#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የጣርያው ስር ክፍል
የጠዋቱ አራት ሰዓት መጣ፣ ሄደ፡
በየቀኑ ከሚመጣልን ምግብ የሚተርፈንን በቤቱ ውስጥ ቀዝቃዛ ሆኖ ባገኘነው በልብስ ማስቀመጫ መሳቢያው ስር አስቀመጥነው፡ በሌላኛው የህንፃው ክፍል አልጋ በማንጠፍ ላይ ያሉት ሠራተኞች ቀጥሎ ደግሞ ወደ ታችኛው ክፍል
መውረዳቸው ስለማይቀር ይህንን ክፍል ለሚቀጥሉት አራት ሰዓታት
አያዩትም፡
እኛም ክፍሉ ስለሰለቸንና የተመደበችልንን የተወሰነች ቦታ በደንብ ለማየት ስለጓጓን የመንትዮቹን እጆች ይዘን ልብሶቻችንን የያዙት ሻንጣዎች ወዳሉበት የልብስ ሳጥን በፀጥታ አመራን፡ እስካሁን ልብሶቻችንን ከሻንጣ አላወጣንም ነገ ብዙ የሚያማምሩ ክፍሎች ወዳሉበት ትልቁ ቤት ስንገባ፣ ልክ ፊልሞች
ላይ እንደምናየው እኛ ለመጫወት ወደ ውጪ ስንወጣ ሠራተኞቹ ደግሞ ሻንጣዎቻችንን ከፍተው ልብሶቻችንን ያስተካክሉልናል በወሩ መጨረሻ ላይ ባለው አርብ ሠራተኞቹ ለማፅዳት ሲመጡ በእርግጠኝነት እዚህ ክፍል ውስጥ አንኖርም።
በትልቁ ወንድሜ መሪነት ወደ ጨለማው፣ ጠባቡና ዳገታማው ደረጃ አመራን የመተላለፊያው ግድግዳዎች ጠባብ ከመሆናቸው የተነሳ በትከሻዎቻችን
እየታከክናቸው ማለፍ ነበረብን፡፡
“ያውና!”
ጣራ ስር የሚሰሩ ብዙ ክፍሎች አይተን የምናውቅ ቢሆንም ይሄኛው ግን በጣም የተለየ ነው በቆምንበት ተገትረን ዙሪያውን በጥርጣሬ ተመለከትን ክፍሉ ጨለም ያለ ሲሆን ቆሻሻና አቧራማ ነው ከአቧራው የተነሳ ሩቅ ያሉት ግድግዳዎቹን ማየት የማይቻል ነበር የሆነ ሞቶ ሳይቀበር የቀረ ነገር ሳይኖር አይቀርም መሰለኝ ሽታው ንፁህ አይደለም፡ ክፍሉ በአቧራ
በመሸፈኑ ምክንያት በተለይ ጨለም ባሉት ጥጋጥጎች ላይ ያለው ሁሉም ነገር የሚንቀሳቀስ
ይመስላል።
ከመግቢያው ባሻገር አራት መስኮቶች ከጀርባው ደግሞ ሌሎች አራት መስኮቶች ሲኖሩት ጎንና ጎኑ ግን መስኮት የለበትም በደንብ ካልተጠጉ በስተቀር ምን
እንዳለ ማየት አይቻልም ተራ በተራ
ከደረጃው ላይ ወረድን፡
ወለሉ ከእንጨት የተሰራ ሲሆን ለስላሳና የበሰበሰ ነው። በፍርሀት ስሜት እየተጠነቀቅን ቀስ እያልን ስንራመድ ወለሉ ላይ ያሉት ነፍሳት በሁሉም አቅጣጫ ተርመሰመሱ ክፍሉ ብዙ ቤቶችን ሊያሳምር የሚበቃ ቁሳቁስ ተቀምጦበታል ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ነገሮች የተሸፈኑበት ነጭ ጨርቅ
አቧራው ለብሶ ግራጫ ሆኗል፡ የተሸፈኑትን ዕቃዎች ዝም ብዬ ስመለከት የሚያንሾካሹኩ ጣዕረሞቶች ስለመሰሉኝ ጀርባዬን በረደኝ፡፡
ራቅ ያለውን ግድግዳ ተደግፈው በመደዳ የቆሙ ጌጠኛ ቁምሳጥኖች አየን ጠጋ ብለን ስንመለከት እያንዳንዳቸው በጥንታዊ ልብሶች የተሞሉ ሆነው
አገኘናቸው: እኔና ክሪስቶፈር በጥርጣሬ እየተመለከትናቸው ሳለን መንትዮቹ ደግሞ እኛ ላይ ተለጥፈው በትላልቅና በፈሩ አይኖቻቸው ዙሪያውን ያጤናሉ።
“እዚህ ይሞቃል ካቲ” አለች ኬሪ
“አዎ ይሞቃል”
“እዚህ መሆን አስጠልቶኛል!”
ወደ ኮሪ ስመለከት ትንሽ ፊቱ በፍርሀት ተውጧል ዙሪያውን እየተመለከተ ጎኔ ልጥፍ ብሏል በድሮ ሰዎች ልብሶችና አለባበሶች መመሰጤን አቁሜ የእሱንና የኬሪን እጆች ግራና ቀኝ ያዝኩና ሁላችንም ይህን ቦታ እንዴት
እንደምናደርገው ማሰብ ጀመርን፡ መታየት ያለበት ነው፡ በሺዎች የሚቆጠሩ አሮጌ መፃህፍት፣ ጥቋቁር የሂሳብ ሰነዶች፣ የቢሮ ጠረጴዛዎች ሁለት ትልልቅ ፒያኖዎች ሬዲዮኖች፣ በሁሉም መጠንና ቅርፅ ያሉ የቀሚስ
አይነቶች የወፍ ጎጆ ከነመስቀያው መጥረጊያ፣ አካፋዎች፣ በፍሬም ውስጥ የተቀመጡ የሞቱ ዘመዶቻችን ፎቶግራፎች ይታያሉ። ፎቶግራፉ ላይ ያሉት
ሰዎች አንዳንዶቹ ቀላ ያሉ አንዳንዶቹ ጥቁር ፀጉር ያላቸው ሲሆኑ ሁሉም በሚባል አይነት የሚያስፈሩ፣ ጨካኝ፣ መራራ፣ ያዘኑ፣ ተስፋየለሾችና ባዶ
አይኖች ያሏቸው ናቸው እምላለሁ አንዳቸውም ደስተኛ አይኖች የሏቸውም።አንዳንዶቹ ፈገግ ብለዋል ብዙዎቹ ግን አላሉም አንድ በመጠኑ ፈገግ ያለች፣ እድሜዋ ምናልባት አስራስምንት አመት የሚሆናት ልጅ ፎቶ ቀልቤን
ሳበው ፈገግታዋ ሞናሊዛን አስታወሰኝ፡ ይቺ ግን የበለጠ ቆንጆ ናት።ጡቶቿ ተለቅ ያሉ ከመሆናቸው የተነሳ ክሪስቶፈር አንዱን ቀሚስ እያመለከተ
“የእሷ ነው!” አለ
“ቁንጅና ማለት ይሄ ነው” አለ በአድናቆት ተሞልቶ :: የተርብ የመሰለ ወገብ፣ ሞላ ያለ ዳሌ፣ ጎላ ያሉ ጡቶች: ካቲ… እንደዚህ አይነት ቅርፅ ቢኖርሽ ሀብታም ትሆኚ ነበር:"
“እውነት?” አልኩት በመሰላቸት፡ “ምንም አታውቅም ማለት ነው ይህ የሴት ተፈጥሯዊ ቅርፅ አይደለም ከውስጥ ኩርሲ ለብሳ ነው፡ ኩርሲው ወገቧን አጣብቆ ይይዛትና ከላይና ከታች ያለውን ጎላ አድርጎ እንዲታይ ያደርገዋል ''
“የሌለው ስለጨመቅሽው አይወጣም” አለ፡ ሌላ ቅርፅዋ የሚያምር ወጣት ሴት ተመለከተና “ታውቂያለሽ የሆነ ነገሯ እናታችንን ይመስላል፡ ፀጉር አሰራሯ ቢቀየርና ዘመናዊ ልብስ ብትለብስ ቁርጥ እሷን ነው የምትመስለው:"
“ይህቺ ልጅ ደስ ትላለች እናታችን ግን የበለጠ ውብ ናት” ብሎ አጠቃለለ
ይሄ ትልቅ ቦታ ፀጥታና ጭር ያለ ከመሆኑ የተነሳ የራስን የልብ ትርታ
መስማት ይቻላል ሆኖም ግን እያንዳንዱን ነገር መመርመር፣ እያንዳንዱ ሳጥን ውስጥ ያለውን መፈተሽ፣ እነዚያን ያረጁና የሚሸቱ ልብሶች መሞከርና እንደነሱ ማስመሰል ደስ የሚል ነገር ነበር ግን በጣም ይሞቃል። ያፍናል
ሳምባዬ ከሰበሰበው አቧራና ቆሻሻ አየር የተነሳ የተዘጋ መሰለኝ፡
ክሪስቶፈር መንትዮቹ ማማረር እንደጀመሩ ስለተመለከተ። “አሁን ተመልከቱ መስኮቶቹን በትንሹ እንከፍታቸዋለን፡ ከዚያ ንፁህ አየር በትንሹም ቢሆን ይገባል ማንም ሰው ከምድር ሆኖ የመስኮቶቹን መከፈት ማየት አይችልም::”
አለ፡፡ ከዚያ እጄን ለቀቀና ሳጥኖቹንና ዕቃዎቹን እየዘለለ ትቶኝ ወደ ፊት ሮጠ፡ ከዚያ የማይታይበት ቦታ ሆኖ ኑ ያገኘሁትን ተመልከቱ!” ሲል
ተጣራ ድምፁ ውስጥ መደነቅ ይሰማል።
የሆነ ደስ የሚል አስገራሚ ነገር ለማየት ሮጥን፡ ያሳየን ግን አንድ ክፍል ነው ክፍሉ ቀለም አልተቀባም ግን ኮርኒስ ነበረው፡ ፊት ለፊት ያለውን መቀመጫ ስንመለከት ክፍሉ ለአምስት ልጆች የሚሆን የመማሪያ ክፍል
ይመስላል ክፍሉ ውስጥ ከተቀመጠው ባረጁ መፃህፍት ከተሞላው መደርደሪ? በላይ ጥቁር ሰሌዳ ተሰቅሏል፡ የእኔ ሁሉንም እውቀት ፈላጊ! ወዲያውኑ የመፅሀፍቱን ርዕሶች ጮክ ብሎ ማንበብ ጀመረ፡ መፃህፍቱ ስሜቱን ከፍ
ለማድረግ በቂ ነበሩ ወደ ሌላ አለማት የማምለጫ መንገድ እንዳገኘ አወቀ:
ወደ ትንንሾቹ መቀመጫዎች ቀረብ ብዬ ስመለከት ስሞችና ቀኖች ተፅፎባቸዋል:: ለምሳሌ ጆናታን፣ ዕድሜ 11፣ 1864: አዴል፣ ዕድሜ 9፣ 1879። ይህ ቤት እንዴት አሮጌ ነው! ይህን ጊዜ መቃብራቸው ሳይቀር በአፈር ተሸፍኗል እነሱ ግን በአንድ ወቅት እነሱም ወደዚህ ተልከው እንደነበረ ሊነግሩን ስማቸውን
ትተውልናል። ግን ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያጠኑ ብለው እንዴት ወደዚህ ይልኳቸዋል? ግን አያቶቻችን እንደሚጠየፉን እንደኛ አይነት ልጆች ሳይሆኑ የሚፈለጉ ልጆች ይመስሉኛል፡ ምናልባት ለእነሱ ጊዜ መስኮቶቹ በደንብ
ተከፍተው ይሆናል ወይም ሰራተኞቹ ጥጉ ላይ ባሉት ምድጃዎች ላይ ከሰልና
እንጨት ያነዱላቸው ይሆናል።

👍35🥰5👏1
የሆነ ሰው ሆድ በረሀብ እስኪጮህ ድረስ በግማሽ ልባችን ያንንም ያንንም ስናይ ቆየን፡ ሰዓቴን ተመለከትኩ ስምንት ሰዓት ታላቅ ወንድሜ አተኩሮ
አየኝ፡ እኔ ደግሞ መንትዮቹን እያየሁ ነበር። የእነሱ ሆድ መሆን አለበት። ትንሽ ነው የበሉት የምግብ ፕሮግራማቸው በአንድ ሰዓት ቁርስ፣ በስድስት ሰዓት ምሳና በአስራአንድ ሰዓት እራት እንዲሁም በአንድ ሰዓት መኝታና
ከዚያ በፊት ግን ትንሽ ምግብ መብላት ነው።
“ምሳ ሰዓት” ስል በደስታ ተናገርኩ።
በደረጃ ልንወርድና እዚያ አስቀያሚ ጨለማ ክፍል ልንመለስ ነው
“መጋረጃዎቹን ከፍተን ትንሽ የፀሀይ ብርሃን ቢገባ እንኳን
አልጎመጎምኩ።
ጮክ ብዬ ተናግሬያለሁ መሰለኝ ክሪስቶፈር መጋረጃዎቹ ቢከፈቱ እንኳን ክፍሉ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ስለሆነ የፀሀይ ብርሀን እንደማይገባ ነገረኝ፡
ድሮ ስንማር ሳንተጣጠብ ማዕድ ላይ መቀመጥ ትክክል እንዳልሆነ ተነግሮናል።እናም እግዚአብሔር ህጉን እንደምንታዘዝና እንደምናስደስተው የሚያይ አይን
ስላለው፣ በእሱ አይን ኮሪና ኬሪ ከአንድ ማህፀን የወጡ በመሆናቸው አንድ ገንዳ ላይ ገላቸውን ብናጥባቸው አይናደድብንም፤ ይናደድብናል?
ክሪስቶፈር ኮሪን ሲይዝ እኔ ደግሞ ኬሪን አጥቤና አልብሼ ሀር የመሰለውን ፀጉሯን እስኪያንፀባርቅ ድረስ በማበጠር በጣቶቼ ጠቅልዬ ሪቫን አሰርኩላት። እኔ ስታጠብ ክሪስቶፈር ቢያዋራኝ ገና ልጆች ስለሆንን ማንንም አይጎዳም ብዬ
አሰብኩ። ይህ ማለት አንድ ላይ መታጠቢያ ቤት መጠቀም ማለት አይደለም።አባዬና እማዬ እያሉ ራቁት መሆን ምንም ስህተት አልነበረም የአያትየው
አስፈሪና ንቅንቅ የማይል ፊት በአይኔ ላይ ውል ሲልብኝ ግን ፊቴን ብቻ ታጠብኩ አያትየው ብታይ ስህተት ነው ብላ ልታስብ ትችላለች።
“ሁለተኛ እንደዚህ አናደርግም!” አልኩት ለክሪስቶፈር፡ “ያቺ አያት ተብዬ ልትይዘንና ክፉ ነገር ነው ብላ ልታስብ ትችላለች" ምንም እንዳልሆነ አይነት ጭንቅላቱን ነቀነቀ የሆነ ነገር ከፊቴ ላይ አንብቦ መሆን አለበት። ወደ እኔ
መጣና አቀፈኝ። የማለቅስበት ትከሻ እንደምፈልግ እንዴት አወቀ?
ካቲ…” አለኝ ጭንቅላቴን ትከሻው ላይ አስደግፌ ማልቀስ ስጀምር፡ “ስለወደፊቱ አስቢ ሀብታም ስንሆን ሁሉም የእኛ ይሆናል። ሁልጊዜም በጣም ሀብታም
መሆን እፈልጋለሁ ለተወሰነ ጊዜ ዘና የምል ወጣት ሀብታም እሆናለሁ።ከዚያ አባዬ እንደሚለው ሁሉም ሰው ለሰው ልጅ ትርጉም ያለው አንድ
ጠቃሚ አስተዋፅኦ ማድረግ ስላለበት ያንን ማድረግ እፈልጋለሁ። ይህንን የማደርገው ኮሌጅና የህክምና ትምህርት ቤት እስክገባ ድረስ ትንሽ መዝናናት
ስላለብኝ ነው:
“መዝናናት ስትል አንድ ድሀ ሰው ሊያደርገው አቅሙ የማይፈቅድለትን ነገር ማለትህ መሆኑ ገብቶኛል፡ የምትፈልገው ያንን ከሆነ አሪፍ ነው እኔ ግን የምፈልገው ፈረስ እንዲኖረኝ ነው: ህይወቴን ሙሉ ፈረስ እንዲኖረኝ
እጓጓለሁ: እስከዛሬ የምኖረው ፈረስ እንዲኖረኝ የሚፈቀድበት ቦታ አልነበረም: አሁን ግን ስላደግኩኝ ፈረስ ይኖረኛል። በእርግጥ በዓለም አንደኛ ዳንሰኛ ሆኜ በግሌ ለራሴ ዝናና ሀብት እንዲኖረኝ እሰራለሁ። ዳንሰኞቹ እንዴት
እንደሚበሉ ታውቃለህ በጣም መብላት አለባቸው አለበለዚያ ቆዳና አጥንት ነው የሚሆኑት። ስለዚህ በየቀኑ መዓት አይስክሬም እበላለሁ። አንዳንድ ቀን ደግሞ ከቺዝ በስተቀር ምንም አልበላም ሁሉንም የቺዝ አይነት እበላለሁ
ከዚያ ብዙ፣ በጣም ብዙ አዳዲስ ልብሶች ይኖሩኛል። በዓመቱ ውስጥ በየቀኑ የተለያየ ልብስ መልበስ እፈልጋለሁ: ልብሶቼን አንድ ጊዜ ከለበስኳቸው
በኋላ ለሌላ ሰው እሰጣቸዋለሁ ከዚያ ቁጭ ብዬ ቺዝ፣ በቺዙ ላይ ደግሞ አይስክሬም እበላለሁ። እና ውፍረቴን ደግሞ በዳንስ አጠፋዋለሁ"
ርጥብ ጀርባዬን እያሻሸኝ ነው: ላየው ስዞር በሀሳብ ጭልጥ ብሏል።
“አየሽ ካቲ… ለአጭር ጊዜ እዚህ ውስጥ መዘጋታችን መጥፎ አይደለም ገንዘባችንን በምን እንደምናጠፋ በማሰብ ስራ ስለሚበዛብን ድብርት ውስጥ
ለመግባት ሰዓት አይኖረንም: ሁልጊዜ ቼዝ መጫወት መማር እፈልግ ነበር::አሁን ጊዜ ስላለን እማዬ የቼዝ መጫወቻ እንድታመጣልን እንነግራታለን::
ማንበብም እንችላለን፡፡ ማንበብ ልክ እንደመስራት ጥሩ ነው፡ እናታችን እንዲሰለቸን ስለማትፈልግ አዳዲስ መጫወቻዎችና የምንሰራው ነገር
ታመጣልናለች። ይሄ ሳምንት ወዲያው ያልፋል” አለና በደስታ ፈገግ አለ: “እና እባክሽ ክሪስቶፈር ብለሽ መጣራትሽን አቁሚ! ከአባቴ ጋር በተመሳሳይ
ስም መጠራት አልችልም: ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ክሪስ ብቻ ነኝ እሺ?"
“እሺ ክሪስ” አልኩት “ግን አያትየው መታጠቢያ ቤት አብረን ብትይዘን ምን የምታደርግ ይመስልሀል?”
“ሲኦል ውስጥ ትከተናለች ከዚያ ምን እንደሚሆን እግዚአብሔር ያውቃል "
ከመታጠቢያው ወጥቼ ሰውነቴን ሳደራርቅ ወደ እኔ እንዳያይ ልነግረው አሰብኩ፧ እሱ ግን እየተመለከተ አልነበረም:: ማስታወስ እስከምችለው ድረስ
ብዙ ጊዜ እርቃናችንን ተያይተን ስለምናውቅ የእያንዳንዳችንን ሰውነት ምን እንደሚመስል እንተዋወቃለን፡ እና በእኔ አመለካከት የእኔ ሰውነት በጣም
ምርጥ ነው- ፅድት ያለ፡
ሁላችንም ንፁህ ለብሰንና ጥሩ ጥሩ እየሸተትን ምሳችንን ለመብላት ተቀመጥን ክሪስ የእጅ ሰዓቱን አየት አደረገ፡ መንትዮቹ ምሳ ካለቀ በኋላ እረፍት የለሽ
ሆነው ዙሪያውን እያንዣበቡ ነው አለመደሰታቸውን ለማሳየት በአካባቢው ያለውን ሁሉንም ነገር በእርግጫ ይመቱ ጀመር፡ ክፍሉ ውስጥ እየተንጎራደዱ እኔና ክሪስን ግንባራቸውን ቋጥረው ተመለከቱን፡ ክሪስ መፅሀፍ ሊያነብ ጣሪያው ስር ወዳለው ክፍል ሲሄድ ተከተልኩት
“አይሆንም” ኬሪ ጮኸች: “ወደዛ ቦታ መሄድ አልፈልግም! ያ ቦታ ደስ አይለንም! ይህንንም ቦታ አልወደውም! ምኑንም አልወደድኩትም! አንቺም
እናቴ እንድትሆኚ አልፈልግም:: ካቲ እውነተኛዋ እናቴ የት ነች? የት ሄዳ ነው? ተመልሳ እንድትመጣና ከዚህ የአሸዋ ሳጥን ውስጥ እንድታወጣን ንገሪያት!” አለች ከዚያ ወደ በሩ ሄዳ የበሩን እጄታ ይዛ ለመክፈት ሞከረች በሩ አልከፈት ሲላት ልክ እንደቆሰለ እንስሳ ጮኸች: እንደ አውሬ አድርጓት ትንንሽ እጆቿን ጨብጣ እናታችን መጥታ ከዚህ ጨለማ ክፍል እንድታወጣት እየጮኸች ጠንካራውን እንጨት በር መቀጥቀጥ ጀመረች።
ሮጬ ሳቅፋት እየተራገጠች መጮኋን ቀጠለች: ልክ አውሬ ድመት እንደመያዝ ነበር ክሪስ መንትያውን ለመከላከል እየሮጠ የነበረውን ኮሪን ለቀም አደረገው: ማድረግ የቻልነው ሁለቱንም በአንዱ ትልቅ አልጋ ላይ
ማስቀመጥ፣ የተረት መፃህፍቶቻቸውን ማሳየትና እንዲተኙ ማግባባት ነበር
እምባቸው በአይናቸው እንደሞላ በሀዘን እየተመለከቱን ነበር።
“መሽቷል?” አለች ኬሪ ከብዙ ፍሬ አልባ የነፃነት ፍለጋ ጩኸትና የማትመጣ እናት ከመጠበቅ በኋላ፡ “እናቴን በጣም ፈልጌያታለሁ ለምንድነው
የማትመጣው?”
“እባካችሁ ክሪስ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ሄዶ መፅሀፍ ያንብብ፡ እሱ ያንን ሲያደርግ እኔ ደግሞ ለእናንተ ፒተር ጥንቸሉን አነብላችኋለሁ። እስቲ
ፒተር ዛሬ ማታ ገበሬው እርሻ ውስጥ ገብቶ ካሮትና ጎመን ሰርቆ እስኪጠግብ ይበላ እንደሆነ እናያለን፡ እኔ እያነበብኩ ሳለ እንቅልፍ ከወሰዳችሁ የታሪኩን

👍26
መጨረሻ በህልማችሁ ታዩታላችሁ ሁለቱም እንቅልፍ ሲወስዳቸው አምስት ደቂቃ አልፈጀም ኮሪ ፒተር ጥንቸሉን በተቻለ መጠን በቀላሉ ወደ ህልሙ ለመውሰድ መፅሀፉን ትንሽዬ ደረቱ ላይ ልጥፍ አድርጎለታል የሆነ ሞቃት ስሜት ተሰማኝ፡ የአስራ ሁለት አመት ልጅ ሳይሆን ትልቅ እናት ለሚያስፈልጋቸው ትንንሾቹ ልጆች ልቤ ታመመ: እዚህ ቦታ ለረጅም ጊዜ ስለማይዘጋብን እግዚአብሔር ይመስገን ቢታመሙ ምን አደርጋለሁ? አደጋ ቢያጋጥም… መውደቅ ወይም መሰበር
ቢኖርና ከተቆለፈው በር ጋ በኃይል ብጋጭ ጨካኟ አያታችን ሮጣ ትመጣልኝ ይሆን? ክፍሉ ውስጥ ስልክ እንኳን የለ እዚህ የተረሳ የህንፃ ክፍል ውስጥ
ሆኜ ለእርዳታ ብጮህ ማን ይሰማኛል?
ተቀምጬ ሳወጣና ሳወርድ ክሪስ ጣሪያው ስር ካለው የልጆች መማሪያ ክፍል ውስጥ ካሉት አቧራ ከለበሱት አሮጌ መፃህፍት መካከል መኝታችን ላይ
ሆነን የምናነባቸው ጥቂት መፃህፍት መርጦ አመጣ ሌላም መጫወቻ ይዞ መጥቷል።
“ያዢ” አለ አንድ አሮጌ መፅሀፍ እጄ ላይ እያስቀመጠ የሚያስደነግጠኝ ምንም
አይነት ነፍሳት እንዳይኖርበት አድርጎ እንዳራገፈው ነገረኝና “ጨዋታውን ልጆቹ ሲነሱ እንጫወታለን፡” አለኝ፡፡
ወንበር ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠና እግሩን ወፍራሙና ክብ የሆነው የወንበሩ መደገፊያ ላይ አድርጎ የሚያነበው መፅሀፍ ከፈተ፡ እኔም ብቸኛው ባዶ አልጋ ላይ ጋደም ብዬ ስለ ንጉስ አርተር ማንበብ ጀመርኩ። አመናችሁም
አላመናችሁ ከዚህ በፊት መኖሩን የማላውቀው በር ተከፈተልኝ፡....
✨ይቀጥላል ✨

❤25👍25
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
...አነሱ በዚህ ጉይ ምን ማድረግ እንዳለባቸ ሲመካከሩ ፡ ሳቤላ በኀዘንና በሐሳብ ተውጣ ሰማይ ተደፍቶባት ተቀምጣለች ሎርድ ማውንት እስቨርን ከእርሱና ከሚስቱ ጋር አብራ መኖር እንዳለባት ነግሯታል ላፏ ብታመሰግነውም እሱ
ሲወጣ ዕንባዋ ዐይኗ እስኪፈርጥ ይወርድ ጀመር " « ከሚስዝ ቬን ጋር ከመኖር ለምን ለአንዱ ግርድና ተቀጥሬ ፍርፋሪ በልቸ ውሃ ጠጥቸ አልኖርም ከሏ ጋር ከመኖር መሞት ይሻላል » ይህ የወጣት ሴቶች ጠባይ ነው " የማይሆነው ሐሳብ ሁሉ ሲመጣላቸው የሚሆን ይመስላቸዋል " በተለይ ሳቤላ ደግሞ ታበዛዋለች " ከሰው ቤት ገብቶ እየሠሩ መኖር ሲያስቡት ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሐሳብና ተግባር የጨለማና የብርሃን ያህል የሚፈራራቁበት ጊዜ አለ " ደግነቱ አማራጭ አግኝታለች " ሎርድ ማውንት እስቨረን የሰጣትን ጥግኝነት ተቀብላ ከሚስ ሼን ጋር መኖር ነበረባት " እንዲያውም እሱስ ወዲያው አሳፍሮ ወደ ካስል ማርሊንግ ሊልካት ነበር » እሷ አይሆንም አለችና ከቀብሩ በኋላ እንድትሔድ ተወሰነ" ለጊዜው ስታስበው አንግፈግፋት - ነገር ግን የብሶቷን ያህል ብዙ ብትናገርም ከዛያ የተሻለ ዕድል እንዶሌላት ተንዝባ ለመሔድ ተስማማች "
ሚስተር ዋርበርተን ኧርሎ በሰጠው ሥልጣን እነዚያን ሬሳ አጋቾች ከዚያ ክፍል አስወጥቶ ቀብር እስኪፈጸም ድረስ ከአንድ ክፍል ዘግቶ አስጠበቃቸው .
ለዚህም ከአንዳንዶቹ ይሰማ የነበረው ምክንያት ወዲያው ነጻ ከተለቀቁ አሁንም ሌላ አፈና ያደርጉ ይሆናል የሚል ነበር።
ቀብሩ ዌስት ሊን በሚገኘው በቅዱስ ይሁዳ ቤተ ክርስቲያን ዐርብ ጠዋት ተፈጸመ ። ሳቤላ ማውንት እስቨርን ሔዶ መቀበር ነበረበት ብላ እንደገና ትክን ብላ አዘነች " ኧርሎ ግን እሷ እየሰማች አይዴለም እንጂ ለቀብሩ ሥርዓት የማያስፈልግ ወጭ መጨመር አያስፈልግም ብሎ ተናግሮ ነው የተወው » ቢሆንም ከሱ የሚፈለገውን ሁሉ በሚገባ ፈጽሞአል ።
የባለሱቆችን የዱቤ ዕዳ የአሽከሮቹን የአንድ ወር ደሞዝና እንደዚሁም በድንገት ስለ ተሰናበቱ በተጨማሪ የአንድ ወር ደሞዝ በቀለብና በመጠለያ ሒሳብ ስም ጨምሮ ከፈላቸው የቤት አዛዥ የነበረውን ፖውንድን እሱ ዘንድ አስቀረው "ለሳቤላም ከክብሯና ከደረጃዋ ጋር የሚመጣጠን ማንኛውንም ለኀዘን የሚያስፈልጋትን ልብስ ሁሉ እንዲኖራት አደረገ ። እገዳ ተደርጐባቸው የነበሩት ሠረላዎችና ፈረሶች በጥሩ ሁኔታ ስለነበሩ ዋጋቸውን ከፍሎ አስቀራቸው
አስክሬኑን የተከተሉት ዋና ኀዘንተኞች ሁለት ብቻ ነበሩ ። አዲሱ ኧርልሬይ ሞንድቬንና ሚስተር ካርላይል " ሁለተኛው በቅርብ ቀን የተገኘ ወዳጅ እንጂ ዘመድ ባይሆንም ምናልባት ኧርሎ የኀዘን ልብስ ለብሶ ብቻውን መታየቱን ስላልወደዶ
ሳይሆን አይቀርም እንዲያቋቁመው ጠይቆት ነበር» አስክሬኑን አንዳንድ የገጠር
መኳንንት ተሸከሙት ! ብዙ የግል ሰረገላዎችም አጀቡት።
በበነጋው ጧት ሁሉም ሽር ጉድ ይል ጀመር ኧርሉ ሊሔድ ተነሣ ሳቤላም ለመሔድ ተዘጋጀች " ግን መንገዳቸው ለየብቻ ነበር " አሽከሮቹም የሚበተኑበት
ቀን ነበር » ኧርሉ ወደ ሎንደን ለመሒድ ባቡር ጣቢያ ድረስ የሚወስዶው ሠረገላ ከበሩ ሲጠብቀው ሚስተር ካርላይል ደረሰ "
« አንተ ሳትመጣ መሔዴ ነው ብዬ ሠግቼ ነበር አሁንም ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ጊዜ የለኝም ። ስለመቃብሩ ድንጋይ ግን በደንብ ገብቶሃል ? »
« አዎን በደንብ » አለ ሚስተር ካርላይል " « ሳቤላ እንደ ምን ናት? »
« ምን የሷ ነገር በጣም ያሳዝናል " ሰማዩ ተደፍቶባታል " ቁርስም አብራኝ አልበላችም ሜዞን እንደምትነግረኝ ኀዘኑ በጣም ጠንቶባታል " ምስኪን ልጅ
ክፉ ሰው ነበር አባቷ ! » አለ ንድድ ብሎ ደወሉን እየደወለ " በደውሉ ጥሪ የመጣውን አሽከር ሳቤላን እንዲጠራት ላከው "
« እሷ እስክትመጣ ድረስ ሚስተር ካርላይል ምስጋናዬን እንዳቀርብልህ ፍቀድልኝ " አንተን ባላገኝ ኖሮ ምኑን ከምኑ አደርገው እንዶነበር አላቅም መጥተ
እንደምታየኝ ነግረኸኛል ስለዚህ በቅርቡ እጠብቅሃለሁ » »
« አዎን ምናልባት እርስዎ ወዳሉበት አካባቢ የሚያስመጣ ጉዳይ ያጋጠመኝ እንደሆነ ነው ቃል የገባሁት »
ሳቤላም ለመነሣት ተዘጋጅታ ነበርና ለባብሳ መጣች " ፊቷን በኀዘን ዐይነ ርግብ ሸፍናው ስለ ነበር ' ስትቀርብ መሸፈኛዋን ወደኋላ ገለጠች።
« ሰዓት ደረሰብኝ ሳቤላ ... መሔዴ ነው የምትነግሪኝ ነገር አለሽ ? »
ለመናገር ከንፌሯን ስትከፍት ወደ ሚስተር ካርይል አየችና አመነታች
ጀርባውን ወደነሱ አድርጎ ከመስኮቱ አጠገብ ቁሞ ነበር
«የምትናሪው ያለሽ አይመስለኝም» አለ ለመውጣት የቸኮለው ኧርል «በይ የኔ ልጅ ከመንግድ ምንም ችግር አይገጥምሽም » ለማንኛወም ነገር ፖንድ ይረዳሻል ብቻ ከራት ሰዓት በፊት ካስል ማርሊዓግ መድረስ ስለማትችይ ከመንገድ መብላት አለብሽ " ለሚስዝ ቬን አሁን ጊዜ ስላጣሁ ከለንደን እንደምፅፍላት ንገርያት።»
ሳቤላ ግን አንድ ነገር ለመናር እንምትፌልግ ሁሉ እየተጠራጠረች ከፊቱ ቆሠች።
« ምንድነው ሳቤላ ? ልትነግሪኝ የፈለግሺው ነገር አለሽ ? »
በርግጥ አንድ ነግር ለመናገር ፈልጋ ነበር ግን እንዴት አድርጋ እንደምትነግረው ግራ ገባት በጣም ተጨነቀች " ሁኔታወን ያባሰው የሚስተር ካርላይል
መኖር ነበር " እሱ ደግሞ ይህን አላወቀም ።
« እኔ እንኳን ልጠይቅህ አልፌለግሁም ነበር ግን በእጄ ምንም ገንዘብ የለኝም » አለችው።
« እልም አድርጌ ረሳሁትኮ ... ሳቤላ " በይ እኔም ከመንገድ ከሚያስፈልገኝ የሚተርፍ የለኝም» ለጊዜው ሦስት ፓውንድ ይበቃሻል ለመንገድ የሚያስፈልገውን ወጭ የሚሸፍን ገንዘብ ለፖውንድ ስጥቸዋለሁ ካስል ማርሊንግ ከደረስሽ በኋላ ግን ወይዘሮ ማውንት እስቨርን የሚያስፈልግሽን ሁሎ ትሰጥሻለች ግን መናገር አለብሽ : አለበለዚያ እሷ አታውቅም » አላትና ከሚስተር ካርላይ ጋር እስከ ሠረላው ድረስ ሽኝቷት ተሰነባበቱ » ከዚያ ሳቤላ ወደ ነበረችበት ክፍል ተመለሰች።
«እባክህን አንድ ነገር ላስቸግርህ ... ሚስተር ካርላይል»
« የምችለውን ሁሉ አደርግልሻለሁ»
« በል እንግዲያው » አለችና አንድ ፓውንድ ተኩል አውጥታ « አንዱ ፓውንድ የቲኬቶቹ ዋጋ የቀረውን ፒያኖውን ለቃኘበት ለሚስተር ኬን ስጥልኝ " አንዱ አሽከር እንዳልሰጠው ለመሔድ ሲጣደፍ እንዳይረሳብኝ ፌርቸ ነው » አለችው
« ታዲያኮ ኬን አንድ ፒያኖ ለመቃኘት የሚጠይቀው አምስት ሽልንግ ነው አላት ሚስተር ካርላይል
« ብዙ ሰዓት ነው የፈጀበት » ቆዳውንም ጠጋግኖታል አይበዛበትም የበላውን እንኳን አላዘዝኩለትም ከኔ የባሰ ችግረኛ ነው የሱ ነገር ሆኖብኝ ነው
እንጂ ሎርድ ማውንት እስቨርንን ደፍሬ ገንዘብ አልለምነውም ነበር እሱን ፈርቼ ባልጠይቀው ኖሮ ገንዘብ ሳገኝ የምሰጥህ አንተ እንድትከፍልልኝ አደርግ ነበር ' '
ሳቤላና ካርላይል ፡ ስለዚህ ጉዳይ ሲነጋገሩ ሳቤላ ወደ ኢስት ሊን በገባችበ ክብር እንድትወጣ በማሰብ ይመስል ነበር ሎርድ ማውንት እስቨርን በአራት
ፈረሶች ይሳብ የነበረውን ያባቷን ሠረገላ ባቡር ጣቢያ ድረስ እንዲወስዳት ላከላት
ሠረገላው ተጫነ " ማርቭል በስተውጭ ተቀመጠች።
« እንግዲህ ሁሉ ነገር ተዘጋጀ » አለችው ሳቤላ የመሔጃዬ ሰዓት ደረሰ ሚስተር ካርይል ከጥቂት ሳምንቶች በፊት የገዛኹዋቸውን እነዚያን ወርቅማና ብርማ ዓሣዎቼን ላንተ ልተውልህ ነው ።
« ለምን ይዘሻቸው አትሔጅም ? »
« ለሚስዝ ቬን ይዣቸው ልሔድ አንተ ዘንድ ብተዋቸው ይሻለኛል አንዳንድ ጊዜ ፍርፋሪ ጣልላቸው»

👍16
ፊቷ በእንባ ታጠበ የያዛትን የሆድ ብሶት ሲቃ ለመሸፈን ቶሎ ቶሎ ስትናገር ካርላይል ገባውና «እስቲ ለጥቂት ደቂቃ አረፍ በይ » አላት።
«የለም የለም ብሔድ ይሻለኛል " »
እጅዋን ያዛትና ወደ ሠረገላው አመሩ አሽከሮቹ ሁሉ ከመተላለፊያው ቁመው
ይጠብቁት ነበር አንዳንዶቹ አባቷ ቤት ሲያለግሉ የሸበቱ ነበሩ» እጂዋን ዘረጋች።የምስጋናና የስንብት ቃል ለመናገር ፈልጋ ነበር ነገር ግን መንቅሰቋን ለመግታት ስትጣጣር 'እንባዋ እንደሚያንቃት አወቀችና በርኀራኄ ከተመለከተቻቸው በኋላ
እጆቿን ብቻ በናፍቆት አወዛወዘች ከሚስተር ካርላይል ጋር ዐለፈች " ፖውንድ ሠረገላውን ሊያስነሣ ሲል ሚስተር ካርላይል እንደገና በሩን አስከፍቶ እጂዋን ያዛት"
«ለደግነትህ አንድ እንኳን የምስጋና ቃል አልተነፈስኩም "
ካርላይል » አለችው ትንፋሿ እየተናነቃት « አልሆንልኝ ብሎ መሆኑን እንዳወቅህ ግን እርግጠኛ ነኝ »
« ከዚህ የበለጠ ባደርግልሽ በወደድኩ " ከዚህ አሁን ከወደቀብሽ ፈተና ከገጠመሽ መከራ : ጋሻና ከለላ ሁኘ ባድንሽ እወድ ነበር " እንግዲህ ፈጽመን ላንገናኝ ነው ? » አላት ሚስተር ካርላይል ።
« እንዴ እንገናኛለን እንጂ ለሎርድ ማውንት እስቨርንኮ ቃል ገብተሃል»
« እውነት ነው ፡ ድንገት እንግናኝ ይሆናል " ነገር ግን የዕለት ኑሯችን መንገዳችን የተለያዩና የተራራቁ ናቸው " ደሀና ሁኚ ሳቤላ ! »
ሠረገላ ነጅዎች ፈረሶቹን ቀስቀሱና ሠረገላው ገሠገሠ ። ሳቤላ መጋረጃውን ዘግታ ለቃው ለምትሔደው ቤቷና ለሞተው አባቷ እንባዋን እንደ ውሃ ታወርደው ጀመር » እየቆየች የሸበረው ልቧ እየረጋ እንባዋ እየደረቀ መጡና ዐይኖቿ ደኅና
አድርገው ማየት ሲጀምሩ አንዲት የተጣጠፈች ቁራጭ ወረቀት ከጭኗ ላይ አየች"ከእጅዋ የወደቀ መሰላትና እንደ ተራ ነገር ዝም ብላ አንሥታ ስትገልጠው የአንድ
መቶ ፓውንድ ኖት ተጠቅሎ አገኘች።
ሳቤላ አይኖችዋን አፍጣ መልሳ መልሳ ተመለከተችው " ከዚህ ምን አመጣው? ከየት ሊመጣ ይችላል ? ኋላ ቆይታ የማያጠራጥር ትክክለኛ ነገር ትውስ አላት " ሚስተር ካርላይል ጥሎላት እንዴሔደ ገባት
ጉንጮቿ እንደ እሳት ነደዱ " ጣቶቿ ተንቀጠቀጡ እሳት ሆና ተቆጣች "
ልክ ከምን እንዶ መጣ ትውስ ሲላት ክብሯ እንደ ተዋረደ ቆጠረችው እንዴት አንድ ተራ ሰው የገንዘብ እርዳታ ይሰጣታል ? ነገሩ አልቆየም " ባለፉት ጥቂት
ቀኖች የሰነበተችበትን ሁኔታ ስታስበው ቁጣዋ ወደ ምስጋና ተለወጠ " የራሴ የምትለው ቤት እንዶሌላትና እንደዚሁ በምጽዋት ከምታገኘው በቀር ፍጹም ቤሳ
አልባ መሆኗን አስታውሶ ባደረገላት አስገራሚ ችሮታ በጣም አደነቀች » ነገር ግን አሁን ገንዘቡን ልትጠቀምበት ስለማትችል ልትመልስለት ወሰነች ሆኖም ቸኩላ በፖስታ የላከችለት እንደሆነ ይቀየማል ብላ ሠጋችና በሌላ ጊዜ ራሷ አስረድታ
ብትሰጠው እንደሚሻል አሰበች"
ባርባራ ሔር ወይዘሮ ሳቤላ የምትነሣበትን ሰዓት አስቀድማ ስምታ ስለነበር ያቺን የሐሳብ ጣውንቷን ስታልፍ ለማየት ከቤታቸው በር ከዐጽዱ ዛፎች ዘንድ ተገን ተደግፋ ስትጠብቅ ሰረገላው ደረሰ መገረጃዎቹ ተዘግተው ስለነበር ፈረሶቹን
ሠረገለውንና ከውጭ የቀመጡ አጃቢዎችን እንጂ ሳቤላን ሳታያት ዐልፎ ሔደ » ከዚያ ቁማ ከቆየች በኋላ አባቷ ከወደ ዌስት ሊን መጣ
« ሚስተር ካርይልን አየሺው ... ባርባራ ? »
« አላየሁትም.. አባባ ! »
« ወደ ቢሮ ብሑድ ወደ ኢስት ሊን ሳይሔድ እንደማይቀር ነገሩኝ" ብልችል እንዳገኘው እፈልጋለሁ » አለ ዳኛው ሔር "
ሚስተር ሔር ክርኑን ከበሩ መዝጊያ አስደግፎ እሱ ከውጭ ባርባራ ከውስጥ ቆሙ ሁለቱም ለየግል ጉዳያቸው ሚስተር ካርላይልን ይጠብቁ ነበር ።
« ሰምኑን ስለሚወራው ወሬ ምን ይሰማሻል »አላት ድንግት ሳታስበው
« በየቦታው ሌላ ወሬ የለም " ሚስተር ካርላይል... »
ዳኛው ሔር የጀመረውን ዐረፍt ነገር ሳይጮርስ የኢስት ሊንን መንገድ ደህና አድርጐ ለማየት ወደ መንገዱ አንድ ርምጃ ፈንጠር ብሎ መመልከት ጀመረ በዚህ
ጊዜ የባርባራ ልብ ተሰቀለ ፊቷ ወዲያው ፍም መሰለ።
« ሚስተር ካርላይል ምን አደሪግ ተባለ አባባ ? » አለችው ወዶ ነበረበት መልሶ ሲቆም
« ያውና መጣ ረጃጅም ቅልጥሞቹ የሱ ይመስላሎ ሚስተር ካርላይል ኢስት ሊንን ገዝቷል እየተባለ ነው »
« ኧረ አባባ !... እውነት ሊሆን ይችላል ? ሚስቴር ካርላይል ኢስት ሊንን ገዛ ! »
« ሊሆንም ላይሆንም ይችላል " ዲልን አግኝቼ ብጠይቀው ነውም አይምም ሳይል ነገሩን አድበሰበሰው እሱ መቸም ይኸው ነው ዱሮውንም አይናገርም.. እንዴት አደርክ ! » አለ ጻኛው ሔር' ካርላይል ከነሱ ሲጢጋ "
ከዚያ ስለ አንድ የፍርድ ቤት ጉዳይ ትንሽ ተነጋግሩና «እንግዲያው ደኅና ነው » ካለው በኋላ መልሶ፡ «ካርላይል... ሰዎች ኢስት ሊንን ገዝተኸዋል ይላሉ“
« ይላሉ ? በጣምም አልተሳሳቱም ኢስት ሊን የኔ ሆኗል" »
መቸም እናንተ ጠበቆች ለራሳችሁ ጉዳይ ከቆማችሁ ከመ ቅጽበት ነው ከፍ የምታደርሱት ኧርሎ ከሞተ ሳምንት እንኳን አልሞላውም ፡ ኢስት ሊን ግን
በስምህ ተዛውሮ አልቆታል " »
« እንደሱ እይደለም ... ዳኛው ሔር " ኢስት ሊንን የተረከብኩት ኧርሎ
ከመሞቱ ብዙ ወርች ቀዴም ብሎ ነው … »
« እንዴ እንግዲያውማ ገብቶ ሲሰነብትበት ብዙ ኪራይ ተቀብለኸዋላ?»
« ኪራይ የሚባል ነር የለም ለጊዜው የክብር እንግዳ ሆነሙ ነበር የሰነበቱት
«በዚህስ በጣም ተሞኝተሃል » አለው ዳኛው ሔር "« ይቅርታ አድርግልኝ . ካርላይል መቸም አንተ ገና ልጅ ነህ» እኔ እንግዲህ ሸምግያለሁ " ኧርሎ ደግሞ እንደዚይ ሆኖ በዕዳ መነከሩ እርባና ቢስ ሰው ነበር »
« በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው » አለች ባርባራ ሔር " « ወይዘሮ ሳቤ ለቀብር ማስፈጸሚያ እንኳን ምናምን አንዳልነበራት ሰማሁ" የስሚዝ ቤተሰቦች ለሔር
በርት ቤተሰቦች ነግረዋቸው ኖሮ እኔ ከነሱ ሰማሁ ነግሩ እውነት ይመስልሃል...አርኪባልድ ? »
« ነገሩ እንኳን ትንሽ ተጋንኗል » አለ ሚስር ካርላይል "
« እንዴ ! ምን ማለት ነው » አለ ጆስቲስ ሔር « ሠረገላው በአራት ፈረሶች እየተሳበ እሷ በውስጥ ደንገጡሯና ነጂው ከውጭ ተቀምጠው ሲያልፍ አይቸዋለሁ
በዚያ ዐይነት ሁኔታ የምትጓዝ ሴትዮ ንዝብ ልታጣ አትችልም »
« ሰዎችኮ ወሬ ማናፈስ አለባቸው ጌታዬ የሰውን ነገር ያውቁት የለ " የኔ ኢስት ሊንን መግዛት ጀንበሯ ሳትጠልቅ ዌስት ሊንንም እንደ ገዛሁት ተደርጎ ሊወራ ይችላል በሉ ደኅና ዋሉ ደኅና ዋይ ባርባራ»
አዲሱ ሎርድ ማውንት እስቨርን ለንደን ደርሶ ሁልጊዜ ከሚያርፍበት ሆቴል ሲገባ ከቤቷ ካሰል ማርሊንግ ናት ብሎ ያሰባትን ሚስቱን አገኛት ምክንያቱን
ጠየቃት » እሷም በነገሩ ምንም ሳትዶነግጥ የሀዘን ልብስ ልትለካና ልጃቸው ዊልያም ትንሽ ስለከበደው አየር እንዲለውጥ ብላ ይዛው መምጣቷን ነገረችው
« ወደ ከተማ በመምጣትሽ አዝናለሁ ኤማ አላት ምክንያቷን ካዳመጠ በኋላ « ሳቤላ ዛሬ ወደ ካሰል ማርሊንግ ሐዶች »
« ምን ልታደርግ ነው ወደዚያ የሔዶች ?» አለችው አንገቷን ቶሎ ቀና አድርጋ "
« ነግሩ በጣም አስፈሪ ነው » አላት ወዶ ጥያቄዋ ቀጥታ መግባቱን ተወና ።
«ሎርድ ማውንት እስቨርን ገንዘብ አጥቶ ተዋሮዶ ሞተ » ለሳቤላ አንዲት ሽልንግ እንኳን አልተወላትም " ዛሬ እንኳን ለመንገድ አንድ ሁለት ፓውንድ የሰጠኋት እኔ ነኝ »
ኤማ ዐይኖችዋን አፈጠጠች » የት ልትቀመጥ ነው ? አሁን እንዴት ልፈትሆናለች ? »
«ከእኛ ጋር መቀመጥ አለባት »

👍22
«ከእኛ ጋር? » ብላ በጩኸት
አቋረጠችው «እሱ እንኳን በጭራሽ አይደረግም።»
« በግድ ነው . . ኤማ ሌላ መድረሻ የላትም እኔም በነገሩ ብዙ ካሰብኩበት በኋላ ነው ከዚህ ውሳኔ ለመድረስ የተገደድኩት " ስለዚ እንደ ነገርኩሽ ወደ
ካስል ማርሊንግ ሔዳለች " »
ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ከንዴቷ ብዛት ፊቷ ተለዋወጠ " ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ከባሏ ፊት ተደቀነች ጠረጴዛው ብቻ በመኻላቸው ነበር "
« ስማ ሬይሞንድ . . . ሳቤላ ቬንን ከቤቴ አላስገባትም አንተስ እንዴት እንዲህ ያለውን ልመና ተባብለህ ትቀበላለህ ? »
« በዚህ ጉዳይ ማንም አላባበለኝም " ማንም አልጠየቀኝም ሐሳቡን ያመጣሁት
እኔ ነኝ ካለዚያ የት ትደርሳለች ? »
« የትም ብትደርስ ግድ የለኝም " ከአኛ ጋር መቀመጥ አትችልም " »
« እስቲ ነገሩን በቅን ልቦና አመዛዝነሽ ተመልከቺው » አላት ሎርድ ማውንት ስቨርን ሌላ ዘመድ ወይም ሀብት የላትም " አባቷ ጥሩ ኑሮ ቢኖር ኖሮ እስከ ኻያ ዓመት ጠብቄ እንኳን የማላግኘው የነበረውን ጉልቱንና ሹመቱን በመውረስ የተካሁት እኔ ስለሆንኩ ለልጁ መጠጊያ ለመስጠት የሕሊናና የሥነ ምግባር ግዴታ.
አለብኝ " ይኸን ሁሉ አመዛዝነሽ አታይውም ? »
« የለም አላየውም»
" አልቀበላትም»
« አሁን እሷ ካሰል ማርሊንግ ገብታለች " የመጣችውም እኛን አምና ሆኝ አሁን ወዴቤትሽ ስትመለሽ ይህችን ልጅ ከቤት አስወጥተሽ በመንድ እንድትንከራተት ወይም ከድኩማን መርጃ መጠለያ ገብታ እንድትረዳ ወይም የጡረታ ዳረጐት ለማግኘት እንድትለምን በማድረግ ራስሽን ለሕዝብ ዓለም ስድብና እርግማን አጋልጠሽ ለመስጠት የምትደፍሪ አይመስለኝም " ኤማ... ለዚህች ልጅ ያለሽ አስተሳሰብ መለወጥ ያለበት ይመስለኛል»
ኤማ ማውንት እስቨርን ባሏ ላቀረበላት ምክንያት የሚያረካ መልስ ስላልነነበራት በደፈናው በቁጣ አጉተመተመች ዝም አለች። ፊቷ ግን እሳት መሰለ።
« ደሞኮ ብዙም አታስቸግርሽም » አለ ኧርሎ እንደ ዋዛ አድርጐ ሳቤላን የመሰለች ቆንጆ ቶሎ እንደምታገባ አይጠረጠርም " እንደማያት የረጋችና ተግባብታ
መኖር የምትችል ጠባዬ ጥሩ ልጅ ናት " እኔ ያንቺ ጥላቻ በምን ተነሣሥተሽ እደሆነ ሊገባኝ አልቻለም " ብዙ ወንዶች ለውበቷ ሲሉ የገንዘብ ድሀነቷን ከቁም
ነገር አይቆጥሩትም »
« በመጀመሪያ የሚመጣላትን ጠያቂ ማግባት ይኖርባታል» አለችና እንዲያውም የተናደደችው እመቤት ነገሯን በመቀጠል «ግድየለም የማደርገውን እኔ
አውቃለሁ » ስትል ንጭንጯን ቀጠለች "....
💫ይቀጥላል💫

👍18
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
...ወንበር ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠና እግሩን ወፍራሙና ክብ የሆነው የወንበሩ መደገፊያ ላይ አድርጎ የሚያነበው መፅሀፍ ከፈተ፡ እኔም ብቸኛው ባዶ አልጋ ላይ ጋደም ብዬ ስለ ንጉስ አርተር ማንበብ ጀመርኩ። አመናችሁም
አላመናችሁ ከዚህ በፊት መኖሩን የማላውቀው በር ተከፈተልኝ እጅግ ውብ አለም ጀብደኝነት ያለበት፣ ፆታዊ ፍቅር ያለበትና ስርዓት ያላቸው ሴቶች እንደምሰሶ ቆመው ከሩቅ የሚመለኩባት ናት። ለእኔ የመካከለኛው ዘመን የፍቅር ግንኙነት የተጀመረው የዚያን ቀን ነው። ከሁሉም በላይ ብዙ
የባሌት ዳንሰኞች መሰረታቸው ተረት ነው፣ አይደል? ሁሉም ተረቶች ደግሞ በመካከለኛው ዘመን ካሉ ተረትና ምሳሌዎች አይደል የመጡት።
እኔ ሁልጊዜ ተረት ላይ ያሉ አስማተኛ ፍጡራን ሳር ላይ ሲደንሱ ማየት የምፈልግ ልጅ ነኝ፡ በጠንቋዮች፣ በድግምት፣ በአስማት፣ በጭራቅ ማመን
እፈልግ ነበር፡ አስማቶች ሁሉ በሳይንሳዊ ማብራሪያ ከአለም ላይ እንዲጠፉ አልፈልግም: የዚያን ጊዜ ግን በጠንቋይና በጭራቅ በሚተዳደር ጠንካራና
ጨለማ ቤተመንግስት ውስጥ ለመኖር እንደምመጣ አላውቅም ነበር አንዳንድ የሰለጠነው ዘመን ጠንቋዮች ድግምት ለመስራት ገንዘብ ይጠቀማሉ ብዬ ገምቼም አላውቅም።
የቀኑ ብርሃን ከከባድ መጋረጃዎቹ ጀርባ ሲሸሽ ትንሽዋ ጠረጴዛችን ላይ ለእራት ተቀመጥን፡፡ እኔና ክሪስ ቀዘቀዘም አልቀዘቀዘም ምግባችንን እንበላለን። መንትዮቹ ግን ገና ምግባቸውን ሲያዩት ሁልጊዜ አይጣፍጥም
ብለው ይነጫነጫሉ ኬሪ የምትነጫነጭ ባይሆን ኖሮ ኮሪ የተሻለ ይመገብ እንደነበር ይሰማኛል።
“ብርቱካኖቹ የሚያስቅ መልክ ነው ያላቸው" አለ ክሪስ ብርቱካን እንድልጥ እየሰጠኝ፡ “ፈሳሽ የፀሀይ ብርሀን ናቸው":: አሁን ትክክለኛ ነገር ተናገረ።
መንትዮቹ በደስታ ሊበሉት የሚችሉት ነገር አገኙ: “ፈሳሽ የፀሀይ ብርሀን”።
አሁን መሽቷል። ክፍሉ ግን ቀን ከነበረው የተለየ አልሆነም አራቱንም መብራቶች አበራናቸው፡፡ እናታችን ይዛት የመጣችውን ትንሽዬ የራስጌ
መብራት ደግሞ ጨለማ ለማይወዱት መንትዮች አደረግንላቸው:ከእንቅልፋቸው ሲነቁ እንደገና ንፁህ ልብስ አልብሰን ፀጉራቸውን አበጥረንና
ፊታቸውን አጥበን እንቆቅልሽ እንዲጫወቱ ወለሉ ላይ አስቀመጥናቸው በጣም ቆንጆ ሆነው ነበር። ምስል የመገጣጠሙን እንቆቅልሽ ለእነሱ አዲስ ስላልነበር የትኛው የቱጋ እንደሚገጠም ማወቅ ቀላል ሆኖላቸው ነበር በውድድር መልክ እንዲያደርጉት ሞከርን ግን ወዲያው ተሰላቹ ከዚያ አልጋ
ላይ አስቀመጥናቸውና ራሳችን የፈጠርናቸውን ታሪኮች እንነግራቸው ጀመር
ያም አሰለቻቸው እኔና ወንድሜ ምን ማድረግ እንዳለብን አላወቅንም: ቀጥሎ ክሪስ ከሻንጣ ውስጥ የመጫወቻ መኪናዎች አወጣና እየገፉ እንዲጫወቱ ነገራቸው።
በጠረጴዛው ስር በአልጋው ስር እየገቡ እንደገና እስኪቆሽሹ ድረስ መጫወት ጀመሩ።
ሲደክመን ክሪስ ቼከርስ እንድንጫወት ሀሳብ አቀረበና መንትዮቹ የብርቱካን
ልጣጮቹን በመኪናቸው ጭነው ወስደው ፍሎሪዳ ላይ እየደፉ ነበር። ያም ጥግ ላይ የተቀመጠው የቆሻሻ ቅርጫት ነበር።
“በቀያዮቹ መጠቀም ትችያለሽ እኔ እንዳንቺ ጥቁር ተሸናፊ ቀለም ነው ብዬ አላምንም” አለ ግንባሬን አጨፈገግኩት በቀንና በማታው መካከል ዘለአለም የሚመስል
ጊዜ አልፏል፤ ይህም እንደገና እንዳልመለስ አድርጎ ለውጦኛል። “ቼከርስ መጫወት አልፈልግም” አልኩት።
ሊመጣ ካለ ነገር ፍራቻና ውስጤን ከሚያሰቃዩኝ ጥርጣሬዎች ለመገላገል
እናታችን ሁሉንም እውነት ብትነግረን ኖሮ የሚለውን ማለቂያ የሌለውን ፀሀሳቤን ተውኩት ነገር ግን አራታችንም እናታችን እንድትመጣ እየጠበቅን
ሳለ ሀሳቦቼ ያልዳሰሱት ቦታ አልነበረም: አብዛኛው ፍራቻዬ እሳት፣ ጣዕረሞትና ሌሎች ጣሪያው ስር ካለው ክፍል ውስጥ ያሉ አስፈሪ ነገሮች ነበሩ። ከሁሉም በላይ ትልቁ ፍራቻዬ በተቆለፈ ክፍል ውስጥ ሊነሳ የሚችል እሳት ነበር።
ጊዜው በዝግታ አለፈ ክሪስ ወንበሩ ላይ ተቀምጦ እያነበበ አልፎ አልፎ ሰዓቱን ይመለከታል፡ መንትዮቹ የብርቱካን ልጣጮቻቸውን እያመላለሱ
መጫወት ሰለቻቸው:
ሲኦልንና በሲኦል ያሉ ቅጣቶችን የሚያመለክተውን ስዕል ስመለከት አያታችን ምን ያህል ብልጥና ጨካኝ እንደሆነች እያሰብኩ ነበር ለምንድነው ስለ ሁሉ ነገር ማሰብ ያለባት? እግዚአብሔርም ራሱ ውጪ ስንትና ስንት መጥፎ
ነገሮች የሚሰሩ እያሉ ተቆጣጣሪ አይኖቹን በአራት ትንንሽ ልጆች ላይ ማድረጉ ፍትሀዊ አይደለም እኔ በእግዚአብሔር ቦታ ብሆን ኖሮ ሁሉንም ነገር ማየት የምችል ከመሆኔ አንፃር፣ የተቆለፈባቸውን አባት የሌላቸውን አራት ህፃናት በመቆጣጠር ጊዜዬን ከማጠፋ ሌላ በጣም የሚያዝናና ነገር ላይ
ትኩረት አደርግ ነበር በዛ ላይ አባታችን ያለው እዛው ከእግዚአብሔር ጋር ስለሆነ፣ እግዚአብሔር በደንብ እንዲንከባከበንና አንዳንድ ስህተቶቻችንን አይቶ እንዲያልፍ ሊነግረው ያስፈልጋል።
ክሪስ አኩራፊና ተቃዋሚነቴን ችላ ብሎ መፅሀፉን አስቀመጠና የመጫወቻውን ሳጥን አነሳ፡
“ምን ሆነሻል?” ሲል ጠየቀኝና የመጫዎቻውን ሠሌዳ ዘርግቶ ጥቁሩን በጥቁሩ፣ ቀዩን በቀዩ መደርደር ጀመረ፡ “ለምንድነው ፀጥ ብለሽ የተቀመጥሽው?
ለምንድነው የፈራሽ የመሰልሽው? እንደገና እንዳላሸንፍሽ ነው?”
ስለ እሳት ያሰብኩትን ለክሪስ ነገርኩት ከዚያ ልክ የድሮ ፊልም ላይ እንዳየሁት ከእሳቱ ለማምለጥ መሬት ላይ እንዲያደርሰን አንሶላውን ተልትለንና ቋጥረን
እንደመሰላል መስራት እንደምንችል አወራሁት “ምናልባትም ዛሬ ማታ እሳት ከተነሳ መስኮቱን ከስበርን በኋላ መሬት የምንደርስበት መንገድ ይኖረናል ማለት ነው እና እያንዳንዳችን መንትዮቹን አንድ አንድ ተካፍለን ጀርባችን ላይ
እናስራቸዋለን” አልኩት።
ሰማያዊ አይኖቹ በአድናቆት በሩ እንደዚህ አይነት አክብሮት ሲያሳዩኝ አይቼ አላውቅም፡ “ዋው ካቲ እንዴት የሚገርም ሀሳብ ነው! አስደናቂ ነው! ልክ ነሽ እሳት ቢነሳ ማድረግ ያለብን አሁን እንዳልሽው ነው ግን አይነሳም ከአሁን
በኋላ አልቃሻ ህፃን አለመሆንሽን ማወቄ በጣም ጥሩ ነው ስለ ወደፊት አስብሽ ሳይጠበቅ ለሚመጣ ነገር እቅድ ካወጣሽ አድገሻል ማለት ነው እናም
ወድጄዋለሁ” አለኝ።
ከአስራ ሁለት አመታት ከባድ ሙከራ በኋላ፣ ማግኘት ይቻላል ብዬ የማላምነውን የክሪስን አድናቆትና ማረጋገጫ የማግኘት ግቤን በመጨረሻ አሳካሁ በዚያች ደቂቃ በተለዋወጥናቸው ፈገግታዎች እስከ ሳምንቱ መጨረሻ አብረን መዝለቅ እንደምንችል ቃል ገባን።
እናታችን እንግዳ ገፅታ ተላብሳ በሚያስቅ ሁኔታ እየተራመደች ወደ ክፍሉ መጣች መምጣቷን ለረጅም ሠዓታት እየጠበቅን የነበረ ቢሆንም፣ እንደገና
ከእሷ ጋር መሆናችን ግን የገመትነውን ያህል ደስታ አልሰጠንም ምናልባት
አብራት ተከትላ የመጣችው አያታችን በክፉ ግራጫ አይኖቿ ስትመለከተን ጉጉታችንን ገድላው ይሆናል።
አንድ ልክ ያልሆነ ነገር ተፈጥሯል፡ ምን ይሆን? ክሪስና እኔ አልጋ ላይ
ተቀምጠን ቼከርስ ስንጫወት የአልጋ ልብሱን በማጨማደድ የሰራነው ጥፋት የአያትየውን እይታ ስቧል።
አንድ ህግ ተጥሷል አይ ሁለት... መተያየትም የአልጋ ልብሱን እንደማጨማደድ ሁሉ የተከለከለ ነው።
መንትዮቹ ደግሞ ሲጫወቱ የነበረው የመገጣጠም እንቆቅልሽ እዚህና እዚያ
ተበታትኗል፡ የመጫወቻ መኪናዎቻቸውም በየቦታው ተዝረክርከዋል ክፍሉ ንፁህ አልነበረም
ሶስት ህጎች ተጥሰዋል።

👍41❤2🥰2🔥1
ወንዶችና ሴቶችም አንድ ላይ መታጠቢያ ቤት ገብተዋል
ሌሎችም ህጎች ጥስን ይሆናል፡ ምንም ነገር ብናደርግ ሁልጊዜም በሚያየን በእግዚአብሔርና በአያታችን መካከል ያለው የሚስጥር ግንኙነት እንዳለ ነው።
የእግዚአብሔር ቁጣ
እናታችን እያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ የሚያሳምማት በሚመስል ሁኔታ
እየተራመደች ነበር የመጣችው:: እግሮቿ ከመወጠራቸውና መገጣጠሚያዎቿም ድርቅ ከማለታቸውም በተጨማሪ የሚያምረው ፊቷ ገርጥቶና አብጦ ነበር።አይኖቿም አብጠው ደም መስለዋል። በሰላሳ ሶስት አመት እድሜዋ የሆነ ሰው ከመጠን በላይ ስላዋረዳት አይኖቻችንን እንኳን ማየት አልቻለችም:
የተሸነፈች፣ የተጣለች የተዋረደችና በጭካኔ የተቀጣ ልጅ መስላ በክፍሉ መሀል ቆመች: መንትዮቹ የሆነችውን ባለማስተዋል ሰላም ሊሏት ወደሷ ተንደረደሩና በመጓጓት እጆቻቸውን እግሮቿ ላይ ጠምጥመው በደስታ ድምፅ
እየጮሁና እየሳቁ “እማዬ እማዬ የት ነበርሽ?” አሉ።
እኔና ክሪስ ደግሞ እያዘገምን በማያስተማምን ሁኔታ አቀፍናት። ሁኔታችንን የሚያይ ሰው ቢኖር ለአንድ ሮብ ብቻ ሳይሆን ለአስር ሳምንቶች ያልነበረች ሊመስለው በቻለ ነበር እንደዚያ ያደረግን ምክንያት ግን እሷ ተስፋችንን፣
እውነታችንን፣ ከውጪው አለም የመገናኘት መስመራችንን የምትወክል በመሆኗ ነበር።
ደጋግመን ሳምናት? የመጓጓትና የመራብ ጥብቅ እቅፋችን በህመም አሸማቀቃት ወይስ አስጨነቃት? በገረጣ ፊቷ ላይ እምባዋ በጉንጮቿ ላይ ሲወርድ
ስመለከት፣ የምታለቅሰው ለእኛ በማዘን እንደሆነ አሰብኩ ሁላችንም በተቻለ መጠን ወደ እሷ ለመቅረብ በመፈለግ በአንደኛው አልጋ ላይ ተጠጋግተን ተቀመጥን፡ እኔና ክሪስ ጎንና ጎኗ ላይ መጠጋት እንድንችል መንትዮቹን
አንስታ ጭኖቿ ላይ አስቀመጠቻቸው ሁላችንንም ተመለከተችንና በንፅህናችን መደሰቷን ነገረችን: ኬሪ ፀጉር ላይ ከልብሷ ጋር የሚመሳሰል
አረንጓዴ ሪባን እንዳሰርኩላት ተመልክታ ፈገግ አለች ስትናገር ልክ ጉንፋን እንደያዛት አይነት ድምፅዋ ጎርንኖ ነበር “እስቲ እውነቱን ንገሩኝ… ዛሬ
ቀናችሁ እንዴት አለፈ?” አለች።
የኮሪ ፊት በኩርፊያ ተውጦ በደንብ በማይሰማ ድምፅ ቀኑ ምንም ጥሩ እንዳልነበረ ተናገረ ኬሪ ኩርፊያዋን ወደ ቃላት ለውጣ “ቲና ክሪስ ክፉ ናቸው!” ብላ ጮኸች “ቤት ውስጥ መሆን አልፈለግንም ነበር! እነሱ ግን
ቀኑን ሙሉ ቤት ውስጥ እንድንውል አደረጉን! አሪፍ ነው ያሉንን ያንን ትልቅ ቆሻሻ ቦታም አልወደድነውም! እማዬ ምንም ጥሩ አልነበረም፡”
ኬሪን ለማባበል ስትሞክር የተቸገረችና ያመማት ትመስል ነበር ለመንትዮቹ ሁኔታዎች እንደተለወጡና ታላቅ ወንድምና እህታቸውን እንዲሰሙና ልክ
እንደ ወላጆች አድርገው በማሰብ ሊታዘዙን እንደሚገባ ነገረቻቸው
“አይሆንም! አይሆንም!” ስትል ኬሪ በጋለ ቁጣ ተናገረች፡ “እዚህ መሆን አስጠልቶናል! የምንፈልገው የአትክልቱን ቦታ ነው፡፡ እዚህ ጨለማ ነው
ክሪስና ካቲን አንፈልግም የምንፈልገው አንቺን ነው እማዬ! ከዚህ አውጪንና ቤታችን ውሰጅን፡”
ኬሪ ቤቷ መሄድ እንደፈለገች በመናገር እየጮኸች መማታት ጀመረች: እኔን፣ ክሪስንና እናቴንም ጭምር ተማታች። እናቴ ራሷን ለመከላከል ሳትሞክር
ዝም ብላ ተቀምጣ ነበር። እናታችን ባልሰማቻት መጠን ኬሪ በባሰ ሁኔታ ትጮህ ነበር። ጆሮዎቼን ያዝኩ፡ “ኮሪን! አያትየው አዘዘች: “በዚህ ሰከንድ
ያቺን ልጅ ከመጮህ አስቁሚ!” እንደ ድንጋይ የጠነከረ ፊቷን ስመለከት ኬሪን በአንድ ጊዜ እንዴት ዝም ማሰኘት እንዳለባት በትክክል እንደምታውቅ
ገብቶኛል። በእናቴ ሌላኛው ጉልበት ላይ የተቀመጠው ትንሽ ልጅ መንትያ እህቱን የምታስፈራራው ረጅም ሴትዮ ላይ አፈጠጠ ከዚያ ከእናቴ ጭን
ላይ ወርዶ አያትየው ፊት ለፊት ቆመ፡ ኬሪ ትናንሽ እግሮቿን ከፍታ ቆማ፣ጭንቅላቷን ቀና አድርጋ እምቡጥ አበባ የመሰለ አፏን ከፈተችና ለቀቀችው!
ልክ በጣም አሪፉን ዜማውን ለመዝጊያ እንደሚያቆይ የኦፔራ ኮከብ ሆነች።የቀድሞው ለቅሶዋ የትንሽ ድመት ጬኸት ይመስል ነበር አሁን ደግሞ ነብር
ሆናለች- በቁጣ!
ቀጥሎ በሆነው ነገር በጣም ፈራሁ፡
አያትየው ኬሪን በፀጉሯ ስታንጠለጥላት ኮሪ እንደ ድመት ፈጥኖ አያትየው ላይ ተከመረ፡ አይኔን ባርገበገብኩበት ፍጥነት እግሯን ነከሳተ። አሁን በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም እንዳለንበት በማወቄ በውስጤ ተሸማቀቅኩ:
ቁልቁል ተመለከተችውና ልክ አናዳጅ ትንሽ ውሻ እንደሆነ ሁሉ ከእግሯ ላይ ገፈተረችው፡ ንክሻው ግን ኬሪን እንድትለቃት አድርጓታል። ኬሪ ከወደቀችበት በር ጋ ተነስታ ፈጥና በእግሮቿ ቆመችና ፈጣን እርግጫ
ስትዘነዝር የአያትየውን እግር ሳተችው:
መንትያ እህቱ በመሳቷ ኮሪ ትንሹን ነጭ ጫማውን አነሳና በጥንቃቄ አልሞ በቻለው መጠን በሀይል የአያትየውን እግር መታ:
በእርግጥ መታወስና መቀረፅ የሚገባው ትዕይንት ነበር።
ይህ ሁሉ ሲሆን ኮሪ ቃል አልተናገረም: ወይም አላለቀሰም፡ ይህ የእሱ የማያወላውል የፀጥታ መንገድና ነው: ኮሪ ትንሽ ልጅ ቢሆንም እንኳን ማንም
ሰው መንትያ እህቱን እንዲያስፈራራትም ሆነ እንዲጎዳት አይፈቅድም ለምን
የሰማይ ስባሪ የሚያክል ቁመትና መቶ ኪሎ ክብደት አይኖረውም! ኮሪ፣ ኬሪ ላይ የተደረገውን ወይም እሱ የሆነውን እንዳልወደደው ሁሉ አያትየውም እሷ ላይ የተደረገውን አልወደደችውም። ዘመም ብሎ የሚመለከታትን ትንሹን
እምቢተኛ ቁጡ ፊት አየችው: እስኪረጋጋና ሰማያዊ አይኖቹ ላይ ያለው ቁጣ እስኪረግብ ጠበቀች እሱ ግን በቆራጥነት ማድረግ የምትችለውን መጥፎ ነገር እንድታደርግ ፈተናት። ስስ ቀለም አልባ ከንፈሮቿ ጥብቅ ወዳለ ደማቅ ጠማማ የእርሳስ መስመር ተለወጡ።
ከላይ እጇ መጣ፡ በአልማዝ ቀለበቶች የደመቀ ትልቅና ከባድ እጅ። ኮሪ ፍንክች አላለም። በዚህ ግልፅ ሁኔታ ውስጥ የእሱ ምላሽ ትንንሽ እጆቹን ጨብጦ በፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ቴክኒክ ለመፋለም መዘጋጀት ነበር።
የአምላክ ያለህ! ከእሷ ጋር ተደባድቦ ለማሸነፍ ያስባል?
እናታችን የኮሪን ስም ስትጠራ ሰማሁ። ድምጽዋ ከመታፈኑ የተነሳ እንደ ሹክሹክታ ነበር። አያትየው አሁን ማድረግ ያለባትን በመወሰን፣ ከባድ ጥፊ
ስታሳርፍበት ወደኋላ ተንገዳግዶ ወለሉ ላይ ወደቀ: ግን ወዲያው ተነስቶ ያንን ትልቅ በጥላቻ የተሞላ የስጋ ተራራ ለመግጠም ዙሪያውን ተሽከረከረ ሀሳቡን አለመቁረጡ አሳዛኝ ነገር ነበር አቅማማ… ደግሞ አሰበና ያለበትን ሁኔታ መረዳቱ ቁጣውን እንዲያሸንፈው አድርጎት ኬሪ ተኮራምታ ወደ
ተቀመጠችበት ግማሹን እየዳኸ ግማሹን እየሮጠ ሄዶ ተንበረከከና ክንዶቹን በአንገቷ ዙሪያ አደረገ ከዚያ ጉንጭ ለጉንጭ ተጣብቀው በመተቃቀፍ ጩኸቱን ወደ እሷ አስተላለፈ::
ክሪስ ከጎኔ ቆሞ ፀሎት የሚመስል ነገር ያልጎመጉማል።
“ኮሪን፣ ያንቺ ልጆች ናቸው ስለዚህ አሁኑኑ ዝም አስብያቸው!"
መንትዮቹ አንዴ ማልቀስ ከጀመሩ እነሱን ዝም ማሰኘት አይቻልም
ምክንያታዊነት ዋጋ የለውም: የሚሰሙት የራሳቸውን ፍርሀት ብቻ ነው፡ የሚያቆሙት ሲበቃቸው ነው:: አባታችን በህይወት በነበረ ጊዜ እንደዚህ አይነት ሁኔታዎችን መያዝ ይችል ነበር፡ ሁለቱንም በእያንዳንዱ ክንዱ ስር ይይዝና
ወደ ክፍላቸው ይወስዳቸዋል ከዚያ ዝም እንዲሉ አለበለዚያ ግን ዝም ማለት እስኪችሉ ድረስ ብቻቸውን ክፍላቸው ውስጥ ያለ ቲቪ፣ ያለ አሻንጉሊት፣ ያለምንም ነገር እንደሚቆዩ ያስጠነቀቅቃቸዋል፡ እምቢተኛነታቸውን የሚሰማ
ምስክር በሌለበት ወይም ለቅሷቸውን የሚሰማ በሌለበት በሩ ከተዘጋባቸው በኋላ ባሉት ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ጩኸታቸው ያበቃል፡ ከዚያ ይወጡና በፀጥታ ወደ አባታችን ሄደው ጭኑ ላይ ይቀመጡና በትንንሽ ድምጻቸው “ይቅርታ” ይላሉ፡

👍26🥰2❤1
አሁን ግን አባዬ ሞቷል ለቅጣት የሚቀመጡበት ሌላ የመኝታ ክፍልም የለም ትልቁ ቤታችን ይህ አንድ ክፍል ነው፡ እና እዚህ መንትዮቹ ታዳሚያቸውን በሚያሳምም ሁኔታ ማርከዋል። ፊታቸው ከሮዝ ወደ ቀይ፣
ከቀይ ወደ ደም መምሰል፣ ደም ከመምሰል ወደ ሀምራዊ እስኪቀየር ድረስ ጮኸዋል። ዛሬ ትልቅ ትርኢት ነበር አያትየው በነገሩ እንደተመሰጠች ቆይታ፣ እንዳትንቀሳቀስ የያዛት ነገር ድንገት ድግምቱን ለቀቀ ነፍስ ዘራች ከዚያ ሆነ ብላ መንትዮቹ ተቃቅፈው ወደ ተንበረከኩበት ጥግ ሄደች፡
ጎንበስ ብላ ሁለቱን የሚያለቅሱ ህፃናት ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ
ማጅራታቸውን ይዛ አነሳቻቸው: እየተንፈራገጡና እጆቻቸውን እያወናጨፉ ከሚያሰቃያቸው ሰው ለማምለጥ በደመነፍስ እየተወራጩ ሲጮኹ አያትየው
ከእሷ ራቅ አድርጋ በእጆቿ አንጠልጥላቸው እናታችን ፊት አደረገቻቸው ከዚያ ልክ የማይፈለግ ቆሻሻ እንደሆኑ ሁሉ ወደ ወለሉ ጣለቻቸውና ከእነሱ
ጩኸት በላይ በሚሰማ ጠንካራና የሚጮህ ድምፅ “በዚህ ቅፅበት ጩኸታችሁን ካላቆማችሁ፣ ሁለታችሁንም ከቆዳችሁ ደም እስኪያልቅ ነው የምገርፋችሁ "
አለች።
ኢሰብአዊ ነገሯ ላይ ይህ ማስፈራሪያ ተጨምሮበት የተናገረችውን የምታደርግ መሆኗ እኔን እንዳሳመነኝ ሁሉ መንትዮቹንም አሳመናቸው።
መንትዮቹ በሚያስደነግጥና በሚያስፈራ አይነት ከማልቀሳቸው
አፋቸው እንደተከፈተ ፍጥጥ ብለው ተመለከቷት። ደም ምን እንደሆነ በእሱ መውጣት ህመም አብሮት እንዳለ ያውቃሉ በጭካኔ ሲያዙ ማየት በጣም የሚያሳምም ነበር፡ አጥንታቸው ቢሰበር ወይም ሰውነታቸው ቢበልዝ ግድ ያላት አትመስልም፡ ከልጆቹ በላይ፣ ከሁላችንም በላይ ቆማለች ከዚ
ስታሰላስል ቆይታ እናታችን ላይ ተኮሰች፡ “ኮሪን፣ ሁለተኛ እንደዚህ አይነት አሰልቺ ትዕይንት ማየት አልፈልግም: ልጆችሽ እንደተሞላቀቁ ግልፅ ነው:
እና የስነስርዓትና የመታዘዝ ትምህርት ያስፈልጋቸዋል: እዚህ ቤት ውስጥ የሚኖር ልጅ አልታዘዝም ማለት፣ መጮህ፣ ወይም እምቢተኛነት ማሳየት
የለበትም ሰማሽ! የሚናገሩት ሳናግራቸው ብቻ ነው: ድምፄን ለመታዘዝ መዝለል አለባቸው አሁን ልብስሽን አውልቂና እዚህ ቤት ውስጥ አለመታዘዝ
የሚያመጣውን ቅጣት አሳያቸው" አለች።
በዚህ ጊዜ እናታችን ተነሳች ረጅም ተረhዝ ያለው ጫማዋ ሲወልቅ ያነሰች መሰለች እና ፊቷ ነጭ ሆኖ “አይሆንም! አሁን ያ አስፈላጊ አይደለም::ተመልከቺ መንትዮቹ ማልቀስ አቁመዋል ... አሁን እየታዘዙ ነው" አለች።
የአሮጊቷ ፊት ተኮሳተረ። “ኮሪን ላለመታዘዝ የሚያበቃ ስርዓት አልበኝነት መሆኑ ነው? አንድ ነገር እንድታደርጊ ሳዝሽ ያለምንም ጥያቄ ታደርጊያለሽ ወዲያውኑ! ያሳደግሻቸውን ተመልከቺ: አራቱም ደካማ፣ ሞልቃቃና ስርዓት
የሌላቸው ልጆች ናቸው መጮህ ስለቻሉ የሚፈልጉትን እንደሚያገኙ ያስባሉ። እዚህ ጩኸት ምንም ጥቅም የለውም፡ ለማይታዘዙና የእኔን ህግ ለሚጥሱ ምንም ምህረት እንደሌለኝ እነሱም ማወቅ አለባቸው: ይህንን ማወቅ ይገባሻል ኮሪን፡ ምህረት አሳይቼሽ አውቃለሁ? እኛን ከመክዳትሽ በፊት ይህ ቆንጆ ፊትሽና ማራኪ አቀራረቦችሽ ለቅጣት የተዘጋጀ እጄን መልሰውታል? አባትሽ
እጅግ ይወድሽ እንደነበረና አንቺን ለመከላከል ከእኔ ጋር ሲጣላ እንደነበር አስታውሳለሁ እነዚያ ቀናት አልፈዋል። እኔ ነሽ የምልሽ አይነት በማታለል የተሞላሽ፣ ውሸታምና ቆሻሻ መሆንሽን አረጋግጠሽለታል:"
እነዚያን እንደ ባልጩት ድንጋይ የሆኑትን አይኖቿን ወደእኔና ወደ ክሪስ መለሰች: “አዎ አንቺና አጎትሽ እጅግ በጣም ቆንጆ ቆንጆ ልጆች አፍርታችኋል። ያንን አምናለሁ፤ ቢሆንም ግን ባትወልዱ ይሻል ነበር፡ ሲታዩ ደግሞ ለስላሳና ለምንም የማይጠቅሙ ምናምንቴ ናቸው" ክፉ አይኖቿ እነዚያ ጥፋቶች
ከእሷ የሚጋቡብን ይመስል እናታችንን በንቀት ተመለከቷት። ግን ገና አልጨረሰችም።
ኮሪን ልጆችሽ እናታቸው ላይ የሆነውን ሲመለከቱ እነሱ ላይ ሊሆን ስለሚችለው ነገር ጥርጣሬ አይገባቸውም᎓ ልጆችሽ በእርግጥም የሚጨበጥ
ትምህርት ያስፈልጋቸዋል"
እናቴ ቀጥ ብላ ቢያንስ በአራት ኢንች የምትበልጣትንና እጅግ ብዙ በሆነ ኪሎ
"እሷ የምትከብደውን ባለ ብረት አጥንት ሴት በድፍረት ተጋፈጠች: “ልጆቼ ላይ ጨካኝ ከሆንሽባቸው..." ጀመረች እናቴ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ “… ዛሬ
ማታ ከዚህ ይዣቸው እወጣና እነሱንም ሆነ እኔን በድጋሚ አታይንም፡" አለች ይህንን ስትናገር ቆንጆ ፊቷን ቀና አድርጋ አስቀያሚ ግዙፍ ነገር የሆነችውን እናቷን በቆራጥ አስተያየት እያየች ነበር የእናታችንን ማስፈራሪያ
ትንሽዬ ቀዝቃዛ ፈገግታ አገኘው:
አይ ፈገግታ አይደለም ፌዝ ነው “ዛሬ ማታ? ውሰጃቸው! አሁኑኑ! አንቺም ሂጂ! ልጆችሽን ደግሜ ባላያቸው ወይም ከአንቺ ድጋሚ ባልሰማ ግድ ያለኝ ይመስልሻል?” በውስጤ በደስታ እየጮህኩ ነው እናታችን ከዚህ ልታወጣን
ነው: ልንሄድ ነው! ደህና ሁን አንተ ክፍል ክፍል እናንተ ሚሊየኖች ደህና ሁኑ… አልፈልጋችሁም!
ደህና ሁን የጣሪያው ስር
ነገር ግን እናታችን በተረከዟ ዞራ ሻንጣዎቻችንን ለማውጣት ወደ ልብስ ማስቀመጫ ትሄዳለች ብዬ ስጠብቅ በተቃራኒው የእናታችን ገፅታ በቅፅበት ሲናድ ተመለከትኩ አይኖቿ በሽንፈት ወደታች ሲረግቡ ስሜቷን ለመደበቅ በቀስታ አንገቷን ደፋች።
እየተንቀጠቀጥኩና እየፈራሁ የአያትየው ፌዝ እያደገ ጨካኝ የድል ፈገግታ ሲሆን ተመለከትኩ እማዬ፣ እማዬ፣ እማዬ! ነፍሴ እየጮኸች ነው እንዲህ
እንድታደርግሽ አትፍቀጂ!
“ኮሪን አሁን ሹራብሽን አውልቂ!”
እያመነታች በዝግታ የገረጣ ፊቷን አዙራ ጀርባዋን ሰጠችን፡ እንደምንም ግትር ያሉ ክንዶቿን አንቀሳቅሳ እያንዳንዱን የሹራቧን ቁልፎች በጣም በችግር ፈታች: ከዚያ በጥንቃቄ ሹራቧን ዝቅ አድርጋ ጀርባዋን አሳየችን።
ከሹራቧ ስር የውስጥ ልብስ ወይም ጡት መያዣ አልለበሰችም: ለምን እንደሆነ ለማወቅ ቀላል ነበር: ክሪስ ትንፋሹን ሲስብ ሰማሁት ኬሪና ኮሪ የድንጋጤ ድምፃቸው ወደ ጆሮዬ ደረሰ አይተው መሆን አለበት አሁን ሁልጊዜ ግርማ ሞገስ ተላብሳ የምትራመደው እናቴ ወደ ክፍሉ ስትገባ
በአስቸጋሪ ሁኔታ እየተራመደችና አይኖቿ ቀልተው እያለቀሰች የነበረው ለምን እንደሆነ አወቅኩ።
ጀርባዋ ከአንገቷ እስከ ሰማያዊ ጉርድ ቀሚሷ ወገብ ድረስ በረጃጅም ደም የሚመስል የግርፋት ምልክት ተሸፍኗል፡ አንዳንዶቹ ቁስሎቿ በደረቀ ደም
ተሸፍነዋል በግርፋቱ ሰንበሮች መካከል ያልደማ ምንም ቦታ የለም::
አያታችን ለእኛና ለእናታችን ስሜት ምንም ግድ ሳይሰጣት ሌላ ትዕዛዝ አስተላለፈች: “ልጆች በደንብ ተመልከቱ! እነዚህ የግርፊያ ምልክቶ እስከ እናታችሁ እግር ድረስ ይዘልቃሉ። ሰላሳ ሶስት ግርፋቶች ናቸው.
አንዳንድ አመታት የሚወክሉ
ናቸው። እያንዳንዳቸው
የህይወቷን ተጨማሪዎቹ አስራ አምስቱ ደግሞ ከአባታችሁ ጋር በኃጢአት ለኖረችባቸው
አስራ አምስት አመታት የተሰጡ ናቸው፡፡ ቅጣቱን ያዘዘው ወንድ አያታችሁ ነው፡ የገረፍኳት ግን እኔ ነኝ፡ የእናታችሁ ወንጀል በእግዚአብሔር ላይ
የተፈፀመና ማህበረሰቡ ከሚኖርበት ስርዓት ያፈነገጠ ስለሆነ ነው: ጋብቻዋ የተቀደሰ ጋብቻ አልነበረም: የረከሰ ነበር፡ በእግዚአብሔር አይኖች ፊት
አፀያፊ የሆነ ጋብቻ ነበር፡ እና ያ ሳይበቃቸው ልጆች ወለዱ። ለዚያውም አራት ከሰይጣን የተፈለፈሉ ልጆች! ከመፀነሳቸው ጀምሮ ክፉ የሆኑ ዘሮች:"

👍21🤔3🥰2
አባታችን በፍቅርና በእርጋታ ይይዘው የነበረው በሰውነቱ ላይ የነበሩትን አሳዛኝ ጠባሳዎች በማስታወስ አይኖቼ አበጡ: ማን ወይም ምን ስለመሆኔ
እርግጠኛ ያለመሆን ሽብር ውስጤን አመሰው እግዚአብሔር በፍቃድና በመባረክ እንዲወለዱ ካደረጋቸው ጋር በዚህ ምድር መኖር ይኖርብኝ እንደሆነ አላውቅኩም: አባታችንን፣ ቤታችንን፣ ጓደኞቻችንንና ንብረቶቻችንን አጥተናል፡ ከዚያ ምሽት በኋላ እግዚአብሔር ትክክለኛ ዳኛ ነው ብዬ
አላምንም: ለማንኛውም እግዚአብሔርንም አጣሁት።
ብዙ ነገር ከእኛ በጭካኔ የወሰደችብንን ያቺን አሮጊት ሴት በእጆቼ በመግረፍ መልሼ ላጠቃት ፈለግኩ። በእናቴ ጀርባ ላይ ያለውን ደም የያዙ ግርፋቶች
አተኩሬ ስመለከት ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ጥላቻ ወይም ንዴት ተሰምቶኝ አያውቅም የጠላኋት እናታችንን ስላደረገቻት ነገር ብቻ አይደለም ከዚያ ክፉ አፏ ስለሚወጡት አስቀያሚ ቃላቶች ጭምር እንጂ።
ቀጥላ ወደኔ ተመለከተች ያቺ አስቀያሚ አሮጊት የተሰማኝን ያወቀች ትመስል ነበር፡ ከዚች ቅፅበት ጀምሮ ከእሷ ጋርም ሆነ ምድር ቤት ከተኛው ሽማግሌ
ጋር ያለኝን የደም ዝምድናና እንዴት እንደካድኩት ማየት እንድትችል ተስፋ በማድረግ በድፍረት አፍጥጬ ተመለከትኳት፡ ከእንግዲህ አላዝንላትም!
ምናልባት አይኖቼ የያዝኩትን በቀል እያሽከረከሩ የሚያሳዩ መስተዋቶች ሳይሆኑ አይቀሩም: እና አንድ ቀን እንደማለቃቸው ማልኩ፡ ምናልባት የሆነ
የመበቀል ስሜት ሳታይ አልቀረችም፤ ምክንያቱም የሚቀጥሉት ቃላቶቿ
ለእኔ የተሰነዘሩ ነበሩ: “ልጆች” የሚለውን ቃል ነበር የምታመጣው፡
“አያታችሁ ልጆች ይህ ቤት ለማይታዘዙና ህግ ለሚጥሱ ከባድና ምህረት የለሽ ሊሆን ይችላል: ምግብ፣ መጠጥና መጠለያ እንሰጣለን፡ ነገር ግን
ደግነት፣ ሀዘኔታ፣ ወይም ፍቅር በጭራሽ አንሰጥም! ስነ ምግባራዊ ያልሆነን ነገር ከመፀየፍ በስተቀር ምንም ነገር ሊሰማን አይችልም ህጌን ጠብቁ… አለንጋዬን አትቀምሷትም ከምግብና ከመጠጥ
አትከለከሉም እኔን ላለመታዘዝ ከደፈራችሁ ወዲያውኑ ምን ላደርግ እንደምችልና ምን ልከለክላችሁ እንደምችል ትማራላችሁ፡" ሁላችንንም ተራ
በተራ አተኩራ ተመለከተች:
አዎ በዚያ ምሽት ልጆች የዋሆች፣ ሁሉን የምናምን፣ የመኖርን ጣፋጭ ጎኑን ብቻ የምናውቅ መሆናችንን ልትወስድብን ፈልጋለች፤ ነፍሳችን ልታጠወልግና
ትንሽና ደረቅ ልታደርገን… ምናልባትም እንደገና በራሳችን ኩራት እንዳይሰማን
ለማድረግ ፈልጋለች።
ግን አላወቀችንም!
ማንም እናቴን ወይም አባቴን እንድጠላ ሊያደርገኝ አይችልም! ማንም በእኔ ላይ የህይወትና የሞት አይነት ስልጣን ሊኖረው አይችልም: ለዚያውም
በህይወት እያለሁና አሁንም መልሼ መታገል እየቻልኩ!
ክሪስን በአይኖቼ ገረፍ አደረግኩት እሱም አያትየው ላይ አፍጥጦ ነበር።
ሊያጠቃት በምክር ምን አይነት ጉዳት ሊያደርስባት እንደሚችል ለመገመት ይመስል አይኖቹ በቁመቷ ወደ ላይና ወደ ታች አሉ፡ ይሁንና ገና አስራ አራት አመቱ በመሆኑ እንደሷ አይነቶቹን ለማሸነፍ ወደ ትልቅ ሰውነት
ማደግ አለበት አሁንም እጆቹ ቡጢ ጨብጠው በጎንና ጎኑ ቀጥ ብለዋል።
በመገደቡ ከንፈሮቹን ጥብቅ አድርጎ ገጥሞ ልክ እንደ አያታችን ከንፈሮች መስመር አስመስሏቸዋል። አይኖቹ ብቻ እንደ ሰማያዊ በረዶ የጠነከሩ ቀዝቃዛ ሆነዋል።
ከሁላችንም በበለጠ እናታችንን ይወዳታል። መልካምነቷን፣ ልባዊነቷን፣ እንዲሁም በህይወት ካሉ ሴቶች ሁሉ እጅግ ማመዛዘን የምትችል መሆኗን ከግምት በማስገባት ለእሱ የፍፁምነት መለኪያ ናት፡ ሲያድግ የሚያገባው እንደ እናታችን ያለች ሴት እንደሆነች ነግሮኝ ያውቃል: ሆኖም ማድረግ የቻለው በከረረ ቁጣ ማፍጠጥ ብቻ ነው የሆነ ነገር ለማድረግ በጣም ልጅ
ነበር።
አያታችን አንድ የመጨረሻ ረጅም የንቀት እይታ ሰጠችንና የበሩን ቁልፍ እናታችን እጅ ላይ አስቀምጣ ወጣች ከሁሉም ነገር በላይ አንድ ጥያቄ ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ ይታያል። ለምን?
ለምንድነው እዚህ ቤት የመጣነው? ይህ ደህንነቱ የተጠበቀ መጠለያ፣ መደበቂያ፣ ወይም የስደተኞች ማቆያ ቦታ
አይደለም እናታችን ይህ ሁሉ እንደሚሆን በእርግጠኝነት ታውቅ ነበር።
ይህንን እያወቀች ነው በዚያ ምሽት ወደዚህ የመራችን፡ ለምን?...
✨ይቀጥላል✨

👍26❤4
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሎርድ ማውንት እስቨርንና ባለቤቱ ወይዘሮ ኤማ ከለንዶን ወደ ካሰል ማርሊንግ ሲመለሱ ሳቤላ ቬን ከአዲሱ መኖሪያዋ ከመጣች ዐሥር ቀን ሆኗት ነበር ።ካስል ማርሊንግ የከተማ እንጂ የግንብ ስም እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል የሬይሞንድ ቬን አዲሱ የማውንት እስቨርን ኧርል መኖሪያ ከካስል ማርሊንግ ከተማ አጠገብ ነበር ደርሰውም ሎርድ ማውንት እስቨርን በደስታ †ቀብሎ ሲያነጋግራት የማውንት እስቨርኗ ወይዘሮ ግን እንደ ዐመሏ በንቀትና በኩራት ገጽታ አየቻት የሳቤላ ጉንጮችም ደም መሰሉ ። እያደርም በዚህ ዐይነት የተጀመረው ግንኙነት የሚያበሳጩ የንቀት ንግግሮች የሚያበግኑ ጥቃቅን ድርጊቶች እየተጠራቀሙ ትዕግሥቷን እስከ መጨረሻ ተፈታተኑት " ብቻዋን በምትሆንበት ጊዜ እጆቿን እያፋተገች ወዴትና እንዴት አድርጋ ሌላ መጠጊያ እንደምታገኝ ታወጣና ታወርድ ጀመር።
ኤማ ቬን እየተደነቀችና እየተወደሰች መኖር ትወድ ስለነበር ይኸንኑ ፍላጐቷን የሚያራግቡላትንና የሚያረኩሳትን በዙሪያዋ ሰብሰባ ስትቃበጥና ስትዳራ ለሰውነቷና ለመልካም ስሟ በመጠበብ ረገድ ግድ አልራትም " ድርጊቷና ጠባይዋ
ሁሉ እሷን ከምታህል አገር ያወቃትና ክብር ያላት ወይዘሮ የሚጠበቅ አልነበረም።
የራስ ወዳድነትና የምቀኝነት ምንጭ ነበረች መልከ ቀና ልጅ እግር ሴት እቤቷ ጠርታ አታውቅም " ይኸን ከማድረግስ ክፉ ገላ የያዘውን ወንድ ብትጋብዝ
ትመርጥ ነበር ።
ሳቤላ ቬንም ያንን የመሰለ መልክና ለጋነት ይዛ ለዘለቄታ አብራት ለመኖር መምጣቷን ገና ስትሰማ ያናደዳት ይኸው ዐመሏ ነበር " በገና በዓል እንግዶች መጡባቸወ ከነሱም አብዛኞቹ ወጣት ወንዶች ነበሩ " እነዚያ ሰዎች ስለሚፈጠረው
ስሜት ሳያስቡ አፋቸው እንዳመጣቸው ማን አህሎኝ ከምትለው የቤቱ እመቤት
ይልቅ ወጣቷ ቆንጆ በጣም እንደምትበልጥ ሲናገሩ ባለቤቲቱ ሰማች ። ሕሊናዋን ለመሳት እስክትቃረብ ድረስ ተናደደች ከንዴቷ በስተቀር ሌላውን ሥነ ምግባር ጨርሳ ረሳችው ሳቤላን ለብቻዋ ጠርታ የተጠላች ቀላዋጭ ሳትፈለግ የመጣችባት መሆኗን ነገረቻት " ወትሮውንም ተግዳ እንጂ ወዳ እንዳላስገባቻት እየነገረች ሙልጭ አድርጋ ሰደበቻት " ኧርሉና ባለቤቱ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩዋቸው : አንዱ የብዙ ጊዜ ታማሚ ስለነበር በየካቲት ሞተ ። ፋሲካ እንደዋለ
ወደ ለንደን በመሔድ የነበራቸው ዕቅድም በኀዘኑ ምክንያት ተለውጦ ወደ ግንቦት ተሳበ ሬይሞንድ ቬን በልጁ ሞት ከእናቲቱ የበለጠ አዝኖ ነበር ። ጊዜውን ከፊሉን በዚያን ጊዜ በመታደስ ላይ የነበረውን የማውንት እስቨርንን ዕድሳት በመቆጣጠር ካሳለፈው በኋላ በመጋቢት ወደ ፓሪስ ሔደ ።
ፋሲካ ሚያዝያ ውስጥ ዋለ ። እመቤቲቱ ወደ ለንደን ለመሔድ ተዘጋጅታ ቀን ስትቆጥር አያቷ ሚስዝ ሌቪዞን ፋሲካን አብራት ለመዋል ወደ ካስል ማርሊንግ
እንደምትመጣ ጻፈችላት " አንጀቷ እርር አለ ። እንድትቀር ገልጻ አትጽፍላት ችግር ሆነባት " ባልቴቷን እንዳትመጣባት ለማድረግ በገንዘብ የሚለወጥ ነገር ቢሆን ኖሮ አይከፍሉ ከፍላ ታስቀራት ነበር ነገር ግን የማይሆን ነገር ሆነና ሚስዝ ሌቪ
ዞን ፍራንሲዝ ሌቪዞንን ብቻ አስከትላ የሕማማት ሰኞ ካስል ማርሊንግ ገባች "
ነገሩ ተከድኖ እበሰለ ላይ ላዩ ሰላም እየመስለ እስከ ዓርብ ስቅለት በደህና ሰነበቱ » ካፒቴን ሌቪሰን ዐይኑን ሳቤላ ላይ ጣለ "
የማውንት እስቨርን እመቤት
የካፒቴኑን አዝማሚያ እያየች ልታብድ ተቃረበች በቅናት ተቃጠለች " በፊት መጥቶ የነበረ ጊዜም ሳቤላ ልቡን እንደ ማረከችው አይታ ልታብድ ነበር" ያሁኑ ደግሞ በጣም ባሰ። ይህ Oይኖቹን በሳቤላ ይ የጣለው ስው ፍሬንሲዝ ቪን ባይ ሆን ኖሮ ! ለእመቤት ሳቤላ ከእሱ በቀር ዓለሙ ሁሉ ቢስግድላትና ቢረግፍላት ሚስዝ ቬን ደስታን አትችለወም ነበር።
ምክንያቱም ወጣቱ መኮንን ምንም እንኳን ያክስቷ ልጅ ቢሆንም ክፉኛ ከልቧ ገብቶ ነበር እንዲያውም ሴትዮዋ ገመናዋን ለመሸፈን ባትጠነቀቅ ኖሮ ውርደት
ላይ ትወድቅ ነበር ።
ዓርብ የስቅለት ዕለት ከሰዓት በኋላ ሳቤላ ሕፃኑን ዊልያም ቬንን ይዛ በእግሯ ለመንሽርሸር ወጣች " ካግቴን ሌቪሰንም ከነሱ ጋር ተጨመረና አብሮ ሔደ የራት
ሰዓት ሊደርስ ጥቂት ሲቀረው ተመለሱ ሚስዝ ቬን አያቷን ሚሲስ ሌቪሰንን ከቤት ጥላ ከነሱ ጋር መወት ባለመቻሏ በንዴት ስታር ስትተክን አመሸች ሦስቱም ተያይዘው እንደግቡ የራት ሰዓት ደርሶ ስለ ነበር ሳቤላ ልብስ ለመቀየር ቀጥታ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች ልብሷን አውልቃ የመቆያ ቀሚሷን አጥልቃ ተቀመጠችና ማርቨል ጸጉሯን ስትሠራላት ዊሌም መጣ ከጉልበቷ ተደግፎ ሲለፈልፍ መዝጊያው ድንገት ብርግድ ብሎ ተከፈተ እመቤቲቴ ጥልቅ አለች።
ጀየት ነበርሽ ? ” አለቻት በቁጣ እየተንቀጠቀጠች "
ሳቤላ ምልክቱ ገባት።
“ በመስኩና በቁጥቋጦቹ ስንንሸረሸር ቆይተን መጣን " "
· እንዴት ራስሽን እንደዚሀ ከመሰለ ውርደት ትጥያለሽ ? ”
“ የምትይው አልገባኝም ” አለቻት እሷም የልቧ ምት እየጨመረ
“ተይ እንጂ" ቀስ በይ ማርቨል ጸጉሬን እኮ ነጨሺኝ " አለቻት "
“ ከቤቴ መጠጊያ ማግኘትሽ አነሰና ታስደፍሪው ? ሦስት ሰዓት ሙሉ ፍራንሲዝ ሌቪሰን ጋር ተያይዘሽ እንደዚህ ትጠፊያለሽ?ከመጣሽ ጀምሮ ከሱ ጋር ከመዳራት በቀር ምንም ነገር አልሠራሽም ። የገና ጊዜ እንዶሁ ከሱ ጋር እንደ ተቃበጥሽ እንደተዳራሽ አሳለፍሽው "
ዘለፋ ከዚህ የበዛ ቢሆንም ፍሬ ነገሩ ይኸው ነበር " ሳቤላም ከሰዳቢዋ ያላነሰ ንዴት ተናነቃት በተለይም እሷን ሳቤላ ቬንን የታላቁ መኮንን የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ ባባትም ከኤማ ማወንት እስቨርን የምትበልጠን ከገዛ ገረዴ ከማርቨል ፊት ስለ ሰደበቻት ይቅርታ የሌለው ድፍረት አድርጋ ቆጠረችውና ነገሩ
ጥቂት በሐሳቧ ካገላበጠችው በኋላ ራሷን ስትሠራላት ከነበረችው መንጭቃ ብድግ
አለችና ከቤቱ እመቤት ጋር ተፋጠጠች "
ባለቤቲቱ የንዴቷን ያሀል ስትንጨረጨር ድምጿን ገትታ በትዕግሥትና በዕርጋታ
ስትሰማት ቆየችና “ እኔ አልዳራም ” አለቻት “ተዳርቸም አላውቅም። እንደዚህ ያለውን ሥራ ከባለትዳች ይልቅ ያላገቡ ሴቶች ቢፈጽሙት ጥፋቱ ቀለል ሊል ሊችል ቢመስልም እኔ ለእነሱ ትቸዋለሁ እኔ ከዚህ ከመጣሁ ጀምሮ ሁልጊዜ ስትዳራ የማያት አንዲት ሴት ብቻ ናት " እሷም እኔ ሳልሆን አንቺ ነሽ " '
ኤማ ቬን ፊቷ ልውጥውጥ አለ " የምታደርገው የምትሆነው ጠፋት በእጅዋ አንድ ጊዜ በጥፊ ጉንጯ ላይ አጮለቻት " ድንጋጤዋ ሲለቃት በግራ እጅዋ መታቻት " ሳቤላ እርር ብላ ጮኸችና ራሷን ስትሠራበት ከነበረው ወንበር ላይ ጥቅልል አለች ማርቨል ደነገጠችና እጅዋን ወደላይ ዘረጋች ዊልያምም ሳቤላ ስለተመታች አለቀሰ " ራሱ ተገርፎ ቢሆን ኖሮም ከዚያ የበለጠ አያለቅስም ነበር "
ወይዘሮ ማወንት እስቨርን ልጅዋን በቡጢ አንድ ጊዜ አፍንጫው ላይ ካለችው በኋላ አንገቱን ይዛ ወዶ ውጭ ገፈተረችው " እሷም ወጥታ ሔዶች ሳቤላ ሌሊቱን ሙሉ እንዳለቀሰች አደረች " ከዚያ ቤት ለመኖር አልቻለችም "በዚህ ጭካኔ ሌላ ሰውም ቢሆን ሊኖር አይችልም ግን የት ትድረስ ? እስኪነጋ ድረስ ሙታ ብታርፍና ከአባቷ ጐን ብትቀበር ብዙ ጊዜ ተመኘች መንፈሷ ሲረጋጋ

ግን ማንም ልጅነትና ጤንነት ያለ ሁሉ እንደሚያደርገው የሞትን ነገር ስታስበው ዘገነናት ብዙ ሐሳቦች በአእምሮዋ ተመላለሱባት ወደ ፈረንሳይ ተሻግራ ችግሯን ለእርሱ ዘርዝራ ተናግራ ከአሮጊቷ ከሚስዝ ሌቪዞን ወይም ያባቷ ቤት ጠባቂ የነበረችውን ሚስዝ ሜዞንን ከደረሰችበት ፈልጋ እሷ ዘንድ ለመቀመጥ ልትጠይቀው
አሰበች " ሲነጋ ያ ሁሉ አማራጭ ሐሳብ ቀረ እሷ ካፒቴን ሌቪዞን ጋር አልተዳራችም ነገር ግን የሰጣትን ትኩረትና ያደርገው የነበረውን ክትትል ይገልጽላት
የነበረውን አድናቆት ትቀበለው ስለነበር ልቧ ወደ ፍቅሩ ያዘነበለ መሰለ!ሴት ደግሞ ከወደደችው ሰው ጋር አትዳራም "
ሌሊቱን አንዳዘነች ' እንዳሰበች እንደ ተናደደች ስለ አደረች ጧት ድቅቅ ብላ ደክማ ነበር ማርቨል ቁርሷን አመጣችላት » ዊልያም ቬን ትንሽ ቆየት ብሎ ተሸሽጎ ወደ ሳቤላ ክፍል መጣ እሷን በጣም ይቀርባትና ይወዳት ነበር።
“ እማማ ወደ ውጭ እየሔደች ነው እያት .... ሳቤላ ” አላት "
በመስኮት በኩል ስትመለከት ወይዘሮ ማወንት እስቨርን በሠረገላ ተሳፍራ ፍራንሲዝ ሌቪሰን እየነዳ ሲሔዱ አየቻቸው
“ አሁን ማንም ስለሌለ ከታች መውረድ እንችላለን ” አላት "
አሳቡን ተቀብላ ከፎቅ ወረዱና ከሳሎን እንደ ደረሱ አንድ አሽከር አንድ ካርድ በማቅረቢያ ላይ አድርጎ አመጣና ሰጣት ።
“ አንድ አንቺን የሚጠይቅ ሰው መጥቷል ... እመቤት ” አላት "
“ እኔን ነው ወይንስ ወይዘሮ ማውንት ስቨርንን "
“ አንቺን ነው የጠየቀ "
ካርዱን አንሥታ ስታየው “ ሚስተር ካርላይል ” ሲል የደስታ ድንጋጤ ደነገጠችና ' ' አስገባው ” አለችው
ሰው የሕይወትን ገመድ ሲከታተሉ በመኖር ጕዞው ላይ ከሚያጋጥሙትና ከቁም ነገር ይገባሉ ተብለው ሊታሰቡ ቀርቶ የማይጠረጠሩ አነስተኛ ነገሮች በኑሮው ዘይቤ ላይ የደስታን ወይም መከራን ማጣትን ወይም ማኘትን ለመሳሰሉ ለታላላቅ ሁኔታዎች መከሠት ምክንያት እየሆኑ ሲገኙ ብዙ ጊዜ ታይተዋል የሚስተር ካርላይል ደንበኛ የሆነ አንድ ሰው በኢንግላንድ ልዩ ልዩ ቦታዎች ሲዘዋወር ካስል
ማርሊንግ ከተማ ሲደርስ በሚያሠጋ ሁኔታ ታመመና ለኑዛዜውም ሆነ ለሌሎች
ልዩ ልዩ ሕግ ነክ ጉዳዮች ክትትል እንዲያደርግለት ሚስተር ካርይልን በቴሌግራፍ እንዲጠሩለት ስለጠየቀ ጥሪው ተላለፊለት ሚስተር ካርላይልም ጥሪ እንዶ ደረሰው ወዲያው መጣ " እንደዚህ የመስለ ያልተጠበቀ ጉዞ ለሚስተር ካርላይል የተለመደ ተራ ነገር ነበር
ሚስተር ካርይል ሲገባ ሳቤላ ደስታው ከፊቷ እየፈለቀ ወደሱ ተንደርድራ በመሄድ እንዴት ያልታሰበ አጋጣሚ ነው ሳይህ አንዴት ደስ አለኝ መስለህ
አለችው።
"ለአንድ ሥራ ትናንት ወደ ካስል ማርሊንግ መጣሁና አሁን ሳላይሽ አልሔድም ብዬ ብቅ ማለቴ ነው ሎርድ ማውንት እስቨርን ባገር አለመኖራቸውን ሰማው።
« እሱ አሁን ያለው ፈረሳንይ ነዉ ዳግመኛ እንደምንገናኝ አርግጠኛ
ነበርኩ እኮ ታስታውሳለህ ... ሚስተር ካርላይል ? አንተ እንኳን .. ” ብላ ሳትጨርሰው ዝም አለች ስለ ማስታወስ ስታነሣ ለራሷ ሌላ ነገር አስታወሰች
«ራሴ ባግኘው እሰጠዋለሁ ” ብላ ያኖረችው አንድ መቶ ፓውንድ ትውስ አላት አሁን ከንዘቡ አጥፍታለታለች " የምታደርገው ጠፋት እሱም ምክንያቱ አልገባውም እንጂ ብዙ መጨነቋን ተመልክቶ ነበር
እንዴት የደስ ደስ ያለው ልጅ ነው ? ”አለ ዊልያምን እያየ
ሎርድ ቬን ነው ” አለችው ሳቤላ
ግልጽና ቀና መንፈስ ያለው ልጅ ይመስላል " ስንት ዓመትህ ነው? የኔ ጎበዝ አለው ሚስተር ካርላይል
"
“ እኔ ስድስት ዓመቴ ነው ወንድሜ ደሞ አራት ዓመቱ ነበር ”
ሳቤላ ወደ ልጁ ጐንበስ ብላ'' ይህን ሰውዬ እውቀው . . .ዊልያም " ሚስተር
ካርላይል ይባላል " ለኔ በጣም ደግ ሰው ነው ” አለችው ።
ለሷ ደግ ሰው ከሆኑ እኔም እወደዎታለሁ " እውነት እርስዎ ደግ ነዎት ? አለው ዊልያም ሚስተር ካርላይልን አሻቅቦ እያየ
“ በጣም ነው የሚያዝንልኝ . . ዊልያም " አለችውና ወደ ሚስተር ካርላይል ቀና ብላ እያየችው
እ . . . የምለውም ጠፋኝ ግን ላመሰግንህ ይገባኛል " ሐሳቤ
እንኳን ” ብላ ዝም ስትል ልትናገረ የፌለገችው ነገር ሲምታታባት አይቶ ፈገግ ብሎ በይ ተይው ” አላት " ከዚያ ሌላ ርዕስ አመጣ
“ ከዓሣዎችሽ ሁለቱ ሞቱ " ውርጩ ግደላቸው " በጥር ወር የነበረ ክፉ ውርጭ ትዝ ይልሻል ? ያን ጊዜ ነው ያለቁት " "
“ ቢሆንም አንተ ማድረግ የምትችለወን ያህል አድርገሃልና አመሰግናለሁ "
ለመሆኑ ኤስትሊን ምን መስሏል ? ሰው ገባበት ? አዬ ኤስትሊን ! ”
አለች በናፍቆት አነጋገር
“ የለም አልገባበትም ገና እያሳደስኩት ነው „ ”
በሚስተር ካርላይል መምጣት የተሰማት ድንገተኛ ደስታ አፍላው ዐለፈ እንደገና ያለችበትን ሁኔታ አስታወሰችና ማዘን መተከዙ ተመለሰባት እሱም ፊቷ
ሲለዋወጥ ተመለከተ ።
“ እኔ መቸም ካስል ማርሊንግ ተቀምጬ ኤስትሊን እንደ ነበርኩበት ጊዜ ይመቸኛል ብዬ አልጠብቅም ” አለችው "
“ ቢሆንም እንዶማይከፋሽና የደስታ ቤት እንደ ሆነልሽ አምናለሁ
ቀና አለችና እስከ መቸም ከልቡ በማይጠፋ አመለካከት አየችው " እሱም የተስፋ መቁረጥ አስተያየት መሆኑ ቶሎ ገባው "..

👍19
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
የእናታችን ታሪክ
ከአያታችን መሄድ በኋላ ከማዘንና ከመበሳጨት ውጪ ምን ማድረግ ወይም ምን ማለት ወይም ምን ሊሰማን እንደሚገባ አልገባንም እናታችን ሹራቧን መልሳ ስትለብስ ስመለከታት ልቤ በውስጤ ተርገበገበ፡ ሹራቧን ቀሚሷ
ውስጥ እየወሸቀች ወደ እኛ ዞራ ደህና እንደሚሆን ለማረጋገጫ ለሁላችንም ደስ የሚል ፈገግታ አሳየችን እንደዚያ ካለው ፈገግታ ውስጥ የሆነ ነገር መጨበጥ አለመቻሌ ያሳዝናል፡ ክሪስ አይኖቹን ወለሉ ላይ ተክሎ የተነጠፈው አሮጌ ምንጣፍ ላይ ያሉትን ዲዛይኖች በጫማው በመከተል ገና ያልተረጋጋ
ቁጣውን እየገለፀ ነው።
“አሁን ተመልከቱ አለች እናታችን በውሸት ደስታ። “ብዙምኮ አያምም። ከስጋዬ ይልቅ የተሰቃየው ክብሬ ነው እንደ ባሪያ ወይም እንደ እንስሳ መገረፍ በጣም የሚያሳፍር ነገር ነው በተለይ ደግሞ በራስህ ወላጆች።
ግን እንደዚህ አይነት ግርፊያ እንደገና ይኖራል ብላችሁ አትጨነቁ። በቃ አንድ ጊዜ ብቻ ነው: ከአባታችሁና ከእናንተ ጋር የኖርኳቸውን አይነት በደስታ የተሞሉ ተጨማሪ አስራ አምስት አመታት ለመኖር ብችል የዚህን
ግርፊያ መቶ እጥፍ እንኳን እቋቋማለሁ ነፍሴን ቢያሸማቅቃትም ያደረጉኝን
እንዳሳያችሁ አደረጉኝ...” አልጋ ላይ ተቀመጠችና ተጠግተን እንድናቅፋት እጆቿን ዘረጋችልን ሁላችንም ወደሷ ሄደን ተጠመጠምንባት እኔ ግን
ሳቅፋት እንዳላሳምማት እየተጠነቀቅኩ ነበር። መንትዮቹን ብድግ አድርጋ ጭኖቿ ላይ አስቀመጠችና ለእኛ አልጋውን መታ መታ እያደረገች አልጋው
ላይ እንድንቀመጥ ነገረችን፡ ከዚያ መናገር ጀመረች: ልትናገር የፈለገችው ነገር ለእሷ ከባድ ቢሆንም፣ እኛም ለመስማት የዚያኑ ያህል ከባድ ሆኖብን
ነበር።
“በጥንቃቄ እንድታዳምጡኝና አሁን የምነግራችሁን ነገሮች እድሜያችሁን ሙሉ እንድታስታውሷቸው እፈልጋለሁ" መናገሯን ቆም አድርጋ ግድግዳዎቹ ወደ ውጪ ያሳዩ ይመስል እና በእነሱ ውስጥ የዚህን ግዙፍ ቤት ሌሎች
ክፍሎች የምታይ ይመስል ግድግዳው ላይ አፍጥጣ ቆየችና “ይሄ እንግዳ የሆነ ቤት ነው: በውስጡ የሚኖሩት ሰዎች ግን፣ እንግዶችም ሠራተኞችም
ሳይሆኑ ወላጆቼ ናቸው- አያቶቻችሁ አክራሪ ሀይማኖተኞች ስለመሆናቸው ላስጠነቅቃችሁ ይገባ ነበር በእግዚአብሔር ማመን ጥሩና ትክክል ነገር ነው፡ ነገር ግን እምነታችሁን ከብሉይ ኪዳን ላይ የምትፈልጓቸውን ቃላት
ብቻ በመውሰድ የምታጠነክሩ ከሆነና የእናንተን ፍላጎት በሚያሟላ መንገድ የምትተረጉሙት ከሆነ፣ ያ ግብዝነት ነው፡ እና ወላጆቼም ልክ እንደዚያ ናቸው።
“አባቴ እየሞተ ነው፡ ነገር ግን ሁልጊዜ እሁድ እሁድ ተሸክመው ወደ ቤተክርስቲያን ይወስዱታል ሻል ካለው በዊልቸር ላይ፣ ከባሰበት ደግሞ ቃሬዛ ላይ አጋድመው ይወስዱትና የሚፈለግበትን አስር በመቶ አስራቱን ከአመት ገቢው ላይ ይሰጣል።
“ቤተክርስቲያኗን ለማሰራት ገንዘብ ሰጥቷል፤ መስኮቶችን ሁሉ ያስገጠመው ራሱ ነው: ቤተክርስቲያኗንና አገልግሎቱን ሁሉ ተቆጣጥሯል። በዚህም
የመንግስተ ሰማያት መንገዱ በወርቅ ላይ እንደሚሆን አረጋግጧል አባቴ በእርግጠኝነት ለቅዱስ ጴጥሮስ ጉቦ በመስጠት መንግስተ ሰማያት መግባት
እንደሚችል ያስባል። በዚያ ቤተክርስቲያን እሱ ራሱ እንደ አምላክ ወይም እንደ ቅዱስ ይታያል እናም ከቤተክርስትያን መልስ ወደ ቤቱ ሲመጣ፣
የሚፈልገውን ለማድረግ ሙሉ በሙሉ ፈቃድ እንዳለው ያስባል ምክንያቱም እዚያ የሚጠበቅበትን ሰርቶ ጨርሷል፡ በራሱ መንገድ ከፍሏል፤ ስለዚህ ከገሀነም ድኗል።
“ከሁለት ታላላቅ ወንድሞቼ ጋር ስናድግ ቤተክርስቲያን እንድንሄድ እንገደድ ነበር፡ ከአልጋ የማያስነሳ በሽታ ቢያመንም እንኳን መሄድ ነበረብን ኃይማኖት ኑሯችንን አንቆ ይዞት ነበር። መልካም ሁኑ፣ መልካም ሁኑ፣ መልካም ሁኑ፣ ሁልጊዜ የምንሰማው ይህንን ነበር ሁልጊዜም ሌሎች ሰዎች
አድርገውት የሚደሰቱበት ነገር ሁሉ እኛ ጋ ሲደርስ ኃጢአት ይሆናል። ወንድሞቼና እኔ ዋና መሄድ አይፈቀድልንም ነበር ምክንያቱ ደግሞ ዋና
መዋኘት ማለት የዋና ልብስ በመልበስ አብዛኛውን የሰውነታችንን ክፍል ለእይታ ማጋለጥ ስለሆነ ነበር። ካርታ መጫወትም ሆነ ሌሎች ቁማርን
የሚያመለክቱ ጨዋታዎችን መጫወት የተከለከለ ነበር: ወደ ዳንስ ቦታዎች መሄድ አይፈቅድልንም:: ምክንያቱ ደግሞ ምናልባት ሰውነታችን ከተቃራኒ ፆታ ሰውነት ጋር ሊነካካ ስለሚችል ሀሳቦቻችንን እንድንቆጣጠርና ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት እንዳናስብ መጠንቀቅ ነበረብን፡ የኃጢአት ሀሳቦች እንደ ድርጊቶቹ
ሁሉ ክፉ ናቸው እንባል ነበር እንዳናደርጋቸው ስለምንከላከላቸው ነገሮች
ብዙ መቀጠል እችላለሁ በአጠቃላይ አስደሳችና አስገራሚ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ለእነርሱ ኃጢአት ይመስሉ ነበር ህይወት በጣም ስርዓት የበዛበት ሲሆን
ልጆች የተከለከሉትን ነገሮች ለማድረግ የበለጠ ፍላጎት እንዲያድርባቸውና እንዲያምፁ የሚያደርጋቸው የሆነ ነገር አለ ወላጆቻችን ሶስቱን ልጆቻቸውን
እንደ መልአክትና ቅዱሳን አድርገው ለማሳደግ ቢፈልጉም፣ የተሳካላቸው መጥፎ ሆነን እንድናድግ ማድረግ ብቻ ነው::"
አይኖቼ ፈጠው አፌ እንደተለጎመ ተቀመጥኩ፡ ሁላችንም እንደዚያ ሆነን ነበር መንትዮቹ ሳይቀር: “ከዚያ አንድ ቀን…” እናታችን ቀጠለች በዚህ ሁሉ መሀከል አንድ ቆንጆ ወጣት ከእኛ ጋር ሊኖር መጣ፡ አባቱ አያቴ ነበር። የሞተውም ይህ ወጣት ገና የሶስት ዓመት ልጅ ሳለ ነበር። የእናቱ ስም አሊሺያ ሲሆን፣ የአምሳ አምስት አመት ዕድሜ የነበረውን አያቴን ስታገባ ገና
አስራ ስድስት አመቷ ነበር፡ አሊሽያ በልጅነቷ ነው የሞተችው: የአያቴ ስም ጋርላንድ ክሪስቶፈር ፎክስወርዝ ነበር፡ እና እሱ ሲሞት ግማሽ ሀብቱ የሶስት አመት እድሜ ወደ ነበረው ወደ ትንሹ ልጅ ሄደ ነገር ግን አባቴ ማልኮልም ራሱን በሞግዚትነት ሰይሞ የአባትየውን ንብረት ሁሉ መቆጣጠር ቻለ።በእርግጥም የሶስት አመት ህፃን በጉዳዩ ላይ ድምፅ አልነበረውም እናቱም
እንድትደግፍ አልተደረገችም:
“አባቴ አንድ ጊዜ ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኋላ አሊሺያንና ትንሹን ልጅ አስወጥቶ አባረራቸው: የአሊሺያ ወላጆች ወደሚኖሩበት ሪችመንድ ሄዱና
ለሁለተኛ ጊዜ እስክታገባ ድረስ እዚያ ተቀመጡ። ከልጅነቷ ጀምሮ ትወደው ከነበረ ሰው ጋር ለተወሰነ አመት በደስታ ኖረችና እሱም ሞተ። ሁለት ጊዜ አገባች ሁለት ጊዜም ባሎቿ ሞቱባት አሁን ወላጆቿም ሞተው ስለነበር
ከትንሹ ልጇ ጋር ብቻዋን ቀረች: ከጥቂት ዓመታት በኋላ እሷም በካንሰር ሞተች፡ የዚያን ጊዜ ነው ልጇ ጋርላንድ ክሪስቶፈር ፎክስርወርዝ አራተኛ እዚህ ሊኖር የመጣው: ክሪስ ብለን ነበር የምንጠራው…” አመነታች ከዚያ
ክሪስና እኔን በክንዶቿ ጠበቅ አደረገችን፡ “…ስለማን እያወራሁ እንደሆነ አውቃችኋል? ያ ወጣት ልጅ ማን እንደሆነ ገመታችሁ?”
ተንቀጠቀጥኩ ሚስጥራዊው አጎት እና በሹክሹክታ “አባዬ የምታወሪው ስለ አባዬ ነው:” አልኩ
“አዎ” አለች። ከዚያ በከባዱ ተነፈሰች።
ትልቅ ወንድሜን ለማየት ወደፊት ሳብ አልኩ። አይኖቹ መስታወት መስለው ፊቱ ላይ መገረም እየተነበበ በፀጥታ ተቀምጧል።

👍33👏3❤1
እናታችን ቀጠለች: “… አባታችሁ አጎቴ ነበር። ከእኔ በሶስት አመት ብቻ ነበር የሚበልጠው በመጀመሪያ ጊዜ ሳየው አስታውሳለሁ። አይቼውም ሆነ
ስለሱ ሰምቼ የማላውቀው ይህ ወጣት አጎቴ እንደሚመጣ ሳውቅ፣ ቆንጆ ሆኜ መታየት ፈልጌ ነበር ስለዚህ ቀኑን ሙሉ ፀጉሬን ስጠቀልል፣ ስታጠብና ራሴን ሳዘጋጅ ቆየሁና በጣም የሚያምር ነው ብዬ ያሰብኩትን ቀሚስ ለበስኩ::አስራ አራት አመቴ ነበር አንዲት ሴት በወንዶች ላይ ያላት ኃይል ሊሰማት የሚጀምርበት እድሜ ነው፡ በብዙ ወንዶች ቆንጆ የምባል አይነት እንደሆንኩ
አውቅ ነበር።
“አባታችሁ አስራ ሰባት አመቱ ነበር፡ የፀደይ ማብቂያ አካባቢ ነበር። ያረጁ ጫማዎቹ አጠገብ ሁለት ሻንጣዎቹን አስቀምጦ አዳራሹ መሀል ቆሞ ነበር።
ልብሶቹ ያጠሩና ያለቁ የሚመስሉ ነበሩ እናቴና አባቴ አብረውት ነበሩ።እሱ ግን ባላቸው ሀብት ተገርሞ ፊቱን እያዟዟረ እያንዳንዱን ነገር በትኩረት
ይመለከት ነበር እኔ ራሴ በዙሪያዬ ላለ ነገር ምንም ትኩረት አልነበረኝም። የምፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ ያሉት እዚያው ክፍል ስለነበር አግብቼ ያለ ሀብት
መኖር እስክጀምር ድረስ ልዩ በሆነ ቤት ውስጥ ማደጌን አላስተዋልኩም ነበ።
“አያችሁ አባቴ ለየት ያለ የጥበብ ስራ የመሰለውን ነገር ሁሉ ይገዛ ነበር። ጥበብ አድናቂ ስለሆነ ሳይሆን ዕቃ እንዲኖረው ስለሚፈልግ ብቻ ነው። ሁሉንም ነገር የራሱ ማድረግ ይፈልግ ነበር በተለይ ቆንጆ ቆንጆ ነገሮችን፡
እኔም ከሚሰበስባቸው የጥበብ እቃዎች አንዷ እንደሆንኩ አስብ ነበር ማለትም ለራሱ ሊያስቀምጠኝ የሚፈልገው: በመኖሬ ሊደሰት ሳይሆን፣ ሌሎች የእሱ በሆነው ነገር እንዳይደሰቱ ለመጠበቅ ነበር”
እናታችን ቀጠለች ፊቷ ቀልቶ አይኖቿ ባዶ ቦታ ላይ ተተከሉ። ያ ወጣት አጎቷ ወደ ህይወቷ መጥቶ እንደዚያ አይነት ልዩነት ያመጣበትን ያንን ልዩ ቀን ወደኋላ እየተመለከተች እንደነበር ግልፅ ነው “አባታችሁ ወደ እኛ ሲመጣ በጣም የዋህ፣ ሰው የሚያምን፣ ደስ የሚል፣ ታማኝ፣ ፍቅር ብቻ የሚያውቅና ደሀ ነበር አራት ክፍል ከነበራት ትንሽ ጎጆ ወደ ትልቅ ቤት መምጣቱ አይኑን እንዲከፍትና ተስፋውን ከፍ እንዲያደርግ አድርጎት ነበር። እና ዕድል በምድር ላይ ባለ ገነት ውስጥ እንደጣለችው አስቦ ነበር አባቴንና እናቴን አይኖቹ ላይ ጎልቶ በሚታይ አመስጋኝነት እየተመለከታቸው ነበር፡ እዚህ በመምጣቱ ምክንያት አመስጋኝ የመሆን ምስኪንነቱን ሳስበው አሁንም ያመኛል፡ ምክንያቱም እያያቸው ከነበሩት
ነገሮች ግማሹ የእሱ የራሱ ነበር ወላጆቼ ግን እንዳያውቅና ዝምድናውም የጠበቀ ሆኖ እንዳይሰማው የሚችሉትን ሁሉ አደረጉ።
በመስኮቶቹ የሚገባው የፀሀይ ብርሀን አርፎበት ቆሞ ነበር ወደታች በሚወርደው ደረጃ ግማሽ ላይ ቆሞ አየሁት ወርቃማ ፀጉሩ በብራማው ብርሀን ያንፀባርቃል በጣም ውብ ነበር መልከ መልካም ብቻ አልነበረም
ውብ ነበር፡ እውነተኛ ውበት ከውስጥ ወደ ውጪ የሚንፀባረቅ ነው እሱም ያ ነበረው።
“አንገቱን ቀና እንዲያደርግ ሰማያዊ አይኖቹ እንዲያበሩ የሚያደርግ ትንሽ ድምፅ አሰማሁ፡ ኦ ኦ... አይኖቹ እንዴት እንደበሩ አስታውሳለሁ እና ማን
መሆኔን ሲያውቅ ብርሀኑ ጠፋ ለካ የወንድሙ ልጅ ነኝ፡ የተከለከልኩ እና ቅር አለው እኔም እንደዚያው፡ በዚያን ቀን እኔ ደረጃው ጫፍ ላይ ሆኜ እሱ ታች ወለሉ ላይ ቆሞ በመካከላችን የተፈጠረው ብልጭታ… እያደገ እያደገ
ሄዶ ልንክደው የማንችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ።”
ክሪስ ፊቱን ለመደበቅ ሲዞርና እኔ ከአጠገቧ ፈቀቅ ስል ከብዷት “ስለፍቅር ታሪካችን በመንገር እያሳፈርኳችሁ አይደለም” አለች: “አንዳንድ ጊዜ እንደዚያ አይነት ነገር ስለሚያጋጥም፣ በመጀመሪያ የመጣ ፍቅር ብሎ መናገር ይቻላል። ምናልባት እሱም እንደኔ ፍቅር ለመያዝ ተዘጋጅቶ ይሆናል ወይም ምናልባት ሁለታችንም የሆነ ሰው እንዲያሞቀንና እንዲያፈቅረን እየፈለግን ስለነበር
ሊሆን ይችላል፡ የዚያን ጊዜ ሁለቱም ወንድሞቼ በአደጋ ሞተው ነበር።ጥቂት ጓደኞች ብቻ ነበሩኝ ለዚያውም ለማልኮም ፎክስወርዝ ልጅ ማንም
ብቁ አልነበረም ለሚያገኘኝ ለየትኛውም ሰው ሽልማትና ደስታው ነበር የምሆነው እጅግ በጣም በጣው ውድ የሆነች ሽልማት ስለዚህ አባታችሁና
እኔ አልፎ አልፎ አትክልት ቦታ ውስጥ እንገናኝና ቁጭ ብለን ለሰዓታት እናወራ ነበር፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ዥዋዥዌ ላይ እየገፋ ያጫውተኛል።ወይም እኔ እገፋዋለሁ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ዥዋዥዌው ላይ እንቆምና
በእግራችን እያንቀሳቀስነው ወደ ላይ ከፍ ስንል እርስ በርስ እንተያያለን ሚስጥሮቹን ሁሉ ነገረኝ፡ እኔም የእኔን ነገርኩት ብዙም ሳይቆይ ጥልቅ ፍቅር ውስጥ መሆናችን ይፋ ወጣ ስህተትም ቢሆን እንኳን መጋባት
እንዳለብን አመንን፡ ከዚያ ወላጆቻችን እንደሚፈልጉት የእነሱ ግልባጭ ሳያደርጉን ከዚህ ቤትና ከወላጆቻችን ሕግ ማምለጥ አለብን ብለን ተነጋገርን፡.....

👍27❤14🥰1
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
....ቀና አለችና እስከ መቸም ከልቡ በማይጠፋ አመለካከት አየችው " እሱም የተስፋ መቁረጥ አስተያየት መሆኑ ቶሎ ገባው "
“ አይደለም ” አለችው ራሷን ነቅንቃ ። “የሥቃይ ቤት ነው እኔም ከእንግዲህ ከዚህ ቤት መኖር አልችልም " ወዴት አባቴ እንደምሔድ ዛሬ ሌሊት ሳስብ
አንዳችም ብልሃት ሳላገኝ ተጎልቸ አደርኩ " እኔ በዚህ ሰፊ ዓለም አንድም ሁነኛ ሰው የለኝም "
ከልጆች ፌት ምስጢር መጫወት ተገቢ አይደለም ከሚገምቱት በላይ መስማትና ማስተዋል እንደሚችሉ ማወቁ ተገቢ ነው ትንንሽ ጋኖች ትልልቅ ጆሮዎች
አሏቸው የሚባለው አነጋገር የሚያስገርም ሐቅ ነው ሎርድ ቬን አንገቱን ቀና አድርጎ ሚስተር ካርላይልን ሽቅብ ይመለከተው ጀመር "
“ ሳቤላ “ ኮ ከኛ ቤት እወጣለሁ ብላ ዛሬ ጧት ነገረችኝ " ለምን እንደሆነ ልንገርዎት ? ትናንት ማታ እማማ ተናድዳ ስለ መታቻት ነው "
“ ዝም በል ዊልያም ” ብላ አቋረጠችው ሳቤላ „ “ ሁለት ጊዜ በጥፌ መታቻት ጉንጮ ላይ ” አለና ልጁ ነገሩን በመቀጠል “ሳቤላም አለቀሰች እኔም ጮህኩ በዚህ ጊዜ እማማ እኔንም አጮለችኝ " ልጆች ለመመታት ነዉ የተፈጠሩት ትላለች ሞግዜቴ። ሻይ ስንጠጣ ማርቨል መጥታ ለሞግዚቴ ነገረቻት እማማ ሳቤላን የምትመታት እኮ ሳቤላ በመልክ ስለምትበልጣት ...>>
ሳቤላ ፡ አፉን ይዛ አቋረጠችውና አንዲት ሠራተኛ ጠርታ ወደ ልጆች ክፍል አስወሰደችው : የሚስተር ካርላይል ዐይኖች በንዴትና በኅዘን ብርዝ አሎ „ “ እውነት ነው ? ” አላት ፊቷን ወደሱ ምልስ ስታደርግ “ እውነትም ሁነኛ ሰው ያስፈልግሻል።
ዕድሌ የጣለብኝን ዕጣ መቀበል አለብኝ ' ሲቀር ሲውል ሎርድ ማውንት እስቨርን እስኪመለስ ድረስ ”
“ ከዚያ በኋላስ ምን ትሆኛለሽ ? ''
ከዚያ በኋላ የምሆነውን ምንም አላውቅም ” አለችው ልማደኛው እንባዋ ልትቈጣጠረው ከማትችለው ፍጥነት በላይ እየገነፈለ „ “ እሱ ለኔ የሚሰጠኝ ሌላ ቤት የለውም ። እኔ ደግሞ ከወይዘሮ ማውንት እስቨርን ጋር አብሬ መኖር አልችልም "
መንፈሴን ድቅቅ አድርጋ እንደ ስበረችው ሁሉ አሁንም ልቤን ታፈሰዋለች » እኔ በሷ ይህን ያሀል መበደል የሚገባኝ ስው አልነበርኩም ... ሚስተር ካርላይል
በርግጥ አልነበርሽም ” አላት ሚስተር ካርላይል “ አሁን ምን ላድርግልሽ እችላለሁ ? ''
“ አሁን አንተም ሆንክ ሌላ ምንም ሊያደርግልኝ አይችልም : ”
“ አንቺን መርዳት የምችልበት መንገድ ባገኝ በጣም ደስ ይለኝ ነበር " መቸም ኢስትሊንም ላንቺ የደስታ ቤት አልነበረም ነገር ግን ከለቀቅሺው ወዲህ የባሰ ተጐሳቁለሻል
የደስታ ቤት አልነበረም አልከኝ ? ” አለችው የኢስትሊን የኑሮ ትዝታ ድቅን እያለባት “ ኧረ እሱስ ነበረ እንግዲህም እንደሱ ደስ የሚል ኑሮ የማገኝ አይመስለኝም ሚስርተር ካርላይል ኢስትሊንን አቃለህ አትንገረኝ " ምነው አሁን
እነዚያ ያሳለፍኩዋቸው የመከራ ወሮች ወደ ሕልም በተለወጡና አባቴን በሕይወቱ አግኝቸው ኢስትሊን ውስጥ እንደ ዱሮአችን በሰላም ስኖር ከእንቅልፌ በነቃሁ . .
“ ወደ ኢስትሊን የምትመለሽበት አንድ መንገድ ብቻ አለ ” አላት መንፈሱ ጭንቅ ጭንቅ እያለው ልቡ በጣም እየመታ እጂዋን ያዝ አድርጎ ምናልባትም ሳይታወቀው ሊሆን ይችላል · ጣቶቹ ከጣቶቿ ጋር እየተጫወቱ " ንግግሬ የሚያስከፋሽ ከሆነ መልሽኝ : በጥፋቴም ይቅርታ አድርጊልኝ "የኢስትሊን እመቤት ሆነሽ
እንድትመለሽበት ብጠይቅሽ ድፍሬት ይሆንብኛል ? ”
ምን ለማለት እንደ ፈለገ ፍጹም አልገባትም „ “እመቤት ሁኜ ወደ ኢስትሊን መመለስ ? ” አለችው ድንግጥ ብላ "
“ አዎን ' የኢስትሊን እመቤት የኔ ባለቤት ሆነሽ " ብሎ መላሰላት
አሁን ገባት መገረምም መደንገጥም †ነባበሩባት " በርግጥ ሚስተር ካርላይል
ብዙ ውለታ የዋለላት ከደግንቱ እንከን ያላገኘችበት ሰው ስለነበር ትወደው ነበር ሚስቱ የመሆን ጉዳይግን እሱ አፍ አውጥቶ እስከ ጠየቀበት ሰዓትድረስ አሰባው
አታውቅም ደነገጠችም ለዚሁ ነበር እጅዋንም ከእጁ አስለቅቃ ሊሆን እንደማይችል ልትነግረው ቃጣትና እጅዋን ሳብ ስታደርግ እሱ ደግሞ ጠበቅ አደረጋት።
የመናገር ፈራ ተባው ለቀቀው " ጠቅላላ ስለሷ ያለውን ስሜት የትዳሩን ዓላማና የፍቅሩን ነገር በማይስቱና ልብን በሚወጉ የቃላት ቀስት ነደፋት ልብን በሚነካ ንግግር ሐሳቡን በሙሉ በምታውቀው ሐቀኝነቱ ግልጽልጽ አድርጎ አጫታት ሁለቱ በዚህ ሁኔታ እንዳሉ ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ገባች ደነገጠችና ምንም ሳትናገር በሐሳቧ ብቻ ላቀረበችው ጥያቄ መልስ የምትጠብቅ
ይመስል ቀጥ ብላ ቆመች።
ሚስተር ካርላይል ሳቤላን ያዳነ መሰለውና ራሱን ለማስተዋወቅ ወደሷ ቀረብ ሲል ሳቤላ ደግሞ ተረጋጋችና “ ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ” ብላ አስተዋወቀች ,
ሎርድ ማውንት እስቨርን ባለመኖራቸው በጣም አዝናለሁ " እሳቸው ያውቁኝ ነበር እኔ ሚስተር ካርላይል እባላለሁ ” አላት "
“እኔም ስለአንተ ሰምቻለሁ " አለችው ሸጋ መልኩን እየቃኘችና አክብሮቴን ለማትወዳት ሴት ሲሰጥ በማየቷ ቅር እያላት “ከወይዘሮ ሳቤላ ቬን ጋር ይኸን ያህል የቀረበ ወዳጅነት እንዳላችሁ ግን አልሰማሁም " ”
“ እስካሁን እንኩዋን ለእርስዎ የመሰለዎትን ያህል የጠና ወዳጅነት አልነበረንም” አላት ወንበር ጠጋ ካዪረገላት በኋላ ለራሱም ሌላ እያስተካከለ „ “ አሁን ግን ወዳጅነታችንን የጠና ለማድረግ ሚስቴ እንድትሆን እየለመንኳት ነበር '
እመቤቲቱ ከዚያች ከምትጠላት ልጅ የምትላቀቅበት ፍንጭ በማግኘቷ የከፋው ፊቷ የደስታ ብርሃን ፈነጠቀበት " ሚስተር ካርላይልን እንደ ትልቅ ባለውለታዋ
አድርጋ አየችው ።
“ግድ የለሹ አባቷ ያለምንም አለኝታ ጥለዋት እንደሞቱ • አንተም ታውቃለህ ስለዚህ እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የጋብቻ ጥያቄ ሲቀርብላት ሳቤላ በደስታ መቀበል አለባት " ደግሞም እንደ ሰማሁት ኢስትሊን በጣም የሚያምር ቦታ ነው ይባላል
አለችውና ፊቷን ወደ ሳቤላ መልሳ “ ለመሆኑ የሷ መልስ ምንድነው? ” ብላ ጠየቀችው።
ኅቤላ ለሷ በቀጥታ መልስ እንደ መስጠት ራሷን ዝቅ እንደ ማድረግ ቆጠረችውና ሚስተር ካርላይልን 'እንዳስብበት ጥቂት ሰዓት ልትሰጠኝ ትችላለህ ? '' አለችው "
“ በነገሩ በደንብ ብታስቢበት ለኔም በጣም ደስ ይለኛል " ስለዚህ ከሰዓት በኋላ እመለሳለሁ ” ብሏት ሔደ ።
ሚስተር ካርይል ከወይዘሮ ማውንት እስቨርን ጋር ሲነጋገር ሳቤላ ከክፍሏ ግብታ ብቻዋን በጣም ግራ የሚያጋባ ሙግት ጀመረች " ሳቤላ ከልጅ እምብዛም
አትሻልም ነበር አስተሳሰቧና ክርክሯ ሁሉ እንዶ ልጅ ላይ ላዩን እንጂ ጥልቀትና ብስለት አልነበረውም " ሚስተር ካርላይል የተራ ቤተሰብ ልጅ መሆኑንና እንደሷ ከትልቅ ሰው ባለወለዱ አቻዋ ያለመሆኑን ነገር አላሰበችውም " ኢስትሊን ለዘለቄታ መኖሪያነት ጥሩ ቦታ ነበር " በመጠን በውበትና በጠቃሚነትም ረገድ
አሁን ከምትኖርበት ከካስል ማርሊንግ በጣም የላቀ ነበር " ነገር ግን ኢስትሊንን የሚስተር ካርላይል ሚስት ሆና ስትገባበት የሎርድ ማውንት እስቨርን ልጅ ሆና እንደ ኖረችበት እንደማይሆንላት አላሰበችውም " ተወልዳ ካደገችበት ድምቀት

👍19❤2
ቅንጦትና ክብር ተገልላ ከአንድ ጭልል ካለ ቤት ተወስና እንደምትኖርም አልተረዳችውም ሚስተር ካርላይልን በጣም ትወደው ነበር። ከአጠቡ መሆንና ከእሱ ጋር መጫወትና መወያየትም ልዩ ደስታዋ ነበር " ባጭሩ ተሠርቆ ከልቧ የገባው
ሰውዬ ሐሳብ ባይኖርባት ኖሮ ከዚህኛው ጋር ፍቅር በያዛት ነበር " ቢሆንም ከወይዘሮ ማውንት እስቨርን ጥግኝነት ጨርሳ ከመላቀቅ አኳያ ስታየው እሷ እንዳለችው ኢስትሊን እንደ ኤደን ገነት የሚቀጠር ነበር “
ነግሩ እስካሁን እንደማየው ጥሩ ይመስላል አለች » በሐሳቧ ቢሆንም እኔ ሚስተር ካርላይልን በደግነቱ ልውድደው” እንጂ ከሱ ጋር የፍቅር ስሜት የለኝም »
ከዚህ ሌላ ደግሞ በካፒቴን ሌቪዞን ፍቅር ተይዣለሁ ብዬ እሠጋለሁ » ወይም ከፍቅሩ ወጥመድ ልገባ ምንም ያሀል አልቀረኝም " ምነው እንዲያው አሁን እወድሻለሁ ላግባሽ ባለኝና ባረፍኩ ወይም ከዚህ ሁሉ ከነጭራሹ ሳላውቀው በቀረሁ ። "
ሳቤላ ' ምን መልስ እንደምታቆየው ለመወሰን ተቸግራ ብቻዋን ስታወራና ስታመዛዝን ሚስዝ ሌቪንና ኤማ ማውንት እስቨርን ከክፍሏ ሲገቡ ሐሳቧ ተቋረጠ " ባለቤቲቱ ስለጉዳዩ ለአያቷ በደንብ አድርጋ አስተካክላ ከመንገሯም በላይ ፥ ባልቴቷም የዕድሜ ብቻ ሳይሆን የዚ ዐይነቱ ልምድም ባለጸጋ ስለነበረች ' ሁለቱም እየተጋገዙ የሚስተር ካርላይልን ጥያቄ እንድትቀበል እየተነተኑ ለማስሪዳት የተቻቸውን ያሀል መከሯት በተለይ ባልቴቷ ሚስተር ካርላይልን አንድ ደርዘን ኳኳቴ የትውልድ ትምክህተኞቹን እንደሚበልጥ ነገረቻት ሳቤላ ልቀበል አልቀበል እያለች ከአንደኛው ሐሳብ ወደ ሌላሙ ከሌላው ወደ አንደኛው ሐሳብ እየተላጋች ስታዳምጥ ቆየችኖ በሀሳቧ በጣም ስለ ተጨነቀችበት
ራሷን አመማት » ከቁርጥ መልስ ለመድረስ የግረገራት የፍራንሲዝ ሌቪዞን ነገር ነበር ።
ሚስተር ካርላይል ሲመጣ በመስኮት አይታው ምን መልስ እንደምትሰጠው ምንም ሳታውቅ ወደ ሳሎን ወረደች - ሲጨንቃት ረዘም ያለ ጊዜ ጠይቃ መልሷን
በጽሑፍ ልትገልጽለት አሰበች ።
ወርዳ ከሳሎን ስትገባ ፍራንሲዝ ሌሺዞን ተቀምጦ አገኘች • የልቧ ምት ጨመረ ። ይሀ ኃይለኛ የልብ ምት ከፍራንሲዝ ሌቪሰን በቀር ሌላ ማግባት እንደሌለባት የሚያሳምናት መስሉ ተሰማት "
“ የት ተደብቀሽ ነበር ? ” አላት“ በድንኬው ሠረግላ ስንሔድ የደደረብንን ሰምተሻል?”
“ የለም አልሰማሁም ” ብላ ዝም አለች።
“ ሰረገላውን አኔ እየነዳሁ ኤማን ወደ ከተማ ስወስዳት ነበር - ፈረሱን አንድ ነገር ሲያስደነግጠው ተራገጠ "ዘለለ ተፈራንገጠና መጨረሻ በርከክ ብሎ ወደቀ እሷም ደማሞ በበኩሏ ደገጠችና በእግሯ ተመለሰች እኔም ያን ፈረስ ሙልጭ አድርጌ ከገረፍኩት በኋላ ልቡ እስኪጠፋ አስሮጥኩት» አምጥቼ ከጋጡ አገብቼው
ስወጣ ' ሚስተር ካርላይል ጋር ለመተዋወቅ ደኅና ደረስኩ ምንም እንከን የማይወጣለት ጥሩ ሰው ይመስላል “ ስለዚህ ሳቢላ ... እንኳን ደስ አለሽ እልሻለሁ : "
ቀና ብላ አየችው ።
አትደንጭ " ኤማ እንደምትነግረኝ ሁላችንም አንድ ቤተስብ ነን እኔ
ወሬውን የትም አልንዛውም ኤስትሊን ሊመኙት የሚገባ ቦታ ነው ትለኛለች ስለዚህ አሁንም መልካም ዕድል እመኝልሻሁ ።
"አመሰግናለሁ አለችው በማሾፍ ጉሮሮዋ ለብቻው እየመታ ሲተናነቃት ከንፈሮቿ ሲንቀጠቀጡ ለመቁጣጠርና ለመሸፈን እየሞከረች » ግን ካፒቴን ሌቪዞን ... ደስታህን ለመግለጽ በጣም ቸኰለሃል "
ቸኮልኩ እንዴ ? እንግዲያውስ መልካም ምኞቴን ልብሽ የሚፈልገውን አይነት ወንድ እስኪመጣልሽ አስቀምጪው እኔ ለራሴ እንደ ሆንኩ እንደዚህ የመሰለውን ዕድል እንደ ሌሎች ሁሉ እመኘዋለሁ እንጂ ቆርጨ እንድገባበት ዐቅሜ አልፈቀደልኝም » ደኅና አስተማማኝ የሆነ የወደፊት ተስፋ የሌለው የኔ ብጤ ሰው ዕድሜ ልኩን እንደ ቢራቢሮ ከአንዱ ወደ አንዱ እንደ ተንከወከወ ይኖራል ” አላትና ወጣ።
ሰውየው ቀጣፊና ጨካኝ መሆኑ በአእምሮዋ ብልጭ አለባት " ነገር ግን ከልቧ ልታወጣው አልቻለችም ከአሽከሮቹ አንዱ ገብቶ የሚስተር ካርይል መምጣት ነገራትና አስገባው ሚስተር ካርላይል በሩን በስተኋላው ዘግቶ ወደሷ ተጠጋ " ምንም አልተናረችም ከመጨነቋ የተነሣ የነጡት ከንፈሮቿ ተንቀጠቀጡ ሚስተር ካርላይል ዝም ብሎ ጠበቃት።
"ታዲያስ ” አላት በርጋታ ጠብቆ ጠብቆ“ ጥያቄዬን ለመቀበል ወስንሽ
“ አዎን ግን . . .” አለችና ቀጥ አለች " ስሜቷን መግታት አልቻለችም ግን ልነግርህ ፈልጌ ነበር።
አሁን '' አላት ካርላይል ወደ ሶፋው ሳብ አድርጎ አስቀመጣትና ' “ አሁን እስከ ፈለግነው መጠበቅ እንችላለን " በጣም አስደስተሽኛል "ልነግርህ ይገባኛል መንገርም አለብኝ ”አለችና አቋርጦ እንባዋ መጣባት
“ ምንም እንኳዋን እሺ ብልህም በርግጥ አንተን በጣም እወድሃለሁ " ላንተ ያለኝ ግምትና አክብሮት ከፍተኛ ነው " ግን እስካሁን አንተን በወንድምነት ፍቅር ብቻ እንጂ በባልነት ፍቅር አስቤህ አላውቅም " አሁንም አንተን በዚህ ዐይነት ፍቅር አልወድህም "
“ ካሁን ቀዶም አፈቅርሃለሁ ብትይኝ ኖሮ እኔም ባጣም ይገርመኝ ነበር ግን ሳቤላ እንድትወጅኝ ለማድረግ ትፈቅጅልኛለሽ ? ”
“ እንዴ አዎን ” አለችው ከልቧ - “ እኔ መቸም ተስፋ አደርጋለሁ ”
ወደሱ ሳብ አደረጋትና ከንፈሮቿን ሳማት " እሷም ምናልባት ባለመብት ሆኗል ብላ በማመን እንደሆነ አይታወቅም ምንም አልተግደረደረችም “ የኔ ፍቅር
ይኸው ብቻ ነበር የምጠይቅሽ ” አላት።
ሚስተር ካርላይል በማግሥቱ ወደ አገሩ ከመመለሱ በፊት በሥነ ሥርዓቱ ጊዜና አፈፃፀም ተነጋገረበት ጋብቻው በቶሎ እንዲፈፀም ሁሉም የየራሳቸው ምክንያት ነበራቸው "
ሚስተር ካርይል ያቺን የምታምር ቆንጆ አበባ አንዱ ቀድሞ ሳይቀጥፍበት በእጅ ለማድረግ ይቸኩል ነበር ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ከካስል ማርሊንግና ከሰዎቹ
ለመላቀቅ በጣም ጓጕታ ነበር "
ወይዘሮ ማውንት እስቨርን ሳቤላ ቬንን ከፊቷ የምታርቅበትን ምክንያት ፈላጊ ነበረች " ስለዚህ ሁሉም በነገሩ ተወያይተውበት ጋብቻው አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ
ውስጥ እንዲፈጸም ሲስማሙ ካፕቴን ፍራንሲዝ ሌቪን ብቻ ' ' ምን ዐይነት ቅጥ ያጣ ጥድፊያ ነው ? '' ብሎ ነበር " ሚስተር ካርላይል ሁኔታውን ለኧርሎ ጸፈለት " ወይዘሮ ማውንት እስቨርንም የሙሽራይቱን ሙሉ የሠርግ ልብስ እንደምትችል ተናግራ ስለነበር እንዲዘጋጅላት ወደ ለንደን ጻፈች።
“ አሁኑኑ ይዠሽ ብሔድ እንዴት ደስ ባለኝ . . .የኔ ፍቅር ” አላት ሚስተር ካርላይል - “ እዚሀ ትቸሽ መሔዱ ያለመጠን ከበደኝ ”
“ ብትችልስ እኔንም በጣም ደስ ይለኝ ነበር '' አለችው በረጅሙ ተንፍሳ "
“ የወይዘሮ ማውንት እስቨርንኮ ደግነቷን ብቻ ነው ያየሽው"....

👍28
#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አንድ
፡
፡
#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ
....ሚስጥሮቹን ሁሉ ነገረኝ፡ እኔም የእኔን ነገርኩት ብዙም ሳይቆይ ጥልቅ ፍቅር ውስጥ መሆናችን ይፋ ወጣ ስህተትም ቢሆን እንኳን መጋባት እንዳለብን አመንን፡ ከዚያ ወላጆቻችን እንደሚፈልጉት የእነሱ ግልባጭ ሳያደርጉን ከዚህ ቤትና ከወላጆቻችን ሕግ ማምለጥ አለብን ብለን ተነጋገርን፡.
“ታውቃላችሁ፣ ወላጆቼ አላማቸው አባታችሁን እናቱ ከእሷ በእድሜ አጅግ የሚበልጥ ሰው በማግባት ለሰራችው ኃጢአት እንዲከፍል
ሊያደርጉት ሁሉንም ነገር ሰጥተውት ነበር ያንን አምናለሁ: ባጧቸው ሁለት ልጆቻቸ
ምትክ እንደልጅ ነበር የሚቆጥሩት። ወደ ዩኒቨርስቲም አስገቡት: በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበር። ክሪስቶፈር አንተም ጉብዝናህን ከእሱ ነው የወረስከው: በሶስት ዓመት ተመረቀ በሶሰት አመቱ ከዩኒቨርስቲ ቢመረቅም የተመረቀበትን የማስተርስ ዲግሪውን አልተጠቀመበትም ምክንያቱ ደግሞ ዲግሪው ላይ
ያለው ትክክለኛ ስሙ ስለነበረና ማንነታችንን ከአለም ሁሉ መደበቅ ስለነበረብን ነበር። የኮሌጅ ትምህርት ውጤቱን መጠቀም ስላልቻልን በመጀመሪያዎ የጋብቻችን አመታት ነገሮች ከባድ ሆነውብን ነበር።”
መናገሯን ገታ አደረገችና መጀመሪያ ክሪስን ቀጥሎ ደግሞ እኔን ተመለከተች:: መንትዮቹን አቅፋ ጭንቅላታቸው ላይ ሳመቻቸው: ፊቷ በጭንቀት
ተኮማትሮና ቅንድቦቿ ተኮሳትረው ካቲ… ክሪስቶፈር… እንድትረዱኝ
የምጠብቀው እናንተን ነው: መንትዮቹ ገና ልጆች ናቸው: የኛ ነገር እንዴት እንደነበረ ለመረዳት ሞከራችሁ?”
“አዎ፣ አዎ፣” ሁለታችንም ጭንቅላታችንን ነቀነቅን።
እየተናገረች ያለችው የእኔን ቋንቋ ነበር የሙዚቃና የዳንስ ቋንቋ! የፍቅርና የሚያምሩ ቦታዎች ውስጥ ያሉ ቆንጆ ቆንጆ ፊቶች ታሪክ! ለካ ተረትም እውነት ሊሆን ይችላል።
በመጀመሪያ እይታ የተፈጠረ ፍቅር! እኔም የሚያጋጥመኝ እንደዚህ እንደሚሆን አውቃለሁ። ልጁ እንደ አባዬ ልብን የሚነካና የሚያንፀባርቅ ቁንጅና ያለው ይሆናል
“አሁን በደንብ አዳምጡኝ" አለች ቀስ ባለ ድምፅ ለስለስ ማለቷ ለምትናገራቸው ነገሮች ትልቅ ግምት እንድንሰጣቸው አደረገን: “እዚህ የመጣሁት አባቴ እንደገና እንዲወደኝ ለማድረግ የተቻለኝን ለመሞከርና በአባት ብቻ
የሚገናኘውን ወንድሙን በማግባቴ ይቅር እንዲለኝ ለማድረግ ነው አያችሁ፣
ልክ አስራ ስምንተኛ አመት እድሜዬ ላይ ስደርስ አባታችሁና እኔ ኮበለለን ከዚያ ከሁለት ዓመት በኋላ ተመልስን መጥተን ለወላጆቼ ነገርናቸው: አባቴ
እጅግ ተናድዶ በቁጣ አበደ በሸቀ ሁለታችንም ቤቱን ለቀን እንድንወጣ አዘዘ፡ በጭራሽ ተመልሰን እንዳንመጣ ነገረን በጭራሽ! ለዚያ ነው ከውርሱ
እንድሰረዝ የተደረግኩት አባታችሁም ጭምር ከውርስ ውጪ የሆነው አባቴ ለአባታችሁ ትንሽ ውርስ ሊሰጠው እቅድ ነበረው ትልቁ ድርሻ የእኔ ነበር ምክንያቱም እናቴ የራሷ ገንዘብ ነበራት በመጀመሪያ ደረጃም አባቴ ያገባት ከወላጆቿ ገንዘብ ወርሳ ስለነበረ ነው: በዚያ ላይ በልጅነቷ ቆንጆ ባትባልም መልኳ ደህና ነበር በዚያ ላይ ባለስልጣን የሚያስመስላት ቁመና ነበራት።
አይሆንም! ለራሴ በምሬት አሰብኩ. ያቺ አሮጊት አስቀያሚ ሆና ነው የተወለደችው!
“አሁን አባቴ እንደገና እንዲወደኝ ለማድረግ እዚህ መጥቻለሁ። አጎቴን በማግባቴ ይቅር እንዲለኝ አደርጋለሁ: ይህንን ለማድረግ ደግሞ የቅን፣ የትሁትና በደንብ የተቀጣ ልጅን ሚና መጫወት አለብኝ፡ የሚጠበቅብኝን ገፀ
ባህርይ ሚና መጫወት ሳልጀምር በፊት ሙሉ በሙሉ ራሴን በሆንኩበት ሰዓት ልትሰሙት የሚገባችሁን ነገር አሁን ማለት ስለፈለግኩ ነው:ስለዚህ ነው ይህንን ሁሉ የነገርኳችሁና በቻልኩት መጠን ታማኝ ልሆን
የቻልኩት መንፈሰ ጠንካራና በራሴ መቆም የምችል አይደለሁም። ጠንካራ የነበርኩት አባታችሁ ስለሚደግፈኝ ነበር አሁን እሱ የለም። ምድር ቤት አንደኛ ፎቅ ላይ ከትልቁ ቤተ መፃህፍት ባሻገር ባለች ትንሽ ክፍል ውስጥ
ፍቅሩን ያላሳያችሁ ሰው አለ እናቴን አውቃችኋታል፡ በትንሹም ቢሆን ምን እንደምትመስል አይታችኋታል። አባቴን ግን አልተዋወቃችሁትም። እና
ይቅርታ እስኪያደርግልኝና ከትንሽ ወንድሙ አራት ልጆች የመውለዴን ሀቅ እስኪቀበል ድረስ እንድታገኙት አልፈልግም።
“ለእሱ ይህንም መቀበል በጣም ከባድ ነው አሁን ግን አባታችሁ ስለሞተና ሞቶ በተቀበረ ሰው ላይ ቂም መያዝ አስቸጋሪ ስለሆነ፣ ለእኔ ይቅርታ ማድረግ ብዙም የሚያስቸግረው አይመስለኝም:"
ለምን እንደሆነ እንጃ አንድ ፍርሃት ተሰምቶኛል፡
“አባቴ እንደገና ኑዛዜው ውስጥ እንዲያስገባኝ የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ግዴታ ውስጥ ነኝ፡”
“መታዘዝና ክብር ከማሳየት በስተቀር ካንቺ ምን ሊፈልግ ይችላል?” አለ ክሪስቶፈር በትልቅ ሰው የአነጋገር መንገድ።
ሁሉም ነገር ለምን እንደሆነ
የተረዳ ይመስል ነበር፡ እናታችን ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ተመለከተችው እጆቿ ጉንጮቹን እየዳበሱ ደስ በሚል ሀዘኔታ አስተዋለችው: በቅርቡ የቀበረችው
ባሏ ትንሹ ምስል ነው ስለዚህ አይኖቿ በእምባ ቢሞሉ አይገርምም
“ምን እንደሚፈልግ አላውቅም: ነገር ግን ምንም እንድስራ ቢፈልግ ያንን አደርጋለሁ። እንደምንም ኑዛዜው ውስጥ ሊያስገባኝ ግድ ነው ለአሁኑ እንርሳው: እያወራሁ ሳለ ፊታችሁን እየተመለከትኡ ነበር።እስቲ የተናገረችው ሁሉ እውነት እንደሆነ እንዳይሰማችሁ። አባታችሁና እኔ ያደረግነው ነገር ከስነምግባር ያፈነገጠ ነገር አልነበረም: የሚፋቀሩ ጥንዶች
እንደሚያደርጉት በቤተክርስቲያን ነው የተጋባነው: ምንም ያልተቀደሰ የሚባል ነገር የለውም፡ እናንተም ከሰይጣን የተፈለፈላችሁ ወይም ክፉ አይደላችሁም ይህ አባታችሁ እንደሚለው የማይረባ ንግግር ነው። እናቴ እኔንና እናንተን የመቅጫ ሌላው መንገዷ ራሳችሁን የማይረባ አድርጋች
እንድታስቡ ማድረግ ነው:
“የህብረተሰቡን ህጎች የሚሰሩት ሰዎች እንጂ እግዚአብሔር አይደለ በሌሎች የአለማችን ክፍሎች የቅርብ ዝምድና ያላቸው ስዎች ተጋብተው ልጆች ይወልዳሉ: ይህም እንደ ትክክል ይቆጠራል፡ ለማህበረሰቡ
መገዛት ያስፈልገን ስለነበር፣ ያደረግነው ነገር ትክክል መሆኑን ለማሳት እየሞከርኩ አይደለም፡ ይህ ማህበረሰብ የቅርብ ዝምድና ያላቸው ወንድና ሴት ጋብቻ መፈፀም አይገባቸውም፣ ከተጋቡ የሚወልዷቸው ልጆች በአእምሮ
ሆነ በአካል እንከን ያለባቸው ይሆናሉ ብሎ ያምናል። ግን ማነው ፍፁም?
ከዚያ ሁላችንንም አቅፋ እየሳቀች በግማሽ ደግሞ እያለቀሰች ነበር። “አያታችሁ ልጆቻችን ቀንድ ኖሯቸው፣ ጀርባቸው ጎብጦ፣ መንታ ጭራ ኖሯቸው እግራቸው ላይ ሸኮና ኖሮ እንደሚወለዱ ይተነበይ ነበር እንደ እብድ ሊረግመን እየሞከረ ነበር። የተረገምን እንድንሆንና ልጆቻችን ትክክለኛ ቅርፅ ያላቸው እንዳይሆኑ ይፈልግ ነበር ግን የተነበያቸው ነገሮች ሁሉ እውነት ሆኑ? ራሷም በከፊል እብድ የሆነች ትመስል ነበር። “በጭራሽ!” የራሷን ጥያቄ
መለሰች። ለመጀመሪያ ጊዜ ልወልድ ስል አባታችሁና እኔ ትንሽ ተጨንቀን ነበር፡ ሌሊቱን ሙሉ እስኪነጋ ድረስ በሆስፒታሉ ኮሪደሮች ላይ ሲንጎራደድ

👍43❤2
ነበር። ነርሷ መጥታ በሁሉም ነገር ፍፁም የሆነ ወንድ ልጅ እንደተወለደለት ስትነግረው ራሱ ሊያይ ወደ ህፃናት ማቆያው ሮጠ እኔ ወደተኛሁበት ክፍል ሲገባ ፊቱ ላይ የነበረውን ደስታ ለማየት እዚያ ብትሆኑ ጥሩ ነበር። ሁለት
ደርዘን ቀይ ፅጌረዳዎች በእጆቹ ታቅፎ ነበር፤ ሲስመኝ አይኖቹ ላይ እምባ ነበር። በአንተ በጣም ኮርቶ ነበር ክሪስቶፈር እጅግ በጣም። ለሰዎች ስድስት ሳጥን ሲጋራ በስጦታ አበረከተ። ወዲያውኑ ሄዶ የቤዝቦል ኮፍያ፣ መያዣና
የእግር ኳስ ገዝቶ መጣ ጥርስ ስታወጣ የምታኝከው የቤዝ ቦሉን ኳስ ነበር። ወደ ውጪ መውጣት መፈለግህን እንድናውቅም አልጋህን ወይም ግድግዳውን በኳስ ትመታ ነበር።
“ቀጥሎ ካቲ መጣሽ፤ አንቺም የኔ ውድ ልክ የወንድምሽን ያህል ቆንጆና እንከን የለሽ ነበርሽ: አባትሽ እንዴት ይወድሽ እንደነበር ታውቂያለሽ፡፡ የእርሱ ቆንጆዋ ደናሽዋ ካቲ…ወደ መድረክ ስትወጣ አለምን ቁጭ ብድግ
የምታደርገው ካቲ። መጀመሪያ የባሌት ዳንስ ስራሽን አስታውሳለሁ አራት አመትሽ ነበር: የመጀመሪያውን ሮዝ ቀለም ያለው የዳንስ ልብስሽን ለብሰሽ ስትደንሺ የተወሰኑ ስህተቶችን ሰራሽና የሚመለከቱት ሰዎች ሁሉ
ሳቁ አንቺ ግን በኩራት እጆችሽን አጨበጨብሽ፡፡ አባትሽ ደግሞ ደርዘን ጽጌረዳዎች ላከልሽ: ታስታውሻለሽ? የሰራሻቸውን ስህተቶች አላየም። በእሱ አይን አንቺ እንከን አልባ ነበርሽ፡፡ አንቺ በመጣሽ በሰባት አመትሽ
መንትዮቻችን ተወለዱ አሁን ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆች አሉን እጣ ፋንታን አራት ጊዜ ፈትነናት አሸንፈናል! አራት እንከን የለሽ ልጆች ስለዚህ እግዚአብሔር ሊቀጣን ቢፈልግ ኖሮ ለእኛ ቅርፃቸው የተበላሽ ወይም
የአእምሮ ዘገምተኛ የሆኑ ልጆች ለመስጠት አራት እድሎች ነበሩት። በዚያ ፈንታ ግን የሰጠን በጣም ምርጦቹን ነው: ስለዚህ አያታችሁም ሆነች ሌላ ማንም ሰው ከተወዳዳሪነት ያነሳችሁ ወይም ጥቅም ካላቸው በታች የሆናችሁ ወይም በእግዚአብሔር አይኖች አስደሳች ያልሆናችሁ እንደሆናችሁ አድርጎ እንዲያሳምናችሁ አትፍቀዱ ኃጢአት ተሰርቶም ከሆነ ኃጢአቱን የሰሩት ወላጆቻችሁ እንጂ እናንተ አይደላችሁም:: አሁንም ግላድስተን ውስጥ
የሚገኙ ሁሉም ጓደኞቻችሁ የሚቀኑባችሁ የድሬስደን አሻንጉሊቶች ብለው የሚጠሯችሁ አራት ልጆች ናችሁ ግላድስተን ውስጥ የነበራችሁን ነገሮች
አስታውሱ፡ እሱን ያዙ: በራሳችሁ፣ በእኔና በአባታችሁ እመኑ፡ ቢሞትም እንኳን እሱን መውደድና ማክበር እንዳታቋርጡ፡ ይገባዋል፡፡ መልካም ወላጅ ለመሆን በጣም ጥረት አድርጓል የእሱን ያህል ግድ ያላቸው ብዙ ወንዶች አሉ ብዬ አላስብም:” እምባዋ ያቀረረ ቢሆንም ብሩህ ፈገግታ አሳየችን
“አሁን ማን እንደሆናችሁ ንገሩኝ”
“የድሬስደን አሻንጉሊቶች!” ክሪስና እኔ ጮክ ብለን ተናገርን፡
“አሁን ታዲያ አያታችሁ ከሰይጣን የተፈለፈሉ የምትለውን ነገር ታምናላችሁ?”
“አይ በፍፁም፣ በፍፁም!”
ሆኖም ከሁለቱ ሴቶች የሰማሁትን ነገር በኋላ አጥብቄ አስበዋለሁ በጥልቀት አስበዋለሁ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚደሰት ማመን እፈልጋለሁ: ማንና ምን በመሆናችን ደስ እንዲለው እመኛለሁ፡ ይህንን ማመን አለብኝ ክሪስ እንደሚያደርገው አዎ በይ እያልኩ ለራሴ እነግረዋለሁ። ምንም ነገር ባለመረዳት ዝም ብለው እናታችንን አተኩረው እንደሚመለከቱት መንትዮች
አትሁኚ፡ ተጠራጣሪ አትሁኚ . በጭራሽ!
ክሪስ በማያወላውል አሳማኝ ድምፅ “አዎ እማዬ፣ ያልሽውን ሁሉ
አምናለሁ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከአባታችን ጋር የነበረውን ጋብቻችሁን ባይቀበለው ኖሮ አንቺና አባቴን በልጆቻችሁ ይቀጣችሁ ነበር እግዚአብሔር እንደ አያቶቻችን ባለ ጠባብ አእምሮ እንዳልሆነ አምናለሁ: ያች አሮጊት
አስቀያሚዎች ወይም ቅርፃችን የተበላሸ እንዲሁም ዘገምተኛ አለመሆናችንን ለማየት አይኖች እያሏት እንዴት እንደዚያ አይነት አስቀያሚ ነገር ልትናገር
ትችላለች?”
እፎይታ ልክ ተገድቦ እንደተለቀቀ ወንዝ በእናታችን ፊት ላይ እምባ
እንዲወርድ አደረገ ክሪስን ወደ ደረቷ አስጠግታ ጭንቅላቱ ላይ ሳመችው።ሌሎቻችንን ትታ ፊቱን በሁለት መዳፎቿ መሀከል ያዘችና አይኖቹን በጥልቀት ተመለከተች: ከዚያ “ልጄ ስለተረዳኸኝ አመሰግናለሁ” አለች በጎርናና ድምፅ “በሰሩት ስራ ወላጆችህን ባለመኮነንህ እንደገና አመሰግናለሁ:"
“እማዬ እወድሻለሁ፡ ምንም ነገር ሰርተሽ ቢሆን ወይም ብትስሪ እንኳን ሁልጊዜ እረዳሻለሁ።"
“አዎ” አጉረመረመች፡ “ትረዳኛለህ፣ አውቃለሁ ትረዳኛለህ" ከዚያ በማይመች
ሁኔታ የሰማሁትን ሁሉ ወስጄ ነገሩንና እሷን እየመዘንኩ የቆምኩትን እኔን በአይኖቿ ገረፍ አደረገችን፡ “ፍቅር ሁልጊዜ ስትፈልጉት አይመጣም፡ አንዳንድ
ጊዜ ድንገት ይመጣል ካለፍቃዳችሁ" ጭንቅላቷን ዝቅ አድርጋ የወንድሜን እጆች ጭብጥ አድርጋ ያዘቻቸው፡ “አባቴ ልጅ እያለሁ በጣም ይወደኝ ነበር።ሁልጊዜ የእሱ ብቻ እንድሆን ይፈልግ ነበር፡ ማንንም እንዳገባ አይፈልግም ነበር፡ ገና በአስራ ሁለት አመቴ አርጅቶ እስከሚሞት ድረስ አብሬው ከቆየሁ ንብረቱን ሁሉ እንደሚሰጠኝ የነገረኝን አስታውሳለሁ”
ድንገት ጭንቅላቷን ቀና አድርጋ ተመለከተችኝ፡ የሆነ የሚያጠራጥርና አጠያያቂ ነገር አየች እንዴ? የክሪስን አንድ እጁን ለቀቀችና ትከሻዋን ነቅነቅ አድርጋ “እጅ ለእጅ ተያያዙ” ስትል በሀይል አዘዘች: “ከእኔ ቀጥሎ እንድትደግሙት እፈልጋለሁ፤ እንከን የለሽ ልጆች ነን፡ በአእምሮ፣ በአካል፣ በስሜትም ስነምግባር ያለንና በሁሉም መንገድ የእግዚአብሔር ልጆች ነን
ምድር ላይ እንዳሉ ሌሎች ልጆች ያህል የመኖርና ህይወትን የማጣጣም መብት አለን፡”
ፈገግ አለችልኝና ነፃ በሆነው እጇ እጄን ይዛ ኬሪና ኮሪ እንዲቀላቀሉን ጠየቀች “እኔ እዚህ በማልኖርበት ጊዜ ቀኖቹን የምታሳልፉበት መረጋገጫ ድንጋይ እንዲሆኗችሁ አንዳንድ ስርዓቶች ስለሚያስፈልጓችሁ እንድትጠቀሙባቸው ጥቂት እነግራችኋለሁ። ካቲ አንቺን ሳይሽ ራሴን በአንቺ እድሜ ላይ ሆኜ
አየዋለሁ ውደጂኝ ካቲ እመኚኝ እባክሽ”
እንዳዘዘችን አደረግንና ጥርጣሬ በተሰማን ጊዜ ሁሉ ልንለው የሚያስፈልገንን ከእሷ ቀጥሎ እንደ ፀሎት ደግመን እንድንለው አደረገች: ስንጨርስ በአድናቆትና በማረጋገጥ አይነት ፈገግ አለች:
“እዚያ እያለሁ! አለች: ደስ በሚል እፎይታ: “አራታችሁም ያለ ማቋረጥ አእምሮዬ ውስጥ ሳትሆኑ የዋልኩበት ጊዜ የለም ስለ ወደፊታችን ብዙ አስቤያለሁ ሁላችንም በእናቴና በአባቴ እየተገዛን እዚህ መኖር መቀጠል
እንደሌለብን ወስኛለሁ እናቴ እኔን ሳታስበው ስለወለደችኝ ፍቅሯን ሁሉ ለወንዶች ልጆቿ ሰጥታ ለእኔ ትንሽ ፍቅር እንኳን አሳይታኝ የማታውቅ ጨካኝና የሚያዝን ልብ የሌላት ሴት ናት ደብዳቤዋ ሲመጣ እኔን ታደርገኝ
ከነበረው በተለየ ታስተናግደኛለች ብዬ ማሰቤ ሞኝነት ነበር። አንድ ጊዜ ስታያችሁና ስታውቃችሁ እንደገና የሚወደዱ ልጆች በማግኘቷ እንደ ሌሎች
አያቶች እጇን ዘርግታ የምትቀበላችሁ መስሎኝ ነበር። ተስፋ ያደረግኩት አንድ ጊዜ ፊታችሁን ስታይ... እምባ አነቃት “ክሪስቶፈርን መጥላቷን
እረዳታለሁ።” ይንንን ስትል ጥብቅ አድርጋ አቅፋው ጉንጩን ሳመችው። “ምክንያቱም በጣም አባቱን ይመስላል አንቺን ስትመለከትሽ ደግሞ ካቲ፣
እኔ እታያታለሁ። ወዳኝ አታውቅም ለምን እንደሆነ አላውቅም ምናልባት አባቴ በጣም ይወደኝ ስለነበረ በዚያ እየቀናች ይሆናል ነገር ግን ስለእናንተ ጨካኝ ትሆናለች ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ለመንትዮቹም እንደዚያው
ሰዎች ከእድሜ ጋር ይቀየራሉ ብዬ ራሱን አሳምኜ ነበር። አሁን እንዴት
እንደተሳሳትኩ አውቄያለሁ” ስትል እምባዋን ጠረገች።

👍36😁2
“ለዚያ ነው ነገ ጠዋት በማለዳ ቀረብ ወዳለው ትልቅ ከተማ የምሄደው።ፀሀፊነት የሚያስተምረኝ የንግድ ስራ ትምህርት ቤት እገባለሁ። መፃፍ፣
ማስታወሻ መያዝ፣ መዝገብ አያያዝና ማህደር ማደራጀት እንዲሁም አንድ ጥሩ ፀሀፊ ማወቅ ያለባትን ሁሉ እማራለሁ: ነገሮች እንዴት እንደሚሰሩ ሳውቅ በቂ ደሞዝ የሚከፈልበት ጥሩ ስራ አገኛለሁ፡ ከዚያ እናንተን ከዚህ ለማውጣት በቂ ገንዘብ ይኖረኛል። እዚሁ ቅርብ አካባቢ አፓርታማ እናገኛለን፡፡ ለዚህም አባቴን መጠየቅ እችላለሁ በቅርቡ አንድ
ጣራ ስር እንኖራለን የራሳችን ጣራ ስር፤ እና እንደገና እውነተኛ ቤተሰብ እንሆናለን፡
“ኦ… እማዬ!” ክሪስ በደስታ ጮኸ፡ “የሆነ መንገድ እንደምታገኚ አውቅ ነበር እዚህ ክፍል ውስጥ ተቆልፎብን እንደማትተይን አውቅ ነበር ምንም ያህል የተወሳሰበ ይሁን ውድ እናቱ ችግሮችን መፍታት እንደምትችል ገና አሁን
እንዳወቀ ሁሉ ወደፊት ሳብ ብሎ በእርካታ ወደኔ ተመለከተ።
“እመነኝ፣” አለች እናታችን፡ አሁን በፈገግታ ተሞልታና በራሷ ተማምና ነበር እንደገና ክሪስን ሳመችው።
እንደምንም እንደ ወንድሜ ክሪስ ልሆን ብችልና የተናገረችውን ሁሉ
እንደማይታጠፍ ቃል አድርጌ ብወስደው ተመኘሁ። ነገር ግን አሳባቂ ሀሳቦቼ ቃላቶቿ በጠንካራ መንፈስ ላይ የተመሰረቱ አለመሆናቸውን ወይም አባቴ
ሊደግፋት አጠገቧ ከሌለ በራሷ ልትቆም የምትችል አለመሆኗን ይነግሩኛል ተስፋ በቆረጠ ስሜት ጥያቄ አቀረብኩ። “ጥሩ ፀሀፊ ለመሆን ምን ያህል ጊዜ
ይፈጃል?”
በፍጥነት በጣም በፍጥነት እንደመለሰችልኝ አሰብኩ። “ጥቂት ጊዜ ብቻ ካቲ ምናልባት አንድ ወር ከዚያ የበለጠ ከፈጀብኝም መታገስና እንደዚህ አይነት
ነገሮች ላይ ብዙም ጎበዝ እንዳልሆንኩ መረዳት አለባችሁ: የእኔ ጥፋት አይደለም።” ልክ ብቁ ባለመሆኗ እንዳመካኘች እንዳሰብኩ ማየት እንደቻለች
ሁሉ በችኮላ ቀጠለች።
“ሀብታም ቤተሰብ ውስጥ ስትወለጂና የሀብታምና የባለስልጣን ልጆች
የሚማሩበት አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ ስትማሪ፣ ከዚያ ደግሞ ሴቶች ልጆች ብቻ የሚማሩበት ሌላ ትምህርት ቤት ስትላኪ፣ የምትማሪው የማህበራዊ ስነ
ምግባር ህጎችን፣ የቀለም ትምህርቶችን፣ ባብዛኛው ደግሞ ስለ ልጃገረዶች ግብዣና ሰዎችን ለማዝናናት እንከን የለሽ እንግዳ ተቀባይ ስለመሆን ነው።
ምንም አይነት ተግባራዊ ነገር አልተማርኩም ምንም አይነት የስራ እውቀት ያስፈልገኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ሁልጊዜም የሚንከባከበኝ ባል
እንደሚኖረኝ አስብ ነበር። ባል ባይኖረኝ እንኳን አባቴ ያንን ማድረግ ይችላል ብዬ አስብ ነበር፡ በተጨማሪም፣ ሁልጊዜም ከአባታችሁ ፍቅር ይዞኝ ስለነበር
ልክ አስራ ስምንት አመት በሚሞላኝ ቀን እንደምንጋባ አውቅ ነበር"
በዚያች ደቂቃ፣ ህይወት ጨካኝ ነገር ሰጥታኝ ሰው ላይ ጥገኛ ከሆንኩ ወደ
አለም ለመግባት መንገድ እንደማይኖረኝ አስተማረችኝ፡ ነገር ግን ከሁሉም በላይ ቁጣ፣ ንዴት፣ እፍረትና ጥፋተኝነት ተሰማኝ፡ ምክንያቱም ህይወት ለሁሉም ነገር ጥፋተኛ እንደሆነች እየተሰማኝ ነበር። ግን ከፊት ያለውን እንዴት ልታውቅ ትችላለች?
ለመሄድ እየተነሳች “አሁን መሄዴ ነው” ስትል መንትዮቹ ተላቀሱ፡...

👍36❤13
#ሳቤላ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ
ሚስተር ካርይል ከካስል ማርሊንግ ወደ ዌስትሊን እንደ ተመለስ ጥፋቱ እንዳይሰማበት ለመደበቅ የተገደደ ተማሪ ይመስል ተጨነቀ ምንም እንኳን ሰውየው ነገሩ ሁል ጊዜ ግልጽ ቢሆንም • በአሁኑ ጊዜ የተፈጸውን ነገር ከመግለጽ መቆጠቡ የተሻለ መስሎ ታየው ምክንያቱም እኅቱ የሱን ጋብቻ እንድትሰማ የማትፈልግ ከመሆኗም በላይ ለመልከ ቀና ሴቶች ደግሞ አዘኔታም ፍቅርም ስላልነበራትና ወይዘሮ ሳቤላንም እንደማትወዳት ያውቅ ስለነበር ነው ስለዚህ ነገሩ
ከሚስ ካርላይል ጆሮ የደረሰ እንደሆነ የምትቃወመውና ምናልባትም ጋብቻቸውን ለማፍረ
መሞከሯ እንደማይቀር አሰበና ተነጋግሮ መምጣቱን ደበቃት እንዲያውም ኢስትሊን ለመከራየት መጥተው የነበሩትን ሰዎች ከልክሎ እንደ መለሳቸው እንኳን አልነገራትም "
ሚስተር ካርላይል ከካሰል ማርሊንግ ከተመለሰ ከሶስት ሳምንት በኋላ ባርባራ ሔር አንድ ቀን ማታ ሚስ ካርላይልን ለማየት መጥታ ከተለመደው ሰዓት ቀደም
ብለው ሻይ ሊጠጡ ሲሉ አገኘቻቸው "
ቀደም ብለን ራት በላንና አርኪባልድ ሻይ ሳይጠጣ እንዳይቀር ብዬ ገበታ ሲነሳ ወድያው ቶሎ ሻይ እንዲቀርብ አዘዝኩ ” አለቻት ሚስ ካርላይል ።
ባልጠጣም ምንም አይለኝ” አለ ሚስተር ካርይል ገና የማከናውነው ብዙ ሥራ አለብኝ።
“ ለምን ተብሎ? እኔም ካልጠጣህ ደስ አይለኝም " ቆብሽን አውልቂው ባርባራ ሥራው ሁሉ ከሰው የተለየ ነው ይውልሽ ነገ ወደ ካስል ማርሊንግ ልሔድ ነው ይላል እስከ ዛሬ ዝም ብሎ ገና አሁን ነው የነገረኝ ”
ታመመ የተባለው ሰውዬ እስከ ዛሬ እዚያ ነው እንዴ ያለው ?
“ እስከ ዛሬ እዚያ ነው " አለ ሚስተር ካርላይል "
ባርባራ ስለምትቸኩል አይሆንም ብትልም በግድ ሻይ ለመጠጣት እንድትቀመጥ ሆነ » ሚስ ካርላይል ደግሞ ባርባራ ንግግሯን ሳትጨርስ አቋረጠቻትና
ወንድሟን ዞር ብላ ዕቃውን ልታዘጋጅለት እንደምሔድ ነገረችው "
“ አይ የለም ” አላት ፈጠን ብሎ " ዕቃውን እኔ ራሴ አሰናዳዋለሁ ፒተር ሻንጣውን ወደ ክፍሌ አስገባልኝ » ትልቁን ነው ... ገባህ ? ”
“ ትልቁን ” ብላ ጮኸች ያለ እሷ ጣልቃ ገብነት ምንም ነገር የማያልፈው ኮርነሊያ“ ደሞ ቤት የሚያህል ሻንጣ እየጎተትክ የምትሔደው ለምንህ ነው?
“ከልብሴ ሌላ ጨምሬ የምይዛቸው ሰነዶችና ሌሎችም ነገሮች አሎኝ "
“ እኔ እንተ የምትላቸውን ነገሮች ሁሉ በትንሹ ሻንጣ ማስገባት እችላለሁ ብላ ድርቅ አለች ኮርነሊያ « “ እሞክረዋለሁ አንተ ብቻ የምትፈልገውን ዕቃ ንገረኝ ፒተር ... ትንሹን ሻንጣ ከጌታህ ክፍል አስገባ " አለችው "
ሚስተር ካርሳይል ፒተርን ሲያየው መልሶ አየውና ራሱን በእሽታ ነቀነቀ“ ዕቃዩን ራሴ ሳሰናዳው ነው ደስ የሚለኝ ኮርነሊያ እጅሽን ደግሞ ምን አደረግሽው? ” አላት "
“ዕብደት አታውቅም አለችው ሚስ ኮርነሊያ አለልቧ ከቢላዋ ጋር ስትጫወት ጣቷን ቆረጠችና ' ' ልጥፍ የሚል ፕላስተር አለህ ? " አለችው "
“ የኪስ ማስታወሻ ደብተሩን ከጠረጴዛው ላይ አድርጎ ገለጠውና ከውስጡ አንድ ጥቁር ፕላስተር ሲያወጣ የማያርፉት የኮርነሊያ ዐይኖች አንድ ደብዳቤ ከደብተሩ ውስጥ አዩ " ምንም ሳትጠይቅ እጅዋን ሰዳ ብድግ አድርጋ ገለጠችው።
“ ከማን የመጣ ነው የሴት ጽሕፈት ነው "
ለማንበብ ከመሞከሯ በፊት ሚስተር ካርላይል እጁን ዘርግቶ ሸፈነባትና ፡ “ይቅርታ ኮርነሊያ. . . . የግል ደብዳቤ ነው " አላት "
“ ኧረ ወዲያ ምስጢር ብሎ ነገር ' ከኔ የሚደበቁ የምስጢር ደብዳቤዎች እንደ ማይዶርሱ እርግጠኛ ነኝ የፖስታ ቤቱ ማኅተም የትናንት ነው ።
“ ይሀን ደብዳቤ ልቀቂልኝ” አላት ሚስ ካርላይል በዚያ ረጋ ያለ ሥልጣን አዘል ድምፁ ሲነግራት ከበዳትና ለቀቀችለት "
"ምን ነካህ... አርኪባልድ?”
ምንም ” አላት ፕላስተሩን ከአወጣላት በኋላ ደብዳቤውን ወደ ኪስ ደብተሩ እየመለሰ “ የወንድ ልጅ ደብዳቤዎችን ማየት ደግ አይደለም " ነው እንዴ ! ባርባራ ? '' አለና ወደሷ እየተመለከተ ሣቀ " በዚህ ጊዜ ፊቱ ሲለዋመጥ አየችው "
በቀላሉ የማትለቀው ኮርነሊያ ደግሞ ፡ “ ደብዳቤው የቬን ቤተሰብ ዐርማ ታትሞበታል ” አለችው "
“ የቬን ዐርማ ከደብዳቤው ላይ ኖረውም አልኖረውም ጽሑፉ ለኔ ዐይኖች ብቻ የተላከ ነው ” ሲል ቁርጥ ያለው አነጋገሩን ሰምታ ዝም አለች
ሁሉም ዝም ሲባባሉ ጊዜ 'ባርባራ ዝምታውን ጥሳ ንግግር ጀመረች "
“ ባሁኑ ጊዜ ማውንት እስቨርኖችን ትጠይቃቸዋለህ እንዴ ? ”
“ አዎን ”
“ስለ ወይዘሮ ሳቤላ ጋብቻ ምን ይወራል... ልጄ የሰማኸዉ ነገር አለን ? ”
“እኔ የሰማሁትንና ያልሰማሁትን ማስታወስ ይቸግረኛል ባርባራ ሻይሽ ሱካር ሳያንሰው አልቀረም " አይደለም እንዴ ! ”
“ አዎን ጥቂት ” ስትለው ' የሱኳሩን ማቅሬቢያ ጠጋ አደረገና ተው ከመባሉ በፊት አምስት አንኳር አንሥቶ ጨመረበት።
“ለምንድነው ይህን ያህል?” ስትለው ከት ብሎ ሣቀና የምሠራውንም ረሳሁ "
ባርባራ ይቅርታ አድርጊልኝ ኮርኒሊያ ሌላ ስኒ ትሰጥሻለች ” አላት "
“ ባንድ ስኒ ሻይ የባከነው ይኸ ሁሉ ሱኳርስ ቀላል ነገር መሆኑ ነው ? ” አለችው ኮርኒሊያ ቆጣ ብላ "
ሻይ ተጠጥቶ እንደ አበቃ ባርባራ ለመሔድ ተነሣች “ አቤት ጨለመብኝ በዚህ ጨለማ ብቻዬን በመውጣቴ እማማ ትቆጣኛለች ” አለች "
“እርኪባልድ ያደርስሻል " አለቻት ኮርኒሊያ "
ባርባራ ሚስ ኮርነሊያን ተሰናብታ ከሚስተር ካርላይል ጋር ወጣች ጃንጥላዋን ተቀበላትና በእርሻዎቹ መካከል አቋርጠው እየተጫወቱ ሔዱ።
ባርባራ ሳቤላ ቬንን ልትረሳት አልቻለችም ሚስተር ካርይል ወደ ኢስትሊን ሲመላለስ በነበረበት ጊዜ ከልቧ አድሮባት የነበረው ቅናት አልጠፋም " አሁንም
በጫወታቸው ወደዚሁ ርዕስ ተመለሰችበት "
ወይዘሮ ሳቤላ ቬን ስለ ማግባቷ ጉዳይ የሰማኸው እንዳለ ጠይቄህ እኮ መልስ አልሰጠኸኝም .. አርኪባልድ ” አላችው "
አኔ የምሰማውን ሁሉ ማስታወሱ አልችልም ብዬ አልነገርኩሽም? ”
“ብልኸኝ ነበር ? ”
“አስጨንቀሽ ያዝሺኝ አይደለም እንዴ ! " ብሎ ሣቅ አለና አዎን ነምቴገባ ይመስለኛል ” አላት "
" ማንን ? ” አለችው ያስጨነቃት ሐሳብ እንደ መልቀቅ እያደረጋት "
አሁንም ፈገግታው ከከንፈሩ ሳይለቅ “ ሁሉን ነገር ባንድ ጊዜ ማወቅ እችል ይመስልሻል ?
ምናልባት ከካስል ማርሊንግ ስመለስ ልነግርሽ እችል ይሆናል "
“ በል አረጋግጠህ እንድትመጣ ምናልባት ሎርድ ቬንን ይሆን የምታገባው !ማን እንደሆነ እንጃ እንጂ ብዙ ጋብቻዎች የሚጠነሰሱት ብዙ ጊዜ ከመቀራሪብ ነው ብሏል ” ስትለው ትክ ብሎ አያትና ሣቀባት "
“እንዴት ያለሽ ግምት ዐዋቂ ነሽ ? ሎርድ ሔል እኮ ያምስት ወይም የስድስት ዓመት ልጅ ነው " ይልቁንስ ካነሣሺው እንዴት ያለ ጥሩ ልጅ መሰለሽ " እኔ ልጆች
ቢኖሩኝ እንደሱ ቢሆኑልኝ ነው የምመኘው "
ድፍን ዌስት ሊንን ሳታገባ መቅረትህን ካሳመንከው በኋላ እንዲህ መናገርህም
ትልቅ የምሥራች ነው "
“ እኔ ከዌስትሊን ሰው አላገባም ብዬ ቃል መግባቴን አላስታውስም
ባርባራ ሣቀች” “ ዌስትሊን በመልክ ግምት ይሔዳል መሰለኝ አንድ ሰው ሠላሳ ዓመት ከሞላው ...ኀ
“ እና ታዲያ ሠላሳ አልሞላኝ ደግሞ ሠላላ ሳይሞላኝ አባ ወራ እሆናለሁ” አላት ሚስተር ካርላይል ከመንገዱ ዳር የነበረውን የድንበር ቅጠል በያዘው ጃንጥላ ያለ ልቡ እየጨፈጨፈ ሲጓዝ "
ሚስትህን መርጠህ አኑረሃል ማለት ነው ? ”

👍13