አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
‹‹ያለእቅድ መንቀሳቀስ ህይወት ሊያስከፍለን ነበር ...አሁን አረፍ ብለን እንረጋጋ ..እሱም ከህመሙ ጥቂት ያገግም ...በዚህ መካከል እግዜር የሆነ ተአምር ሊልክልን ይቾል ይሆናል።
አለችን››
‹‹በሰላም ሀሳብ እኔም እስማማለው›› አለች አይዳ
‹‹ስሟ ሰላም ነው ….ይሄንን ስም ደጋግሜ ሰምቼዋለው …እንዴት ልዘነጋው ቻልኩ?››
ማንም የተካራከራ የለም..በእያበራን ያለነውን ባትሪ አጥፍተን በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሁላችንም ጥግ ይዘን ተጠጋግተን በመቀመጥ በየራሳችን ሀሳብና ጭንቀት ተዋጥን፣እስኪ እኔም አብረውኝ ስለታገቱት አራት ሰዎች ፀባይና አጠቃላይ አካላዊ ሁኔታ በመጠኑ በማወቀው ልክ ልንገራችሁ፡፡

በሪሁን ጠይም ቀጭንና ሞጋጋ ቢጤ ነው፡፡ግን ጫወታ አዋቂና ሰውን ወደራሱ በፍቅር የመሳብ አስማታዊ ማግኔት ያለው ሰው ነው፡፡ጫወታው አፍ ያስከፍታል ይላሉ ለእኔ ግን ቀልዶቹ አንድም ቀን ገብተውኝ ወይም እሰፈግገውኝ አያውቁም ፡፡እንደውም ከሚገባው በላይ ነው የሚያበሳጩኝ….በሪሁንን ብዙ ጊዜ ሰበብ ፈልጌ ከስራ ላባርረው አቅጄ ነበር ግን በሁለት ዋና ዋና ምክንያት አልተሳካልኝ…አንደኛው በስራው ጥንቅቅ ያለ ባለሞያ ነው….እሱ ብቻ ሳይሆን በሱ ስር ያሉ ፌራዬዎች ብዙ ተመሳሳይ የኮንስትክሽን ድርጅቶች ሊያስኮበልሏቸው የሚሞክሮቸው ግን ደግሞ ከሱ ላለመለየት ብለው ታምነው የሚሰሩ ናቸው…ሌላው ምክንያት ከሪዞልቱ ባለቤት ጋር ያለው የተለየ ቀረቤታ ነው…ሴትዬዋ ስራውን ለማየት እዛ ሳይት በተገኘችበት አጋጣሚ ሁሉ ከእሱ ጋር ሳታወራና ሳትስቅ ሄዳ አታውቅም..አንድአንድ ቀን እንደውም እኛን ሁሉ ችላ ብላ እሱን ምሳ አባላኘ ብላ ይዛው ትወጣለች፡፡እና እሱን ማባረሩን ከልብ ብፈልግም በእነዚህ ሁለት ምክንያቶች አላደረኩትም….
የምሳ ሰዓት ሁሉም ሰራተኛ በተለይ ሴቶቹ የምሳ ዕቃቸውን እየያዙ እሱ ወዳለበት በሽቅድምድም ነው የሚሄዱት፤ደግሞ የሚገርመኝ ባለትዳሯም ትዳር አልባውም በሱ ዙሪያ ለመኮልኮል ልዩነት አለማሳየታቸው ነው፡፡እሱ ብዙውን ጊዜ ስራዬ ብሎ ምሳ ይዞ አይመጣም…እንዷ አንድ ጉርሻ ሌላዋ በሞቴ ብላ ሌላ ጉርሻ ስታጎርሰው የሁሉን ጉርሻ ከማዳረሱ በፊት ይጠግባል፡፡ …አንቺን ነበር ማግባት……አንቺ ደግሞ ይሄን ሞያሽን ነገም ከደገምሽ ለእኔ ባይሆን እንኳን ለወንድሜ እድርሻላው ፡፡መሰል ቀልዶችን በመወርወር ሴቶቹን በተሰበሰቡበት ጥሎ ከመካከላቸው ሹልክ ብሎ ወደወንዶቹ ይሮጣል፡፡እዛም የሚጠብቀው አቀባበል የተለየ አይደለም፡፡በሬ ብና በእኔ ሂሳብ ነው ጠጣ….ማታ ድርፋት ጋብዝሀለው እንዳትጠፋ…ይፎካከሩበታል፡፡

ጋሽ አህመድ ከሁላችንም በእድሜ አንጋፍ ነው...በአብዛኛው ሰው ጋሽ አህመድ እየተባለ ነው የሚጠራው...በግምት ከ45_50 አመት ይሆነዎል"ግን በስራ የጎለበተ ስለሆነ የሠውነት አቋሙ ጥብቅ ነው።ከቴክኒክ እና ሞያ ማሰልጠኛ በቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን ዲፕሎማ ያለው ሲሆን የእድሜውን አጋማሽ በዚህ ስራ ያሳለፈ በመሆኑ ሙሉ ፎርማን የሚባል ሰው ነው። ከእሱ ጋር መስራት መባረክ ነው።ጋሽ አህመድ በሰውነት አቋሙ ግዙፍ ነው….የቀይ ዳማ ሆኖ ጥቅጥቅ ፀጉር ያለው ባለ ግርማ ሞገስ ደስ የሚል ሰው ነው፡፡

ለስራ ጉዳይ ሳይት ውስጥ ጎን ለጎን እየተራመድን ስናወራ አዲስ የሚያየን ሰው እሱ ሀለቃዬ ሆኖ የስራ ትዕዛዝ እየሰጠኝ ወይም የፕሮጀክቱ ባለቤት ሆኖ ስለተሰራው ስራ ሪፖርት እያቀረብኩለት እንደሆነ ነው የሚገምተው፡፡ከጋሽ አህመድ አጠቃላይ ሁኔታ የማደንቅለት አንድ ነገር ቢኖር ለሆነ ስራ ሰዎችን የማስተባር ችሎታውን ነው፡፡በቃ መሰራት ያለበት የሆነ ስራ ካለ ቅደም ተከተሉን ለእሱ ማስረዳት ብቻ ነው..ሌላውን እሰተባብሮና አነቃቅቶ በተገቢው ጥራትና በተፈለገው ሰዓት ያደርሳል…ለዚህም በጣም የማከብረው ሰው ነው….ይሄንን ግን በግልፅ ነግሬው አላውቅም፡፡

ሌላዎ ሠላም ነች ..ስሞንም በቅጡ ያወቅኩት ዛሬ አሁን እዚ ወጥመድ ውስጥ ከገባን ብኃላ ሲጠሯት ስለሠማው ነው።በኘሮጀክታችን ከተቀጠረች ገና 15 ቀኗ ነው።እንደአጋጣሚ ሆኖ ዘመዴ ነች ብሎ ያመጣትም ባለቤቷን ጨቅጭቆ ዋስ ሆኖ ያስቀጠራትም በሪሁን ነው።እስቶር ሆኖ የሚሰራ ሰው ብዙ ንብረት በሀላፊነት የሚረከብ ስለሆነ የቤት ካርታ ዋስ ሳያመጣ የሚቀጠር ሰው አልነበረም ...በሪሁን ግን ይሄንን አሰራር አስትቶ በመታወቂያ ዋስ ብቻ አስቀጥሯታል። ሰላም ስትታይ ከሁላችንም ልጅ ትመስላለች ምናልባት 21 ወይም 22 አመት ቢሆናት ነው :: የተኮሳተረ ፊቶ የ50 አመት የሠለቻት ሴት ያስመስላታል ።ቆንጆ የምትባል አይደልችም ግን ደግሞ የደነደነ ሰውነትና ማራኪ ቅርፅ አላት፡፡ ከሁሉም በላይ ሰላም ጥልቅ መንፈሳዊ እና ቁጥብ ተናጋሪ ነች፡፡

አይዳ ጋ ደረስኩ…በሪሁንን እጠላዋለው ብያችሁ ነበር አይደል …..አይዳን ደግሞ በጣም በጣም ነው የምጠላት….ለዛም ነው ሰበብ ፈልጌ ከስራ ያሰናበትኮት.. ደሩ ምን ዋጋ አለ ጨርቆን ጠቅልላ ከአካባቢዬ እርቃ የምትሰወርበት ቀን ስናፍቅ እሷ ይሄው አሁን ከመሬት በታች አብራኝ ታግታለች….አይዳ ማንም የሚስማማባት ምጥን ቆንጆ ነች….በዝቶ ያልተዝረከረከ አንሶ ውይ እዚህች ጋ እንዲህ ቢሆን የማያሰኝ የተመጠነ ውበት አላት፣በዛ ላይ ከማውቃቸው ሴቶች ሁሉ ጀንትሏ ሴት ነች…ግን ደግሞ ጭንቅላቷን ሙሉ ለሙሉ ለጥፋት….ሰው ለማበሳጭጽ…ነገሮችን ለማውደም…..የሰውን ሞራል ለማንቀሻቀሽ ነው የምትጠቀምበት….ብላሽ የሆነች ብሽቅ ሴት ነች…እድሜዋን ከፈለጋችሁ 25 የሚሆናት ይመስለኛል፡፡እንግዲህ አብረውኝ የተጋቱት ከሞላ ጎደል እኚ ናቸው፡፡

ዋናው ጥያቄ አምስታችንም ከዚህ ወጥመድ በተአምር እንተርፍ ይሁን…..?ስንቶቻችን ሞተን ስንቶቻችን እንተርፍ ይሆን….?.እኔስ ከሞቾቹ ነኝ ወይስ ከተራፊዎቹ…?.ነው ወይስ ሁላንም በቀናቶቹ ውስጥ ታሪክ ሆነን እዚሁ ከቢሾፍቱ ሀይቅ ጠርዝ ከምድር ከርስ ስራ ተቀብረን ለዘላለም እንቀር ይሆን…?አዎ ዋናው ጥያቄ ይህ ነው፡፡ጊዜ ብቻ የሚመልሰው ጥያቄ….


ይቀጥላል....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️
👍17👏1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳቤላ ከላይኛው ከተማ ምሽጎች ትንሹ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራው ቦታ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጣለች - ሚስተር ካርላይል ወደ ቤቱ ከተመለሰ 0ሥር ቀን ያህል አልፎታል በጤናዋ በኩል ጉልህ የሆነ መሻሻል አድርጋለች
በጥንካሬዋ የታየው ለውጥም ለማመን የሚያስቸግር ነበር ከቤቷ ወጥታ የእንግሊዛዊያኑን የመቃብር ጽሑፍ እየተዘዋወረች ስታነብ ቆየችና በመጨረሻ ልትሔድ ስትል ለማሪፍ ተቀመጠች እንደ ሁልጊዜው በእግር ስትንሸራሸር ፍራንሲዝ ሌቪስን አሁንም አብሯት ነበር እሱን አራግፋ መጣል አልሆነላትም። የመውጫ ሰዓቷን ብትለውጥ የምትሔድበትን መንገድ ብትቀይር ዱካዋን ፈልጎ ከች ይልባታል ምናልባት እሷ
እንደጠረጠረችው አስቀድሞ በመምጣት ከምቹ ቦታ እየሆነ ይጠባበቃት ኖሮ ይሆናል እሷም ቁርጥ ያለ ነገር ነግራ ዳግመኛ እንዳይመጣባት ለማድረግ አልቻለችም ቢጠይቀኝ ምን ምክንያት ልሰጠው ነው? የሚል ጭንቀት ይመጣባታል " መሰጠት ያለበትን ምክንያት ደግሞ ልትሰጠው ቀርቶ ልታስበው አትፈልግም ምንአባቱ እንግዲህ የቀረኝ ትንሽ ቀን ነው ወደ ቤቴ የምሔድበት ጊዜ ደርሷል ብላ
በማሰብ ራሷን ታጽናናለች ነገር ግን እሷ ይህን ታስብ እንጂ ከሱ ጋር መገናኘቷ እየቀጠለ •እየረዘመ ሲሔድ የራሱን ፍሬ ማፍራት ጀመረ " ብቅ ባለ ቁጥር ፊቷ
ልውጥ ልቧ ድንግጥ ይልባታል ላለመደንገጥ ላለመሸበር ብዙ ጊዜ ብትሞክርም ነፋስን እንዳይነፍስ ለማድረግ እንደ መሞከር እየሆነባት ተቸገረች።

ጊዜው መሽቷል ቅዝቃዜው የሞቃቱ የሐምሌ ማታ አይመስልም" ከነፍሳት ልዩ ልዬ ጥዝታና ጭርጭርታ በቀር ምንም ድምፅ አይሰማም " ወይዘሮ ሳቤላ አመፀኛው ልቧ በራሱ የደስታ ስሜት እየመታ ከጓዶኛዋ ጋር ጸጥ ብለው ተቀምጠዋል
በውስጧ የጠነከረባት የሕሊና ድምፅ ባያስቸግራት የትክክለኝነትና የጥፋተኝነት
ፍርድ ባይደቀንባት ባጭሩ ሚስት የመሆኗ ነገር ባይከብዳት ኖሮ የነበረው ዝምታ ሳይነካ እሷም ከተቀመጠችበት ንቅንቅ ሳትል እሱም ከጐኗ እንዳለ እስከ ዘለዓለም ቢቀጥል የምታገኘውን የሚያረጋ ደስታ ታስብ ጀመር "

“ትዝ ይልሻል እመቤት ሳቤላ ?” አላት „ “ ልክ እንዶ ዛሬው በመስለ ሁኔታ አባትሽ : ሚስዝ ቬን አንቺ ' እኔና ሌሎችም ሆነን ሪቸመንድ የሔድን ጊዜ ''

“ አዎን ትዝ ይለኛል " ጥሩ ቀን ነበር የዋልነው " ሁለቱ ሚስ ቫሎነሮች አብረውን ነበሩ " አንተ ሚስዝ ቬን በሠረገላ ወደ ቤቷ ወሰድካት እኔ ከአባባ ጋር
ሔድኩ " በኃይል እየነዳህ ሰለ አስደነገጥካት • ሁለተኛ አንተ ሠረገላ ላይ እንደማትሳፈር ከቤት ከተመለስን በኋ ነገረችህ "

“ የማትጨክነውን እኮ ነው በተናገሩት ከማይረጉ ተገለባባጮችና ታይታ ወዳድ ሴቶች ሁሉ ኤማ ማውንት እስቨርንን የሚያህል የለም አሁንም “ ኤማ ማውንት
እስቨርን” ተብላ ማዕረግ ጨምራ እንኳን ያው ነች ከመዳራት በቀር ሌላ ቁም ነገር የላትም እኔም በዚያን ጊዜ በኃይል የነዳሁት ሆነ ብዬ እሷን ለማስደንገጥ ነበር

" ምን አደረገችህ ?

"በጣም አናደደችኝ " እኔ ሌላ ወዳጅ ስፈልግ እሷ የግድ ከላዬ ተጠምጥማ ከላዬ አልለቅም አለችኝ "

"ብላንሽ ሻሎነርን ነበር አንተ የፈለግህ?

“ብላንሽ ሻሎነር ?!” አለና ጮኸ ካፒቴን ሌቪሰን » እሷ ደግሞ ምኔ ናትና? ”

ሳቤላ ያሥራ ስባት ዓመት ቆንጆ ከነበረችው ከመልከ መልካሚቷ ከብላንሽ ሻሎነር ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንደ ነበረው አስታውሳ “ምነው ሚስስ ቬን ከሷ ጋር ብርቱ ፍቅር ይዞሃል ብላ ታማህ አልነበረም ?

“ እሷ እንኳን ከብላንሽ የበለጠ በሌላ ስው ነበር ስሜን የምታነሣው ” አላት ማንን ለማለት እንዶሆነ ለመገመት በሚያመች አነጋገርና አስተያየት "

“ እና ደግሞ የቅናት ግምቷ አለቦታው ያላረፈ አልነበረም " እኔም ልለው የፈለግሁት ብላንሽ ሻሎነርን አልነበረም " አንቺስ በዚያን ወቅት የተሻለ መገመት
አትችይም ነበር ? " አላት ወደሷ ዞር ብሎ "

ምን ለማለት እንደ ፈለገ በድምፁ አነዛዘርም ሆነ በዐይኑ አመለካከት ስለገባት መልኳ ሲለዋወጥ ተስማትና ፊቷን ወደ ሌላ አዞረች "

“የዱሮ ነገር ኣልፏል ተመልሶ ሊመጣ አይችልም በጊዜው ግን ሁለታችንም የየዕድላችንን ተውተን አሳልፈነዋል " ለመፋቀር የተጠሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ ቢባል አንቺና እኔ ነበርን እንዲያውም ያን ጊዜ የልቤን ሐሳብ የምታነቢው ይመስለኝ ነበር "

ለጊዜው ድንግጥ ብላ በዝምታ ከቆየች በኋላ ኮስተር ብላ አቋረጠችው ::

“ ልናገር እንጂ. . .ወይዘሮ ሳቤላ ጥቂት ቃላት ልናገርና ከዚያ በኋላ ለዘላለም ምንም አልተነፍስም - ብችል ኖሮ ያን ጊዜ አሳልፌ አልሰጥሽም ነበር " ነገር ግን
ያልተደላደለው ሁኔታዬና ዕዳዎቼ ሚስት እንዲኖሬኝ አላስቻሉኝም ቁልቁል ..ተጫኑኝ ስለዚህም የሎርድ ማውንት እስቨርንን ልጅ
ለማግባት እንድጠይቅ ከሚያበቃ
ደረጃ እንዲያደርሰኝ ሰር ፒተርን በመለመን ፈንታ ተስፋዎቼን በውስጤ ከለከልኳቸውና ከእጄ አምልጠሽ ስትሔጅ “ዐይኔ እያየ ዝም ብዬ ሰደድኩሽ » ”

“ እኔ ይኸን ነገር ለመስማት አልፈልግም ካፒቴን ሌቪሰን " አለችና ተቆጥታ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች "

እንድትቀመጥ ክንዷን ነካ አድርጎ ባክሽን ትንሽ ልንግርሽ " ለምን እንዳመለጥሽኝ እነግርሻለሁ እያልኩ ከተመኘሁ ብዙ ዘመኔ ነው ሌላ ስለ ወሰደሽ እስከ ዛሬ ሆድ ሆዴን ሲያቃጥለኝ ይኖራል የሌላ ሚስት በመሆንሽ ቁርጤን ዐውቄ እስካርፍ ድረስ ምን ያህል እወድሽ እንደ ነበር መግለጽ ያቅተኛል ያ ፍቅር ዛሬም ከልቤ አልጠፋም " ሙሉ በሆነ ልባዊ ስሜት እወድሻለሁ አላት »

" እንዴት እንደዚህ ደፍረህ ትናገረኛለህ ? አለችው "

የትዳር ኃላፊነትና ግዴታ ስለነበረባት ተቆጣች ተጀነነችበት ነገር ግን ቆጣ ጅንን ትበል እንጂ ይህ አነጋገር በሌላ ወቅትና ሁኔታ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ለልቧ ታላቅ ሐሴት የሚሰጥ ይሆን እንደ ነበረ በመግንዘቧ ለቁጣው ንግግሯ ተቃራኒ የሆነ ኃይለኛ ስሜት ውስጥ ለውስጥ በሠራ አካላቷ ሲሯሯጥባት ተስማት "

የአሁኑ ንግግሬ እኮ ምንም ጉዳት የለውም ” አለና ካፒቴን ሌቪሰን ንግግሩን በመቀጠል ' ' ነገሩ ጊዜ ያለፈበት ነው » ባለትዳርነትሽን አንችም ሆንሽ እኔ መዝንጋት አንችልም ሁለታችንም የየራሳችንን የኑሮ ጎዳና መርጠናል ስለዚህ አንድ ጊዜ የያዝነውን ፈር አክብረን መያዝ አለብን በመካከላችን ያለው ባሕር ሊያገናኘን አይችልም
በራሴ ጥፋት አምልጠሽኛል እንግዲህ በየትም አልፈ ላገኝሽ
አልችልም ያን ግዜ እንደምወድሽ
እንደምፈልግሽ ልገልጽልሽ ሲገባኝ ራስሽን ከሚስተር ካርላይል እጅ ስትጥይ ዝም ብዬ አየሁሽ

ራስሽን ስትጥይ አልክኝ ? ብላ ቱግ አለች "ሚስተር ካርይል እኮ የምወደውና የማከብረው በራሴ ምርጫ ያገባሁትና እሱን በማግባቴም የምመካበትና
የማልጸጸትበት ባሌ ነው ኧረ ለመሆኑ አንተ ከሱ ጋር ብትወዳደር ከምኑ ትደርሳለህ!
ራስህንም ረስተኽዋል . . . ፍራንሲዝ ሌቪሰን

ከንፈሩን ነከስና “ የለም አልረሳሁም ” አላት

እንዴዚህ ብለህ ልትናገረኝ አትችልም » ከዚሀ ብቸኝቴን አይቶ የሰደበኝ ካንተ ሌላ ማን አለ ? ሚስተር ካርላይል ካጠገቤ ቢኖር እንዲሀ ብለህ ልትናገረኝ አትደፍርም ነበር ? በል ደኅና እደር ጌታዬ !
👍16🔥1
ደካማው ቁመናዋ በፈቀደላት መጠን በችኮላ ውንትር ውንትር
እያለች መንገድ ጀመረች እጁዋን በግድ ያዘና በክንዱ አድርጎ እባክሽ ያመለጠኝን ንግግር እርሽውና ይቅርታ አድርጊልኝ " ፊት እንደ ነበረው አዛኝ ጓደኛሽ : አሳቢ ወንድምሽ ሚስተር ካርላይል በሌለበት በችግርሽ የምደርስ እውነተኛ ወዳጅ አድርገሽ እይኝ

ይኽንማ ብዬ ነበር እንደ እንዶ ዘመድ አይቼ የቀረብኩሀ ” አለችው ግንባሯን ቋጥራ እጁዋን ከክንዱ ነጠቀችና " ይኸን ባላስብ ኖሮ አልቀርብሀም ነበር "
አንተ ግን ምላሹን እንዲህ አድርገኸው ዐረፍክ " ባሌ አንተ ያዴረግሀልኝን አስቦ
አመሰገነህ በዚU በእምነተ ቢሱ ልብህ የቋጠርከውን ሐሳብ ለማንበብ ቢችል ኖሮ ሌላ ዐይነት ምስጋና ነበር የሚሰጥህ " "

“ አሁንም ይቅርታሽን እለምንሻለሁ " ጥፋቴን ዐውቄዋለሁ አይደግመኝም ሁለተኛ እንደዚህ አላስቀይምሽም የፍቅር ስሜቶች የኑሮን ሥርዓት ጥሰው
ትዕግሥታችንና ይሎኝታችንን ጥለው በመውጣት በይፋ እንድንጋለጥ የሚያደርጉበት ጊዜ አለ ዕብደት ነው!አሁን ብዙ መንግድ ስለ ሔድሽ ደክሞሻል • ስለዚህ ባይሆን ይህንን ከባድ ቁልቁለት ደግፌ እንዳወርድሽ ፍቀጅልኝ " "

“ ይኸን በፊት ነበር ማሰብ የሚገባህ አሁን ተወኝ አልፈልግም " እለችው " አሱም የዘረጋላትን አጁን ሰብስቦ ከጐኗ እየሔደ ያለምንም ድጋፍ ከበሯ
ደረሰችና በኩርፊያ ገጽታ “ ደኅና እደር ! አለችውና ወደ ሆቴሎ አቅጣጫ ተመለሰ።

ሳቤላ ከሆቴሏ ገብታ ፒተርን ጀፍታው ዐለፈችና ከፎቅ ወጣች " በእመቤቷ አለ መኖር አጋጣሚ የክት ልብሷን ለብሳ በሳሎኑ መስኮት ስትዘባነን የነበረችውን
ዊልሰንን በድንግት ደርሳ አስደነጠቻት "

ዊልስን ...የጽሕፈት ጠረጴዛዬን ወዲህ በይልኝ ! ፈጠን በይ ” አለቻት ጓንቲዎቿን አውልቃ ያንገት ልብሷን አኖረች " ፒተርን ደግሞ ፖስታ ቤት የሚያዶርሰው ደብዳቤ ስለአለው ተዘጋጅ በይው " ወደ ኢንግላንድ የሚላከው ፖስታ ከመታሰሩ በፊት መድረስ አንደሚኖርበት ንገሪው "

ፍራንሲዝ ሌቪሰን ስለ ፍቅሩ ሲነግራት የበዳይነት ደስታ ምልክቶች ልቧን ስልብ ሲያደርጋት ተሰማት የስብከቱ አደግኝነትና ከዚህ ሰውም ግንኙነቷን
ባስትኳይ ማቋረጥ እንዳለባት ግልጽ ሆነላት " ስለዚህ እሱ ካለበት ምድር ለቃ ባሕር ተሻግራ ለመሔድ ቆረጠች ከዚያ ቦታ መቆየት ጭራሽ ስለ አልቻለች ባስቸኳይ እንዲመጣ ለባሏ ጻፈችለት እንዲያወም ለማንኛውም አስፈጊ ነገር ከፍላ ይተርፋት የነበረውን ገንዘብ ለመጓጓዣ ቢበቃት ኖሮ የሱን መምጣት ሳትጠብቅ ሳትሔድ አትቀርም ነበር ።

ሚስተር ካርላይል ደብዳቤው ሲደርሰው ግራ ተጋባ። ካርላይል እሑዱን እንደ ሚመጣና ከዚያ ስለ መቆየቷና ስለ መመለሷ እሱ ከደረሰ በኋላ እንደሚመካከሩበት
ወዲያው ጻፈላት ከፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ላለመናኘት ቆረጠችና ባሏ እስኪመጣላት ድረስ በሽፍን ሠረገላ ትወጣ ጀመር " አንድ ቀን ሊጠይቃት ቢመጣ ከሳሎን
እንዲገባ አድርጋ ከክፍሏ ሳትወጣ ፒተርን ላከችውና እሜቴ ምስጋኖቸውን አቅርበዋል ነገር ግን ዛሬ እንግዳ አይቀበሉም ” ብሎ እንዲነግር አዘዘችው "

ከዚያ ቀደም ብሎ መምጣት አልሆንለት አለና ሚስተር ካርላይል እሑድ ጠዋት ደረሰ ስድስቱን ሳምንት መጨረስ ስለሚገባት ምንም ቢሆን ሊወስዳት እንደማይችል ድርቅ ብሎ ተከራከራት እሷ ግን ምንም ቢሆን እንደማትቀር ቁርጡን ነገ
ረችው "

“ ሳቤላ...” አላት „ “ ምክንያትሽን ንገሪኝ" ለኔ እንደሚመስለኝ አንድ
ምክንያት አለሽ ። እዚህ በመሰንበትሽ በጣም ረድቶሻል ቸከኝ የምትዪው ነገር የልጅ ጫወታ ነው ከዚሀ የተለየ ምክንያት ካለሽ ንገሪኝ ” አላት "

የነበረውን ነገር ግልጽልጽ አድርጋ ልትነግረው ፈለገች ነግሩን አዙራ ስታየው ደግሞ የፍራንሲዝ ሌቪሰን ፍቅር ያገረሸባት መሆኑንና እሱም ምን ብሎ እንደ ተናገራት፡ ለባሏ መንገሩ ጥሩ ነገር ያለመሆኑ ተሰማት ከመጠን በላይ የምታከብረውን ባሏን ይኸን ደስ የማይል ነገር ነግራ ልታሳዝነው አልፈለገችም ኋላ ደግሞ በጉዳዩ
እንደገና አሰበችበት መንገሩ የበለጠ ከሚኮራባትና ከሚወዳት እንዲሁም ከማንኛውም አደጋ የበለጠ ተጠንቅቆ ከሚጠብቃት በቀር ሌላ ክፋት እንዳልነበረው
ታያት " ልትነግረው ስትል ሚስተር ካርላይል አንድ ደብዳቤ አውጥቶ ሰጣት ይህን በመሰለ እንደክር በቀጠነ ምክንያት ትልቁን ጉዳይ መልሳ ዋጠችው ሐሳቧን
ወደ ደብዳቤው መለሰች ደብዳቤው ከሚስ ካርላይል የተላከ ነበር

"አጻጻፉም እንደ ባለቤቱ እንደ ሚስ ኮርኒ ድርቅ ያለ ነበር “ ልጆቹ ደህና ናቸው ቤቱም በደንብ እየተካሔደ ነው" አንቺም በጎ እንደ ሆንሽ ተስፋ አለኝ ”
ከማስታወሻ ደብተር በተቀደዶ ወረቀት ሦስት ገጽ ሙሉ ቢሆንም ዋናው ወሬ ይኸው ነበር “ ብቻ” አለች ደብዳቤውን ስትዘጋ “ ባርባራ ሔር ከኛ ጋር ለመዋል አሁን ስለ ደረሰች ነው እንጂ ብዙ ልጽፍልሽ እችል ነበር " "

“ አሃ ! ባርባራ ሔር ከነሱ ጋር ልትውል ! ” ሳቤላ ያ ብቻ በቃት" ልቧንም እምነቷንም ከባሏ ዘጋች “ እኔ ወደ ልጆቼ መሔድ አለብኝ » ከእንግዲሀ ወዲህ ከነሱ ተለይቸ መቀመጥ አልችልም ” ብላ እያለቀስች ስትነግረው ' ' ግድ የለሽም አንቺ ወደ ቤትሽ መመለሱን እንደዚህ አጥብቀሽ ከፈለግሽ ከኔ ጋር ትመለሻለሽ ” ሲላት ልክ ከትምህርት ቤት እንደ ተለቀቀ ሕፃን በደስታ ፈነደቀች
" እንደ ልቧ መሣቅ መጫወት ጀመረች ባሏም ጥያቄዋን ስለ ተቀበላት በማመስገን እየመላለሰች ሳመችው በተለይም ከሱ ተለይታ መቀመጥ እንደማትችል ስትነግረው ለሱ የነበራትን ፍቅር መግለጿ መሆኑን አድርጎ ተረጐመው "

" ሳቤላ ” አላት በፈገግታና በፍቅር አመለካከት ወደሷ እያየ “ ያኔ ገና
አንደ ተጋባን እንደማታፈቅሪኝ የገለጽሽልኝና እኔም ፍቅር ቀስ በቀስ እያደገ እንደ ሚመጣ የነገርኩሽን ታስታውሻለሽ ? እንዳልኩሽም አሁን የመጣ መሰለኝ "
ሳቤላ በባሏ አነጋገር ፊቷ ተለዋወጠ ዕንባዋ መጣ ከፊቷ ግልጽ የሆነ ጭንቀት ታየባት ካርላይልም ያን ፈጣን መለዋወጥ ሲያይ · · አዎን ያልከው ደረሰ
ለማለት እንደ ፈለገች አድርጎ በመውሰድ ከደረቱ ዕቅፍ አደረጋት።

አንድ ቀን ብቻ ቀራቸው ከዚያ
አንድ ቀን -እሷና ያ ሰውዬ ሊለያዩ
ወዲያ በመካከላቸው ያለው ሰፊው ባሕር ይገላግላታል የመለየቷን ነገር ስታስበው እንድታመሰግን አደረጋት ። በርግጥ እሱን ጥላ መሔድ ማለት ፀሐይን ከኋላ ትታ ጨለማ ውስጥ መግባት ማለት መሆኑንና ለጊዜውም ቢሆን አገሯም ሆነ ቤቷ እሱ ከሌለበት ቀፋፊና ማስጠሎ እንደሚሆንባት ብታውቅም በመሔዷ በሙሉ ልቧ
ተደስተች " የመቤት ሳቤላ እምነት ኢያጠራጥርም " ቀና አስተሳሰብ አላት ትክክለኛ ሥራ ለመሥራት ትመኛለች ትጥራለች ክፉ ሥራ የምሯን ትጠላለች መንፈሷ ቅንና እውነተኛ ነው አስተላሰቧ ንጹሕ ነው ።

ካፒቴን ሌቪሰን መጥቶ ከሚስተር ካርላይል ጋር ተገናኘና ሰር ፒተርን ለማነጋገር ጊዜ አግኝቶ እንደሆነ ጠየቀው " ሚስተር ካርይል ግን በሥራ ብዛት አለመሞከሩን ከጥቂት ቀኖች በኋላ ግን በቂ ጊዜ ሊኖረው ስለሚችል እንደሚሞክርለት አስረዳው ።

ከቀትር በኋላ የባሕር ሞገድ ተነሣ ፎክስቶን የተባለችው ጀልባ በሰባት ሰዓት እንደምትነሣ ተገለጸ። ሚስተር ካርላይል ከሚስቱና ከሠራተኞቹ ጋር በሰዓቱ
ተሳፈረ " ካፒቴን ሌቪሰንም ወደቡ ድረስ አብሮ መጥቶ ወደ ጀልባዋ ሲገቡ ሰላምታ ሰጥቶ ተስናበታቸው " ወይዘሮ ሳቤላ ከመድረኩ ላይ ስትቀመጥ ባለቤቷ ከጐኗ ቁሞ ነበር " ገመዱ ተፈታና ጀልባዋ ተንቀሳቀሰች » ፍራንሲዝ ሌቪሰን ከድንበሩ
ቁሞ እንቅስቃሴውን ፡ በተለይ ደግሞ ሳቤላን ይመለከት ነበር "
👍13
ሌቪሰን ከዐይኗ ሲጠፋ በሠራ አካላቷ የተሰራጨው የእፎይታ ስሜቷ ከግር እስከ ራሷ አንቀጠቀጣት ሳታስበው የሚስተር ካርላይልን እጅ ጨምደድ አድርጋ ያዘችው "

“ በረደሽ እንዴ ? አላት አንገቱን ወደሷ ዘንበል አድርጎ "

“ ኧረ የለም ደኅና ተመችቶኛል በጣም ደስ ብሎኛል "

ታዲያ ምነው አንቀጠቀጠሽ ?”

ዛሬም ብቻዬን እዚያ ጥለኝ መጥጠህ ቢሆን ኖሮ ምን ይውጠኝ እንደነበር ሳስበው ነው ያንቀጠቀጠኝ " አርኪባልድ .... ካንተ ነጥለህ የትም እንዳትሰደኝ ሁልጊዜ ካጠገብህ እንዳትለየኝ »

የልመናዋን መልስ በመጠበቅ ይቁለጨለ የነበሩት ዐይኖቿን በፍቅር ስሜት ቁልቁል እየተመለከተ ፡“ ሁልጊዜ .. ሳቤላ ሁልጊዜ አልለይሺም ከኔ
ተለይተሽ በመሰንበትሽ ካንቺ የበለጠ የተጨነቅሁት እኔ ነበርኩ
ከቶ እንዴት ቃሉ ይጠረጠራል ይህ ሰው' ስትል አሰበች ....

💫ይቀጥላል💫
👍16
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


...አሁን ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ ባለው ሚስጥር ላይ ቆሻሻና የሚሸቱ ጨርቆች በሻንጣዎቹ ውስጥ በመክተት ሌላ ሚስጥር ጨመርንበት.

ስለ ሁኔታው አብዝተን ባለማውራታችን ከነገሩ እጅግ አስፈሪ መሆን አመለጥን:
ጠዋት እንነሳና ፊታችን ላይ ውሀ ረጨት እናደርጋለን። ጥርሶቻችንን በባዶ ውሀ እናፀዳለን፤ ጥቂት ውሀ እንጠጣና ትንሽ ወዲያ ወዲህ እንላለን፡ ከዚያ ጋደም ብለን ቴሌቭዥን እናያለን ወይም እናነባለን፡

መንትዮቹ ምግብ ፈልገው ሲያለቅሱ መስማቴ ህይወቴን ሙሉ ልቤ ላይ የሚኖር ጠባሳ አስቀመጠልኝ፡ አያታችንን እንዴት እንደጠላኋት። ያቺ አሮጊት እና እናታችን ይህንን ስላደረጉብን ጠላኋቸው።

የመመገቢያ ሰአታችን ያለ ምግብ ሲያልፍ እንተኛለን፡ ለሰዓታት እንተኛለን::እንቅልፍ ሲወስደን የርሀብ ወይም የብቸኝነት ወይም የምሬት ስቃይ አይሰማንም በእንቅልፍ በውሸት የደስታ ስሜት ውስጥ እንሰምጣለን ከዚያ
ስንነቃ ስለምንም ነገር ግድ አይኖረንም።

እንደ ፈዘዝኩና እንደደከምኩ ጭንቅላቴን ዞር አድርጌ ክሪስንና ኮሪን እያየሁ ነበር ከዚያ ክሪስ ከኪሱ ሰንጢ አውጥቶ የእጁን አንጓ ሲቆርጥ ያለምም
ስሜት ጋደም ብዬ እየተመለከትኩ ነው። የሚደማ እጁን ወደ ኮሪ አፍ አስጠጋና ኮሪ ቢቃወምም እሱ ግን ደሙን እንዲጠጣ አደረገው: ከዚያ የኬሪ ተራ ሆነ ሁለቱ ምንም ነገር ያልበሉ በመሆናቸው፣ የትልቁ ወንድማቸውን ደም ጠጥተው፣ በደበዘዘ፣ በፈጠጠና በተቀባይነት አይን አተኩረው ተመለከቱት።

ማድረግ ባለበት ነገር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰምቶኝ ፊቴን አዞርኩ። ያንን በማድረጉ አድናቆት ተሰምቶኛል። ሁልጊዜ ከባባድ ችግሮችን ማቃለል
ይችልበታል።

ከዚያ ክሪስ ወደኔ አልጋ መጣና፣ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ሲመለከተኝ ከቆየ በኋላ አይኖቹ ወደተቆረጠው አንጓው ዝቅ
አሉ አሁን መድማቱን አቁሟል። እኔም ደሙን ጠጥቼ ረሀቤን እንዳስታግስ ሌላኛውን ደም ስሩን ለማድማት ሰንጢውን አወጣ እንዳያደርገው ነግሬ ሰንጢውን ቀምቼ ወረወርኩት። ብርታት ለማግኘት ስል የእሱን ደም
እንደማልጠጣ ምዬ ተገዝቼ ብነግረውም መሀላዬን ከቁም ነገርም ሳይቆጥር ሰንጢውን በአልኮል ማፅዳት ጀመረ።

“ተመልሳ ባትመጣ ምንድነው የምናደርገው ክሪስ?" ስል ጠየቅኩት አያታችንን ለሁለት ሳምንት አላየናትም: አይጥ ለማጥመድ ወጥመዱ
ላይ ያደረግነውን ቺዝ የሚላስ የሚቀመስ ባጣን ጊዜ በልተን ጨርሰነዋል።ምግብ የሚባል ሳንቀምስ ሶስት ቀናችን ሆኗል፡ መንትዮቹ እንዲጠጡት
የተውንላቸው ወተትም ካለቀ አስረኛ ቀን ሆኖታል።

“በረሀብ አትገድለንም” አለ ክሪስ አጠገቤ ተኝቶ በደካማ ክንዱ እያቀፈኝ። “እሷ ያንን እንድታደርግ ከፈቀድንላት ደደቦች ነን ማለት ነው ነገ ምግብ ይዛ ካልመጣች ወይ ደግሞ እናታችንም ብቅ ካላለች አንሶላ ተልትለን መሰላል
እንሰራና ወደ መሬት እንወርዳለን” አለ፡

ጭንቅላቴ በደረቱ ላይ ስለሆነ ልቡ ሲመታ ይሰማኛል። “ምን እንደምታደርግ ታውቃለህ? ስለምትጠላን እንድንሞት ትፈልጋለች። መወለድ የማይገባን
የሰይጣን ልጆች መሆናችንን ስንት ጊዜ ነው የነገረችን?

ካቲ፤ ያቺ ጠንቋይ አሮጊት ደደብ አይደለችም: እናታችን ካለችበት ከመምጣቷ በፊት ምግብ ይዛ ትመጣለች::”

የተቆረጠ እጁን ላሽግለት ተንቀሳቀስኩ ከሁለት ሳምንት በፊት እኔና ክሪስ ለማምለጥ መሞከር ይገባን ነበር። የዚያን ጊዜ ሁለታችንም ጥንካሬ ነበረን
አሁን ብንሞክር ግን በእርግጠኝነት ወድቀን እንሞታለን፡ መንትዮቹን
በጀርባችን አዝለን ከሆነ ደግሞ የበለጠ ከባድ ይሆንብናል።

በማግስቱ ጠዋት ምንም ምግብ እንዳልመጣ የተመለከተው ክሪስ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል እንድንሄድ አስገደደን፡ እኔና ክሪስ ለመራመድ እጅግ ደክመው
የነበሩትን መንትዮች ተሸከምናቸው የመማሪያ ክፍሉ ጥግ ላይ ስናስቀምጣቸው አቅማቸው ስላልቻለ እንደመተኛት
እያሉ ግድግዳውን ተደግፈው ቁጭ አሉ። ክሪስ መንትዮቹን ጀርባችን ላይ የምናስርበትን ገመድ እያዘጋጀ ነው

“በሌላ መንገድ እናደርገዋለን” አለ ክሪስ እንደገና እያሰበ “በመጀመሪያ እኔ እሄዳለሁ መሬት ስደርስ ኮሪን ታስሪውና ቀስ እያልሽ ወደታች ትለቂዋለሽ
ቀጥሎ ኬሪንም እንደዚያው ታደርጊያለሽ: በመጨረሻ አንቺ ትመጫለሽ ስለ እግዚአብሔር ብለሽ የምትችይውን ጥረት ሁሉ አርጊ! አደጋ በሚደርስበት
ወቅት ከፍተኛ ንዴት ከሰው በላይ የሆነ ጥንካሬ እንደሚፈጥር ሰምቻለሁ።"

“አንተ የበለጠ ጠንካራ ስለሆንክ እኔ መጀመሪያ ልሂድ” አልኩት በድካም ስሜት “አይሆንም! ድንገት ፈጥነው ከመጡ ለመያዝ ታች መሆን አለብኝ ያንቺ ክንዶች የኔን ያሀል ጥንካሬ የላቸውም: ክብደቱ ሁሉ አንቺ ላይ
እንዳይሆን ገመዱን ጭስ መውጫው ላይ አስርልሻለሁ እና ካቲ ይvህ የአደጋ ጊዜ ነው!”

በአይጥ መያዣ ወጥመዱ ላይ አራት የሞቱ አይጦችን በድንጋጤ ተመለከትኩ።“ትንሽ ጥንካሬ እንድናገኝ እነዚህን አይጦች መብላት አለብን፡” አለ ኮስተር ብሎ፡ “ማድረግ ያለብንን ሁሉ ማድረግ አለብን::''

እነዚያን የሞቱ ትንንሽ ወፍራም ነገሮች በመጠየፍ እየተመለከትኩ “ጥሬ ስጋ? ጥሬ አይጥ? አይሆንም!" አልኩ በቀስታ:
በጣም ተናዶና አስገዳጅ በሚመስል አይነት መንትዮቹንም ሆነ ራሴን በህይወት ለማቆየት የሚያስፈልገውን የትኛውንም ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ነገረኝ፡ “ተመልከቺ ካቲ፣ መጀመሪያ እኔ ሁለቱንም እበላለሁ ገመዶቹን
በደንብ ለመቋጠርም የልብስ መስቀያ ስለሚያስፈልገኝ ላምጣ… ታውቂያላሽ ኬቲ እጆቼ አሁን በደንብ አይሰሩም” አለ፡

ሁላችንም በጣም ከመድከማችን የተነሳ የምንንቀሳቀሰው የግዳችንን ነው::

አየት አደረገኝና “በእውነት አይጦቹ በጨውና በበርበሬ በጣም የሚጣፍጡ ይመስለኛል” አለ፡፡

ጭንቅላታቸውን ቆርጦ ቆዳቸውን ገፈፈና አንጀታቸውን አወጣው: ትንንሽ ሆዳቸውን በመሰንጠቅ ረጃጅምና ቀጫጭን አንጀቶቻቸውን እንዲሁም ትንንሽ
ልቦቻቸውንና ሌሎች የውስጥ እቃዎቻቸውን ሲያወጣ እየተመለከትኩት ነበር ሆዴ ባዶ ባይሆን ኖሮ ሊያስመልሰኝ ይችል ነበር።

ክሪስ ጨውና በርበሬ ሊያመጣ ሲሄድ አይኖቼ ቆዳቸው ተገፍፎ ለምግብነት የተዘጋጁት አይጦች ላይ ተተክለው ቀሩ። አይኖቼን ጨፍኜ የመጀመሪያውን
ጉርሻ ለመጉረስ ሞከርኩ እርቦኛል ግን ይህንን ለመብላት የሚያክል አይደለም ረሀቤ።

ወዲያው እጅ ለእጅ ተያይዘው፣ ግንባራቸውን አጋጥመውና አይናቸውን ጨፍነው ጥጉ ላይ የተኙትን መንትዮች አሰብኩ በእናታችን ማህፀን ውስጥም እንደዚህ ተቃቅፈው የነበሩ ይመስለኛል: ምስኪን ልጆች! በአንድ ወቅት በጣም የሚወዷቸው እናትና አባት ነበሯቸው።

እነሱን በደህና መሬት ለማድረስና ከጎረቤት ምግብ ለማግኘት አይጦቹ ለእኔና ለክሪስ በቂ ጥንካሬ እንደሚሰጡን ተስፋ አድርገናል።

ክሪስ ቀስ እያለ ወደኛ ሲመለስ ሰማሁ። በሩ ላይ ቆም ብሎ አመነታ።ሽራፊ ፈገግታ እያሳየ ነው ሰማያዊ አይኖቹ ወደኔ እየተመለከቱ አንፀባረቁ።
በሁለት እጆቹ በደንብ የምናውቀውን ትልቅ የሽርሽር ቅርጫት ይዟል። ቅርጫቱ መክደን እስከሚያስቸግር ድረስ በምግብ ተሞልቷል ሁለት ትልልቅ
ፔርሙዞች አወጣ አንደኛው ውስጥ የአትክልት ሾርባ፣ ሌላኛው ውስጥ ወተት ነበረበት በማየው ነገር ግራ ተጋባሁ። እናታችን አምጥታልን ነው?
ከሆነ ታዲያ ለምን ወደታች እንድንሄድ አልጠራችንም? ለምንስ ደግሞ እኛን ፍለጋ ወደዚህ አልመጣችም?
👍252👏2
ክሪስ ኬሪን፣ እኔ ደግሞ ኮሪን ጭኖቻችን ላይ አስቀምጠን ሾርባውን በማንኪያ
ማጉረስ ጀመርን። ደሙን እንደተቀበሉት ሁሉ ሾርባውንም እየተቀበሉ ነው:: ሳንድዊቹንም እየቆረስን አበላናቸው: እኛም ተስገብግበን በላን፡ ክሪስ
እንዳያስመልሰን እያስጠነቀቀ ነበር።

ምግቡን ሁሉ ኮሪ አፍ ውስጥ መጠቅጠቅ ፈለግኩ። እሱ ግን ቀስ እያለ ነበር ይበላ የነበረው: አእምሮዬ ውስጥ በሺ የሚቆጠሩ ሀሳቦች ተመላለሱብኝ፡ ለምን ዛሬ ዛሬ ለምን ምግብ አመጣች? ለምን ትናንትና ወይም ከዚያ በፊት
አላመጣችም? ምክንያቷ ምንድነው? በመጣልን ምግብ እየተደሰትኩ መብላቴን ትቼ ነገር አብሰለስል ጀመር እፎይ ለማለት በጣም ተጠራጣሪ ሆኜ ነበር።

ክሪስ ቀስ እያለ ጥቂት ሾርባና ግማሽ ሳንድዊች በላ፡ የተሸፈኑትን ሁሉ ሲገልጥ ደቃቅ ስኳር የተነሰነሰባቸው አራት ዶናቶች ተመለከትን፡ ምንም አይነት ጣፋጭ ተሰጥቶን ለማናውቀው ለእኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ከምግብ በኋላ የምንመገበው ጣፋጭ ከአያትየው ተሰጠን። ይቅርታ የመጠየቂያ መንገዷ ይሆን: አላማዋ ምንም ይሁን ምን እኛ ግን የተረጎምነው በዚያ መንገድ
ነበር።

ጠኔ ሊይዘን በተቃረብንበት ሳምንት ውስጥ በእኔና በክሪስ መካከል ለየት ያለ ነገር ተከስቶ ነበር: በዚያን ቀን የተነሳሳበት ምክንያት ምናልባት እኔ የሞቀው ገንዳ ውስጥ በአረፋው መሀል ተቀምጬ እሱ ፀጉሬ ላይ ያለውን
ሬንጅ ለማስለቀቅ ልፋት ላይ ስለነበረ ሊሆን ይችላል
ከዚያ አሰቃቂ ቀን በፊት ለመንትዮቹ የወላጅነት ገፀ ባህርይ ወስደን ትወና የምንሰራ ወንድምና እህት ነበርን አሁን ግን ግንኙነታችን ተቀይሯል
ከአሁን በኋላ ትወና አንሰራም: ለኬሪና ለኮሪ ትክክለኛ ወላጆች ነን እነሱ የእኛ ሀላፊነት፣ የእኛ ግዴታ ናቸው እኛም ራሳችንን ሙሉ በሙሉ ለእነሱና ለእርስ በራሳችን ሰጥተናል።

አሁን ምንም ብንሆን እናታችን ለእኛ ግድ እንደሌላት ግልፅ ሆኖልናል።

ክሪስ የእናታችንን መለወጥ አስመልክቶ ምን እንደሚሰማው መናገር አይፈልግም፡ አይኖቹና ግድ የለሽ እንቅስቃሴዎቹ ግን የበለጠ ይናገራሉ።የእናታችንን ፎቶ አልጋው አጠገብ አስቀምጦ ነበር። አሁን ግን አንስቶታል:
እኔ ከማምናት የበለጠ ሁልጊዜ በእሷ ያምን ስለነበር በጣም የተጎዳው እሱ ነው እኔ ከታመምኩት በላይ እየታመመ ከሆነ እውነትም ስቃይ ላይ ነው:

አሁን ወደ መኝታ ክፍላችን መመለስ እንደምንችል ለማመልከት በወዳጅነት
መንፈስ እጄን ያዘኝ፡ እንቅልፍ ላይ ያሉ ጣረሞቶች መስለን ደረጃውን
ወረድን: ሁላችንም ህመምና ድካም ተሰምቶናል በተለይ መንትዮቹ::መንትዮቹም ሆነ ክሪስ ምን እንደሚመስሉ አይቻለሁ: ራሴ ምን እንደመሰልኩ ግን ማየት አልቻልኩም: መልበሻው ላይ ባለው ሰፊና ረጅም መስተዋት
ከፊቱ የተቆረጠ፣ ከኋላው ግን ረጅም ፀጉር ያላትን ዳንሰኛ ለማየት በመጠበቅ አይኖቼን ሳማትር መስታወቱ የለም።

ፈጠን ብዬ ወደ መታጠቢያ ቤቱ በመሄድ የመድኃኒት ማስቀመጫው ቁምሳጥን
ላይ ያለውን መስታወት አየሁት ተሰብሯል ተመልሼ ወደ መኝታ ክፍል ገብቼ ክሪስ እንደ ጠረጴዛ የሚጠቀምበትን የመልበሻውን ጠረጴዛ ክዳን አንስቼ ስመለከት እዛ ውስጥ ያለው መስተዋትም ተሰብሯል።

በተሰባበረው መስታወት የራሴን የተቆራረጠ ምስል ተመለከትኩ። ማየቱ ደስ አይልም:: የምግቡን ቅርጫት ክፍሉ ውስጥ ባለው ቀዝቀዝ በሚለው ጥግ ቦታ
አስቀምጬ ጋደም አልኩ። ስለተወሰደውም ሆነ ስለተሰባበሩት መስታወቶች
ክሪስን አልጠየኩትም ለምን እንዳደረገችው አውቄያለሁ። ኩራት ኃጢአት ነው ስለምትል በእሷ አይን እኔና ክሪስ እጅግ የከፋን ኃጢአተኞች ነን እኛን
ለመቅጣትም መንትዮቹም መሰቃየት ነበረባቸው:: ግን ለምን እንደገና ምግብ አመጣችልን? መገመት አልቻልኩም

የምግብ ቅርጫቶች የመጡባቸው ሌሎች ማለዳዎች መጡ፡ አያትየው የምግብ ቅርጫቱን ይዛ ብትመጣም አንድም ቀን ግን ወደኛ ማየት አልፈለገችም።
አይኖቿን ዞር ታደርግና በፍጥነት ወደበሩ ትሄዳለች: የተቆረጠውን ፀጉሬን እንዲያሳይ አድርጌ ከፎጣ የተሰራ ጥምጥም ጭንቅላቴ ላይ ጠምጥሜያለሁ። እሱን እንኳን አይታ አስተያየት ትሰጣለች ብዬ ባስብም ምንም አስተያት
አልሰጠችም አያትየው ስትመጣና ስትሄድ እናያታለን እንጂ ስለ እናታችን እንኳን ልንጠይቃት አልቻልንም: እናታችን የት እንዳለችና መቼ እንደምትመጣ
እንኳን አናውቅም: አያትየው ያለንበትን ሁኔታና የተሰማንን እንድታውቅ ዞር ብላ እንድታየን በሚል በጥላቻና በቁጣ ተሞልተን ብናፈጥባትም እሷ ግን
አይኖቻችንን መመልከት አልፈለገችም: እንድታየን ለማድረግ ስል መጮ ሁሉ እመኛለሁ መንትዮቹን እንድትመለከትና ምን ያህል እንደከሱና ትላልቅ አይኖቻቸው እንዴት እንደፈዘዙ እንድታውቀው ፈልጌያለሁ: እሷ ግን አይታይም።

ከኬሪ አጠገብ አልጋ ላይ ጋደም ብዬ ወደራሴ በጥልቀት ተመለከትኩና ነገሩን ቀድሞ ከነበረበት እንዴት የከፋ እንዳደረግኩት አስተዋልኩ ክሪስ በአንድ ወቅት ደስተኛና መልካም ነገሮችን ብቻ የሚመለከት ከነበረበት ወጥቶ አሁን ግን ተስፋ ቆራጭና የእኔ ግልባጭ ሆኗል። በፊት እንደነበረው አይነት ሳቂታ፣
ብሩህና ከመጥፎ ነገሮች መሀል ጥሩውን የሚያይ እንዲሆን እፈልጋለሁ።

ነሀሴ መጨረሻ አካባቢ አንድ ምሽት ክሪስ ወደ አልጋዬ መጣና “መንትዮቹ ድብን ያለ እንቅልፍ ይዟቸዋል እዚህ ደግሞ ይሞቃል። ወደ ዋና ብንሄድ አሪፍ አይመስልሽም?” አለኝ:

ዋና? እንዴት ያለ የደደብ ሀሳብ ነው: ብንችል እንኳን እሱ የሚያሸንፍበትን ምንም ነገር ማድረግ አልፈልግም: “የት ነው ለመዋኘት የምንሄደው?መታጠቢያ ገንዳው ላይ?” አልኩ

እናታችን የነገረችን ሀይቅ ውስጥ ነው እንጂ፣ ከዚህ ብዙም አይርቅም በዚያው የሰራነው ገመድ መሬት ያደርሰን እንደሆነ እንሞከረዋለን አሁን ጠንካሮች ስለሆንን ምናልባት እሳት ቢነሳ እንኳን በቀላሉ መሬት መድረስ
እንችላለን: ረጅም ጊዜ አንቆይም” ሲል በጣም አብዝቶ ለመነኝ፡ ህልውናው እንደምንችል ለማረጋገጥና ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳን ከዚህ ቤት ወጣ በማለት
ላይ የተገነባ ይመስል ነበር

“መንትዮቹ ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ቢያጡንስ?”

“ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ውስጥ እንደሆንን የሚገልፅ ማስታወሻ
እናደርግላቸዋለን፡ በዚያ ላይ እስከ ጠዋት ድረስ ለሽንት እንኳ አይነቁም”

እስክሸነፍ ድረስ ተከራከርን ብዙ ለመነኝ፡ በመጨረሻ ተስማማሁና ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሄድን፡ ከዚያም በተተለተለ አንሶላ የሰራው መሰላል ወዳለበት የጭስ መውጫ ጣራ ላይ ወጣን፡ ጣሪያው ላይ ስምንት የጭስ
መውጫዎች አሉ ቋጠሮዎቹን አንድ በአንድ እየፈተሸ መመሪያ ሰጠኝ፡ “ትልቁን ቋጠሮ
ለመርገጫ ተጠቀሚ፤ እጆችሽን ከላይኛው ቋጠሮ በላይ አድርገሽ ቀስ እያልሽ ወደ ታች ውረጂ፡ የሚቀጥለውን ቋጠሮ በእግርሽ ፈልጊና ገመዱ በእግሮችሽ
መሀል መሆኑን እርግጠኛ ሁኚ: እንደዚያ ከሆነ ተንሸራተሽ አትወድቂም''

በልበ ሙሉነት እየሳቀ ገመዱን ወደ ጣሪያው ጠርዝ ወሰደ። ከሁለት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መሬት እየወረድን ነው...

ይቀጥላል
👍46😢16😁4
በህይወት መንገድ ላይ…
(አጋቾቹ)
ምዕራፍ-3
///
ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እርስ በርስ ተጠጋግተን ተቀምጠናል...ዙሪያችንን ሽፍቶች የከበብን ይመስል ስናወራ በሹክሹክታ ነው።ከጎኔ ያለችው ሠላም ስለሆነች ለጊዜው ወሬዬ በዋናነት ከእሷ ጋር ነው።
"ደህና ነሽ አይደል?"
"ደህና ነኝ ....አንተስ እንዴት ነህ ? ተመቸህ?"አለቺኝ በለሠለሠ የእናት መሳይ ድምፅ
"በጣም ተመችቶኛል .ግን.. ትንሽ ስለሚቀዘቅዝ ማሞቂያውን ብትለኩሺው"ስል ቀለድኩባት
"ይሻላል?" አለቺኝ
"አዎ...በነገራችን ላይ ስምሽን ዘሬ ነው ያወቅኩት"ተናዘዝኩ።
"አንድ ላይ መስራት ከጀመርን እኮ 15 ቀን ሆኖናል...ስሜን ለማወቅ እስከዛሬ መጠበቅህ ይገርማል?"
"ይቅርታ ይደረግልኝ...በዚህ ጉዳይ ደካማ ሰው ነኝ"
"ድክመት እንኳን አይደለም የትኩረት ጉዳዮ ነው?"
"ትኩረት ማለት?"
"ተወው ለጫወታው ብዬ ነው...ስሜ ሰላም ይባላል"
"አሁንማ አውቄዋለው ባይሆን የእኔ...."
"የአንተንማ በደንብ አውቃለው ኢንጂነር በቃሉ ...ሀለቃዬ አይደለህ አለማወቅ እራሱ አይፈቀድልኝም እኮ።"
"ለጊዜው ኢንጂነሩን ተይውና በቃሉ ብቻ ይበቃል?..
"ካልክ እሺ"
"ይሄኔ ቤተሠቦችሽ የት ሄደች ብለው ይጨነቃሉ አይደል?"
"ያንተስ?"
"ምን ጥያቄ አለው እሰከአሁን ከመቶ ጊዜ በላይ ስልኬ ላይ ደውለዋል...ጓደኞቼን ጠቅላላ በስልክ አደንቁረዋል...እናቴማ ከሰማች ሀገር ተቃጠለ..."
"እኔስ በዚህ ምንም የሚያስጨንቅ ጉዳይ የለብኝም"አለቺኝ
"ማለት?"
"ማለትማ ማንም ትመጣለች ብሎ የሚጠብቀኝ የለም..ቢያንስ እስከ አስር ቀን"
"ምን..?"ንግግሯ አስገረመኝ።
"እሺ ለመሆኑ አስር ቀን ሙሉ ጠብቆ ዘናና ሰከን ብሎ የሚፈልግሽ ማን ነው ባክሽ?
"የቤት አከራዬ"መለሠችልኝ...
ቀላል አልሳቅኩም"በቃ"
"አዎ በቃ"
"ምንድነው እንዲህ የሚያስቃችሁ ለእኛም አጋሩን እንጂ"አይዳ ነች ሰርጎ ገብ ተናጋሪዋ
"ድንበር መዝለል አይቻልም ...እዛው ጎንሽ ካለው ሰው ጋር አውሪ"አልኳትና
ትኩረቴን ወደ ሰላም መልሼ"የቢሾፍቱ ልጅ ነሽ?"ስል ሌላ ጥያቄ ጠየቅኳት
"አይደለሁም ...የሀዋሳ ልጅ ነበርኩ .....ቢሾፍቱ ከመጣው ገና ሁለት ወሬ ነው"
"ነው ገባኝ "
"ምኑ ነው የገባህ ?"አለችኝ ጠንከር ባለ የንግግር ቃና።
"ያው ማለት እንደማንኛዋም የደረሰች ወጣት በሆነ አለመግባባት የተነሳ ከቤተሠብሽ ኮብልለሽ በራስሽ ለመቆም ተሸሽገሽ ለመኖር እየሞከርሽ ያለ መሠለኝ...?"
"በእንደዚህ አይነት ደካማ የመገመት ችሎታህ ሁለተኛ ምንም ነገር እንዳትገምት "
"እሺ..እንደዛ ካልሆነ ምንድነው ?"
"በሰላም ከወጣን አንድ ቀን እነግርሀለው"
"ካልወጣንስ?"
"ካልወጣንማ ያው ግልግል ነው...የእናንተን አላውቅም እኔ በህይወት ብኖርም ደስተኛ ነኝ...ብሞትም እንደዛው ደስተኛ ነኝ...እግዚያብሄር የፈቀደው ሁሉ ይሁን?"
"አክራሪ ሀይማኖተኛ ነሽ አይደል?"
"አክራሪ ሀይማኖተኛ ..?አይ እኔ ሀይማኖተኛ አይደለውም...መንፈሳዊ ሰው በሚለው ቢስተካከልልኝ እመርጣለው።
"ልዩነቱ ምንድነው?"
"ሀይማኖት ማለት ስለ ድርጅት አባልነትና ታማኝነት ነው የምናወራው...ሀይማኖት ከሠማያዊ ሀሳብ ጋር የተቀየጠ አለማዊ ጉዳይ ይበዛዎል...መንፈሳዊነት ግን እንደዛ አይደለም ይለያል...ግንኙነት ከእግዚአብሄር ጋር ታማኝነትህም ለሠማያዊው አለም ብቻ ነው የሚሆነው።ሀይማኖት የመንጋ ጉዞ ነው..መንፈሳዊነት ግን ለብቻህ የምትጓዝበት የፅሞና መንገድ ነው።
"አሁንም ሙሉ በሙሉ ግልፅ አልሆነልኝም..እግዚያብሄር በህብረት ሆነን እንድናመልከው ያበረታታናል.. ሁለትም ሶስትም ሆናችሁ በስሜ ካላችሁ በመካከላችሁ እገኛለሁ ብሎል...ታዲያ ካንቺ ሀሳብ ጋር አይጋጭም"
ይሄንን ጥያቄ ሳትመልስልኝ"ይቅርታ ለጊዜው ጭውውታችን እዚህ ጋር ይቁም...የሆነ ነገር ሊከሰት ነው?"
"የምን ነገር ...ምን እያልሽ ነው?"
"እመነኝ ..ትከሻዬ ነግሮኛል...ቆይ ልፀልይ "ብላ ከስሬ ተነሳች

ድሮም በቋፍ ያለ ልቤን በፍርሀት አራደችው።‹‹ይህቺ ልጅ ጥንቆላም ትሞካክራለች እንዴ?›በውስጤ ነው ያሰብኩት፡፡ስሬ ያለውን ባትሪ አነሳውና አበራው...ሰላም ከእኔ በአንድ ሜትር ርቀት እግሮቾን እንደ ብድሀ መነኩሴ እርስ በርስ አቆላልፋ መሬት ላይ በመቀመጥ እጆቾን እንደሰንደቅ አንድ ላይ አነባብራ ግንባሯ አካባቢ ሰቅላ በፍፅም መመሠጥ ውስጥ ገብታለች።ባትሪውን ዙሪያ ገባውን አበራው ..ሁሉ ነገር እንደነበረ ነው።አይዳና በሪሁን እርስ በርስ ተጣብቀው የሞቀ ወሬ ላይ ናቸው...ጋሽ አህመድ ከእነሱ ትንሽ ፈንጠር ብሎ እንቅልፉን እያስነካው ነው....ባትሪውን አጠፋውና በጭለማ ውስጥ ከፍርሀቴና ከሀሳቤ ጋር መታገል ጀመርኩ፡፡
ብዙም ሳይቆይ"ምንድነው የሚተረማመሰው?"አይዳ ጠየቀች
"ምን ሰማሽ...?"
‹‹እኔ እንጃ.. የሆነ ነገር አይሰማችሁም...?ባትሪውን አብራው እስኪ"
አበራውት"ሠላም በቦታዋ በተመስጦ ላይ ነች...ባትሪውን አርቄ ወደ ማዶ አበራው.... ከዎሻው ስንጥቅ የሆነ ነገር ፈልቅቆ ለመውጣት ሲታገል ይታየኛል... አዎ ሽብልልል እያለ ወጣ..‹‹.እባብ ነው..እባብ"እኔነኝ ያልኩት ..ስቅጥጥ ብሎኝ
"ኢንጂነር እባብ አይደለም....ዘ...ንዶ ነው"በሪሁን በሚርገበገብ ድምፅ አረመኝ።
ሰውነቴን አንድ ላይ አኮማትሬ ጭብጥብጥ አልኩ .... እውነትም ሽብልል እያለ በግማሽ ሲወጣ በፊልም ላይ እንኳን በሙሉ አይኔ ደፍሬ አይቼው የማላውቀው አስፈሪ ዘንዶ ነው..
"አሁን አፉን ከፍቶ ሊውጠን ስራችን ቢደርስ ምን አደርጋለው? ሁላችንንም ለማትረፍ እፍለማለው ወይስ ከመካከላችን አንድ ሰው ወርውሬለት እኔን እንዲምረኝ እማፀናለው?በአእምሮዬ የተሠነቀረ ቀሺም ሀሳብ ነበር..
."ምን አናድርግ?"አለ ጋሽ አህመድ...እኛ እንዲህ ስንተረማመስ ሰላም ሰላማዊ በሆነ ፅሞና ውስጥ እንዳለች ነው. .ዘንዶው ሙሉ በሙሉ ከስንጥቁ ውስጥ ወጥቶ በእኛ አቅጣጫ እየተጓዘ ግማሽ መንገድ ደርሷል...ርዝመቱን ስገምት ስድስት ወይም 7 ሜትር ይሆናል።..በሪሁን ቀስ ብሎ ልክ እንደ ዘንዶ እየተሳበ ሄደና ቅድም የተደፈነብንን ከበላያችን ያለውን አለት ሲቧረብርበት የነበረውን ብረት ቀስ ብዬ አነሳና በእጇቹ አጥብቆ ያዘ ..ጋሽ አህመድም ሌላውን ብረት ያዘ ...እኔ በቆምኩበት እንደደነዘዝኩ ነው።

".ምን እየሰራችሁ ነው?"ስትል ጠየቀቻቸው አይዳ...እንግዲህ የምናወራው ንግግራችን ዘንዶ ጆሮ እንዳይደርስ ይመስል በሹክሹክታ ነው..ግን የዘንዶን የመስማት ችሎታ ሁለታችንም የምናውቅ አይመስለኝም፡፡

"እንዴ ሊውጠን እየመጣ እኮ ነው...ቢያንስ እየተፋለምን እንሙት"በሪሁን ነው በቁርጠኝነት የመለሠው

አይዳ"ቆይ ...የተሻለ ሀሳብ አለኝ "አለችና ከእኔ እጅ ላይ አንከርፍፌ የያዝኩትን ባትሪ ተቀበለቺኝ.... ሁለተኛውን ባትሪ ከነበረበት ቦታ አነሳችና አበራችው...አንድን በቀኛ አንድን በግራ እጆ ያዘችና አንድ ላይ አቆራኝታ ቀጥታ ዘንዶ አይኖች ላይ አበራችበት፡፡ሽምቅቅ አልኩ...ከፍራቻዬ የተነሳ ሽንቴ ሁሉ ሳያመልጠኝ አልቀረም ።

"ምን እየሠራሽ ነው ?ከመካከላችን ማንን ቀድሞ መዎጥ እንዳለበት አይቶ እንዲመርጥ ነው?"አላት በሪሁን

‹‹ዝም በል እስኪ…አንዳንድ እንስሳቶች መብራት አይወዱም…እድሌን ልሞክር ነው››አለች
👍24😁3
ዘንዶ ባለበት ተረጋግቶ እንቅስቃሴውን አቁሞል...ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለበት በማሰብ ላይ ያለ መሠለኝ።አይዳ ፍርጥም ብላ ተረኛ ጥበቃ ላይ እንዳለ ስልጡን ወታደር
ባትሪዎን አጥቂዎ ላይ እንደክላሽ ሰድራ በተጠንቀቅ እንደቆመች ነው።
ዘንዶ በአይዳ ዘዴ ለሁለት ደቂቃ ባለበት ከቆመ ብኃላ ጭንቅላቱን ወደላይ አስግጎ መልሶ መሬት አስያዘና ወደእኛ መጓዙን ቀጠለ...

"ሠላም ...ዘንዶ ሊውጠን ነው ..ሠላም"አርገፈገፋናት "ጭራሽ ነፍሶ ውስጦ ያለ አይመስልም...ልንጎትታትም ብንሞክር አልቻልንም...ዘንዶ ደግሞ እየቀረበን ነው..ለዛውም በሠላም ትክክል.

መሁላችንም እንደተማከርን ነገር ሰላመን ባለችበት ጥለናት ከኃላዋ ወደሁለት ሜትር ያህል ርቀት ላይ ወደሚገኝ ከለላ መሰል አለት ሄደን እርስ በርስ ተረባርበን ና አንድ ላይ ተፋፍገን ተደበቅን… የዘንዶውን ሁኔታ አጮልቀን ማየት ጀመረን…
የሰላም ሁኔታ በቃ ያከተመለት ሆኗል…አሁን ጥያቄው ይህ አስፈሪ ዘንዶ ሰላምን ከዋጠት ቡኃላ በቃኝ ብሎ ፊቱን አዙሮ ይሄዳል ወይስ ተጨማሪ ቀለብ ፈልጎ ወደእኛ ጉዞውን ይቀጥላል የሚለውን ነው…አዎ አንደ ሜትር ቀርቧታል..አሁን ግማሽ ሜትር…በቃ የፍፃሜው ሰዓት ደርሷል…እሷ ካለችበት ልክ እንደበድን አይኖቾን ጨፍና በፅሞናዋ ውስጥ እንደጠፋች ነው….ሞባይሌን አወጣውና መቅረፅ ጀመርኩ .ይሄማ ለታሪክ ተቀርፆ መቅረት ያለበት ትዕይንት ነው…በመጨረሻ የሆነው ነገር ግን ካሰብነው በተቃራኒ ከመሆኑም በተጨማረም ታአምራዊ የመሰለ ትዕንግርት ነው..

መገመት ካልቻልኩት ትንፋሽ አስቆራጭ ጊዜ ብኃላ ዞንዶ ልክ ታቦት እንደሚያነግስ ብርቱ አማኝ ሰላምን ሶስቴ ከዞራት ብኃላ ፊቱን ወደመጣበት አዙሮ ሽብልል ብሎ ወደ ስንጥቅ ገብቶ ተሠወረ...

"ሄደ...ተርፈናል ..ሄዳ"አይዳነች እየፈነጠዘች ከተወሸቅንበት ቀድማን በመውጣት ወደሰላም የተንደረደችው....ሁላችንም ከኃላዋ ተከተልናት...በዚህ ጊዜ ሰላም ከስጋዋ ኮብልላ የነበረችውን ነፋሷን ወደነበረችበት መልሳ...ጨፍና የነበውን አይኖቾን ገልጣ...የተጣጠፍ እግሯቾን አላቃ ...ከቧታዋ እየተንቀሳቀሰች ነበር፡፡ ከጋሽ አህመድ በስተቀር ሁላችንም ተጠመጠምንባት
"አዎ ተርፈናል...አተረፍሽን....ልዩ ሰው ነሽ"ሁላችንም ዙሪያዋን ከበናት በአድናቆትና በአክብሮት የተሠማንን እንቀባጥራለን።
‹‹ሁሉም በአምላክ ነው የሆነው…ምስጋናውን ለፈጣሪ አድርጉት››አለቺን

‹‹አዎ እግዚያብሄር ይመስገን…አንቺንም ግን በጣም ነው የምናመሰግንሽ.ልዩ ሰው ነሽ››አልኳት

"አሁን ተመልሶ ይመጣ ይሆን?"በሪሁን ነው በመጠራጠር የጠየቀው
እርግጠኛ ሆኖ መመለስ የደፈረ ሰው የለም ..

ጋሽ አህመድ"ምን አልባት ስንጥቁን መድፈን ብንችል ጥሩ ነው"የሚል ሀሳብ አመጣ..

"...እሺ አዎ እውነትህን ነው›› አልነውና ..ከሰላም በስተቀር ሌሎቻችን ልክ አይጥ እንደሚያድን ድመት በዝግታ እየተሳብን ወደስንጥቁ ቀረብን ...ተመለከትነው ...‹‹አዎ በጊዜያዊነትም ቢሆን መደፈን ይችላል...››ተስማማን፡፡
ከእኛ ጋር ከላይ ተንከባሎ መጥቶ ወለሉ ላይ እዚህም እዛም ከወዳደቀው ድንጋይ መካከል ጠንካራውን እየመረጥን ስንጥቁ ውስጥ በመጨመር ለመድፈን ከ20 ደቂቃ በላይ ፈጀብን ፡፡ከዛም በተወሰነ መረጋጋት ወደቦታችን ተመልሰን ተደጋጋግፈን ተቀመጥን።ለጊዜው ተርፈናል ማለት ነው፡፡

ይቀጥላል..

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️
👍22🔥1
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


ሳቤላ ጤናዋ ተመልሶላት : ከዚያ አሳፋሪ ፈተና አምልጣ ከአስተማኝ ቦታ ደርሳ ከልጆቿ ጋር ተገናኘች ነገር ግን ጊዜን ጊዜ እየወለዶ ሲሔድ በዓለም የነበሩት
"ምትወዳቸው ሁሎ አልቀውባት ብቻዋን የቀረች ይመስል የሚያስፈራ ስሜት እየተገዳደራትና እያባተታት ኀዘንና ጭንቀት እየገባት መተከዝ መፍዘዝ ጀመረች "ያን ክፉ ሰው ከልቧ ለማውጣት በሞከረች ቁጥር እየታደሰ ይመጣባት ጀመር ራሷም ብትሆን ፍራንሲዝ ሌቪዞንን በሐሳቧ እንኳን እንዳይመጣት እንዳልተጨነቀች ሁሉ አሁን ከሱ መለየቷ ቁርጥ ነገር ሲሆን ጊዜ መልሳ ለአንድ ቀን ኧረ
ሊአንድ ሰዓት እንኳን ቢሆን ብታየውና ናፍቆቷን በዐይን ቢወጣላት ትመኝ ጀመር
አንድ ጊዜ ካየችው በኋላ እንደሚረጋላት ተስፋ ስታደርግና ስትመኝ ራሷን በራሷ
ስትቃረን ከሐሳቧ ብንን ብላ ትነቃለች። ይህ ሐሳብ እሷ ሳትፈልገው ነበር ከልቧ የሚገባው
የፍራንሲዝ ሌቪሰን ምስል ቀኑን ሙሁ እንደ ተደቀነባት ውሎ ሌሊቱንም በሕልሟ ሳይለያት ያድራል " ከእንቅልፋ ስትነቃ ነገሩ ሁሉ ባዶ መሆኑን ስታውቀው ትጨነቃለች እነዚህ ሕልሞች እንደማይመጡባት እሱንም በሔሳቧም ሆነ በሕልሟ እንዳታየው ለማድረግ የፈለገውን መሥዋዕት ለመክፈል አታመነታም ነበር ። ግን ማገድ አልቻችም » ስለዚሀ ምስኪኗ ወይዘሮ ሳቤላ ከዕንቅልፏ በነቃች
ቁጥር የሕሊና ወቀሳ ጭንቀትና ትኰሳት ያጣድፋት ነበር ይህ በሽታ ከሥሩ ተነቅሎ እንዲጠፋላት ብትመኝም ከመልቀቁ በፊት ታላቁ ዋሽ ጊዜ አልፏት እንደ ሚሔድ ታውቅ ነበር

አንድ ቀን ጧት ሚስተር ካርላይል ፈረሱን ጫነና ወደ ሌቪሰን ፓርክ ሔደ ከሰር ፒተር ጋር ለመገናኘት ሲጠይቅ ወደ እመቤት ሌቪሰን አስገቡት " ዐይነ ገብ የሆነ ደማቅ ልብስ የለበሰች መልከኛ ወይዘሮ ነበረች » የመጣበትን ጉዳይ ጠየቀችው ።

"የኔ ጕዳይማ እመቤት .... ከሰር ፒተር ጋር ነው ”

ሰር ፒተር አሟቸው እንደ ስነበተ ስላልተሻላቸው' ባለኍዳዮችን ማነጋር አይችሉም " ይረበሻሉ ይጨነቃሉ ” “ እኔ እንኳን የመጣሁት ራሳቸው በሰጡኝ ቀጠሮ ነው በስድስት ሰዓት ነበር
የቀጠሩኝ " ይኸው አሁን መሙላቱ ነው ።"

ወይዘሮ ሌቪሰን ከንፈሯን ነከሰችና ደስ ላይላት ስትፈቅድለት ወዲያው ወደ ሰር ፒተር የሚያስገባው አሽከር ብቅ አለ " ሚስተር ካርላይል ገባ እዚያ ድረስ
የመጣበትን የፍራንሲዝ ሌቪሰንን ዕዳዎችና ጥፋቶች እንዲሁም ከስደቱ ስለሚመለስበት ነገር አንሥተ ተነጋገሩ "

“ ዛሬ ዕዳውን ሁሉ ከፍዬ ነጻ ባወጣው ነገ ደግሞ ተመልሶ ከዚያ ይገባና ዘለዓለም እንደ ከፈልኩ መኖር ነው እንግዲያ ካያቱ ሌላ ወንድም የለኝም » አባቱም የተባረከ ሰው ነበር " እሱ የሚረባ ሰው አንዳይመስልህ .... ሚስተር ካርላይል " ብላሽ ሰው ነው " አለው ሰር ፒተር "
ታሪኩን ሲነግረኝ አሳዘነኝና እርስዎን እንደማጋግርለት ነገርኩት እንጂ እኔ ስለ ደግነቱና ስለ ክፋቱ የማውቀው ነገር የለም
አለ ሚስተር ካርላይል "

“የሱን ሥራ ባታውቀው ይሻላል አሁን እሱ የሚፈልገው ዕዳውን ሁሉ እንድከፍልለትና እንደገና አዲስ ኑር እንዲጀምር ነው እኔ እዚህ እሱ ባሕር ማዶ ሆነን የሚደረግ ነገር ሊኖር አይችልም ቀርቦ መተሳሰብ አለበት . .

"እሱማ ተደብቆም ቢሆን ወደ ኢንግላንድ መምጣት አለበት »

እዚህ ቤት ግን መግባት አይችልም አለ ሰር ፒተር ፈጠን ብሎ ባለቤቴ ለአንድ ቀን እንኳን አታስጠጋውም።

ኢስት ሊን መጥቶ ሊሰነብት ይችላል መቸም ከዚያ ይመጣል ብሎ ማንም አያስበውም እርስዎ ሊረዱት እየፈለጉ ለመገናኘት ባለመቻላችሁ ብቻ እርዳታው ሊቀርበት አይገባም።

ከሚገባው በላይ አዘነክለትሳ ሚስተር ካርላይል ? ጥብቅና ልትቆምለት አtበሃል ልበል ?

“ አላሰብኩም ! እኔ አልቆምለትም"

ከዚያ ትንሽ ተነጋግረው ካፒቴን ሌቪሰን እንዲላክበት ተስማምተው ሚስተር ካርላይል ተስናብቶ እንደ ወጣ ከወይዘሮ ሌቪሰን ጋር ተገናኙ "
ከባለቤቴ ጋር የተነጋገራችሁት ስለዚያ ስለ ወንድማቸው ልጅ ጕዳይ መስሎኛል።

“ ነው” አላት ሚስተር ካርላይል ።

ስለሱ ያለኝ ግምት በጣም መጥፎ ነው !ይሁንና አንተም በኔ ላይ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲያድርብህ አልፈልግም ። ፍራንሲዝ ሌቪሰን የባሌ የወንድም የልጅ ልጅና ተስፈኛ ወራሽ ነው " ስለዚህ በሱ ላይ ጥላቻ ስለ አደረብኝ ነገሩን የማያውቁ ሰዎች በኔ ሊገርማቸው ይችላል " የዛሬ ሦስት ዓመት ግድም ሰር ፒተርን ሳላገባ እንዲያሙም ሰር ፒተርን ግና ሳላውቃቸው ፍራንሲዝ ሌቪሰን የኔ ወዳጆች ከሆኑ ስዎች
ጋር ተዋውቆ ኖሮ ከነሱ ቤት አግኝቸው ነበር " በነሱ ላይ የሚያሳፍር በደል ፈፀመባቸው » ከቤታቸው ተቀብለው ባስተናገዱት የግፍ በደል ከፈላቸው ስለሱ መጥፎነት ሌላም ብዙ ነገር ሰምቸ ነበር በተፈጥሮውም ሆነ በዝንባሌው ለከስካሳና ወራዳ እንደሆነ ይቀራል ብዬ ነው የማምነው " "

“ በውነቱ እኔ ስለሱ ምንም ያህል አላውቅም " አሁን ባነሡት ሁኔታ የፈፀመውን ጥፋት ሊጠቅሱልኝ ይችላሉ ? አላት ሚስተር ካርላይል

እልም አድርጎ አጠፋቸው ነቅሏቸው ቀረ ... ሚስተር ካርላይል " ስለ ማጭበርበር፡ ስለ ተንኮል ምንም የማያውቁ የዋህ ገጠሬ ብጤዎች ነበሩ እሱ እንደነገራቸውና እነሱም እንዳመኑት ለአንድ ወር ያሀል የሚያስፈልገውን ዕቃ በወሰደበት የዕዳ ሠነድ ተጠሪ ሆነው እንዲፈርሙለት በግር በራስ ገብቶ ያግባባቸዋል እነዚሀ ሰዎች በነበራቸው ትንሽ ርስት እንዳቅማቸው የሚተዳዶሩ እንጂ ከዕለት ፍላጎት የሚተርፍ ገንዘብ አልነበራቸውም " የዚያ ሠነድ መከፈያ ጊዜው ሲደርስ
ድሮውንም ሲያውቅ ያደረገው ስለ ነበረ ዙሮ አላያቸውም። ስለዚህ ቤታቸውን በዕዳ አስረክበው ተሰደዱ " ሌላም ጥፋቶች ሞልተውታል ከዚህ ቤት እንደማላስባው ሰር ፒተር ሳይነግሩህ አልቀሩም " እኔ የጠላሁት የሳቸው ወራሽ በመሆኑ ቀንቸበት ሳይሆን ባመሎ ነው " እኔ ሰብአዊ ክብሬን ሳልጥል በጤናዬ ቁሜ እየሔድኩ እሱን
ከዚህ ቤት ምንም አላስጠጋውም ሰር ፒተር ሊቀበሉት ሊረዱት ዕዳውንም ከፍለው ከደረሰበት ችግር ሊያወጡት ይችላሉ እኔ ግን ከዚህ ቤት አላስገባውም ”

“ እርስዎ እንደማይቀበሉት ሰር ፒተር ነግረውኛል " ነገር ግን ከገባበት ጣጣ ለመላቀትና ነገሮችን ለማስተካከል ወደ ኢንግላንድ መጥቶ ከሰር ፒተር ጋር መገናኘቱ አስፈላጊ ነው "

“በስውር ካልሆነ በቀር' አሁን ባለው ሁኔታ እንዴት አድርጎ ወደዚህ ሊመጣ ይችላል ? አለችው "

“ እሱ በስውር ካልሆነ ሊመጣ አይችልም ስለዚህ ወደ ኢስት ሊን መጥቶ እንዲያርፍ አድርጌዋለሁ" መቸም እንደሚያውቁት ከሳቤላ ጋር የዝምድና ግንኙነት አላቸው " "

“ መልካሙን አድራጎትህን በክፋት እንዳይከፍልህ ተጠንቀቅ አለችው
ወይዘር ሌቪሰን ይህ የሱ የተለመደ ተግባሩ ነው !!

ሚስተር ካርይል ሣቀ « ምንም የክፋት ፍላጎት ቢኖረው ምን ጉዳት ሊያደርስብኝ ይችላል ? ደንበኞቼን አያባርርብኝ ልጆቼን አይመታብኝ ገንዘቤን እጠብቃለሁ ደሞ እኮ ከኛ ጋር የሚቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው"

የሰር ፒተር ባለቤትም እንደ መሣቅ ብላ ጨበጠችውና፡ “ምናልባት ያንተ ቤት ለለከስካሳው ዐመሉ ላይመቸው ይችላል ግን ተጠንቀቅ ትንሽ አጋጣሚ ካገኘ አንድ ጥፋት ሳይፌጽም እንደማይሔድ ዕወቅ።
👍14
ሚስተር ካርይል ስር ፒተርን ለማነጋገር ወዶ ሌቪሰን ፓርክ የሔደው ዓርብ ለት ነበር ከዚያ እንደ ተመለሰ ቀጥታ ወደ ቢሮዉ ሔዶ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወዶ
ኢስት ሊን እንዲመጣ ጻፈለት ለሳቤላ ግን ሳይነግራት አደረ » ረሳው በበነጋው ቅዳሜ ማታ ማለት ነውና ሚስተር ሚስዝ ካርላይል ከጐረቤት ራት ተጠርተው ከሔዱበት ከገበታ ላይ እያሉ ሲጫወቱ ሳለ ሚስዝ ዱሲ ነግር ተነሣ የሷ ነገር ሲነሣ ትዝታዎች እየተሳሳቡ መጡ " ሚስተር ካርላይልን ' የቡሎኝና የሌቪሰንን ነገር አስታወሱት " ከዚያ ተያይዞ የፍራንሲዝ ሌቪሰንን ወደ ኢስት ሊን መጠራት ለሚስቱ
እንዳልነግራት ትዝ አለው እስኪወጡ ድረስ ነገሩን በልቡ አቆይቶ በሠረገላቸው ተግፍረው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ መንገድ ላይ ነገራት።

“ ሳቤላ .... የተዘጋጁ የእንግዳ ክፍሎች አሉ አይደለም? ምክንያቱም የምጠብቀው እንግዳ አለ "

“ አሉ እንጂ ! እስካሁን ባይዘጋጁም ማዘጋጀቱ ጊዜ አይፈጅም ”

"ነገ እሑድ ነው ስለዚህ ነገ ሳይገባ አይቀርም " አዝናለሁ ትናንትና ረሳሁትና ሳልነግርሽ ቀረሁ

" ማነው የሚመጣው ?

"ካፒቴን ሌቪሰን "

"ማን አለችው በድንጋጤ "

“ካፒቴን ሌቪሰን ነው ስር ፒተር ዘንድ ሔጀ አነጋግሬለት ስለ ዕዳው ጕዳይ ሊያነጋግሩለት ፈቅደዋል " ነገር ግን ሚስዝ ሌቪሰን ከቤታቸው እንዲያርፍ ስላልፈቀዱ ለጥቂት ቀኖች ኢስት ሊን ሰንብቶ ጉዳዩን እንዲያስፈጽም ጠርቸዋለሁ " አላት "

ልብ ወደ አፍ ይዘላል የሚባል አነጋገር አለ " የሳቤላም ልብ ወደ አፏ ዘለለ "ዞረባት " ስሜቶቿ ሁሎ የከዱዋት መሰላት » በመጀመሪያ መሬት ተከፍታ የገነትን መንገድ ያሳየቻት መሰላት " ትንሽ አሰበችና ደግሞ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ወደዚያ ቤት መምጣት እንደሌለበትና እሷም ከሱ ጋር ጨርሳ መተያየት እንዶሌለባት ታያት ሚስተር ካርይል ስለ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ችግር ስለሰር ፒተርና ስለ ሚስቱ አስተያየት ሲያጫውታት እሷም በበኩሏ ሰውየው ከቤቷ እንዳይመጣ የምታደርግበትን መንገድ ስታስብ ስለ ነበር የነገራትን ሁሉ አልሰማችውም

አርኪባልድ • • • እኔ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ኢስት ሊን እንዲያርፍ አልፈልግም።"

"ለጥቂት ቀኖች ብቻ እኮ ነው ግፋ ቢል ሁለት ቀን ያህል ቢቆይ ነው " ሰር ፒተር ስለዕዳው ሁኔታ ከሱ ጋር ተነጋግረው ከተሪዱ በኋላ ሊከፍሉለት አስበዋል ዕዳው እንደሚከፈልለት ከታወቀለት ደግሞ በቢክቶሪያ ግዛት ሁሉ እንደ ልቡ መዘዋወር ይችላል "

“ እሱ ስለ ራሱ እንደ ፈለገው ይሁን " ግን ወደኛ ቤት ምን ያመጣዋል?”

"እኔ ነኝ የጠራሁት " አንቺ የሱን መምጣት አለመፈለግሽን አላውቅም ነበር” ደሞስ ወደኛ ቤት እንዳይመጣ "ማትፈልጊበት ምክንያት ምንድነው?"

እኔ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ይከብደኛል አልወደውም ስለዚህ እሱ ኢስት ሊን መጥቶ አንግዳዬ እንዲሆን አልፈልገውም

“ የኔ ፍቅር . . . እንግዲህ ማድረግ የሚቻል ነገር ያለ አይመስለኝም " ምናልባት አሁን በጉዞ ላይ ስለሚሆን ነገ ሳይገባ አይቀርም " ስለዚህ እኔው ጠርቸ እኔው ከገዛ ቤቴ በራፍ መልሼ ላባርረው አልችልም : ቀድሞውኑም በነገሩ እንደማትስማሚበት ባውቅ ኖሮ እኔም ከቤቴ የማሬፉን ሐሳብ አላቀርብለትም ነበር "

“ ነገ ! ” አለችው ይኸን ቃል ብቻ ነበር ልብ ብላ የስማችው » “ ነገ ሊመጣ ነው አልhኝ ? ”

“ ቀኑ እሑድ በመሆኑ ነጻ ቀን ስለሆነ በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሞ ሳይመጣ አይቀርም " ግን የሱን ወደዚህ መምጣት ይህን ያህል የጠላሽው ምን አድርጎሽ ነው
ብሎኝ ሳለን ደግሞ ሰውዬውን እንደምትጠይው የነገርሽኝ ነገር አልነበረም ”

“ ምንም አላዶረገም ብላ አልጐመጐመች " የቅሬታ ምክንያቶቿ ሁሉ ከልቧ እንደ ተዳፈኑ ሟምተው መጥፋት እንደሚገባቸው ተሰማት "

“ሚስዝ ሌቪሰንም ስለሱ ያላቸው አስተያየት መጥፎ ነው እንዲያውም እውነት መሆኑን እንጃ እንጂ እሱ ስለ ፈጸማቸው መጥፎ ነገሮች ሁለቱን ያህል እንደ ምላሌ አድርገው ነግረውኛል " ሰውዬውን በፊትም ደኅና አድርው ያውቁት
ነበር ።

“ የሷ እንኳን የጥላቻ ወሬ ነው” አለችው ሳቤላ “ እንዲያው ሳይሆን አይቀርም ብዬ ነው " ቡሎኝ ሆነን ፍራንሲዝ ሌቪለን ራሱ ሁለቱ ምን ጊዜም ተግባብተው እንደማያውቁ አጫውቶኛል ።

“ያም ሆነ ይህ የሱ ክፋት ኢስት ሊን በሚቆይበት አጭር ጊዜ ውስጥ ምንም ሊያደርገን አይችልም አንቺም እንዳይመጣብሽ የፈለግሽው ዝምብለሽ ስለ ጠላሽው መሰለኝ ... ሳቤላ ”

ሚስተር ካርላይል ራሱ ባመጣው ሐሳብ ዝም ብለሽ ስለ ጠላሽው ነው ብሎ አምኖ እንዲቀመጥ ዝም አለችው " እሷ ግን ሁኔታዎች እንዳሤሩበት ተሰማትና እጆቿን አቆላልፋ ጨብጣ ትተክዝ ጀመር
ይህ ሰው ከቤቷ እንዲግባና ከሷ ጋር እንዲቀመጥ ከተደረገ እሱን የመርሳት ግዴታዋን እንዴት ልትወጣው እንደምትችል ጨነቃት ወደ ባሏ ምልለ ብላ ጉንጮቿን ትከሻው ላይ አስደግፈቻቸው ።

እሱም የደከማት መስሎት ክንዱን በሽንጧ አዙሮ ፊቷን አመቻችቶ ወደሱ አስጠጋት በፍቅር ሰመመን ዐይን ዐይንዋን አቆልቁሎ ይመለከታት ጀመር እንደዚያ ሁና እንደ ተጋደመች አሁንም ከሐቁ ትንሽ ቆንጥራ ልትነግረው አማራት"ያቀፋት ክንድ ጠንካራ ተገን ፡ የተደገፈችው ሰውዬ እንደ ምሰሶ የማይነቃነቅ መከታ መሆኑን ደኀና አድርጋ ታወቅ ነበር ደፍራ መናገር ስለ ፈራች ብቻ አንድ ሁለት ጊዜ የጀመሪያዎቹ ቃሎች ከከንፈሯ ይደርሱና ሳያልፉ ቀጥ እያሉ ምንም ሳትናገር
ሠረገላው ኢስት ሊን ገብቶ ቆመ ። የመናገር እድሏም ዐለፈ ።

በበነጋው ጥዋት መሬቱ በዝናብ ርሶ ነበር ዕኩለ ቀን ላይ ደኅና ካባራ በኋላ እንደገና ከቀትር በኋላ ዝናብ ጣለ ። እነሱ ገና ቤተ ክርስቲያን ነበሩ።

ኮርኒሊያ....አላት ካርላይል ወደሷ ጠጋ ብሎ ፡ በሹክሸክታ “ እየዘነበ ነው ስለዚህ ጆን በእግሩ መሔድ ስለሚችል አንቺ በሠረገላ አብረሽን ተመለሽ ።

እሷ እንደዚህ ያለውን ነገር መቸ ትነካውና ። ምን ዶፍ ቢወርድ ሚስ ካርላይል ወደዚያ ስትሔድም ሆነ ስትመለስ በእግሯ ካልሆነ በቀር በሌላ መጓጓዣ አትንቀሳቀስም ። አሽከር ማስከተልንም ደግሞ ከሠረገላው የበለጠ ትንቀውና ትጠላው ነበር " ስለዚህ ትልቅ ጃንጥላዋን ዘርግታ መንገድ ጀመረች በበጋው ሙቀት
በክረምቱ በረዶ ፡ በለስላሳ ካፊያ ፡ በኃይለኛ ዝናብ ሁሉ በፀሐይ ጊዜ የፈለግኸውን አድርግ የሚለውን ምሳሌ በመከተል የድርቆሽ ክምር ሊያለብስ የሚችለውን ታላቁ ጃንጥላዋን በወጣች ቁጥር ከእጅዋ ለይታው አታውቅም "

ሚስተር ካርላይል ሰረገላውን እየነዳ በሩን ዐልፎ በግቢ ውስጥ ሲጠመዘዝ የጭንቀት ድምዕ ስሙ ወዲያውም ትንሿ ሳቤላ እየጮኸችና እየተንስቀሰቀች
ወደነሱ ስትሮጥ አይዋት ሚስተር ካርላይል ወርዶ ተቀበላት "

“ አባባ ! አባባ !እባክህ ና! ሙታለች መሰለኝ !

ልጅቱን እቅፍ አድርጎ ያዛትና
ተይ ዝም በይ የኔ ልጅ እናትሽን ታስደነግጫታለሽ ። አይዞሽ አትንቀጭቀጭ ፤በይ እስቲ ነገሩ ምን እንደሆነ ንገሪኝ "

ልጅቱ ታሪኳን ተናዘዘች " ጆይስ አትውጩ እያለቻት ለቀልድ ብላ በእምቢታ ወጣችና ዝናቡ ባረጠበው የመናፈሻው ሣር ስለ ሮጠች ጆይስ ደግሞ እሷን ለመያዝ ተከትላት ስትሮጥ አዳልጧት ወደቀች " እዚያው እንደ ተዘረጋች ቀረች " ሚስተር
ካርላይል ልጅቱን ለናቷ ሰጥቶና አይቶ እስከሚመጣም እንዳትከተለው ነግሮ ጆይስ ወደ ወደቀችበት ሔደ -ሊያነሣት ሲሞክር “ አያንቀሳቅሱኝ ጌታዩ | እግሬ ተሰብሯል መሰለኝ ” አለችው
👍151
“ ብዙ የጐዳሽ አይመስለኝም " ለመሆኑ ምን አግኘሽ ?” አላት "
የሆነውን ሁሉ ልክ ልጅቱ እንዶ ተናገረችው አስረዳችው ጆን ሠረገላውን ይዞ ሚስተር ዌይንራይትን ሊጠራ ሔደ ወዲያው አሽከሮቹም ከሔዱበት
ስለመጡ በሸክም አስገብተው አልጋ ላይ አስተኟት ሚስተርና ሚስዝ ካርላይል አብረዋት ተቀመጡ « ኮርኒሊያም ነበረች ይፈልጉ ይሆናል የምትላቸውን ነገሮች ለማሰናዳት አንዱን ዕቃ ስታነሣ ከሌላው ስታጋጭ ስታላትም ፡ የአዘኔታ ስሜቷን
በቁጣና በማስተዛዘን መካከል በሆነ አነጋገር ትገልጽላት ጀመር » ባጠቃላይ ካገልግሎቷ ጥፋቷ በለጠ " ትንሿ ሳቤላ ቀስ ብላ መጣችና እናቷን ከልጋው አስሥታ
ይዛት ሔደች »

"እማማ.. አለቻት አንድ የልብስ ከረጢት የያዘ ሰው አንቺንና አባባን ይጠይቃል ።

ሳቤላ ሰውነቷ ክፍል ያለ መሰላት "

"ማነው • • ሳቤላ ? አለቻት እናቲቱ "
“ኧረ እንጃለቱ እኔ ግን አልወደውም " ይዞኝ ነበር፤ዐይኑ ሲያይ ማስቀየሙ! አለቻት "

ሒጅና እንግዳ መጣ ብለሽ ላባትሽ በጆሮው ንገሬው ”አለቻት።

እንግዳው በርግጥ ካፒቴን ሌቪሰን ነበር ሚስተር ካርላይል ወርዶ ተቀበለው ሳቤላ በጆይስ አደጋ አመካኝታ ሳትመጣ ቀረች

ሚስተር ዌይንራይት መጥቶ የጆይስን እግር አይቶ ቀለል ያለ ስብራኑ መሆኑን ቢያረጋግጥም ከሦስት እስከ አራት ሳምንት መተኛት እንዳለባት አዘዘ"

ማታ ትንሿ ሳቤላና ዊልያም ከአባታቸው ጋር ከሳሎን ነበሩ - -
የሚያማምሩ ልጆች ናቸው ? አለ ፍራንሲዝ ሌቬሰን "

“ እናታቸውን ነው የሚመስሉት እሷም በጣም ደስ የምትል ልጅ ነበረች" አለ ሚስተር ካርላይል

“እመቤት ሳቤላን በልጅነቷ ታውቃት ነበር ? ” አለ ሌቪሰን በመገረም ድምፅ።

“ ሁልጊዜ አያት ነበር ከወይዘሮ ማውንት እስቨርን ጋር ከዚህ ብዙ ጊዜ ትቀመጥ ነበር እኮ ።

“አሃ ለካ !!ይህ ቦታ የማውንት እስቨርን ነበር እንዴት ያለው ብላሽ ሰው ኖሯል ! አንቺ ቆንጂት እኔ አንቺን መውሰድ አለብኝ ” አለና እጁን ወደ ልጅቱ ዘርግቶ ሳብ አደረጋት “መጀመሪያ ስመጣ ስምሽን እንዳትነግሪኝ ጥለሽኝ ሮጥሽ!

“ እኔ የእርስዎን መምጣት ለናቴ ልነግር ነው ከጆይስ ጋር ነበረች ''

“ ጆይስ ጆይስ ማናት ?

“ የእመቤት ሳቤላ ደንገጡር” አለ ካርላይል ጣልቃ ገብቶ“ ያቺ አደጋ አገኛት ያልኩህ እኮ ናት " ጆይስ በቤታችን ከሁሉም የተለየ ከፍተኛ ቁም ነገር ያላት ሠራተኛ ናት ● "

ግን ለኔ እንግዳ ስም ነው ” አለ ሌቪሰን “ ጆይስ ! . . . ጆይስ ! እንዲህ ያለ ስም ሰምቼ አላውቅም የክርስትና ስም ነው ወይስ የቤተሰብ ስም ?

« ያልተለመደ ስም አይደለም » ስሟ ጆይስ ሆሊጆን ነው ከኛ ዘንድ ከገባች ብዙ ዘመኗ ነው

በዚህ ጊዜ ትንቯ ሳቤላ እጂዋን ከሰውየው ለማስለቀቅ ሞክራ ቢያቅታት አለቀሰች አባቷ ምን እንደ ሆነች ቢጠይቃት “ እንዲይዘኝ አልፈልግም” አለችው

ካፒቴን ሌቪሰን እየሣቀ ጠበቅ አድርጎ ያዛት " ሚስተር ካርላይል ብድግ ብሎ አስለቀቃትና ከጉልበቱ ላይ አስቀመጣት እሷም ፊቷን ደብቃ አንገቱን በትንሿ
ክንዷ አንቃ “ አባባ. . . አልወደውም እፈራዋለሁ " ሁለተኛ እንዳይነካኝ አለችው "

ሚስተር ካርላይል ልጅቱን ጥብቅ አድርጎ አቅፎ የልጅ ልምድ የለህም ካፒቴን ሌቪሰን " ልጆች ለጋ ተክል ናቸው " ትንሽ ነገር ይበቸዋል ”

እውነትም ልጆች በጣም አስቸጋሪ ነገሮች ናቸው ” አለና አሁንም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ዊልያምን እየሣቀ አንሥቶ በጂዋጅዌ አወዛወዘው " እሱ ግን እንደ
እህቱ ሳይደነግጥ ይሥቅ ይደሰት ጀመር "....

💫ይቀጥላል💫
👍16
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የመንግስተ ሰማያት ጣዕም

ክሪስ በቀስታና በጥንቃቄ እጁን ከእጁ ስር፣ እግሩን ከእግሩ ስር እያደረገ ወደ መሬት ወረደ እኔ ደግሞ ጣሪያው ጠርዝ ላይ በደረቴ ተኝቼ ወደታች ሲወርድ እያየሁ ነው እጁን አንስቶ ሲያውለበልብልኝ ጨረቃዋ ወጥታ ብሩህ ሆና እያበራች ነበር፡ እንድወርድ ምልክት እየሰጠኝ ነበር። ክሪስ
እንዴት እንደወረደ አይቻለሁ: ዥዋዥዌ ከመጫወት የተለየ አይደለም ብዬ
ለራሴ ነገርኩት። ቋጠሮዎቹ ትልልቅና ጠንካሮች ናቸው: በዚያ ላይ በበቂ ሁኔታ አራርቀን ነው የሰራናቸው አንድ ጊዜ ጣሪያውን ከለቀቅኩ በኋላ ወደ
ታች እንዳልመለከት አስጠንቅቆኛል መጀመሪያ አንደኛውን እግር ካሳረፍኩ
በኋላ በሌላኛው እግሬ የታችኛውን ቋጠሮ መፈለግ ላይ እንዳተኩር ነገረኝ።
እንዳለኝ እያደረግኩ ከአስር ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መሬት ላይ ከክሪስ አጠገብ ቆምኩ።

“ዋው!” አለ ወደሱ አስጠግቶ እያቀፈኝ ከእኔ በተሻለ አደረግሽው”

የፎክስወርዝ አዳራሽ የጓሮ አትክልት ቦታ ውስጥ ነን፡ ክፍሎቹ በሙሉ ጨለማ ውጧቸዋል። የሠራተኞቹ መኖሪያ መስኮቶች ሁሉ ደማቅ ቢጫ ናቸው፡ ዝቅ ባለ ድምፅ “በል መንገዱን ካወቅከው ወደ መዋኛው ምራኝ አልኩት:

በእርግጥም መንገዱን ያውቀዋል እናታችን እሷና ወንድሞቿ ከጓደኞቻቸው
ጋር እንዴት ተደብቀው ወደ ዋና እንደሚሄዱ ነግራናለች:
እጄን ይዞ በጣቶቻችን እየተራመድን ከትልቁ ቤት ወጣን በሞቃታማው
የበጋ ምሽት ውጪ መሬት ላይ መሆን ለየት ያለ ስሜት አለው መንትዮቹን ብቻቸውን የተቆለፈ ክፍል ውስጥ ትተናቸዋል፡ ትንሽዬዋን ድልድይ ስናቋርጥ አሁን ከፎክስወርዝ ግዛት ውጪ መሆናችንን ስላወቅን ደስታ ተሰማን:: ነፃ የሆንን መሰለን፡ ቢሆንም ማንም እንዳያየን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። ወደ ሜዳውና እናታችን ወደ ነገረችን ሀይቅ ሮጥን።

ጣሪያው ላይ ስንወጣ አራት ሰዓት ነበር: በዛፎች የተከበበውን ትንሽ የውሀ
አካል ስናገኝ አራት ሰዓት ተኩል ሆኖ ነበር። ሌሎች ሰዎች እዚያ ኖረው ምሽታችን ይበላሽብናል ብለን ፈርተን ነበር። ነገር ግን የሀይቁ ውሀ ፀጥ ያለና
በንፋስ እንኳን የማይንቀሳቀስና የሚዋኙም ሆኑ በጀልባ የሚቀዝፉ ሰዎች የሌሉበት ነበር።

በጨረቃ ብርሃን በኮከቦች በደመቀ ሰማይ ስር ሆኜ ሀይቁን እየተመለከትኩ እንደዚህ አይነት የሚያምር ውሀ አይቼ እንደማላውቅና እንደዚህ በሀሴት
የሞላኝ ምሽት ኖሮ እንደማያውቅ አሰብኩ።

“እርቃናችንን እንዋኛለን?” ሲል ክሪስ ለየት ባለ ሁኔታ እያየኝ ጠየቀኝ፡

“አይ የውስጥ ሱሪያችንን ለብሰን ነው የምንዋኘው” አልኩት።

ችግሩ አንድም የጡት መያዣ የሌለኝ መሆኑ ነበር። አሁን ግን እዚህ ደርሰናል: አጉል የሆነው የጨዋነት ጥያቄ በዚህ በጨረቃ ብርሀን በደመቀ ውሀ ከመደሰት አያስቆመኝም። ልብሴን አውልቄ የመርከብ ማቆሚያ ወደ
ሆነው ጥልቀት የሌለው ጥግ ጋ ሮጥኩ። ስደርስ ግን ውሀው እንደ በረዶ ይቀዘቅዝ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ በመጀመሪያ እግሬን ነከር አድርጌ አረጋገጥኩ እውነትም በጣም ቀዝቃዛ ነው! ክሪስን ሳየው ሰዓቱን ከእጁ ላይ ፈትቶ ወደጎን
በማስቀመጥ ወደ እኔ እየሮጠ መጣና ደፍሬ ወደ ውሀው ከመግባቴ በፊት ጀርባዬ ጋ ደርሶ ገፈተረኝ: ውሀው ውስጥ በደረቴ ወደቅኩና ሙሉ በሙሉ
ውሀ ውስጥ ጠለቅኩ።

ከውሀው ስወጣ እየተንቀጠቀጥኩ ነበር። ወደ ክሪስ ተመለከትኩ ከፍ ያለ ድንጋይ ላይ ቆሟል ክንዶቹን ወደ ላይ አነሳና ወደ ሀይቁ ተወርውሮ ገባ፡ በድንጋጤ አቃተትኩ። ውሀው በቂ ጥልቀት ያለው ባይሆንስ? መሬቱ
መትቶት አንገቱ ወይም ጀርባው ቢሰበርስ?

ክሪስ ወደ ላይ አልተንሳፈፈም: አምላኬ! ሞቷል ሰምጧል!

“ክሪስ!” እየጠራሁትና እያለቀስኩ ገብቶ ወደተሰወረበት ቦታ መዋኘት ጀመርኩ።

ድንገት የሆነ ነገር እግሬን ያዘኝ! ጮህኩና ወደ ውስጥ ገባሁ የጎተተኝ ክሪስ ነበር፡ በጥንካሬ እግሮቹን እያወራጨ ወደምንስቅበትና ውሀ ወደምንረጫጭበት ወጣን

“እዚያ የተረገመ የሚሞቅ ቤት ውስጥ ከመዘጋት ቅዝቃዜው አይሻልም? ሲል ጠየቀኝ፡ ልክ እንደ እብድ ዙሪያውን እየዞረ ሲጮህ ላየው ይህች ትንሽ ነፃነት እንደ ጠንካራ የወይን ጠጅ አናቱ ላይ ወጥታ ያሰከረችው ይመስል
ነበር። ዙሪያዬን እየዞረ ዋኘና እግሬን ይዞ ወደታች ሊጎትተኝ ሞከረ: አሁን
ግን አልቻለም:

ውሀ እየተረጫጨንና እየዘፈንን፣ ከዚያ ደግሞ አቅፎኝ ስንስቅና ስንጮ ነበር። ልክ እንደገና ልጆች የሆንን ይመስል ታገልን… አበድን ውሀ ውስጥ በጣም ጎበዝ ነው ልክ እንደ ዳንሰኛ: እየዋኘን እያለ በድንገት ደከመኝ::በጣም ከመድከሜ የተነሳ እንደ እርጥብ ፎጣ ሆኜ ነበር። ክሪስ በክንዱ ደግፎ ወደ ዳር እንድወጣ አገዘኝ።

ሁለታችንም ሀይቁ ዳር ላይ ያለው ሳር ላይ በጀርባችን ተጋድመን ማውራት ጀመርን።

“አንድ ጊዜ እንዋኝና ወደ መንትዮቹ እንመለስ” አለ ሁለታችንም
የሚያብረቀርቁና የሚጣቀሱ የሚመስሉት ኮከቦች ላይ አተኩረናል። ደስ የምትል ግማሽ ጨረቃ ደመናው ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያለች ድብብቆሽ
የምትጫወት ትመስላለች፡ “ምናልባት ወደ ጣሪያው መውጣት ባንችልስ?” አልኩ

“እንችላለን፡ ምክንያቱም ማድረግ አለብን” ክሪስቶፈር ሁልጊዜ እንደሚቻል የሚያምን ልጅ ነው: ሰውነቱ በውሀ ረጥቦ፣ ፀጉሩ ግንባሩ ላይ ተጣብቆ አጠገቤ ተጋድሟል። አፍንጫው እንደ አባታችን አፍንጫ ቀጥ ያለ ነው: ከንፈሮቹ የሚያምር ቅርፅ አላቸው:: አገጩ አራት ማዕዘን ሲሆን ደረቱ መስፋት ጀምሯል። እያደገ ያለው ወንድነቱ በጠንካራ ጭኖቹ መሀል ማበጥ ጀምሯል። ስለ ወንዶች ሳስብ አንድ ነገር ይማርከኛል
ያም ጥሩ ቅርፅ ያላቸው ጭኖች ናቸው፡ ጥፋተኝነት ሳይሰማኝና ሳላፍር ቁንጅናውን በአይኖቼ ለመመገብ ባለመቻሌ አዝኜ ጭንቅላቴን አዞርኩ።

ፊቱን አዙሮ አይኖቼን ተመለከተ: እኔም አየሁት። ሌላ ቦታ መመልከት
የማንችል እስኪመስል ድረስ እይታዎቻችን ተቆላለፉ ለስላሳ የደቡብ ነፋስ ፀጉሬ ውስጥ እየተጫወተና ፊቴ ላይ ያለውን ውሀ
እያደረቀው ነው፡ ምሽቱ በጣም ጣፋጭና በጣም ደስ የሚል ቢሆንም ፍቅርን የመራብ ከፍተኛ ስሜት ውስጥ ባለ ዕድሜ ላይ ያለሁ በመሆኔ ብቻ ምንም
ምክንያት ሳይኖረኝ ማልቀስ ፈለግኩ: ከዚህ በፊት እዚህ የነበርኩ አይነት ስሜት ተሰማኝ፡ ከሀይቁ አጠገብ ሳሩ ላይ እንደተጋደምኩ እንግዳ የሆነ
ሀሳብ በመጀመሪያ እንደ ተሳዳጅ ወደዚህ ወደመጣንበትና ከማይፈልገን አለም ወደተሸሸግንበት ወደዚያ ምሽት መለሰኝ።

ክሪስ፣ አሁን አስራሰባት አመት ሊሆንህ ነው፣ አባቴ እናቴን በመጀመሪያ ሲያገኛት የነበረበት እድሜ ማለት ነው”

አንቺ ደግሞ አስራ አራት፤ ልክ በእሷ እድሜ” ድምፁ ጎርነን ብሎ ነበር።

መጀመሪያ እይታ በሚፈጠር ፍቅር ታምናለህ?”

“በዚህ ርዕስ ላይ ጠቢብ አይደለሁም ትምህርት ቤት እያለሁ፣ አመነታ አንዲት የምታምር ልጅ አይቼ ወዲያው ፍቅር ይዞኝ ነበር ስናወራ ግን የሆነች ደነዝ ነገር ሆና ሳገኛት ለሷ የነበረኝ ስሜት ጠፋ፡ ግን ውበቷ በሌሎች
ነገሮች ከተደገፈ በመጀመሪያ እይታም ፍቅር ሊይዘኝ ይችላል ብዬ አስባለሁ ነገር ግን እንደዚያ አይነት ፍቅር አካላዊ መሳሳብ ብቻ እንደሆነ አንብቤያለሁ።

“እኔስ ደነዝ እመስልሀለሁ?”

“በጭራሽ! እንደሆንሽ እንደማታስቢ ተስፋ አለኝ፡፡ ምክንያቱም አይደለሽም።ፈገግ ብሎ ፀጉሬን ሊነካ እጁን እየዘረጋ ችግሩ ካቲ፣ ብዙ ተሰጥኦዎች ስላሉሽ ሁሉንም መሆን ትፈልጊያለሽ ያ ደግሞ የማይቻል ነው:"

“ዘፋኝም ተዋናይም መሆን እንደምፈልግ እንዴት አወቅክ?”
👍332
ቀስ ባለ ለስላሳ ድምፅ ሳቀ፡ “ሞኝ! ዘጠና በመቶ ጊዜሽን ትተውኛለሽ፡
ስትደሰቺ ደግሞ ለራስሽ ትዘፍኛለሽ፤ እንዳለመታደል ሆኖ ያን የምታደርጊው ብዙ ጊዜ አይደለም”
“አንተ ብዙ ጊዜ ደስ ይልሀል?”
አስደሳቹ ምሽት እንደገና ስለተፈጥሮና እንግዳ ስለሆኑ መንገዶቹ እንዳስብ አደረገኝ፡ የተፈጥሮ አብዛኞቹ መንገዶቹ ሙሉ በሙሉ አልረዳቸውም፣በሌሊት የማልመውን አይነት ነገር የማልመው ለምንድነው? ለምንስ ልቤ እየመታ ልደርስበት የማልችል የሆነ እርካታ እናፍቃለሁ?

ክሪስ እንድመጣ ስላሳመነኝ ተደስቻለሁ። እንደገና ሳር ላይ ጋደም ማለት፣ ቀዝቀዝ ማለትና መታደስ ከሁሉም በላይ ደግሞ እንደገና ሙሉ በሙሉ
ህያውነት እንዲሰማ መሆን እንዴት ደስ ያላል!

“ክሪስ…” አልኩ። ይህንን የሚያምር ምሽት እንዳላበላሽ እየፈራሁ፡ “እናታችን የት ትመስልሃለች?
ኮከቦቹ ላይ ሲያፈጥ ቆየና በመጨረሻ “የት እንደሆነች አላውቅም” ሲል መለሰልኝ።

“ምንም የምትጠረጥረው ነገር የለም?”

“እንዴ! አለ እንጂ”

“ምንድነው?”

“ታማ ሊሆን ይችላል”

“አልታመመችም! እናታችን ታማ አታውቅም:"

“ለአባቷ የስራ ጉዞ የሆነ ቦታ ሄዳ ይሆናል”

“ታዲያ ለምን እንደምትሄድና መቼ ልትመለስ እንደምትችል አልነገረችንም?”

“አላውቅም!” አለ በንዴት ምሽቱን ያበላሸሁበት ይመስለኛል። እውነቱን ነው ማወቅ አይችልም ከኔ የበለጠ ሊያውቅ አይችልም:

“ክሪስ… በፊት የምትወዳትና የምትተማመንባትን ያህል አሁንም
ትተማመንባታለህ?” “እንደዚህ አይነት ጥያቄ አትጠይቂኝ… እናቴ'ኮ ናት። ያለችን እሷ ብቻ ናት። እዚህ ተኝቼ ስለሷ መጥፎ ነገር እንድናገር ጠብቀሽ ከሆነ አላደርገውም! ዛሬ ማታ የትም ብትሆን ስለኛ ማሰቧ አይቀርም: እናም ተመልሳ ትመጣለች። ስለ መሄዷና ይህንን ያህል ጊዜ ሳታየን ስለመቆየቷ
ጥሩ ምክንያት ይኖራታል። በዚያ መተማመን ትችያለሽ፡”

የማስበውን ልነግረው አልቻልኩም መጥታ ስለ እቅዶቿ ለእኛ ለመንገር ጊዜ ልታጣ አትችልም እሱም ይህንን እውነታ ያውቀዋል

ህመም ሲሰማው ድምፁ ላይ የሚደመጥ ጎርናና ድምፀት
አለ፡ ህመሙ ግን አካላዊ አልነበረም: በጥያቄዎቼ ያመጣሁበትን መጎዳት ልወስድለት
ፈለግኩ: “ክሪስ… በቲቪ ስመለከት በእኔ እድሜ ያሉ ሴቶችና በአንተ እድሜ ያሉ ወንዶች እየተቀጣጠሩ መገናኘት ይጀምራሉ እና… በቀጠሮ ጊዜ ምን እንደሚደረግ ታውቃለህ?”

“አዎ ቲቪ ላይ ብዙ አይቻለሁ”

“ማየት ግን ከማድረግ ጋር አንድ አይደለም::”

“ምን እንደምታደርጊና ምን እንደምታወሪ አጠቃላይ ሀሳብ ይሰጥሻል። በዛ ላይ አሁንም አንቺ ወንዶችን ለመቅጠር ገና ልጅ ነሽ”
የሆነ ነገር ልንገርህ? በእኔ እድሜ ያለች ሴት በአንተ እድሜ ካለ ወንድ
በአንድ አመት ትበልጣለች::"

“እብድ ነሽ!”

"እብድ? ይህንን ሀቅ ያነበብኩት ከመፅሄት ላይ ነው የፃፈው ደግሞ በዚህ ርዕስ ላይ በደንብ የሚያውቅ የሳይኮሎጂ ዶክተር ነው" አልኩ በጣም ተገርሟል። “እሱ እንዳለው፣ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ በስሜት ቶሎ ይበስላሉ”

የዚህ ነገር ፀሀፊ በራሱ አለመብሰል የሰው ዘርን ሁሉ እየገመተ ነው፡”
ክሪስ አንተ ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ ታስባለህ፤ ግን ማንም ሰው ሁሉንም ነገር አታውቅም” ብዙ ጊዜ
እንደሚያደርገው ጭንቅላቱን ወደ እኔ ዞር አድርጎ አይኖቼን
ተመለከተ። “ልክ ነሽ!” ሲል ደስ በሚል ስሜት ውስጥ ሆኖ ተስማማ “የማውቀው ያነበብኩትን ብቻ ነው በውስጤ የሚሰማኝ ግን ልክ እንደ አንደኛ ክፍል ተማሪ ግራ የተጋባ ነው: እናታችን ባደረገችው ነገር እጅግ ተናድጃለሁ ስለሚሰሙኝ በርካታ ስሜቶች የማወራው ወንድ አጠገቤ የለም”
በክርኑ ደገፍ ብሎ ቀና አለና ወደታች ፊቴ ላይ አፍጥጦ “ፀጉርሽ ተመልሶ ለማደግ ብዙ ጊዜ እንደማይፈጅ አስባለሁ: ያንን መቀስ ባልተጠቀምኩ ኖሮ
ምንም ጥሩ ነገር አላመጣም::” ስለፎክስወርዝ አዳራሽ እንዳስብ የሚያደርገኝ ምንም ነገር ባይኖር የተሻለ ነበር።

“እንሂድ ክሪስ…” አልኩት።
እያመነታ ተነስቶ እጆቹን አፍታታና “አንድ ዙር እንዋኝ?” ሲል ጠየቀኝ
“አይ እንመለስ…”
ከሀይቁ እየራቅን በጫካው ውስጥ አድርገን ደስ በሚል ፀጥታ ውስጥ በቀስታ እየተራመድን ነው:: ከእስር ቤቱ ውጪ መሬት ላይ በመሆናችን ያገኘነውን ነጻነት እያጣጣምነው ተጓዝን፡

ራሳችን ሰርተን ጭስ ማውጫው ላይ ያሰርነው ገመድ አጠገብ ለረጅም ጊዜ ቆምን: “ክሪስ የተለየ ነገር ተሰምቶሀል?” ስል ጠየቅኩት
“hመራመድ… መሬት ላይ ከመሮጥና ለአጭር ጊዜ ከመዋኘት በስተቀር ያደረግነው ነገር የለም: ነገር ግን በጣም በተስፋ የተሞላሁና ህያው እንደሆንኩ
ተሰምቶኛል” አለኝ፡

“ብንፈልግ ዛሬ ማታ እናታችንን ሳንጠብቅ ማምለጥ እንችል ነበር። ወደ ላይ ወጥተን መንትዮቹን የምንይዝበት ማንጠልጠያ እንስራና በእንቅልፍ ላይ እንዳሉ ወደታች ማውረድ እንችላለን፡ ማምለጥ እንችላለን! ነፃ እንሆናለን::

መልስ ሳይሰጥ ዝም ብሎ ወደጣሪያው መውጣት ጀመረ። ከተቀዳደደ አንሶላ የተሰራውን መሰላል በፍጥነት በእግሮቹ መሀል እየያዘ ወደ ላይ ወጣ። ልክ
ጣሪያው ላይ እንደደረሰ እኔ መውጣት ጀመርኩ: ገመዱ የሁለት ሰዎችን ክብደት ይይዛል ብለን ስላልተማመንበት ተራ በተራ መውጣታችን ግድ ነበር።

ወደታች ከመውረድ ወደ ላይ መውጣት ይከብዳል። ከእጆቼ ይልቅ እግሮቼ ጠንካራ እንደሆኑ ተሰማኝ፡ ላይ ወዳለው ወደሚቀጥለው ቋጠሮ ደርሼ የቀኝ
እግሬን አነሳሁ ድንገት ግራ እግሬ አሟለጨኝና በደካማ እጆቼ ብቻ ገመዱን እንደያዝኩ አየር ላይ ተንጠለጠልኩ

አጭር ጩኸት ከከንፈሬ አመለጠ! ከመሬት በጣም ከፍ ብያለሁ

“ጠብቂ!” ክሪስ ከላይ ሆኖ ተጣራ: “ገመዱን ቀጥታ በእግሮችሽ መካከል ነው ማድረግ ያለብሽ፤ ከዚያ በእግሮችሽ ጨምቀሽ መያዝ ነው: ፍጠኚ!” እየሰራሁ ያለሁትን ማየት አልቻልኩም: ማድረግ የምችለው ትዕዛዙን
መከተል ብቻ ነው፡ ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ ገመዱን በጭኖቼ መካከል ለመያዝ ጣርኩ ፍርሃት አድክሞኛል: አንድ ቦታ ላይ ረጅም በቆየሁ ቁጥር የበለጠ እየፈራሁ መጣሁ። መብረክረክ፣ መንቀጥቀጥ ጀመርኩ ከዚያ
እምባዬ መጣ የሚያናድድ የሴት እምባ!

“እጄጋ ልትደርሺ ትንሽ ቀርቶሻል። "ክሪስ አደፋፈረኝ “ጥቂት እርምጃዎች ብቻ… ከዚያ እኔ እይዝሻለሁ: አትፍሪ ካቲ! መንትዮቹ ምን ያህል እንደሚፈልጉሽ እያሰብሽ ብቻ ውጪ… ሞክሪ… አይዞሽ ሞክሪ!” ከላይ ያለውን ሌላኛውን ቋጠሮ ለመያዝ እጄን ከያዝኩበት ለማስለቀቅ ለራሴ
መንገር ነበረብኝ፡ ደግሜ ደጋግሜ ለራሴ ማድረግ እችላለሁ! ማለት ጀመርኩ እግሮቼ ሳሩን በመርገጤ ምክንያት ያሟልጫሉ። ግን ደግሞ ክሪስም ሳሩ ላይ ነበር፡ ቢሆንም መውጣት ችሏል እሱ ከቻለ ደግሞ እኔም እችላለሁ።

ቀስ በቀስ የክሪስ እጅ እጄን መያዝ የሚችልበት ርቀት ላይ ደረስኩ
ጠንካራ እጆቹ ሲይዙኝ ከእጆቼ ጣት ጀምሮ እስከ እግሮቼ ጣት ድረስ ደሜ በእፎይታ ሲሞቅ ታወቀኝ በጥቂት ሰኮንዶች ውስጥ ወደላይ ስቦ አወጣኝና በሳቅና በለቅሶ ታጅበን ተቃቀፍን፡ ከዚያ ዳዴ እያልን ጭስ መውጫው አጠገብ ደረስን፡ የዚያን ጊዜ ነው እየተንቀጠቀጥን የተለመደው ግዛታቸው ውስጥ ያረፍነው ክሪስ አልጋው ላይ ተጋድሞ አተኩሮ እያየኝ ካቲ… ሀይቁ ዳር ጋደም ያልን ጊዜ ለአንድ ወይም ለሁለት ሰከንድ ትንሽ መንግስተ ስማያት ያለን
አልመሰለሽም ነበር? ከገመዱ ላይ ልትወድቂ ስትይ ደግሞ እኔም የምሞት መስሎኝ ነበር። ሁለተኛ እንደዛ አናደርግም ክንዶችሽ የኔን ክንዶች ያህል ጠንካራ አይደሉም ያንን በመርሳቴ ይቅርታ አድርጊልኝ”
👍361
የምሽቱ መብራት ጥጉ ላይ ሆኖ እየበራ ነው፡ በድንግዝግዙ ውስጥ አይኖቻችን ተገናኙ። “ስለሄድን አላዘንኩም: ደስ ብሎኛል፡ የእውነት ስሜት ከተሰማኝ ረጅም ጊዜዬ ነበር።"

“እንደዚያ ነው የተሰማሽ?” ሲል ጠየቀኝ: “እኔ ... ረጅም ጊዜ ከቆየ መጥፎ ህልም ላይ ለትንሽ ጊዜ የነቃን አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ፡"

እንደገና አነሳሁበት። ማንሳት ነበረብኝ፡፡ “ክሪስ እናታችን የት ያለች
ይመስልሀል? ቀስ በቀስ እኮ ከእኛ እየራቀች ነው ከዚህ በፊት ይህንን ያህል ጊዜ ሳታየን ቆይታ አታውቅም ከጠፋች ከወር በላይ ሆኗታል፡”

ከባድና የሀዘን ትንፋሹን ስማሁ። “የምሬን ስነግርሽ ካቲ፣ አላውቅም! ለአንቺ ከምትነግርሽ የተለየ ምንም አልነገረችኝም: ግን ጥሩ ምክንያት ይኖራታል ብለሽ መወራረድ ትችያለሽ"

“ግን ያለምንም ማብራሪያ ትታን ለመሄዷ ምን አይነት ምክንያት ሊኖራት ይችላል? ልታደርገው የምትችለው ትንሹ ነገር ያ አይደል እንዴ?”

“ምን እንደምል አላውቅም”

“ልጆች ቢኖሩኝ እሷ እንደተወቻቸው አልተዋቸውም ነበር። አራት ልጆች
አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፌ አልረሳቸውም ነበር”

“ልጆች አይኖሩሽም አስታወስሽ?”

“ክሪስ፣ አንድ ቀን በሚያፈቅረኝ ባል ክንዶች ውስጥ እደንሳለሁ እና የእውነትም ልጅ ከፈለገ አንድ ለመውለድ ልስማማ እችል ይሆናል"

“እርግጥ ነው እያደግሽ ስትመጪ ሀሳብሽን እንደምትቀይሪ አውቃለሁ"

“ወንድ ሊያፈቅረኝ እንዲችል የሚያደርግ በቂ ቁንጅና ያለኝ ይመስልሀል?"

“ከበቂ በላይ ቁንጅና አለሽ፡'' ያፈረ ይመስላል

“ክሪስ፣ እናታችን አለምን የሚሽከረክራት ገንዘብ ነው እንጂ ፍቅር አይደለም ያለችንን ታስታውሳለህ? ሳስበው የተሳሳተች ይመስለኛል:"

“እውነት? በደንብ አስቢው ለምን ሁለቱም አይኖርሽም?”

አሰብኩት ብዙ አሰብኩት ጋደም ብዬ ኮርኒሱ ላይ እንዳፈጠጥኩ ፍቅርና ህይወትን ደግሜ ደጋግሜ በጥልቀት አሰላሰልኳቸው: ካነበብኳቸው መፃህፍት ውስጥ አንድ የጥበብ ፍልስፍና እወስድና ህይወቴን ሙሉ በዚያ ለማመን
እይዘዋለሁ

ፍቅር መጥቶ በሬን ካንኳኳ ያ ለኔ በቂ ነው።

አንድ ያልታወቀ ደራሲ ሲፅፍ “ዝና ቢኖርህም በቂ አይደለም፤ በዚያ ላይ ሀብት ቢጨመርበት እንኳን አሁንም በቂ አይደለም ዝና ሀብት እና ፍቅር ቢኖርህም... አሁንም በቂ አይደለም” ብሎ ነበር እና እጅግ አዝንለታለሁ።

ምክንያቱም ፍቅር ብቻውን እንኳን በቂ ነው...

ይቀጥላል
23👍18👏1
በህይወት መንገድ ላይ.
(ታጋቾቹ)
ምዕራፍ-4
(በዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)

///
ሀገር ፅልመት ለብሳለች....ዜጎቾ የተስፍ ምክነት በሚባል ክፍ በሽታ ተጠቅተው እየማቀቁ ነው።በሽታው በወረርሺኝ ደረጃ ተሠራጭቶ ሚኒዬኖች የቁም ሞት እንዲሞቱ ምክንያት ሆኗል።ግን ደግሞ ቀባሪ አጥተው በድናቸውን ይዘው በየአደባባዩ ይንገላወዳሉ።ሁሉም ሰው የተጨማደደ ጭለማ ፊት ነው ያለው.አዎ ሁለችንም እንደዛው ነን፤. ብንስቅ እንኳን ሳቃችን ትወና ፈገግታችንም የለበጣ ነው።
በአእምሮችን የሚብላላው ሀሳብ ስለመገፋታችን የሚዘምር፤ስለስብራታችን የሚያንጎራጉር ብቻ ነው። ከአንደበታችን ሰቆቃ፤ ምሬትና እሮሮ ያዘሉ ቃላት ናቸው እየተንከባለሉ የሚወጡት።አዎ ይሄ ከመሬት በላይ ያለው አሁናዊ የአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ነው፡፡እኛም የዚህ እውነታ አካል ነበርን....አሁን ግን ተነጥለናል…ለቅሶችንም ሆነ ጩኻታችን ሀይወታችንን ለተወሰነ ቀንም ቢሆን ባለችበት ስጋ ውስጥ አስሮ የማቋየት የሰርቫይቫል ትግልን መሰረተ ያደረገ ነው ፡፡.እንዲያ ሲሆን ደግሞ ነገሮችን የምናይበት እይታ የተለየ ይሆናል.. እኛ አሁን እዚህ ከምድር በታች የታገትን አምስት ግለሰቦች ከሶስት ቀን በፊት እንደምናደርገው አሁን የዘይት ዋጋ መወደድ ጭራሽ አያሳስበንም..ዘይት እራሱ እስከወዲያኛው ቢጠፋ ግድ ያለው ሰው ከመካከላችን የለም…የኢኮኖሚ ግሽበቱም ሆነ የኑሮ ንረቱ የቅንጦት ወሬዎች ናቸው፡፡መንግስት ኖረ ተገረሰሰ አያሳስበንም..አረ ከዛም አልፎ የሀገር ህልውና እራሱ ከአጀንዳችን ውጭ ነው፡፡ከዚህ ጭለማና አስፈሪ የአለት ክመምር በሆነ ተአምር በህይወት እንውጣ እንጂ ስንወጣ ሱማሌያዊ እንሁን ሱደናዊ ቡኃላ የምናስብበት ጉዳይ ነው የሚሆነው፡፡:ኣይገርምም ግን ስለምንም ነገር ያለን እይታና ተርጉም ቆመን በምናስብበት ቦታና ሁኔታ እንደዚህ የተንቦረቀቀ የትርጉም ልዩነት መኖሩ ….
////
ምንም አይነት እርዳታ ሳይደርስልን ከምድር በታች እንደተቀረቀርን 16 ሰዓት አለፈን።አሁን ረሀብና የውሀ ጥም እየተፈታተነን ነው።በሪሁን እና አይዳ እንኳን ደክሟቸው መሰለኝ ከንግግራቸው ቆጠብ ከቀልድቸውም ለዘብ ብለዋል።
"ጋሽ አህመድ አረ አንድ ነገር እናድርግ"እኔ ነኝ ግራ ገብቶኝ በንጭንጭ የጠየቅኩት
"ኢንጂነር ምን እናድርግ ...የታየህ ነገር አለ?"
"ቢኖርማ እነግራችሁ አልነበር"
"እኔ ግን ምን ማድረግ እንዳለብን የመጣልኝ መሠለኝ ።››በሪሁን ነው ተናጋሪው፡፡
ምን?..ምን.."በጉጉት ሁላችንም ጠየቅነው፡፡
ሠላምን ጨምሮ ሁላችንም በያለንበት አይናችንንም ቀልባችንንም ወደ እሱ አዞርን"
"ሽንታችሁ አልወጠራችሁም?" ከሀሳባችን ጋር የማይገናኝ ግን ደግሞ ወቅታዊና ወሳኝ ጥያቄ ጠየቀን፡
"ምን..?"
"ሁላችሁም ጮኸችሁ እኮ....ሽንታችሁ ወጥሯችሆል ወይስ አልወጠራችሁም…?.ቀላል ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩት.?"
‹‹እኔ ጭርቅ ላደርገው ነው›አለች አይዳ
"እሱማ እኔም ..."አልኩ የኩላሊቴን ጥዝጣዜ በውስጤ እያስታመምኩ
ሠላም ባለችበት ተንቆራጠጠች...ጋሽ አህመድ አንገቱን ደፋ....
"በሪሁን ከተቀመጠበት ተነሳና ትናንትና ከበላያችን የተጫነንን አለት ለመናድና መውጫ ለማግኘት ስንጠቀምበት የነበረውን እናም በተጨማሪ. ከዘንዶ ጋር ልንፋለምበት የነበረውን… ባለ 32 ዲያሜትር የአርማታ ጉማጅ ብረት ይዞ እኛ ከተቀመጥንበት በተቃራኒ ትናንት ዘንዶው ሾልኮ ከወጣበት ቀዳዳ አካባቢ በመሄድ መቆፈር ጀመረ...
"እንዴ ምን እየሠራህ ነው....?እዚህ ለመሰንበት እኮ የወሰንክ ነው የምትመስለው"አልኩት

"አይ የእኔ ውሳኔ ምን ይረባል ብለህ... አሁን ወሳኙ ከዚህ የቢሾፍቱ ሀይቅ መሠረት ስር የቀረቀረን አባታችን ቆሪጥ ነው"

"ቢስሚላሂ አለ ጋሽ አህመድ››
ሰላም ‹‹በኢየሱስ ስም ››ስትል እኔ ባለውበት ሽምቅቅ አልኩና በፀጥታ አማታብኩ....አይዳ በግዴለሽነት ትከሻዋን ከፍ ዘቅ አደረገች፡፡
"እንግዲህ የእውነት በሀይማኖት መቻቻል ማለት እንዲህ ነው...ሁላችሁም የየራሳችሁን አምላክ ጠርታችሆል..ምን አልባት በእነሱም መካከል መቻቻል ካለ ተጋግዘው ከዚህ ሲኦል ያወጡን ይሆናል"
መአቱን ለእኛ እያወራ አንድ ሜትር በአንድሜትር ጥልቀቱ 50 ሤ ሜትር የሚሆን ጉድጎድ ቆፍሮ አጠናቀቀና
"ጋሽ አህመድ ደግሞ ርብራብን ስራልን››አለና ቀጣዩን ስራ ለእሱ በመልቀቅ… ከፋውንዴሽኑ ብረት ጋር አብረው የወረድ የፎርም ወርክ ጣውላዎችን ይሰበስብለት ጀመር...እኔ ፤አይዳና ሰላም እጃችንን አጣምረን እየተመለከትን በአንድ ሰአት ውስጥ ቅልብጭ ያለች ሽንት ቤት ተሠራ...ሶስት የሚሆኑ ብረቶች መሬት ላይ ተተከሉና የሠላም ጋዎን እንደከለላ ተደረገበት..
"እሺ ...ከሁለት አንዳችሁ ግቡና ባርኩልን"አለ በሪሁን ወደ ሁለቱ ሴት እየተመለከተ
ሰላም አፈረች..."አረ እናንተ ቀድማችሁ ተጠቀሙ"
‹‹ግቢ አንጂ ..እኛ ነን መቅደም ያለብን››"አይዳ አበረታታቻት ..ሰላም ፈራ ተባ እያለች መራመድ ጀመረች
"ሠላም"ጠራት በሪሁን
"አቤት"አለችና ባለችበት ቆመች
ምን ሊላት ነው ብዬ ስጠብቅ ቀጥታ ወደእኔ መጣና "ኢንጂነር ኪስህ ውስጥ ሶፍት ያየው መሠለኝ"

"አዎ..አለኝ"እጄን ወደ ኪሴ ሰደድኩና ያለኝን ሶፍት እጅ ላይ አስቀመጥኩለት…..እኩል ሶስት ቦታ ከፈለና , አንዱን ለእኔ መልሶ የተቀረውን አንዱን ለሰላም አንዱን ለአይዳ አደለ..."ብሩህ የሆነ አንፀባራቂ ፈገግታ ከሁለተ ሰቶች ተቸረው "በፈጣሪ ይህቼ ሰላም ሚሏት መለኩሴ መሳይ ሴት ፈገግ ስትል ሌላ አስደማሚ ወጣት ነች ከውስጧ ፈጣ የምትወጣው...ሰው እንዴት ቆንጆ መልክ ሳይኖረው እንዲህ ያምራል››.ሶፍቱን ተቀብላ ገባች።
እጄ ላይ የተወልኝን ሶፍት ወደ ፊት ዘርግቼ .."ለእናንተም ውሰድአ"አልኩኝ.እሱንና ጋሽ አህመድን ማለቴ ነው፡፡
"አይ ይቅርብን ..ኦኛ መላ ነገራችን የጠነከረ ነው ...ሳሩንም ድንጋዩንም ብንጠቀም ምንም አይለንም...ባይሆን የሚሆነው አይታወቅምና ቆጠብ አድርጋችሁ ተጠቀሙ›› የሚል ምክር ሰጠን፡፡

የሽንት ቤቱ ትዕይንት ከተጠናቀቀ ብኃላ መልሰን ወደቁዘማችን ገባን ...አሁን አቀማመጣችን የተለየ ነው።ወንዶቹ ሠላምን ኤደን, መሀከል አድርገው እነሡ ከግራና ከቀኝ አጅበዎቸው ተጠባብቀውና ተደጋግፈው ተቀምጠዋል ።እኔ ከእነሡ በአንድ ሜትር ፈንጠር ብዬ ለብቻዬ ኩርምድ ብዬ ተቀምጫለው።ውስጤ ግን ከእነሱ ጋር መለጠፍን ነው የተመኘው...ከሙቀታቸው መቆደስ ..ከተስፋቸው መጋራት።
//
አሁን ቅርቃር ውስጥ ከገባን 22 ሰዓት ሆኖናል"በጣም እየተራብን ነው...ከረሀብ በላይ ደግሞ ውሀ ጥሙ...
"ቆይ ቆይ እስቲ...."ሰላም ነች ጆሮዎን ወደአናታችን ቀስራ ዝም እንድንል ያስጠነቀቀችን።
‹‹ምነው አሁንም ሌላ ነገር ሊፈጠር ነው እንዳትይይኝ ብቻ››ስጋቴን ተናገርኩ
‹‹አዎ ሊፈጠር ነው…ግን ጥሩ ነገር መሰለኝ››

ሁላችንም ተነቃቃን....እሷ የሰማችውን ነገር ለመስማት ሁላችንም በተመሳሳይ ጆሮአችንን ቀሰርን..አዎ ቃቃ ...የሚል ነገር ይሰማል… አረ እንደውም አፈሩ ከላያችን የተፈረፈረ ወደመሬት እየረገፈ ነው።

"እንዳልኩት አምላኮቻችን ተቻችለው እኛን ነፃ ለማድረግ እየተባበሩ መሠለኝ"አለ በሪሁን።
👍21
"እውነትህን ሳይሆን አይቀርም"አልኩት ...ምክንያቱም አሁን ከበላያችን የሚበነው አቧራ ብቻ ሳይሆን የሆነ ቱቦ መሳይ ነገር እየቦረቦረ ሲወጣ እየታየኝ ነው...አምስታችንም እርስ በርስ ተጣብቀን ቆመን አይናችንን አንጋጠን ሰርስሮ የሚወጣውን ነገር ምንነት ለመለየት እየጣርን ነው።
"ወይ አላህ ከልጆቼ መልሰህ ልታገናኘኝ ነው"አለ ጋሸ አህመድ፡፡
"ከዚህ እንደወጣው እሮጬ ሶስት ጆንቦ ድራፍት ነው የምጠጣው....ኢንጂነር ሂሳብ ባንተነው እሺ"በሪሁን ነው ፍላጎቱን በጉጉት የተናገረው፡፡
‹‹እንውጣ እንጂ አብረን ነው የምንገለብጠው..››አይዳ ነች
‹ትክክል እንደውም ቃልሽንም ትጠብቂያለሽ…መለቴ ሰጥሀለው ያልሽውን ነገር ወዲያው ነው የምትሰጪኝ››
‹‹ይመችህ…ላንተ ብቻ መሰለህ.ከዚህ በሰላም ልውጣ አንጂ ለጠየቀኝ ሁሉ ነው የማድለው..ድግሞ ይሄን ሚስጥር ለአገር ምድሩ ንዛና ወንዱ ሁሉ ትሰጠኛለች እያለ እንደዳቦ ቤት ወረፋ ይያዝ አሉ››
‹‹ደሞ ለሞላ ሴት ምን ስለሆነ ነው ወንዱ ላንቺ ወረፋ የሚሰለፈው?›እኔ ነኝ በንዴት የተናገርኩት
‹‹ኢንጂነር አንዴ ብትቀምስ አንተም መሰለፍህ አይቀርም››አለቺኝ….ከአይዳ ነገሮች በጣም የሚያበሳጨኝ ምንም ነገር ብናገር ላናድዳት አለመቻሌ ነው፡

እሷን ችላ አልኩና ወደ በሪሁን ዞሬ "ተስማምቼለው"አልኩት ከእሱ ጋር ጃንቦ ቤት ገብቼ ጎን ለጎን ተቀምጬ ስጠጣ ታይቶኝ ፈገግ አልኩ...
ሠላም በራሷ ሀሳብ ውስጥ ነበረች"አልገባኝም እየሰረሰረ እየመጣ ያለው እኮ ባለ 160 ዲያሜትር የብረት ቱቧ ነው።በዚ መቼስ አይጥ ካልሆነ ሰው ሊመጣም ሆነ ሊወጣበት አይችልም።››አለ ጋሽ አህመድ
"አይ መጀመሪያ በህይወት መኖራችንን ለማረጋገጥ እየጣሩ ነው ...አየህ ዝም ብለው በሰፊው እንዳይቆፍሩ የመሬቱን መናድ ፈርተው መሰለኝ...."አብራርቼ ሳልጨርስ
ሠላም ሌላ ጩኸት ጮኸች"ቱቦ ጫፍ ላይ የሆነ ነገር አለ"
"አዎ መገናኛ ሬዴዬ ነው"ጋሽ አህመድ ነው ተናጋሪው።
"ጎምበስ በል"አለው በሪሁን ጋሽ አህመድ ፊት ቆሞ
‹‹ምን እየሆንክ ነው ?ለምንድነው የማጎነበሰው?"
"ለአላህ ምስጋና ለማድረስ ነዎ..ባክህ ስቀልድ ነው ቱቦ ገና ቦርብሮ ስራችን እስኪደርስ ትእግስት የለኝም ....ትከሻህ ላይ ተሸከመኝና ሬዲዪኑን ለውርደው"
"አዎ እውነቱን ነው"ሁላችንም ተጋግዘን አንጠለጠልንና ጋሽ አህመድ ተከሻ ላይ ጫነው....ሬዲዬኑን ይዞ ወረደ.. ጋሽ አህመድ ተቀበለውና መጎርጎር ጀመረ...
አዎ ድምፅ ተሠማ .."
""አህመድ ነኝ ..ይሰማል"
"አዎ ይሰማል...በህይወት አላችሁ?የተጎዳ ሰው አለ?"

"ሁላችንም ሰላም ነን .. በሪሁን ትንሽ ጭንቅላቱን ተፈንክቷል ..ቢሆንም ጉዳቱ ለክፍ የሚሠጥ አይደለም"
"በሪሁን ..በርዬ...አይዞኝ"የብዙ ሰው መንጫጫት በሬዲዬ ይሰማል።
ከላይ ያለው ሰውዬ ጥያቄውን ቀጠለ"ለመሆኑ ስንት ናችሁ..?እርግጠኛ መሆን አልቻልንም"
‹‹አምስት ነን"እኔ ..በሪሁን ..ኢንጂነር በቃሉ ፤አይዳ እና አዲሷ እስቶር ኪፐር ሰላም ነች።
"እሺ እንግዲህ በህይወት በመኖራችሁ ደስተኛ ነን ...ያው ከ35 ሜትር ርቀት ላይ ስላላችሁ በጣም አስቸጋሪ ስራ ነው የሚጠብቀን...ከአሁን ብኃላ ቢያንስ የስድስት ሰአት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ ቁፎሮ ይጠብቀናል።እስፍተን እየቆፈርን ያለነው ይሄ ቱቦ በመጣበት አቅጣጫ ስለሆነ ...በተቻለ መጠን ከዛ ዞር የምትሉበት እድል ይኖራል?"
"አዎ ሰፊ ዎሻ መሳይ ቦታ ላይ ነን ያለነው ቢያንስ ሰባት ስምንት ሜትር አፈግፍገን መቀመጥ ስለምንችል ሳትሳቀቁ መቆፈር ትችላላችሁ"
"ጥሩ ዜና ነው ያሰማሀን ..አሁን ቱቦውን ወደላይ ስበን ከማውጣታችን በፊት ምግብና መጠጥ ልንልክላችሁ ነው ...ሌላ የምትፈልጉት የተለየ ነገር ይኖራል..?
"ፍሻና የቁስል አልኮል ...እና የህመም ማስታገሻ ኪኒን"እኔ ነኝ እንዲህ ያልኩት
"በሪሁን ተነጫነጨ ..አሁን ለስድስት ሰዓት ይሄ የመድሀኒት ዝርዝር ምን ያደርጋል ...ባይሆን ከቻሉ አረቄ ነገር ቢልኩ"
"ከላይ ያለ ድምፅ መጣ....ቤተሰቦቻችሁ በጣም ስላጨናነቁን ሁላችሁንም ተራ በተራ አንዳንድ ሰው ያናግራችሆል››
"መጀመሪያ ኢንጂነር..."
ሬዲዬኑን ተቀበልኩ...ወንድሞቼ...እናቴ ወይስ
"ሄሎ ቤብ..."እጮኛ ተብዬዎ ነች
"አለው እንዴት ነሽ?"
"ውይ ቤብ ...አጣውህ ብዬ ውስጤ ተሠብሮ ነበር ...ለሀገር ጠቅላላ ጥር ላይ ላገባነው ብዬ ተበጥርቄ አንድ ነግር ብትሆን ምን ይውጠኝ ነበር?በጣም ነው ሚስ ያደረኩህ እሺ...እንደውም ጥር ድረስ መጠበቅ የለብንም...››
ወሬዎ አቅለሸለሸኝ.‹‹...ምን ነክቶኝ ነው ይህቺን አይነት ቀፎ ያፈቀርኩት"
"የእሷን ወሬ እንዳልሰማ ሆኜ ‹‹..እነእማዬ አልሰሙም እንዴ"
"እኔማ ይረበሻሉ ብዬ ደብቄያቸው ነበር ..አሁን ግን ሚዲያው ሆነ ፌስ ብኩ ጠቅላላ የሚያወራው ስለናንተ ስለሆነ ሰምተው ከወንድሞችህ ጋር ወደእዚህ እየመጡ ነው።ብታይ አይደለም እናንተ እኔ ራሴ ፌመስ ሆኜያለው እስከአሁን አራት ጋዜጠኛ ነው ኢንተርቪው ያደረገኝ።››
"ቸው በቃ"
ሬዲዎኑን ለጋሽ አህመድ አቀበልኩና ጥግ ይዠ ኩርምት ብዬ በመቀመጥ ቀጣዪን መከታተል ጀመርኩ።ጋሽ አህመድ እየተላቀሰ ሚስቱንና ልጆቹን አወራ..ከዛ በሪሁን እናቱን አወራና ..ለአይዳ አቀበላት..እሷም በተመሳሳይ ታላቅ እህቷን አወራችና ለሠላም አቀበለቻት....
"አልፈልግም›› አለቻት
‹‹ለምን.?.››.
‹‹የሚያናግረኝ ሰው የለማ"
ሁላችንም ተገርመን እርስ በርስ ተያየን"ጋሽ አህመድ ከአይዳ እጅ መገናኛ ሬዲዬኑን ተቀብሎ እላይ ካሉት ጋር ተገናኘ
"ሠላምን ለማናገር የቀረበ ቤተሠብ አለ?"
ፀጥ አለ
"ይሠማል..ሠላምን ማናገር የሚፈልግ ሰው አለ?"ደግሞ ጠየቀ
"አትልፋ ማንም አይኖርም"አለችው ሠላም
እውነትም ሠላምን ለማናገር የቀረበ ሰው የለም.አይዳ‹‹የእውነት እንነጋግር ከተባለ ሰው አናገረሽ አላናገረሸ ምን ይፈይድልሻል..አማልክቱ በቀጥታ እያናገረሽ እያየን›አለች.ለመጀመሪያ ጊዜ በአይዳ ሀሳብ ተስማማው፡፡›
ከላይ የሚያናግረን ሰው ‹‹..አሁን የሚያስፈልጋችሁን ነገር በቱቦው እንልካለን"ከሚል ንግግር ብኃላ የሬዳዬ ግንኙነቱ ተቆረጠ ...ከተወሰነ ደቂቃ ብኃላ ከገመትነው በላይ ብዙ ነገር በቱቧ እየተንጠባጠበ ይወርድ ጀመረ...ሁላችንም ልክ እንደተማከረ ሰው በቅድሚያ ያነሳነው ባለግማሽ ሊትር ውሀ ነው።የቻልነውን ያህል ተጎነጨንለት"ብስኩቶች ፤ኩኪሶች፤እሽግ ጅውሶች፤ሙዝ"መስቲካ ቸኮሌቶች ፤አልኮል፤:ኪኒኒ…"
የመጣው እቃ የሳምንት ስንቅ ይመስላል
"በስድስት ሰዓት ነው በስድስት ቀን ነው እናወጣችኃለን ያሉት"
ቱቦው ተግባሩን ሲጨርስ እንዳመጣጡ እየተሸበለለ ወደውስጥ በመግባት ከእይታችን ተሰወረ....
፤የተላከልንን እቃ በወግ በወጉ ማሰናዳት ጀመርን..የእቃ ብዛት ምክንያት ተገለፀልን።ለካ እያንዳንድ ሰው አጋርነቱን ለማስረዳት በእያንዳንድ ዕቃ ሽፍን ላይ ስሙንና መልካም ምኞቱን በአጭሩ በመግለፅ ስለተላከ ነው። ከተላከው ዕቃ ባለማጋነን 80 ፐርሰንቱ ለበሪሁን እና ለአይዳ የተላከ ነው"ቀሪው 20ፐርሰንት ለሦስታችን"
👍144
ለበሪሁን"ምነው አብሬህ በሆንኩ "ብላ የላከች አፍቃሪ ሁሉ አለች።እና ደግሞ ለምን እንደተላኩልን ያልገብን ዕቃዎችም አግኝተናል ለምሳሌ ከእሽጋቸው ያልተፈቱ ሶስት የተለያየ መጠን ያላቸው ቢላዎዎች "ሁለት ላይተር"
‹‹አይዳ ሲጋራ ታጬሻለሽ እንዴ;?››ላይተሮቸን በማየቴ ነው የጠየቅኳት..ከመሀከላችን እሷ ብታጬስ አይገርመኝም
‹‹ለምን ጠየከኝ…?ይዘሀል አንዴ?››
አይ ላይተሩ ምን አልባት የተላከው ላንቺ ከሆነ ብዬ ነው?››
‹‹ጎበዝ ነቄ እኮ ነህ››አለቺኝ
የተላከልን እቃ ሁሉ የበሪሁንን ቱታ እንደ ከረጢት በማዘጋጀት በእሱ ጠቀጠቅንና ይቆፈራል ከተባለበት ስፍራ በተቃራኒ አርቀን በመውሰድ አደላድለን አስቀመጥንና እኛም ተረጋግተን በመቀመጥ ከተላከልን የሚበላ ነገር የሚስማማንን በመምረጥ መመገብ ጀመርን።

ይቀጥላል ....


ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj
❤️
👍109
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ


በበነጋው ምንም ዳመና ያልነበረው ብራ ደማቅና ሞቃት ቀን ሆኖ ዋለ የፀሐይ ብርሃን በሚስዝ ሔር መኝታ ቤት ተንጣሏል” እመቤቲቱ ትኰሳት የዞረባት መስላ ፊቷ ቀልቶ ዐይኖቿ እየተቁለጨለጩ አልጋዋ ላይ ተጋድማለች ማስተርና ሚስዝ ሔር ከዘመናዊ ኑሮ ጋር እምብዛም አልተላመዱም " የመልበሻ ክፍል
የሚባል አያውቁም » መኝታ ቤታቸው ሰፊ ነበርና ሌላ ክፍል የመኖሩን ነገር አያምኑበትም ነበር።

ሚስተር ሔር ለቁርስ የምትፈልገውን ቢጠይቃት ፡ ከሻይና ከትንሽ የተጠበሰ ዳቦ በቀር ሌላ ምንም እንደማትቀምስ ነግራው '' ይልቅ እባክህን ከመውጣህ በፊት መስኮቱን ክፈትልኝና አየሩ ሲገባ ይሰማኝ " አለችው

“ የኔኮ እምነት ይህ አሞኛል የምትይው አን ...የታመምሽ እየመስልሽ እንጂ እውነት ይህን ያህል ታመሽ አይደለም ከመኝታሽ ተነሥተሽ የተጫጫነሽን
የሀሳብ በሽታ አራግፈሽ ወደ ምግብ ቤት ብትወርጂ ቁርሱም ተስማምቶሽ ቀኑን
ሙሉ ደስ ብሎሽ በዋለ ነበር በተረፈ ከዚ ተጋድመሽ ከማይረባ ሻይ በቀር ምንም ሳትቀምሺ ከተቀመጥሽ ትርፉ ድካም፡መንቀጥቀጥና እርባና ቢስነት ብቻ ይሆናል "

ለቁርስ መነሣት ከተውኩ ብዙ ሳምንት እንደሆነኝ ታውቃለህ ሪቻርድ
አሁንም ቢሆን ጭራሽ መነሣት አይሆንልኝም ” አለችው

'' በይ እንግዲያው ይኸኛውን መስኮት ብከፍትልሽ አየሩ በጣም ይቀርብሻል አለና ራቅ ያለውን ከፍቶላት ወጣ " ሚስተር ሔር ምን ጊዜም ሁሉ ነገር እሱ እንዳለው ብቻ እንዲሆን ስለሚፈልግ ራቅ ያለውን መስኮት እንዲከፍትላት ብትጠይቀው ኖሮ የቅርቡን ይከፍተው ነበር

ከአንድ ከሁለት ደቂቃ በኋላ ባርባራ ገባች " ባርባራ የኋላ የኋላ ትዕግሥተኛ
አዛኝ መሆን ጀምራ ነበር " የጭንቀቷ ምሬት ሁሉ ዐልፋል " ጠይባዋ ሁሉ
በኀዘንና በብስጭት ብዛት ለዝቧል "

“ እማማ ... አሞሽ አደረ እንዴ ? ሰሞኑን እንኳን ዶህና ነበርሽ " ትናንት ደኅና ነበር የተኛሽ " አሁን አባባ

“ ባርባራ ! ሰማሽኝ ? እነዚያ ክፉ ሕልሞች እንደገና ታዩኝ

“ እዬ እማማ !ለምን እንደዚህ ትሆኛለሽ ! " አለች ባርባራ በንዴት ብድግ ብላ " “እንዶዚህ ሆነሽ እስክትታመሚ ድረስ በማይረባ ቅዠት ትሞኛለሽ?
በሌላው ጉዳይ ሁሉ ልባም ነሽ እንዶዚህ የመሰለ ነገር ሲመጣብሽ ግን ብልህነትሽ
ሁሉ የት እንደምትጥይው ይገርመኛል "

“ ልጄ ... ታድያ ምነው እንዴት እንደማዶርግ ብትነግሪኝ " አለች ሚሲስሔር የባርባራን እጅ እንደገና ወደሷ እየሳበች “ እነዚህ ሕልሞች በኔ ፈቃድ አያመጡም በትኩሳት ሲያቃጥሉኝ : በሽተኛ ሲያደርጉልኝ ልከለክላቸው አልቻልኩም " ትናንትና ደህና ነበርኩ ቀሎኝ ደስ ብሎኝ ተመችቶኝ ነበር የተኛሁት ቀኑን ሙሉ ስለ ሪቻርድ ማሰቤን ምንም ትዝ አይለኝም ሕልም እንዲታየኝ በሐሳብም ሆነ በተግባር ምንም ያደረኩት ነገር የለም
ህልሙ ግን መጣ " ምን ላድርግ ?

ግን እኮ እነዚህ ደስ የማይሉ ሕልሞች ከተዉሽ ብዙ ጊዜያቸው ነበር ”

“ ብዙ ነው እንጂ ባርባራ ያኔ ሪቻርድ ተደብቆ ከመጣ ወዲህ አንድ ሕልም እንኳን ማየቴ ትዝ አይለኝም "

“ እና ' በጣም መጥፎ ሕልም ነበር እማማ ?

“አዬ ልጄ በጣም!እውነተኛው የሆሊጆን ገዳይ ዌስት ሊን መጥቶ አየሁት !
ከዚህ ከኛ ጋር ሆኖ

በዚህ ጊዜ መኝታ ቤቱ በር ድንገት ተከፈተና የጀስቲስ ሔር ፊት ብቅ አለ " ሚሲዝ ሔር ከመደንገጧ የተነሣ ትራሷም እስኪርገበገብ ድረስ ስትንቀጠቀጥ
ባርባራ ከእልጋው ተፈንጥራ ሔደች" ደግነቱ የንግግራቸውን ርዕስ አላወቀውም "

“ ዛሬ ቁርስም አታቀርቢ ባርባራ ? እኔ እንድሠራው ትልጊያለሽ መስለኝ አላት

“ አሁን ትመጣለች ... ሪቻርድ ” አለችው ሚስዝ ሔር ከመቼም በበለጠ
ስልል ባለ ድምፅ "

ባርባራ አባቷን ተከትላ ሮጠችና ቁርሱን አቅርባለት ቡናውን ቀድታለት ስታበቃ ለናቷ ሻይና የተጠበሰ ዳቦ ይዛላት ግባች "

“ እስኪ ስለ ሕልምሽ ንገሪኝ እማማ ” አለቻት "

“ ቁርስ እንዳይበርድብሽ እንጂ ልጄ ?

“ አይ ግድ የለም ... ስለ ሪቻርድ አለምሽ ?

“ ስለሱ እንኳን እስከዚህም አላየሁም ትዝ ይልሽ የለ! ባርባራ ያን ጊዜ ሪቻርድ ሌሊት መጥቶ ግድያውን ሌላ ሰው እንጂ እሱ እንዳልፈጸመው ሲነግረኝ እኔ እንኳን ኦትዌይ ቤተል እንደሆነ ብዬ ብጠይቀው ሌላ እንግዳ ሰው ነው ; ኦትዌይ ቤተል አይደለም አለኝ ዛሬ በሕልሜ ያ እሱ ያለው ሰውዬ ይመስለኛል ወደ ዌስት ሊን መጥቶ ከቤቴል ጋር ከቢታችን ገብቶ ስናነጋግረው ፡ እኛ እሱ እንደ ገደለ ስንነግረው እሱ አይደለሁም ብሎ ሲከራከር ነገሩን ወደ ሪቻርድ ሲያላክከው ጭንቀቴ እንደዚህ አይምሰልሽ " እንዲያውም ፍራቱ መሰለኝ የቀሰቀሰብኝ

ምን ይመስል ነበር ? ” አለቻት ድምጿን ዝቅ አድርጋ

“ አሁን አላስታውሰውም መልኩ ሁሉ ከሕልሙ ጋር አብሮ ጠፋ » አለባበሱን ሁሉ ሳየው የትልቅ ሰው ይመስል ነበር " እኛም በእኩልነት አይተን በአክብሮት ነበር የምናነጋግረው

የባርባራ አእምሮ በካፒቴን ቶርን ነገር ተይዟል " ስሙ ለሚስዝ ሔር አልተነገረም ነበር አሁንም ቢሆን ልትነግራት አልፈለገችም " በራሷ ግን በጥልቅ ሐሳብ
ተዋጠች

"ባርባራ . . ይህ ሳይታሰብ ላይጠራ የመጣብኝ ሕልም ደስ አለለኝም ምናለች በይኝ ያንን አስቀያሚ ግድያን የሚመለከት አንድ ነገር መነሣቱ አይቀርም"

“እማማ ... እኔ በሕልም እንደማላምን ታውቂያለሽ » ሰዎቹ ሕልምን የዚህ ምልክት ነው የዚያ ምሳሌ ነው ብለው ሲተረጕሙት ስሰማ ይገርመኛል" ቢሆንም ይህ በሕልምሽ የታየሽ ሰው ቁመቱ እጉሩ ምን እንደሚመስል ብታስታውሺው ኖሮ ደግ ነበር "

“እኔ ትዝታው ሁሉ ከሕልሙ ጋር አብሮ ጠፉ አላልኩሽም ? ቁመቱ እንኳን ረጂም ይመስለኛል ብቻ ተቀምጦ ነው የነበር
ኦትዌይ ቤተልም በስተኋላው ቁሟል ሪቻርድ ከደጅ ተደብቆ ከቤት የገባው ሰውዬ ውጥቶ እንዳያየው ፈርቶ ይንቀጠቀጥ እንደ ነበር ተሰማኝና እኔም እንደሱ እንቀጠቀጥ ጀመር ህልሙ
ቁልጭ ያለና ግልጽ ከመሆኑ የተነሣ ነፍሰ ገዳዩ ዌስት ሊን ላይ በአካለ ሥጋ አለ መኖሩን ለጥቂት ደቂቃ አጠራጥሮኝ ነበር በርግጥ እዚህ እንዳለ ወይም ወደዚህ እንደሚመጣ ይሰማኛል " እውነትም ነገሩን ልብ ብዪ ሳስበው ግን መሠረት የሌለው ቅዠት መሆኑን ዐውቀዋለሁ " አለችና አንገቷን ደፍታ በልጁዋ ክንድ ደገፍ ብላ“ መች ነው ይህ መከራ የሚያበቃው ? አንድ ዓመት እንደ ዋዛ እልፍ ሲል ሌላ ይተካል ዓመት እስካመት ዓመቶች እየተከታተሉ ሲመጡ ሲያልፉ ልጄ ግን እንደ ተሰደደ ቀረ አንቺ ልጄ
እኔስ የሪቻርድን ነገር ሳስበው ያመኛል” ልቤ አልችል አለ! ናፈቅሁ እስካየው ጓጓሁ የምወደው ፊቱን ሳላይ በሕይወት መኖሩን አንዲት ቃል እንኳን ከሱ ሳልሰማ ይኽው ሰባት ዓመቱ ሊሆን ነው " እውነት እኔ የተቀበልኩትን መከራ የተቀበለች እናት ትኖር ይሆን ?

“ እንደዚህ ራስሽን አታስጨንቂው እማማ አለበለዚያ ሕመምሽ እየጠ
ናብሽ ይሔዳል ”

“ ታምሜአለሁ እኮ
ባርባራ ! ሌላ ምን እሆናለሁ ?

“ዐውቃለሁ ግን ይህ ኀዘን
ይህ ጭንቀት ከባሰ በሽታ ይጥልሻል " በየሰባት
ዓመቱ አንድ ለውጥ አለ ይላሉ አባቶች አሁንም ይህ ሰባተኛ ዓመት ሲያልፍ
ስለ ሪቻርድ አንድ ነገር ያሰማን ይሆናል ምናልባትም ነጻነቱን ያገኝ ይሆናል ተስፋ አትቁረጭ "

“ ተስፋስ አልቆርጥም አንድ ቀን ሐቁ ወደ ብርሃን ይወጣ ይሆናል " እኔማ
በሱ እያመንኩ እንዴት ተስፋ እቆርጣለሁ ?

“ሻይ ጨምሬ ላምጣልሽ እማማ ?'' አለቻት ከአጭር ዝምታ በኋላ
👍174
“ የለም ልጄ !አትምጪ ሻዩን ላኪልኝ አሁንም እንደጠማኝ ነው " አንቺ ወርደሽ ከአባትሽ ጋር ሁነሽ ቁርስሽን ብይ ምናልባት ፊታችን አዝኖ ያየ እንደሆነ ስለ ሪቻርድ እያሰባችሁ ነው እንዳይለን እፈራለሁ "

“ ቢልስ ? የማሰብ ነጻነትም የለንም ማለት ነው ?”

“ ኧረ ዝም በይ ልጄ ራሱ ለፍርድ ሊያቀርበው እንደማለ ታውቂያለሽ "
የሪቻርድን ወንጀለኝነት በትክhል አምኖበታል አሁን ደግሞ ስለሱ ማሰባችንን
ካወቀ ይጠረጥርና አገር ላገር ያስፈልገዋል አባትሽ እኮ በጣም . .

“ ያበዛዋል ” አለች ባርባራ ከእናቷ አፍ ነጥቃ "

ባርባራ ! እኔ የውነት ሰው ለማለት ነበር የፈለግሁት ” አለች እናቲቱ የልጅዋን አነጋገር በመቃወም "

“የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ለመስጠት አገር ላገር የሚያሳድዶው ከሆነ አረመኔ ነው የምለው " አለች እንባዋ በሽፋሽፍቷ እየተንቆረዘዘ " ከዚያ ዐይኗን ተጠንቅቃ አደራረቀችና ወደ ቁርስ ቤት ገባች።.....

💫ይቀጥላል💫
👍104🥰1
በህይወት መንገድ ላይ
(ታጋቾቹ)

ምእራፍ 5

ዘሪሁን ገመቹ

"""
-ምንበላው ብስኩትና ኩኪስ የመሠሉ ደረቅ ምግቦች ቢሆኑም አልተራብንም፤ውሀም በተመሳሳይ ቢያንስ ሁለት ደርዘን የሚሆን አለን፤አሁን ያጣነው ትዕግስት ነው። በ6 ሰዓት ውስጥ እናወጣችሆለን ብለው እኛጋ ለመድረስ የላኩትን ቱቦ መልሰው በመሳብ የተገኘውን ቀዳዳ ሙሉ በሙሉ የደፈኑት ሰዎች እንሆ ከ20 ሰዓት በላይ ሆኖቸዋል። ምንም የሙከራ ምልክት ሆነ ከላይ የሚረግፍ አፈር የለም።እንግዲህ እዚ ወጥመድ ውስጥ ከተያዝን ሁለተኛ ቀናችንን አጠናቀን ሶስተኛውን ልንይዝ ነው።
"ሰዎች ይሄ ነገር እያስፈራኝ ነው"አለ ጋሽ አህመድ።
"ጋሽ አህመድ አንተስ ሁለት ልጅ ወልደህ ዘርህን ተክተሀል፤እኔ አለው እንጂ ያን ሁሉ ዘመን አርሼ አርሼ ባዶዬን ልመርሽ ነው። እስኪ ልጅስ ይቅር ለማስለቃሻ የሚሆን ደህና ፎቶ እንኳን ተነስቼ ለእናቴ ብሰጣት አትሉም...የማረባ ነኝ"
"ትቀልዳለህ አይደል፤ይልቅ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ?"አይዳ ነች
"ቀጥይ"
"ትናንትና በሬዲዬ ሲያናግሩን ወደውስጥ የተቀበርነው ወይም አሁን የምንገኝበት ወደ 30 ሜትር ጥልቀት እርቀን ነው።እንደምናየው ያለንበት ክፍል ድፍን ነገር ነው ....ታዲያ አየር ከየት እያገኘን እስከአሁን ቆየን?እንዴት ሳንታፈን?"
"በጣም ነው የተገረምኩባት "you are a gunies " እንዴት እስከአሁን ታፍነን ሳንሞት?"ጥያቄዎን መልሼ ጠየቅኩ..ሁሉም መልስ ለማግኘት ጭንቅላቱን ማሠራት ጀመረ
"ስንጥቁ" ?"
"የምን ስንጥቅ?"ጠየቅኩ
"የእኔ ስንጥቅ አልልህ መቼስ....የማወራው የደፈነው..ዘንዶው የመጣበት"ይሄንን የምትናገረው ወደዛው እየተንቀሳቀሰች ነው...ሠላምን ጨምሮ ሌሎቻችንም ተከተልነው።
"ይሄን እኮ ደፍነነዋል...መድፈን ይቅርና በሙቀት ጊዜ እቤታችንን መስኮት እንኳን ስንዘጋ እንዴት ነው?
"አዎ እውነትህን ነው....ግን ስለዚህ ቦታ ብዙም የምናውቀው ነገር የለም"
"እሺ ምን እናርግ?""
"እኔ ይሄንን የደፈነውን ስንጥቅ መልሰን እንክፈተው..ከቻልን ሰፋ እናድርግና እስከየት እንደሚወስድ እንወቅ"፤ንግግሬን ሳልጨርስ በሪሁን ወደኃላ ተመልሶ ብረት በማምጣት መቆፈር ጀመረ።
"ቀስ ይሄ የተነደለ ጭንቅላትህ ሳይድን ሌላ አደጋ እንዳያጋጥምህ ?"ሰላም ነች ያስጠነቀቀችው
"መበርቀሱ ቀላል ነው ይልቅ ያ ዘንዶ መጥቶ እንዳይውጠኝ ፀልይልኝ፤ቆይ እንደውም"አለና መቆፈሩን አቋርጦ ትናንት ከተላከልን ዕቃዎችን ማተረማመስ ጀመረ
"ምን ፈልገህ ነው?"ጠየቀችው ሰላም
"ትናንት ቢላዋዎች ተልከውልን ነበር አይደል፤አዎ አገኘሁት ይሄው አለና ከሶስቱ ቢላዎ መካከል ተለቅ ያለውን አነሳና ሽፍኑን ገልጦ ወገብ ላይ ሸጉጦ ወደቁፋሮ ተመለሠ
"በቢላዎ ብቻ ልትቆፍር እንዳይሆን?"
"አይ አይደለም ቅድመ ጥንቃቄ ነው...ዘንዶ ከዎጠኝ ሆድን በዚህ ቀድጄ ነፃ ወጣለው"
ጋሽ አህመድና በሪሁን ተጋግዘው ሲቆፍሩ ቆዩና ከ30 ደቂቃ ብኃላ አንገት የሚያሾልክ አይነት ቀዳዳ ተገኘ...ሁላችንም በየተራ አንገታችንን አስግገን በማስገባት አሻግረን ለማየት ሞከርን፤ጭለማ ነው ምንም የሚታይ ነገር የለም ግን ልኬቱን መገመት በሚያስቸግር እሩቅ ቦታ ላይ ምንነቱን መለየት የማይቻል አነንፀባራቂ ነገር ይታያል።
"ሠማይ ነው እንዴ ሚታየው?"እኔ ነኝ ግራ ገብቶኝ የጠየቅኩት
"ምን አልባት ውሀም ሊሆን ይችላል...ማለት የቢሾፍቱ ሀይቅ ውሀ"አይዳ
ውሀ ከሆነ እኮ የሀይቁ ወለል ነው ሚሆነው ሰባና ሰማኒያ ሜትር ዎኝተን ነው የላይኛውን ወለል የምናገኘው?"
አልኩኝ ሀሳብ ይዞኝ
"ታዲያ ምን ችግር አለው...እዛ ለመድረስ ያብቃንጂ"
"ሁለችሁም ዋና ትችላላችሁ እንዴ?"
"እኔ አልችልም" አለ ጋሽ አህመድ
"አንተስ ኢንጂነር ?" ጠየቀችች ሠላም ችላለው የሚል መልስ እንድመልስ በመመኘት
"አረ እኔ በፍፅም አልችልም"
"እኔ ጋሽ አህመድን አዝዬ ዋኛለው..ሠላምና አይዳ ደግሞ ኢንጂነሩን..ግን ቅድሚያ መስማማት አለብን የአመት ደሞዛችሁን ለእኛ ትለቃላችሁ"
"የአመት ደሞዜን ለቅቄ ዲቃላዎቼን ምን ላበላልህ ነው?"
"በህይወት ስትተርፋ አይደል የምታበላቸው ተወው እንደውም በአመት ደሞዝ አያዎጣኝም..እናንተስ ያዋጣችሆል..?አለ ወደ ሴቶቹ ዞሮ
"ባክህ ቀልድን ተውና ምን እናድርግ የሚለውን ብንመካከር ነው ሚሻለው"
አንቺ ደግሞ ዛሬም ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተፋጠን ቁምነገር ብቻ እንዳወራ ትጠብቂያለሽ..እንደውም ደክሞኛል የሚበላ ነገር ስጪን ..ብሎ ባለበት ቁጭ አለ ..ጋሽ አህመድም ተከትሎት ተቀመጠ፤እኔና ሰላም ተጋግዘን እቃችን ያለበትን ጋወን ወደእነሡ አስጠጋነው
👍24