንቨር ሸለቆ ቢወርዱ ዋጋ የለውም » እንደሷ ያለ የድካም ሰመመን ላለበት ግን አየርና ቦታ ለወጥ በጣም ይጠቅማል " ብርታቷን
በእንደዚህ ዐይነት ጥረቶች እያባበልክ ለመመለስ ከመሞክር በቀር ሌላ ምንም ማድረግ አይቻልም ”

“ እስኪ ከሷ ጋር ልምከርበት ”

“ እኔም ነግሬያት ነበር” አለ ዶክተር ማርቲን ፡ የሐሳቧ አቅራቢ : አልተቀበለችኝም በሽተኞቹ ሁልጊዜም ከቤታቸው መራቅ ደስ አይላቸውም መሔዷ ግን አስፈላጊ ነው።

ንግግሩ ስለ እመቤት ሳቤላ ነበር በአሁኑ ጊዜ በኢስት ሊን ሳቤላ ዊልያምና አርኪባልድ የሚባሉ ፡ የመጨረሻዉ የዐሥራ ሁለት ወር ልጅ የሆነ : ሦስት ልጆች
ደርሰዋል ሁለት ወር ያሀል ቀደም ብሎ ሳቤላ ክፉኛ ታማ ዳነች ግን ድቅቅ አድርጎ ስለ ለቀቃት ሰውነቷ አልጠነክር አለ ሚስተር ዌይንራይት ያላደረገው ጥረት
አልነበረም ግን ከመባስ በቀር ምንም አልተሻላትም በመጨረሻ ዶክተር ማርቲን ከሊንበራ ተጠርቶ መጣ እሱም ሁኔታውን አይቶ ያየርና የቦታ ለውጥ አዘዘ

ሳቤላ የሐኪሙን ትእዛዝ ለመቀበል በተለይ እስከ ፈረንሳይ ጠረፍ ለመሔድ አልፈቀደችም

በሚስተር ኬን ትርዒት ጊዜ ያየናት ሚስዝ ዱሲ ፓሪስ ላይ ዐሥራ ስምንት ወር ስትቀመጥ ለሳቤላ ሁለት ጊዜ ጽፋላት ነበር አሁን ደግሞ ወደ ቡሎኝሱር ሜር ሔዳ አንድ ሁለት ወር እንደምትቆይ ጻፈችላት » የሳቤላ እመቢታ የብቸኝነት ፍራቻ እንደሚሆን በመገመት አሁን ግን ዱሲ ካለችላት እሺ ማለት እንዳለባት
ሐኪሞቹ አመኑ ዶክተር ማርቲንና ሚስተር ዌይንራይት ሊያግባቧት ሞከሩ

“ ደሞ ለዚያውም ቡሎኝሱርሜር ! እሱማ ደኅናውና ባለጌው ሁሉ የሚጠራቀምበት ነው ይባል የለ ? አለች ሳቤላ ነገሩን በመቃወም
ሚስተር ካርላይልም አብሯት ለመሔድና ለመቆየት ስለማይመቸው ሚስቱን
ወደዚያ ለመላክ ደስ አላለውም " እንዲያውም ትሩቪል ወደሚባለው አርፍለር አጠገብ ወደሚገኘው የባሕር ዳርቻ መናፈሻ ብትሔድለት መረጠ " ሐኪሞቹ ግን ብቸኝነት አንድ በሽታ በመሆኑ የፈለገው ሕዝብ ቢጠራቀምበትም መዝናናት ስለምትችል ቡሎኝ ሔዳ ከሚስዝ ዱሲ ጋር እንድትገናኝ መከሩ ።

ሚስተር ካርላይልም ተሸነፈና አመነበት « እሷም እነዚያን ሁሉ መቃወም ስለተሳናት ተቀበለች "

በርግጥ ሰውነቷ ያለመጠን ተጐሳቁሉ ነበር " ፊቷ እልቅ ብሎ ወቷል ደስ የሚሉት አሳዛኝ ዐይኖቿ ጥቁርቁር ብለው ገውለል ገውለል ይላሉ እጆቿ ጅማታቸው ወጥቶ በትኰሳት ይፋጃሉ ጊዜው ሙቀት ቢሆንም የሚሞቅ ልብስ ደራርባ ሳትንቀሳቀስ እንደ ተቀመጠች ትውላለች ልጆቿ ሲጫወቱ ትመለከታለች" ያካባቢ ገመግሞችንና ሜዳዎችን ተራሮችን ትመለከታለች " አንዳንድ ጊዜ በዝግ ሰረገላ ተንቀሳቅሳ ትመለሳለች።

እንደዚያ እንደ ሆነች የባሏና የባርባራ ግንኙነት ነገር እንደገና ተመለሰባት ለጥቂት ዓመታት ደህና ረስታው ነበር " አዲስም ሆነ አሮጌ ቅሬታ ሲሰማት ድካሟ
ይጠናባታል የሆነ ያልሆነ ሐሳብ ይመጣባታል ሚስተር ካርላይል በርግጥ የሚወዳት መሆኑንም ትጠራጠራለች ምናልባት ልቡ ባርባራን እየወደደ እሷን ለዝና
ሲል በጌታ ልጅነቷና በውበቷ ብቻ የመረጣት መስሎ ይታያታል " በተጋቡ በመጀመሪያ ዓመት ያሳያት የነበረው እንክብካቤ ቀስ በቀስ ወደ ስክነት ተለውጧል መቼም ይህ ዐይነት ጠባይ ያልተከሠተበት ጋብቻ አይገኝም " ምክንያቱም ፍቅር ስለሚቀነስ ሳይሆን የጊዜና የተለምዶ አሠራር ነው ማንኛውም እየቆየ የተለመደ ነገር ሁሉ እንደ አዲስ አያስደንቅም ፣ አያስጨንቅም በጋብቻ ዓለምም እጮኛና አዲስ ባል አፍለኛ ፍቅሩን ለመግለጽ ብዙ ነገር ቢቀባጥር ሴቶች ሊያምኑት ይችላሉ " እየቆየ መጨነቅ መጠበቡን እየቀነሰ ቢመጣ ግን ሊቀየሙት አይገባም " ለምሳሌ ሕፃናትን እንመልከት " አዲስ ታምቡር የተገዛለት ወንድ ልጅና የልጅ ምስል አሻንጉሊት የተገዛላት ሴት ልጅ አዲሶቹን መጫወቻዎች ይስሟቸዋል ያቅፏቸዋል እንቅ አድርገው ይዘው ከመሬት እንኳን አያስቀምጧቸውም ሌላውን
👍111
መጫወቻ ይረሱታል ትንሽ ቆይቶ ግን ታምቡሩ ካንድ ጨለማ ጥግ ይቀመጣል አሻንጉሊቷ ከቦታዋ ትጣላለች " ዙረው እንኳን አያዩዋቸውም " በዚህ ጊዜ ልጆቹን በቅርብ የተሰጡዋቸውን መጫወቻዎቻቸውን አምጥተው እንዲጫወቱባቸው
ብትነግሩዋቸው ደስ አይላቸውም በግልጽ ይከፋቸዋል ሰልችተዋቸዋላ ይህ የሰው ተፈጥሮ ጠባይ ስለሆነ ልጆቹ ወረተኞች ሆኑ ተብለው መውቀስ ዋጋ የለውም "

ታዲያ ያደጉ ልጆችስ ምን ልዩነት አላቸው ? ሁላችንም ወንዶችም ሆን ሴቶች ተጨንቀንና ተጠበን የያዝናቸውን አሻንጉሊቶቻችንን ከጊዜ በኋላ ቸለል አንላቸውም? በግድ የለሽነት አንመለከታቸውም ? ስለዚህ ወጣት ሴቶች! ለወደፊት ባል
የሚሆን ጐበዝ በፍቅር ነሁልሎ 'ለዘላለም አመልክሻለሁ ሲላችሁ • ከፈለጋችሁ ልታምኑት ትችላላችሁ ! እሳቱ እያደር እየቀነሰ ሲመጣ ግን አትቀየሙት ያ ሁሉ መቅበዝበቅ ቀርቶ ፍቅሩ የሚሰክንበት ጊዜ ይመጣል " ይህ ጥላቻ ወይም ግድ የለሽነት አይደለም ስክነት ነውና ተረድቶ በትዕግሥት መቻል ይገባል “

ሳቤላም የባሏ መለወጥ በዚህ መሠረታዊ ጠባይ ምክንያት መሆኑ አልገባትም“ የባርባራ ሔር ተጽዕኖ አድርጋ ነበር የተረጎመችው " መጀመሪያ ሚስት ሆና ኢስትሊን ስትገባ ' የፒያኖው ! የመዝሙሩ ፡ የመሳሳሙ በጠቅላላው ለሷ ያሳየው የነገበረው መጨነቅ ሁሉ ይታወሳት ጀመር ።

ከመጀመሪያም ሳቤላ የሚስተር ካርላይል ፍቅር ይዟት እንዳልነበር እናስታውሳለን " ነገር ግን ለሷ ያሳያት ከነበረው አዘኔታና የርኅራኄ ሐሳብ የተነሣ ባለውለታነቷን ባለመርሳት ልታፈቅረው ትጣጣር ነበር " በሙሉ ልቧ ታከብረው
ታደንቀውና ከማንም የላቀ አድርጋ ትገምተው ስለነበር በጥረቷ ለማፍቀር ያደረገችው ሙከራ የተሳካላት መስሎ ታይቷት ሊሆን ይችላል መቸም ከሌሎች ወንዶች
ጋር እያነጻጸረች ምን ያህል እንደሚበልጣቸው ስትረዳው የደግነቱን የጨዋነቱን
ነገር ስታስበው ፡ ሌሎች ከሱ ምን ያህል አንሰው እንደሚታይዋት ስትገነዘበው የሱ ሚስት በመሆኗ ልቧ በኩራት ከፍ ከፍ ይላል " በአርኪባልድ ካርላይል ለመመረጥ በመብቃቷ የክብር ኩራት ይሰማታል ከልቡ አንዲት ጥግ ከፈል አድርጐ ለባርባራ መተው የማይቃጣ ጉዳይ ነው " ፍጹምም ከምትታገሰውና ከምትችለው በላይ ነው !!

አንድ ቀን በጉዞው የተቆረጠበት ዕለት እመቤት ሳቤላ ከሦስት ልጆቿ ጋር ከሳሎን ተቀምጣለች የመጨረሻው ሕፃን ከሥጋጃው ላይ ቁጭ ብሏል " አምስተኛ ዓመቷን የያዘችው ትንሿ ሳቤላ ስልክክ ያለች ቆንጆ ልጅ ሆናለች ዊልያም በናቱ ወጥቷል " አርኪባልድ ልክ ሚስተር ካርላይልን ይመስላል "

“ ኑ እስቲ ወዲህ .. ዓለሞቼ ” አለቻቸው " ሳቤላና ዊልያም ወደሷ ሮጠው ሲመጡ ሁለቱንም በአንዳንድ ክንዷ ጥምጥም አድርጋ ያዘቻቸው አርኪባልድ ምን
ጣፉን በተረከዞቹ እየመታ ተጐልቶ ቀረ " ቀና ብለው እናታቸውን ተመለከቷት።

“ ከእናታችሁ ጋር በመርከብ ተሳፍራችሁ ባሕር ተሻግራችሁ እሩቅ መንገድ ብትሔዱ ደስ ይላችኋል ?” አለቻቸው "

የናቷን ይሉኝተኛ ጠባይ ያነሣችው ትንሿ ሳቤላ ፈቃደኝነቷን በፈገግታ
ገለጸች " ዊልያም አጨበጨበ “ አዎን በመርከብ ! አርኪባልድም ይሔዳል ? ”

አርኪባልድና ሌሎችም ” አለች ሳቤላ “ ጆይስም ዊልሰንም እንዲሁም በመስኮቱ አጠገብ ተቀምጣ ልብስ ትሰፋ የነበረች ኮርኒሊያ የልጆቹን ደስታ ስትሰማ ለመበጥበጥ ቶሎ ብላ ወደነሱ ዞረች " እሷ ፊቱንም ቢሆን በግልጽ አልተቃወመችም እንጂ በወይዘሮ ሳቤላ ጉዞ አላመነችበትም ነበር " ያየር ለውጥ ብሎ ነገር! ምን ሊረባ ነው? እሷ, እንደሆነ አንድም ቀን እንደዚህ ያለ ለውጥ አስፈልጓት
አያውቅም አንድ መንጋ ዐወቅን ባይ ዶክተሮች ተጠራቅመው ለሁሉ ነገር ያየር ለውጥ የሚል አባዜ ይዟቸዋል አሁንማ ለተጫረ ጣትም የአየር ለውጥ ሳይሉ አይቀሩም !! ወይዘሮ ሳቤላም ፡ ብትጥር ብትሞክር ኖሮ ከቤቷ ሳትወጣ በጎ ትሆን ነበር እያለች ስታስብ ነበር ። አሁን ይህን ደስታ ስትሰማ ልጆቹ ወደ ባሕር ዳርቻ
አይሔዱም” አለች ' “ ሐኪሞቹ ወደ እዚያ እንዲሔዱ አላዘዙላቸውም”

“ ቢታዘዝላቸውም ባይታዘዝላቸውም ከኔ ጋር መሔድ አለባቸው " የሚቀሩበት ምክንያት የለም»

“ምክንያቱማ ወጪ ነዋ ! አንድ ሠረገላ ሙሉ ልጆች ሳይጨምሩ እንኳን ላንቺ ' ለፒተርና ለጆይስ የሚወጣው ገንዘብ ብቻ ለባለቤትሽ የውድቀት መንገዱን
ደኅና አድርጐ ይጠርግለታል "

ሳቤላ ልቧ ፍስስ አለ "

“ አንቺ የምትሔጂው ዕረፍት አግኝተሽ ለማገገምና ጤናሺን ለማግኘት ከሆነ ልጆቹ አብረውሽ ሔደው ካስቸገሩሽ ምኑን አገገምሺው?” አለቻት ሚስ ካርይል"

ሳቤላ ከተቀመጠችበት ተነሥታ ሕፃኑን አልችለው ብላ በግድ ከወለሉ ምንጣፍ አንሥታ ጉልቡቷ ላይ አስቀመጠችውና ከወንበሩ ተቀምጣ ፊቱን ከፊቷ ጥብቅ
አድርጋ ያዘችው ።

አሁን ይህ ሕፃን እናቱ ጥላው ስትሔድ ይወዳል?”ብላ ዕንባዋ ዝርግፍግፍ ብሎ በመውረድ በደረቷ ከተዘናፈለው ጸጉሩዋ ላይ ዐረፈጀ። እኔስ ትቻቸው አልሔድም ” አላች የልመና ፊቷን ወደ ሚስ ካርይል መልሳ።

"ብቻዬን ሔጄ በጎ አልሆንም የልጆቼ ናፍቆት ዕረፍት አይስጠኝም "

"ብቻዬን አልሽ እመቤት ሳቤላ ? ባልሽንሳ ከምንም አልቆጠርሺውም
“ ባሌ እኮ ያደርሰኛል እንጂ አብሮኝ አይሰነብትም ‥ ‥

«አይ መቸም እሱ ካንቺ ጋር ተቀምጦ ከዚህ ሥራው ይበላሽና ይጥፋ አትይም " አለቻት ሚስ ኮረነሊያ።

“ እሱማ ይኸ ሁሉ መዓት ወጪ እያለበት እንዴት አድርጐ ከሥራው ተለይቶ ከአንቺ ጋር ይሰነብታል ? ልጆቹ ሁሉ ተጠራቅመው ከአንቺ ጋር ሔደው ከባሕሩ ውሃ እንዲጫወቱ ከመደረጉ በፊት ምን ያህል ገንዘብ እንደሚጠይቅ ቁጭ ብሎ ማስላቱ ሳይሻል አይቀርም " ነገር ግን ወይዘሮ ሳቤላ ... እኔ ሐሳቤን ነው ያቀረብኩት አንቺ የአርኪባልድ ሚስት የቤቱ እመቤት ስለሆንሽ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያለሽ "

ማታውኑ ሚስተር ካርላይል ከሥራ ሲገባ ትንሿ ሳቤላን አንሥቶ በትከሻ ተሸክማት " ወደ ልጆቹ ቤት ሊገባ ' የሚስ ካርላይልንና የሚስዝ ካርላይልንን ንግግር
በመጠኑ ስትሰማ የነበረችው ጆይስ ለመናገር ጥሩ ኢጋጣሚ መሰላትና እሜቴ ልጆቹን ይዘው ለመሔድ ይፈልጋሉ ከነሱ ተለይተው ቢሔዱም ናፍቆቱን አይችሉትም” አለችው። "

“ ለምን አይሔዱም?” አላትና ሚስተር ካርላይል ተነሥቶ ወደ ሳሎን ሔደ! ሚስቱ ብቻዋን ተቀምጣ ነበር " “ሳቤላ ... ልጆቹን ይዘሻቸው ለመሔድት ትፈልጌያለሽ ? ” አላት "

ገንዘቡ ይበዛ እንዴሆነ ብዬ ፈራሁ እንጂ እኔማ እፌልጋለሁ ፡ አርኪባልድ ''

“ሊሔዱ ይችላሎ " ላንቺ ብቻ ሳይሆን ለነሱም ለውጥ ነው" የወጪው ጉዳይ የኔ እንጂ ያንቺ ሐሳብ አይደለም" እኔ ካላልኩሽ በቀር ስለ ወጯ ጉዳይ ምንም አታስቢ "

“ወጪውም እስከዚህ ብዙም አይጨምርም አለች በደስታ ፈገግ ብላ “ እነሱን ባጠገቤ ከያዝኩ ደግሞ ቶሎ በጎ እሆናለሁ "

“ለምን ከፈለግሽ እስከ አጽናፍ ዓለም አትወስጂያቸውም » አንቺ ለምቾትሽ ለደህንነትሽ ብቻ ካልሆነ ለሌላው ለምን ታስቢያለሽ ?”

እጁን በፍቅርና በምስጋና ያዘችው " አነጋገሩ እንዳለ በሙሉ ስለሷ ክብካቤና ሐሳብ ነበር አነጋገሩ ሁሉ ከዱሮው የለሰለሰለና የረጋ ስለነበር በዚያች ቅጽበት የቅናት ሐሳቧ ሁሉ ጨርሶ ተረሳ ።
“አርኪባልድ ! ሁልጊዜ እንደምታደርገው ለኔ ብዙ እንደምትጨነቅልኝ አምናለሁ " አለችው "

አባባሏ አልገባውም ቢሆንም ልክ እንደ መጀመሪያው የጋብቻቸው ወራት ወደሱ ሳብ አድርጐ ይዞ ሳማት „ “ ብርቄ ነሽ ሳቤላ ... ለኔ ከምን ጊዜም የበለጠ ብርቄ ነሽ ” አላት።
👍10👏1
ልጆቹ እንዲሔዱ መፍቀዱን ሰማችና ኮርነሊያ ወደሱ እየተንደረደረች ገባች ልጆቹን ከእናታቸው ጋር አንዲሔዱ ማድረማ ማለት ሚስቱ እንዳትድን
ከእነሱ ጋር እየተዳረቀች የባሰ እንድትታመም ማድረግ መሆኑን እንዲገነዘብና ጸጸት ላይ ከመውደቁ በፊት እንዲያስብበት ስትነግረው ፈራ " ልቡ መንታ ሆነ " ሐኪሞቹን ቢማክር ደግሞ የኮርነሊያን ሐሳብ ደገፉ " ሳቤላ ተሸነፈች " ባሏም ሐሳቡን
ለወጠ ልጆቹን ጥላ እንድትሔድ ተገደደች "

ጆይስ... እኔ ዊልሰንን ይዤ እሔዳለሁ አንቺ ከልጆቹ ጋር ትቀሪያለሽ " አየሽ ልጆቼን ይዤ መሔድ ካልቻልኩ ላንቺ ጥያቸው ከመሔድ የተሻለ ምርጫ
የለኝም ለሚስ ካርላይል አልተዋቸውም " ለዊልሰንም ቢሆን አምኜ ልጆቼን አደራ ልሰጣት አልችልም "

“ ለእርስዎ ጥሩ የመሰለዎትን ሐሳብ እቀበላለሁ " ከነሱ ሳልለይ ብከተልዎ እወድ ነበር ነገር ግን ሁለቱን ነገር ባንድ ጊዜ ማድረግ አልችልም "

"ስሚ ጆይስ . . . ጤንነቴንና ጥንካሬዬን እንዳገኝ እንዳገግም ተብሎ ነው ግን በዚያው ልሞት እችላለሁ " ስለዚህ ምናልባት እንደ ወጣሁ ብቀር ከልጆቼ ጋር እንዳትለዪ ቃል ልትገቢልኝ ትችያለሽ ?

ጆይስ አንድ ስሜት በደም ሥሮቿ ተፍላከለከባት » ልቅሶዋ መጣባት ዕንባዋ ተናነቃት ነገር ግን እንደ ምንም ብላ ዋጠችው ድምጿን በብዙ ጥረት አስተካክላ
“ እሜቴ . . ድነው እንደ ድሮዎ ሆነው ይመለሳሉ " እርስዎም ለመዳን ተስፋ እንደሚያደርጉ እንጂ ለተስፋ መቁረጥ በር እንደማይሰጡ ተስፋ አለኝ ” አለቻት ጆይስ "

“ በርግጥ ተስፋ አደርጋለሁ » ቢሆንም በጣም ስለ ታመምኰ የምሆነውን አላውቅም " ስለዚህ ምናልባት የመጨረሻ ክፉ ነገር ቢያኘኝ ስለ ልጆቼ ነገር ቃል
ግቢልኝ ”

“ እኔ እስከ ተፈቀደልኝ ድረስ ጥያቸው አልሔድም " ከእርስዎ የተቀበልኰትን አደራ እጠብቃለሁ"

በይ አደራ ራሪላቸው እዘኝላቸው ውደጃቸው ከሚደርስባቸው የጭካኔ ነገር ሁሉ ጠብቂያቸው " አለቻት ስለ ኮርኒሊያ ካርላይል እያሰበች አንዳንድ ጊዜም ስለ ምስኪኒቱ እናታቸው አጫውቻቸው

“ እሺ ያሎኝን ሁሉ እፈጽማለሁ " አለቻትና ሳቤላ ስትወጣላት ጆይስ እንደ ተቀመጠች ልቅሶዋን ለቀቀችው ".....

💫ይቀጥላል💫
👍12😢4🤔2
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የክሪስቶፈርፍለጋና ውጤቶቹ

ድንገት የሆነ እጅ ትከሻዬን እየወዘወዘ ቀሰቀሰኝ! በድንጋጤና በመርበትበት እናቴ መሆኗን እንኳን መለየት ያልቻልኳት ሴት ላይ በፍርሀት አፈጠጥኩ::
መልሳ አፍጥጣብኝ እጅግ በተቆጣ ድምፅ “ወንድምሽ የት ነው?" ስትል ጠየቀችኝ፡፡

በጣም ከቁጥጥር ውጪ ሆና ስትናገር ስሰማት እንዳትመታኝ እየተሸማቀቅኩ አይኖቼን ክሪስቶፈር ወደሚተኛበት አልጋ ወረወርኩ ባዶ ነበር። አምላኬ
በጣም ብዙ ቆይቷል።

መዋሸት ይገባኝ ይሆን? ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄዷል ብዬ ልከላከልለት? አይሆንም እቺ እናታችን ናት፤ ትወደናለች… ትረዳናለች… “ክሪስ እዚህ ፎቅ
ላይ ያሉ ክፍሎችን ለማየት ወጥቷል” አልኩ።

ግልፅነት መልካም ነው አይደል? እርስ በርሳችን ተወሻሽተንም ሆነ ለእናታችን ዋሽተን አናውቅም፡ የምንዋሸው ለአያትየው ነው እሱም አስፈላጊ ሲሆን ብቻ።

“የተረገመ! የተረገመ! የተረገመ! ስትል እየጮኸች ወደ እኔ ባተኮረ አዲስ የቁጣ ማዕበል ነደደች ውዱ ትልቁ ልጇ፣ ከሁሉም የምታስበልጠው ልጇ፣ የዲያብሎስ ተፅዕኖ ካላረፈበት በስተቀር በጭራሽ አይከዳትም፡ ትከሻዬን ይዛ ልክ እንደሚራገፍ ጨርቅ አራገፈችኝ፡፡

“በማንኛውም ሁኔታ ሁለተኛ አንቺና ክሪስቶፈር ከዚህ ክፍል እንድትወጡ አልፈቅድላችሁም ሁለታችሁም ቃላችሁን ሰጥታችሁኝ ነበር ግን ቃላችሁን
አጠፋችሁ አሁን ታዲያ እንዴት ላምናችሁ እችላለሁ ላምናችሁ የምችል መስሎኝ ነበር የምትወዱኝና በፍፁም የማትከዱኝ ይመስለኝ ነበር!”

አይኖቼ ፈጠጡ እኛ ነን የከዳናት? እንደዚህ አይነት ሁኔታ ስላሳየችን
ደንግጫለሁ። ለእኔ እሷ የከዳችን ነው የመሰለኝ፡

“እማዬ ምንም መጥፎ ነገር አልሰራንም: የተደበቅንበት ቦታ የቆየነው በፀጥታ ነበር፡ ሰዎች በዙሪያችን ሲመጡና ሲሄዱ ነበር፡ ግን ማንም እዚያ መሆናችንን አላወቀም ማንም እዚህ እንዳለን አያውቅም: ሁለተኛ ከዚህ
አላስወጣችሁም ማለት አትችይም ከዚህ ልታስወጪን ግድ ነው፡ ለዘለዓለም እዚህ ውስጥ ልትደብቂንና ልትቆልፊብን አትችይም:” ምንም መልስ ሳትሰጠኝ በእንግዳና በንቀት አይን ተመለከተችኝ፡፡ በጥፊ የምትመታኝ መስሎኝ ነበር
ግን አላደረገችውም ትከሻዬን ለቀቀችኝና ለመውጣት ፊቷን አዞረች።

ልክ ክፍሉን ለቃ ወጥታ ራሷ ልትፈልገው ስትል በሩ ተከፈተና ወንድሜ ሹክክ ብሎ ወደ ውስጥ ገባ:: በሩን ለቀቀና ዞሮ ወደ እኔ ተመለከተ። ከዚያ ለመናገር ከንፈሩን አላቀቀ: የዚያን ጊዜ እናታችንን ሲመለከት እጅግ እንግዳ የሆነ ስሜት ፊቱ ላይ ታየ።

ለምን እንደሆነ ባላውቅም፣ እንደ ሁልጊዜው እናታችንን ሲያይ አይኖቹ በደስታ አልበሩም።

እናታችን በቅፅበት አጠገቡ ደረሰችና አንዴ በጥፊ አላሰችው: የንዴቷ ብዛት ከድንጋጤው ሳይመለስ ግራ እጇን አነሳችና ሌላኛው ጉንጩ ላይ በጥፊ
መረገችበት።

የክሪስ የገረጣ ፊት ሁለት ትልልቅ ቀያይ ምልክቶች አወጣ።

“ክሪስቶፈር ፎክስወርዝ፣ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት ነገር ብታደርግ እኔ ራሴ ነኝ የምገርፍህ! አንተን ብቻ ሳይሆን ካቲንም ጭምር” ክሪስ የተፈጥሮ ቀለሙ ጠፍቶ ፊቱ በጥፊ የተመታበት ምልክቶች የደም አሻራዎች ሆነው
ይታዩ ነበር የራሴ ደም ወደ እግሬ ሲወርድ ከጆሮዎቼ ኋላ የሚያቃጥል ስሜት ተሰማኝ
ጥንካሬዬ እያነሰ መጥቶ እንግዳ እየመሰለች የመጣችው ሴት ላይ አፈጠጥኩ።

ልክ እንደማላውቃትና ለማወቅም ግድ የሌለኝ አይነት ሴት ሆነችብኝ፡ እውነት ይህቺ ሁልጊዜ በደግነትና በፍቅር የምታነጋግረን እናታችን ናት? ረጅም ጊዜ ተዘግቶብን በመቆየታችን የሚሰማንን ስሜት እጅግ ትረዳን የነበረችው
እናታችን ናት? ቤቱ እንደዚህ እንድትሆን የሆነ ነገር አደረጋት ይሆን? ፈጥኖ የመጣልኝ ሀሳብ ይሄ ነው ...ትንንሾቹ ነገሮች ሁሉ ተደምረው እንድትለወጥ አደረጓት
የሚለው፡ በፊት እንደምታደርገው ብዙ ጊዜ አትመጣም: መጀመሪያ አካባቢ እንደምታደርገው በቀን ሁለት ጊዜ ወይም በየቀኑ አትመጣም አሁን የምናምንበትና የምንጠጋበት ነገር ሁሉ ከእግራችን ስር ሾልኮ፣ ሁሉን ነገር አጥተን አሻንጉሊቶች፣ መጫወቻዎችና ስጦታዎች

ብቻ የቀሩን ስለመሰለኝ ፈራሁ።

በክሪስ የደነገጠ ፊት ላይ ንዴቷን የሚያጠፋ የሆነ ነገር አይታ መሆን አለበት በክንዶቿ አቅፋ የጎዳችውን ለመካስ በጥፊ ተመትቶ የቀላውን ፊቱን
በችኮላና በትንንሹ በመሳም ልታፅናናው ሞከረች። ሳመችው፣ ሳመችው፣ሳመችው ፀጉሩን በጣቶቿ አበጠረች ጉንጮቹን አሻሸች: ጭንቅላቱን ወደ ጡቶቿ አስጠግታ አቀፈችው

“ይቅርታ አድርግልኝ ውዴ” አይኖቿና ድምፅዋ ውስጥ እምባ አለ፡ “ይቅር በለኝ… እባክህ ይቅር በለኝ. ስለ መግረፍ ያወራሁት ከልቤ አይደለም:እንዴት እኔን ልትፈራኝ ትችላለህ? እወድሀለሁ እኮ ታውቃለህ አንተንም
ሆነ ካቲን በጭራሽ አልገርፋችሁም: ገርፌያችሁ አውቃለሁ? ራሴን ስላልሆንኩ ነው እንደዚያ የተናገርኩት። ሁሉም ነገር ባሰብኩት መንገድ
እየሄደልን ስለሆነ ያንን ለማበላሸት ምንም ነገር ማድረግ ስለሌለባችሁ ነው በጥፊ የተማታሁበት ብቸኛው ምክንያት ያ ብቻ ነው።” አለችው:

ፊቱን በመዳፎቿ መሀል ጥብቅ አድርጋ ይዛ፣ የተጨማደደ ፊቱን እያየች ጉንጩ ላይ ሳመችው: የሆነ ስሜት እየተሰማኝ ቁጭ ብዬ በመገረም እየተመለከትኩ ነበር… ግራ ከመጋባቴና ልጅ ከመሆኔ ውጪ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ አላውቅም በዙሪያችን ያለው አለም ግን በሙሉ ያረጀ በጣም
ያረጀ ነበር።

ይቅርታ አደረገላት በእርግጥም ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማወቅ አለብን። “እባክሽ እማዬ፣ ምን እንደሆነ ንገሪን እባክሽ?”

“ሌላ ጊዜ” አለች ወደ ዳንሱ ለመመለስ ጥድፊያ ላይ ነበረች: ሁለታችንንም እንደገና ሳመችን፡ “ሌላ ጊዜ ምናልባት ነገ ሁሉንም ነገር እነግራችኋለሁ"አለችና በችኮላ እየሳመችን የሚያፅናኑ ቃላት ነገረችን: በእኔ ላይ ተንጠራርታ ኬሪን ሳመቻት ከዚያ ወደ ኮሪ ሄዳ ጉንጩን ሳመች።

“ይቅር ብለኸኛል ክሪስቶፈር?”
“አዎ እማዬ፤ ልክ ነሽ እዚሁ ክፍል ነው መቀመጥ ያለብን ለማየት መውጣት አይገባኝም ነበር”
ፈገግ አለችና “መልካም የገና በዓል፣ በቅርቡ አያችኋለሁ:" ከዚያ ወጣችና በሩን ቆልፋ ሄደች።

እዚህ ከመጣን ያሳለፍነው የመጀመሪያው የገና በዓላችን አለቀ: አዳራሹ ውስጥ ያለው ሰዓት ሰባት ሰዓት መሆኑን አመለከተ: በስጦታ የተሞላ
ክፍል፣ ቲቪ፣ የጠየቅነው የቼዝ መጫወቻ፣ የሚሞቁ አዳዲስ ልብሶችና ብዙ የሚበሉ ጣፋጮች ነበሩን፡፡ እኔና ክሪስ ደግሞ አስገራሚ ግብዣ ነበረን
ሆኖም የሆነ አዲስ ነገር ወደ ህይወታችን መጥቷል የማናውቀው አዲሱ
የእናታችን ባህርይ ለአጭር ደቂቃ እናታችን ልክ አያታችንን መስላ ነበር።

በጨለማ አንድ አልጋ ላይ በአንደኛው ጎን ኬሪ፣ በሌላው ጎን ክሪስ ተኝቶ እኔና ክሪስ እጅ ለእጅ ተያይዘናል፡ ጠረኑ ከእኔ የተለየ ነው ጭንቅላቴ ደረቱ ላይ አርፏል። ከሩቅ ወደ ጆሯችን ከሚመጣው በትንሹ ከሚሰማው ሙዚቃ
“ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል ፀጉሬን በጣቶቹ እያፍተለተለ ነበር።

ክሪስ ትልቅ ሰው መሆን በጣም የተወሳሰበ ነገር ነው አይደል?"

“ይመስለኛል”

“ትልቅ ሰው ስትሆን የትኛውንም አይነት ሁኔታ መቋቋም እንደምትችል አስባለሁ መቼም ቢሆን ስህተትና ትክክል ለሆነው ነገር ጥርጣሬ ገብቶህ አያውቅም ትልልቅ ሰዎች እንደኛ ይፍጨረጨራሉ ብዬ አልገምትም
👍33
“ስለ እናታችን እያሰብሽ ከሆነ የምትለውና የምታደርገው የእውነቷን አይደለም እርግጠኛ ባልሆንም አንድ ጊዜ ትልቅ ከሆንሽ በኋላ በሆነ ምክንያት
ወላጆችሽ የሚኖሩበት ቤት ተመልሰሽ መኖር ከጀመርሽ እንደገና እንደልጅ ጥገኛ ትሆኛለሽ ብዬ አምናለሁ ወላጆቿ በአንድ በኩል ይጎትቷታል እኛ በሌላ መንገድ እንጎትታታለን፡ በዚያ ላይ ያንን ባለ ፂም ሰውዬ አግኝታለች። እሱም ወደሱ መንገድ እየጎተታት ይሆናል።”

“እንደገና እንደማታገባ ተስፋ አደርጋለሁ! ያ ሰውዬ ከሚፈልጋት በላይ እኛ እንፈልጋታለን፡”

“ያመጣችልን ቲቪ ሳይቀር አባቷ ሌላ እስኪሰጣት ከመጠበቅና ለራሷ አዳዲስ ልብሶች ከመግዛት ይልቅ ከወራት በፊት ልታመጣልን ትችል ነበር። ሁልጊዜ አዳዲስ ጌጣጌጦች፣ አዳዲስ ቀለበቶች፣ አዳዲስ ሽዋሊያዎችና የአንገት ጌጦች ታደርጋለች ”

የእናታችንን ምክንያት በጣም በዝግታና በጥንቃቄ መግለፅ ጀመረ፡ “ይህንን መንገድ ተመልከቺ ካቲ፡ በመጣን በመጀመሪያው ቀን ቲቪውን ሰጥታን ቢሆን፣ ቀኑን ሙሉ ከቲቪው ፊት ተቀምጠን እንውል ነበር ከዚያ ጣሪያው
ስር ያለው ክፍል ውስጥ ለመንትዮቹ በደስታ የሚጫወቱበት የአትክልት ቦታ
አንፈጥርም ነበር። ምንም ነገር ሳንሰራ ቁጭ ብለን ቲቪ ስንመለከት እንውል ነበር። በነዚህ ረጃጅም ቀናት ምን ያህል እንደተማርን ተመልከቺ ልክ አበቦችና እንስሳት መስራት አይነት ነገሮችን ማለቴ ነው: ስንመጣ ከነበረው የተሻለ ስዕል መሳል ችያለሁ: እና አእምሯችንን ለማሻሻል ያነበብናቸውን መህፍት
ብዛት ተመልከቺ… አንቺም ደግሞ ካቲ… አንቺም በጣም ተቀይረሻል:

“እንዴት? እንዴት ነው የተቀየርኩት? ንገረኝ፡"

በማፈር አይነት ትራሱ ላይ ያለውን ጭንቅላቱን ከጎን ወደጎን አንከባለለ “ተወው፣ ስለኔ ጥሩ ነገር ማለት የለብህም ይሆናል። ግን ይህንን አልጋ ለቀህ ወደራስህ አልጋ ከመሄድህ በፊት ያገኘኸውን ሁሉ ንገረኝ ሁሉን ነገር ሳታስቀር… ያሰብከው እንኳን ሳይቀር አጠገብህ አብሬህ እንዳለሁና
ያየኸውን፣ የተሰማህንና የሰራኸውን ሁሉ አብሬህ ሆኜ እንዳደረግኩ እንዲሰማኝ አድርገህ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።"

ምድር ቤት ባለው በሽተኛ ሰው የሚተዳደረው ይህ ግዙፍ ቤት አስፈርቶታል ከድምፁ ያስታውቃል “እጅግ በጣም ትልቅ ቤት ነው ካቲ፡ በጣም ውድ በሆኑ ዕቃዎች ያጌጡ እጅግ ብዙ ክፍሎች አሉት። ግን አንዳቸውንም
ተጠቅመውባቸው እንደማያውቁ ያስታውቃል። በዚህ ፎቅ ላይ ብቻ አስራ አራት ክፍሎች ቆጥሬያለሁ እና እንደውም የተወሰኑ ትንንሽ ክፍሎችን እየዘለልኩ ሁሉ ይመስለኛል” “ክሪስ” ጮክ ብዬ ጠራሁት “በእንደዚያ አይነት መንገድ አትንገረኝ፡ አጠገብህ እንደነበርኩ እንዲሰማኝ አድርገኝ፡ ከአይኔ ከተሰወርክ ሰከንድ ጀምሮ እንዴት እንደነበር ንገረኝ፡” “እሺ” አለ በረጅሙ እየተነፈሰ፡፡ ሊነግረኝ የማይፈልግ ይመስል ነበር። “በጨለማው ኮሪደር ውስጥ ተደብቀንበት ወደ ነበረበት ቦታ የሚወስደውን አቅጣጫ ይዤ ሄድኩ። ወደ ሰሜን ያሉትን ክፍሎች ማየት አልፈለግኩም: እዚያ ስደርስ ሰዎች እንዳያዩኝ
መጠንቀቅ ነበረብኝ፡ ግብዣው በማለቅ ላይ ነበር።

እናታችንን ለማየት እየፈለግኩ ነበር፡ እና አያቶቻችንን አየኋቸው: ወንዱ አያታችን የደከመው ይመስል ነበር አንዲት ነርስ መጥታ እየገፋች ወሰደችው:: "

“ነጭ ዩኒፎርም ለብሳ ነበር?”

“እና ታዲያ እንዴት ነርስ መሆኗን አውቅ ነበር?”

“እሺ ቀጥል አንድም ነገር እንዳታስቀር "

“እሺ! ወንዱ አያቴ እንደሄደ ሴት አያቴም ወዲያው ሄደች ከዚያ ከአንደኛው ደረጃ መውጫ የሚመጣ ኮቴ ሰማሁ። ማንም ሰው እንደ እኔ ሲፈጥን አይተሽ
አታውቂም:: ሳልታይ በፊት የተደበቅንበት ቦታ መግባት አልቻልኩም ስለዚህ አንድ ጥግ ላይ ተደበቅኩ። በደረጃው ላይ እናታችን ከባለ ጥቁር ፀጉርና ረጅም ፂም ካለው ሰውዬ ጋር ሲወርዱ አየኋቸው"

“ለምንድነው ወደፎቅ የመጡት? ምን እየሰሩ ነበር?”

“ጨለም ያለ ቦታ ስለተደበቅኩ አላዩኝም: እንደምገምተው ያላዩኝ እርስ በርሳቸው በጣም እያወሩ ስለነበረ ነው ብዬ አስባለሁ ያ ሰውዬ እናታችን ክፍል ውስጥ ያለውን አልጋ ማየት ፈልጓል::”

“አልጋዋን? አልጋዋን ማየት ፈለገ? ለምን?”

የተለየ አልጋ ስለሆነ መስለኝ ካቲ። እናም… አሁን ያንን ለረጅም ጊዜ
ስታወሪልኝ የነበረውንና ብዙ የሰማሁለትን አስደናቂ አልጋ የማይበት ጊዜ ነው ሲላት ሰማሁ። በግልፅ እንደሚያስታውቀው እናታችን አሁንም እዚያ
ያስቀመጠችን ቦታ ላይ የተደበቅን መስሏታል፡ ወደዚያ እየተገላመጠች ነበር።ከዚያ ተስማማችና እሺ ባርት ለትንሽ ደቂቃ ብቻ ነው ምክንያቱም እዚህ ብዙ ከቆየን ሁሉም ሰው ይጠራጠራልአለች። ሁሉም ሊያስብ የሚፈልገውን
መገመት አልችልም፡ ምን እንደሚጠረጥሩ ንገሪኝ፡ ለኔ ይሄ ሁሉም ሰው የፈለገውን እንዲያስብ እድል መስጠት ነው አለ እንደዚህ ሲል ስሰማ አናደደኝ፡” እዚህ ቦታ ላይ ክሪስ ዝም አለና ትንፋሹ ከባድና ፈጣን ሆነ።

“የሆነ ነገር ደብቀኸኛል” አልኩት ልክ መቶ ጊዜ እንዳነበብኩት መፅሀፍ ነው የማውቀው፡ “እየተከላከልክላት ነው! ልትነግረኝ ያልፈለግከው የሆነ ነገር አይተሀል! ልክ አይደለህም! እዚህ ቤት ከመጣን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ሁልጊዜ አንዳችን ለአንዳችን ታማኝ እንድንሆንና እውነት ብቻ እንድንነጋገር
ተስማምተን ነበር አሁን ያየኸውን ንገረኝ!”

“አምላኬ!” አለ ጭንቅላቱን አዙሮ አይኖቼን እየሸሸ “የተወሰኑ መሳሳሞች ምን ልዩነት ያመጣሉ?”

“የተወሰኑ መሳሳሞች? ጮህኩ: “እናታችንን ከአንድ ጊዜ በላይ ሲስማት አይተሀል? ምን አይነት መሳም ነበር? እጇ ላይ ነው የሳማት ወይስ የምር አፍ ለ አፍ መሳሳም ነው?”

“ምን ልዩነት አለው?” ሲል ድምፁ እየታፈነበት መለሰልኝ “ምንም ያድርግ ምን እሷ ምንም አልመሰላትም እኔን ግን አመመኝ፡"

እኔንም አሳምሞኛል፡ ባሏ ከሞተ ገና ስምንት ወሩ ነው: ግን አንዳንዴ ስምንት ወርም ልክ እንደ ስምንት አመት ሊሰማን ይችል ይሆን? እና የአሁኑ አስደሳች ከሆነ፣ ያለፈው ምን ዋጋ ይኖረዋል? ክሪስ ያልነገረኝ ብዙ ነገሮች እንደተከናወኑ መገመት ቻልኩ

“አሁን ካቲ፣ ምን እያሰብሽ እንደሆነ አላውቅም እናታችን ግን እንዲያቆም እየነገረችው ነበር፡ ካላቆመ መኝታ ክፍሏን እንደማታሳየው እያስጠነቀቀችው
ነበር::”

“አምላኬ፣ የሆነ ትልቅ ነገር እያደረገ እንደነበር እወራረዳለሁ!”

“መሳሳም ነው” አለ ክሪስ አሻግሮ የገና ዛፉን እየተመለከተ፤ “መሳሳም ጥቂት መተሻሸት ብቻ የእሱንና የእሷን አይኖች እንዲያበሩ አድርጓቸው ነበር::
ከዚያ ያ ልዩ አልጋ በአንድ ወቅት የንጉስ አልጋ እንደነበረ ጠይቋት ነበር።

“በእግዚአብሔር! የንጉስ አልጋ ምን ማለት ነው?”

ክሪስ ጉሮሮውን አፀዳና “ሀብታሞችን የምታስደስት ሴት ተኝታበት ነበር ወይ ማለቱ ነው"

“ማስደሰት ምን አይነት ማስደሰት?”

“ሀብታሞች የሚከፍሉበት አይነት” አለ ፈጠን ብሎ ከዚያ ዝም እንድል እጁን አፌ ላይ አደረገና “እናታችን እንደዚህ አይነት አልጋ ቤት ውስጥ እንደሌለ በእርግጠኝነት ነገረችው: እዚህ ቤት ውስጥ ምንም ያህል ቆንጆ ቢሆን፣ኃጢአት የተሰራበት አልጋ ካለ ማታ እንደሚቃጠል ወይም ከኃጢአት እንዲነፃ ፀሎት እንደሚደረግበት ነገረችው: ይሄ ልዩ አልጋ ደግሞ የአያቷ አልጋ
👍232
እንደሆነና እናታችን ትንሽ ልጅ እያለች ከምንም ነገር በላይ የአያቷ መኝታ ክፍል ውስጥ መሆን ትፈልግ እንደነበር አወራችው: ነገር ግን ወላጆቿ ጥሩ ሰው አልነበረችም የሚሏት የአያቷ መንፈስ እሷንም መጥፎ እንዳያደርጋት በመፍራት እዚያ ክፍል ውስጥ መሆን አይፈቅዱላትም ነበር ከዚያ እናታችን ሳቀች: ሳቋ ምሬት ያዘለ ነበር፡ እና ወላጆቿ አሁን የተበላሸች ስለሆነች ምንም ነገር ቢሆን አሁን ካለችበት የበለጠ እንደማያበላሻት በማመን ክፍሉን
እንደሰጧት ለባርት አጫወተችው ታውቂያለሽ ይህንን ስሰማ መጥፎ ስሜት ተሰማኝ፡፡ እናታችን የተበላሸች አይደለችም:
ተጋብተው ነበር ... እና የተጋቡ ሰዎች በግል የሚያደርጓቸው ነገሮች ደግሞ... አባታችን ይወዳት ነበር ...የማንም ጉዳይ አይደሉም:”

ትንፋሼን እየያዝኩና እየለቀቅኩ ነበር ክሪስ ሁሉንም ነገር ያውቃል
ሁሉንም:

hዚያ እናታችን “አንድ ጊዜ ብቻ አየት አድርጋው ወደ ግብዣው እንመለስ፡ አለችውና ተያይዘው ሄዱ: በዚህ አጋጣሚ የእሷ ክፍል የቱ እንደሆነ እንዳውቅ አደረገኝ፡ ከዚያ ከተደበቅኩበት ጥግ በጥንቃቄ ወጣሁና መጀመሪያ
ወዳየሁት የተዘጋ ክፍል ሄድኩ። ጨለማ ስለሆነና በሩ ስለተዘጋ ማንም አይኖርም ብዬ ፈጥኜ ወደ ውስጥ ገባሁ ከዚያ በሩን በቀስታ ዘጋሁና እዚያ ውስጥ መሆን የሚፈጥረውን ስሜትና ስለ ክፍሉ እንዲሁም እንግዳ ስለሆነው
ጠረን ለማወቅ ቆም አልኩ መብራቱ በርቶ ቢሆን ኖሮ ምናልባት ክፍሉን የሞላውን ያልተለመደና እንግዳ ጠረን አላስተውለውም ነበር። የሚያስፈራ ጠረን ነበር፡ እጅግ ፈርቼ ነበር!”

ምንድነው?” ዝም ሊያስኘኝ የሚሞክረውን እጁን እየገፋሁ
“ምንድነው “ምንድነው ያየኸው?” አልኩት᎓“በጣም ብዙ የተቆረጡ እንስሳት ጭንቅላቶች! በመስኮት የሚገባው ብርሃን ሲያርፍባቸው ጥርሶቻቸው እንዴት እንደሚያስፈሩ! በሆነ ምክንያት አሳዘኑኝ”

እኔ ስለ እንስሳትና ስለተቀመጡበት ክፍል ምን አገባኝ? ማወቅ የምፈልገው
ስለ ሰዎቹ ነው ስለ ሚስጥሮቻቸው፤ ያንን ነው የምፈልገው።

“ቀጥል…”

“ስዟዟር ማንም ስላላየኝ እድለኛ ነኝ፡ ምክንያቱም እያንዳንዱ ክፍል ውስጥ እየገባሁ ነበር በመጨረሻ የእናታችንን ክፍል አገኘሁት ከሁለት ደረጃዎች በላይ ያሉ ሁለት በሮች አሉት እና ወደ ውስጥ ስመለከት ቤተ መንግስት
የማይ መስሎኝ ነበር። ሌሎቹ ክፍሎች በጣም ያማምራሉ። የእሷ ክፍል ግን ከምታምኚው በላይ ነው። የእናታችን ክፍል መሆኑን እርግጠኛ ነኝ።
ምክንያቱም ክፍሉ ውስጥ የአባታችን ፎቶግራፍ ነበረበት ጠረኑም የእሷ ሽቶ ይመስል ነበር። ክፍሉ መሀከል ላይ አይተሽው የማታውቂው ልዩ አልጋ
ተቀምጦ ነበር፡ እዛ ቆሜ አንድ ሰው ይህንን የሚያክል ትልቅና ሰፊ ከላዩ ደግሞ አንዲት ጠባብና ትንሽ ተደራቢ ያለበት አልጋ ለምን እንደሚፈልግ እያሰብኩ እየተገረምኩ ነበር: ትልቁን አልጋ ሳያበላሹ ትንሹ ላይ ሸለብ
ለማድረግ ከመሆኑ ባሻገር አንድ ጥሩ ምክንያት መኖር አለበት ካቲ
እንድታምኒኝ ያንን አልጋ ራስሽ ማየት አለብሽ!"

ከተናገረው በላይ ብዙ እንዳየ አውቄያለሁ። ተመልሶ መጥቶ ሁሉንም ነገር ሳይነግረኝ ስለ አልጋው ብዙ ነገር እንደነገረኝ ገብቶኛል፡

“ይህ ቤት ግላድስተን ከነበረው ቤታችን የበለጠ ያምራል?” ብዬ ጠየቅኩት።ምክንያቱም ለእኔ ስምንት ክፍሎችና ሁለት መታጠቢያ ቤቶች የነበሩት
ቤታችን እጅግ ምርጥ ቤት ነበር፡ አመነታ የሚናገራቸውን ትክክለኛ ቃላት ሲመርጥ ጥቂት ደቂቃዎች ወሰደበት፡ በዚያ ምሽት ቃላቶቹን በጥንቃቄ እየመረጠ መሆኑ ብቻ ብዙ ነገር ይናገራል "ይህ ቤት አያምርም። ግዙፍ ነው ትልቅ ነው ቆንጆ ነው...ግን የሚያምር ብዬ አልጠራውም።

ምን ማለቱ እንደሆነ የገባኝ መሰለኝ ማማር ከግዙፍነት ከሀብታምነት ከቁንጅናና ከትልቅነት ይልቅ ከመሞቅና ከመመቸት ጋር ይመሳሰላል።

አሁን ከደህና እደር በስተቀር የቀረ ነገር የለም።ጉንጩን ሳምኩትና ከአልጋው ላይ እንዲወርድ ገፋሁት። በዚህ ግዜ መሳም ለልጆችና ለሴቶች ብቻ ነው ብሎ አልቀለደብኝም። በፍጥነት ሄዶ ኮሪ አጠገብ ተኛ።

በጨለማው ውስጥ የሚያበሩት የገና ዛፍ ላይ ያሉት ባለቀለም መብራቶች እንባ ባረገዙት የወንድሜ አይኖች ውስጥ ያንፀባርቁ ነበር።

ይቀጥላል
👍375
#ሳቤላ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

..ሚስተር ካርይልና ሳቤላ ዊልሰንን አስከትለው በምዕራብ ፈረንሳይ ቡሎን በምትባል ከተማ ደርሰው ወደ ቤንስ ሆቴል አመሩ " ፒተር የሚስ ካርላይል አሽከር
የነበረ ሲሆን ወደ ኢስትሊን ሲዛወሩ ወደነሱ ዙሮ እንደ ነበር እዚህ መጥቀሱ ተግቢ ይሆናል " ቡሎኝ እንደገቡ ወደ ቤንስ ሆቴል ሔደው ሚስዝ ዱሲ መኖሯን ጠየቁ ቀድማ ዴርሳ ልትቀበላቸውና ሳቤላንም ልታላምድ ታስባ የነበረችው ሚስዝ ዱሲ በቤተሰብ ችግር ምክንያት ወደ ጀርመን መሔዷን ከተወችላት ደብዳቤ ተረዱ"

“ ፊቱንም ቢሆን ማወቅ ነበረብኝ እንደሷ በቃሏ የማትገኝ ሴት የለችም አለች ሳቤላ "

ሚስተር ካርላይልም እሷ ከሌለች ወደ ትሩቪል መሔድ መሻሉን አማክሯት ነበር ሳቤላ ግን አንድ ጊዜ ቡሎኝ ከገባች ከዚያው መቆየቱን መረጠች " እሱም
ቤንስ ሆቴል ግርግር ይበዛበት ስለነበር፡ ጸጥታና ክብር ያለበትን ሆቴል ፈልጎ በኤኩ መንግድ በኩል ከወደቡ አጠገብ አንድ በጣም ጥሩ ሆቴል አገኘና ወዶፈደዚያ ተዛወሩ ወዟ ቶሎ ምልስ ሲል አይቶ ሚስተር ካርላይል ጉዞው ደኅና የረዳት መሰለው እሷም ብርታት እንደ ተሰማት ነገረችው አንድ ቀን ብቻ ውሎ ለመመለስ የመጣውን
የብርታቷ መታደስና የፊቷ መለምለም ሲያይ ስለ ተደሰተ የዚያች ወጭ ወራጅ አላፊ አግዳሚ የበዛባትና የተጨናነቀችውን ከተማ ሁኔታ እያየ ጭምር ሦስት ቀን አደረ።

“ እኔ እዚህ ከማንም ጋር ለመተዋወቅ አልፈልግም
አለችው ሳቤላ ከወደቡ መድረክ አንድ ጫፍ ላይ ተቀምጠው ባጠገባቸው እየተጋፉ ሲያልፉ የነበሩትን ብዙ ደስተኛ ሥራ ፈቶችን እየተመለከቱ "

“ በደፈናው እንደዚህ ማለቱ እንኳን ደግ አይሆንም ” አላት ሲመልስላት እንዳጋጣሚ የምታውቂው ሰው ታገኚ ይሆናል " ብዙ ዐይነት ሰዎች ወደዚህ
ይመጣሉ አንዳንዶቹ ሐቀኞችና የተከበሩ ሆነው ለተከበረ ዓላማ ይመጣሉ አንዳንዶቹ ደግሞ በተግላቢጦሹ በመጥፎ ጠባያቸው ዕዳና ዱቤ በማብዛታቸው ኢንግላንድ ውስጥ መኖር ስለአልቻሉ ካገር እየሸሹ በሀብት የከበሩና የቅዱሳን ኑሮ የሚኖሩ መስለው የሚታዩ አጭበርባሪዎች ናቸው "

“ አንተ ወደ ባሕር ማዶ እንኳን መጥተህ አታውቅም እንዴት ታውቃቸለህ.. አርኪባልድ ?”

“ ቦታውን ከሚያውቁ ብዙ ሰዎች ጋር እገናኛለሁ ለምሳሌ ባክስታንን ተመልከቼው እሱም አይቶኛል " ወደፊት በመምጣት ወይም ወደ ኋላ በመሸሽ መካከል ሊቆርጥ አልቻለም ።

"ማን ? የቱ ነው እሱ ?”

“ ያ ረጂም ጸጉረ ቀይ ደኅና ልብስ ለብሶ በሰዓቱ ማሰሪያ ብዙ ጌጥ ያንጠለጠለው " ሚስቱ ደግሞ ከሌሎች ሴቶች ጋር ሆና ስትከተለው ተመልከቻት
የለበሰችው ልብስ ያጠለቀቻቸው ሐብሎችና በእጅዋ ያደረገቻቸው አምባሮች ሁሉ ሰው አማኝ ከሆኑ ነጋዴዎች በማጭበርበር የተወሰዱ ናቸው " እዚህ ባለው የእንግሊዝ ኅብረተሰብ መኻል ግን ትልልቅ ስዎች መስለው ለመታየት እንደሚሞክሩ አይጠረጠርም ደከመሽ እንዴ ? አላት ።

"አዎን ትንሽ ! እንግዲህ ወደ ቤት ብገባ ይሻለኛል "

ከወደቡ መድረክ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ቀስ እያሉ ሲወርዱ በጠቅላላ ሁኔታቸው ዐይነ ገቦች ሆኑና ብዙ ሰው አተኩሮ ይመለከታቸው ጀመር "

በበነጋው ጧት በሁለት ሰዓት በሚነሣው ጀልባ ወደ ኢንግላንድ ለመመለስ ሲሰናበታት : “ ደኅና ሁኚ . . . የኔ ፍቅር” አላትና ዝቅ ብሎ ከሳማት በኋላ “ራስሽን ጠብቂ አላት ።

“ ልጆቼን ሳምልኝ ... አርኪባልድ እና እ ... እና .. እ. እ” “ እና ምን ? ” አላት “ ሰዓት ደረሰብኝ ”

“ እኔ አለመኖሬን አይተህ ከባርባራ ሔር ጋር እንዳትዳራ ” አለችው የቀ
ለደች መስላ " እሱም እንደ ቀልድ ወሰደውና እየሣቀ ወጣ አነጋሯ ከልቧ መሆኑ አልገባውም "

ሳቤላ ተነሥታ ለቁርስ እንደ ተቀመጠች የቀሩትን ሳምንቶች እንዴት እንደ ምታሳልፋቸው ጨንቋት ትተክዝ ጀመር ። ከደሬሰችበት ቀን ጀምሮ ሁለት ጊዜ ከባሕሩ ሔዳ ታጥባ ነበር : ግን ጭንቀትና እንቅጥቅጥ ለቀቀባትና የሚስማማት ስላልመሰላት አቋረጠችው "

አየሩ በጣምደስ የሚል ስለነበር ማታ ከባሏ ጋር ካመሹበት የወደብ መድረክ ዘልቃ ለመሞከር አሰበች " ስለዚህም ፒተርን አስከትላ ሔዳ ከተቀመጠች በኋላ አንድ ሰዓት ቆይቶ እንዲመጣ ነግራ መለሰችው እሷ ከዚያ የተለያዩ ተላላፊዎችን ትመለከት ጀመር " አንድ እግረ በሺተኛ ሰውዬ በጨርቅ ማማ ሲሔድ አየች " ቀጠሉና ሦስት ቆነጃጂት ከሞግዚታቸው ጋር ብቅ አሉ ከዚያ ዴግሞ ዳንዴ ዳንዴ የሆኑ ጎረምሶች የአደን ጃኪት ለብሰው መነጽር አድርገው መጡ ሳቤላን ትንሽ ትኩር አድርገው ካዩዋት በኋላ ዐልፈው ሔዱ " ከነሱ በኋላ ትንሽ ቆይቶ ደግሞ ከሁኔታው ትልቅ ሰው የመሰለ · አንድ ረጂም መልከኛ ሰውዬ ዘለቀ » ሳቤላ
ገና ስታየው ዐይኖቿን ጣለችበት " ያ እስከዚያ ድረስ ገና ከልቧ ያልጠፋው ሰው መሆኑን ስታይ ' የጠቅላላ ሰውነቷ ሥሮች ተርገፈገፉ።

ካፔቴን ሌቪስን በበኩሉ ገና ሲያያት እንዴት ያለች ቆንጆ ነች ? ማን ትሆን?” እያለ ወደ ተቀመጠችበት መድረክ አድናቆቱንና አክብሮቱን በግንባሩ እየገለጸ ሲጠጋ ማን መሆኗን አወቃት ወዲያው ባርኔጣውን አንሥቶ' ፊቱ በፈገግታ ፈክቶ
እጁን ለሰላምታ እየዘረጋ፡ “ ከእመቤት ሳቤላ ቬን ጋር እንደገና ለመገናኘት እንደታደልኩ አልጠራጠርም ” አላት

እሷም መንፈሷ ተሸብሮ የምትናገረው ጠፋት » እጅዋን ለሰላምታ ስትዘረጋላት ጥቂት ቃሎች በማልጐምጐም መለሰችለት "

ይቅርታ አድርጊልኝ ... እመቤት ሳቤላ ፡ ካርላይል ማለት ነበረብኝ ከተለያየን ብዙ ጊዜ ሆነና አሁን እንዲህ ድንገት ሳገኝሽ ጊዜ ከደስታዬ ብዛት የተነሣ
አንቺን ያሰብኩሽ ልክ ያን ዘመን እንደ ነበርሽው አድርጌ ነው "

እንደገና ተቀመጠች " በስሜት ፍላት ጉንጮቿን አልብሷት የነበረው ቅላት ቀስ በቀስ ለቀቀ " ፍራንሊዝ ሌቪሰን ከዚያ በፊት ካያት ጀምሮ እንደሷ ያማረ ፊት
አይቶ የሚያውቅ አልመሰለውም።

ከዚህ ምን እግር ጣለሽ ?” አላት ከጐኗ እየተቀመጠ ።

አመመኝና ወደ ባሕር ዳርቻ እንድሔድ ታዘዝኩ ሚስዝ ዱሊን ከዚህ እናገኛታለን ብለን ባንጠብቅ ኖሮ አንመጣም ነበር ሚስተር ካርላይልም አብሮኝ መጥቶ ሦስት ቀን ቆየና ዛሬ ጧት ተመልሶ ሔደ „

ሚስዝ ዱሲማ ወደ ኤምዝ ሄዶች እነሱን ዐልፎ 0ልፎ አያቸዋለሁ
ለጥቂት ጊዜ ፓሪስ ተቀምጠው ነበር " እውነትም የታመምሽ ትመስያለሽ ልጄ " ኣላት አስተዛዝኖ “ በጣም ታመሻል " እኔ የምረዳሽ ነገር አለ ?

እሱን ስታይ ድንገት የያዛት ድንጋጤና የመንፈስ መረበሽ እየለቀቃት ሲሔድ ደም መስሎ የነበረው ፊቷ ዐመድ ሲያለብሰው ከመጠን በላይ የታመመች
መምሰሏን ለሷም ታውቋት ነበር ። ከሱ ጋር ስለ ተገናኘች መንፈሷ በመረበሹ በራሷ በጣም ተናደደች እስከዚያች ቅጽበት ድረስ ለፍራንሲዝ ሌቬስን የተዳፈነ ስሜት ይዛ መኖሯን አልታወቃትም ነበር።

“ምናልባት በጥዋት ለመምጣት በመድፈሬ ይሆናል " አለችው እንዳዲስ ያመማት ለመምሰሏ ምክንያት ስትሰጥ “ ልመለስ መሰለኝ " አሽከሬን አገኘዋለሁ " ደኅና ዋል .. . ካፒቴን ሌቪሰን”

ግን ብቻሺን በእግርሽ ችለሽ መሔድ የምትችይ አትመስይም ስለዚህ ከቤትሽ ድረስ እንድሸኝሽ ፈቃድሽ ይሁን "

ድሮ ሲገናኙ ያደርገው እንደ ነበረው ክንዷን ሳብ አድርጎ ከብብቱ አስገብቶ
ከወደቡ መድረክ እየደገፈ አወረዳት በርግጥ ከሱ ጋር እንዶዚያ ተያይዛ መሔዱ'
ደግ ያለ መሆኑ ቢታወቃትም እሱም የቤተሰቧ ዘመድ ብዙ ስለሆነ ክንዷን ለመከልከል የምትሰጠው ምክንያት አልተገለጸላትም
👍11🔥1🥰1
“ ወይዘሮ ማውንት እስቨርንን በቅርቡ አይተሻት ታውቂያለሽ ?” አላት"

“ጥቢው ላይ ከሚስርተ ካርላይል ጋር ለንደን ሔጀ ሳለ አይቻት ነበር " አንጻጻፍም ሎርድ ማውንት እስቨርን ግን ኢስት ሊን ድረስ መጥቶ አይቶናል " እስከ
ዛሬም ገና ለንደን ሳይሆኑ አይቀሩም"

“ እኔ ግን እነሱንም ኢንግላንድ ካየሁዋቸው ዐሥር ወር ዐለፈኝ እስከ ዛሬ ፓሪስ ነበርኩ " ወደዚህ የመጣሁት ገና ትናንት ነው ። ”

ረጅም የፈቃድ ጊዜ ነው ያገኘኸው ማለት ነው ?”

ከውትድርና እኮ ወጥቻለሁ ነገሩ እንዴት መስለሽ እመቤት ሳቤላ ..
ላንቺ እውነቱን ብነግርሽም ግድ የለኝም በአሁኑ ጊዜ ኑሮ አልተሳካልኝም" አጎቴም የሚያሳሳር ነገር ፈጸመ " እንደገና ሚስት አገባ !!”

“ አዎን ሰር ፒተር ማግባታቸውን እኔም ሰምቻለሁ

ሰባ ሦስት ዓመቱ እኮ ነው ጽ የሞተ ሽማግሌ ይህ አድራጎቱ ደግሞ የኔን የሀበት ተስፋ ያቃውሰዋል “ ምናልባት ሚስቱ ወንድ ልጅ ልትወልድለት
ትችላለች " ይኸን በመፍራት ባለዕዳዎቼ ሁሉ ተነሡብኝ " የማዕረጉ " የሀብቱና ርስቱ ወራሽ መሆኔን በማወቅ የፌለግሁትን ያህል ብድር ሲሰጡኝ ኖሩና " አሁን የሱ ጋብቻ በጋዜጦች ሲወጣ ክብሬ ተገፈፈ ተዋረድኩ ዱቤ ተከከልኩ "ያለብኝን
ዕዳ እንድከፍል ተጠየቅሁ " ስለዚህ ኮበለልኩ ወደ ባሕር ማዶ መጣሁ

"ባለዕዳዎችህን ከዚያዉ ጥለህ ?''

ሌላ ምንም ማድረግ አልቻልኩም አጎቴም ሊከፍላቸው አልፈለም :
ወይ ደግሞ አበሌን አልጨመረልኝም

" አሁን ያለህ ተስፋ ምንድነው ?"

"ተስፋ ? ያ እዚያ ወደ ወደቡ ድንጋይ የሚወረውረው ድሪቶ የለበስ ልጅ ይታይሻል ? ፖሊሶች ካልደረሱበት ዕድለኛ ነው " ተስፋው ምን እንደሆነ ብትጠይቂው ዐይኑን አፍጦ ያይሽና ምንም ይልሻል የኔም ተስፋ እንደሱ ነው "

• የሆነው ሁኖ ሰር ፒተርን ትተካቸው ይሆናል "

ሊሆንም ላይሆንም ይችላል እነዚህ ደደብ ሽማሌዎች ወጣት ሚስት ሲያገቡ

“ ከሰር ፒተር ጋር ተጣልተሃል ?''

የሚጠቅም ቢሆን ኖሮ መጣላት ነበረብኝ አየሽ የራስን ጥቅም መጠበቅ አስፈላጊ ነው ስለዚህ ያቺን የሚሰጠኝን አበልም እንዳትቋረጥብኝ ስለፈራሁ
ልጣላው አልፈለግሁም "

"ቡሎኝ ውስጥ ብዙ ለመቆየት ታስባለህ ?

" እንጃ ከዚህ እንደማገኘው ደስታ ነው ፓሪስ ሞቅ ሞቅ ያለ ከተማ ነው እዚህ የመጣሁት በባሕሩ ውሃ ለጥቂት ቀን ልታጠብ ብዬ ነበረ ... ሮጥኩብሽ መሰለኝ ?"

“ ስለ ሰር ፒተር ጋብቻ እያወጋህ የኔን ደካማነት ረሳኸውና በጣም ፈጠንክ ነገር ግን ምን ያህል እንደ ተሻለኝ ለመገመት ስለ ቻልኩ ጥሩ ነው የዛሬ ሳምንት ይህን ያህል መሔድ አልችልም ነበር "

ከሆቴሏ አዶረሳትና እንዲገባ ሳይጠየቅ ዝም ብሎ ገብቶ ለሩብ ሰዓት ያህል ሲያጫውታት ቆይቶ ለመሔድ ሲነሳ “ምናልባት ኋላ ለመውጣት ያሰብሽ እንደሆነ
አሽከር አስከትለሽ ከመዞር እኔ ስለምሻልሽ እንድረዳሽ ፍቀጅልኝ " ሚስተር ካርላይል ሲመጣም ያደረግሁልሽን ዕርዳታ ሲሰማ በጣም ደስ ይለዋል ”

የሌቪሰን አቀራረብና አነጋገር በቅንነት ለመርዳት ይመስል ነበር እሷም ያ ተዳፍኖ የኖረውና አሁን ጨርሶ የጠፋ አስመስላ እፍን ድፍን አድርጋ በመያዝና
ለወደፊትም በዚያው ዐይነት ልትቈጣጠረው እንደምትችል በማመን ' የካፒቴን ሌቪሰንን ቀረቤታ በትዕግሥት ለመቀበል ወሰነች "......

💫ይቀጥላል💫
👍21
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ሶስት

ማደግ፣ ብልህ መሆን

ልክ እንደ መጀመሪያው አመት ሁሉ ሌላኛውም አመት አለፈ እናታችን ልትጎበኘን የምትመጣበት ቀን እየቀነሰ መጣ ከስንት አንድ ጊዜ ስትመጣም
ሁሌም ከዚህ ለመውጣት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደቀሩን እንድናምንና ተስፋ እንድናደርግ የሚያደርገን ቃል ትገባልናለች። በእያንዳንዱ ምሽት መጨረሻ ላይ የምናደርገው ነገር ቢኖር የቀን መቁጠሪያው ላይ በትልቁ
የኤክስ ምልክት ማድረግ ነው።

አሁን ትላልቅ ቀይ የኤክስ ምልክቶች ያሉባቸው ሶስት የቀን መቁጠሪያዎች አሉን፡ የመጀመሪያው በግማሽ ብቻ ቀይ የኤክስ ምልክት የተደረገበት ነው።
ሁለተኛው ሙሉ በሙሉ ምልክት ተደርጎበታል፡ ሶስተኛው ደግሞ ግማሹ በኤክስ ምልክት ተሞልቷል፡ እየሞተ ያለው አያታችን አሁን ስልሳ ስምንት
አመት ሆኖታል። ሁልጊዜም የመጨረሻ ትንፋሹ ነው እየተባለ እኛ በተረሳ ቦታ እየተጠባበቅን እሱ ግን አሁንም መኖሩን ቀጥሏል ስልሳ ዘጠኝ አመት
እንዲሆነው እየኖረ ይመስላል።

ሀሙስ ሀሙስ በፎክስወርዝ ቤት ውስጥ ያሉ ሠራተኞች ወደ ከተማ
የሚሄዱበት ቀን ነው፡ እኔና ክሪስቶፈር ጥቁሩ ጣራ ላይ ወጥተን ጋደም በማለት የፀሀይ ብርሃን የምናገኘውና ከጨረቃና ከኮከቦች ስር ሆነን አየር
የምንቀበለው እነሱ በሚወጡ ጊዜ ነው በጣም ከፍ ያለና አደገኛ ቢሆንም ንፁህ አየር የተጠማው ቆዳችንን ማስታገስ የምንችልበት ብቸኛ ቦታ ቢኖር ጣሪያው ብቻ ነው።

እግራችንን በጭስ ማውጫው በኩል የሁለቱ ቤቶች ጣራዎች የሚገናኙበት ጥግ ላይ ስናደርግ ደህንነት ተሰማን የተደበቅንበት ቦታ መሬት ላይ ካለው ሰው ሁሉ ይከልለናል: የአያትየው ቁጣ ገና መተግበር ስላልጀመረ እኔና
ክሪስ ግዴለሾች ሆነን ነበር መታጠቢያ ቤት የምንጠቀመው ሁሌ ተጠንቅቀን አይደለም። አንዳንዴ ልብሶቻችንን ሙሉ በሙሉ ላንለብስ እንችላለን አንድ
ክፍል ቤት ውስጥ ውለን እያደርን ሁልጊዜ ውስጣዊ የአካል ክፍሎቻችንን ከተቃራኒ ፆታ ሚስጥር ማድረግ ከባድ ነበር።

እውነቱን ለመናገር ማንኛችንም ማን ምን እንዳየ ግድ አልነበረንም።

ግድ ሊኖረን ግን ይገባ ነበር

መጠንቀቅ ነበረብን መቼም ቢሆን የእናታችንን በአለንጋ የተተለተለ ጀርባ መርሳት አልነበረብንም።
እናታችን የተገረፈችበት ጊዜ እጅግ ሩቅ፣ የዘለአለም ያህል የራቀ ሆኖ
ተሰምቶን ነበር።

አሁን እስካለሁበት አስራዎቹ የእድሜ ክልል ድረስ አንድም ቀን የራሴን እርቃን ሙሉ በሙሉ አይቼው አላውቅም: እርቃኗን የሆነች ሴት በስዕልም
እንኳን አይቼ አላውቅም ከእምነበረድ የተሰሩ እርቃን ሀውልቶች አይቼ የማውቅ ቢሆንም እነሱ ግን ሁሉንም አያሳዩም።

ስለዚህ እርቃኔን ለማየት መስታወት ፈለግኩ። የመድኃኒት ማስቀመጫው ቁምሳጥን ላይ ያለው መስተዋት ከፍ ብሎ የተሰቀለ ስለሆነ በደንብ አያሳይም፡ ስለዚህ ሙሉ በሙሉ እርቃን ሆኜ ራሴን ለማየት ክፍሉ ውስጥ ብቻዬን እስክሆን መጠበቅ አለብኝ ከዚያ ከመልበሻው መስታወት ፊት እርቃኔን ቆሜ እንደፈለግኩ አተኩሬ እመለከታለሁ። በራሴ ሰውነት እደሰታለሁ፣ አደንቃለሁ።

ተሳካልቶልኝ መኝታ ክፍላችን ውስጥ ያለው መስተዋት ፊት ለፊት እርቃኔን ቆምኩ የሆርሞኖች መለወጥ ያመጣው ነገር የሚገርም ነው! በእርግጠኝነት
እዚህ ስመጣ ከነበርኩት በላይ በጣም ቆንጆ ሆኛለሁ። ፊቴን፣ ፀጉሬን፣ እግሮቼን፣ እንዲሁም ደረቴን እያየሁ ነው: ከአንድ ጎን ወደ ሌላ ጎን እየተሽከረከርኩ መስታወቱ ላይ ያለውን ምስሌን እያደነቅኩ ነው። በራሴ
ተመስጫለሁ።

የሆነ ሰው ከጀርባ እየተመለከተኝ እንደሆነ ስለተሰማኝ ድንገት ስዞር ክሪስ ቁም ሳጥኑ የፈጠረው ጥላ ውስጥ ቆሞ ሲያየኝ ያዝኩት: ጣሪያው ስር ካለው
ክፍል እየመጣ ነበር እዚያ ቆሞ የነበረው ለምን ያህል ጊዜ ይሆን? ሳደርግ የነበረውን እርቃንን የማየት ብልግና አይቶ ይሆን? አምላኬ እንዳላየ ተስፋ
አለኝ:

ክሪስ በቆመበት ደንዝዟል፡ ልክ ከዚህ በፊት አይቶኝ እንደማያውቅ ሁሉ ሰማያዊ አይኖቹ ላይ የተለየ ብርሀን ይታይ ነበር፡ ምናልባት እርቃናችንን ሆነን ፀሀይ ስንሞቅ መንትዮቹም አብረውን ስለሚሆኑ ሀሳቡን ወንድማዊና ንፁህ ያደርግ ስለነበረ አፍጥጦ አያየኝም ነበር ማለት ነው።

አይኖቹ በእፍረት ቀልተው፣ ከፊቴ ወደታች ወደ ጡቶቼ ከዚያ ወደ ታች...ወደ ታች ሄደው እግሮቼ ጋ ደረሱና እንደገና በዝግታ ወደ ላይ ተመለሱ።

በፈለገ ጊዜ እንዴት ማሾፊያ እንደሚያደርገኝ ጠንቅቆ በሚያውቀው ወንድሜ
አይን አጉል ስርአት አጥባቂ ሆኜ ላለመታየት ምን ማድረግ እንዳለብኝ እርግጠኛ ባለመሆን እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ፡ ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀው አይነት እንግዳና ትልቅ ሰው መሰለኝ፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ሰውነቴን ለመሸፈን ብንቀሳቀስ ለማየት የተራበውን ነገር የምነጥቀው ይመስል
የደከመው፣ የፈዘዘና ግራ የተጋባ ይመስል ነበር።

እዚያው እንደተገተረ ሰአቱም የቆመ ይመስል ነበር። እኔም አይኖቹ ከኋላ መስታወት ውስጥ የሚያንፀባርቀውን ምስል በውስጣቸው ለማስቀረት ሲሞክሩ
ስመለከት እያመነታሁ “ክሪስ እባክህ ሂድ” አልኩት።

የሰማኝ አይመስልም ዝም ብሎ አፍጥጠጧል በጣም አፈርኩ ብብቴ ስር እርጥበት ተሰማኝ፡፡ ልቤም እንግዳ በሆነ ሁኔታ
መምታት ጀመረ፡ እጁን ስኳር የሚቀመጥበት ዕቃ ውስጥ ሲከት እንደተያዘ ህፃን ልጅ የሆንኩ መሰለኝ፡ ይሁንና አስተያየቱና አይኖቹ ወደ ህይወት
መለሱኝና ልቤ በሚያስፈራ ሁኔታ በከባዱ መምታት ጀመረ፡ በፍርሀት
ተሞላሁ: ለምንድነው የፈራሁት? ክሪስ እኮ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የምር የሆነ እፍረት ተሰማኝ፡ ከዚያ ፈጠን ብዬ ያወለቅኩትን
ቀሚሴን ብድግ አደረግኩ: በዚህ ራሴን መከለልና እንዲሄድ መንገር እችላለሁ።

“ተይ” አለኝ፡ ቀሚሱን በእጄ እንደያዝኩ

“አንተኮ…” ተንተባተብኩ የበለጠ ተንቀጠቀጥኩ፡

“አውቃለሁ ማየት እንደሌለብኝ፡ ግን ደግሞ በጣም ቆንጆ ነሽ፡ ከዚህ በፊት አይቼሽ የማውቅ ሁሉ አልመሰለኝም: አብሬሽ ውዬ እያደርኩ እንዴት እንደዚህ ቆንጆ ሆነሽ ስታድጊ አላስተዋልኩም?"

እሱን ከመመልከትና በአይኖቼ ከመለመን በቀር እንደዚህ አይነት ጥያቄ እንዴት ይመለሳል? ይሄኔ ከኋላዬ በበሩ የቁልፍ ማስገቢያ መክፈቻ ቁልፉ ሲገባ ሰማሁ። አያትየው! ከመግባቷ በፊት በፍጥነት ቀሚሴን በጭንቅላቴ
አጥልቄ ወደታች ጎተትኩት። አምላኬ! እጅጌውን ማግኘት አልቻልኩም ጭንቅላቴ በቀሚሱ ተሸፍኖ ሌላው ሰውነቴ ግን እርቃን ሆኖ ነበር። እናም አያትየው አጠገቤ ነች! ላያት ባልችልም ግን ተሰምቶኛል!

በመጨረሻ እንደምንም እጅጌውን አስገባሁና ቀሚሴን ወደታች ሳብኩት። ነገር ግን እነዚያ ግራጫ ድንጋይ አይኖቿ ውስጥ እርቃኔን በደንብ እንደተመለከተችኝ
አይቻለሁ አይኖቿን ከእኔ ላይ አንስታ ክሪስን ዘልቆ የሚወጋ በሚመስል አይነት አፈጠጠችበት፡ እንደፈዘዘ ነው። “በመጨረሻ ያዝኳችሁ! ፈጠነም ዘገየም እንደምይዛችሁ አውቅ ነበር!” አለች:

ይህ ልክ ከቅዠቶቼ እንደ አንዱ ነው... ልብስ ሳልለብስ በአያትየውና በእግዚአብሔር ፊት
ክሪስ ከቆመበት ጥግ ወጣና መልስ ለመስጠት ወደፊት ተራመደ። “ያዝሽን?
ምንድነው የያዝሽው? ምንም:”

ምንም...
ምንም...
ምንም...

የሚያስተጋባ ድምፅ፡፡ በእሷ አይን ግን ሁሉንም ነገር ስናደርግ ይዛናለች።
👍391
“ኃጢአተኞች!” እነዚያን ጨካኝ አይኖቿን እንደገና ወደኔ አዙራ ጮኸች። “አይኖቼ ምህረት የላቸውም ቆንጆ እንደሆንሽና እነዚያ እያደጉ ያሉ ጡቶችሽ
ማራኪ እንደሆኑ ታስቢያለሽ አይደል? በየቀኑ እያበጠርሽ የምትጠቀልይውን ይሄንን ረጅም ወርቃማ ፀጉርሽን ትወጂዋለሽ አይደል?" እያለችኝ አይቼው
የማላውቀው አይነት አስፈሪ ፈገግታ አሳየችኝ፡
ጉልበቶቼ እየተንቀጠቀጡ እርስ በርስ እየተጋጩ ነው: እጆቼም እንደዚያው፡ የቀሚሴ ዚፕ ከጆርባው ሳይዘጋ በሰፈው ተከፍቶ ስላለና የውስጥ ሱሪ ስላልለበስኩ ውርደት ተሰማኝ! አይኖቼን ወደ ክሪስ ወረወርኩ ቀስ እያለ
በአይኖቹ የሆነ መሳሪያ ፍለጋ ክፍሉን እያሰሰ ነው:

“ወንድምሽ ለምን ያህል ጊዜ ሰውነትሽን እንዲጠቀም ፈቀድሽለት?” ስትል ጮሀ ጠየቀችኝ፡፡ ምን ማለቷ እንደሆነ ስላልገባኝ መናገር አልቻልኩም።

“እንዲጠቀም? ምን ማለትሽ ነው?”

አይኖቿን አጥብባ ክሪስ ሲያፍር ለመያዝ ድንገት ዞረች: ፊቱን ስመለከት፣ እኔ ባይገባኝም እሱ ግን ምን ማለቷ እንደሆነ እንደሚያውቅ ለእኔ እንኳን
ግልፅ ነበር።

“እኔ የምለው.” አለ ክሪስ ፊቱ ደም መስሎ: “…ምንም መጥፎ ነገር
አላደረግንም ነው:: አሁን ድምፁ ወፍሮ ጎርናና እና ጠንካራ ሆኗል።
“ቀጥይ በጥርጣሬና በጥላቻ አይን ተመልከቺኝ፡ እኔና ካቲ ግን አንድም ክፉ ነገር ወይም ኃጢአት ወይም የረከሰ ነገር አላደረግንም: ካላመንሽ ማመን የፈለግሽውን ማመን ትችያለሽ”

“እህትህ እርቃኗን ነበረች: እርቃን ሰውነቷን እንድትመለከት ፈቅዳልሀለች።ስለዚህ ስህተት ሰርታችኋል" ስትል በጥላቻ በአይኖቿ ገርፋኝ ፊቷን አዙራ
ክፍሉ ወጣች እየተንቀጠቀጥኩ ነበር ክሪስ ተናደደብኝ ካቲ ለምንድነው እዚህ ክፍል ውስጥ ሆነሽ ልብስሽን ያወለቅሽው? የሆነ ነገር ስናደርግ ለመያዝ አድብታ እንደምትጠብቅ እያወቅሽ…” አለኝ፡ ተጨንቆ
ሲቆጣ ያረጀ ይመስላል: “ምንም ሳታደርግ ወጣች ማለት አትመለስም ማለት አይደለም ልትቀጣን ነው::”

“አውቃለሁ አውቃለሁ። መግረፊያ ይዛ ልትመጣ ነው"

መንትዮቹ እንቅልፋቸው መጥቶ እየተነጫነጩ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ተመለሱ። ኬሪ ወደ አሻንጉሊቱ ቤት ስትሄድ ኮሪ ደግሞ ቲቪው ፊትለፊት
ተረከዙ ላይ ቁጢጥ አለና ጊታሩን አንስቶ መጫወት ጀመረ። ክሪስ በር በሩን እየተመለከተ አልጋው ላይ ተቀምጧል። እኔ ደግሞ ስትመለስ ሮጬ መታጠቢያ ቤቱ ውስጥ ገብቼ ልቆልፍ ተዘጋጅቻለሁ። መታጠቢያ ቤት እገባና በሩን ቆልፌ ከዛ እኔ ..

የበሩ ቁልፍ ተከፍቶ እጄታው ተንቀሳቀሰ፡

ዘልዬ ስነሳ ክሪስም ደንግጦ በመነሳት ካቲ ወደ መታጠቢያ ቤት ግቢና እዚያው ቆይ!” ሲል ጮኸ፡

አያታችን እንደ ዛፍ ገዝፋ ወደ ክፍሉ ገባች አለንጋ አልያዘችም እጇ ላይ ያለው ሴቶች ልብስ ለመስፋት ጨርቅ የሚቆርጡበትን አይነት ትልቅ መቀስ ነው፡ መቀሱ ረጅም ሲሆን በጣም ስለት ያለው ይመስላል

“ተቀመጪ! አለችኝ “ከዚህ በኋላ መስተዋት ስታይ ኩራት እንዳይሰማሽ ፀጉርሽን በሙሉ እቆርጠዋለሁ" ድንጋጤዬን ስትመለከት በንቀትና በጭካኔ
ፈገግ አለች:

ብገረፍ ይሻለኛል። ብገረፍ ቆዳዬ ቶሎ ይድናል። አባቴ ረጅም ፀጉር ያላቸው ልጆች ደስ እንደሚሉትና የእኔም ፀጉር እንደሚያምር ከነገረኝ ጊዜ ጀምሮ ያለማቋረጥ ስንከባከበውና ስወደው የኖርኩትን የሚያምር ረጅም ፀጉር ግን ላጣው አልፈልግም። መልሶ ለማሳደግ ደግሞ አመታት ይወስዳል: አምላኬ
ሆይ! በህልሜ በየምሽቱ ወደ መኝታ ቤታችን ተደብቃ በመምጣት በተኛሁበት
ፀጉሬን ልክ እንደ በግ ፀጉር ስትሸልተው እንደማይ እንዴት አወቀች? በዛ ላይ አንዳንዴ ፀጉሬ ተሸልቶ መላጣና አስቀያሚ ሆኜ ብቻ ሳይሆን ጡቴንም
ቆርጣው ጡት አልባ ስታደርገኝ ሁሉ በህልሜ አያለሁ።

ባየችኝ ቁጥር የምታየው የሆነ ነገሬን ብቻ ነው። ሙሉ እኔን አይታኝ አታውቅም: ንዴቷን የሚያነሳሱትን ቦታዎች ብቻ ነው እየመረጠች የምትመለከተው… የተመለከተችውን ቦታ ደግሞ የተናደደች ጊዜ ልታጠፋው
ትነሳለች ማለት ነው።

ሀሳቤ ወደ መታጠቢያ ቤቱ ገብቼ በሩን ለመቆለፍ ነበር። በደንብ የሰለጠኑት የዳንሰኛ እግሮቼ ግን በሆነ ምክንያት አልንቀሳቀስ አሉ። ያንን ረጅምና አንፀባራቂ መቀስ ሳይ በተፈጠረብኝ ፍርሀት እንዲሁም በንቀትና በጥላቻ
በሚያበሩት የአያትየው አይኖች ምክንያት ሽባ ሆንኩ።

የዚያን ጊዜ ክሪስ በጠንካራ ድምፅ “የካቲን አንድ ዘለላ ፀጉር ለመቁረጥ ብትሞክሪ
በዚህ ወንበር ጭንቅላትሽን እልሻለሁ!” ብሎ ስንመገብ ከምንቀመጥባቸው ወንበሮች አንዱን አነሳ፡ ወዲያው የእሱ ሰማያዊ አይኖች እሳት፣ የእሷ ደግሞ ጥላቻ ረጩ።

ከላይ እስከታች በግልምጫ አነሳቸው፡ የእሱ ትንሽዬ ወኔ የብረት ተራራ የምትመስለዋን በጭራሽ ሊያሸንፋት እንደማይችል ሁሉ ማስፈራሪያው
ውጤት አልነበረውም። “በጣም ጥሩ… እንግዲያው ምርጫ እሰጥሻለሁ።ፀጉርሽን ብታጪ ይሻልሻል ወይስ ሳምንቱን ሙሉ ምንም አይነት ምግብም
ሆነ ወተት ባታገኚ?”

“እባክሽ መንትዮቹ ምንም አላጠፉም…” ስል ለመንኳት። “ክሪስም ቢሆን ምንም ያደረገው ነገር የለም:: ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ሲመለስ ራቁቴን እንደሆንኩ
አላወቀም ነበር ጥፋቱ ሁሉ የእኔ ነው ሳምንቱን ሙሉ ያለ ምግብና ያለ ወተት መቆየት እችላለሁ አንቺ ግን ይህን ላድርግ ብትይ እንኳን እማዬ ይህንን እንድታደርጊ አትፈቅድልሽም: ምግብ ታመጣልናለች" አልኳት። እንደ እውነቱ ግን በልበ ሙሉነት አልነበረም ያልኳት ምክንያቱም እናታችን ከመጣች ረጅም ጊዜዋ ስለሆነ ቅጣቱ ቢጣልብኝ እንደምራብ አውቃለሁ።

“ፀጉርሽ ወይም ለሳምንት ምንም ምግብ አለማግኘት!” ስትል በማይበገርና ፍንክች በማይል አነጋገር ደገመችው: “አንቺ አሮጊት የምታደርጊው ሁሉ ስህተት ነው" አለ ክሪስ ወንበሩን አንስቶ እየተጠጋ ካቲን ድንገት ነው ያየኋት። ምንም ኃጢአት የሆነ ነገር አላደረግንም፣ አድርገንም ደግሞ አናውቅም ገና ለገና ይሆናል ብለሽ ፈርተሽ ነው”

ሁልጊዜ እንደምታደርገው ክሪስን ችላ ብላ “ፀጉርሽ ወይስ ለሳምንት
አለመብላት?” አለች: “መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብታችሁ ብትቆልፉም ሆነ ጣሪያው ስር ያለ ክፍል ውስጥ ብትደበቁ አንዳችሁም ለሁለት ሳምንት ምግብ አይሰጣችሁም!”

ቀጥሎ ቀዝቃዛና ስሌት የሚሰሩ በሚመስሉ አይኖቿ ክሪስን ረዘም ላለ ጊዜ ተመለከተችውና “እንዲያውም የእህትህን ቆንጆ ፀጉር የምትሸልተው አንተ
መሆን አለብህ!” ብላ ሚስጥራዊ ፈገግታ ብልጭ አደረገችና በመልበሻው አናት ላይ መቀሱን አስቀመጠች: “ተመልሼ ስመጣ እህትህ ፀጉሯ ተቆርጦ ካገኘሁ
ብቻ አራታችሁም ምግብ የማግኘት እድል ይኖራችኋል።" ስትል ክሪስ እኔ ላይ፣ እኔም ክሪስ ላይ እንዳፈጠጥን ጥላን ሄደች:...

ይቀጥላል
👍24😢11😱96
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ማደግ፣ ብልህ መሆን ልክ እንደ መጀመሪያው አመት ሁሉ ሌላኛውም አመት አለፈ እናታችን ልትጎበኘን የምትመጣበት ቀን እየቀነሰ መጣ ከስንት አንድ ጊዜ ስትመጣም ሁሌም ከዚህ ለመውጣት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደቀሩን እንድናምንና ተስፋ እንድናደርግ የሚያደርገን ቃል ትገባልናለች። በእያንዳንዱ ምሽት መጨረሻ ላይ የምናደርገው ነገር ቢኖር የቀን መቁጠሪያው ላይ…»
በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-አንድ
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
///
እኛ የዘላለም ተጓዦች ነን…..ለዘላለም በሁለንተና ውስጥ ቅርፃችንን እየቀያርን ከአንዱ አፅናፍ ወደ ሌላ አፅናፍ እየተላጋን የምንኖር ተንከራታች እና ተቅበዝባዥ ፍጡሮች፡፡ይህ ታርክ ግን ስለዘላለም አይደለም የሚተርከው… ስለቅፅበት ነው፡፡ሰው ተብለን ከተፈጠርንበት ሬሳ ተብለን እስከምንሸኝበት ስላለችው ቅፅበት አንድ ነጠላ ታሪክ ነው…..ከዛ በፊትም ሆነ ከዛ ቡኃላ ስላለው ብዙም እውቀቱ ስለሌለን ብንናገርም መቀባጠር ብቻ ነው የሚሆንብን፡፡
ተወልደን ወደሞታችን እየተጎዝን ነው፡፡በእያንዳንዱ ቀን ተኝተን ስንነቃ ከበላያችን የተሰቀለውን የሞት ቅርንጫፍ ዘንጥለን ወደገደሉ ለመሽቀንጠር እየተንጠራራን…. በተንጠራራንበት ቅፅበት ሁሉ የሆነች መጠን ወደቅርንጫፉ እየቀረብን ነው፡፡ግን ይህን ለማሰብ ዳተኞች ነን፡፡ስለዚህም የዘላለማዊነትን ምኞት በጭንቅላታችን ጠቅጥቀን ትርምሱ ውስጥ ገብተን እንንቦራጨቃለን….ማግበስበስ ውስጥ እንዳክራለን…..ትንፋሽ እስኪያጥረን ብኩንና ተቀበዝባዥ እንሆናለን፡፡በዛም የተነሳ መንገዳችንን ለመመርመርና ለማጣጣም እድል አይኖረንም….ጉዞችን የእውር ድንብር እይታችንም በደመነፍስ ነው፡፡እኔም ያው ሰው ነኝና እንደዚሁ ነበር ጉዞዬ…

እድሜዬ ሰላሳ ስድስት ሆኖታል፡፡ይህን ያወቁት እንግዲህ ከልደት ሰርተፍኬታ ላይ መነሻውን በመውሰድ እስከአሁን ያለውን ዓመት ቆጥሬ ነው፡፡..የፀሀይ መውጣት እና መጥለቅ ከሰው ልጅ መወለድና መሞት ጋር ይመሳሰልብኛል፡፡የፀሀይ መውጣት ከመወለድ ጋር የፀሀይ መጥለቅ ደግሞ ከመሞት ጋር፡፡

ፀሐይ ወጣች ስንል ተፈጠረች ማለታችን ሳይሆን ለእኛ እይታ ተከሰተች ብርሀኗ እና ሙቀቷ ምድራችን ጎበኛት ማለታችን ነው እንጄ ከመውጣቷ በፊተ ባለው ለሊት የለችም ማለት አይደለም በትክክልም አለች፡፡አንድ ሰውም ተወለደ ስንል ከመወለዱ በፊት የለም ማለት አይደለም በሌላ ዓለም በሌላ ቅርጽ ወይም በማንገምተው ህልውና ነበር..(ምክንያቱም እግዚያብሄር የሰውን ልጅ አንድ ቀን አንድ ላይ ነው የፈጠረው..)ሲወለደ በዚህ ምድር ተከሰተ ማለታችን ነው እንጂ ስለመፈጠር ማውራታችን አይደለም፡፡ፀሀይ የቀን ውሎዋን አጠናቃ ስትጠልቅም ከሰመች ጠፋች ማለታችን አይደለም….ከጠለቀችም ቡኃላ ከነምሉዕነቷ መኖሯን እንደምትቀጥል እናምናለን እናውቃለንም ፡፡ ሰውም ሞተ ስንል ነፍሱ ከምድር ህልውና ተነጠለች፤ ጊዜያዊ ቆይታዋንም አጠናቀቀች ማለታችን እንጄ ጭሩሹኑ ወደአለመኖር ተሸጋገረች ከሰመች ማለታችን አይደለም፡፡

ያው እንደነገርኮችሁ እድሜዬ 36 ነው ፡፡ግን ደግሞ እድሜ እንደዛ አልነበረም መቆጠር ያለበት….በህይወታችን እርባነቢስ ሆነው ዝም ብለው የሚያልፉ ትርጉመቢስ የሆኑ ቀናቶች፤ ሳምንታቶች እና አመታቶች አሉ..አሁን እነሱ ከእድሜያችን ተደምረው እንደኖርንባቸው መቆጠር ነበረባቸው?፡፡ደግሞ አንዳንድ ጊዚያቶች አሉ አንፀባራቂና ወርቃማ የሆኑ…ማንነታችንን የሰራንባቸው፤ ለነፍሳችን መዝናኛ በአበባ ያጌጠ አፅድ ፤ በፍራፍሬ የተሞላ ጋርደን ማዘጋጀት የቻልንባቸው፤ ጥቂት ግን ደግሞ በተደራራቢ ድርጊት የተሞሉ..በመከራና አሰቃቂ ድርጊቶች የታጠሩ…ተስፋ በማስቆረጥ እና መልሰው ደግሞ ብጣቂ ተስፋ በመስጠት በህይወት ዥዋዝዌ እያላጉ እያፈረሱ መልሰው የሚሰሩን …ለዘመናት የገነባነውን መኮፈሳችንን የሚቦረቡሩ….ኩራታችንን ከአመድ ሚደባልቁ….የማናውቀውን እራሳችንን የሚያስተዋውቁን…በስቃይ እሾህ የታጠሩ ግን ደግሞ ፍሬያማ ጊዜያቶች…እና እነሱ ከእድሜያችን ጋ ሲደመሩ በሁለት ሶስት እጥፍ መባዘት አልነበረባቸውም….?
እና ለዚህ ነው እድሜዬን ሲጠይቁኝ ስንት ማለት እንዳለብኝ ግራ የሚገባኝ፡፡ለማንኛውም አሁን ስለነዛ በልኬት ጥቂት ግን ደግሞ በተደራራቢ ትንፋሽ አስቆራጭ ድርጊት የታጨቀ ኩነቶች ነው የማወራችሁ..ከዘልዛላው ህይወቴ ላይ ተቦጭቀው በጉልህ ስለሚነበቡ አይረሴ ቀናቶች ፡፡
እለቱ አርብ ነው፡፡ሰዓቱ ደግሞ 12.30 ….ስራ ላይ ነኝ…የስራ ቦታዬ በተፈጥሮ ውበት በደመቀችው የመዲናይቱ አዲስ አበባ ኮረዳ ጎረቤት በሆነችው ቢሾፍቱ ከተማ ነው፡፡
በትክክል ከቢሾፍቱ ከተማ እንብርቶ በሆነው ቢሾፍቱ ሀይቅ ጠርዝ ላይ ነው ያለውት ፡፡ይዚህን ሀይቅ ጠርዝ ታከን እዚህ አስቸጋሪ ገደልና ኮረብታማ ቦታ ላይ አስደማሚ ሪዞልት እየገነባን ነው፡፡በዚህ የሪዞልት ግንባታ ላይ ፕሮጀክት ኢንጂነር ሆኜ በመስራት ላይ እገኛለው፡፡ ስራ ከጀመርኩ አመት ከስድስት ወር ሆኖኛል፡፡ፕሮጀክቱ በሁለት ፌዝ የሚገነባ ሲሆን አሁን አንደኛውን ፌዝ ገንብተን ጨረሰን ፊኒሽንግ ላይ ስንሆን አንደኛውን ደግሞ ገና ቁፋሮ ጨረሰን ፋውንዴሽን እየሞላን ነው፡፡አንደኛውን ፌዝ ሰርተን ለማጠናቀቅ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሚባል መስዋዕትነት ከፍለናል፡፡አንድ ሰው ሞቶብናል.ከአራት በላይ ሰዎች በስራ ላይ እያሉ አደጋ ደርሶባቸው አካለጎደሎ ሆነዋል፡፡ሁለተኛውን ፌሰዝ ግን ከመጀመሪያው ያገኘነው ልምድ ቀላል የሚበል ስላልሆነ በዛ መጠን እንደማንፈተን እርግጠኞች ነኝ፡፡
ሪዞርቱ የሚያሰርፍበት ቦታ እጅግ ሳቢና አስደማሚ መልካአምድር ያለበት ቢሆንም ለግንባታ ግን በጣም አስፈሪና ፈታኘ ነው፡፡አሁን የቆምኩበት አለት ላይ ሆኜ ቁልቁል የግዙፍ እስትዲዬም ሜደ የመሰለውን ክቡ ሀይቅ ከነውበቱና አስፈሪነቱ ይታየኛል፡፡፡፡በዚህ ሰዓት ሰራተኛ ሁሉ ወጥተው ሄደዋል…እኔ ፤ የሳይቱ ፎርማኑ ጋሽ አህመድ ፤ዋናው ፌራዩ(የብረት ሰራተኛ) በሪሁን እና ከአመት ቆይታ ቡኃላ ሰሞኑን ከስራ ልትሰናበት በርክክብ ላይ ያለችው እስቶር ኪፐሯ አይዳ እና እሷን ተክታ ሰሞኑን የተቀጠረች አንድ ለጊዜው ስሞን የማላውቃት ልጅ ነን በሳይቱ ውስጥ ያለነው፡፡ ፡፡ሰራተኛ ከወጣ ቡኃላ ወደኃላ ቀርቶ በእለቱ የተሰራውን ስራ ማየት የዘወትር ልምዴ ነው፡፡ሳይቱ ከግርግር ነፃ ከወጠ ቡኃላ በስክነት የእለቱን ስራ ማየት..በእለቱ የተሰራውን መልካም ስራና የጠፋና የተበላሸም ካለ ግልፅ ሆኖ ስለሚተይ የሚቀጥለውን ቀን ፐሮግራም ለመከለስ ከፍተኛ እገዛ ያደርግልኝል፡፡
ነገ ኮንክሪት ለመሙላት የተዘጋጁ አስር የሚሆኑ footing ስላሉ ዛሬውኑ የብረት ስራቸው በትክክል በዲዛይኑ መሰረት መቀመጣቸውን እያረጋገጥን ነው፡፡
አና እንደተለመደው ከአንዱ ኮረነር ወደሌላወ ኮርነር እየተዘዋወርኩ በመመልከት ላይ ሳለው ከኃለዬ ድምፅ ሰማው
‹‹…አንጂነር የምትፈልገው ነገር አለ..?ልወጣ ነበር ››አለችኝ..አዲሶ እስቶር ኪፐር
‹‹ቆይ ትንሽ ጠብቂንና መኪና ስለያዝኩ እሸኝሻለው….እነበሪሁንም አሉ አንድ ላይ እንሄዳለን…. አንድ 10 ደቂቃ ጠብቂን…እሷ ግን መሄድ ትችላለች››አልኳት..አይዳን ማለቴ እንደሆነ ሁለቱም ገብቶቸዋል፡፡እሷ.እንድትቆይ የፈለኩት ምን አልባት ከስቶር የምንፍልገው እቃ ይኖራል የሚል ግምት ስለወሰድኩ ነው፡፡
‹‹እሺ …እጠበቅሀለው››አለቺኝ
‹‹እኔም እሷን እጠብቃለው…..ሆሆይ ከስራ ሰዓት ውጭ እህቴን ሶስት ወንዶች መካከል ትቻት አልሄድም…..ምን ይታወቃል››አለች አይዳ..እንግዲህ ነገር እየፈለገች መሆኑ ነው……ከስራ የለቀቀችው እሷ ፈልጋ ሳይሆን እኔ አባርሬያት ነው….ለምን የሚለውን ሌላ ጊዜ ነግራችሆነው..እሷም ታዲያ አሁን በዚህን ሰዓት እዚህ ሳይት ላይ የተገኘችው ከአስራአምስት ቀን በፊት ስለተዋወቀቻት ሴት ደህንነት ተጨንቃ ሳይሆን እኔን ምቾት ለመንሳትና ለማበሳጨት ነው…አዎ አይዳ እንዲህ ነች፡፡የተናረችውን እንዳልሰማው ሆኜ ትኩረቴን ወደስራዬ መለስኩ፡፡
👍29👏2
ጉብኝቴ አጠናቅቄ መጨረሻ አካባቢ አንድ ተቀፍሮ ለነገ የተዘጋጀ ብረት ብቻ የታሰረበት Footing ጋር ደረስኩ…..ስመለከተው አሰራሩ የተወታተፈና ሴንተሩን ያልጠበቀ ሆኖ ታየኝ፡፡በርቀት ላይ ስራ ሲሰሩ የነበሩትን ጋሽ አህመድንና በሪሁንን ጠራዋቸው….ቦታውን በደንብ ለማየት ጨለም ስላለኝ እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም…
‹‹ማነሽ እህት…ማን ነበር ስምሽ.እስኪ ባትሪው ይዘሺልኝ ነይ››
‹‹የትኛውን?›
‹‹አንዱን… ደህና የሚያበራውን››
‹‹እሺ›› ብላ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ወደ ተሰራው እስቶር ሮጣ ሄደች...በፍጥነት በግራዋ አንድ ባትሪ በቀኞ ሌላ ባትሪ ይዛ መጣች፡
ሁለቱንም ተራ በተራ እየሞከረች ‹‹የትኛውን ልስጥህ ››አለቺኝ…..በዚህን ጊዜ በሪሁንና ጋሽ አህመድ መጥተው ስድስት ሜትር የሚረዝመው ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ነበር…አይዳ ደግሞ ከልጅቷ ጎን ልክ እንደጋርድ ተገትራ ቆማለች፡፡እኔ የጉድጎዱ ከንፈር ላይ ቆሜ አንዱን ባትሪ ከልጅቷ ተቀበልኩና እታች ላሉት ለማቀበል ሞክር ጀመር… እሷም እንደእኔው የጉድጓዱ ከንፈር ጋር ቆማ ሁላችንም እንዲታየን ወደታች ማብራት ጀመረች፡፡
አያችሁ እዛ ጋር ያለው ኦቨርላፕ ትክክል አይመስለኝም..እስቲ ቼክ አድርጉት …››ላስረዳቸው ገና ስጀምር ….የቆምንበት አፈር የመንሸራተት ስሜት አሳየ.. እርስ በርስ ተያይተን ሌላ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የማሰቢያ ጊዜ ከማግኘታን በፊት ከእኛ ውጭ ያለ ከጥልቁ ሲኦል የተላከላ የሚመስል ኃይል ጎትቶ እንደጨመረን አይነት እግራችን ከዳንና ወደጉድጎዱ ተስፈንጥረን ገባን…
እንግዲህ የጉድጎዱ ጥልቀት ስድስት ሜትር ከሰላሳ ነው…. የሚቀበለን እንደአልጋ የተረበረበ ባለ 32 ዲያሜትር የአርማታ ብረት ንጣፍ እና ብረቱን ዙሪያውን አቅፎ የያዘው ወፍራም ፎርምወርክ (ጣውላ )ነው….ወይንም እድለኖች ከሆን ከታች ጉድጓድ ውስጥ ስራ ላይ በሚገኙትን ጋሽ አህመድ ና በሪሁን ጭንቅላት ላይ እናርፋለን…..እኛ ከከባድ ጉዳት እንተርፋለን…እነሱ ደግሞ ምን አልባት አንገታቸው ይቀነጠሳል፡፡
ስንት ሜትር ላይ እንደሆነ አናውቅም አዲሷን እስቶርን ኪፐር በአንድ እጄ በሌላ እጄ ደግሞ የአይዳን ቀሚስ ጨምድጄ ይዤ ነበር … ..በዛ ጭንቅ ላይ ሆኜ ‹‹አሁን እንዲሀ አንድ የተከበርኩ እና የተፈራው ፕሮጅት ኢንጂነር በሁለት ሴቶች መካከል ተጣብቄ ያየኝ ሰው ምን ይላል…?›› እያልኩ አስባለው ፡፡
…አዲሶ ልጅ . ኢየሱስ ድረስልኝ….ኢየሱስ ድረስልኘ.. እያለች ትጮኸለች
ከበታቻችን‹‹ አላዋክበር …አላዋክበር….››የሚል ድምፅ ይሰማኛል…….ጋሽ አህመድ መሰለኝ
.በጉጉት ወደሚሄድበት ሽርሽር ቦታ ለመድረስ እንደጎጎ ህፃን<<ቆይ አንደርስም እንዴ?..››ስትል ጠየቀች አይዳ ነች….ምንም የመለሰላት የለም
በእውነት ግን አንደርስም እንዴ ?ስል በውስጤ እራሴን ጠየቅኩ….ስድስት ሜትር ይሄን የህል እሩቅ ነው….?ነው ወይስ የቆሪጥ መንፈስ ወደ ጥልቁ የቢሾፍቱ ሀይቅ እየጎተተን ይሆን…?ምንድነው ጉዱ ?ቢሾፍቱ ሀይቅ አፋፍ ላይም የቤርሙዳ ትርያንግልን አይነት ታአምራዊ ማጅክ አለ እንዴ…?››በውስጤ ያሰብኩት ጭንቀት ወለድ ሀሳብ ነው፡፡
ከረጅምምምም የእድሜ ልክ ያህል ከሚረዝሙ ደቂቃዎች ቡኃላ መሬት ስናርፈ እኔ በሁለቱ ሴቶች መካከል እንደተጣበቅኩ ነበር.. እርስ በርስ ተያየን….
‹‹ወይኔ እማዬ ድረሽ…ቂጤ ተጨፈለቀ…››ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማውት የአይዳ ንግግር ነው፡፡
‹‹ቂጥሽ መጨፍለቁ ምንም አይደል ነፍሽ ግን አለ?››
‹‹ቂጤ ከሌለ ነፍሴ ምን ያደርግልኛል?››የእሷ መልስ ነበር ፡፡
.ዙሪያችንን ስናይ እንደእስፖንጅ የሚያነጥር ቄጤማ የተነጠፈበት መሬት ላይ ነው ያረፍነው ….በሁለታችንም በእጃችን ያለው ባትሪ እየበራ ነው፡፡ያለንበት 2.5×2.5 ስፋት የተቆፈረ የfoothing ጉድጓድ ሳይሆን አንድ መለስተኛ ሳሎን ስፋት ያለው ግዙፍ ዋሻ መሳይ ክፍል ነው፡፡ ከእኛ ወደኣራት ሜትር እርቀት ላይ ጋሽ አህመድና በሪሁን ጎን ለጎን ተዘርረው እርስ በርስ በድንጋጤና በገረሜታ እየተያዩ ነው፡፡ምንድነው እየሆነ ያለው..?ለ foothing የተቀመጠው ብርት ከእኛ በአንድ ሜትር ርቀት ዘፍ ብሎ ቁጭ ብሎል፡፡ጣውላዎቹና መቀሰቻ እንጨቶቹ ተበታነው ወለሉን ሞልተውታል፡፡አይኔን ወደላይ አቀናው ትልቅ አለት ድንጋይ በመጣንበት አቅጣጫ ተቀርቅሮ አፈርና ብስባሽ ነገሮች ደፍነውታል፡፡አዎ ጉድጎዱ ተደርምሶል፡፡
በአስፈሪው የቢሾፍቱ ገደል ሀይቁ ጠርዝ ስር..ምን አልባትም ከሀይቁ ወላል በታችም ሊሆን ይችላል የአንድ ድርጅት ሰራተኞች የሆን ሁለት ሴት እና ሶስት ወንዶች በድምሩ አምስት ሰዎች የተፈጠሮ ታጋቾች ሆነናል…ከነነፍሳችን ተቀብረናል…ምን አልባትም አልቆልን ሊሆን ይችላል፡፡

ይቀጥላል .....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️
👍213👎1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


...የሌቪሰን አቀራረብና አነጋገር በቅንነት ለመርዳት ይመስል ነበር እሷም ያ ተዳፍኖ የኖረውና አሁን ጨርሶ የጠፋ አስመስላ እፍን ድፍን አድርጋ በመያዝና
ለወደፊትም በዚያው ዐይነት ልትቈጣጠረው እንደምትችል በማመን የካፒቴን ሌቪሰንን ቀረቤታ በትዕግሥት ለመቀበል ወሰነች እመቤት ሳቤላ ከጊዜ ወደ ጊዜ በጣም እየተሻላት ሔደ ጧት ጧት እየተነሣች ወደ ባሕሩ ዳር አሸዋ እየመጣች ትቀመጥና የባሕሩን አየር እየተቀበለች ሞገዱን ሲገፋና ሲሸሽ ትመለከታለች " ከዚያ ቦታ ከማንም ጋር አልተዋወቀችም "
አነጋጋሪ ሰው ካገኘች ሌቪሰን ብቻ ነበር" ብዙ ጊዜ ከወደቡ መድረክ እየሔዴ ሲያጫውታት አንዳንድ ጊዜም ከቤት እየመጣ ወደ ባሕሩ ይወስዳት ነበር" ይህ ሁሉ ሲሆን ሲወስዳትም ሆነ ሲመልሳት ክንድ ለክንድ ተያይዘው ስለሚጓዙ ይህን ነገር ብትተው አንደሚሻላት
ሕሊናዋ ጠቅ ያረጋት ነበር "
አንድ ቀን እንደ ቀልድ አስመስላ
አምርራ መናገር አይሆንላትም
በደንብ ስለ ጠነከረች የሱን ድጋፍና አጀብ እንደማያስፈልጋት ነገረቸው " ባሏ ባጠገቧ ተገኝቶ ሊደግትና ሊያካሒዳት እስካልቻለና እሱም እሷን ለመርዳት እስካልተቸገረ ድረስ የማትፈልግበት ምክንያት ምን እንደሆነ በመደነቅ ጠየቃት በአባባሏ የምትገፋበት ምክንያት መናግር ስለ አልቻለች በዚው ቀጠሉ ክንድ ለክንድ ተያይዘው ይመላለሱ ጀመር አትምጣብኝ
እንዳትለው ድፍረት ጠፋ ከቤት ዘግታ አልወጣም ብላ ብትቀመጥ ለጤንነት ይበጃል ተብላ የተላከችበት የባሕሩ አየር ሊቀርባት ሆነ ስለዚህ መላቀቂያ
መላ አላገኘችም እሱም ወደ መርከቡ መድሪክ ለመውሰድ ማታ ማታ ሁልጊዜ ይመጣ ጀመር ሔደው ጫጫታ ትርምስ መጣበብ ከበዛበት ቦታ ፈንጠር ብለው ለብቻቸው ይቀመጡና ! በዚያ የብርሃንና የጨለማ መሰነባበቻ በሆነው አስደሳች
የማታ ሰዓት ለሌቪስን ሐሳብና ፍላጎት የሚስማማ ለሌላ ለማንም ጆሮ አደገኛ ሊሆን የሚችል ወሬ ይይዛሉ ከዚያ ይነሡና ከበራፉ አድርሷት ይመለሳል " ማታ ከሆነ
እሶም እንዲገባ ጠይቃው አታውቅም እሱም ጧት አንዳንድ ጊዜ ያደርገው እንደ ነበረው ያለፈቃድ ለመግባት ሞክሮ አያውቅም "

hዚህ ሁኔታ ለመላቀቅ ባሏ ቶሎ መጥቶ ወደ ቤቷና ወደ ልጆቿ እንዲመልሳት በጣም ፌለች

ሚስተር ካርላይል በሔደ በሁለተኛ ሳምንቱ ስለሚመጣ ትጠብቀው ነበር እነዚያ ሁለት ሳምንቶች በእመቤት ሳቤላ የሠሩት ተአምር ግን በጣም የሚያስገርም ነበር " የልጅነቷን ትኩስ ስሜትና አዲስ ንቃት መልሳ እንዳገኘችው እየታወቃት
ስሜቶቿን ለመተንተን ምክንያቱን ለመረዳት ግን ራሷም አልደፈረች "
የጠራው ሰማይ የነጠረ ዕንቁ መሰለ በነፋስ እየዘመሙ የሚታዩት ለምለም አዝመራዎችና ዛፎች አረንጓዴ ዕንቁ መስለው አምረው ነበር አበቦች ከማንኛውም ሽቶ በበለጠ ጣፋጭ መዓዛቸውን ያውዳሉ " እነዚህ ነገሮች ሁሉ ዱሮ ከነበሩበት አለመለወጣቸውን ይህ ሁሎ ለውጥ ይህ ሁሉ የደስታ አመለካከት ይህ ሁሉ የመንፈስ
መታደስ እውነት በውጭ የምታየው ነገር ተለውጦ ሳይሆን ከውስጧ ከልቧ የፈለቀ አንደነበርም ይገባት ነበር ስለዚህ “ ለምን? ብላ ሕሊናዋን ለመመርመር መፍራቷ አያስገርምም

ከዚያ ሁሉ መዝለፍለፍና መፍዘዝ መተከዝና ማዘን ወጥታ ካሁኑ ለውጥ ስትደርስ መልኳም ወዟም ቀለሟም አብሮ በስሜቷ ልክ ታደሰ ባሏ በመጣበት ምሽት ከካፒቴን ሌቪሰን ጋር ልትቀበለው ወደ ወደቡ የወረዶች ጊዜ ሚስተር ካርላይል ከጉምሩክ መፈተሻ ክልል ሆኖ አሻግሮ ሲያያት ሌላ መሰለችው
ጉንጮቿ ሞልተውና ወዝተው የጤንነት ቅላት አየባቸው " ዐይኖቿም ከባሏ ጋር
እንደግና በመግናኘቷ የደስታ ብርሃን አበሩ "

" በሰውነትሽ ምን አድርገሽበት ይሆን ... የኔ ፍቅር ? አላት ከጉምሩክ መጣና እጆቿን ያዝ አድርጎ " " በጣም በጎ የሆንሽ ትመስያለሽ "

“ አዎን በጣም ተሽሎኛል
አርኪባልድ አሁን ግን በጣም ሞቀኝና ሰውነቴም ደም መሰለ " እዚህ አንተን ስንጠብቅህ የማታ ፀሐይ ሙሉ ለሙሉ አገኘን " ጀልባው እንዴት ይኸን ያህል ቆየ ?

“ንፋስ ከወደፊታችን በኃይል ይነፍስብን ነበር” አላት ፡ ያ አብሯት የነበረዉ አለባበሰ መልካም ሰውዬ ማን እንደሆነ አሰበ ሰውዬውን ከዚያ በፊት አይቶት የሚውቅ መሰለው "

“ ካፒርቴን ሌቪስን ይባላል ” አለች ወይዘሮ ሳቤላ “ ስለሱ እኮ በአንዱ ደብቤዬ ገልጨልህ ነበር ረሳኸው እንዴ ?” አለችው እሱ ግን እውነትም ዘንግቶት ነበር "

« ወደዚህ በምጣቴ በጣም ደስ አለኝ” አለ ስውዬው ነገራቸውን አቋርጦ " ምክንያቱም እመቤት ሳቤላ በእግሯ ስትመላለስ ለመርዳት ዕድል አገኘሁ " መጀመርያ ብቻዋን ለመምጣት አትችልም ነበር :አሁን ግን በጣም ጠንከራልች "

እመቤት ሳቤላ የባሏን ክንድ ይዛ ፍራንሲዝ ሌቪሰን በሌላሙ ጎን ሆነው ሲጓዙ እውነቱን ልንገርህ አለው ሌቪሰን ድምጡን ለካርላይል ጆሮ ብቻ እንዲደርስ
መጥኖ። “እመቤት ሳቤላን መጀመሪያ ሳያት የምትሞትበትን ቀን ብቻ የምትቆጥር መስላኝ ነበር " ስለዚህ እኔ በምችለው ሁሉ ልረዳት ግዴታ ሆነብኝ "

“ እሷም ውለታህን እንደማትረሳው እርግጠኛ ነኝ ” አለው ሚስቴር ካርላይል ጫወታውን በመቀጠል
ስለ በጐነቷ ግን እንደ ተአምር የሚታይ ነው " ከደብዳቤዎቿ እንደተረዳሁት ተሽሏት እንደማገኛት ተስፋ አድርጌ ነበር " አሁን ግን መሻል ብቻ ሳይሆን ደኅና የሆነች ትመስላለች " የምንለውን ትሰሚያለሽ ሳቤላ ? የዱሮ አበባነትሽ እንደዚህ ሆኖ የተመለሰው በተአምር ካልሆነ በቀር በሁለት ሳምንት ውስጥ ይህን ያህል መለወጥ አስቸጋሪ ነው " በውነትም ይህ አየር በበሽታ
ለተሰነከሉ ፍቱን መድኃኒት ነው ለማለት ይቻላል ” ብሎ መደነቁን ገለጸ "

የማበቧን ነገር ከሚስተር ካርላይል ስትሰማ ፊቷ የቅላት ዘረረት ጣለበት ነገር ግን መልኳን ያለመለመው ልቧን ያደስው አየሩ ወይም ቦታው አለመሆኑን ታውቅ ነበር ። ማወቁንም ለራሷ ጭምር ምስጢር አድርጋ አፍና ልትይዘው ብትመኝም ከራስ መሰወር ስለማይቻል በደንብ ታወቃት ስለዚህ የባሏን ከንድ ጭምድድ አድርጋ ይዛ ይህን ውስጥ ለውስጥ እየተስፃረግና እየተሳበ ፡ መንፈሷን የያዛውን አደገኛ ጠላት ነቅላ ለመጣል የመንፈስ ኃይል ለማግኘት ከልቧ ትጥር
ጀመር።

ስለ ልጆቹ ምንም ነገር አልነገርከኝም” አለችው ሳቤላ : ከባሏ ጋር ከክፍሎቿ ደረሱ " ፍራንሲዝ ሌቪሰን እንዲገባ ስለ አልተጠቀ ከደጅ ተመለሰ "

ሁሎም አንዳንድ ጊዜ ሳምልን አላሉህም ? አርኪባልድ ልጄስ ሳምልኝ ብሎ አልላከህም ?

ሚስተር ካርላይል ሣቀ “ እሱ አባት እንጂ እናት አይደለ " ኤርኪ በአንድ ዓመቱ እናቴን ሳምልኝ ብሎ ሊልክ ! ማሰቧም ቢጨንቃት ነው "

“ እንደኔ ከቤት ውጥተህ ብትሆን ኖሮ ጥቂት ይልክልህ ነበር እኔ ብሆን አንድ ሺ ጊዜ ስሜው ሳበቃ ለአባትህ እሰጥልሃለ እለው ነበር "

“በይ እንዲያው እኔም አሁን ስመለስ አንድ ሺ ጊዜ እስምሽና እስድለታለሁ”አላት ሚስተር ካርላይል ሚስቱን ከልቡ ልጥፍ አድርጐ እያቀፈ " የኔ ፍቅር
አንቺን በማየት ብቻ ልቤ በደስታ ተሞላ "

በበነጋው እሑድ ነበር » ፍራንሲዝ ሌቪሰን ለመጀመሪያ ጊዜ ራት ተጠርቶ መጣ " ከራት በኋላ ሳቤላ ትታቸው ስትወጣ ከሚስተር ካርላይል ጋር የምስጢር
ወግ ያዙ ህልቆ መሳፍርት የሌለውንና ውስብስብ ያለውን ችግሩንና ጣጣውን ዘከዘከለት
አሁን በዚህ የግዳጅ ስደት ካገር ወጥቸ መኖሩን አልችለው አልኩ
በተለይ የፓሪስ ነሮ አስጨነቀኝ » አሁን ለኔ ኢንግላንድ የምመለስበትን መንግድ
ብትመክረኝ ” አለው "
👍14
“ እንደምትነግረኝ ከሆነ የባለዕዳዎችህን ጥያቄ በከፊል እንኳን ካላሟላህ ምንም መንግድ አይታየኝም -ሰር ፒተር አይረዱህም ?

“ ነገሩ በደንብ ሊብራራለት ቢችል እንኳን ይረዳኝ ነበር ብዬ አስባለሁ" ግን እንዴት አድርጌ ቀርቤ ማስረደመት እችላለሁ
በቅርቡ ብዙ ደብዳቤዎች ጽፌለት ነበር አንድም መልስ አጣሁ በዚያ ወር ፒተር ሌቪሰን ስለ ታመሙ ማንኛውንም
ጉዳይ ማየት እንደማይችሉ የሚገልጽ አንድ አጠር ያለ ደብዳቤ ከወይሮ ሌቪሰን
ደረሰኝ "

ሊታመሙ አይችሉም” አለው ሚስተር ካርላይል ባለፈው ሳምንት በግልጽ ሰረግላቸው ሆነው በዌስት ሊን ሲያልፉ አይቻቸዋለሁ "

«ሊረዳኝ ይገባዋል ሚስቱ ካልወለደችለት በቀር ወራሹ እኔ ነኝ እሷም ብትሆን እስከ አሁን ማርገዟን አልሰማሁም "

“ እንደ ምንም ብለህ ልታገኛቸው ይገባል።

በርግጥ ከሱ ጋር መገናኘት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ እነዚህ መብረቅ ያዘሉ ጥቁር ደመናዎች በኔ እያንዣበቡብኝ ፊቴን ወደ ኢንግላንድ አልመልሰውም
ከሔድኩ አፉን ከፍቶ ወደሚጠብቀኝ ወህኒ ቤት ያስገባኛል " እኔ አንዳንድ ፈተናዎችን መቀበል እችላለሁ " የወሀኒ ቤትን ነገር ግን ሳስበው እንኳን ይዘገንነኛል ።

“ ሌላ ሰው ሊያነጋግርልህ ይችላል "

“ ሌላ ሰው ማን ? ከጠበቆቼ ጋር እንደሆነ ተቆራርጫለሁ " አጎቴ ካገባ በኋላ በጣም ነው የተጫወቱብኝ

“ ታድያ ሰር ፒተር ሌቪሰንን እኔ ላነጋግርልሃ ?

"አዬ ! -- ከሆነማ ”

ከፈለግህ በወዳጅነቴ ነው
ገባህ ? በጠበቃነቴ አይደለም “ ከእኔ ጋር እንኳን ደህና አድርገን አንተዋወቅም " ከአባቴ ጋር በደንብ ይተዋወቁ ነበር "
ስለዚህ ምን ያህል እንደሚሳካልኝ አላውቅም እንጂ አንተ ሚስቴን ስለ ረዳህልኝ እኔም እሳቸውን አነጋግርልሃለሁ " ነገር ግን በነዚህ ሁለት ሦስት ሳምንቶች ውስጥ
ቃል ልገባልህ አልችልም ምክንያቱም በጣም ሥራ ይበዛብኛል ይህ ውጥረት
ባይኖርብኝ ኖሮ ከሚስቴ ጋር እዚህ እሰነብትም ነበር።"

ፍራንሲዝ ሌቪሰን ምስጋናውን ገለጸለት " ምንም እንኳን ወደ ኢንግላንድ የመመለሱ ተስፋ እሩቅና ያልተጨበጠ ቢሆንም በጣም ተደሰተ እነሱ ወጋቸውን
ሲቀጥሎ ሳቤላ ከነሱ ቀጥሎ ከነበረው ክፍል በመስኮቱ አጠገበ ተቀምጣ የእሑድ ልብሶቻቸውን ለብሰው ወዲያና ወዲሀ ሲተረማመሱ ወደቡን ያጣበቡትን ፈረንሳዮች በልቧ ሳይሆን በዐይኗ ብቻ ፍዝዝ ብላ ትመለከታቸው ነበር ልቧማ ከሷ ጋ ሙግት ገጥሞ ነበር ደስ የማይል ሙግት አንድ የጋለ ስሜት ወደ ፍራንሲዝ
ሌቪሰን የሚስብ ስሜት ሳትለው ሳትፈልገው ከቁጥጥሯ ውጭ በውስጧ እንደሚላወስ ይታወቃት ነበር " ልታምቀው እንደሌለ አድርጋ ልታጠፋው አልቻለችም
የሕሊናዋ ድምፅ ደግሞ፡ ከዚህ ስሜት ጋር ተደባልቆ ልብ ከሚያጠፋ ጭንቀት አስግብቷታል ይህን ስሜት ለማሸነፍ ከዚህ ሰው ጋር ባንድ ጊዜ ለዘለአለም ለመለያየት ያላትን ሀብት ሁሉ ብትከፍል ወይም ከቀሪው ዕደሜዋ ግማሹን ብትሰጥ ትወድ ነበር ።

ጭንቀት ሲባል ሳቤላ ቬን ራሷን ትጠራጠር ነበር ማለት አይደለም በራሷ ሥነ ምግባርና ጠባይ ትተማመን ነበር » እንደሷ ያለች የታረመች የጨዋ ልጅ የሚስትነት ግዴታዋን ትጥላለች ማለት ፀሐይ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ጠለቀች ማለት መሆኑን ታምንበት ነበር " እሷ የፈራችውና የጠላችው ከዚህ ሰው ጋር ጓዶኝነት መግጠሙን በተለይ ደግሞ ሁለቱ ብቻ ሲሆኑ ለሱ ያላትን ስሜት ከፍ አድርጎ
እንዳያስብና መጪው ሕይወቷንም የሀዘንና የሠቀቀን ዘመን እንዳይሆንባት ነበር ከሁሉ በላይ ደግሞ ይህን ስሜት በባሏ አንጻር ስትመለከተው ከሕሊና የማይጠፋ መራራ በደል መሆኑ ሲሰማት ሽምቅቅ ትል ነበር ።
አርኪባልድ. . . አንድ ነገር ልለምንህ " አለችው ካፒቴን ሌቪሰን ከወጣ በኋላ አብረው እንደ ተቀመጡ እሺ ልትለኝ ቃል ግባልኝ በመጀመሪያ።

" የምችለው ከሆነ ግድ የለም ። "

ከእንግዲህ እዚህ ለምቆይበት ጊዜ አብረኸኝ እንድትሰነብት እፈልጋለሁ በመገረም ቀና ብሎ አያትና የኔ ፍቅር . .. ወቅቱ ተዘዋዋሪ ዳኞች የሚመጡብት መሆኑን እያወቅሽ እንዴት እንደዚህ ብለሽ ትጠይቂኛለሽ ?

“ አርኪባልድ ምንም ቢሆን አብረኸኝ መሰንበት አለብህ …”
ቢሆንልኝ ኖሮ በጣም ደስ ባለኝ ግን የሚሆን አይደለም " የማይቻል መሆኑን አንቺም ታውቂዋለሽ " ከጥቂት ሳምንት በኋላ እንኳን ቢሆን እስከ መጨረሻ አብሬሽ መቆየት እችል ነበር በእነዚህ አሁን ወደዚህ በመጣሁባቸው ሁለት ሦስት
ቀኖች ውስጥ እንኳን ብዙ ነገር ይበላሽብኛል "

“ እና ነገ መሔድህ ነው?”

“ ለብሶት ሕግ የለውም የኔ ፍቅር

“ በል እንግዲያውስ ይዘኼኝ ሒድ

ሚስኵር ካርላይል ሣቅ አለ ። ይኸማ አይሆዓም ... ሳቤላ " ለውጡ ብዙ እንደ ረዳሽ እያየሁ አቋርጬ አልወስድሽም " ደግሞ እነዚህ ክፍሎች የስድስት ሳምንት ሒሳብ የከፈልኩባቸው ስለሆነ ባይሆን ከዚ በላይ መቆየትሽ ይቅር እንጂ የሒሳቡ ጊዜ እስከያበቃ መሰንበት አለብሽ "

ፊቷ የኀዘን ጭጋግ ለበሰ “ እኔ አን† በሌለህበት መቆየት አልችልም ”

“ ለምን እኮ?ምክንያቱን ንግሪኝ ” አላት ሚስተር ካርላይል ሳቅ ብሎ ምን ብላ ትንገረው ? የተሻለ መከራከሪያ መልስ ሆኖ ያኘችው አንተ አጠግቤ ከሌለህ
ሁሉ ነገር ያስጠላኛል ” ማለት ብቻ ነበር " በቂና ሊቀበላት የሚችል ምክንያት እንዳልነበርም ዐውቃው ነበር "

እውነትም ተቀባይነት አልነበረውም ሚስተር ካላይልም በበነጋው ተነሥቶ ሔደ ልክ ሲሳፈር ካፒቴን ሌቪሰን ሚስቱን እንዲረዳለት ወደፊትም ዕርዳታው
እንዳይለያት አደራ አለው የዚህ ዐይነቱ አደራ መልካም እንዳልነበር በአእምሮ አልመጣለትም የራሱን ታማኝነትና በጎ ሰውነት በማየት ካፒቴን ሌቪሰንንም ከሱ ያነሰ ምግባር ይኖሪዋል ብሎ አልጠረጠም ሚስቱን እንደሆነ ከሌቬስን ጋርም ሆነ ከሌላ ሰው ከማይኖርበት ምድረ በዳ ቢተዋትም አይሰጋባትም ነበር "
በሷ ላይ ፍጹም የሆነ እምነት ነበረውና.....

💫ይቀጥላል💫
👍112
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አራት


#ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ


“እንዲያውም የእህትህን ቆንጆ ፀጉር የምትሸልተው አንተ
መሆን አለብህ!” ብላ ሚስጥራዊ ፈገግታ ብልጭ አደረገችና በመልበሻው አናት ላይ መቀሱን አስቀመጠች: “ተመልሼ ስመጣ እህትህ ፀጉሯ ተቆርጦ ካገኘሁ
ብቻ አራታችሁም ምግብ የማግኘት እድል ይኖራችኋል።" ስትል ክሪስ እኔ ላይ፣ እኔም ክሪስ ላይ እንዳፈጠጥን ጥላን ሄደች:...

ክሪስ ፈገግ አለ: “አይዞሽ ካቲ መቼም ቢሆን ፀጉርሽን አልቆርጥሽም።እናታችን በየትኛውም ሰአት ተመልሳ ስለምትመጣ እንነግራታለን፡ አይዞሽ አትፍሪ መቼም ቢሆን ፀጉርሽን አልቆርጥሽም::” ሊያቅፈኝ ወደኔ መጣ፡ “በዛ
ላይ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል አንድ ካርቶን ብስኩትና አይብ መደበቃችን መታደል አይደል? ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ይህንን ስለማታውቅ ለዛሬ ምግብ
ይኖረናል:” አለ።

ድንገት እናታችን ካልመጣች ብለን በመስጋት ያን ዕለት ትንሽ ብቻ በላን።ግማሹን ወተትና ጥቂት ብርቱካኖች አስቀመጥን፡ ይሁንና እናታችን ሳትመጣ ቀኑ አለቀ: ምሽቱን ሙሉ አንዴ ስተኛ፣ አንዴ ስነቃ እንዲችው ስገላበጥ
ሌሊቱ ተጋመሰ፡ እንቅልፍ ሸለብ ሲያደርገኝ አሰቃቂ ቅዠት ይመጣብኛል።ኮሪና ኬሪ ጠፍተውብን ክሪስና እኔ ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ በጨለማ ስንፈልጋቸው አየሁ ስማቸውን እየጠራን ብንፈልጋቸውም እነሱ
ግን መልስ አይሰጡንም፡ በፍርሀት ውስጥ ሆነን በጨለማ እየሮጥን ነበር።
በጣም የሚያስጨንቅ ህልም ነበር። ስነቃ ክሪስም መንትዮቹም ተኝተዋል።እንደገና እንቅልፍ እንዳይወስደኝ ፈለግኩ፡ ልከላከለው ሞከርኩ፡ ቀስ እያልኩ
እየሰመጥኩ እየሰመጥኩ እንደገና ጥልቅ ቅዠት የተቀላቀለበት አስፈሪ ህልም ውስጥ ገባሁ፡ በጨለማ እየሮጥኩ በደም የተሞላ ኩሬ ውስጥ ወደቅኩ ደሙ ልክ እንደሬንጅ ያጣብቃል ሽታውም እንደ ሬንጅ ነው: በአልማዝ ያሸበረቀ፣ጭንቅላቱ የወርቅና አይኖቹ ቀይ የሆኑ አሳ እየሳቀ ደም በደም አደረገኝ፡
ከዚያ ደጋግሞ የሚያስተጋባ ድምፅ “እይ! እይ! ማምለጥ አትችይም!” እያለ ጮኸ፡

ማለዳው ቢጫውን የተስፋ ብርሃን ከዘጋው ከባድ መጋረጃ ጀርባ የገረጣ መስሎ ይታያል፡ ኬሪ በእንቅልፍ ልቧ ወደኔ እየተጠጋች “እማዬ፣ ይህንን ቤት አልወደውም” ስትል አጉረመረመች: ኬሪ ያለ እረፍት ስትገላበጥ ላቅፋት ፈልጌ ክንዴን ለመዘርጋት ብሞክርም ማንቀሳቀስ አልቻልኩም:: ምን ሆኛለሁ? ራሴ ልክ ድንጋይ እንደተጫነ አይነት ከበደኝ፡ ከህመሙ የተነሳ ጭንቅላቴ
ሊከፈል መሰለኝ፡ የእግሮቼና የእጆቼ ጣቶች ላይ ይወረኛል። ሰውነቴ ድርቅ ብሏል ግድግዳዎቹ ሁሉ የተጣመሙ ይመስሉኛል። ሁሉም ነገር ቀጥ ያለ መስመር የለውም።

ከአልጋው ባሻገር ባለው በሚያብረቀርቀው መስተዋት ራሴን ለማየት ሞከርኩ::
ሆኖም የከበደኝን ጭንቅላቴን ዞር ላደርገው ብሞክርም አልንቀሳቀስ አለኝ::ሁልጊዜ ከመተኛቴ በፊት ጭንቅላቴን እንደልብ ማዘዋወር እንድችል ፀጉሬን ትራሱ ላይ እበትነዋለሁ ግማሹ ጉንጬ ላይ ያርፋል: እና ደስ የሚል ሽታውና ልስላሴው በጣም ደስ ይለኛል። የፀጉሬ ጉንጬ ላይ መነስነስ ወደ
ጣፋጭ የፍቅር ህልም ይወስደኛል።

ዛሬ ግን ትራሱ ላይ ፀጉር የለም: ፀጉሬ የት ሄዶ ነው?

መቀሱ አሁንም መልበሻው አናት ላይ እንደተቀመጠ ነው: በድንግዝግዝ ይታየኛል፡ ጉሮሮዬን ለማርጠብ ምራቄን ደጋግሜ ዋጥኩና በግድ ትንሽ ድምፅ
አውጥቼ የክሪስን ስም ተጣራሁ። ወንድሜ ክሪስ እንዲሰማኝ እንዲያደርግ ወደ እግዚአብሔር ፀለይኩ። በመጨረሻ እንግዳ በሆነ ድምፅ “ክሪስ፣ የሆነ
ነገር ሆኛለሁ፡” ብዬ በሹክሹክታ መናገር ቻልኩ። ደካማዎቹ ቃላቶቼ እንዴት እንደተሰሙ ባላውቅም ክሪስን አነቁት ከእንቅልፉ በደንብ ሳይነቃ አይኖቹን እያሻሽ ካቲ ምን ፈልገሽ ነው?” አለኝ።

ከአልጋው ላይ አስፈንጥሮ ያስነሳው የሆነ ነገር አልጎመጎምኩ፡ አልጋዬ
አጠገብ ደረሰ፡ ትንፋሹን ውጦ በድንጋጤና በፍርሀት ድምፅ አወጣ፡

“ካቲ… ወይኔ አምላኬ ሆይ!”

ጩኸቱ በፍርሀት አሳቀቀኝ

'ካቲ ‥. ወይኔ ካቲ" ሲል አቃሰተ።

አይኖቹ እንዲህ በድንጋጤ እንዲፈጡ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ለማወቅ አልታዘዝ ያሉኝን ክንዶቼንና ያበጠ የመሰለኝን ከባድ ጭንቅላቴን ለማንቀሳቀስ
ሞከርኩ፡ እንደምንም እጄን ማንሳት ቻልኩ ከዚያ ለመሰማት የሚችል ጮክ ያለ ድምጽ አገኘሁና የእውነት ጮህኩ። ደግሜ ደጋግሜ ጮህኩ ክሪስ
በክንዶቹ አቅፎ እስኪያባብለኝ ድረስ ልክ አእምሮው እንደተነካ ሰው እየጮህኩ ነበር።

“እባክሽ አቁሚ… እባክሽ” ተንሰቀሰቀ። “ስለ መንትዮቹ ስትይ... የባሰ አታስፈራሪያቸው.
እባክሽ ካቲ አትጩሂ፡ ያሳለፉት
ይበቃቸዋል።እስከመጨረሻው ፈሪ እንዲሆኑ እንደማትፈልጊ አውቃለሁ: ካልተረጋጋሽ
ይደነግጣሉ። እመኚኝ በህይወቴ እምልልሻለሁ። ዛሬ እንደምንም ሬንጁን ከፀጉርሽ ላይ አስለቅቅልሻለሁ "

አያትየው ከእንቅልፌ እንዳልነቃ የሆነ መድኃኒት የወጋችኝን ምልክት ክንዴ ላይ አገኘሁ እና እንደተኛሁ ትኩስ ሬንጅ ፀጉሬ ላይ አፍስሳብኛለች: አንድም
ዘለላ እንዳይቀር ሬንጁን ከመጠቀሟ በፊት ፀጉሬን በደንብ ሳትሰበስበው አልቀረችም።

ክሪስ መስተዋት እንዳላይ ቢከለክለኝም ገፍትሬው መስታወቱ ላይ ተሰየምኩ።
ጭንቅላቴ አስፈሪ ጥቁር ጓል የተቀመጠበት መስሎ ሳይ አፌ በድንጋጤ ተከፈተ በመጀመሪያ የነቃው ኮሪ ነበር የተዘጋውን መጋረጃ ገለጥ አድርጎ ከእሱ
የተሸሸገችውን ፀሀይ ለማየት ከአልጋው ወጥቶ ወደ መስኮቱ እየሮጠ ሳለ ድንገት ሲያየኝ አይኖቹ ፈጠጡ፡ ከዚያ ትንንሽ እጆቹ አይኖቹን ለማሻሽት
ከፍ አሉና ባለማመን እንደገና አተኩሮ ተመልክቶኝ፡-

"ካቲ አንቺ ነሽ?” አለ፡

“አዎ”

“ፀጉርሽ ለምን ጥቁር ሆነ?"
ለዚያ ጥያቄ መልስ ከመስጠቴ በፊት ኬሪ ነቃች። “ወይኔ!” ስትል ጮኸች። ካቲ ጭንቅላትሽ ምን ሆኖ ነው?! ትልልቅ እምባዎች ከአይኖቿ ወደ ጉንጮቿ ወረዱ፡ “አሁን ጭንቅላትሽን አልወደድኩትም” ስትል ሬንጁ እሷ
ፀጉር ላይ እንደሆነ ሁሉ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች።

“ተረጋጊ ኬሪ” አለ ክሪስ በተረጋጋ ድምጽ። ካቲ ፀጉር ላይ ያለው ሬንጅ ነው: አሁን ስትታጠብና ሻምፑ ስታደርግበት ልክ እንደ ትናንቱ ይሆናል፡ እሷ ስትታጠብ እናንተ ሁለታችሁ ደግሞ ቁርስ እስኪቀርብ ብርቱካን እየበላችሁ
ቲቪ ተመልከቱ፡ በኋላ የካቲ ፀጉር ንፁህ ሲሆን ሁላችንም ቁርሳችንን
እንበላለን፡" አለ፡ ስለ ሁኔታችን የባሰ ፍርሀት እንዳይሰማቸው በማለት የአያታችንን ስም አልጠቀሰም ስለዚህ ወለሉ ላይ ተጠጋግተው በመቀመጥ
እርስ በርስ እየተረዳዱ ብርቱካኑን እየላጡ እየበሉ ራሳቸውን በቴሌቭዥን በሚተላለፈው የቅዳሜ ጠዋት የካርቱን ፊልም ውስጥ ከተቱ..

ክሪስ ገንዳው ውስጥ የሞቀ ውሀ ሞላልኝ: በዚያ በሚፋጅ ውሀ ውስጥ ፀጉሬን ደግሜ ደጋግሜ ነከርኩት። ክሪስ ደግሞ ሬንጁ እንዲላላ ለማድረግ ሻምፑ እያደረገ ነበር። ሬንጁ ቢላላም ከፀጉሬ ውስጥ ሊወጣ አልቻለም:
ጣቶቹ በሚያጣብቀው የሬንጅ ክምር ውስጥ ገቡ። ፀጉሮቼን ሳይነቅል ሬንጁን
ለማውጣት እየሞከረ ነው: ግብግቡ ስላደከመኝ ማሰብ የቻልኩት ስለ መቀሱ ብቻ ነው: አያትየው መልበሻው አናት ላይ ስላስቀመጠችው የሚያንፀባርቅ
መቀስ።

ክሪስ ገንዳው አጠገብ ተንበርክኮ የሬንጁን ክምር ከፀጉሬ ውስጥ ሲያወጣ ሬንጁ በፀጉሮቼ የተሸፈነ ነበር፡ ሬንጁን ከፀጉሬ ውስጥ ለማውጣት ስንሞክር
ከሁለት ሰዓት በላይ ሆኖን ነበር። “መቀሱን መጠቀም አለብህ!” ብዬ ጮህኩ።

“አይሆንም መቀስ የመጨረሻ ምርጫችን ነው” አለ እናታችን ያመጣችለትን የኬሚስትሪ ዕቃዎች በመጠቀም ፀጉሬ ሳይጎዳ ሬንጁን የሚያሟሟ ኬሚካል መቀመም እንደሚችል አስቧል።
👍303👏3
“ካቲ” አለ ጫማ ያላደረገ ተረከዙ ላይ ቁጢጥ እያለ። “ጣራ ላይ ወዳለው የመማሪያ ክፍል ሄጄ ሬንጁን ከፀጉርሽ ላይ የሚያስለቅቅ የሆነ ነገር
ለመቀመም ልሞክር” ሲል የእፍረት ፈገግታ ፈገግ አለልኝ። hኮርኒሱ ላይ የሚመጣው ብርሃን የላይኛው ከንፈሩን የሸፈነውን ሳሳ ያለ ፀጉር አሳየኝ ልክ እንደኔ በታችኛው የሰውነት ክፍሉ ላይ የዚህ አይነት የጠነከረና የጠቆረ
ፀጉር እንዳለው አውቃለሁ። “ካቲ፣ ሽንቴን መሽናት አለብኝ፡ አንቺ ፊት
አድርጌው ስለማላውቅ ትንሽ አፍሬያለሁ። ብትፈልጊ ጀርባሽን ማዞርና ጆሮዎችሽን በጣቶችሽ መድፈን ትችያለሽ፡ በሽንቱ ውስጥ ያለው አሞኒያ ፀጉርሽን ያስለቅቅልሽ ይሆናል።

በመገረም አተኩሬ ተመለከትኩት በሞቀ ውሀ ውስጥ ተቀምጨ ፀጉሬን በሽንት ልታጠብ ነው? ይህ ነገር በውኔ ነው? ሊሆን አይችልም: ይህ እውነት አይደለም ይሄ ህልም ነው አልኩ ለራሴ።

ግን እውን ነበር ኮሪና ኬሪ እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ መታጠቢያው መጡና
በጥያቄ ያደርቁኝ ጀመር።

“ካቲ፣ ፀጉርሽ ላይ ያለው ነገር ምንድነው?”

“ለምንድነው ፀጉርሽን ሬንጅ የቀባሽው?”

“በእንቅልፍ ልቤ አድርጌው መሆን አለበት”

“ሬንጁን ከየት አገኘሽው?”

“ጣሪያው ስር ካለው ክፍል”

“ሬንጅ ፀጉርሽን መቀባት የፈለግሽው ለምንድነው?”

መዋሸት አስጠልቶኛል: ለኬሪ ፀጉሬ ላይ ሬንጅ ያደረገብኝ ማን እንደሆነ ልነግራት ብፈልግም ያንን ግን ማድረግ አልችልም እሷና ኮሪ አሁንም ያቺን አሮጊት በጣም ይፈሯታል፡ “ሂዱና ቲቪ ተመልከቱ ኬሪ” ስል አዘዝኳት።
በምትጠይቃቸው ጥያቄዎች ስሜቴ በመነካቱ የጎደጎዱ ከሲታ ጉንጮቿንና ወደ ውስጥ የገቡ አይኖቿን ማየት ከብዶኛል፡

ካቲ ከአሁን በኋላ አትወጂኝም?” ጠየቀ ኮሪ

“እንዴ! እወድሀለሁ እንጂ ኮሪ… ሁለታችሁንም እወዳችኋለሁ። ሬንጁን ፀጉሬ ላይ ያደረግኩት በስህተት ነበር አሁን ግን በራሴ ተናድጃለሁ።"

ኬሪ እንደገና ኮሪ አጠገብ ሄደችና እነሱ ብቻ በሚግባቡበት የተለየ ቋንቋ ተንሾካሾኩ: አንዳንድ ጊዜ እኔና ክሪስ ከምናውቃቸው በላይ ብልሆች ይመስሉኛል።

ለሰዓታት መታጠቢያ ገንዳው ውስጥ ነበርኩ። ክሪስ በደርዘን የሚቆጠሩ ውህዶችን በትንሹ የፀጉሬ ክፍል ላይ እየሞhረ ነበር ሁሉንም ነገር ሞከረ ውሀውን ቶሎ ቶሎ እንድቀይርና በጣም ሞቅ ያለ እንዳደርገው ነገረኝ፡ ቀስ
በቀስ ሬንጁ ከፀጉሬ ላይ እየለቀቀ መጣ ብዙ ፀጉሮቼን የነቃቀለው ሬንጅ በመጨረሻ ሙሉ በሙሉ ለቀቀ 😄 አስለቅቀን ስንጨርስ ቀኑ አልቆ ነበር። በዛ ላይ እኔም ሆንኩኝ ክሪስ አንድ ጉርሻ ምግብ እንኳን በአፋችን አልዞረም ነበር።

ለልጆቹ አይብና ብስኩቶች ሰጣቸው ለራሱ በመብላት ግን ጊዜ ማባከን አልፈለገም፡ እኔም በፎጣ ተጠቅልዬ አልጋው ላይ ተቀምጬ የሳሳውን ፀጉሬን ማድረቅ ጀመርኩ። የቀረው ፀጉሬ አቅም ያጣ በቀላሉ የሚሰባበርና
ቀለሙም የተለየ ሆኖ ነበር
ክሪስ በተራበ ስሜት ሁለት ብስኩቶችን በቺዝ እየበላ “ሙሉ ፀጉርሽን እስካልቆረጥሽው ድረስ ምግብ የሚባል አታመጣም፡ ራስሽን ለማበርታት ጥረት ማድረግ አለብሽ፡" አለኝ፡፡

ብስኩትና ቺዝ ከአንድ ብርጭቆ ውሀ ጋር በሳህን ላይ አድርጎ ወደኔ ይዞ መጣና! “ብይ… ጠጪ እናሸንፋታለን፡ ነገ ምግብ ካላመጣችልንና እናታችንም
ካልመጣች ከፊት ከግንባርሽ ጋር ያለውን ፀጉርሽን እንቆርጠዋለን፡ ከዚያ ፀጉርሽ በሙሉ የተቆረጠና መላጣ መሆንሽ እንዳይታይ አፍረሽ እንዲመስል ጭንቅላትሽን በአንገት ልብስ ትጠመጥሚያለሽ፡ ፀጉርሽ ፈጥኖ ያድግልሻል::
ምንም መልስ ሳልሰጥ ቺዙንና ብስኩቶቹን በላሁ። ከመታጠቢያ ቤቱ ቧንቧ በተቀዳ አንድ ብርጭቆ ውሀ የቀኑን ምግቤን አወራረድኩት። ክሪስ ያንን
የሳሳና ብዙ ነገር የቻለ ፀጉሬን አበጠረልኝ፡ ከዚያ በጣም ደክሞኝ በጀርባዬ አልጋው ላይ ጋደም አልኩ፡ ክሪስ አልጋው ላይ ተቀምጦ እያየኝ ነው እንቅልፍ ወሰዶኝም እየጠበቀኝ ነበር፡ እጆቹ እንደ ሸረሪት ድር የቀጠነውን
ረጅሙን ፀጉሬን ይዘው ነበር።

ያን ዕለት ምሽት እንቅልፍ ሸለብ መለስ እያደረገን ማረፍ አቅቶን ነበር:: አቅመቢስነት፣ ንዴትና ተስፋ መቁረጥ ተሰማኝ፡ ከዚያ ክሪስን አየሁት።

ቀን የለበሰውን ልብስ እንደለበሰ ነው ከባዱን ወንበር በሩ አጠገብ አድርጎታል።በእጁ ደግሞ መቀስ ይዟል፡ አያትየው እንደገና ሳትታይ ገብታ መቀሱን እንዳትጠቀም መንገድ መዝጋቱ ነበር በእንቅልፍ ላይ ሆኖ እንኳን ከሷ እየጠበቀኝ ነው።

ወደ እሱ ስመለከት አይኑን ከፈተና ጥቃት ደርሶብኝ ሳይከላከልልኝ የቀረ መስሎት ዘሎ ተነሳ፡ በዚያ በተቆለፈ ክፍል ደብዛዛ ብርሀን አይኖቻችን ተገናኙ: ፈገግ አለና በቀስታ “ሰላም” አለኝ።

“ክሪስ እባክህ ተኛ! ለዘለዓለም ልትጠብቃት አትችልም” አልኩት።

“አንቺ ስትተኚ ልጠብቃት እችላለሁ”

“እንደዚያ ከሆነ ተራ እንግባ”
“ወንዱ ማነው አንቺ ወይስ እኔ? በዚያ ላይ እኔ ካንቺ የበለጠ በልቻለሁ''

“ምን አገናኘው?”

“አሁን አንቺ በጣም ቀጭን ነሽ፡፡ በዚያ ላይ ሌሊቱን ሳትተኚ ካደርሽ የበለጠ ቀጫጫ ትሆኛለሽ፡፡ እኔ ግን ትንሽ ክብደት ብቀንስ ምንም አይደል"

እሱ ራሱም ከክብደት በታች ነው: ሁላችንም እንደዚያ ነን፡ እና አያትየው የእውነት በሩን ለመክፈት ከፈለገች የሱ ክብደት ሊያስቀራት አይችልም እሱ አይሆንም ሲል አጥብቆ ቢቃወመኝም ከተኛሁበት ተነስቼ አብሬው ወንበር ላይ ተቀመጥኩ፡

“ግዴለህም. አንድ ላይ ከሆንን በተሻለ እንቋቋማታለን አሁን ሁለታችንም መተኛት እንችላለን"

አልኩትና እቅፍቅፍ ብለን ተኛን፡
ያለ አያትየው ያለ ምግብ ጠዋት ሆነ።

የረሀብ ቀናቶቻችን ያለማቋረጥ እያለፉ ነው በቅርቡ ቺዙና ብስኩቶቹ ያልቃሉ: ያን ጊዜ የበለጠ መሰቃየት እንጀምራለን
እኔና ክሪስ ውሀ ብቻ እየጠጣን ወተቱን ለመንትዮቹ እያስቀመጥን ነው ።

ምግቡአሁንም ስላልመጣ፣ ክሪስ አይኖቹ እምባ እንዳቀረሩ መቀሱን ይዞ ወደኔ መጣና የራስ ቅሌ እንዲታይ አድርጎ ከፊት ያለውን ፀጉሬን ቆረጠው፡ ክሪስ እንደዚያ ሲያደርግ መስታወት አላየሁም: የተረፈውን ረጅሙን ፀጉር
ጠቀለልኩትና የአንገት ልብሱን እንደ ጥምጥም ተጠቀምኩበት
እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ነገር አያትየው ፀጉሬ መቆረጡን ለማየት እንኳ አለመምጣቷ ነው ምግብ ወይም ወተት ወይም ፎጣዎች ወይም ሊያልቁብን
የሚችሉ እንደ የልብስና የጥርስ ሳሙና የመሳሰሉትን ነገሮች እንኳን አላመጣችልንም የመፀዳጃ ወረቀትም እንኳን። አሁን ላይ ውድ ልብሶች የተገዙልን ጊዜ የተጠቀለሉበትን ለስላሳ ወረቀቶች መጣሌ ቆጨኝ። ማድረግ የምንችለው ነገር ስላልነበረ hአሮጌዎቹ መፃህፍት ገፆች እየቀደድን መጠቀም
ነበረብን።

ከዚያ የሽንት ቤቱ ማጠራቀሚያ ተዘጋና ወደ ውጪ መፍሰስ ጀመረ።ቆሻሻው መታጠቢያ ቤቱን ሲሞላው ኬሪ መጮህ ጀመረች። የተደፈነውን ቱቦ መምጠጫ ስለሌለን ክሪስና እኔ ምን ማድረግ እንዳለብን ተጨነቅን፡ ሮጦ
የልብስ መስቀያ ሽቦ አመጣና ቀጥ እንዲል አድርጎ መተላለፊያውን የዘጋውን
ነገር ወደታች ለመግፋት ሞከረ፡ እኔም ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄጄ ፈሳሹን የምጠርግበት አሮጌ ልብሶች አመጣሁ።

የሆነው ሆኖ ክሪስ የልብስ መስቀያ ሽቦውን በመጠቀም ሽንት ቤቱ እንደገና መስራት እንዲችል አደረገ ከዚያ ቃል ሳይናገር አጠገቤ በጉልበቱ ተንበርክኮ ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ሻንጣዎች ውስጥ ባመጣሁት ጨርቆች ወለሉን
አብረን ማፅዳት ጀመርን።

አሁን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባለው ሚስጥር ላይ ቆሻሻና የሚሸቱ ጨርቆች በሻንጣዎቹ ውስጥ በመክተት ሌላ ሚስጥር ጨመርንበት....

ይቀጥላል
👍3216🔥4😢2👏1
አትሮኖስ pinned «#የጣሪያ_ስር_አበቦች ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #ትርጉሜ_ሀኒም_ኤልያስ “እንዲያውም የእህትህን ቆንጆ ፀጉር የምትሸልተው አንተ መሆን አለብህ!” ብላ ሚስጥራዊ ፈገግታ ብልጭ አደረገችና በመልበሻው አናት ላይ መቀሱን አስቀመጠች: “ተመልሼ ስመጣ እህትህ ፀጉሯ ተቆርጦ ካገኘሁ ብቻ አራታችሁም ምግብ የማግኘት እድል ይኖራችኋል።" ስትል ክሪስ እኔ ላይ፣ እኔም ክሪስ ላይ እንዳፈጠጥን ጥላን ሄደች:...…»
በህይወት መንገድ ላይ……
( ታጋቾቹ)

ምዕራፍ-2
በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
///
እንደምንም ከተቀመጥኩበት ተነሳውና ቆምኩ ….ራመድ ራመድ ብዬ ተንቀሳቀስኩ.‹‹ሰላም ነሽ…?ምንም ጉዳት አልደረሰብሽም…?››አዲሷን ልጅ ነው የጠየቅኩት
‹‹ደህና ነኝ መሰለኝ..ግን ምንድነው የሆነው .?ማለቴ ህልም አይደለም አይደል?፡፡››እያለች በቀስታ ተነሳችና እኔ እንዳደረኩ በማድረግ ደህንነቷን አረጋገጠች››
ቀድማ ተነስታ በአፈር የተበከለውን ቀሚሷን እያራገፈች ያለችው አይዳ‹‹ እኔም ደህና ነኝ››አለቺኝ የአሽሙር ለዛ ባው ንግግር፡፡
እሷን ችላ አልኳትና አዲሷን ልጅ ‹‹ህልም ይሁን አይሁን እርግጠኛ አይደለሁም…››ስል መለስኩላት፡፡
‹‹እናንተስ ጋሽ አህመድ?››
‹‹አረ በአላህ….ምንድነው የሆነው?››
‹‹ተገላገልን ….በአቆራጭ ወደገነት እየተጓዝን ሳይሆን አይቀርም››በሪሁን ነው የተጋጋጠ እጁን እያሻሸ የተናገረው፡፡
‹‹.ሁላችንም አለመሰበራችንና አለመቁሰላችንም አንድ ነገር ነው፡፡››አልኩ
‹‹አለመቁሰላችንን ነው እንዴ ያያችሁት ….እሙሙዬ እኮ ቀላል አፈር አልቃመችም››ያቺው አይዳ ነች መላሿ
‹‹አሁን ምን እናድርግ?.››ጋሽ አህመድ ናቸው ተናጋሪው
‹‹ቆይ ሀሳብ መጣልኝ፡፡›እልኩና እጄን ወደኪሴ በመስደድ ሞባይሌን አወጣው ..ለመደወል ሞከርኩ …ምንም አይነት ኔት ወርክ የለም፡፡
‹‹አረ ምንም አይነት ኔት ወርክ የለም*››

ከአይዳ በስተቀር አራታችንም በየኪሳችን ሞባይላችን ይዘናል…የሁላችንም ግን ኔትወርክ ባዶ ስለነበር ለመደወልንና እርዳታ ለማግኘት አልቻልንም፡፡

‹‹ቆይ ጉድጓድ በጣም እሩቅ ነው እንዴ?››አዲሷ ልጅ ጠየቀች

‹‹እኛ ምናውቀው ጉድጓድማ ስድስት ሜትር ብቻ ነው፡፡ ይሄ ግን ጉድጓድ ጭምር ነው ተንዷ የሰመጠው...ወደታች ስንወርድ ረጂም ደቂቃ ነው የወሰደብን…. ምን አልባት 20 እና 30 ሜትር ወደውስጥ ሳንሰምጥ አልቀረንም...በጣም የሚገርመው ግን እዚህ አካባቢ ያለው መሬት አለታማና ድንጋያማ ነው፣እንዴት እንዲህ አይነት ነገር ሊከሰት እንደቻለ ለእኔ እንቆቅልሽ ነው ››ግምቴን ተናርኩ

‹‹እንደዛማ ከሆነ አልቆልናል በለኛ....ነግቶ እስከሚያዩን ድረስ ማንም አይደርስልንም ማለት ነው...ዘበኞቹም ወጥተን የሄድን ነው የሚመስላቸው" ጋሽ አህመድ ነው ስጋቱን የተናገረው፡፡

‹‹አሁን ተረጋግተን ማሠብ አለብን ››አልኳቸው እንዴት መረጋጋት እንደለብን እኮ ለራሴም አላውቅም።

አይዳ‹‹እሺ እንረጋጋ እውነትህን ነው›› ብላ ባለችበት ቁጢጥ አለች።

በሪሁን ከፊት ለፊታችን ወደ ወደቀው የ foothing ብረት ተንቀሳቀሰ….. ቀበቶው ላይ የሻጣውን ጉጠት አወጣና ስሩ ሲደርስ በርከክ በማለት በጉጠት እየተጠመዘዙና እርስ በርስ የተሳሰሩትን ብረት ለማላቀቅ ሽቦዎችን መፍታት ጀመረ ....እንደምንም አንድነጠላ ብረት አላቀቀ።ቀጥ አድርጎ ማቃናት ግን አይሞከርም።ብረቱ እንዳለ አጥብቆ ይዞ ከበላያችን ያለውን ከተቀረቀረው አለት ጎንና ጎን የተሠገሠገውን አፈር መግርጎር ጀመረ..እንግዲህ እንደገባኝ እቅዱ አፈሩ ተቦርብሮ ወደታች በመውረድ ከላይ ከመጣንበት የመሬት ወለል የሚያገናኝ ጭላንጭል ቀዳዳ ቢሆንም ማግኘት ነው።ሳስበው ጥሩ እቅድ ነው…፡፡

የታሰበው ቀዳዳ ከተገኘ ቢያንስ …. ኡ ኡ ብሎ በመጮህ ከላይ እርዳታ ለማግኘት ወይም ለምንደውለው ስልክ የሚሆን የሚቆራረጥም ቢሆን ኔት ወርክ ለማግኘት ይረዳን ይሆናል…ከዛም አልፎ በጣም እድለኞች ከሆን ደግሞ እንደምንም በመቧጠጥ ቢያንስ አንዳችን ወደላይ መውጣት እንድንችል ይረዳን ይሆናለል፡፡

በእውነት እቅዱ ጥሩ ነበር ግን ከላይ ያለውን አፈር በነካካነው መጠን አፈሩ ወደታች እየረገፈ በምትኩ ኮረትና ትላልቅ ድንጋይ እየመጣ በመሸንቀር እና በመጠቅጠቅ ክፍተቱን መድፈን ጀመረ …እንደውም ሲታይ ይበልጥ የታሰበበት ግንባታ መሠለ...ጋሽ አህመድና በሪሁን ተስፋ ከልቆረጡም፤ በእልክና በንዴት መናዳቸውን ቀጠሉ .

ድንገት የሆነ ከሰይጣን እጅ አፈትልኮ የወጣ የሚመስል አለት ድንጋይ ተምዘግዝጎ የበሪሁንን መሀል ጭንቅላት ላይ ቧ ብሎ አረፈ...ዋሻው ተናጠ…ወደኃላው ዘፍ ብሎ ወደቀ…….ዝርግትግት …ፀጥ..አለ…፡፡ ከጭንቅላቱ በቀይና በጥቁር መካከል ቀለም ያለው ደም ቡልቅ ቡልቅ እያለ ወለሉን አጠበው…..ሁለቱ ሴቶች እሪታቸውን አቀለጡት …አንደኛዋ ከጭንቅላቱ አንደኛዋ ከወደእግሩ ከበቡት…አይዳ እየተንቀተቀጠች አዲሷ ልጅ ደግሞ በመንሰቅሰቅ ላይ ነች፡፡ ..ጋሽ አህመድ ሲሰራበት የነበረውን ብረት ጥሎ ስሩ በርከከ ብሎ በህይወት መኖሩንና አለመኖሩን እጁን አንገቱ ጋር በመነካካት ለማረጋገጥ እየሞከረ ነው…..
ጌታ ሆይ ከአሁኑ የአንድ ሰው ህይወት አጣን ማለት ነው…..?ስል ደንዝዤ በቆምኩበት አሰብኩ …..መላ ሰውነቴ ልቆጣጠረው በማልችለው ፍርሀት እየተንቀጠቀጠ ነው፡፡ እንግዲህ እንዲህ እንዲህ እያለ የሁላችንም ፍፃሜ በቅርብ አንደሚሆን መገመቱ ቀላል አይደለም፡፡

አዲሷ ልጅ መሬት ላይ ዘርፍጥ ብላ ቁጭ አለችና ጭንቅላቱን ሰቅስቃ በማንሳት ታፋዋን እንደትራስ በማመቻቸት አስተካክላ አስቀመጠችው… አይዳ ጭንቅላቷ ላይ ያለውን ነጭ ሻሽ መዥርጣ አነሳችና በስነስርአት አጣጥፋ በተፈነከተው ጭንቅላቱ ላይ በማድረግ ዙሪያው እየጠመጠመች አሰረችለት….ቀስ በቀስ የሚፈሰው ደም ቆመለት…..ከምን ያህል ደቂቃ ብኃላ እንደሆነ አላውቅም ከገባበት ኮማ ነቃ፡፡

"እ ምን ሆኜ ነው?"ጠየቀ

አዲሷ ልጅ በደስታ ፊቷ በርቶ‹‹ወይ ተመስገን …በእየሱስ ስም …በህይወት አለህ አልሞትክም...››አለች፡፡

"ይሞታል ብለችሁ ነበር እንዴት? ››በመገረም መለሰ

‹‹አዎ በደንብ አስበን ነበር..እኔማ መቼም አይድንም ብዬ ተስዬ ነበር….››

‹‹ምን ብለሽ››በሪሁን ጠየቃት፡፡

‹‹ካተረፍከው ባለፈው ጠይቆኝ እምቢ ያልኩትን እሰጠዋለው ብዬ››

‹‹በምስክር ፊት ነው…..እንዳትክጂ››

‹‹አንቺም እምቢ ትያለሽ እንዴ?››አልኳት በንግግራቸው መካከል ጣልቃ ገብቼ …እንደዛ ያልኳት ለዛ በሌለው ጫወታዋ ላሸማቅቃት ፈልጌ ነበር…..

እሷ እቴ‹‹አልፎ አልፎ…..እምቢ ልል እችላለው….ለማንኛውም ጠይቅና አረጋግጥ››አለችኝ

በሪሁን እንደምን ከተጋደመበት ለመነሳት ሞከረ...ግን ጭንቅላቱ ግን ከበደው መሰለኝ ወደ ነበረበት ተመለሰ‹‹የእውነት ተጎድቼያለው እንዴ?››
‹‹አዎ...ለ20 ደቂቃ እኮ እራስህን ስተህ ነበር...ትንፍሽ አልነበረህም..በዛ ላይ ጭንቅላትህ ተፈንክቶ በመከራ ነው ደሙን ማቆም የቻልነው"አዲሷ ልጅ አብራራችለት

‹‹እውነቷን ነው እንዴ ?››ብሎ እጁን ወደ ጭንቅላቱ ሰዶ መዳበስ ጀመረ…
‹‹እንዴ የምን ጨርቅ ነው?››
መቼስ እዚህ ቁስል ማፅጃ አልኮል እና ማሸጊያ ባንዴጅ እንደማናገኝ ታውቃለህ… ዝም ብዬ ነው በሻሼ አጥብቄ ያሠርኩልህ…ደግሞ ሁለት መቶ ብር የተገዛ ሻሽ ነው…እንውጣ እንጂ አፍንጫህ ይዤ ነዋ የማስከፍልህ"

‹‹አሁን ምን እናድርግ›› ጋሽ አህመድ ነው መልሶ ስለመፍትሄ ፍለጋ ጥያቄ ያነሳው፡፡
👍153😢1